ራዕይ 6 - ክፍል 3 - ስሕተት መናገር ኢየሱስን መግደል ነው



በፓስተር የሚተዳደሩ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ። 6ኛውን ማሕተም ለመፍታት በቂ ኃይል ያላቸው ሙሴ እና ኤልያስ ብቻ ናቸው።

First published on the 20th of December 2021 — Last updated on the 16th of January 2022

ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በተክርስቲያን ከሃዲ ናት

 

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ስለ አራተኛው ማሕተም የሚናገረው ይህ ጥቅስ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በምድር ላይ ስለሚሆነው ሁኔታ ይገልጻል። ይህችም ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን አልፈልግህም ብላ ያስወጣችው ከሃዲዋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ናት። የእግዚአብሔርን ቃል ከመቀበል ይልቅ የዊልያም ብራንሐምን ንግግር ጥቅሶች መሰነጣጠቅና እንደሚፈልጉት አድርገው እየገጣጠሙ የተለያዩ ሃሳቦችን መፈልፈል መርጠዋል። ሰዎች የሚያምኑት ነገር በሚኖሩበት አካባቢ መልክአ ምድር ይወሰናል። በዚህኛው የዓለም ክፍል የምትኖሩ ከሆነ አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ በሚያስተዳድርበት ቤተክስቲያን ውስጥ ልትሆኑ ትችላላችሁ። ወደ ሌላ የዓለም ክፍል ብትሄዱ ደግሞ ሌላ ቦታም የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ የሚገዛ ግለሰብ ሌላ ዓይነት ሃሳብ ሲያስተምር ታገኙታላችሁ። ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያለችዋ ቤተክርስቲያን ዕውር መባሏ አያስደንቅም።

ከዚያም በላይ የሚያስፈራው ነገር እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ከአፉ እንደሚተፋቸው የተናገረው ቃል ነው። የእግዚአብሔር አፍ ማለት የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

ይህም ማለት የዳኑ የቤተክርስቲያን አባላት ወደ ታላቁ መከራ እየተነዱ ናቸው።

ወንድም ብራንሐም የተናገራቸውን ጥቅሶች የተጠቀመባቸው የመጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ለመግለጥ ነው። ይህም መረዳት ከታላቁ መከራ ያድነናል።

አሁን ግን የሜሴጅ ሰባኪዎች ወንድም ብራንሐም ያስተማረውን ትምሕርት በጣም በርዘው ከማበላሸታቸው የተነሳ ሰዎች የሚያምኑትን እምነት ከመጽሐፍ ቅዱስ አመሳክረው ማረጋገጥ አልቻሉም።

ከእንግዲህ በኋላ የሜሴጅ ተከታዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ርቀው ስለሚሄዱ ከእግዚአብሔር ቃል የሚመጣላቸውን ተግሳጽ አይቀበሉም። ደግሞም በሰው ንግግር ጥቅስ ላይ የተመሰረቱት ሃሳቦቻቸው ትክክለኛ ስለመሆናቸውም እርግጠኞች ሆነዋል ብለው ስላመኑ እነርሱን ከታላቁ መከራ ማዳን የማይቻል ነገር ነው፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል ማየት እንዳይችሉ በመንፈስ ታውረዋል።

የሜሴጅ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉ ሰዎችንም ጭምር ከመንገድ ማስወጣት ይፈልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የመከተል ፍላጎታቸውን አስጥለው እነርሱንም ማሳወር ይፈልጋሉ። እዚያ ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ ማንም ሰው ከታላቁ መከራ አይድንም።

ማቴዎስ 24፡22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።

ዛሬ የሜሴጅ ሰባኪዎች የወንድም ብራንሐምን ስሕተቶች የሚያርሙ ሰዎችን ያወግዛሉ። ስለዚህ የሜሴጅ ሰባኪዎች የወንድም ብራንሐም ስሕተቶች እንኳ ሳይቀሩ ፍጹም እንከን የሌለባቸው እውነቶች ናቸው ብለው እንዲያምኑ ይገደዳሉ።

ዛሬ ወደ 45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያንነት ወደ ተባዙት የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ይህ ግራ መጋባትና ስሕተት የተስፋፋው እንዴት ነው? ሁሉም የተለያየ አስተምሕሮ አላቸው ነገር ግን ሁሉም እኔ ትክክል ነኝ ይላሉ። ይህ ትልቅ መንፈሳዊ ድፍርስ ኩሬ ሲሆን ሊያደርቀውና አቃጥሎ ሊያነጻው የሚችለው ታላቁ መከራ ብቻ ነው። ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ ይገደላሉ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ለአርማጌዶን ጦርነት ተመልሶ ሲመጣ ሁሉም ሰው ያለቅሳል። ክርስቲያኖች ሁሉ ተገድለዋል። ጌታ ለበቀል ሲመጣ ክርስቲያኖችን የገደሉ ሁሉ ፊት ለፊት ስለሚያዩት በፍርሃት ያለቅሳሉ።

ራዕይ 1፡7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።

በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ሲመጣ በምድር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ማንም ደስተኛ አይሆንም።

ማቴዎስ 24፡30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤

መጀመሪያ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል። ከፍላግስታፍ በስተሰሜን አሪዞና ውስጥ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ሰባት መላእክት ታላቅ ደመና ሰርተዋል። ከዚያም ማርች 8 ቀን 1963 እነዚያ 7 መላእክት ወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች ገልጦ እንዲያስተምር ትዕዛዝ ሰጡት። እርሱም ከማርች 17 – 24 ቀን 1963 ሰባቱን ማሕተሞች ገልጦ አስተማረ። ይህንም በማድረጉ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስራት ስለገለጠ ግለሰቦች የእርሱን ንግግር ወስደው በመጽሐፍ ቅዱስ በመመርመር እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲመሰርቱ አስቻለ። ከዚህም የተነሳ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት ይችላሉ።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

በመንፈስ የሚመሩ ሰዎች ጌታን ለመገናኘት ወደ ሰማይ ተነጥቀው ይሄዳሉ።

ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤

10 ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ

ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ የተጠቀሱት ልባሞቹ ቆነጃጅት ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራዊ ምሳሌዎች ትርጉም ያስተውላሉ።

የተቀሩት የብራንሐምን ትምሕርት ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያላረጋገጡና ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ያልቻሉ ሰዎች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ፤ በዚያም ይሞታሉ። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መገለጥ ከልባቸው አጥብቀው አልተቀበሉም። “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማወቅ አለብን” በማለት ፈንታ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማወቅ ምን ያደርግልናል?” ሲሉ ነበሩ።

ከዚያ በኋላ እነርሱን የገደሏቸው ሰዎች ደግሞ ኢየሱስ ከሙሽራይቱ ጋር በደመና ሲመጣ እራሳቸውም የሚሞቱበት ተራ ስለሚደርሳቸው ያለቅሳሉ።

 

ስሕተት የሌለበት መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን ብቻ መሆኑን ማስታወስ አለብን

 

ቤተክርስቲያን ዕውር ተብላ ለመጠራት ያበቃት ትክክል ባልሆነ የቤተክርስቲያን አወቃቀር መዋቀሯ ነው።

አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ አጥቢያ ቤተክርስቲያንን እንዲመራ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ስልጣን አልተሰጠውም።

ስለዚህ ከመጀመሪያው ጀምሮ ፓስተሩ ራስ የሆነበት የቤተክርስቲያን አወቃቀር ስሕተት ነው።

እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን አወቃቀር በገለጠ ጊዜ ፓስተሮችን ጭራሽም አልጠቀሳቸውም።

እግዚአብሔር አገልገዮችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ባስቀመጠ ጊዜ ፓስተሮችን አልጠቀሳቸውም።

1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።

አዲስ ኪዳንን የጻፉ ሐዋርያት ከሁሉም በላይ ታላቅ ናቸው።

ከዚያ በዘመን መጨረሻ የተላከው ነብይ ወደ ሐዋርያት እምነት ሊመልሰን ይገባል። ነብይ የራሱን ሃሳብ ይዞ መምጣት አይችልም። ነብይ ሐዋርያቱ የጻፉትን እየገለጠ ነው የሚናገረው።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል

ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች አገልግሎት ነው፤ እነዚህም ነብዩ የተናገረውን ቃል ተቀብለው ሐዋርያት ከጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ያመሳክሩታል። የዛኔ እምነታችን የሚመሰረተው በሰው ንግግር ጥቅስ ላይ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ በተጠቀሰ ስብከት ነው።

63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቅ ወደ ፍርድ አያመጣውም

አስተማሪ ልዩ ሰው ነው። አስተማሪው ከመንፈስ ቅዱስ ቅባት ስር ተቀምጦ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየተረተረ ፓስተሩም ሆነ ወንጌላዊው ሊገልጡት በማይችሉበት መንገድ ይገልጠዋል።

አንድ ትምሕርት ትክክለኛ መሆኑን መርምሮ ለማረጋገጥ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ ስጦታ ሊኖረው ይገባል።

 

አስተማሪው ሃሳቡን ለመረዳት ጥቅሶቹን ያነባቸዋል። ከዚያም ተያያዥ የሆኑ ጥቅሶችን እያገጣጠመ ሃሳቦቹ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ትክክለኛ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

ይህ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምሮ የማረጋገጥ ብቃት የመጽሐፍ ቅደስ አስተማሪ አገልግሎት ነው።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውን ዓይነት የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ራሱን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ የሾመው ግለሰብ ከእርሱ ጋር የማይስማማውን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ከቤተክርስቲያን ማባረር አለበት።

ከዚያም ራሱን የሾመው የቤተክርስቲያን ራስ መጽሐፍ ቅዱስን እራሱ ሊያስተምር ይሞክራል፤ ነገር ግን ሃሳቦቹ ትክክለኛ መሆናቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፎ ማሳየት አይችልም፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ይልና በሰው ንግግር ጥቅሶች ይተካዋል። የሰውን ንግግር ጥቅሶች እየገጣጠሙ ያበጁትን አስተምሕሮዋቸውን የሚቃረን ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አይፈልጉም።

ስለዚህ የፓስተሩ ትክክለኛ አገልግሎት ምንድነው? የመጽሐፍ ቅዱስን ትምሕርት ሚስጥር መፍታት ሳይሆን እንደ እረኛ የሰዎችን የግል ችግር መፍታት ነው።

63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያቀርበውም

ነገር ግን አያችሁ በቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተሩ አለ፤ ፓስተሩም ልዩ ሰው ነው። የሰዎችን ጭንቀት መሸከም እንዲችል የተዘጋጀ ሰው ነው። ሸክም ተሸካሚ ሰው ነው፤ የሕዝቡን ቀምበር መሸከም የሚችል በሬ ነው። ፓስተሩ ሰው ከሰው ጋር ወይም አንድ ቤተሰብ ከሌላ ቤተሰብ ጋር ተጣልቶ ሳለ (ለማናቸውም ሳይወግን) ከሁለታቸውም ጋር አብሮ መቀመጥና ሁለቱንም አነጋግሮ ወደ እርቅ ማምጣት የሚችል ሰው ነው። አያችሁ? እርሱ ፓስተር ነው፤ እንዴት ችግር መፍታት እንደሚችል ያውቃል።

ወንጌላዊው ልዩ ሰው ነው። እንደ እሳት ኳስ የሚነድድ ሰው ነው። ወንጌላዊው ወደ ከተማ ገብቶ መልእክቱን ይሰብካል፤ ከዚያም ይወጣና ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳል። ወንጌላዊው ልዩ ሰው ነው።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጎመው በ1611 እና በ1769 መካከል በአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ነው፤ አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የጀመረው በ1750 ነው። በራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ከተጠቀሱት እንስሳት መካከል በሰው ዘመን እግዚአብሔር የሰውን እውቀት ባረከ። ስለዚህ በሰው የተመሰለው እንስሳ ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አዘጋጀ። ከዚያ በኋላ ጊዜው ንስሩ በተሰጠው ልዩ የማየት ተሰጥኦ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የሚያስተውልበት ነው።

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

ኒቆላዊነት እየተስፋፋ ይሄዳል፤ ትርጉሙ ምዕመናንን መግዛት ነው፤ በራሳቸው እንዳያስቡ ማድረግ ነው

 

ብዙ የሜሴጅ ፓስተሮች ወንድም ብራንሐምን ለማረም መሞከር ሐጥያት ነው ይላሉ።

ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም አንድ እውነት መጋፈጥ አለብን፤ የወንድም ብራንሐም ንግግሮች ውስጥ አንዳንድ ስሕተቶች አሉ።

“የዳንኤል 70 ሱባኤዎች” በሚለው በአንድ ስብከት ውስጥ ወንድም ብራንሐም የሆሳዕና ዕለት የዋለው አንዴ በ30 ዓ.ም ነው ይላል አንዴ ደግሞ በ33 ዓ.ም ነው ይላል። ከሁለቱ ቀናት አንዱ ስሕተት ነው።

በሌሎች ስብከቶች ውስጥ ደግሞ ታይተስ ኢየሩሳሌም ያፈረሳት በ70 ዓ.ም ነው ይላል ሌላ ጊዜ ደግሞ በ96 ዓ.ም ነው ይላል። ስለዚህ ከሁለቱ በአንዱ ተሳስቷል።

የእባቡ ዘር በሚለው ስብከቱ ውስጥ የተሰሎንቄ የቤተክርስቲያን ዘመን አለ ይላል፤ የጨለማው ዘመን 1,500 ዓመታት ነበር ይላል፤ ኒቅያ ፈረንሳይ ውስጥ ናት ይላል፤ በ325 የተደረገው የሎዶቅያ ጉባኤ ብሎ ይናገራል። ለእውነት ዋጋ የምትሰጡ ከሆነ እነዚህ ሁሉ መታረም ያለባቸው ስሕተቶች ናቸው።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን በተጠራጠረ ጊዜ እርማት ያስፈልገው ነበር። ስለዚህ እውነተኛ ነብያትም ሊሳሳቱ ይችላሉ። ነገር ግን ሁለቱ የዮሐንስን ስሕተት ያመኑ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለተኛ አልተጠቀሱም። (ስሕተትን የምታምኑ አማኞች ሁሉ ልብ በሉ)።

እግዚአብሔር ኒቆላዊነትን ይጠላል። የአምባ ገነንነት መንፈስ አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ መሆንን እንዲመኝ ያደርገዋል። የሰውየውን ስልጣን በሕዝብ ላይ ለማጽናጽት የተወሰኑ ሰው ሰራሽ ሥርዓቶች ቀስ በቀስ ይዘጋጃሉ። ዘመን እያለፈ ሲሄድ ሰዎች እነዚህን ሥርዓቶች ይላመዱዋቸዋል፤ ከዚያም እነዚህ ሥርዓቶች በሕዝቡ ወይም በምዕመናኑ ላይ በግድ ተጭነውባቸው ሕዝቡ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ ያደርጋሉ።

በመሰረቱ ኒቆላዊነት ሕዝቡ በራሳቸው አእምሮ እንዳያስቡ ያደርጋቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱን ቃል የተኩትን የሰው ንግግር ጥቅሶች ለመተርጎም በፓስተሩ ላይ ነው የሚደገፉት።

ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና

ኒቆላውያን። ይህ አንድን ቅዱስ ሰው ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ ማድረግ ነው። በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያንም አንድን ግለሰብ ከቤተክርስቲያን በላይ ከፍ የማድረግን ሥራ ትጠላው ነበር።

ነገር ግን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ በ170 ዓ.ም ቤተክርስቲያኖች ጳጳስ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆንላቸው ፈለጉ።

ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

በ312 ዓ.ም በጀመረው በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ሰውን ራስ አድርጋ መቀበልን መጥላት አቆመች።

ቤተክርስቲያን ሰውን ራስ አድርጋ የመቀበልን ሃሳብ ወደደች። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን እንደ መሪ እና የቤተክርስቲያን ራስ አድርጋ የምታየው ጳጳስ ነበራት።

ከዚያ በኋላ የጳጳሱ ስልጣን ጨመረና በአንድ ከተማ ለሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ራስ ወደ መሆን አደገ።

በ606 ዓ.ም ፖፑ እራሱን ዓለም አቀፍ ጳጳስ ብሎ ሾመ። የጳጳሶች ሁሉ አለቃ ሆነ። ይህም ከዚያ ቀጥሎ በመጡት 900 ዓመታት ውስት ቤተክርስቲያን የወደቀችበትን የጨለማ ዘመን መምጣት አፋጠነ።

የጨለማው ዘመን የጀመረው በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ነው፤ በዚህ ጉባኤ ላይ እውነት ተጨፍልቃ በቤተክርስቲያኖች ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ የስላሴ ትምሕርት በግድ ተጫነባቸው (የጨለማው ዘመን ከጀመረ ከ1,200 ዓመታት ነው የተጠናቀቀው)። በ350 ዓ.ም መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀውን ክሪስማስ እና ዲሴምበር 25 ቀን ቤተክርስቲያን ተቀበለቻቸው። ተጨማሪ ስሕተቶች ተከትለው መጡ፤ የሚቃወሙ ሁሉ ተገደሉ። አስር ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች ተገድለው ሰማዕት ሆኑ። በስተመጨረሻ በ1520 ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ብቻ እንጂ በሥራ እንዳልሆነ የሚናገረውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ።

ፈላጭ ቆራጭነት በቤተክርስቲያን ውስጥ በዚህ መንገድ ነው የሚሰራው። አንድ ሰው ብቻ የቤተክርስቲያን ራስ ይሆናል፤ እርሱም የሚቃወሙትን ሰዎች ሁሉ ይገድላቸዋል። ዛሬስ እንደ ድሮው የሚቃወሙዋቸውን ሰዎች በአካል መግደል አይችሉም፤ ነገር ግን የቤተክርስቲያን መሪዎች የሚቃወሟቸውን ሰዎች ስም በማጥፋት ማንም አይተካከላቸውም። መንፈሱ አንድ ዓይነት ነው።

ሰዎች የቤተክርስቲያን ራስ ሲሆኑ የሚፈጠረው ክፋት ይህ ዓይነት ነው።

ችግሩን አስተውሉ። ለ1,800 ዓመታት በላይ ቤተክርስቲያንን በአንድ ግለሰብ ስልጣን ስር ማስተዳደር ተቀባይነት አግኝቶ ቆይቷል። ከተሃድሶው በፊት ይህ ግለሰብ ጳጳስ ተብሎ ይጠራ ነበር። አሁን ደግሞ ፓስተር ተብሎ ይጠራል። የቤተክርስቲያን አወቃቀር ለረጅም ዘመን የቆየ ከመሆኑ የተነሳ በሰዎች አእምሮ ውስጥ ትክክለኛ ተደርጎ ተወስዷል። ስለዚህ ከዚህ የተለየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ አወቃቀር መኖሩን ማሰብ እንኳ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የቤተክርስቲያን አወቃቀር ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ በማስቀመጥ ቤተክርስቲያን እንዳትለወጥ ያደርጋታል ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ራስ የተደረገው ሰው ስልጣኑን ወይም ገንዘቡን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም።

ሶስተኛው የጴርጋሞን የቤተክርስቲያን ዘመን አደገኛ ነበረ። በዚህ ዘመን ውስጥ ሰው ከፍ ብሎ የቤተክርስቲያን መሪ መሆኑን ቤተክርስቲያን አልጠላችም (ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም) ቀጥላ ደግሞ አሁንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን የስላሴ አስተምሕሮ ተቀበለች። ከዚያ በኋላ ማንም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቆ መከተል አቆመ።

አሁን ሰዎች ለብ ያሉ ሆነዋል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚመቻቸውን ክፍል ይቀበላሉ፤ ከቤተክርስቲያናቸው ሃሳብና እምነት ጋር አብሮ የማይሄደውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ቸል ይላሉ። ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች ልክ እንደ ሮማ ካቶሊኮች እና እንደ ሌሎች ብዙ ቤተክርስቲያኖች በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ያምናሉ። ከዚህ የባሰ ውድቀት የለም።

 

እግዚአብሔር እያንዳንዱ ግለሰብ እምነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምሮ በራሱ እንዲያረጋግጥ ይፈልጋል

 

በጳውሎስ ዘመን ቤርያ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን እያሉ ይመረምሩ እንደነበሩት እኛም በዚህ ዘመን መመርመር አለብን።

የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤

11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።

ይህንን በአግባቡ ለማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም እንከን የሌለበት ፍጹም ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማመን አለባችሁ።

62-0627 ኢየሱስን ልናይ እንፈልጋለን

አሁን በማቀርብላችሁ መልእክት የተቻለኝን ያህል ቀለል ላደርግላችሁ እፈልጋለው፤ ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማችሁት እንደመሆኑ መጠን … ሰዎች ወደዚህ ጉባኤ መጥተው ያውቁ ይሆናል። ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ ሊሆንባችሁ ይችላል። ከሆነባችሁም በትዕግስት አብራችሁኝ እንድትቆዩ እጠይቃችኋለው (አያችሁ?) ሁልጊዜ እኔ ስናገር የሰማችሁትን መርምሩ። የተናገርኩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ከሆነ አትመኑ

መጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ያልሆኑ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማገናኘት አይችሉም፤ ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ቸል ወደ ማለትና የሰው ንግግር ጥቅሶችን ወደ ማገጣጠም ፈቀቅ ብለዋል፤ አስተምሕሮዋቸውንም በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ማረጋገጥ አይችሉም።

ሙሽራይቱ፡- “መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን እንደተጻፈ ማወቅ አለብኝ” ትላለች።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ግን፡- “የሰው ንግግር ጥቅሶች ይዣለሁ እኮ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማወቅ የግድ ያስፈልገኛል እንዴ?”

የሙሽራይቱ አቋም “… ተብሎ ተጽፏል” የሚል ነው።

የሰነፎቹ ቆነጃጅት አቋም ደግሞ፡- “የሰው ንግግር ጥቅስ አለኝ” የሚል ነው።

ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆንን አያስፈልግም ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን አለመስማት እንደ ጤናማነት እስኪቆጠር ድረስ መጽሐፍ ቅዱሳዊነትን ይነቅፋሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተል ሰው እንግዳ ተደርጎ ይታያል።

1963-1201 ፍጹሙ

ለዚህ ነው በክርስትና ሕይወት ውስጥ ሊኖር የቻለው። የማቆምያ ቦታ አለ፤ ደግሞም የመሄጃ ቦታ አለ። የእግዚአብሔር ቃል ይህንን ያህል ፍጹም ነው

የፓስተር አገልግሎት እንደ እረኛ ሰዎችን መንከባከብ ነው፤ በግል ችግራቸው መድረስና መርዳት፤ የቤተሰብ ጉዳዮችን፣ ከሥራ ጋር የተያያዙ ችግሮችን መፍታት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ሕብረት መከታተል ነው። አስተምሕሮአዊ ችግሮችን መፍታት የፓስተሮች ጥሪ አይደለም።

ነገር ግን አንድ ግለሰብ ብቻውን የቤተክርስቲያን መሪ በሚሆንበት ጊዜ እጆቹን አስራቱ ላይ ማሳረፍ ይፈልጋል።

ሰባኪነትን ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሙያ እንደሆነ አድርገው ያዩታል።

በብዙ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪው ከሁሉ የተሻለ መኪና ይነዳል፤ ከሁሉ የተሻለ ቤት ውስጥ ይኖራል፤ ስለዚህ ሰባኪነትን ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ሙያ አድርጎ ይዞታል።

ስለዚህ በቤተክርስቲያን ላይ በሃላፊነት ይቀመጡና ከመረጡዋቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች ውስጥ የተለያዩ አስተምሕሮአዊ ጉዳዮችን ይፈጥራሉ። ከዚህም የተነሳ ነው የሜሴጅ ቡድኖች በተለያዩ እምነቶች እየተከፋፈሉ ቁጥራቸው እየበዛ የሄደው፤ ከእነርሱ ግን አንዳቸውም እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አይችሉም።

ቤተክርስቲያኖች በአንድ ሰው ወይም በአንዲት ሴት ወደ መመራት ከመውደቃቸው ጋር ተያይዞ በቀይ ፈረስ የተመሰለው ፖለቲካዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰተት ብሎ ገብቷል። እንዲህ ዓይነት መሪዎች ከሕዝቡ ይልቅ ስልጣንን ስለሚወዱ ሰዎችን እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን ማመን እንዳለባቸው በራሳቸው ፈቃድ ይመሯቸዋል። በሰው ላይ የያዙት ይህ ስልጣን ከሐይማኖታዊ አሳችነት ጋር በአንድነት የሚሰራ ኃይል ሆኗል። ሰዎች ስሕተትን እንዲያምኑ በማድረግ ስሕተቱን የፈጠረውን መሪያቸውን እንዲፈሩትና እርሱን እንዳይቃወሙት ያደርጋሉ፤ ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመሆን ፍላጎታቸው ይጠፋል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን ብዙም አስፈላጊ አይደለም ብለው ሲያምኑ ፕሮፓጋንዳዎች በቀላሉ ይስፋፋሉ። ሐይማኖታዊ ሽንገላ ልክ እንደ ቫይረስ ዓይነት ጠባይ አለው፤ በቀላሉ ይሰራጫል።

የቤተክርስቲያን መሪ ሁልጊዜ እንዲህ ይላል፤- “አዲስ ሃሳብ እንድታስቡ እፈልጋለው፤ ነገር ግን ከእኔ ሃሳብ የተለየ ሃሳብ እንድታስቡ አልፈልግም”።

ይህ አደገኛ ስሕተት ነው ምክንያቱም ማንም ሰው ያችን ቤተክርስቲያን ሊያርማት አይችልም።

የቤተክርስቲያን መሪ መፈክር፡- “እያንዳንዱ ሰው የእኔን አመለካከት የመቀበል መብት አለው” የሚል ነው።

የዘመናችን ሰባኪዎች ደሞዝ ተከፍሏቸው ነው የሚሰብኩት፤ ስለዚህ ሰባኪነት ሥራ ላጡ ሰዎች ጥሩ የስራ አማራጭ ሆኖላቸዋል። ተቀባይነት አግኝተው ለመኖር የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን መካድ አለባቸው።

ፓስተርነትን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ ጥሩ የንግድ እቅድ ሆኗል።

 

የምናየው ማየት የምንመኘውን ነው፤ የአመለካከታችንን ተጽእኖ ማምለጥ አንችልም

 

ሰዎች በአዲስ መረጃዎች ላይ ተመርኩዘው መረዳታቸውን ለማስተካከል ዝግጁ አይደሉም። እኛ ሰዎች ከተፈጥሮዋችን የራሳችንን ድክመቶችና ስሕተቶች ለማረም ፈቃደኞች አይደለንም። የሌሎችን ሰዎች ስሕተት አጥርተን እናያለን፤ የራሳችን ስሕተት ግን አይታየንም። ይህም የማስተዋል ችሎታችንን ያደነዝዘዋል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች በታላቅ ክብር ተከብረው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው ስለዚህ በመሪነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ለማንቀላፋት ተፈቅዶላቸዋል።

63-0707

የፈለጋችሁትን ብታምኑ ግድ የለኝም፤ እኔ የምከተለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ነው።

63-0707

በማን እጅ ነው እርሱ የተሰቀለው? በፓስተሮች እጅ። እናንተ ግብዞች።

ከዚያ በጥቁር ፈረስ የተመሰለው የገንዘብ ኃይል በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እየጋለበ ያልፋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ከተናገረው ቃል ውጭ ፓስተሩ የአስራት ገንዘብ በሙሉ የእኔ ነው ይላል።

ስለዚህ ገቢያቸው የሚጠበቀው የቤተክርስቲያን ራስ ሆነው በመቀመጣቸው ነው። ስለዚህ ይህን ስልጣናቸውን አይለቁትም።

ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት ኢየሱስ በሆሳዕና ዕለት የሐይማኖት ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደስ ውስጥ እየገረፈ አስወጣቸው፤ ከዚያም በቀጣዩ ሰኞ እንደገና አስወጣቸው፤ ይህንም በማድረጉ ካሕናቱ፣ ሊቀ ካሕናቱ፣ እና ሰዱቃውያኑ የገቢ ምንጫቸው ላይ ስጋት መጣባቸው።

የሐይማኖት መሪዎችን ግብዞች፣ ሰነፎች፣ ዕውር መሪዎች፣ ንጹሕ የምትመስሉ መቃብሮች፣ የእፉኝት ልጆች፣ እና ወደ መጨረሻችሁም ገሃነም ነው ብሏቸዋል።

ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩ የሐይማኖት መሪዎችን እንዲህ ነው ያላቸው። በ2020 የሚኖሩ የሐይማኖት መሪዎችንስ ምንድነው የሚላቸው?

ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎችን በገሰጻቸው ጊዜ ምንም አላደረጉትም፤ ነገር ግን በነዚያ ሁለት ቀናት ገንዘብ ለዋጮችን በማባረር የገቢ ምንጫቸውን ስጋት ላይ በጣለባቸው ጊዜ አሁንስ በዛ አሉ።

ሐሙስ ዕለት ገደሉት።

የቤተክርስቲያን መሪን በገንዘቡ አትምጣበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ አስራት የፓስተሩ ነው ብሎ ባይናገርም አስራቱ በሙሉ እንዴት ያንተ ይሆናል ብለህ አትገዳደረው።

ገንዘቡን ካጣ ደጋፊዎችን በምን ሊከፍላቸው ነው እንዴትስ አድርጎ የራሱ ደጋፊ አድርጎ ያቆያቸዋል? ይህ የአምባገነኖች ሁሉ የተለመደ ታክቲካቸው ነው።

አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚልበት ዋነኛው ምክንያት የቤተክርስቲያኒቱን የአስራት ገንዘብ የራሱ ለማድረግ ነው። ይህንም የሚያደርገው መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው እንደማይል እያወቀ ነው።

በተጨማሪ ደግሞ የአስራቱን ገንዘብ መቆጣጠሩ እርሱን የሚቃወሙ ሌሎች አገልግሎቶችን ሁሉ ለማፈን ኃይል ይሰጠዋል። በዚህም መንገድ የማይፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች ሁሉ ከቤተክርስቲያን ያስወግዳቸዋል።

በፖለቲካዊ ፓርላማ ውስጥ ብቻ ነው መንግስት ተቃዋሚዎችን እንዲቃወሙት ብሎ የሚከፍላቸው።

ይህ ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ማንኛውም ተቃውሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ አይሰጠውም። ይህም የአምባ ገነኖች ባህርይ ነው።

ስለዚህ አምባ ገነንነት በቤተክርስቲያን ውስጥ አለ፤ ፖፑ አውሮፓ ውስጥ በይፋ እውቅና ያገኘ ብቸኛ አምባ ገነን ነው። ፕሮቴስታንት ልጆችም የእናታቸውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አርአያነት ይከተላሉ።

በጥቁር ፈረስ የተመሰለው የገንዘብ ኃይል በሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሁሉ በሕይወት እየኖረ ይገዛል።

 

የአጋንንት ሥራ ዋና ዓላማው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር እንድናምን ማድረግ ነው

 

የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን

እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንደተጻፈችዋ ቤተክርስቲያን ለመሆን ትሞክራለች ብያለው። ይህም ትክክል ነው። ደግሞም ቃሉ በመጨረሻው ቀን ጌታ ሊገለጥ ሲል እውነት ሙሉ በሙሉ ተደምስሳ እስክትጠፋ ድረስ የስሕተት ወረራ በቤተክርስቲያን ላይ እንደሚመጣ እንደሚናገር አይተናል።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመከተል ቢጸኑ ስሕተት ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባት አይችልም ነበር።

ነገር ግን የቤተክርስቲያን መዋቅር የተሳሳተ መዋቅር ከሆነ ስሕተት ቀድሞ ገብቷል ማለት ነው።

አንድ ግለሰብ ብቻውን መሪ ሲሆን የማይቀር ስሕተት ይህ ነው።

እንደ ስላሴ፣ የስቅለት አርብ፣ ክሪስማስ፣ ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ነው፣ ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው እና የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገሮች ሰዎችን ስለሚያስደንቁዋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመሆን ፍላጎታቸውን ይሰርቁባቸዋል

63-0707 ክሱ

ምንም ብታምኑ ግድ የለኝም፤ እኔ የማምነው መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ነው።

61-1119 ፍጹም ብርታት በፍጹም ድካም

ኦህ የማንቆርቆሪያ ክዳን ሲከፈት አስቡ፤ አጋንንት ወጥተው ሲፈነጩ፤ በክርስትና ስም የሰይጣን ኃይላት የሰውን ትዕዛዝ የእግዚአብሔር ቃል ብለው ሲያስተምሩ፤ የስነ መለኮት ሴሚናሪዎች አስተምሕሮ፤ መጽሐፍ ቅዱስን የማይከተሉ ሁሉ

62-0727 ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ፍጹም እውነት እንደሆነ አምናለው።

ይህ ግልጽ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

54-0217 ኢየሱስ ስለ ቃሉ ስልጣን

አሁን ለጥቂት ደቂቃዎች ስለ “እግዚአብሔር ቃል ስልጣን” እንናገራለን። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቃል ተጽፏል፤ መሃላ የተደረገበት ስልጣን ነው።

ይህም የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ አማኙ ምንም እንከን የሌለው ፍጹም ትክክል የሆነ ቃል አድርጎ የመቀበል ሙሉ መብት አለው።

61-0108 ራዕይ ምእራፍ አራት - 3

“በጎቼ ድምጼን ያውቃሉ።” የእግዚአብሔር ድምጽ ቃሉ ነው

60-0804 ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ

መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆኑን እናውቃለን፤ ይህም የሚናገረው የእኔ ድምጽ አይደለም፣ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው

በዘመናችን ቀይ፣ ነጭ፣ እና ጥቁር ፈረስ አንድ ሲሆኑ ታላቁ መከራ ሊጀምር መድረኩ እየተዘጋጀ ነው። በቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውስጥ እንደ ደራሽ ውሃ እየተሰራጩ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ልናስቆማቸው አንችልም።

ቤተክርስቲያኖች የተናገሩትን ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ነው ማመን ያለብን።

 

አሁን በሆንንበት ጸንተን የምንቀር ከሆነ መሆን የምንፈልገውን መሆን አንችልም

 

አምባ ገነናዊ የሰው አገዛዝን ለማምለጥ ጥሩ ሃሳብ በቤት ውስጥ ቤተክርስቲያን ሆነው ወደሚሰበሰቡበት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመን መመለስ ነው።

የቤተክርስቲያን ራስ ከተባለ ሰው ስር ሆኖ መመራት የጥንቷ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳናዊ ሃሳብ አይደለም።

ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማብራራት የማይችሉት ክፍል አለ ምክንያቱም ትኩረታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን የሰው ንግግር ጥቅስ ላይ ነው። ሃሳባችሁን የሚቃረንን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ቸል ብሎ ማሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ረግጦ እንደመሄድ ነው። ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ማብራራት አለመቻል መጽሐፍ ቅዱስን የማይታወቅ ትርጉም የሌለው ምድረበዳ ያደርግብናል። ነገር ግን ማንም አያስተውልም። በቤተክርስቲያን ውስጥ እስከሆናችሁና መሪያችሁን እስካመናችሁ ድረስ መዳናችሁ እርግጥ ነው ብለው ያስባሉ። በተለያዩ የቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል ያለውን የአስተምሕሮ ልዩነት እንዳላዩ አስመስለው ዝም ይላሉ።

11 ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።

ኤርምያስ 12፡12 በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥

“በዝባዦች” ጥቅሶችን ተጠቅመው መጽሐፍ ቅዱስን በማብራራት ፈንታ ጥቅሶችን አጣመው ይተረጉማሉ።

በዝባዦች የቤተክርስቲያን አለቃ ለመሆን ብለው ከፍተኛውን ቦታ ይፈልጋሉ።

ከዚያ በኋላ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መረዳት እስኪያቅታቸው ድረስ በሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ ያተኩራሉ። ግልጽ ያልሆኑና ሰዎች ያልገቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሰዎች ባዶነት እንዲሰማቸው ያደርገሉ። ማናችንም ብንሆን መረዳት ካልቻልነው ነገር ልንማር አንችልም

የሜሴጅ ተከታዮች ከጊዜ ወደጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ እየሆኑ ናቸው ምክንያቱም ሰባኪዎቻቸው ራሳቸው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መረዳት አልቻሉም፤ ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምንም ትኩረት አያደርጉም።

 

የጥንቷ ቤተክርስቲያን መሰብሰቢያዋ በቤት ውስጥ ነበር

 

ሳውል ክርስቲያኖችን ወደ ወኅኒ ቤት ሊያስገባ ሲፈልግ በቤት ውስጥ ባሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ነው ያገኛቸው።

የሐዋርያት ሥራ 8፡3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ቤተክርስቲያን ተብሎ የሚታወቀው ግለሰቦች በቤት ውስጥ ሲሰባሰቡ ነው።

ሮሜ 16፡3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤

5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

በሎዶቅያ ከተማ ይኖሩ የነበሩ ወንድሞች የሚሰባሰቡት በቤቶች ውስጥ ነው።

ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።

ይህ ትልቅ ትርጉም አለው። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሎዶቅያ የቤት ውስጥ ቤተክርስቲያን ተብላ ተጠቅሳለች።

ጳውሎስ ለሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ምን መናገር ፈልጎ ነው።

ጳውሎስ ለፊሊሞና እንዲህ ብሎ ጻፈለት፡-

ፊሊሞና 1፡2 ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን

በቤት ውስጥ የሚሰባሰቡበት አንዱ ምክንያት የሮማ ገዥዎች ያሳድዷቸው ስለነበረ ነው፤ ይህም ስደት የቆመው በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ በ312 ዓ.ም ነው። አንድ የታሪክ ምሑር እንደተናገረው እስከዚያ ባላፉት ዓመታት ውስጥ 3 ሚሊዮን የሚያህሉ ክርስቲያኖች ተገድለዋል። በተጨማሪ ስደት ክርስቲያኖች ትልቅ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዳይሰሩና እንዲበታተኑ አድርጓቸዋል።

ሆኖም ራዕይ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ ስለነዚህ ትንንሽ ሕብረቶች መልካም ምስክርነት ነው የተጻፈላቸው።

በመጨረሻው የሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ትልልቆቹ ቤተክርስቲያኖቻችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ውግዘት ብቻ ነው የመጣላቸው።

ዛሬ ተራርቀው የሚኖሩ ጥቂት ሰዎች የZOOM ቴክኖሎጂ በመጠቀም መሰባሰብ ይችላሉ። ከዚህም የተነሳ ከትላልቅ ቤተክርስቲያን መሪዎች ስሕተት ተጽእኖ ነጻ መሆን ይችላሉ።

የZOOM ስብሰባዎችን በተመለከተ ግለሰቦች በኢንተርኔት churchages.net ብለው በመግባት ማነጋገር ይችላሉ።

ተራርቀው የሚኖሩ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች የራሳቸውን ZOOM ስብሰባ ማዘጋጀት ይችላሉ።

ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና

እግዚአብሔር በሎዶቅያ ስላሉት ትልልቅ ሕብረቶች ይህንን አልተናገረም።

በሎዶቅያ እግዚአብሔር ለግለሰብ ነው ጥሪ የሚያቀርበው እንጂ ለቤተክርስቲያን አይደለም።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ

በውስጣችን የሚወቅሰን የእግዚአብሔር ድምጽ ቃሉ ነው

ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ሊገልጥ ነው የመጣው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

64፡0614 ብቸኛው ኳስ

መልአኩ የነገረኝ ይህ ነው፡- “ሰዎች እንዲያምኑህ አድርግ።”

እኔም ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ብናገር “እኔን እመኑኝ” አይደለም የምለው፤ “እግዚአብሔርን እመኑ” ነው የምለው

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ አማካኝነት በግልጽ ሲጠራቸው መስማት ይችላሉ

መጽሐፍ ቅዱን አድምጡ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የሚጠራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው

ኢየሱስ ከትልልቆቹ ሕብረት ቤተክርስቲያኖች በር ውጭ ቆሟል። ከቤተክርስቲያን ውስጥ የወሰኑ ግለሰቦች እንዲወጡ ጥሪ ያቀርባል እንጂ ሕብረቱን በሙሉ አይጠራም።

ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

ይህ ኃይል እና የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን የተሞላ መልአክ ነው። አገላለጹ ልክ የወንድም ብራንሐምን አገልግሎት ይመስላል።

ራዕይ 18፡2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤

የሰባተኛው መልአክ ድምጽ በዘመኑ የነበሩትን ሐይማኖታዊ ድርጅቶች አውግዟል። በ1965 ከምድር ከተለየ ወዲህ አንድ ግለሰብ ጉባኤዎችን በራሱ አመለካከትና ከሰው ንግግር በተወሰዱ ጥቅሶች ትርጓሜ የሚገዛበት ዲኖሚኔሽናዊ አሰራር ወደ ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልኮ ገብቷል።

ስለዚህ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ለሚፈልጉ ግለሰቦች መናገር ሲፈልግ እግዚአብሔር ከሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውጡ ይላቸዋል።

“እኔ የሜሴጅ አባል ነኝ” ብሎ መናገር “እኔ ቫቲካን ነኝ” የማለትን ያህል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ አባባል ነው። እነዚህ ሰዎች ግን ከሌሎቻችን ይልቅ ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ ይመስላቸዋል።

“እኔ የሜሴጅ አማኝ ነኝ” ማለት “እኔ የካቶሊክ አማኝ ነኝ” የማለትን ያህል መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አነጋገር ነው።

“እኔ ብራንሐማዊ ነኝ” ማለት “እኔ ሉተራን ነኝ” የማለትን ያህል መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አነጋገር ነው።

“ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም” ማለት “ፖፑ አይሳሳትም” የማለትን ያህል መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አነጋገር ነው።

የሜሴጅ ሰዎች ከራሳቸው የጀመሩት ምንም ነገር የላቸውም፤ የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ስርዓቶችን እየኮረጁ አንዳንድ ቃላትን በመለወጥ ብቻ ነው የሚጠቀሙት።

የአዲስ ኪዳንን ጥንታዊት ቤተክርስቲያን መኮረጅ ነበረባቸው።

 

ሌላ ድምጽ “ሕዝቤ ሆይ ከመካከሏ ተለይታችሁ ውጡ” አለ

 

ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ

“ሌላ ድምጽ”።

ውስጣዊው የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ። ይህ ድምጽ ከቤተክርስቲያን እንድንወጣ ይናገረናል፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን ገፍታ ያስወጣቻቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ክርስቶስን ማግኘትና መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚችሉት።

የሜሴጅ ተከታዮች አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ ወደ ሜሴጅ ቤተክርስቲያን መሄድ አለበት ብለው ያምናሉ።

65-0220

ወደዚያ እነርሱ ወደሚሉት ቤተክርስቲያን ካልሄዳችሁ መንግስተ ሰማያት የማትገቡ ይመስላቸዋል። ይህ ስሕተት ነው። እንደዚህ ብሎ ማመን የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆን ነው። እኔም እንዲህ እላለው፡- እንዲህ ዓይነቱን መንፈስ ካመናችሁ ጠፍታችኋል።

መቅሰፍቶች እየመጡ ናቸው። በ2020 የመጣው የኮቪድ-19 ቫይረስ ማስጠንቀቂያ ነው።

አብዛኛዎቹ ሐዋርያት ከ70 ዓ.ም በፊት ከኢየሩሳሌም ወጥተው ሄደዋል። በሮማዊው ገዥ በዶሚሺያን ዘመን ሐዋርያው ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ላይ በእስር ቤት ውስጥ ነበረ። ከዚያም ከእስር ቤት የተለቀቀው በ96 ዓ.ም ዶሚሺያን ሲሞት ነው።

ከ70 ዓ.ም እስከ 120 ዓ.ም ድረስ ምንም ያልተጻፋቸው የዝምታ ዓመታት ነበሩ። በነዚያ የዝምታ ዓመታት ውስጥ በሆነ መንገድ ሰዎች ባላስተዋሉበት ሁኔታ ጳጳስ መጽሐፍ ቅዱስ እውቅና ባልሰጠው መንገድ ቀስ በቀስ የቤተክርስቲያን ራስ ወደ መሆን ስልጣን ወጣ።

የታሪክ ምሑሩ ፍራንሲስ ሱሊቫን እንደጻፈው እስከ 150 ዓ.ም ድረስ አንድም የሮም ጳጳስ የሚባል ሰው አልነበረም።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም የተጠናቀቀው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው ጳጳሶች እንደ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ ተደርገው መቆጠር የጀመሩት። በዚህም መንገድ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን የሐዋርያት አሰራር ማለትም አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት የምትመራበትን አሰራር ወደጎን ትታ ሄደች።

የጥንት ቤተክርስቲያኖች በሰው ቤት ውስጥ መሰብሰብ የሚችሉ ትንንሽ ሕብረቶች ነበሩ።

62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን

ታውቁ እንደሆን እነዚያ የጥንት ሰዎች ሲወጡ አንዳንዴ ለስድስት ወይም ለስምንት ብቻ ሆነው ነበር የሚወጡት። እንደዚያ ጥቂት ሆነው ግን ዓለምን አናወጡ። እንደምታውቁት አቂላ እና ጵርስቅላ አጵሎስ አብሯቸው በተገኘበት በዚያ ታላቅ መነቃቃት ውስጥ ስድስት ወይም ስምንት ወንዶችና ሴቶች ብቻ ነበሩ የተገኙት። ያ ቤተክርስቲያን በሙሉ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ። ዛሬ በዚህ ጉባኤ ውስጥ በዚያ ዘመን ይሰባሰቡ ከነበሩት ሰዎች አምስት ወይም ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ ሰዎች አሉ።

1ኛ ቆሮንቶስ 16፡19 የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ከ222-235 ዓ.ም በፊት የተሰራ የቤተክርስቲያን ሕንጻ በተመለከተ ምንም መረጃ የለንም።

ይህም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም ከተጠናቀቀ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።

ስለዚህ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የቤተክርስቲያን ሕንጻ አልነበራቸውም፤ የሚሰባሰቡት በሰዎች ቤት ውስጥ ነበረ።

ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው

ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።

 

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በ2020 ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ አዘግቶ ሰዎች በቤታቸው ተዘግተው እንዲቀመጡ አስገደደ።

በዚህ ውስጥ እግዚአብሔር ሊነግረን ያሰበው ነገር ይኖር ይሆን?

በመጀመሪያው ፍልሰት ውስጥ አይሁዶች ከግብጽ በወጡ ጊዜ የመጀመሪያውን ሌሊት አይሁዶች ሁሉ በቤታቸው ተዘግተው ተቀምጠው ነበር። በቀጣዩ ቀን እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ሊያለማምዳቸው ወደ ምድረ በዳ ይዟቸው ወጣ።

በሁለተኛው ፍልሰት ክርስቲያኖች ከአይሁዶች መካከል ተለይተው ሲወጡ ከኢየሱስ እርገት ጀምሮ በበዓለ ሃምሳ ቀን እስከ መንፈስ ቅዱስ መውረድ ድረስ ለ10 ቀን በአንድ ቤት ተዘግተው ቆይተዋል። ከዚያ ወዲያ ቤተክርስቲያን አይሁዶች ከኖሩበት የኑሮ ዘይቤ ፍጹም በተለየ ሕይወት መኖር ጀመረች።

እኛ አሁን በሶስተኛው ፍልሰት ውስጥ ነን፤ በዚህም የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ግለሰቦች ከቤተክርስቲያን ይወጣሉ። በኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት በ2020 ለረጅም ጊዜ ተዘግተን ተቀምጠናል። እኛም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ከተደረገው ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ እግዚአብሔርን የምናገለግልበት አዲስ መንገድ መፈለግ አለብን።

በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በሽማግሌዎች መሪነት መሰብሰባቸው ሐዋርያት ወደመሰረቷት የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን የሚያስጠጋ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢንተርኔት ZOOM ስብሰባ ቴክኖሎጂ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተሻሽሎ በመምጣቱ በየቤት ሆኖ ከወገኖች ጋር መሰብሰብ ቀላል ሆኗል። የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደው በመመርመር የሚያረጋግጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርቶች አሁን በኢንተርኔት መሰራጨት ችለዋል።

ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚገልጹ ሰባት የመንግስተ ሰማያት ምሳሌዎች አሉ።

ሰባተኛው ምሳሌ ባሕር ውስጥ ተጎትቶ የሚወጣ መረብን ይገልጻል። እግዚአብሔር ኢንተርኔትን የመረጃ መረብን መጠቀሙ በዓለም ዙርያ እንደ ባሕር እረፍት በሌላቸው ሕዝቦች መካከል የተበታተኑ ግለሰቦችን ለመድረስ አስቦ ነው፤ በኢንተርኔት አማካኝነት እነዚህ ሰዎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተስበው ይመጣሉ።

ማቴዎስ 13፡47 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

48 በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።

ዕድሜ ለኢንተርኔት፤ አሁን ታላላቅና የተከበሩ ቤተክርስቲያኖች ከቁምነገር በማይቆጠሩበት ዘመን እውነት በኢንተርኔት በዓለም ዙርያ ሁሉ መድረስ ትችላለች።

 

ኤርምያስ እንዲህ አለ፡- “ለእረኞች (ፓስተሮች) ወዮላቸው”

 

አስተማሪዎች የነብዩን የዊልያም ብራንሐም መገለጦች መልሰው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመውሰድ እውነትን ማረጋገጥ ነው ሃላፊነታቸው፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔር የሰጣቸው ቦታ ይህ ነው።

ፓስተሮች የእነርሱን ሃሳብ የማይቀበሉ ብዙ ሰዎችን ከቤተከርስቲያን አባርረዋል። እነዚህ የተባረሩ ሰዎች አሁን በኢንተርኔት አማካኝነት ሕብረት ማድረግ ይችላሉ።

 

ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ሰዎች ራሱን የቤተክርስቲያን ራስ ካደረገው ፓስተር ጋር አልስማማም ካሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈልጋቸው ስለሌለ ይበተናሉ።

“አባርራችኋቸውማል” አልስማማም ካሉ። ሰባኪዎች ለእነርሱ በማያጎበድዱ ሰዎች ላይ ሊጨክኑባቸው ይችላሉ።

ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን ልትታረም አትችልም።

ኤርምያስ 2፡8 … ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥

ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።

ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥

ኤርምያስ በፓስተሮች ምንም አልተደነቀም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ለተጠቀሰ አገልግሎት ይህ በጣም ብዙ ውግዘት ነው።

ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ባልፈቀደላቸው መንገድ የቤተክርስቲያን ራስነትን ነጥቀው ስለያዙ ቤተክርስቲያንን በተሳሳተ መንገድ መምራታቸው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ለነገሩ ከመጀመሪያውም መጽሐፍ ቅዱስ በእንዲህ ዓይነቱ ሃላፊነት ቦታ አላስቀመጣቸውም።

 

ሞት እንደ ፈረሰኛ እየጋለበ መጣ

 

ከዚህም የተነሳ ቀጣዩ ነገር ምዕራፍ 6 ቁጥር 8 ላይ የሚጀምረው ታላቁ መከራ መሆኑ ምንም አያስደንቅም።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

 

 

በራዕይ 6፡8 እንደተጻፈው ታላቁ መከራ የሚጀምረው ሕይወት የሆነው መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ለመንጠቅ ምድር ትቶ ሲሄድ ሞት በፈረስ እየጋለበ ሲገባ ነው።

ሞት እየጋለበ ሲገባ ማለት ወንጌል ወደ አይሁዶች ሲሄድ ማለት ነው።

እነርሱ መሲሁን ገድለዋል፤ ስለዚህ በተራቸው ደግሞ መሲሁ ሲመጣ እነርሱ ይገደላሉ። ደም በደም ይከፈላል።

በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ አይሁዶች በሌሎች ሕዝቦች ጥላቻ በግፍ ተገድለዋል። በዚህም ስለፈሰሱት የመሲሁ ደም ሲከፍሉ ቆይተዋል።

ራዕይ 6፡9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።

እነዚህ አይሁድ በመሆናቸው ብቻ የተገደሉ አይሁዶች ናቸው። ባለፉት የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በአይሁዶች ላይ የተሰነዘረ ጥላቻ ይህን ያህል ብርቱ ነበረ።

ሮማዊው ጀነራል ታይተስ ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን ካፈራረሰ በኋላ 1,100,000 አይሁዶችን ገድሏል።

ይህ በአረማዊው በሮማ መንግስት ታሪክ ውስጥ በጭካኔ እና በግፍ ወደር የሌለው ጭፍጨፋ ነው። አረማውያኑ ሮማውያን ለእግዚአብሔር ሕዝብ ለአይሁድ በውስጣቸው ስር የሰደደ ጥላቻ ነበራቸው።

በ132 እና 135 ዓ.ም መካከል ሃድሪያን የተባለው ሮማዊ ገዥ 580,000 አይሁዶችን ገድሎ በሕይወት የቀሩት አይሁዶች እስራኤል ውስጥ እንዳይኖሩ በበየሃገሩ እየሰደደ በታተናቸው።

ከ1939 – 1945 በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ክፉ የሆነው አምባገነን መሪ ሒትለር እነዚያኑ የጥላቻ አጋንንት ጀርመኒ ውስጥ በመልቀቅ 6 ሚሊዮን አይሁዶችን ሆሎኮስት በተባለው ጭፍጨፋ ገደለ። በ1800ዎቹ ዓመታት ውስጥ በብዙ ሃገሮች ውስጥ በተደጋጋሚ አይሁዶችን ዘርፈዋቸዋል፤ ገድለዋቸዋል፤ ከሃገራቸውም አባርረዋቸዋል። እነዚህ አይሁዶች የተገደሉት ቤተመቅደስ እና መስዋእት ሳይኖራቸው የብሉይ ኪዳን እምነታቸውን በተቻላቸው መጠን በታማኝነት አጥብቀው በመከተላቸው ነው።

ራዕይ 6፡10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።

ዓይን ለዓይን፣ ጥርስ ለጥርስ የሚለው የብሉይ ኪዳን ሕግ ነው። የተገደሉት አይሁዶች በቀል ይፈልጋሉ።

ዘጸአት 21፡24 ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥

ክርስቲያኖች ግን እንደ ኢየሱስ እና እንደ እስጢፋኖስ የሚገድሏቸውን ሰዎች እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው እየጸለዩ ይሞታሉ።

ክርስቲያኖች ለበቀል አይጸልዩም።

ይህ ማሕተም ሲፈታ ከዙፋኑ ዙርያ የተጠቀሰ አንድም እንስሳ የለም።

ስለዚህ የቤተክርስቲያን ዘመናት አልቀዋል፤ ሙሽራይቱም ወደ ሰማይ ተነጥቃለች ማለት ነው።

አይሁዶችም በታላቁ መከራ ዘመን ወደ ምድር መውረድ ይፈልጋሉ፤ የታላቁ መከራ ዘመን የሚጀምረው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው። ይህ ዘመን እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር የቀረውን ጉዳይ የሚፈጽምበት ነው።

ራዕይ 6፡11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።

 

 

አይሁድ በመሆናቸው ብቻ ስለተገደሉ እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወት እንደሚሰጣቸው ታውጇል። ነገር ግን 3½ ዓመት የሚፈጀውን አጭር የመከራ ጊዜ ታግሰው ማሳለፍ አለባቸው። ያም ኢየሱስን እንደ መሲህ የሚቀበሉት 144,000 አይሁዶች በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ መገደል ስላለባቸው ነው።

ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ኢየሱስ የክርስቶስ ተቃዋሚ አውሬውን ፖፕ እና ነፍሰ ገዳይ ሰራዊቶቹን ለመደምሰስ በአርማጌዶን ጦርነት ላይ ሊዋጋ ይወርዳል።

 

ለእስራኤል የተላኩት ሁለቱ ነብያት ብቻ ናቸው 6ኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት

 

ስድስተኛው ማሕተም ሲፈታ የታላቁ መከራ አሰቃቂ መቅሰፍቶች ሁሉ ተፈተው ይለቀቃሉ።

ወደ ሰማይ ተነጥቃ የሄደችዋ ሙሽራ ብቻ ናት ከዚህ ሁሉ ሰቆቃ እና መከራ የምታመልጠው፤ እርሷም ይህን ሁሉ መከራ አምልጣ ጌታን በአየር ላይ ትቀበለዋለች።

ራዕይ 6፡12 ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥

ታላቁ መከራ ሊጀምር የሚችለው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ በመነጠቋ ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ምድርን ትቶ ሲሄድ ብቻ ነው።

ታላቅ የምድር መናወጥ። መኖር የምንችለው ምድር ሳትናወጥ ጸንታ ስትቆም ነው። ምድር ስትንቀጠቀጥ በሰላምና በእርጋት የመኖር ተስፋችን አብሮ ይጠፋል። ከዚያ በኋላ የምንታመንበት ነገር አይኖረንም።

ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ በተነጠቀች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ምድርን ትቶ ሲሄድ ከዚያ ወዲያ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው መረዳት አይችሉም። በአእምሮዋችን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ሊገልጥልን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ከንጥቀት በኋላ መንፈስ ቅዱስ በሌለበት ምድር ላይ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ብቻቸውን ይቀራሉ። ከዚያ ወዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ለልባቸው ሊናገራቸው አይችልም። ከዚያ ወዲያ መንፈሳዊ ምሪት አይኖራቸውም። ጊዜ ልክ ፀሃይ እንደምትጨልምበት ጊዜ ይሆናል። ጨረቃ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ጨረቃ ወደ ደም መለወጧ ሰነፎቹ ቆነጃጅት እንዲሞቱ ይፈረድባቸዋል ማለት ነው። የወንድም ብራንሐምን መገለጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው በማረጋገጥ እግዚአብሔር ሊያሳየቸውን የፈለገውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ንቀዋል፤ ለመቀበልም እሺ አላሉም። ለዚህም ስሕተታቸው በራሳቸው ደም ዋጋ ይከፍላሉ። ነገር ግን ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት አስቀድመው ድነው ከነበረ ከፍርድ ቀን በኋላ በመንግስተ ሰማያት ውስጥ ይኖራሉ፤ ሆኖም ግን ከታላቂቱ ከተማ ከአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ውጭ ይሆናሉ።

መንግስተ ሰማያት መግባት መቻላቸው መልካም ነው፤ ነገር ግን በሰው መጠላትን ታግሰው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በፍቅር ተቀብለው የሙሽራይቱ አካል ለመሆን የበቁትና በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከተማ ለዘላለም የሚኖሩትን ያህል ደስተኞች አይሆኑም። ሙሽራይቱ ሁልጊዜ ለኢየሱስ ቅርብ ሆና ትኖራለች።

 

የመጀመሪያዎቹ 5 ማሕተሞች የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከሄደችና በኋላ ታላቁ መከራ በምድር ላይ በሚሆንበት ጊዜ ነው።

ስለዚህ ማሕተሞች በእውን የሚፈቱት ታላቁ መከራ በምድር ላይ ሲጀምር ነው።

የሙሽራይቱ አካላት የማሕተሞቹን መፈታት የሚያዩት በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ሆነው ነው።

ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሱት ስድስቱ ማሕተሞች የሚፈቱት ከንጥቀት በኋላ ሙሽራይቱ በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ከቆመች በኋላ ነው።

ስድስተኛው ማሕተም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ በሁለቱ ነብያት ነው የሚፈታው።

ስድስተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ነው፤ ከተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎች እንዲከሰቱ የማድረግ በቂ ኃይል ያላቸው ሁለቱ ነብያት ብቻ ናቸው፤ ለምሳሌ ሙሴ በግብጽ ፈርኦን ላይ እንዳመጣቸው መቅሰፍቶች ዓይነት።

63-0323

ይኸው። አያችሁ? በምድር ላይ በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ማሕተሞቹ ተፈተው ሰማዕታትን እንዴት እንደገለጡ አያችሁ? አሁን ተመልከቱ እነዚህን ሁለት ነብያት፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሆነው በመቆም በፍጥረት ላይ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፤ ምድርንም ያናውጣሉ። እነዚህንም ነገሮች የሚያደርጋቸው ማን እንደሆነ ያስታውቃል። ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው፤ ምክንያቱም የእነርሱ አገልግሎት ነው በድጋሚ በምድር ላይ የሚገለጠው፤ የሁለቱም። ገባችሁ አሁን? ስድስተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ገባችሁ? እነዚያ ነብያት ናቸው።

አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምን61ኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ።

ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም አልፈታም፤ ምክንያቱም ስድስተኛውን ማሕተም የሚፈቱት ሁለቱ ነብያት ናቸው።

የታላቁን መከራ ዝርዝር መረዳት የሚችሉት እነዚያ ሁለት ነብያት ብቻ ናቸው።

ወንድም ብራንሐም የስድስተኛውን ማሕተም ትርጉም ገልጧል፤ ማለትም ታላቁን መከራ የሚመለከት መሆኑን ተናግሯል።

ነገር ግን ስለ ታላቁ መከራ ዋና ዋና ነገር ብቻ ነው ሊነግረን የቻለው። ሰባቱን መለከቶችና ሰባቱን ጽዋዎች የመሳሰሉ ሚስጥራት ከእርሱ ተሰውረዋል።

 

ወንድም ብራንሐም ስድስቱን ማሕተሞች ገለጣቸው እንጂ አልፈታቸውም

 

የአንድ ማሕተም የመፈታት መገለጥ በተሰጠ ጊዜ የሚፈጸሙ ነገሮችን ዋና ዋና ክስቶቻቸውን ያሳውቃል ግን ነገር ግን ሙሉ ዝርዝርና በፍጻሜው ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ስሜትና ሃሳብ የሚታወቀው በእርግጥ ማሕተሙ በሚፈታበት ጊዜ ነው።

መገለጡ ከፊል የሆነ እውቀት ሰጥቶናል፤ ወደፊት የሚሆነውን መፈታት ግን በግልጽ ያሳውቀናል።

1ኛ ቆሮንቶስ 13፡12 ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

የታላቁን መከራ ዘመን በትክክል ምን እንደሆነ በዝርዝር አናውቀውም ምክንያቱም በታላቁ መከራ ውስጥ የማያልፉትን የሙሽራይቱን አካላት አይመለከትም።

ወንድም ብራንሐም ከስድስተኛው ማሕተም የተወሰኑትን ሚስጥራት የታላቁ መከራ ዘመንን የሚመለከቱ አድርጎ ተርጉሟል ነገር ግን አብዛኛው ዝርዝር ነገር አልተገለጠለትም።

ያ ዘመን የተፈጥሮ ዘመን የተዛባበት ድብልቅልቁ የሚወጣበት ጊዜ ነው የሚሆነው።

ከሚሆኑት ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ነው መገመት የምንችለው።

ራዕይ 6፡13 በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፥

ይህ መንፈሳዊ ነው ወይስ በጥሬው መረዳት ያለብን ቃል ነው? አናውቅም። ስለ ታላቁ መከራ የተነገሩ ምሳሌዎችን በትክክል መፍታት የሚችሉት ሁለቱ የእስራኤል ነብያት ናቸው። እስከዚያ እኛ መገመት ብቻ ነው የምንችለው።

ለዚህ ቃል ተቀራራቢ ትርጉም ሊሆን የሚችለው በታላቁ መከራ ውስጥ በሚፈጸመው ብዙ ነፍስ ግድያ ምክንያት የብዙ ሰዎች ሕይወት በአጭር መቀጨቱ ነው።

የሰማይ ከዋክብት የሚወክሉት ሰነፍ ቆነጃጅት ሰባኪዎችን ነው፤ እነርሱም ከመጽሐፍ ቅዱስ ሰማያዊ እውነቶችን መስበክ ያቆሙ ሰባኪዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ዓለማዊ በሆኑ ምኞቶች፣ ሴቶችን እና ገንዘብን በመመኘት ወድቀዋል። አስተዋዮች ናቸው ለመባልና የአስራት ገንዘብ ለመውሰድ ብለው ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችን ተከትለዋል። ሕዝቡን ለመቆጣጠር ብለው ነው ይህን ሁሉ ስሕተት የሰሩት። ከታላቁ መከራ በፊት አምነው በመዳናቸው በከፊል ትክክለኞች ናቸው። ነገር ግን ሰው ሰራሽ ከሆኑት የቤተክርስቲያን ልማዶቻቸውና ሃሳቦቻቸው አንጻር ተሳስተዋል።

እነዚህ ከዋክብት ከሰማይ ወድቀዋል፤ ስለዚህ በሰርጉ እራት ላይ በሰማይ አይገኙም ማለት ነው።

ስለዚህ እነዚህ ሰባኪዎች በንጥቀት ጊዜ ወደ ሰማይ አይነጠቁም።

ከዚህም የተነሳ ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

ብርቱ ነፋስ የሚወክለው ረጅም ዘመን የሚፈጀውን የታላቁን መከራ ጦርነት ነው።

ፍሬው ከመብሰሉ በፊት ነው የተቆረጠው። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ድነዋል በቅድስናም ኖረዋል፤ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መገለጥ አልተከታተሉም። በዚያ ፈንታ የሚያባብል የሰው ጥበብና አመለካከት እንዲሁም የሰውን ወግ ሲከተሉ ቆይተዋል። ሕይወታቸውም በታላቁ መከራ ውስጥ ይቀጠፋል ምክንያቱም የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ዋጋ አልሰጡዋቸውም ደግሞም በሙሉ አልተረዱዋቸውም።

ራዕይ 6፡14 ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፥ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ።

ሰማይ ከነዚህ ሰነፍ ቆነጃጅት ሸሸ። ሰነፎቹ ቆነጃጅት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አይችሉም። በታላቁ መከራ ውስጥ መሆን ማለት ዘግናኝ ሞት እንዲሞቱ ይረገማሉ ማለት ነው ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው አይኖርም።

በቤተክርስቲያን መንግስታቸው የገነቡት ነገር ሁሉ ወይም የተመኩበት ተራራቸው ትቷቸው ይሸሻል ወይም ይናዳል። ከፊታቸው ከሞት በቀር ምንም እርግጥ የሆነ ነገር የለም፤ ሊገደሉ የተወሰነባቸው መሆናቸውን ሲያውቁም ሞታቸውን በፍርሃትና በጭንቀት ይጠብቃሉ።

ራዕይ 6፡15 የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥

ራዕይ 6፡16 ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤

 

 

በጣም አስፈሪ ጊዜ ነው የሚሆነው። ኢየሱስ በተቆጣ ጊዜ ማንም በቁጣው ፊት መቆም አይችልም።

ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ሳለ ወደ እርሱ ኑ። ንሰሃ ግቡ፤ መዳንን ተቀበሉ። ከዚያም እርሱ የፍቅር አምላክ ይሆናችኋል።

ነገር ግን ለአርማጌዶን ጦርነት ሲመጣ የዛኔ በቁጣ ነው የሚመጣው። የቁጣ እና የበቀል አምላክ ሆኖ በሚመጣ ጊዜ እርሱን መጋፈጥ አስፈሪ ነገር ነው።

ሮሜ 12፡19 ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

 

በብሉይ ኪዳን ዘመን ሐጥያተኞች በድንጋይ ተወግረው ይሞቱ ነበር።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት እና ሌሎች ሰዎች ሁሉ በታላቁ መከራ ውስጥ በድንጋይ ተወግረው ለመሞት ይለምናሉ። ይህን በመጠየቃቸው ክፉ ሐጥያት መስራታቸውን በራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ናቸው፤ ሐጥያታቸውም የተጻፈውን ቃል መረዳት ያስችላቸው የነበረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ አለመቀበላቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቀው መከተል የፈለጉ ሰዎችን ማውገዛቸውና መተቸታቸው ትልቅ ስሕተት መሆኑን ዘግይተው ያስተውላሉ። በከባድ ጸጸት ውስጥ ሆነው ይሞታሉ።

ማናችንም ብንሆን መሞኘታችንን መስማት አንፈልግም። እንዲመሩን ብለን ገንዘብ በከፈልናቸው የቤተክርስቲያን መሪዎች አማካኝነት መታለላችንን ማመን አንፈልግም።

እኛ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መገለጥ አስፈላጊነት እና በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደነበረው እምነት መመለስ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን በቅጡ አልተረዳንም።

ራዕይ 6፡17 ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።

በሚወድቁ ድንጋዮች መፈጨት ዘግናኝ ሞት ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ በፊቱ ከመቆም ይሻላል።

 

ሰባተኛው ማሕተም የኢየሱስ ዳምግ ምጻት ነው

 

ለግማሽ ሰዓት ያህል ዝምታ ሆነ።

ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።

ከሚስጥራት ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ይህ ነው። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

እኛም ስለ ጌታ ምጻት አንዳች የምናውቀው ነገር የለም።

 

 

1964-0719 የመለከቶች በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈጸመም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

7ኛው ማሕተም እስካሁን ካልተፈታ 7ቱ ማሕተሞች ተፈተዋል ማለት አትችሉም።

1964-07-19 የመለከቶች በዓል

ሰባተኛው ማሕተም ወደ ምድር መልሶ ያመጣዋል።

7ኛው ማሕተም በጊዜ እና በስፍራ ውስን ሆነን መኖራችንን ያበቃልናል፤ ከዚያም ከጊዜ ቀጠና ውጭ ወደሆነ ከፍ ወዳለ ዳይሜንሽን እናልፋለን።

ስለዚህ አሁን በለበስነው አካል፣ አሁን ባለን ውስን የአእምሮ አቅም የ7ኛውን ማሕተም አንድምታዎች መረዳት አንችልም። ለዚህ ነው እግዚአብሔርም ዝም ያለው።

በሰባተኛው ማሕተም ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ መረዳት እንድንችል አዲስ አካል እና አዲስ አእምሮ ያስፈልገናል።

7ኛ ማሕተም እስኪፈጸም ድረስ ልንረዳው አንችልም።

ከዚያም በኋላ ይህንን የሚሞት አካላችንን እግዚአብሔር ወደማይሞት አካል ይለውጠዋል።

ጌታ ሊመጣ በጣም መቅረቡን የምታውቁበት የመጨረሻው ምልክት በውስጡ ደም የሌለው አካል መልበሳችሁ ነው፤ በደምስራችሁ ውስጥ የሚፈስሰውም መንፈስ ቅዱስ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23