ራዕይ 10፡1-3 ወደፊት ስለሚፈጸሙ ነገሮች ነው የሚናገረው



ሰዎችን በቀላሉ ማሳሳቻ ዘዴ ወደፊት የሚፈጸሙ ነገሮችን ተፈጽው አልፈዋል ብሎ ማሳመን ነው። ከዚያ ዓይናቸው እያየ ሲፈጸም ይቃወሙታል።

First published on the 5th of August 2021 — Last updated on the 5th of August 2021

ራዕይ 10፡1 ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፎቶ በተነሳው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና አማካኝነት አልተፈጸመም፤ ምክንያቱም ደመናው ደመናው ሰሜን አሪዞና ውስጥ በምትገኘው ፍላግስታፍ ከተማ ላይ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ደቂቃዎች ብቻ ነው የታየው።

 

 

ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በአንድ ጊዜ ሁለት ደመናዎች ናቸው የታዩት። አንዱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ትንሹ ደመና ከኃይለኛ የሮኬት ፍንዳታ በኋላ የተፈጠረ ጭስ ነው።

 

 

ማርች 28 ቀን 1963 ዓ.ም በፍላግስታፍ ከተማ ላይ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ሲሄድ ፎቶ ግራፍ የተነሳው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና በማቴዎስ 24፡30 “የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ” የተባለለት ምልክት ነው።

አጠገቡ የነበረው የጭስ ደመና ደግሞ በኢዩኤል 2፡30 “የጢስ ጭጋግ” ተብሎ የተጠቀሰው ነው።

እስከ 1964 ድረስ ወንድም ብራንሐም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ይወርዳለ ብሎ ሲጠባበቅ ነበር።

64-0112 ሻሎም

በሰባተኛው ሰዓት ግን ሰባተኛው መልእክተኛ እነዚህ ሁሉ ሚስጥሮች ይፈጸሙ ዘንድ ይመጣል።

… ከዚያም በኋላ ቀጥሎ ሌላ መልአክ ሲወርድ አየ

ብርቱው መልአክ ሊወርድ የሚችለው ሚስጥራቱ በሙሉ ተፈጽመው ሲያልቁ ብቻ ነው። ሚስጥራቱ ታሕሳስ 1965 ዓ.ም ተጠናቀዋል።

ስለዚህ ብርቱው መልአክ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሊመጣ የሚችለው።

ደመናው ፎቶ ግራፍ በተነሳ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ከታክሰን 200 ማይልስ ርቀት ላይ ነበረ፤ ስለደመናውም ምንም አላወቀም።

ከስምንት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ሰባት መላእክት ሳንሴት ፒክ አጠገብ ወንድም ብራንሐምን ሊጎበኙ መጡ። በዚያን ቀን ሲመጡ ምንም ደመና አልሰሩም። ወደ ጄፈርሰንቪል እንዲመለስና ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ስለተጻፉት ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ገልጦ እንዲያስተምር ትዕዛዝ ሰጡት።

 

 

መላእክቱ ወደ እርሱ የመጡበት የሳንሴት ፒክ ከተማ ደመናው ከታየበት ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቆ የሚገኝ ከተማ ነው።

ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድ ከታክሰን የጠፈር ምርምር ጣቢያ ትልቁን ደመና ፎቶግራፍ ያነሳው ጊዜ ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ከፊኒክስ እና ከፕሬስኮት የተነሱ ሌሎች ፎቶግራፎችም ትንሹን ደመና አያሳዩም ምክንያቱም ትኩረታቸው ትልቁ ደመና ላይ ብቻ ነበር።

ወንድም ብራንሐም የሰራው ትልቅ ስሕተት ደመናው መላእክቱ ከእርሱ ጋር ቆይተው ሲመለሱ የፈጠሩት ምልክት እንደሆነ አድርጎ ማሰቡ ነው።

ስለ ትልቁ ደመና ብዙ ስሕተት ተነግሯል፤ ስለዚህ ስለ ደመናው የተረጋገጡ እውነታዎችን መጀመሪያ መመልከት አለብን።

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

ይህ ማርች 28 ቀን 1963 ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድ በፍላግስታፍ ከተማ ላይ ከታክሰን ሆኖ ፎቶግራፍ ያነሳው ደመና ነው።

ደመናው ውስጥ ምንም የፊት ምስል የለም።

 

 

ምንም እግሮች አልታዩም ስለዚህ እንደ እሳት አምድ የሆኑ እግሮችም አልነበሩም።

በዚያ አካባቢ ባሕርም የለም።

ምንም እጅ አልታየም፤ ስለዚህ በእጅ ውስጥ የተከፈተ መጽሐፍም የለም።

የደመናው መሃሉ ፊት ሊኖርበት የሚችልበት ቦታ ጨለማ ነው፤ ደግሞም እንደ ፀሃይም አያበራም። ደመናው ውስጥ የሚታይ ፊት አልነበረም።

በዙርያውም ቀስተ ደመና የለም።

ስለዚህ ይህ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10፡1 ፍጻሜ አይደለም።

ደግሞም መልአኩ ወደ ምድር እንደሚወርድ ነው የተጻፈው፤ ይህ ደመና ግን በ43 ኪሎሜትር ከፍታ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ለ28 ደቂቃ እየተንሳፈፈ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ አግድም ሄደ እንጂ አልወረደም። ደመናው ወደ ምድር አልመጣም።

ፍጥረታዊ ደመና እስ 43 ኪሎሜትር ሁሉ ከፍ አይልም። ከ20 ኪሎሜትር በላይ ደመና ለመፍጠር የሚበቃ እርጥበት የለም።

ፍላግስታፍ ከታክሰን እና ከሳንሴት ፒክ በ200 ማይልስ ወደ ሰሜን ርቆ የሚገኝ ከተማ ነው፤ ሳንሴት ፒክ ወንድም ብራንሐም 7ቱን መላእክት ያገኘበት ቦታ ነው።

ስለዚህ ይህ ደመና የመልአኩ ወደ ምድር የመምጣት ፍጻሜ አይደለም።

[እስቲ ደመናው የመልአኩ ወደ ምድር መምጣት ነው ብለን እናስብ። ለማን ብሎ ነው የመጣው?

ፍላግስታፍ ከተማ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለመፈጸም በቂ መንፈሳዊነት ያለው ሰው አልነበረም። ወንድም ብራንሐም 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቃ በምትገኘው ታክሰን ከተማ ውስጥ ነበር፤ እርሱም ስለ ደመናው ለጥቂት ወራት ምንም የሰማው ነገር አልነበረም፤ የሰማው ፎቶ ግራፍ ካየ በኋላ ነበር፤ ፎቶግራፉም በባለሙያዎች ተነካክቶ ስለነበረ ውስጥ የፊት ምስል ነበረው እንጂ እውነተኛው የመጀመሪያ ፎቶ አልነበረም።

ከዚያ በኋላ ወንድም ብራንሐም ትልቅ ስሕተት ሰራ፤ ደመናው ማርች 8 ቀን 1963 እርሱን የጎበኜ ሰባት መላእክት ሲመለሱ የተፈጠረ መሰለው።

ከዚህም የተነሳ ደመናው ወደላይ የሄደ መሰለው እንጂ ደመናው የመልአኩ መውረድ ነው ብሎ አላሰበም።]

 

ችግር መፈጠር የጀመረው ወንድም ፔሪ ግሪን የደመናውን ፎቶ ከላይፍ መጽሔት የጀርባ ሽፋን ላይ ኮፒ አድርጎ ከወሰደው በኋላ ነው።

 

 

ፎቶኮፒው በቴክኒካዊ ችግሮች ምክንያት የመጀመሪያው ፎቶግራፍ ትክክለኛ ቅጂ ሆኖ አልወጣም፤ ምክንያቱም ቅጂው ውስጥ ጠቆርና ደመቅ ያሉ ምልክቶች ብቅ ብለዋል። ፎቶኮፒው ውስጥ ሁለት ዓይኖች እና አፍንጫ በከፊል እንዲሁም ከደመናው በታች ደማቅ ብርሃን ታይቷል።

ፎቶኮፒው ላይ ምን ዓይነት ትኩረት እንደምታደርጉ መወሰን ያስፈልጋችኋል፤ ምክንያቱም የመጀመሪያውን ፎቶ ለውጦታል።

ፎቶኮፒውን በማየት ደመናው የዳኛ ዊግ ይመስላል ብላችሁ መከራከር ትችላላችሁ።

ደመናው የሰው ጭንቅላት ምስል ከሆነ ፊቱ ወደ ምድር እያየ ይመስላል።

ከደመናው ራስ ጋር የተያያዘ አካል ቢኖር አካሉ ከምድር ጋር ትይዩ ሆኖ የተኛ ይመስል ነበር።

ደመናው ምድር ላይ ለቆመ አካል ራስ ሆኖ አልታየም።

 

 

ከላይ ያለው ስዕል ዮሐንስ ምን እንዳየ ያሳየናል። ደመናው የመልአኩ ልብስ ሲሆን መልአኩም ፎቶግራፍ የተነሳውን ደመና አይመስልም።

ትንሹ የጭስ ደመናስ?

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ካሊፎርኒያ ውስጥ ቫንደንበርግ አየር ኃይል ጣብያ ላይ በ43 ኪሎሜትር ከፍታ አንድ ሮኬት ፈነዳ። ነፋስ ጭሱን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ እየገፋው አሪዞና ውስጥ ወደሚገኘው ወደ ፍላግስታፍ አመጣው። ከዚህ በታች ያለው ካርታ ውስጥ በነጠብጣብ የተሰራውን ሰማያዊ መስመር ተመልከቱ።

 

 

ከታች ያለው ካርታ አሪዞናን በትልቁ ያሳያል።

 

 

ቀስቱ ከፀሃይ መጥለቅ በላ ትልቁ ደመና እና የጭሱ ደመና ወዴት እንደተንቀሳቀሱ ያሳየናል። ትንሹ የጭስ ደመና ይንቀሳቀስ ከነበረው ከትልቁ ደመና በ20 ማይልስ ከኋላ ይከተል ነበር።

ከሁለቱ ደመናዎች ፊት የነበረው ብቸኛው ከተማ ዊንስሎው ነበር።

 

 

ዶ/ር ማክዶናልድን ግራ ያጋባው ነገር ይህ ነው። ከዊንስሎው በኩል በተነሱ ፎቶግራፎች ውስጥ ሁለት ደመናዎች አየ።

የሜሴጅ ሰዎች ይህንን እውነታ በጭራሽ አይጠቅሱትም። ደግሞም ዶ/ር ማክዶናልድ ስለ ሁለቱ ደመናዎች ያቀረበውን ሪፖርትም አይጠቅሱም። ሁለት ደመናዎችን በተመለከተ አንዳችም ፍጥረታዊ ማብራሪያ ሊገኝ አልቻለም። ለዚህ ነው የደመናዎች ሚስጥር የሚል ስያሜ የሰጠው።

ከኋላ የታየው የጭስ ደመና በሮኬት ፍንዳታ የተፈጠረ ሲሆን ከፊት ያለው ትልቁ ደመና ደግሞ መላእክት የፈጠሩት ደመና ነው።

ትልቁ ደመና ግን ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ርቆ ነው የታየው፤ ወንድም ብራንሐም ሳንሴት ፒክ አካባቢ ከስድስት ቀናት በኋላ ማርች 6 ቀን 1963 ለአደን ሄዶ ነበር። ሰባቱ መላእክትም ከሁለት ቀናት በኋላ በጥዋቱ ማርች 8 ቀን መጥተው አገኙት። ስለዚህ ሰባቱ መላእክት እርሱን ያገኙት ደመናውን ከሰሩበት ቀን ስምንት ቀናት ካለፉ በኋላ ነው።

ማርች 8 ቀን አንዳችም ደመና አልተፈጠረም። ወንድም ብራንሐም የዚያን ቀን የሆነ መሰለው እንጂ።

በደምብ መረዳት እንድንችል በከፍታ ላይ ስለሚፈጠሩ ደመናዎች ጥቂት መመርመር አለብን።

 

 

አብዛኞቹ ደመናዎች ከ20 ኪሎሜትር በላይ አይፈጠሩም ምክንያቱም ከዚያ ከፍታ በላይ ደመና ለመፍጠር የሚሆን እርጥበት የለም።

በ80 እና 85 ኪሎሜትር ከፍታ መካከል በሌሊት የሚደምቁ ደመናዎች ይፈጠራሉ፤ የሚፈጠሩትም የውሃ ትነት ቀዝቅዞ ወደ በረዶ ቅንጣቶች ሲለወጥ ነው። እነዚህም የበረዶ ቅንጣቶች በሌሊት ብርሃን ያንጸባርቃሉ። እነዚህ የበረዶ ቅንጣቶች የሚፈጠሩበት ከፍታ ላይ አየሩ ከዜሮ በታች 126 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ውስጥ ነው። በዚህ ዓይነት ቅዝቃዜ ውስጥ በአቧራ ብናኝ ወይም በእሳተ ገሞራ ጭስ ብናኝ ላይ በረዶዎች ይፈጠራሉ።

እነዚህ ሁለት ደመናዎች ግን ያን ያህል ከፍታ ላይ አልነበሩም። ስለዚህ ደመና በማይገኝበት ከፍታ ላይ ነው የታዩት። በ20 እና በ80 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ሰው ሰራሽ ደመና ሊገኝ የሚችልበት መንገድ ከሮኬት ፍንዳታ ወይም ከአውሮፕላን ጭስ የተነሳ የሚፈጠር ደመና ብቻ ነው።

ከሮኬት ፍንዳታው የተፈጠረው ጭስ አንዱን ደመና ብቻ ነው የፈጠረው። በዚያ ቀን አውሮፕላኖች ወይም ሮኬቶች በዚያ በኩል አላለፉም።

ወደ ላይ ከፍ እያልን ስንሄድ አየር ስለሚበታተን እየሳሳ ይሄዳል። ከዚህም የተነሳ ከፍታ ላይ የሚገኙ ደመናዎች በጣም በስሱ ስለሚበታተኑ በፀሃይ ብርሃን አይታዩም።

 

 

ሲመሽ ፀሃይ ስትጠልቅ ፀሃይዋ ከታች ያሉትን ደመናዎች ስለማታገኛቸው ይጠቁራሉ፤ ወደ ላይ ከፍ ያሉት ደመናዎች ግን ለጥቂት ጊዜ የፀሃይ ብርሃን ስለሚያገኛቸው ይታያሉ። ፀሃይ በምትጠልቅበት እና በምትወጣበት ሰዓት ብዙውን ጊዜ ሳተላይቶች ይታያሉ።

 

 

ከዚህ በታች ያለው ምስል ፎቶግራፍ አይደለም፤ ነገር ግን ሁለቱ ደመናዎች ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ለ28 ደቂቃ እንዴት ሊታዩ እንደቻሉ ያሳያል።

 

 

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ሌላም ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ እርሱም ደመናን ተጎናጽፎ ነበር …

በእጁም ትንሽ የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ ነበር (በዚህ ጊዜ ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ ነው። አሁን ማሕተሞቹን እየፈታናቸው ነን፤ ይህ ነገር ግን ተፈቷል።) … ቀኝ እግሩን ባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን ደግሞ ምድር ላይ አደረገ

 

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን በመፍታት ተጠምዶ ነበር።

ብርቱው መልአክ የሚመጣው ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ ነው።

መልአኩ የሚመጣው ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ ነው ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ነው ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት የሚችሉት። ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች ሳይገለጡ በፊት የታየው ደመና የመልአኩ መውረድ ሊሆን አይችልም።

ይህም ደግሞ ሰባተኛው ማሕተም ገና ያልተከፈተ በመሆኑ ሌላ ችግር ይፈጥራል። ስለ ሰባተኛው ማሕተም የተነገረን ዝምታ ብቻ ነው። ዝምታን ደግሞ መተርጎም አይቻልም። ስለዚህ እግዚአብሔር ዝም ባለ ጊዜ እኛም ዝም ማለት አለብን።

64-0719M የመለከት በዓል

እንደምታቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተከፈተም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

መልአኩ ሊወርድ የሚችለው ሰባተኛው ማሕተም ሲፈታ ብቻ ነው። ይህም የሚሆነው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ገና ወደ ፊት ነው።

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች እየሰበከ ሳለ መልአኩ እንደሚወርድ ሲጠባበቅ ነበር።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ሙሽራይቱ የምትወሰድበት ሰዓት ቢመጣስ? ጊዜ እና ዘመንን መቁጠር የሚያበቃበት ጊዜ ቢመጣስ?

ብርቱው መልአክ ቢመጣና አንድ እግሩን በምድር ሌላኛው እግሩን ደግሞ በባሕር ላይ አድርጎ ከራሱ በላይ ደግሞ ቀስተ ደመና አድርጎ “ጊዜ አብቅቷል” ብሎ ሊያውጅ በደጅ ነው። ከዚያም በተጨማሪ እጁን ወደ ላይ አንስቶ ይህ ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ጊዜ እንደማይኖር ምሏል።

 

ይህ ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከ18 ቀናት በኋላ ሲሆን እርሱም እንዲህ አለ፡- “መልአኩ ሊመጣ ተዘጋጅቷል”። ስለዚህ እስከዚያ ጊዜ ድረስ አልተፈጸመም።

ልብ በሉ። መልአኩ እግሮች እንዳሉት በአጽንኦት ነው የተናገረው።

ደመናው ግን ብርቱው መልአክ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ደመናው ራስ ብቻ እንጂ እግሮች አልነበሩትም።

 

የሚስጥራቱ መገለጥ አስቀድሞ መጠናቀቅ አለበት። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ሊገለጥ የሚችለው።

ስለዚህ ሚስጥራቱ እስኪገለጡ ድረስ መልአኩ ሊወርድ አይችልም።

63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት

… አሁንም ወደ 10ኛው ምዕራፍ ተመልሶ ከሚመጣው ጊዜ በኋላ ሚስጥራቱ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይናገራል፤ ማሕተሞቹም ይፈታሉ ከዚያም በኋላ ዘመን እንደማይኖር ይታወጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ሁሉ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል። ከዚያ ጊዜ ብዙም እሩቅ አይደለንም።

ቁልፉ ነጥብ መልአኩ የሚወርድ ሚስጥራቱ ሁሉ ተገልጠው ከተጠናቀቁ በኋላ መሆኑ ነው።

መልአኩ ሚስጥራቱን ለመግለጥ አይደለም የሚወርደው።

ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ጥቅስ ተመልከቱ። በምድር ላይ ሚስጥራቱን ያጠናቀቀ ሰባተኛ መልአክ ነበረ። “ከዚያ በኋላ ሌላ መልአክ” ሲወርድ አየ።

ብርቱው መልአክ ይወርዳል ሰባተኛውም መልአክ ከዚያ ወዲያ ሚስጥራቱን መግለጥ ይጨርሳል።

64-0112 ሻሎም

በሰባተኛው ሰዓት ግን እነዚህ ሁሉ ሚስጥራት ይፈጸሙ ዘንድ ሰባተኛው መልእክተኛ ይመጣል።

ሰባተኛው የምድር መልእክተኛ ተመልከቱ ቃሉ የሚናገርለት ይህ መልአክ በዚያ ሰዓት በምድር ላይ ነው። መልአክ ማለት “መልእክተኛ” ነው። ከዚያም በኋላ ደግሞ ሌላ መልአክ ሲወርድ አየ፤ ይህም መልእክት የተሰጠው ምድራዊው መልአክ አይደለም ከእርሱ ሌላ የሆነ በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ያለው ከሰማይ የሚወርድ ብርቱ መልአክ ነው እንጂ፤ እርሱም እግሩን በምድር እና በባሕር አድርጎ ቆመ፤ ለዘላለምም በሚኖረው ምሎ “ከዚህ በኋላ አይዘገይም” አለ።

ሰባቱን ማሕተሞች ፈቶ ከመግለጡ በፊት ተዓምራትን እንዳደረገ መጀመሪያም በሰማያት ተዓምር እንዳደረገ ይናገራል።

 

ያ ጊዜ 1964 ዓ.ም ነበረ፤ ማለትም ከደመናው አንድ ዓመት በኋላ። ስለዚህ መልአኩ የሚወርደው ሰባተኛው መልአክ ሚስጥራቱን ገልጦ ከጨረሰ በኋላ ነው። ሚስጥራቱ እስከ ዲሴምበር 1965 ድረስ ተገልጠዋል። አገልግሎቱም የተጠናቀቀው የዛኔ ነው።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ነገር ግን ይህ መልአክ ቀጣዩን አዋጅ ይዞ ይመጣል። መልአክ ማለት “መልእክተኛ” ነው። ከሰማይም ያንን የብርሃን አምድ፣ ደመና በራሱም ላይ ቀስተ ደመና አድርጎ ይወርዳል። ቀስተ ደመና ደግሞ የቃልኪዳን ምልክት ነው። ስለዚህ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን ደግሞ በባሕር ላይ አድርጎ “ከእንግዲህ አይዘገይም” ብሎ የሚያውጀው ክርስቶስ ነው።

… እርሱም ከሰማይ ይወርዳል ምክንያቱም በዚያ ጊዜ ሚስጥሩ ሁሉ ይፈጸማል።

ሚስጥሩም በሙሉ በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከዚህ በኋላ አይዘገይም” ሰባቱም ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።

 

ብርቱው መልአክ ከአሁን በኋላ መውረድ ይችላል ምክንያቱም ሚስጥራቱ ተገልጠው አልቀዋል።

ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና በሰማያት ላይ የተገለጠ ምልክት ነው።

የአንድ ክስተትን ምልክት ክስተቱ ራሱ ነው ብላችሁ አትሳቱ።

64-0112 ሻሎም

በዚያን ዕለት በደቢባዊው ዩናይትድ እስቴትስ እና ሚክሲኮ ውስጥ ብዙ ቦታ ፎቶ አነሱ። ፎቶው አሁንም ላይፍ መጽሔት ውስጥ አለ፤ እነርሱም ፎቶው አልገባቸውም። እርሱ ግን በምድር ላይ ሳይሰራው በፊት በሰማያት ላይ ያውጀዋል። ሁሌ እንደዚህ ያደርጋል። በመጀመሪያ ምልክቶችን በሰማያት ላይ ያሳያል።

 

ስለዚህ የ1963 ደመና ወደ ምድር አልወረደም፤ እዚያው ሰማይ ላይ በ27 ማይልስ ከፍታ ተንሳፍፎ ቀርቷል፤ እርሱ በሰማያት ላይ የተገለጠ ምልክት ነው።

ወንድም ብራንሐም በ1965 ከምድር ከመሰናበቱ አምስት ወራት በፊት ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።

1965-0718M

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። ዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል። እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የምድር መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ይታያል። ”

 

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

ይህም ደመናውን በትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቦታው ያስቀምጥልናል። “የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ”።

ይህም እግዚአብሔር ሚስጥራቱን ሊገልጥቅ ጊዜው መቅረቡን የሚያሳይ ምልክት ነው፤ ከዚህም የተነሳ ሰባተኛው መልአክ አገልግሎቱን መፈጸም ይችላል።

63-0707M ክሱ

እንዲህ አለ፡- “ይህ የእግዚአብሔር ቃል ነው! በነብዩ የተነገረው ይህ ነው! መንፈሴን በስጋ ለባሾች ሁሉ ላይ አፈስሳለው። ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ። በሴቶች ባርያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈስሳለሁ፤ በላይ በሰማያት ምልክቶችን አሳያለው፤ በምድርም እሳት፣ እና የጢስ ጭጋግ ይሆናል።”

“የጢስ ጭጋግ” በሰማዩ ላይ እንዲታይ ከቫንደንበርግ አየር ኃይል የተወነጨፈው ሮኬት ሰማዩ ላይ ፈነዳና በከፍታ ላይ ጭሱ በመታየቱ የኢዩኤል ትንቢት ሊፈጸም ችሏል።

 

ኢዩኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።

 

ይህ ቀጣዩ ጥቅስ ደግሞ መልአኩ ለሙሽራይቱም ለአይሁዶችም እንደሚወርድ ስለሚያስመስል ብዙ ነገሮችን ያወሳስባል።

ስለዚህ መልአኩ ሊመጣ የሚችለው ልክ ሙሽራይቱ ከመወሰዷ በፊት ነው።

1963 ክፍተት

በራሱ ላይ … ቀስተ ደመና

ልብ ብላችሁ ብታስቡ ይህ ክርስቶስ ነው (አያችሁ?) ምክንያቱም እርሱ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የቃልኪዳኑ መልእክተኛ ተብሎ ተጠርቷል፤ እርሱም በቀጥታ ወደ አይሁዶች ይመጣል፤ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ዘመን አብቅቷል። አያችሁ? እሺ።

… ፊቱም ደግሞ … እንደ ጸሐይ ያበራል፤ እፍሮቹም እንደ እሳት ነበልባል፤

(ይህ ቃል ቤተክርስቲያን ጊዜዋን ጨርሳ ስትወሰድ መልአኩ ወደ አይሁዶች እንደሚመጣ ይናገራል)።

ራዕይ ምዕራፍ 1 ውስጥ ያለውን መልአክ ታስታውሱታላችሁ? መልአክ መልእክተኛ ነው፤ እርሱም የእስራኤል መልእክተኛ። ይህ ጊዜ ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ነው። አያችሁ? ወይም ደግሞ ለመነጠቅ በምትዘጋጅበት ሰዓት ነው። ቤተክርስቲያንን ሊወስዳት ይመጣል።

 

መልአኩ ለመነጠቅ ለተዘጋችው ቤተክርስቲያን አገልግሎት አለው፤ መልአኩ እንዲሁም ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ለቤተክርስቲያን መልእክት አለው።

ስለዚህ መልአኩ ልክ ቤተክርስቲያን ከመነጠቋ በፊት ለትንሳኤ ይመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይሁዶች ወደ ታላቁ መከራ ሊገቡ ሲሉ ወደ እነርሱ ይመለሳል፤ ይህም ዳንኤል ታላቁ አለቃ ሚካኤል ለአይሁዶች ይቆማል ብሎ የተናገረው የሚፈጸምበት ጊዜ ነው።

ዳንኤል 12፡1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።

 

ይሁዳ 1፡9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።

የመላእክት አለቃ ማለት ኢየሱስ እንደ መልአክ ሆኖ ሲገለጥ ነው።

የመላእክት አለቃ ተልእኮው ከሙታን ትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው። የሙሴን አካል ከሰይጣን ነጥቆ ወሰደ፤ በዚህም ምክንያት ሙሴ በመገለጥ ተራራ ላይ ተገልጦ ከኢየሱስ ጋር ሊነጋገር ችሏል።

ስለዚህ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ የመላእክት አለቃ ነው።

55-0109E የአሕዛብ ዘመን መጀመሪያ እና ማለቂያ

“በዚያን ጊዜ ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” በእርግጥ ሚካኤል ክርስቶስ ነው፤

ስለዚህ መልአኩ ወደ ቤተክርስቲያን የሚወርደው ለምንድነው? ቅዱሳንን ከሙታን ለማስነሳት ነው።

64-0119 ሻሎም

ያም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ አንድ እግሩን ባሕር ላይ አንድ እግሩን ደግሞ በምድር ላይ አድርጎ በቆመ ጊዜ እና በራሱ ላይ ቀስተደመና በወጣ ጊዜ “ከእንግዲህ አይዘገይም” ብሎ ማለ። ያ ጊዜ ሲመጣ ከሙታን መካከል ተለይታችሁ ትነሳላችሁ።

በትንሳኤ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ ትሄዳለች፤ ወንጌሉ ደግሞ ተመልሶ ወደ አይሁዶች ይሄዳል።

 

ወንድም ብራንሐም ራዕይ 10፡1-7 ሙሉ በሙሉ ወደ ፊት እንደሚፈጸም ተናግሯል።

የመጀመሪያው ማሕተም

ስለዚህ በፊት ተሰውረው የነበሩ ሚስጥራትን ሁሉ ይገልጣል፤ ራዕይ 10፡1-7። ይህ ሁሉ ይፈጸማል።

 

ይህን በተናገረ ጊዜ ጊዜ 1963 ነበረ፤ እርሱም ራዕይ 10፡1-7 ወደፊት ነው የሚፈጸመው አለ።

በዚያ ጊዜ ደመናው መጥቶ ሄዷል። ሆኖም ራዕይ 10፡1-7 የሚፈጸመው ገና ወደፊት ነው።

ግራ የሚያጋባው ክፍል ይህ ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ራዕይ 10፡7 ሚስጥራትን ለመግለጥ ብቻ አይደለም የተጻፈው፤ ወንድም ብራንሐም ሲያስተምር ሚስጥራትን ገልጧል። ይህ ክፍል የተጻፈው በተጨማሪ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ለመፈጸም ነው፤ ይህም የመጨረሻው ዘመን አማኞች ከመጀመሪያው ዘመን አማኞች ጋር አንድ ዓይነት እምነት ማመናቸው ነው።

ወንድም ብራንሐም ይህን ሊያደርግልን አይችልም። ወንድም ብራንሐም ሚስጥራቱ ምን ማለት እንደሆን ለእኛ በማስተማር ሃላፊነቱን ተወጥቷል፤ እኛ ግን ከእኛ የሚጠበቅብንን ገና አላደረግንም።

ወንድም ብራንሐም ሚስጥረቱን ገለጠና ድምጹን በቴፕ ቀድቶ አስቀመጠልን። ይህ ሁሉ ግን ጥቅሱ ከሚናገረው ግማሹ ብቻ ነው።

ሙሽራይቱ የወንድም ብራንሐምን ትምሕርት አድምጣ ንግግሮቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር በማመሳከር መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እና የተጻፈውን ቃል በማመን ልክ እንደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መመላለስ አለባት።

መጀመሪያ ማንበብ እንማራለን፤ ከዚያ ለመማር እናነባለን።

መጀመሪያ ከወንድም ብራንሐም ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ምልክቶችን እና ምሳሌዎችን እንዴት እንደምንተረጉም እንማራለ፤ ከዚያ በኋላ ሚስጥራትን መረዳት እንችላለን። ከዚያ በኋላ በዚህ መረዳት አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን እናነባለን፤ በዚህም መሰረት ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ እንማራለን። መረዳታችንም ሁልጊዜ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ካስተማረችው ትምሕርት ጋር መስማማት አለበት።

የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ስትመለስ ብቻ ነው የመጨረሻው ዘር መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር ሊመሳሰል የሚችለው። ከዚያ በኋላ በመከር ጊዜ የመጨረሻው ዘር ከሞተው ተክል ላይ ይታጨድና ወደ ሰማይ ይወሰዳል።

የመጀመሪያው ዝናብ የትምሕርት ዝናብ ነው።

ወንድም ብራንሐም ወደ ሰማይ ለመነጠቅ ማወቅ የሚያስፈልገንን ሚስጥራት ገልጦልናል። እኛ ግን አሁን ከጥቅሶቹ በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንተረጉም ራሳችንን ማስተማር አለብን። ዘሩ በሞተችው የቤተክርስቲያን ተክል ላይ ሆኖ በስሎ ለመታጨድ ይደርሳል፤ እውነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ከመጥፋቷ በፊት እንደነበረው የጥንቷ ቤተክርስቲያንን የመጀመሪያ አስተምሕሮ እስኪመስል ድረስም ይለወጣል።

ከዚያም ኋላኛው ዝናብ፣ የመከሩ ዝናብ ይመጣል።

ለመከር የደረሰው ዘር መጀመሪያ የተዘራውን ዘር በመሰለ ጊዜ ከሞተው ተክል ላይ ታጭዶ ይወሰዳል።

ኋለኛው ዝናብ ወይም የመከር ዝናብ የሚባለው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን በትንሳኤ ከመቃብራቸው ሲወጡ ነው። በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት በሰባቱ ነጎድጓዶች አማካኝነት አካላቸው ይለወጣል፤ ከዚያም ሁለቱም ወገኖች ከምድር ተነጥቀው ወደ ሰማይ ይሄዳሉ።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

የእኛ ችግር መጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ቅዱሳንን ትንሳኤ መለየት ነው። መጨረሻው መድረሱን የሚጠቁመን ብቸኛ ምልክት ይህ ነው። ኢየሱስ ከትንሳኤው አርባ ቀናት በኋላ ወደ ሰማይ አረገ።

ስለዚህ በዚህ ዘመን የሚሆኑ ክስተቶች ከጥንቱ ጋር የሚመሳሰሉ ከሆነ እኛም አካላችን እስኪለወጥ ተመሳሳይ የጊዜ ገደብ ነው የሚሰጠን። ሰባቱ ነጎድጓዶችም ሚናቸውን የሚጫወቱት በዚህ በአካላችን መለወጥ ላይ ነው። ምን እንደሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ለይተን ካላወቅናቸው ሲመጡ እንቃወማቸዋለን፤ ይህም ለእኛ አደጋ ነው። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ ባወጀ ጊዜ 128 የተባበሩት መንግስታት ሃገራት እንደተቃወሙት ሁሉ እኛም ባለማስተዋል ሰባቱን ነጎድጓዶች ልንቃወማቸው እንችላለን። የነዚህ ሃገሮች ተቃውሞ የእግዚአብሔርን እቅድ ባለማወቅ መታወራቸውን ያሳያል።

አካላችን ሲለወጥ ብቻ ነው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል የምንነጠቀው።

 

መጽሐፍ ቅዱስ “በሰባተኛው መልአክ ዘመን” አይልም። የሰባተኛው መልአክ ዘመን እርሱ ከዚህ ምድር በ1965 በተሰናበተ ጊዜ አብቅቷል።

“ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” መጽሐፎቹ፣ በቴፕ የተቀረጹ ድምጾቹ መልእክቱን በሚያስተጋቡበት ጊዜ፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ የመጨረሻዋን ዘመን ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ጋር ተመሳሳይ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ትፈጽማለች።

“ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” የሚለው ቃል እርሱ ከዚህ ምድር ከተሰናበተ በኋላ፤ ድምጹን በቴፕ ላይ ቀድቶልን ከሄደ በኋላ ያሉትን 50 ዓመታት የሚሸፍን የጊዜ ወሰን ነው።

አሁን ግን የሚያሳዝነው ነገር “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” በዚህ ዘመን “የእግዚአብሔር ድምጽ” ተደርጎ ተቆጥሯል። በአዲስ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሚመጣ የሚናገር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምጽ ብሎ መናገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ልክ እንደ ዲኖሚኔሽኖች ሜሴጅ ቡድኖችም መጽሐፍ ቅዱስን መከተል አቁመዋል።

 

63-0324E ሰባተኛው ማሕተም

… አስተውሉ። አሁን የመጨረሻውን ዘመን መልእክት፣ ይህንን ማሕተም ልብ በሉ። ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጦልናል፤ ስለ ሰባተኛው ማሕተም ግን ምንም አልተናገረም። የመጨረሻው ዘመን ማሕተም በሚጀምር ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ይሆናል። ይህን ከማወቅ በፊት … ደግሞም አስተውሉ፣ ራዕይ 10፡1፣7 (1-7፣ ምዕራፍ 10፡1-7) በሰባተኛው መልአክ መልእክት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ይታወቃሉ። አሁን በመጨረሻ ዘመን ማለትም ሰባተኛው ማሕተም በሚከፈትበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው።

 

ሚስጥራቱ የሚታወቁት በሰባተኛው መልአክ መልእክት መጨረሻ ላይ ብቻ ነው። የመልእክቱ ዓላማ እነዚህን ሚስጥራት ለመግለጥ ነው።

እርሱም ስብከቱን በታሕሳስ 1965 ጨረሰ። በዚያ ጊዜ እርሱ ሚስጥራትን ተረድቶ ነበር፤ ሙሽራይቱ ግን አልተረዳችም፤ በተለይም በዚያ ዘመን ያልተወለዱ ሰዎች አልተረዱም።

ስለዚህ እግዚአብሔር ከወንድም ብራንሐም መልእክቶች በመነሳት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እንዴት መረዳት እንደምንችል እና ከዚህም የተነሳ የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ካመነችው እምነት ጋር ተመሳሳይ እምነት ይኖረን ዘንድ ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቶናል።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥

መጽሐፉ መከፈቱ ሚስጥራቱ በሙሉ መገለጣቸውን ያመለክታል። ሚስጥራቱ ተገልጠው ያለቁት ወንድም ብራንሐም ተረድቷቸው ጨርሶ ዲሴምበር 1965 ከዚህ ምድር በተሰናበተ ጊዜ ነው። አሁን ደግሞ እኛም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አለብን። የዚያን ጊዜ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል።

62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

… እርሱም ከሰማይ ይወርዳል ምክንያቱም የዛኔ ሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመው ያልቃሉ።

እግዚአብሔር ሰው እንድንከተል እና ሰው የተናገረውን እንደ ገደል ማሚቶ እንድንደግም አይፈልግም። እያንዳንዳችን መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችን መረዳት መቻል አለብን። ስለዚህ እስካሁን ሚስጥራቱ ለሙሽራይቱ ገና አልተጠናቀቁም ምክንያቱም ገና ሁሉንም አልተረዳንም። እምነታችንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አልቻልንበትም።

ምድር እና ባሕር። ክርስቲያኖች ባለፉት የ2,000 ዓመታት የክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ባሕር እና ምድር ውስጥ ነው የተቀበሩት።

በአንድ ነገር ላይ መቆም የእኔ ነው ብሎ እንደማወጅ ነው።

ኢያሱ 1፡1 እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦

2 ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።

3 ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።

መልአኩ የሚወርደው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱት ቅዱሳን የእኔ ናቸው ብሎ ሊያውጅ ነው። እግሮቹም በባሕር እና በምድር ላይ ረግጠው ይቆማሉ።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

አንበሳ የአራዊት ሁሉ ንጉስ ነው። የይሁዳ ነገድ አንበሳ በመጀመሪያው ትንሳኤ ሙታንን በማስነሳት በሞት ላይ ድልን በተቀዳጀ ጊዜ በታላቅ ድምጽ ድሉን ለመግለጽ ያገሳል። ይህም ኢየሱስ በሰይጣን ላይ ያለውን ኃይሉን ለመጨረሻ ጊዜ የሚገልጥበት ወቅት ነው።

“በታላቅ ድምጽ ጮኸ” የሚለው ቃል አላዛርን ከሞት ከማስነሳቱ ጋር የተያያዘ አገላለጽ ነው።

ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

ዮሐንስ 11፡44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም፦ ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

“በጮኸም ጊዜ” የሚለው ቃል ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ጋር የተያያዘ አገላለጽ ነው።

ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

ማቴዎስ 27፡53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

ይህ የራዕይ 10፡3 ጥቅስ ከሙታን ትንሳኤ ጋር የተያያዙ ሁለት አገላለጾች አሉት።

ይህ ብርቱ መልአክ ሙታንን ለማስነሳት ወደ ምድር ይወርዳል።

ሙታን ሲነሱ ታላቅ የመለከት ድምጽ ይሰማል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

የዘመኑ ምልክት፡- በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር መለከት ለማለት በ “trumpet” ፈንታ “trump” ወይም “ትራምፕ” የሚለውን ቃል ነው የተጠቀመው።

ፕሬዚዳንት ትራም የእግዚአብሔርን እቅድ በማስፈጸም ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የተበታተኑት አይሁዶች እንደሚሰበሰቡ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ ለማወጅ አልፈራም። ስለዚህ የዘመን ፍጻሜ ክስተቶች ከአሁን በኋላ ስለሚፈጸሙ ኢየሱስ ወደ አይሁዶች ይመለሳል።

ኢሳይያስ 27፡13 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፥ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።

ኢዩኤል 3፡1 እነሆም፥ በዚህ ወራትና በዚህ ዘመን፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥

2 አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን ምድሬንም የተካፈሉአትን እፋረድባቸዋለሁ።

እስራኤልን በከፋፈሉ ሰዎች እግዚአብሔር አይደነቅባቸውም። እንግሊዝ የእስራኤልን መሬት 78% በመስጠት ትራንስ ጆርዳን የተባለ የአረቦች መንግስት መሰረተች። (ይህ በአረንጓዴ ቀለም የተመለከተው ቦታ ነው።) ከዚያም የጎላ ተራሮች ደግሞ ለሶሪያ ተሰጡ። (ካርታው ላይ ጥቁር)። ቀሪው 22% በፓለስቲኒያን አረቦች (ቢጫ) እና በአይሁዶች (ቀይ) መካከል ተከፈለ። ካርታው ላይ ወደ ታች አካባቢ የሚታየው ትልቁ ቀይ ክፍል ደረቁ እና ምድረበዳው የነገብ በረሃ ነው። ፓለስቲኒያን አረቦች ያንን ቦታ አልፈለጉትም።

 

 

ፍልስጥኤም የሚባል አገር ወይም መንግስት አልነበረም፤ ፓለስታይን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ እና ፓለስቲኒያን አረብስ የሚባሉ ሰዎች ብቻ ነበሩ እንጂ።

የፓለስታይን አረቦች አይሁዶችን በሙሉ አጥፍተው የእስራኤልን ምድር በሙሉ መያዝ ስለፈለጉ ይህንን ፕላን አንቀበልም አሉ።

በ1948 ጦርነት አወጁ፤ አይሁዶች ግን በመሳሪያም ሆነ በሕዝብ ብዛት ቢያንሱም እንኳ አሸነፉ። ከዚህም የተነሳ ከታች ያለው ካርታ ውስጥ በቀይ ቀለም ማየት እንደምንችለው የአይሁዶች ግዛት ተስፋፋ።

 

 

የትራንስ ጆርዳን መንግስት ተስገብግቦ ዌስት ባንክን እና ምስራቃዊ ኢየሩሳሌምን ተቆጣጠረ፤ ይህም ካርታው ላይ ከዮርዳኖስ ወንዝና ከሙት ባሕር በግራ በኩል በአረንጓዴ የተደረገው ምልክት ነው። ጋዛን ግብጽ ተቆጣጠረች (ካርታው ላይ በቢጫ የተደረገው ምልክት ነው)፤ ሶሪያዎች ደግሞ የጎላን ተራሮችን እንደያዘች ቀረች፤ ይህ ሁሉ ሲሆን የፓለስታይን አረቦች አንዳችም ቅሬታ አላቀረቡም። ይህንን ሁሉ ቦታ የያዙት በዚያ ጊዜ በተደረገ ጦርነት ስላሸነፉ ነው።

ነገር ግን በ1948ቱ የነጻነት ጦርነት ደግሞ አይሁዶች አሸንፈው ግዛታቸውን አሰፉ።

ዘካርያስ 8፡7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፤

8 አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።

ከ1967ቱ ጦርነት በኋላ አይሁዶች ኢየሩሳሌምን እና ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ በአረንጓዴ ቀለም የተቀባውን ዌስት ባንክ እንዲሁም ጋዛን ሁሉ ተቆጣጠሩ።

ዘካርያስ 12፡3 በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።

ብዙ ሃገሮች እስራኤልን ይቃወማሉ። ኢየሩሳሌም የብዙ ጭቅጭቅ መንስኤ ትሆናለች።

ከ750,000 የሚበልጡ ከአይሁድ ግዛት የተባረሩ ወይም በራሳቸው ፈቃድ የወጡ አረቦችን የአረብ መንግስታት ለመቀበል እምቢ አሉ። ይህም እምቢታቸው አረቦችን ስደተኛ አድርጎ በማስቀረቱ ዓለም ሁሉ በአይሁዶች ላይ የተቃውሞ አስተያየት እንዲሰነዝሩ አደረጉ። የአይሁድ ግዛት ውስጥ የቀሩት አረቦች የእስራኤል አረብ ዜጎች ተደርገው ተቆጠሩ። ዛሬ ድምጽ የመስጠት ሙሉ መብት ካላቸው የእስራኤል ዜጎች ውስጥ 20% የሚሆኑት አረቦች ናቸው።

አይሁዶች ግን የበቀል እርምጃ መውሰድ በፈለጉ የአረብ መንግስታት የተባረሩ 800,000 አይሁዶችን ተቀበሉ። በዚህም መንገድ አይሁዶች በራሳቸው ዜጎች ላይ የስደተኝነት ችግር ሳይፈጥሩ ቀሩ።

መለከት የሚያመለክተው የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምጽ ነው።

ኤርምያስ 4፡19 አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።

ፕሬዚዳንት ትራምፕን ልዩ የሚያደርገው ነገር ዓለምን ሁሉ ማስደንገጡ ነው። ትራምፕ ሽብርተኝነትን ለመቀነስ ብሉ ብዙ ሙስሊም ስደተኞችን አላስገባም ብሎ አገደ። ፕሬዚዳንት አሳድ በሶሪያ ሕዝብ ላይ የመርዝ ጋዝ በተጠቀመ ጊዜ ትራምፕ ብዙ ሚሳኤሎች ወደ ሶሪያ ተኮሰ። ሚሳኤሎቹ ኢላማቸውን በትክክል ይመቱ ስለነበረ ፕሬዚዳንት አሳድ ጦርነት ለመጀመር አልደፈረም። ነገር ግን በሶሪያ ሕዝብ ላይ የመርዝ ጋዝ መጠቀም አቆመ።

ከዚያም በኋላ ትራምፕ ከቻይና እና ከሌሎች ሃገሮች ጋር የንግድ ጦርነት ጀመረ። ይህም ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል

ስለዚህ ወደ መጨረሻው ዘመን በጣም እየቀረብን ይመስላል።

ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ስትሄድ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ቀን የተባለው እጅግ አስጨናቂው ታላቁ መከራ ዓለም አቀፍ ጦርነቶችን እና ብዙ አስፈሪ እልቂቶችን ይዞ ይጀምራል።

ታላቁ መከራ ሲቀርብ የሚሆኑ ነገሮችን ተመልከቱ።

ሶፎንያስ 1፡14 ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፤ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል።

15 ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥

16 በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።

በረዘሙ ግንቦች ላይ። በሁለት የመንገደኛ አውሮፕላኖች ተመተው የፈረሱትን ሁለቱን መንትያ ሕንጻዎች አስቡ።

17 በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፤ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።

አሁንም መለከቱ የሚነፋው የማስጠንቀቂያ ተምሳሌት እንዲሆን ነው።

ድቅድቅ ጨለማ የሰዎችን አስተሳሰብ ያጨልማል፤ ይህም የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስን መገለጥ ለመቀበል እምቢ ስላሉ ነው።

ልክ እንደ ዕውሮች ይሄዳሉ።

እግዚአብሔር እንዳለው የመጨረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዕውር ናት ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን መግለጥ ወይም መረዳት አይችሉም።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

ይህች የመጨረሻ ዘመን ቤተክርስቲያን በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ናት። ሆኖም ግን ሁሉም ቤተክርስቲያን በትክክለኛ መንገድ ላይ ነን ይላል።

ኢሳይያስ 28፡20 ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጐናጸፊያ ጠባብ ነው።

ራሳችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ለማጽደቅ የምናደርገው ጥረት ሁሉ ጎደሎ ነው። የራሳችን የቤተክርስቲያን ጽድቅ የጥፋታችንን መርገም ጨርቅ ሊሸፍንልን አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ትተን ቤተክርስቲያን የምትለውን አምነናል።

ሎዶቅያ። ሃብታም የሆነችዋ እና በንብረት ብዛት ያደገችዋ ምንም ነገር አልፈልግም የምትለዋ የቤተክርስቲያን ዘመን። በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ ስለሚያስቡ መታረም አያስፈልገንም ይላሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንኳ እርማት አይቀበሉም። ከቤተክርስቲያናቸው ውጭ ማንንም አይሰሙም።

በያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተራቸውን ብቻ ነው የሚያደምጡት።

ፓስተሩ አለቃ ስለሆነ ከእርሱ ጋር መስማማት ግዴታ ነው፤ የቤተክርስቲያኒቱ አባል ሆናችሁ ለመቀጠልም በራሳችሁ አእምሮ ማሰብም እንድታቆሙ ትገደዳላችሁ።

ፓስተሮች ግን እርስ በርሳቸው አይስማሙም። ለዚህ ነው 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኖሽኖች ያሉት። ሁሉም የተለያዩ ሆነው ነገር ግን ሁላቸውም እኔ ትክክል ነኝ ይላሉ።

ሰዎች የቤተክርስቲያን አባል በመሆናቸው የተነሳ ከችግር የሚያመልጡ ይመስላቸዋል። የሚያምኑት ቤተክርስቲያን የምታምነውን ነው።

ከዚያም የሚያምኑትን እምነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አያስፈልገንም ብለው ራሳቸውን ያታልላሉ፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ለእነርሱ አድካሚ ሥራ ይሆንባቸዋል።

64-0119 ሻሎም

ሁለት ብርሃናት አንድ ላይ ሊበሩ አይችሉም።

የቤተክርስቲያን ብርሃን እና የእግዚአብሔር ብርሃን በአንድነት ሊበሩ አይችሉም። የእግዚአብሔር ብርሃን ሲበራ የቤተክርስቲያንን ብርሃን ያጠፋዋል። ዛሬ እየሆነ ያለው ይህ ነው። እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ወግ ከራሱ ብርሃን እየለየ ነው፤ የእግዚአብሔር ብርሃን ለዚህ ዘመን በተስፋ ቃሉ ውስጥ ያበራው ብርሃን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ብርሃን ነው፤ ስለዚህ የምናምነውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አለብን።

65-1128M እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛው ሥፍራ

እዚያ ታክሰን ውስጥ ዛሬ በማለዳ የሚያዳምጥ አለ፤ እኔ ደግሞ እንዲህ አስብ ነበር … ሁልጊዜ እንዲህ ብለው የሚጨቀጭቁኝ ሰዎች ነበሩ፡- “የትኛውም ቤተክርስቲያን ቢሆን ብቻ ሁልጊዜ ቤተክርስቲያን ሂድ።” ሰዎችም ወደ ኋላ ተመልሰው በዚህ መንገድ ሲሄዱ አይቻለው። እኔም “ምን ሆኑ?” ስል ራሴን ጠይቃለው።

ወደ አንዳንዶቹ ሄድኩ፡- “መጀመሪያ በሄዳችሁበት ቀን ይቀርቧችሁና፣ የኛ ቤተክርስቲያን አባል ሁኑ ይሏችኋል። የአባልነት ግብዣቸውን ካልተቀበላችሁ አይቀበሏችሁም።” አያችሁ? አያችሁ? ግዴታ ያደርጉታል፤ በግድ አባል እንድትሆኑ ይፈልጋሉ፤ ይህም ባቢሎን ነው። በክርስቶስ ግን ተመርጣችሁ ነው የምትመጡት፤ ልባችሁ ወደ እርሱ ይስባችኋል።

እግዚአብሔርም በዚያ ጊዜ ስሙን በባቢሎን አላኖረም። አሁንም ስሙን በባቢሎን አያደርግም። እግዚአብሔር ስሙን በባቢሎን፣ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሊያደርግ አይችልም። እነርሱማ ስሙን በዚያ ያደርጋሉ፤ እርሱ ግን አያደርግም።

እናንተም “እሺ እንግዲህ ወንድም ብራንሐም” ትላላችሁ። ቆይ ቆይ፤ አንዴ ሰጥ ብላችሁ ተቀመጡና ጠብቁ። ጥቂት እንድቆይ ጠየቃችሁኝ። መልካም። እነርሱ ስሙን በዚያ አደረጉ፤ እርሱ ግን ስሙን በዚያ አላደረገም።

 

ብዙ ቤተክርስቲያኖች ሰዎችን በግላቸው ይድኑ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ያመጧቸዋል። ይህም መልካም ነው። ከዚያ በኋላ ግን እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን እርሷ የምታምነውን እንድታምኑ ታስገድዳችኋለች። ከእነርሱ ጋር ባትስማሙ የእናንተ አመለካከት ተቀባይነት አይኖረውም፤ ከዚያም ብዙም ሳትቆዩ እንደማይፈልጓችሁ ያሳውቋችኋል።

አንድ ነገር ሳትፈልጉ ጫና ተደርጎባችሁ ስታምኑ የአውሬው ምልክት ማለት ይህ ነው።

የአውሬው መንፈስ አሰራሩ ሰዎች በፓስተሩ እምነት እንዲስማሙ በማስገደድ ነው። የሚቃረኑ ግለሰቦች አይፈለጉም።

65-1128M እግዚአብሔር ያዘጋጀው ብቸኛ የአምልኮ ሥፍራ

ቀጥሎም እንዲህ አለ፡- “ካንተ ጋር የምገናኝበትና መስዋዕትህን የምቀበልበት ቦታ እኔ ስሜን አኖርበት ዘንድ የምመርጠው ቦታ ነው። በዚህ በር ትገባለህ፤ ስሜን አደርግበት ዘንድ በምመርጠው በር። በዚያ ነው የምትመጣው።”

መቸም “ይህች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት” የሚል ስያሜ ይሰጣሉ። በዚያ ስያሜ ውስጥ የጎደለ ነገር ቢኖር “ተቃዋሚ” የሚለውን ቃል ማጉደላቸው ነው። ክርስቶስ ያስተማረውን ሁሉ ይቃወማሉ። ዘመናዊ ፈሪሳውያን ሁሉ።

 

አንዲት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን በተቃረነች ጊዜ ወዲያው የክርስቶስ ተቃዋሚ ትሆናለች። ፓስተሩ ፈሪሳዊ ነው።

ፓስተሩ ፈሪሳዊ ነው ማለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንደ ወደደ እየተረጎመ እና እየሰነጣጠቀ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ለመግለጥ ይሞክራል ማት ነው፤ ማለትም ልክ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ያልተጻፈውን እንደሚናገሩት። በሶስተኛው እና በአራተኛው ነጎድጓዶች መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ ጠይቁት። ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፉ ሰባት ነገሮች ይገልጻሉ ማለት አንችልም።

ፖፑም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ያምናል፤ ለምሳሌ፡- ስላሴ፣ ፑርጋቶሪ፣ ክሪስማስ እና ኩዳዴ፣ ወዘተ.።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ማመን በእግዚአብሔር ፈቃድ እንድትመላለሱ አያደርጋችሁም።

እግዚአብሔር ግን ያልታወቀውን አድራጎቱን ሊያደርግ የተስፋ ቃል ሰጥቷል።

ኢሳይያስ 28፡21 እግዚአብሔርም ሥራውን ማለት እንግዳ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፥ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፥ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል።

ፐራሲም ማለት ጥሶ ማለፍ፣ ገንጥሎ መውጣት ነው፤ ቦታውም ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል የነሳበት ቦታ ነው። ፍልስጤም ስሟ የመጣው በ135 ዓ.ም በፍልስጤማውያን ከሰየማት በንጉስ ሃድሪያን አማካኝነት ነው፤ ይህንን ስም ያወጣው አይሁዶችን ከእስራኤል ካባረራቸው በኋላ ነው።

በዚያ ጥቅስ አማካኝነት ዘመናችንን ተመልከቱ።

ዛሬ አይሁዶች የጥንት ፍልስጤማውያንን እንደተዋጉ በዚህም ዘመን ካሉት ፍልስጤማውያን ጋር እየተዋጉ ናቸው።

ጥሶ መውጣት። በ1967 ዮርዳኖስ ውስጥ የነበረ ራዳር ግብጽን ለመምታት እየሄዱ የነበሩ 200 የአይሁድ አውሮፕላኖችን ተመለከተ። ከዚያ አንድ ቀን ቀድሞ ግብጻውያን ወታደራዊ ኮዳቸውን ቀይረው ነበር ግን ለዮርዳኖስ አላሳወቁም። ከዚህም የተነሳ ግብጽ ማስጠንቀቂያ ሊደርሳት አልቻለም። ስድስት የግብጽ የአየር ማረፊያዎች እና 300 የግብጽ አውሮፕላኖች ወደሙ። የግብጻውያን የአየር ኃይል መውደሙ የእስራኤል የምድር ጦር የጠላቶቻቸውን የምድር ጦር ጥሰው እንዲያልፉ ረድቷቸዋል።

የምድር ጦርነቱ አምስት ቀን ፈጅቷል፤ ነገር ግን ድሉ የተረጋገጠው በመጀመሪያው ቀን ነው። እውነተኛው ጥሶ መውጣት የአረቦች አየር ኃይል መውደሙ ነው።

ኢያሱ ኃይለኛ ጦረኛ ስለመሆኑ ዝናውን የሰሙ የገባኦን ሰዎች ኢያሱን አታለሉትና የሰላም ስምምነት እንዲፈርም አደረጉት። እነዚህ ሰዎች እዚያው ቅርብ እየኖሩ የመጣነው ከሩቅ ቦታ ነው አሉ።

በ1967 ከተደረገውና አይሁዶች ካሸነፉት የስድስት ቀን ጦርነትም በኋላ የፍልስጤማውያን መሪ አራፋት የማታለልን ዘዴ ተጠቀመ። የእስራኤል መከላከያ በጣም ኃይለኛ መሆኑን በመገንዘብ እና ከእስራኤል ጋር መዋጋት ከባድ መሆኑን በመረዳት አራፋት እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ አረቦች ራሳቸውን የቻሉ ፍልስጤማውያን ናቸው የሚል አፈ ታሪክ ፈጠረ። በዚህም ውሸት ላይ ተመስርቶ የፍልስጤም አረቦች እስራኤል ውስጥ የፍልስጤማውያን መኖሪያ ይሰጠን የሚል ጥያቄ አቀረቡ። ፍልስጤም ለ400 ዓመታት በኦቶማን ተርኮች በተመራችበት ጊዜ ሁሉ የደቡባዊ ሶሪያ አካል ተደርጋ ትቆጠር ነበር። እዚያ የኖሩትም አረቦች ፍልስጤማውያን አረቦች ተብለው ይጠሩ ነበር።

ዓለም ሁሉ በአራፋት ፈጠራ ተታለለና ትንሽዋ ሃገር እስራኤል ትንሽዬ ግዛቷን ለ23ኛ የአረብ መንግስት ትልቀቅ ብለው ጠየቁ።

አረቦች ከዚያ በፊትም የነበራቸው 22 ግዛቶች አንድ ላይ በስፋት ከአውሮፓ የሚበልጥ ነበር።

ወደ ኢያሱ እንመለስ።

ገባኦኖች ከኢያሱ ጋር የሰላም ስምምነት በማድረጋቸው ምክንያት አምስት የከነዓን ነገስታት ገባኦንን ሊወጉ ተነሱ።

ኢያሱ ግን በእግዚአብሔር ተዓምር በመታገዝ ድባቅ መታቸው። ከዚያም ኢያሱ ጠላቶቹን አሳዶ ገድሎ እስኪጨርስ ድረስ በገባኦን ፀሃይዋ ቀጥ ብላ እንድትቆምና እንዳትጠልቅ ትዕዛዝ ሰጠ።

ኢያሱ 10፡20 እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

ስለዚህ እግዚአብሔር ያልታወቀ አሰራሩን በመጠቀም እስራኤል ውስጥ እንግዳ ነገር ሊያደርግ የተስፋ ቃል ሰጥቷል። እግዚአብሔር ለኢያሱ ብሎ ተፈጥሮ ላይ ያልተለመደ ነገር አድርጓል። ኢሳይያስ ግን ኢያሱ ከሞተ ከ700 ዓመታት በኋላ ነው የጻፈው። ስለዚህ ኢሳይያስ ወደ ፊት ስለሚሆን ነገር ነው ትንቢት የተናገረው።

እንግዳ ነገር አይተን እናውቃለን።

ትራምፕ በፖለቲካ ምንም ልምድ ሳይኖረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነ። ከምርጫው በፊት ባለሙያዎች በሰጡት ግምት ሁሉም አያሸንፍም ብለው ነበር። ሆኖም ግን አሸነፈ። ከዚያ በኋላ ምንም ሳይፈራ የተባበሩት መንግስታት አባላት ሁሉ እየተቃወሙት ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ አወጀ። በተባበሩት መንግስታት ውስጥ በተሰጠው ድምጽ ትራምፕን የደገፉ 9 ሲሆኑ የተቃወሙት ደግሞ 128 ነበሩ።

እግዚአብሔር ግን ተበታትነው የነበሩ አይሁዶች እንደሚመለሱ እና የእስራኤል ምድር ለእነርሱ እንደምትሰጥ ቃል ገብቷል።

ስለዚህ እግዚአብሔር ባልተጠበቀበት ሰዓት ትራምፕ ምርጫውን እንዲያሸንፍ ፈቀደ። ይህም ልዩና አስደንጋጭ ነገር ነበር።

ኦባማ፣ ቡሽ፣ እና ክሊንተን ዘንድ ያልነበረ ቆራጥነት በትራምፕ ዘንድ ተገኝቷል። የዓለም ሃገራት ሁሉ እየተቃወሙት ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጓል።

ሰዎች ትራምፕ ላይ አቃቂር እያወጡበት ሳለ ትንቢት እየተፈጸ መሆኑን ማስተዋል አቃታቸው።

ሕዝቅኤል 11፡16 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፥ ወደ አገሮችም በትኛቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ፥ በመጡባቸው አገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።

17 ስለዚህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአሕዛብ ዘንድ አከማቻችኋለሁ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።

ትራምፕ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ሁሉ ቢነቅፉትና ቢተቹትም እንኳ እርሱ ግን ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች ባወጀ ጊዜ አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደሚመለሱ ጥንት የተነገረ ትንቢት እንዲፈጸም አስተዋጽኦ አድርጓል።

ማንም ሰው ትራምፕ እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ያስነሳው ሰው እንደሆነ አላሰበም። በእውነትም እግዚአብሔር እንግዳ የሆነ አሰራር አለው።

የእግዚአብሔር ቀን ተብሎ የሚጠራው ታላቁ መከራ የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱ በኋላ ወዲያው ይጀምራል።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

የጩኸቱ ድምጽ ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትነት ያስተማረበት መገለጥ ነው። ይህን ወንድም ብራንሐም ከ1947 እስከ 1965 ድረስ ያስተማረባቸውን ዓመታት ለማለት ብቻ አይደለም።

በ1965 እርሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በደምብ ተረዳ፤ የክርስቶስ ሙሽራ አልተረዳችም። ሁሉም ባይሆኑም እንኳ ብዙዎቹ የሙሽራይቱ አካላት ከ1965 በኋላ ነበር የተወለዱት። ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል የኢየሱስ ደቀመዝሙር የሆነው እንድሪያስ ብቻ ነው። ልክ እንደዚሁ ወንድም ብራንሐምን በደምብ ማወቅ በራሱ ምንም ጥቅም የለውም።

ሁለት የዮሐንስ ታማኝ ደቀመዛሙርት ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን ሊጠይቁ መጡ። ስለዚህ ዮሐንስ በተሳሳተ ጊዜ የተናገረውን ቃል አምነዋል። የዮሐንስ ታማኝ ደቀመዛሙርት በመሆን ያምናሉ፤ ከዚህም የተነሳ ዮሐንስ የተሳሳተ ነገር በተናገረ ጊዜ ያንን ንግግሩን እየጠቀሱ ቀሩ። እርሱ ነብይ ስለሆነ ቢሳሳትም እርሱን ማረም የማይፈቀድላቸው መሰላቸው። ስለዚህ እርሱ የተናገረውን ሁሉ ያለ ምንም ጥያቄ አመኑ።

ኢየሱስ ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመጥቀስ የነብዩን የተሳሳተ ጥቅስ አረመ። ከዚያም ኢየሱስ እየተናገረ ሳላ ቃሉን ትተው መንገዳቸውን ሄዱ፤ እነርሱም ከዚያ በኋላ ሁለተኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተጠቀሱ ተረሱ። ቃሉን ትተው መሄዳቸው ትክክል አልነበረም።

ኢየሱስ ዮሐንስን አልተቸውም። እነዚህ ሁለት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ግን ዮሐንስን ከሰሙ በኋላ የኢየሱስ ተከታዮች መሆን እንደሚገባቸው አላወቁም። ስለዚህ እነሱ የሰሩትን ዓይነት ስሕተት እንዳንሰራ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን የሰው ንግግር ጥቅስ ወይም የጥቅስ ትርጓሜ ላይ ሙጭጭ ብሎ መቅረት ከኢየሱስ ይልቅ ነብዩን መምረጥ ነው። ይህም የሚያዋጣ አካሄድ አይደለም።

ከ1947 እስከ 1965 እነዚያ 18 ዓመታት ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ የኖረበትና ስብከቱን በቴፕ የቀዳበት “የሰባተኛው መልአክ ዘመን” ነበሩ።

አሜሪካኖች በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጠላቶቻቸው ላይ ድምጽ በመቅረጽ ስለላ ለማድረግ የፈጠሩት ሚስጥራዊ የድምጽ መቅጃ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ በገበያ የተለቀቀው በ1947 ነበረ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በ1947 ድምጹን በቴፕ የቀረጸ ሰባኪ ወንድም ብራንሐም ነበር።

ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ …

ይህ ቃል ትኩረት የሚያደርገው ወንድም ብራንሐም በ1965 ከዚህ ምድር ከተሰናበተ በኋላ ያለፉት 50 ዓመታት ላይ ነው። ከዚያ ወዲህ የወንድም ብራንሐም ድምጹ ብቻ ነው ያለን፤ ይኸውም በቴፕ የተቀዳ ትክክለኛ ቅጂ ነው።

የኛ ሃላፊነት ሃሳቡን ከቴፑ አዳምጠን በማግኘት ከዚያ በኋላ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ተከታትለን ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ነው። በዚህ መንገድ የነብያትን ሃሳቦች እንሰማለን ነገር ግን ሃሳባቸውን የምንከተው ቃሉ ውስጥ ስለተጻፉ ነው። ከዚህም የተነሳ ቃሉ የሆነው የኢየሱስ ተከታይ እንሆናለን።

ቀጥሎ የሚመጣው የመላእክት አለቃ ድምጽ ነው፤ እርሱም ሲናገር ሙታንን ያስነሳቸዋል። ይህም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ነው።

64-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ከዚያ በኋላ በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት በሰባቱ ነጎድጓዶች አማካኝነት ይለወጣሉ፤ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሙሽራይቱ የምትነጠቅበትን እምነት ብቻ ሳይሆን በአየር ላይ ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን የተለወጠ አካል የምታገኝበትን እምነትም ይሰጧታል።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

አሁኑኑ የመነጠቅ እምነት ቢኖራችሁም እንኳ በዚህ ስጋዊ አካል ውስጥ ሆናችሁ ወደ ሰማይ መሄድ አትችሉም። የምትነጠቁበትን እምነት ከመለማመዳችሁ በፊት አዲስ አካል ያስፈልጋችኋል።

ከ50 ዓመታት በላይ ብዙዎች ለመነጠቅ ስለሚያስፈልገን እምነት ሰብከዋል፤ እንዲህም ሆኖ ግን እስካሁን ማንም አልተነጠቀም። ስለዚህ ያ ትምሕርት የሆነ ችግር አለበት።

ከዚያ በኋላ ወደ እግዚአብሔር መለከት እንመጣለን። ይህም ወደ ላይ እንድንሄድ የሚጠራን የእግዚአብሔር መለከት ነው። እግዚአብሔር በመለከቱ ወደ ላይ እስኪጠራን ድረስ ምንም ዓይነት መነጠቅ አይኖርም።

ይህም የሚሆነው ከትንሳኤው በኋላ ብቻ ነው።

ስለዚህ ከትንሳኤው በኋላ ብቻ ነው የምትነጠቁበት እምነት የሚኖራችሁ።

“የእግዚአብሔር መለከት”። በእንግሊዝኛ trump ይባላል።

እግዚአብሔር ፕሬዚዳንት ትራምፕን የዘመኑ ምልክት አድርጎ አስነስቶታል። ትራምፕ ኢየሩሳሌምን የእስራሴል ዋና ከተማ አድርጓል፤ ደግሞም የጦርነትን ማስጠንቀቂያ አሰምቷል።

በእርግጥ የራሱ የሆኑ እንከኖች አሉበት። ፍጹም ሰው አይደለም። ግን እኛ ስለምንረሳ እንጂ ራኬብ ጋለሞታ ነበረች። ሙሴ ነፍሰ ገዳይ ነበረ። ዳዊት ነፍሰ ገዳይ እና አመንዛሪ ነበረ። እግዚአብሔር እኛ ትኩረት የማንሰጣቸውን ያልጠበቅናቸውን ሰዎች በመጠቀም ሰይጣንን ግራ ያጋባዋል።

ኢዩኤል 2፡1 የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤

2 የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘላለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ እስከ ብዙ ትውልድ ድረስ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።

የእግዚአብሔር ቀን ታላቁ መከራ ነው። ያ ጊዜ እየቀረበ ነው።

እግዚአብሔር እንግዳ የሆነ ባህርያ ያለውን ሰው ትራምፕን በመጠቀም ታላቁ መከራ የተባለው የእግዚአብሔር ቀን እየቀረበ መሆኑን እያመለከተን ነው።

 

ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለተናገሩት ነገር የምናውቀው ምንድነው? ምንም።

63-0324E ሰባተኛው ማሕተም

የዚያ [ሰባተኛው] ማሕትም አንዱ ሚስጥር፤ ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ምንም እንከን አይወጣላቸውም፤ ምክንያቱም ማንም ስለ ነጎድጓዶቹ ቃል አያውቅም፤ ምክንያቱም ምንም አልተጻፈም። ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ላይ ደርሰናል።

ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

ስላልተጻፈ ነገር ልናውቅ አንችልም።

64-0614 የእግዚአብሔር መገለጥ

እርሱም እንዲህ አለ፣ “ያው እንግዲህ፣ እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አያችሁ” አለ፤ ቀጥሎም “እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ማሰማታቸው ለሆነ አንድ ሰው መገለጥ አይሆንለትምን?”

እኔም እንዲህ አልኩ፡- “በፍጹም፤ ይህ ከተጻፈው ላይ መቀነስ ወይም በተጻፈው ላይ መጨመር ነው።”

ሁሉም ነገር እዚያው ውስጥ ተገልጧል፤ ሰባቱ ማሕተሞችም የዚያም መገለጥ አሳይተዋል። በቃ እንዲያው እንደተባለው ነው። አያችሁ፤ ሁሉም ነገር ያለው ቃሉ ውስጥ ነው። ደግሞ ከቃሉ መውጣት አትችሉም። የእግዚአብሔርም መንፈስ ቃሉን ትቶ አይሄድም። የእግዚአብሔር መንፈስ ሁልጊዜ ከቃሉ ጋር ነው፤ የአንዳንዶችን ዓይን ያሳውራል፤ የአንዳንዶችን ደግሞ ያበራል። ሁልጊዜ ይህን ያደርጋል።

እንግዲህ ሰባቱ ማሕተሞች ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ምንድነው የነገሩን?

64-0830E ጥያቄዎችና መልሶች 4

ከሰባቱ ሚስጥራት ጋር በቁጥር የሚመሳሰሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ተገልጠዋልን? በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠው ነገር ግን ለእኛ እስከ አሁን ድረስ እንደ ነጎድጓድ አልተገለጡልንምን?

የለም፤ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠዋል፤ የነጎድጓዶቹ ትርጉም በማሕተሞቹ ውስጥ ነው።

 

ሰባቱ ማሕተሞች የገለጡት ነገር ቢኖር ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለ ምን እንደሆኑ ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር ሥራቸው ምን እንደሆነ ማለት ነው።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ሰባቱ የራዕይ ነጎድጓዶች … ለታላቁ የአካል ለውጥ የሚሆነውን እምነት ጌታ ለሙሽራይቱ ይግለጥላት።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ነገር ግን እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተናገሩ ጊዜ “እንዳትጽፍ” ተብሎ ተነገረው። ሚስጥሮች ናቸው። ምን እንደሆኑ እስከ አሁን ድረስ አናውቅም፤ ነገር ግን ኋላ በጊዜያቸው ይገለጣሉ ብዬ አምናለው። ሲገለጡም ቤተክርስቲያን ከዚህ ዓለም የምትወጣበት ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት እና ጸጋ ይሰጧታል።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ከትንሳኤ በኋላ ሙሽራይቱ እንዴት ወደ ከበረ አከሏ እንደምትለወጥ ያሳዩዋት ዘንድ ድምጻቸውን ያሰማሉ።

የዚያን ጊዜ ብቻ ነው እርሷ ወደ ሰማይ ልትነጠቅ የምትችለው።

 

ሰባቱ ነጎድጓዶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኙ ተምሳሌቶች መካከል ተሰውረዋል።

65-0718E መንፈሳዊ ምግብ በጊዜው

ሁልጊዜ ሳስበው በመጽሐፉ ጀርባ ላለይ የተጻፈ ነገር እና ውስጡ ያልተጻፈ ነገር ይመስለኝ ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ሊያደርገው የማይችለው ነገር መሆኑ ተገለጠ። መጽሐፉ ውስጥ የተጻፈ ነገር አይደለም … መጽሐፉ ውስጥ ሆኖ የተሰወረ ነገር ነው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች በመጡ ጊዜ ልናውቃቸው እንችል ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ማወቅ አለብን (ይህም የመጀመሪያው ወይም የትምሕርት ዝናብ ነው)።

ሰባቱ ነጎጓዶች ሰነፎቹን እና ልባሞቹን ቆነጃጅት (የዳኑ ክርስቲያኖችን በሙሉ) ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው ድምጽ በሚመጣበት በዚያው ሰዓት ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት።

አስተውሉ። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ለአይሁዶችም ጭምር ያሰማሉ።

63-0321 አራተኛው ማሕተም

ትናንትና ማታ ትልቅ ሰይፉን ይዞ ለመግደል ሲመጣ አግኝተነው ነበር። ነገር ግን እርሱ እራሱ በሰይፍ እንደሚገደል አይተናል፤ ይህም የቃሉ ሰይፍ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፤ በሁለት ወገን የተሳለው ሰይፍ ይገድለዋል፤ ያጋድመዋል። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋር የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። እርሱም ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ይገደላል፤ ይህም ቃል በሁለት ወገን ከተሳለ ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው። እነርሱ ከፈለጉ መቶ ቢሊዮን ዝንቦችን መጥራት ይችላሉ። አሜን። እነርሱ የሚናገሩት ነገር ሁሉ ይፈጸማል፤ ምክንያቱም ቃላቸው ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ የእግዚአብሔር ቃል ነው። አሜን። እግዚአብሔር ሁልጊዜ … ቃሉ ነው፣ ነገር ግን ሥራውን ለመፈጸም ሰውን ይጠቀማል። እነዚያን ዝምቦች ግብጽ ላይ እንዲመጡ እግዚአብሔር እራሱ ሊጠራቸው ይችል ነበር፤ ነገር ግን እንዲህ አለ፡- “ሙሴ፤ ይህ ያንተ ሥራ ነው። ምን ማድረግ እንዳለብህ እነግርሃለው፤ አንተም ሄደህ ታደርገዋለህ።”

 

ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት፤ ሙሴ እና ኤልያስ ቃል በመናገር ብቻ የተፈጥሮ ኡደትን የማቋረጥ አስፈሪ ኃይል ይቀበላሉ።

ራዕይ 11፡6 እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።

1ኛ ነገሥት 17፡1 በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፦ በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም አለው።

አስደናቂ ወደሆነው ልዕለ ተፈጥሮአዊ አገልግሎታቸው ለመግባት የሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጽ ያስፈልጋቸዋል።

እነርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ፈጽመው ስለሚግባቡ እርሱ እንዲናገሩ ያዘዛቸውን ብቻ ይናገራሉ።

ሙሽራይቱም መማር ያለባት ሚስጥር ይህ ነው።

እኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ቃል ጋር ፈጽመን መስማማት አለብን፤ እርሱም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ነው፤ ከቃሉ ጋር ስንስማማ ብቻ ነው ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ልናውቃቸው የምንችለው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23