የቤተክርስቲያን ዘመናት - ፊልድልፊያ (የወንድማማች መዋደድ) - ስድስተኛው ዘመን - ከ1750 ዓ.ም. እስከ 1906 ዓ.ም.
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ፊልድልፊያ ማለት የወንድማማች መዋደድ ነው። ይህም በዓለም ዙርያ ሁሉ ላልዳኑ ሰዎች ወንጌልን ለማሰራጨት ሲሉ መከራን ለመቀበልና ነፍሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ የነበሩትን የወንጌላውያን እና ሚሽነሪዎች ፍቅር ያመለክታል። የሚያሳዝነው ነገር ግን በፖለቲካው በኩል ደግሞ በቅኝ ግዛት ዘመን ስግብግብነት እና ግፍ ነግሰው ነበር። እግዚአብሔርም ሰይጣንም ይንቀሳቀሱ ነበር። የሕይወት ዛፍ (የክርስቶስ መንፈስ) እና መልካምና ክፉውን የምታሳውቀዋ ዛፍ (የሰይጣን ሃሳብ) በዓለም ዙርያ ሁሉ የሰዎችን ሃሳብ ለመግዛት ይፎካከሩ ነበር።
በአየር ሁኔታ ለውጥ ላይ የሚመክረው የመንግስታት ኮሚቴ እና የተለያዩ አካላት 1750 ዓመተ ምሕረትን እንግሊዝ ውስጥ የኢንዱስትሪ አብዮት የተጀመረበት ዓመት አድርገው ይቆጥሩታል።
የኢንዱስትሪ አብዮት ከ1750 ዓ.ም. እስከ 1850 ዓ.ም. ድረስ በግብርና፣ በፋሪካ፣ በማዕድን ቁፋሮ፣ በመጓጓዣ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ የመጡ ለውጦች በዘመኑ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የፈጠሩበት ጊዜ ነበር። እንግሊዝ ውስጥ ከጀመረ በኋላ ወደ ምዕራብ አውሮፓ በመዛመት ወደ ሰሜን አሜሪካ፣ ጃፓን በስተመጨረሻም ወደ ቀረው ዓለም ሁሉ ተሰራጨ። የኢንዲስትሪ አብዮቱ በታሪክ ውስጥ ታላቅ ክስተት ነው፤ የኢንዱስትሪ አብዮቱ በሰዎች የእለት ተለት ሕይወት ውስጥ ያልዳሰሰው ገጽታ የለም። (www.freeman-pedia.com/industrial-revolution)
በ1750 ፖርቹጋል ኢንክዊዚሽንን (በሐይማኖት ያፈነገጡ ሰዎችን በማሰቃየት እንዲመለሱ የማድረግ ዘዴ) ሙሉ በሙሉ አቋረጠች። ከዚህም የተነሳ ፖርቱጋል ውስጥ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በፕሮቴስታንቶችና በአይሁዶች ላይ የምታደርገው ስደት ቀነሰ።ስለዚህ ወንጌል እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ።
በ1750 የዳሆሚ ንጉስ (በምዕራብ አፍሪካ የናይጄሪያ ጎረቤት የሆነች ሃገር፤ ዛሬ ቤኒን ተብላ ትጠራለች) ባርያዎችን ከባሕር ማዶ ለመጡ ሰዎች በመሸጥ 250 000 ፓውንድ አትርፏል። ይህ አጸያፊ ሥራ ነበር። ዊሊያም ዊልበርፎርስ እንግሊዝ ውስጥ በ1785 ዳግመኛ ከተወለደ በኋላ ሳይታክት በመስራት የባሪያ ንግድን ለማስቆም የመጀመሪያው አዋጅ በ1807 እንዲጸድቅ አደረገ። ከዚያም የባሪያ ንግድ በ1833 በእንግሊዝ ግዛቶች ውስጥ እንዲቆም ተደረገ።
በዚህ ጊዜ ከ1756 እስከ 1763 የቆየው የሰባት ዓመታት ጦርነት በዘመኑ የነበሩትን የዓለም ታላላቅ ሃገሮች ያሳተፈ ስለነበረ አውሮፓን፣ ሰሜን አሜሪካን፣ ማዕከላዊ አሜሪካን፣ የምዕራብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻዎችን፣ ሕንድ እና ፓለስታይንን ሁሉ ተጽእኖ አድርጎባቸዋል። እንግሊዝ ፈረንሳይን ስላሸነፈች ሕንድን መቆጣጠር ችላለች።
ከዚያ በኋላ እንግሊዝ ያገኘቻቸው ድሎች ያልጠበቀችውን ፈተናዎች አመጡባት። እንግሊዝ ካናዳ ውስጥ ፈረንሳይን በማሸነፏ ካናዳን ተቆጣጠረች። 13ቱ የአሜሪካ ግዛቶችም ከፈረንሳይ በኩል ይመጣባቸው የነበረ ስጋት ተቋረጠ። ከዚያ ወዲያ የእንግሊዝ ጥበቃ ስላላስፈለጋቸው በ1776 እንግሊዝ ላይ አመጹ፤ ነጻነታቸውንም አወጁ።
ሰሜን አሜሪካኖቹ ደግሞ እየተስፋፉ የአሜሪካ ኢንዲያኖችን በግፍ አንበርክከው ገዙ (ይህም በአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ጥላሸት ትቶ አልፏል)። ይህም ሆኖ ግን በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከሮማ ጳጳሳትና ከነገሥታት ጭቆና ነጻ እንደመሆናቸው የወንጌል አርበኞች ሆነው ሊገለጡ ሲዘጋጁ ነበር። እውነትና መልካም ብለው ላመኑበት ዓላማ ሁሉ ለመዋጋት የሚያስፈልገውን ቆራጥነትም በውስጣቸው አዳብረዋል።
ከ1860 እስከ 1865 የነበረው የእርስ በርስ ጦርነም መዋጋት አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ እና የሚዋጉበትም ዓለማ ተገቢ ነው ብለው ካመኑ ለመዋጋት ወደ ኋላ እንደማይሉ አሳይቷል። በዚያ ጦርነት ውስጥ ወደ 700 000 ያህል ወታደሮች ሞተዋል። ከአውሮፓ ሃገራት መካከል በዚያ ዘመን 700 000 ወታደሮች ለጦርነት ማሰለፍ የሚችል አንድም ሃገር አልነበረም። አንዳንድ የታሪክ ምሑራን የምዕራብ አውሮፓ ሃገራት በአንድነት ተሰብስበው እንኳ 700 000 ወታደሮችን ማሰለፍ ይችሉ እንደሆን ይጠራጠራሉ። ታላቁ የዎተርሉ ጦርነት በአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከሃያ ጊዜ በላይ “ተደጋግሟል”። ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ አሜሪካውያን ታላላቅ ጦርነቶችን መዋጋት ተለማመዱ። ሰሜን እና ደቡብ ለአራት ዓመታት በጀግንነት፣ በጽናት እና በጥበብ ተዋጉ።
አሜሪካውያን እነዚህን መልካም ባሕርያት በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተደራጁ ቤተክርስቲያኖችን በመቃወም ጴንጦቆስጤያዊ መነቃቃት ሲጀምሩ ይጠቀሙባቸዋል። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከአሜሪካ ብቻ የተነሱ የወንጌል ሰባኪዎች በቁጥራቸው ከዓለም ዙሪያ ሁሉ ከተነሱት ይበልጣሉ። የአሜሪካ ገንዘብ በዓለም ዙርያ ሁሉ የወንጌል አገልግሎትን ይደግፋል። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን አሜሪካ በዓለም ዙርያ ለሚደረገው ታላቅ የወንጌል ስርጭት እጅግ ብዙ ድጋፍ ትሰጣለች። አሜሪካኖች በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ለውጊያ ያሳዩትን ቆራጥነት በጴንጤቆስጤ መነቃቃት ዘመን ውስጥም አሳይተዋል። ከዚያም በኋላ ዘመናዊ ትምሕርት ያልተማረው ዊልያም ብራንሃም በከፍተኛ ደረጃ የተማሩት የቤተክርስቲያን ሰባኪዎች የሚያነሱበትን ተቃውሞ አልፎ የተጻፈውን ቃል ምስጢር በድንቅ ለመግለጥ ተመሳሳይ ቆራጥነትን አሳይቷል።ሰባኪዎቹ የስነ መለኮት ዶክትሬት ይዘዋል፤ እርሱ ግን አስደናቂ መለኮታዊ ኃይል የሚገለጥበት አገልግሎት ውስጥ ነበረ። ዊልያም ብራንሃም በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የነበረው የመረዳት ጥልቀት ወደር አልነበረውም።
በ1848 ካሊፎርኒያ ውስጥ ወርቅ ተገኘ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰፋሪዎችም ሐብት ፍለጋ ወደ ካሊፎርኒያ ተንጋግተው ሄዱ። ከዚያ ግን በ20 ዓመታት ውስጥ ከካሊፎርኒያ የመጀመሪያ ነዋሪዎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሞተው አለቁ። ሕዝቡ ወርቅ ፍለጋ ተንጋግተው በመጡበት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ 100 000 የሚሆኑ የጥንት አሜሪካ ነዋሪዎች ሞቱ። ብዙዎች በአዳዲስ በሽታዎች ምክንያት አለቁ። በ1850 ካሊፎርኒያ የአሜሪካ ግዛት ወይም እስቴት ሆነች። በግዛቱም የታወጀ ፖሊሲ ለገዳዮች ሽልማት በመስጠት የዘር ጭፍጨፋን በማበረታታቱ 16000 የጥንት አሜሪካ ነዋሪዎች በግፍ ተገደሉ። ከአስር ሺ በላይ የሚሆኑት ባሪያ ተደረጉ፤ ከእነዚህም ብዙዎቹ በሥራ ብዛት ሞተው አለቁ። ይህም የአሜሪካ ታሪክ አስቀያሚ ገጽታ ነው።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሎስአንጀለስ የተባለውን የካሊፎርኒያ ከተማ በመምረጥ 312 አዙዛ እስትሪት በተባለው መንደር ውስጥ መንፈስ ቅዱስን በኃይል አፈሰሰ። ይህም እግዚአብሔር በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ለሚያስነሳው ታላቅ መለኮታዊ እንቅስቃሴ የመጀመሪያው ነበረ።
ከዚህም የተነሳ በአንድ ቦታ ላይ ግራ የሚያጋባ የመልካም እና የክፉ ድብልቅልቅ ይታይ ነበር።
ከዚህ በመቀጠል በ1750 እና 1906 መካከል ለተፈጠሩት ክስተቶች መንስኤ የሆኑትንና ፊልድልፊያ ወይም የወንድማማች መዋደድ የተባለውን ስድስተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን የሚወክሉ ነገሮች እንመልከት።
ራዕ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አጋንንታዊ አሰራርን በሃሪቱ ላይ እየነሰነሰ ነበር። በባሪያዎች ላይ የተፈጸመው አሳፋሪ ግፍ እንዲሁም ደም በማፍሰስና በዝርፊያ የተሰበሰበ ሃብት ብዛት ካፒታሊዝም ገዥ ኃይል እንዲሆን ረድቷል። በነዚያ ዘመናት በካፒታሊዝም የተቃኘ የቅኝ አገዛዝ ጥቁር ጥላ የዓለምን ሁሉ ፊት ጋርዶ ነበር። የእንግሊዝና የአውሮፓ ኢኮኖሚ የተገነባው ከባሪያ ንግድ በተገኘ ብዙ ገንዘብ ነበር።
እስፔይንና ፖርቹጋል ከደቡብ አሜሪካ እና ከሜክሲኮ እጅግ ብዙ ወርቅ ዘረፉ። የአውሮፓ ሃገራት ሌሎች ሃገሮችን በቅኝ ግዛት ሲይዙ አጀማመራቸው በእንደዚህ አይነት አጸያፊ ሥራ ነበረ። ፈንጣጣ እና ሌሎች የአውሮፓ በሽታዎች በእስፔይናውያን አማካኝነት ወደ አሜሪካ አሕጉር በመዛመት በዚያ ምድር ላይ ከነበሩ ነዋሪዎች ለ90 በመቶዎቹ ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል።
ከዚያም ደግሞ እንግሊዝ ከግዛቶችዋ ሁሉ እጅግ ባለጠጋ የሆነችዋን ሕንድ ለ190 ዓመታትሙልጭ አድርጋ ዘረፈች። ከዚሁ ዝርፊያ በተገኘ ሃብትና ገንዘብ ነው እንግሊዝ በ1750 በተጀመረው የኢንዱስትሪ አብዮት ውስጥ ፈር ቀዳጅ ለመሆን የበቃችው። ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የተደረገው ሽግግር በብዙ ግፍ፣ በብዙ ብክነትና በብዙ ሰዎች ገንዘብ አማካኝነት ነው የተከናወነው። እንግሊዝ በግብር ሰበብ ባደረገችው ታላቅ ዝርፊያ አማካኝነት የሕንድ ሃብት ተበዝብዞ በ1760ዎቹ እና በበ1770ዎቹ ውስጥ ለእንግሊዝ በእንፋሎት ኃይል የሚሰራ ሞተር እና የኢንዱስትሪ ኃይል ለማሳደግ አገልግሏል። በእንፋሎት ኃይል የሚንቀሳቀሰው ሞተር ለማዕድን ቁፋሮ፣ ለትልልቅ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ምርት፣ በጀልባ እና በባቡር ፈጣን የመጓጓዣ አገልግሎቶች ለመስጠት ኃይል አበርክቷል። በታላላቅ ኢንዱስትሪዎች የተከፈቱ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንግሊዛውያንን በፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው በየዕለቱ ተደጋጋሚ ለሆነ የረጅም ሰዓት ከባድ ሥራ እንዲሰሩ አስገድደዋቸዋል፤ ሲሰሩ የሚውሉባቸው ፋብሪካዎችም ሆኖ የሚያድሩባቸው ቦታዎች ንጹሕና ምቹ አልነበሩም። ሰራተኞቹ በሙሉ ድሆች ሲሆኑ በየቀኑ ለ12 ሰዓታታ በእግሮቻቸው ቆመው የእንፋሎት ኃይልን ለማመንጨት ከሚቃጠለው የድንጋይ ከሰል በሚወጣው ጭስ የተበከለውን አየር እየሳቡ ነበር ሲሰሩ የሚውሉት። የእንግሊዝ የባሕር ኃይልም በባሕር ዳርቻ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ያገኛቸውን ሰዎች ሁሉ በግዳጅ እየሰበሰበ መርከበኛ ያደርጋቸው ነበር። በዚህም መንገድ እንግሊዞቹ ከዓለም ሁሉ በኃይል አንደኛ የሆነ የባሕር ኃይል መሰረቱ።
ከቤተክርስቲያን የፈለቁ ቆራጥ የወንጌል ሰባኪዎችና ሚሽነሪዎች ወደ ዓረማውያን ዘንድ ሁሉ ሄደው ወንጌልን አሰራጩ። ነገር ግን ብዙ ቤተክርስቲያኖች የተበረዙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን እውነተኛ የሕይወት እንጀራ አስመስለው በመሸጥ ገንዘብ የማካበት ሩጫ ውስጥ ገቡ። በሰዎች ወግና ባሕል ላይ በመመስረት ብዙ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ተከፈቱ። እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው አምላክ የሆኑ ሦስት አካላት ያሉት ነገር ግን አንድ አምላክ እንደሆነ ተደርጎ ትምሕርት ተሰጠ። ይህም ግራ አጋቢ ትምሕርት የክርስቲያኖችን አእምሮ አደነዘዘና ለራሳቸው ማሰብ እንዳይችሉ አደረጋቸው። ሦስት ሰዎች በአንድ ስም ሊጠሩ እንደማይችሉ ሁሉ እግዚአብሔርም ሦስት ተደርጎ ሲታሰብ ስሙ ተረሳ። ብዙ አማኞችም ይህንን ትምሕርት እንዲቀበሉ በመደረጋቸው የተነሳ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በውሃ መጠመቅን እምቢ አሉ፤ ከዚያም ጴጥሮስ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ ብሎ የተናገረ ጊዜ ተሳስቷል አሉ።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም አላቸው፦ ንስሐግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ብለው ማሰብ ጀመሩ። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የለበትም ብለው የሚያምኑ ክርስቲያኖች በጣም ጥቂት ናቸው።
ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በመጣ ጊዜ በኢየሱስ ስም መጠመቅ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል።
የሐዋርያት ሥራ 19፡5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚለው ሥም ባልታወቀ መንገድ የእግዚአብሔር ስም ሆኖ ቀረ። ማሰብ የሚችል አእምሮ ያላቸው ሰዎች ሳይቀሩ ሦስት ማዕረጎች ስም ናቸው ብለው ተቀበሉ። ይህ ቃላት ትርጉማቸውን የሚያጡበት መንፈሳዊ እውርነት ነው።
ከዚያ ወዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ አንዴ እንኳ ያልተጠቀሰውን ክሪስማስን እና በጌጣ ጌጥ ያሸበረቀውን የአረማውያን የገና ዛፍ መቀበሉ በጣም ቀላል ሆነ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ የጌታን ልደት እንድናከብር ትዕዛዝ አልተጻፈልንም።
ኤርምያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦የአሕዛብን መንገድ አትማሩ
3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥
ዛፉ የክርስማስ በዓል ዋነኛ መገለጫው ነው።
የክርስቶስን ስም ከአሕዛብ ልማድ የመጣ ዛፍ ላይ መለጠፍ እውነት አያደርገውም።
ካሕን ወይም ፓስተር የእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስ ተደርጎ ሲሾም የኒቆላውያን ትምሕርት እየተስፋፋ ሔደ። ጨለማ የብርሃንን ቦታ ያዘ፣ ክርስትና ግን ገንዘብ ማትረፊያ ንግድ ሆነ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቫቲካን ውስጥ ልትሰራ ላሰበችው ትልቅ የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ገንዘብ ለማሰባሰብ ብላ የስርየት ወረቀት ለመሸጥ ወስና ነበር። የስርየት ወረቀት መግዛት ማለት ከሐጥያትችሁ ንሰሃ ሳትገቡ ወረቀቱን በገንዘብ በመግዛት ብቻ ስርየት ወይም ይቅርታ የምታገኙበት መንገድ ነው። ከፈለጋችሁ ደግሞ ከቤተሰቦቻችሁ መካከል ለሞቱ ሰዎችም ጭምር የስርየት ወረቀት መግዛት ትችላላችሁ። የካቶሊክ ፖፕ የፈጠረው ሌላ ትምሕርት ደግሞ ከሞታችሁ በኋላ ለሐጥያታችሁ ዋጋ ለመክፈል የምትሰቃዩበት ፑርጋቶሪ የሚባል ቦታ አለ የሚል ነው። ገንዘብ በስማችሁ ለቤተክርስቲያን ከተከፈለ ከፑርጋቶሪ ትወጡና ወደ መንግስተ ሰማያት ትገባላችሁ። በዚህ መንገድ ፖፑ ከሞቱ ሰዎች እንኳ ሳይቀር ገንዘብ ያገኝ ነበር። ይህም ጥሩ ንግድ ነገር ግን የረከሰ ሐይማኖት ሆነ።
እግዚአብሔርም እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ በተባለ ሰው በተጀመረው የቅድስና እንቅስቃሴ አማካይነት የመንፈስ ቅዱስ ዘይት እና የመገለጥ መነቃቃ እንዳይዳፈን አደረገ። ይህም በስተመጨረሻ አድጎ በ1792 ወደ ሕንድ ሄዶ ወንጌልን እስከሰበከው እስከ ዊልያም ኬሪ የወንጌል ዘመቻ ደረሰ። የወንጌል መልዕክተኞች እንቅስቃሴ ውበቱ ሚሽነሪዎች አውሮፓ ውስጥ ካሉት ቤተክርስቲያኖችና ከአስተምሕሮ ስሕተቶቻቸው ብዙ ርቀው መሄዳቸው ነው። ለአረማውያን ወንጌልን በሚሰብኩበት ጊዜ ትኩረታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በግል መዳን ላይ ብቻ ነበር። ይህም ትኩረት የሚሽነሪዎችን ሥራ እና እንቅስቃሴ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ብዙ ርቆ እንዳይሄድ አድርጎታል።
እግዚአብሔር ሰው ሆነ። የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ አደረ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሰውኛ ስም ተሰይሞ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተባለ። ሊያድነን የሚችለው ስም ይህ ብቻ ነው። ሚሽነሪዎቹ ሲሰብኩ የነበሩት መዳን ይህ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
አውሮፓ ውስጥ የሥላሴ ትምሕርት ሕዝቡን ሁሉ ስለተቆጣጠራቸው የእግዚአብሔርን ስም ማግኘት አልቻሉም።
እግዚአብሔር አብ ከኢየሱስ የተለየ አካል ከሆነ እርሱ አልሞተም ደግሞም አልተቀበረም። ከሞትም አልተነሳም። ስለዚህ በውሃ ጥምቀት ውስጥ በሚከናወነው ተምሳሌታዊ እውነት ውስጥ ማለትም የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር እና ትንሳኤ ውስጥ ምንም ሚና የለውም ።
“እግዚአብሔር አብ” ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም። “እግዚአብሔር ወልድ” በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሙሉ የለም፤ “አንድ እግዚአብሔር በሦስት አካላት” የሚሉ ቃላትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የሉም። ሆኖም ግን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር “ስም” ስም ነው የሚለው አስተሳሰብ በቤተክርስቲያኖች እና በከፈቱዋቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ እየተንሰራፋ መጥቷል። ከዚህም የተነሳ በዓለም ላይ ቤተክርስቲያን በብዙ ቡድኖች እየተከፋፈለች ሄደች።
ራዕይ 3፡7 በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል።
ስድስተኛው የቤተክርቲያን ዘመን የጀመረው በ1750 ዓ.ም.ነው። ይህ ወቅት እስኮትላንድ ውስጥ በ1776 ጄምስ ዋት በእንፋሎት ኃይል የሚንቀሳቀስ ሞተር የፈጠረበት የለውጥ ዘመን ነበር። በእንፋሎት ኃይል በሚንቀሳቀሱ ሞተሮች አማካኝነት የወንጌል ሰባኪዎች በመርከብ ባሕር አቋርጠው በምድርም ላይ በባቡር ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተሻግረው ወንጌልን በየሃገሩ ማሰራጨት ቻሉ። እንግሊዛውያን ወንጌልን ማሰራጨት ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር የዓለምን አንድ አራተኛ ግዛት እንግሊዝ እንድትይዝ አደረገ። ከዚያም በተጨማሪ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ሁሉ ይሰራጭ ዘንድ እንግሊዝኛ ዓለም አቀፍ ቋንቋሆነ።
መጽሐፍ ቅዱስ በ47 ምሑራን ተተርጉሞ በ1611 ዓ.ም. ታተመ። ከዚያም ለ158 ዓመታት በጥንቃቄ ተፈትሾ ታርሞ በ1769 ዓ.ም. በብዛት ታተመ። ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ካሉት አራት ሕያዋን ፍጥረታት ሦስተኛው ሰው ነው። ይህ ዘመን ከሕያዋኑ ፍጥረታት ውስጥ ሁለተኛውን ማለትም የበሬውን ዘመን የተከተለ በመሆኑ በጨለማው ዘመን ውስጥ ብዙ እልቂት ሆኗል። እግዚአብሔር በዚሁ ዘመን ውስጥ ታላላቅ የስነ ጥበብ ሰዎችን እነ ማይክል ኤንጅሎ እንደ ቢቶቨን ያሉ ታላላቅ ሙዚቀኞችንና እንደ ሼክስፒር ያሉ ታላላቅ ደራሲዎችን ለምድር ሰጠ። በዚህ ታላቅ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች በተነሱበት ወቅት ውስጥ እግዚአብሔር በእብራይስጥ እና በግሪክ ቋንቋዎች የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወደ እንግሊዝኛ የሚተረጉሙበት ጥልቅ ማስተዋልን ሰጣቸው።
የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ትርጉሞች ሁሉ በትክክለኛነቱ አንደኛ ደረጃ የያዘ ትርጉም እንደመሆኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በዓለም ዙርያ በተስፋፋ ጊዜ በእንግሊዝ ግዛቶች ሁሉ ተሰራጨ። ትክክለኛነቱ በቋንቋ አተረጓጎም ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለሰዎች በማስተላለፍም ጭምር እንጂ።
የጆን ዌስሊ እና የጆርጅ ዋይትፊልድ ስብከት ወንጌልን ከቤተክርስቲያን አውጥቶ በአደባባዮችና በሜዳዎች ሁሉ እንዲሰማ አደረገ። ይህም ተከትሎት ለመጣው ታላቅ የሚሽነሪዎች እንቅስቃሴ መሰረት ጣለ። ዌስሊ እንደ አስተምሕሮ ቅድስና ላይ ትኩረት አደረገ። የራሱ ሕይወትም ለክርስቶስ ቅድስና ትልቅ ምስክርነት ነበረ።
ዌስሊ እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንጂ ፖለቲካ ውስጥ እንዳልሆነ ለሰዎች አስተማረ። ዌስሊ እንግሊዝን በፈረንሳይ አብዮት ውስጥ ከተፈጸሙ ብዙ ክፋቶች በማዳን ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
በሚሽነሪዎቹ ዘመን የወንጌል ሰባኪዎቹ ባሕር ተሻግረው ለሚያገኙዋቸው ሃገሮች መሰረታዊውን እውነት ብቻ በመናገራቸው ኢየሱስ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሆነ አድርገው አስተማሩዋቸው። በዚህም እግዚአብሔርን በትክክል ለማወቅ በሩ ተከፈተ። አውሮፓ ውስጥ የተቀመጡ የስነ መለኮት ምሑራን (ቲዮሎጂያኖች) ሥላሴ ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ብዙዎች ግን ኢየሱስን የእግዚአብሔር መንፈስ በሙላት ያደረበት ሰብዓዊ ሰው አድርገው ማየት ጀምረዋል። ኢየሱስን እና እግዚአብሔርን ሁለት የተለያዩ አካላት አድርጎ በማየት ፈንታ የእግዚአብሔር መንፈስ በኢየሱስ አካል ውስጥ አድሯል የሚለው እይታ እየጎላ መጣ። እግዚአብሔር ማለት በኢየሱስ አካል ውስጥ ያደረው መንፈስ መሆኑ እየተገለጠ ሲመጣ ከዚያ በኋላ ይህንን መገለጥ ማንም ሁለተኛ ሊያዳፍነው አልቻለም። በሥላሴ የሚያምኑ ቤተክርስቲያኖች በቁጥር ቢበልጡም ደግሞም ተቃውሞዋቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም እንኳ የእግዚአብሔር እውነተኛ ማንነት ለሰዎች እየተገለጠ እየተገለጠ ሊሄድ ችሏል።
ራዕይ 3፡8 ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።
ይህ የታላቁ የሚሽነሪዎች ዘመን ውብ መገለጫ ነው። በቋንቋ ሳይንስ የተካነው ዊልያም ኬሪ የተባለ ጫማ ሰፊ በ1792 ወደ ሕንድ ሄደ። እርሱንም ተከትለው በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሽነሪዎች ሄዱ። ይህ ዘመን የወንጌል ስርጭት ወርቃማ ዘመን ነበረ። ታዋቂው ወንጌል ሰባኪ ሃድሰን ቴይለር በ1853 ወደ ቻይና ሄደ፤ ዴቪድ ሊቪንግስተን በ1841 ወደ አፍሪካ ሄደ። ሚሽነሪዎቹ ሃብታሞች አልነበሩም ግን የተሰጡ ነበሩ፤ ያለማቋረጥ እንግልት ቢደርስባቸውም ጸንተው ይቋቋሙ ነበር። ዓይኖቻቸውን በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ አነጣጥረው እስከ ዛሬ ድረስ የሚያስቀርም የወንጌል ፈር ቀዳጆችና ታላቅ ምሳሌዎች ሆነዋል።
ሚሽነሪዎቹ ብዙም ብርታት አልነበራቸውም ምክንያቱም የጴጥጤ ቆስጤ ኃይል ገና እስከ 1906 ዓ.ም. በአዙሳ ጎዳና ላይ እንደሆነው መነቃቃት በኃይል አልፈሰሰም ነበር።
በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት ባገኘው የሥላሴ ትምሕርት ተጽዕኖ ውስጥ ስለነበሩ የውሃ ጥምቀትን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለማከናወን የሚበቃ ድፍረት አልነበራቸውም።
ሆኖም ግን ወንጌልን በዓለም ዙርያ በማሰራጨት ያስመዘገቡት ውጤት የዚህን ዘመን ሰው የሚያንገዳግድ ነው።
ራዕይ 3፡9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
በፍርድ ቀን ስሕተትን ያደረጉ ሰዎች እውነትን ባደረጉ ሰዎች ማለትም በፈራጆቻቸው ፊት ወድቀው ይሰግዳሉ።
1ኛ ቆሮንቶስ 6፡2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን?
የሰይጣን ማሕበር ይህንን ዘመን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አሉታዊ አገላለጽ ነው። ይህ ዘመን ሚሽነሪዎች ወንጌልን በማሰራጨት የሰሩትን አስደናቂ ሥራ ተከትለው ክርስቲያኖች ነን ብለው የሚያምኑ ቅኝ ገዥ ሃገሮች በግፍ እና በስግብግብነት የተገለጡበት ዘመን ነው። በተጨማሪም በተለያዩ ስሞች የተከፋፈሉት ቤተክርስቲያኖች ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆኑ ትምሕርቶች እና ለሰው መሪዎች በማስገዛት ኃይላቸውን ያጠናከሩበት ወቅትም ነው።
ምኩራብ ወይም ማሕበር በግሪክ ሲናጎግ ሲሆን (ሲናጌይን ማለት መሰብሰብ ነው) ቃሉ “የመሰብሰቢያ ሥፍራ” የሚል ትርጉም አለው።
ለአምልኮ ዋነኛው መሰብሰቢያ መቅደሱ ነበረ፤ የአምልኮ መሪዎች ደግሞ ካሕናቱ ነበሩ።
ረቢ፣ ፈሪሳዊ፣ እና ሰዱቃዊ የሚሉ ቃላት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ አይገኙም።
አይሁዳውያን በ600 ዓመተ ዓለም አካባቢ በባቢሎናውያን ተማርከው ባቢሎን ውስጥ በግዞት ይኖሩ ነበር፤ እዚያ በነበሩበት ጊዜ ያሉበትን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የሉይ ኪዳን ሥርዓቶችን እንደሚመቻቸው ማሻሻል ጀመሩ።
በአራቱ ወንጌሎችና በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ምኩራቦች 65 ጊዜ ተጠቅሰዋል። ስለዚህ ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ምኩራቦች ወደ አይሁድ የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ ሰተት ብለው በመግባት ትልቅ ሥፍራ ይዘው ነበር፤ ደግሞም ትልቅ ሚና ተጫውዋል።
ከዚያም ስሕተት እየተዛመተ ሄደ። ምኩራቦች የአይሁድ የእምነት ማዕከል ወደመሆን ሲመጡ በእምነት ውስጥ ሰው ሰራሽ የሆኑ የሥልጣን ተዋረዶችም እንደ አረም በብዛት በቀሉ። ረቢ (መምሕራን)፣ ፈሪሳውያን (የሐይማኖት መሪዎች የሆኑ ነጋዴዎች)፣ እና ሰዱቃውያን (ለንጉሳውያን ቤተሰቦች የሚቀርቡ የሐይማኖት መሪዎች) ብቅ ብቅ አሉ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሕን በለቀቀ መዋቅር ውስጥ የሥልጣን ጥማት ላለባቸው ሰዎች የመሪነትን ሥፍራ ለመቆናጠጥ ያመቻቸዋል።የሥልጣን ጥማትና የገንዘብ ፍቅር አይነጣጠሉም። የአይሁድ ሐይማኖት ንግድ ላይ ትልቅ ትኩረት አለው። ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከመቅደስ ውስጥ አባረራቸው። ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ለገንዘብ ነው።
አይሁዶች በብሉይ ኪዳን ጸንተው አልኖሩም። አብዝተው በምኩራቦች ውስጥ በመሰብሰብ የብሉይ ኪዳን ሥርዓትን ለውጠዋል፤ ይህም ለውጥ ለአዳዲስ ሥልጣን ፈላጊ የሐይማኖት መሪዎች በር ከፍቶላቸዋል።
የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንም ተመሳሳይ ስሕተት ሰርታለች። በአዲስ ኪዳን አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰውን “ፓስተር” (እረኛ) የሚለውን (ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ ስድስት ጊዜ የተወገዘውን) ቃል ወስደው በዚህ ማዕረግ የሚጠራውን ሰው ከፍ ከፍ በማድረግ የቤተክርስቲያን ገዥ አደረጉት።
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ፓስተሩ መጽሐፍ ቅዱስ ባይደግፈውም የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ሲል የቤተክርስቲያን አባላት መስማማት ግዴታቸው ነው። በፓስተሩ ሃሳብ አልስማማም ካልክ ቤተክርስቲያኔን ልቀቅ ይልሃል። ከዚህ የተነሳ በፓስተሩ ሃሳብ የማይስማሙ ሰዎች ይበተናሉ፤ ቤተክርስቲያንም ተመልሳ የመታደስ ተስፋ የላትም። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከነበሩዋት መነኩሴዎች ከሁሉ የተሻለውን ማርቲን ሉተርን አባረረችው። አንግሊካኖች በመካከላቸው ድንቅ ሰባኪ የነበረውን ጆን ዌስሊ አባረሩት። አዲስ የተገለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ለመቀበል እምቢ በማለት ብዙ ቤተክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እድገታቸው ተገድበው ቀሩ።
ፓስተሮች በኃይል ሥልጣን ይይዛሉ። በእነርሱ ሃሳብ የማይስማሙ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን ያባርራሉ። ከዚያም በቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተሮችን ለመቃወም የሚበቃ እውቀት ከሌላቸው ወይም ለእውነት ለመቆም ወኔ የሌላቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ይቀራሉ። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማወቅ ብዙም ግድ በሌላቸው ሰዎች ትሞላለች። በስተመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው እጅግ አናሳ በመሆኑ ምክንያት ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሲገለጥ መረዳት ያቅታቸዋል።
አንድ ምሳሌ እንመልከት፡- ኢየሱስ በተዓምራት እንጀራና ዓሳ አብዝቶ 5000 ሰዎችን እና 4000 ሰዎችን በተዓምራት እንደመገበ ሲሰሙ ክርስቲያኖች ይገረማሉ። ነገር ግን በዚህ ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ሚስጥር አያስተውሉም። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለነዚህ ታምራት ሲጠይቃቸው ስንት መሶብ ቁርስራሽ እንደተረፈ ትኩረት ሰጥቷል። እኛ ደግሞ የቁጥሩን ጉዳይ ብዙም ልብ አንለውም። ስለትራፊ ቁርስራሽ እንጀራ ማን ይገደዋል? እኛ ምንም አይጠቅምም ብለን የምንረሳውን ክፍል ኢየሱስ ግን የተዓምራቱ ዋነኛ ቁም ነገር አድርጎ ይቆጥረዋል።
ማቴዎስ 16፡8-9 ገና አታስተውሉምን? ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
12 መሶብ እና 7 መሶብ። ምን ማለት ነው?
ኢየሱስ ይህንን ጥያቄ የጠየቃቸው ደቀ መዛሙርቱ በመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር መሰረት እንዲያስቡ ብሎ ነው።
የሙሴ ድንኳን ውስጥ ሰባት ቅርንጫፎች ያሉት መቅረዝ እና አሥራ ሁለት የገጽ ሕብስት ያሉት ገበታ ነበረ።
በመቅደሱ ቅድስት ውስጥ ሰባት ቅርንጫፎች ያሉት መቅረዝ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክል ነበረ፤ እነዚህም ቤተክርስቲያኖች በ2000 የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ለዓለም የሚያበሩ ናቸው።
መቅደሱ ውስጥ በቅድስት ሥፍራ የሚበሉ አሥራ ሁለት የገጽ ሕብስቶችም ነበሩ። እነዚህም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ከአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገዶች መካከል የሚድኑትን 144 000 ሰዎች የሚወክሉ ናቸው። እነዚህ አይሁዶች መሲሑን ሊገናኙ የሚችሉበት ብቸኛው ቦታ ወደሆነው ወደ እሥራኤል ምድር መመለስ አለባቸው።
ስለዚህ መቅደሱ ሁለቱን ማሕበሮች የሚወክል ነው፤ እነዚህም ሁለት ማሕበሮች ቤተክርስቲያን እና አይሁዶች ኢየሱስን በመግደል አንቀበልም ካሉ በኋላ ወንጌልን የሚቀበሉ 144 000 አይሁድ ናቸው።
አሁን ደግሞ ወደ አሥራ ሁለቱ መሶብ እና ሰባቱ መሶብ ቁርስራሾች እንመለስ። ይህ የእግዚአብሔርን ታላቅ የማዳን እቅድ ይገልጻል። አይሁድ በቀራንዮ ወንጌሉን አንቀበል ብለዋል፤ ይህም ኢየሱስ ተዓምር በሰራ ጊዜ ሕዝቡ አንበላም ብለው የመለሱትን ቁርስራሾች ያመለክታል። እንጀራ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው።
ስለዚህ እንጀራ ኢየሱስን ይወክላል።
ዮሐንስ 6፡35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ … አላቸው
ቁርስራሹን እንጀራ ደቀመዛሙርቱ ይሰበስቡና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አድርገው ይጽፉዋቸዋል። ሰባቱ መሶብ ቁርስራሾች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክሉ ሲሆኑ ሙሽራዋ በነዚህ ዘመናት ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት በእጃቸው የጻፉትን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንደ እንጀራ እየበላች ትኖራለች።
ከዚያም በኋላ 12 መሶብ ቁርስራሽ ሲተርፍ ለአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገዶች ከመካከላቸው በታላቁ መከራ ዘመን በሁለቱ ነብያት አማካኝነት 144 000 ሰዎች በሚለዩ ጊዜ ይቀርብላቸዋል።
ከሚሽነሪዎች ዘመን ወዲህ አሁን ወደ ትንቢታዊው የንሥር ዘመን ማለትም ጠለቅ ያለ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ወዳገኘንበት ዘመን ተሸጋግረናል።
ማንም ሰው ፓስተርም ሆነ ቄስ ተብሎ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ አልተሾመም። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። ክርስቶስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን አዳኝ። ፓስተርም ይሁን ሌላ ማንኛውም አይነት ሰው ቤተክስቲያንን ሊያድን አይችልም።
በፍጥረታዊው አካላችን ውስጠ ራስ ከቀረው ሰውነት ጋር የተጋጠመው አከርካሪ ውስጥ ባለው የጀርባ አጥንት አማካኝነት ነው።
ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለመቆም እንድንችል የጀርባ አጥንት ያስፈልገናል።ራስ ከአካል ጋር የሚጋጠመው በጀርባ አጥንት ነው።
አከርካሪ ውስጥ ያሉ የመጀመሪያዎቹ 7 አጥንቶች አንገትን የሚደግፉ ሲሆኑ ቀጣዮቹ ወደ ታች ያሉት 12 አጥንቶች ደግሞ ጎድኖቻችንን ይደግፋሉ።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የምታልፈው ሙሽራይቱ እና 144 000 ሆነው ከታላቁ መከራ ውስጥ ወጥተው የሚመጡት አሥራ ሁለቱ ነገዶች ናቸው ክርስቶስን ከአካሉ ጋር የሚያጋጥሙት።
ሰይጣን ግን ቤተክርስቲያንን ከባዕድ ራስ ጋር ሊያጋጥማት ይፈልጋል።የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሱ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ትላለች። ፕሮቴስታንቶች ፓስተሩ የቤተክርቲያን ራስ ነው ይላሉ።
ማንኛውም ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ቢል ተሳስቷል።
አንድ አገልጋይ ከቤተክርስቲያን አባላት በላይ ከፍ ሲል ይህ የኒቆላውያን ትምሕርት ይባላል። እግዚአብሔር ደግሞ ይጠላዋል።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
ስሕተት ቀስ ብሎ ሾልኮ ይገባል፤ ከዚይ በኋላ የተከታዮቹ ቁጥር እየጨመረ ሄዶ ሁሉም ሰው እየኮረጀ ሲለማመደው እንደ ትክክለኛ ነገር ተቀባይነት ያገኛል።
ሰውን የቤተክስቲያን ራስ አድርጎ መሾም የተዋጣለት ሐይማኖታዊ ድርጅት ለመመስረት ይጠቅማል። እግዚአብሔር ግን ቤተክርስቲያን በዚህ መንገድ እንድትሄድ አልፈለገም።
ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
16 እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።
ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገን ከሾምን እግዚአብሔር ንሰሃ እንድንገባ ይጠይቀናል። ከአፉ የሚወጣው ሰይፍ ቃሉ ነው። የትኛውም የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ፓስተርን ወይን ቄስን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ አይሾምም። ፓስተር የቤተክርስቲያን ነው የሚል ትምሕርት ሐሰተኛ ትምሕርት ነው።
የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ስለሆነ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ሲሆን እግዚአብሔር ደስ አይለውም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነ አይናገርም። አንድ አካል ሁለት ራስ ሊኖረው አይችልም።
መምረጥ አለባችሁ። ወይ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ወይ ደግሞ ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ነው፤ ነገር ግን ሁለቱም በአንድ ጊዜ ራስ ሊሆኑ አይችሉም።
ኤፌሶን 4፡15 ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ባይደግፋቸውም የቤተክርስቲያን ራስ መሆናቸውን እንደምንም ብለው በክርክር ያሳምናሉ። የኒቆላውያን ትምሕርት የሚለው ቃል (አንድ ሰው የቤተክርስቲያን አለቃ የሚሆንበት) በውስጡ ትንቢትን የመረዳት ትምክሕት አለበት። በነብይ ስም የሚመጣ ሐሰተኛ ትምሕርት ሐይማኖታዊ አሳችነትን ለመሸፈን ያገለግላል፤ ይህም እውነት ነጩን ፈረስ በሚጋልበው የተመሰለው የሰዎች ንግግር የእግዚአብሔርን ቃል ቦታ እንዴት እንደሚወስድ ለማሳየት ነው።ከዚያም በኋላ የሰዎች ገዥነትና ፈላጭ ቆራጭነት በሥልጣን ጥማት ቤተክርስቲያንን ለመምራት ይነሳል። ይህም የተገለጠው የቀይ ዳማው ፈረስ ላይ በተቀመጠው የተመሰለ ሲሆን እርሱም ተቃዋሚዎቹን ሁሉ የሚያጠፋ እና የራሱን ታላቅነት ለማሳየት ፖለቲካዊ ስልጣን ውስጥ የሚሳተፍ ሰው ነው።በስተመጨረሻም ዓለማዊ ሃብትን በመውደድ የሚመጣ አጋንንታዊ አሰራር ክርስትናን በታላላቅ ንግዶች ውስጥ በማጠላለፍ ያረክሳል። ዘመናዊዎቹ ቤተክርስቲያኖች የሚሉት “አሥራት በሙሉ የፓስተሩ ድርሻ ነው”። ነገር ግን እንዲህ የሚያስተምር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም።
ሆኖም ፓስተሩ አሥራትን ሁሉ (የራሱ ገንዘብ ያልሆነውን) ከሕዝቡ ይሰበስብና ለራሱ እና የእርሱን ሃሳብ ለሚደግፉ ብቻ ገንዘብ ይሰጣል።ሌሎቹ ሰባኪዎች በሙሉ ክፍያ ለማግኘት ሲሉ ፈጥነው ከፓስተሩ ሃሳብ ጋር ይስማማሉ። በዚህም መንገድ አንድ ሰው ሁሉን የሚቆጣጠርበት ሥርዓት ይፈጠራል።ገንዘብ የሚከፍል ሰው ሁል ጊዜ እንደ አለቃ ይታያል። እርሱ ገንዘብ የሚከፍላቸው ሰዎች አንዲህ የሚል መፈክር አላቸው፡- “እንጀራ የሚያበላኝን፤ መዝሙሩን እዘምርለታለው”።
አፈንጋጭ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ወዲያ ፈላጊ እንደሌላቸው ያያሉ። ይህ አሳዛኝ ነገር ግን ሰዎችን በአንድ ሰው ሥር እስረኛ አድርጎ ለማስቀረት አይነተኛ ዘዴ ነው።
በ1792 እና በ1906 ዓ.ም መካከል ወደተከሰተው የሚሽነሪዎች ዘመን እንመለስ።
እግዚአብሔር እንግሊዝ ኃይለኛ የባሕር ኃይል እንድትመሰርት ፈቀደላት፤ ይህም በሚሽነሪዎች ዘመን የወንጌል ሰባኪዎችን በባሕር ላይ ወደተለያዩ ሃገሮች ለማመላለስ መንገድ ከፈተ።እንግሊዞች እስኮትላንድ ውስጥ በእንፋሎት ኃይል የሚሰራ ሞተር በመፈልሰፍ የኢንዱስትሪ አብዮት እንዲጀመር አደረጉ፤ ከዚህም የተነሳ በእንፋሎት ኃይል የሚንቀሳቀሱ መርከቦች እና ባቡሮች በታላቅ ፍጥነት እንዲሄዱ በማድረግ በብዙ ሃገሮች ውስጥ በምድር ላይ ዘልቀው መግባት ቻሉ።የዚህ ሁሉ ቴክኖሎጂ እድገት ምስጢራዊ ዓላማ ወንጌል በሚሽነሪዎች አማካኝነት በዓለም ላይ ለብዙ ሃገሮች ይዳረስ ዘንድ ነው።
ነገር ግን የኢንዱስትሪ አብዮቱ እንግሊዝ ከሌሎች ሃገሮች የሚበልጥ ኃይልና ብቃት ያለው የጦር መሳሪያ እንድታመርት ስላስቻላት ሌሎች ሃገሮችን አሸንፋ በቅኝ እንድትገዛቸው አስቻላት። ከዚያም እንግሊዝ ስለራሷ ስልጣን እና ጥቅም ብቻ እንጂ ስለ ሌሎች ሃገሮች ሰላም ማሰብ አቆመች።
የወንጌል አገልጋዮች ሥፍራቸውን ረስተው ራሳቸውን የቤተክርስቲያን መሪ አድርገው እንደሚሾሙት ሁሉ እንግሊዝም ሌሎች ሃገሮችን ልትገዛ ልታስተዳድር ተነሳች።
አንድ ሰውን ከፍ በማድረግ በሌሎች ላይ ገዥ እንዲሆን መሾም ወይም የኒቆላውያን ትምሕርት ተብሎ የሚጠራው የተጀመረው በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። ይህም ሥርዓት ፖለቲካ ውስጥ ሁሉ ገብቶ አውሮፓ በቅኝ የያዘቻቸውን ሃገሮች የምታስተዳድርበት መንገድ ሆነ።ቀጥሎ ደግሞ ፕሮቴስታንቶች የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሥርዓት በመቅዳት በሃሳብ ከእርሱ ጋር የሚስማሙ ተከታዮችን የሚገዛ ፓስተርን በመሾም ቤተክርስቲያንን እንዲመራ አደረጉ።
የአውሮፓ ሕዝቦች በሄዱበት ሃገር ሁሉ ራሳቸውን ከሃገሬው ሰው የሚሻሉና የሚበልጡ አድርገው ቆጠሩ።በቅኝ የተገዙ ሃገሮች ሕዝቦች ብቸኛው የኑሮ ዓላማቸው ገዢዎቻቸው ለሆኑት የአውሮፓ ሃገሮች ዝቅ ብሎ መገዛት ነበር።አውሮፓውያኑ በቴክኒክና በስልጣኔ ከሌሎቹ ሃገሮች ስለቀደሙ ብቻ በተፈጥሮዋቸውም ጭምር ከሌሎች ሕዝቦች የሚበልጡ መሰላቸው። እነርሱ ቅኝ በገዙዋቸው ሃገሮች ውስጥ ያገኙዋቸውን ሕዝቦች የበታች አድርገው ተመለከቱ፤ ይህም አመለካከታቸው ለመርዛማው የዘረኝነት ሃረግ ሥርና ዘር ሆነ።
በ2000 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ቁጥራቸው ከ45000 ለሚያልፉት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች መፈጠርና ለቤተክርስቲያን መከፋፈል መንስኤው “የቤተክርስቲያን ራስ” ነን፤ ለቤተክርስቲያን ምን እንደሚያስፈልግ ሁሉን እናውቃለን፤ ሰዎችን ሁሉ መርዳት እንችላለን የሚሉ ፓስተሮች ናቸው።ቤተክርስቲያን መፍትሄ የሌላት የመከፋፈል የመሰነጣጠቅ ቤት ከሆነች ሰንብታለች። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን እኛ ትክክል ነን ይላል። ነገር ግን ሁሉም ትምሕርታቸው ልዩ ልዩ ነው። ስለዚህ አንድ ችግር አለ ማለት ነው።
ዘረኝነትና እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ለራሱ ያበጀው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርት በቀላሉ የሚፈታ ችግር አይደለም።እስከዛሬ ድረስ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ከተከተሉዋቸው የተሳሳቱ ትምሕርቶች አልተላቀቁም።በቅኝ ግዛት ሃገሮች ውስጥ ሰዎች በራሳቸው ሃገር ዝቅተኛ እንደሆኑ ተደርገው የተቆጠሩበት ግፍ ዘሩ እስከ ዛሬ ድረስ መራራ ፍሬ እያፈራ ይኖራል።ማክቤዝ በተባለው ድራማ ውስጥ ሼክስፒር ሲጽፍ እንዲህ ብሎ ነበር፡- “ለራሳችን ክፉ እናጭድ ዘንድ፣ የጨለማ ሰራዊቶች እውነትን ይነግሩናል”።
ሚሽነሪዎች ሩቅ ሃገር ሄደው እውነትን ሰበኩ፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ስለታጠቁ ብቻ ሄደው እነዚያን ሃገሮች በኃይል በመግዛት በጭካኔ በዘበዙዋቸው። በቅኝ የተገዙ ሕዝቦች በሁለት ተቃራኒ ነገሮች መካከል ግራ ተጋቡ። በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ከሐጢያት ነጻ ስለመውጣት የሰበኩ ሚሽነሪዎች መልካም የሕይወት ምሳሌ አሳይተው ነበር። ነገር ግን በቅኝ ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በገዢዎቻቸው በተፈጸመባቸው የተደራጀ ዝርፊያ ምክንያት ብዙ ችግር ውስጥ ወደቁ፤ ይህም በዝርፊያ የተገኘ ሃብት እንግሊዝን አበልጽጓታል።ይህ በዝርፊያ የተገኘ ሃብት በተለይም ከግዛቶች ሁሉ በተፈጥሮ ሃብት ከበለጸገችው ሕንድ የተሰበሰበ ሃብት ነው የኢንዱስትሪ አብዮቱን ወጭዎች የሸፈነው።ሃብታም መንግስታት የተመሰረቱት በባሪያ ጉልበትና ብዙ ሃገሮችን በመዝረፍ ነው።በቅኝ ግዛት የተገዙ ሕዝቦች በራሳቸው ሃገር ውስጥ ዝቅተኛ ባሪያዎች ሆኑ።ይህም በቅኝ ግዛት ውስጥ ተገዝተው የሚኖሩ ሕዝቦች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠሉ አደረገ፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የገዢዎቻቸው የጨቋኞቻቸው መመሪያ መጽሐፍ ነበረ።ከዚህም የተነሳ ጨለማ እየሰፋ ሄደ።
ገንዘብ ማግበስበስን የሚወክለው ጥቁር ፈረስ ወይም በዚህ የተመሰለው አጋንንታዊ አሰራር ከ1757 እስከ 1947 እንግሊዝ ሕንድን በገዛችበት 190 ዓመታት ውስጥ 35 ሚሊዮን ሕንዳውያን በረሃብ እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል።ለገንዘብ በመስገብገብና ግብዝነት በሞላበት ጭካኔ እንግሊዞቹ ሕንድ ውስጥ የተመረተውን አብዛኛውን ምግብ በመርከብ ጭነው ወደ እንግሊዝ በመላካቸው ሕንድ ውስጥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በረሃብ ተሰቃዩ። እንግሊዝ ግን በሕንድ ሃብት ራሷን አበለጸገች፤ የኢንዱስትሪ አቅሟንም አሳደገች።ሚሽነሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው መጡ፤ ይህም መልካም ነበር ግን እንግሊዛውያኑ ቅኝ ገዥዎች ሳንጃ እና ውስኪ ይዘው ገቡ። ሕዝቡን ለማረጋጋት ይጠቀሙ የነበረው ኃይልና ግፍ ነበር። ስለዚህ የቅኝ ግዛት ዘመን በብዙ ሃገር ሕዝቦች ላይ አሳዛኝ ትዝታ ጥሎ አልፏል።
አንዳንድ የታሪክ ጸሐፊዎች በአፍሪካ ውስጥ በእንግሊዝ ግዛቶች የተፈጸመውን ብዙ ግፍ እና አሰቃቂውን የባሪያ ንግድ መዝግበዋል። ቻይና ውስጥ በተደረገው የአደንዛዥ ዕጽ ጦርነት ብዙ ቻይናውያን በግዴታ ኦፒየም የተባለ ዕጽ ገዝተው እንዲያጨሱ በመደረጋቸው 100 ሚሊዮን ቻይናውያን ያለ እድሜያቸው በሱስ ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል።ለአብዛኞቹ አውሮፓያን ቅኝ ገዥዎች ጉቦ፣ ግድያ፣ ስርቆትና ዝርፊያ የኑሮ ዘይቤያቸው ነበር።ከገንዘብ ፍቅር ጋር የሚሰሩ አጋንንት አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎችንይህን ያህል ነበረ ያዘቀጡዋቸው።
ይህ ከገንዘብ ፍቅር ጋር የሚሰራ አጋንንት በቤተክርስቲያኖች ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንዳሳደረ መገመት ከባድ አይደለም።
በአንድ በኩል ለአገልግሎታቸው ከነፍሳቸው የተሰጡ ሚሽነሪዎች ብዙ ሰዎችን ከሐጢያት ተጽዕኖ ነጻ ለማውጣት ሲለፉ ነበር።በሌላ በኩል ደግሞ ቅኝ ገዢዎች ገንዘብ ለማጋበስ ባደረጉት ሩጫ ሕዝቡን የበታች አድርገው ረግጠው በኑሮ አስመርረውታል።ቤተክርስቲያኖች ደግሞ የሮማ ካቶሊክን ካሕናትን የስልጣን ተዋረድ የተከተለ ግትር የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር አበጅተው ነበር። በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ራሳቸውን ከፍ ያደረጉ አምስት የአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎች ነበሩ። እነርሱም ክርስቲያኖች ሁሉ ካሕናት መሆናቸውን ረስተዋል።ከካሕናት በላይ የሆነው ሊቀካሕናቱ ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ … ናችሁ፤
ዳግመኛ የተወለድክ ክርስቲያን ከሆንክ ካሕን ነህ።ካሕን እንደመሆንህ ካንተ በላይ አንድ ብቻ ነው ያለው፤ እርሱም ሊቀ ካሕናቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ቤተክርስቲያን ለሚመላለሱ ብዙ ሰዎች የዘወትር ምግባቸው ሰው ሰራሽና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የስሕተት ትምሕርቶች ሆኑ። ከዚህም የተነሳ ቀስ በቀስ ብዙ ሰዎች የሚሰሙዋቸውን ትምሕርቶች ትክክለኛነት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የመፈተሽ አቅማቸው እየመነመነ ሄደ።
በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባላት ዘንድ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስን ያለማወቅ ዝንባሌ ቀስ በቀስ ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን አባላት ተጋባ።
በፕሮቴስታንት ሰባኪዎች ዘንድ እንዲህ እያሉ መናገር እየተለመደ መጣ፡- “ይህ በኪንግ ጄምስ ትርጉም ውስጥ የተፈጠረ ስሕተት ነው…”። ከዚህም የተነሳ ፕሮቴስታንቶች ኪንግ ጄምስ ባይብልን ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል አድርገው መውሰድ አቆሙ።
የሮማ ካቶሊኮች ከድሮም ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ በላይ የሆነ መጽሐፍ እንደሆነ አያምኑም። ለእነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችና ሲኖዶሶች ውስኔ አይበልጥም።
ዛሬ ድግሞ ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስን ከፓስተሮቻቸው አመለካከት የማይበልጥ መጽሐፍ አድርገው ነው የሚያዩት።ስለዚህ ፓስተሩ እና መጽሐፍ ቅዱስ ባይስማሙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን አባላት ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ የፓስተሩን አመለካከት ነው የሚቀበሉት።
ዌስኮት እና ሆርት በ1881 ቫቲካን ውስጥ እና የሲና ገዳም ውስጥ በተገኘ ሰነድ ላይ የተመሰረተ የአዲስ ኪዳን ትርጉም አዘጋጁ።ሆርት መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ስሕተት የሌለው ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ የሚያምን ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን የዳርዊን ኤቮልዩሽን ቲዎሪ አድናቂ ነበር።ሆርት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን የሕጻናት ጥምቀት ለሰዎች መዳን አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል።ዌስኮት ደግሞ የዘፍጥረት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕራፎች እንደ ወረደ እውነት ናቸው ብሎ አያምንም። ነገር ግን ዌስኮት እና ሆርት ታላላቅ የግሪክ ቋንቋ ምሑራን ተደርገው በመቆጠራቸው እነርሱ ያዘጋጁት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኪንግ ጄምስ ባይብልን ለመተካት በቅቷል።አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ደግሞ በድፍረት ኪንግ ጄምስ ባይብል ውስጥ 40¸000 የትርጉም ስሕተቶች ተገኝተዋል ይላሉ።ይህም አሉባልታ ለብዙ አዳዲስ ትርጉሞች በር ከመክፈቱ የተነሳ ዛሬ በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 በላይ የተለያዩ ትርጉሞች አሉ። ከዚህም አልፈው አንዳንዶቹን አዲስ ትርጉሞች በየጊዜው ያሻሽሏቸዋል። በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የሌለው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ መቀበል ትተዋል።የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከብዛታቸው የተነሳ አንባቢዎች የትኛውን ትርጉም ሙሉ በሙሉ እውነት እንደሆነ ለመለየትና ለመምረጥ ተቸግረዋል።
ከዚህም ሌላ ደግሞ ክርስቲያኖች ለሚሄዱበት ቤተክርስቲያን ልማዶች እንዲገዙ ይገደዳሉ።
ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የጀመሩት ኢየሱስን አዳኝና የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው በመቀበልና ከእርሱ ጋር የግል ሕብረት በማድረግ ነበር። ግን ከዚያ በኋላ ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ወደ ማየትና መሪዬን እከተላለው የሚል አዝማሚያ ውስጥ ገቡ።ከዚያም የቤተክርስቲያናቸውን አስተምሕሮ መከተል ጀመሩ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያገኙት አዲስ ልምምድ ከኢየሱስ ጋር የነበራቸውን ሕብረት ተክቶ ተቀመጠ። ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ የቤተክርስቲያን አባላት ከደገፉዋቸው ትክክል እንደሆኑ ያምናሉ።በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ቤተክርስቲያኒቱ እንደምታስተምረው መመላለስና ከዚያ ፈቀቅ አለማለት ብቻ በቂ ነው።
ክርስትና ማለት የሐይማኖት ባሕል መከተልና ለቤተክርስቲያን መሪ መገዛት ሆኖ ቀረ።
ራዕይ 3፡10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
ትዕግሥት፡- ወደ ባዕድ ሃገር ሄዶ የሃገሬውን ቋንቋ መልመድ። ሚሽነሪዎች በጨካኝ አረማውያን እጅ በግፍ መገደላቸው፤ እንዲሁም በምድር ወገብ አካባቢ ባሉ ልዩ ልዩ በሽታዎች መሞታቸው። የሚሽነሪዎች ዘመንና አገልግሎት ረጅምና አድካሚ ነበር።
እግዚአብሔር ግን ሕይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉት ሰዎች በእድሜያቸው ሁሉ የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ከሚገጥማት ፈተና እንደሚጠብቃቸው ቃል ገባላቸው።ይህ እኛ የምንኖርበት የመጨረሻው ዘመን የፍጥነት የወከባና የሩጫ ዘመን ነው፤ የዚህ ዘመን ሰው እውቀቱ እንኳ ሳይቀር በችኮላ ከኢንተርኔት በመቅዳት የመጣ ጥልቀት የሌለው እውቀት የሚከታተለው መረጃ ውስጥም ሐሰተኛ ዜና የበዛበት ነው።ብዙ ሰባኪዎች በትምሕርቶቻቸው ውስጥ ብዙ አይነት አመለካከቶች ከማስተናገዳቸው የተነሳ ከግራ ማጋባት በቀር ምንም ፍሬ ነገር የላቸውም። የጨለማው ዘመን ሰዎች ማየት ያልቻሉት ብርሃን ስላልነበራቸው ነው። የኛ ዘመን ሰዎች ግን እርስ በርሳቸወ በሚጣሉ የብርሃኖች ብዛት ዓይናቸው ታውሮ ነው ማየት ያልቻሉት።የኛ ዘመን ግራ የመጋባት ዘመን ነው፤ ከእውነት ስተን በጨለማ የምንመላለሰው ብርሃን አጥተን ሳይሆን ዓይናችን ላይ ብርሃን በዝቶብን ነው።
ይህ የመጨረሻ ዘመን ብዙ ክፉ መናፍስት በመጨረሻው የቤተክርስቲያነ ዘመን ውስጥ በአንድነት ተባብረው የሚሰሩበት ጊዜ ነው። እነዚህም ክፉ መናፍስት ተግተው ከሚሰሩት ሐሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ሥራ የተነሳ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ በውሸታቸው ያስቱዋቸዋል። ይህንን ሁሉ የማሳት ሥራ በሚሰሩበት ጊዜ ግን ትክክለኛ ዓላማቸውን ደብቀው ነው የሚንቀሳቀሱት።
ክፉ ወደ መልካም ውስጥ ሾልኮ ከገባ በኋለ በደምብ ከመቀላቀሉ የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመለየት እንኳ አስቸጋሪ ሆኗል።እስካሁን በተዘጋጁት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መለያየት የተነሳ ኪንግ ጄምስ ባይብልን ትክክለኛ እውነትን የያዘ መጽሐፍ ቅዱስ አድርጎ ለማየት እንኳ አስቸጋሪ ሆኗል።የመጨረሻው ዘመን ነብይ የተናገራቸው ቃላት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ተክተዋል። መንገዱን እንዲጠቁም የተተከለው ምልክት በራሱ መዳረሻ ሆኖ ቀረ።
የክፋት አይነት ሁሉ ተሰብስቦ በአንድነት መነሳቱ የመጨረሻውን የቤተክርስቲያን ዘመን ችግሮች ለመፍታት ከባድ ያደርጋቸዋል።
አንዱ ትልቅ ችግር በስኬት ምክንያት የመጣ ውድቀት ነው።
ክትባትና መድሐኒት ብዙ በሽታዎችን እንድንቆጣጠር አስችለውናል።በክኒን መልክ የተዘጋጁ ንጥረነገሮች እድሜያችንን ከ60 ወደ 80 ከፍ አድርገውታል።ብዙ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች መድሐኒት ይወስዳሉ።
ክትባቶች ከመጡ ወዲህ ብዙ ሕጻናት እንዳይሞቱ አድርገዋል።እነዚህ ለውጦች የሕክምናው ዓለም ታላላቅ ስኬቶችና በረከቶች ናቸው።ነገር ግን የዚህ መልካም ነገር አሉታዊ ውጤቱ ደግሞ ዓለም በፍጥነት በሕዝብ ብዛት መጥለቅለቋ ነው። ጥቂቶች ብቻ እየሞቱ ብዙዎች ግን እስከ ሽምግልና ይቆያሉ።
በ1750 የኢንዱስትሪ አብዮት በስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መነሻ ላይ ሲጀምር በምድር ላይ አንድ ቢሊዮን ሰዎች ይኖሩ ነበር።ከኖኅ የጥፋት ውሃ ማለትም ከክርስቶስ ልደት 2000 ዓመት በፊት አንስቶ እስከ 1750 ዓ.ም. ድረስ 3750 ዓመታት አልፈዋል። ስለዚህ የሰዎች ቁጥር አንድ ቢሊዮን እስኪሞላ ድረስ 3750 ዓመታት ፈጅቷል።
ዛሬ ግን የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ15 ዓመታት ብቻ አንድ ቢሊዮን ያህል እየጨመረ ነው።
ስለዚህ የዓለም ሕዝብ ቁጥር ከ1750 ወዲህ ብቻ ከሰባት እጥፍ በላይ ጨምሯል፤ በ2018 በተደረገው ጥናት የዓለም ሕዝብ ቁጥር 7.6 ቢሊዮን ደርሷል።
ለዚህ ሁሉ ሕዝብ መኖሪያ፣ ንጹሕ ውሃ፣ ሕክምና፣ ሥራ፣ ልብስ፣ መጓጓዣ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች መሟላት መፍትሔ የሌለው ድካም ሆኗል።በየከተሞቻችን የላስቲክ ቤቶች እየበዙ ነው። ድሆችና ሥራ አጥ ሰዎች የሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ጽንፈኝነት ሰለባ ናቸው።
የሚሽነሪዎቹ ዘመን ያልገጠመው ሌላ ፈተና ደግሞ የቻይና በሃብትና በሕዝቦቿ ቁጥር ማደግ ነው።በምሥራቁ ዓለም ቻይና በድንገት ብቅ ያለች ስጋት ሆናለች።ቻይና ውስጥ ሊታመን ከሚችለው በላይ ብክለት አለ።የኢንዱስትሪ ማዕከላቸው 1400 ኪሎሜትር ስፋት እና 1400 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ቦታ ነው።የሚጠቀሙት የጥሬ እቃ ብዛት ከግምት የሚያልፍ ሲሆን ዛሬ የዓለም ሁሉ የምርት ማዕከል ሆነዋል።
በዓለም ላይ ከሚከሰቱ አካባቢያዊ አደጋዎች ሁሉ ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው የአይር ብክለት ነው።የአየር ብክለት ቻይና ውስጥ ብቻ በቀን 4400 ሰዎችን እየገደለ ነው።
ሕንድ ውስጥም በተመሳሳይ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይሞታሉ።
ለዚህም ችግር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መፍትሄ አልተገኘለትም።
በሳይንስ ምርምር የተገኙ ፈጣን ለውጦች ብዙ በረከቶችን አምጥተዋል፤ ግን እነዚሁ የሥልጣኔ ውጤቶች ከባድ የብክለት ችግር አስከትለዋል። አፈር ውስጥ የማይበሰብሱ የፕላስቲክ ምርቶች፣ መርዞች፣ የተበከለ ውሃ፣ በሳምባ በሽታ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ የአየር ብክለት፣ ጎርፍ፣ ድርቅ፣ ከባድ ሙቀት፣ የእሳት አደጋ -- እነዚህ ሁሉ ሳይንስ ላመጣልን ብዙ ጥቅም ከባድ ዋጋ መክፈል እንደጀመርን ያመለክቱናል። ብክለት የሳይንስ ድክመት ነው።
ሳይንስ ሐሰተኛ አዳኝ ነው። ሳይንስ የአጭር ጊዜ አስቸኳይ ችግሮቻችን ይፈታልንና ለረጅም ጊዜ የማይፈቱ ከባድ ችግሮችን ያስከትልብናል። የወደፊት የረጅም ጊዜ ሃሳባችንን ለማሳካት ሳይንስ ላይ እንደ ምርኩዝ መደገፋችን እውን የማይሆን የቀን ቅዠት ነው።
የእድገት ክፋቱ ብዙ ገንዘብ እንዲገኝ ቢያደርግም እንኳ የተገኘውን ገንዘብ ግን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲከፋፈል አለማድረጉ ነው። ድሆች የባሰ እየደኸዩ ጥቂት ሃብታሞች ብቻ ግን በሃብት እየጨመሩ ይሄዳሉ። የሃብት አለመመጣጠን እየተባባሰ ይሄዳል። ከእነዚህ ሁለት ጽንፎች መካከል በመሃከለኛ ገቢ የሚኖሩ ከቀድሞ ይልቅ ኑሮዋቸው የተሻሻለላቸው ሰዎች አሉ። ነገር ግን ሲባክኑ እና ሲጨነቁ ነው እድሜያቸውን የሚያሳልፉት። የብዙ ሰዎች ሕይወት በቅሬታ የተሞላ ሆኗል። በኑሮ መሻሻል ሰዎችን ከጭንቀት ሊገላግላቸው አልቻለም።
የመጨረሻው ዘመን ታላቅ ፈተና ሐይማኖትን የሚወክለው ነጭ ፈረስ እና ፖለቲካዊ ኃይልን የሚወክለው ቀይ ፈረስ በአንድነት መንቀሳቀሳቸው ነው፤ ነጩ ፈረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፉ ትምሕርቶችን እንደ እውነት እንድንቀበላቸው ተጽዕኖ የሚያደርግብን ሲሆን ቀዩ ፈረስ ደግሞ ራሳችንን በብቃት ማስተዳደር አለመቻላችንን የሚያመለክት ነው። ከዚያም የገንዘብ ኃይልን የሚወክለው አጋንንታዊ አሰራር በጥቁር ፈረስ ላይ ተቀምጦ ይመጣል። የእነዚህ ሦስት መናፍስት ውሕደት የሚፈጥረው መርዝ ማራከሻ የለውም።
ሦስት ፈረሶች እና አንድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ፈረሰኛ ናቸው ያሉት። ሦስቱ ፈረሶች ማለትም ነጩ፣ ቀዩ እና ጥቁሩ ፈረሶች ተደምረው በመጨረሻው ዘመን የሚነሳውን አንድ ሐመር ፈረስ እርሱም የስሕተት ብዛትና ግራ መጋባትን የሚወክል ሲሆን በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚያመጣው አለማመን የተነሳ ሞትን ያስከትላል። የመልካምና የክፉ እውቀት ዛፍ ፍሬ መብላት የሚያመጣው የሰው ጥበብ ምንጩ ሰይጣናዊ ነው።
“መልካም” የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ቆራርጦ እየጠቀሰ የሚያሞኘን ሲሆን “ክፉ” የሚባው ደግሞ እራሱ መጽሐፍ ቅዱስን ፊት ለፊት የሚቃረነው ትምሕርት ነው።
እነዚህ ሁሉ በአንድነት ተደባልቀው የነጣ የገረጣ እሬሳ የሚመስል ፈረስ ይፈጥራሉ፤ እርሱም የሞተ ነገር ግን የሚራመድ ፈረስ ነው።
“ሐመር” የሚለው ቃል የተተረጎመው “ክሎሮስ” ከሚል ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አረንጓዴ” ነው። እሬሳ መጀመሪያ ይነጣል ምክንያቱም ደሙ ከቆዳው ስር ይሸሻል። (ሥዕል ውስጥ ንጣትን ለማሳየት ነጭ ቀለም ይጨመራል።) ከዚያም ደሙ ወደ ውስጥ እየገባ የሚያቀላው ኦክስጂን ስለሌለ መጥቆር ይጀምራል። (በሥዕል ውስጥ ጨለማ የሚፈጠረው ጥቁር ቀለም ሲጨመር ነው።) ከዚያም ጠቆር ያለው ቀይ ቀለም (የነጭ፣ ቀይ እና ጥቁር ድብልቅ የሆነው) ሬሳው መሽተትና መበስበስ ሲጀምር ወደ አረንጓዴ ይለወጣል። ስለዚህ ሞት በሞቱ እና በሸተቱ ቤተክርስቲያንች ላይ እየጋለበ ይሄዳል፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት እንደሚከረፋ ጥንብ ናች። ታላቁ መከራ ይህንን ይመስላል።
ይህ የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን የሚገጥማት አሰቃቂ ፈተና ነው ነገር ግን ይህ ፈተና እያባበለ እያታለለ ነው ወደ ታላቁ መከራ ይዟት የሚገባው።
እግዚአብሔር ግን የሚሽነሪዎችን ዘመን ከዚህ አይነቱ ዘግናኝ ፈተና ጠብቆ አሳለፈ። ስለዚህ በእነርሱ ዘመን አልሆነም።
ቻርለስ ዳርዊን የኤቮልዩሽን ቲዎሪውን የጀመረው በ1859 ነው፤ ነገር ግን ይህ ቲዎሪ ክፉ ፍሬውን የሚያፈራው ዳርዊን ከጻፈው በኋላ ዓመታት ዓልፈው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ነው፤ ፍሬውም ሳይንቲስቶች የእግዚአብሔርን መኖር እንዲክዱ እና ብዙ ክርስቲያኖች ዘፍጥረትን እንዲጠራጠሩ ማድረግ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ላይ እምነታቸው ቀነሰ።
ካርል ማርክስ በ1848 ነው ኮምዩኒስት ማኒፌስቶ የተሰኘው ጽሑፉን የጻፈው፤ ነገር ግን የካርል ማርክስ ዘር መራራ ፍሬውን ያፈራው እስታሊን 20 ሚሊዮን ራሺያኖችን በረሃብ በገደለ ጊዜ እና ማኦ ዜዶንግ 60 ሚሊዮን ቻይናዎችን በረሃብ በገደለ ጊዜ ነው፤ እነዚህ መሪዎች ይህን ግፍ የፈጸሙት በሃገራቸው ታላቅ የኮምዩኒስት መንግሥት እንመሰርታለን ብለው ነው። የሚሽነሪዎቹ ዘመን ከእንዲህ አይነቱ ዘመን ሰዎች በኮምዩኒስት አጋንንታዊ ጭካኔ ከሚጨፈጨፉበት ዘመን በእግዚአብሔር ምሕረት ተጠብቋል።
የነጣ የገረጣ ፈረስ ላይ የሚጋልብ ሞት ለመጨረሻው ትክክለኛ ተምሳሌት ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡20 ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤
ሳይንቲስቶች ኤቮልዩሽን ቲዎሪን እንደ ትልቅ ግኝት ይቆጥሩታል። ጳውሎስ ግን ከንቱ መለፍለፍ ይለዋል።
ማቴዎስ 24፡24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ
ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር ካልተጣበቅን በሰዎች ንግግር እና ለንግግሮቻቸው በሚሰጡ ትርጉሞች እንታለላለን።
ያወቅን መስሎን እንደ ኤቮልዩሽን እና ቢግ ባንግ የመሳሰሉ ሳይንሳዊ ቲዎሪዎችን ብንከተል እንታለላለን። እነዚህ ቲዎሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ይቃረናሉ፤ ስለዚህ እውነት ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ በነዚህ ቲዎሪዎች አትታለሉ።
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
የሰዎች ንግግር እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ተደርጎ በተጠቀሰ ጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አንጻር ፈትሹት። እውነተኛ መገለጥን ለመለየትና ለመቀበል ብቸኛ ሚዛናችሁ መሆን ያለበት መጽሐፍ ቅዲስ ነው።
ይህ ዘዴ ቀላል አይደለም፤ ምክንያቱም ልትጠቀሙት የምትገልጉ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ አለባችሁ።
ስለዚህ ብዙዎች ይህንን ዘዴ አይመርጡም።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ
በስተመጨረሻ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ጸንተው የሚቆሙ ሰዎች ብዙ አይሆኑም።
ራዕይ 3፡11 እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
የዚህ ዘመን አደጋ በመልካም ሥራ ላይ የተደረገው ትኩረት ነው። መልካም ሥራዎች በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም የማንንም ነፍስ አያድኑም።
የዚህ ዘመን ሰዎች ግን መዳን በእምነትና በመልካም ሥራዎች አማካኝነት ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ።
ለክርስቲያኖች ትልቁ ወጥመድ የሚሆነው በኢየሱስ አምነው ድነው ከእርሱ ጋር የግል ሕብረት ከጀመሩ በኋላ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚደረግ ልምምድ መደገፍ ሲጀምሩ ነው። ከዚያም እንዲህ ብለው ማሰብ ይጀምራሉ፡- “ቤተክርስቲያን ሁሌ ስለማልቀርና የፓስተሬን ሃሳብ ስለማልቃረን ድኛለው”።“በመንጋ ማሰብ” አደገኛ ነው ምክንያቱም በግል እንዳታስቡ ያደርጋችኋል።
“ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ”፡- እግዚአብሔር በሕይወትህ ልዩ ዓላማ አለው።
ቤተክርስቲያን የምትጠብቅብህን ብቻ እያደረግህ ስትኖት ወይም የቤተክርስቲያን መሪህን ስትከተል ራስህን መሆን ታቆማለህ። በዙርያህ ባሉ ሌሎች ሰዎች መልክ እና አምሳል የተሰራህ ሰው ሰራሽ ሰው ትሆናለህ። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚፈልግህን ባለመሆንህ አክሊልህ ይወሰድብሃል። መንጋውን ስንከተል የመንጋው አካሄድ ውሳኔያችን ውስጥ ጣልቃ ይገባል። እግዚአብሔርም በሕይወታችን ውስጥ እድል ፈንታ ያጣል።
ክርስቲያኖች ለራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን ከመመርመር ይሰንፋሉ፤ ስለዚህም የቤተክርስቲያን መሪዎች የሚሉዋቸውን እያመኑ ብቻ ይኖራሉ።
የሌሎች ሰዎችን ንግግር እየጠቀሰ የሚያስተምር ፓስተር የሌሎች ሰዎችን ንግግር የሚጠቅሱ ምዕመናንን ያፈራል። እኛ ግን ወደ ቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መመለስ አለብን። የቤርያ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እለት እለት ይመረምሩ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
የዚያ ዘመን ታላቅ መልዕክተኛ እን ሐዋርያ ከነበረው ከጳውሎስ ከራሱ ነበር የተማሩት።
ሆኖም ግን ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ይመዝኑ ነበር።
ምንም ነገር ሳንመረምር እንዲሁ መቀበል የለብንም።
2ኛ ቆሮንቶስ 13፡1 … ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።
ከማንኛውም ሰው አፍ ተወስዶ የተጠቀሰ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ ወንፊት መጣራት አለበት።
አንድ መገለጥ ትክክለኛ መሆኑን ለማጣራት የሚያስፈልጉ ሁለት ምስክሮች ማለት እነዚህ ናቸው።
በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጦ ግዴ የለሽ መሆን በጣም ይቀለናል። ሰዎች ሁሉ በተፈጠሮዋችን በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት እንፈልጋለን። በፍጹም በዙርያችን ካሉ ሰዎች ለየት ብለን መታየት አንፈልግም። ደግሞም ሰዎች በፈጠሩት ሥርዓት ስናመልክ እግዚአብሔር የሚደሰትብን ይመስለናል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወሩትን ጥልቅ ምስጢራት ፈትሾ ማግኘት ግን ብዙ ጥረት ይጠይቃል።
ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጣ ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው አለማወቃቸውን ለመሸፋፈን “ደህንነቴ ላይ ችግር እስካልፈጠረ ድረስ…” ብለው መናገርን ይለምዳሉ። ነገር ግን የእውነት ንሰሐ በመግባትና ኢየሱስን እንደ አዳኝህ አድርገህ ከዳንክ ደህንነትህን ሊነካብህ የሚችል አንዳችም ኃይል የለም። ስለዚህ ደህንነቴን ካልነካብኝ የሚለው ንግግር መጽሐፍ ቅዱስን ላለማወቅ በቂ ምክንያት አይደለም።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት እንዲህ ይላሉ፡- “ባላውቅስ ምን ችግር አለው?” ትጉዎቹ ቆነጃጅት ግን “ማወቅ አለብኝ” ነው የሚሉት። ስለዚህ የአመለካከት ጉዳይ ነው።
ቃሉ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ ስለዚህ ከቃሉ ውስጥ ለተወሰኑ ክፍሎች ግድ የሌለህ ከሆንክ ስለ ኢየሱስ ምንም ግድ የለህም ማለት ነው።
ይህ ደግሞ የሚያኮራ አቋም አይደለም።
ስለ ኢየሱስ እና ስለ ቃሉ የምንችለውን ሁሉ ለማወቅ ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን አለብን።
ራዕይ 3፡12 ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
ዓምድ መሰረቱን ከጣሪያው ጋር ያገናኛል።
ዓምድ ማለት በብሉይ ኪዳን ነብያት እና በአዲስ ኪዳን ሐዋርያት በተጻፈው በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ላይ ጸንቶ የተተከለ ሰው ነው።
ኤፌሶን 2፡19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤
22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።
በወንጌል ስብከትና በአገልግሎት ውስጥ ሁሉ ክርስቶስን ማዕከል በማድረግ ሚሽነሪዎች በጽኑ መሠረት ላይ ሲገነቡ ነበር።
ዓምድ ብቻውን ይቆማል።
በቤተክርስቲያን ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪን ከፍ ለማድረግ ከምዕመናን ሁሉ የሚመጣብህን ግፊትና ጫና ማሸነፍ አለብህ።
ሰዎች እንደመሆናችን በአንድ ቡድን ውስጥ አባል የመሆን ዝንባሌ አለን፤ ይህም ለራሳችን በራሳችን አእምሮ ማሰብን እንድናቆም ያደርገናል፤ የቤተክርስቲያን ልማዶችና አስተምህሮዎችም ላይ ጥያቄ እንዳናነሳ ያደርገናል።
ክርስትና አንድ ጊዜ የቤተክርስቲያን አባል ከሆንን በኋላ የማስመሰል ኑሮ ይሆንና ከዚያ ክርስትናነቱ ቀርቶ ቤተክርስቲያናዊነት ይሆናል።
ሌሎች ሰዎች እንድንለብስ የሚጠብቁብንን ጭምብል እንለብሳለን።
በዚህ ምክንያት ምን ማድረግ እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ይነግሩናል።
በዚህ አይነት ኑሮ ስንመላለስ ተራ ክርስቲያኖች እንሆናለን።
• የገና በዓል የሚከበርበት ቀን ዲሴምበር 25 ከየት እንደመጣ ለመጠየቅ ድፍረት እናጣለን። ይህ ቀን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
• “ክሪስማስ” የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ ለመጠየቅ ድፍረት እናጣለን። ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
• የጌታን የልደት ቀን እንድናከብር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ ትዕዛዝ አለመሰጠቱን ለመናገር ድፍረት እናጣለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለት ነፍሰ ገዳዮች ብቻ እነርሱም ፈርዖን እና ሔሮድስ ልደታቸው እንደተከበረላቸው ለመናገር ድፍረት እናጣለን።
ኤርምያስ ምዕራፍ 10 የገና ዛፍን እንደ አሕዛብ ልማድ እንደሚያወግዘው መናገር ድፍረት የለንም። ይህ ልማድ መነሻው ከባቢሎናውያን አምልኮ ነው።
ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ስሕተቶች ገልጠን ብንናገር ማንም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እናጣለን። ልክ መጥምቁ ዮሐንስ ለሔሮድስ የወንድሙን ሚስት ማግባት እንዳልተፈቀደለት በድፍረት እንደተናገረው ማለት ነው። ስለዚህ ሔሮድስ ዮሐንስን ገደለው። የገደለውም ደግሞ በልደት ቀኑ ነው።
ማቴዎስ 14፡3 ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤
4 ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤
ዮሐንስ ለሔሮድስ የወንድሙን ሚስት ማግባቱ ትክክል አለመሆኑን ስለነገረው ዮሐንስ ተቀባይነት አጣ።
ስለዚህ ዮሐንስ በሔሮድስ የልደት ቀን ተገደለ። ከዚህ እንደምናየው መጽሐፍ ቅዱስ ለልደት ቀኖች ትልቅ ቦታ አይሰጣቸውም።
ማቴዎስ 14፡6 ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤
7 ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤
8 እርስዋም በእናትዋ ተመክራ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው።
ሔሮድስ የተባለ ክፉ ሰው በራሱ ልደት ቀን ለኢየሱስ መንገድ ጠራጊ የነበረውን መልዕክተኛ መጥምቁ ዮሐንስን ገደለው።
እና የምር እግዚአብሔር የልደት ቀን በማክበር የሚገረም ይመስላችኋል?
እኛ ሰዎች ለልደት ቀን ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን። ከዚያም እግዚአብሔር በሃሳባችን የሚደነቅ ይመስለናል። ደግሞም ይባስ ብለን የራሳችንን ሃሳብ በግድ የእግዚአብሔር ሐሳብ እናደርጋለን። ቀጥለን ደግሞ ለኢየሱስ የልደት ቀን እንመርጥለታለን። ነገር ግን የመረጥነው ቀን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን ነው።
የክሪስማስ በዓል በዲሴምበር 25 እንዲከበር ቀኑን የመረጠው የሮማው ገዥ ኦሬልያን ነው። ነገር ግን ኦሬልያን ራሱ ደግሞ የክርስቲያኖች አሳዳጅና ገዳይ ነው። ሌላኛው መጠሪያ ስሙ "manu ad ferrum" ይባል ነበር፤ ማለትም “እጅ ከሳንጃ”። ማኝኛውንም ችግር ሚፈታው የቃዋሚዎቹን በመግደል ነበር። ስለዚህ በዲሴምበር 25 ቀን እንኳ ሳይቀር ክርስቲያኖችን ገድሏል።
ደግሞ ቀኑ እሥራኤል ውስጥ አጥንት የሚቆረጥም ቅዝቃዜ ያለበት የክረምት ወቅት ውስጥ ነው የሚውለው።
ኢየሱስ አይሁድን ሽሽታችሁ በክረምት አይሁን ብሎ ያስጠነቀቃቸው በብርዱ እንዳይሞቱ ነው።
ማቴዎስ 24፡20 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤
ኢየሱስ የተወለደ ዕለት ግን በምሽት እረኞች ከበጎቻቸው ጋር በሜዳ ነበሩ።
ሉቃስ 2፡8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
9 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
ስለዚህ ኢየሱስ የተወለደበት ቀን በክረምት ሊሆን አይችልም።
አውግስጦስ ቄሳርም ቢሆን ሰዎች ከባድ ቅዝቃዜ ባለበት ክረምት ውስጥ ረጅም መንገድ አቋርጠው ወደ ትውልድ መንደራቸው ሄደው ግብር እንዲከፍሉ አያዛቸውም።
ስለዚህ ይህንን ሁሉ ስሕተት ማመናችን በቤተክርስቲያን ቄሶችና ፓሰተሮች አማካኝነት እንድንደነዝዝ መደረጋችንን ይመሰክራል።
ይህ ልማዳችን ያመጣብን ባህርይ የፈለግነውን ማሰብ እና አምልኮ ብለን ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንደምንችል ነው፤ እግዚአብሔርም የሚቀበለን ይመስለናል።
እንዲህ አይነቱን ፍጥጥ ያለ ስሕተት ከማመን እግዚአብሔር ይርዳን፤ እኛንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የተሳሳቱ ትምሕርቶች እንቀበል ዘንድ ያሳወሩንን ቄሶችና ፓስተሮች እግዚአብሔር ይርዳቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ሊያስተምሩን ሲገባቸው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪዎች እውነትን ከእግራቸው በታች ረግጠው የአሕዛብ ልማዶችን ተከትለው ሄዱ። ከዚያም ከአሕዛብ ያመጡትን የማይረባ ትምሕርታቸውን ከእነርሱ ውስጥ ለወጣነው ለፕሮቴስታንቶች አወረሱን።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
አሁን የክሪስማስን ውሸት በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጋልጣችሁ ብትናገሩ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተፈላጊነት ታጣላችሁ። ሰዎች ከእውነት ይልቅ የአሕዛብ ልማድ የሞላበትን ምድረ በዳ ይመርጣሉ። ከአሕዛብ ልማድ ይኮርጁና የኢየሱስን ስም ለጥፈውበት የክርስትና ታላቅ በዓል ይሉታል። በጣም ይቀልዳሉ።
ክሪስማስ ግን በጣም እየገነነ የመጣው በ1800 አካባቢ ነው።
ስለዚህ የቤተክርስቲያንን ልማድ መከተል እና በማሕበር ውስጥ ተቀባይነትን ማግኘት እውነትን ከመቀበል በልጦብናል።
እግዚአብሔር ግን ለራሳቸው ጸንተው የሚቆሙ ዓምዶችን እየፈለገ ነው።
እነዚህ ዓምዶች ደግሞ በእውነት ላይ የሚሰነዘሩ የጥላቻ ተቃውሞዎችን ሁሉ መቋቋም አለባቸው።
ልክ ሚሽነሪዎች በብዙ ሃገሮች ውስጥ የደረሰባቸውን ጥላቻና ተቃውሞ ተቋቁመው እንዳለፉት ሁሉ እኛም እውነትን ስነደግፍ የሚቃወሙንን መቋቋም አለብን። ሚሽነሪዎች በብዙ ሥፍራ ተገድለዋል።
ኢየሱስ አዲስ ስም አለው። አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የወደፊት መኖሪያችን ናት።
አንድ ቀን ሁሉም ነገር አዲስ ይሆናል።
ስለዚህ በቤተክርስቲያናችን የቆየውን ያለማመን ዝንባሌ እና የአሕዛብን ልማዶች መተው አለብን።
እንደገና መጀመርና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመከተል መጣር አለብን።
የአሕዛብን ሃሳቦች እየተከተልን መኖራችንን ብንቀጥል የተገለጠውን የእግዚአብሔር እውነት ሳናገኝ እንቀራለን።
ራዕይ 3፡13 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
የስኬት ምስጢር ጆሮ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን ልንከተለው እንችላለን? የቤተክርስቲያንን ስሕተቶች ጸንተን መቃወም እንችላለን?
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
የእግዚአብሔር መንፈስ እኛን ዝነኛ ለማድረግ ወይም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ሊያስገኝልን አይደለም የሚመጣው።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሚመጣው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ሊነግን ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ብቻ ነው ከታላቁ መከራ ሊያድነን የሚችለው።
“የአምላኬ ስም”፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ መሆኑ ለብዙ ሰዎች ቀስ በቀስ እየተገለጠላቸው ነበር።
ከሰማይ የምትወርደው አዲሲቱ የእግዚአብሔር ከተማ፡ ሽልማታችን በዚያች ከተማ ነው ያለው።
ሚሽነሪዎች በዚህ ዓለም ውስጥ የነበራቸውን ምኞት ጥለው በአደጋ እና በመከራ ውስጥ እግዚአብሔርን አገለገሉ። በዚህ ምድር ብዙ አጥተዋል፤ በተለይ በምድር ወገብ አካባቢ ከነበሩ በሽታዎች ጋር ያለ በቂ መድሐኒትና ሕክምና በሌለበት ብዙ ታግለዋል።
ትኩረታቸው ግን ወደፊት የሚጠብቃቸው ክብር ላይ ነበር። ሽልማታቸው በአዲሲቱ ከተማ ውስጥ የተዘጋጀ መኖሪያ ነው። ብድራታቸው ታላቅ መሆኑን ተመልክተው የጊዘውን መከራ ሁሉ ከሚጠብቃቸው ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳልሆነ ቆጥረዋል።
የክርስትና ብርታት ለጊዜ መከራ ውስጥ ማለፍ ካስፈለገም ብዙ ነገር ማጣት ወደፊት ግን ብዙ ማትረፍ ነው።
ዮሐንስ 14፡2 በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
በምድር ላይ ለራሳችን የምንሰራው ምንም ነገር ቢሆን ኢየሱስ ለወደፊት መኖሪያችን ብሎ አሁን እያዘጋጀልን ካለው ጋር ሊወዳደር አይችልም።
ኢየሱስ በአባቱ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ብሏል።
ይህን ስንሰማ ሁል ጊዜ ስለ ትልቅ ቤት ነው የምናስበው።
ምክንያቱም ሰማይ ቤት ምን አይነት መሆኑን ስለማናውቅ ነው።
ሰማይን በምድር ላይ በምናውቃቸው በማናቸውም ነገሮች ልንመስለው አንችልም።
እንደውም አተም እንኳ ምን እንደሚመስል አለማወቃችንን ካሰብን ሰማይ ምን እንደሚመስልማ በፍጹም ልንገምት አንችልም።
1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9 ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
ስለዚህ ሰማይ እኛ በምናባችን ልንገምት ከምንችለው ሁሉ የተለየ ነው የሚሆነው። ስለ ሰማይ ያለን ግምት ሁሉ ተዘቅዝቆ በአፍጢሙ ይደፋል።
ኋላ ስናየው ከገመትነው እጅግ በጣም ልዩ በፍጹም ያሰብነውን የማይመስል ሆኖ እናገኘዋለን። እግዚአብሔር ያሰበልንን ታላቅ ነገር በሐጥያት ምክንያት የተዳከመው አእምሮዋችን ሊገምተው አይችልም።
ኢየሱስ አዲስ ስም አለው።
ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
ማንም ሰው ይህንን ሰም ከጊዜው ቀድሞ ሊያውቀው አይችልም።
በኢየሱስ ዳግም ምጻት የማይሞተውን አካላችንን ስንለብስ ነው ይህ ስም የሚገለጠው።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከመነጠቃችን በፊት ግን ከቀደሙት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስት የሞቱ ቅዱሳን በአዲሱ በማይሞተው አካላቸው ይነሳሉ። ከዚያም ብዙ የዚህ የሚሽነሪዎቹ ወርቃማ ዘመን ጀግኖች ተነስተው እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።
ዳንኤል12፡2 ዳንኤል በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።
3 ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።
ስናያቸው ጥልቅ በሆነ አክብሮት ሰላምታ እንሰጣቸዋለን።
እድሜያቸው ውስጥ በአስደናቂ መሰጠትና በጀግንነት የተሰጣቸውን ሚና በሚገባ ተጫውተዋል።
ስለ እነርሱ ብዙ በተማርን ቁጥር በቆራጥነታቸው ብዙ እንደነቃለን።
“አዲሱን ስሜን እጽፍበታለው”፤ ሙሽራዋ በሰርጓ ቀን በባልዋ ስም ትሰየማለች።
የዚህ ዘመን ቅዱሳን አዲሱን የኢየሱስ ስም በክብር ይጎናጸፉታል። እንዴት በድህነትና በመከራ ኖረው የእውነትን ብርሃን እንዳበሩ ስናስብ በእርግጥ በክርስቶስ አካል ውስጥ ልዩ የሆነ ሥፍራ እንዳላቸው እንረዳለን። እነርሱ በመከራ ወንጌልን ሲሰብኩ ወገኖቻቸው ግን በዚያው ጊዜ ሃገሮችን ይዘርፉና ይበዘብዙ ነበር።
አውሮፓ ውስጥ የነበሩት በብዙ ስሞች የሚጠሩት ቤተክርስቲያኖች ደግሞ አባሎቻቸውን በዘረጉት ሥርዓት አማካኝነት ለራሳቸው ማሰብ የማይችሉ እሥረኞች እያደረጉዋቸው ነበር።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን ማስተማሯን ቀጠለች።
ፖፑ ለራሱ ባለ ሦስት ድርብ ዘውድ ጫነ።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
“ድልም እየነሳ ወጣ”፤ ባሕር ተሻግረው የተመሰረቱት የእስፔይን፣ ፖርቹጋል እና የፈረንሳይ ግዛቶች የሮማ ካቶሊክን እምነት በዓለም ዙርያ ሁሉ አዳረሱት።
ብርሃንና ጨለማ ሁለቱም እየተስፋፉ ነበር።
የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በአሳሳቹ ነጭ ፈረስ ላይ እየጋለበ ይዞር ነበር።
መንፈሱም አክሊል መጫን በሚችል ሰው አማካኝነት ሥጋ ለበሰ።
ዮሐንስ አጋንንታዊ አሰራር በምድር ላይ በስፋት መሰራጨቱን ለመግለጽ እርሻ ላይ የሚሰማሩ አጥፊ የአንበጣ መንጋዎችን ተምሳሌት ይጠቀማል፡-
ራዕይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።
እነዚህ አጋንንት በራሳቸው ላይ ንጉሥ አላቸው። የስሙ ትርጉም በዕብራይስጥ የሞት መልአክ ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጥፊው ነው።
ሐይማኖታዊ አጋንንት የሚንቀሳቀሱት አክሊል በጫነ የቤተክርስቲያን መሪ አማካኝነት ነው፤ እርሱም ፖፑ ነው። ፖፑ የጥልቁ መልአክ ወይም መልእክተኛ ነው። አንዳችም ጽኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም።
ትምሕርቶቹ በሙሉ የተመሰረቱት በማንኛውም ከጥልቁ ጎትቶ በሚያመጣቸው ሃሳቦች ላይ ነው።
ከዚያም እነዚህ እንደ አንበጣ የበዙ አጋንንታዊ ሰራዊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ እንደ ሥላሴ፣ ኤቮልዩሽን፣ ሰባቱ ነጎድጓዶችና የመሳሰሉ ትምሕርቶችን ተቀብለው ለቤተክርስቲያኖቻቸው ራስ ለሆኑ ፓስተሮች በሙሉ ያከፋፍላሉ።
የሲዖል ጥልቅ ጉድጓድ ተከፍቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ አሳሳች ትምሕርት ወደ ምድር እየፈሰሰ ነው።
ራዕይ 9፡10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።
በራዕይ ውስጥ “ጅራት” ማለት እነርሱ የሚያወሩት “ተረት” ማለት ነው።
በጅራታቸው ላይ ያለው መውጊያ ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እምነት ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ያስገባናል ማለት ነው። አሁን እንኳ የታላቁ መከራ ቅምሻ የሚሆን ዘመን ውስጥ ነው የምንኖረው። ዋናው መከራ እስከመጣ ጠብቁ።
በጀርመኒ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን ያለቁበት ሆሎኮውስት የታላቁ መከራ ቅምሻ ነበር።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባለሆኑ ሃሳቦች ላይ ሲመሰርቱ ይህ ራሱ ሞት በሚነግሥበት ጊዜ በይፋ የሚገለጠው የታላቁ መከራ ቅምሻ ነው።
የሰይጣን የመጨረሻ ግቡ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ እንዲጥሉ ማድረግ ነው።
እምነታችንን በራሳችን ሃሳብ እየገነባን ስንሄድ ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱስን ሊያስጥለን ይገፋፋናል።
ነገር ግን ጨለማው እየበረታ በሄደ ቁጥር ብርሃንም እየደመቀ ይሄዳል።
ይህም የሚሆነው ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ለመቆም ስትበረቱ ነው።