ራዕይ 12 - እስራኤል እና አሜሪካ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
አሜሪካ እና እስራኤል ግንኙነት እንዳላቸው የሚያመለክቱ ማስረጃዎች አሉ።
First published on the 15th of October 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ምዕራፍ 12 በአይሁድ ታሪክ እና በቤተክርስቲያን ታሪክ መካከል እየተፈራረቀ ነው የተጻፈው።
ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እስራኤል ናት፤ ከዚህም የተነሳ ስለ ፍጥረታዊቷ እስራኤል በምሳሌ የተነገሩ አንዳንድ ምሳሌዎች በቤተክርስቲያንም ይፈጸማሉ።
እግዚአብሔር ከ2,000 ዓመታት በፊት አይሁዶችን በተወ ጊዜ ወደ አሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘወር አለ።
ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስሕተት ውስጥ የገባችዋን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ትቷት ሲሄድ ፊቱን ወደ አይሁዶች ይመልሳል።
ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን የአምልኮ ስርዓቶች እና ልማዶች በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ጠለቅ ያለ ፍጻሜ ከማግኘታቸው አንጻር አይሁዶች እና ቤተክርስቲያን ብዙ የሚወራረሱዋቸው ነገሮች አሉዋቸው።
ለምሳሌ የአይሁድ ሊቀካሕናት የመጀመሪያው ሊቀካሕን አሮን ነበር፤ እርሱም በነብዩ በሙሴ እጅ ከታጠበ በኋላ ነበር የተቀባው።
ዘጸአት 40፡12 አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ።
13 የተቀደሰውንም ልብስ አሮንን ታለብሰዋለህ፤ በክህነትም ያገለግለኝ ዘንድ ቀብተህ ትቀድሰዋለህ።
ቤተክርስቲያን አንድ ሊቀ ካሕናት ብቻ ነው ያላት፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን እርሱም በብሉይ ኪዳን ውስጥ የነበረውን ያንኑ ስርዓት ተከትሎ ነው የመጣው።
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ለማጥመቅ ብቁ እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበረ፤ ነገር ግን ሕጉ መፈጸም እንዳለበት የተረዳ ጊዜ ለማጥመቅ እሺ አለ።
ማቴዎስ 3፡15 ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።
ከመጀመሪያው ኪዳን ለሚበልጠው ኪዳን ሊቀካሕናት ሆኖ የመጣውም በነብይ እጅ መታጠብ አለስፈልጎታል። ስለዚህ ዮሐንስ ኢየሱስን ውሃ ውስጥ በማጥለቅ በጥምቀት አጠበው።
እግዚአብሔር ለዮሐንስ የነበረው እንዲያጠምቅ ብቻ ነው።
ዮሐንስ ኢየሱስን ለመቀባት የሚሆን ዘይት አልያዘም ነበር፤ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ መልክ ወርዶ በኢየሱስ ላይ ሲያርፍበት በትኩረት ይመለከት ነበር፤ ኢየሱስን ልዕለ ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ተቀባ።
ይህም ታላቁ መሲህ፣ ታለቁ ሊቀካሕናት ታጥቦ እንደተቀባ እግዚአብሔር የሰጠን ማረጋገጫ ነው።
ዮሐንስ 1፡32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።
33 እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።
ቅባቱ የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ ማረፉን ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጡ አልገባም።
መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጡ መግባቱ አልፈላጊ አልነበረም ምክንያቱም የመለኮት ሙላት ሁልጊዜም በአካል በእርሱ ውስጥ ነበረ (ቆላስይስ 2፡9)።
ኢየሱስ ደግሞ ተለውጦ አያውቅም።
ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።
በውስጡ የነበረው መንፈስ እራሱ ነው ወደ ውጭ እርግብ መልክ ሆኖ የተገለጠው፤ ይህም በይፋ እንደተቀባ ይታይ ዘንድ ነው።
ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ በተርሴሱ ሳውል ላይ ዓይን በሚያጠፋ ደማቅ ብርሃን መልክ መንፈሱን አበራበት።
ራዕይ 12፡1 ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።
“ታላቅ ምልክት በሰማይ” ማለት ራዕዩ መንፈሳዊ አንድምታ አለው ማለት ነው።
ሴት የቤተክርስቲያን እና የአማኞች ተምሳሌት ናት። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት።
2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
ይህ ራዕይ ከሁሉ በፊት የሚወክለው በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ አይሁድ አማኞችን ነው።
ፀሃይን ተጎናጽፋ የሚለው ቃል እግዚአብሔር ከግብጽ ባወጣቸውና እና ቀይ ባሕርን አሻግሮ በሰባት ዓመታት ውስጥ የተስፋይቱን ምድር ባስወረሳቸው ጊዜ የእግዚአብሔርን ጸጋ ለብሰው እንደነበረ ያመለክታል።
በባሪሎን ተማርከው በሄዱ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ የፋርሱን ንጉስ ቂሮስን በመጠቀም ተማርከው ከሄዱበት ሃገር ወደ ምድራቸው መለሳቸው።
ጨረቃ ከእግሮቿ በታች። አይሁዶች በሕጉ ላይ ነው የቆሙት።
12 ከዋክብት ያሉበት አክሊል የሚወክለው 12ቱ የእስራኤል ነገዶች የተሰየሙባቸውን 12 ሰዎች ነው።
በሁለተኛ ደረጃ ከቤተክርስቲያን አንጻር 12ቱ ከዋክብት 12ቱን ሐዋርያት ይወክላሉ፤ ይህ ቁጥር በይሁዳ ቦታ የተተካውን ሐዋርያው ጳውሎስን ይጨምራል። 12ቱ ሐዋርያት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የእውነትን መሰረት መስርተዋል፤ እኛም ወደነዚያ የመጀመሪያ እምነቶች መመለስ አለብን። ጳውሎስ እና ሌሎቹ ሐዋርያት የሽልማት አክሊል ተቀብለዋል።
ፀሃይ የምትወክለው ጸጋውን ነው። እኛም የዳንነው የእግዚአብሔርን ጸጋ በእምነት በመቀበል ነው።
ኤፌሶን 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ጨረቃ መሰረታችን ናት። ጨረቃ ፀሃይን ታንጸባርቃለች። የቤተክርስቲያን መሰረት የሚሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ብርሃን በንግግራችን እና በድርጊታችን ስናንጸባርቅ ነው።
ራዕይ 12፡2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።
የመጨረሻው አይሁዳዊ የብሉይ ኪዳን ነብይ ሚልክያስ ሲሆን ዶ/ር እስኮፊልድ እንዳለው ያገለገለበት ዘመን በ397 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነው። ከዚያ ወዲያ አይሁዶች ነብይ አልነበራቸውምና ብዙ ችግር ውስጥ ገቡ።
በግሪኮች ቅኝ ተገዝተው ነበር፤ ግሪኮችም በረቀቀው ፍልስፍናቸው አማካኝነት የአይሁዶችን አስተሳሰብ አጣጣሉባቸው። መቃዕብያን የሚባሉት ቡድኖች ተነስተው በመዋጋት እስኪከላከሉ ድረስ ታላቁ አንቲዮከስ የተባለ ግሪካዊ በአይሁዶች ላይ ብዙ ተጫውቶባቸዋል። አይሁዶችም ግሪኮችን አባረሩ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ ደግሞ ኤዶማውያንን ገዙ። ኤዶም ከእስራኤል በስተደቡብ የምትገኝ ሃገር ስትሆን የተስፋይቱ ምድር አካል አልነበረችም። አይሁዶች ኤዶማውያንን የአይሁድን እምነት ተቀበሉ ብለው አስገደዷቸው። ይህም ትልቅ ስሕተት ነበረ።
ቀጥሎ ደግሞ የሜዲተራንያን ባሕርን አካባቢ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሮማውያን እስራኤልን ጨቁነው ገዙ። ሮምም ኤዶማዊውን ሔሮድስ በአይሁዶች ላይ ንጉስ አድርጋ ሾመችው። ሔሮድስ በአይሁዳውያን ላይ ከነገሱ ነገስታት ሁሉ ጨካኝ ንጉስ ነበረ፤ ደስ እንዳለው እየተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዶችን ገድሏል። ሔሮድስ ዕድሜውን በሙሉ አንድ ቀን የአይሁድ መሲህ ተነስቶ ከስልጣን ያወርደኛል በሚል ስጋት ውስጥ ነው የኖረው። ለዚህ ነው ኢየሱስን ሊገድል የፈለገው።
ለአይሁድ ሕዝብም በዚህ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የግፍ ዘመን ውስጥ ነው መሲሁ የተወለደው።
ራዕይ 12፡3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥
ሌላ ሰማያዊ ራዕይ። ይህም ራዕይ የሰይጣን ጨለማ መንግስትን በጥልቀት የሚያጋልጥ ራዕይ ነው።
ሰይጣን በፊት ሉሲፈር ነበረ፤ ከመላዕክት ሁሉ የሚበልጥ መልአክ።
የሰይጣንን ተንኮል እና ማሳሳቻ ዘዴዎች ማጋለጥ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
እኛ ሰዎች በራሳችን ማስተዋል ስንታመን ሰይጣን በቀላሉ ያሞኘናል።
ኢየሱስ በማርቆስ ወንጌል ውስጥ አስጠንቅቆናል፡-
ማቴዎስ 24፡4 “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።”
እኛ ሰዎች የየረቀቁ የሰይጣን ማታለያዎች እንዳያታልሉን ዓይናችንን የሚከፍትልን ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ሕብረት ነው።
ቀይ ዘንዶ። ይህ ዓይነት ምስል በሮማውያን ሰራዊት ባንድረሰ ላይ ይገኛል። ዘንዶ የሰይጣን ምሳሌ ነው።
ሰይጣን ሥራውን ለመስራት ሰዎች እና የሰዎች ሥርዓት ያስፈልጉታል።
በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ ከተነሱ መንግስታት ሁሉ ኃይለኛ መንግስት የሮም መንግስት ነው።
ስለዚህ ሰይጣንም የሰዎችን ሰፈር ለሥራው ማዕከል አድርጎ መርጦታል።
ሮሙለስ ሮምን የመሰረታት የቲበር ወንዝ ማቋረጫ አጠገብ በወንዙ መካከል ደሴት ያለበት ቦታ ነው። ዋነኛ ሥራው በመንገድ ላይ እየሸመቀ መንገደኞችን መዝረፍ ነበር። ወንዙን ማቋረጥ የሚፈልጉ ሰዎችን እየጠበቀ ገንዘብ ክፈሉኝ ይል ነበር። ይህም በቀላሉ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ ንግድ ሆነለት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰባት ኮረብታዎች ላይ ታላላቅ ሕንጻዎችን መስራት ቻለ። በሰባቱ ኮረብታዎች ዙርያ ግምብ አጥር በሰሩ ጊዜ ሮም ከተማ ተብላ ተጠራች። የሰባት ኮረብቶች ከተማ ተባለች።
ቀዩ መስመር በሰባቱ ኮረብቶች ዙርያ የተሰራው አጥር ነው።
የሮማ መንግስት ማዕከል በካፒቶላይን ኮረብታ ላይ የተሰራው የጁፒተር ቤተመቅደስ ነው።
ካኤልያን ኮረብታ ላይ የተሰራው የላተራን ቤተመንግስት በንጉስ ኮንስታንቲን አማካኝነት በ313 ዓ.ም አካባቢ ለሮም ጳጳስ ተሰጥቷል፤ ይህም ቤተመንግስት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ማዕከል ሆነ።
ዮሐንስ አውሬው ወይም የሰይጣን ሃይል ከባሕር ማለትም በሁካታ ውስጥ ከሚኖሩ የአውሮፓ ሕዝብ መካከል ሲወጣ አይቷል።
ራዕይ 13፡2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፣ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፣ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉን እና ዙፋኑን ትልቅም ስልጣን ሰጠው።
“ዘንዶውም ኃይሉን እና ዙፋኑን ትልቅም ስልጣን ሰጠው”። ሰይጣን የሮማ መንግስትን ኃይል ተጠቅሞ የሮማ ካቶሊክ ፖፕን ስልጣን አደራጀ። ንጉስ ኮንስታንቲን ለፖፑ የላተራንን ቤተመንግስት እና ብዙ ገንዘብ በስጦታ ሰጠ። ከቤተመንግስቱ ጎን ትልቅ ቤተክርስቲያን ወይም “ባሲልካ” ተሰራ፤ ይህም ባሲልካ “የጴጥሮስ ዙፋን” ተብሎ የተጠራ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። ከዚህም የተነሳ ፖፑ በዓለም ዙርያ በ1.4 ቢሊዮን ካቶሊኮች ላይ ስልጣን አለው። በምድር ላይ በአንድ ሐይማኖት ስር የተሰባሰቡ የሰዎች ቁጥር መካከል ከሁሉ ትልቁ ይህ ነው። ይህም ታላቅ ስልጣንን ያሳያል። የሮማ ነገስታት ብዙውን ጊዜ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር የማይስማሙ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ያዘወትሩ ነበር። ይህም ከነገስታቱ የተሰጠ ወታደራዊ ድጋፍ የፖፑን ትዕዛዝ አስገዳጅ ለማድረግ አስተዋጽኦ አድርጓል።
ዳንኤል በሕልም ባየው የሰው ምስል ውስጥ በውጭ በኩል ጠንካራ የሚመስሉ አራት የአሕዛብ መንግስታትን ነበሩ።
እነርሱም ባቢሎን፣ ፋርስ እና ሜዶን፣ ግሪክ፣ እና ሮማውያን ናቸው።
ዳንኤል እንደገና ሌላ ራዕይ አየ፤ በዚህ ራዕይ ውስጥ ያያቸው አራት አውሬዎች የአራቱን የአሕዛብ መንግስታት ውስጣዊ ባሕርይ የሚወክሉ ነበሩ።
አንበሳ፣ ድብ፣ ነብር፣ እና ልዩ አውሬ።
የባቢሎን፣ የፋርስና የሜዶን፣ እና የግሪክ መንግስታት ጭካኔ እና ግፈኝነት ተደምሮ ከሁላቸውም የባሰ ግፈኛ የሆነውን የሮማ መንግስት አውሬ ፈጠረ። ይህ እጅግ ክፉ የነበረ የሮማ መንግስት ሲወድቅ ከውድቀቱ ውስጥ የሮማ ካቶሊክ መንፈስ ተነሳ።
“አውሬው ነብር ይመስል ነበር”። የዳንኤል ራዕይ ውስጥ ነብሩ ግሪኮችን ይወክል ነበር። የግሪኮች ፍልስፍና በጣም የረቀቀ በመሆኑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ትታ ለመሄድ ተጠቅማበታለች። ሶስት በአንድ የሚሉትን የሥላሴ አምላክ ፈጠሩ። አንድ አምላክ ሶስት አካላት። “አንድነት በሶስትነት” የሚለው ሃሳብ የግሪክ ፍልስፍና እንጂ የመጽፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።
“አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው”። “ባህሪ” የሚለው ሃሳብ የግሪክ ፍልስፍና እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።
የግሪክ ፍልስፍና ኢየሱስን በመለኮት ውስጥ አስገብቶ ሁለተኛው አካል አደረገው። ይህም ከመጽፍ ቅዱስ ቃል ውጭ ነው። ጳውሎስ በቆላስይስ 2፡9 የመለኮት ሙላት በክርስቶስ ውስጥ በአካል ተገልጦ እንደሚኖር ጽፏል።
የስላሴ አስተማሪዎች እንዲህ ይላሉ፡- “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም”፤ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።
በዚህ መልክ የግሪክ ፍልስፍና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይታወቀውን “ሥላሴ” የተባለ ቃል አምጥቶ በሐዋርያት ሥራ 2፡38 ውስጥ ጴጥሮስ ሕዝቡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ እንዳለባቸው የተናገረውን ቃል ስሕተት ነው ብሎ ያስተምራል።
ግሪኮችም ስሕተትን ተከራክረው ትክክል በማስባል የተካኑ ነበሩ። እንደ ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ ፖፕ የመሳሰሉ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይኖሩም እንኳ ግሪኮቹ ያቀረቡት ብልሃት የተሞላ ክርክር እነዚህን እንግዳ ትምሕርቶች ትክክል ናቸው ብለው ሰዎች እንዲቀበሉ ማድረግ ችሏል። ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች የሥላሴ ትምሕርት አስተዋዮች እንዳደረጋቸው አድርገው ያስባሉ። በእነርሱ አስተሳሰብ አስተዋይ መስሎ መታየት መጽሐፍ ቅዱስን ከመከተል የሚበልጥ ዋጋ አለው።
“የድብ እግሮች” የመጀመሪያው የፋርሶች እና የሜዶናውያን ዓለም አቀፍ መንግስት የነበረውን ጉልበት እና ጠላቶቹን የማድቀቅ ሃይል እና ጭካኔ የሚገልጽ ቃል ነው። ዛሬ በዚህ ዘመን አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባገነን መንግስት ቫቲካን ውስጥ የተሰየመው የካቶሊክ ፖፕ ነው። ቫቲካን በዓለም ዙርያ ሁሉ ላሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያኖች ዋነኛ መቆጣጠሪያ ማዕከል ነው። 1.4 ቢሊዮን ተከታዮች ያሏት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ከሁሉም በላይ ኃያል ድርጅት ናት።
ሆኖም ግን የቫቲካን ከተማ 800 ዜጎች ብቻ ያሏት ሲሆን በምድር ላይ ካሉ መንግስታት ሁሉ ትንሽዋ ናት። ዳንኤል ቫቲካንን “ታናሽ ቀንድ” በማለት ነው የገለጻት።
“የአንበሳ አፍ”።
ኢየሱስ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው።
ፖፑ እራሱን “ቪካሪየስ ክሪስቲ” ወይም የክትስቶስ ተወካይ ብሎ ይጠራል፤ ማለትም በክርስቶስ ፈንታ ይናገራል።
ስለዚህ ፖፑ በጴጥሮስ ዙፋን ላይ ተቀምጦ (ከመቅደሱ ሆኖ) ሲናገር እግዚአብሔር ተናገረ ማለት ስለሆነ ፖፑ አይሳሳትም ማለት ነው። ፖፑ የእግዚአብሔር ቃል አቀባይ ነው ብላ ማመኗ ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዘመናት ውስጥ ታላቅ ክብር እና ተዓማኒነት እንዲኖራት አድርጓል። ይህ ሁሉ የሆነው ቤተክርስቲያኒቱ መጽሐፍ ቅዱስን የማትከተል ሆና ሳለ ነው።
ከዚህም ብሶ ደግሞ በ754 ዓ.ም ፖፕ እስቲቨን ዳግማዊ ወደ ፔፒን ሄዶ ፓሪስ ውስጥ የፍራንኮች ንጉስ አድርጎ ቀባው። ለዚህ ውለታው ምላሽ ፔፒን ኢጣሊያ ውስጥ የፖፑ ግዛት የሚሆን ቦታ እንዲሰጠው ለመነው። ኮንስታንቲን በምዕራብ ያሉ መሬቶችን በሙሉ ለፖፑ እንደሰጠ የሚናገር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጀ። ይህ ሐሰተኛ ሰነድ ግን ከቅዱስ ጴጥሮስ እንደመጣ የሚናገር ሰነድ ነው። በዚህ ሰነድ ውስጥ ጴጥሮስ “ቪካሪየስ ፊሊ ዴይ” (Vicarivs Filii Dei) ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ይህም “በእግዚአብሔር ልጅ ፈንታ” ተብሎ ማለት ነው።
ስለዚህ ስትሞቱ ወደ መንግስተ ሰማያት የምትገቡበትን በር ቁልፍ በእጁ ይዟል የተባለለት ጴጥሮስ ከኢየሱስ የሚበልጥ ክብር ተሰጥቶታል። በሩ ኢየሱስ ነው። ፖፑ ግን ለእናንተ በሩን ለመክፈት ወይም ላለመክፈት የሚወስነው ጴጥሮስ ነው ይላል።
በዚህ ውሸት ተጠቅሞ ባርቤሪያውያን ነገዶችን በሙሉ አታሏቸዋል፤ ከዚያም የሮማ መንግስትን ባፈራረሱ የባርቤሪያውያን ነገዶች ሁሉ ላይ ፖፑ ወዲያ አለቃ ሆነባቸው። ባርቤሪያውያን ጴጥሮስን ሊያስደስቱ እና የመንግስተ ሰማያትን በር እንዲከፍትላቸው ሊያደርጉ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ለፖፑ በመታዘዝ እና ለፖፑ መሬት በመስጠት ነው። በተጨማሪም ደግሞ ፖፑ ላይ ጠላቶቹ ጥቃት እንዳይሰነዝሩበት ባርቤሪያውያን ጥበቃ ያደርጉለት ነበር።
አንዳንድ የላቲን ፊደሎች ቁጥሮችን ይወክላሉ።
V I C A R I V S F I L I I D E I
5 1 100 1 5 1 50 1 1 500 1
የእነዚህ ቁጥሮች ድምር 666 ነው።
የአውሬው ምልክት ማለት ኢየሱስ የበለጠ ሰው ለተናገረው እና ሰው ለሰራው ሥራ ክብር ስትሰጡ ነው።
ራዕይ 13፡18 አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
“የሰው ቁጥር”። አንድ ሰው። በታሪክ ውስጥ ቪካሪየስ ፊሊ ዴይ ወይም በእግዚአብሔር ልጅ ፈንታ ተብሎ የተጠራ ብቸኛው ሰው ጴጥሮስ ነው።
በዚህ ጥፋት ጴጥሮስ ተጠያቂ አይደለም። ጴጥሮስ ይህንን ማዕረግ ለራሱ አልወሰደም።
ፖፑ ግን ጴጥሮስን ወክዬ ነው የምናገረው በማለት ለራሱ ትልቅ ስልጣን ወሰደ። ሥልጣኑን ከፍ ለማድረግ ብለው ጴጥሮስ በኢየሱስ ቦታ የመንግስተ ሰማያት በር ጠባቂ ሆኗል አሉ።
በ1302 ፖፑ ሰዎች ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የሚችሉት ለፖፑ ከታዘዙ ብቻ ነው የሚል ሕግ አወጀ።
ፖፑ በተጨማሪ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍተው ለፖፑ እና ለፖፑ ተተኪዎች ታዛዥ ለሆኑ ሰዎች ብቻ ነው ብሎ አወጀ።
ስለዚህ እያንዳንዱ ፖፕ የጴጥሮስ ተተኪ ነኝ አለ።
ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ውስጥ ጴጥሮስ ሰዎች ሁሉ ንሰሃ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ እንዳለባቸው ሰብኳል።
የካቶሊክ ፖፕ ግን ይህን እውነት አይሰብክም።
የካቶሊኮቹ የስላሴ አስተምሕሮ ፕሮቴስታንቶች እንኳ ሳይቀሩ የሐዋርያት ሥራ 2፡38ን እንዲክዱ አድርጓቸዋል። ብዙ ፕሮቴስታንቶች በዚህ ቃል መሰረት አያጠምቁም።
አስሩ ቀንዶች ሁለት ትርጉም አላቸው።
የሮማ መንግስትን በማፈራረስ ውስጥ ከተሳተፉ ብዙ ባርቤሪያውያን ነገዶች መካከል የፖፑን ስልጣን በመደገፍ እና ከፍ እንዲል በመርዳት ዋነኛ ሚና የተጫወቱት አስር የባርቤሪያውያን ነገዶች ናቸው።
ይህ የሮም ባህርይ ነው። ሮም የገዙዋትን ትገዛለች።
(በዘመን መጨረሻ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በፊት ከጉያዋ ተገንጥለው የወጡ እና ፖፑን የክርስቶስ ተቃዋሚ ብለው ያወገዙ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን ትገዛቸዋለች። ፕሮቴስታንቶችም እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ ወደ መሳሰሉ የካቶሊክ እምነቶች ከተመለሱ ቆይተዋል። ስለዚህ ፕሮቴስታንቶች የአውሬው ምስል የሚሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ ድርጅት እያዘጋጁ ናቸው። አውሬው የሚያመለክተው ዓለም አቀፉን ሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ ድርጅት ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ነው።)
አውሬው የሚለው ስያሜ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ፖፑንም የሚያመለክት ቃል ነው።
ስለዚህ እነዚህ 10 ባርቤሪያውያን ነገዶች አውቀውትም ሆነ ሳያውቁ ፖፑ እንዲነሳ እና ከዚያ በፊት በሮማ ንጉስ እጅ የነበረውን ስልጣን እንዲጎናጸፍ ረድተውታል፤ ከዚህም የተነሳ የሮማ መንግስት ከወደቀ በኋላ ፖፑ በአውሮፓ ላይ በስልጣን ሊገን ችሏል።
ታሪክ ራሱን ይደግማል።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ይነጥቃታል። ከዚያ ወዲያ ዓለም ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባል።
ከዚያ በኋላ ሰይጣን አንድ ሰው ውስጥ ይገባል፤ ከዚህ በፊት የአስቆሮቱ ይሁዳ ውስጥ ገብቶ እንደነበረው፤ ይሁዳም ደግሞ ሐዋርያ፣ የቤተክርስቲያን መሪ ነበረ።
ሉቃስ 22፡3 ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤
ብዙውን ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚባለው የአመጽ ሰው የቤተክርስቲያኖችን አመራር ቀምቶ ይቆጣጠራል። ከሁሉ በላይ ተጽእኖ ያለው የቤተክርስቲያን መሪ ፖፑ ነው። ስለዚህ ሰይጣን የሚያዘጋጀው ኃይለኛ ሰው የፖፑን ስልጣን ቀምቶ ይወስዳል።
እርሱም የአይሁዶችን እስቶክ ገበያ ገንዘብ ፍለጋ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል።
ከዚያም አስር አምባ ገነን መሪዎች የክርስቶስ ተቃዋሚ ለሆነው ፖፕ ወታደራዊ ኃይላቸውን ይሰጡታል፤ እርሱም ይህንን ኃይል ተጠቅሞ ዓለምን ይገዛል።
ስለዚህ 10ሩ ቀንዶች በፊት ፖፑ ወደ ስልጣን በመጣ ጊዜ በአውሮፓ ውስጥ ሁሉ በሚኖሩት ባርቤሪያውያን ነገዶች ላይ ከፍ ካረደጉት አስር ባርቤሪያውያን ነገዶች ጋር ይዛመዳሉ።
አስሩ ቀንዶች በተጨማሪም ወደፊት በሚመጣው የታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነውን ፖፕ በዓለም ላይ ሁሉ በስልጣን ከፍ ሊያደርጉት ኃይላቸውን የሚሰጡትን አስር ወታደራዊ አምባ ገነን መንግስታት ይወክላሉ።
ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ድርብ ፍጻሜ ካላቸው ትንቢቶች መካከል ዓይነተኛ ምሳሌ ነው።
(ለምሳሌ፡ የአብርሃም ዘር ይሳቅ ወይም አይሁዶች ናቸው። ደግሞም ኢየሱስ ነው። ቤተክርስቲያንም የአብርሃም መንፈሳዊ ዘር ናት።)
ሰባቱ ዘውዶች የሮማ ሪፓብሊክን ያፈራረሱትን ኋላም የሮማ መንግስትን የመሰቱትን የመጀመሪያዎቹን ሰባት ፈላጭ ቆራጮች ይወክላሉ።
የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ ከአንድ ቤተሰብ የመጡ ናቸው፤ የተወሰኑት የወለዱ የተወሰኑት ደግሞ በማደጎ ልጅ የሆኑ ናቸው። ሰባተኛው ወታደራዊ መንግስት ገልባጭ ኃይል ነው።
ዩልየስ ቄሳስ የሮማ ሪፓብሊክን አፍርሶ ራሱን የዕድሜ ልክ አምባ ገነን መሪ አድርጎ ሾመ።
የእህቱ የልጅ ልጅ አውግስጦስ ራሱን ንጉስ ብሎ ከሾመ በኋላ በፈላጭ ቆራጭነት ገዛ።
እርሱን ተከርለው ጢባርዮስ፣ ካሊጉላ፣ ክሎዲየስ፣ እና ኔሮ ነገሱ።
ኔሮ በ64 ዓ.ም የሮም ከተማ ለተቃጠለችበት የእሳት አደጋ ተጠያቂዎች ክርስቲያኖች ናቸው ብሎ ክርስቲያኖችን ባሳደደበት ዘመን ነበር ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ላይ የታሰረው።
ራዕይ 17፡10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።
“አምስቱ ወድቀዋል”። ይህ በተጻፈበት ጊዜ ቄሳር፣ አውግስጦስ፣ ጢባርዮስ፣ ካሊጉላ፣ እና ክሎዲየስ ሞተዋል።
“አንዱም አለ”። ኔሮ በ68 ዓ.ም እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ነግሷል።
ሰባተኛው ንጉስ ወታደራዊ ጀነራል የነበረው ጋልባ ሲሆን እርሱም የንጉስነትን ስልጣን ቀምቶ ከያዘ ከሰባት ወር በኋላ ተገድሏል።
ሰባት የአንድ ሥርዓት ሙላት ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰባት ቀናት አሉ። ስምንት የአዲስ ሥርዓት ጅማሬ ነው።
ራዕይ 17፡11 የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
የመጀመሪያዎቹ ሰባት ሰዎች አንድ ሥርዓት አስጀመሩ። መሪያቸው ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ይገዛል። ከዚያም ክርስቲያኖችን መሳደድ ተጀመረ። ይህም ስርዓት ያበቃው ለአጭር ጊዜ በቆየ ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ነው።
ስምንተኛው አዲስ ሥርዓት ነው። ይህም ከመጀመሪያዎቹ ሰባት ሮማውያን ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንፈስ የተመሰረተ ቤተክርስቲያን ነው።
“ከሰባቱም አንዱ ነው” ማለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ ሰባት የሮማ ገዥዎች ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አላት ማለት ነው።
ፖፑ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን እንደ አምባ ገነን ንጉስ ነው የሚመራት። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖችን ገድላለች። የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ለሶስት ዓመት ተኩል ዓለምን ለመግዛት የአስር ወታደራዊ አምባገነን መንግስታትን ኃይል ይጠቀማል።
ኔሮ ክርስቲያኖችን በግፍ ማሳደድ ጀመረ። እነዚህ አምስት ግፈኛ ነገስታት አንድ ሰው ብቻ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የሚገዛበትን የሮማ መንግስት መሰረቱ። ከዚያም በኋላ ወታደራዊው ጀነራል ጋልባ ለሰባት ወራት የንጉሱን ስልጣን ቀምቶ ተቆጣጠረ። ሰባቱ ዘውዶች ማለት እነዚህ ናቸው ሌሎቹም የእነርሱን ፈለግ ተከትለዋል።
አረማዊቷ ሮም በባርቤሪያውያን እጅ በወደቀችበት ጊዜ የአምባገነንነትን መንፈስ ተቀብሎ የተነሳው ፖፕ እስከ ዛሬ ድረስ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባገነን መሪ ሆኖ ቀጥሏል።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ ሰይጣን ሐዋርያ በነበረው የቤተክርስቲያን መሪ በነበረው ይሁዳ ውስጥ ገባ።
ስለዚህ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ሊነጥቅ ሲመጣ ሰይጣን በሰማያት ሆኖ ወንድሞችን ሲከስ ከቆመበት ቦታ ይባረራል።
ከዚያ በኋላ ልክ ጋልባ የሮማ መንግስትን ስልጣን ቀምቶ እንደ ወሰደ የቤተክርስቲያንን ታላቅ የስልጣን ሥፍራ ፖፑ የተቀመጠበትን ቀምቶ የሚወስድ ሰው ውስጥ ሰይጣን ይገባል። ከዚህም የተነሳ በምድር ላይ በሃብት አንደኛ የሆነችውን የቫቲካንን ገንዘብ የራሱ ያደርጋል። ሃብት ሰይጣንን እንደ ማግኔት ይስበዋል። ለዚህ ነው ኢየሱስ “እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ” ያለው።
ጋልባ ወታደራዊ ጀነራል ነበረ። ልክ እንደዚሁ የፖፑን ስልጣን የሚቀማው የክርስቶስ ተቃዋሚ አስር አምባ ገነን መሪዎች ወታደራዊ ኃይላቸውን እንዲሰጡት ያሳምናቸዋል።
አሁን ደግሞ ወደ ኢየሱስ ዘመን እንመለስ።
ራዕይ 12፡4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
ሰዎች ይህ ቃል የሚናገረው በጥንት ዘመን ከመላእክት አንድ ሶስተኛውን ስላሳተው ስለ ሉሲፈር ነው ይላሉ። ነገር ግን እውነቱ እንደዛ አይደለም። ሉሲፈር የእግዚአብሔርን ያህል ብርቱ አይደለም፤ ደግሞም ከመላእክት አንድ ሶስተኛዎቹ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው የጸኑትን ሁለት ሶስተኛዎቹን ሊያሸንፉ አይችሉም። አቅሙ ከእግዚአብሔር በጣም የሚያንስ ሉሲፈር ከመላእክት ጥቂቶቹን ብቻ አሰልፎ እስኪያምጽ ድረስ ሞኝ አይደለም።
ሰይጣን ሁልጊዜ በብዙሃኑ ውስጥ ሆኖ ነው የሚሰራው። የማያምኑ ሰዎች በቁጥር ከአማኞች ይበልጣሉ። ቻይና በሕዝቦቿ ብዛት የተነሳ ለዓለም ሰላም ስጋት ናት።
ይህ ራዕይ የሚናገረው ኢየሱስ በምድር ላይ ስለሞሆንበት ዘመን ነው።
በመንፈሳዊ አእምሮ አስቡ። አንድ ሶስተኛ የሚለው ቃል ቁጥርን የሚገልጽ አይደለም። ልብን ነው የሚገልጸው።
ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።
የአብርሃም ዘር ማለትም አይሁዶች እንደ ከዋክብት ይሆናሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የሰውን ልጆች በሶሰት ቡድን ከፈለ። አይሁድ፣ አሕዛብ (አይሁድ ያልሆኑ ሰዎች)፣ እና ሳምራውያን (የአይሁድ እና የአሕዛብ ክልሶች)።
ሰይጣን በአይሁዳውያን ልብ ውስጥ መሲሃቸውን አንቀበልም እንዲሉ የሚያደርግ ክፉ ሃሳቡን እየፈጸመ ነበር። ሰይጣን ሁል ጊዜ ሰዎችን ከወቅቱ የእግዚአብሔር ዓላማ ለማዘናጋት የሚጠቀመው የወቅቱን ፖለቲካዊ ቀውስ ነው። በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በማሰብ ተጠምደን ሳለ የእግዚአብሔርን ሚስጥራዊ ዓላማ ሳናስተውል እንቀራለን። ሰዎች ስሜታቸው በታወከ ጊዜ ትክክለኛ ውሳኔ የማድረግ አቅም ያጣሉ።
በመቃዕብያን ሥር ሆነው ለጥቂት ጊዜ ነጻነትን ካገኙ በኋላ እሥራኤሎች በሮማውያን ተሸንፈው፣ ቅኝ ግዛት ተገዝተው ከ63 ዓመተ ዓለም ጀምሮ በብዙ ግፍ ተጨቁነዋል። ከዚህም የተነሳ አይሁዶች በሮማውያን ላይ መራራ ጥላቻ ነበራቸው።
ራዕዩ ውስጥ የተጠቀሰው “ጅራት” የሚያመለክተው ሰይጣን በአይሁዶች አእምሮ ውስጥ የሞላባቸው “ተረት” ነው።
“ተመልከቱ እነዚህ ሮማውያን እንዴት ክፉዎች እንደሆኑ”።
“መሲሁ አሁን ቢመጣ እና ሮማውያንን ቢያባርራቸው ታላቅ ንጉስ ይሆን ነበር”።
አይሁዶች መንፈሳዊነትን በሙሉ ረስተው ፖለቲካዊ ነጻነታቸውን በማግነት ሃሳብ ላይ ሙሉ በሙሉ ተጠመዱ። የሚያስፈልጋቸው ዋነኛው ነገር ከሐጥያት ባርነት ነጻ መውጣት ሲሆን ለዚህ ምንም ትኩረት አልሰጡም።
ሮማውያን በገሃድ የፈጸሙት ግፍ እንዲሁም አይሁዶች በምናባቸው ተፈጸመብን ብለው ያሰቡት ሁሉ በሮማውያን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ አባባሰው።
ከዚህም የተነሳ የሚፈልጉትንና የእነርሱን ፍላጎት የሚፈጽምላቸው መሲህ በምናባቸው ፈጠሩ።
ትልቁ ናፍቆታቸው ሮማውያንን ድል የሚነሳ ወታደራዊ መሪ እንዲነሳላቸው ነበር።
ስለዚህ አይሁዶች መሲሃቸው ሮማውያንን ረግጦ ከምድራቸው የሚያስወጣላቸው ታላቅ ወታደራዊ መሪ ነው በሚለው ሃሳባቸው ተውጠው ቀሩ። የሮማውያን ጫካኔ እና ግፍ ሲበዛባቸው በሃሳባቸው የሚናፍቁት ወታደራዊ መሲህ ይበልጥ በምናባቸው ውስጥ እየደመቀ መጣ። በተለይም ደግሞ በሚጠሉዋቸው በሮማውያን የተሾመባቸው ሔሮድስ የተባለ ክፉ ንጉስ ባስጨነቃቸው ቁጥር አይሁዶች ሃሳባቸው ሁልጊዜ ሮማውያንን መበቀል ሆነ።
ከዚህም የተነሳ አእምሮዋቸው ስለጨለመ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ሕብረት ተቋረጠ።
ስለዚህ በራሳቸው ምናብ በፈጠሩት ቅዠት ሃሳባቸው ከመታወሩ የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በፊታቸው እየተፈጸመ ሳለ ማስተዋል አልቻሉም። በዚህም ምክንያት እውነተኛውን መሲሃቸውን ገፉት፤ ምክንያቱም እነርሱ የተጠባበቁትን ዓይነት ሆኖ አልተገለጠም።
መሲሁን በመግደላቸው ከዚያ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር እነርሱን ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንዲደመስሳቸው አድርገዋል።
በዚህ መንገድ ሰይጣን ከሰው ዘር ውስጥ አንድ ሶስተኛውን ወደ ሰማይ ከመግባት ተስፋቸው ጎትቶ አስወጥቷቸዋል፤ አንድ ሶስተኛ ሲባል በቁጥራቸው ሳይሆን በወገናቸው አይሁድ በመሆናቸው ነው።
ዘንዶው ከሴቲቱ ፊት ቆመ።
በ63 ዓመተ ዓለም ሮማዊው ጀነራል ፖምፔይ እስራኤልን ተቆጣጠረ።
በ37 ዓመተ ዓለም ሮማውያን ሔሮድስን በይሁዳ አውራጃ ውስጥ አሻንጉሊት ንጉስ አድርገው ሾሙት።
ሔሮድስ የአይሁድ ንጉስ መሆን ሳይገባው በሮማውያን ጉልበት ነው የነገሰው። ከዚህም የተነሳ ሔሮድስ እውነተኛው የእስራኤል ንጉስ በሆነው በመሲሁ ላይ ፍርሃት እና ጥላቻ አደረበት።
በዚህም አጋጣሚ የሮማ ዘንዶ ኢየሱስን የሚያጠፋበት እድል አገኘ።
ራዕይ 12፡5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
እግዚአብሔር በ2400 ዓመተ ዓለም አካባቢ አብርሃምን ተናገረው። ይስሐቅ በ2300 ዓመተ ዓለም አካባቢ ተወለደ።
ስለዚህ ኢየሱስ በ33 ዓመቱ በሞተ ጊዜ እስራኤል እንደ ሕዝብ (ሴቲቱ) የ2000 ዓመት ዕድሜ አስቆጥራለች። ስለዚህ እርሱ ከእስራኤል ታሪክ ርዝመት አንጻር እንደ ሕጻን ልጅ ነበር።
በሚመጣው የሺ ዓመት መንግስት ጊዜ ግን እርሱ ዲያብሎስን በጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ በሰንሰለት አስሮ ይጥለዋል፤ ይህም ሰንሰለት ዲያብሎስን አቅም የሚያሳጡ የብዙ ክስተቶች ሰንሰለት ነው። የሰይጣን ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ በተወገደበት ዓለም ውስጥ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ምድርን በሙሉ በብረት በትር ቀጥቅጦ ይገዛል። ለሐጥያት አንዳችም ዕድል ፈንታ አይሰጠውም።
“ወደ እግዚአብሔር ተነጠቀች”። ኢየሱስ ከትንሳኤው ወዲያ ከ40 ቀናት በኋላ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ሄደ።
እነዚህ ክስተቶች አይሁዶችንም ቤተክርስቲያንንም የሚመለከቱ ናቸው።
መሲሁ ወደ እስራኤል የመጣው ስለሰው ልጆች ሁሉ ሐጥያት ሊሞት ነው።
ይህ ታላቅ ክስተት ቤተክርስቲያን እንድትወለድ ምክንያት ሆኗል።
በመንፈሳዊው ዓለም ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ሽግግር ተደረገ።
በናቡከደነጾር ሕልም ውስጥ የታየው የአሕዛብ ምስሉ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
በብሉይ ኪዳን ዘመን መዳን ለአይሁዶች ነበረ።
በነዚያ ዘመናት ዓለምን ይገዙ የነበሩት አራቱ የአሕዛብ መንግስታት ፖለቲካዊ ኃይላቸው መንግስታቸው ውስጥ ሾልከው በገቡ በባቢሎናውያን ሚስጥራት የተበከለና የተበላሸ ነበር።
በስተመጨረሻም በሮማ መንግስት ውስጥ እነዚያ የባቢሎን ሚስጥራት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሾልከው ገብተዋል። እነዚያ የባቢሎን ሚስጥራት ዋነኛ የጥፋት ተልዕኮዋቸውን የሚፈጸሙት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲሆን ዘዴያቸውም መጽሐፍ ቅዱስን በማጣመም ነው።
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ አይሁዶች የኢየሱስን ወንጌል አንቀበልም አሉ። ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ አሕዛብ ዘወር አለ።
በዚያ ጊዜ የዳንኤል ራዕይ ውስጥ ከታየው በአሕዛብ ምስል አማካኝነት ከተገለጹ ታሪካዊ ክስተቶች ውስጥ ተወገዱ።
መሲሁን አንቀበልህም ብለውት ገድለውታል።
በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል ታይተስ 1,100,000 አይሁዶችን ገድሎ ቤተመቅሱን ከነመስዋዕታቸው ደምስሶታል። በ135 ዓ.ም ሐድሪያን የተባለው ሮማዊ ንጉስ 580,000 አይሁዶችን ገድሎ የቀሩትን በትኗቸዋል።
ስለዚህ በብዙ ጭፍጨፋ አይሁዶች ተወገዱ።
የአሕዛብም ቤተክርስቲያነ በሮማ መንግስት ግዛቶች እና ከግዛቶቹም አልፋ ተስፋፋች።
ታሪክ ራሱን ይደግማል።
ከዚያም የመጨረሻው ዘመን ሲቀርብ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ወደ ሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ክሕደት ማፈግፈግ ጀመረች፤ ሎዶቅያውያን የድራም ምት ሙዚቃ በመጠቀም የራሳቸውን የቤተክርስቲያን አምልኮ ስርዓት አበጅተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድራም አንድም አልተናገረም። ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ የማይገኝለት የራሳቸው የሆነ አስተምሕሮ አዘጋጅተዋል። የክርስቶስን ልደት አክብሩ አልተባልንም። ነገር ግን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የካቶሊክን ክራይስት ማስ የዓመቱ ታላቅ የንግድ በዓል አድርገው ተቀብለውታል።
ሮማዊው ንጉስ ኦሬልያን ዲሴምበር 25ን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን ብሎ በ274 ዓ.ም አወጀ፤ ይህንንም ያደረገው የሮማ ጳጳስ የነበረውን ፈሊክስን ዲሴምበር 22 ቀን 274 ዓ.ም አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ ነው። ከዚያም በቀጣዩ ዓመት ኦሬልያን በራሱ ጠባቂዎች እጅ ተገደለ።
የሮም ጳጳስ የነበረው ዩልየስ ቀዳማዊ በ352 ዓ.ም ከመሞቱ በፊት ክራይስትስ ማስ የተባለውን የአረማውያንን የፀሃይ አምላክ ልደት ቀን ዲሴምበር 25ን የእግዚአብሔር ልጅ ልደት ቀን ነው ብሎ ኮርጆ ተቀበለ። በዚህም መንገድ ቤተክርስቲያን አረማውያንን ለመሳብ ብላ አረማዊ ልማዶችን ተከተለች።
የአረማውያን ስለሴ ተኮርጆ በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት የቤተክርስቲያን ስላሴ ሆኖ ተቀባይነትን አገኘ። ነገር ግን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ስላሴያዊው አምላክ ስም የለሽ ሆነ፤ ምክንያቱም ሶስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። በተለይም ደግሞ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም። ቤተክርስቲያን “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ማለት ጀመረች ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ልትነግረን አልቻለችም።
የስላሴ ትምሕርት ኢየሱስን በስላሴ ውስጥ ሁለተኛ አካል አድርጎ አስገባው። ጳውሎስ ግን የመለኮት ሙላት በሙሉ በአካል በኢየሱስ ውስጥ እንደሚኖር ጽፏል (ቆላስይስ 2፡9)።
ስለዚህ ከአረማውያን የመጣው የስላሴ ትምሕርት የዚህን ዘመን ቤተክርስቲያን ተመላላሾች የእግዚአብሔርን ሚስጥር መረዳት እንዳይችሉ አደንዝዟቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተጠቀሰ ስላሴ ያወራሉ፤ ደግሞ እራሳቸውም እንዳልገባቸው ሳይክዱ ይናገራሉ።
ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያኖች የወንድም ብራንሐምን የዘመን መጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ለመቀበል እምቢ ይላሉ።
በዚህ ዘመን እግዚአብሔር አይሁዶችን መልሶ ወደ ፓለስታይን መሰብሰብ ጀምሯል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና በሰጠ ጊዜ ትንቢት ተፈጽሟል።
እስራኤል ወደ እግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ተመልሳ ስትገባ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ቀስ በቀስ እየደበዘዘ እየጠፋ ነው።
በ1900 ዓ.ም አካባቢ አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው መመለስ ጀመሩ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተፈጸመው የ6 ሚሊዮን አይሁዶች ጭፍጨፋ ዓለም ሁሉ ተደናግጦ ለአይሁዶች እስረኤል ውስጥ ትንሽ መኖሪያ ሃገር እንዲሰጡዋቸው አደረገ። አረቦች በስግብግብነታቸው ይህንን ትንሽ ሃገር ለራሳቸው ፈለጉ፤ ስለዚህ በአራት ጦርነቶች አይሁዶች ላይ ጥቃት ቢሰነዝሩም በሁሉም ተሸንፈው አስቀድመው ይዘው የነበረውን ግዛት ሁሉ አጡ። እነዚህ የዮርዳኖስ አረቦች በአይሁዶች ከተሸነፉ በኋላ ራሳቸውን ፍልስጥኤማውያን ብለው መጥራት ጀመሩ። ያሲር አራፋት የተባለ ግብጻዊ ወደ ራሺያ ሄዶ ኬጂቢዎች ፍልስጥኤማዊ የሚል ፓስፖርት አተሙለት፤ ከዚያም የፍልስጥኤም መሪ ሆነ። ይህም አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው እንዳይመለሱ ለመከላከል የተደረገ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል ነው።
ስለዚህ አይሁዶች ለ2,000 ዓመታት ያህል ከሃገራቸው ተሰደው ከቆዩበት ተመልሰዋል። የትኛውም ሌላ ሕዝብ እንዲህ ዓይነት ታሪክ አልሰራም።
እግዚአብሔርም አሕዛብን ትቶ እስራኤል ውስጥ ወዳሉት አይሁዶች የሚመለስበት ዘመን ደርሷል። ይህም ታላቁ መከራ ይባላል።
ራዕይ 12፡6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።
አንድ ቀን 24 ሰዓት ነው ብለን ከቆጠርን ይህ ትንቢት ለአይሁዶች ተፈጽሟል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚታወቀውን ባለ 30 ቀናት ወር ተጠቅመን ካሰላን 1,260 ቀናት ማለት ሶስት ዓመት ተኩል ነው።
42 ወራት 1,260 ቀናት ከሆኑ የመጽፍ ቅዱስ አንድ ወር 30 ቀናት ነው ማለት ነው። (1,260/42 = 30)
ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
ታላቁ መከራ የሚቆየው ለሶስት ዓመት ተኩል ነው።
ሙሴ እና ኤልያስ የተባሉ ሁለት ነብያት የአይሁድ ሕዝብን በአዲስ ኪዳን የወንጌል እውነት ይመግቡዋቸዋል።
አይሁዶች በ33 ዓ.ም ከእግዚአብሔር እቅድ ተቆርጠው ወጥተው ነበር፤ በታላቁ መከራ ዘመን ደግሞ ተመልሰው ወደ እግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ይገባሉ። አይሁዶች ከእግዚአብሔር እቅድ በተሰረዙ ጊዜ በ70 ዓ.ም ታላቅ ጭፍጨፋ ተደርጎ ነበር፤ ቀጥሎ ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች ጀርመኒን በመሩበት ጊዜ አይሁዳውያን መመለስ ሲጀምሩም ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል።
በዚህ ክፍተት ውስጥ እግዚአብሔር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ወቅት ፊቱን ወደ አሕዛብ አድርጎ ነበር።
በጨለማው ዘመን እና በጸረ ተሃድሶ ዘመን ውስጥ የክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ተጨፍጭፈውባታል። ከ300 ዓ.ም እስከ 1600 ዓ.ም ድረስ ካቶሊክ ላልሆኑ ሰዎች የከባድ ስጋት ጊዜ ነበረ።
ራዕይ 12፡14 … ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
እነዚህ ሁለት አይሁዳዊ ነብያት የታላቁ ንሥር ሁለት ክንፎች ናቸው።
“ታላቅ ንሥር” ማለት እነዚህ ነብያት የተፈጥሮ ኡደት እንዲቋረጥ የሚያደርጉበት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል አላቸው ማለት ነው። ይህም እውነት መሆኑን በሰባቱ መለከቶች እና በሰባቱ ጽዋዎች አማካኝነት የሚፈጸሙትን ሰቆቃዎች በማየት መረዳት እንችላለን።
ምድረበዳው የሚያመለክተው አይሁዶች ከሚጠሉዋቸው የዓለም ሕዝብ ሁሉ ተነጥለው መቀመጣቸውን ነው። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ከተማ ናት ብሎ እውቅና በሰጠ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት በ128 ለ9 ድምጽ ተቃወሙት። የዓለም ሕዝብ ለእስራኤል ያላቸው ጥላቻ ይህን ያህል ነው። ጸረ-ሴማዊነት (አይሁዶችን መጥላት) በዓለም ዙርያ እየጨመረ ነው።
በታላቁ መከራ ወቅት ግን አሜሪካ ከወደመች በኋላ ዓለም ሁሉ እስራኤልን ለማጥፋት ይነሳል።
የዚያን ጊዜ የሚሆነው ብቸኝነታቸው መንፈሳዊ ምድረበዳ ነው።
ሁለቱ ነብያት ግን አስደናቂ በሆነው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸው አይሁዶችን ከሁሉም ዓይነት ጥቃት ጥበቃ ያደርጉላቸዋል፤ በአዲስ ኪዳናዊ እውነት ይመግቡዋቸዋል፤ መሲሁ 144,000ዎቹን አይሁዶች ሊጊበኛቸው ለሚመጣበትም ጊዜ ያዘጋጇቸዋል።
እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ድርብ ፍጻሜ ነው ያላቸው፤ ምክንያቱም በጨለማው ዘመን ውስጥ በቤተክርስቲያን ላይ ስለሚሆነውም ነገር ነው የተጻፉት።
የሚከተሉት ሁለት ጥቅሶች በጨለማው ዘመን ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች ላይ ከባድ ስደት ባስነሳችባቸው ጊዜ ያደረሰችባቸውን መከራዎችን እና እንግልቶች ይገልጻሉ።
ራዕይ 12፡6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።
ራዕይ 12፡14 … ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
54-0513 የአውሬው ምልክት
ይህች ራዕይ ምዕራፍ 12 ውስጥ ያለችዋ ሴትልጇ የእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ሊቀመጥ የተነጠቀ ጊዜ እናም በተቀመጠ ጊዜ እርሷ ወደ ምድረበዳ ተሰደደች፤ በዚያም ለአንድ ሺ ሁለት መቶ ስድሳ ቀናት ሲመግቧት ቆየች፤ ይህም ቀን ቤተክርስቲያን ከአውሮፓ ተሰድዳ ወደ ፕሊማውዝ ሮክ አሜሪካ መጥታ ነጻነት በማግኘት የመሰረተችበት ቀን ድረስ ነው።
የአሕዛቦች ዓመት 365.24 ቀናት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ቀን 360 ቀናት ነው።
ስለዚህ 69 የአሕዛብ ዓመታት ማለት 69 x 5.24 = በ361 ቀናት ከመጽሐፍ ቅዱሱ 69 ዓመታት ይበልጣል።
361 ቀናት ግን ከመጽሐፍ ቅዱሱ ባለ 360 ቀናት ዓመት ጋር እኩል ነው ማለት ይቻላል።
ስለዚህ 69 የአሕዛብ ዓመታት = 69+1 = 70 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት።
በሌላ አነጋገር ለእያንዳንዱ 70 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት 69 የአሕዛብ ዓመታት እንቆጥራለን ማለት ነው።
ስለዚህ 1,260/70 = 18
ማለትም 1,260 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት = 1,260 – 18 = 1,242 የአሕዛብ ዓመታት።
የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከመጣባት ስደት የተነሳ ለ1,242 ዓመታት መከራ ውስጥ አልፋለች።
እነዚህ ማቆሚያ የሌላቸው ስደቶች በጨለማው ዘመን ውስት ስለ እግዚአብሔር ብለው ሲተጉ በብዛት የተገደሉትን እውነተኛ አማኞች አደከሙዋቸው።
ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
አረማዊው የሮማ አምባ ገነን መሪ ዩልየስ ቄሳር የዘመን አቆጣጠርን በ46 ዓመተ ዓለም ቀየረ።
ከዚያም በኋላ የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ግሪጎሪ 13ኛው ለመጨረሻ ጊዜ በ1582 የዘመን አቆጣጠር ላይ ለውጥ አደረገ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የሮማ መንግስትን በባርቤሪያውያን እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም የሮማ መንግስትን ለሞት የሆነ ቁስል አቆሰሉት፤ ከዚያም በኋላ አገግሞ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተመስሎ ተነሳና የዘመን አቆጣጠር ካላንደርን ከወቅቶች ጋር አብሮ እንዲሄድ በማለት ቀየረው።
የሮማ ካቶሊኮች ከአረማውያን ጋር ለማጣጣም ብለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሕጎችን ለወጡ።
ይህም ድርጊት ከእግዚአብሔር ሕግ ፈጽሞ ተቃራኒ ነበረ።
ዘዳግም 12፡30 በምድራቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ ከፊትህ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመድ፦ እነዚህስ አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔ አደርጋለሁ ብለህ ስለ አማልክቶቻቸው እንዳትጠይቅ ተጠንቀቅ።
የስቅለት አርብ ክርስቶስ የሞተበት ቀን ሆኖ ተቆጠረ፤ ነገር ግን እርሱ የሞተው ሐሙስ ነው።
የኢየሱስ ልደት ታሕሳስ 25 ቀን ነው ተባለ። ኤርምያስ ምዕራፍ 10 ውስጥ አሕዛብ ዛፍ ቆርጠው በወርቅ እና በብር እንደሚያስጌጡት ተጽፏል። እነዚህ ዛፎች የክሪስማስ ዛፎች ሆኑ።
መጽሐፍ ቅዱስ ያልመሰከረላቸውን “የገና” ወይም የክሪስማስ ስጦታዎች መግዛት ግዴታ ሆነ።
ትልቅ ሰዎች መጠመቃቸው ቀረና ልጆች ክርስትና ይነሳሉ።
የውሃ ጥምቀት በኢየሱስ ስም ከመደረጉ ተለውጦ ምንም ትርጉም በሌለው አባባል “በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም” ተብሎ ተተካ። ምክንያቱም በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ አያውቁም።
አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች በሽማግሌዎች መተዳደር አቆሙ። በነሱ ፈንታ አንድ ቄስ የቤተክርስቲያን ተቆጣጣሪ ሆነ። ጳጳስ ደግሞ የተወሰኑ ቄሶች ላይ አለቃ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች፣ እና ፖፕ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የስልጣን ተዋረድ ስርዓት ዘርግተው ሰዎች ከፍ ከፍ አደረጉ።
መዳን የቤተክርስቲያን ስርዓቶችን በመፈጸም ሆነ።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጠቀሰው ፖፕ የጴጥሮስ ተተኪ ሆነ። በ1302 ፖፑ የምትድኑት ለፖፑ ከታዘዛችሁ ብቻ ነው ብሎ አወጀ።
በራዕይ ውስጥ የታየችዋ ሴት የአሕዛብ ቤተክርስቲያንንም ትወክላለች፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መነሻ አካባቢ የእግዚአብሔርን ቃል ወልዳለች።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ስምንት ሰዎች አዲስ ኪዳንን ጻፉ፤ በ100 ዓ.ም አካባቢ ከመሞቱ በፊት ሐዋርያው ዮሐንስ በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት ኋላ አዲስ ኪዳን ተብለው የተሰየሙትን 27 መጽፎች አጸደቃቸው።
የአዲስ ኪዳን እውነት ወደ ሰማይ ተነጥቆ ሳይበረዝ በዚያ ይቆያል። ሰይጣን የእነዚህን 27 መጽሐፎች ቅጂ ሊበርዝና ሊያጠፋ ብዙ ሙከራ ቢያደርግም እግዚአብሔር ግን በተዓምራት ሳይጠፉ ሳይበረዙ ተጠብቀው እንዲቆዩ አድርጓል።
ቤተክርስቲያን ከሮማ መንግስት በተነሳባት ስደት ሳትጠፋ መቆየት እንድትችል ወደ ምድረበዳ ሸሸች፤ በዚያ ጊዜ በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ካቶሊክ ያልሆኑ አማኞች ተገድለዋል።
በደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ የነበሩት አልቢጀንሶች ሃያ ዓመታት በፈጀ አሰቃቂ የጥፋት ዘመቻ ውስጥ ተጨፍጭፈው አልቀዋል፤ ይህ ዘመቻ የተደረገው በ1209 ዓ.ም በፖፕ ኤነሰንት 3ኛው ትእዛዝ ነበር። በቅርበት ይኖሩ የነበሩ ዋልደንሶች ደግሞ ከጥፋት ለመትረፍ በአልፕስ ተራሮች ውስጥ ወደሚገኘው ምድረበዳ ሸሽተው ተሸሸጉ።
ከሞት የተረፉትን የረዱዋቸው ሁለቱ የታላቁ ንሥር ክንፎች በእጆቻቸው የነበሩ፣ በትጋት የታዘዙዋቸው የብሉይ ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ነበሩ።
ፖፑ ቫልጌት የተባለ በላቲን ቋንቋ የተተረጎመ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲዘጋጅ አዘዘ፤ ይህም የላቲን ትርጓሜ ብዙ ጥቅሶችን በማጣመም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በጨለማው ዘመን ውስጥ እውነትን ማግኘት እንዳይችሉ አደረገ።
57-0705 ጎጆው ውስጥ ያለው ንሥር
ከዚያም ንስሩ ሁለት ክንፎች እንዳሉት እንደገና እናያለን። እነዚያ ክንፎችም የማዳን ክንፎች ናቸው። ደግሞም አዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን ናቸው።
ስለ እምነታቸው ተሰድደው ከእንግሊዝ የሄዱ አማኞች አውሮፓ ውስጥ ያለማቋረጥ የደረሰባቸውን ስደት ሸሽተው ነበር ወደ ሰሜን አሜሪካ የሄዱት። በ1620 ዓ.ም ፕሊማውዝ ሮክ የተባለ ቦታ ደረሱ።
አሜሪካ ውስጥ በተቀመጡ ጊዜ ከካቶሊክ ስደት አመለጡ።
ስለዚህ ንጉስ የሌለበት ሃገር መስርተው ፖፕ በሌለበት ቤተክርስቲያን ውስጥ እያመለኩ መኖር ሲጀምሩ ስደታቸው አበቃ።
ደግሞም በቤተክርስቲያን ልማድና ወግ ወይም በተበረዘ ላቲን መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን እምነታቸውን በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ላይ መመስረትም ችለዋል።
ዛሬ በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 በላይ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። ከዚህም የተነሳ እውነት እየጠፋ ነው።
ነገር ግን በሐዋርያት የተጻፈው የመጀመሪያው እውነት እንዳይጠፋ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን መነሻ ላይ ተነጥቆ ወደ ሰማይ ተወስዷል።
ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱሶችን ለማጥፋት እና አጣሞ ለማስተርጎም ያደረገው ሙከራ በሙሉ በሰማያት የተቀመጠውን እውነት ምንም ሊያደርገው አልቻለም።
የመጀመሪያው እውነት በስተመጨረሻ ምሑራንን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በማገዝ ከ1604 እስከ 1969 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ ፍጹም በሆነው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ተሰጥቶናል።
እነርሱ ሲሸሹት የነበረው የስደት ዘመን የጀመረው መች ነበር?
ስደቱ ለ1,2042 ዓመታት ነበር የዘለቀው፤ ከዚያም በ1620 ዓ.ም ቆመ።
1620 – 1242 = 378
በ378 ዓ.ም የተፈጸመ ምን ታሪካዊ ክስተት አለ?
ኮንስታንቲኖፕል ከተማ አጠገብ አድሪያኖፕል ውስጥ በባርቤሪያውያን ጎቶች እና በምስራቃዊው ሮማን መንግስት ንጉስ ቫለንስ መካከል ወሳኝ ጦርነት ተደረገ። ቫለንስ ተገደለ። ሮማውያንም ተጨፈጨፉ።
አንዳንድ የታሪክ ምሑራን የምዕራባዊው ሮማ መንግስት ውድቀት የተጀመረው ከዚህ ጦርነት ነው ይላሉ።
ከጎቶች ጋር የተዋጉት ሃኖች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሱት በዚህ ጊዜ ነው። ሃኖች ከግፈኛው መሪያቸው ከአቲላ ጋር የሮማ መንግስት ግዛቶችን አወደሙ፤ በዚህም ሌሎች የባርቤሮያ ነገዶች ተበረታቱና የሮማ መንግስትን ሙሉ በሙሉ አፈራረሱት።
ቫለንስ በ378 ዓ.ም በሞተ ጊዜ ቴዎዶሲየስ የሮማ ገዥ ሆነ።
በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተጽእኖ ምክንያት ቴዎዶሲየስ የሮማ ካቶሊክን እምነት የሮመ መንግስት ግዛቶች ላይ ብሔራዊ ሐይማኖት አድርጎ አወጀ እና አረማውያንን ማሳደድ ጀመረ።
ይህም ስደት ተስፋፍት ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ወደ ማሳደድ ተዛመተ።
በዚያም ዘመን ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ማሳደድ በይፋ ተጀመረ።
ዳማሰስ የተባለ የቴዎዶሲየስ አጎት ከቴዎዶሲየስ ጋር ያለውን ዝምድና ተጠቅሞ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስልጣን ባለው ቦታ ላይ ተቀመጠ። በ366 ዓ.ም እርሱ የቀጠራቸው ወንበዴዎች የእርሱን ተቀናቃኝ የኡርሲነስን 137 ተከታዮች ከገደሉ በኋላ እርሱ የሮም ጳጳስ ሆኖ ተሾመ። ከዚያ ቀጥሎ የተደረገ ሁለተኛ ዙር ግድያ ውስጥ የኡርሲነስ ተከታዮች የነበሩ 160 ወንዶች እና ሴቶች ሮም የሚገኘው የሊበሪየስ ባሲልካ (ትልቅ ቤተክርስቲያን) ውስጥ ተገደሉ።
በ380 ዓ.ም ቴዎዶሲየስ የተባለው የሮም ገዥ ዳማሰስ የተባለውን የሮም ጳጳስን “ፖንቲፍ” የሚል የማዕረግ ስያሜ ሰጠው።
ቴዎዶሲየስ እንዲህ ብሎ ጻፈ፡-
… ለሮማውያን በሐዋርያው ጴጥሮስ አማካኝነት የተሰጣቸውን እምነት አሁን ፖንቲፍ ዳማሰስ እና የአሌግዛንድሪያ ጳጳስ የሆነው በጴጥሮስ እንደተከተለው እስከ ዛሬ በታማኝ ወጎቻችንና ባህላችን ተጠብቆ የቆየው እምነታችንን …
ይህን እምነት የተከተሉ ሰዎችን ሁሉ ካቶሊክ ክርስቲያን በሚል ስያሜ እንዲጠሩ በስልጣን አጽድቀናል።
በሁለት ዙር የግድያ ዘመቻዎች አማካኝነት ወደ ስልጣን የመጣው የሮማ ጳጳስ ዳማሰስ ከዚያ ወዲያ ፖንቲፍ ተብሎ ተጠራ።
በእግዚአብሔር ላይ ዓመጸኛ ከነበረው ከናምሩድ ዘመን የጀመሩት የባቢሎን ሚስጥራት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው ስር ሰደው ተደላደሉ፤ ስለዚህ የካቶሊክን ቤተክርስቲያን “ሚስጥራዊቷ ታላቂቱ ባቢሎን” አደረጓት።
አንድ የታሪክ ምሑር ከጻፈው ጽሑፍ ውስጥ የተወሰዱ ሁለት ጥቅሶችን ተመልከቱ።
“የፖፕ ዳማሰስ ዘመነ መንግስት የሚታወስበት አንድ ነገር በቴዎዶሲየስ የስልጣን ዘመን ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተቃወማትን እና በፊቷ የቆሙትን ሁሉ በግፍ እየገደለች በሰዎች ሁሉ ላይ አለቅነትን የተለማመደችበት የጭካኔ፣ የደም ማፍሰስ እና የሽብር ዘመን በመሆኑ ነው።”
“”ዳማሰስ ፖፕ በነበረበት ዘመን በነፍስ ግድያ እና በዝሙት ተከስሶ ነበር። ደግሞም በ383 ዓ.ም በንጉስ ግራቲያን ፊት ተከስሶ ቀርቦ ነበር፤ በዚያ ችሎት ላይ ግን በእርሱ ሥር የነበሩ ጳጳሳት በሙሉ ስለፈጸማቸው ክፉ እና ሰይጣናዊ ወንጀሎች እንዲጠየቅ ተስማምተው ፈርመዋል። እርሱም ከተከሰሰበት ክስ አምልጦ ጳጳሳቱን በመሉ አስገደላቸው። ነገር ግን ከዓመት በኋላ እርሱ ራሱ ሞተ።”
ጨካኙ ፖንቲፌክስ ወይም ፖንቲፍ ዳማሰስ በነፍሰ ገዳዩ ንጉስ ቴዎዶሲየስ አማካኝነት በምዕራባውያን ቤተክርስቲያኖች ላይ ተሾመ። በዚያም ጊዜ በፍርሃት፣ በሽብር፣ እና በነፍስ ግድያ የታወቀችዋ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተወለደች።
(ከ2012 ጀምሮ ፖፑ ለትዊተር አድራሻው @pontifex የሚለውን መለያ መጠቀም ጀምሯል። ያ ክፉ መንፈስ እስካሁንም እየሰራ ነው።)
የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች በ1620 ወደ አሜሪካ በመሸሽ ከዚህ ሁሉ ሐይማኖታዊ ነፍስ ግድያና ደም መፋሰስ ማምለጥ እና አሚሪካ በምድር ላይ ኃይል ሃገር ሆና ስትነሳ አብረው ሊበለጽጉ ችለዋል።
አሜሪካ በመንፈሳዊነት ዓለምን የመራችው ከ1906 ጀምሮ ነው። ሁለቱ ዋነኛ እንቅስቃሴዎች በ1906 ዓ.ም 312 አዙሳ እስትሪት በሚባለው አመካባቢ ሎሳንጀለስ ውስጥ የጀመረው ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት እና ከ1947-65 ድረስ የዘለቀው የዊልያም ብራንሐም ድንቅ አገልግሎት ናቸው። ዊልያም ብራንሐም በአገልግሎቱ የፕሮቴስታንት ተሃድሶ መሪዎች ያልተረዱዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገልጦ አስተምሯል።
እነዚህ መገለጦችም ዓላማቸው ሙሽራይቱን ለጌታ ኢየሱስ ዳግም ምጻት እንድትዘጋጅ መርዳት ነው።
ራዕይ 12፡7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥
የቤተክርስቲያን እና የአይሁዶች ፍጻሜ በጌታ ዳግም ምጻት ጊዜ እየተቀራረቡ ይመጣሉ።
ኢየሱስ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ነጥቆ ከመውሰዱ በፊት መጀመሪያ ሰይጣንን ከሰማይ አባሮ ያስወጣዋል። ሰይጣን እና አጋንንቱ ክርስቲያኖችን በሐጥያት ለመክሰስ ወደ ሰማይ መግባት ይፈቀድላቸዋል። እንደ አቃቤ ሕግ ሰይጣን በሰማይ የተፈቀደለት ቦታ አለው።
8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።
9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
ሰይጣም ከመጀመሪያው ከሰማይ ተባሮ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ሐጥያት እስከ ሰራበት ጊዜ ድረስ ሰማይ መኖሪያው ነበረ።
የዛሬ 2,000 ዓመታት ኢየሱስ ሰይጣን ከሰማይ እንደ መብረቅ ሲወድቅ አየሁ አለ።
ሉቃስ 10፡18 እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።
ነገር ግን ፍትህ በትክክል እንዲከናወን ሰይጣን ሐጥያት የሚሰሩ ክርስቲያኖችን ሁሉ መክሰስ እንዲችል ተፈቅዶለታል። በሰማይ ውስጥ መግባት የሚችልበት ቦታ ክስ የሚመሰርትበት ቦታ ብቻ ነው። ሰይጣን ሲከሰን መንፈስ ቅዱስ ስለ ሐጥያታችን ይወቅሰናል። ከዚያም ንሰሃ ከገባን የኢየሱስ ደም ሐጥያታችንን ያስወግደዋል።
ራዕይ 1፡5 ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ራዕይ 12፡11 እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ክርስቲያኖች ሐጥያታቸውን በፈሰሰው በኢየሱስ ደም ሲያጥቡ ቆይተዋል። በተለይም ደግሞ ይህ የሆነው በጨለማው ዘመን ውስጥ ነፍሰ ገዳዩ ፖፕ ዳማሰስ እና ጨካኙ ሮማ ካቶሊክ ተከታይ ንጉስ ቴዎዶሲየስ ወታደራዊ ኃይል ተጠቅመው የሮማ ካቶሊክ እምነትን የተቃወሙ ሰዎችን ሁሉ እየገደለ ንብረታችውንም ባወደመበት ዘመን ነበር። በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሞተዋል።
ራዕይ 12፡12 ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
ሰይጣን ከሳሽ ሆኖ ከቆመበት ከሰማይ ሲባረር ሁለት ግልጽ ነገሮች ይሆናሉ።
መጀመሪያ ሙሽራይቱን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ትነጠቃለች። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሙሽራይቱን ለቀጣዮቹ 3½ ዓመታት የሰርግ ግብዣ ወደ ሰማይ ይወስዳታል።
በሰርጉ ላይ በሚቀርበው ግብዣ በሰማይ ሙሽራይቱ እየበላች ትደሰታለች።
የቀረው ዓለም ሕዝብ የክርስቶስ ተቃዋሚው አውሬ ሲመጣባቸውና ሲበላቸው እያለቀሱ ያሳልፋሉ።
ሁለተኛው ደግሞ ዓለም በሙሉ 3½ ዓመታት ወደ ሚፈጀው አሰቃቂ ታላቅ መከራ ይገባል። ይህም ሰይጣን ብዙ ሰዎችን የሚገድልበትና የሚያጠፋበት የመጨረሻው አጭር ጊዜ ነው። የቀረውን አጭር ጊዜ ተጠቅሞ የተቻለውን ያህል ብዙ ጥፋት ያደርሳል።
ዳንኤል 12፡1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።
55-0109 የአሕዛብ ዘመን ጅማሬ እና ፍጻሜ
በእርግጥም ሚካኤል ክርስቶስ ነው።
ሚካኤል ማለት ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን ለማስነሳት በመላእክት አለቃ መልክ ተገልጦ ሲመጣ ነው።
ከዚያም በኋላ ክርስቶስ እንደ መላእክት አለቃ ጣልቃ ገብቶ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ 144,000ዎቹን ከክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ያድናቸዋል።
ራዕይ 12፡13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
ሰይጣን ዘንዶው ከሰማይ በሚወርድበት ጊዜ አንድ ዓላማ ብቻ ነው ያለው፤ እሱም አይሁድ አማኞችን ማጥፋት ነው።
አይሁዶች ከ2,000 ዓመት በፊት ኢየሱስን አንቀበልም ብለው ገፍተውት በ70 ዓ.ም ከቤተመቅደሳቸው ጋር አብረው ጠፉ። በዚያ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያን ተገድለዋል።
ናዚዎች ጀርመኒ ውስጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ባስነሱት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ 6 ሚሊዮን አይሁዳውያን ተጨፍጭፈዋል፤ ይህም እግዚአብሔር ወደ አይሁድ የሚመለስበት ጊዜ መድረሱን የሚያሳይ ምልክት ነው።
ናዚዎች የፈጸሙት ጭፍጨፋ ዋነኛው ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምሳሌ ነው።
ናዚዎች የፈጸሙት ጭፍጨፋ በእግዚአብሔር ዓይን “የሕጻን ጨዋታ” ነው።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
አሁን ደግሚ ይህን ስሙ። ኢየሱስ በማቴዎስ 29 – 24፡29 እና 30 እንዲህ አለ።
ከነዚያ ወራት መከራ በኋላ። ይህ መከራ፣ ይህ የሕጻን ጨዋታ የሚመስል መከራ ካለፈ በኋላ።
ስለዚህ ታላቁ መከራ ምን ያህል አስከፊ እንደሚሆን ከመገመት በቀር ምንም ማድረገ አንችልም።
ራዕይ 12፡14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
አስደናቂ የማየት ችሎታ ያለው ንሥር የነብይን መንፈሳዊ የማየት ችሎታ የሚገልጽ ምሳሌ ነው፤ ይህም ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ገልጦ ያስተምራል። ሁለቱ ክንፎች ሁለቱን ነብያት ሙሴ እና ኤልያስን ይወክላሉ፤ እነርሱም 144,000ዎቹን አይሁዶች መሲሁ ኢየሱስ ሲመጣ እንዲቀበሉት ያዘጋጁዋቸዋል።
አሜሪካ ከወደመች በኋላ አይሁዶች ከምድር ሕዝቦች ሁሉ ተለይተው ብቸኞች ይሆናሉ። በዚያ መንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ በምድር ሕዝብ ሁሉ የተጠሉ ይሆናሉ። የክርስቶስ ተቃዋሚው ሙሉ ወታደራዊ ኃይል ሊያጠፋቸው ሲመጣባቸው አይሁዶች ራሳቸውን ማዳን በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ይሆናሉ። በዚያ ጊዜ ግን ሁለቱ ነብያት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸውን በመጠቀም የተፈጥሮ ኡደትን በማቋረጥ እስራኤልን ከጥፋት ይታደጋሉ።
“ከእባቡ ፊት”።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከጴጥሮስ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስልጣን የምትለው ብዙ ፖፕ እየተተካካ የደረሰበት መስመር ረጅም እባብ ይመስላል።
ይህ እባብ የቀረው የመጨረሻው ራስ ነው፤ እርሱም የክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ነው።
አስቀድሞ የነበረው አውሬ (ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነው ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም በየዘመኑ አንድ ፖፕ በስልጣን ላይ ነበረ) አሁንም እንደ ሌለ (ፖፑ ሲሞት ማለት ነው) ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ (አዲስ ፖፕ ይመረጣል ማለት ነው)። በምድር ላይ ከሁሉም ረጅም የመሪዎች የመተካካት ታሪክ የካቶሊክ ፖፕ ነው።
ራዕይ 17፡8 … አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ
ካቶሊኮች በሐሰት ከቅዱስ ጴጥሮስ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የፖፑ ስልጣን ብለው የሰየሙትን የአውሬውን አስፈሪ ፊት ይጋፈጠዋል። ይህ ፖፕ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ነው።
ዳንኤል 8፡23 በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል።
ይህ ሰው ብዙዎች ፈርተውት እንዲታዘዙት ያደርጋል።
አይሁዶች ከግብጽ ለወጡበት ለመጀመሪያው ፍልሰት ሙሴ በጣም የሚያስፈራ እባብ በመጋፈጥ ነው ስልጠና የወሰደው።
ዘጸአት 4፡2 እግዚአብሔርም፦ ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት? አለው። እርሱም፦ በትር ናት አለ።
3 ወደ መሬት ጣላት አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፥ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ።
4 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ … እጅህን ዘርግተህ ጅራትዋን ያዝ አለው። እጁንም ዘርግቶ ያዛት በእጁም ውስጥ በትር ሆነች።
የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ሊመጣ ገና 3,500 ዓመታት ይቀሩት በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር ለሙሴ የእባቡን ፊት እንዳይፈራው ነገረው።
እባቡ አስፈሪ ስለ ነበረ ሙሴ ሸሽቶት ሮጠ፤ ኋላ ግን ፍርሃቱን አስወግዶ በጭራው ያዘው።
ወደፊት በሚመጣው ታላቅ መከራ ወቅት ሙሴ ከክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ጋር ፊት ለፊት ይጋፈጣል።
በዚህ ትንቢት ውስጥ “ጭራው” የሚወክለው ሰይጣን የሚናገረውን “ተረት” ወይም የሐሰት “ታሪኩን” ነው። ሰይጣን የሚናገረው ሐሰት በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ነው።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ሁሉ ሐሰት እና ለማሳሳት የተዘጋጀ ነው።
የኢየሱስን እና የሙሴን ምሳሌ መከተል ብቻ ነው የሚያስፈልገን።
ንግግሩን (ተረቱን ወይም ጭራውን) ያዙና “ተብሎ ተጽፏል…” ከሚለው ጋር ይስማማ እንደሆን እዩ።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ካላገኛችሁት፤ ወዲያ ጣሉት።
ራዕይ 12፡15 እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
ውሃ አስተምሕሮዎችን እና ብዙ ሕዝቦችን ነው የሚወክለው።
ሰይጣን የሰው ብዛት ለሥራው ይመቸዋል።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
በተደራጁት ቤተክርስቲያኖች አማካኝነት በጣም ብዙ የተበላሸ የተጣመመ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮ አይሁዶች ላይ ይለቀቃል። ከብዙ ሃገሮች የተሰበሰበ ሰራዊት ሊያጠቃቸው ይነሳባቸዋል።
ሰይጣን ብዙ ሕዝብ በመጠቀም አይሁዶችን ያሸንፋቸዋል። ለጊዜው ድል ያደረጋቸው ይመስላል።
ራዕይ 12፡16 ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።
አሁን ግን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይገለጣል።
በነብያቱ ትዕዛዝ የምድር መንቀጥቀጥ ይመጣና ታንኮችን ከነሰራዊታቸው ይወጣቸዋል። አይሁዶችም ተደንቀው እነዚህ ነብያት የሚናገሩትን የወንጌል እውነት ማዳመጥ ይጀምራሉ። ነብያቱ ተፈጥሮን እንደ ጦር መሳሪያ አድርገው መጠቀም ከቻሉ ከጠላቶቻቸው በላይ ኃያላን ናቸው ማለት ነው።
ሙሴ “ዝንቦች ይምጡ” ብሎ ያውጃል። ብዙ ቢሊዮን ዝንቦች ይመጡና የጠላትን ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች አፍነው አውሮፕላኖቹን ይከሰክሷቸዋል።
ማቴዎስ 21፡21 ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤
በጣም ብዙ ትልልቅ የጦር መርከቦች እስራኤልን ለማጥቃት በሜዲተራንያን ባሕር ይመጣሉ። ሙሴ ደግሞ ለተራራ ቃልን ይናገራል።
የዚያን ጊዜ አንድ ትልቅ ተራራ ከእስራኤል ምድር ተነቅሎ በአየር ላይ ተወርውሮ ባሕር ውስጥ የጦር መርከቦች መካከል ሲወድቅ የሚፈጥረውን ወጀብ እና ነውጥ አስቡ። ከዚህ አደጋ ሰዎች በሕይወት ቢተርፉና መጥተው ቢያወሩ ማንም አያምናቸውም።
ራዕይ 12፡17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
የሴቲቱ የእስራኤል ዘር ኢየሱስ ነው።
እርሱም የአካሉ ራስ ነው፤ አካሉ ደግሞ ቤተክርስቲያን ናት።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ …
ስለዚህ የክርስቶስ ሙሽራ የፍጥረታዊቷ እስራኤል መንፈሳዊ ናት። የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ለብዙዎቹ የተሰወሩ የብሉይ ኪዳን ሚስጥራት ፍጻሜ እና መገለጥ ናት።
እግዚአብሔር የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ምን ልትመስል እንደሚገባት ቅርጽዋን አስቦ ወስኗል። ቤተክርስቲያንን ለመስራት የተጠቀበት ጥሬ እቃ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የኖሩ የአዲስ ኪዳን አማኞች ናቸው። ለዘመናቸው የተሰጣቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች የተቀበሉ አማኞች የቤተክርስቲያን አንድ አካል ክፍል ሆኑ። የተቀሩ በየዘመኑ የዳኑ ክርስቲያኖች ለዘመናቸው የተሰጣቸውን እውነት ለመቀበል የሰነፉ እና ቸልተኛ የሆኑ ፍላጎትም ያልነበራቸው ክርስቲያኖች ሁሉ ተቆርጦ የተጣለው የጥሬ እቃ ትራፊዎች ቅሬታዎች ሆነዋል። ሙሽራይቷ ልብሷን ስታዘጋጅ የምትፈልገውን ቅርጽ ብቻ ቆርጣ ትወስዳለች (ይህ ቅርጽ ልባሞቹ ቆነጃጃት ናቸው)። የቀረው ጥሬ እቃ ጥሩ ነው ግን ለልብሱ ቅርጽ አይጠቅምም።
እነዚህ ተቆርጠው የተጣሉ ቁርጥራጮች ቅሬታዎች ናቸው።
እነርሱም ሰነፎች ቆነጃጅት ይባላሉ። ለዘመናቸው የተሰጣቸውን የእውነት መገለጥ ለመቀበል አልተጉም።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት ማለትም ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የተገለጠውን እውነት ፈልገው ለመቀበል ያልተጉ ክርስቲያኖች ለሰይጣን የጭቃኔ ጥቃት ኢላማ ይሆናሉ። እርሱም ያለ ርህራሄ ያጠፋቸዋል።
ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
ሰው ሰራሽ የሆነው ዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሬውን ይወክላል። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ህብረት የሰው ሰራሹ የካቶሊክ ድርጅት ሰው ሰራሽ ምስል ናቸው። ይህም የአውሬው ምስል ነው።
የማንኛውን ድርጅት ሕይወቱ ገንዘብ ነው።
ዓለም አቀፍ የፕሮቴስታንቶች ሐይማኖታው ድርጅት ለመመስረት የሚበቃ ገንዘብ ያላት ሃገር አሜሪካ ብቻ ናት።
ሰዎች ብዙ ከመታለላቸው የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሳይሆን ቤተክርስቲያናቸው የምትላቸውን ያምናሉ።
በታላቁ መከራ ወቅት የፕሮቴስታንት ምስል በስልጣን ይናገራል።
የቤተክርስቲያን ድርጅት የአስሩን ፈላጭ ቆራጭ ወታደራዊ መንግስታት ድጋፍ ያገኛል። ሰዎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን ባያደምጡና ባይታዘዙ ወታደራዊ አምባገነን መሪዎች ይገድሏቸዋል።
አምባገነኖች እንደ ንጉስ ይመራሉ። የንጉስ ዓይነት ስልጣን ይኖራቸዋል ግን ዘውድ አይጭኑም።
ወታደራዊ ስልጣናቸውንና ኃይላቸውን ለመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ይሰጡታል። ዓላማቸው እግዚአብሔር ለአይሁዶች ያለውን ዓላማ መቃወም እና ከታላቁ መከራ በፊት የሚድኑትን ሰነፎቹን ቆነጃጅት ማጥፋት ነው።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤
ንጉስ ቴዎዶሲየስ የሮማ ፖፕን የተቃወሙ ሰዎችን እያሳደደ መግደል ያስደስተው እንደነበረ ሁሉ ልክ እንደዚሁ አስሩ ወታደራዊ ኃይላት በስተመጨረሻ ነቅተው ቤተክርስቲያኖችን የሚቃወሙትን አስሩን ቆነጃጅት ያጠፉዋቸዋል።
ከነዚህ አስቀድመው ከዳኑ ሰነፍ ቆነጃጅት መካከል ማናቸውም በታላቁ መከራ ውስጥ አይተርፉም። በቆራጥነታቸው ይሞታሉ። የሚጸጽታቸው ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያን መሪዎች በሚያባብል ስብከታቸውና በሚያዝናና የአምልኮ ፕሮግራማቸው ቤተክርስቲያኖችን እንቅልፍ ሲያስተኙ በጊዜ ነቅተው አለመቃወማቸው ብቻ ነው።
ኢየሱስ ደሙ በስርየት መክደኛው ላይ በነበረ ጊዜ ከታላቁ መከራ በፊት ሰነፎቹን ቆነጃጅት አድኗቸዋል።
ስለዚህ መዳናቸው በኢየሱስ ሕይወት ምስክርነት እንጂ በራሳቸው ምስክርነት ላይ የተመሰረተ አይደለም። ሥራዎቻችን ሊያድኑን አይችሉም።
ራዕይ 12፡17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
በታላቁ መከራ ውስጥ ግን የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት ለቤተክርስቲያናቸው እና ለቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ተሰጥተው መገዛታቸው ስሕተት እንደነበረ ያስተውላሉ ምክንያቱም መጨረሻ ይህ ታዛዥነታቸው ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይጥላቸዋል። የታላቁ መከራ ስቃይና ሰቆቃ አንቀላፍተው ደንዝዘው ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው እውነቱን ያላወቁትን ሁሉ ያነቃቸዋል።
የዚያን ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመላላሽነታቸውን ትተው መጽሐፍ ቅዱስን ወደ መታዘዝ ይመለሳሉ።
ነገር ግን ሐሰተኛ የሆነችዋን ቤተክርስቲያን መቃወማቸውም ደግሞ የሞት ፍርድ ያስፈርድባቸዋል።
ነገር ግን በድንጋጤ ባንኖ እንደሚነቃ ሰው ነው የሚነቁት፤ በነቁም ጊዜ ስለ እምነታቸው ለመሞት ተዘጋጅተው ይነሳሉ።