ራዕይ 6፡ ክፍል 1 – 7 የቤተክርስቲያን ዘመናት
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ይህ ምዕራፍ ለማጥናት ከባድ ነው ምክንያቱም በ7ቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያሉ ክፋቶችን ያጋልጣል። ሰዎች በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ያሉ ስሕተቶችን ይክዳሉ።
- የመጀመሪያዋን የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው መምሰል ያለብን
- የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር አልመጣም
- 7ቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አላሰሙም
- ወንድም ብራንሐም ፌብርዋሪ 28 ቀን 1963 የታየውን ደመና በተሳሳተ መንገድ ተረድቶታል
- ወንድም ብራንሐም የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሊገልጥ ነው የመጣው እንጂ ሊተካው አይደለም
- 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እጅግ በጣም እየተበላሸ ነው
- መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት ነው
- ሰባቱ ማሕተሞች የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ ነው
- ሁለት ሰዎች በሰማይ በአንድ ዙፋን መካከል ሊቀመጡ አይችሉም
- ሰባቱ ማሕተሞች ከመከፈታቸው በፊት በሰማይ የአንድ ነጎድጓድ ድምጽ መሰማት አለበት
- የራዕይ ምዕራፍ 6 የመጀመሪያዎቹ 7 ቁጥሮስ 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ
- በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቁ ችግር የሐይማኖት አሳችነት መሆኑን ኢየሱስ ተናግሯል
- ሁለተኛው የፖለቲካ ኃይል ማሕተም
- ሶስተኛው ማሕተም የትልቅ ንግድ አጋንንታዊ አሰራር በቤተክርስቲያን ውስጥ
- 4ኛው ማሕተም ሲከፈት ንስሩ ነብይ እና ታላቁ መከራ ውስጥ እየጋለበ የሚመጣው ሞት ይገለጣሉ
- ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው የተሳሳተው ስሕተት
የመጀመሪያዋን የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው መምሰል ያለብን
ራዕይ ምዕራፍ 1 ሰባት ቤተክርስቲያኖችን ያስተዋውቀናል፤ እነዚህም ቤተክርስቲያኖች በባህሪያቸው በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከነበሩት ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር በትክክል ይዛመዳሉ።
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በሐዋርያት ነው፤ እነርሱም እያንዳንዷን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሽማግሌዎች ነው አደራ የሰጧት። ከዚያም ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ አንድ ሰው ማለትም ጳጳስ የቤተክርስቲያንን አመራር ከሽማግሌዎች ነጥቆ ለብቻው ተቆጣጠረ። ይህ ቤተክርስቲያኖች ነጻ ከሆኑ ትንንሽ የቤተ ለቤት ሕብረቶች ወደ አንድ ትልቅ በሰው ሰራሽ ሕጎች የሚተዳደር ድርጅት እንዲያድጉ አደረገ። በ325 ዓ.ም ከተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ የስላሴ ትምሕርት ቤተክርስቲያን ላይ በግድ ተጫነ። እውነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ፈጽማ ልትጠፋ እስክትቃረብ ድረስ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ተጨመሩ። ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እውነት በተሃድሶ ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ተተረጎመ። ጆን ዌስሊ የቅድስናን ትምሕርት በተሃድሶ አመጣ፤ የወንጌል ስብከት ዘመንን አስጀመረ። አሜሪካ ውስጥ የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት መጣ፤ ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት ገለጠ፤ እነዚህም ሚስጥራት የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ይመልሷታል።
ከሰባቱ ቤተክርስቲያኖች መካከል ግን አንዷ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል የያዘች፤ ሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ይህችን ቤተክርስቲያን ሊከተሏት ይገባ ነበር። ይህች ቤተክርስቲያን ኤፌሶን ናት።
ራዕይ ምዕራፍ 2 በሐዋርያት የተመሰረተችዋን “የኤፌሶን” ቤተክርስቲያን ዘመንን ያስተዋውቀናል።
ይህች ቤተክርስቲያን “የቤተክርስቲያን ዘመን ምን መምሰል እንዳለበት” ማሳያ ናት።
ራዕይ 2፡1 በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
የዚህ የመጀመሪያው ዘመን ዋነኛው መልአክ (መልአክ ማለት መልእክተኛ ነው) ቅዱስ ጳውሎስ ነበረ። ጳውሎስ የአዲስ ኪዳንን ግማሹን ያህል ጽፏል፤ አዲስ ኪዳን ፍጹም እውነት ነው። ከውስጡ አንዳችም ነገር መለወጥ የለበትም።
ይህም የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ዘመን ነበረ።
ስለዚህ ልብ በሉ። ሰይጣን የመጀመሪያ ስራው ፍጹም ትክክለኛ ትርጉም በሆነው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት ተገኘ ብሎ ማውራት ነው።
ቀጣዩ የማሳሳት ዘመቻ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን በዊልያም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች መተካት ነው። “ብራንሐም እንዲህ ብሏል” የሚለው ንግግር “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል…” የሚለውን ይተካዋል።
አዲስ የመጣው ማሳሳቻ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ የሚሉ የሜሴጅ ሰዎች ናቸው፤ በሜሴጅ ውስጥ (በወንድም ብራንም መልእክት ውስጥ) ግን ምንም ስሕተት የለም ይላሉ። ይህ ፈጽሞ የእውነታው ግልባጭ ነው። የወንድም ብራንሐም መልእክቶች ውስጥ ስሕተቶች ታገኛላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን አንድም ስሕተት አታገኙም።
የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር አልመጣም
ከዚህም የባሰው ችግር ደግሞ የሜሴጅ ሰዎች እርሱ የተናገረው ቃል ጠቅሰው አጣመው መተርጎማቸው ነው፤ ከዚህም ጠማማ አተረጓጓም ወንድም ብራንሐም ያልተናገራቸው ቃልት መጥተዋል፤ ለምሳሌ፡-
“የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ ሳለ መጥቷል”። ስለዚህ ራዕይ ምዕራፍ 10 ተፈጽሟል።
ወንድም ብራንሐም በ1964 ምን እንዳለ ተመልከቱ። ያ ብርቱ መልአክ ገና ወደፊት በትንሳኤ ሰዓት እንደሚመጣ ነበር የተናገረው።
64-0119 ሻሎም
ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።”
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”።
ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
7ቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አላሰሙም
“7ቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል”።
ወንድም ብራንሐም እንዲህ ብሎ ተናግሮ አያውቅም።
ነጎድጓዶቹ ቃላቸውን የሚያሰሙት ለሙሽራይቱ ነው፤ ይኸውም ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ የምትነጠቅበትን እምነት ማግኘት እንድትችል ነው። ደግሞም ወደፊት ለኤልያስ እና ለሙሴም ድምጻቸውን ያሰማሉ፤ ለኤልያስም ድምጻቸውን የሚያሰሙት ኤልያስ ዝናብን ለሶስት ዓመት ከግማሽ የሚያስቆምበት ኃይል እንዲያገኝ ነው።
63-0321 አራተኛው ማሕተም
ትናንትና ማታ ትልቅ ሰይፉን ይዞ ለመግደል ሲመጣ አግኝተነው ነበር። ነገር ግን እርሱ እራሱ በሰይፍ እንደሚገደል አይተናል፤ ይህም የቃሉ ሰይፍ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፤ በሁለት ወገን የተሳለው ሰይፍ ይገድለዋል፤ ያጋድመዋል። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋር የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን በተናገሩ ጊዜ እጅግ ታላቅ ኃይል ይለቃሉ። አዲስ የማይሞት አካል እንዴት እንደምትቀበሉ ያሳዩዋችኋል።
“ምሕረት አብቅቷል”።
1965 የሎዶቅያውያን ቤተከርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9
የእግዚአብሔር ምሕርት አሁን ባለበት ዘመን ውስጥ ሙሉ ሕይወታችሁን ምንም ሳትሰስቱ ለኢየሱስ ክርስቶስ እንድትሰጡ እለምናችኋለው፤ እርሱም ታማኝ እረኛ እንደ መሆኑ መጠን ያድናችኋል፤ ይንከባከባችኋል፤ ያለ ነቀፋ በታላቅ ደስታ እና በክብር በፊቱ ያቆማችኋል።
ወንድም ብራንሐም ፌብርዋሪ 28 ቀን 1963 የታየውን ደመና በተሳሳተ መንገድ ተረድቶታል
ወይም ከዚህም ይበልጥ የከፋው ስሕተት የሜሴጅ ሰዎች ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት መሆኑን ለማሳየት ብለው የወንድም ብራንሐም ስሕተቶች ስሕተት እንዳልሆኑ እና ትክክል እንደሆኑ ለማሳየት የሚያደርጉት ሙከራ ነው። ይህም ድርጊት ማስተዋል ያላቸው ሰዎች ከእነርሱ እንዲርቁ ያደርጋል። የሚያስተውሉ ሰዎች እውነት የሚገኝበት መንገድ አንዳንድ ስሕተቶችን በማመን ነው ብለው አያምኑም።
አንዱ ታላቅ ስሕተት ወንድም ብራንሐም ማርች 8 ቀን 1963 ሳንሴት ፒክ የተባለ አካባቢ ለአደን በወጣበት ዕለት ከልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ስር ቆሞ እንደነበረ ማሰቡ ነው። ደመናው ከእርሱ ተለይተው በሄዱት 7 መላእክት የተፈጠረ መሰለው። ደመናው ከዚያን ዕለት 8 ቀናት ቀድሞ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከሳንሴት ፒክ በስተ ሰሜን 200 ማይልስ ርቃ ከምትገኘው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ሰሜን ለ28 ደቂቃ ታይቶ ፎቶግራፍ እንደተነሳ አላወቀም። ደመናው ሲመጣ እርሱ በዕለቱም በቦታውም አልነበረም።
እውነታውን እናጣራ። የአደን ወቅት የተከፈተው ማርች 1 ቀን ነው። ደመናው ወደ ሳንሴት ፒክ አልመጣም። 7ቱ መላእክት ማርች 8 ቀን ወደ ሳንሴት ፒክ መጥተው በጎበኙት ጊዜ ምንም ደመና አልሰሩም።
ስለዚህ የሜሴጅ ሰባኪዎች እውነትን በሐሰተኛ ዜና ጉም ጠቅልለው ነው የሚያቀርቡት። ወንድም ብረንሐም ስለ ደመናው በተሳሳተበት ጉዳይ ላይ ነው የእነርሱ ትኩረት። ሊያፍሩ ይገባቸዋል። መቸም ሰነፎቹን ቆነጃጅት የሚያታልላቸው አንደ ሰው መኖር አለበት። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች መታለል ይፈልጋሉ፤ እንደውም የመታለልን ዕድል ለማግኘት ብለው ገንዘብ ይከፍላሉ።
ወንድም ብራንሐም የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሊገልጥ ነው የመጣው እንጂ ሊተካው አይደለም
ገላትያ 1፡9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
በዚህ ዘመን የሚመጣው እርግማን በታላቁ መከራ ውስጥ ከሚፈነዳው ኑክሊየር ሚሳኤል የሚወጣው ጨረር ሳይጠፋ ለረጅም ጊዜ መቆየቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር የምታምኑ ከሆነ ታላቁ መከራ ውስጥ ትገባላችሁ። ስለምናምነው ነገር በጣም መጠንቀቅ አለብን።
ሐዋርያት ሁሉ ከምድር ከተሰናበቱ በኋላ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመከተል መጽናት ነበረባት።
ሐዋርያው ዮሐንስ 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሰብስቦ ጠረዛቸውና በእነርሱ ላይ አንዳችም እንዳንጨምር አስጠነቀቀን። አትጨምሩባቸው፤ ከተጻፉትም ላይ አንዳች አታጉድሉ። አዲስ ኪዳን ምንም ስሕተት የሌለው ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ዮሐንስ ያስተላለፈውን ይህንን ትዕዛዝ ባለመስማት የሜሴጅ ሰባኪዎች ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው በማለት የራሳቸውን ሃሳብ ጨምረዋል (አዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሐየርን ድምጽ የመስማት ተስፋ አልተሰጠንም)፤ የሜሴጅ ሰባኪዎች ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ያሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሱ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ እና በዙፋኑ ዙርያ ካሉት ከአራቱ እንስሳት መካከል የአራተኛው የንስሩ ድምጽ ነው ስለሚል ነው።
ክርስቲያኖች የአዲስ ኪዳን አማኞች መሆን አለባቸው፤ አዲስ ኪዳንም የተጻፈው በብሉይ ኪዳን ላይ ተመስርቶ ነው።
የጥንቶቹ ሐዋርያት የጻፉትን ማንም ሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ መለወጥ አይችልም።
ኤፌሶን 2፡20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
መሰረታዊ እምነቶቻችን ወደ ኢየሱስ የሚያመለክቱ መሆን አለባቸው እንጂ ወደ ዊልያም ብራንሐም የሚያመለክቱ መሆን የለባቸውም። እርሱ በኢየሱስ ቀኝ እጅ ውስጥ የተያዘ ኮከብ ነው። ኮከብ አስተዋይ ሰዎችን በቃሉ አማካኝነት ወደ ኢየሱስ መገለጥ ይመራቸዋል፤ ፀሃይ ከወጣች በኋላ ግን ከዋክብት ደብዝዘው ይጠፋሉ።
ኮከቡ ፀሃይን ሊተካት አይችልም።
ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንችል ዘንድ የሚረዱንን ሚስጥራት ሊገልጥ ነው የመጣው።
ራዕይ 22፡18 በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
እነዚህ መቅሰፍቶች የሚመጡት በታላቁ መከራ ውስጥ ነው። የቀደመው እባብ አሉታዊ ቃልን ጨመረና “አትሞቱም” አለ።
ሔዋን ሞተች፤ እባቡም እግር የሌለው መርዘኛ እንስሳ ሆኖ ተለወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳች መጨመር አደጋ አለው።
19 ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ መጨመርም ሆነ ከቃሉ አንዳች ማጉደል ሁልጊዜም ቢሆን ስሕተት ነው።
ዘዳግም 4፡2 እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም።
አይሁዶች መጽሐፍ ቅዱስን ልክ እንደተጻፈው መታዘዝ ነበረባቸው። ቤተክርስቲያንም መጽሐፍ ቅዱስን ሳትጨምርበት ሳትቀንስበት መታዘዝ አለባት።
ዘዳግም 12፡32 እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል።
ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ ክስተቶች ራሳቸውን የመድገም ባህሪ አላቸው። ስለ ወደፊቱ እንድናውቅ ካለፈው መማር አለብን።
በቀጣዮቹ አምስት ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የተፈጸሙ ነገሮች ሁሉ ከእነርሱ ጋር በሚዛመዱ አምስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ይፈጸማሉ። (ሎዶቅያ ከእነዚህ ሁሉ ተለይታለች ምክንያቱም ይህች የቤተክርስቲያን ዘመን በክርስቶስ ላይ ያመጸች እና ብዙ ነገሮች ያበላሸች ናት። ይህን በተመለከተ ለብቻ ጥናት እናደርጋለን)።
ከኤፌሶን ቤተክርስቲያን የሚቀጥሉት አምስት የቤተክርስቲያን ዘመናት የየራሳቸው ችግሮች አሉዋቸው፤ እነዚሀም በራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ እንደተገለጸው እውነት ከመካከላቸው መጥፋቷ ወይም በራዕይ ምዕራፍ 3 እንደተገለጸው እውነት በተሃድሶ ዘመን ወደ ቤተክርስቲያን በከፊል መመለሷ ነው።
ራዕይ 2፡8 በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡-
“በሰምርኔስ” ማለት አንድ ጳጳስ ሰው ሆኖ ሳለ በሐሰት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ብሎ ራሱን ከፍ ባደረገበት ዘመን ማለት ነው። ከዚያ በኋላ የስልጣን ጥማቱ አድጎ በአንድ ከተማ ውስጥ ላሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ራስ ነኝ አለ። ስለዚህ ከ150 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ሰው ብቻውን የሮም ጳጳስ ሆነ።
ራዕይ 2፡12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
“በጴርጋሞን” ማለት በ325 ዓ.ም የኒቅያ ጉባኤ አረማዊውን ስላሴ እውነተኛ አምላክ ብሎ ያስተማረበትና የእግዚአብሔርም ስም የጠፋበት ጊዜ ነው ምክንያቱም ለሶስት አካላት አንድ ስም መስጠት አይቻልም። በዚያ ዘመን እውነት እየደበዘዘች ሄደች። ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው የተባለበት ዘመን ስለነበረ ራስ ተብሎ የተሾመው ጳጳስ ስሕተቶቹን በቤተክርስቲያን ላይ መጫን ይችላል። ልዩ ልዩ ጳጳሳት ልዩ ልዩ ሃሳቦች ነበሩዋቸው።
ራዕይ 2፡18 በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
“በትያጥሮን”። ምዕራፍ 4። አራት ማለት የ7 መካከለኛ ቁጥር ነው። ይህም በመካከለኛው ዘመን ውስጥ ወይም በጨለማው ዘመን ማለት ነው። ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ማለት ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን ጨቁና ተቆጣጥራለች። በዚያ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፈጽሞ ሊጠፋ ትንሽ ብቻ ነበር የቀረው።
የአይሁዶች ቤተመቅደስ ውስጥ በነበረው መቅረዝ ላይ ያሉት የመጀመሪያዎቹ አራት መብራቶች እውነት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በሐዋርያት ተተክላ እንዴት እንደ ጸናች ያመለክታሉ፤ ከዚያ በኋላ ግን እውነት በቤተክርስቲያን መሪዎች አመለካከት አና በአረማውያን ልማዶች እየተተካች ሄደች። በ4ኛው ቤተክርስቲያን ዘመን እውነት ሙሉ በሙሉ ጠፍታለች ማለት ይቻላል።
ኋላም ቤተክርስቲያን ከሐዋርያት የአዲስ ኪዳን እምነት እየራቀች ሄዳለች።
ቀጥሎ ራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ የእውነት ተሃድሶ ተጀመረ።
ራዕይ 3፡1 በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ብቻ የሚለውን እውነት በተሃድሶ አመጣ።
ከዚያ ቀጥሎ እንግሊዝ ውስጥ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ተተረጎመ።
ራዕይ 3፡7 በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
እንግሊዝ ውስጥ 6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲደርስ ጆን ዌስሊ የቅድስናን ትምሕርት በተሃድሶ ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ፤ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭትም በዊልያም ኬሪ አማካኝነት ተጀመረ፤ ዊልያም ኬሪ ከእንግሊዝ ወጥቶ ሕንድ በመሄድ በዚያ የወንጌልን ስራ ሰራ።
አሜሪካ ውስጥ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሎሳንጀለስ ውስጥ በአዙዛ እስትሪት ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት ተጀመረ፤ ይህንን መነቃቃት ተከትሎ ከ1947-1965 የትምሕርት ዝናብ ሲመጣ ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጦ አስተማረ። ይህ ሁሉ የተደረገው በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ነው።
ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ለዳንኤል ቃል ገብቶለታል።
ዳንኤል 12፡4 ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤
በሌላ አነጋገር በመጨረሻው ሰዓት እግዚአብሔር ለብዙ ዘመናት ለሰው አእምሮ ሚስጥር ሆነው ለመፍታት ያስቸገሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተምሳሌቶችን ለሰዎች ይገልጣል ማለት ነው።
ሕያው መሆን ማለት የጥንቶቹ ሐዋርያት ወደሚያምኑት እምነት መመለስ ነው።
ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።
የመጀመሪያው እና 7ኛው ወይም የመጨረሻው ዘመን ቦታቸውን ይለዋወጣሉ።
ደግሞም እጅግ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ አንዱን ስናይ ሌላኛውን መስሎን እስክንሳሳት መድረስ አለባቸው፤ ምክንያቱም በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የቤተክርስቲያን ታሪክ መጨረሻ ላይ የሚመጡ ልጆች የአዲስ ኪዳንን ቤተክርስቲያን ወደመሰረቷት ወደ ጥንት ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ አለባቸው።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር ዋነኛ ሃሳቡ እኛን ወደ መመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን ሊመልሰን ነው።
የእኛም አቅጣጫ እና ትኩረታችን መሆን ያለበት ይህ ነው ምክንያቱም የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እናት ቤተክርስቲያናችን ናት።
ነገር ግን አሁን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እየተመለስን አይደለንም።
7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እጅግ በጣም እየተበላሸ ነው
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች እግዚአብሔርን በፈለግነው መንገድ ማምለክ መብታችን ነው የሚል ጥያቄ አነሱ።
“የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” “በሕዝቡ መብት” ጥያቄ በመጥለቅለቋ የተነሳ በዘመናችን ብዙዎቹ ቤተክርስቲያኖች ፍላጎታቸው እግዚአብሔርን ደስ ባላቸው መንገድ ማምለክ ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡ የሚፈልጉትን መስማት አለበት ይላሉ። ሰዎች ለራሳቸው በመረጡት መንገድ ሲያመልኩት እግዚአብሔር ደስ መሰኘት አለበት። ራሳቸውን የሚያስደስታቸውን የሚመቻቸውን እምነት በራሳቸው ይፈጥራሉ።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ቤተክርስቲያኒቱ “የ ሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሆናለች”። የሕዝቡ ቤተክርስቲያን። የሕዝቡ መብት ቤተክርስቲያን (ሎዶቅያ ማለት መብት ነው)። የሰብዓዊ መብቶች እና የግብረ ሰዶማውያን መብቶች ቤተክርስቲያን። ጽንስ የማስወረድ መብት። የሴቶች መብት። ጾታቸውን የሚቀይሩ ሰዎች መብት። እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች መብት። የፓስተሮች አስራት የመሰብሰብ መብት። ሰው የቤተክርስቲያን ራስ የሚሆንበት መብት። የቤተክርስቲያን ራስ የሆነ ሰው አመለካከቱን የሚቃወሙትን ሰዎች ሁሉ የማባረር መብት።
መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ሁሉ በተመለከተ አስጠንቅቋል።
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
የዘመን መጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጦች ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ ሙሉ በሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታይ እንዲሆኑ እና ወደ መጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እንዲመለሱ ያስችሏቸዋል።
ቤተክርስቲያኖች በሙሉ በሰባኪዎች እየተመሩ ከአመለካከቶቻቸው እና ልዩ ልዩ ልማዶቻቸው አንጻር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወዳልሆኑ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ይሄዳሉ።
ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
ቤተክርስቲያኖችን፣ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችን፣ እና የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ በአሁኑ ሰዓት ዋነኛው የሚያንቀሳቅሳቸው ኃይል ወደ ሮማ ካቶሊክ እናት ቤተክርስቲያን ለመመለስ የጀመሩት ጊዜ ነው።
በነጩ ፈረስ ጋላቢ እየተነዳ የሚሄደው የዘመኑ መንፈስ ነው በአዳዲስ እና በተሻሻሉ ሐይማኖታዊ አሳሳች መንገዶች እየተገለጠ ሕዝብን የሚያስተው።
ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እየጎደላቸው ስለሚሄዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን ማመን ይቀጥላሉ።
ወንድም ብራንሐምን እንከተላለን እያሉ እርሱ የተናገራቸውን ቃሎች ወስዶ አጣሞ በመተርጎም ሰዎች ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ ከማድረ የበለጥ አሳሳችነት የለም።
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ የሐዋርያት ሥራ ውስጥ ያለችዋን ቤተክርስቲያን ለመምሰል ትሞክራለች። ይህ ነው እውነቱ። ነገር ግን በመጨረሻው ቀን ጌታ ከመገለጡ በፊት ጨለማ ሙሉ በሙሉ እስኪውጥ ድረስ ከፍተኛ የስሕተት ወረራ እንዲመጣ ከቃሉ ተረድተናል።
ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።
ለምንድነው ብዙዎች ተጠርተው ነገር ግን ትቂቶች ብቻ የተመረጡት?
ቀጣዩ ስዕል የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የአብዛኞቹ ሰዎች አመለካከት ምን እንደሚመስል ያሳያል። ሰነፎቹ ቆነጃጅት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር አንብበው መረዳት አይችሉም።
ቆነጃጅት ማለት ክርስቲያኖችን የሚወክሉ ንጹህ ሴቶች ናቸው።
ነገር ግን እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አይችሉም።
ስለዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየጨመረ ከመሄድ ይልቅ እየጠፋ ይሄዳል።
የቤተክርስቲያን መሪዎችን ገቢ እና በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ስልጣን ለማስጠበቅ ተግተው የሚዋጉ አምባገነን ሐይማኖታዊ መናፍስት አሉ። ይህን ለማድረግ በጉን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ይዋጉታል። ከመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ ወጥተው ይሄዳሉ። ብዙዎቹን እምነቶቻቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አይችሉም።
ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑን ማሳየት አይችሉም።
ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ አስራትን ሁሉ የሚሰበስበው ይህ የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው አንድ ሰው መሆኑን ማሳየት አይችሉም።
ራዕይ 17፡14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
ብዙዎች ተጠርተዋል፤ ጥቂቶች ተመርጠዋል ምክንያቱም ጥቂቶች ብቻ ናቸው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥሪያቸው ጸንተው የቆዩ።
ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ጠርቷችሁ ከሆነ ሁልጊዜ ለተጻፈው ቃል ታማኝ ሆናችሁ ትኖራላችሁ።
የጠራቻችሁ ቤተክርስቲያን ከሆነች ለጠራቻችሁ ቤተክርስቲያን ታማኝ ሆናችሁ ትኖራላችሁ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን ታምናላችሁ ምክንያቱም ዋነኛው መመሪያችሁ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም።
ታማኝነታችሁ ለቤተክርስቲያን ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት እና እርስ በርሱ የሚጋጭ ሃሳብ አለ ትላላችሁ። ነገር ግን ከቤተክርስቲያናችሁ ወይም ከቤተክርስቲያናችሁ መሪ ጋር ለመቃረን ወኔ አይኖራችሁም። የሰዎችን አእምሮ ለመቆጣጠር የተጀመረው ጦርነት ይህ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት ነው
የዘመናችን የቤተክርስቲያን ፕሮፓጋንዳ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት አይደለም ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ፍጹም የማይሳሳት ሰው ነው የሚል ነው።
ሙሽራይቱ ማንም ሰው የሚናገረው ነገር አይገርማትም። ሙሽራይቱ የምትፈልገው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለማየት ብቻ ነው።
የሙሽራይቱ አካላት የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችውን ማመን ብቻ ነው የምትፈልገው።
መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ እንደምንሰማ ቃል ገብቶልናል። ይህም ድምጽ በቴፕ ተቀርጾ የተቀመጠው የወንድም ብራንሐም ስብከት ነው።
አዲስ ኪዳን በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔርን ድምጽ ትሰማላችሁ አላለንም። የእግዚአብሔርን ድምጽ ትሰማላችሁ የሚለን መጽሐፍ ቅዱስን የማይመረምሩትን ሰነፎቹን ቆነጃጅት ለማሳት የተለቀቀ ሐሰተኛ ዜና ነው። የብሉይ ኪዳን ነብያት እራሳቸውን የእግዚአብሔር ድምጽ ብለው መጥራት ይችላሉ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰብኩ እና እንዲጽፉ ተልከው ነበር።
ነገር ግን ሐዋርያው ዮሐንስ የመጨረሻውን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ከጻፈ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ድምጽ። መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ተጠናቅቋል። ማንም ሰው ምንም ሊጨምርበት አይችልም።
ድምጻችሁ ሃሰባችሁን ይገልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሃሳብ ምን እንደሆነ የሚነግረን ድምጽ ነው።
60-0804 ንስሯ ጎጆዋን ትበታትነዋለች
መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆኑን እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የኔ ድምጽ አይደለም የሚናገረው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው እንጂ።
የመላእክት አለቃ ድምጽ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ሙታን እንደሚያስነሳ ቃል ተገብቶልናል። ይህ ግን እስካሁን ገና አልተፈጸመም። ስለዚህ ለዚያ ቀን ነው መዘጋጀት እና መጠባበቅ ያለብን።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ የእኛ እና የእነርሱ እምነት አንድ ሆኖ ይገኝ ይሆን?
ዘሩ በመከር የሚሰበሰበው ከሰብሉ ላይ በሚታጨድበት ጊዜ ነው።
የመከር ዝናብ የሚያበቃው ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከምድር በምትነጠቅበት ጊዜ ነው።
በመጨረሻ በመከር ታጭዶ የሚሰበሰበው ዘር በመጀመሪያ በሐዋርያት ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
በ7ኛው መልአክ ድምጽ የእግዚአብሔር ሚስጥር ማለትም ቃሉ ይፈጸማል።
“ይፈጸማል” የሚለው ቃል ውስጡ የማመንታት ድምጸት አለው። ቤተክርስቲያኖች ቸልተኛ እየሆኑ ሄዱ። የሰሙትን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ማጽናት ትተዋል። የሰውን ንግግር ወስደው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሃሳቦች ይተረጉማሉ፤ ከዚህም የተነሳ የሚያምኑትን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመው ማብራራት እስከማይችሉ ደርሰዋል።
በዚህ መንገድ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው ሄደዋል።
ዮሐንስ 1፡1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር መረዳት እንድንችል የሰባተኛው መልአክ ድምጽ (የንግግሩ ጥቅስ) መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ በአንድ ተፈትሾ መታየት አለበት። እርስ በርስ ተያያዥ የሆኑ ጥቅሶችን አያይዞ ማጥናት መጽሐፍ ቅዱስ እራሱን በራሱ እንዲተረጉምልን ያደርጋል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ኤልያስ አዲስ አስተምሕሮ ይዞ አይመጣም። ኤልያስ በጨለማው ዘመን ውስጥ የጠፋውን የመጀመሪያዎቹን ሐዋርያት ትምሕርት ይዞ ነው የሚመጣው።
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ … የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ከፊታችን ክፉ ቀን እየመጣ ነው። እርሱም ታላቁ መከራ ነው። ከምድር ላይ ሳይጠፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆየው የኑክሊየር ቦምብ እና የሚሳኤል ጨረር እርግማን አፈር ውስጥ ስለሚቀር ምንም እንዳይበቅል ያደርጋል።
የመጨረሻው ዘመን ልጆች ልብ ሐዋርያት ወደ ጻፉት ቃል መመለስ አለበት።
ልብ ማለት የሙሽራይቱ ፍላጎቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው ማለት ነው።
አሳማኝ ጥበብ የሚመስሉ ሰው ሰራሽ አመለካከቶችን አይፈልጉም። የሙሽራይቱ አካላት ማመን የሚፈልጉት ሐዋርያቱ ያመኑትን ብቻ ነው።
ሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ለመረዳት ሞክረው አያውቁም፤ ለምሳሌ 7ቱ ነጎድጓዶች፣ የጌታን መምጣት የሚያመለክተው 7ኛው ማሕተም፤ የጌታ መምጣት እና የኢየሱስ አዲስ ስም በዓለም ውስጥ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ ታላቅ ሚስጥራት ናቸው።
ራዕይ 19፡12 … ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
ቤርያ ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ጳውሎስ የሰበከው ስብከት እውነት ይሆን ብለው ለማረጋገጥ መጽሐፍ ቅዱስን ይመረምሩ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጳውሎስ የተናገረው ቃል እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትመረምር ነበር።
ዛሬ የሜሴጅ ሰባኪዎች የወንድም ብራንሐምን ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ መመርመር እና እርሱን ማረም ሐጥያት ነው ይላሉ።
ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ስለሆነ አይሳሳትም ይላሉ።
አንድ ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን መርምሮ ለማየት መፍራት ስውር ነገር ግን አደገኛ የሆነ የስሕተት መንፈስ ሾልኮ ገብቷል ማለት ነው።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
በመጨረሻ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የሚረዱት። እምነት የሚመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጋችሁ ማግኘት የማትችሉትን ጥቅስ እንደ ገደል ማሚቶ መድገም ንስር አያደርጋችሁም።
ሰባቱ ማሕተሞች የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ ነው
ይህንን ማስታወስ አስፈላጊ ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ዮሐንስ ወደ ላይ ተጠርቶ ይወጣል።
ራዕይ 4፡1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።
2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ዮሐንስ እንደ አንድ ግለሰብ የሙሽራዋን መነጠቅ የሚወክል ተምሳሌት ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ ንጥቀት ይባላል።
“ከዚያ በኋላም”። ከምን በኋላ? በምዕራፍ 2 እና 3 ከተገለጹት ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ።
የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መቋጫ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ የሚወስዳት ንጥቀት ነው።
በዙፋን ላይ ያለው አንድ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ስላሴ የለም።
ራዕይ 4፡6 … በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
ዓይኖች የሚወክሉት ማስተዋልን ነው። “በፊት በኩል ያሉ ዓይኖች” ማለት የወደፊተን ዘመን ያውቃሉ ማለት ነው። “በኋላ በኩል ያሉ ዓይኖች” ደግሞ ያለፈውን ዘመን ያውቃሉ። እጅግ አስተዋይ ስለሆኑ ሊታለሉ አይችሉም። ማስተዋላቸው ነው በሰማይ ዙፋን ውስጥ የሚያኖራቸው።
እውነተኛ ማስተዋል ሊኖረን የሚችለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሕብረት የምናደርግ ከሆነ ነው። ከመታለል ልንተርፍ የምንችለው ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን በመከተል ብቻ ነው።
ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
ዮሐንስ በዙፋን ላይ ያየው አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ነው፤ በዙፋኑ ዙርያ ደግሞ አራት እንስሳትን አይቷል፤ እነዚህ አራት እንስሳት ሃላፊነታቸው በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ለቤተክርስቲያን ጥበቃ ማድረግ ነው።
አንበሳው እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስን ያመኑትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል። ኢየሱስ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው።
1,200 ዓመታት በፈጀው በጨለማው ዘመን በ325 ዓ.ም በተደረገው በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ስላሴ ወደ ቤተክርስቲያን በመግባቱ የተነሳ እውነት ደብዝዛ በጠፋችበት በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጥጃው አድጎ ብርቱ በሬ ሆነ። በሬ ለመታረድ የተፈጠረ እንስሳ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፈጽሞ ሊጠፋ በተቃረበበት በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ አስረ ሚሊዮን የሚሆኑ ክርስቲያኖች በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ተገድለዋል።
ከአራቱ እንስሳት አንዱ የሆነው ሰው የተሃድሶ መሪዎችን ጥበብ ይወክላል። በአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ነው የሚለውን እውነት በተሃድሶ ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ። ፍጹም ስሕተት የሌለበት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንግሊዝ ውስጥ ተተረጎመ። ደግሞም እንግሊዝ ውስጥ በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጆን ዌስሊ የቅድስናን ትምሕርት መለሰ፤ ዊልያም ኬሪ ታላቁን የወንጌል ስብከት ዘመን ለመጀመር ወደ ሕንድ ሄደ።
ንስሩ በ7ቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ዝርዝር ጉዳዮችን በሙሉ አጥርቶ ማየት የሚችልበት አስደናቂ ዓይን አለው። ይህም አስደናቂ እይታው በዊልያም ብራንሐም አገልግሎት አማካኝነት ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት እንዲገለጡልን አስችሏል። ነገር ግን መገለጦቹ ሁልጊዜ ጥርት ያለ አቅጣጫ ነበራቸው። ዓላማቸው በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያሉ አማኞችን ወደ መጀመሪያው ወደ ሐዋርያት የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ ነው።
ስለዚህ ምዕራፍ 5 ከሕዝቦች እና ከነገዶች ሁሉ ተዋጅታ የወጣችውን ሙሽራ በሰማይ በጉ ማንም ሊከፍተው ያልቻለውን መጽሐፍ በሚወስድበት በዙፋኑ ዙርያ ቆማ ያሳየናል። መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ በዝርዝር ተረድቶ ያወቀ ማንም የለም። እነዚያን ሚስጥራት መግለጥ የሚችለው በጉ ብቻ ነው።
ራዕይ 5፡8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
9 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
ከወገን ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ። የተዋጀችው ሙሽራ የምትመጣው ከ7ቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው።
ሁለት ሰዎች በሰማይ በአንድ ዙፋን መካከል ሊቀመጡ አይችሉም
ይህ ቀጣዩ ጥቅስ የስላሴ አማኞች የሚስቱበት ጥቅስ ነው። በዚህ ክፍል ሁለት አካላት ሉ ይመስላል ግን አንድ ብቻ ነው ያለው።
ራዕይ 5፡6 በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
በጉ በዙፋኑ መሃል ነው የቆመው። ሁለት ሰዎች በአንድ ዙፋን መሃል ላይ መቀመጥ አይችሉም። በዙፋን ላይ ሆኖ ዮሐንስ ያየው እና በጉ አንድ ናቸው። ስለዚህ በዙፋን ላይ ያለው ኢየሱስ ነው።
ይህ ሰውኛ ዘይቤ ነው። የኢየሱስን ሁለት ባሕርያት እንደ ፈጣሪ እና እንደ አዳኝ ያሳያል። ፈጣሪ በመጽሐፉ የፍጥረት ባለቤተነትን ማረጋገጫ ይዟል፤ ነገር ግን ፍጥረትን ከውድቀት ማዳን እና መጽሐፉን መክፈት የሚችለው በጉ ብቻ ነው።
ኢሳይያስ 43፡1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።
ራዕይ 5፡7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።
በጉ መጽሐፉን ሊወስድ የሚመጣው ፍጥረትን እንዴት እንዳዳነ ለመግለጥ ነው።
በጉ መጽሐፉን ሊወስድ ወደ ዙፋኑ ከመጣ ነገር ግን አስቀድሞም በዙፋኑ መካከል ከነበረ ታድያ ከየት ነው የመጣው?
በቦታ ርቀት ሊንቀሳቀስ አልቻለም፤ ስለዚህ በጊዜ ርቀት ውስጥ ማለፍ አስፈለገው፤ ስለዚህ በዘመናት ውስት ወደ ኋላ እስከ መጀመሪያው ድረስ ሄዶ የቤዛነት ስራው በፍጹምነት ተከናውኖ እንደሆነና አንዲትም ነፍስ ሳትታይ እንዳላለፈች አይቶ ያረጋግጣል። ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ያረጋግጣል። አንድም ነገር በዘፈቀደ እንዲሆን አይተውም።
ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፉ ክስተቶች የሚፈጸሙት ሰማይ ውስጥ ነው።
ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ በዙፋኑ ዙርያ ናት። በምድር ላይ ደግሞ ታላቁ መከራ ተጀምሯል።
ስለዚህ ሶስቱ ምዕራፎች ማለትም ራዕይ ምዕራፍ 4፣ 5፣ እና 6 በሰማይ የሚከናወኑ ነገሮች ነው የሚገልጹት እንጂ የምድሩን አይደለም።
በመጨረሻም በሰማይ በጉ ማሕተሞቹን ይፈታቸዋል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ማርች 1963 የተከናወነው የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ከንጥቀት በኋላ በሰማያት ከሚከናወነው የማሕተሞቹ መፈታት ጋር ተምታታባቸው። እነርሱ ግን ክርክራቸውን ማጠናከሪያ የሚጠቀሙት የሰው ንግግር ጥቅስ ነው፤ ጥቅሳቸውን ተጠቅመው ሰባቱ ማሕተሞች የተፈቱት ማርች 24 ቀን 1963 ወንድም ብራንሐም ስለ 7ኛው ማሕተም የሰበከ ዕለት ነው ይላሉ።
ነገር ግን ከሰው ንግግር ጥቅስ እየተረጎሙ የሚሰብኩ ሰባኪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች አይደሉም፤ ስለዚህ ብዥታንና ግራ መጋባትን በማሰራጨት ተሳክቶላቸዋል።
ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት መገለጥ አለባቸው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ማሕተሞቹን የፈታቸው ወንድም ብራንሐም ከሆነ የገለጣቸውስ ማነው?
ማሕተሞቹ ምን እንደሆኑ የነገረን ማነው? ማንም። የትኛዋም ቤተክርስቲያን እነዚህን ማሕተሞች ተርጉማ አታውቅም።
ወንድም ብራንሐም ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ የ6ቱን ማሕተሞች መከፈት በራዕይ ተገልጦለት አየ። ከዚያም ወደፊት 6ቱ ማሕተሞች በሚፈቱ ጊዜ ምን እንደምናይ ሊነግረን ተመልሶ መጣ።
መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል በማያውቁ ሰባኪዎች አትታለሉ።
የሰባቱ ማሕተሞች መከፈት መገለጥ የማሕተሞቹ መፈታት አይደለም።
ሰባቱ ማሕተሞች ከመከፈታቸው በፊት በሰማይ የአንድ ነጎድጓድ ድምጽ መሰማት አለበት
ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት የሚጀምረው በአንድ ነጎድጓድ ድምጽ ነው።
ማሕተሞቹ ገና አልተፈቱም ምክንያቱም ይህ አንድ ነጎድጓድ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም።
በ7ቱ መላእክት የተፈጠረው ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ከታየ ከ18 ቀናት በኋላ እና 7ቱ መላእክት እርሱን ባናገሩ ጊዜ ከጸፈጠረው ፍንዳታ 10 ቀናት ካለፉ በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም ስለዚህ አንድ ነጎድጓድ ሲናገር ገና ወደፊት እንደሚመጣ ነው የተናገረው።
63-0318 ሁለተኛው ማሕተም
እግዚአብሔር ሆይ፡ አለማመናችንን እርዳ። ከእኛ ላይ አስወግድልን ጌታ ሆይ። በንጥቀት የምንሄድበትን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን። ያ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ድምጹ በሚያስተጋባበት ጊዜ እና ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ በምትሄድበት ጊዜ ዝግጁ መሆን እንፈልጋለን።
ከዚያም በኋላ ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ ወንድም ብራንሐም ያ ሚስጥራዊ አንድ ነጎድጓድ ድምጹ እንዲያስተጋባ ሲጠባበቅ ነበር።
ስለዚህ የነጎድጓዱ ድምጽ በእርሱ ዘመን አልመጣም።
1965-1127
ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ይህን ቃል የተናገረው ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ነበር፤ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያ አንድ ነጎድጓድ ወደ ፊት እንደሚመጣ ሲጠባበቅ ነበር። ደግሞም ታላቁ “ድምጽ” ራሱ ወደፊት ነው የሚመጣው።
ስለዚህ “ድምጹ” ማለት ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በገለጠ ጊዜ አይደለም፤ ነገር ግን ድምጹ መጣ የሚባለው በሙሽራይቱ ውስጥ ያሉት አካላት በየግላቸው የሚያምኑትን ከትክክለኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትቅሶች ጋር እያመሳኩ ማረጋገጥ የቻሉ ጊዜ ነው።
የመጀመሪያው እንስሳ አንበሳ ነው። ይህም ሐዋርያቱ የጻፉት እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የራዕይ ምዕራፍ 6 የመጀመሪያዎቹ 7 ቁጥሮስ 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ
የመጀመሪያው ማሕተም በሁለት ቁጥሮች ውስጥ ነው የተጻፈው፤ ስለዚህ የሚገልጸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
ይህ ወታደራዊ ድል ነሺ የሚጭነው የድል ዘውድ ነው - (በግሪክ እስቴፋኖስ ይባላል)።
የመጨረሻው ፖፕ የቤተክርስቲያን እና የዓለም ንጉስ ብለው እንዲሾሙት በ10ሩ ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች በመጠቀም ዓለምን ሁሉ ይገዛል።
(ራዕይ 19 የንግስና ዘውድ ነው። ይህንን ዘውድ የሚጭነው ኢየሱስ ነው፤ እርሱ ሲወለድም የዓለም ንጉስ ሆኖ ነው የተወለደው)።
ይህ ደጋን አብሮት ቀስት የለውም። ስለዚህ ቀልደኛ ነው ማለት ነው፤ ሊዝትባችሁ ይችላል እንጂ የእውነት ሊጎዳችሁ አይችልም።
ነጭ የሐይማኖተኛ ቀለም ነው። ሐይማኖታዊ አሳችነት።
ፈረሰኛው ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይከተሉ የሚያደርገው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው።
እንደ አውሬ ጨካኝ የሆነው አረማዊው የሮማ መንግስት በ476 ዓ.ም በባርቤሪያውያን እጅ በፈራረሰ ጊዜ ይህ ክፉ አረማዊ የሮማ መንፈስ ከሙታን ተነስቶ በፈራረሰው አረማዊ የሮማ መንግስት ቦታ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆኖ ተመሰረተ።
በ860 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ ከሌሎች ነገስታት ጋር እኩል ለመሆን አንድ ዘውድ ይጭን ነበር።
በ1315 ዓ.ም ይህ ዘውድ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ሆነ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የጫነውም ፖፕ ክሌመንት 5ኛው ነበር።
ክሌመንት 5ኛው በ1315 ሞተ። በ1316 ፖፕ አልተመረጠም ነበር።
በ1316 የፖፑ ንብረት የሆኑ ወርቅ እና እንቁዎች ሁሉ ሲመዘገቡ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድም አብሮ ተመዝግቧል።
ክሌመንት 5ኛው ፖፕ ሆኖ የተሾመው በ1305 ነበር።ፖፕ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ተጫነለት።
ዘውዱ የሚያመለክተው እያደገ የነበረውን የፖፑን ሐይማኖታዊ ስልጣን እና ፖለቲካዊ ስልጣን ነው።
የካቶሊክ ፖፕ ሁሉ በ1963 ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች እስከ ሰበከበት ጊዜ ድረስ ባለ ሶስት ድርቡን ውድ ይጭኑ ነበር። በዚህ ርዕስ ላይ ገልጦ በማስተማር ያበራው ብርሃን ፖፑን ስላስደነገጠው ፖፑ ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ መጫን አቆመ።
“ድል ለመንሳት ወጣ”።
ይህ የመጀመሪያው ማሕተም ምልክት የባቢሎን ፖንቲፎችን የክሕነት ሐረግ ተክተው የመጡትንና በስልጣን የሚተካኩትን ፖፕ የሚገልጽ ነው፤ አስቀድሞ ፖንቲፎቹ በእግዚአብሔር ላይ የመጀመሪያው አመጸኛ ሆኖ የተነሳውን ናምሩድን ተክተው የባቢሎን ሚስጥራት ጠባቂ ነበሩ። ዋነኛው ተልዕኮዋቸው አረማዊነትን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የተሳሳቱ ትምሕርቶችን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ በማስገባት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን ማቃለል ነበር።
በነጩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ፈረሰኛ በቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ውስጥ እየጋለበ እስከ 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ይደርሳል፤ ሰባተኛው ዘመን ውስጥ ሲደርስ ከቀዩ ፈረስ እና ከጥቁሩ ፈረስ ጋር ተደባልቆ የታላቁ መከራ ሐመር ፈረስ ይሆናል። ይህም ማለት ሐይማኖታዊ አሳችነት ሁልጊዜም የቤተክርስቲያን ዘመናት አካል ይሆናል።
በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቁ ችግር የሐይማኖት አሳችነት መሆኑን ኢየሱስ ተናግሯል
ደቀመዛሙርት ኢየሱስ መች እንደሚመጣ ለመጠየቅ ደፍረው አያውቁም። የጠየቁት የመምጣቱን ምልክት ብቻ ነው።
ማንም ሰው ኢየሱስ መች እንደሚመጣ አውቃለው ወይም መጥቷል ቢላችሁ በጭራሽ አትስሙት። ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ብንመለስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አንጠይቅም።
ስለ መምጣቱ ምልክት ሲጠይቁት ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ነው የመለሰው፡-
ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ አሳችነት እየበዛ ይሄዳል፤ ይህም ዘመኑ ወደ መጨረሻ መቅረቡን አመልካች ነው።
ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች፣ ዲኖሚኔሽኖች እና የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እነዚህ ሁሉ በአስተምሕሮዋቸው ይለያያሉ፤ ነገር ግን ሁሉም እኔ ትክክል ነኝ ይላሉ። የቤተክርስቲያን ዓለም መንፈሳዊ ረግረግ ሆኗል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ የተበላሸችው በአማዊው የሮማ መንግስት መንፈስ የተለከፈች ጊዜ ነው።
ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም እንደ ስላሴ፣ የስቅለት አርብ፣ ክሪስማስ፣ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን አለቃ ይሁን፣ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ትተው በሶስት ማዕረጎች ማጥመቅ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን ባስተማረቻቸው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተጽእኖ ተበላሽተዋል።
ዊልያም ብራንሐም ሙሽራይቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ወደ ማመን ሊመልሳት ይገባል፤ የሚመልሳትም ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት እንዲችሉ በማድረግ ነው፤ መረዳት የሚችሉትም እርሱ የጠቀሳቸውን ጥቅሶች ሄደው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማመሳከር ነው።
ሰይጣን ግን ሰዎች የዊልያም ብራንሐምን ትምሕርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያመሳከሩ መቀበላቸውን ስላልፈለገ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ላይ የጥቃቱን ኢላማ በማድረግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው እንዲሄዱ አደረጋቸው። ከዚያ ወዲያው የሜሴጅ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ማመን ጀመሩ።
ነጩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ሐሰተኛ መንፈስ የሜሴጅ ሰባኪዎች ዊልያም ብራንሐምን የሰው ልጅ፣ ፍጹሙ የማይሳሳተው የእግዚአብሔር ድምጽ ብለው በመጥራት ወደ መለኮትነት ደረጃ ከፍ እንዲያደርጉት አነሳሳቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምትክ የዊልያም ብራንሐምን ንግግር ተኩ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ክሪስማስ እና የስቅለት አርብ የሚባሉ በዓላትን አከበሩ።
ልክ እንደ ካቶሊክ እና እንደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የሜሴጅ ፓስተሮችም ከጉባኤው በላይ ከፍ ማለት እና የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አለብን አሉ። ከዚያ በኋላ ስውር የሆነው ስሕተታቸውን ማስተማር ቀጠሉ። ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል አሉ፤ ምሕረት አብቅቷል፤ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መጥቷል አሉ፤ ደግሞም የኢየሱስን አዲስ ስም እናውቃለን አሉ (ከዚያም ስሙን እናውቃለን ብለው ብዙ አዲስ ስሞችን ፈጠሩ)።
መጽሐፍ ቅዱስ ምንም የተናገረው ነገር ባይኖርም እንኳ እነርሱ ግን 7ቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል አሉ (ከዚህም የተነሳ የተለያዩ ሜሴጅ ቡድኖች ስለ 7ቱ ነጎድጓዶች የተለያዩ ትምሕርቶችን ሊከተሉ ችለዋል)።
በዚህ ምክንያት የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ወደ ብዙ ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖች ተከፋፈሉ። ግጭቶች እና አለመግባባቶች እየተካረሩ ከመሄዳቸው የተነሳ የተለየ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች መገፋትት ሲበዛባቸው ቤተክረስቲያኒቱን ለቀው ለመሄድ ይገደዳሉ። አንዳንዶች በግልጽ ተባረው ወጥተዋል። የሃሳብ ልዩነቶች በጣም እየሰፉ ሄደዋል። በ1963 የታየውን ደመና በተመለከተ በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ፓስተር ከስልጣን እንዲወርድ ተገድዷል (ይህ ደመና ለተለያዩ የሜሴጅ ቡድኖች የተለያዩ ትርጉሞች አሉት)።
ነጩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ፈረሰኛ ዛሬም ስራውን እየሰራ ነው፤ በቤተክርስቲያኖችም ሁሉ ውስጥ እስከ መጨረሻው ድረስ አዳዲስ የስሕተት ዓይነቶችን እየዘራ ስራውን መስራት ይቀጥላል።
በመጨረሻ ካቶሊክ ያልሆኑት ቤተክርስቲያኖች በመጨረሻው ፖፕ አመራር እና ተጽእኖ ስር ይወድቃሉ፤ እርሱም የሮማ ካቶሊክ አውሬ ራስ ነው። ካቶሊክ ያልሆኑት ቤተክርስቲያኖች ደግሞ በአንድነት ተጣምረው የአውሬው ምስል ይሆናሉ፤ ይህ የአውሬ ምስል የሚገለጠው በመጨረሻው አንድ የዓለም ቤተክርስቲያን በሚመሰርተው ፖፕ አመራር ስር ቤተክርስቲያኖችን ወደ አንድነት በማምጣት ነው።
ሰባቱ ማሕተሞች ቢገለጡም እንኳ ለምን እንዳልተፈቱ ግልጽ የሆነው ምክንያት ነጩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ፈረሰኛ ወደፊት ይዞ የሚያመጣቸው ስሕተቶች ምን እንደሆኑ ገና ስለማናውቅ ነው።
ነገር ግን ይህ ነጭ ፈረስ ላይ የጠቀመጠ ፈረሰኛ በአንድ ነገር ተሳክቶለታል፤ እርሱም የሜሴጅ ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስን መከተል እንዲተዉ ማድረግ ነው።
በሜሴጅ ተከታዮች መካከል መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ መጠን እየጨመረ ሄዷል፤ እነዚህም ሰዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለባቸው ብለው የሚያስቧቸውን ጥቅሰች ለማሳየት የሚቸኩሉ ናቸው። አለማዊ አለባበሳቸውን ስለማይደግፍላቸው ወይም አንዳንድ እውነት ብለው የሚያስቡትን ትምሕርታቸውን ስለማይደግፍላቸው ወይም ደግሞ ጥቅሶቹ ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት ባለመቻላቸው ምክንያት ነው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ የሚሉት። ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ምንም ስሕተት የለበትም ብለው ያስባሉ። ስለዚህ በጣም ተታልለዋል።
ሁለተኛው የፖለቲካ ኃይል ማሕተም
ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
ይህ ጥጃ ኋላ በጨለማው ዘመን ውስጥ ብርቱ በሬ ሆኖ ያደገው እንስሳ ነው፤ የጨለማው ዘመን ከቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ 60% የሚያህለውን ጊዜ ይሸፍናል። ማለትም ከ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ 1,200 ዓመታትን ይዟል። በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ስላሴ የሚባል ትምሕርት ቤተክርስቲያን ላይ በግድ በተጫነ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን በበተክርስቲያን ውስት ደብዝዞ ጠፋ።
በነዚያ አስቸጋሪ ዘመናት ውስጥ ክርስቲያኖች ብረቱ መሆን ይጠበቅባቸው ነበር።
በነዚያ የማያልቁ በሚመስሉ ረጅም ዘመናት ውስጥ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው አማኞች በእምነታቸው ሲተጉ ቆይተው አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ተሰቃይተው ተገድለዋል። በሬ በትጋት እርሻ ሲያርስ ከቆየ በኋላ ስጋው ለመብል ተፈላጊ ስለሆነ ይታረዳል። እነዚህ ክርስቲያኖች እጅግ ብርቱ ከመሆናቸው የተነሳ ይህን ሁሉ መከራ ታግሰው አልፈዋል።
ራዕይ 6፡4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
ቀይ ቀለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓ ውስጥ በፖለቲካዊ ስልጣን በተነሳች ጊዜ የፈሰሰውን ደም ያመለክታል። ሰይፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቃዋሚዎቿን በተለይም ፕሮቴስታንቶችን የገደለችበትን ፖለቲካዊ ኃይል ያመለክታል። እስፔይኖች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ለመመስረት ብለው ሜክሲኮ እና ደቡብ አሜሪካ ውስት 15 ሚሊዮን የሚያህሉ የአህጉሪቱን ቀደምት ነዋሪዎች ገድለዋል።
ፖፑ እጅግ በጣም ታላቅ ተጽእኖ ማምጣት የሚችል ፖለቲከኛ ነው። ከሁሉም ጊዜ በላይ እጅግ ብዙ የዓለም መንግስታት መሪዎች የተገኙበት ዝግጅት በ2005 የተደረገው የፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ የቀብር ስነ ስርዓት ነው። ዛሬ ፖፑ የጎደለው ነገር የጦር መሳሪያ እና የጦር ሰራዊት ነው። የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ሲነሳ ወታደራዊ ኃይሉን ከ10ሩ ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ያገኛል። በዚያም ወታደራዊ ኃይል ተጠቅሞ ዓለምን ሁሉ በአንድ መንግስት ስር አድርጎ ይገዛል።
ፖለቲካ ማለት በሌሎች ሰዎች ላይ አለቃ ሆኖ የመግዛት ጥማት ነው።
ፖለቲካ አንድ ሰው ብቻ በሃገር ሁሉ ላይ በስልጣን ገዥ እንዲሆን ያደርጋል።
ይህ በሰዎች ላይ ጌታ የመሆን ዕድል ነው ከማርቲን ሉተር ተሃድሶ በፊት የነበሩ የካቶሊክ ጳጳሳትን ባለ ስልጣን ለመሆን እንዲጓጉ ያደረጋቸው።
ከተሃድሶው ወዲህ ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ ባደረጉ ጊዜ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የገባው ይህ አለቅነትን የመውደድ መንፈስ ነው።
ነገር ግን ስልጣንን መውደድ ስሐተት ነው። የጥንቷ ቤተክረስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት እንጂ በግለሰብ አልተመራችም።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
በምድር ላይ ከፈሰሰ ደም ሁሉ በላይ ታላቅ ዋጋ ያለው ደም የእግዚአብሔር ደም ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዷን አጥቢያ ቤተክርስቲያን መምራት የሚፈልገው በአጥቢያዋ ሽማግሌዎች ሕብረት አማካኝነት ነው።
ሶስተኛው ማሕተም የትልቅ ንግድ አጋንንታዊ አሰራር በቤተክርስቲያን ውስጥ
ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
ጥቁር የሚገልጸው መንፈሳዊ ጨለማን እና አጋንንታዊ አሰራርን ነው። በታሪክ ውስጥ ሁሉ ቤተክርስቲያን ከገባችባቸው ክፋቶች ሁሉ እጅግ የከፋው ክፋት የገንዘብ ፍቅር ነው። ምድራዊ ሃብት ለማከማቸት ሲሯሯጡ ሰማያዊ ራዕይ ደብዝዞ ይጠፋባቸዋል።
አገልጋይ ሁሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛውን ስልጣን ለመያዝ ይሽቀዳደማል፤ ምክንያቱም ከፍተኛው ስልጣን ላይ የተቀመጠው ሰው ከፍተኛውን ክፍያ ያገኛል። ከአስራት የተሰበሰበውን ገንዘብ ሁሉ ለራሱ ስለሚያደርግ ከሌሎች አገልጋዮች ዘንድ ፉክክር ይገጥመዋል። ከዚያም ወደ ራሱ ያስጠጋቸውን ደጋፊዎቹን ገንዘብ ይከፍላቸዋል፤ እነርሱም በሕዝቡ ላይ ያለውን ስልጣን ያስጠብቁለታል።
ሃብቱን እና ስልጣኑን ተጠቅሞ ሃበቱን እና ስልጣኑን ያስጠብቃል።
ገንዘብ የድርጅት ሕይወት ነው፤ ሐይማኖታዊ ድርጅት ደግሞ የአውሬው ምልክት ነው።
የቤተክርስቲያን የመጨረሻ ትልቁ ውድወቷ የገንዘብ ብዛት ነው፤ ምክንያቱም የገንዘብ ብዛት መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የመከተል መንፈሳዊ እይታን ያሳውራል፤ ከዚያም ፉክክር ውስጥ አስገብቶ እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ቤተክርስቲያኖች በልጣ ለመታየት እንድትጥር ያደርጋል። የቤተክርስቲያን ራዕይም ገንዘብ እና የአባላት ብዛት ይሆናል። ይህ ሁሉ በገንዘብ ብዛት እና በአባላት ቁጥር አንደኛ የሆነችዋን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መኮረጅ ነው።
ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች እናት በሆነችው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስኬት ተጽእኖ ስር ወድቀዋል። ልጆቿም ልክ እንደ እናታቸው የስኬት መለኪያ የገንዘብ ክምችት ብዛት እና የአባላት ቁጥር ብዛት ነው ብለው ያምናሉ።
ራዕይ 6፡6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
ገብስ እና ስንዴ ዳቦ ለመጋገር ያገለግላሉ፤ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተምሳሌት ነው።
በምሳሌው ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ዲናር ለቀን ሰራተኛ የአንድ ቀን ክፍያ ነው።
ማቴዎስ 20፡2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።
የተጠየቀው ዋጋ ከልክ በላይ የበዛ ነው። የአንድ ቀን ስራ ክፍያ ዳቦ ብቻ ነው የሚገዛው።
ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል እየሸጠች ብዙ ገንዘብ አከማችታለች።
ቁጥር 5 እና 6 በ5ኛው እና በ6ኛው ዘመን የመጡትን ተሃድሶዎች ይወክላሉ። በነዚያ ዘመናት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስርየት ወረቀት ብትገዙ ሐጥያታችሁ ይቅር ይባልላችኋል እያለች ወረቀት በመሸጥ ሃብታም ሆነች። በዚህ ሽያጭ ገቢ ፖፑ ቫቲካን ውስት የሲስቲን ቻፕል እና የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተክርስቲያን መስራት ችሏል።
ሐይማኖት ትልቅ ንግድ ሆነ።
እግዚአብሔር ግን የሰውን አእምሮ ባረከ። ዘይቱ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። ወይን በመገለጥ የሚመጣ መነቃቃት ምሳሌ ነው፤ ይህም መገለጥ ተሃድሶ እንዲመጣ አድርጓል።
ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት ብቻ የሚለው እውነት በተሃድሶ እንዲመጣ አድርጓል።
እግዚአብሔር የሰውን አእምሮ በመባረኩ እንግሊዝ ውስጥ 47 ሰዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉመዋል።
እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ የቅድስናን ትምሕርት በተሃድሶ አምጥቷል፤ ደግሞም በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን እነዲጀመር አድርጓል።
4ኛው ማሕተም ሲከፈት ንስሩ ነብይ እና ታላቁ መከራ ውስጥ እየጋለበ የሚመጣው ሞት ይገለጣሉ
ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
“የሰባተኛው መልአክ ድምጹ”። እውነትን ክዳ ባፈገፈገችው በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ባለችው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ብቸኛው ዋጋ ያለው አገልግሎት የንስር ዘመን አገልጋይ የሆነው ዊልያም ብራንሐም ይዞር የመጣው አስደናቂ እይታ እና መገለጥ ነው። የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ዘመን ታሪክን አጠቃሎ በአንድ ጊዜ በማየት በዚህ ዘመን ውስጥ የነበሩ ጥቃቅን ዝርዝሮችን ሁሉ አጥርቶ ማየት ችሏል።
የእግዚአብሔር ሚስጥራት መገለጥ የሚያበቃው ለሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት ሊሰጧት ድምጻቸውን በሚያሰሙት በሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥራዊ ንግግር ነው።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?
ነገር ግን ይህ ከምድር አልመጣም። እርሱ የመጣው ከሰማይ ነው ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመዋል። ሚስጥሩም በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ዘመን አይኖርም” በዚያን ጊዜም ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።
እንደው ለመነጠቅ ወደሚያበቃው እምነት ውስጥ እንዴት አድርገን እንደምንገባ የሚያሳውቀን ነገር ቢሆንስ? ነውን? እንሮጣለንን፤ ከግድግዳዎቹ በላይ እንዘላለንን? አንድ ነገር ሊሆንና እነዚህ ያረጁ የተበላሹ ስጋዎቻችን ሊለወጡ ጊዜው ቀርቦ ይሆን? ጌታ ሆይ ይህ እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት ታኖረኝ ይሆን? እኔ በሕይወት ሳለው አየው ዘንድ ቀርቧልን? በዚህ ትውልድ ይፈጸማልን? ወንድሞች ሆይ ሰዓቱ ስንት ነው? የት ነው ያለነው?
ሚስጥሩ በሙሉ ተፈጽሟልን? የመለከቱ ድምጽ ተሰምቷል? በእውነቱ እነዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸውን፤ ቃላቸውን ሊናገሩ ተዘጋጅተው ይሆን፤ በሕብረት የተሰበሰበው ታናሽ ወገን ለመነጠቅ የሚያበቃውን እምነት ሊቀበል ይሆን፤ እርሱ ሲመጣ ተነጥቀው ለመሄድ? “ሁላችንም እንለወጣለንና፤” እነዚያ መላእክት ሲመጡ በፍጥነት “በድንገት፣ በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ በአየር ላይ ጌታን እንቀበለው ዘንድ አንቀላፍተው ከነበሩት ጋር እንነጠቃለን።”
2ኛ ሳሙኤል 22፡30 በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።
ቅጥሩን እዘላለሁ። ይህ ምን ማለት ነው? በአዲሱ አካላችሁ በጦር ሰራዊት መካከል ትሮጣላችሁ ግን ሊነኳችሁ አይችሉም። ፍጥረታዊውን ዓለም ከመንፈሳዊው ዓለም ከሚለየው የጊዜ ቅጥር በላይ ትዘላላችሁ። በንጥቀት ጊዜ 7ቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ሲያሰሙ የሚሆነው ይህ ነው። አካላችሁን እንዴት እንደምትለውጡ ያሳዩዋችኋል። አዲሱን አካል ለሚለብሱ ሁሉ ከጊዜ ዓለም ወጥተው “ጊዜ ወደማይቆጠርበት” ዘላለማዊ ዓለም እንዴት እንደሚገቡ ያሳዩዋቸዋል።
63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያቀርበውም
ኦ የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉ ሰዎች ምንኛ አስደናቂ እንደሚሆኑ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ! እንዲህ ይላል፡- “በሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ ቅጥሩንም ይዘላሉ።” አዎ፤ የሞት “ሰራዊት” ሊይዛቸው አይችልም፤ በመካከሉ ሮጣ ታልፋለች። በፍጥረታዊው እና በልዕለ ተፈጥሮአዊው መካከል ያለውን “ግድግዳ” ዘላው ታልፈዋለች፤ ከዚያም ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ትገባለች። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው በጣም እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።
7ቱ ነጎድጓዶች ሙሽራይቱ ጌታ ሲመጣ በአየር ላይ ትቀበለው ዘንድ ወደ ሰማይ ለመነጠቅ እንድትችል አካሏን ለመለወጥ የሚያስችላትን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል እንዴት እንደምታገኝ ያሳዩዋታል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም። አሆን፤ እውነት ነው። እኔም ደግሞ በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ እንዴት እንደምትዘጋጅ እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምትቀበል ይገለጥላታል። ምክንያቱም አሁን ባለን እምነት መነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ መጨመር ወደፊት መግፋት አለብን፤ ለመለኮታዊ ፈውስ እንኳ የሚበቃ እምነት የለንም። ከመቅስፈት ተለውጠን ከዚህ ምድር ተነጥቀን ለመሄድ ከመቅስፈት የምንለወጥበት እምነት ያስፈልገናል፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እግዚአብሔር ሲፈቅድ የትጋ እንደተጻፈ እናገኘዋለን።
ከዚያም ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ታላቁ መከራ ይጀምራል።
ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።
ማሕተሙ እስካሁን አልተፈታም ምክንያቱም ሞት የተባለው ፈረሰኛ ማን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም።
ሞት የተባለው ፈረሰኛ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን ሰውየው ማን እንደሆነ አናውቅም።
በምድር ላይ 8 ቢሊዮን ሰዎች አሉ። አንድ አራተኛው ማለት 2 ቢሊዮን ሰዎች ናቸው። እስካሁን ድረስ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች አልተገደሉም። ስለዚህ እነዚህም ሰዎች ማን እንደሆኑ አናውቅም።
ስለ አራተኛው ማሕተም በተጻፈበት ቃል ውስጥ ሁለተኛው ቁጥር (ራዕይ 6፡8) የሚናገረው ስለ ታላቁ መከራ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ነው። ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ እንድትቀበለው መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰማይ በሚነጥቃት ጊዜ ሕይወት ከምድር ላይ ይወገዳል። ሕይወት ምድርን ለቆ ከሄደ በኋላ ብቻ ነው ሞት መግባት የሚችለው።
ስለዚህ ቁጥር 8 የሚናገረው ሙሽራይቱ ከሄደች በኋላ ስለሚሆኑ ክስተቶች ነው።
7 ሙላትን ወይም ፍጻሜን የሚያመለክት ቁጥር ነው፤ ለምሳሌ በሳምንት ውስጥ 7 ቀናት አሉ። 8 ደግሞ የአዲስ ስርዓት ጅማሬ ነው፤ ማለትም የታላቁ መከራ ጅማሬ።
ቁጥር 7 የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚጠናቀቁበትን 7ኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን በተመለከተ ነው የሚናገረው።
ቁጥር 8 አዲስ ስርዓት ነው፤ እርሱም ታላቁ መከራ እና ወንጌል ወደ አይሁዶች የሚዞርበት ነው።
በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው አማካኝነት ተታልለው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት ያልቻሉ ነገር ግን የዳኑ ክርስቲያኖች ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይጠፋሉ።
ሐመር ፈረስ የሚፈጠረው ሶስት የተለያዩ ቀለማት ያሏቸው ፈረሶችን አንድ በማድረግ ነው፤ ነጭ፣ ቀይ፣ እና ጥቁር።
7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ይህ አንድነት የሚጀምርበት ዘመን ነው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሐይማኖት አሳችነትን የሚወክለው ነጩ ፈረስ በነጻነት ይፈነጫል፤ ለዚህም ነው የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን “የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ተብላ የተጠራችው።
የሎዶቅያ ከተማ ሳትሆን የሎዶቅያ ሕዝብ፤ ማለትም “የሕዝቡ መብት”።
የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን የመተቸት መብት እና መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው እንዲመቻቸው አድርገው የመተርጎም መብት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ከዚህም የተነሳ ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ተተርጉመዋል፤ እያንዳንዱ ተርጓሚ የራሱን አጀንዳ ማራመድ ፈልጎ ነው የተረጎመው። ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እግዚአብሔርን እራሳቸው በፈለጉበት መንገድ የማገልገል መብት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ዛሬ ከ100 በላይ ልዩ ልዩ ዓይነት የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ ሁሉም የራሳቸው የተለያየ ትምሕርት አላቸው።
ድራም የተባለው የሙዚቃ መሳሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጠቀሰም፤ ዛሬ ግን ድራም ሙዚቃ የቤተክርስቲያን አምልኮ ማድመቂያ ሆኗል። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በዓለም ውስጥ እንዳለው ዓይነት የሚያዝናና ዲስኮ ሙዚቃ፣ ሰው ሰራሽ መጋጌጫ ሜካፕ መጠቀም ይወዳሉ፤ ይህንንም ለእግዚአብሔር ሊያቀርቡ ይፈልጋሉ። ጽንስ ማቋረጥን ይደግፋሉ፣ ግብረ ሰዶማዊነትንና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በእግዚአብሔር ፊት ይፈጽማሉ። የሚያሳዝነው ነገር በያንዳንዱ ዓይነት ቤተክርስቲያን ውስጥ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚፈልጉትን ጥቅስ መርጠው ስለሚታዘዙ፣ ሌሎች ጥቅሶችን እንደ ፍላጎታቸው ትርጉማቸውን ይለውጣሉ፤ ስሕተት ናቸው ይላሉ፤ ወይም እንዳልተጻፉ ያህል ቸል ይሏቸዋል። ከብዙ ልዩ ልዩ የሰው አመለካከቶች እና ልማዶች የተነሳ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ጨምሮ ዲኖሚኔሽናዊ የሆኑ እና ያልሆኑ 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሊኖሩ ችለዋል። የቤተክርስቲያን ዓለም ከገቡበት መውጣት የማይችሉት አስቸጋሪ መንፈሳዊ አረንቋ ሆኗል፤ በዚህ የቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ለአዲስ አማኝ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ፈልጎ ማግኘት ጭራሽ የማይቻል ነገር ሆኗል። ከ100 ዓይነት የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እና ከ45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች መካከል እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ፈልገው ለማግኘት ይሞክራሉ። በተጨማሪ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ለብ ያለች እና እውር ተብላ ተወግዛለች።
ይህም ውግዘት እያንዳንዷን የሜሴጅ ቤተክርስቲያን ይመለከታል ምክንያቱም የትኛዋም ቤተክርስቲያን ከዚህ ውጭ ናት አለተባለችም።
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ … ዕውርም ስለሆንህ
ስለዚህ በሁሉም ነገር ትክክል የሆነች አንዳችም ቤተክርስቲያን የለችም። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የምትፈልጉ ከሆነ ከቤተክርስቲያኖች መካከል ብትፈልጉ በከንቱ ትደክማላችሁ።
በፊት መሸሸጊያ የነበሩ እውነትን የምታገኙባቸው ቤተክርስቲያኖች አሁን የስሕተት እና እየተስፋ የሚሄዱ መንፈሳዊ ቫይረሶች መራቢያ እና መሰራጫ ቦታዎች ሆነዋል።
ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች እንኳ ሳይቀሩ ተሰነጣጥቀው ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት መንፈሳዊ ቫይረሶች ሆነዋል። ለምን? ምክንያቱም የሜሴጅ ሰባኪዎች እምነታቸውን የሚመሰርቱት በመረጡት የሰዎች ንግግር ጥቅሶች ላይ ነው። የሜሴጅ ሰባኪዎች መልእክት በየሰባኪው መረዳት አንጻር ይለዋወጣል። ሰዎችም የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች በድንግስግዙ እና በተጭበረበረው የሰባኪዎቻቸው የአመለካከት መነጽር አማካኝነት ነው የሚያዩት።
የሜሴጅ ተከታዮች እምነታቸው እንደሚኖሩበት አካባቢ እና እንደ ሰባኪዎቻቸው ይለያያል። ሰባኪዎቻቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በዊልያም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች ተክተዋል፤ መልእክታቸውም የብራንሐምን ንግግሮች በየግላቸው እንደሚፈቱት አፈታት የተለያየ ነው።
ብዙዎቹ ወንድም ብራንሐምን እርሱ የማይሳሳት የእግዚአብሔር ድምጽ ነው በማለት ወደ መለኮትነት ደረጃ ከፍ አድርገውታል። ፖፑ በ1870 ዓ.ም ፍጹም የማይሳሳት ነው ተብሎ እንደታወጀለት ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ነው ማለት የካቶሊክ መንፈስ ነው። ስለዚህ ፕሮቴስታንቶች በራዕይ ምዕራፍ 17 እንደተነገረው ትንቢት ወደ ጋለሞታ እናታቸው እየተመለሱ ናቸው።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው የተሳሳተው ስሕተት
ወንድም ብራንሐም ማርች 8 ቀን 1963 ቱክሰን አጠገብ ሳንሴት ፒክ የሚባል ቦታ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ለአደን በወጣበት ጊዜ 7 መላእክት ጎብኝተውታል። ያን ዕለት 7ቱ መላእክት ሊጎበኙት ሲመጡ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሰርተዋል በማለት እና እርሱም ከደመናው ስር ቆሞ እንደነበረ በማሰቡ ታላቅ ስሕተት ሰርቷል።
7ቱ መላእክት እርሱን ሊጎበኙ ወደ ሳንሴት ፒክ የመጡ ዕለት አንዳችም ደመና አልሰሩም።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ልክ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን መላእክቱ ደመና ፈጠሩ፤ ይህም የአደን ወቅት ሊጀር አንድ ቀን ሲቀር ነው። እርሱ ለአደን ወጥቶ ከሆነ ሕገወጥ ስራ እየሰራ ነበር ማለት ነው።
ነገር ግን እርሱ በዚያ ቦታ አልነበረም፤ ምክንያቱም የልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና መታየት እና የ7ቱ መላእክት ጉብኝት የተለያዩ ክስተቶች ናቸው፤ እነዚህ ሁለት ክስተቶች በ8 ቀናት እና በ200 ማይልስ የተራራቁ ነበሩ። ሁለቱ የሆኑበት ጊዜ አንድ አልነበረም። መላእክቱ በጥዋት ነበር የመጡት ደመናው ግን የታየው ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ። ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ደመናውን አላየውም።
ደመናው ሲወርድ ወይም ሲወጣ ወይም ሰማይ ላይ ሲንሳፈፍ (እንዲህ እያለ በየጊዜው ንግግሩን ይለዋውጣል) ብራንሐም ከደመናው ስር ቆሞ ነበር ብለው የእርሱን ንግግር ትክክል እንደሆነ የሚሟገቱለት የሜሴጅ ሰባኪዎች ትልቅ ግራ መጋባት ፈጥረዋል። ዊልያም ብራንሐምን የሚነቅፉ ተቺዎች ንግግሩ በየጊዜው መለዋወጡን ተጠቅመው ብዙ ሐሰተኛ ነብይ ነው ብለው ትችት ሰንዝረውበታል።
63-0623 በፈረሰበት በኩል መቆም
እኔም በሰዓቱ መላእክቱ መልእክት ይዘው ከሰማይ እየወረዱ ሳለ ሳይንቲስቶች ፎቶግራፍ እያነሱ እንደነበር አላወቅሁም።
… የደመናው ፒራሚድ ይታያችኋል? ልክ ከዚህ ስር ቆሜ ነበር።
65-0718E መንፈሳዊ ምግብ በወቅቱ
… ወደ ላይ በወጣ ጊዜ እኔ እና ወንድም ጂን ኖርማን እዚያው ቆመን ነበር። እነርሱ ፎቶ አንስተዋል ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ምን እንደሆነ አያውቁም።
63-0628M ጌታ ሆይ አንድ ጊዜ ብቻ
እንግዲህ ሳይንስ ፎቶግራፍ አንስቶልናል፤ አይታችሁታል፤ በአሶሼትድ ፕሬስ ተላልፏል። ምን መሆኑን አላወቁም። ሃያ ስድስት ማይልስ ከፍታ ላይ የተንሳፈፈ ደመና ብቻ ነው ያዩት።
ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ጥርት ያለ ምርጫ እንድታደርጉ ግድ ይላችኋል፤ ምክንያቱም ዊልያም ብራንሐም አሳዛኝ ስሕተት ሰርቷል።
እርሱ ፍጹም የማይሳሳት ሰው ነው ለማለት ብላችሁ ስሕተቱን ትክክል ብላችሁ ትሟገቱለታላችሁ?
ቀጥላችሁ ደግሞ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት ልታገኙ ነው፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ከስሕተት ነጻ ነው ብላችሁ አታምኑም።
ስሕተት የሌለበት ፍጹም አንድ ብቻ ነው፡ መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ዊልያም ብራንሐም።
ወይ ደግሞ እርሱ መሳሳቱን ተቀበሉ። ስሕተቱን አርሙ እና ወደ ቀጣዩ ጉዳይ እለፉ።
የዚያን ጊዜ የሜሴጅ ሰባኪዎች ሁለት ከባድ “ስሕተት” ሰርታችኋል ብለው ይወቅሷችኋል።
“ነብዩን ለማረም ሞክራችኋል፤ ደግሞም ፍጹም አይደለም ይሳሳታል ብላችኋል”። የሜሴጅ ሰባኪዎች ምንም ሳትፈሩ ስሕተታቸውን በመግለጥ ከተቃወማችኋቸው እንዲህ ብለው ነው የሚያወግዟችሁ።
ወደድንም ጠላንም ሁላችንም ይህ ምርጫ ይቀርብልናል።
ዋናው መሪያችሁ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ ወይስ የሜሴጅ ፓስተር?
ደግሞ የሜሴጅ ፓስተሮች ራሳቸው ምን ያህል እርስ በርሳቸው እንደሚቃረኑ አስቡ።