ራዕይ ምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 13 - ጠቅላላ ሃሳብ



ሰይጣን የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍን በጣም ይጠላዋል፤ ምክንያቱም የዮሐንስ ራዕይ ሰይጣን ወደ ቤተክርስቲያን አሹልኮ ያስገባቸውን ብዙ ስሕተቶች ስለሚያጋልጥ ነው።

First published on the 18th of June 2021 — Last updated on the 18th of June 2021

ምዕራፍ 1 በ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን የነበራት ታሪክ መግቢያ።

ክርስቶስ አልፋ እና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው፣ ፊተኛው እና ኋለኛው ነው። የዚህ ምዕራፍ ሙሉ ትኩረቱ ዋነኛው ገጸባሕርይ ማለትም ክርስቶስ ላይ ነው። ሰባቱ መቅረዞች ኢየሱስ በመካከላቸው የሚመላለስባቸውን የሰባቱን ቤተክርስቲያኖች ሚስጥር ይወክላሉ። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሚያልፉ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ትወክላለች። ሰባቱ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ የመጡ ለውጦች የቤተክርስቲያን ዘመናት ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖዎች እንደደረሱባቸው ያሳያሉ።

 

 

በኤፌሶን የነበረችዋ የመጀመሪያዋ ጥሩ በተክርስቲያን በሐዋርያት የተተከለችዋን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነችዋን የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመን ትወክላለች። ሌሎቹ ከተሞች ከኤፌሶን እንደመራቃቸው መጠን ቤተክርስቲያኖቻቸውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እየራቁ ወደ ጨለማው ዘመን ገቡ። ወደ ጨለማ ዘው ብለው የገቡበት ዘመን ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲሆን ይህም ከተማ በትንሹ እስያ ውስጥ ዋና ከተማ በሆነችዋ በጴርጋሞን ስም ተጠርቷል። በ325 ዓ.ም በተደረገው በኒቅያ ጉባኤ የሮማ መንግስት ገዥ የነበረው ኮንስታንቲን በቤተክርስቲያን ላይ ፖለቲካዊ ስልጣን ጨበጠ፤ ከዚያም ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን እንድትቀበል እና የአሕዛብ እምነቶችን እንድትከተል አስገደዳት። ከዚያ ወዲያ ከተሞች በተለይ ከአምስተኛዋ ከተማ ጀምሮ ወደ ኤፌሶን ቤተክርስቲያን መመለስ ሲጀምሩ እናያለን፤ ስለዚህ ከተሃድሶው ዘመን ጀምሮ ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ቃል ትመለሳለች። የመጨረሻው የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ከኤፌሶን ቤተክርስቲያን ላይ በአንድ ውሃ ልክ ነው ያለው፤ ስለዚህ ልክ እንደ መጀመሪያው ቤተክርስቲያን ወደ መሆን እንደሚመለስ ይጠበቃል። የመጀመሪያው እና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመናት ብቻ ናቸው ሙሉውን እውነት የሚያገኙት። ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ነው እውነት። ሰባቱ ከዋክብት በኢየሱስ በስልጣኑ ቀኝ እጅ ውስጥ ያሉትን መልእክተኞች ይወክላሉ፤ እርሱም ማለትም ኢየሱስ በያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያንን ይመራታል።

ራዕይ 1፡17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ።

 

ዮሐንስ እንደ ዳኛ በነጭ ጸጉር በተገለጠው በኢየሱስ ፊት ወደቀ። እርሱም የሚፈርደው በቃሉ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።

ዓይኖቹ እንደ ዕሳት ነበልባል የሆኑት ከቃሉ ውጭ በሚመላለሱ ሰዎች ላይ ተቆጥቶ ነው በደረቱ ዙርያ የታጠቀው የፍርድ መታጠቂያ ነው።

 

 

ሐጥያታችንን በሰይጣን ላይ ሊያራግፍ በሄደ ጊዜ እግሮቹ ስለ እኛ በሲኦል ዕሳት ውስጥ ተራምደው ሄደዋል። እኛስ ስለ እርሱ በተቃውሞ እና በትችቶች መካከል አልፈን ለመሄድ ዝግጁ ነን? ወይስ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ብለን ከቤተክርስቲያናችን ጋር ዝም ብለን እንስማማለን።

ጸጉሩ እንደ ዳኛ ጸጉር ነጭ ጥጥ ይመስላል።

ራዕይ 1፡14 ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤

15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።

 

ምዕራፍ 2

 

ይህ ምዕራፍ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ከመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እየራቁ እንዴት ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ እንደገቡ ያሳያል።

ኤፌሶን ለሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ምሳሌ የምትሆን የመጀመሪያዋ ጠንካራ ቤተክርስቲያን ናት። በኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዕሳቱ የተለኮሰው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ እርሱም የበዓለ ሃምሳ ዕለት በሐዋርያት ላይ የወረደው ዕሳት ነው። በዚያ ዘመን ሐዋርያት እራሳቸው የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ተከሏት፤ አብዛኞቹንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጻፉ። የጥንቷን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ማንም ሊያሻሽላት አይችልም።

ዓመታት ሲያልፉ የቆሙበትን እውነት እየለቀቁ ሄዱና ለመጽሐፍ ቅዱስ የነበራቸውን የቀደመ ፍቅር ጣሉ። ቤተክርስቲያንም በሰው አመራር ስር ሆነች።

ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።

ኒቆ ማለት ገዥ ነው። እርሱም ምዕመናን ነው የሚገዛው። ይህ አንድ ቅዱስ ሰው ይባልና ከጉባኤው በላይ ከፍ ይደረጋል። እግዚአብሔር ይህንን አሰራር ይጠላዋል።

ምዕመናን ማለት በእንግሊዝኛ LAITY ሲሆን የዚህን ቃል ፊደሎች ቦታ ስናቀያይር ITALY ወይም ኢጣሊያ የሚለውን ስም ይሰጠናል። ኢጣሊያ በምድር ላይ ካሉ አንደኛ ፈላጭ ቆራጭ የሆነችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማዕከል ናት። ይህች ቤተክርስቲያን አለቃ ሆኖ ለተሾመባት ሰው ለፖፑ ሙሉ በሙሉ ተገዥ ናት።

እያንዳንዷ የካቶሊክ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በአጥቢያይቱ ውስጥ ለሚያገለግለው ቄስ ሙሉ በሙሉ ተገዥ ናት።

ሐዋርያት ግን አንድን ሰው በየትኛዋም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ላይ ሃላፊ አድርገው አልሾሙም።

“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ ይህም በቤተክርስቲያን ላይ ሃላፊ እንዲሆን ስልጣን የሚሰጠው አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እረኛ “ፓስተር” ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም።

ክርስቲያኖች ሁሉ ካሕናት ናቸው፤ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ እኩል ናቸው።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

ስለዚህ የትኛውም ክርስቲያን ከየትኛውም ክርስቲያን በላይ አይደሉም።

እረኛ መንጋውን ይመግባል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ሃላፊነት የተሰጠው ለአንድ ግለሰብ ሳይሆን ለሽማግሌዎች ሕብረት ነው።

የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በተመሰረተችበት ዘመን ውስጥ ጳውሎስ የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን ለሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ምሳሌ እና መሰረት እንድትሆን አድርጎ ተከለ።

የሐዋርያት ሥራ 20፡16 ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና።

17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መጨረሻ አካባቢ ጴጥሮስም ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤

አገልጋዮች ሰራተኞች ስለሆኑ ራሳቸውን ከመንጋው በላይ ከፍ ለማድረግ መሞከር የለባቸውም።

የአጥቢያ ሽማግሌዎች ቤተክርስቲያኒቱን ማስተዳደር እና መመገብ አለባቸው። ይህንንም አገልግሎት በሕብረት ነበር የሚፈጽሙት። አንድ ግለሰብ አለቃ የሚሆንበት አሰራር አይከተሉም ነበር። ፓስተር የሚባልም አገልጋይ ተጠቅሶ አያውቅም።

ስለዚህ የእረኛ ስራ በጎችን መመገብ ሲሆን ይህም ስራ የተሰጠው በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያገለግሉ ሽማግሌዎች በጋራ እንዲያከናውኑት ነው።

እያንዳንዱ ሽማግሌ ከሌላው ሽማግሌ ጋር በማዕረግ እኩል ነው። በአምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎችም ውስጥ እንኳ ከሽማግሌዎች በላይ የሆነ ማንም የለም። በአምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ውስጥ የሚያገለግሉትም ሽማግሌዎች ናቸው። ጴጥሮስ ለሽማግሌዎች ሲጽፍላቸው እራሱን ከሽማግሌዎች እንደ አንዱ ቆጥሮ ነው የሚጽፍላቸው። ሐዋርያ በመሆኑ እያሳበበ እራሱን ከሽማግሌዎች በላይ ከፍ አያደርግም።

 

ነብያት ብሉይ ኪዳንን ጻፉ። ሐዋርያት አዲስ ኪዳንን ጻፉ።

ስለዚህ ሽማግሌዎች የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ ቢከተሉ ነብያት እና ሐዋርያት የተናገሩትን ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ የሐዋርያት እና የነብያት አገልግሎት በቤተክርስቲያን ውስጥ ይገኛሉ።

እሽማግሌ ሁሉ ሰባኪ ወይም አስተማሪ አይደለም።

1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።

አንዳንዶቹ ሽማግሌዎች ይሰብካሉ አንዳንዶቹ ደግሞ አይሰብኩም። ችግሮችን እና በሰዎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በሰላም መፍታት ለሰባኪዎችና ለአስተማሪዎች ብቻ የተሰጠ ስራ አይደለም። ማበረታታት፣ ማረም፣ እና ሰዎችን መርዳት ማንኛውም ሽማግሌ እንዲያከናውነው የተሰጠው አገልግሎት ነው።

ሰባኪዎች አገልጋዮች ናቸው፤ ማለትም ባሮች ናቸው።

ባሮች የተሰጣቸውን ስራ ሲሰሩ ሰው እንዲያደንቃቸው አይጠብቁም። በሰዎች ላይ መሰልጠንም አይፈልጉም። ከሰዎች በልጦ መከበርን አይፈልጉም። ማንም ሳያያቸው ወይም ትኩረት ሳይሰጣቸው ስራቸውን ሰርተው ሲጨርሱ ወደ ሌላ ስራ ይሄዳሉ።

የትኛውም የእግዚአብሔር አገልጋይ የተሰጠውን ስራ ፍጹም ስሕተት ሳይኖርበት መስራት አይችልም።

ሉቃስ 17፡9 ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?

10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።

 

እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ አይነግድባቸውም። እግዚአብሔር ሰው ሳያገለግለው ስራውን በራሱ በጣም ጥሩ አድርጎ መስራት ይችላል። አገልጋዮች ለእግዚአብሔር መፍትሄ ሰጭዎች ሳይሆኑ ይልቁኑ ችግር ነው የሚፈጥሩበት።

ኢየሱስ እና መጥምቁ ዮሐንስ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን ሲናገሩዋቸው ተለሳልሰው አያውቁም።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ናቸው ሕዝቡ ኢየሱስን ከኢየሩሳሌም ከተማ አስወጥተው እንዲገድሉት ገፋፍተው ያሳመኗቸው።

ስለዚህ ሎዶቅያ ውስጥ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ እንዲቆም ያደረገ ማነው? በሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከሁሉም ቤተክርስቲያኖ ውጭ ነው ያለው ምክንያቱም ቃሉ የተነገረው በሎዶቅያ ዘመን ስላሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የቤተክርስቲያን ራስ ማነው? ፓስተሩ ነው።

አንድ አካል ሁለት ራሶች ሊኖሩት አይችልም። ስለዚህ እውነተኛው ራስ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ሊቆም ችሏል።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ … ባል የሚስት ራስ ነውና።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

በመጨረሻው መልእክቱ ሐዋርያው ዮሐንስ እንደጻፈው አንድ የቤተክርስቲያን መሪ በአንዲት አጥቢያ ላይ እራሱን አለቃ አድርጎ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመላለስ አለብን የሚለውን ዮሐንስ አልቀበልህም በማለት ከራሱ ጋር አልስማማ የሚሉ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን ያባርር ነበር። ዛሬ ይህ ስልጣን በፓስተሮች እጅ ሆኗል፤ እነርሱም “ይህች የኔ ቤተክርስቲያን ናት። ስለዚህ እኔ እንደምለው አደርጉ፤ አለዚያ ከቤተክርስቲያን ውጡ ይላሉ።”

3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።

10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።

ታላቅ የመሆን ጥማት። ፓስተሩ ከጉባኤው በላይ ከፍ ማለትን ይወዳል።

በሰማያት የተፈጸመው የመጀመሪያው ሐጥያት ትዕቢት ነው። “እኔ ከአንተ እበልጣለው። እኔ ከአንተ እሻላለው።”

ዘረኝነት የአዲስ ኪዳን ትምሕርት አይደለም።

ክሎዲየስ የተባለው ሮማዊ ንጉስ አይሁዶች እንዲሁም አይሁድ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ክርስቲያኖች ወደ ሮም እንዳይገቡ ከለከለ። ስለዚህ አይዶች እና ክርስቲያኖች ተበታተኑ።

ጴጥሮስ መልእክቱን የጻፈው ውስጥ ከኢየሱስ ለሚያምኑ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ጭምር ነው።

1ኛ ጴጥሮስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

ወደ ልዩ ልዩ ሃገሮች የተበታተኑት በስደት ምክንያት ነው። ክርስቲያኖች ትንንሽ ቡድኖች ነበሩ።

62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን

እነዚያ ሰዎች በጥንት ጊዜ ሲወጡ አንዳንዴ ስድስት ወይም ስምነት ብቻ ሆነው በአንድ ተሰብስበው ይሄዱ እንደነበር ታውቃላችሁ? እነርሱም ጥቂት ሆነው ሳሉ ሃገሩን በሙሉ ነቀነቁ። እንደምታውቁት አጵሎስ ከአቂላ እና ከጵርስቅላ ጋር ታላቅ መነቃቃት ውስጥ በነበረ ጊዜ በዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስድስት ወይም ስምነት ሰዎች እና ሴቶች ብቻ ነበሩ። ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁ ሰዎች በቁጥር ከእነርሱ ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ ትበልጣላችሁ።

እንደምታውቁት ኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋርያት ብቻ ነበሩት። እኛ ግን ሁልጊዜ ብዙ ሕዝብ ነው የምናስበው። እግዚአብሔር ግን ከትልልቅ ቁጥሮች ጋር አይደለም የሚሰራው። እግዚአብሔር የሚሰራው ከጥቂት ሰዎች ጋር ነው። ገብቷችኋል? በዘመናት ውስጥ ሁሉ ሰውን የጠራበትን ጊዜ ተመልከቱ። ሁልጊዜ ከጥቂት ሰዎች ጋር ነው፤ ጥቂቶቹን ያናግራቸዋል፤ ከዚያ ለአገልግሎት ይሾማቸዋል። ይህን ሊያደርግ እግዚአብሔር ፈቃዱ ነው። እንደዚህ ነው ጌታ መስራት የሚወደው። እኛም እግዚአብሔር በመካከላችን እንዲሆንና ተነስተን እርሱ ያዘዘንን ማድረግ እንፈልጋለን።

53-0216 መልአኬ ከፊትህ ይሄዳል

እንደምታውቁት በጣም መንፈሳዊ መነቃቃት የታየባቸው ጉባኤዎቻችን ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ብቻ የተገኙባቸው ናቸው፤ ምክንያቱም ጌታ እራሱ ይገኛል። ብዙ ክርስቲያኖች በቤት ውስጥ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሆነን የጸሎት ሕብረት ያደረግንባቸውን ጊዜዎች እንደምታስታውሱ እግርጠኛ ነኝ። መንፈስ ቅዱስ ወደ መካከላችን መጥቶ የእውነት የተባረክንባቸው ጊዜያት በተለይ ጥቂት ሆነን በተሰባሰብንባቸው ሕብረቶች ውስጥ ነው። ጌታ እራሱ “ሁለት ወይም ሶስት ሆናችሁ በስሜ በተሰበሰባችሁበት እኔ በመካከላችሁ እገኛለው” ብሎ ቃል ገብቷል።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

ክርስቲያኖች ሁሉ ካሕናት ናቸው። ከሊቀ ካሕናት በቀር ከካሕናት በላይ ማንም የለም፤ ሊቀ ካሕናት ደግሞ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ሁላችንም እኩል ነን። ማንም ሰው ከእናንተ በላይ ከፍ ያለ ስልጣን የለውም።

ክርስቲያኖች ሁሉ በእግዚአብሔር ዓይን አንድ ሕዝብ ናቸው ምክንያቱም ክርስቲያኖች ከክርስቶስ መንፈስ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች እንደመሆናችን የተለያዩ ብሔሮች ልንሆን አንችልም።

ዳግመኛ ለተወለደ ክርስቲያን አንድ ዘር ብቻ በምድር አለ፤ እርሱም የሰው ዘር ነው።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡10 እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

ሁላችንም በተለያዩ ብሔሮች የምንጠራበት የተለያየ መነሻ ነበረን። ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። እርሱ አባታችን ነው፤ እኛም ደግሞ ወንድሞች እና እሕቶች ነን።

ኤፌሶን 3፡14-15 … በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት…

በሰማይ አንድ ቤተሰብ ብቻ ነው ያለው።

ክርስቲያኖች ከተለያዩ ብሔሮች የመጡ ሰዎች አይደሉም፤ ሁላቸውም አንድ ቤተሰብ ናቸው።

የአንድ ቤተሰብ አባላት ከተለያዩ ብሔሮች ሊመጡ አይችሉም።

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን በሰሎሞን እና በአንዲት ጥቁት ሴት መካከል የፍቅር ግንኙነትን ነው የሚተርከው።

መኃልየ መኃልይ 1፡5 እኔ ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ፥

ዘኁልቁ 12፡1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።

ኢትዮጵያውያን ጥቁር ናቸው።

ዘኁልቁ 12፡9 እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።

10 ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።

እግዚአብሔር ሙሴን ለምን ጥቁር ሴት አገባህ ብሎ አልቀጣውም። ይህንን ጋብቻ ስለተቃወመች ግን ማርያምን ቀጥቷታል።

ሮሜ 10፡12 በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤

ገላትያ 3፡28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥

በስጋ ስንመለከት በሰዎች መካከል የዘር ልዩነት አለ፤ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ግን ይቅር እንደተባሉ፤ በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ እንደተጠሩ ሐጥያተኞች እርስ በራሳቸውን በመንፈሳዊ ዓይን ነው የሚያዩት።

ገላትያ 3፡29 እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።

የምንድነው በስጋ በምናደርገው ነገር አይደለም። መዳናችን የሚረጋገጠው የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል በማንበብ ነው። በስጋ ስንታይ ከተለያዩ ሃገሮች የተውጣጣን የተለያዩ ሕዝቦች ነን። ነገር ግን ከመንፈስ በመወለዳችን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ወራሽ እንሆናለን።

በእግዚአብሔር መንፈስ ዘንድ ምንም የቀለም ልዩነት የለም። ስለዚህ እግዚአብሔር በሰዎች መካከል ያለውን የቆዳ ቀለም ልዩነት አይመለከትም። ከሰሜን አፍሪካ የመጣው የቀሬናው ስምኦን ኢየሱስን መስቀል በመሸከም አግዞታል። ኢየሱስ የሰው እገዛ የፈለገበት ብቸኛው ጊዜ ይህ ነበር። እርዳታ በአስቸኳይ ባስፈለጋችሁ ጊዜ የሚረዳችሁ ሰው የቆዳው ቀለም ምንም ይሁን ምን ግድ አይኖራችሁም።

ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን መንፈስ ተካፍለዋል። የበዓለ ሃምሳ ዕለት የእግዚአብሔር መንፈስ ለ120 ተከፋፈለ። 120ዎቹ ሰዎች በሙሉ አንድ ዓይነት መንፈስ ነው የተቀበሉት፤ ስለዚህ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እነዚያ ሰዎች በሙሉ አንድ ዓይነት መልክ ነው ያላቸው። መንፈስ ቀለም ያለው ከሆነ ሁላቸውም የመንፈስ ቀለም ነው የነበራቸው።

ይህ ከጾታ ጋር አይሄድም፤ ምክንያቱም እግዚብሔር የወንድ የሴትም ባሕርያት አሉት። ወንዶች እና ሴቶች እኩል ይድናሉ፤ እኩል የእግዚአብሔር ተስፋ ቃል ወራሾች ናቸው። ነገር ግን በወንድ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ የወንድ ባህሪ ያለው ሲሆን በሴት ውስጥ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ የሴት ባህሪ ይዞ ነው የሚኖረው።

ስለዚህ የመጀመሪያው የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን ሰባት ቅርንጫፎች ባሉት መቅረዝ የሚወከል ሲሆን መቅረዙም ከመካከሉ የበዓለ ሃምሳ ዕለት በመንፈስ ቅዱስ የተለኮሰ የዕሳት ነበልባል ነበረው።

 

 

ሰምርኔስ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነበረ፤ የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ከሮማውያን ገዥዎች ዘንድ በጣም ብዙ መራራ ስደት ደርሶባታል፤ በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች ወንጌልን ለማሰራጨት ስለተበታተኑ ያቺ ቤተክርስቲያን ወዲያ ሳትበላሽ መቆየት ችላለች፤ ምክንያቱም እውነተኞቹ አማኞች የተበላሸ የሰው ትምሕትር የሚያስተምሩ መምሕራን ከሚኖሩባቸው ከከተሞች ሸሽተው ወጥተው ነበር።

በዚያ ጊዜ አዲስ ልማድ ተጀመረ። አንድን ግለሰብ ከፍ ያደርጉ እና የከተማ ጳጳስ ብለው ይሾሙታል። ይህም ድርጊት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። የፊልጵስዩስ ከተማ ብዙ ጳጳሳት ነበሯት።

ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

1965 የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ፤ ምዕራፍ 5 ጴርጋሞን

ይህ አስተምሕሮ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በወጣ ደምብ ነው የተጀመረው። ችግሩ ያለው በሁለት ቃላት ውስጥ ነው፡- እነርሱም “ሽማግሌዎች” (ፕሬስቢተርስ) እና “ጠባቂዎች” (ቢሾፕስ) ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሽማግሌዎች እንዳሉ ቢያሳይም አንዳንዶች (ከእነርሱም መካከል ኢግናሺየስ አንዱ ነው) ቢሾፕ ወይም ጳጳስ ከፍ ያለ ከሽማግሌዎችም በላይ የሆነ ሥልጣን ያለው አገልጋይ ነው ብለው ማስተማር ጀመሩ።

እውነታው ግን ምን መሰላችሁ፤ “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ሰውየውን የሚያመለክት ሲሆን ቢሾፕ ወይም ጳጳስ የሚለው ቃል ግን የዚህኑ ሽማግሌ የአገልግሎት ክፍል ወይም ዘርፍ የሚያመለክት ቃል ነው። ሽማግሌው ሰውየው ነው። ቢሾፕ የሰውየው የአገልግሎት ዘርፍ ነው። “ሽማግሌ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰውየው በጌታ ሆኖ ያሳለፋቸውን ዓመታት ብዛት ነው። የዚህ ቃል ትርጉሙ በፊትም ሁልጊዜም እንደዚሁ ነው። ሰውየው ሽማግሌ የሆነው ስለተመረጠ ወይም ስለተቀባ አይደለም፤ ነገር ግን በጌታ ሆኖ ከሌሎች በላይ እድሜ የገፋ ስለሆነ ነው። ይህ ሰው ከሌሎች ይልቅ የበሰለ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በደምብ የተማረ፣ ሊታመን የሚችል፣ ጀማሪ ወይም አዲስ ክርስቲያን ያልሆነ ነው፤ ልምድ ያለው እና በረጅም ዓመታት የክርስትና ሕይወቱ የተመሰከረለት ሰው ነው።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ነበልባል እየደበዘዘ ሄደ። የሰው አመለካከት በመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ እየተተካ ነበር።

1965 የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ፤ ምዕራፍ 8

እነርሱ በሙሉ የሰይጣን መንጋ ናቸው፤ ምክንያቱም በዚያ ዘመን ነበር ሰዎች አገልግሎት ውስጥ የተሰማሩ ወንድሞች ላይ ራሳቸውን ጌታ ማድረግ ሲጀምሩ ያየናቸው። (በየአውራጃው ጳጳሳት ለሽማግሌዎች የበላይ ተደርገው ተሾሙ።)

57-0908M ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት.1

እኔ ግን በአጥቢያ ጉባኤዎች ስልጣን አምናለው። አዎን። እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የራሷ ትሁን፣ የራሷን ፓስተሮች ትምረጥ፤ የራሷን ዲያቆናት ትሹም። በዚህ መንገድ አገልጋዮቿን ካሰማራች በኋላ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሰው ከበላዩ ጌታ የሚሆንበት ጳጳስ አይኖረውም። መንፈስ ቅዱስ ለዚያች ቤተክርስቲያን አንድ ነገር መናገር ይፈልጋል፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማንንም ሰው ማማከር ወይም መጠየቅ አያስፈልጋቸውም። እያንዳንዱ ግለሰብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ያደርጋል። እስቲ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጣችሁ በአንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሽማግሌው በላይ ስልጣን ያለው ሰው ይኖር እንደሆን አሳዩኝ። አዎን፤ እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በራሷ ራሷን ማስተዳደር ትችላለች። ወንድማማችነት ደስ የሚል ሕይወት ነው። ሁሉም ቤተክርስቲያኖች እንደ ወንድማማች መተያየት አለባቸው። ነገር ግን አንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ማንም ከሌላ ቦታ ሆኖ ሊነግስባት አይገባም።

53-0614A ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ስለ ተሰጠው ሐይማት መጋደል

ልንገራችሁ፤ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የምትመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። መንፈስ ሲንቀሳቀስ ነው የሚንቀሳቀሱት። እግዚአብሔር ጳጳሳትን ብቻ እንደሚመራ አልተናገረም። በያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የቤተክርስቲያን ራስ ሽማግሌዎች ናቸው።

ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ሁለተኛው ሻማ ሲበራ ይታያል። ነገር ግን ሲበራ እሳቱ ከመጀመሪያው ሻማ በተቃራኒ አቅጣጫ ነው የሚነድደው። ክርስቲያኖች ከመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየራቁ በሄዱ ቁጥር ነበልባሉም መጠኑ እየቀነሰ ይሄዳል።

በዚያ ዘመን እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ግለሰብ በቤተክርስቲያን ላይ ከፍ ተደርጎ ሃላፊ ሆኖ ነበር።

 

 

ጴርጋሞን የሮማው ግዛት ንጉስ ኮንስታንቲን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትንን በግዳጅ ወደ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ውስጥ ያስገባበት ሶስተኛው ዘመን ነው፤ ይህም የሆነው በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ ነው። እነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን) ሶስት አካላት ያሉትን የስላሴ አምላክ ፈጠሩ። ሶስት ግለሰቦች አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ስሙን አጣ፤ በስሙ ቦታ ሶሰት የማዕረግ መጠሪያዎች ተተኩ። ክርስቲያኖች “በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ፤ ግን ያ ስም ማን እንደሆነ መናገር አይችሉም። አንድን ክርስቲያን “የእግዚአብሔር ስም ማነው?” ብላችሁ ጠይቁት፤ ከዚያም ግራ የተጋባ ፊት ያሳያችኋል። ከዚህም የተነሳ ሶስተኛው ትዕዛዝ ትርጉሙን አጥቷል። በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ላይ የሚሳደብ ሰው የለም። በጣም ታዋቂ የሆነው እና ክርስቲያኖች በተደጋጋሚ በሐጥያተኞች ሲሰደብ በመስማት የሚያዝኑበት ስም “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው ስም ነው።

 

 

በስላሴ የሚያምኑ ሰዓሊዎች ስላሴን ለመግለጽ ከሚስሏቸው ስዕሎች አንዱ ይህ ነው።

 

 

ይህ ደግሞ ይበልጥ ዘመናዊ ስዕል ነው።

 

 

ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ሲያስቡ እነዚህ የመሰሉ ግልጽ ያልሆኑ ምስሎች ናቸው በአእምሮዋቸው ውስጥ የሚመጡባቸው።

ስለዚህ ስላሴ ብለው ለሚያመልኩት አምላካቸው አንድ ስም ማጣታቸው አያስገርምም።

አሁን ድግሞ በጥንት ዘመን ግብጻውያን ዘንድ የነበረውን የስላሴ እምነት የሚገልጽ የተቀረጸ ምስል እንይ። ሃሳቡ አንድ ነው፤ ማለትም ሶስት አካላት ነገር ግን አንድ መለኮት። የግብጻውያኑ ግን የሚለየው ሶስቱም አካላት እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ስም ያላቸው መሆኑ ነው፤ ስማቸውም አይሲስ፣ ኦረስ እና ሴብ ነው ምክንያቱም ግብጻውያን ለሶስቱ አምላኮቻቸው የሚሆን አንድ ስም ሊያገኙ እንደማይችሉ ስለገባቸው ነው። የጥንት ግብጻውያን ከዚህ ዘመን ክርስቲያኖች ይልቅ ሃቀኞች ናቸው። ሶስት ማዕረጎችን እንደ አንድ ስም እያስመሰሉ የእምነት ተከታዮቻቸውን ለማታለል አልሞከሩም።

 

 

እኔ ልጅ በነበርኩ ጊዜ የተማርኩበት የቤተክርስቲያን ትምሕርት ቤት ሰባኪው የሚቆምበት መድረክ ላይ “I H S” የሚሉ የእንግሊዝኛ ፊደሎች የተጻፉበት ጨርቅ ይነጠፍ ነበር። እነዚህ “I H S” ፊደሎች በተጨማሪ የግብጽ ቤተመቅደሶች ውስጥ የመሰውያው ልብስ ላይም ተጽፈዋል፤ ምክንያቱም ፊደሎቹ አይሲስ፣ ኦረስ፣ እና ሴብ የተባሉትን የግብጽ አማልክትን ስም ነው የሚወክሉት።

ባዕድ እምነቶች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው መግባት የጀመሩት በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ከሶስተኛው ዘመን ጀምሮ በብዛት ገብተው ቦታ ይዘዋል።

ለምንድነው እስልምና በ630 ዓ.ም አካባቢ የተጀመረው? ምክንያቱም መሃመድ ሶስት አካላት ያሉትን አምላክ መቀበል ስላልቻለ ነው። ከዚህም የተነሳ ስም የሌለውን አምላክ መከተል አልቻለም። ስለዚህ ለአምላክ የሚሆን አንድ ስም ፈልጎ አመጣና አላህ አለው። ሙስሊሞች ለአምላካቸው ስም አላቸው፤ ክርስቲያኖች ግን ለአምላካቸው ስም የላቸውም። ስለዚህ የስላሴ ስም ነው የእስልማና ሐይማኖት እንዲፈጠር ያደረገው፤ ምክንያቱም እስልምና አምላክ ስም ስለማጣቱ ምላሽ ለመስጠት የተፈጠረ ሐይማኖት ነው። በክርስትና ላይ ከቤተክርስቲያን ውጭ ከሚመጡ ስጋቶች መካከል ትልቁ ስጋት እስልምና ነው። ለቤተክርስቲያን ከውስጥ በኩል የሚመጡባት ስጋቶች መድረክ ይዘው በመስበክ በባዕድ እምነት ልማዶች እና በፖለቲካ አመለካከቶች ሃሳባችንን የሚበርዙ ሰባኪዎች ናቸው።

ኢየሱስ እና ጳውሎስ የኖሩት ክፉዎችና ጠማማ የሮም ባለስልጣናት በኖሩበት ዘመን ነው። እንደዚያም ሆኖ ግን ኢየሱስ እና ጳውሎስ ለነገስታት ስለመጸለይ እና ግብር ስለ መክፈል በቀር ስለ ፖለቲካ ሰብከው አያውቁም።

ቤተክርስቲያና ሙሉ በሙሉ ከአሕዛብ ልማዶች እና ከፖለቲካ ጋር ተጋባች። ንጉስ ኮንስታንቲን የሮማ ጳጳስን በምዕራባዊው የሮማ ግዛት ውስጥ የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ ሾመው።

ይህም ሐዋርያት ከመሰረቷት ከመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ማፈንገጥ ነው። ስለዚህ የእውነት ብርሃን እየደበዘዘ ሄደ። የሰዎች አመለካከት የእግዚአብሔርን ቃል ቦታ ያዘ።

ሰዎች በመሪነት ስፍራ በመቀመጥ በኢየሱስ ቦታ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኑ።

 

 

ትያጥሮን አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲሆን በዚህ ዘመን ነበር የሮማ ቤተክርስቲያን አውሮፓን በሙሉ ስትቆጣጠር የጨለማው ዘመን በክፋቱ የተገለጠው። በዚያ ዘመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ብዙ ቃላትን ተቀብለው መጠቀም ጀመሩ፤ እንዲሁም የዓለም ብርሃን የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ለወጡት። ብርሃንን በአግባቡ ካልተጠቀማችሁበት ይጠፋል።

ክፋት ማለት ከተጻፈው ቃል ውጭ መሄድ ነው።

ክፋት ማለት ከአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መንገድ ማፈንገጥ ነው። የአሕዛብ ልማዶችን እና የሰው አመለካከቶችን መቀበል ነው። ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የጻፉትን እውነት መካድ ነው። ብርሃኑ በጣም እስኪጨልም ድረስ ደበዘዘ። በቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረው የአዲስ ኪዳን እውነት በብዛት ጠፋ።

የምታምኑት ማንኛውም ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው። በብዛት የተላመድናቸው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን ልብ በሉ፤ ለምሳሌ “ሜሪ ክሪስማስ፣” “ስላሴ፣” “ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣” “የፋሲካ እንቁላሎች፤ የፋሲካ ጥንቸሎች፣” “የገና ዛፍ፣” “ዲሴምበር 25” “ሴት ሰባኪዎች፣” “ሕጻናትን ማጥመቅ፣” “ማጽናት፣” “ካተኪዝም፣” “ዲኖሚኔሽን” እና የመሳሰሉት። ከዚያ በኋላ ግን የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ እንኳ ሳናውቅ እንቀራለን።

ከመጀመሪያው እውነት ምን ያህል ርቀናል?

 

 

 

ምዕራፍ 3

 

ይህ ምዕራፍ ቤተክርስቲያን ወድቃ ከነበረችበት በተሃድሶው ዘመን ተመልሳ ስትነሳ ስታንሰራራ ያሳያል፤ ይህም በስተመጨረሻው እንደ ገና ከመውደቋ በፊት ነው።

አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰርዴስ ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ ጻድቅ በእምነት እንደሚኖር በመስበኩ ፕሮቴስታንቶች ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያመለጡበት ዘመን ነው። ሉተር መዳን በጸጋ እና በእምት እንጂ በስራ አለመሆኑን ሰበከ። ትልቁ ቁምነገር ያመጣው የአቅጣጫ ለውጥ ነው።

ይህ የተሃድሶ እንቅስቃሴ መጽሐፍ ቅዱስን ትቶ ከመሄድ ይልቅ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለመመለስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነበር።

በዚህም ዘመን እንኳ የሚበራው የእውነት ብርሃን በጣም ደማቅ አልነበረም። ቤተክርስቲያን ውስጥ ከዚያም በኋላ እንኳ ብዙ ስሕተት ነበረ። ማርቲን ሉተር ባለማወቅ ፖለቲካ ውስጥ ገባ፤ ከዚህም የተነሳ የተቀሰቀሰው የገበሬዎች አመጽ ለ100,000 ሰዎች ነፍስ መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

ሉተር እግዚአብሔር ስለ አይሁዳውያን የነበረውን ሃሳብ ባለማወቁ አይሁዳውያንን አወገዘ።

ነገር ግን ዕድሜ ለሉተር የቤተክርስቲያን አቅጣጫ ተለወጠ።

አውሮፓን በሙሉ አንቀጥቅጣ ትገዛ የነበረችዋን እርሱንም ልትገድለው ትፈልግ የነበረችዋን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሳይፈራ ያሳየው አቋም አስደናቂ ነው።

እርሱም ሰዎች ለቤተክርስቲያን በመታዘዝ በሚፈጽሟቸው ስርዓቶች ሳይሆን እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ እንዲጥሉና ከክርስቶስ ጋር በግል ሕብረት እንዲያደርጉ አስተማረ።

በዚያ ዘመን አንድ ነበልባል መንደድ ጀመረ፤ አቅጣጫውም ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት እሳት ሲሆን ወደ መጀመሪያው የጴንጤ ቆስጤ ዕለት ወደ ወረደው እሳት እየተጠጋ ነበር።

 

 

ፊልደልፊያ፣ አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ትርጓሜው የወንድማማች መዋደድ ሲሆን ይህም እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና ያስተማረበት እና የወንጌልን ስብከት ያስፋፋበት ዘመን ነው። የእንግሊዝ ንጉስ በየጊዜው በእብደት ይሰቃይ ነበር። ሃገሪቱም አልተረጋጋችም። እንግሊዞችም በዚያ ጊዜ እንደ ፈረንሳዮች ወደ አብዮት እየተንደረደሩ ነበር፤ ፈረንሳይ ውስጥ አብዮት ከፈነዳ በኋላ ንጉሳቸውን አስወገዱ፤ በቦታው ግን ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ የሆነውን ናፖሌዎንን ሾሙ። ናፖሌዎን ባደረጋቸው 60 ጦርነቶች የተነሳ ፈረንሳዮች ከዜጎቻቸው አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተውባቸዋል። ዌስሊ ስለ ፖለቲካ አልሰብክም በማለት ሕዝቡ መዳን፣ ቅድስና፣ እና ወንጌል መስበክ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አስተማረ። ዌስሊ ያመጣው ተጽእኖ ሃገሩን እንግሊዝን ከአብዮት እና ከደም መፋሰስ አዳነ። ይህም እንግሊዝ ለታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት በር እንድትከፍት በማድረግ የተሃድሶውን ወርቃማ ዘመን አስጀመረ። እግዚአብሔር እንግሊዝ በታላቁ የባሕር ኃይሏ አማካኝነት የዓለምን አንድ አራተኛ በሙሉ እንድትገዛ አደረገ፤ ከዚህም የተነሳ ወንጌል ሰባኪዎች እና እግሊዝኛ ቋንቋ በዓለም ዙርያ ሁሉ ደረሱ። በ1611 ዓ.ም በ47 ምሑራን አማካኝነት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን የተባለው እንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ተተርጉሞ የሼክስፒር ሥራዎች እና ሥነ ጽሑፍ በገነኑበት ዘመን የሰው ጥበብ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ካሉት አራት እንስሳት መካከል ሰው በሚመስለው እንስሳ አማካኝነት ተባርኮ ተሰራጨ። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በ1750 ዓመተ ምሕረት ሙሉ በሙሉ ተፈትሾ ከመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች በትክክል የተተረጎመ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ ተረጋግጧል። በ1792 ዓ.ም ጫማ ሰፊው ዊልያም ኬሪ ወደ ሕንድ በሄደ ጊዜ የተጀመረው የወንጌል ስብከት ዘመን የጀርባ አጥንት የነበረው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የትኛውም መጽሐፍ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ያህል በሰው ላይ ተጽዕኖ አላደረገም። ከዚህም የተነሳ ሰይጣን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱን ይጠላዋል፤ ደግሞ ሰዎች ደጋግመው እንዲነቅፉት እና “እንዲያሻሽሉት” ያደርጋል። እባካችሁ በዚህ ዓይነት ወጥመድ ውስጥ አትቅደቁ። ከሁሉም መጽሐፍ ቅዱሶች የተሻለ ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ ደግሞም ባለፉት 400 ዓመታት ውስጥ ከቢሊዮኖች በሚበልጡ ቅጂዎች ታትሞ ተሽጧል።

ዛሬ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ ተቀናቃኝ ኒው ኢንተርናሽናል ቨርዥን (NIV) የተባለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የታተመው በ1978 ዓ.ም ሲሆን ውስጡ ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን የሚለይበት 36,000 ልዩነቶች አሉት።

ይህም አልበቃ ብሎ በ1984 እንደገና ተሻሽሎ ታተመ እና በወንጌላውያን ዘንድ ተወዳጅ መጽሐፍ ቅዱስ ሆነ። 1984 የታተመው NIV እንደገና በ2005 ተሻሽሎ የዛሬ NIV ወይም TNIV ተብሎ መጣ።

እንደገና ያሻሻሉት ትርጉም የተዘጋጀው በጾታ በኩል ያሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ተብሎ ነው። “ሰው” ተብሎ በተጻፈበት ቦታ ለወንድ የሚያደላ እንዳይመስል “ሰዎች” ብለው ተክተውበታል። በሴት ጾታ የተጻፉ ቃላት ግን አልተነኩም። ይህም ተርጓሚዎቹ ሚዛናዊነት እንደጎደላቸው በግልጽ ያሳያል። ነገር ግን አንድ ጊዜ መነካካት ከተጀመረ ማቆሚያ የለውም። ስለዚህ በ2011 እንደገና ሌላ ማሻሻያ ተደረገ፤ ከዚህም የተነሳ ተወዳጁ የ1984 እትም ከገበያ ወጣ። ወንጌላውያንም ደነገጡ።

በ33 ዓመታት ውስጥ ብቻ አራት ጊዜ እየተለዋወጠ ተተረጎመ። ለመሆኑ እግዚአብሔር በየዘመኑ ሃሳቡን ይለዋውጣል? ከዚህ በኋላ የሚያዘጋጁትን NIV ደግሞ ተመልከቱ።

ጥንታዊ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ሰዎች ለተጠናወታቸው የጾታ እኩልነት ተብሎ አይለወጥም። እግዚአብሔር ልክ እንደ እኛ እንዲያስብ ብለን ልንለውጠው አንችልም። እኛ ነን እንደ እርሱ ለማሰብ መንገዳችንን መለወጥ ያለብን።

 

 

ሎዶቅያ የሰባተኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ስትሆን መጨረሻዋ በመንፈሳዊ ውድቀት ነው የሚያበቃው።

ይህች ቤተክርስቲያን ሃብታም እና የተደላደለች ብትሆንም ዕውር፣ ምስኪን እና ራቁቷን ናት፤ ነገር ግን እንዲህ መሆኗን አታውቅም። ይህች ቤተክርስቲያን ለብ ያለች ስለሆነች እግዚአብሔር ከአፉ ይተፋታል። ስኬት የሚለካው በሃብት ሆኗል። ቃሉ ማለትም ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አልቀበልህም ስላለችው ከውጭ ቆሟል፤ ስለዚህ በውጭ ቆሞ እንዲከፍቱለት ለሚሰሙት ግለሰቦች ጥሪ ያቀርባል። ጥቂት ግለሰቦች ያሉባት ሙሽራ ተዘጋጅታ ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ትመለሳለች።

ዘመኑ በ1904 ዌልስ ውስጥ በተነሳው መነቃቃት እና አሜሪካ ውስጥ በሎሳንጀለስ ከተማ አዙዛ እስትሪት በ1906 በተነሳው የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ በመልካም አጀማመር ተጀመረ። ነገር ግን ይህ መነቃቃት ለአራት ብቻ ነበር የቆየው፤ ስለዚህ በ1917 ዓ.ም ጴንጤቆስጤ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ መሆኑ ቀርቶ የተደራጀ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ሆኖ ቀረ።

 

 

ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ትክክለኛ መንፈስ የመመለስ እንቅስቃሴ ተጀመረ።

ከዚያ የጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴ በ1920ዎቹ ከቀዘቀዘ በኋላ በ1940ዎቹ እንደገና ተነሳ። ከመንፈሳዊ ኃይል አንጻር እነዚህ እንቅስቃሴዎች ታላላቅ እንቅስቃሴዎች ነበሩ። በእርግጥ የእውነት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው አምጥተዋል።

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መገለጥ ግን የእንቅስቃሴው የመጨረሻ ግቡ አልነበረም። ቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ወደተመሰረተችበት ሙሉ እውነት መመለስ ያስፈልጋታል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ይህ ለሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የተላከው መልአክ ወይም መልእክተኛ የተሰጠው አገልግሎት ነበር። አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም የተሰወሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገለጣቸውና አስተማረ፤ ይህንንም ያደረገው የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችውን ትምሕርት ማመን እንድንችል ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

መጥምቁ ዮሐንስ ወንጌልን እንዲያስጀምር እና ኢየሱስን እንዲያስተዋውቅ በኤልያስ መንፈስ ተነሳ። ነገር ግን ምንም ነገር አላቀናም። ለዘመኑ አዲስ የነበረውን የንሰሃ ጥምቀት አስተዋወቀ። ነገር ግን እርሱ ራሱ ተገደለ።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ኢየሱስ በዘመን መጨረሻ ስለሚነሳ ሌላ ነብይ ይናገራል፤ ይህም የመጨረሻ ነብይ ቤተክርስቲያንን ወደ መጀመሪያው ዘመን እምነቷ ይመልሳታል።

ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት ተመለስን የሚባለው ሙሉው እውነት የተገለጠልን ጊዜ ነው።

የሜሴጅ ሰባኪዎች ግን ወንድም ብራንሐም ያስተማረው ትምሕርት ውስጥ ንግግሩን ወስደው በመተርጎም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ትምሕርቶችን አስተማሩበት።

እነዚህን ትምሕርቶች የጥንቷ ቤተክርስቲያን አላመነችባቸውም።

በተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ያልተመሰረቱ ትምሕርቶችን ፈጠሩ፤ ለምሳሌ ሰባቱ ነጎድጓዶች፣ የኢየሱስ አዲስ ስም፣ እና የጌታ ምጻት።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 አንድ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ከፍላግስታፍ ከተማ በሰሜን በኩል ከምድር 43 ኪሎ ሜትር ከፍታ አግድም እየተንሳፈፈ ሲሄድ ፎቶግራፍ ተነሳ። ከኋላውም በ28 ማይልስ ርቀት ላይ ሁለተኛ ደመና ታየ፤ ሁለተኛውም ደመና የተፈጠረው ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው ከቫንደንበርግ አየር ኃይል የተወነጨፈ ሮኬት ሲፈነዳ የተፈጠረ ጭስ ነበረ። ፍጥረታዊ ደመናዎች ከምድር በ20 እና 80 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ አይፈጠሩም።

 

 

ይህ ከዊንስሎው የተነሳው ፎቶግራፍ ሁለት ደመናዎችን ያሳያል። ታናሹ የጭስ ደመና ከታላቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ኋላ ነው የታየው።

 

 

 

ሁለቱ ደመናዎች ከምዕራብ ተነስተው በፍላግስታፍ ከተማ አየር ላይ ወደ ምስራቅ ሄዱ። ሁለተኛው (የጭስ) ደመና ከዊንስሎው የተነሱ ፎቶዎች ውስጥ ብቻ ነበር የሚታየው ምክንያቱም ሁለቱም ደመናዎች ወደ ዊንስሎው አቅጣጫ ነበር የሚሄዱት። ከታክሰን፣ ፊኒክስ፣ እና ፕሬስኮት የተነሱ ፎቶግራፎች በሙሉ ደመናው ሲሄድ ከጎኑ ስላገኙት ፊተኛውን ትልቅ ደመና ብቻ ያሳያሉ፤ ይህም የመላእክት ክንፎች የፈጠሩት ደመና ነው፤ ምክንያቱመ በዚያ ሰዓት በዚያ ከፍታ ላይ አንዳችም ሮኬት ወይም አውሮፕላን አላለፈም። አውሮፕላኖች እና የሮኬቶች ነዳጅ በጭሱ ውስጥ የውሃ ትነት እየፈጠሩ ደመና ይሰራሉ።

ከስምነት ቀናት በኋላ ወደ ደቡብ በ200 ማይልስ ርቀት ላይ ሳንሴት ፒክ እና ራትልስኔክ ሜሳ አካባቢ ሰባት መላእክት ወደ ወንድም ብራንሐም መጡ፤ የመጡትም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ገልጦ እንዲያስተምር ትዕዛዝ ሊሰጡት ነበር።

ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ፎቶግራፍ በተነሳ ጊዜ ምንም ያላየውና ያልሰማው ወንድም ብራንሐም ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና የተፈጠረው ሰባቱ መላእክት ማርች 8 ቀን ሳንሴት ፒክ አካባቢ እርሱን አናግረው ወደ ሰማይ ሲመለሱ መሰለውና ተሳሳተ። መላእክቱ ግን ደመናውን የሰሩት ያን ዕለት ሳይሆን ከስምንት ቀናት በፊት ነበር። ከእርሱ ተለይተው ሲመለሱ ምንም ደመና አልሰሩም።

የሚያሳዝነውም ነገር የሜሴጅ አማኞች እውነታውን አለማጣራታቸው ነው፤ አክራሪነት ብዙውን ጊዜ እውነታን ለመመልከት ፈቃደኝነት ይጎድለዋል። የሜሴጅ ፓስተሮች “ደመናው” የጌታ ምጻት ነው አሉ። ከዚህም የተነሳ የምሕረት ዘመን አብቅቷል ብለው አወጁ። ኢየሱስ መጥቷል። ከዚያ ደግሞ ይህንኑ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ ነው ብለው ተረጎሙ።

ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ከተጠቀሱት ከሰባቱ ነጎጓዶችም ጋር አያያዙት። የሰው መፈላሰፍ መቸም ማብቂያ የለውም። ሁልጊዜም ደግሞ የሰማውን ሁሉ የሚያምን አንድ ሞኝ አይጠፋም።

ደመናው ውስጥ የማንም ፊት ምስል አልነበረም። ላይፍ ከተባለው መጽሔት የጀርባ ሽፋን ላይ የተገኘ የደመናው ፎቶ ግን ውስጡ የፊት ምስል የሚያሳይ ነበር።

በታክሰን ካለው የጠፈር ምርምር ጣቢያ የተነሳው የመጀመሪያው የደመናው ትክክለኛ ፎቶ ውስጡ ምንም የፊት ምስል የለውም።

 

 

ይህ የፊት ምስል የታየው ወንድም ፔሪ ግሪን የመጀመሪያውን ፎቶ ወስዶ ከዚያ ላይ ቅጂ ሲያዘጋጅ ነው።

 

 

ከዚያ በኋላ አንዳንድ የሜሴጅ ተከታዮች የደመናው ፎቶ ውስጥ የፊት ምስል ጨምረው ሳሉበት። ዛሬ ብዙ የሜሴጅ አማኞች ደመናው ውስጥ የእውነትም የፊት ምስል ነበረ ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ስሕተት እየተስፋፋ ሄደ። ደግሞ ፊቱን ቀና ለማድረግ የመጀመሪያውን ፎቱ ዘጠና ዲግሪ ያህል ማዞር እንደሚያስፈልግም ልብ በሉ።

 

 

የሜሴጅ ፓስተሮች በተጨማሪ ሰባቱ ማሕተሞች ተገልጠው ብቻ አልቀሩም፤ በእርግጥም ተፈተዋል ብለው ያስተምራሉ።

ማሕተሞቹ ሊፈቱ የሚችሉት በጉ የምሕረት ዙፋኑን ትቶ ሲነሳ ነው፤ ስለዚህ ለሙሽራይቱ በስተቀር ከ1963 ጀምሮ ምሕረት አብቅቷል ይላሉ። (የዚህ ሁሉ ትርጉም ምንም ይሁን ምን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ አልተጻፈም)።

በሰባቱ ማሕተሞች ላይ የተጻፈው የስብከት መጽሐፍ ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ እንደተቀበለ ያሳያል። በመጽሐፉ ውስጥ እንደተብራራው ማሕተሞቹ ሲፈቱ እርሱ ቆሞ ያየ ያህል ነው የተገለጠለት።

ነብይ ማለት እንደዚህ ማየት የተሰጠው ሰው ነው። እግዚአብሔር ዘመናትን አሻግሮ ይወስደውና ወደፊት የሚሆነውን ነገር ከመሆኑ በፊት እንደሆነ ያህል አድርጎ ያሳየዋል። ከዚያም ነብዩ ተመልሶ በመምጣት ወደፊት ምን ሊሆን እንዳለ ሊነግረን ይችላል።

 

 

እግዚአብሔር አንድን ነገር አስቀድሞ ሳይገልጥ በፊት አያደርገውም።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ማንም ሰው ሰባቱን ማሕተሞች በትክክል ገልጧቸው አያውቅም። ሰባቱን ማሕተሞች ገልጦ ለማስተማር ወንድም ብራንሐም የመጀመሪያው ሰው ነው።

ማሕተሞቹ የሚፈቱት ሙሽራይቱ ጌታን ለመቀበል በአየር ላይ ተነጥቃ ከዚያም ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ ነው።

እግዚአብሔር ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሲናገር እንዲህ አለ፡-

ራዕይ 3፡15 በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።

16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

ይህ ጨለማ እና የክሕደት ዘመን ነው። በዚህ ቃል ውስጥ የተነገረው ፍርድ እኛን ይመለከተናል ብሎ የሚያምን ቤተክርስቲያን የለም። ቤተክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ሲጣራ መስማት የሚችሉት ግለሰቦች ብቻ ናቸው። እነዚህም ሰዎች ከቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ለመቃረን ድፍረት ያስፈልጋቸዋል።

ሐይማኖታዊ ስሕተት ከራሳቸው ቤተክርስቲያን መድረክ እንደሚጀምር ለማወቅ በቂ ማስተዋልና መረዳት ሊኖራቸው ያስፈልጋል። ከመድረክ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተሰብኮ ቢሆን ኖሮ ቤተክርስቲያን ዛሬ ላለችበት ውድቀት ባልተዳረገች ነበር።

ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ትክክል የሆኑበት ነጥብ አላቸው፤ ነገር ግን በብዙ ነጥቦች ደግሞ ተሳስተዋል። ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የተነገራት ቃል ንሰሃ ለመግባት ቅና የሚል ነው። ስለዚህ መስተካከል ያለባቸው ብዙ ስሕተቶች አሉ ማለት ነው።

እንደዚህም ሆኖ ግን እያንዳንዱ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ሙሉውን እውነት እኔ ብቻ ነኝ የያዝኩ ማለት የሚወዱ ናቸው። ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ራሳቸውን ሙሉ እንደሆኑ እና ምንም እንዳልጎደላቸው አድርገው ያስባሉ። ስለዚህ ምንም ማስተካከል እንደማያስፈልጋቸው እርግጠኛ ሆነዋል።

ውድድር በሞላበት የዛሬ ዘመን ክርስትና ውስጥ እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ራሱን ከሌሎች ቤተክርስቲያኖች የተሻለ አድርጎ ይቆጥራል።

ወደ ታላቁ መከራ እየተንደረደሩ ያሉ የዳኑ ክርስቲያኖች የሚያሳዝን ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን መቃረን፣ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን አስፈላጊ እንዳልሆኑ በመቁጠር ቸል ማለት፣ እና መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ አለማወቅ ምንም ችግር አይፈጥርም ብለው ያስባሉ።

ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ከቤተክርስቲያን ገፍቶ ያስወጣ ብቸኛው ዘመን ይህ ነው። የሜሴጅ ተከታዮች እየጠመዘዙ የሚተረጉሟቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአንድ ጥቅስ ወደ ሌላ ጥቅስ ተያይዘው መልእክት ሊሰጡ አይችሉም። ሰባቱ ነጎድጓዶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም፤ ሆኖም ግን የሜሴጅ ፓስተሮች ስለ ነጎድጓዶቹ ሰፊ ትምሕርት ያስተምራሉ። ስለ ነጎድጓዶቹ የሚሰጠው የትምሕርት ዓይነት ከመብዛቱ የተነሳ “የሜሴጅ” ተከታዮች ተከፋፍለውበት እንደተሰበረ መስታወት ተሰነጣጥቀዋል።

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

ክርስቶስ ማለትም የእግዚአብሔረ ቃል ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል። ደግሞ ጥሪውን ሲያቀርብ እንኳ ለመላዋ ቤተክርስቲያን አይደለም።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከሚወዱት የበለጠ ቤተክርስቲያናቸውን ይወዳሉ። ዋናው ዓላማቸው በሰው ዘንድ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ማትረፍ ነው።

ኢየሱስ ጥሪውን የሚያቀርበው ለግለሰቦች ብቻ ነው።

ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ እኔ ነኝ ይላል። አንድ አካል ሁለት ራሶች ሊኖሩት አይችልም። ስለዚህ እውነተኛው ራስ የሆነው ኢየሱስ ወጥቶ በደጅ ቆሟል።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ … ባል የሚስት ራስ ነውና።

የሚገርመው ነገር ግን “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ቢሆንም የቤተክርስቲያን ራስ በመሆን የክርስቶስን ቦታ መቀማት መቻሉ ነው።

ፓስተሩ “በእግዚአብሔር ልጅ ቦታ” ራስ ሆኖ ተቀምጧል።

በላቲን ይህ VICARIVS FILII DEI ይባላል። አንዳንድ የላቲን ፊደሎች ቁጥሮችን ይወክላሉ።

I = 1    V = 5     L = 50    C = 100    D = 500

V     I      C        A      R   I    V    S      F       I       L    I    I    D    E     I

5 + 1 + 100 + _ + _ + 1 + 5 + _ + _ 1 + 50 + 1 + 1 + 500 + _ + 1

 

እነዚህን ቁጥሮች ስንደምራቸው የምናገኘው 666 ነው። እርሱም የአውሬው ቁጥር ነው።

ሮማውያን ፊደሎችን በድንጋይ ላይ ሲቀርጹ በ U ፈንታ V ፊደልን ይቀርጻሉ ምክንያቱም ቀጥ ያሉ መስመሮች በድንጋይ ላይ ለመቅረጽ ቀላል ናቸው።

(ለዚህ ነው “ደብል ዩ” ወይም UU የተባለው ፊደል VV ተደርጎ የሚጻፈው፤ እርሱም ኋላ አሁን የምናውቀውን W ሆነ።)

በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመታለላችን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች በታማኝነት ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርገን በመከተል ሳናውቀው የአውሬውን ምልክት እየኮረጅን ነን።

 

ምዕራፍ 4

 

ራዕይ 4፡1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

ከዚያ በኋላም። ከምን በኋላ? ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ከተጠናቀቁ በኋላ። ከቤተክርስቲያን ዘመናት መጠናቀቅ በኋላ ዮሐንስ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ወጣ፤ ይህም የቤተክርስቲያንን መነጠቅ ያመለክታል። ወደ ሰማይ እንዲወጣ በተከፈተው በር በኩል የመለከት ድምጽ ወደ ላይ ጠራው። ወደ ሰማይ መግቢያ በር ኢየሱስ ነው።

ከ2017 ጀምሮ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን በሕዝብ ሁሉ ታውቋል። እግዚአብሔር ይህንን ሰው ለዘመኑ ምልክት አድርጎ እየተጠቀመበት ይሆን? (ትራምፕ የሚለው ስም መለከት የሚል ትርጉም አለው) እርሱም ኢየሩሳሌም ተመልሳ የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን ለማድረግ ጥረት ጀምሯል።

ዮሐንስ ወደ ላይ የወጣው ከዚህ በኋላ ማለትም ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ የሚሆኑ ነገሮችን ለማየት ነው።

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

4 በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።

አንድ እግዚአብሔር በእጁ የቤዛነትን መጽሐፍ ይዞ በዙፋኑ ተቀምጧል። ሃያ አራት ሽማግሌዎች ማለትም 12 የብሉይ ኪዳን አባቶች እና 12 የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት በዙፋኑ ዙርያ ተቀምጠዋል፤ ይህም ቤትከርስቲያን ከሙታን ተነስታ በሰማያት መቀመጧን እና በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ መሆኗን ያሳያል።

 

ምዕራፍ 5

 

መጽሐፉን መውሰድ እና መፍታት የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ነው ሊያድነን እንዲሁም ዓይናችንን ከፍቶ መጽሐፍ ቅዱስን እንድናስተውል ሊያደርገን የሚችለው።

ራዕይ 5፡4 መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።

5 ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።

ራዕይ 5፡7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።

በሰማያት የትኩረት ሁሉ ማዕከል ኢየሱስ ነው። የቤዛነትን መጽሐፍ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን መያዝና መክፈት የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።

እርሱ ብቻ ነው መጽሐፉን ወስዶ በመፍታት በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሚፈጸመውን የማዳን እቅድ መግለጥ የሚችለው። በጸጋ በነጻ ለሚቀርብልን መዳን የሚያስፈልገውን ዋጋ ከፍሎ መግዛት የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።

 

ምዕራፍ 6

 

ይህ ሚስጥር ያለበት ምዕራፍ ነው።

ኢየሱስ በሰባት ማሕተሞች ታትሞበት የታሸገውን የቤዛነት መጽሐፍ ይፈታዋል።

ነገር ግን እኛ ደግሞ ለጌታ ምጻት ዝግጁ እንሆን ዘንድ ከእነዚያ ሚስጥራት ብዙዎቹን ማወቅ ያስፈልገናል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በሰባተኛው ወይም በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሰባተኛውን መልእክተኛ ወስዶ ይህ እውነት ሲፈጸም እርሱ በአካል ተገኝቶ የተመለከተ ያህል እንዲያየው ለእርሱ በራዕይ ገለጠለት።

ከዚህም የተነሳ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መገለጥና እውቀት አገኘ።

ስለ ስድስቱ ማሕተሞች ነግሮናል፤ ሰባተኛው ግን የጌታን ምጻት በተመለከተ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ለዚህ ነው ሰባተኛው ማሕተም ከስድስቱ ማሕተሞች የተለየው። ምንነቱ በጭራሽም ስላልተገለጠ ሰባተኛው ማሕተም ምዕራፍ ስድስት ውስጥ አልተጠቀሰም።

በመጨረሻው ዘመን ነብይ አማካኝነት ማሕተሞቹ መገለጣቸው ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ከሚሆነው የማሕተሞቹ መፈታት ጋር አንድ ነው፤ አንድነቱም እነዚህ ማሕተሞች ውስጥ ተሰውሮ የነበረው መልእክት በሰባተኛው መልአክ ከመገለጡ አንጻር ነው። ይህን እውነት ወደፊት ሲፈጸም አይቶ ወደ እኛ ተመልሶ መጣና ነገረን። ስለዚህ እርሱ ሲፈቱ ያያቸው ልክ በሚፈቱበት ሰዓት እንደሚፈቱት ነው።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

እግዚአብሔር ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት የማሕተሞቹን መፈታት ገልጦ ያሳያል፤ የሚፈቱት ግን ምዕራፍ 6 ውስጥ እንደተጻፈው ከቤተክርስቲያን መነጠቅ በኋላ ነው።

 

 

ዊልያም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የሰበከበት የስብከቶች መጽሐፍ ርዕሱ The Revelation of the Seven Seals ወይም “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” ይባላል። ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱ በምድር ላይ ወደ ፊት ምን እንደሚሆን በመገለጥ አስቀድሞ ታይቷል፤ በዚያ ጊዜ ሙሽራይቱ በሰማይ ትቀመጣለች።

ነገር ግን የክስተቶቹ መገለጥ እራሱ የክስተቶቹ መፈጸም ነው ብለን ከመሳሰት እንጠበቅ።

በመገለጥ እና የተገለጠው ነገር በመፈጸሙ መካከል አንድ ትልቅ ልዩነት አለ። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ሰባቱ ማሕተሞች በእርግጥ በሚፈቱ ጊዜ የዛኔ ሚስጥራቱ በሙሉ በዝርዝር ግልጥ ይደረጋሉ።

ነገር ግን የእነዚህ ክስተቶች ቀድሞ በመገለጥ መታየት ማለትም ማሕተሞቹ ሲፈቱ በራዕይ መታየቱ እግዚአብሔር የተወሰኑ መረጃዎችን መሰወር እንዲችል ይጠቅመዋል። ስለዚህ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የማናውቀው ምንድነው?

ስለ “ሰባተኛው ማሕተም” ምንም አናውቅም፤ እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

64-0719M የመለከቶች በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

ስድስተኛው ማሕተም ታላቁን መከራ እንደሚወክል እናውቃለን።

ያ ማሕተም ሊፈታ የሚችለው በሁለቱ ነብያት ማለትም በሙሴ እና በኤልያስ ብቻ ነው፤ እነርሱም በፍጥረት ላይ የፈለጉትን የማድረግ ኃይል አላቸው። ስለዚህ እኛ በአንጻሩ ስለ ታላቁ መከራ ጥቂት ዋና ዋና ሃሳቦችን ብቻ እናውቃለን እንጂ ስለ ታላቁ መከራ የማናውቀው ብዙ ነገር አለ። የአይሁድ ነብያት ግን ሁሉን በዝርዝር ያውቃሉ። እነርሱ እኛ ከምናውቀው እጅግ አብልጠው ያውቃሉ።

63-0323 ስድስተኛው ማሕተም

አሁን ደግሞ እነዚህ ሁለት ነብያት በፍጥረት ላይ ማንኛውንም ነገር የሚያደርጉበትን ታላቅ ኃይል ይዘው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ቆመዋል። እነዚህ ነብያት ምድርን ያንቀጠቅጣሉ። ማን እንደሚያደርግም በግልጽ ይታያል። ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው ምክንያቱም የሁለቱም ሰዎች አገልግሎት እንደገና ይፈጸማል። በጣም ያስደንቃል። አሁን ይታያችኋል? ስድስተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ይገባችኋል? ሁለቱ ነብያት ናቸው።

አሁን ልብ በሉ። አትጨነቁ፤ ነገር ግን ያን ማሕተም ማን እንደሚፈታው ተመልከቱ፤ ነብያት ናቸው። አያችሁ? አሜን። ይኸው። ይገርማል፤ በንስር ዘመን ነው የምንኖረው፤ ራሳችን እላይ ደመናዎች መካከል ነው ያው። እነርሱም ስድስተኛውን ማሕተም ፈቱ። ማሕተሙን የመፍታት ኃይል አላቸው። አሜን። እነሆ ስድስተኛው ማሕተም እየተከፈተ ነው። ይታያችኋል?

ስድስተኛውን ማሕተም የሚፈቱት ሁለቱ ነብያት ስለሆኑ ቤተክርስቲያን ስለ ታላቁ መከራ ዘመን ብዙ አታውቅም። ወንበራችን ላይ ተመቻችተን ተቀምጠን የተፈጥሮ ኡደቶች ሲቋረጡ ምን እንደሚመስሉ ልናወራ እንችላለን፤ ነገር ግን እሥራኤሎች ፊት ለፊት ለአደጋ በተጋለጡበት ሥፍራ አስፈሪ ክስተት ነው የሚሆነው፤ እኛ በቃላት ብቻ የምናወራው ልዕለ ተፈጥሮአዊ መልካም ነገር ሲሆን እነርሱ በዓይናቸው ያያሉ።

አምስተኛው ማሕተም በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ስለተሰደዱ አይሁዶች ነው የሚገልጠው። ከዚህ በታች ባለው ፒራሚድ ውስጥ እነርሱ የተወከሉት በሌላ ጎን ነው። አይሁዶች ከደረሱባቸው ስደቶች ሁሉ እጅግ የከፋው 6 ሚሊዮን አይሁዳውያን የሞቱበት ሆሎኮስት የተባለው ጭፍጨፋ ነው። እርሱም ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል አስቀድሞ ማሳያ ነው። አስቀድሞ ማሳያ እንደመሆኑ መጠን ከታላቁ መከራ ጋር ሲነጻጸር ምንም ማለት አይደለም። ታላቁ መከራ ጀርመኒ ውስጥ ከተደረገው የአይሁዶች ጭፍጨፋ በብዙ እጥፍ የከፋ ነው የሚሆነው።

ምዕራፍ 6 ውስጥ በተጻፉት ስድስት ማሕተሞች እና ምዕራ 8 ውስጥ በተጠቀሰው ሰባተኛ ማሕተም መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከጌታ ምጻታ ጋር የተያያዙትን ሚስጥራት ይወክላል። ሰባተኛው ማሕተም ወይም መደምደሚያው የጌታ ምጻት ነው።

 

 

ነገር ግን ይህ ስድስተኛ ማሕተም በተጨማሪ በታላቁ መከራ ማብቂያ ላይ ስለሚገደሉት ስለ 144,000ው አይሁዳውያን ይጠቅሳል። ስለ አይሁዳውያን የቀደመ ታሪክ በደምብ እናውቃለን፤ ነገር ግን ይህ አምስተኛ ማሕተም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ በሚቀጥልበት ጊዜ ምን እንደሚፈጠር ተከታትለን ማየት አንችልም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ ምጻቱ ምንም አልነገንም፤ ደግሞም ስለ ታላቁ መከራም ብዙ አልነገረንም። ሙሽራይቱ ከታላቁ መከራ ታመልጣለች፤ ስለዚህ ስለ ታላቁ መከራ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ቆፍሮ ማጥናት እኛን ብዙም አይመለከተንም።

ኢሳይያስ 57፡1 ጻድቅ ይሞታል፥ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ …

ራዕይ 3፡10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።

ደስ የሚለው ነገር እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ታላቁ መከራ ውስጥ አታልፍም።

በአራተኛው ማሕተም አጋማሽ አካባቢ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ትሄዳለች (ከታች ቀዩን ቀስት ተመልከቱ)። አራተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ አልተገለጠም፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ተቃዋሚ ሆኖ ፈረስ ላይ የተቀመጠው የመጨረሻ ፖፕ ማን እንደሆነ አናውቅም። ስሙ ሞት ይባላል።

ሞት መግባት የሚችለው ሕይወት ከሄደ በኋላ ብቻ ነው።

ስለዚህ የመጨረሻው ፖፕ ሊገለጥ የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ከነጠቃት በኋላ ብቻ ነው። ከክርስቶስ ተቃዋሚ ኋላ ተከትለው ሞት እና ሲኦል ይመጣሉ፤ ስለዚህ ከመገመት ውጭ ብዙ ልናውቅ አንችልም ምክንያቱም በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚከሰቱ ነገሮች በተመለከተ ሙሉ መረጃ የለንም።

ስለዚህ የአራተኛው ማሕተም ሁለተኛ አጋማሽ በታላቁ መከራ ውስጥ ለሚያልፉት ለሰነፎቹ ቆነጃጅት ነው። ይህም የታላቁ መከራ ወይም የስድስተኛው ማሕተም አካል ነው። ለዚህ ነው ከላይ ባለው ስዕል ውስጥ ሁለቱ ቢጫ ክፍሎች በተመሳሳይ መስመር ላይ የተገኙት።

የሞት መልአክ የሚቀመጥበት ሐመሩ ፈረስ ከእርሱ በፊት የነበሩ የሶስት ፈረሶች ቀለም ድብልቅ ነው። ስለዚህ ያለንበት ዘመን ያለፉት ዘመናት ክፋት ሁሉ ወደ አንድነት የሚሰበሰብበት ነው።

የምዕራፍ 6 የመጀመሪያ ሰባት ዓመታት ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር አብረው ይሄዳሉ። ስምነተኛው ቁጥር (8 አዲስ ስርዓትን የሚወክል ቁጥር ነው) የሚናገረው ለሶስት ዓመት ተኩል የሚዘልቀውን ታላቁን መከራ በተመለከተ ነው።

 

 

የመጀመሪያው ማሕተም ነጭ ፈረስን ያሳያል፤ እርሱም በሐይማኖት ውስጥ ያለ አሳሳችነት ሲሆን እስከ ታላቁ መከራ ድረስ በሁሉም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ይቀጥላል። ስለዚህ ምን እንደምትሰሙ ተጠበቁ። ዛሬ ከየቤተክርስቲያኑ መድረክ በስተጀርባ አሳሳቾች አሉ። ሰይጣን ግን በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ብዙ ተምሯል፤ ስለዚህ የሰይጣን ውሸቶችም ከበፊቱ ይልቅ ረቀቅ እያሉ መጥተዋል።

የቤተክርስቲያን መድረክ የሰይጣን አሳሳች ውሸት ማስተላላፊያ ይሆናል ብሎ ማንም አይጠብቅም። ለዚህ ነው በማሳሳት የተሳካለት።

ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ብዙ የምትሰሙት ፓስተሮችን ነው። ስለዚህ ተጠንቀቁ። የምትሰሙትን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምሩ።

የአራተኛው ማሕተም የመጀመሪያ ግማሽ (ከሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር የሚገጣጠመው ቁጥር 7) ከሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ተሰባስበው አንድ ስለሚሆኑት የሐይማኖት ማሳሳቻዎች ይናገራል። ስለዚህ የዚህ ዘመን ስሕተቶች እጅግ የረቀቁ ናቸው። መሳሳታችሁን የምታውቁት እነዚህን ትምሕርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ ተከታትላችሁ ትክክል መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደማትችሁ ስታዩ ነው። ራሳችሁን ከስሕተት የምታድኑበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው። ፓስተሮች በጥቅስ ብዛት ግራ ያጋቧችኋል። ከሰው ንግግር ወስደው መገለጥ ብለው የሰጧችሁን ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ትክክል መሆኑን እንዲያሳዩዋችሁ ጠይቋቸው። አይችሉም።

በተጨማሪ ደግሞ ይህ የሐይማኖት አሳችነት በቀይ ቀለም ከተወከለው የፖለቲካ ተጽእኖ ጋር አንድነት ፈጥሯል። ፖለቲካ ሁልጊዜም አንድ ሰውን በስልጣን ላይ ይሾማል። ከዚያ በኋላ እነዚህ ከገንዘብ ኃይል ጋር አንድነት ይፈጥራሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች በወንጌል ገንዘብ እየሰሩበት ነው። ኢየሱስ ከአገልግሎቱ መጀመሪያ እንዲሁም መጨረሻ ላይ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አባሯቸዋል። በሕዝቡ እምነት ተጠቅመው ብዙ ገንዘብ ሰብስበዋል። ዘመኑ አሁንም አልተለወጠም። አሁንም ቤተክርስቲያን ትልቅ የንግድ ማዕከል ናት። ለዚህ ነው የቤተክርስቲያኖች አስተዳደር ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፈው። አሁንማ የቤተሰብ ንግድ ሆኗል።

የሐይማኖት አሳሳችነትን የሚወክለው ነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ቀስተኛ ቀስት የለውም። ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ በ860 ዓ.ም ዘውድ ጫነ።

ፖለቲካዊ ኃይልን የሚወክለው ቀይ ፈረስ ፖፑ የባርቤሪያውያን ነገዶች መሪ የሆነውን ሰው አውሮፓ ውስጥ እንደ ንጉስ አድርጎ የመሾም ስልጣን አለኝ ብሎ ዘውድ እንዲጭንለት አደረገ። በ1200 ዓ.ም ፖፕ ኤነሰንት 3ኛው የአውሮፓ ነገስታት ሁሉ ላይ ስልጣን አለኝ አለ።

የአጋንንትን አሰራር የሚወክለው ጥቁር ፈረስ በ1520 ዓ.ም በማርቲን ሉተር የተጀመረውን ተሃድሶ ሊቋቋም ወጣ፤ ምክንያቱም ማርቲን ሉተር ሕዝቡ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲመለሱ እያደረገ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን በመቃረን የሮማ ቤተክርስቲያን ሕዝቡ እውነትን አጥተው እንዲራቡ አደረገች።

ምዕራፍ 7 በመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች እና በ7ኛው ማሕተም መካከል የተቀመጠ ክፍተት ነው።

 

 

ምዕራፍ 6 ስለ ታላቁ መከራ የሚገልጠውን ስድስተኛ ማሕተም በማሳየት ይጠናቀቃል።

 

ምዕራፍ 7

 

ምዕራፍ 7 የታላቁ መከራ ዓላማ 144,000ውን አይሁዶች ለይቶ ለማውጣት እና እጅግ በጣም ብዙ ከታላቁ መከራ በፊት የዳኑ ነገር ግን በቤተክርስቲያናቸው ትምሕርቶች ተዘናግተው እንቅልፋቸውን የተኙ ሰነፍ ቆነጃጅትን ነቅንቆ ከተኙበት ለማንቃት መሆኑን ይነግረናል። አዘውትረው ወደ ቤተክርስቲያን ስለሚመላለሱ በዚያ መዳን የሚሆንላቸው መስሏቸው ተዘናግተዋል፤ ስለዚህ ከቤተክርስቲያናቸው ውጭ ሆነው ሊረዷቸው የሞከሩ ሰዎችን ሁሉ አልቀበልም አሉ። ከዚህም የተነሳ ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሊያገኙ አልቻሉም። በታላቁ መከራ አስፈሪ ሰቆቃ ውስጥ ሲገቡ ግን ለቤተክርስቲያን አባልነት የነበራቸው ፍቅር እና ለቤተክርስቲያናቸው መሪ የነበራቸው ፍቅር ወዲያ ከውስጣቸው ይወጣል። ማንም ሰው ያሳወረውን እና ያሳተውን ሰው ሊወድ አይችልም። እነዚህ ሁሉ ለቁጥር እጅግ የሚበዙ የዳኑ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሕዝብ በመንግስተ ሰማይ ውስጥ ለዘላለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ዝቅ ብለው የሚቀመጡ ዜጎች ሆነው ይኖራሉ። ሽማግሌዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ በሃላፊነት ቦታ ላይ ቢቀመጡ ኖሮ ለአስተማሪዎች ዕድል ይሰጧቸውና አስተማሪዎችም ሕዝቡን ከተጻፈው ቃል ብቻ እውነትን ያስተምሩት ነበር። ሕዝቡም ትምሕርት ቢያገኙ የሙሽራይቱ አካል በሆኑ ነበር።

 

ምዕራፍ 8

 

ይህ ምዕራፍ በሰባተኛው ማሕተም ይጀምራል።

ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።

ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ ሚስጥራት ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ነው፤ ምክንያቱም የሚናገረው ስለ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ነው፤ ስለ ዳግም ምጻቱም ሙሉ መረዳት የለንም። “ዝምታን” መተርጎም ወይም ማብራራት አይቻልም። እግዚአብሔር ምጻቱን ሚስጥር አድርጎ ለመያዝ ወስኗል። ስለ ሰባተኛው ማሕተም እናውቃለን የሚሉ ፓስተሮች እያታለሏችሁ ነው። ያወቁ መስለው ለመታየት እየታገሉ ነው። ስለዚህ በዚህ ርዕስ ላይ ዝም እንዲሉ ብትጠይቋቸው ለእናንተ መልካም ይሆንላችኋል።

ቀደም ብለን ከላይ ያየነው ምስል አናቱ ላይ ጉልላት የጎደለውን ፒራሚድ እንድናስብ ያደርገናል።

ጉልላቱ የጌታ ምጻት ነው።

እግዚአብሔርን ከዓይናችን የሚሰውርብን ታላቅ ሚስጥር አለ።

ይህም ሚስጥር የተገለጸው በፒራሚዱ እና በጉልላቱ መካከል ባለው ክፍተት ነው። ምንም ያህል ብናውቅ ይህ ክፍተት የማናውቀውን ሚስጥር ይወክላል። ክፍተቱ የእውቀታችን ክፍተት ነው።

1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤

ምዕራፍ 8 አይሁዶች ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ የሚያስገድዷቸውን በታላቁ መከራ ውስጥ የሚነፉ የመጀመሪያዎቹን አራት መለከቶች ይገልጣል። እነዚህ ሰባት መለከቶች በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አይነፉም ምክንያቱም የወንጌል መለከቶች አይደሉም፤ የፍርድ ጊዜን የሚያመለክቱ መለከቶች ናቸው። በነዚህ መለከቶች ውስጥ ምሕረት የለም።

የወንጌል መለከት ምንግዜም ምሕረትን እና ከፍርድ በፊት ማስጠንቀቂያን ያውጃል።

የመጀመሪያው መለከት ውስጥ በረዶ እና እሳተ ይወርዳሉ፤ ይህም ልክ በመጀመሪያው ፍልሰት ሙሴ እሥራኤልን ከግብጽ ይዞ ከመውጣቱ በፊት እንደሆነው ነው። ይህም በዓለም ዙርያ ያሉ አይሁዶች ሁሉ ወደ እሥራኤል መመለስ እንዳለባቸው ይነግራቸዋል።

ዘጸአት 9፡23 ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፥ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ላይ በረዶ አዘነበ።

ራዕይ 8፡7 ፊተኛውም መልአክ ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፥ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።

ሰባቱ መለከቶች የፍርድ መለከቶች እንደመሆናቸው ልዩ ናቸው።

በተለምዶ የወንጌል መልእክተኛ መልእክቱን ይዞ ሲመጣ የወንጌል መለከት መንፈሳዊ ጦርነትን የሚያውጅ መለከት ነው። ከዚያም ቤተክርስቲያን የተገለጠውን እውነት አልቀበልም ስትል እግዚአብሔር ጊዜያዊ የመቅሰፍት ፍርድ ያፈስሳል።

ወንጌሉ ልክ እንደ ዮናስ መጀመሪያ ምሕረትን ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ሰዎች ምሕረትን አልቀበልም ሲሉ ነው ፍርድ የሚከተለው።

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በሕዝብ ላይ እንድትፈርድ አይፈቅድም።

ማቴዎስ 7፡1 እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤

ስለዚህ ሰዎች የፍርድ መለከትን እንዲነፉ አልተፈቀደላቸውም። ሰዎች እንዲፈርዱ አይፈቀድላቸውም።

ሰባቱ መለከቶች ግን ፍርድን ብቻ ነው የሚያውጁት። ይህም እግዚአብሔር ቁጣውን በዓለም ላይ የሚያፈስስበት የታላቁ መከራ ጊዜ ነው። ይህንን ቁጣ በታማኝነት ሊያስፈጽሙ ለሚችሉ የሰማይ መላእክት ነው ይህ ሥራ የተሰጠው።

ደግሞም በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ተደጋግሞ የሚታይ ነገርም አለ። ምዕራፍ 2 የመጀመሪያዎቹን አራት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይገልጣል። ምዕራፍ 8 ደግሞ ስለ መጀመሪያዎቹ አራት የፍርድ መለከቶች ይናገራል።

 

 

 

ምዕራፍ 9

 

አምስተኛው መለከት ሲነፋ የሲኦል ጉድጓድ ተከፍቶ አጋንንታዊ ሰራዊት ይወጣና ዓለምን ለመቆጣጠርና ለማሸበር ይነሳል፤ ይህም በምሳሌ የተገለጠው በአጥፊ አንበጦች መልክ ነው። እነዚህ ሐይማኖታዊ አጋንንት ናቸው። በላያቸው ዘውድ የጫነ ንጉስ አላቸው። ከ1300 ዓ.ም በኋላ ወዲያው ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ጫነ፤ እስከ 1963 ድረስም ዘውድ እንደ ጫነ ቆየ። 1963 ሰባቱ ማሕተሞች የተገለጡበት ዓመት ነበር። የዚህ መገለጥ አስደናቂ ብርሃን የጨለማውን መንግስት እንደ መብረቅ መታው። በዚያው ዓመት ውስጥ ፖፑ ሞተ፤ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥም ብቸኛው ካቶሊክ ፕሬዚዳንት የነበረው ኬኔዲ ተገደለ። አዲሱ ፖፕ ፖል 6ኛው እንኳ ሳይቀር ዘውዱ ትክክል አለመሆኑን ተረድቷል፤ ምክንያቱም ሹመቱን ከተቀበለ በኋላ ዘውዱን አውልቆ አስቀመጠው፤ ከዚያ ወዲያ ሁለተኛ አልጫነውም። ስለዚህ ጥቂት ብርሃን ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥም ዘልቆ ገብቷል።

ከዚያ በኋለ ስድስተኛው መለከት ከበፊቶቹ የሚበልጡ ታላላቅ አጋንንትን ይዞ ይመጣል፤ እነዚህም አጋንንት የተወከሉት በፈረሶች ነው፤ ቁጥራቸው 200 ሚሊዮን ያህላል። የኤፍራጥስ ወንዝ ከኤደን ገነት ወጥቶ የሚፈስስ ወንዝ መሆኑ ተጽፏል፤ በተጨማሪ ደግሞ የተስፋይቱ ምድር ዳር ድንበርም ነው። ስለዚህ እነዚህ አጋንንት ሐይማኖታዊ አጋንንት ናቸው። ከአጋንንት ሁሉ ክፉ የሆኑ አጋንንት ናቸው።

ምዕራፍ 10 ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ስድስት መለከቶች እና በሰባተኛው መለከት መካከል ክፍተት እናገኛለን።

ዘኁልቁ 10፡2 ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።

ጉባኤውን ለመጥራት የሚያገለግሉ ሁለት መለከቶች በታላቁ መከራ ጊዜ የሚመጡትን ሙሴ እና ኤልያስን ይወክላሉ፤ እነርሱም አይሁዶችን በዓለም ዙርያ ካሉበት ሁሉ ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ ይጠሩዋቸዋል። አይሁዶች እነዚህን ሁለት የወንጌል መለከቶች ይቀበላሉ። የቀረው ዓለም ግን የፍርድ መለከት ነው የሚነፋለት።

በታላቁ መከራ ጊዜ ድምጻቸውን የሚያሰሙት የፍርድ መለከቶች ወደ እስራኤል ለመመለስ የሚያመነቱትን አይሁዶች እንዲመለሱ ያስገድዷቸዋል።

ታላቁ መከራ የማያቋርጥ ፍርድ የሚደረግበት ዘመን ነው። ስለዚህ አይሁዶች እንዴት ነው የሚተርፉት? መትረፍ ይችሉ ዘንድ ስለ ታላቁ መከራ እኛ ከምናውቀው በላይ በዝርዝር ማወቅ አለባቸው።

ዊልያም ብራንሐም የመጣው እርሱ ያቀረበው መልእክት ለእኛ ለአሕዛብ ቀስ በቀስ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲገልጥልን እና አእምሮዋችንን ሊከፍትልን ነው። እርሱም አገልግሎቱን በ1933 ከጀመረ በኋላ ቀስ በቀስ እግዚአብሔር ዓይኖቹን በመክፈት የቃሉን ሚስጥራት ገለጠለት። ከሰላሳ ሁለት ዓመታት በኋላም በ1965 እግዚአብሔር ወሰደው። እርሱም ከዚህ ዓለም በተሰናበተበት ጊዜ በቂ መጻሕፍት እና በድምጽ ተቀርጸው የተዘጋጁ መልእክቶችን ስለተወልን በካሴቶች እና በኤምፒ3 አማካኝነት ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በኢንተርኔት እና በመጻሕፍቱ አማካኝነት ጌታ ሲመጣ ለመቀበል ማድረግ የሚያስፈልገንን ዝግጅት እናደርግ ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መማር እንችላለን። እርሱ ከሞተ ከሃምሳ ዓመታት በኋላ እንኳ እስካሁን እርሱ የተናገራቸውን ቃሎች በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ጥረት እያደረግን ነን። ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች ግን የንግግሩን ቃሎች እንደ ገደል ማሚቶ በመደጋገም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ባለማመሳከራቸው መግቢያና መውጫው ጠፍቶባቸዋል። የሜሴጅ ፓስተሮች በ2016 ሒላሪ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆና ትመረጣለች ብለው ነበር። እርሷ ግን በምርጫው ተሸነፈች፤ በዚህም የሜሴጅ ፓስተሮች ምን ያህል ከእግዚአብሔር ሃሳብ የራቁ መሆናቸው ተገለጠ።

ሁለቱ የእሥራኤል ነብያት 144,000 አይሁዶችን ለይቶ ለማውጣት የተሰጣቸው ጊዜ ሶስት ዓመት ከግማሽ ብቻ ነው። ስለዚህ መጽሐፉን ገልጠው ሚስጥራቱን የሚማሩበት ጊዜ የላቸውም። ሚስጥራቱ አስቀድሞ በዊልያም ብራንሐም ተገልጠዋል፤ እርሱም ከታላቁ መከራ ሚስጥራት በቀር ሌሎቹን ሚስጥራት ገልጧቸዋል። የታላቁ መከራ ሚስጥራት ሙሽራይቱን አይመለከቱም ምክንያቱም በመከራው ሰዓት ሙሽራይቱ ሰማይ ውስጥ ነው የምትሆነው።

 

ምዕራፍ 10

 

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

 

 

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

 

ብርቱው መልአክ ከደመናው ጋር በጭራሽ አይመሳሰልም።

 

 

ደመናው መጀመሪያ በተነሳው ፎቶ ውስጥ የፊት ምስል አልነበረም። ከፎቶው ላይ በተደረገው ቅጂ ውስጥ ግን በስሱ የፊት ምስል ይታይ ነበረ። መልአኩ ደግሞ ፊቱ እንደ ፀሃይ የደመቀ ፊት ነው። ዓይን የሚያጠፋ ድምቀት።

በ1963 የታየው ደመና ራስ ብቻ እንጂ አካል አልነበረውም። መልአኩ ግን በደመና የተሸፈነ አካል አለው። እግሮቹ ሁለት ደማቅ የእሳት አምዶች ናቸው። በ1963 የታየው ደመና ውስጥ እግሮች አልነበሩም። የሚታዩ ሁለት የእሳት ነበልባሎችም አልነበሩም። መልአኩ ወደ ምድር እንደሚወርድ ተጽፏል፤ ደመናው ግን ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ደቂቃዎች ከመታየት በቀር ወደ ምድር አልወረደም። በ43 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ እንደሆነ ከምዕራፍ ወደ ምስራቅ ተንቀሳቀሰ እንጂ ወደ ምድር አልመጣም። ይህ ደመና ከፍላግስታፍ በስተሰሜን ነው ፎቶ የተነሳው። ወንድም ብራንሐም ደግሞ ስለ ደመናው ምንም አላወቀም ነበር። በዚያ ሰዓት እርሱ 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቆ በሚገኘው የታክሰን ከተማ ውስጥ ነበር። በዚያ ሰዓት ፍላግስታፍ ውስጥ ደመናው የሚወርድለት መንፈሳዊ ሰው አልነበረም።

ስለዚህ የ1963ቱ ደመና የዚህ ጥቅስ ፍጻሜ ነው ብሎ መናገር ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ኢየሱስ በመላእክት አለቃ መልክ ሙታንን ከምድር እና ከባሕር ሊያስነሳ ይመጣል። እንደ መልአክ መምጣ “የጌታ ምጻት” ተብሎ አይቆጠርም ምክንያቱም የጌታ ምጻት የሚሆነው ጌታ በሰብዓዊ አካሉ ወደ ምድር ሲመጣ ነው።

64-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ይህ መልእክት የቀረበው በ1964 ማለትም ደመናው ከታየ እና ማሕተሞቹ ከተገለጡ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው። እርሱ ግን ስለ መልአኩ መምጣት ገና ወደ ፊት እንደ ሆነ አድርጎ ነበር የሚናገረው።

ይህ የአልአዛር ትንሳኤ ሳይሆን እናንተ ከሙታን የምትነሱበት ትንሳኤ ነው፤ ጌታ ሳይመጣ ከሞታችሁ በዚህ ትንሳኤ ጊዜ ትነሳላችሁ። ለሙሽራይቱም ከዚያ በኋላ ዘመን ወይም ጊዜ መቁጠር የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም ወደ ዘላለም ውስጥ ትገባለች። ይህ ለሙሽራይቱ የዘመን ቁጥር የሚያበቃበት የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ነው፤ ምክንያቱም አካላቸው ወደማይሞት አካል ስለሚለወጥ ዘመን ወይም ጊዜ በእነርሱ ላይ አንዳችም ተጽእኖ የለውም። አዲሱን አካላችሁን ስለትለብሱ አትለወጡም፤ ደግሞም አታረጁም።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ሰዎች ሁሉ በምድር ወይም ባሕር ውስጥ ነው የተቀበሩት። ክርስቶስ እንደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ሆኖ በትንሳኤው ይመጣና ለራሱ ይወስዳቸዋል።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

ድምጹ የሰባተኛው መልአክ መልእክት ሲሆን ዓላማውም ሙሽራይቱን ለዳግም ምጻት ማዘጋጀት ነው።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

ይህ ሙታንን የሚያስነሳቸው የመላእክት አለቃ ድምጽ ነው።

ራዕይ 10፡3 ውስጥ የተጻፉት ሁለቱም ቃሎች ስለ ትንሳኤ ነው የሚናገሩት።

ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤

ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

ባለ ሶስት ዳይሜንሽን ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው፤ እነዚህም ሶስት ዳይሜንሽኖች ዝርመት፣ ስፋት፣ እና ከፍታ ናቸው። በተጨማሪም የጊዜ እሥረኞች ነን፤ እርሱም አራተኛው ዳይሜንሽን ነው። ዙርያችንን በከበበን የጊዜ አጥር ውስጥ ሆነን ከድሮ ወደ ዘንድሮ እና ወደ ፊት ስንጓዝ በጊዜ ላይ ምንም አቅም የለንም።

 

 

በምድር ላይ እየኖርን ሳለን ከጊዜ እስር ቤት የምንወጣበት ብቸኛው መንገድ አዲሱን የማይሞተውን አካል መልበስ ነው። እድሜያችን ሲጨምር ጊዜ እንድንለወጥ ያደርገናል። ጊዜ እስከ 25ኛው ዕድሜያችን ድረስ በጥበብ ብዙም ሳንጨምር በአካላዊ ብርታት ግን ብዙ አቅም እንድንጨምር ያደርገናል። ከዚያ በኋላ ግን አካላዊ ጉልበታችን እየቀነሰ ነው የሚሄደው ምክንያቱም ጊዜ ከመበስበስ ጋር የተቆራኘ ነው። በስተመጨረሻም እንሞታለን፤ ይህም ደስ የማያሰኝ ነገር ነው።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

ከሙታን ትንሳኤ በኋላ ከሞት ከተነሱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሰማይ ተነጥቀን እንድንሄድ አካላችን መለወጥ አለበት።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

ይህ እውነታ ከላይ ባለው ስዕል ውስጥ በሰማያዊው መስመር ተገልጧል።

ሰማይ ከምድር እና ከጊዜ ተነጥሎ ነው የተገለጸው። ሰማይ ከጊዜ ውጭ ነው ምክንያቱም ሰማይ ውስጥ የጊዜ ቆጠራ የለም። ይህ ምን ማለት ነው?

ራዕይ 10፡6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ ወደ ፊት አይዘገይም፥ አለ።

“ወደ ፊት አይዘገይም።”

ይህ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ የምትሄድበት ጊዜ ነው፤ በዚያም ጊዜ እና የመበስበስ ሕግ በእነርሱ ላይ አይሰለጥንም። ጊዜ በማይቆጠርበት ዓለም ውስጥ ምንም ነገር አይበላሽም። በሽታም የለም፤ ምክንያቱም በሽታ ራሱ የመበስበስ ውጤት ነው። በዚያ ሞት የለም ምክንያቱም ጊዜ በሌለበት ዓለም ውስጥ ምንም ነገር ሕይወቱ አያበቃም። ሐጥያትም የለም ምክንያቱም ሞት ከሐጥያት ጋር ነው የገባው። ሞት የሰዎች ዕድሜ ውስን እንዲሆን አደረገ ምክንያቱም ሰዎች ኖረው ይደክሙና ይሞቱ ነበር።

ስለዚህ ሉሲፈር በሰማይ ውስጥ ሆኖ ሐጥያት በሰራ ጊዜ ባለ ሶስት ዳይሜንሽን ምድር እና የቀረው ዓለም ተፈጥረው ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሉሲፈር እንዲኖርበት አራተኛ የጊዜ ዳይሜንሽን አዘጋጀ።

ሉሲፈር ወደ ሰይጣንነት ስለተቀየረ የሚኖርበት መንፈሳዊ ዳይሜንሽን ያስፈልገው ነበር። እግዚአብሔር እርሱን እና የጥልቁን ጉድጓድ በጊዜ ዳይሜንሽን ውስጥ አስቀመጣቸው፤ ከዚያም አንድ ቀን በእሳት ባሕር ውስጥ ተቃጥሎ ይጠፋል። ሰይጣን ለውስን ጊዜ ብቻ ነው የሚኖረው።

በሰማያት በፊትም የተለያዩ ነገሮች ሲከናወኑ ደቂቃዎች ያልፉ ነበር፤ ነገር ግን ሉሲፈር ሰማይ ውስጥ ሐጥያት እስከ ሰራበት ጊዜ ድረስ አንዳችም አሉታዊ ውጤቶች አልነበሩም።

ጊዜ መቆጠር የተጀመረው ሰይጣን የሰራው ሐጥያት አሉታዊ ውጤቶችን ማስከተል ሲጀምር ነው።

ሰይጣን የስርዓት መቃወስን አመጣ። ጊዜ የስርዓት መቃወስ ምልክት ነው። የስርዓት መቃወስ ሲበዛ ጊዜ ለምንለው ክስተት አቅጣጫ ያበጅለታል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰይጣንን እና ነገሮች እንዲበሰብሱ የማድረግ ችሎታውን ለበቻ ጊዜ የተባለ በዓይን የማይታይ መንፈሳዊ ዳይሜንሽን ውስጥ አስሮ አስቀመጠው። ሰይጣን ማለትም የመልካም እና የክፉ ነገር መንፈስ ኤደን ገነት ውስጥ መልካም እና ክፉውን በምታሳውቅ ዛፍ ተመስሎ ነው የተገለጠው።

እግዚአብሔር ሉሲፈርን ወደ ዲያብሎስነት ቀየረውና እሚኖርበትን መንፈሳዊ ክልል ፈጠረለትይህም መኖሪያው እርሱ በአጋንንታዊ ዓለም ውስጥ በሚያደርጋቸው “መልካም እና ክፉ” ላይ ገደብ የሚደረግበት ጊዜ የተባለ ዳይሜንሽን ነው። በዚህ መንገድ ሐጥያት ጊዜ የተባለውን ዳይሜንሽን አስከተለ በዚህ ዳይሜንሽን ውስጥ መልካም (አሳሳች) እና ክፉ (ጎጂ) ሥራዎችን መስራት የሚችሉ መናፍስት ያሉበት ጥልቅ ጉድጓድ አለ።

አዳም ከጊዜ ክልል ውጭ ስለተፈጠረ ይህ የመልካም እና ክፉ መናፍስት የጊዜ ዳይሜንሽን ምንም ተጽእኖ አላሳደረበትም። ሐጥያት በሰራ ጊዜ በሶስት ዳይሜንሽኖች ውስጥ የነበረችዋ ምድር ጊዜ በሚባል አራተኛ ዳይሜንሽን እስር ቤት ውስጥ ገባች። ከሐጥያት የተነሳ የተረገመችዋ ምድር የምትኖረው ለውስን ጊዜ ነው። ሰይጣን እነዚህን መንፈሳዊ ተጽእኖዎችን ከፍ ካለው የጊዜ ዳይሜንሽን አምጥቷቸው በእነርሱ አማካኝነት ምድር ላይ ሞት፣ ሲኦል እና መቃብር የመሳሰሉ ክፉ ነገሮችን ሔዋን በከፈተችለት በር በኩል ለቀቃቸው። የሞቱ ሰዎች መንፈሶችም በአራተኘው የመልካም እና ክፉ ዳይሜንሽን ውስጥ ተቀምጠው እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ይጠብቃሉ። በመልካም ሥራቸው ይታመናሉ። ነገር ግን ሐጥያቶቻቸው ክፉ ሥራዎች ናቸው። “መልካም እና ክፉ” ቅልቅል ስለሆነ ንጹህ አይደለም ምክንያቱም በዚህ መንፈሳዊ አራተኛ ዳይሜንሽን ውስጥ መልካም ነገር ሁሉ በክፉ ተመርዟል። አደንዛዥ እጾች ለጥቂት ሰዓት ሰዎች “እንዲመረቅኑ” እና ደስታ እንዲሰማቸው ያደርጋሉ፤ ከዚያ በኋላ ግን ረጃጅም ጥፍሮች እንዳሉት አወሬ የሰዎችን አንጎል ይበጫጭቃሉ።

የዘላለም ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱ መልካም ብቻ ነው።

የሙሽራይቱ አካላት አዲሱ አካላቸውን ሲለብሱ ከአራተኛው ዳይሜንሽን አምልጠው ስለሚወጡ በውሰጡ ባሉ ክፉ ተጽእኖዎች ጉዳት ሊደርስባቸው አይችልም።

ስለዚህ ጊዜ ሲያበቃላችሁ ሐጥያትም በእናንተ ላይ ያለው ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ ይቋረጣል።

ራዕይ 20፡14 ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።

በአራተኛው ዳይሜንሽን የሚኖሩ መንፈሳዊ ፍጡራን ሁሉ መጨረሻቸው የእሳት ባሕር ውስጥ ነው። እነርሱ በሙሉ ተቃጥለው እስኪጠፉ ድረስ ጊዜ ይቀጥላል። በስተመጨረሻ ሰይጣን ሲጠፋ የዛኔ የአራተኛው ዳይሜንሽን ፍጻሜ ይሆናል። ከዚያ ወዲያ አራተኛው ዳይሜንሽን በማንም ላይ ክፉ ተጽእኖ ማድረግ አይችልም። በዚያን ጊዜ ጊዜ የሚባለው ነገር ህልውናው ያበቃል፤ ምክንያቱም በዓለም ላይ ያሉ ግጭቶችን እና ቀውሶችን ሁሉ ይዞ የመጣው ጊዜ የተባለው ዳይሜንሽን ነው።

የሙሽራይቱ አካላት ከጊዜ ውጭ መኖር የሚችሉት በአዲሱ አካላቸው አማካኘነት ብቻ ነው። አሁን የለበስነው አካል ያረጃል ይበሰብሳል፤ አዲሱን አካል የለበሱ ግን አያረጁም አይበሰብሱም። ከሙሽራይቱ አካልት ውጭ የቀረው ዓለም ግን በጊዜ ውስጥ መኖሩን ይቀጥላል። ይህም ጊዜ የሶስት ዓመት ተኩል መከራ እና እርሱን ተከትሎ የሚመጣው የ1,000 ዓመት ሰላም ነው። ከዚያ በኋላ የፍርድ ቀን ይመጣል። ሰነፎቹ ቆነጃጅት አስቀድመው ስለዳኑ የከበረ አካል ይለብሱ እና ከጊዜ ቀጠና ይወጣሉ። ወደ እሳት ባሕር እንዲገቡ የተፈረደባቸው ደግሞ ቅጣታቸውን ጨርሰው ይደመሰሳሉ። ለእነርሱ የጊዜ ማብቂያ ሲጠፉ ነው።

የሙሽራይቱ አካላት ግን የከበረ አካላቸውን ከለበሱበት ሰዓት ጀምሮ ከጊዜ ክልል ውጭ ናቸው። ከዚያ በኋላም ቢሆን እየኖሩ ሳለ ደቂቃዎች ያልፋሉ ግን በእነርሱ ላይ አንዳችም አሉታዊ ተጽእኖ አይኖራቸውም፤ ምክንያቱም አሮጌው ተፈጥሮዋቸው ተወግዶ በደምስራቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለሚኖር ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራቸዋል። ከዚያ በኋላ በጊዜ ዳይሜንሽን ውስጥ የነበረው ክፋት በፍጹም ሊጎዳቸው ወይም ተጽእኖ ሊያደርግባቸው አይችልም። አዳም ሲፈጠር እንደነበረው ያለ ሐጥያት ይኖራሉ። ሆኖም ግን ልዩነት አለ። ሔዋን ስለ ሐጥያት ምንም እውቀት አልነበራትም፤ ነገር ግን የማወቅ ጉጉት የነበረው ሰብዓዊ ፍላጎቷ ሐጥያትን እንድትመራመር አደረጋት።

እግዚአብሔር አስፈሪ እና አስጨናቂ ወደሆነ የሐጥያት ዓለም ውስጥ ጥሎናል። ስለዚህ ሰማይ ውስጥ ስንገባ ፈጽሞ የሐጥያት ፍላጎት አይኖረንም ምክንያቱም አስከፊነቱን በደምብ አይተናል። ብንረሳ እንኳ በኢየሱስ እጆች ላይ ያሉ ጠባሳዎች ያስታውሱናል። የእኛ ሐጥያት ነው እነዚያን ጠባሳዎች በእጆቹ ላይ ያሳረፈበት። ስለዚህ ሰማይ ውስጥ ስንሆን አንዳችም ትምክህት አይኖረንም፤ ምስጋና ብቻ ነው የሚኖረን።

ጊዜ ካበቃ በኋላ ሙሽራይቱ ሙሉ በሙሉ ያለ ሐጥያት መኖር ትችላለች።

አንድ እውነታ እናካፍላችሁ፡- ብርቱው መልአክ የሚወርደው መጽሐፉን ሊከፍት አይደለም።

ብርቱው መልአክ የሚወርደው መጽሐፉ ስለተከፈተ ነው፤ የእግዚአብሔር ሚስጥርም ስለተፈጸመ ነው።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

ይህኛው ግን ከምድር አይደለም የመጣው። እርሱ ከሰማይ ነው የወረደው፤ ምክንያቱም ሚስጥሩ በሙሉ ተጠናቋል። ሚስጥሩ ሲጠናቀቅ ደግሞ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከእንግዲህ አይዘገይም” ከዚያ በኋላ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።

እንደው ለመነጠቅ ወደሚያበቃው እምነት ውስጥ እንዴት አድርገን እንደምንገባ የሚያሳውቀን ነገር ቢሆንስ? ነውን? እንሮጣለንን፤ ከግድግዳዎቹ በላይ እንዘላለንን? አንድ ነገር ሊሆንና እነዚህ ያረጁ የተበላሹ ስጋዎቻችን ሊለወጡ ጊዜው ቀርቦ ይሆን?

ብርቱው መልአክ የሚወርደው ሚስጥሩ በሙሉ ሲፈጸም ሙሉ በሙሉ ሲገለጥ ነው።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ፣ መጽሐፉ ውስጥ የነበሩ ማሕተሞች፤ የተሰበኩት ሚስጥራት፡- ጽድቅ፣ መቀደስ፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ ፕሮቴስታንቶች! የእነዚህ ሁሉ ጦርነት ቃሉ ውስጥ ብዙ ያልተቋጩ ጫፎችን ትተው ሲሄዱ ሰባተኛው መልአክ ይመጣና ሁሉንም ይሰበስባቸዋል፤ ያብራራቸዋል። አያችሁ? ከዚያም እርሱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ።

የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር የተጻፈው ቃል ሚስጥር አካል አይደለም፤ የተጻፈው ቃል ሚስጥር በሰባተኛው መልአክ አገልግሎት ነው የሚገለጠው።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ቃሉ ይመጣል። እነዚህ ሚስጥራት በሙሉ ተፈጽመው ሲያልቁ የዚያን ጊዜ “በውጥ የተጻፈው መጽሐፍ” ይጠናቀቃል።

ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን ለመግለጥ ነው የመጣው እንጂ እንደ ሰባቱ ነጎድጓዶች፣ የኢየሱስ አዲሱ ስም፣ እና የጌታ ምጻት የመሳሰሉ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ለመግለጥ አይደለም። እነዚህን ሚስጥራት በተመለከተ ምንም አናውቅም።

62-1230E ይህ የፍጻሜው ምልክት ነውን

ራዕይ 5፡1ን አስተውሉ። አሁን ይህንን አድምጡ።

በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው እጅ ውስጥ መጽሐፍ አየሁ፤ መጽሐፉም በውሰጡ የተጻፈበት (ጽሕፈቱ በውስጥ በኩል ነበር) በጀርባው ደግሞ በሰባት ማሕተሞች የታተመ ነበር።

መጽሐፉ በውስጡ ጽሕፈት አለበት። ጀርባው ግን ሰባት ማሕተሞች አሉበት፤ በጀርባው ላይ ማለትም እነዚህ ማሕተሞች በውስጡ ያልተጻፉ ናቸው። አሁን ባለ ራዕዩ ዮሐንስ የሚናገረውን ስሙ። አሁን ልብ በሉ፤ የተጻፈው መጽሐፉ ውስጥ አይደለም።

“በሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ሚስጥር በሙሉ ይፈጸማል።” በዚያ ዘመን ሁሉም ተደርጎ ይጠናቀቃል።

… “በዚያን ዘመን ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ ተፈጽመው ይጠናቀቃሉ።”

ብርቱው መልአክ በእጁ የያዘው የተከፈተ መጽሐፍ በምሳሌነት የሚገልጠው ሰባተኛው መልአክ በመጣ ጊዜ የገለጣቸውን ሚስጥራት ነው።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ወንድም ብራንሐም በታህሳስ 1965 ሚስጥራቱን ሰብኮ ጨረሰ። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው መጽሐፉ ተከፍቷል ማለት የሚቻለው ምክንያቱም ሚስጥራቱ ተገልጠዋል። ከዚያ ጊዜ በፊት መልአኩ ወደ ምድር ሊወርድ አይችልም።

ኢየሱስ ለምን ሁለት ጊዜ መሬት ላይ በእጁ እንደጻፈ ማብራራት ካልቻላችሁ መጽሐፉ ለእናንተ አልተከፈተም። ሰባተኛው መልአክ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መገለጥ ሊሰጠን ነው የመጣው፤ ይህም መገለጥ ለዳግም ምጻት ያዘጋጀናል። ያ መገለጥ ሙሉ ሆኖ ከመጣ በኋላ (ታህሳስ 1965 ነበር የተጠናቀቀው) ከዚያ በኋላ ብቻ ነው የተከፈተ መጽሐፍ በእጁ የያዘው መልአክ መምጣት የሚችለው። ከታህሳስ 1965 በፊት ያልተገለጡ ሚስጥራት ነበሩ፤ ይህም መጽሐፉ እስከዚያ ጊዜ ድረስ አልተከፈተም ነበር ማለት ነው።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ነገር ግን ይህ ከምድር አልመጣም። እርሱ የመጣው ከሰማይ ነው ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመዋል። ሚስጥሩም በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ዘመን አይኖርም” በዚያን ጊዜም ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።

እንደው ለመነጠቅ ወደሚያበቃው እምነት ውስጥ እንዴት አድርገን እንደምንገባ የሚያሳውቀን ነገር ቢሆንስ? ነውን? እንሮጣለንን፤ ከግድግዳዎቹ በላይ እንዘላለንን? አንድ ነገር ሊሆንና እነዚህ ያረጁ የተበላሹ ስጋዎቻችን ሊለወጡ ጊዜው ቀርቦ ይሆን?

መልአኩ የሚወርደው ሚስጥሩ ተፈጽሞ ስለተጠናቀቀ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ጊዜ ያበቃና ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ።

63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቅ ወደ ፍርድ አያመጣውም

ኦ የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉ ሰዎች ምንኛ አስደናቂ እንደሚሆኑ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ! እንዲህ ይላል፡- “በሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ ቅጥሩንም ይዘላሉ።” አዎ፤ የሞት ሰራዊት ሊይዛቸው አይችልም፤ በመካከሉ ሮጣ ታልፋለች። በፍጥረታዊው እና በልዕለ ተፈጥሮአዊው መካከል ያለውን “ግድግዳ” ዘላው ታልፈዋለች፤ ከዚያም ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ትገባለች። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው በጣም እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።

ሙሽራይቱ በቁጥር ብዙ አይደለችም። የጊዜ ግድግዳ ከልዕለ ተፈጥሮአዊው ዓለም ይለየናል። ሙታን ሲነሱ እነርሱ እና በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት በሞት እና በአጋንንት ሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ እነርሱም ሊያስቆሟቸው አይችሉም፤ ስለዚህ በትንሳኤ የተነሱት ሰዎች እኛ ሕያው የነበሩት የሙሽራይቱ አካላት ከጊዜ ቅጥር በላይ ዘለው ወደ ዘላለማዊው ዓለም ተነጥቀው ይሄዳሉ።

2ኛ ሳሙኤል 22፡30 በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

በእውነቱ እነዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸውን፤ ቃላቸውን ሊናገሩ ተዘጋጅተው ይሆን፤ በሕብረት የተሰበሰበው ታናሽ ወገን ለመነጠቅ የሚያበቃውን እምነት ሊቀበል ይሆን፤ እርሱ ሲመጣ ተነጥቀው ለመሄድ? እነዚህ መላእክት በሚመጡበት ፍጥነት “እንለወጣለንና” የምንለወጠውም “ከመቅስፈት ወይም በዓይን ጥቅሻ ፍጥነት ነው” ከዚያም ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል አንቀላፍተው ከነበሩት ጋር አብረን እንነጠቃለን።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም። አሆን፤ እውነት ነው። እኔም ደግሞ በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ እንዴት እንደምትዘጋጅ እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምትቀበል ይገለጥላታል። ምክንያቱም አሁን ባለን እምነት መነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ መጨመር ወደፊት መግፋት አለብን፤ ለመለኮታዊ ፈውስ እንኳ የሚበቃ እምነት የለንም። ከመቅጽፈት የምንለወጥበትና ከዚህ ምድር ተነጥቀን የምንሄድበት በቂ እምነት ሊኖረን ይገባል

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት አካላችን በሚለወጥበት ሰዓት ነው። አሁን በለበስነው ሐጥያተኛ ስጋችን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል መነጠቅ አንችልም።

ሰባቱ ነጎድጓዶች በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት አካላቸው በሚለወጥበት ሰዓት ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት፤ ድምጻቸውን የሚያሰሙትም ለሙሽራይቱ አካላት ጌታን ለመቀበል በአየር ላይ የሚነጠቁበትን እምነት ለመስጠት ነው። አሁን በለበስነው ስጋ ውስጥ ሆነን አየር ውስጥ ወደ ላይ እየተራመድን መንሳፈፍ አንችልም። ይህን ለማድረግ አዲስ አካል ያስፈልጋችኋል። ይህ መነጠቅ በሚፈጸምበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ሕጎችን ጥሶ ነው የሚፈጸመው።

ስለዚህ በዚያው ሰዓት ሰባቱ ነጎድጓዶች ለሁለቱ ነብያት የተፈጥሮ ሕጎችን የሚያስቆሙበትን ኃይል ይሰጧቸው ዘንድ ድምጻቸውን ያሰማሉ፤ በዚህም ኃይል ተጠቅመው ሁለቱ ነብያት የተፈጥሮ ሕጎችን እያቋረጡ “ተፈጥሮ ቀውስ ውስጥ ስትገባ” በተፈጥሮ መቃወስ አማካኝነት ለአይሁዳውያን ጥበቃ ያደርጋሉ።

በ2018 ዓ.ም ቱርክ ከሰሜናዊው አፍሪን ክልል የተወሰኑ ግዛቶችን ለመቆጣጠር ዘመናዊ ታንኮችን ወደ ሶርያ ላከች። በታላቁ መከራ ውስጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ እጅግ ብዙ ታንኮችን ወደ እሥራኤል ሲልክ ሙሴ ልክ ቆሬ እና ዳታን መሬት አፏን ከፍታ እንደዋጠቻቸው የምድር መንቀጥቀጥ አስነስቶ ታንኮቹ እንዲዋጡ ያደርጋል።

ዘኁልቁ 16፡31 እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤

32 ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ዕቃዎቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።

33 እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።

ራሺያ እሥራኤልን ለማጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር አውሮፕላኖችን ብትልክ ሙሴ ሰማዩን በዝንቦች ወይም በአንበጣ መንጋ ይሞላውና አንበጦቹ የአውሮፕላኖቹን ሞተሮች ሞልተው ሲያኗቸው አውሮፕላኖቹ ይከሰከሳሉ።

የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ሰይፍ ተመቶ መጥፋት አለበት፤ ይህም የእግዚአብሔር ሰይፍ በሁለቱ ነብያት አፍ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ስለተቃወሟት ብላ ለመግደል በምድር ነገስታት ሰይፍ የተመሰለውን የፖለቲካ ኃይል ተጠቅማለች።

63-0321 አራተኛው ማሕተም

ትናንትና ማታ ትልቅ ሰይፉን ይዞ ለመግደል ሲመጣ አግኝተነው ነበር። ነገር ግን እርሱ እራሱ በሰይፍ እንደሚገደል አይተናል፤ ይህም የቃሉ ሰይፍ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፤ በሁለት ወገን የተሳለው ሰይፍ ይገድለዋል፤ ያጋድመዋል። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋር የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

ከአፉ በሚወጣው ቃል ይገደላል፤ ይህም ቃል ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው። እነርሱም ከፈለጉ ከአንድ መቶ ቢሊዮን በላይ ዝንቦችን መጥራት ይችላሉ። አሜን። እነርሱ የሚናገሩት ሁሉ ይፈጸማል፤ ምክንያቱም የእነርሱ ንግግር በሙሉ ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ የእግዚአብሔር ቃል ነው። አሜን።

 

ሰባቱ ነጎጓዶች ሙሽራይቱ ስትነጠቅ እና ሁለቱ ነብያት ለአይሁድ አገልግሎታቸውን ሲጀምሩ ብቻ ነው ድምጻቸውን ማሰማት የሚችሉት፤ ምክንያቱም ሰባቱ ነጎድጓዶች ለአይሁድም ለአሕዛብም ነው የሚናገሩት። ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥራዊ ክስተቶች ናቸው፤ ስለነርሱ ምንም ስላልተገለጠ የምናውቀው ምንም የለም። ነገር ግን አንዴ መናገር ከጀመሩ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ የምናውቅ ከሆነ በነጎድጓዶቹ ድምጽ መመራት እንድንችል የሚያስፈልጉንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍንጮች መከተል እንችላለን።

63-0324E ሰባተኛው ማሕተም

“ወንድም ብራንሐም፡ ይህ መችነው የሚሆነው?” ልነግራችሁ አልችልም። እኔ አላውቅም። ነገር ግን ከዚህ በኋላ ባሉት ቀናት ምድር ላይ ድጋሚ ባንገናኝ ወዲያ ማዶ ተሻግረን -- በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንገናኛለን። እናንተም በዚያ ቤት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣው መገለጥ(እንደ ሌሎቹ መገለጦች ሁሉ) እንደዚሁ… የዚያ ማሕትም አንዱ ሚስጥር፤ ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ምንም እንከን አይወጣላቸውም፤ ምክንያቱም ማንም ስለ ነጎድጓዶቹ ቃል አያውቅም፤ ምክንያቱም ምንም አልተጻፈም።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ገና ወደፊት ነበሩ። “ይህ መች ነው የሚሆነው?” ደመናው ከዚህ ቀን አንድ ወር ቀድሞ ነበር ፎቶ የተነሳው። ስለዚህ ደመናው ነጎድጓዶቹ አይደለም።

ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ማናችንም ምንም አናውቅም።

ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች በምታስቡት ነገር ሁሉ ተሳስታችኋል። ራሳችሁን እና ሌሎችን እያታለላችሁ ነው።

63-0320 ሶስተኛው ማሕተም

ሙሽራይቱ እስካሁን መነቃቃት አላገኛትም። አያችሁ? እስካሁን መነቃቃት አልመጣም፤ ሙሽራይቱን ሊያነቃቃ የሚችል የእግዚአብሔር መገለጥ አለመጣም። አያችሁ? እኛም ይህንን መነቃቃት እየተጠባበቅን ነን። ሙሽራይቱን ለማነቃቃት እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸው መምጣት አለበት። እርሱም ይልከዋል። ቃል ገብቷልና። አሁን ልብ በሉ። እርሷ ሞታለች።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን እስኪያሰሙ ድረስ ሙሽራይቱ በሞት ውስጥ ናት።

ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

እኩለ ሌሊት ላይ የሚሰማው ጩኸት ሰባቱ ነጎድጓዶች የሚያስነሱት ብዙ ታላላቅ ነውጦች የሞሉበት ክስተት ነው፤ እነዚህም ነውጦች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ሁሉ፣ ሙሽራይቱን እና ሰነፎቹን ቆነጃጅት ሁሉ ከእንቅልፍ ያነቋቸዋል።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ቆነጃጅቱ በሙሉ (ንጸህ ቤተክርስቲያኖች) ልባሞቹን እና ሰነፎቹን ጨምሮ ሁሉም እንቅልፍ ተኝተው ነበር። ይህም ሜሴጅ እና ዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያኖች በሙሉ አሁን ያሉበት ሁኔታ ነው። በፓስተሮቻቸው እሹሩሩ አማካኝነት እንቅልፍ ተኝተዋል፤ ፓስተሮቻቸውም ለሕዝቡ የሚነግሩዋቸው በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን ቢመላለሱና እነርሱ የሚነግሯቸውን ሁሉ ቢያምኑ ችግር የለም ብለው ነው። እሽሩሩሩሩ። ሕዝቡም በእሽሩሩው ተመችቷቸው እንቅልፍ ተኝተዋል። ሁሉም ቤተክርስቲያኖች “ሙሽራይቱ እኛ ነን” ይላሉ። ይህን የሚሉት በምድር ላይ 45,000 የተለያዩ የሜሴጅ እና ዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያኖች ናቸው። ከእነዚህ ቤተክርስቲያኖች መካከል የሚመጣውን ታላቅ መከራ ለማምለት በቁም ነገር እውነትን ፍለጋ መጽሐፍ ቅዱስን የሚፈትሽ የሚያጠና አንድም የለም። ፓስተሮቻችን እያታለሉን ይሆናል ብሎ የሚፈራ የለም። ፓስተሮቻቸው እያታለሏቸው ሊሆን እንደሚችል ማሰብ እንኳ አይፈልጉም።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

የትኛዋም ቤተክርስቲያን በዚህ ቃል ግለሰቦችን አትመክርም።

በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ መቆሙን ክርስቲያኖች አያምኑም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የትኛዋንም ቤተክርስቲያን ለይቶ በእርሷ ውስጥ ክርስቶስ አለ አላለም፤ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል ብቻ ነው የሚለው። ስለዚህ መጠጊያ ብለው ያሰቧቸው ቤተክርስቲያን “መጽሐፍ ቅዱስን ያለማወቅ” ግዞት ቤቶች ናቸው ምክንያቱም የትኛዋም ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅማ እምነቷን አታስረዳም። የትኛውም ፓስተር ጥቅሶችን ሁሉ ማብራራት አይችልም፤ ስለዚህ ማብራራት ያልቻሉትን ጥቅሶች እንደማያስፈልጉ ያጣጥሏቸዋል። ሁሉም ፓስተር ሙሉ መረዳት አለኝ ይላል። “እኔን ብታዳምጡን ብቻ ማወቅ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ታውቃላችሁ” ይላሉ።

እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የተወሰኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮ አሉት፤ ነገር ግን በተጨማሪ ደግሞ በሰው ንግግር ጥቅሶች እና የአባቶች ወግ ላይ ወይም በአንድ ታዋቂ ሰው ንግግር ላይ የተመሰረቱ አስተምሕሮዎችም አሉት።

በፍርድ ቀን ማንም ታዋቂ ሰው የለም፤ ቦታ የሚሰጠው የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሰዎች በዚያ ቀን ማንንም አያስገርሙም።

ያ ብርቱ መልአክ በተጨማሪ ለሁለቱ ነብያት የሚሰጣቸው የተከፈተ መጽሐፍ በእጁ ይዟል፤ ነብያቱም የተከፈተውን መጽሐፍ እንደተቀበሉ የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ይማራሉ።

63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት

… ሌላም ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ በዙርያውም ደመና እና ከራሱም በላይ … ቀስተ ደመና ነበረ… ልብ ብላችሁ ካስተዋላችሁ ይህ ክርስቶስ ነው (አያችሁ?)፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የቃልኪዳን መልእክተኛ ተብሎ ተጠርቷል፤ እርሱም በቀጥታ ወደ አይሁዶች ይመጣል፤ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ዘመን አልቋል። አያችሁ? እሺ። … ፊቱም … እንደ ፀሃይ የሚያበራ፤ እግሮቹ ደግሞ እንደ እሳት አምድ ናቸው፤ ራዕይ ምዕራፍ 1 ውስጥ ያለውን መልአክ ታስታውሳላችሁ? ከእርሱ ገር አንድ ናቸው። መልአክ ማለት መልእክተኛ ነው፤ እርሱ ለእሥራኤል የተላከ መልእክተኛ። አያችሁ? ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ ሄዳለች። አያችሁ?

አሁን ወይም ለመነጠቅ እየተዘጋጀች ነው።

የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ የተሰጠውን ሁለት ተልእኮ ተመልከቱ።

ለመነጠቅ ለተዘጋጀችው ቤተክርስቲያን ይመጣላታል፤ ቤተክርስቲያንም ወዲያው ትሄዳለች።

ይህ መልአክ ደግሞም በቀጥታ ወደ አይሁድ ይመጣል ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ወዲያ ወደ አይሁዶች ነው የሚዞረው።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ነገር ግን የቃሉ ሚስጥር የሆነውን የእግዚአብሔር ሚስጥር ለማግኘት መጽሐፉን የገለጠው ማነው?

ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን …

“ዳሩ ግን” የሚለው ቃል የምዕራፉን ፍሰት ሙሉ በሙሉ ይለውጠዋል።

“እወዳችኋለው ግን …” ብዬ ብናገር የንግግሬ ሃሳብ ሊለወጥ መሆኑን ትረዳላችሁ።

ስለዚህ ራዕይ 10፡7 ትኩረቱን ትንሳኤውንና ሙሽራይቱን በአየር ላይ ለመነጠቅ በማዘጋጀት ለጌታ ምጻት በሩን የሚከፍቱት ነጎድጓዶች ከሚያመጣው እንዲሁም ለሁለቱ ነብያት የተፈጥሮ ኡደቶችን እንዲያቋርጡ ኃይል ከሚያስታጥቃቸው ከብርቱው መልአክ ድምጽ ወደ ሌላ አቅጣጫ ዘወር ያደርጋል።

የመላእክት አለቃው የተከፈተውን መጽሐፍ ለሁለቱ ነብያት ይሰጣቸዋል ግን መጽሐፉ ከብዙ ዓመታት በፊት አስቀድሞ የተከፈተ መሆኑን ያብራራላቸዋል፤ የተከፈተውም በሰባተኛው መልአክ የአገልግሎት ዘመን ውስጥ በመጡ መገለጦች አማካኝነት መሆኑን ይነግራቸዋል።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መፈጸም አለበት። በዚህ ቃል ውስጥ የማመንታት ድምጸት አለ። ዮሐንስ በራዕይ ዘመናትን ወደፊት አሻግሮ ሲመለከት የሜሴጅ ፓስተሮች ጥቅሶችን ተጠቅመው መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት ፈንታ ጥቅሶችን ተጠቅመው የራሳቸውን አመለካከት በማራመድ ብዙ ነገር ሲያበላሹ አይቷል። የሜሴጅ መሪዎች በትክክል ማስተማር ነበረባቸው፤ እነርሱ ግን በትክክል አላስተማሩም።

ሐዋርያው ዮሐንስ እንደ ነብይ መጽሐፉን መብላት ይችላል። በእውነት ላይ ከሚሰነዘሩ ተቃውሞዎች አንጻር መራራ ነው ስለዚህ ተቃውሞውን ይታገሰዋል፤ ነገር ግን ባጋጠመው መከራ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር ስላደረገለት ማዳን ሲመሰክር ቃሉ በአፉ ውስጥ ጣፋጭ ነው።

ሁለቱ የአይሁድ ነብያት በታላቁ መከራ ውስጥ አሕዛብ እና የምስራቅ ነገስታት ተባብረው ሲነሱባቸው ብዙ መራራ መከራ ውስጥ ያልፋሉ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ከሚሆንላቸው መዳን የተነሳ ደግሞ ጣፋጭ የምስክርነት ቃል ይኖራቸዋል።

የሜሴጅ አማኞች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተሳሳቱበት ቦታ ይህ ነው።

የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቁጥሮች የተገለጡን ሚስጥራት የያዘ የተከፈተ መጽሐፍ ለዊልያም ብራንሐም ለመስጠት የደመናውን መውረድ በተመለከተ ነው የሚናገሩት ይላሉ።

ይህ ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው። ዊልያም ብራንሐም ነው መጽሐፉን የከፈተው፤ ይህም ከ1947 እስከ 1965 ያሉትን ዓመታት ፈጅቶበታል።

የምዕራፍ 10 የመጀመሪያዎቹ 10 ቁጥሮች ብርቱው መልአክ ሲመጣ መጀመሪያ ሙታንን እንደሚያስነሳ ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ ሰባት ነጎድጓዶች ቤተክርስቲያን የተፈጥሮ ሕጎችን አሸንፋ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል እንድትነጠቅ ያስችሏታል። በዚያ ጊዜ ሰባቱ ነጎድጓዶች በተጨማሪ ለሁለቱ የአይሁድ ነብያት የተፈጥሮ ሕጎችን አልፈው የሚሰሩበት ስልጣን ይሰጧቸዋል፤ እነርሱም ተፈጥሮን በማዛባት የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ፖፕ የሚያስነሳቸው ሰራዊት ላይ ታላቅ ነውጥ ይፈጥሩባቸዋል።

በስተመጨረሻም ብርቱው መልአክ የተከፈተውን መጽሐፍ ለሁለቱ ነብያት ይሰጣቸውና ሚስጥራቱ በሰባተኛው መልአክ አማካኝነት መገለጣቸውን ይነግራቸዋል። ከዚያም ሁለቱ ነብያት ሙሽራይቱ የምታውቀውን ሁሉ ያውቃሉ፤ ከዚያም በተጨማሪ እኛ የማናውቃቸውን የታላቁን መከራ ሚስጥራት በሙሉ ይማራሉ።

ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነብያት ከሁሉም ሰው የበለጠ ያውቃሉ።

 

ምዕራፍ 11

 

ይህ ምዕራፍ የሚናገረው ስለ ሁለቱ ነብያት አገልግሎት ነው፤ እነርሱም 144,000ው አይሁዶች እሥራኤል ውስጥ ጌታን ፊት ለፊት እስኪያገኙ ድረስ የክፋት ኃይላትን አፍነው ይይዟቸዋል። ከዚያ በኋላ ሁለቱ ነብያት ይገደሉና ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ ይሄዳሉ። ይህም የታላቁ መከራ ፍጻሜ ይሆናል፤ ይህም ጊዜ አሕዛብ ሁሉ ለአርማጌዶን ጦርነት የሚሰበሰቡበት ወቅት ይሆናል፤ ሲሰበሰቡም ጌታ ይወርድና ያጠፋቸዋል።

ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ዳግም ምጻት ሚስጥር ነው።

ሰባተኛው መለከት ጌታ በአርማጌዶን ጦርነት ላይ ድል ለመንሳት እና መንግስቱን ለሺህ ዓመት ለመመስረት የሚመጣበትን ምጻት የሚገልጽ ተምሳሌት ነው። ይህም መምጣቱ አስቀድሞ በምድር መንቀጥቀጥ እና በታላቅ በረዶ ነው የሚታወጀው።

በሰማይ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በኢሱስ ፊት ይሰግዳሉ። ስለዚህ ቅዱሳን ወደ ሰማይ ከተነጠቁ በኋላ ይህ ሰባተኛ መለከት ይነፋል።

ራዕይ 11፡15 ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።

16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ

ይህ ሰባተኛውን መለከት የሚነፋ መልአክ ጌታ ለአርማጌዶን ጦርነት እንዲወርድ የሚያደርግ ፍርድን ወደ ምድር የሚልክ ሰማያዊ መልአክ ነው፤ ጌታ ለአርማጌዶን የሚመጣበትም ምጻት ሶስተኛ ምጻት ነው።

ራዕይ 3፡14 ውስጥ ያለው የሎዶቅያ ሰባተኛ መልአክ እና ራዕይ 10፡7 ውስጥ ያለው መልአክ የተሰወሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የሚገልጥ ምድራዊ መልአክ ነው፤ ሚስጥራትን የሚገልጠውም በሕይወት ያለችውን ሙሽራ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት ለማዘጋጀት ነው።

ሰባተኛው መልአክ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ያመጣላት መልእክት ከታላቁ መከራ እናመልጥ ዘንድ የምሕረት እና የማስጠንቀቂያ መልእክት ነው። መልእክቱን አንቀበልም በሚሉ ወይም በሚያጣምሙ ሁሉ ላይ በታላቁ መከራ ውስጥ ፍርድ ይመጣባቸዋል።

የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ብቻ እንዳገኘን ማወቅ አለብን።

የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት የሚሆነው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ብቻ ነው።

61-0101 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 2

አሁን ያንን በኋላ የሚለውን ቃል እናገኛለን፤ “ከዚያ በኋላም።” በኋላ ማለት “የቤተክርስቲያን ዘመን ካበቃ በኋላ” ማለት ነው።

ለዮሐንስም ወደ ላይ እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጠው፤ “ወደዚህ ውጣ” ማለትም ወደ ላይ ውጣ። በዚያም በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሚሆነውን ሁሉ አሳየው። ከዚያም የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ዮሐንስ ወደ ላይ እንዲወጡ በክርስቶስ ጥሪ የሚደረግላቸው የእውነተኛ ክርስቲያኖች ሁሉ ተምሳሌት እንደሆነ እናያለን። ልክ አይደል? “ወደዚህ ውጣ” ተብሎ ተጠራ።

 

የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ - ምዕራፍ አንድ

እስከ ራዕይ 5፡6-8 (ይህ ክፍል በጊዜ ቅደም ተከተል ከራዕይ 4፡2-3 ተከትሎ የሚመጣ ነው) በራዕይ 4፡2-3 እና 9-10 ውስጥ እንደተገለጸው “በጉ” መጽሐፉን በዙፋኑ “ከተቀመጠው” እጅ ሲወስደው አናይም።

ምዕራፍ 4 ዮሐንስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ ያሳየል፤ ይህም የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲጠናቀቁ የሚሆነውን መነጠቅ የሚያመላክት ነው።

ከዚያም በጊዜ ቅደም ተከተል ሲቀመጥ ምዕራፍ 5 ከምዕራፍ 4 በኋላ ይመጣል።

ይህ ትዕይንት በሚከፈትበት ጊዜ 24ቱ ሽማግሌዎች በሰማይ ናቸው፤ ከእነርሱም መካከል 12ቱ የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ናቸው። ስለዚህ ማሕተሞቹ በእርግጥ የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው።

የዚህን ሁነት ቅድሚያ እይታ ሰባቱ መላእክት ለወንድም ብራንሐም እንደ መሰረታዊ መረጃ የሚሆን መገለጥ ያመጡለት ጊዜ አይተናል፤ ይህንም ያደረጉት ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መስበክ እንዲችል ነው። ነገር ግን ዋነኛው ሁነት ማለትም የማሕተሞቹ መፈታት አሁንም ገና ወደፊት ነው የሚፈጸመው። የማሕተሞቹ መፈታት ከመፈጸሙ በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ መገለጥ ልኳል፤ ይህንም ያደረገው እኛ ማሕተሞቹ ለሚፈቱበት ጊዜ እንድንዘጋጅ ነው።

63-0324M ስለ ማሕተሞቹ ጥያቄና መልሶች

ጥያቄ፡ በራዕይ ምእራፍ 5 ቁጥር 9 በጉ መጽሐፉን ሲወስድ የሚዘምሩት እነማን ናቸው?

የተነጠቁት ቅዱሳን ናቸውን?

መልስ፡ አይደሉም

… የሆነ የረሳነው ነጥብ አለ። የሆነ የረሳነው ነጥብ አለ።

[ከጉባኤው መካከል አንድ ሰውዬ ወንድም ብራንሐም ራዕይ 5፡9ን በድጋሚ እንዲያነብ ይጠይቃል -- ኤዲተር]

እነርሱም እንዲህ እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፡- መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማሕተሙንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና… (ይኸው። ይኸው። ይህን በተመለከተ ተሳስቼ ነበር። አያችሁ?) … ከነገድ ሁሉ በደምህ ለእግዚአብሔር ዋጅተኸናል…

… ነገር ግን እዚህጋ ሲያስቆመኝ ታያላችሁ? ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

የዚህን የቀረ ክፍል አንብቤ አላውቅም። ተመልከቱ አሁን ደግሞ ወደዚህ መጣለው፡ ተመልከቱ “አዲስ መዝሙር ዘመሩ” ከዚያም አቆምኩ። አያችሁ? ነገር ግን ተመልከቱ “የዘመሩትን መዝሙር እንዲህ እያሉ፡- ከነገድ ከቋንቋ ከሕዝብም ሁሉ ዋጀኸን።”

ያለጥርጥር እነርሱ ናቸው።

 

ስለዚህ ኢየሱስ ማሕተሙን በሚፈታበት ሰዓት ሙሽራይቱ ከእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ናት።

ወደ ራዕይ ምዕራፍ 11 እንመለስና ሰባተኛውን መለከት የሚነፋውን መልአክ እንይ።

ራዕይ 11፡15 ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።

16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ

ሰባተኛው የፍርድ መለከት ሲነፋ 24ቱ ሽማግሌዎች በሰማይ ወድቀው ይሰግዳሉ። ስለዚህ ሰባተኛው መለከት የሚነፋው 12ቱ ሐዋርያት በሰማይ ባሉበት ነው። ይህ የሚሆነው ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ በሶስተኛ ምጻቱ ለአርማጌዶን ጦርነት እንዲመጣ የሚያደርገውን ልክ ከአርማጌዶን ጦርነት በፊት የመጨረሻውን የታላቅ መከራ ፍርድ የሚያመጣውን ሰባተኛውን መለከት የያዘው ይህ ሰባተኛ መልአክ የራዕይ 10፡7 ሰባተኛ መልአክ አይደለም ምክንያቱም የራዕይ 10፡7ቱ መልአክ ዋነኛ አገልግሎቱ ማሕተሞቹን መግለጥ እና ሙሽራይቱ ለዳግም ምጻት ትዘጋጅ ዘንድ የተጻፈውን ቃል መገለጥ ማስተማር ነው።

 

ራዕይ ምዕራፍ 12

 

ይህ ምዕራፍ ድርብርብ ትርጉሙች ስላሉት ለመረዳት ቀላል አይደለም።

የምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ የወረደው ለሙሽራይቱም ለአይሁዶችም ነው።

ይህ ምዕራፍ ስለ አይሁዶችም ስለ ቤተክርስቲያንም ነው የሚናገረው። ስለ አይሁዶች የሚናገረው ኢየሱስ በመወለዱ እና ወደ ተነጥቆ ሰማይ በመወሰዱ ነው። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ወደ እኛ ወደ አሕዛብ ዘወር ያደረገ ጊዜ አይሁዶችን በማሳወር ጥበቃ አድርጎላቸዋል።

አይሁዶች ከባድ ስደቶች ደርሰውባቸዋል፤ ነገር ግን ምዕራፍ ስድስት ውስጥ እንደተጻፈው ከመሰዊያው በታች ያሉት ነፍሳት ከተገደሉ በኋላ ነጭ ልብስ ተሰጥቷቸዋል። አይሁዶችን በዓለም ዙርያ በመበተን እግዚአብሔር ለአይሁዶች ጥበቃ አድርጎላቸዋል። አንድ አካባቢ ያሉ አይሁዶች ተገድለው ቢያልቁ ሌላ ቦታ ያሉት አይሁዶች ይተርፋሉ። በአሕዛብ መካከል በተበተኑ ሰዓት በመንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ ነበሩ። ከዚያ በኋላ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ አካባቢ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ጥበቃ ለማድረግ አሜሪካ የተባለች ልዕለ ኃያል ሃገርን አስነሳ።

ከዚያ በኋላ በታላቁ መከራ ውስጥ እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ይመለሳል፤ በዚያም ጊዜ ሙሴ እና ኤልያስ በተፈጥሮ ላይ የተሰጣቸውን ኃይል ተጠቅመው ምድር አፏን ከፍታ በእሥራኤል ላይ የተነሱትን የክፋት ሰራዊት እንድትውጣቸው ያደርጋሉ። በዚያ ሰዓትም የምድር ሕዝብ ሁሉ አይሁዶችን ስለሚከዱዋቸው አይሁዶች በምድረበዳ ውስጥ ይሆናሉ። ፕሬዚዳንት ኦባማ በ2017 ከስልጣን ከመውረዱ በፊት የተባበሩት መንግስታት እሥራኤልን እንዲቃወሙ አድርጓል። እንደ መንፈሳዊ ሰው ስንመለከተው ኦባማ እሥራኤልን መቃወም ትልቅ ስሕተት ነው። አይሁዶች ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ የተነገረውን ትንቢት መቃወም የእግዚአብሔር ፈቃድ መቃወም ነው። በ2017 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን በተስማማ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት በ128 ለ 9 ድምጽ ተቃወሙት። ትራምፕ ይህንን ሁሉ ተቃውሞ ሳይፈራ ጆሮዬን አልሰጥም አለ። እሥራኤል እየገባችበት ያለው ምድረበዳ ይህን ይመስላል። የምድር ሕዝቦች ሁሉ ይከዱዋታል። ነገር ግን በታላቁ መከራ ጊዜ ሁለት ነብያት ጥበቃ ያደርጉላቸዋል።

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተነጠቀ በኋላ የራዕይ መጽሐፍ ስለ አይሁዶች መናገሩን ያቆምና የአሕዛብን ቤተክርስቲያን አጉልቶ ያሳየናል።

ራዕይ 12፡1 ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ይህ አክሊል መጀመሪያ 12ቱን የእሥራኤል ነገዶች የያዘው የአይሁዶች ጉባኤ ወይም ቤተክርስቲያን ነው፤ ቀጥሎም 12ቱ ሐዋርያት የመሰረቱት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ነው። ጨረቃ የብሉይ ኪዳን ነብያት ሕግ ናት። ፀሃይ ደግሞ የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ጸጋ ናት። ሐዋርያት እና ነብያት ማለትም አዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን የአሕዛብ ቤተክርስቲያንን እና አይሁዶችንወደ ጌታ ይመራሉ።

ራዕይ 12፡2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።

አብርሃም የኖረበት ዘመን 1900 ዓመተ ዓለም ነበር። ኢየሱስ 33 ዓመት በሞላው ጊዜ ከአይሁድ ሕዝብ ዕድሜ አንጻር እንደ ሕጻን ልጅ ነበር። ይህም እግዚአብሔር አይሁዶችን ለመቤዠት ያዘጋጀውን የረጅም ጊዜ እቅድ ያሳያል።

አይሁዶች በመንፈሳዊ ሕይወት ደርቀው ነበር። ለ430 ዓመታት ያህል አንድም ነብይ አልተናገራቸውም። ሮም ደግሞ ከ63 ዓመተ ዓለም ጀምሮ ስትገዛቸው በቆየችበት ዘመን ግፈኛ፣ ስግብግብ እና ምግባረ ብልሹ ባለስልጣኖችን በላያቸው ሾመችባቸው።

ራዕይ 12፡3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥

ዘንዶው የሰይጣን ምሳሌ ነው። ሰይጣን የሮማ መንግስትን በመቆጣጠር ኢየሱስን ለማጥፋት ሊጠቀምበት ነበር። ሰባቱ ራሶች ሮም ውስጥ ያሉት ሰባት ኮረብታዎች ናቸው። አስሩ ቀንዶች ደግሞ ወታደራዊ ኃይላቸውን በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ዓለምን በሙሉ ይገዛ ዘንድ ለመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ የሚሰጡ የመጨረሻዎቹ አስር ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት ናቸው። ፖምፔይ የተባለው ሮማዊ ጀነራል እሥራኤልን በ63 ዓመተ ዓለም ሲቆጣጠር በዚያው ዓመት ዩልየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ ፖንቲፍ ወይም ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ሆኖ ተመረጠ፤ ይህም በናምሩድ የተጀመረው የባቢሎናውያን ሚስጥራት ሊቀካሕናት መሆን ማለት ነው። ሰባቱ ዘውዶች በፈላጭ ቆራጭነት ይገዙ ዘንድ ራሳቸውን የሮም ገዥዎች አድርገው የሾሙ ሰባቱ የዩልየስ ቄሳር ቤተሰብ አባላት ናቸው።

ዩልየስ ቄሳር ዕድሜውን በሙሉ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ኖረ። ከእርሱ በኋላ የመጀመሪያው ገዥ የእሕቱ ልጅ ኦጋስተስ ቄሳር ነው። እርሱም ጥባሪዮስን እንደ ልጁ አድርጎ በማደጎ አሳደገው። ኢየሱስ በተገደለበት ሰዓት የሮም ገዥ ጥባሪዮስ ነበረ። የጥባሪዮስ ወንድም ልጅ ካሊጉላ ለጥቂት ወራት ገዥ ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ አበደ። ከሶስት ዓመት ተኩል በኋላም ተገደለ። (እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አሰበ፤ ስለዚህ እንደ ኢየሱስ የሶስት ዓመት ተኩል አገልግሎት አገልግሎ ሞተ።) አጎቱ ክሎዲየስ በእርሱ ቦታ ነገሰ እና የኔሮን እናት አገባ። የኔሮ እናት ክሎዲየስን ገደለችው፤ ኔሮ ደግሞ እናቱን እና የተለያዩ ሐዋርያትን ጨምሮ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ። ከዚያ ሰባተኛው ደግሞ ከእስፔይን የመጣ ጋልባ የተባለ ሮማዊ ጀነራል ነው፤ እርሱም የቄሳርነትን ስልጣን ቀምቶ ያዘ፤ ከሰባት ወራትም በኋላ ተገደለ። የዩልየስ ቄሳር ቤተሰብም በወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ አማካኝት ተደመሰሰ።

ይህ ቤተሰብ ነበር የሮማ መንግስትን የመሰረተው። ሮም እሥራኤልን የተቆጣጠረቻት በ63 ዓመተ ዓለም ነበር። ዩልየስ ቄሳር ወደ ስለጣን በመጣ ጊዜ አይሁዳዊ ያልሆነውን ሔሮድስን የአይሁዶች ንጉስ አደረገው፤ ምክንያቱም የሔሮድስ አባት ቄሳርን ረድቶታል። ስለዚህ ሮም ኢየሱስ የሁለት ዓመት ሕጻን በነበረ ጊዜ ለመግደል እንዲያመቻት ሔሮድስን በስልጣን ላይ አስቀመጠችው።

ራዕይ 12፡4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።

በራዕዩ ውስጥ የታየው “ጅራት” ሰይጣን ሰዎችን ያሳተበትን “ተረት”ወይም ሐሰተኛ ወሬ ይወክላል።

ሲሶ ወይም አንድ ሶስተኛ የሚለው የሰዎች ብዛት አይደለም። እግዚአብሔር ዓለምን በሶስት ከፍሎ ነው የሚያየው። አይሁዶች፣ ሳምራውያን (የአሕዛብ እና የአይሁድ ክልሶች)፣ እና አሕዛብ።

ስለዚህ እግዚአብሔር አይሁዶችን በቁጥራቸው ሳይሆን በሕዝብ ምድብ እንደ አንድ ሶስተኛ ያያቸዋል።

የአብርሃም ልጆች ከዋክብት ይባላሉ። በሌላ አነጋገር አይሁዶችነ ማለት ነው።

ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።

ዳንኤል 8፡9 ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።

10 እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ፤ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም።

ቀንድ የመንግስትን ኃይል ይወክላል። ታናሹ ቀንድ ማት በምድር ላይ ከመንግስታት ሁሉ ትንሽ የሆነችውም ቫቲካን ናት። ቫቲካን የግዛቷ ስፋት አንዲ ኪሎ ሜትር ካሬ እና የዜጎቿ ብዛት ደግሞ ከአንድ ሺ በታች ነው። ነገር ግን ቫቲካን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ ናት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ቅዱሳንን አማላጆች ትላቸዋለች ስለዚህ ተከታዮቿ ወደ ቅዱሳን ይጸልያሉ። ወደ ሙታን መጸለይ መናፍስት ጠሪነት ነው። ስለዚህ ወደ ሞተ ሰው ሲጸልዩ ያንን ሰው ከሰማይ እያስወጡት ነው ምክንያቱም ሰማይ ውስጥ መናፍስት ቦታ የለውም። ለቅዱሳን ሐውልቶችን ይሰሩላቸዋል፤ ወይም ጣኦት ያበጁላቸዋል፤ እነዚህንም ጣኦታት በቤተክርስቲያናቸው በሚያስቀምጧቸው ጊዜ ጣኦታቱ ሙታኑን ወደ ምድር ያወርዱላቸዋል።

ራዕይ 12፡4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።

ሰይጣን የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን በመጠቀም የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስን በደስታ ተቀብለውት የነበሩት ሕዝብ በቀጣዩ አርብ ይሰቅሉት ዘንድ እንዲያሳምኑዋቸው አደረገ። መርዙ ያለው ታሪኩን ወይም ተረቱን ባወሩት መሪዎች ውስጥ ነበረ፤ ውጤቱ ወይም መዘዙ ግን የመጣው በመሪዎቻቸው ተታለው በታዘዙት ሕዝብ ላይ ነው።

በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል ታይተስ የኢየሩሳሌምን ከተማ እና ቤተመቅደሱን ባፈራረሰ ጊዜ 1,100,000 አይሁዶች አልቀዋል። ኢየሱስ ይገደል ብለው የጮሁ አይሁዶች ስማቸው በሰማያት ካለው የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይደመሰሳል ምክንያቱም እነርሱ ሰይጣን ያወራላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ተረት አድምጠዋል።

ራዕይ 12፡5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።

አብርሃም በ1900 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነበረ የኖረው። ያም የአይሁድ ሕዝብ ጅማሬ ነው። ኢየሱስ 33 ዓመት በሞላው ጊዜ በስጋ ከእነርሱ የተገኘበት የአይሁድ ሕዝብ በምድር ላይ ከቆዩበት ዘመን አንጻር ለእርሱ “እናት” ናቸው።

የብረት በትሩ የሚገልጸው ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ የሚመጣውን የ1,000 ዓመት ሰላም ነው። በዚያ ጊዜ ሐጥያት ቦታ አይኖረውም።

ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ ከ37 ዓመታት ያህል በኋላ አይሁዶች ከሃገራቸው ጠፉ። በ70 ዓ.ም ከሃገራቸው የተባረሩት ሮም እና አጋሮቿ አይሁዶችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በከፈቱባት ዘግናኝ ጦርነት ተሸንፋ ነው። ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዶች ሞቱ። በአንድ ከተማ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ያን ያህል ሰው ከዚያ በኋላ የሞተው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀርመኒ ራሺያን በወረረች ጊዜ የእስታሊንግራድ ከተማ ላይ በተደረገው ጦርነት ብቻ ነው።

ከ70 ዓ.ም በኋላ አይሁዶች በንጉስ ሐድሪያን ላይ አመጹበት፤ እርሱም በ135 ዓ.ም ከኢየሩሳሌም አባረራቸው። ከዚያ ወዲያ አይሁዶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ይጠፉና ቆይተው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሰቃቂው የሆሎኮስት እልቂት ሒትለር ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን በገደለ ጊዜ በድጋሚ ብቅ ይላሉ። ከታላቁ መከራ አንጻር ይህ የሕጻን ጨዋታ ነው። ስለዚህ የታላቁ መከራ ቅምሻ ነው።

ከዚህም ቀጥሎ መጽሐፍ ቅዱስ አቁሞት የነበረውን የአይሁዶች ታሪክ በታላቁ መከራ ውስጥ ይቀጥለዋል።

ራዕይ 12፡6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

1,260 ቀኖች ወይም ሶስት ዓመት ተኩል ታላቁ መከራ የሚቆይበት የጊዜ ርዝመት ነው። በታላቁ መከራ ጊዜ እሥራኤል በምድር ሕዝቦች ሁሉ ተከድታ ተቀባይነት በማጣት ምድረበዳ ውስጥ ትቆያለች።

ራዕይ 12፡7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥

ራዕይ 12፡8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።

ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ሰይጣን የወንድሞች ከሳሽ ሆኖ ከቆየበት ከሰማይ ወደ ምድር ይወድቃል። ከዚያም አይሁዶች ላይ እና መጽሐፍ ቅዱስን በማያውቁ የሰነፎች ቆነጃጅት ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ሲሰነዝር ታላቁ መከራ ይጀምራል።

መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱም ወደ ሰማይ ለመውሰድ ምድርን ትቶ ይሄዳል። ሕይወት ምድርን ትቶ ሲሄድ ሞት ወደ ምድር ይገባል።

ሚካኤል በድምጹ ሙታንን የሚያስነሳው የመላእክት አለቃ ነው።

ይሁዳ 1፡9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል

ስለዚህ ሚካኤል ሰይጣንን ከሰማይ አውጥቶ በጣለው ጊዜ ሰማይ ይነጻል፤ ወዲያውም ሚካኤል ወደ ምድር ወርዶ ቅዱሳንን ከሙታን ያስነሳቸዋል።

ክርስቶስ እንደ መላእክት አለቃ በሚገለጥ ጊዜ ራሱን ሚካኤል ብሎ ይጠራል።

63-0728 ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ሚስጥር ነው

ሉሲፈር የእግዚአብሔርን እና የሰውን ሕብረት ለማቋረጥ ያደረገው የመጀመሪያው ነገር ሚካኤል ማለትም ክርስቶስ ከመሰረተው በክብሩም በኃይሉም የሚበልጥ መንግስት ለራሱ ለመመስረት መፈለጉ ነው።

55-0109E የአሕዛብ ዘመን ጅማሬ እና ፍጻሜ

“በዚያን ጊዜ ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” ሚካኤል ክርስቶስ ነው፤ እርሱ ነው በሰማያት ከሰይጣን ጋር በተደረገው ጦርነት ውስጥ ሰይጣንን የተዋጋው።

ራዕይ 12፡14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።

በስተመጨረሻም እባቡ ፊት ወይም ራስ አለው ይላል፤ እርሱም የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ነው። ድንቅ በሆነ የማየት ችሎታው ንስር የነብይ ተምሳሌት ነው። ሁለቱ ታላላቅ የንስር ክንፎች ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ለ144,000ዎቹ አይሁዶች ጥበቃ ያደርጉላቸዋል።

ራዕይ 12፡15 እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።

ይህም የሕዝብ እና የአስተምሕሮዎች ጎርፍ ነው።

ራዕይ 12፡16 ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።

ሁለቱ ነብያት በምድር ላይ ኃይል አላቸው። ምድር አፏን ከፍታ ጠላቶቻቸውን መዋጥ ትችላለች።

ስለዚህ በሰው ታሪክ ውስጥ ከሁሉም ታላቅ ጀነራሎች የሆኑት ሁለቱ ነብያት “ተፈጥሮን የማዘዝ” ኃይላቸውን ተጠቅመው በአውሎ ነፋስ፣ በምድር መንቀጥቀጥ፣ በከባድ ማዕበል፣ በዝምብ እና በአንበጣ መንጋ፣ በሚዳሰስ ጨለማ፣ እና በከባድ ቁስል አማካኝነት የክርስቶስ ተቃዋሚውን ፖፕ ሰራዊት ይከላከላሉ። ከዚያም ፖፑ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናትና እውነትን ለመማር የሚዘናጉትን ሰነፎቹን የዳኑ ክርስቲያኖች ለማጥፋት ይዘምታል። እነርሱም “መሪዬን እከተላለው” በሚል ጨዋታ ሲዘናጉ ቆይተው ወደ ታላቁ መከራ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ። የክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ በሁለቱ ነብያት ከተመታ በኋላ ከታላቁ መከራ በፊት የዳኑ ነገር ግን ሰነፎች የሆኑ የቤተክርስቲያን አባላትን በማጥፋት የበቀል እርምጃ ይወስዳል። ኢየሱስ ሙሽራይቱን ለመውሰድ በሚመጣ ጊዜ በምሕረት ዙፋን ላይ ተቀምጦ አይደለም የሚመጣው። በዚያ ጊዜ ምሕረት ያበቃል።

ራዕይ 12፡17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤

ይህ ጥቅስ በመጨረሻ በታላቁ መከራ ውስጥ የሚጠፉትን ነገር ግን የዳኑትን ሰነፎቹን ቆነጃጅትም ያጠቃልላል።

ሴት የሰርግ ልብሷን ከጨርቅ ቀድዳ ነው የምታዘጋጀው። እርሷ የፈለገችውን መልክ ያልያዘ ጨርቅ ሁሉ እንደ ጨርቅነቱ ጠቃሚ ቢሆንም እንደ ትርፍ ወይም ቅሬታ ትጥለዋለች። ስለዚህ ታላቁ መከራ የሰነፎቹ ቆነጃጅት መጨረሻቸው ነው። እነሱ ጠቃሚ ጨርቆች ወይም የዳኑ ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚፈልገውን ዓይነት መልክ አልያዙም ምክንያቱም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ትተው በዘመናዊ ትርጉሞች ተክተውታል። ደስ ሲላቸው መጽሐፍ ቅዱስን ይቃረናሉ፤ የማይመቿቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደግሞ እንደማያስፈልጉ በመቁጠር ይጥሏቸዋል። ሰባቱን ነጎድጓዶች በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ባልተናገረበት ደግሞ ያልተገለጠውን ለማስተማር የራሳቸውን አስተምሕሮ ፈጥረዋል። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል የሚፈልገውን ዓይነት መልክ አልያዙም። ከዚያም እግዚአብሔር እንደ ትርፍ ጨርቅ ጣላቸው፤ ስለዳኑ ጥሩ ንጹህ ጨርቆች ናቸው ግን እግዚአብሔር ባዘጋጀው እቅድ ውስጥ ቦታ አልነበራቸውም ምክንያቱም ቃሉን ለመረዳት አንዳችም ጥረት አላደረጉም።

አሁን ወደ ምዕራፍ 12 በመመለስ የቤተክርስቲያንን ታሪክ እንዴት አድርጎ እንደሚነግረን ማየት እንችላለን።

ራዕይ 12፡6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

1,260 ቀናት ከቤተክርስቲያን ጋር የሚያያዙት እንዴት ነው?

ትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ሊወክል ይችላል።

ላባ ለያዕቆብ እንዲህ አለ፡-

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

የአይሁዶች አንድ ወር 30 ቀን ነው።

ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።

1,260 ቀናት 42 ወራት ከሆኑ እያንዳንዱ ወር 30 ቀናት ነው ማለት ነው።

12 የአይሁድ ወራት ማለት አንድ ዓመት 12 x 30 = 360 ቀናት ናቸው።

የእኛ የአሕዛብ ዓመት 365.25 ቀናት ሲሆን ከአይሁዶች ዓመት በአምስት ቀን ከሩብ ይረዝማል።

ማለትም በእኛ አቆጣጠር 70 ዓመታት ሲያልፉ የሚገኙት ትርፍ ቀኖች 5.25 x 70 = 367 ትርፍ ቀናት ወይም አንድ ዓመት ያህል ተጨማሪ የአይሁድ ዓመት ያስገኛሉ። ስለዚህ የእኛ 70 ዓመታት ከአይሁዲች 71 ዓመታት ጋር እኩል ናቸው። (የእኛ አቆጣጠር የተፈጠረው በዩልየስ ቄሳር ነው።)

ትንቢቶችን መረዳት የምንችልበት ሚስጥር ይህ ነው።

ሴቲቱ (ቤተክርስቲያን) ለ1,260 ቀናት ከስደት ለማምለጥ ወደ ምድረበዳ ትሸሻለች።

ስደት የጀመረው መች ነው?

378 ወሳኝ ዓመት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሃንሶች (የሮማ መንግስት መውደቅ እና የፖፑ ወደ ስልጣን መውጣት መንስኤ የሆኑነት የሃን ሕዝብ) ንጉስ ቫሌነስን እና አብዛኞቹን ሰራዊቱን በአድሪያኖፖል የገደሉ የጎቲክ ሰራዊት አካል ነበሩ። ከዚያ በኋላ ቴዎዶሲየስ ገዥ ሆነ። እርሱ ሲሞት መንግስቱን ለሁለቱ ልጆቹ አካፈለ። ይህም የዳንኤል ባየው የአሕዛብ ምስል ራዕይ ውስጥ በሁለቱ የብረት እግሮች አማካኝነት ተገልጧል። ቴዎዶሲየስ በ63 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳር የተቀበለውን ፖንቲፍ ወይም ፖንቲፌክስ ማክሲመስ የሚለውን ማዕረግ ለመቀበል እምቢ በማለት የመጀመሪያው ገዥ ነው። ዩልየስ ቄሳር የተቀበለው ማዕረግ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት አድርጎታል። ከዚያ በኋላ ይህን ማዕረግ ወስዶ የተጠቀመበት የሮም ጳጳስ ሲሆን እስከ ዛሬም ድረስ ፖንቲፍ ተብሎ ይጠራል። ስለዚህ በዚህ መንገድ የባቢሎን ሚስጥራት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገብተው ቤተክርስቲያኗን የባቢሎን ሚስጥር አደረጓት። ቴዎዶሲየስ የስላሴ አስተምሕሮን እውነተኛ ነው ብሎ እወቅና በመስጠት ትምሕርቱን በተቃወሚ ሁሉ ላይ መራራ ስደት አስነሳባቸው። በስተመጨረሻም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉስ ላይ ስልጣን እንዳላት እውቅና ሰጠ።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ለስራዋ ምቹ መድረክ ተዘጋጀላት። የሮማ ጳጳስ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የተቃወሙ መናፍቃንን ሁሉ እንዲያሳድድ ንጉሱን ማዘዝ ቻለ። የንጉሱ ፖለቲካዊ ስልጣን ለቤተክርስቲያን መጠቀሚያ ሆነ።

ክርስቲያኖች በሕይወት መኖር ከፈለጉ ወደ ሩቅ ቦታዎች መሸሽ ግድ ሆነባቸው።

ግድያው እስከ ቆመበት እስከ 1700 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ተገድለዋል።

“በምድረበዳ ስነበረችው ቤተክርስቲያን” ከሁሉም በላይ ትልቅ ምስክር የሚሆኑት ዋልደንሶች ናቸው። እነርሱም የአልፕስ ተራሮች ሸለቆ ውስጥ ሸሽተው ብዙዎቹ በብርድ ሞተዋል። ወደነዚህ ሩቅ ቦታዎች ተበታትነው ሸሽተው ነፍሰ ገዳይዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልታጠፋቸው ካሰማራቻቸው ሰራዊት ማምለጥ ችለዋል።

 

 

ከ1150 ጀምሮ በጨለማው ዘመን ውስጥ የዋንደንስ አሕዛብ ክርስቲያኖች በአልፕስ ተራሮች ውስጥ ባሉ ሸለቆዎች ውስጥ ተደብቀው ከሞት ተጠብቀዋል። የራይን እና ሮን ወንዞችን ከላይ ያለው ካርታ ውስጥ ማየት ይቻላል። ዋልደንሶች በአልፕስ ተራሮች ውስጥ ብዙ ቦታ በመድረስ በዙሪያ ባሉ ብዙ ሃገሮች ውስጥ ወንጌልን አሰራጭተዋል። ያለፉበት መከራ እና ብርታታቸው በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት ነው። በ1520 ዓ.ም ተሃድሶ ሲጀመር ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥቃት ተጠብቀው መኖር የሚችሉበት ቦታ አግኝተዋል።

በስተመጨረሻ ፒልግሪም ፋዘርስ የተባሉት የአውሮፓ ክርስቲያኖች በ1620 ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስደት ለማምለጥ ባሕር አቋርጠው ወደ አሜሪካ ሄደዋል። ከዚያም ከዚህ በታች ያለው ካርታ ላይ ቀይ ነጥብ ያለበት ማሳቹሴትስ የተባለ ቦታ ሰፍረው ኖሩ።

እነዚህ ሰዎች ሐይማኖታዊ ነጻነት ፈልገዋል። ፖፕ የሌለበት ቤተክርስቲያን፤ ንጉስ የሌለበት ሃገር ፈልገዋል።

ከ378 እስከ 1620 ድረስ 1,242 የአሕዛብ ዓመታት አልፈዋል።

ነገር ግን በያንዳንዱ 70 የአሕዛብ ዓመታት አይሁዶች አንድ ተጨማሪ ዓመት ያተርፋሉ። ስለዚህ 1,242ን ለ70 ስናካፍል 17 ዓመት ከሶስት ሩብ ዓመታት ማለትም ሲጠጋጋ 18 ትርፍ ዓመታት እናገኛለን።

18 + 1,242 = 1,260 የአይሁድ ዓመታት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ሁሉ የሚሰላው በአይሁድ ዓመታት ነው።

በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያን ከካቶሊክ ስደት ነጻ ሆነች። የፕሮቴስታንቶች የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት እና የፕሮቴስታንቶች የሥራ ታታሪነት ምደረበዳ የነበረችውን አሜሪካ በምድር ላይ አንደኛ ልዕለ ኃያል ሃገር አደረጓት።

የእስፔይን ቅኝ ገዥዎች በ1500ዎቹ ውስጥ ሜክሲኮን እና ደቡብ አሜሪካን ተቆጣጠሩ። እነርሱም ይዘውት የመጡትን የፈንጣጣ በሽታ የአሜሪካ ኢንዲያኖች ሊቋቋሙት አልቻሉም። የአሜሪካ ኢንዲያኖችም ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሞቱ፤ ከዚህም የተነሳ ሰሜን አሜሪካ ሰፊ ምድረበዳ ሆነች፤ የሚኖሩባትም ነዋሪዎች አውሮፓ ውስጥ ከሚርመሰመሱት የሕዝብ ብዛት አንጻር እጅግ ጥቂት ነበሩ።

 

 

እነዚህ ክስተቶች ሁሉአሜሪካ ከመጀመሪያዎቹ 13 ግዛቶች ተነስታ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የዛሬዋ ልዕለ ኃያል ሃገር እንድትሆን አበቋት። አሜሪካም በተራዋ እሥራኤል ወደ ተስፋ ምድሯ ስትመለስ ጥበቃ አደረገችላት። በ1948 ዓ.ም ለተመሰረተችዋ የእሥራኤል መንግስት እውቅና በመስጠት የመጀመሪያው የሃገር መሪ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትሩማን ነበረ። በ1973 ደግሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኒክሰን እሥራኤሎች ዮም ኪፑር የተባለውን በዓላቸውን እያከበሩ ሳለ አረቦች በድንገት ሊሰነዝሩባቸው ካሰቡት ጥቃት አድኗቸዋል። አሜሪካ በአውሮፕላን ጭና ለእሥራኤል ያቀበለቻት የጦር መሳሪያ አይሁዶች ራሳቸውን ከአረቦች እንዲከላከሉና እንዲያሸንፏቸው ጠቅሟቸዋል። እሥራኤል በጎላ ተራሮች በኩል የመጡባትን የሶሪያ ታንኮች ድባቅ መታቸዋለች። እሥራኤል ሶሪያዎችን የመታችበት ዘዴ አሜሪካኖችን በጣም ከማስደነቁ የተነሳ አሜሪካኖች የእሥራኤልን ታክቲክ በማጥናት እንዲሁ ብዙ ቦምብ ከመጣል ይልቅ በሚሳኤል እየተመሩ የሚሄዶ ቦምቦችን ወደ መጠቀም የጦር ስልቷን ቀይራለች። ይህም በዘመናዊ የጦር ስልት ላይ ታላቅ ለውጥ ፈጥሯል።

ቀጥሎም በ2017 ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚያዛውር አወጀ። ከእርሱ በፊት የነበሩ ፕሬዚዳንቶች፤ ፕሬዚዳንት ኦባማን ጨምሮ ይህን ለማድረግ በጣም ፈርተው ነበር። ፕሬዚዳንት ኦባማ እንደውም ስልጣን ከመልቀቁ በፊት እሥራኤልን ተቃውሟል። የተባበሩት መንግስታት አባላት 128 ለ9 ድምጽ በመስጠት ፕሬዚዳንት ትራምፕን ተቃውመውታል። እርሱ ግን ጆሮም አልሰጣቸውም። ትራምፕ እነዚህን ሁሉ መንግስታት በመጋፈጡ አስደናቂ ወኔ ያለው ሰው መሆኑን አሳይቷል። የፒልግሪም ፋዘርስ የተባሉት የሐይማኖት ስደተኞች ሄደው በተጠለሉባት የአሜሪካ ምድረበዳ ውስጥ የተገነባው የአሜሪካ ብርቱ ሰራዊት አሁን እሥራኤልን እየረዳ ነው።

ትሩማን Truman (T) ኒክሰን Nixon (N) ትራምፕ Trump (T)። TNT። በእንግሊዝኛ TNT የሚባል ፈንጂ አለ። መንፈሳዊ ፈንጂ። 2,500 ዓመታትን ያስቆጠረ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ አይሁዶች ወደ እሥራኤል መመለሳቸው፤ ዓለማችን እንዲህ ዓይነት ነገር ከዚህ በፊት አይታ አታውቅም።

ዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ USA ትባላለች።

የኢየሩሳሌምን ስም በእንግሊዝኛ ተመልከቱ፡- Jerusalem። አስተውላችኋል፡- Jer USA lem በኢየሩሳሌም ስም መሃከል ላይ USA የሚል አለ።

ጥንት በብሉይ ኪዳን ዘመን ይህ ስም ለዳዊት ከተማ በተሰጠ ጊዜ አሜሪካ ወደፊት ለእሥራኤል ጥበቃ እንደምታደርግ እግዚአብሔር አስቀድሞ አውቋል።

የዳዊት ኮከብ የእሥራኤል አርማ እና ባንዲራቸው ነው። ከየትኛውም ሃገር ባንዲራ ጋር የተያያዘ ጥንታዊ ስም።

 

 

ግን በዚህ ባለ ስድስት ጫፍ ኮከብ ውስጥ የተሰወረ ሚስጥር ይኖር ይሆን?

 

 

ሙሴ የአይሁድ ሕዝብ ከግብጽ የወጡበትን ፍልሰት መራ። ከዚያ በኋላ መሳፍንት አስተዳደሩዋቸው። ከዚያ በኋላ ነገስታት ሊያስተዳድሩዋቸው ሞከሩ። ብዙውን ጊዜ ሊጠቅማቸው የሚችል እነርሱ ግን ቸል ያሉት ምክር የሚመጣላቸው ከነብያት ነበረ። ከዚያ በኋላ ፍጹሙ መሲህ መጣ። እርሱን ደግሞ ገደሉት። ይህም ለ2,000 ዓመታት በአሕዛብ መካከል ተበታትነው እንዲኖሩ ምክንያት ሆነባቸው። አሁን ወደ ተስፋይቱ ምድር እየተመለሱ ናቸው፤ ነገር ግን ለሰባተኛ ምድብ ቦታ የለም። ስለዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ የሚጠብቃቸው ሙሴ ነው። የእግዚአብሔር እቅድ ሁልጊዜ በጀመረበት ቦታ ነው የሚጠናቀቀው።

እኛም ይህህን መንገድ መከተል ካለብን ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት መመለስ አለበት።

ሙሽራይቱ ኢየሱስን እንድታገባ ታጭታለች። የጋብቻ ቀለበት ያስፈልጋታል፤ እርሱም ክብ ብረት ነው ምክንያቱም ክብ ቅርጽ ከጀመረበት ቦታ ነው የሚያበቃው። በዚህም ዘላለማዊነትን ያመለክታል። ክብ ቅርጽ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም።

 

 

ነገር ግን እግዚአብሔር በታላቅ ፍጥነት የሚሰራበት ጊዜ በመሆኑ ተጠንቀቁ። እግዚአብሔር ወደ እሥራኤል ዘወር በማለት ፊቱን ከአሕዛብ ቤተክርስቲያን እየመለሰ ነው።

ከዚያም በታላቁ መከራ ውስጥ ወንጌል ወደ እስራኤል ይመለሳል፤ በዚህም ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባለቸው እምነት ሁሉ ትኩስም በራድም ያልሆኑ ለብ ያሉ ነገር ግን የዳኑ ቤተክርስቲያኖች አንድ በአንድ እየተለቀሙ ይገደላሉ።

በታላቁ መከራ ውስጥ የአውሬውን ምልክት (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ዲኖሚኔሽናዊ ሃሳቦች አእምሮን መሙላት) ትቀበላላችሁ፤ አለዚያ ትሞታላችሁ።

ልባሞቹ ቆነጃጅት ሊበሉ ወደ ሰርግ ግብዣ ይሄዳሉ። ሰነፎቹ ቆነጃጅት አውሬው ሊበላቸው ወደ እርሱ ይሄዳሉ።

ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥

ግምባራችሁ ውስጥ ማሰቢያችሁ የሆነው አንጎላችሁ ነው ያለው። ሃሳባችሁ በቤተክርስቲያናችሁ መሪ ቁጥጥር ውስጥ ከገባ በኋላ ቀኝ እጃችሁ፤ ማለትም የምትሰሩት ሥራም በቤተክርስቲያን ቁጥጥር ውስጥ ይወድቃል። ከዚያ በኋላ በራሳችሁ ጭንቅላት ማሰብ አትችሉም።

በተመሳሳይ መንገድ የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስን በደስታ የተቀበሉት አይሁድ በቀጣዩ አርብ በሐይማኖት መሪዎቻቸው ግፊትና አሳማኝነት አማካኝነት ሊገድሉት ችለዋል።

 

ምዕራፍ 13

 

ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።

 

 

የሰምርኔት ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 4

አውሬው በኒቅያ ጉባኤ ውስጥ እንደተነሳው ሁሉ ምስሉም በእውነተኛው የእግዚአብሔር የወይን ተክል ላይ በቀልን ለመፈጸም ክፉ የሆነ ሰይጣናዊ ኃይልን ሁሉ ተላብሶ ከዓለም አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ውሰጥ ተነስቶ ይመጣል። ይህም የሰይጣናዊ ተንኮል፣ ጭካኔ እና አሰራሮች ሁሉ በአንድነት የሚገለጡበት ክስተት ነው።

በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ የሮማ ገዥ ኮንስታንቲን የሮማ ጳጳስን ሮም ውስጥ ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ ስልጣን ሰጥቶ ሾመው። ኮንስታንቲን እራሱ ደግሞ ወደ ኮንስታንቲኖፕል ሄደ። ደግሞም ለሮማ ጳጳስ በጣም ብዙ ገንዘብ ሰጠው። የስላሴ አስተምሕሮ በኒቅያ ጉባኤ ተወስኖ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት በግዴታ ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደረገ።

ይህ ምዕራፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንዴት በዓለም ላይ ገዥ ሆና እንደተነሳች ነው የሚያሳየው።

ይህ ግን አውሮፓ ሁለተኛዋ የሮማ መንግስት ሆና ተነሳች ማለት አይደለም።

የሮማ ማንሰራራት የተገለጠው በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓለምን ለመቆጣጠር እንደ ቤተክርስቲያን እና እንደ ገንዘብ ኃይል ሆና መነሳቷ ነው። እንደ ሐይማኖታዊ የዲኖሚኔሽን መሪነታቸው የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲክዱና የሰው አመለካከቶችን እንዲሁም የአሕዛብ ልማዶችን እንዲቀበሉ ማሳመን ነው።

ክሪስማስ እና ስላሴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ቃላት ናቸው፤ ሁለቱም አመጣጣቸው የአሕዛብ ልማድ ነው። የፋሲካ እንቁላሎችን እና የፋሲካ ጥንቸሎችንማ ባንጠቅሳቸው ይሻላል። ሊቀጳጳሳት፣ ካርዲናሎች፣ ፖፕ፣ ፖንቲፍ።

እግዚአብሔርም የሚጠራው በሶስት ማዕረጎች በመሆኑ ስም እንዳይኖረው ተደርጓል። በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም። ይህ ስም ማነው? ስሙን ካላወቁ ያ ቤተክርስቲያን በሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽናዊ ወጥመድ ውስጥ ወድቋል።

አሕዛብ የሆኑት የሮማ ቄሳሮች ካፒቶላይን በተባለው ኮረብታ ላይ ነበር ቤተመንግስታቸው። የሮማ መንግስት ማዕከል ወይም መናገሻው ካፒቶላይን ኮረብታ ላይ ያለው የጁፒተር ቤተመቅደስ ነው።

ከዚህ በታች ያለው ስዕል ሮም ኢጣልያ ውስጥ የተመሰረተችባቸውን የመጀመሪያዎቹን ሰባት ኮረብታዎች ያሳያል።

 

 

ቄሳሮቹ ኦዶዋሰር በተባለው መሪ አማካኝነት በባርቤሪያኖች እጅ ስልጣናቸውን ተቀምተው ተደመሰሱ። ካፒቶላይን ኮረብታ የስልጣን ማዕከል ወይም መናገሻ መሆኑ ቀረ። ከዚያ ወዲያ ፖፑ ቀስ በቀስ ካኤልያን ኮረብታ ላይ ካለው ከላተራን ቤተመንግስት ተነስቶ ወደ ስልጣን ወጣ፤ ላተራን ቤተመንግስት እስከ አሁንም ድረስ የፖፑ መኖሪያ ነው። ፖፑ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ሐይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው። የዓለም ሁሉ መንግስታት እጅግ ብዙ ሆነው የተሰበሰቡት በፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ ቀብር ሥነ ስርዓት ላይ ነው። ለሞቱ የሆነው ቁስል ተፈሷል። ከቄሳር እጅ የወጣው ስልጣን በፖፑ እጅ ገብቷል፤ በአሁኑም ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ እያደረገ ነው። አሕዛቦቹ ሮማውያን ብዙ ግዛቶችን ተቆጣጠሩ፤ ነገር ግን የግዛታቸው ስፋት በዝቶ ያን ሁሉ ምድር ከወረራ ለመከላከል ያስከተለባቸው ወጪ ከብዷቸው ኪሳራ ውስጥ አስገባቸውና፤ ምክንያቱም ያላቸውን ገንዘብና ሃብት ሁሉ ግዛታቸውን ለማስጠበቅ ወጪ ያወጡበት ነበር። የሮማ ቤተክርስቲያን ግን ከሮማ መንግስትም ይልቅ ብልጥ ናት። እርሷ የሰዎችን አእምሮ በመግዛት ወደ ተከታዮቿ ገንዘብ እንዲሰጧት ታደርጋለች። በዚህ መንገድ ወደየሃገሩ በተስፋፋች ቁጥር ሃብቷ እየጨመረ ይሄዳል።

ሰባቱ የሮም ኮረብታዎች።

የባለ ሰባት ራሱ አውሬ ሚስጥር መፍቻው ይህ ነው። ሰባቱ ራሶች የመጀመሪያዋ የሮም ከተማ የተመሰረተችባቸው ሰባት ኮረብታዎች ናቸው። ሮሙለስ እና ተከታዮቹ ራሳቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ ሲሉ መኖሪያቸውን በኮረብቶቹ አናት ላይ ሰሩ። ሰባቱንም ኮረብቶች ከተቆጣጠሩ በኋላ ለጥበቃ ብለው በሰባቱ ኮረብቶች ዙርያ አጥር ሰሩ (ከላይ ያለው ካርታ ላይ ቀዩን መስመር ይመልከቱ)። በጥንት ዘመን አንድ መንደር ዙርያ አጥር ከተሰራ በኋላ መንደሩ ከተማ ይባላል። ስለዚህ ሮም የሰባቱ ኮረብቶች ከተማ በመባል ታወቀች።

ባሕር እረፍት የሌላቸውን የአውሮፓ ሕዝብ ይወክላል፤ የሮም ቤተክርስቲያንም በእነዚህ ሕዝብ መካከል ነው የተነሳችው።

ይህ ባለ ሰባት ራሱ አውሬ ወድቆ የነበረውን የሮማ መንግስት ነገር ግን ኋላ የቤተክርስቲያን እና የገንዘብ ኃይል ሆኖ ተነስቷል። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትበልጣቸዋለች። ከየትኛውም የሐይማኖት መሪ የበለጠ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን የሚሰጠው ለፖፑ ነው።

63-0319 ሁለተኛው ማሕተም

ራሺያ በሁሉ ላይ አትነግስም፤ እኛ በሁሉ ላይ አንነግስም። በሁሉ ላይ የሚነግስ አንድ ንጉስ ብቻ … የናቡከደነጾር ምስል ውስጥ ያለው የብረት እግር ብረቱ ወደ ጣቶቹ ሁሉ እንደሚደርስ፤ ሮምም እንደዚያው ናት።

ሮም ግን እንደ ሕዝብ አይደለም እንቅስቃሴዋ፤ እንደ ቤተክርስቲያን ነው።

አውሮፓ የሮማ መንግስት ማንሰራራት አይደለችም።

ሮም ዓለምን በሙሉ መግዛት ትፈልጋለች። ሮም ዓለምን ሁሉ መግዛት የምትችልበት መንገድ እንደ ቤተክርስቲያን (ነጭ ፈረስ) ሆና ዓለምን በማሳት፤ እንዲሁም ፖለቲካዊ ኃይልን (ቀዩ ፈረስ) በመጠቀም፤ እና የገንዘብ ኃይል (ጥቁሩ ፈረስ) በመጠቀም ነው። እነዚህ ፈረሶች ሁሉ ወደ አንድነት እየመጡ እና የሚቀመጥባቸውን ሞት የተባለ ፈረሰኛ እየተጠባበቁ ናቸው።

የትኛውም ሕዝብ መሬትና ግዛት በመቆጣጠር በአካል ዓለምን መምራት አይችልም። እንግሊዝ ከቀረው ዓለም ሁሉ በቁጥር የሚበልጡ ብዙ መርከቦች ነበሯት፤ በእነዚህም መርከቦች ተጠቅማ የዓለምን አንድ አራተኛ ተቆጣጥራ ነበር። ነገር ግን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አከሰራትና ግዛቶቿ ሁሉ ተበታተኑ።

ኮምዩኒስቶች ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ኃይለኞች ሆኑና የዓለም አንድ ሶስተኛ ተቆጣጠሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን ራሺያ ከሰረች። እስካሁንም ኃይለኞች ናቸው ግን ገንዘባቸው አቅሙ ውስን ነው።

ቻይና ከራሺያ ይልቅ ጥበበኛ ናት። ቻይናዎች ኮምዩኒስት መንግስት መስርተው ኢኮኖሚያቸውን ግን የካፒታሊስት ኢኮኖሚ በማድረጋቸው በረቱ። ቻይናዎች አሁን ግዛት ለማስፋት እየተሯሯጡ አይደሉም፤ ነገር ግን የገንዘብን ኃይል በመጠቀም ኢንቨስት እያደረጉ እየነገዱ በብዙ ሃገሮች ላይ ተጽእኖዋቸውን ለመጨመር እየሰሩ ናቸው።

ሮም ልብ ብላ ትምሕርቷን ተምራለች። መሬት መያዝ ብዙ ተቃውሞ ያስነሳል፤ ወጭም ያበዛል። ነገር ግን እንደ ቤተክርስቲያን ፖፑ የሰዎችን አእምሮ መቆጣጠር እና ሰዎችም መንግስተ ሰማያት ውስጥ ቦታ ለማግኘት ሲሉ ለቤተክርስቲያን በሚሰጡት ገንዘብ ሃብታም መሆን ይችላል። የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ የተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ነኝ በማለት ፖፑ መንግስተ ሰማያት መግባት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎችን ማስከተል ችሏል።

በሩን የሚከፍተውን ቁልፍ የያዘው ቤጥሮስ እራሱ በሩ ከሆነው ከኢየሱስ የሚበልጥ ተደርጎ መቆጠሩን ልብ በሉ። ይህ አሳዛኝ ስሕተት ነው።

ራዕይ 13፡4 ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም፦ አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።

ሰይጣን በፖለቲካ ውስጥ ይሰራል። ስለዚህ ሰይጣን ፖፑ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ማድረግ እንዲችል ረድቶታል። ሰይጣን ለኢየሱስ ፖለቲካዊ ስልጣን ባቀረበለት ጊዜ ኢየሱስ አልቀበልም ብሎታል።

“ፖፑን ማን ሊዋጋው ይችላል?” ማንም።

ፖላንድ ውስጥ ኮምዩኒስቶች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሊያጠፉ ሞከሩ ነገር ግን ፖላንዳዊው ፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ ፖላንድ ውስጥ ኮምዩኒዝምን በማፈራረስ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይህም ኮምዩኒዝም ሙሉ በሙሉ በወደቀ ጊዜ ራሺያ በምሥራቅ አውሮፓ ውስጥ የነበራትን ተጽእኖ እንድታጣ ምክንያት ሆኗል። ስለዚህ የዓለም መሪዎች ፖፑን በአክብሮት ያዩታል። ፖፑ በዓለም ዙርያ እርሱን የሚደግፉ አስራ ሁለት መቶ ሚሊዮን ካቶሊኮች አሉት። የሮማ ካቶሊክ ተከታዮች በሁሉም ሃገር ውስጥ አሉ፤ ስለዚህ የትኛውም ሃገር ፖፑን ለመውጋት ቢያስብ ይቃወማሉ። ቫቲካን ሒትለርን እና ናዚዎችን ረድታለች፤ ነገር ግን ሁሉም በፖፑ ላይ ብዙ ክስ ለመመስረት ስለፈሩ ቫቲካን ሳትጠየቅ አመለጠች። በዓለም ዙርያ በሚኖሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ካቶሊኮች የተነሳ የፖፑ ተጽእኖ ይህን ያህል ታላቅ ነው።

ራዕይ 13፡5 ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ አብዛኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ስርየት በገንዘብ ይሸጥ ነበር፤ ካቶሊኮች ገንዘብ ከከፈሉ የሐጥያት ይቅርታ ይቀበሉ ነበር። አንድ የሞተ ሰው ፑርጋቶሪ ውስጥ ገብቶ ቅጣቱን እየተቀበለ ከሆነ በሕይወት ያለ ዘመዱ ለቤተክርስቲያን ገንዘብ ቢከፍልለት ፖፑ የሰውየውን ነፍስ ከፑርጋቶሪ የማውጣተ ስልጣን አለው ተብሎ ይታመን ነበር። ፖፕ ፍራንሲስ አሁን ጽንስ ለሚያስወርዱ ሴቶች ሐጥያታቸውን ይቅር እንዲሏቸው ለቄሶች ፈቃድ ሰጥቷቸዋል። ሐጥያትን ይቅር የማለት ስልጣን አለኝ በማለት ፖፑ ራሱን በእግዚአብሔር ቦታ አስቀምጧል።

አርባ ሁለት ወራት ማለት ሶስት ዓመት ተኩል ነው። ይህም ታላቁ መከራ ጀምሮ እስኪያበቃ የሚፈጀው ጊዜ ነው። ያም የመጨረሻው ፖፕ በዓለም ሁሉ ላይ የሚገዛበት ጊዜ ነው። አንድ ፖፕ ዳገማዊ ጴጥሮስ ነኝ በሚል ጊዜ በጣም ተጠንቀቁ።

የሮምን ከተማ የቆረቆራት ሰው ሮሙለስ ነው። የመጀመሪያው ገዥ ደግሞ ኦጋስተስ ነው። የመጨረሻው የሮም ገዥ ደግሞ ሮሙለስ ኦጋስተስ ነበር። እንዴት እንደሆን ሮማውያን የመጨረሻው ንጉሳቸው የመጀመሪያዎቹን ሰዎች ስም እንዲኖረው ማድረግ ችለዋል። በእነርሱ ቤት “ፊተኛ እኘ ኋለኛ” የሚለውን የኢየሱስን ማዕረግ ለመኮረጅ መሞከራቸው ነው።

እነርሱ እንደሚሉት የመጀመሪያው የሮም ፖፕ ጴጥሮስ ነበረ። ነገር ግን ይህም እንኳ ውሸት ነው ምክንያቱም የሮም ጳጳስ ራሱን ፖፕ ብሎ መጥራት የጀመረው በ400 ዓ.ም ነው። ይህም ጴጥሮስ ከሞተ ከሶስት መቶ ዓመታት በኋላ ነው።

ስለዚህ ዳግማዊ ጴጥሮስ የሚለው ስም ለመጨረሻው ፖፕ በጣም ተስማሚ ስም ይሆናል።

ራዕይ 13፡6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።

63-0321 አራተኛው ማሕተም

እርሱም እግዚአብሔርን ለመሳደብ አፉን ከፈተ፤ ስሙን ለመሳደብ … (መጠሪያ ማዕረግ ሊሰጥ) … ማደሪያውንም ሊሰድብ … (ይህም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስፍራ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስን መኖሪያ ሮም ውስጥ ለማድረግ፣ ቫቲካን ከተማ ውስጥ፤ እያለ ይቀጥላል) … በሰማያት የሚኖሩትንም [ቅዱሳንን]። (ቅዳሳንን የተሳደበው አማላጆች ናቸው በማለት ነው)

“በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” የሚለው ንግግር ስም አይደለም። ሶስት የተያያዙ ማዕረጎች ብቻ ነው እንጂ። ነገር ግን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዚህ መንገድ ነው የእግዚአብሔርን ስም ያስወገደችው፤ ከዚያ በኋላ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ይህንኑ እንደ ምሳሌ እንዲከተሉ አሳመነቻቸው።

ወደ ማርያም እና ወደ ሞቱ ቅዱሳን የሚያደርጓቸው ጸሎቶች መልካቸውን ቀይረው የመጡ ጣኦት አምልኮዎች ናቸው።

ራዕይ 13፡7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።

63-0321 አራተኛው ማሕተም

ለእርሱም ቅዱሳንን ይዋጋ ዘንድ ተሰጠው… (እርሱም ተዋጋቸው።) … እንዲያሸንፋቸውም… (እርሱም አሸነፋቸው፡ በእንጨት ላይ አስሮ በእሳት አቃጠላቸው፤ እንዲሏቸው ለአንበሶች ጣላቸው፤ በሌላም በሚችለው መንገድ ሁሉ ገደላቸው።) … በነገዶች፣ በቋንቋዎች፣ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ኃይል ተሰጠው።

ይህም አሕዛብ የነበረችዋ ሮም ወደ ፓፓል ሮም ከተለወጠች በኋላ እና የካቶሊክ ኃይል ወደ ዓለም ሁሉ ከተሰራጨ በኋላ ነው ሮም ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ ያለው ኃይል ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆኖ የተነሳው።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ግድያውም በመጠኑ የቆመው በ1700 ዓ.ም አካባቢ ነው።

ነገር ግን ሁለተኛ አውሬ ወይም ኃይል ደግሞ ከምድር ይወጣል። ባሕር በሕዝብ ብዛት የተጨናነቁትን የአውሮፓ ሃገሮች ነው የሚወክለው።

ምድር ደግሞ ሕዝብ ተነታትነው የሚኖሩባቸው የአሜሪካ ሰፋፊ ግዛቶች ይወክላል። እስፔይኖች ፈንጣጣ እና ሌሎች በሽታዎችን ወደ ሜክሲኮ እና ደቡብ አሜሪካ አመጡ። የአሜሪካ ኢንዲያኖች ይህንን በሽታ ሊቋቋሙ ስላልቻሉ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሞቱ። ፒልግሪም ፋዘርስ የተባሉት የሐይማኖት ስደተኞች አውሮፓ ውስጥ ከደረሰባቸው ስደት ለማምለጥ ማሳቹሴትስ ውስጥ የምትገኘው ፕሊማውዝ ሮክ የምትባለው ቦታ በ1620 ዓ.ም ሲደርሱ በምድሪቱ ላይ ብዙም ኢንዲያኖች አልነበሩም።

እነዚህ ፕሮቴስታንቶች ንጉስ የሌለበት ሃገር እና ፖፕ የሌለባት ቤተክርስቲያን ፈልገው ነው የመጡት። የሐይማኖት እና የመናገር ነጻነት ፈልገዋል። (ሁለቱ የበጉ ቀንዶች)። ኮንግረስ ከፈለገ ወደብ መዝጋት ይችላል ግን የአንድ ዜጋን አፍ መዝጋት አይችልም። የመጀመሪያዎቹ መሪዎቻቸው እንደ ዋሺንግተን እና ሊንከን የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎች ነበሩ። ሃገሪቱ ግን በኃይል እያደገች ስትሄድ እግዚአብሔርን መምሰል በፖለቲካዊ ኃይል እና ገደብ በሌለው የገንዘብ ፍቅር ተተካ።

ራዕይ 13፡11 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።

ቤተክርስቲያኖች ፖለቲካ ውስጥ መግባት ጀመሩ። በ1906 አዙዛ እስትሪት ሎሳንጀለስ ውስጥ የተጀመረው የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት በ1917 የተደራጁ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ሆነ። ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት እንዲመልሰን የመጣው የዘመን መጨረሻው የዊልያም ብራንሐም መልእክት እንደተሰነጣጠቀ መስተዋት ወደ ብዙ ቡድኖች ተከፋፈለ፤ ይህም የሆነው ፓስተሮች የዊልያም ብራንሐምን ንግግሮች እየወሰዱ አስተዋዮች እንዲባሉ ሲጣደፉ የገዛ ሃሳባቸውን እንዲደግፍላቸው አድርገው በመተርጎማቸው ነው። ማድረግ የነበረባቸው ግን የዊልያም ብራንሐምን ንግግሮች ተጠቅመው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገጣጠም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮዎችን ማዘጋጀት ነበር።

ራዕይ 13፡12 በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።

አሜሪካ በዓለም ዙርያ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችን የምትደግፍበት የገንዘብ አቅም አላት። አንድ ዘገባ እንዳመለከተው አሜሪካ ውስጥ ያሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ብዛታቸው በዓለም ሁሉ ካሉ አገልጋዮች ቁጥር ይበልጣል። የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች የስላሴ አስተምሕሮ እንዲሰራጭ አድርገዋል (ይህም ከካቶሊክ የኮረጁት ነው)፣ ሌላ ደግሞ ክሪስማስ (ከካቶሊክ የተኮረጀ)፣ ፓስተር የቤተክርስቲያን ሃላፊ እንዲሆን ማድረግ (ካቶሊኮች እንድ ቄስ የአንድ ቤተክርስቲያን ሃላፊ እንዲሆን ከሚያደርጉበት ልማድ የተኮረጀ)፣ ቤተክርስቲያኖች ፖለቲካ ውስጥ መሳተፋቸው (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ ጋር ከመጠላለፏ የተኮረጀ)፣ የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደነበረ ማብራራት አለመቻል፤ ምክንያቱም አዳምና ሔዋን የዛፍ ፍሬ ነው የበሉት ስለሚሉ (ይህም ከካቶሊክ የተኮረጀ ነው)። ይህ የዛፍ ፍሬ ምሳሌያዊ እንጂ ቁሳዊ ፍሬ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር በሶስተኛው ቀን ሁሉንም የዛፍ ፍሬዎች መልካም ናቸው ብሏል። ኢየሱስ ደግሞ ሰው ወደ አፉ በሚገባ ነገር አይረክስም ብሏል። ስለዚህ መልካም እና ክፉውን የምታሳውቀዋ ዛፍ ፍጥረታዊ ዛፍ አይደለችም።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

13 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን።

ማቴዎስ 15፡11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው።

ፍራፍሬ ሁሉ መልካም ነው፤ የሚበላ ነገር ደግሞ ሰውን ሊያረክስ አይችልም። ስለዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና የሚከተሏት የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች ሔዋን የዛፍ ፍሬ በልታ ለምን ልጅ በመውለድ እንደተቀጣች ማብራራት አይችሉም። እግዚአብሔር አዳም እና ሔዋንን ለምን ንሰሐ ግቡ እንዳላላቸው ማብራራት አይችሉም። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደሆነ ሳያውቁ መሃይም ሆነው ቀርተዋል። ባለማወቃቸውም ምንም ሳይመስላቸው ተደላድለው ይኖራሉ።

ራዕይ 13፡13 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።

13 የአሜሪካ ቁጥር ነው ምክንያቱም አሜሪካ ስትመሰረት በ13 ግዛቶች ነው የጀመረችው። ስለዚህ 13፡13 የአሜሪካ ሳይንሳዊ ልዩ ቁጥር ነው። የአሜሪካ ብርታቷ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ ነው።

ታላላቅ ሳይንሳዊ ምልክቶች። አሜሪካ የመጀመሪያውን አቶሚክ ቦምብ በሒሮሺማ ከተማ ላይ ከ700 ሜትር ከፍታ በመልቀቅ አፈንድታዋለች። የዕሳት ዝናብ ወረደና ከተማይቱን አጋያት። በዚህ ታላቅ ሳይንሳዊ ግኝት እጅግ ዘግናኝ ኢሰብአዊ ጭካኔ ተፈጽሟል ግን ደግሞም ጦርነቱ እንዲያቆም በማድረግ የብዙ ሰዎችን ሕይወትም አድኗል። የምንኖርበት ዘመን ጨለማ ዘመን ነው። የሳይንሳዊ እውቀት ዛፍ ስሮቹ መራራ ናቸው። የሰው ፈጠራዎች ሁሉ ክፉ ጎን አላቸው፤ ልክ እንደሚፈውሱ ነገር ግን የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላቸው መድሐኒቶች ናቸው።

አሜሪካኖች የመጀመሪያዎቹ (እስከ 2017 ደግሞ ብቸኞቹ) ጨረቃን የረገጡ ሕዝብ ናቸው። በሰዓት ከ40,000 ኪሎ ሜትር በላይ እየፈጠነ የተመለሰው የጠፈር መንኩራኩር ከባቢ አየር ውስጥ በሚፈጠረው ሰበቃ ለሶስት ደቂቃ ከግማሽ እንደ ዕሳት ኳስ እየነደደ ወረደ። ይህም በግልጽ ወደ ምድር የሚወርድ ዕሳት ነው፤ መንኩራኩሩ በምድር አጠገብ ባለው ጥቅጥቅ ያለ አየር ምክንያት ፍጥነቱ ቀንሶ ፓራሹቶቹ እስኪከፈቱ ድረስ እንደ እሳት እየነደደ ነው የሚወርደው።

የአሜሪካ ሳይንሳዊ ግምባር ቀደምነት በዓለም ሁሉ ታውቋል። በተለይም ደግሞ ወደ ጠፈር የሚደረገውን እሽቅድምድም ካሸነፉ በኋላ።

ራዕይ 13፡14 በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።

ዛሬ የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች የሚያደርጓቸው ተዓምራት ዓላማቸው የቤተክርስቲያንን ድርጅታዊ ኃይል እና የገንዘብ ብዛት በመጠቀም የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት አምጥቶ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅጂ ወይም ምስል ለማድረግ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቀስ በቀስ ተገፍቶ እየወጣ ነው። ለምስጋና እና ለአምልኮ ዲስኮ ሙዚቃ መጠቀም ተጀምሯል። ፍቅር እና ሕብረት ላይ ትልቅ ትኩረት እየተደረገ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ግን ጊዜ “ያለፈባቸው” ፋሽኖች ተደርገው ተቆጥረዋል። ስለዚህ ማንም በቁም ነገር አይቀበላቸውም።

ወንጌላውያን ቤተክርስቲያኖች መዳን እና መልካም ሕይወት በንጽሕና መኖር ላይ ያተኩራሉ። ይህም ለእነርሱ አመቺ ስለሆነ ነው። አንዳንዶች በልሳናት መናገር ላይ ያተኩራሉ። ከዚያ በኋላ “አዘውትራችሁ ቤተ ክርስቲያን ሂዱና ትድናላችሁ” ነው የሚሉት። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እየቀነሰ ሲሄድ ቤተክርስቲያኖችን የሚለያያቸው ነገርም በዚያው ይጠፋል። ስለ ሁሉ ነገር የሚያስበው ፓስተሩ ነው፤ ሕዝቡ እንደ ከብት ዝም ብለውት ይከተሉታል። መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሰዎች ከተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲሰባሰቡ በሚያውቋት ጥቂት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ላይ በቀላሉ (ከጌታ ምሕረት የተነሳ) መስማማት ይችላሉ።

ለአስተምሕሮ የሚሰጠው ቦታ በጣም ትንሽ ነው። “ቢያንስ ማወቅ የሚጠበቅብኝ ምንድነው?” የሚለው የብልጦች ጥያቄ ተደርጎ ይቆጠራል።

የሮማ ካቶሊኮች ስለ እነርሱ የሚናገሩ ትንቢቶችን ላለመጋፈጥ ብለው ትንቢቶች ሁሉ የሚፈጸሙት ወደፊት በታላቁ መከራ ዘመን ነው ብለው ያስተምራሉ። ይህንን ሃሳብ ፕሮቴስታንቶች በሙሉ ልባቸው ተከትለውታል። ሲያስተምሩ ብታዳምጧቸው የሁለት ሺ ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ከዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ጥርግ ብሎ ይጠፋል፤ ምክንያቱም በእርሱ አስተምሕሮ መሰረት ይህ ሁሉ የሚሆነው ወደፊት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው። ማንም ጥያቄ የሚያነሳ የለም ምክንያቱም በታላቁ መከራ ውስጥ ሙሽራይቱ ስለማታልፍበት በትክክል ተረዳነው አልተረዳነው ምን ለውጥ እናመጣለን ይላሉ።

ስለዚህ የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ያሉ ትንቢቶች ሁሉ ለሰነፎቹ ቆነጃጅት በታላቁ መከራ ውስጥ ተፈርዶባቸው በገቡ ጊዜ ምን እንደሚከናወን ለማሳወቅ ነው የተጻፉት። ሰነፎቹ ቆነጃጅት የቤተክርስቲያን ዘመናት ምን እንደሆኑ መረዳት እንዲችሉ ለማገዝ የተጻፉ ትንቢቶች የሉም። የሚገርም ነው። ታዲያ ልባም ሊያደርጋቸው የሚችለው ምንድነው?

ፕሮቴስታንቶች የሰባት ዓመት መከራ አለ ብለው ያምናሉ፤ አይሁዶች በታላቁ መከራ ወቅት ቤተመቅደሳቸውን መልሰው ይገነባሉ ብለው ያስተምራሉ፤ የአውሮፓ ሕብረት መሪ የመጨረሻው አውሬ ሆኖ ይነሳል ብለው ያምናሉ፤ ፍልስጥኤሞች (ከ1967 በፊት መንግስት ያልነበራቸው) እና እሥራኤል የሚያደርጉት የሰላም ስምምነት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ዋነኛ ትኩረት ነው ብለው ያስተምራሉ።

ከእነዚህ እምነቶች ውስጥ አንዳቸውም እንኳ ጥቅስ በጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተፈትሸው መረጋገጥ አይችሉም።

ዝርዝር ጥያቄ ሲቀርብላቸው ሁሉም መልስ የላቸውም።

ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ስሕተቶች የሚያምኑ ፕሮቴስታንቶች ናቸው “ምሑር” ተብለው ተቆጥረው በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ ቅዠት የመሰሉ ቲዎሪዎችን የሚያስፋፉት። ነገር ግን ዋነኛውን ትምሕርታቸውን እስከተቀበላችሁ ድረስ ከሌሎቹ ጋር አንድ ላይ ትቆጠራላችሁ። በተሳሳተ እውቀት ላይ የተመሰረተ ወንድማማችነት ሰዎችን ያስተሳስራቸዋል።

ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

ቤተክርስቲያን ፖለቲካውን መቆጣጠር ትፈልጋለች። ገንዘብ የሁሉም ድርጅት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ነው። ከሃገሮች መካከል ደግሞ አሜሪካ ብቻ ናት በስም ፕሮቴስታንት የሆነ ነገር ግን ብዙ የካቶሊክ እምነቶችን አቅፎ የያዘ ዓለም አቀፍ ዲኖሚኔሽናዊ ድርጅት ለመክፈት የሚበቃ የገንዘብ አቅም ያላት። ይህም ዓለም አቀፋዊ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ድርጅት የመጀመሪያዋ የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽን ምስል ነው። የምንኖርበት ዘመን የዲኖሚኔሽኖች መብራት የሚበራበት እንጂ በቃሉ ብርሃን የምንመላለስበት አይደለም።

ራዕይ 13፡16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥

ይህ በዲኖሚኔሽኖች አማካኝነተ የሚደረግ አእምሮን የመቀየር ስራ ነው። ቤተክርስቲያኖች የሰዎችን አስተሳሰብ በመቆጣጠር ብልሃት ባለው መንገድ ከመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ አስወጥተው ወደ ሰው ሰራሽ መንገድ ይመሯቸዋል። ክርስቲያኖች እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉ ልዩ ልዩ ጥቅሶች አማካኝነት ተከታትለው ማረጋገጥ ትተዋል። ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያናቸው የምታስተምራቸው ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው ቃል ይበልጣል ብለው ማሰብ ከጀመሩ ቆይተዋል። መጽሐፍ ቅዱስን ከማመን የበለጠ ቤተክርስቲያንን እናምናለን።

ቤተክርስቲያን አንዴ አስተሳሰባችንን ከተቆጣጠረች በኋላ ድርጊታችንንም ማለትም ቀኝ እጃችንንም ትቆጣጠራለች።

ከዚያ በኋላ የቤተክርስቲያን እንጂ የክርስቶስ አይደለንም።

65-0829 የሰይጣን ኤደን

አሁን ደግሞ ይህንን የሚኖሩበትን ትልቅ ኤደን አምጥቷል፤ እርሱም የቤተክርስቲያን ዓለም ኤደን ነው። አሁን ሁላቸውም በታላቁ ኢክዩሜኒካል ምክር ቤት በኩል ወደ አንድነት እየመጡ ናቸው፤ የዓለምን ሁሉ ቤተክርስቲያናት በአንድ ራስ ስር ለማስተዳደር እየጣሩ ናቸው፤ በዚህም አንድነት ውስጥ ሰይጣን በዙፋን ተቀምጦ ይገዛል።

65-0801M የዚህ ክፉ ዘመን አምላክ

ታላቅ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን የመገንባት እቅዱን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ የዓለም ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት፤ ይህ ትልቅ ዲኖሚኔሽን ነው፤ ይህን የሚዘጋጀው ዓለም ሁሉ ወደ አንድነት በመጣች ቤተክርስቲያን ስም አውሬውን እንዲያመልኩት ነው። ይህን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማንበብ ትፈልጋላችሁ? ራዕይ 13፡6 እና 8። ይህ ዘመናዊ የባቢሎን ግምብ ነው።

ያ ናምሩድ የተባለ ግብዝ ያንን ታላቅ ግንብ ሰርቶ ሌሎቹ ታናናሽ ከቶሞች በሙሉ ለእርሱ ግብር እንዲከፍሉ ማድረጉን አታስታውሱም? ባቢሎን እና ለፍላፊነት ማለት አንድ ናቸው። ስም ብቻ ቀይራ ነው እንጂ። ሮም የዛሬዋ ባቢሎን ናት። ዓለም ሁሉ ወደ ባቢሎን ትመጣለች፤ ወደ ባቢሎን የምትመጣውም በዓለም ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት በኩል ነው። ይህ ምክር ቤት እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ለባቢሎን እንድትሰግድ ያደርጋል። ቤተክርስቲያኖችም ምን እንዳደረጉ ሳያውቁ የአውሬውን ምልክት ይቀበላሉ። ምክንያቱም …

የተመረጡት ግን ቃሉን ይሰሙና ከባቢሎን ይወጣሉ።

ራዕይ 13፡17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።

ቤተክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ገዥ ትሆናለች።

ራዕይ 13፡18 አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

በ750 ዓ.ም አካባቢ የኮንስታንቲን ስጦታ የሚል ሐሰተኛ ሰነድ ተዘጋጀ። ይህ ሐሰተኛ ሰነድ ኮንስታንቲን ኢጣሊያ ውስጥ ያሉ ግዛቶችን እና ምዕራቡን ዓለም በሙሉ ለፖፑ ለመስጠት ቃል እንደገባ ይናገራል። ይህ ሰነድ ኢጣልያ ላይ በ751 ወረራ ባደረገው የባርቤሪያውያን ሎምባርድ ነገድ ከመሸነፍ ፖፑን አድኖታል። ሎምባርዶች ከዚህ በታች ባለው ካርታ ውስጥ ከኢጣልያ ቢጫ ቀለም የተቀባውን ግዛት ተቆጣጠሩ።

 

 

ፖፑ የፍራንኮች መሪ የሆነው ፔፒን ሎምባርዶችን እንዲያስወጣለት ለምኖታል፤ ፔፒንም ፖፑ እንደጠየቀው አድርጓል። ፖፑ ለፔፒን የመንግስተ ሰማያት በር መክፈቻ ቁልፍ ያለው በቅዱስ ጴጥሮስ ዘንድ ብቻ መሆኑን እንዲሁም ጴጥሮስ ይህንን ቁልፍ የጴጥሮስ ተተኪ ለሆነው ለፖፑ እንዳስተላለፈ አሳምኖታል። ይህ ሃሳብ ለባርቤሪያኖች ተስማምቷቸዋል። ስለዚህ ሮም ውስጥ ለተቀመጠው ፖፕ ጥበቃ ያደረገለት ባርቤሪያን ሲሞት ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር ይከፍትለታል።

ይህ አስተምህሮ ለፖፑ በባርቤሪያውያን መካከል ትልቅ ተቀባይነት አስገኝቶለታል። ይህንን ክብር ማንም ሊነጥቀው አልቻለም። ወደ መንግስተ ሰማያት የሚገቡበትን በር መክፈቻ የያዘው ፖፑ ብቻ ነበር፤ ይህንንም ስልጣን ያገኘው በአንድ ሰው በጴጥሮስ ዝና አማካኝነት ነበር። የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ የተሰተው ለጴጥሮስ ብቻ ነበር። (የመንግስተ ሰማያት በር ኢየሱስ ነው፤ ጴጥሮስ ግን ከኢየሱስም የሚበልጥ ስልጣን እንዳለው ተደርጎ ነበር ትምሕርት የሚሰጠው ምክንያቱም ቁልፉ በጴጥሮስ እጅ ነው፤ ለመክፈትና ለመዝጋትም ውሳኔ በጴጥሮስ እጅ ነው ተባለ።) ስለዚህ ፖፑ ይበልጥ ኃያል እየሆነ ሄደ። በማንኛውም ነገር ፖፑን ከደገፋችሁ ጴጥሮስ ወዳጃችሁ ይሆናል።

ይህ የተጭበረበረ ሰነድ ውስጡ አንድ የሚገርም ዓረፍተ ነገር ነበረው።

“የተባረከው ቅዱስ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ልጅ ምትክ ተደርጎ ስለተሾመ የእርሱ ተተኪ የሆኑት ፖንቲፎችም በእኛ እና በግዛታችን ሁሉ በምድር ላይ የበላይ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል”።

ፖፑ የጴጥሮስ ተተኪ ነው። የካቶሊክ ጳጳሶች እስከ ዛሬ ድረስ የጴጥሮስ ተተኪ ነን ይላሉ።

ጴጥሮስ ሰው ሆኖ ሳለ “የእግዚአብሔር ልጅ ተወካይ” አሉት። በላቲን ይህ VICARIVS FILII DEI ይባላል።

አንዳንድ የላቲን ፊደሎች ቁጥሮችን ይወክላሉ። I = 1 V = 5 L = 50 C = 100 D = 500

V    I    C    A    R    I    V    S    F    I    L    I   I               D E I

5    1   100  _   _     1     5    _   _    1   50  1   1               500 _ 1

እነዚህን ቁጥሮች ስንደምራቸው የምናገኘው 666 ነው።

(ሮማውያን ፊደሎችን በድንጋይ ላይ ሲቀርጹ በ U ፈንታ V ፊደልን ይቀርጻሉ ምክንያቱም ቀጥ ያሉ መስመሮች በድንጋይ ላይ ለመቅረጽ ቀላል ናቸው።

ለዚህ ነው “ደብል ዩ” ወይም UU የተባለው ፊደል VV ተደርጎ የሚጻፈው፤ እርሱም ኋላ አሁን የምናውቀውን W ሆነ።)

እስከ ዛሬ አንድ ሰው ማለትም ጴጥሮስ ብቻ ነው VICARIVS FILII DEI ወይም የእግዚአብሔር ልጅ ምትክ በሚል ማዕረግ የተጠራው።

የካቶሊክ ጳጳሳት ግን የጴጥሮስን ዝና በመጠቀም በቤተክርስቲያን ላይ ራሳቸውን የበላይ አድርገው አንግሰዋል፤ ምክንያቱም ራሳቸውን የጴጥሮስ ተተኪዎች ብለው ሰይመዋል።

ስለዚህ በእነርሱ ትምሕርት መሰረት ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት አለመግባታችሁ የሚወሰነው በኢየሱስ ሳይሆን በጴጥሮስ ነው፤ ምክንያቱም በሩ ይከፈትላችሁ እንደሆን የሚወስነው ጴጥሮስ ነው። ከዚህ የከፋ ውሸት የለም።

ጴጥሮስን ልንወቅሰው አንችልም፤ ምክንያቱም ጴጥሮስ እኔ የኢየሱስ ምትክ ነኝ ብሎ አያውቅም።

ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን ደጅ በተሰጠው ቁልፍ ከፍቷል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ሁለተኛው አውሬ ማለትም ፕሮቴስታንት አሜሪካ ከመጀመሪያው አውሬ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ተባብሮ በመስራት ዓለም ሁሉ ለመጀመሪያው አውሬ እንዲሰግዱ ያስገድዳል። አሜሪካ በዓለም ላይ ኃያል ሃገር ሆና የተነሳችው ይህ ትንቢት በእርሷ እንዲፈጸም ነው።

 

ምዕራፍ 13

 

13 ከአሜሪካ ጋር በተያየዘ ብዙ ትርጉም ያለው ቁጥር ነው።

አሜሪካኖች ነጻነታቸውን ያወጁ ጊዜ መንግስት ሆነው የጀመሩት በ13 ግዛቶች ነው።

ባንዲራቸው ውስጥ 13 ቀይ እና ነጭ መስመሮች አሏቸው።

13 ቁጥር የአሜሪካ መንግስት አርማ ውስጥ ሁሉ ሳይቀር አለ።

 

 

የአሜሪካ መንግስት አርማ ውስጥ ያለው መፈክር “E Pluribus Unum” ይላል። “ከብዙዎች፣ አንድ” ማለት ነው። የፊደሎቹ ብዛት 13።

ከላይ በኩል ክብርን የሚወክለውን ሰማያዊ ቀለም የከበበ ደመና አለ። በዚህ ሰማያዊ ቀለም ውስጥ 13 ከዋክብት አሉ።

የአሜሪካ አርማ ላይ ያለው ንስር በአንድ እግሩ የያዘው የወይራ ቅርንጫፍ 13 ቅጠሎች አሉት፤ ይህም የሰላም ምልክት ነው።

በተጨማሪ በቅርንጫፉ ላይ 13 የወይን ፍሬዎችም አሉ።

ያለፈው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰላማዊ የሳይንስ ዘመቻ ጨረቃ ላይ መውጣት ነበረ። ወደ ጨረቃ በተላኩት አፖሎ ሮኬቶች ውስጥ በእያንዳንዱ ሶስት የጠፈር ተመራማሪዎቸ ነበሩ። ሰው ተሳፍሮ የሄደባቸው የመጀመሪያዎቹ ወደ ጨረቃ የተደረጉት የሮኬት በረራዎች አፖሎ 7፣ 8፣ 9 እና 10 ነበሩ። ሶስት ሶስት ሰዎች የተሳፈሩባቸው አራት ሮኬቶች በአጠቃላይ 12 ሰዎችን ነው ይዘው የሄዱት። ስለዚህ ወደ ጨረቃ በሚደረገው በረራ ውድድር ውስጥ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል በ1969 ጨረቃ ላይ በእግሩ የቆመው ኒል አርምስትሮንግ 13ኛው ሰው ነበረ። ይህ ሰው ጨረቃ ላይ በእግሩ መቆሙ ለአሜሪካ ታላቅ ሳይንሳዊ ዝና አጎናጽፏታል። 49 ዓመታት ካለፉ በኋላ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ ከትኛውም ሌላ ሃገር አንድ ሰው እንኳ ጨረቃ ላይ አልቆመም።

የአተም ኑክልየስ ባህሪው ምን ዓይነት እንደሆነ የተደረሰበት በ1932 ኒዩትሮን በተገኘ ጊዜ ነው። ከዚያ በኋላ የተደረገው ጥድፊያ የዩራኒየምን አተም ለመሰንጠቅ ነው። ከጦር መሳሪያዎች ሁሉ እጅግ አደገኛው አቶሚክ ቦምብ ከ13 ዓመታት በኋላ በ1945 በአሜሪካኖች አማካኝነት ፈነዳ። ይህም የአሜሪካኖችን ሳይንስ ዝነኛም አስፈሪም አደረገው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23