ራዕይ 13 - ሮም በአሜሪካ ኃይል ትነሳለች
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እግዚአብሔር በክፋት ላይ ገደብ ይጥላል። ሮም እና አሜሪካ የአውሬውን ምልክት በዓለም ላይ አሰራጭተዋል።
First published on the 15th of October 2021 — Last updated on the 15th of October 2021ራዕይ ምዕራፍ 13
አሜሪካ እና ሮም ያሰራጩት - የአውሬው ምልክት
የአውሬው ምልክት የሚያስፈራ ነገር ነው ምክንያቱም የሚወክለው ሰይጣን ያታለላቸውን እና በቁጥጥሩ ስር ያደረጋቸውን ሰዎች ነው። በምድር ላይ ክፋት እጅግ መብዛቱ ሰይጣን ሥራውን በደምብ እንደሰራ ያሳያል። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች ሰይጣን እንደፈለገ መሆን የሚችል እና ስሕተትን መገደብ የማይቻል ይመስላቸዋል።
እግዚአብሔር ግን በክፋት ላይ ገደብ ያደርጋል፤ ደግሞም ለክፋት የታሰበውን ተጠቅሞ በጎ ፈቃዱን ይፈጽምበታል።
ምዕራፍ 13 በክፉው ላይ የተጣለበትን ገደብ በጣም ግልጽ ነገር ግን ውብ በሆነ መንገድ ያሳያል፤ ክፉውም ከተጣለበት ገደብ ማለፍ አይችልም። ገደቡን የሚገልጸው ቃል የባሕር አሸዋ ነው። ባሕር (ማለትም እረፍት የሌለው ብዙ ሕዝብ) ሲተባበር ታላቅ ኃይል ይኖረዋል። ትልልቅ ማዕበሎች ሲነሱ በምድር ላይ ጥፋት ማድረስ የሚችል ሞገድ ያመጣሉ፤ ሆኖም ግን ባሕሩ ከማዕበል በኋላ በተፈጥሮ ወደተደረገለት ገደብ ይመለሳል። የባሕሩ ዳርቻ (ማለትም ጻድቃን) ሳይጠፋ ይኖራል፤ ለባሕሩም ገደብ ያበጅለታል። መልካም ሰዎች በመልካም ሥራቸው እና በመልካም ምሳሌነታቸው ክፋት እንዳይስፋፋ ገደብ ያደርጋሉ። ብዙ ስጋ ቢኖር እንዳይበላሽ ለማድረግ ትንሽ ጨው ይበቃል፤ ማለትም ጥቂት መልካም ሰዎች ሕዝቡ በሙሉ በክፋት እንዳይበላሹ የማድረግ ኃይል አላቸው።
ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
አውሬው የአረማውያንን አጋንንታዊ አምልኮ እና አረማዊ የሆነውን የሮማ መንግስት ግፈኝነት ይወክላል።
የሮማ መንግስት በባርቤሪያውያን ወረራ አማካኝነት ፈራርሶ ጠፍቶ ነበር፤ ነገር ግን አረማዊው የሮማ መንፈስ ከፍርስራሹ ውስጥ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ተነስቶ አንሰራርቷል። አንድ የታሪክ ምሑር የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሲገልጽ ክርስትና የተነሳ አረማዊነት አለ።
አውሬው የሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ቤተክርስቲያን ስልጣን በጥምረት ተነስቶ የብዙ ሃገሮችን አእምሮ እና እምነቶች የሚቆጣጠር ኃይል ነው። አውሬው በተጨማሪ የሰው ትዕዛዛት የእግዚአብሔርን ቃል ተክተው እስኪቀመጡ ድረስ የሰው አመራር ቤተክርስቲያንን ሊቆጣጠር የሚነሳበት ስርዓት ነው።
ሰባቱ ራሶች የሮም ከተማ መጀመሪያ የተመሰረተችባቸውን ሰባት ተራሮች ይወክላሉ።
በካኤልያን ተራራ ላይ ያለው የላተራን ቤተመንግስት እስከ ዛሬ ድረስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋነኛው ጽሕፈት ቤት ነው። የአረማዊው ሮማ መንግስት ዋነኛ ማዕከል በካፒቶላይን ተራራ ላይ የነበሩት የጁፒተር፣ የጁኖ፣ እና የሚነርቫ ቤተመቅደሶች ነበሩ፤ የላተራን ቤተመንግስት የእርሱን ቦታ ተክቷል።
አስሩ ቀንዶች ወታደራዊ ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ የሚሰጡ አስር አምባ ገነን መሪዎች ናቸው፤ ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ የሚሰጡትም የመጨረሻው ፖፕ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ዓለምን መምራት እንዲችል ነው።
እነዚህ መሪዎች እንደ ነገስታት ዘውድ አልጫኑም፤ ነገር ግን እንደ ነገስታት ስልጣን አላቸው።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
“የስድብ ስም”።
ስድብ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን መቃረን ወይም በውስጡ ከተጻፈው ማጉደል ነው።
ቤተክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ስም አጉድለዋል። ስላሴያዊው አምላክ ስም የለውም። ለሶስት አካላት አንድ ስም ሊገኝላቸው አይችልም።
እግዚአብሔር ግን ስም አለው።
እንደ አብ እግዚአብሔር ያህዌ ተብሎ ይጠራ ነበር (ይህም ጌታ ማለት ነው)፤ እርሱም ከአይሁዶች በላይ ይኖር ነበር።
የመለኮት ሙላት በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ሆኖ በአካል በተገለጠ ጊዜ ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ሆኗል። “እግዚአብሔር ወልድ” ማለት አንችልም፤ አንደኛ ይህ መጠሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፣ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ነው - እግዚአብሔር ደም እና ስጋ አይደለም። ስለዚህ ኢየሱስ የተባለው ሰው እግዚአብሔር አልነበረም።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ [በኢየሱስ] የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
ሰው በሆነው በኢየሱስ ውስጥ የኖረው መንፈስ እግዚአብሔር ነው። ሰው በሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ኖረ። አማኑኤል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር።
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
ዮሐንስ 14፡17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
ዛሬ “የእግዚአብሔር መንፈስ” በክርስቶስ አካል ውስጥ እየኖረ ነው (ክርስቶስ የሚለው ቃል ትርጉሙ የተቀባ ነው) የክርስቶስም አካል በሰማያት በምሕረት ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል። እግዚአብሔር ያንኑ መንፈስ ያመኑ ሰዎች እና ሴቶች ልብ ውስጥ ማፍሰስ ይችላል። ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወይም በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ይባላል። እያንዳንዱ አማኝ ከእግዚአብሔር መንፈስ ላይ በመጠን ተሰፍሮ ይሰጠዋል። ቤተክርስቲያን በሙሉ በአንድነት የእግዚአብሔር ሙላት ይኖርባታል። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” ብሎ አይናገረም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ መስዋእት ሆኖ በምሕረት ዙፋን ላይ የተቀመጠውን የክርስቶስን አካል አያካትትም። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ በሕዝቡ ልብ ውስጥ መኖር ይችላል።
እግዚአብሔር እንደ አብ ሆኖ በተገለጠ ጊዜ ከሕዝቡ በላይ ይኖር ነበር። እግዚአብሔር እንደ ልጅ ሆኖ ሲገለጥ ከሕዝቡ ጋር ነበረ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊቀባ ሲመጣ እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ማደሪያውን ሕዝቡ ውስጥ አደረገ። ስለዚህ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ስሙ ኢየሱስ ነው። ጌታ እና ክርስቶስ የሚሉት ቃላት ማዕረጎች ናቸው። ኢየሱስ ተብለው የሚጠሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ስለ የትኛው ኢየሱስ እየተናገርን እንደሆን ግልጽ ለማድረግ አንዱን ወይም ሁለቱንም ማዕረጎች በስሙ ላይ አክለን መጥራት አለብን። ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ጌታ ኢየሱስ ወይም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ።
የእግዚአብሔር ስም “አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ” ነው ማለት ስሕተት ነው። ሶስት ማዕረጎች አንድን ስም ሊተኩ አይችሉም።
የእግዚአብሔር ስም “አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ” ነው ካልን የክርስቲያኖችን አምላክ ስም የለሽ አድርገነዋል።
እግዚአብሔር ሰው ሆነ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የውሃ ጥምቀት የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ ተምሳሌት ነው። መንፈስ ቅዱስ አልሞተም፤ ደግሞም አልተቀበረም። እግዚአብሔር አብ አልሞተም፤ ደግሞም አልተቀበረም። ስለዚህ አብ እና መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ የተለዩ አካላት ከሆኑ የውሃ ጥምቀት ከአብ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለውም።
በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ቦታ የእግዚአብሔር ስም ነው ተብሎ የተጠራ ስም ሁሉ ትልቅ ስሕተት ነው።
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የባሕር ዳርቻ የራሱ የሆነ ትርጉም አለው። እርሱም በየብስ እና በባሕር መካከል የሚከፍል መስመር ነው።
ባሕር እረፍት የሌላቸውን፤ የሰዎችን አመለካከት በመከተል እና ከጊዜው ሁኔታ ጋር አብረው የሚዋከቡ ሐጥያተኞችን ይወክላል። ከባሕር ዳርቻ የሚገኝ አሸዋ በማዕበል እና በሌሎች የተፈጥሮ ኃይላት አማካኝነት ከዓለቶች ላይ እየተሸረፈ የደቀቀ ድንጋይ ነው። ክርስቶስ ቃሉ ዓለታችን ነው። አማኞች ዳግመኛ የተወለዱት ከእርሱ ነው፤ ደግሞም የቃሉ (የመጽሐፍ ቅዱስ) አካል ናቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 10፡4 ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
ስለዚህ በባሕር ዳርቻ የሚገኘው አሸዋ ጻድቃንን ይወክላል። የባሕሩ ዳርቻ የሚወክለው የባሕሩን ገደብ ነው። ጻድቃንን ሊያጠፉ ለሚነሱ ሐጥያተኞች (ባሕር) እግዚአብሔር እስከ ተወሰነ ርቀት ብቻ ነው እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቅድላቸው። ጻድቃን ክፋት አልፎ መሄድ የማይችልበትን ገደብ ይወክላሉ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላችሁ አቋም ስሕተት እንዳይስፋፋ የሚደርገው አስተዋጽኦ ከምታስቡት በላይ ነው። የጥንት ክርስቲያኖች በሮም ከተማ እስታዲየም ውስጥ በአንበሶች ተበልተዋል። ነገር ግን አንድ አማኝ በአንበሳ በተበላ ቁጥር ብዙ አረማውያን በአማኞቹ የእምነት ጽናት ተደንቀው ጌታ ኢየሱስን ተቀብለዋል። በስተመጨረሻ አማኞችን ለአንበሳ አሳልፎ መስጠት እንዲቆም ተደረገ። አንድ የክፋት ገጽታ ገደቡ ላይ ደርሶ ቆመ ማለት ነው። እንዲህ ዓይነቶቹ ዘግናኝ ነፍስ ግድያዎች ግን ብዙዎች አረማውያንን ወደ መዳን አምጥተዋቸዋል። አንድ ሌባ የዘላለምን ሕይወት ያገኘው ከኢየሱስ ጎን ተሰቅሎ ነው። በስጋ የሚደርስብን መከራ ትዕቢተኛና ግብዝ፣ ግዴለሽ እና በራሳችን የምንመካ ሰዎችን ከራሳችን አልፈን የሚያድነንን ጌታ እንድንመለከት ያደርገናል። እግዚአብሔር ክፉውን በመጠቀም ከተኛንበት እንቅልፍ ነቅንቆ ይቀሰቅሰናል፤ ነገር ግን ይህ ክፉ ሰዎችን ሁሉ እንዳያጠፋ ገደብ ያደርግበታል።
ኢዮብ 26፡10 ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥
በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ።
ይህች የምንኖርባት ምድር ገደብ አላት። የምድር አንድ ቀን 24 ሰዓታት ነው። ብርሃን እና ጨለማ እርስ በራሳቸውን ይገድባሉ፤ ስለዚህ ሁለቱም ውስን ሰዓት አላቸው። ምድር በባሕር ይገደባል። ሕይወት በሞት ይገደባል። በስተመጨረሻ ጨለማ በብርሃን ይተካል፤ ባሕርም ለዘላለም ይጠፋል። ሞት፣ ባሕር፣ እና ጨለማ በምድር ላይ ለሚኖሩ ችግሮች ሁሉ ተምሳሌት ናቸው። እነዚህ ሁሉ ለእድገታችን ያስፈልጉናል። መከራ፣ ሃዘን፣ ሐጥያት፣ ስሕተት፣ ሽንገላ፣ ዓለማዊነት፣ ወዘተ. እኛን ለመፈተን፣ ለማጠንከር፣ ለመቅጣት እና የምንፋለመው ጠላት እንዲኖረን ይጠቅማሉ።
ትግል የእድገት መርህ ነው።
ሽንፈት እና መከራ የእኛ ባሕርይ ተቀጥቅጦ የሚቃናባቸው የሚስተካከልባቸው እና የሚጠነክርባቸው መዶሻዎች ናቸው። ከስሕተት ጋር ስናመቻምች የታላቁ መከራ ማገዶ ሆነን እንቀራለን።
ስለዚህ በዚህ ምድር ላይ ያሉ ችግሮች ሁሉ ለጥቂት ጊዜ እኛን ቀጥቅጠው ለማቃናት እንዲሁም እግዚአብሔር በፈለገው ቅርጽ ለመቅረጽ የተቀመጡ መሳሪያዎች ናቸው፤ እነዚህም መሳሪያዎች በሕይወታችን ውስጥ እኛ የፈለግነውን ሳይሆን እግዚአብሔር የፈለገውን ውጤት ያስገኛሉ።
ራዕይ 21፡1 አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።
ራዕይ 21፡25 በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥
ባሕር የማይኖርበት እና ጨለማም የማይኖርበት ዘመን ይመጣል።
ስሕተት እና ክፋት የተላኩበትን አገልግሎት እስኪፈጽሙ ድረስ ብቻ የሚኖሩ ጊዜያዊ ክስተቶች ናቸው።
ኢዮብ 14፡5 ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
ማንም ቢሆን እግዚአብሔር ካዘጋጀለት ገደብ አልፎ መሄድ አይችልም። የወደቀው የሰው ባህርይ ከተፈጥሮአዊ ስግብግብነቱ እና ራስ ወዳድነቱ መላቀቅ አለበት።
እያንዳንዳችን እግዚአብሔር ከጣለብን ገደብ ጋር ተስማምተን መኖርን መለማመድ አለብን።
እነዚህ ገደቦች እኛ ከምድር ላይ እንዳንጠፋ የሚጠቅሙ ናቸው።
በሰውነታችን ውስጥ እያንዳንዱ ሴል ወይም ሕዋስ ከመጠኑ እና ከአገልግሎቱ አንጻር የተገደበ ነው። ካንሰር ማለት የተሰጠውን ገደብ አልፎ የሄደ ሴል ነው፤ ይህ ሴል ለማድግ ብሎ ያድጋል። እግዚአብሔር ክፋትን እና ስሕተትን በሰባት የተለያዩ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያንን ለመቅረጽ ይጠቀምባቸዋል፤ ነገር ግን በስተመጨረሻ ክፋት ፈጽሞ ይወገዳል። እስከዚያው ግን ቤተክርስቲያን በዘመኗ ያሉ ክፋቶችን መጋፈጥ እና መቃወም ይጠበቅባታል።
ኤርምያስ 5፡22 በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።
ደግሞም መልካም በክፉው ላይ ገደብ ይጥልበታል። ክፋት እውነትን ሊያጠፋ አይችልም። አማኞች በስደት ምክንያት ሊበታተኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእነርሱ መበታተን የተነሳ እውነት እየሰፋች ትሄዳለች። አማኞችም እምነታቸውን ሊክዱ ይችላሉ ግን በቦታቸው አዳዲስ አማኞች ይተካሉ። መበስበስ እንዳይስፋፋ ጨው ይከላከላል። ልጆቹን ለማዳን እግዚአብሔር የክፋትን መስፋፋት እና ኃይል ይገድበዋል። ክፋት መፍሰስ የሚችለው እግዚአብሔር በፈቀደለት ቦይ ውስጥ ብቻ ነው። እግዚአብሔር እስከፈቀደለት ብቻ እንጂ ከዚያ አያልፍም።
(የሞንጎል ሰራዊት ሱቦዳይ በተባለው ብልህ ወታደራዊ መሪ እና ጀነራል እየተመራ ራሺያን እና ምሥራቅ አውሮፓን ወረረ። የሃንጋሪያ ሰራዊት ተደመሰሰ። ምዕራብ አውሮፓም ለዚህ ወረራ አደጋ ተጋልጣ ነበር ምክንያቱም ፖፑ ጀርመናዊ የሆነውን የሮማ መንግስት ገዥ በመዋጋት ተጠምዶ ነበር። አውሮፓ ደግሞ የሞንጎሎቹን ጀነራል ሱቦዳይ ሊገጥም የሚችል ጀነራል አልነበራትም። ከዚያም ከሩቅ ከሞንጎሊያ ኦጌዴይ የተባለው የጌንጂስ ካን ሶስተኛ ልጅ የሞንጎሎች ንጉስ ለ12 ዓመታት ከነገሰ በኋላ በመጠጥ ብዛት ሞተ። አውሮፓ ውስጥ ከሱቦዳይ ጋር የነበረው የመጀመሪያ ልጁ ጉዩክ አዲስ ኑጉስ በሚመረጥበት ምርጫ ለመሳተፍ ሰራዊቱን በሙሉ ከአውሮፓ ወደ ሞንጎሊያ መለሳቸው። ጉዩክ በአባቱ ቦታ ንጉስ ሆኖ ተመረጠ። ራሷን ማዳን ያልቻለችው አውሮፓ አንድ ሰው እሩቅ ቦታ በመሞቱ የተነሳ ልትተርፍ ቻለች። ስለዚህ እግዚአብሔር ፈቃዱ እንዲፈጸም በፈለገበት ቦታ የፈለገውን የማድረግ ኃይል አለው።)
ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
አሞጽ 3፡6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
ስዕል ውስጥ ርቀት እና ጥልቀትን ለመፍጠር ሰዓሊ ደመቅ ያሉ ቀለሞችን ብርሃን እንዲወክሉ ደብዘዝ ያሉ ቀለሞችን ደግሞ ጥላ እንዲወክሉ አድርጎ ይጠቀማል። ስዕል ውስጥ ብርሃን እና ጥላ ሙሉ በሙሉ በሰዓሊው ቁጥጥር ስር ናቸው። እያንዳንዱ የብርሃን እና የጥላ ቀለም ስዕል ውስጥ የተሰጠውን ውስን ቦታ ብቻ ነው መያዝ የሚችለው።
በእኛ ውስጥ መልካም ባህርይ ለመፍጠር እግዚአብሔር ብርሃን እና ጥላ የመሰሉ ክስተቶች ውስጥ እንድናልፍ ያደርጋል። ስለዚህ እግዚአብሔር መልካም እና ክፉ ሰዎችን እየተጠቀመባቸው እኛን ይፈትነናል፤ ይቀርጸናል። ሁለቱም ዓይነት ሰዎች ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ ናቸው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
መጽሐፍ ቅዱስ የትንቢቶች መጽሐፍ እንደመሆኑ ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮች ፍንጭ ይሰጠናል።
ምዕራፍ 13 የሁለት ኃይላትን መነሳት ይነግረናል፤ እነርሱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና አሜሪካ ናቸው። እነዚህ ሁለት ኃይላት ዓለምን ሁሉ የአውሬውን ምልክት ወደ መቀበል በማምጣት ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
1ኛ ተሰሎንቄ 2፡6 የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም።
እግዚአብሔር ክፋትን አያስወግድም። አልፎ አልፎ ክፋት እንዲያድግ ለመፍቀድ እግዚአብሔር የራሱን ኃይል ሰብሰብ ያደርጋል። እኛም የምንጋፈጠው ያ ክፋት የእምነታችን መፈተኛ ሆኖ ያገለግላል። ክፋት ሁልጊዜም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እውነት የሚቃረን ነገር ነው። እኛ ከተጻፈው ጋር ጸንተን እንቆም ይሆን? በተጻፈው እውነት ጸንተን መቆም ካልቻልን እኛ ራሳችን የክፋት አካል ሆነናል ማለት ነው፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን በሚቃረን መንገድ እየተንቀሳቀስን እግዚአብሔርን እያገለገልን ነን ካልን ራሳችንን እያታለልን ነን።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡7 የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።
እግዚአብሔር ክፋትን አላስቆመም። ሰዎች ዛሬም ሲጋራ ወይም መጠጥ ልጋብዝህ ብለው ይመጣሉ። ሰዎች በፊታችሁ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ እየጠሩ ይምላሉ። እናንተም ምን ዓይነተ ምላሽ እንደምትሰጡ እግዚአብሔረ ለማየት ይመለከታል። በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ከሚደረግባችሁ ጫና የተነሳ እጅ ብትሰጡና ከእነርሱ ጋር ብትመሳሰሉ የእውነት ከልባችሁ እግዚአብሔርን አታምኑም ማለት ነው።
እግዚአብሔር ግን በክፋት ላይ ገደብ ይጥላል። ክፋት እውነትን ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ላይ እንዲያጠፋት እግዚአብሔር አይፈቅድለትም። ሁልጊዜ የእውነተኛ አማኞች ቅሬታዎች ይኖራል፤ እነዚህንም ሰዎች ገለልተኛ ያደርጓቸዋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ጻድቃን እንዳይጠፉ ብሎ የክፋትን ሃይል ገደብ አድርጎበታል።
“ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን (ክፋት በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ) የሚከለክል (ክርስቶስ) አለ።”
ኢየሱስ በዳግም ምጻቱ ተገልጦ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ሲወስዳት የክርስቶስ ቅዱስ መንፈስ ከምድር ላይ ስለሚወሰድ ዓለም በሙሉ ወደ ታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ትገባለች።
ነገር ግን ክርስቶስ ቅዱሳንን በሰማያት ወደተዘጋጀው የሰርግ ግብዣ ለመውሰድ ቤተክርስቲያንን ከምድር ሲነጥቃት ክፋት በሙሉ ኃይሉ ምድርን ያጥለቀልቃል፤ ምክንያቱም በመዚያ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከምድር ላይ ይወሰዳል። ክፋት አሁን ብዙ መጥፎ ነገሮችን እየፈጸመ ነው የምትሉ ከሆነ ታላቁ መከራ እስኪጀምር ድረስ ጠብቁ።
“የዓመፅ ሚስጥር አሁን ይሰራልና።” የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ስሕተት የዚያን ጊዜ ጀምሮ በስራ ላይ ነበር። መከፋፈል ተጀምሮ ነበር።
1ኛ ቆሮንቶስ 1፡12 ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።
1ኛ ቆሮንቶስ 1፡13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?
ክርስቲያን መሆናችን አልበቃ ብሎናል። ስለዚህ የሆነ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል ለመሆን ስንል የሰው አመለካከት መቀበል ያለብን ይመስለናል። ከሰዎች ጋር አንድ የምንሆንበት መለያ ላያችን ላይ መለጠፍ እንፈልጋለን።
በዲኖሚኔሽን የተከፋፈሉ ቤተክርስቲያኖች የዓመፅ ሚስጥር ናቸው። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች የሰውን አመለካከት ለመደገፍ ብለው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ይለውጣሉ። ለአመራር ወደ ሰው ይመለከታሉ።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡8 በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል፤
በስተመጨረሻ ኢየሱስ በአርማጌዶን ጦርነት የክርስቶስ ተቃዋሚ እና ተከታዮቹን ያጠፋቸዋል። ከተከታዮች መካከል አትሁኑ።
ሌላኛዋ ዲኖሚኔሽን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ፕሮቴስታንት ልጆቿ ወደ እናታቸው ወደ ሮማ ካቶሊክ እየተመለሱ ናቸው። ይህ የሐይማኖቶች አንድነት እንቅስቃሴ ኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚው የሚነግስበትን ፖለቲካዊ-ሐይማኖታዊ ጥምረት ይፈጥራል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ጸንተው ቢኖሩ የክርስቶስ ተቃዋሚ የፖፑን ስልጣን በሚይዝበት ሰዓት እንደ ልቡ መስራት አይችልም። ፖፕ፣ ካርዲናል፣ ሊቀ ጳጳሳት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም፤ ከዚህም የተነሳ ሌላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ነገር ሲሰማ ግድ የሚለው ማነው። መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ እና አለመከተል በታላቁ መከራ ዘመን በምድር ላይ እንደ ጥፋት ውሃ በብዛት ለሚለቀቀው ክፋት በር ይከፍታል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡9 የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
የክርስቶስ ተቃዋሚ አሰራሩ ለብዙዎቻችን ግልጽ ስላልሆነ በቀላሉ ሊያስተን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈ በማመን የማትጸኑ ከሆነ ሰይጣን እናንተን ለማሳት ቀላል መንገድ ያገኛል። ከሰይጣን ተንኮል ራሳችንን የምናድንበት ብቸኛው መከላከያችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ስለዚህ መምረጥ አለብን። እንደ ብዙሃኑ እረፍት የሌለው ባሕር አካል ለመሆን ወይም ደግሞ እንደ ጥቂቶች ንጹህ የባሕር አሸዋ ለመሆን መምረጥ አለብን።
ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
ሰባት ራሶች።
ራዕይ 17፡9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት ምክንያቱም እውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ትባላለች።
ሮማ የሰባቱ ተራሮች ከተማ ተብላ ነው የምትታወቀው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ በሮም ከተማ ላይ ተሰይማለች። በጥንት ጊዜ አንድ አከባቢ ከተማ የሚባለው በዙርያው ግምብ አጥር ሲሰራለት ነው። ከዚህ በታች ያለው ካርታ የሮም ከተማ ከተመሰረተችባቸው ሰባት ተራሮች ዙርያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራውን ግምብ አጥር (በቀይ ቀለም) ያሳያል።
ሮሙለስ የንግድ መስመር በታይበር ወንዝ የሚያልፍበት ቦታ የክፍያ ጣቢያ አዘጋጀ። ተከታዮቹም በዙርያው በነበሩ ኮረብቶች ላይ መኖሪያ ቤታቸውን ሰሩ። በ7 ኮረብታዎች ላይ ቤቶቻቸውን ከሰሩ በኋላ በ7ቱ ኮረብቶች ዙርያ ግምብ አጥር ሰሩ። በዚያ ዘመን የተወሰኑ ቤቶች ወይም ሕንጻዎች በዙርያቸው አጥር ከታጠረ ያ ቦታ ከተማ ይባል ነበር።
የሰባቱ ኮረብቶች ከተማ እያደገች ሄዳ ሮም ከተማ ተባለች።
አስር ቀንዶች፡ እነዚህ ታላቅ ወታደራዊ ኃይል ያላቸው አስር አምባ ገነን መሪዎች ናቸው።
ቀንድ የአውሬዎች የኃይል ምልክት ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚ ዓለምን በሚመራ ጊዜ እነዚህ አስር አምባ ገነን መሪዎች ወታደራዊ ኃይላቸውን ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይሰጣሉ።
በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ለጥቂት ጊዜ በስልጣን ይቀመጣሉ።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
የተለያዩ ሃገሮች ሊሆኑ ይችላሉ (ለምሳሌ፡ ራሺያ እና ቻይና)፤ ነገር ግን በክርስቶስ ተቃዋሚው አመራር ስር ሆነው በአንድነት ይቆማሉ፤ ወታደራዊ ኃይላቸውንም ለክርስቶስ ተቃዋሚው ይሰጣሉ። የካቶሊክ ፖፕ ሆኖ ስለሚቀመጥ የክርስቶስ ተቃዋሚው ሲመጣ ሐይማኖታዊ ስልጣን ይይዛል፤ ደግሞም ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ይሆናል፤ ከዚህም በላይ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተከታዮች በቁጥር ብዙ እና በዓልም ዙርያ ብዙ ሃገሮች ውስጥ የተሰራጩ እንደመሆናቸው ሰፊ ፖለቲካዊ ስልጣንም ይኖረዋል። ኢክዩሜኒካል የተባለው የክርስትና ሐይማኖቶችን ሁሉ ወደ አንድነት ለማምጣት የተጀመረው ዘመናዊ እንቅስቃሴ ፕሮቴስታንቶችን እና ሌሎችንም ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለመሳብ ጥረት እያደረገ ነው። እነዚህ ሁሉ በካቶሊክ እምነትና ልማዶች በቀላሉ የሚታለሉ ስለሆኑ በዘመን መጨረሻ ለሚነሳው የክርስቶስ ተቃዋሚ ድጋፍ ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ የሚያስቆመው አይኖርም።
“በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ”።
ሮም የተባለችው በሰባቱ ተራሮች ላይ የተመሰረተችዋ ከተማ ከእግዚአብሔር ስም ጋር በተያያዘ ትልቅ ስሕተት ሰርታለች። “ስድብ” በጣም ጠንከር ያለ ቃል ነው። ስለዚህ በጣም ጠንቀቅ ማለት አለብን።
የስላሴን ጽንሰ ሃሳብ የፈተሩት አረማውያን ናቸው። አንድ አምላክ በሶስት አካላት። የሮማ ካቶሊክ እናት ቤተክርስቲያን ይህንን የስላሴ እምነት የተቀበለችው ከአረማውያን ነው። ልጆቿ የሆኑት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ይህንን ትምሕርት ከካቶሊኮች ነው የተቀበሉት። ስላሴ የሚለው ቃል ምፍ ቅዱስ ውስት አንድ ጊዜ እንኳ አልተጻፈም።
ስላሴ የተባለው አምላክ ስም የለውም።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “እግዚአብሔር አብ” ይናገራል፤ ነገር ግን አንድም ጊዜ እንኳ “እግዚአብሔር ወልድ” ወይም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” አይልም። “የመለኮት የመጀመሪያው አካል፣” “የመለኮት ሁለተኛው አካል፣” እና “የመለኮት ሶስተኛው አካል” የሚሉ አነጋገሮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ አይገኙም። ክርስቶስ በመለኮት ውስጥ ሁለተኛው አካል ነው ብሎ መናገር ትልቅ ስሕተት ነው፤ ምክንያቱም የመለኮት ሙላት በሙሉ በክርስቶስ ውስጥ መሆኑን በግልጽ ጽፏል።
እግዚአብሔር አብ የሚል ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።
ኢየሱስ እስከሚወለድ ድረስ እግዚአብሔር የሚያድርበት ልጅ አልነበረውም። ስለዚህ ኢየሱስ እግዚአብሔር በሙላት ያደረበት እና የተገለጠበት የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
ቆላስይስ 2፡8-9 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
የስላሴ ትምሕርት እግዚአብሔር ስም እንዳይኖረው ያደርጋል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚታወቀው ዘላለማዊ መንፈስ ማለትም አብ ባህርያቱን የሚገልጹ ብዙ ስሞች አሉት። ለምሳሌ JHVH ወይም YHWH ይባላል፤ እነዚህ ቃላት ግን አጠራራቸው ስለማይታወቅ ስሞች መሆን አይችሉም። ስም ማለት ሊጠራ የሚችለው ቃል ነው። ሰዎች በነዚህ ፊደሎች ላይ አናባቢዎችን በመጨመር ያህዌ ወይም ይሆዋ የሚሉ ቃላትን ፈጠሩ፤ እነዚህ ግን ጌታ የሚል ትርጉም ያላቸው ሰው ሰራሽ ማዕረጎች ናቸው። ልጁ ስም አለው፤ ስሙም ኢየሱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስም የለውም።
መንፈስ ቅዱስ እራሱን የቻለ አካል ነው ይላሉ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም። ይህም አያሳምንም።
እስቲ አሁን ለሶስቱም የሚሆን አንድ ስም አምጡ። ይህ የሚቻል አይደለም። ስለዚህ የክርስቲያኖች አምላክ ስም አልባ ሆኖ ይቀራል። የስላሴ ትምሕርት ጠፍቶ እንዳይቀር ቤተክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ስም ቦታ ሶስት ማዕረጎችን ተክተዋል፤ እነርሱም፡- አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው። እነዚህ ሶስት ማዕረጎች በራሳቸው ምንም ችግር የለባቸውም፤ ነገር ግን እነዚህ ማዕረጎች ስም ናቸው ብሎ መናገሩ አደገኛ ስሕተት ነው።
“የስድብ ስም”። በጣም መጠንቀቅ አለብን። ማንኛውም ሌላ ስም ወይም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ስም ነው ብሎ መናገር ትልቅ ችግር ውስጥ ይከተናል። የክርስቲያኖች አምላክ አንድ ሰብዓዊ ስም ብቻ ነው ያለው፤ እርሱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንን ስም በሌላ ስም እንድትለውጡ ማንም አያሳስታችሁ።
እግዚአብሔር መንፈስ በነበረ ጊዜ ያህዌህ ይባል ነበር። እግዚአብሔር እንደ ሰው ሆኖ በተገለጠ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተጠራ። አንድ ጊዜ የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ተብሎ ከተጠራ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛ ያህዌ (አንዳንዶች እንደሚሉት ይሆዋ) የሚለውን ስም አይጠቅሰውም። በብሉይ ኪዳን ዘመን ያህዌ (ወይም ይሆዋ) ተብሎ ይጠራ በነበረ ጊዜ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አንድም ጊዜ ኢየሱስ የሚለውን ስም አይጠቅሱም።
ስለዚህ የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ (JHVH) የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ ሆኗል።
ራዕይ 13፡2ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
አሁን ወደ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እንመለስ። ዳንኤል አራት ዓለም አቀፍ መንግስታት ሲነሱ አየ። የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ እዚሁ ተጠቅሰዋል። እነዚህ ሁሉ ለጥቂት ጊዜ ዓለምን ገዝተው ከዚያ በጦርነት ተሸንፈው ጠፉ። አራተኛው አውሬ አረማዊው ሮም ነው፤ ነገር ግን ባርቤሪያውያን ሮምን ባሸነፉ ጊዜ የሮም መንግስት እንደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆኖ “ከሞት ተነሳ”። ከዚህም የተነሳ የሮማ መንግስት መንፈስ አሁንም ዓለምን ይገዛል። ዳንኤል ባየው ራዕይ ውስጥ የምስሉ የብረት እግሮች የሮማ መንግስት ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ ግዛቶች ናቸው። እግሮቹ ውስጥ ንጹህ የነበረው ብረት የእግሮቹ ጣቶች ውስጥ የብረት እና የሸክላ ቅልቅል ሆነ። የአረማዊቷ ሮም መንፈስ ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ ስለገባ የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ማለት ክርስትና የተነሳ አረማዊነት ነው።
መዳን የአይሁድ እንጂ የአሕዛብ አልነበረም፤ ከዚያ በኋላ ግን መዳን መዳን በመስቀሉ አማካኝነት ወደ ምሰሉ እግሮች “ተሻገረ”፤ እነዚህም እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
ዳንኤል ለሁለተኛ ጊዜ ያየው ራዕይ ውስጥ እነዚያ አራት የአሕዛብ መንግስታት በጨካኝ አውሬዎች ተመስለዋል።
ባቢሎን አንበሳው ነው። አንበሳው በንስር ክንፎች ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ በመውጣት ከአማልክት ዘንድ ሚስጥርን ይሰማል።
ከዚህም የተነሳ የባቢሎናውያን ካሕናት ስርዓት የተዋጣለት የአረማውያን ክሕነት ተብሎ ይታወቃል፤ የባቢሎናውያን ሚስጥራትም በአረማውያን አሕዛብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ነበራቸው።
“የአንበሳ አፍ”። ነገር ግን አረማዊቷ ሮም እና የሮማ ቤተክርስቲያን አመሰራረታቸው ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሶስት አውሬዎች ማለትም የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዓለም አቀፍ መንግስታት ተጽእኖ ነበረባቸው። ባቢሎን አንበሳው ነበረ። የባቢሎን ሚስጥራት ልክ እንደ ስላሴ ከባቢሎን መጥተው ወደ ጴርጋሞን አለፉ ከዚያም ወደ ሮም ተሻገሩ።
የባቢሎን ሊቀ ካሕናት ፖንቲፍ ይባል ነበር። ፖፑ እስከ ዛሬም ድረስ ፖንቲፍ ይባላል። ፖፑ እስከ ዛሬም ስለ ስላሴ ያስተምራል። ሰዎች በግልጽ መረዳት የማይችሏቸውን ሚስጥራት ማስተማር ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈቀቅ እንዲሉ እና በሐይማኖታዊ ድርጅቶች ውስጥ ታስረው እንዲኖሩ ማድረጊያ ዘዴ ነው። እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ የገና ዛፍ የመሳሰሉ በሐይማኖት ውስጥ ክብር ያገኙ ቃላት ሰዎችን ያስገርሙዋቸዋል፤ ነገር ግን እነዚህ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላት መሆናቸውን እንኳ አያስተውሉም።
የዳንኤል ራዕይ ውስጥ ባቢሎን የወርቅ ራስ ሆና ነው የተመሰለችው። ስሕተት ስር እንዲሰድድ እና ለብዙ ዘመናት ጸንቶ እንዲቆይ ለማድረግ የገንዘብ እና የሃብት ድጋፍ ያስፈልጋል። የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖችም ወርቅ እና ገንዘብ ላይ የመሯሯት ዝንባሌ አላቸው።
“የድብ እግሮች”። የፋርስ መንግስት የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ መንግስት ነበር። ይህን መንግስት ለመመስረት በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የተሾሙ መሪዎች፣ ገዥዎች እና አስተዳዳሪዎች ያሉበት ደርጅታዊ መዋቅር አዘጋጅተዋል። ትልቅ የቤተክርስቲያን ድርጅት ለመመስረትም እንደ ፖፕ፣ ካርዲናሎች፣ የከተማ ገዥዎች፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ወዘተ. የመሳሰሉ ሹማምንጽ ያሉበት ሐይማኖታዊ የስልጣን ተዋረድ ያስፈልጋል። ከእነዚህ ማዕረጎች ውስጥ አንዳቸውም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ለፖፑ ታማኝ በሆነ ቄስ ነው የምትተዳደረው። ስለዚህ በአጥቢያ ቤተክርስቲያኖችም ውስጥ ሳይቀር የአንድ ሰው አመራር ተመስርቷል።
ትልቅ ሐይማኖታዊ ድርጅት እራሱን እያንቀሳቀሰ ይኖራል፤ ስለዚህ አንድ ግለሰብ ሊያስቆመው አይችልም። ብዙ ሰዎች ቢቃወሙትም እንኳ ድርጅቱ መንቀሳቀሱን ይቀጥላል። ስለዚህ ስሕተት እንዲቀጥል ለማድረግ ትልቅ ዲኖሚኔሽና ቤተክርስቲያን ያስፈልጋል። ስሕተት ሳይጠፋ እየተስፋፋ እንዲቀጥል የተከታዮች ቁጥር መብዛቱ አስፈላጊ ነው።
የዛሬ ቤተክርስቲያኖች ውጤታማነታቸውን ለማሳየት ወደ አባላቶቻቸው ቁጥር እንደሚያሳዩ ተመልከቱ። “ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም” ማለት ጀምረናል።
“ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር”። ነብሮች ፈጣን እና ቀልጣፋ ናቸው። ይህም ግሪኮችን ይወክላል። ግሪኮች አእምሮዋቸው ቀልጣፋ ስለሆነ የተዋጣላቸው ተከራካሪዎች ናቸው፤ ፍልስፍና እና የሒሳብ ትምሕርትነ የመሳሰሉ መሰረታዊ ትምሕርቶች የመጡት ከእነርሱ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤቶች እና ሴሚናሪዎች አዳዲስ አማኞች እንደ ዲኖሚኔሽናቸው እንዲያስቡ ማድረጊያ ወጥመዶች ሆኑ። የሚያስተምሩዋቸውን ከተማሩ ብቻ ነው ትምሕርታቸውን ጨርሰው የሚመረቁት። በተመረቁም ጊዜ አባል በሆኑበት ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት በገኘው ዶክትሪን ተሞልተው እድሜያቸውን በሙሉ ያንኑ ዶክትሪን ሲያስተምሩ ይኖራሉ። ሰው አንድ ነገር ከተማረ በኋላ መሳሰቱን ለመቀበል በጣም ይከብደዋል። ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?
“ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።”
ከሰው እይታ አንጻር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትልቅ የስኬት ምሳሌ ናት። ብዙ ስልጣን እና ተጽእኖ አላት። መጽፍ ቅዱስ ግን ከዚህች ትልቅ የቤተክርስቲያን ድርጅት በስተጀርባ ያለው ስልጣን ምንጩ ዲያብሎስ ነው ይላል።
በ312 ዓ.ም ኮንስታንቲን የሮማ ገዥ ሆነ። ከዚያም ለሮም ጳጳስ ውብ የሆነውን የላተራን ቤተመንግስት በስጦታ አበረከተ። ይህ ቤተመንግስት የተሰራው በካኤልያን ተራራ ላይ ነበረ፤ እርሱም ከመጀመሪያዎቹ የሮም ሰባት ተራሮች አንዱ ነው። ይህ ስጦታ ለሮም ጳጳስ ትልቅ ክብርና ተቀባይነት አጎናጽፎታል። ከአንድ ሺ ዓመታት በኋላ የታይበር ወንዝ አጠገብ ወደ ተሰሩት ወደ ትልልቆቹ የቫቲካን ሕንጻዎች ውስጥ ቢዛወሩም እንኳ ይህ የላተራን ቤተመንግስት እስከ ዛሬ ድረስ የሮማ ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት ሆኖ ቀጥሏል። በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ኮንስታንቲን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚሰጠው የስላሴ ትምሕርት እውቅና እና ድጋፍ ሰጠ። ለሮማ ጳጳስ ያደረገውን ድጋፍ ተጨማሪ ብዙ ገንዘብ እና ሀብት በመስጠት አጠናከረው። በ330 ዓ.ም አካባቢ ኮንስታንቲን ወደ ምስራቅ ወደ ኮንስታንቲኖፕል ሲሄድ ሮም ውስጥ በምዕራባዊው ግዛት ውስጥ በራሱ ቦታ እንደ ገዥ ትቶ የሄደው የሮማ ጳጳስን ነው። ከዚህም የተነሳ ጳጳሱ በፍጥነት ፖለቲካዊ ስልጣኑ እየጨመረ ነበር። በ378 ዓ.ም ጎት እና ሃንስ የተባሉ ነገዶች ምስራቃዊውን ገዥ ቫለንስ እና 20,000 ሮማውያንን ገደሉዋቸው።
ከዚያ በኋላ ምስራቃዊውን ግዛት የማስተዳደር ስልጣን ለቴዎዶሲየስ ተሰጠው። እርሱም እንደ ክርስቲያን ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ አልቀበልም አለ (ፖንቲፍ ማለት የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀ ካሕናት ነው)፤ ይህ ማዕረግ ከዩልየስ ቄሳር ጀምሮ በሮማውያን ነገስታት ስም ላይ ተቀጽላ ይደረግ ነበር። ቴዎዶሲየስ ዳማሰስ የተባለውን የሮማ ጳጳስ ፖንቲፍ በሚለው ማዕረግ መጥራት ጀመረ። ዳማሰስ ለሮማ ጳጳስነት የተደረገውን ምርጫ ከተቃዋሚዎቹ ተከታዮች 300 የሚያህሉትን በመግደል አሸነፈ። ዳማሰስ የንጉስ ቴዎዶሲየስ አጎት ነበረ፤ ከዚህም የተነሳ ፖለቲካዊ ጥበቃ ማግኘት ችሏል።
በ390 ዓ.ም ንጉስ ቴዎዶሲየስ ጳጳሱ አምብሮዝ በንጉስ ላይ መንፈሳዊ ኃይል እና ስልጣን እንዲኖረው ፈቀደ። ቴዎዶሲየስ ይህን ያደረገው በተሰሎንቄ ውስጥ ለገደላቸው 7,000 ሰዎች ማካካሻ እንዲሆን ነው። ቴዎዶሲየስ አረማውያንን ማሳደድ ጀመረ፤ ይህንንም ስደት መናፍቃንን ማለትም የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የተቃወሙ ሰዎችን ሁሉ ወደ ማሳደድ አስፋፋው። በ450 ዓ.ም አካባቢ ሊዮ ቀዳማዊ የተባለው የሮም ጳጳስ መናፍቃንን ወይም የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የተቃወሙ ክርስቲያኖችን የመግደል መብት አለኝ ብሎ አወጀ። ስለዚህ የካቶሊክ ፖፕ ስልጣኑ በፍጥነት እያደገ ሄደ።
ራዕይ 13፡3 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።
በ750 ዓመተ ዓለም አካባቢ ሮሙለስ በፓላቲኔት ኮረብታ ላይ ጥቂት ጎጆዎች መስራት ጀመረ፤ ቦታውም የታይበር ወንዝ ላይ ነገዴዎች ሲያልፉ የሚሻገሩበት ቦታ ነበረ። ከዚያም ነጋዴዎቹ ወንዙን ከመሻገራቸው በፊት ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቅ ጀመረ። በዚያም የሚኖረው ማሕበረሰብ እያደገ ሄዶ በዙርያው ያሉ ሰባት ኮረብታዎች ላይ ሕንጻዎች ተሰሩ። ከዚያ በኋላ በሰባቱ ኮረብታዎች ዙርያ ግምብ አጥር ለመስራት ወሰኑ። ሕንጻዎች በዙርያቸው ግምብ አጥር ከተሰራ ከተማ ይባሉ ነበር። ሮም የሰባቱ ኮረብታዎች ከተማ ተብላ ተጠራች። (ከተማይቱ ከታች ባለው ካርታ ውስጥ በቀይ ቀለም ምልክት የተደረገባት ቦታ ናት።) ከኮረብታዎቹ አንዱ ካፒቶላይን ኮረብታ የመንግስት ማዕከል እንዲሆን ተመረጠ። ከዚህ ኮረብታ ነበር በሮማ ግዛቶች ውስጥ ሁሉ መተዳደሪያ የሆነው ሕግ የታወጀው። በ395 ዓ.ም የሮማ መንግስት በሁለት ተከፈለ፤ በዚያን ጊዜም ሮም የምዕራባዊው ግዛት ዋና ከተማ ሆነች።
በጥቁሩ መስመር የተከበበው ቦታ ካፒቶላይን ኮረብታ ነው። የመንግስት ሕንጻዎች በዚህ ኮረብታ አናት ላይ ነበር የተገነቡት። በዚህ ካፒቶል ኮረብታ ላይ የተሰራው ዋነኛው ቤተመቅደስ ለስላሴዎቹ ጁፒተር፣ ጁኖ፣ እና ሚነርቫ የተሰራ ነው።
የታይበር ወንዝ ሰማያዊው መስመር ነው።
ከዚያ ወዲያ ባርቤሪያውያን ምዕራባዊውን የሮማ መንግስት አፈራረሱት። በዋነኝነት ከባርቤሪያውያን የተወጣጣው የሮማ ሰራዊት ጀነራል የሆነው ከጀርመኖቹ ሄሩሊ ነገድ የመጣው ኦዶዋሰር በ476 ዓ.ም የ16 ዓመቱን ወጣት የምዕራባዊ ሮማ መንግስት ገዢ የነበረውን ሮሙለስ ኦጋሰቱለስን ከስልጣን አስወርዶ እራሱ ኦዶዋሰር የኢጣልያ ንጉስ ሆነ። ሮሙለስ ከስልጣን ከመውረዱ በፊት ለ10 ወራት ብቻ ነበር የነገሰው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምዕራባዊው የሮማ መንግስት ፈረሰ። ኦዶዋሰር ሮም ውስጥ አልተቀመጠም፤ በዚህም ምክንያት ሮም ውስጥ መናገሻ የነበረው ካፒቶላይን ኮረብታ የሮማ መንግስት ዋና ከተማነቱ ቀረ። ከዚያ ወዲያ ቦታ ሕግ ማውጫ መሆኑ ቀረ። ካፒቶላይን ኮረብታ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለሞት የሆነ ቁስል ቆሰለ፤ ከዚያ በኋላ ሁለተኛ የዓለም መንግስት ማዕከል ሊሆን አልቻለም። ኢጣልያ ታላቅ ወታደራዊ ኃይል መሆኗ ከመቅረቱ ጋር ሮም እንደ ከተማነቷ ክብሯ እየደበዘዘ ሄደ። ሮም ዓለም የሚተዳደርበት ሕግ መፍለቂያ መሆኗ ቀረ።
ከዚያ በኋላ ብዙዎች ልብ ያላሉት ለውጥ ሆነ።
ዋና ጽሐፈት ቤቱን ሮም ከተመሰረተችበት ከሰባቱ የመጀመሪያ ኮረብታዎች መካከል ካኤልያን ኮረብታ ላይ ባለው ላተራን ቤተመንግስት ውስጥ ያደረገው የሮማ ጳጳስ በባርቤሪያውያን መካከል በስልጣን ከፍ እያለ ሄደ። በፈረሰው የሮማ መንግስት ፍርስራሽ ውስጥ ሕዝቡ ሰላም እና መረጋጋትን ፍለጋ ወደ ቤተክርስቲያን መመልከት ጀመረ።
ባርቤሪያውያን ነገስታት ለአጭር ጊዜ በዙፋን ይቆዩና በግፍ እየተገደሉ ነበር የሚሞቱት። ስለዚህ ለ500 ዓመታት ያህል ሳትወድቅ ጸንታ የቆየችዋ የሮም ቤተክርስቲያን ታስገርማቸው ነበር። 38ኛው የሮማ ጳጳስ ሲሪሲየስ በ400 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ተብሎ መጠራት ጀመረ። ከዚያ በኋላ ክፍለ ዘመናት እያለፉ ሲሄዱ የሮም ጳጳሳት ሁሉ ፖፕ ተብዬ መጠራት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ ማለት ጀመሩ። በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ፖንቲፍ ማለትም የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕን ነኝ አለ። ይህም በአረማዊያኖቹ ባርቤሪያውያን ዘንድ ትልቅ ክብር አስገኘለት። ፖፕ የተባለው የሮማ ጳጳስ ዘውድ እንዲጭንላቸው በማድረግ ባርቤሪያውያን ነገስታት ንግስናቸው ሕጋዊ እንዲሆንላቸው እና ለልጅ ልጆቻቸው እንዲተላለፍላቸው ለማድረግ ለራሳቸው ጥሩ ዘዴ አበጁ። ከዚያ በፊት ግን ንጉስን የገደለ ማንኛውም ሰው ይነግስ ነበር። ከዚህ የተነሳ ፖፑ ስልጣኑ እና ተጽእኖው እያደገ ሄደ። የሮማ መንግስት ሲፈራርስ የሮማ ፖፕ ሕዝቡን በምግብ እና በሚያስፈልጋቸው ነገር በመርዳት ቀስ በቀስ ሮምን እና በዙርያዋ ያሉ ግዛቶችን (የፖፑን ግዛቶች) እንደ መንግስት በማስተዳደር ቀዳሚውን ቦታ ያዘ። ፖፕ ሊዮ 3ኛው ንጉስ ሻርለሜይንን በ800 ዓ.ም የቅዱሱ የሮማ መንግስት ንጉስ አድርጎ በሾመው ጊዜ የፖፑ ክብርና እውቅና በብዙ እጥፍ ጨመረ። በ1200 ዓ.ም ፖፕ ኤነሰንት 3ኛው በአውሮፓ ነገስታት ላይ ሁሉ ስልጣን አለኝ አለ። ኦዶዋሰር የሮማ መንግስት ንጉስን ከስልጣን ባወረደው ጊዜ የሮማ መንግስት ያጣውን ስልጣን ፖፑ የራሱ አድርጎታል።
ከዚህም የተነሳ ካፒቶላይን ኮረብታ የስልጣን እና የሕግ መፍለቂያ መሆኑ ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ የሮም መንግስት ፖለቲካዊ ኃይልና ስልጣን ላይ ተሰንዝሮ የነበረው ለሞት የሆነ ቁስል በፖፑ ከፍ ከፍ ማለት አማካኝነት ተፈወሰ። ካኤልያን ኮረብታ ላይ የተቀመጠው ፖፕ በዓለም መንግስታት መካከል እውቅና የተሰጠው የክብር እና የስልጣን ስፍራ አገኘ። ዛሬም ፖፑ በዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሰሚነት እና ተጽእኖ አለው። እስከ ዛሬ ከተደረጉ የዓለም መንግስታት መሪዎች ትልቁ ስብሰባ በ2005 ዓ.ም የፖፕ ጆን ፖል ቀብር ስነስርዓት ላይ የተደረገው ስብሰባ ነው። ፖፑ 1.4 ቢሊዮን የሚሆኑ በዓለም ዙርያ የሚኖሩ ካቶሊኮች ላይ ታላቅ መንፈሳዊ ስልጣን አለው። ቫቲካን በዓለም ላይ ታላቅ ተጽእኖ ፈጣሪ የቤተክርስቲያን ድርጅት ሆናለች (ይህም በራዕይ ምዕራፍ 6 የመጀመሪያው ማሕተም ውስጥ በነጩ ፈረስ ምሳሌነት የተገለጠው አሳሳች ሐይማኖታዊ ኃይ) እና በሁለተኛው ማሕተም (በቀይ ፈረስ የተመሰለው ፖለቲካዊ ኃይል) እና (በሶስተኛው ጥቁር ፈረስ አማካኝነት የተገለጠው) የገንዘብ ኃይል ነው።
ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ (858 - 67) ከነገስታት ጋር እኩል መሆኑን ለማሳየት ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ ላይ ዘውድ የጫነ ፖፕ ነው።
ሐይማኖታዊ አሳሳችነትን የሚወክለው ነጩ ፈረስ። ቀስት የሌለው ደጋን የቀልደኛ የአታላይ ስራ ነው። ለቀስቱ ምንም ቃል የለውም።
3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
ገዥዎች እና ነገስታት ፖፑን ከጠላቶቹ ለመከላከል ወታደራዊ ኃይላቸውን አቀረቡ። በጨለማው ዘመን ውስጥ ፖፑም የራሱን ወታደራዊ ሰራዊት አደራጀ።
5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
ሐይማኖት ትልቅ ትርፍ ያለው ንግድ ሆነ። የስርየት ወረቀቶችን በመሸጥ ፖፑ የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተክርስቲያን እና የሲስቲን ቻፕልን መስራት ቻለ።
ሐይማኖት፣ ፖለቲካ፣ እና ገንዘብ የዓለም ስልጣን የሚከፈትባቸው ቁልፎች ናቸው።
ራዕይ 13፡4 ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም፦ አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።
አውሬ የስልጣን ተምሳሌት ነው። ሰዎች ሁሉ በውስጣቸው አንድ ሰውን የመከተልና የመታዘዝ ዝንባሌ አላቸው። የሚያደንቁትን ሰው እስከ ማምለክ መድረስ በብዙዎች ዘንድ ስር የሰደደ ችግር ነው። የፊልም ተዋናዮች፣ ዘፋኞች እንደ ጣኦት ሲመለኩ በሰው ውስጥ ያለውን ዝንባሌ ይገልጣሉ።
ሰዎች ለራሳቸው የገነቡት ትልቁ መንፈሳዊ ኃይል የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማርያም እና ቅዱሳን አምልኮ ይቀርብላቸዋል። ለፖፑ ተደፍተው በመስገድ ቀለበቱን ይስማሉ። ዘንዶው የዲያብሎስ ተምሳሌት ነው።
ራዕይ 12፡9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
በምድር የሚኖሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰይጣንን ማምለክ ይመርጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል እንዳለ ተቀብለው ማመን አይፈልጉም። እንደ ምኞታቸው እንዲኖሩ፣ እንደፈለጉ እንዲለብሱ፣ እንዲሁም መዳናቸውን ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ ሰርተው እንዲያገኙ የምትፈቅድላቸው ቤተክርስቲያን ይፈልጋሉ።
ሰዎች ዋነኛ ትኩረታቸውን የሚያደርጉትና የሚሯሯጡለት ጉዳይ ማመቻመች እና ሃብትን በማሳደድ የሚገኘውን ድሎት ነው።
ብዙ ሰዎች የሚጎርፉባት ቤተክርስቲያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት ምክንያቱም ከሁሉም የበለጠ የተከታይ ቁጥር አላት። ይህን ትልቅ ሐይማኖታዊ ድርጅት በይፋ የሚወክለው ፖፑ ነው። እያንዳንዱ ፕሬዚዳንት ምንም ያህል ኃይለኛ ቢሆን እንኳ የራሱን ሃጋር ብቻ ነው የሚመራው። ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ራስ እንደመሆኑ ፖፑ በሁሉም ሃገር ውስጥ ተከታዮች አሉ፤ ከዚህም የተነሳ ስልጣኑ በዓለም ዙርያ ባሉ ተከታዮቹ ዘንድ ሁሉ በመንሰራፋቱ የትኛውም ፕሬዚዳንት ፖፑን ሊወዳደር አይችልም። በፖፑ ላይ ማንም ጦርነት ሊያውጅ ወይም ፖፑን ሊወጋ የሚችል የለም ምክንያቱም በሁሉም ሃገሮች ውስጥ ያሉ እንዲሁም ፖፑን ሊወጋ የተነሳው ሃገር ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ካቶሊኮች ፖፑን ይደግፉታል።
ራዕይ 13፡5 ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።
ፖፑ ተጽእኖው በዓለም ዙርያ ሁሉ መድረስ ችሏል፤ ነገር ግን እርሱ የሚያስተምረው የካቶሊክ አስተምሕሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ አይደለም። ስለዚህ የእርሱን ስራ እግዚአብሔር አይወደውም።
42 ወራት ማለት ሶስት ዓመት ከግማሽ ነው። ይህም ሶስት ዓመት ከግማሽ በስተመጨረሻ የፖፑን ስልጣን የሚቀማው የክርስቶስ ተቃዋሚ ዓለምን የሚጨቁንበትና የሚገዛበት ዘመን ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚ ዓለምን በሚቆጣጠር ሰዓት በዓለም ላይ የሚሰራው ግፍና ጭካኔ አሁን መገመት ከምንችለው በላይ እጅግ የከፋ ነው። ናዚዎች 6 ሚሊዮን አይሁዶችን የጨፈጨፉበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚፈጽመውን ጭካኔ ለማሳየት እንደ ቅምሻ የሚሆን ክፋት ነው።
ይህ የሶስት ዓመት ከግማሽ ጊዜ የፖፑ ስልጣን ወደ መጨረሻ ከፍታው የሚወጣበት ጊዜ ነው። በምድርም ላይ ለሰዎች ከሁሉ እጅግ የከፋ ጊዜ ይሆናል። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ካዘዘው ውጭ ሌላ አማራጭ የፈለጉ ሰዎች በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሰይጣን ያልተቀላቀለ ቁጣ እና ክፋት ይፈስስባቸዋል። ይህ ከባድ መከራ ምን ያህል እንደተሳሳቱ አስደንጋጭ በሆነ መንገድ ያረጋግጥላቸዋል።
ራዕይ 13፡6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።
ፖፑ መጽሐፍ ቅዱስን አይከተልም። መጽሐፍ ቅዱስን መቃረን ስሕተት ብቻ አይደለም - ስድብ ነው። አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ የተባሉ ሶስት ማዕረጎች የእግዚአብሔር ስም ናቸው ማለት ትልቅ ስሕተት ነው። ውብ የሆኑ ሕንጻዎች የሞሉባት ቫቲካን የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት ማለት ከባድ ስሕተት ነው። እግዚአብሔር መኖሪያው ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ነው። ማደሪያ ድንኳኑ ዳግም የተወለዱ ሰዎች ልብ ነው።
ከ2,000 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር ፓለስታይን ውስጥ (ቅድስቲቱ ሃገር) በቤተ መቅደስ (የተቀደሰ ስፍራ) ውስጥ ይኖር ነበር። እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱስ። እነዚህ ቦታዎች ቅዱስ የሆኑት ከእግዚአብሔር መገኘት የተነሳ ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ትቶ ወጣ። በ70 ዓ.ም ሮማውያን ቤተመቅደሱን አፈረሱት። ስለዚህ እግዚአብሔር በዚያ ቤተመቅደስ ውስጥ አይኖርም። አሁን እግዚአብሔር የሚኖረው ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ነው። ስለዚህ አሁን ቅዱሳን ሰዎች አሉ (ምክንያቱም ዳግመኛ ሲወለዱ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ውስጣቸው ይገባል እንጂ ወደሆነ የተቀደሰ ቦታ አይደለም የሚገባው)። ስለዚህ ቫቲካንም ይሁን የትኛውም ሌላ ሕንጻ የእግዚአብሔር መቅደስ ወይም ማደሪያ ሊባል አይችልም።
ፖፑ ወደ ሞቱ ቅዱሳን ይጸልያል። ካቶሊኮች ወደ ማርያም እና ወደ ሌሎች ቅዱሳን ያለማቋረጥ ጸሎት ያቀርባሉ። ወደ ሞቱ ሰዎች ጸሎት ማቅረብ የተሳሳተ መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ይህም ልምምድ ወደ ሟርተኝነት ያመራል። በጥንት ዘመን አያቶች ቅደመ አያቶችን የማምለክ ልማድ ነበረ፤ ወደ ሞቱ ቅዱሳን መጸለይ ከዚህ ዓይነቱ አምልኮ በምንም አይለይም። ትልቅ ስሕተት ነው።
ራዕይ 13፡7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
በ400 ዓ.ም አካባቢ የሂፖው (በሰሜን አፍሪካ የሚኖረው) ኦጋስተን የካቶሊክ እምነትን የሚቃወሙ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ይፈቀዳል ብሎ አስተማረ። ይህን ትምሕርት በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ የካቶሊክ እምነትን የሚቃወሙ ክርስቲያኖች መግደል ይፈቀዳል ብሎ ተረጎመው። ስለዚህ መግደል ተጀመረና ዓመታት ሲያልፉ እየተባባሰ ሄደ። በጨለማው ዘመን እና ማርቲን ሉተር የተባለውን ጀግና የተሃድሶ መሪ ለመቃወም ካቶሊኮች ባስነሱት ጸረ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ገድላለች። በአሁኑ ዘመን ደግሞ ጦርነቱ መንፈሳዊ መልክ ይዟል፤ ስለዚህ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ የሚገዛበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም የአሰራር ሞዴል ሆኗቸዋል። በሰዎች አመለካከት ላይ የተመሰረተ ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት በሰዎች አእምሮ ላይ የሚሰለጥነ የአውሬው ምልክት ነው። አእምሮን መቆጣጠር እና ሰዎች እውነቱን እንዳያውቁ ማድረግ ካቶሊኮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ እና ሌሎች ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ ማድረጊያ ዘዴ ነው።
የአውሬው ምልክት የሚደረገው በግምባር ማለትም አእምሮ ባለበት ቦታ ነው። ስለዚህ አእምሮ በቤተክርስቲያን የተሳሳተ ትምሕርት ይሞላል።
ራዕይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።
ከዘመናት መፈጠር በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ የተወሰኑ ስሞች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲጻፉ አደረገ፤ እርሱም የበጉ ሕይወት መጽሐፍ። እነዚህ ስሞች እኛ ተለውጠን አዲስ አካል ስንለብስ ነው የሚገለጡልን። አዲሱ ስማችሁ የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተጻፈው ቃል ምላሽ ትሰጣላችሁ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ጸንታችሁ በመከተል የክርስቶስ ሙሽራ አካል ትሆናላችሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ተመርምሮ ሊረጋገጥ የማይችል ነገር ማመን ከፈለጋችሁ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ በማመን መዳን ትችላላችሁ ግን የሙሽራይቱ አካል አትሆኑም። በታላቁ መከራ ዘመን ከእንቅልፍ እንድትነቁ አስደንጋጭ የቅስቀሳ ድምጽ ትሰማላችሁ፤ በዚያም ጊዜ ስለ እምነታችሁ እንድትሞቱ ይጠበቅባችኋል። አንድ ሺ ዓመታትም ካለፉ በኋላ ለፍርድ ቀን ከሙታን ትነሳላችሁ። በታላቁ መከራ ውስጥ እምነታችሁን ካልካዳችሁ ትድናላችሁ ግን ለዘላለም ከታላቂቱ ከተማ ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ውጭ ትኖራላችሁ፤ ምክንያቱም አዲሲቷ ኢየሩሳሌም የሙሽራይቱ አዲስ መኖሪያ ናት።
ራዕይ 13፡9 ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
በዚህ ዘመን ትልቁ እና እጅግ አስፈላጊው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ቃል መስማት እና እየታዘዙ መኖር ነው።
ከዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንዱን መምረጥ አለብን።
ቃሉ ወይም ዓለም፤ አንዱን እንምረጥ።
ክርስትና ወይም ቤተክርስቲያናዊነት።
የሰርግ ግብዣውን ወይም አውሬውን።
እራት እንበላለን ወይም አውሬው ይበላናል። ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ እሬሳዎችን የሚበሉ ጥምብ አንሳዎችን አስቡ።
ስለዚህ መምረጥ አለባችሁ።
ራዕይ 13፡10 ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
ትዕግስት ያስፈልጋል ምክንያቱም ክፉው ስራውን ሰርቶ እስኪጨርስ ድረስ ተፈቅዶለታል። የክፋት ጽዋ መሙላት አለበት። የእግዚአብሔርን ጊዜ መጠበቅ አለብን።
እምነት የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት ብቻ ነው።
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
የካቶሊክ እምነት በጣም ብዙ ሰዎችን የዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ባሪያ አድጓቸዋል። የዚህ ዓይነቱ ባርነት መጨረሻው ተመልሰው የማይወጡበትና ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መግባት ነው።
ባቢሎን፣ ግብጽ፣ እና ባርቤሪያውያን በሙሉ ሐይማኖታቸውን ያመጡት ከአረማዊነት ጉድጓድ ውስጥ ነው። ቤተክርስቲያናዊነት (ከክርስትና ጋር አንድ አድርገው ቢቆጥሩትም አንድ አይደለም) ዓላማው ወደ አረማዊነት ጉድጓድ ውስጥ ጎትቶ ሊያስገባን ነው።
በጨለማው ዘመን እና ልክ የጨለማው ዘመን እንዳበቃ ከአስር ሚሊዮን በላይ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎች በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ተገድለዋል። በስተመጨረሻ የክርስቶስ ተቃዋሚ ዓለምን ሁሉ ለመቆጣጠር የፖፑን ስልጣን ቀምቶ ከያዘ በኋላ የእግዚአብሔርን አዲስ ኢየሩሳሌም ለመኮረጅ ቫቲካንን ትቶ ይወጣና ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዳል። ከዚያም ወታደራዊ ኃይላቸውን ለክርስቶስ ተቃዋሚ የሚሰጡት አስሩ አምባ ገነን መሪዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ይጠሉና የቫቲካን ከተማ ላይ ኑክሊየር ቦምብ ይጥላሉ። የኑክሊየር ቦምብ ሰው ከፈጠራቸው የጦር መሳሪያዎች ሁሉ የመጨረሻው ኃይለኛ አውዳሚ መሳሪያ ነው። የዚያን ጊዜም በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የገደለችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእጇን የምታገኝበት ጊዜ ይሆናል።
እግዚአብሔር ያልተናዘዝናቸውን ሐጥያቶች አይረሳቸውም።
ይህ አውሬ የዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ታላቅ ኃይል ነው፤ ይህም ኃይል ሰይጣን የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ተጠቅሞ በቤተክርስቲያን የገንዘብ ዓቅም አማካኝነት ዓለምን ለመግዛት ይመቸው ዘንድ ሰዎች እንዲያዘጋጁለት ያደረገው ኃይል ነው።
በጨለማው ዘመን ፖፑ ሐይማኖታዊ ኃይሉን በነበረው ጊዜ እና የአውሮፓ ካቶሊክ ነገስታትን የጦር ሰራዊቶች ተጠቅሞ ክርስቲያን ተቃዋሚዎቹን መጨፍጨፍ በሚችልበት ጊዜ ስልጣኑን በሚገባ ማደራጀት ችሏል።
ነገር ግን በ1750 ዓ.ም አካባቢ እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ በስድስተኛው የፊልደልፊያ (የወንድማማች መዋደድ) ቤተክርስቲያን ዘመን ቅድስና እና የወንጌል ስርጭነትን በተመለከተ መስበክ ጀመረ። የዚህ አስደናቂ ሰው ተጽእኖ በስፋትና በርቀት ከመሰራጨቱ የተነሳ የመንግስትን ኃይል ተጠቅሞ ወንድሞችን የመግደሉ ሃሳብ ወዲያ ተቀባይነት እያጣ ሄደ።
ስለዚህ ፖፑ በመንፈሳዊ ኃይሉ ዓለም ሁሉ የመግዛት ሃሳቡን የሚደግፍለት ሌላ አውሬ፣ ሌላ ፍጥረታዊ ኃይል እንዲነሳለት አስፈለገው። ክርስቲያኖችን መግደል ፋሽኑ አለፈበት። ስለዚህ ከመግደል ይልቅ የረቀቀ ዘዴ ተፈጠረ፤ እርሱም ክርስቲያኖችን ካቶሊክ ባልሆኑ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ባሪያ እንዲሆኑ ማድረግ እና ከዚያም በታላቅ ኢክዩሜኒካዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት እነዚህን ቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት ማምጣት ነው። ከዚያም የክርስቶስ ተቃዋሚ የፖፑን ስልጣን ቀምቶ ከያዘ በኋላ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ አንድ የማድረግ ኢክዩሜኒካዊ እንቅስቃሴን በራሱ ቁጥጥር ስር ማድረግ ቀላል ይሆንለታል።
በቀጣዩ ምዕራፍ ውስጥ በምድር ላይ ሁሉ ኃያል የሆነችን አንድ ሃገር መነሳት እናያለን፤ እርሷም አሜሪካ ናት።
የአሜሪካ ሚና ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት በስተመጨረሻ በክርስቶስ ተቃዋሚው ስልጣን ስር ይወድቅ ዘንድ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን ወደ አንድነት ወይም ኢክዩሜኒካዊ እንቅስቃሴ ማስገባት ነው።
የተደራጀ ሐይማኖት ዓይኖቹ ትልቅ ገንዘብ እና የአባላት ቁጥር ማብዛት ላይ ነው። በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ መሪነቱን የያዙት የአሜሪካ ትልልቅ ሃብታም ቤተክርስቲያኖች ናቸው። በአሜሪካ ቤተክርስቲኖች ውስጥ ጎልተው የሚታዩት ዓለማዊ ብልጭልጭ፣ የጦፈ ንግድ እና ዲስኮ ሙዚቃ ናቸው። የአምልኮ ፕሮግራሞቻቸው እንደ ዓለማዊ መዝናኛ ፕሮግራሞች ዓይን የሚስቡ ናቸው፤ ማራኪ የንግግር ችሎታ ያላቸው ሰባኪዎቻቸውም የሚሰብኩት የብልጽግና ወንጌልን ነው። በአንድ ግለሰብ ፓስተር የሚመሩ ቤተክርስቲያኖች የዘመኑ ፋሽን ሆነዋል። አፍ የሚያስከፍቱ ሴት ሰባኪዎችም ተነስተዋል። ተፋቶ እንደገና ማግባትም ይቻላል፤ ማን ይጠይቃቸዋል። ወሲባዊ ሐጥያትም ሲፈጸም ማንም ምንም አይልም። ይህ ሁሉ የንግድ ውድድር የሞላበት ቤተክርስቲያናዊነት ውጤት ነው። የኔ ቤተክርስቲያን ካንተ ቤተክርስቲያን የተሻለችና የበለጠች ናት ይላሉ። የኔ ቤተክርስቲያን ካንተ ቤተክርስቲያን ይልቅ ምቹ ናት፤ ደግሞም ተቀባይነት ያላቸውን የሕዝብ አመለካከቶች በተሻለ መንገድ ታስተናግዳለች።
የአሜሪካ ፋሽኖች ዓለምን ሁሉ እየመሩ ናቸው። ጂንስ፣ ቲ-ሸርት፣ ናይኪ ስፖርት ጫማዎች፣ ኬፕ ወደ ፊት እና ወደ ኋላ አዙሮ ማድረግ። ማክዶናልድ በርገር፣ ኮካኮላ፣ እና ፋስር ፉድ። ትልልቅ ሱፐር ማርኬቶች። ኢንተርኔት። ጉግል። የጠፈር ምርምር። አይፎን። አይፓድ። አይፖድ። አቶሚክ ቦምብ መጀመሪያ ያፈነዱት አሜሪካኖች ናቸው፤ ያፈነዱትም አላማጎርዶ የሚባል ቦታ ነው (ስሙ ከአርማጌዶን ጋር ይቀራረባል)።
ከ10 የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች 9ኙ አሜሪካ ውስጥ ነው የሚገኙት። ስለዚህ አሜሪካዊ ሃሳቦች በአሜሪካ ዶላር ብርታት የተነሳ ዓለምን ሁሉ አጥለቅልቀዋል። አሜሪካ ሁሉን ነገር የምታደርገው በስፋት ነው፤ የቀረው ዓለም ደግሞ ይከተላታል። አሜሪካን ይወዷታል፤ ይጠሉዋታልም፤ ግን ቢወዷትም ቢጠሏትም ሁልጊዜ ታስገርማቸዋለች። የአሜሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ዓለንም በሙሉ ያንቀሳቅሳል። ዓለም ሁሉ ከሚበላው ስንዴ ግማሹ አሜሪካ ውስጥ ነው የሚመረተው። አሜሪካኖች በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች አሸንፏል። አሜሪካኖች የጀመሩትን የኑክሊየር ጦር መሳርያ መታጠቅና ጠፈርን የማሰስ ፖሊሲ ራሺያዎች ተከትለውታል። ነገር ግን ራሺያ ራሷን በኑክሊየር ለማስታጠቅ እና ጠፈርን ለማሰስ ባደረገችው ሙከራ ውስጥ የኢኮኖሚ ኪሳራ ደርሶባታል። አሜሪካኖች ቬትናም ውስጥ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ የረቀቀ ቦምብ እና በራዳር የማይታዩ የጦር አውሮፕላኖችን በመፍጠር የጦር ሰራዊታቸውን እንደገና አደራጅተዋል። አሁን ዓለም በሙሉ የአሜሪካን የጦር ሰራዊት አደረጃጀት ስርዓት ለመከተል እየተፍጨረጨረ ነው። ይህች አሜሪካ የምትባል አስደናቂ ሃገር ዓለምን በሙሉ ከኋላዋ ታስከትላለች።
ነገር ግን ወዴት እየሄዱ እንዳሉ ማወቅ አለብን።
ራዕይ 13፡11 ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።
ሌላ አውሬ፤ አሜሪካ ውስጥ ብቻ የሚገኝ እንስሳ፤ የአሜሪካ ጎሽ። የአሜሪካ ጎሽ ከትከሻው ጀምሮ እስከ ራሱ ድረስ የበግ ጠጉር በመሰለ ጠጉር የተሸፈነ እንስሳ ነው።
ዮሐንስ እንደዚህ ዓይነት እንስሳ አይቶ አያውቅም፤ ስለዚህ ከበግ ጠቦት ጋር አቀራርቦ አሰበው።
ዮሐንስ ይህንን እንስሳ በግ ይመስላል ማለት ይችል ነበር። የበግ ጠቦት መምረጡ መንፈሳዊ አንድምታ አለው። ክርስቶስ የእግዚአብሔር በግ ነው፤ ስለዚህ ይህች በኢኮኖሚ ታላቅ የሆነች ሃገር አነሳሷ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነበር። የአሜሪካ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሺንግተን “በፍጹም በአፉ ውሸት ባለመናገር” ይታወቃል። አብራሃም ሊንከን “እውነተኛው አብርሽ” ተብሎ ነበር የሚታወቀው። አሜሪካኖች በ1776 ነጻነታቸውን ካወጁ በኋላ ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የመጣ ፈረንሳዊ ስለ አሜሪካ ሲናገር መድረኮቿ በጽድቅ እሳት የደመቁባት ሃገር ብሎ ነበር።
የአሜሪካ ነጻነት መግለጫ በሰው እጅ ከተጻፉ ሕገ መንግስታዊ ሰነዶች ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ ታላቁ ሰነድ ነው። እነደዚህ በመልካም መንፈሳዊነት የተነሳችው አሜሪካ ቀስ በቀስ ማንም ሳያስተውል የዓለም ታላቅ ኃያል ሃገር ወደ መሆን ደረሰች። ከሁለት የዓለም ጦርነቶች በኋላ አሜሪካኖች የዓለም ኃያል ሃገር ሆነው ተገለጡ። ከዚያ በኋላ ግን ብዙ ነገሮች ተለወጡ። ግፍ በዛ፤ ከመጀመሪያዎቹ የአሜሪካ ነዋሪዎች ጋር የተደረጉ ብዙ ውሎች ተጣሱ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፕሬዚደንት ሩዚቬልት የአቶሚክ ቦምብ ሚስጥር የያዙ ሰነዶች በዲፕሎማሲያዊ አውሮፕላኖች ወደ ራሺያ እንዲገቡ አድርጓል። ራሺያ ምስራቅ አውሮፓን እንድትቆጣጠር አድርጓል። ለሚስቱም ታማኝ አልነበረም። ፕሬዚደንት ክሊንተን ዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ውስጥ ከምትሰራ ሴት ጋር ዝሙት ፈጽሟል። ኔልሰን ሮክፌለር ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሊወዳደር አልቻለም ምክንያቱም ሚስቱን ፈቶ አግብቷል። ከዚያ በኋላ ግን ሚስቱን ፈቶ ያገባ ሮናልድ ሬገን በ1980 ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመርጧል። አሜሪካ ውስጥ ስነ ምግባር እየወደቀ ሄደ።
ፕሬዚዳነት ኦባማ የተባበሩት መንግስታት በእስራኤል ላይ ያደረገውን ውግዘት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣኑን ተጠቅሞ መሻር ሲችል አልሻረም።
አሜሪካ ጉልበቷ እየጨመረ ቢሄድም በስነ ምግባር ግን እየተበላሸች ነው የሄደችው። ዘንዶው ማለትም ሰይጣን ፖለቲካዊ ስልጣንን በመቆጣጠር አሜሪካ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቃ እንድትሄድ አድርጓል። ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ የአሜሪካ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይነበብ የሚከለክል ሕግ ወጣ። ያም ዓመት ዊልያም ብራንሐም የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የተጻፉትን የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ገልጦ ያስተማረበት ዓመት ነው። በዚያው ዓመት ውስጥ ፖፑ እና የአሜሪካ ካቶሊክ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ ሞቱ።
የአሜሪካ ልዕለ ኃያልነት ዓለምን ሁሉ ስላስደነቀ ዓለም ሁሉ አሚሪካ በመራችው መንገድ እየተከተለ ነው። አሜሪካ ደግሞ ዲኖሚኔሽናዊ “ቤተክርስቲያናዊነትን” በማራመድ ፋና ወጊ ሆናለች።
ይህ አውሬ የተነሳው ከምድር ነው። የሮም አውሬ ደግሞ በ1620 ዓ.ም የተሰደዱ ክርስቲያኖች አሜሪካ በደረሱ ጊዜ በ70 ሚሊዮን ሕዝብ ብዛት ከተጨናነቀችው ከምዕራብ አውሮፓ ነው። ይህም የሕዝብ ብዛት የተመሰለው በባሕር ነው። ስለዚህ ምድር ጥቂት ሕዝብን ይወክላል። የታሪክ ምሑራን ሰሜን አሜሪካ መጀመሪያ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢንዲያኖች ይኖሩባት እንደነበረ ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እስፔይኖች ሚክሲኮን ተቆጣጠሩና ፈንጣጣ የተባለ ክፉ በሽታ ወደ ሜክሲኮ አመጡ። የአሜሪካ የመጀመሪያ ነዋሪዎች ይህንን በሽታ የሚቋቋሙበት የመከላከል ብቃት በሰውነታቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ከሕዝባቸው ብዙዎቹ በበሽታው አለቁ። ስለዚህ ከአውሮፓ በክርስትና ምክንያት ተሰደው የመጡ አባቶች በ1620 ዓ.ም አሜሪካ ሲደርሱ የሰሜን አሜሪካ ውስጥ ተበታትነው የሚኖሩ የመጀመሪያ የምድሪቱ ተዋሪዎች ከ10 ሚሊዮን አይበልጡም ነበር። አሜሪካ ከምዕራብ አውሮፓ በስፋት ስለምትበልጥ ሕዝቦቿ ተበታትነው ነበር የሚኖሩት። ወደ አሜሪካ የሄዱ አባቶች ወደዚያ የሄዱበት ምክንያት አውሮፓ ውስጥ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይደርስባቸው የነበረውን ስደት ለማምለት ነው።
ዘንዶው ሰይጣን ነው።
አሜሪካ ድሮ ነዋሪዎቿ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሸሽተው ነበር የመጡት፤ አሁን ግን ስልጣንን ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰጥታለች።
በ2020 አሜሪካኖች ሶስት ካቶሊኮች እንዲመሩዋቸው መርጠዋል። እነርሱም ባይደን፣ ሃሪስ፣ እና ፔሎሲ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ናቸው።
ካፒቶላይን ኮረብታ ላይ የነበረው የመጀመሪያው ቤተመቅደስ ለወንድ አምላክ ማለትም ጁፒተር እና ለሁለት ሴት አምላኮች ለጁኖ እና ሚነርቫ የተሰራ ነበር።
ወንድም ብራንሐም ከተናገራቸው ትንቢቶች መካከል ስድስተኛው ትንቢት ሊፈጸም ጊዜው እየቀረበ ነው።
60-1113 ኩነኔ በውክልና
ከዚያ ወዲያ እነዚህ ሴቶች መመረጥ የሌለበት ሰው እንዲመረጥ ያደርጋሉ፤ ቀጥሎ አንዲት ታላቅ ሴት አሜሪካ ውስጥ ስትነሳ አያለሁ። እርሷም ዝንጥ ብላ የለበሰችና ቆንጅዬ ነች፤ ነገር ግን ጨካኝ ናት። የአሜሪካን ሕዝብ ወደ ጥፋት ትመራለች። (ይህች ሴት “የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልትሆን ትችላለች።”)
ራዕይ 13፡12 በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
ሮም የዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖቶች እናት ናት። አሜሪካ በሃብት ብዛት እና በቤተክርስቲያኖች ብዛት አንደኛ ናት። ስለዚህ በዲኖሚኔሽናዊ አስተሳሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ታደርጋለች። ዲኖሚኔሽናዊ አስተሳሰብ መሰረቱ የሰው ጥበብ እና ልማድ ነው። የሮማ ካቶሊኮች በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ሁሉ የሚኮረጅ የረጅም ጊዜ ልማዶች አሉዋቸው። ከካቶሊክ ልማዶች መካከል ዋነኛዎቹ የስላሴ ጽንሰ ሃሳብ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈንታ በሶስት ማዕረጎች ማጥመቅ ናቸው። ፕሮቴስታንቶችም እነዚህን ልማዶች ተቀብለዋል፤ ልማዶቹን በመቀበል አንደኛ መሪ ናት። ክሪስማስ መከበር የተጀመረው አረማውያን የፀሃይ አምላክ ልደት ነው ብለው በስፋት የሚያከብሩትን በዓል ለመቀናቀን ነው። ዛሬ የፀሃይ አምላክ የተወለደበት ቀን ብለው የሚያከብሩ ሰዎች የሉም ነገር ግን በቁሳዊነት እና በንግድ እንዲሁም በብልጽግና ወንጌል የተተበቡ የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች ክሪስማስን በማክበር ዓለምን ሁሉ ይመራሉ (ክሪስማስ እራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል ነው፤ የሚከበርበት ቀን ዲሴምበር 25ም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም)። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት አክብሩ አላለንም። ስለዚህ በዓለም ዙርያ ያሉ ቤተክርስቲያኖች የካቶሊክ እምነትን የምታራምደዋን አሜሪካ ተከትለው ነው ክሪስማስን የሚያከብሩት።
ራዕይ 13፡13 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።
13 ልዩ ቁጥር ነው። ከላይ የተጠቀሰው ቃል የሚገኘው ምዕራፍ 13 ቁጥር 13 ላይ ነው።
13 ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ ቁርኝት ያለው ቁጥር ነው።
በዚህ ቃል ውስጥ የተጠቀሱት “ድንቆች” የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ድንቆች ናቸው።
አሜሪካ የፈጠረቻቸው የዘመናዊ ሳይንስ ድንቆች በሕዝብ ዓይን ውስጥ ትልቅ አድናቆትን አትርፈውላታል።
አሜሪካ ራሷን የቻለች ሃገር የሆነችው በ1776 ዓ.ም በምስራቅ በኩል ሕብረት ፈጥረው በተጣመሩ 13 እስቴቶች ነው።
ስለዚህ የመጀመሪያው ባንድራቸው 13 ከዋክብት እና 13 መስመሮች ነበሩት።
ዛሬም ባነድራቸው 13 መስመሮች ናቸው ያሉት፤ ነገር ግን እንደ ኬንታኪ፣ ሉዊዚያና፣ አሪዞና እና የመሳሰሉ ሌሎች እስቴቶች ወደ ሕብረቱ በመቀላቀላቸው ከዋክብቱ 50 ሆነዋል።
የአሜሪካ መንግስት አርማ ውስጥ ንስር አለበት (ይህም አሜሪካ በአየር ኃይል ገዥ መሆኗን ያመለክታል)፤ ንስሩም በእግሮቹ 13 ቅጠሎች ያሉት የወይራ ቅርንጫፍ (የሰላም ምልክት) እና 13 ቀስቶች (የጦርነት ምልክት) ይዟል። ይህ ዓርማ የክብር ክበብ በሚባለው ቦታ 13 ከዋክብት አሉት፤ ባንድራ ውስጥ ደግሞ 13 መስመሮች አሉት። በላቲን የተጻፈው መፈክር 13 ፊደሎች አሉት፡- "E Pluribus Unum" ትርጉሙም “አንድነት በስብጥር” (ከብዙ ወደ አንድ) ማለት ነው።
አርማው አሜሪካ በጦር ሜዳ አሸናፊ መሆኗን (ቀስቶች) እና ሰላም (የወይራ ቅርንጫፍ) ያመለክታል።
አሜሪካ የዓለም ገዥ የሆነችባቸው ያለፈው ክፍለ ዘመን ሁለቱ ትልቅ የሳይንስ ስኬቶች በ1945 ሒሮሺማ ላይ የፈነዳው አቶሚክ ቦምብ እና በ1969 ኒል አርምስትሮንግ ጨረቃ ላይ መውጣቱ ናቸው።
አቶሚክ ቦምቡ ከ10 ኪሎሜትር (6 ማይልስ) ከፍታ ላይ ነው የተወረወረው፤ ከዚያም መሬት ሊደርስ 700 ሜትር ሲቀረው ፈነዳ። ከዚያም ከፀሃይ የደመቀ የእሳት ኳስ ወደ መሬት ወረደና በዙርያው ከሶስት ኪሎሜትር በላይ ያሉ ቦታዎችን በሙሉ አወደመ።
የአሜሪካ አውሬ በጦርነት ወቅት እሳት ከሰማይ አወረደ።
ይህ ቦምብ የፈጠረው ድንጋጤ እና ፍርሃት ጃፓን 2ኛው የዓለም ጦርነት እንዲያበቃ ቶሎ እጅ ለመስጠት አስገድዷታል። አሜሪካ ብቻ ነበረች አቶሚክ ቦምብ ያለት፤ ስለዚህ የዓለም ሃገራት ሁሉ አሜሪካ የሁሉም ታላቅ መሆኗን አምነው ተቀበሉ። የአሜሪካ ክብርም ጨመረ።
ይህ ፎቶግራፍ የኑክሊየር ቦምብ የሚፈጥረውን አስፈሪ የእሳት ኳስ እና ጥፋት ያሳያል።
እንዲህ ዓይነቱን አስፈሪ የጦር ቴክኖሎጂ የፈጠረች ሃገር አሜሪካ ብቻ ናት፤ እስከ ዛሬም ድረስ በጦርነት ወቅት ሁለት አቶሚክ ቦምብ የጣለች ሃገር አሜሪካ ብቻ ናት። ሁለቱም ቦምቦች የጃፓን ከተሞች ላይ ነው የወደቁት።
ሰዎች በዓይናቸው እያዩ እሳት ከሰማይ ወደቀ።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን የረገጠው ሰው ንስር ወይም በእንግሊዝኛ “ኢግል” በተባለ ተሸከርካሪ አማካኝነት ነው ጨረቃ ላይ ያረፈው፤ (ይህም ስም ከአሜሪካ መንግስት አርማ ስም ጋር አንድ ነው)። ከጨረቃ ሲመለሱ ከባድ ሥራ የሆነባቸው ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ተመልሶ መግባት ነው። ወደ ጨረቃ የሄዱበት መንኩራኩር ወደ ምድር ሲመለስ በሰዓት 40,000 ኪሎሜትር እየበረረ ነበር የመጣው። ይህ ከፍተኛ ፍጥነት መንኩራኩሩ ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲደርስ ከሚፈጥረው በጣም ከባድ ሰበቃ የተነሳ የመንኩራኩሩ የሙቀት መከላከያ ከ1,600 ዲግሪ የሚበልጥ ሙቀት ይፈጥራል። ከዚያም እንደ ፍም የቀላው የሙቀት መከላከያ ከላዩ ትናንሽ የእሳት ፍንጣሪዎችን በመርጨት አላስፈላጊ የሆነውን ሙቀት ከመንኩራኩሩ ላይ ያስወግደዋል። ከዚህም የተነሳ መንኩራኩሩ ውስጥ የተቀመጡ ሰዎች ሳይወብቃቸው ይሄዳሉ። መንኩራኩሩ ወደ ምድር ሲወርድ ለሶስት ደቂቃ ከግማሽ ያህል አመጣጡ እንደሚንበለበል ተወርዋሪ ኮከብ ይመስል ነበር። ከዚያም በምድር ዙርያ ጥቅጥቅ ያለው ከባቢ አየር የመንኩራኩሩን ፍጥነት ሲቀንሰው ፓራሹቱ እንዲዘረጋ በመንኩራኩሩ ዙርያ የሚነደው ነበልባል ይጠፋል። ይህ የእሳት ኳስ ወደ ምድር ሲወርድ ወደ ጨረቃ የተደረገው ጉዞ የመጨረሻ ደረጃ ነበር፤ ቀጥሎ ሲመለሱ መርከበኞች እና አውሮፕላኖች ሊቀበሏቸው ይጠብቋቸዋል። ጨረቃን የረገጡ ሰዎች ያሏት ሃገር አሜሪካ ብቻ ናት። ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ የትኛውም ሌላ ሃገር ጨረቃ ላይ አልወጣም። ስለዚህ አሜሪካ በጠፈር ምድምር በተደረገው ውድድር አሸናፊ በመሆኗ በዓለም ዙርያ ዝናዋ ከፍ አለ።
ወደ ጨረቃ ሄዶ የሚመለስ መንኩራኩር በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲገባ ከይህን ፎቶ ይመስላል።
ወደ ጨረቃ ሄዶ የነበረ መንኩራኩር በእሳት ነበልባል ታጅቦ ሲመለስ በርቀት የተነሳ ፎቶ መንኩራኩሩ ከምድር ከባቢ አየር በላይ እየበረረ ሲመጣ ከኋላው የሚከተለው እሳት ርስመቱ 125 ማይልስ ያህላል።
ይህም በሰላም ጊዜ የአሜሪካ አውሬ ከሰማይ እሳት ሲያወርድ ማለት ነው።
እነዚህ ሁለት ክስተቶች አሜሪካ በቴክኖሎጂ ከሁሉ በላይ የመጠቀች መሆኗን እና እነዚህ የሚያክሉ በጣም ውድ ሳይንሳዊ ጀብዱዎች ለመፈጸም የሚበቃ የገንዘብ አቅም ያላት ሃገር መሆኗን ገልጠዋል። ከዚህ የተነሳ ዓለም ሁሉ ወደ አሜሪካ ይመለከታል፤ አሜሪካም ትመራቸዋለች። ራሺያ ወደ ጨረቃ በተደረገው ውድድር ከአሜሪካ ጋር ልትወዳደር ሞከረች ግን አልቻለችም። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ራሺያ የጦር መሳሪያ በማከማቸር ከአሜሪካ ጋር ልትወዳደር ሞከረች፤ በዚህም ሙከራዋ የኢኮኖሚ ኪሳራ ውስጥ ወደቀች። የራሺያ ገጽታ ደበዘዘ፤ የአሜሪካ ገጽታ ግን እየደመቀ ሄደ።
ራዕይ 13፡14 በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።
በሽተኞችን መፈወስ እና ሙታንን ማስነሳት የመሳሰሉ ምልክቶችን ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
በዚህ ቃል ውስጥ “ምልክቶች” የተባለው የቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት መምጣት ነው።
ፕሮቴስታንቶች ከካቶሊኮች ተገንጥለው በመውጣት ፖፑን የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ብለውት ነበር። አሁን ደግሞ ካቶሊኮች እና ፕሮቴስታንቶች እርስ በራሳቸውን የተራራቁ ወንድማማቾች ይላሉ።
የተለያዩ እምነቶች እና አስተምሕሮዎች ያሉዋቸው ቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና እምነታቸው አንድ ዓይነት እንደሆነ እንዲያስመስሉ የሚያስችላቸው “ፈዛዛ የሆነ ዲኖሚኔሽናዊ ተዓምር” ነው።
ዋና ትኩረት የሚደረገው የአምልኮ ፕሮግራሞች ላይ የሚገኝ የሕዝብ ቁጥር ላይ እስከሆነ ድረስ ስለ አስተምሕሮ ማንም ስለማይገደው ማንም የፈለገውን ማመን ይችላሉ። ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ዋነኛው አስተምሕሮ ስላሴ ነው። የስላሴ ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ብዙ ቃላትን የሚጠቀም ትምሕርት ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች አሁን እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ለመመስረት መጨነቅ ትተዋል።
“የመለኮት የመጀመሪያው አካል፣” “የመለኮት ሁለተኛው አካል፣” “የመለኮት ሶስተኛው አካል፣” “አንድ አምላክ በሶስት አካላት፣” “ክርስቶስ የመለኮት አካል ነው፣” “እግዚአብሔር ወልድ፣” “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” - ከእነዚህ ቃላት አንዱ እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም። በዚህ መልኩ የሰዎች አመለካከት የብዙዎችን አእምሮ ባፈዘዘበት ጊዜ ሰዎች የእግዚአብሔር ስም እንደጠፋባቸው እንኳ አላስተዋሉም። ስላሴ ብለው ለሚያውቁት አምላክ አንድ ስም የለውም። ስለዚህ ሰዎች ፍዝ የሆኑ እና ያልጠሩ ትምሕርቶችን እና እምነቶችን በመላመዳቸው የተነሳ ስሕተቶችንም እንዲሁ ሳያስተውሉ ይቀበላሉ፤ ለምሳሌ፡- በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ እና ይህ የእግዚአብሔር ስም ነው ብሎ ማሰብ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዕድሜ ከሁሉ የቀደመች ዲኖሚኔሽን ናት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሮማ መንግስት ሲወድቅ እርሷ ሳትወድቅ በማለፍ ከዚያ በኋላ ለባርቤሪያውያን ነገስታት ዘውድ በመጫን ባርቤሪያውያን ነገዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን እየተቀዳጀች ባርቤሪያኖችን ካቶሊክ አድርጋቸዋለች። በጨለማው ዘመን ውስጥ ሮም የቀደመውን የሮማ መንግስት መልሳ ልታስነሳ ሙከራ አድርጋለች፤ ነገር ግን ከወታደራዊ ኃይል እጥረት የተነሳ ይህ ሙከራ አልተሳካም። ከዚያ ብልጥ ሆኑና ትኩረታቸውን ቤተክርስቲያንን በማጠናከር፣ የገንዘብ አቅማቸውን በማሳደግ፣ እና ፖለቲካዊ ኃይላቸውን በመገንባት ላይ አደረጉ። የዲኖሚኔሽናዊ ስኬት መንገዱ ይህ ነው። ዛሬ ሌሎቹ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች የአሜሪካን ታላቅ ሃብት በመከተል በካቶሊክ ቤተክርስቲያን መንገድ እየሄዱ ናቸው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አሜሪካ ውስጥ በሃብት አንደኛ ድርጅት ናት።
ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
የአውሬው ምስል ማለት ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ በአንድ ላይ እንዲያመልኩ ወደ አንድነት እየሳበ ያለው ኢክዩሜኒካዊ እንቅስቃሴ ነው። በዚህ አንድነት ውስጥ አስተምሕሮ ላይ ትኩረት አይደረግም ምክንያቱም ስለ አስተምሕሮ መነጋገር መለያየትን ያስከትላል። ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ትክክል መሆን ላይ ትኩረት እስካላደረጉ ድረስ የፈለጉትን ማመን ይችላሉ። ከአስር በላይ የተለያዩ የውሃ ጥምቀት ዓይነቶች አሉ፤ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እስካልሆኑ ድረስ ሁሉምን ዓይነት ይቀበሉዋቸዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅን ቤተክርስቲያኖች አይፈቅዱም። ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖትን መከተል ግዴታ ይሆናል። አንድ ሰው የአንድ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን አባል እንዲሆን ይገደዳል። እውቅና የተሰጣቸው ኢክዩሜኒካዊ ቤተክርስቲያኖች ብቻ መናገር ወይም መስበክ ይፈቀድላቸዋል። ከዚህ ውጭ ያሉ ሰዎች ሁሉ መስበክ ይከለከላሉ፤ ተጽእኖዋቸውም ይታፈናል። ታላቁ መከራ ሲጀምር ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ያልተነጠቁ አፈንጋጮች በሙሉ ይገደላሉ። የቤተክርስቲያን አባል የሆኑ ሰዎች ሁሉ ትምክሕተኞች ናቸው። ምንም ስሕተት ወይም አደጋ እንደሌለባቸው ስለሚያምኑ መታረም ያስፈልጋችኋል ሲሏቸው አይቀበሉም። ምንም ነገር አያስፈልጋቸውም፤ መሳሳታቸውን ማንም እንዲነግራቸው አይፈቅዱም። በምቾት ለመኖር የሚበቃ ሃብት እስካላቸው ድረስ ከዲኖሚኔሽናዊ እምነታቸው ፈቀቅ አይሉም። ከ45,000 በላይ የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እያንዳንዱ እኔ ነኝ ትክክለኛ ይላሉ። ግን ሁሉም የተለያዩ ናቸው። ስለዚህ ሁላቸውም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። ነገር ግን ማንም ግድ የለውም። መዳን የሚችሉት አባል ለሆኑበት ቤተክርስቲያን ታማኝ በመሆን ይመስላቸዋል።
አሁን የተጧጧፈው እንቅስቃሴ ሰዎችን ሁሉ ወደ ዲኖሚኔሽናዊ እምነት ውስጥ ለማስገባት ነው። አሜሪካ ከቀረው ዓለም ሁሉ የሚበልጡ የሰባኪዎች ብዛት ስላላት የእንቅስቃሴው መሪ እሷ ናት። ይህን እውነታ ለማየት ከፈለጋችሁ ዝማሬ እና አምልኮ እንዴት እንደተለወጠ ተመልከቱ። አክብሮት በተሞላ አምልኮ ፈንታ የሚያስደንስ ሙዚቃ ተተክቷል። አንዲትን ቤተክርስቲያን ተወዳጅ የሚያደርጋት የምታዘጋቸው መዝናኛ ፕሮግራም ሆኗል።
የአውሬው ምስል ማለት በኢክዩሜኒካዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ወደ አንድ ዓለም አቀፍ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ድርጅት የሚሰበሰቡበት አንድነት ነው።
የየትኛውም ድርጅት ሕይወቱ ገንዘቡ ነው።
አንድ ዓለም አቀፍ የሐይማኖት መሪ ማለትም የመጨረሻውን ፖፕ ለማዘጋጀት እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ በአንድ ሰው ማለትም በፓስተሩ አገዛዝ ስር መውደቅ አለባት። “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጻፈው፤ እንደዚያም ሆኖ ግን ባልታወቀ መንገድ ቤተክርስቲያን ላይ ያለ ቦታው አለቃ ሆኖ ተቀምጧል። ቤተክርስቲያን ለፓስተሩ እየተገዛች ናት፤ ይህም ለዲኖሚኔሽን ለመገዛት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ፓስተሩ እረኛ ነው የሚል ጥቅስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ይህ የሰው አመለካከት ብቻ ነው። የትኛዋም ቤተክርስቲያን ለአንድ ሰው እንድትገዛ አልተባለችም። ይህ አሰራር የመጣው በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ቄስ የአንድ ጉባኤ አለቃ ተደርጎ ከሚሰለጥንበት ልማድ ነው። ነገር ግን ድርጅቶች እንደዚያ ነው የሚያድጉት፤ ስለዚህ ፕሮቴስታንቶች የካቶሊኮችን ምሳሌ ተከትለዋል። የአሜሪካ ፓስተሮች ከባሕር ማዶ በሌሎች ሃገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ፓስተሮች የገንዘብ ድጋፍ ብቻ ካደረጉ ጉባኤዎች የአሜሪካን እምነት እንዲከተሉ ተጽእኖ ማድረግ ይችላሉ። ለምሳሌ ሞርሞኖች ከአሜሪካ ይመጡና ሰዎችን ሞርሞን ለማድረግ ይሰብካሉ። የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ አመለካከታቸው ይህን የሚመስል ነው።
አሜሪካ ከሁሉም ሃገሮች የበለጠ ገንዘብ አላት። አሜሪካ ገንዘቧን በዓለም ዙርያ ሁሉ ታሰራጫለች፤ ገንዘቡዋን የምትሰጣቸው ሃገሮች ሁሉ እምነቷንና አመለካከቷን እንዲቀበሉ ይገደዳሉ። በዚህ ምክንያት በዓለም ዙርያ ሁሉ የሚኖሩ ሰባኪዎች ራሳቸውን ሽጠው ለሃብታሞቹ የአሜሪካ ዲኖሚኔሽኖች ተገዥ ይሆናሉ፤ በዚህም መንገድ እነዚህ ዲኖሚኔሽኖች በዓለም ዙርያ ሁሉ ይስፋፋሉ። “ለቤተክርስቲያን እድገት” ድጋፍ ከሚያደርገው የአሜሪካ ዶላር የተነሳ የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖቶች በዓለም ዙርያ እየተስፋፉ ይሄዳሉ፤ እነዚህ ሁሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉላቸው የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች ጋር ተስማምተው ቢኖሩ ብዙ የገንዘብ እርዳታ ያገኛሉ። የገንዘብ ድጋፍ የሚያቀርብ አካል ሁልጊዜ አለቃ ይሆናል።
ራዕይ 13፡16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥
አሜሪካ ዓለምን ሁሉ ወደ ገንዘብ ባርነት ውስጥ ትጥላለች። ብድር በቀላሉ መቅረቡ ብዙ ሰዎችን የብዙ ገንዘብ ባለ ዕዳ አድርጓቸዋል። ሰዎች ስለ አውሬው ምልክት በሁለት መንገድ ነው የሚያስቡት። አንደኛው ሃሳባቸው በግምባር ላይ የሚደረግ በዓይን የሚታይ ምልክት ሲሆን ይህም ከውጭ በቆዳ ላይ የሚደረግ ምልክት አሁን በምድር ላይ በሚኖሩ ስምንት ቢሊዮን ሰዎች ሁሉ ላይ ለማድረግ የሚከብድ ነው። ክርስቲያኖች የ666 ንቅሳት ወይም ግምባር ውስጥ የሚቀበር የኮምፒዩተር ማይክሮቺፕ ሲጠብቁ ነበር። ይህ ዓይነቱ ምልክት ግን ዓለምን በሙሉ ሊያዳርስ አይችልም። በአሁኑ ሰዓት ዶክተሮች ሕጻናትን እንኳ መከተብ አልቻሉም።
ዓለምን በፍጥነት እያጥለቀለቀ ያለው ግን አእምሮዋችን ውስጥ የሚገባው መንፈሳዊ ምልክት ነው።
አንጎላችን ከግምባራችን ኋላ ነው ያለው። አንጎልን ማግኘት ከፈለጋችሁ በግምባር በኩል ሰርስራችሁ መግባት አለባችሁ። አእምሮዋችን ወይም ሃሳባችን ያለው አንጎል ውስጥ ነው።
የአውሬው ምልክት ሥራው አእምሮን መቆጣጠር (ሃሳብን ማስለወጥ) ነው።
ራዕይ 7፡3 የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ አላቸው።
ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።
ራዕይ 14፡1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
እግዚአብሔር የሰዎች ስጋዊ ግምባር ላይ አይጽፍም። እግዚአብሔር ቃሉን እንድናምን ትዕዛዛቱን በልባችን ወይም አእምሮዋችን ውስጥ ነው የሚጽፈው። ስጋዊው ግምባራችን አንጎል ውስጥ የሚገኘውን መንፈሳዊ አእምሮዋችንን ነው የሚወክለው።
ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እግዚአብሔር በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ የሚያትመው ማሕተም ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት መንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ በመኖር የሰውን የማሰብ እና የማድረግ ችሎታ ሲቆጣጠር ነው። እግዚአብሔር ሐሳባችንን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በመቆጣጠር አእምሮዋችን ላይ የራሱን ማሕተም ያትማል።
ሰይጣን ከራሱ ያመጣው አንድም ነገር የለውም፤ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ነው የሚኮርጀው።
የአውሬው ምልክት የሰዎችን አእምሮ የሚቆጣጠረው የስሕተት መንፈስ ነው፤ ይህም የስሕተት መንፈስ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎችንና ልማዶችን እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። ማንኛውም ዲኖሚኔሽናዊ እምነት ወይም በክርስትና ውስጥ መኖር የሌለበት ትምሕርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ እስከሆነ ድረስ እንደዚሁ ዓይነት ተጽእኖ ይኖረዋል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር እንድናምን አእምሮዋችንን ይለውጠዋል።
በቀኝ እጆቻቸው ላይ የሚደረገው ምልክት የሚወክለው ልባቸው ውስጥ ባለው እምነት መሪነት የሚፈጽሙትን ድርጊት ነው። አእምሮዋችሁ እጃችሁን ይቆጣጠራል። ቀኝ እጃችሁ በልባችሁ የእውነት በማመን የምታደርጉትን ሥራ ሁሉ ይወክላል። ግራ እጃችሁ ደግሞ የሚወክለው ግድ ሆኖባችሁ የምትሰሩትን ስራ ሁሉ ነው።
ራዕይ 13፡17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።
የአውሬው ምልክት የሚገልጸው የሰዎች አእምሮ በዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች አስተሳሰብ እና አስተምሕሮ ቁጥጥር ስር መውደቁን ነው።
“መግዛት እና መሸጥ” የገንዘብ ቁጥጥርን ያመለክታል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ኃይለኛ ሆና የምትነሳው በሐይማኖት ኃይል እና በገንዘብ ኃይል ሰዎችን በመቆጣጠር ነው። አሜሪካ በትልቅ ኢኮኖሚዋ በመጠቀም በንግዱ ዓለም ላይ ቤተክርስቲያን ገዥ እንድትሆን የራሷን ሚና ትጫወታለች። በአሁኑ ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ዓለም ውስጥ ሃብት ለመፍጠር እና የሰዎች ገንዘብ ለመቆጣጠር የሚያገለግለውን ኢንተርኔት የፈጠረችው አሜሪካ ናት። የኮምፒዩተር ሲስተሙ የአንድ ሰውን ክሬዲት ካርድ ካላወቀው ያ ሰው መገበያየት ከባድ ይሆንበታል።
ክሬዲት ካርዶች ወይም የባንክ ሒሳቦች የሚከፈቱት በአንድ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ስም ለተመዘገቡ ሰዎች ብቻ ነው የተባለ ጊዜ ምን ይፈጠራል? የዚያን ጊዜ ሉተራን ወይም ሜተዲስት ወይም ባፕቲስት ወይም ፔንቲኮስታል ወዘተ መሆን ግድ ይሆንባችኋል።
በዚያ ጊዜ መታወቂያው ላይ የአንድ ቤተክርስቲያን ስም የሌለው ሰው ዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ መግባት አይችልም። የቤተክርስቲያናችንን ስም መለያችን አድርገን መቀበል ዲኖሚኔሽን ያደርገናል። “እኔ ባፕቲስት ነኝ”።
እነዚህ ዲኖሚኔሽናዊ ስሞች መነሻቸው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጀመረ መከፋፈል ነው። ይህ መከፋፈል ቀጥለው በመጡ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እየሰፋ ሄዶ ሰዎች የመሪዎቻቸውን ስም መጠቀም ጀመሩ (ፕሪሲሊያኖች) ወይም የአስተሳሰብን ዓይነት የሚወክሉ ስሞች ለምሳሌ ግኖስቲክስ (ሚስጥራትን መረዳት የሚችሉ ሰዎች)።
አዲስ ኪዳን ውስጥ እውነተኛ አማኞች ራሳቸውን የጠሩበት ስም ክርስቲያኖች ወይም አማኞች ወይም ደቀመዛሙርት ብለው ብቻ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 11፡26 ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
ራሳቸውን ከአንድ ታላቅ ክርስቲያን ጋር በማያያዝ የሚጠሩ ሰዎችን ጳውሎስ ይገስጻቸው ነበር።
ክርስቲያን ከሚለው ስም በቀር ለራሳችን ምንም ዓይነት ሌላ ስም ማውጣት የለብንም።
“እኔ የሜሴጅ አባል ነኝ” ብሎ መናገር “እኔ አንግሊካን ነኝ” ወይም “እኔ ካልቪኒስት ነኝ” ከማለት እኩል መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወም አባባል ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 1፡11 ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና።
12 ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።
ኬፋ ማለት ጴትሮስ ነው።
13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?
መከፋፈል የሚፈጠረው መንፈሳዊ በመሆን እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት በመትጋት ፈንታ ስጋዊ ስለሆንን እና በስጋ ስለምንመራ እንዲሁም በቤተክርስቲያን ድርጅት አማካኝነት የሚገኙ ቁሳዊ ጥቅሞች ስለሚያታልሉን ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡4 አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?
የሆነ አንድ ሰውን በመከተል ልዩ ቡድን ውስጥ አባል መሆን የሚያዋጣ አካሄድ አይደለም።
ኢንተርኔት አሁን ብዙ መንፈሳዊ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲፈጠሩ አስችሏል፤ ይህም ትልቅ ንግድ ሆኗል።
የስሙ ቁጥር። ይህ የሚያመለክተው አንድ ሰውን ነው።
“ቤተክርስቲያናዊነት” ወደ 45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ዲኖሚኔሽኖች እየበዛ ሲሄድ ክርስቲያኖች ብዙ ስሞችን ፈጥረዋል። እነዚህ ሁሉ ዲኖሚኔሽናዊ ስሞች የሰውን አስተሳሰብ እና የሰውን አመለካከት ነው የሚወክሉት። ለምሳሌ 105 ሚሊዮን አባላት ያላቸው ባፕቲስቶች በዓለም ሁሉ ካሉ ከክርስቲያን ቡድኖች በሕዝብ ቁጥር አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ይህም ለባፕቲስቶች በቂ መለያ አይደለም። ባፕቲስቶች ካልቪኒስት ናቸውን (አስቀድሞ በመወሰን ያምናሉ ወይ?) ወይስ አርሚንያኖች ናቸውን (በነጻ ፈቃድ ያምናሉን)? ነገር ግን ይህም ቢሆን አይበቃም። ሪፎርምድ ወይም የታደሱ አርሚንያኖች የሚባሉ ባፕቲስቶስ አሉ እንዲሁም ዌስሊያን አርሚኒያኖች እና ነባር አርሚንያኖች የሚባሉም አሉ። ነገር ግን ይህም አይበቃም። የመጀመሪያ ባፕቲስት፣ ሁለተኛ ባፕቲስት፣ አሜሪካን ባፕቲስት፣ ሳዘርን ባፕቲስት፣ ጀነራል ባፕቲስት፣ ኢንዲፔንደንት ባፕቲስት፣ ፕሪሚቲቭ ባፕቲስት - አይነታቸው ተዘርዝሮ አያልቅም። ከተሃድሶ ዘመን በኋላ በጥልቅ ውሃ በማጥመቅ አናባፕቲስቶች የመጀመሪያዎቹ ናቸው፤ ስለዚህ ጥምቀት መደረግ ያለበት ሕጻናትን ውሃ በመርጨት ነው ብለው የሚያምኑ ሌሎች ፕሮቴስታንቶች ከአናባፕቲስቶች ብዙዎቹን ውሃ ውስጥ አስምጠው ገደሏቸው።
ቁምነገሩ ኢየሱስ መጠመቅ እንዳለብን የተናገውን ቃል መፈጸም ነው፤ እርሱ ግን ራሳችንን ባፕቲስት ወይም መጥምቃውያን ብለን እንድንጠራ አላዘዘንም።
ስለዚህ ቁጥር ልናገኝለት የምንችለው አንድ ስም ከየት እናመጣለን? የመጀመሪያውን የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽን ለመገንባት ስሙን ከተጠቀመ ሰው ነው የምናገኘው።
ያ ዲኖሚኔሽን ተጽእኖውን እና ስልጣኑን በአውሮፓ ላይ ካስፋፋ በኋላ ፕሮቴስታንቶች የሮማ ካቶሊኮችን አሰራር ኮርጀው ዓለምን ለመቆጣጠር ከሮማ ካቶሊኮች ጋር መፎካከር ጀመሩ። የካቶሊክ ዲኖሚኔሽኖች ውድድሩን በመምራት የቤተክርስቲያንን ዕድሜ እንዴት ማስረዘም እንደሚቻል እና ቤተክርስቲያንን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል መንገዱን አሳዩ። ልክ ሴት ልጆች እናታቸውን እንደሚኮርጁ ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ እነርሱን ኮረጁ።
በየግላቸው በአባላት ብዛት የፕሮቴስታንት ዲኖሚኖሽኖች በካቶሊኮች ተበልጠዋል። ነገር ግን ፕሮቴስታንቶች በሙሉ ወደ አንድነት ቢመጡ ትልቅ ሕብረት ይሆናሉ፤ በቁጥር የካቶሊኮችን ሁለት ሶስተኛ ያህላሉ።
ፕሮቴስታንቶች እና ካቶሊኮች ቢቀላቀሉ ደግሞ የምድር ሕዝብን አንድ አራተኛ ያህል ይሆናሉ። ሐይማኖተኛ ከሆኑ ሰዎች መካከል ሰላሳ ሶስት በመቶ የሚሆኑት ክርስቲያኖች ናቸው (ካቶሊኮች 1.4 ሺ ሚሊዮን ሲሆኑ ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ 0.8 ሺ ሚሊዮን ናቸው)።
በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የእስልምና ሐይማኖት ሲሆን የተከታዮቹ ቁጥር በዓለም ላይ ካሉ ሐይማኖተኞች መካከል ሃያ አንድ በመቶ ነው።
እስቲ አሁን ደግሞ የካቶሊክ ጳጳሳት በባርቤሪያውያን ላይ ወደ ስልጣን በመውጣት አውሮፓ ውስጥ ከሁሉ በላይ ኃይለኛ የሆነች ቤተክርስቲያን ራስ በሆኑ ጊዜ የተጠቀሙትን የአንድ ሰው ስም እንመልከት።
ራዕይ 13፡18 ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
ብዙ ሰው ያላስተዋለው ዮሐንስ ሄዶ የቆመበት የባሕር አሸዋ ትርጉም የሚከተለው ነው።
እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠውን የተስፋ ቃል ተመልከቱ።
ዘፍጥረት 32፡12 አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።
በባሕር ዳርቻ የሚገኘውን አሸዋ ማንም መቁጠር አይችልም። ምክንያቱም አሸዋው እጅግ ብዙ ስለሆነ ነው። “እንደማይቆጠር” የሚለውን ቃል ልብ በሉ። በሌላ አነጋገር እነዚህ ሰዎች የአውሬውን ቁጥር መቀበል አይችሉም ማለት ነው። ይህ የእውነተኛ አማኞች መለያ እና ክብር ነው። እውነተኛ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ስለሚከተሉ የአውሬው ቁጥር ወይም ምልክት ሊነካቸው አይችልም። እነዚህ እውነተኛ አማኞች የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች የአባላት መዝገብ ላይ አይመዘገቡም።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጴጥሮስን ጳጳስነት ተቀብያለሁ ብላ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ስልጣን አለኝ ብላ ያወጀችው በስምንተኛው ክፍለ ዘመን ነበረ። ይህንንም ያደረገችው “የኮንስታንቲን ስጦታ” የሚል ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅታ ነው። ይህ ሐሰተኛ ሰነድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በ752 ዓ.ም አካባቢ ማለትም ኮንስታንቲን ከሞተ አራት መቶ ዓመታት በኋላ ነው (በ337 ዓ.ም)። ታላቁ ኮንስታንቲን የተባለውን የአራተኛው ክፍለ ዘመን ንጉስን ስም የያዘውን የተጭበረበረ ሰነድ በመጠቀም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ መተካካት የሚለውን አስተምሕሮ ፈጠረች፤ ደግሞም “vicarius filii dei” የተባለውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጠረች።
የላቲን ቋንቋ መናገር ባትችሉም እንኳ የኮንስታንቲን ስጦታ ተብሎ በሐሰት በላቲን ቋንቋ ከተዘጋጀው ሰነድ ላይ ጠቅሰን እናሳያችሁ። ይህ ሰነድ በቤተክርስቲያን መማክርት ጉባኤ ተረጋግጧል፤ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኖና ሕግ ውስጥ በግራቲያን አማካኝነት ተካትቷል፤ ኋላም በፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው ጸድቋል፤ (ይህ ፖፕ የዘመን መቁጠሪያ ካላንደርን የለወጠው ፖፕ ነው)፤ ቀጥሎ በካቶሊክ ምሑር እና የታሪክ ጸሐፊ ሉሺየስ ፌራሪስ ተጠቅሷል፤ እርሱም ሰነዱ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
"Ut sicut Beatus Petrus in terris Vicarius Filii Dei fuit constitutus, ita et Pontiffices eius successores in terris principatus potestatem amplius, quam terrenae imperialis nostrae serenitatis mansuetudo haber videtur"
Lucius Ferraris, Prompta Biblietheca, (የ 1890 እትም), art, "Papa," II, Vol. VI, ገጽ 43.
ትርጓሜው እንዲህ ይላል፡-
የተባረከው ጴጥሮስ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ምትክ ሆኖ እንደታየው ሁሉ የዚያ የሐዋርያት አለቃ የሆነው ሰው ምትክ የሆኑት ፖንቲፎች ሁሉ ከእኛ እና ከግዛታችን ምድራዊ መንግስታችን ካለው የበለጠ ስልጣን ሊቀበሉ ይገባቸዋል።
ክሪስቶፈር ቢ. ኮልማን የኮንስታንቲንን ስጦታ በተመለከተ በጻፈው የሎሬንዞ ቫላ ምርምር ገጽ 13 ላይ እንዲህ ብሎ ጽፏል፡-
ከዚህ ቀደም የቀረበውን ሐሰተኛ ሰነድ ኮንስታንቲን እራሱ ጽፎት ቢሆን እንኳ ሰነዱ የአንድ ቤተክርስቲያን ጳጳስ በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ላይ ስልጣን እንዲኖረው ማድረግ አይችልም፤ ሆኖም ግን ይሕ ሐሰተኛ ሰነድ ፖፑ ከሁሉም የበላይ ነው ለሚለው እና ፖፑ ከጴጥሮስ ስልጣን በመቀበሉ የማይሳሳት ሰው ነው የሚለውን አስተምሕሮ ለማጠናከር “መሳሪያ” ሆኖ አገልግሏል።
ፖፑ የመንግስተ ሰማያት በር ቁልፍ ያለው በጴጥሮስ እጅ ስለሆነ መንግስተ ሰማያት መግባት ከፈለጋችሁ ጴጥሮስን ማስደሰት አለባችሁ ይላል።
ለፖፑ ያደረጋችሁት ለጴጥሮስ እንዳደረጋችሁ ይቆጠራል ብላችሁ እንድታስቡ ይፈልጋሉ።
ፖፑ የራሱን ተሰሚነት የሚያሳድገው ጴጥሮስን የሐዋርያት አለቃ ነው ብሎ ከፍ በማድረግ ነው፤ ቀጥሎም ጴጥሮስ የሐዋርያት ልዑል ነው ብሎ ሲያበቃ እኔ ደግሞ የፖፑ ተተኪ ነኝ አለ።
ጴጥሮስ እራሱ እኔ ፖፕ ነኝ ብሎ አያውቅም፤ ደግሞም ጴጥሮስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የራሷ ሃብት እና ግዛት ትፈልግ እንደነበረው ጴጥሮስ እንደዚህ ዓይነት ፍላጎቶች አልነበሩትም።
ይህ በአንድ ሰው ላይ ማለትም በጴጥሮስ ላይ አብዝቶ ትኩረት የማድረግ ልማድ እና ጴጥሮስ “የእግዚአብሔር ልጅ ምትክ ነው” ብሎ ማስተማር ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብዙ ዕድሎች ከፍቶላታል።
“Vicarivs urbis Romae” ማለት “በሮም ከተማ ምትክ” ማለት ነው።
ይህ ማዕረግ ንጉሱ ሮም ከተማ ውስጥ በሌለበት ሰዓት ለንጉሱ ተወካይ የሚሰጥ ነበረ።
በላቲን ፊደሎች ውስጥ ካፒታል "U" የለም። ስለዚህ "V" በ "U" ፈንታ ያገለግላል።
ድንጋይ ላይ ጽሑፍ ሲቀርጹ ቀጥ ያሉ መስመሮች ያሉት V ከ U ፊደል ይልቅ ይቀልላል።
VV ኋላ W ሆነና “ደብልዩ” ተባለ።
የላቲን ቋንቋ ከፊደሎቹ የተወሰኑትን ለቁጥር ይጠቀማቸዋል።
(D = 500 C = 100 L = 50 V = 5 I = 1)
በእግዚአብሔር ልጅ ምትክ
V I C A R I V S F I L I I D E I (ላቲን U ለማለት V ይጠቀማል)
5 1 100 1 5 1 50 1 1 500 1
እነዚህ ቁጥሮች ሲደመሩ ውጤታቸው 666 ነው እርሱም የአውሬው ምልክት ነው5 1 100 1 5 1 50 1 1 500 1
ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጴጥሮስ ማዕረግ ነው የምትለው ይህ ማዕረግ (ጴጥሮስ ግን ፈጽሞ ለራሱ ያልተጠቀመበት) በዚህ ቁጥር አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማን እንደሆነች ይነግረናል።
ራዕይ 13፡18 ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
የአውሬው ምልክት ከሰው ጋር የተያያዘ ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሐዋርያው ጴጥሮስን አገልግሎት እጅግ ከማበላሸቷ የተነሳ ትምሕርቷ ስርዓቷ በሙሉ ከአውሬው ምልክት ጋር የተያያዘ ሆኗል።
ለዚህ ሁሉ ጥፋት ጴጥሮስን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም፤ ምክንያቱም ጴጥሮስ እኔ ፖፕ ነኝ አላለም።
ጴጥሮስ ከአይሁድ ውጭ ለሆኑ ቤተክርስቲያኖች ሐዋርያ ነበርን? ጴጥሮስ የአሕዛብ ሐዋርያ ነበርን? አልነበረም። ይህን ጉዳይ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጴጥረስ ሐዋርያነት ጥቂት የሚገርሙ እውነቶችን ይነግረናል። በመጀመሪያ ጴጥሮስ የሮም ጳጳስ እንዳልነበረ እናያለን፤ ነገር ግን ጳውሎስ በግልጽ እንደጻፈው የአይሁዶች ሐዋርያ ነበረ፡-
ተመልሰው ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠው እንዲሁ ለእኔ [ለጳውሎስ] ላልተገረዙት [ለአሕዛብ] የሆነው ወንጌል አደራ [በእግዚአብሔር] እንደ ተሰጠኝ አዩ፤
ለተገረዙት [ለአይሁድ] ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት [እግዚአብሔር] ፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና።
ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ [በኢየሩሳሌም ላለችው ቤተክርስቲያን] መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ [ጴጥሮስ] ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም [ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ] ወደ ተገረዙት [ወደ አይሁድ] ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
ገላትያ 2፡7-9
ዱዎይ (የካቶሊክ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም)
ከዊኪፒዲያ፡ ነጻ ኢንሳይክሎፒዲያ
ፔፒን ታናሽየው ወይም ልጅየው የተባለው (ሴፕቴምበር 24 ቀን 768 ዓ.ም የሞተው) በካሮሊንጂያን ሥርወ መንግስት ውስጥ የፍራንኮች የመጀመሪያ ንጉስ ነበረ (752-768)። በ741 ዓ.ም ፔፒን እና ወንድሙ አባታቸውን ቻርለስ ማርቴልን ተክተው በመካከል በነበረው ክፍተት (373-743) የቤተ መንግስት አስተዳዳሪዎች እና የመንግስቱም መሪዎች ሆነው ወደ ስልጣን ወጡ። ካርሎማን ጡረታ ከወጣ በኋላ (747) ፔፒን ከፖፕ ዛካሪ ፈቃድ አግኝቶ ከሜሪቬኒያን ነገስታት የመጨረሻ የሆነውን ቺልደሪክ 3ኛውን ከስልጣን አውረደና ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ (752)።
(ፔፒን እውቅና ያለው የባርቤሪያውያን ፍራንኮች ንጉስ ለመሆን የፖፑ ድጋፍ አስፈልጎታል።
ፖፑ ደግሞ ኢጣልያን እየወረሩ የነበሩትን ባርቤሪያውያን ሎምባርዶች ለማጥፋት የፔፒን ድጋፍ አስፈልጎታል።)
ፔፒን ከነገሰ በኋላ የወሰደው የመጀመሪያ እርምጃ አይስቱልፍ የተባለውን የሎምባርዶች ንጉስ መውጋት ነበር፤ የሎምባርዶች ንጉስ ግዛቱን እስከ ሮም ድረስ አስፍቶ ነበር። ፔፒን ሎምባርዶችን በጦርነት ድል ከነሳ በኋላ የሎምባርዶች ንጉስ ከቤተክርስቲያን የነጠቃቸውን ንብረቶች በሙሉ አስመለሰው። ፔፒን ራቬና እና የፔንታፖሊስ (አምስቱ ከተሞች) የፖፑ ንብረት እንዲሆኑ አደረገ። እነዚህም ከተሞች የፔፒን ስጦታዎች ተባሉ፤ ይህም ሰበብ ተገኘና ከተሞቹ የፖፑ ግዛቶች መሆናቸው ተረጋግጦ የፖፑ ምድራዊ (ፖለቲካዊ) ስልጣን በዚህ አጋጣሚ ተጀመረ።
ፔፒን ፖፑን የረዳው ጴጥሮስ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት እንዲፈቅድለት ብሎ ነው።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከሮም ተነስቶ ኢጣልያን የሚያቋርጥ ግዛት እንዲኖራት ተደረገ፤ እነዚህም ግዛቶች የፖፑ ግዛቶች ተባሉ። ካርታው ውስጥ በቀይ ቀለም ምልክት የተደረገበት ቦታ ከኮንስታንቲን የተሰጠኝ ሰነድ ነው ብሎ ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ፖፑ ወደ ፓሪስ ሄዶ የፔፒንን እርዳታ ከጠየቀ በኋላ ፔፒን ለፖፑ የሰጠው ግዛት ነው።
ፖፑ በ752 ዓ.ም ፔፒን የተባለውን ባርቤሪያዊ የፍራንኮች ንጉስ አድርጎ ሾመው፤ ቀጥሎ በ800 ዓ.ም የፔፒንን ልጅ ሻርለሜይንን ሾመው (ሻርለሜይን ከባርቤሪያውያን ነገስታት መካከል በዝና አንደኛ ነው)። ፖፑ በባርቤሪያውያን ነገዶች መካከል ንጉስ የመሾም ስልጣን ያዘ። ባርቤሪያወያን ወደ ካቶሊክ ሲለወጡ ደግሞ ፖፑ ለእነርሱ መንፈሳዊ ራስ ሆነ። ከሮማ ቄሳሮች እጅ የወጣውን ስልጣን ፖፑ በራሱ እጅ አስገባው።
ራዕይ 17፡2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።
ፖፑ ከነገስታት እና ከዓለም መሪዎች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያበቃው በቂ ኃይል እና ተሰሚነት አገኘ።
“አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” [ማቴዎስ ምዕራፍ 16 ቁጥር 16]
ከደቀመዛሙርት ሁሉ መካከል ኢየሱስ ማን መሆኑን በትክክል የተረዳው ጴጥሮስ ብቻ ነበር።
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “አንተ ጴጥሮስ ነህ፣ በዚችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆች አይችሏትም” [ማቴዎስ ምዕራፍ 16 ቁጥር 18]
1ኛ ቆሮንቶስ 10፡4 ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
ፖፑ ጴጥሮስ ዓለት ነው በማለት ይህንን እውነት ለወጠው። ጴጥሮስ ግን ኢየሱስን ሶስት ጊዜ የካደ ሰው ነው።
ማቴዎስ 26፡33 ጴጥሮስም መልሶ፦ ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም አለው።
34 ኢየሱስ፦ እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው።
ጴጥሮስ ማለት ድንጋይ ወይም ጠጠር ማለት እንጂ ዓለት ማለት አይደለም።
ገላትያ 2፡11 ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
12 አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።
ጴጥሮስ አሕዛብ በአይሁድ ሕግ እንዲኖሩ ፈለገ። በዚህ የተነሳ ጳውሎስ ጴጥሮስን አረመው፤ ማለትም ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ አልነበረም፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ነው ትላለች። ጴጥሮስ በአስተምሕሮው ስሕተት ሰርቶ ያውቃል፤ ስለዚህ የማይሳሳት ሰው አይደለም! ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበረ የሚሉ ሁሉ ይህንን ማስታወስ ያስፈልጋቸዋል።
ማርቆስ 1፡29 ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።
30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።
ማርቆስ 3፡16 ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤
ሁሉም ፖፕ በራሱ ስም ነው የሚጠራው። ጴጥሮስ ግን ስሙ የክብር መጠሪያው ነው። ስምኦን ጴጥሮስ ሚስት አግብቷል። ስለዚህ ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ አይደለም፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን ከፖፕ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛው ቄስ ድረስ አገልጋዮቿ ሚስት እንዳያገቡ ትከለክላለች።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡1 መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ …
3 እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥
ስለዚህ ፖፑ እና ጳጳሳት ወይም ቄሶች ማግባት አይችሉም የሚለው ሕግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ማቴዎስ 16፡19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
የበዓለ ሃምሳ ዕለት ጴጥሮስ የዮሐንስን ጥምቀት አሰረው፤ ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ የዮሐንስ ጥምቀት አስፈላጊነቱ አበቃ። ዮሐንስ ለንሰሃ ብቻ ያጠምቅ ነበር እንጂ የአዳኙን፣ በደሙ ከሐጥያት የሚያነጻውን የመስዋእቱን በግ ስም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አልጠቀሰም።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ … አላቸው
[ከሐጥያት ነጻ የምንወጣው በንሰሐ ነው]
እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
[ይህ ደግሞ በሰዎች አመለካከት አለመታለላችን እና እግዚአብሔር ማን መሆኑን የማወቃችን ማስረጃ ነው]
በዚህ ዓለት ላይ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ማን መሆኑን በመገለጥ ማወቅ ነው። እርሱ እግዚአብሔር አብ ነው፤ ማለትም ሰው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ የሚኖረው ያ ታላቅ መንፈስ። እንደ አብ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከአይሁዶች በላይ ነበረ። እንደ ወልድ እግዚአብሔር ሰው በሆነው በኢየሱስ ውስጥ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ ተመላለሰ። እንደ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በሕዝቡ ልብ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖር ተመልሶ መጣ።)
ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ … የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በንሰሐ ድና በበጉ ደም ታጥበች። ደግሞም በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኞች የነበሩ ሰዎች የአብ፣ ወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አውቀዋል። ይህ ጥምቀት እግዚአብሔር ማን መሆኑን ሰዎች እንዲያውቁ ይህንን መረዳት ፈታው።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚታወቀው ያህዌ በአዲስ ኪዳን የተገለጠው ኢየሱስ እንጂ ሌላ አይደለም።
ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ቢሆንና ፖፕ በመሆኑ የማይሳሳት ከሆነ ሰዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቁን ልብ በሉ። ተተኪዎቹ ጳጳሳት ታድያ ጴጥሮስ ያደረገውን የማያደርጉት ለምንድነው? ሁላቸውም የሚያጠምቁት በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፤ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።
“ማሰር እና መፍታት” ሐጥያትን ይቅር የማለት እና የመያዝ ስልጣን ነው፤ ይህም ስልጣን ፖፑ የእኔ ነው ይላል፤ ይህንን ስልጣን የካቶሊክ ጳጳሳት በጨለማው ዘመን ውስጥ በነበረው የፖለቲካ ፉክክር ውስጥ ተጠቅመውበታል።
ማቴዎስ 16፡22 ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።
ቁልፎቹን ከተቀበለ በኋላ ጴጥሮስ ወዲያው ወደ ስሕተት ገብቶ ኢየሱስን ተቃወመ።
23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።
ይህ ትልቅ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ንግግር ነው። ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ መያዙ ሃሳቡን ሰይጣናዊ ከመሆን አላዳነውም። ስለዚህ የጴጥሮስ ስልጣን አለን የሚለው ፖፕ ሃሳብስ ምን ይሆን። የካቶሊክ ጳጳሳት ስልጣናቸው የመጣው ከጴጥሮስ ሲወርድ ሲዋረድ ተቀብለውት እንደሆነ ይናገራሉ። ስለዚህ የሰውን ሐጥያት ይቅር ማለት እና ይቅር እንዳይባል የመያዝ ስልጣን አለን ይላሉ። ፖፕ ቦኒፌስ ቀዳማዊ (418-22) ኢየሱስ ለጴጥሮስ ሰጥቶ የነበረው የሕዋ አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን አስተዳደር እና ስልጣን ለጴጥሮስ ተተኪዎች ተላልፏል፤ ስለዚህ ፖፑ የሚያደርጋቸው ውሳኔዎች በሙሉ የማይሻሩ ናቸው ብሏል። ስለዚህ ፖፑን የማይታዘዝ ማንኛውም ሰው የክርስቲያን ማሕበረሰብ አባል ሆኖ መቀጠልም ሆነ እድናለው ብሎ ተስፋ ማድረግም አይችልም፤ አለ ቦኒፌስ። (ጴጥሮስን ፊት ለፊት የተቃወመው ጳውሎስስ?) ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን Vicarius Petri (የጴጥሮስ ተተኪ) እንዲሁም Vicarius Christi (የክርስቶስ ተተኪ) ብሎ የጠራው ፖፕ ጌላሲየስ (492-96) ነው።
“Vicarius Petri” ማለት በጴጥሮስ ቦታ ማለት ነው። ፖፑ በምድር ላይ የጴጥሮስ ተወካይ ነው።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡4 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።
[ሃብታምና ውብ የሆነችው ቫቲካን]
እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ
[ፖፑ የመፍታት እና የማሰር ስልጣን ስላለው ሐጥያትን ይቅር ማለት ወይም መያዝ መቻሉ]
በሮማ መንግስት ዘመን የሮማ ጳጳስ የሮማ ንጉስ ሮም ከተማ ውስጥ በማይኖርበት ሰዓት የንጉሱ ተወካይ ሆኖ ያገለግል ነበር። በሌላ አነጋገር የሮማ ጳጳስ “Vicarius urbis Romae” (በሮማ ከተማ ፈንታ) ነበር። ባርቤሪያውያን ነገዶች ለሮማ መንግስትን ስጋት በሆኑ ጊዜ የሮማ ጳጳስ ኢጣልያ ውስጥ እንደ መሪ እና የንጉስ ወኪል ሆኖ ተነሳ። ከዚያ በኋላ ፖፑ የጴጥሮስ ወኪል (Vicarius Petri) ነኝ አለ። ቀጥሎ ደግሞ ፖፑ ጴጥሮስ የክርስቶስ ወኪል (Vicarius Filii Dei) ነበረ አለ። ይህን ማዕረግ ከጴጥሮስ ጋር ብቻ ነበር የሚያያይዙት። የትኛውም ፖፕ ይህንን ማዕረግ ለራሱ ተጠቅሞ እንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃ እስከ ዛሬ ድረስ የለም። ሆኖም ግን ጴጥሮስ የክርስቶስ ወኪል ነኝ ብሎ ይህን ማዕረግ በጭራሽ ለራሱ ተጠቅሞ አያውቅም።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ልጅ ቦታ ወይም Vicarius Filii Dei (666) የሚለው ማዕረግ እስካሁን ባለን ማስረጃ መሰረት በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአንድ ሰው ስም ማለትም ከጴጥሮስ ስም በቀር ከማንም ስም ጋር ተያይዞ ተጠቅሶ አያውቅም።
ለዚህ ስሕተት ጴጥሮስ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ጴጥሮስ እኔ የክርስቶስ ወኪል ነኝ ብሎ አያውቅም።
ጴጥሮስን ከፍ ከፍ ያደረገችውና ያልተገባውን ክብር በመስጠት ስሙን ያጠፋችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት።
የሮማ ቤተክርስቲያን ጴጥሮስን በክርስቶስ ቦታ አስቀምጣዋለች።
በሩ ክርስቶስ ነው፤ ጴጥሮስ ደግሞ የበሩ መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ነው። ይህም ይበልጥ ከጴጥሮስ ጋር መጣበቅ እንደሚያስፈልግ የሚያመለክት ሃሳብ ነው፤ ምክንያቱም ወደ መንግስተ ሰማያት የምትገቡበትን በር የመክፈት ስልጣን ያለው በጴጥሮስ እጅ ነው። እንደ ካቶሊኮቹ እምነት ማን ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚገባ ወይም እንደማይገባ የሚወስነው ጴጥሮስ ነው።
ባርቤሪያውያን ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ ለሮም ድጋፍ ሰጡ ምክንያቱም ድጋፍ በመስጠታቸው ምክንያት በጴጥሮስ ፊት ሞገስ የሚያገኙ እና ጴጥሮስም ወደ መንግስተ ሰማያት እንዲገቡ በሩን የሚከፍትላቸው መስሏቸዋል።
አንድን ቅዱስ ሰው ማምለክ በጣም የሚያሳዝን የሰዎች ድክመት ነው።
ናቡከደነጾር ቅዱስ ለነበረው ዳንኤል ሐውልት ሰራለት፤ ለዚህ ነው ዳንኤል የራሱ ምስል ለሆነው ኃውልት እንዲሰግድ ግድ ያልሆነበት። ለዚህ ሃውልት መሰራት ዳንኤል ተጠያቂ አይደለም። ዮሐንስ ነብይ ለነበረ መልአክ ሊሰግደለት ሁለት ጊዜ በፊቱ ተደፋ።
ራዕይ 19፡10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።
ራዕይ 22፡8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።
እኛ ሰዎች በቀላሉ ቅዱሳንን ከፍ ከፍ እናደርጋለን። በጣም መንፈሳዊ የሆነው ዮሐንስ እንኳ ለአንድ መልአክ ሊሰግድ ተደፋ።
ራዕይ 13፡18 ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
ጴጥሮስ ይህንን ማዕረግ ለራሱ ተጠቅሞ አያውቅም። ጴጥሮስ ለየትኛውም የሮማ ጳጳስ ይህንን ማዕረግ አልሰጠም። ቤተክርስቲያን እንዴት መተዳደር አለባት የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ጴጥሮስ መልስ የጻፈው ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ነው እንጂ ለየትኛውም ጳጳስ ወይም ፓስተር አልጻፈም።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
[ሃብታም ለመሆን ሳይሆን]
በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
[ከፍ ያለ ፖፕ ወይም ፓስተር]
ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ
አንድ ሰው እንደ አለቃ ሆኖ ቤተክርስቲያንን ይምራ በሚለው ሃሳብ ጴጥሮስ ተስማምቶበት እንደማያውቅ ግልጽ ነው።
ፖፑ እያንዳንዱን ቤተክርስቲያን ቄስ እንዲቆጣጠር ፈለገ። ፖፑ ቄሶቹን ሲቆጣጠር በዚያው ሁሉንም ቤተክርስቲያኖች ተቆጣጠረ ማለት ነው።
ፕሮቴስታንቶችም የካቶሊኮችን ልማድ በመከተል አንድ ፓስተር እንድ ቤተክርስቲያንን እንዲቆጣጠር ፈቅደዋል።
እግዚአብሔር ግን ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት እንድትተዳደር ነው የፈለገው።
ጳውሎስ በሮም ለነበሩ ክርስቲያኖች መልእክቱን ሲጽፍ በመጨረሻው ምዕራፍ ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎችን በስም እየጠቀሰ ሰላምታ ሲያቀርብ ጴጥሮስን አንዴ እንኳ አልጠቀሰም። ጳውሎስ መልእክቱን በጻፈ ሰዓት ጴጥሮስ ሮም ውስጥ አለመኖሩ ግልጽ ነው።
ጴጥሮስ ወደ ሮም ሄዶ እንደነበረ የሚመሰክር አንድም ታሪካዊ ማስረጃ የለም።
ጳውሎስ ሚስት ያገቡ ሽማግሌዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በመሪነት ቦታ እንዲያስተዳድሩ ብሎ ተናግሯል። ስለዚህ ጳጳሳት ወይም ሽመግሌዎች ሚስት ማግባት ይችላሉ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን ጳጳሶች ሚስት እንዲያገቡ አትፈቅድም።
ቲቶ 1፡5 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
6 የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።
7 ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥
ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳስ ማለት ነቀፋ የሌለበት ሽማግሌ ማለት ብቻ ነው። ሽማግሌ ሰውየው ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማዕረጉ ነው።
ሽማግሌዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁልጊዜ በብዙ ቁጥር ነው የተጠቀሱት።
ፊልጵስዩስ ከተማ ውስጥ ከአንድ በላይ ሽማግሌዎች ነበሩ።
ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
ጴጥሮስ የአይሁዶች ሐዋርያ ነበር። “አስተርጓሚ” የሚለው ቃል “ፔትር ሮማ” ከሚለው የከለዳውያን ቃል ነው የመጣው፤ ትርጉሙም “ታላቅ አስተርጓሚ” ማለት ነው። አረማውያን ይህ ታላቅ ሰው የአማልክትን ፈቃድ እንደሚተረጉምላቸው ያምኑ ነበር። በአረማውያን ላይ ተጽእኖ ለማድረግ የካቶሊክ ጳጳሳት ልጅ እንደ ባቢሎናውያን እና እንደ ግብጻውያን ስላሴ የሚባል ትምሕርት ፈጠሩ። ባርቤሪያውያን ወደ ሮም ሲመጡ “ፔትር ሮማ” “የሮሙ ጴጥሮስ” ነው ብለው በቀላሉ አሳመኑዋቸው። ስለዚህ የካቶሊክ ሐይማኖት የተመሰረተው የጴጥሮስን ዝና ተመርኩዞ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በጴጥሮስ ላይ የተመረኮዘ የስልጣን መተካካት ከመጀመሪያው ጀምሮ ችግር ያለበት መሆኑን ለማሳየት ጴጥሮስን “ሰይጣን” አለው።
ጴጥሮስ እኔ ፖፕ ነኝ ብሎ አያውቅም። ጴጥሮስ ሚስት አግብቷል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቋል። ጴጥሮስ ንሰሐን ሰብኳል። አንድ ቀን ጴጥሮስ “ብር እና ወርቅ የለኝም” ብሎ አንድ ለማኝን ፈውሷል።
የሐዋርያት ሥራ 3፡6 ጴጥሮስ ግን፡- ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለው፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።
የካቶሊክ ጳጳሶች ሃብታም እና ላገቡ ሰዎች ናቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔር “ስም” “አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ነው” ብለው አስተማሩ። ሶስት ማዕረጎች እንዴት አንድ ስም ሊሆኑ ይችላሉ? እነርሱ በፈጠሩት የስላሴ ትምሕርት ኢየሱስ ክብሩ ተቀንሶ “የመለኮት ሁለተኛ አካል” አካል ወደ መሆን ዝቅ ብሏል።
ጳውሎስ የገለጠው እውነት ከዚህ ተቃራኒ ነው። እርሱ እንደ ጻፈው የመለኮት ሙላት ያለው በክርስቶስ ውስጥ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ማንንም መንፈሳዊ አባታች ብላችሁ አትጥሩ ተብለናል። ዳግመኛ ከተወለድን እግዚአብሔር ብቻ ነው መንፈሳዊ አባታችን መሆን የሚችለው።
ማቴዎስ 23፡9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።
የካቶሊክ ቄሶች “አባ” ተብለው ነው የሚጠሩት። ፖፕ የሚለው ቃል ጳጳስ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ አባት ማለት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፡4 ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል።
ፖፑ ጭንቅላቱን ያልተሸፈነበት ፎቶ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ወደ ሕዝብ ፊት ሲወጣ ሁልጊዜ ራሱ ላይ መሸፈኛ ያደርጋል።
ለምን? ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖንቲፍ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት ነበረ፤ ለክሕነት ሥራውም ሁልጊዜ ራሱን ይሸፍን ነበር። የካቶሊክ ፖፕ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ይህንን ማዕረግ ስለተቀበሉ ራሳቸውን ይሸፍናሉ።
በዚህ ፎቶግራፍ የምታዩት ሰው የመጀመሪያው የሮማ ገዥ ኦጋስተስ ነው፤ እርሱም እንደ ፖንቲፍ ራሱን ሸፍኗል። ይህ ሃውልት የንጉስ ኦጋስተስ ሃውልት ሲሆን እርሱም እንደ ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖንቲፍ (የባቢሎናውያን ሚጥራት ሊቀካሕናት) በልብሱ ራሱን ሸፍናል።
ዘመናዊ ፖፕ እንደ ፖንቲፍ ራሱን ለመሸፈን ነጭ ቆብ ያደርጋል።
ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ የሆነውን ዘውድ ለ600 ዓመታት ያህል በራሱ ላይ ይጭን ነበር።
ኢየሱስ ግን የእሾህ አክሊል ነበር ያደረገው።
መሪያችሁን ዛሬ ምረጡ።