ራዕይ 6 ክፍል 2 - ምልክት፣ ተልዕኮ፣ ሁነት
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ እና መጥምቁ ዮሐንስ ከአይሁድች ጋር ሲነጋገሩ አይለማመጡዋቸውም ነበር። የትኛውም ሰው የቤተክርስቲያን ራስ አይደለም።
- መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር ወደ መጀመሪያይቱ የቤተክርስያን ዘመን ተመለሱ
- ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳተው የእግዚብሔር ድምጽ አይደለም
- በደመና የታየው የሰው ልጅ ምልክት፣ ተልዕኮውና ከዚያም የ6ቱ ማሕተሞች መገለጥ
- የ6ቱ ማሕተሞች መገለጥ የ7ቱ ማሕተሞች መፈታት አይደለም
- ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ሁለት ደመናዎች ነበሩ
- ወንድም ብራንሐም በ1963 ከታየው ደመና ስር ቆሞ አልነበረም
- ነብያት ስሕተት በመስራታቸው ሐሰተኛ ነብይ አይባሉም
- መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ሰው አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር ወደ መጀመሪያይቱ የቤተክርስያን ዘመን ተመለሱ
ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
ይህ ስለ አራተኛው ማሕተም የሚናገረው ጥቅስ በሰባተኛው ማለትም በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ስለሚታዩ ሁኔታዎች ይገልጻል፤ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዕውር እና እውነትን ማየት ያልቻለች ተብላለች።
ይህች ወደ ክህደት ውስጥ የገባች ቤተክርስቲያን የፓስተሮቿ ስብከት ውጤት ናት።
የዚህች ቤተክርስቲያን ፓስተሮች ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ላይ ትኩረት ማድረግ ትተው የሰዎችን ንግግር ጥቅስ ወደ መሰነጣጠቅ እንዲገቡ በማድረግ ተሳክቶላቸዋል።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች የሚተዳደሩ ትንንሽ ቡድኖች ነበረች። አባላትም የሚሰበሰቡት በሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተክርስቲያን ተብሎ ሕንጻ የተጀመረው በታሪከ ማስረጃ መሰረት ከ220 ዓ.ም በኋላ ነው። ስለዚህ በ170 ዓ.ም የተጠናቀቀው የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ለቤተክርስቲያን ተብሎ ተለይቶ የተዘጋጀ ሕንጻ አልነበረም።
ስለዚህ ወደዚያ ዓይነት ስርዓት መመለስ አለብን።
በ2020 የመጣው ኮቪድ-19 ቫይረስ በሕንጻዎች ውስጥ የነበሩ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ዘጋቸው፤ ሰዎችንም በቤታቸው ተዘግተው እንዲቀመጡ አደረጋቸው። በዚህ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊነግረን እየሞከረ ነው።
አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ ፓስተር ቤተክርስቲያንን እንደሚያስተዳድር አልተጻፈም።
ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ አስራት የፓስተሩ ነው ብሎ አልተናገረም።
ብሉይ ኪዳን ደግሞ ፓስተሮችን ስድስት ጊዜ ያወግዛቸዋል። እኛ ልብ ብለን ያላስተዋልነው፤ ኤርምያስ ግን ያየው ነገር ምንድነው?
ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትጐሳቈይማለሽ።
ነፋሱ ጦርነት እና ግጭትን ይወክላል። ይህም የቤተክርስቲያን መሪዎች አስተምሕሮዋቸው ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየትና ማረጋገጥ ባለመቻላቸው የሚፈጠር ማለቂያ የሌለው ክርክርና ጥል ነው። ሰባኪዎች የሚመቻቸው ነገር መጽሐፍ ቅዱስን መክፈት ትተው ከሰው ንግግር ውስጥ በጥንቃቄ የተመረጡ ጥቅሶችን መሰነጣጠቅና ከዚያው ከሰው ንግግር ጥቅስ ውስጥ ለሃሳባቸው የማይስማማቸውን ጥቅስ ትተው ማለፍ ነው። ይህንኑ ደግሞ የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ስለሚያደርጉት የወንድም ብራንሐም ጥቅሶች ወደተለያዩ ዓይነት መልእክቶች ተለውጧል። እያንዳንዱ ጉባኤ ለቤተክርስቲያን መሪያቸው አመለካከት እስረኛ ሆነዋል ምክንያቱም አልስማማም የሚሉ ሁሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ የላቸውም። በተጨማሪ ደግሞ በተለያዩ ቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል የማያቋርጥ አለመስማማት አለ። እነዚህ መሪዎች ሲወያዩ መሰረታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ስላለስሆነ በየትኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ወደ መግባባትና ወደ መፍትሄ መምጣት አይችሉም። አዲሱን የኢየሱስ ስም ለማወቅ ሰባኪዎች 8 የተለያዩ ስሞች ሲያቀርቡላችሁ የትኛው ትክክለኛ ስም መሆኑን ለመለየት ሞክሩ። ደግሞ ከእዚህ ግምቶች የትምኛውንም የሚደግፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም ምክንያቱም የኢየሱስን አዲስ ስም ማንም አያውቀውም ተብሎ ተጽፏል።
ራዕይ 19፡12 … ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
ስለዚህ ሰባኪዎች መርምረው ማግኘት በማይችሉት ነገር ላይ በከንቱ ይደክማሉ።
ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ወንድም ፒሪ ግሪን 27 የተለያዩ ቲዎሪዎች አሰባስቧል። እነዚህ ሁሉ ቲዎሪዎች ስለ ትክክለኝነታቸው የሚጋደሉላቸው ደጋፊዎች አሏቸው። ይሁ ሁሉ ግን ባዶ ነፋስ ነው ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደተናገሩ የተጻፈ አንዳችም ነገር የለም።
ደግሞም ስለ 7ኛው ማሕተም የጥል እና የክርክር ነፋስ አለ፤ ሰባኪዎ ይህንንም እናውቃለን ይላሉ፤ ነገር ግን የጌታ ምጻት በዓለም ላይ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ ታላቁ እና ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው። 7ኛው ማሕተም ምን እንደሆነ አልተጻፈም እነርሱ ግን ገብቶናል ይላሉ። ለተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው አክብሮት ይህን ያህል የወረደ ነው፤ ከዚህም የተነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተረዱት ብዙ ነገር አለ።
ጉባኤዎቻቸውም እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገር ግን የአስተዋይ ንግግር የሚመስሉ ክርክሮች ይሰማሉ፤ ከዚያ በኋላ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምንም ሳያውቁ ይቀራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ማስረጃ የማይገኝላቸውን ጥልቅ ሚስጥራት መግለጥ የቻሉ ይመስላቸዋል፤ ከዚህም የተነሳ ለሌሎቹ አስተምሕሮዋቸውም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደማያስፈልጋቸው ያስባሉ። ስለዚህ ማለቂያ የሌለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። የእምነቶቻቸው መሰረቶች ከሰው ንግግር ውስጥ በጥንቃቄ የተመረጡ ጥቅሶች ናቸው። ሁላቸውም ግን የማይመቻቸውን ሌሎች ጥቅሶች ትተው ማለፋቸውን ልቦናቸው ያውቃል። ማስመሰል ከማብዛታቸውም የተነሳ ሃሳባቸውን በተጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ አሳልፈው ማረጋገጥ አይችሉም። ስለዚህ የእነርሱ ነገር ጊዜ ማባከን ብቻ ነው።
ነገር ግን ጥሩ ክፍያ ይከፈላቸዋል። ለእነርሱም ቁምነገር ማለት የሚከፈላቸው ገንዘብ ነው።
ማርቲን ሉተር ይህን በተመለከተ ሲናገር እግዚአብሔርን ከማገልገል ይልቅ ለሳንቲም መሯሯጥ ነው ብሏል።
የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ሲሰበክ የነበረው ስብከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ዕለት ዕለት መጽሐፍ ቅዱስን ትመረምር ነበር።
ቤርያ ከተማ ውስጥ ጳውሎስን ያዳምጡ ስለነበሩት አይሁዶች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-
የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለብን።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ክሪስማስን አክብረው አያውቁም፤ ደግሞም ክሪስማስ የማክበርን ልማድ የጀመረው ፖፑ ዩልየስ ቀዳማዊ በ350 ዓ.ም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናስብ አላዘዘንም። ታድያ ለምንድነው ክሪስማስን የምናከብረው? ልማድ በመከተል ብቻ ነው፤ የሜሴጅ ሰዎች በጓዳ ውስጥ ካቶሊክ ስለሆኑ ነው። የካቶሊክ አረማዊነትን መከተል የሚችሉ ይመስላቸዋል ምክንያቱም እግዚብሔርን እራሳቸው በፈለጉበት መንገድ ማምለክ መብታቸው እንደሆነ ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት አስቡ ብሎ እንዳላዘዘን ቢያውቁም እንኳ ያስቡታል። ምክንያቱም ዛሬ ሰዎች የተመረጡ የሰው ንግግር ጥቅሶችን ነው የሚያምኑት እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን አይደለም።
አንዳንድ የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የማንንም ልደት አያከብሩም ነበር። ልደት ማክበር የአሕዛብ ልማድ እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሁለት ሰዎች ልደት ብቻ ተመዝግቧል፤ እነርሱም የፈርዖን እና የሔሮድስ ልደት ናቸው። ሁለታቸውም በልደታቸው ቀን ሰው ገድለዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ምን እየነገረን ነው? እኛ ግን በምንኖርበት ዘመናዊ ዓለም ልማዶች ከመጠመዳችን የተነሳ ለመለወጥ ዝግጁ አይደለንም።
በማቴዎስ ምዕራፍ 25 መሰረት ከባድ እንቅልፍ ከመተኛታችን የተነሳ መስማትም ትተናል፤ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ 10 ቆነጃጅት ማለትም ንጹሕ ሴቶች በዘመን መጨረሻ የሚኖሩ ክርስቲያኖችን በሙሉ የሚወክሉ ናቸው። ክርስቲያኖች የየትኛውም ቤተክርቲያን አባል ቢሆኑ እንኳ በነዚህ ቆነጃጅት ተወክለዋል።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
ክሪስማስ፣ ልደት ማክበር፣ እና ግርግር የበዛበት የአሕዛብ የዘመን መለወጫ በዓል አዲስ ኪዳን ውስጥ ተከብሮ አያውቅም። የዚያ ጊዜ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው ዛሬ እኛ ከምንኖርበት አኗኗር በጣም የተለየ ነበር።
ጳውሎስ በዓመት ውስጥ አንድን ቀን ለይተው የሚያከብሩ ክርስቲያኖችን ጠንከር ባሉ ቃላት ነበር የተቆጣቸው። ይህን ዓይነቱን ልማድ ጳውሎስ ለአረማዊነት ባሪያ እንደመሆን ይቆጥረዋል። እነዚህንም ክርስቲያኖች በማስተማር በከንቱ እንደ ደከመ ይሰማው ነበር።
እግዚአብሔር ቢያውቃቸውም እንኳ እነርሱ ግን እግዚአብሔርን ያውቁ እንደሆን ጳውሎስ ተጠራጠረ።
ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
ክሪስማስ። 25ኛው ቀን። 12ኛው ወር። የክሪስማስ ወቅት። በየዓመቱ።
በየዓመቱ በተወሰነ ወር በተወሰነ ቀን የሰውን ልደት ማክበርም ከዚህ የተለየ አይደለም።
አዲስ ዓመት። የመጀመሪያ ቀን። የመጀመሪያ ወር። አረማውያን ይህንን ቀን በብዙ ጩኸት ያከብሩታል፤ ጩኸቱንም የሚፈልጉት አጋንንትን ለማባረር ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ቀን ጩኸት አለ፤ ደግሞም ችቦ እናበራለን፤ ርችትም እንተኩሳለን። ለምን? አረማዊ ልማዶች በደም ስራችን ውስጥ ገብተውብናል እኛም ልንተዋቸው አንፈልግም።
ጳውሎስ ተስፋ መቁረጡ ያለ ምክንያት አይደለም።
ገላትያ 4፡11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
እንዲህ ዓይነቱ ክርስትና የጊዜ ብክነት ነው።
ሐዋርያት ወደ መሰረቱዋት ወደ ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን በመመለስ ፈንታ ከዘመናዊ ልማዶቻችን ጋር እየተጣበቅን የቤተክርስቲያናችን መሪዎች ከጥንቷ ቤተክርስቲያን አርቀው እንዲወስዱን ፈቅደናል።
ከፈለግን በዓመት ውስጥ ደስ ያለንን ቀን የማክበር መብት አለን። የሕዝቡ መብት። ሎዶቅያ ማለት ትርጉሙ የሕዝቡ መብት ነው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
“የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን”። የሎዶቅያ ሰዎች እምነታቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እግዚአብሔርንም እራሳቸው በወደዱት መንገድ ያገለግላሉ።
እግዚአብሔር ግን እነዚህ የሰው ጥቅስ እየተረጎሙ የሚሰብኩ ሰባኪዎች ያሉባትን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ከአፉ አውጥቶ ይተፋታል።
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
ማድረግ የነበረብነ ጥቅሶቹን ተጠቅመን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መሄድ እና ወደ አዲስ ኪዳን መመለስ ነበር።
ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ በሉ፤ ታላቁ መከራ ውስጥ ከገባን በኋላ ግን ምንም መብት አይኖረንም።
ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳተው የእግዚብሔር ድምጽ አይደለም
በሜሴጅ ተከታዮች ዘንድ ያለው ትልቅ ስሕተት ስውር ቀስ በቀስ ዊልያም ብራንሐምን ወደ መለኮትነት ከፍ ማድረጋቸው ነው።
የማይሳሳተው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
በ1870 ፖፑ እኔ አልሳሳትም ብሎ አወጀ። ዛሬ ደግሞ የሜሴጅ ተከታዮች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ኮርጀው ዊልያም ብራንሐም አይሳሳትም ይላሉ። እነዚህ ሴቶች ልጆች ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በመመለስ ፈንታ ወደ እናታቸው ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እየተመለሱ ናቸው።
እግዚአብሔር የሰው ንግግር ጥቅስ የመጥቀስ ልማድ ለተጠናወታቸው ለሜሴጅ ተከታዮች ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳት ሰው አለመሆኑን ሊያሳያቸው ብሎ ዊልያም ብራንሐም እንዲሳሳት ፈቀደ።
ዊልያም ብራንሐም ፍጹም አይደለም። እርሱ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ የእግዚአብሔር ድምጽ አይደለም።
ለምን? ምክንያቱም አንዳንድ ነገሮች ላይ ስሕተት ሰርቷል።
አንድ ስሕተት ብቻ መስራቱ አንድ የተሳሳተ ንግግር ብቻ መናገሩ ከመለኮትነት፣ ከፍጹምነት፣ የማይሳሳት ከመባል፣ የእግዚአብሔር ድምጽ ከመሆን ያጎድለዋል።
የመጀመሪያው ምጻት መንገድ ጠራጊ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን በመጠራጠሩ ስሕተት ሰርቷል።
ነብይ ሁልጊዜ ፍጹም መሆን አይጠበቅበትም።
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ ውስጥ ሲጠራቸው በግልጽ መስማት ይችላሉና
… ዛሬ በዚህ ቀን የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ሲጠራችሁ አድምጡ።
60-0804 ንስር ጎጆዋን እንደምትበታትን
መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆኑን እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ የእኔ ድምጽ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ድምጽ የሚናገርበት እንጂ
62-1007 የበሩ ቁልፍ
አያችሁ ብዙ ነገር የሚያበላሽብን ይህ ነው። እኔ ሳልልካቸው እርሱ ልኮናል እያሉ አንዳንድ ወንድሞች ሄደው ሰዎች ሚስታቸውን መፍታት እና መንፈሳዊ የትዳር አጋራቸውን መፈለግ አለባቸው ብሎ አስተምሯል እያሉ ይሰብካሉ፤ ከዚያም ሌላ ደግሞ እኔ በፍጹም የማልሳሳት እንደሆንኩ። ከዚያም ሌላ ደግሞ… ወይ ሌላም በጣም ዘግናኝ ነገር ይናገራሉ።
ልባም ሰዎች ይህን ያስተውላሉ፤ የሜሴጅ ሰባኪዎች ግን የብዙዎቹን ተከታዮቻቸውን አእምሮ አደንዝዘው ስላስተኙ እውነትን ከፈጠራ ወሬ መለየት እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል።
ሐይማኖታዊ አሳሳችነት በነጩ ፈረስ ላይ ለተቀመጠው የተሰጠው ስራ ነው፤ እርሱም ቀንደኛ ጠላታችን ነው።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ምንም ዓይነት ተፈጥሮአዊ ማብራሪያ ያልተገኘለት በ7ቱ መላእክት የተፈጠረው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ፎቶ ተነስቶ ነበር።
ይህ የሆነው ከሳንሴት ፒክ ከተማ 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ራቅ ብሎ ነው፤ ሳንሴት ፖክ ውስጥ ከ8 ቀናት በኋላ እነዚሁ መላእክት ሰው ሳያያቸው ጉብኝት አድርገው ነበር።
ወንድም ብራንሐም ደመናውን የሰሩት መላእክት እና ከ8 ቀናት በኋላ እርሱን ሊጎበኙ የመጡት መላእክት በአንድ በተመሳሳይ ጊዜ ነው የመጡት ብሎ ከተናገረ በኋላ ብዙ ግራ መጋባት ተፈጠረ።
ደመናው ፎቶግራፍ ተነስቶ ሁለት ወር እስኪያልፈው ድረስ እርሱ ስለ ደመናው ምንም አልሰማም ነበር።
ደመናውን በተመለከተ እርሱ በተናገራቸው ቃላት ላይ የተመሰረተ አስተምሕሮ ብትፈጥሩ እርስ በርሱ የሚጋጭ እና ግራ የሚያጋባ ሃሳብ እንዲሁም ሐሰተኛ ዜና ታገኛላችሁ። ስሕተት እና ሐሰተኛ ዜና እየበረሩ ሲሄዱ እውነት ግን በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እያነከሰች ትሄዳለች። ብዙ የተሳሳቱ የፈጠራ ትምሕርቶች በተሳሳቱ ጥቅሶች ላይ ተመስርተው ተዘጋጅተዋል። እነዚህንም ስሕተቶች ትክክል ናቸው ብለው የሚጋደሉላቸው ሰዎች አሉ።
አስተምሕሮ በሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ ነው መመስረት የለበት። የሰው ንግግር ጥቅሶች በትክክል በተጠቀሱ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ለመግለጥ ነው የሚያገለግሉት።
በደመና የታየው የሰው ልጅ ምልክት፣ ተልዕኮውና ከዚያም የ6ቱ ማሕተሞች መገለጥ
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ የታየው ይህ ደመና ሊመጣ ላለ ነገር ምልክት ነበር፤ እርሱም የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ነው።
6 ማሕተሞች ብቻ ናቸው የተገለጡት ምክንያቱም 7ኛው ደመና የጌታን ምጻት የሚመለከት ሚስጥር ነው።
ከደመናው በታች ምንም ተራራ እንደሌለ ልብ በሉ። ደመናው ከሳንሴት ፒክ ተራራ በላይ አልነበረም።
ደግሞም በደመናው ውስጥ ምንም ፊት አልታየም።
ሊመጣ ያለ ክስተትን የሚያመለክት ምልክት እራሱ ክስተቱ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ስሕተት ነው።
ምልክቱ አስደናቂ ምልክት ነበር፤ የሜሴጅ ፓስተሮችም የተሳሳቱ የሰው ንግግር ጥቅሶችን ተርጉመው ደመናው የጌታ ምጻት እና የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ መውረድ ነው ብለው አወጁ።
የመልአኩ መውረድ ነው ቢሉም ግን ደመናው ከምድር 42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ታይቶ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ከዚያ ከፍታ ምንም ዝቅ ሳይል ቀርቷል።
መላእክቱ በመጡ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ለአደን ወጥቶ ነበር። ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ አደን ላይ አልነበረም።
ምልክትን እራሱ ክስተቱ ነው ብላችሁ አታምታቱ።
1. የሚመጣ ክስተት ምልክት
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፍላግስታፍ አካባቢ የታየው ደመና በሰማያት የተቀመጠው የሰው ልክ ምልክት ነበር፤ ያመለከተውም የማሕተሞቹ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነበር። እነዚያ መገለጦች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር መረዳት እንድንችል በማድረግ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንድንመለስ ያደርጉናል።
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
63-0818 የአንድነት ጊዜ እና ምልክት
ከጥንቱ የቤተክርስቲያን ዘመን ጀምሮ ዛሬ የምናያቸውን ነገሮች አይተው አያውቁም። ይህም ሊሆን የቻለው እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች ስለላከ እና በእነርሱም ምልክት ስለሰጠን ነው፤ ከዚያም ከሰማይ ወደ ምድር ሰባት መላእክት ላከ፤ እነዚህም መላእክት ወደ ምድር በመምጣት በየዲኖሚኔሽኖች ውስጥ ተበታትኖ የነበረውን ቃል ወደ አንድ በመሰብሰብ እንደገና ወደ እግዚአብሔር ቃል በማምጣታቸው መንፈስ ቅዱስ ሊወርድ ችሏል።
ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና የሰው ልጅ በሰማይ መሆኑን የሚያመለክት ምልክት ነበረ። ኢየሱስ እኛን ወደ ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን የሚመልሱንን ሰባቱን ማሕተሞች ሊገልጣቸው ተዘጋጀ።
1965-0718
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል ከዚያ በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል።”
ትልቁ ቁምነገር ምልክቱ አይደለም። ትልቁ ቁምነገር ምልክቱ የሚጠቁምለት የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ነው።
ምልክቱ ማለትም አስደናቂው ደመና ከወንድም ብራንሐም ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም፤ ምክንያቱም እርሱ በ200 ማይልስ ርቀት ያለችው ቱክሰን ውስጥ ነበረ፤ ስለ ደመናውም በሰዓቱ ምንም አላወቀም። እግዚአብሔር ሰባተኛውን መልአክ ማክበር አይደለም ሃሳቡ። የእግዚአብሔር ትኩረቱ በሚስጥራቱ መገለጥ ላይ እንጂ ለዘመን መጨረሻ በተላከው ነብይ ላይ አልነበረም።
ነገር ግን የሜሴጅ ፓስተሮች ያሰራጩትን ሐሰተኛ ዜና ተመልከቱ።
ደመናው በሳንሴት ተራራ ላይ አልነበረም። ከላይ የምታዩት ምስል በፎቶ እስቱድዩ የተስተካከለ ፎቶ ነው፤ በግራ በኩል ከላይ ጥቂት ብርሃን እንዲገባበት ተደርጓል። ይህም ብርሃን የፈጠረው ጥላ ከአፍንጫ በላይ ሁለት ዓይኖች ያሉ እንዲመስል አድርጓል። ስለዚህ ይህንን ይዘው ኢየሱስ ሳንሴት ተራራ ላይ መጥቷል ለማለት እንደ ማስረጃ ተጠቀሙበት።
ልብ በሉ። ይህ የረቀቀ ተንኮል ነው። ፎቶው ውስጥ መሬትን የሚያሳየውን ቦታ ቆርጠው አውጥተውታል ምክንያቱም ፎቶው ውስጥ ተራራ የለም።
2. ተልዕኮው
ማርች 8 ቀን 1963 7ቱ መላእክት ሳንሴት ፒክ አካባቢ ያደረጉት ጉብኝት ዓላማው ከሰባቱ ማሕተሞች ስድስቱን የመግለጥ ተልዕኮ ነው።
በዚያ ቀን ምንም ደመና አልተፈጠረም።
ወንድም ብራንሐማ የሰራው ስሕተት 7ቱ መላእክት ያን ዕለት ሊጎበኙት ወደ ሳንሴት ፒክ ሲመጡ ደመናውን ፈጠሩ ብሎ ማመኑ ነው።
የሜሴጅ ሰባኪዎች እውነታውን ለማጣራት ማስረጃዎችን ፈትሸው አያውቁም። ነብይን መመርመር ስሕተት ነው ብለው ያምናሉ።
ስለዚህ ስሐተቱን ይዘው በመሮጣቸው ብዙ ነገር አበላሽተዋል። መልእክቱን ግራ መጋቢያ አደረጉት።
65-1127 እግዚአብሔር ሳይፈቅድ እርሱን ለማገልገል መሞከር
እኔ ተመለከትኩ፤ ከፊት ለፊቴ ሰባት መላእክት ቆመው አየሁ፤ ልክ እንደዚህ ከፊቴ ቆመው ነበር። … አጠገቤ በቅርበት። በዚያም ጊዜ ምን እንደሆነ አየሁ። ወዲያው … ተልዕኮዬን እና የእግዚአብሔርን ቃል ተቀበልኩ፤ “ሰባቱ ማሕተሞች ሰባቱ ሚስጥራት ናቸው።” አያችሁ?
ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻጽ መሆኑ ተገልጧል ስለዚህ ስለ ምጻቱ በዝርዝር ልናውቅ አንችልም። ከዚህም የተነሳ ወንድም ብራንሐም ስለ መጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች ብቻ ነው መረዳት ማግኘት የቻለው። እንደዚያም ሆኖ ስለ ታላቁ መከራ ጥቂት ነገር ብቻ ነው የተነገረው።
63-1201 ፍጹሙ
እነዚህም ሰባት መላእክት በዚያ ስፍራ ቆመው ተመልሼ እንድሄድና መልእክቱን እንድናገር አዘዙኝ፤ እንዲህም አሉኝ፡- “ሄደህ አንድ በአንድ እነዚህን መልእክቶች ተናገር።” እኔም እንደተባልኩት አደረግሁ።
63-0803 ተጽእኖ
ሰባት መላእክት ወረዱና እንዲህ አሉ፡- “ባለ ስድስት ማሕተሙ የእግዚአብሔር ሚስጥር መገለጥ እነሆ አሁን ይገለጣል።”
3. ዋነኛው ክስተት የማሕተሞቹ መገለጥ ነው።
ከማርች 17 – 24 ቀን 1963 ጄፈርሰንቪል ኢንዲያና ውስጥ ከስድስቱ ማሕተሞች ሰባቱ ተገልጠዋል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
የመጀመሪያውን ማሕተም ይፈታውና ሰባተኛውን መልአክ ይገልጠዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሚስጥራት ወደ ፍጻሜ ማምጣት ብቻ ነው የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት።
የ6ቱ ማሕተሞች መገለጥ የ7ቱ ማሕተሞች መፈታት አይደለም
ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የተሰበከው ታዋቂ ስብከት የተጻፈበት መጽሐፍ ርዕሱ “Revelation of the Seven Seals” (የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ) እንጂ “Opening of the Seven Seals” (የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት) እንዳልሆነ ልብ በሉ። በዚህ ጉዳይ ማንም አያሳስታችሁ።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ከመጀመሪያው ስሕተት ሲያስተምሩ ኖረዋል። በሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ እና በሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መካከል ያለውን ልዩነት ማየት አልቻሉም፤ ሰባቱ ማሕተሞች የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ በሰማይ ነው።
ከጥቅሶች ቆንጥረው በመውሰድ ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን ፈታ ብለው ተናገሩ። ነገር ግን እርሱ ማሕተሞቹን ከፈታ ከእርሱ በፊት ሰባቱን ማሕተሞች የገለጠ ሰው ነበረ ማለት ነው። ነገር ግን ሰባቱን ማሕተሞች የገለጠ ሰው አልነበረም።
ሰባቱ ማሕተሞች ከዚያ በፊት ያልተገለጡ ከሆነ ወንድም ብራንሐም ሊፈታቸው አይችልም።
መጀመሪያ መገለጥ አለባቸው፤ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሊፈቱ የሚችሉት።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል በማለት ያታልሏችኋል። ደመናው ትልቅ ክስተት ነው በማለት ያታልሏችኋል፤ ደመናው ግን ሊመጣ ላለ ታላቅ ክስተት ምልክት ብቻ ነው።
ሰባቱም ማሕተሞች በሙሉ ተፈተዋል ሲሉ ያታልሏችኋል።
7ኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው። ስለ ጌታ ምጻት ምንም አናውቅም። ወንድም ብራንሐም መግለጥ የቻለው የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማሕተሞች ብቻ ነው። ለዚህ ነው ስድስቱ ማሕተሞች ከ7ኛው ማሕተም ጋር አንድ ላይ ሳይሆኑ ለብቻ በሌላ ምዕራፍ የተጻፉት።
ምዕራፍ 7 በምዕራፍ 6 ውስጥ ከተጻፉት ከ6ቱ ማሕተሞች እና በምዕራፍ 8 ከተጻፈው ከ7ኛው ማሕተም መካከል ነው የሚገኘው። ይህም 7ኛው ማሕተም የፒራሚድ ጉልላት እንዲመስል ያደርገዋል። ደግሞም የጌታን ምጻት የሚያሳይ ውብ ምሳሌ ነው።
ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም እውቀት አልነበረውም። እኛም የለንም።
1964-0719 የመለከት በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።
ስድስት ማሕተሞች ብቻ ነበሩ የተገለጡት።
64-08156 ቃሉን ማረጋገጥ
ሰባተኛው መልአክ የተላከው የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር ሊገልጥ ነው። ሚስጥራቱ በሙሉ መቋጫቸው የሰው ልጅ ነው፤ የእርሱ የዘመን ሙላት የአካሉን ሙላት ለመግለጥ ወደ ቃሉ ሙላት መጥቷል። ይህም ቃሉ ነው፤ የተነገረው ቃል በቃሉ መገለጡ ነው፤ የቃሉ መገለጥ ነው።
ወንድም ብራንሐም በአፉ የተናገረው ቃል ሊገለጥ የሚችለው በተጻፈው ቃል ውስጥ ክርስቶስ ሲመላለስ ገልጦ ካሳየን ብቻ ነው።
ከአፍ ንግግር የተወሰዱት ጥቅሶች ለሙሽራይቱ አካል ግለሰቦች የተጻፈውን ቃል የሚገልጡ መሆን አለባቸው፤ ይህ ሲሆን ነው የሙሽራይቱ አካላት በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል ሚስጥራት ከመጽሐፍ ቅዱስ እያብራሩ መረዳት የሚችሉት።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ሁለት ደመናዎች ነበሩ
የሜሴጅ ሰባኪዎች ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና የጌታ ምጻት ነው ወይም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ነው በማለት ብዙ ነገር አበላሽተዋል። ይህን ሁሉ የሚሉት ደመናው ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ደቂቃ ብቻ ታይቶ የጠፋ መሆኑን እያወቁ ነው። ደመናው በጭራሽ ወደ ምድር አልወረደም። ላይፍ መጽሔት በሜይ 17 ቀን 1963 እትሙ ገጽ 112 ላይ ስለ ደመናው ጽሑፍ ከማሳተሙ በፊት ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው ምንም አልሰማም ነበር።
ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ሁለት ደመናዎች እንደነበሩም አላወቀም። በፎቶግራፍ የተደገፈ ማስረጃ ቢኖርም እንኳ፤ ደግሞም ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድ ስለ ሁለቱ ደመናዎች ማብራራት አልቻልኩም ቢልም የሜሴጅ አማኞች እስከ ዛሬ ሁለተኛ ደመና መኖሩን ይክዳሉ። ለዚህ ነው ደመናውን ሚስጥራዊ ደመና ያለው።
ከትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ኋላ የነበረው ትንሹ የጭስ ደመና የተፈጠረው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከቫንደንበርግ አየር ኃይል ጣብያ ተወንጭፎ በትልቅ ከፍታ ላይ በፈነዳ ሮኬት ነው።
ወንድም ብራንሐም ይህንን ደመና በተመለከተ ግራ ተጋብቷል፤ ስለዚህ ስሕተት የሆኑ የተለያዩ ንግግሮችን ተናግሯል። መላእክቱ ደመናውን የሰሩት ወደ ላይ ሲወጡ ነው አለ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲወርዱ ነው አለ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በከፍታ ላይ ሲንሳፈፉ ነው ብሎ ተናገረ። በፍጹም ያላየውን ነገር በተመለከተ በግምት እየተናገረ ነበር።
የውሃ ትነት የዝናብ ደመና ይፈጥራል። የጭስ ትነት የጭስ ደመና ይፈጥራል። ቅዱስ ጴጥሮስ የጭስ ደመና እንደሚፈጠር ትንቢት ተናግሮ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤
ይህ ትንቢት የተፈጸመው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከቫንደንበርግ አየር ኃይል ጣብያ በላይ በትልቅ ከፍታ ላይ ሮኬት ሲፈነዳ ነው።
63-1201
እነዚህም ሰባት መላእክት በዚያ ስፍራ ቆመው ተመልሼ እንድሄድና መልእክቱን እንድናገር አዘዙኝ፤ እንዲህም አሉኝ፡- “ሄደህ አንድ በአንድ እነዚህን መልእክቶች ተናገር።” እኔም እንደተባልኩት አደረግሁ። ወደ ላይ ሲወጡም ወደ ላይ ሰላሳ ማይልስ ከፍታ ሲወጡ በዚያኑ ቀን ሳይንቲስቶች ፎቶ አነሱ ፎቶውም በዓለም ዙርያ ተሰራጨ።
አሁን ደግሞ መላእክቱ ፎቶግራፍ የተነሱት ወደ ላይ ሲወጡ ነው ይላል።
ሳንሴት ፒክ አካባቢ ፌብሩዋሪ 28 ቀን የአደን ወቅት ከመከፈቱ በፊት ፍላግስታፍ አጠገብ ደመና ከሰሩበት ቀን 8 ቀናት ካለፉ በኋላ 7ቱ መላእክት ከወንድም ብራንሐም ተለይተው ሲሄዱ ምንም ደመና አልሰሩም። በዚያ ሰዓት ወንድም ብራንሐም ቱክሰን ውስጥ ነበር።
63-0623 በፈረሰበት በኩል መቆም
እኔም በሰዓቱ መላእክቱ መልእክት ይዘው ከሰማይ እየወረዱ ሳለ ሳይንቲስቶች ፎቶግራፍ እያነሱ እንደነበር አላወቅሁም።
አሁን ደግሞ መላእክቱ ሲወርዱ ነው ፎቶ የተነሱት ይላል። በዚያ ከፍታ የታየው በማታ የሚያበራ ደመና ነበረ፤ ይህም ደመና ቀን ቀን የፀሃይዋ ብርሃን በሚያንጸባርቅበት ጊዜ አይታይም።
63-0630 ሕይወታችሁ ለወንጌሉ ይመጥናል?
ይህ ግን ሃያ ስድስት ማይልስ ያህል ነበረ፤ እርሷም ቀኑን ሙሉ እዚያው ተንሳፍፋ ነበር።
በፍጹም። 7ቱ መላእክት ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና የሰሩት ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ደቂቃዎች ብቻ ነበረ።
ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች። ሶስቱም የተሳሳቱና እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው። መላእክቱ ወረዱ፣ ወይስ ወደ ላይ ወጡ፣ ወይስ ቀኑን ሙሉ ሰማይ ላይ ተንሳፈፉ?
ወንድም ብራንሐም በ1963 ከታየው ደመና ስር ቆሞ አልነበረም
63-0623 በፈረሰበት በኩል መቆም
እኔም በሰዓቱ መላእክቱ መልእክት ይዘው ከሰማይ እየወረዱ ሳለ ሳይንቲስቶች ፎቶግራፍ እያነሱ እንደነበር አላወቅሁም።
… የደመናው ፒራሚድ ይታያችኋል? ልክ ከዚህ ስር ቆሜ ነበር።
ቀጣዩ ትልቅ ስሕተቱ ይህ ነው። እርሱ ሳንሴት ፒክ የሚባል ቦታ ሆኖ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በስተ ሰሜን ካለፈው ደመና ስር ቆሜ ነበር ይላል።
ደመናው ከሳንሴት ፒክ በስተ ሰሜን 200 ማይልስ ርቃ ከምትገኝ ከተማ በላይ 7ቱ መላእክት ወንድም ብራንሐም ዘንድ ከመምጣታቸው 8 ቀናት ቀድሞ ነው የታየው። መላእክቱ ወደ እርሱ የመጡት ከጥዋቱ 2 ሰዓት ስለነበረ በምንም ተዓምር ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ከታየው ደመና ስር ሊቆም አይችለም።
እንደ ገና ደግሞ መላእክቱ ደመናውን የሰሩት እየወረዱ ሳለ ነው ይላል።
65-o718E መንፈሳዊ ምግብ በወቅቱ
… ወደ ላይ በወጣ ጊዜ እኔ እና ወንድም ጂን ኖርማን እዚያው ቆመን ነበር። እነርሱ ፎቶ አንስተዋል ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ምን እንደሆነ አያውቁም።
ቀጥሎ ደግሞ መላእክቱ ወደ ሰማይ ሲመለሱ እና ደመናውነ ሲፈጥሩ እርሱ እና ጂን ኖርማን አብረው ከደመናው ስር ቆመው እንደነቡ ይናገራል።
ማርች 8 ቀን 7ቱ መላእክት ወደ ሰማይ የወጡ ጊዜ ምንም ደመና አልተፈጠረም። ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ከ8 ቀናት በፊት ከተፈጠረው ደመና ስር አልቆሙም።
እነዚህ ነገሮች ሁሉ ግራ የተጋቡ ስሕተቶች ናቸው።
63-1128M ምስክርነት
ልክ እንደ ማርች 17 እንደወጣው የላይፍ መጽሔት እትም በሰማያት ላይ ያንን ክብ ብርሃን አይታችኋል፤ ያ ብርሃን ሰላሳ ማይልስ ከፍታ ላይ ሆኖ ሃያ ሰባት ማይልስ ስፋት ነበረው። እርጥበት ወይም ትነት እስከ ዘጠኝ ማይልስ ያህል ከፍታ ብቻ ነው የሚወጣው፤ ስለዚህ ይህ ምን እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል።
ከዚያ ደመና ስር በቆምኩበት ቦታ ደግሞ አሁን በዚህ የተቀመጠ ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰባት ወላዕክት ሲወርዱ ከጎኔ ቆሞ ነበር፤ እነርሱም በዓይን እየታዩ እዚያው ከእኔ ጋር ቆመው ስለ መጨረሻው ዘመን እየነገሩኝ ነበር። እነዚህንም መገለጦችና የዮሐንስ ራዕይን፣ እና ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ሲነግሩኝ እንዲህ አሉ፡- “ወደ ቤትህ ተመለስና ይህን መልእክት አንድ በአንድ ተናገር።” ከዚያም ወደ ላይ ወጣ፤ ከፍ እያለ ሲሄድም ወደ ነጭነት ተለወጠ።
እንደ ገና ደግሞ ደመናው የተፈጠረው መላእክቱ ወደ ምድር ሲወርዱ ነው ይላል። ጂን ኖርማን ደግሞ ከደመናው ስር ቆሞ ነበር። ከዚያም ደግሞ መላእክቱ ወደ ሰማይ ሲወጡ የተፈጠረው ደመና ነጭ ሆነ ይላል።
ማርች 8 1963 ሳንሴት ፒክ አካባቢ ደመናው የተፈጠረው መልእክቱ ሲወርዱ ነው ወይስ ሲወጡ?
መልሱ፡- በዚያ ቀን መላእክቱ ምንም ደመና አልሰሩም። ደመናውን የሰሩት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነው።
መላእክቱ እርሱን የጎበኙት ማርች 8 ቀን ነበር ግን ያን ዕለት ምንም ደመና አልፈጠሩም። ደመናው ከ8 ቀናት በፊት ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በስተ ሰሜን ሲያልፍ ፍላግስታፍ ውስጥ መንፈሳዊ የነበረ ሰው አልነበረም።
ግራ የሚያጋቡትን ጥቅሶች ተመልከቱ። መላእክቱ ደመናውን የሰሩት ሲወርዱ ነው ወይስ ወደ ላይ ሲወጡ? ሁለቱንም እነዚህ ጥቅሶች ከዚህ በታች የተጠቀሰው ጥቅስ ደመናው በታላቅ ከፍታ ላይ ተንሳፍፎ ብቻ እንደነበረ በመናገር ይቃረናቸዋል።
63-0628M ጌታ ሆይ አንድ ጊዜ ብቻ
እንግዲህ ሳይንስ ፎቶግራፍ አንስቶልናል፤ አይታችሁታል፤ በአሶሼትድ ፕሬስ ተላልፏል። ምን መሆኑን አላወቁም። ሃያ ስድስት ማይልስ ከፍታ ላይ የተንሳፈፈ ደመና ብቻ ነው ያዩት።
ይህ ንግግር ትክክል ነው። ደመናው ከፍታውን እንደጠበቀ ከፍላግስታፍ አልፎ ወደ ዊንስሎው ነው የሄደው።
ወንድም ብራንሐም ከሰራቸው ከነዚያ ስሕተቶች ሁሉ በኋላ (ምክንያቱም ደመናውን አላየውም፤ በግምት ብቻ ሲናገር ነበር) እስካሁንም እርሱ የማይሳሳት ሰው ነው የምትሉ ከሆነ በከባድ ሁኔታ አእምሮዋችሁ ደንዝዟል ማለት ነው።
ስለ ደመናው በጣም ተሳስቷል። ስለዚህ እርሱ የተናገራቸውን ጥቅሶች አርሙና እለፉ።
7ቱ መላእክት ማርች 8 ቀን መጥተው እንደጎበኙት አውቋል። ከዚያ በኋላ ስለ አንድ ሚስጥራዊ ደመና ወሬ ሰማ። ደመናው ልዕለ ተፈጥሮአዊ መሆኑን በተረዳ ጊዜ ደመናው የተፈጠረው እርሱን ሊጎበኙ በመጡት 7 መላእክት ነው ብሎ አሰበ። ያላስተዋለው ነገር ቢኖር የደመናው መታየት እና የመላእክቱ ጉብኝት በተለያዩ ቀናት የሆኑ ክስተቶች እንደነበሩ ነው። ደግሞም ሁለት ደመናዎች እንደነበሩ አላወቀም፤ ሳይንቲስቶች ለዚህ ነው ትልቁን ደመና ሚስጥራዊ ደመና ያሉት። አንድ ሮኬት በከፍታ ላይ ሲፈነዳ አንድ ደመና ብቻ ነው መፍጠር የሚችለው።
ነብያት ስሕተት በመስራታቸው ሐሰተኛ ነብይ አይባሉም
እርሱም ሰው ስለሆነ ትልልቅ ስሕተቶችን ሰርቷል። ስለዚህ ስሕተት ሰርቶ የማያውቅ ሰው የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውርበት።
ወንድም ብራንሐምን የምናስታውሰው በዚህ ስሐተቱ ነው ወይስ በትክክል ገልጦ ባስተማራቸው በአስደናቂ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጦቹ?
አይንሽታይን አንድ ቀን ቤቱ ወዴት እንደሆነ ጠፋበትና የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እንዲያሳዩት ጠየቀ። የሚገርም ስሕተት። የስልክ ቁጥርህን ስጠን ሲሉት ጠፍቶበት የስልክ ማውጫ መዝገብ ውስጥ ፈትሾ አገኘው። ይህም የሚገርም ስሕተት ነው። እና አይንሽታይንን በነዚህ ስሕተቶቹ ነው የማስታውሰው ወይስ ስለ አንጻራዊነት ባረቀቀው አስደናቂ ንድፈ ሃሳቡ? ሬሌቲቪቲ ንድፈ ሃሳብ ጂፒኤስ እንዲሰራ ለማድረግና ከዚህ በፊት ሄጄ የማላውቅባቸውን ቦታዎች ፈልጌ በቀላሉ ማግኘት እንድችል ይጠቅመኛል። አይንሽታይን ለራሱ የቤቱ አቅጣጫ ጠፍቶበታል፤ እርሱ የፈጠረው የጂፒኤስ ንድፈ ሃሳብ ግን እኔ እና ብዙ ቢሊዮን ሰዎች በጉዞ ላይ አቅጣጫ እንዳይጠፋብን ይረዳናል። ስለዚህ አይንሽታይንን ስለ ትልቅ ሳይንሳዊ እውቀቱ እና ፈጠራው በፍቅር ነው የማስታውሰው። ደግሞም እርሱ የፈጠረው የሌሰር ቴክኖሎጂ ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ሰዎች እቃ ገዝተው የእቃዎችን ዋጋ ለመክፈል ተሰልፈው ረጅም ጊዜ እንዳያቃጥሉ ባርኮድ በማንበብ ስራ ማፋጠን የሚችል ማሽን ፈጥሯል። ደግሞም እርሱ የፈጠረው ሌሰር ቴክኖሎጂ የዓይን ቀዶ ሕክምና እንዲሻሻል በማድረጉ ዓይናችን የተሻለ ማየት እንዲችል ረድቶናል።
ይህም ወንድም ብራንሐምን ያስታውሰኛል። በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያመጣው መገለጥ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ከበፊቱ ይበልጥ ማስተዋል እንድችል ረድቶኛል። በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያሉትን ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት እና ሌሎችንም ትልልቅ እውነታዎች እንዳውቅ ረድቶኛል። ከዚያም በኋላ ዝርዝር ጉዳዮችን ለምሳሌ ከሰባቱ ከተሞች ስድስቱ በመጀመሪያው ስማቸው የሚጠሩ መሆናቸውን እንዳይ አስችሎኛል። ከነዚህ ከመተሞች አንዷ ጴርጋሞን የምትባለው ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግሪክኛ ስሟ ነው የምትጠራው። ለምን?
ይህም እርሱ ለተሰጠው መንፈሳዊ የንስር ዓይን ሁነኛ ምሳሌ ነው። የእግዚአብሔርን ትልቅ ዕቅድ በስፋት እየተመለከተ በዚያም ውስጥ ጥቃቅን ዝርዝሮችን ሳያይ አያልፍም።
ወንድም ብራንሐም ብዙ የእግዚአብሔርን ቃል ስላስተማረኝ ባለ ውለታዬ ነው። ኢየሱስ በውሃ ላይ መራመዱን ሉቃስ ለምን እንዳልጠቀሰ፤ ማቴዎስ ኢየሱስ ወደ ሰማይ መሄዱን ለምን እንዳልጻፈ፤ ወይም እልሳእ ለምን 42 ልጆችን በእግዚአብሔር ስም እንደረገመ የትኛዋም ሌላ ቤተክርስቲያን ልታስተምረኝ አትችልም። ለእኔ ወንድም ብራንሐም የዘመናችን መንፈሳዊ አይንሽታይን ወይም ሊቅ ነው። እና እርሱ ስሕተት ቢሰራስ።
ጌታን ተቀብዬ ከዳንኩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አብርሃም ወደ ሃጋር በመግባት ትልቅ ስሕተት መስራቱን አነበብኩ። በአብርሃም ላይ በመፍረድ ፈንታ እፎይ ብዬ ተነፈስኩ። እንደ አብርሃም ያለ ታላቅ ሰው ትልቅ ስሕተት ሊሰራ ከቻለ እኔም ስሕተቶች ብሰራ እንኳ መንግስተ ሰማያት መግባት እንደምችል ተረዳሁ። ሰዎች ይሳሳታሉ። ኢየሱስ አንድም ስሕተት አይሰራም። ስለዚህ ትኩረቴን ከሰዎች ላይ አንስቼ በኢየሱስ ላይ አደርጋለው። ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስን ለእኛ ለመግለጥ በሰው ይጠቀማል። ይህ ግን እንዲገልጥልን የተላከውን ሰው ከፍ ከፍ አድርገን ዓይናችንን ከኢየሱስ ላይ እንድናነሳ ማለት አይደለም።
ስለ ምን እያወራን እንደሆነ ካወቅን ስሕተቶቻችንን ማረም እንችላለን። ከዚያ በኋላ በትክክል ያስተማረንን ትምሕርት ይዘን እንቀጥላለን። ነገር ግን ወንድም ብረንሐም አይሳሳትም እንደሚሉት ዓይነት የሜሴጅ ሰባኪዎች ከሆቻችሁ ስሕተቶቻችሁን ማረም አትችሉም። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች የወንድም ብራንሐምን ስሕተት ስሕተት አይደለም ለማለት ብለው በንግግሩ ዙርያ ሐሰተኛ ዜናዎች ፈጥረው ያወራሉ። ይህ አሳዛኝ ቀልድ ነው።
እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የወንድም ብራንሐም ጥቅሶችን ብታሳዩዋቸው ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም ለማለት የሚሉ ሰዎች በራሳቸው ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ተጠምደው ይቀራሉ። ማሳመን የሚችሉት ከማንም ጋር እንዳይነጋገሩ ብለው ያደነዘዙዋቸውን ሰዎች ብቻ ነው። ሰዎች ለፓስተሮቻቸው መሃይምነት እና ስሕተት ባሪያ ይሆናሉ።
በአእምሮዋቸው ሰነፍ የሆኑ ሰዎች ከተረጋገጡ እውነታዎች ይልቅ ለእነርሱ እንዲመቹ ተደርገው የተፈጠሩ ልቦለዶችን ይመርጣሉ።
ከብዙ ሰዎች ጋር አብረን ስሕተት ውስጥ ስንገባ የራሳችንን ውድቀት እንዳናይ ያደርገናል። በእኔነት ትዕቢት የተሞላው አእምሮዋችን እና ከልኩ ያለፈው በራስ የመተማመን ስሜታችን “የተጣመሙ አመለካከቶች ሁሉ ምንጭ” ነው። ሁላችንም የእኛ ቤተክርስቲያን እውነትን በትክክል የያዘች አድርገን እናስባለን። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሁላችንንም ቤተክርስቲያኖች በአንድነት ያወግዛቸዋል። ስለ ዘመን መጨረሻ በተነገሩ ትንቢቶች እና ምሳሌዎች ውስጥ ስለ ቤተክርስቲያኖች አንድም መልካም ነገር አልተነገረም።
የክርስቶስን ልደት እንድናስብም ሆነ እንድናከብር አልታዘዝንም። ስለዚህ ሕዝቡ በሙሉ በአንድነት ሲስት ሁሉም ክሪስማስ አክባሪ ሆነ። ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ በዓል በማክበር ፕሮቴስታንቶች ወደ ጋለሞታይቱ እናታቸው ተመልሰዋል። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በቀላሉ ይስታሉ። ሰይጣን ከእኛ በላይ በጣም ብልጥ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ትተን መሄድ የለብንም።
ስሕተት የሚታረምበት መንገድ ተሳስቻለሁ ብሎ ማመን እና አልፎ መሄድ ብቻ ነው። ፓስተሮች ግን የቤተክርስቲያን ራስ የሆኑበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው አቋማቸው በሰው ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ብለው በግድ ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብለው ሰዎችን ያሳምናሉ። ከዚህም የተነሳ አለመግባባትና ግራ መጋባት እንደነገሱ ይቀጥላሉ።
ወንድም ብራንሐም የተሳሳተውን ስሕተት ትክክል ነው ብሎ መሟገት ከእርሱ ብዙ ሉጠቀሙ ለሚችሉ ሰዎች ምንም የማይጠቅማቸው እንዲሆን ያደርገዋል፤ ምክንያቱም የጠለቀ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የነበረው ሰው እርሱ ብቻ ነበር።
ብዙ ሰባኪዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙም አያውቁም። መጽፍ ቅዱስን ማጥናት ለእነርሱ ብዙ ከባድ ስራ ይሆንባቸዋል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጎን በመተው በሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ መከራከር ይወዳሉ። ይህም ቀለል ያለው አማራጭ ነው። የሰው ንግግር ጥቅሶች ውስጥ ፍጹም ስሕተት የለም ብለው እንዲያታልሏችሁ አትፍቀዱ።
ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና በተመለከተ ብዙ የተሳሳቱ እና እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ጥቅሶች አንብባችኋል።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ሰው አይደለም።
የወንድም ብራንሐም ስሕተቶች ፍጹም እውነቶች ናቸው ብሎ መናገር ሰዎች ግልጽ የሆነውን እውነታ ከመጋፈጥ ፈቀቅ ብለው ወደ ግራ መጋባትና ወደ ስንፍና እንዲሄዱ የሚያደርግ ቅዠት ነው። ይህ ዓይነቱ ቅዠት በምናባቸው የፈጠሩትን እውነታ የሚመስል ሕልም ሳይጠፋ እንዲቆይላቸው ይረዳቸዋል። ደግሞም ትክክለኛ እውነትን የሚያውቁ ሰዎችን እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል።
64-0614 ብቸኛው ኳስ
መልአኩ እንዲህ ብሎ ነው የነገረኝ፡- “ሕዝቡ እንዲያምኑህ አድርጋቸው።”
እኔም የእግዚአብሔርን ቃል ከተናገርኩ “እኔን እመኑኝ” አይደለም የምላችሁ “ቃሉን እመኑ” ነው እንጂ።
አንድ ነገር የተናገረው ወንድም ብራንሐም ስለሆነ ብላችሁ ማመን የለባችሁም። እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወስዶ መናገሩን በማወቅ ማመን ነው ከሁሉም የተሻለው ነገር።
64-0823 ጥያቄዎች እና መልሶች - 1
ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ግን እኔ ስለ ሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ነው የሚቀበሉት። ቃሉን በነጻነት የሚቀበሉት እነዚህ ሰዎች ቃሉ አስቀድሞ ስለተፈተነ ነው።
ወንድም ብራንሐም የመጣው ከእርሱ ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያብራሩ ነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተኩ አይደለም።
62-0318 የተነገረው ቃል የመጀመሪያው ዘር ነው - 2
ይህን ሁሉ ነገር ተናግረያለው፤ የተናገርኩትም ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይገጥም ከሆነ፣ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ካልተስማማ ስሕተት ነው።
65-0801 የዚህ ክፉ ዘመን አምላክ
… ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ለዚህ ዘመን ብሎ የሰጠኝን መልእክቱ ያመኑ ሰዎች አሁን ምን እየተፈጸመ እንዳለ ማስተዋል ይችላሉ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስም ጋር ማመሳከር ይችለሉ።
63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው
መልእክቱን በሙሉ እመኑ። እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ከሆነ ግን እንዳታምኑ።
60-0804 ንስር ጎጆዋን እንደምትበታትን
መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆኑን እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ የእኔ ድምጽ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ድምጽ የሚናገርበት እንጂ
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ ውስጥ ሲጠራቸው በግልጽ መስማት ይችላሉና
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
ዛሬ በዚህ ቀን የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ሲጠራችሁ አድምጡ።
62-1007 የበሩ ቁልፍ
አያችሁ ብዙ ነገር የሚያበላሽብን ይህ ነው። እኔ ሳልልካቸው እርሱ ልኮናል እያሉ አንዳንድ ወንድሞች ሄደው ሰዎች ሚስታቸውን መፍታት እና መንፈሳዊ የትዳር አጋራቸውን መፈለግ አለባቸው ብሎ አስተምሯል እያሉ ይሰብካሉ፤ ከዚያም ሌላ ደግሞ እኔ በፍጹም የማልሳሳት እንደሆንኩ። ከዚያም ሌላ ደግሞ… ወይ ሌላም በጣም ዘግናኝ ነገር ይናገራሉ።
ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ሰው ነው ብሎ መናገር ከባድ ስሕተት ነው።
በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ሐይማኖታዊ አሳሳች በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ እየጋለበ ሲያልፍ ፈገግ እያለ ይስቃል፤ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችም በሁሉ ነገር ትክክል የሆኑ ይመስላቸዋል።
ስለ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና በሚደረጉ ክርክሮች ውስጥ ሁልጊዜ ተረስቶ የሚቀረው ነገር ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ የታዩት ደመናዎች ሁለት እንደነበሩ ነው። በከፍታ ላይ የፈነዳ አንድ ሮኬት ትንሽዬ ደመና ፈጥሯል።
ወንድም ብራንሐም በጭስ ስለተፈጠረው ስለ ሁለተኛው ደመና ምንም አላወቀም።
እውነት ሁልጊዜ ብዙ ማስረጃዎች አሏት። እውነታ ውስብስብ ነገር ነው።