ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ክፍል 4



እውነት ተጨማሪ እውነትን ይገልጣል፤ ይህም እውነት በስፋትና በጥልቀት እያደገ ይሄዳል። ነገር ግን ማንኛውም ስሕተት በፊት የምናውቀውን እውነት ያጠፋዋል።

First published on the 16th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ከዚህ በታች የቀረበው ምሳሌ እስከ ጌታ ኢየሱስ ምጻት ድረስ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮችን በሙሉ ይዘግባል።

ማቴዎስ 25፡14 ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሊወጣ ጊዜው ደርሶ ነበር። ከፊቱ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይመጣሉ። 5ቱ መክሊት እና 2ቱ መክሊት ተደምረው 7 መክሊት ስለሚሆኑ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

ደግሞም ሌላ መክሊት አለ። ያም ደግሞ ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር የማይገጥም መክሊት ነው።

ነገር ግን 7+1 = 8፤ እርሱም የአዲስ ሥርዓት ጅማሬ ነው። እግዚአብሔር በታላቁ መከራ ውስጥ ወደ አይሁዶች እንደሚመለስ ያሳያል።

ማቴዎስ ኢየሱስ ንጉስ መሆኑን አጉልቶ ነው የጻፈው፤ ስለዚህ ኢየሱስ በአሕዛብም በአይሁድም ላይ እንደሚነግስ ያሳየናል።

ስለዚህ ይህ ምሳሌ ኢየሱስ በሰማይ የሚቆይበትን ጊዜ እንዲሁም ባልተጠበቀበት ሰዓት መመለሱን ይመለከታል። አይሁድንም አሕዛብንም የሚመለከት ምሳሌ ነው።

እስቲ ምሳሌውን በጥንቃቄ እንመልከት።

ማቴዎስ 25፡15 ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።

አንድ መክሊት የተሰጠው ሰው ከክርስቲያኖች ክፍል አይመደብም።

አንድ መክሊት ዋጋው የ30 ኪሎ ግራም ብር ያህል ነው።

ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ለሰላሳ ብር ነው።

አንድ መክሊት የተሰጠው አገልጋይ አይሁዶችን ይወክላል። እነርሱም መሲሃቸውን በመግደል ክደውታል።

እንደ ሕዝብ እግዚአብሔር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ባለው ዕቅድ ውስጥ ምንም ሚና አይጫወቱም። እውነቱን እንዳያዩ ታውረዋል። እውነቱ ከእነርሱ ተሰውሮ ተቀብሯል። ከቀራንዮ በኋላ መሲህ አላገኙም፤ ምክንያቱም በመጣላቸው ጊዜ ገድለውታል። ከ70 ዓ.ም በኋላ ቤተመቅደስ አልነበራቸውም ምክንያቱም ሮማውያን አፍርሰውባቸዋል። መስዋእት ማቅረብ የሚፈቀድላቸው በቤተመቅደስ ውስጥ ብቻ ነበር። ቤተመቅደሳቸው ከፈረሰባቸው በኋላ መስዋእት ማቅረብ አልቻሉም። ስለዚህ ችግር ውስጥ ገቡ። ነገር ግን ሊጠቀሙበት የማይችሉት የተቀበረ መክሊት ነበራቸው።

መክሊታቸው የጌታ ምጻት ነው። ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ ነበር።

እነርሱ ግን አንቀበልህም አሉት።

ኢየሱስን ለመጨረሻ ጊዜ ያዩት ሲቀበር ነበር፤ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ከሙትን መነሳቱን አላመኑም።

ስለዚህ መክሊታቸውን ቀብረዋል።

ስለ አይሁዶች በኋላ ተመልሰን እናያለን።

ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እያንዳንዳቸው በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለፉት።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከሐዋርያት የተነሳ ሙሉው እውነት ነበራቸው።

የነበራቸውን ሙሉውን እውነት አምስት መክሊት ያህል ነው ብለን እንተምነው።

ሁለት መክሊት (መንፈስ ቅዱስ ተሰፍሮ ሲሰጥ በሁለት መስፈሪያ ብለን እናስብ) የዳነ እና በቅድስና የሚኖር ነውን ይወክላል እንበል።

አንድ ሰው ድኖ ነገር ግን በቅድስና ላይኖር ይችላል። ይህም አንድ መክሊት ነው። የመንፈስ ቅዱስ አንድ መስፈሪያ መጠን።

አንድ ሰው በጌታ ያድግ ዘንድ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገዋል።

ለመዳን የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ያስፈልጋል። በቅድስና መኖር ከእግዚአብሔር ጋር ጠለቅ ያለ ሕብረት ነው። አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት የተስተካከለ የቅድስና ሕይወት ይኖር ዘንድ በውስጡ ራሱን መግዛት የሚያስችለው ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገዋል።

ይህ በተለይ ለሴቶች በጣም ያስፈልጋቸዋል፤ ምክንያቱም ሴቶች ገላቸውን አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ መልበስ፣ ሱሪ መልበስ፣ ጌጣ ጌጥ መጠቀም፣ መዋቢያ ሜካፕ መጠቀም፣ ጸጉራቸውን መቆረጥ በጣም ፈተና ይሆንባቸዋል። ይህንን ሁሉ ፈተና ለመቋቋም ብዙ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልጋቸዋል። እነዚህን ፈተናዎች አሸንፈው የሚኖሩት ሴቶች ግን በአለባበሳቸው ብቻ ሕይወታቸው ዕለት ዕለት ለሰዎች ስብከት ይሆናል።

የእግዚአብሔርን አጠቃላይ ሃሳብ ለመረዳት፤ ሙሉውን እውነት ለማመን ሶስት መክሊት (ሶስት የመንፈስ ቅዱስ መጠን) ያስፈልጋል። ያለፈውን የተሳሳተ እምነት እና የተሳሳተ ትምሕርት ከጭንቅላት ውስጥ ለማስወጣት አንድ መጠን ያስፈልጋል። ዓይንን ለመቀባትና እውነቱን አጥርቶ ለማየት ሌላ መጠን ያስፈልጋል። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመረዳት ደጋግሞ መማር ይጠይቃል።

እውነትን በሙሉ ልብ ለመውደድ እና ሁል ጊዜ በነገር ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አቋም ለመያዝ ድፍረት ይኖር ዘንድ ሶስተኛ መጠን ያስፈልጋል። ይህ ድፍረት ጀግና ሰው ለመሆን አይደለም። ብዙ ሐጥያተኞች ጀግኖች አሉ።

ይህ ድፍረት የሚያስፈልገው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመውደድ እና ያለማቋረጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ለማወቅ ፍላጎት ለማዳበር ነው። ይህ ዓይነቱ አቋም አንድን ሰው በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ሊያደርገው ይችላል። ጓደኞችን ማጣት እን በሰዎች እየተገፉ መኖር ደግሞ ብርታት ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱን ከሰው ሁሉ አመለካከት በላይ ከፍ አድርጎ መቀበል ብርታት ይጠይቃል። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን አመለካከት ልክ ስለ ኢየሱስ እንዳለን አመለካከት ለማድረግ ብርታት ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለበት ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ፊልጵስዩስ 2፡13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

ይህም ለደህንነትን ብለህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመደበቅ ይልቅ የቤተክርስቲያንን ስሕተት በመቃወም ራስህን ችለህ መቆም ነው።

በሰው ንግግር ጥቅስ የተጠመዱትን ፓስተሮች እና ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ትቶ ለኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት መቆም ብዙ ቆራጥነት ይጠይቃል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችን ማስረጃው የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መማር መቻላችን ነው።

ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥

ሰባቱ መቅረዞች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

 

 

በበዓለ ሃምሳ ዕለት መንፈስ ቅዱስ የመቅረዙን መሃከለኛ መብራት ለኮሰ። እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል በሐዋርያት አማካኝነት ለዓለም ቀረበ።

ይህ እውነት ወደ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ተሸጋግሮ ነበር። በዚያ ጊዜ የሰው መሪነት ወደ ቤተክርስቲያን ሾልኮ ገባ። እግዚአብሔርም የሮማ መንግስት ክርስቲያኖችን እንዲያሳድዳቸው እና እንዲበታትናቸው ፈቀደ። ይህም ስደት እና መበታተን አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች በአባላት ቁጥር በጣም ትንሽ እንዲሆኑ እና በስልጣን ፈላጊ ሰዎች ምክንያት ሊመጣ የሚችለው ስሕተት እንዳይበዛ አደረገ። እነዚያ ሁለት ዘመናት የመጀመሪያው ማሕተም ውስጥ የሚገለጠው የአንበሳው ዘመናት ነበሩ።

 

 

ከዚያ በኋላ በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት የሥላሴ ትምሕርት ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ እውነት በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ጠፋ። ቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ መሪ በነበረው በንጉስ ኮንስታንቲን ተጽእኖ ስር ወደቀች፤ እርሱም ተቃውሞዎችን ሁሉ ጸጥ ለማሰኘት ወታደራዊ ኃይልና የጦር መሳሪያ ተጠቀመ። ስትሰደድ የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ከመቶ ዓመታት በኋላ እራሷ አሳዳጅ ሆነች።

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በኒቅያ ጉባኤ ተዳፈነ፤ ይህንንም ተከትሎ ሰው ሰራሽ አመለካከቶች የቤተክርስቲያን ይፋዊ አስተምሕሮ ሆነው ቀሩ።

 

 

በ350 ዓ.ም ፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ በዲሴምበር 25 ይከበር የነበረውን የፀሃይ አምላክ ልደት ኮርጆ ክሪስማስ በማለት እንዲከበር አደረገ።

በየዓመቱ ዓመት በዓል ተብለው እየተደጋገሙ ስለሚከበሩ የበዓል ቀኖች እና ወራት ጳውሎስ አስጠንቅቆ ነበር።

ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?

10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።

በየዓመቱ 25ኛው ቀን እና 12ኛው ወር። “ሰሞን”። የክሪስማስ ሰሞን።

ገላትያ 4፡11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።

ንጉስ ቴዎዶሲየስ በ382 ዓ.ም ፖፕ ዳማስከስን ፖንቲፍ በሚለው ማዕረግ ጠራው፤ ይህም የማዕረግ መጠሪያ ትርጉሙ ፖፑ የባቢሎናውያን ሚስጥራት ሊቀ ካሕናት ሆኗል ማለት ነው።

በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ የሮካ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ እየሰጠ ነበር።

በ606 ዓ.ም ፖፕ ቢኒፌስ ሳልሳዊ እራሱን ዓለማቀፋዊ ጳጳስ፣ የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ራስ ብሎ ሾመ።

በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ ነበር ማለት ይቻላል።

በዚያ ጊዜ እውነተኞቹ ክርስቲያኖች እንኳ ሳይቀሩ በሥላሴ እና ጳጳሱ በየከተማው ላሉት ቤተክርስቲያኖች ራስ መሆኑን አምነው ነበር።

በጣም ብዙ እውነት ጠፍቶ ስለነበረ እግዚአብሔር ከእውነተኞቹ ክርስቲያኖች ይጠባበቅ የነበረው እንዲድኑ እና በቅድስና እንዲኖሩ ብቻ ነበር። ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የተቃወሙ ሰዎች እንደ በሬ ታርደዋል። እነዚህ ሰዎች ቆራጥነታቸው አስደናቂ ነው፤ ነገር ግን እውነት እየጠፋች ነበር። ስለዚህ በ3ኛው እና በ4ኛ የቤተክርስቲያን ዘመናት የነበሩ ክርስቲያኖች መክሊት አልነበራቸውም። የአሕዛብ እና የፖለቲካ ተጽእኖ ቤተክርስቲያንን እየተጫናት ስለነበረ ጥርት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጠፍቶ ነበር።

 

 

በእነዚህ ከባድ የስደት እና የእልቂት ጊዜዎች ውስጥ በጣም ጥቂት የዳኑ እና በቅድስና የኖሩ ሰዎች ብቻ ናቸው የተረፉት።

በራዕይ ምዕራፍ 2 የተገለጹት የመጀመሪያዎቹ አራት የቤተክርስቲያን ዘመናት ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው እውነት እንዴት ቀስ በቀስ እየጠፋባት እንደሄደ ያሳያሉ።

 

 

የዚያን ጊዜ ጀርመኒ ውስጥ ብርቱ ሆኖ የተነሳው ማርቲን ሉተር በዘመኑ የነበረውን ስሕተት ገልብጦ መዳን በእምነት ብቻ የሚለውን እውነት ገለጠው፤ ይህም እንድ አንድ መክሊት ይቆጠራል።

 

 

በስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጆን ዌስሊ እንግሊዝ ውስጥ ቅድስና እና ወንጌልን መስበው ወደ ቤተክርስቲያን እዲመለሱ ምክንያት ሆኗል።

ቅድስና እንደ ሁለተኛው መክሊት ይቆጠራል።

 

 

የሰው ጥበብ በእግዚአብሔር የተባረከ ጊዜ መዳን እና ቅድስና ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው እንዲመጡ አድርጓል።

ማቴዎስ 25፡17 እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።

እግዚአብሔር ስጦታዎቹን በተለያየ መጠን ነው የሚያከፋፍለው።

በያንዳንዱ ዘመን ይገለጥ የነበረው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በተለያየ መጠን ነው የተገለጠው።

ለመዳን እና በቅድስና ለመኖር የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች (ዋጋቸው ሁለተ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ወይም ሁለት መክሊት ሲሆን) በ3ኛው እና በ4ኛው የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሳይጠፉ ቆይተው ነበር፤ ኋላ በ5ኛ እና በ6ኛው ዘመናት መዳን እና ቅድስና ወደ ቤተክርስቲያን ሁሉ በአጠቃላይ ተመልሰው መጥተዋል።

ስለዚህ ሁለቱ መክሊቶች በጥጃው ዘመን እና በሰው ፊት ዘመን ተገልጠው ነበር።

 

 

እነዚህ ሰዎች በብዙ መንገድ ሲመዘኑ ብርቱዎች ነበሩ፤ ደግሞም ብዙ መከራ ተቀብለዋል።

ነገር ግን በሐዋርያት ዘመን ከነበረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ብዙም አላገኙም ምክንያቱም የሥላሴ ትምሕርት በቤተክርስቲያኖች ላይ የስሕተት ምሽግ ሰርቶባቸው ነበር።

እግዚአብሔር ደግሞ ሰዎች ወደ እውነት እንዲመለሱ ይፈልግ ነበር። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ከሰዎች ብርታት የሚበልጥ ዋጋ አለው።

የሰዎች ብርታት አስደናቂ ነው፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዓይን ደግሞ ወደ እውነት መመለስ የሚበልጥ ዋጋ አለው።

በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር ለፊልደልፊያ ቤተክርስቲያን ማለትም በወርቃማው የወንጌል ስርጭት ዘመን ላገለገሉ ሰዎች የተናገራቸውን ልብ በሉ። ፊልደልፊያ ማለት የወንድማማች መዋደድ ነው። ከወንድማማች መዋደድ የሚበልጥ ነገር የለም። ብርቱ የወንጌል ሰባኪዎች በዚያ ዘመን ወንጌልን ለአሕዛብ እየዞሩ ሰብከዋል።

ራዕይ 3፡8 ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።

ይህ የተከፈተ በር የወንጌል ስርጭት በር ነው።

ብዙ ድፍረት ቢኖራቸውም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን “ኃይላቸው ትንሽ” እንደሆነ ነው የተናገረው።

ስለዚህ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የሰው ጀግንነት ብዙም ዋጋ የለውም።

ዋጋ ያለው ነገር ቢኖር የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቅ እና ማሰራጨት ነው።

እነዚህ ወንጌል ሰባኪዎች ብዙ አሕዛብን በወንጌል አሳምነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲድኑ አደረጓቸው። በዚህም ምክንያት ጥሩ መክሊት ተሰጣቸው።

በቅድስና ምክንያት ደግሞ ሁለተኛ መክሊት ተሰጣቸው።

ነገር ግን ሥላሴ የሚለው ሃሳብ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት እንዳይችሉ አደረጋቸው። ስለዚህ በአገልግሎታቸው በጣም ትጉህ ቢኖኑም እንኳ የነበራቸው መክሊት ግን ሁለት ብቻ ነበረ። ይህም በጣም ትንሽ ኃይል ነው።

እግዚአብሔር በሐዋርያት ዘመን የነበረው እውነት ተመልሶ እንዲመጣ ማድረግ ጀምሯል።

 

 

ማቴዎስ 25፡16 አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤

እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን እውነት ለማጽናት እና በቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ውስጥ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያልሆነውን ለመለየት ከቤተክርስቲያን ሰዎች ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተለዋወጠ። እምነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የመመርመር ፍላጎት ስለነበረው የእግዚአብሔር ቃል እውቀቱ በጣም አደገ። ብረት ብረትን ይስላል። እምነቱን በተመለከተ በተከራከረ ቁጥር ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን አወቀ።

እምነታችንን ለሌሎች ለማካፈል እንደ መፈለግ የመሰለ የራሳችንን እምነት የማጠናከሪያ ጥሩ መንገድ የለም። የክርስትና እምነት በአፍ ሲናገሩት እየተጠናከረ ይሄዳል፤ ጸጥ ብለው በውስጥ አፍነው ሲይዙት ግን ይዳከማል።

“የሚበትን ነገር ግን የሚበዛለት አለ።”

ጎተራ ውስጥ ተከማችቶ ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ ዘር የነቀዝ መራቢያ ይሆናል፤ የታረሰ እርሻ ላይ ሲበተን ግን ተመልሶ ሊዘራ የሚችል ዘር እና ዘዲውን የሚመግብ እንጀራ ይሆን ዘንድ ይባዛል።

ሐዋርያት በመቅረዙ መካከል መሃለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነበልባል ለኩሰዋል።

ይህም እውነት የቆየው ሐዋርያት በሕይወት እየኖሩ የመጀመሪያውን ዘመን ክርስቲያኖች በመሩዋቸው ጊዜ ብቻ ነው።

ሐዋርያቱ ከሞቱ በኋላ ቤተክርስቲያን ታውቀው የነበረው እውነት እየመነመነ ጠፋ። በአራተኛው ክፍለ ዘመን አብዛኛው እውነት መንምኖ ጠፋ። እያንዳንዱ ዘመን በነበራቸው እውቀት ነበር እግዚአብሔርን ያገለገሉት።

 

 

በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሙሽራይቱ የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት አጥርቶ ማየት የሚችለውን የንስር መንፈስ መቀበል አለባት። በዚህ መንገድ ብቻ ነው ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት ልንመለስ የምንችለው።

እነርሱ ያመኑትን ስናምን እኛም 5 መክሊት ይኖረናል።

ስለዚህ ሰባተኛው ዘመን ሙሉ በሙሉ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት ቅጂ መሆን አለበት።

ከዚያ በኋላ የመጀመሪያው ዘመን ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ ከእምነታቸው ጋር እንስማማለን። በዚህም መንገድ ከእነርሱ ጋር ሆነን አስር መክሊት ይኖረናል።

ማቴዎስ 25፡19 ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።

“ብዙ ዘመን” ማለት ርዝመቱ በውል ያልታወቀ ጊዜ ነው። ሆን ተብሎ ነው በዚህ ቃል የተነገረው። ኢየሱስ በግልጽ ሊነግረን የፈለገው መች እንደሚመለስ አስልተን ማወቅ እንደማንችል ነው። እኛ ባላሰብነው ሰዓት በድንገት ይመጣል።

ማቴዎስ 25፡20 አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፦ ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

የመጀመሪያው ዘመን ቅዱሳን እውነትን አውቀዋል፤ ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ቅዱሳንም እውነትን ያውቁ ዘንድ መሰረትን ጥለውላቸዋል።

ማቴዎስ 25፡21 ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መረዳት ለቻሉ ሰዎች በሰማይ ታላቅ ሽልማት ይጠብቃቸዋል።

ማቴዎስ 25፡22 ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

የሥላሴ ትምሕርት ቤተክርስቲያንን በተቆጣጠራት ዘመን ውስጥ የኖሩትም ጭምር ተመሳሳይ ሽልማት ይቀበላሉ።

ማቴዎስ 25፡23 ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

ይህ ሽልማት ለባለ 5 መክሊቱ ሰው ተስፋ ከተሰጠው ሽልማት ጋር አንድ ዓይነት ነው።

እያንዳንዱ ዘመን ከሙሽራይቱ አካላት የተወሰነውን ስላበረከተ ከየትኛውም ዘመን የመጣ ቢሆንም ሁሉም በሙሽራይቱ ሙላት ከሚሆነው የጌታ ሙሉ ደስታ ይካፈላሉ።

እያንዳንዱ ዘመን የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፍ ተጋድሏል። እያንዳንዱ ዘመን መንገዱን የሚያበራለት የተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን መጠን አግኝቷል። ዋናው ነገር ለዘመናቸው የተገለጠላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በታማኝነት መታዘዛቸው ነው።

ለእያንዳንዱ ዘመን የትኛውንም ያህል እውነት ቢገለጥ እንኳ በሁሉም ዘመን የነበሩ የሙሽራይቱ አካላት በሰማያዊ ሽልማታቸው በአንድነት ለመደሰት አብረው ነው ከሙታን የሚነሱት።

 

ማቴዎስ 25፡18 አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።

አይሁዶች ኢየሱስ ተቀብሮ እንደነበረ አውቀዋል። ከእርሱ ጋር የነበራቸው ሕብረት እስከዚያ ድረስ ብቻ ነበር።

ማቴዎስ 25፡19 ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።

“ብዙ ዘመን” ማለት ርዝመቱ በውል ያልታወቀ ጊዜ ነው። ሆን ተብሎ ነው በዚህ ቃል የተነገረው። ኢየሱስ በግልጽ ሊነግረን የፈለገው መች እንደሚመለስ አስልተን ማወቅ እንደማንችል ነው። እኛ ባላሰብነው ሰዓት በድንገት ይመጣል። ኢየሱስ ሙሽራይቱን ይዟት ለመሄድ ይመለሳል፤ አይሁዶችም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

ማቴዎስ 25፡24 አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤

ኢየሱስ የምድር አገልግሎቱን የጨረሰው አይሁዶች በእርሱ እንዲያምኑ ለማድረግ በመሞከር ነው፤ በምድር አገልግሎቱ አሕዛብን ዞር ብሎ ባያይም እንኳ ከዚያ በኋላ ግን የአሕዛብን ቤተክርስቲያን አጨደ።

ማቴዎስ 25፡25 ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።

አይሁዶች ኢየሱስ ሞቶ መቀበሩን ቢያውቁም እንኳ ከእርሱ ሊመጣ የሚችለውን ተጽእኖ ይፈራሉ።

ደግሞም በምድር ላይ 1,200 ካቶሊኮች እና 800 ሚሊዮን ፕሮቴስታንቶች አሉ። ስለዚህ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች አሉ። ይህም የዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛው ነው።

አይሁዶች ሞቶ ተቀብሯል የሚሉት ሰው እንዴት ነው ይህ ሁሉ ሕዝብ ሊከተለው የቻለው? ይህም አይሁዶችን በጣም ያስፈራቸዋል። እውነታውን መካድ በጣም ያስቸግራቸዋል። ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር ምንም ጉዳይ እንዲኖራቸው አይፈልጉም።

ከጌታ ዳግም ምጻት በፊት ከቤተክርስቲያን ዘመናት በሙሉ የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን ይነሳሉ።

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ የእውነት ከሙታን መነሳቱን አይሁዶች መካድ አይችሉም።

የተቀበረውን መክሎት ቆፍሮ ማውጣት የሚለው ቃል የሚያመለክተው አይሁዳውያን ኢየሱስ እንደተቀበረባት ወደሚያውቋት ወደ ተስፋይቱ ምድር መመለሳቸውን ነው።

በተጨማሪ ደግሞ ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ሳይፈልጉ እውነት መሆኑን እንደሚቀበሉ ያሳያል።

ደግሞም ሳይወዱ በግዳቸው እርሱ ከአሕዛብ ወገን የሆነችውን ሙሽራይቱን ሊወስዳት መምጣቱን እንደሚያምኑ ያመለክታል።

የአይሁዶች መክሊት የሚወክለው ጌታ በመጀመሪያው ምጻቱ ወደ አይሁዶች መምጣቱን ነው።

ይህ ሁሉ ግን አይሁዶች ለ2,000 ዓመታት ከነበራቸው ሃሳብ ጋር አይስማማም።

“እነሆ መክሊትህ አለህ”።

ኢየሱስ ሙሽራይቱን ሊወስዳት ሲመጣ አይሁዶች ለእርሱ መምጣት እውቅና መስጠት ግድ ይሆንባቸዋል (እርሱ የነበራቸው አንድ መክሊት ነውና) ነገር ግን መክሊቱን መልሰው ይኸውልህ ብለው ይወረውሩለታል።

በድርጊታቸውም “እሺ፤ የተናገርከው እውነትህን መሆኑ ገብቶናል። መምጣትህን እናውቃለን።

ነገር ግን ይህንን መክሊት ስንመልስልህ ከዳግም ምጻትህ ጋር ምንም ጉዳይ እንዲኖረን አንፈልግም ማለታችን ነው” የሚሉ ይመስላሉ።

በዚህም መንገድ እጣ ፈንታቸውን ይወስናሉ።

በጌታ ዳግም ምጻት ጊዜ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ በመነጠቅ ከታላቁ መከራ ስታመልጥ አይሁዶች ጌታ መምጣቱን ያምናሉ ነገር ግን ከምጻቱ ጋር ምንም ንክኪ እንዲኖራቸው አይፈልጉም። ስለዚህ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

አይሁዶች እራሳቸው በሚጠሉዋቸው ሮማውያን አማካኝነት በዓለም ዙርያ ተበታትነው ከቆዩበት ከ2,000 ዓመታት በኋላ ተሰብስበው እንደ አንድ ሕዝብ መንግስት በመመስረታቸው “ሃገር አቀፍ” ትንሳኤን ይወክላሉ።

ዕብራይስጥ የተባለው ቋንቋቸው በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍቶ ነበረ ነገር ግን ከዚያ አልፎ አሁን ከሙታን ተነስቶ በሃገራቸው ውስጥ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ነው።

ማቴዎስ 25፡26 ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?

በመጀመሪያው ምጻቱ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ሕዝብ ነበር የመጣው፤ እነርሱ ግን አንቀበልህም አሉት፤ እርሱም ለራሱ ሙሽራ ከአሕዛብ ዘንድ ሰበሰበ።

ለ2,000 ዓመታት ከአሕዛብ ቤተክርስቲያን ጋር ከቆየ በኋላም በሁለተኛው ምጻቱ ተመሳሳይ ነገር ይሆናል። የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን አልቀበልህም ስላለችው አይሁዳውያን ቢቀበሉት በደስታ ይሰበስባቸዋል። እነርሱ ግን የተሰጣቸውን መክሊት መለሱለት። የዳግም ምጻቱ አካል መሆን አልፈለጉም።

ማቴዎስ 25፡27 ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።

አይሁዶች ወንጌልን ቢገፉም እንደገና ደግሞ እግዚአብሔር የመሰረታት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን አካልም ባይሆኑ እንኳ እግዚአብሔር ግን አይሁዶች ገንዘብ በማበደር ሥራ እንዲሰማሩ እና ለተለያዩ ሕዝቦች የባንክ አስተዳዳሪዎች እንዲሆኑ ፈለገ። ገንዘባቸውን በማጠራቀም፤ በሚያበድሩት ገንዘብ ላይ ወለድ ወይም አራጣ በመቀበል ከ1900 ዓ.ም ጀምሮ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከእሥራኤል ምድር ላይ ሰፋፊ መሬት ለመግዛት ቻሉ። ስለዚህ በ1947 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ሕጋዊ ሃገር እንዲሆኑ እውቅና ሰጧቸው፤ ባደረጉት የድምጽ አሰጣጥ ስነስርዓትም ከተስፋይቱ ምድር ላይ በከፊል ለአይሁዶች ሃገር እንዲሆን ሰጧቸው።

የአይሁዶች ገንዘብ ጥቃት ሲሰነዝሩባቸው የነበሩትን የአረብ ሰራዊት ሁሉ ለማሸነፍ የሚበቃ የጦር መሳሪያ ለመግዛት በቂ ነበር። ዛሬ የአይሁዶች ገንዘብ እሥራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ከሁሉም ሃገሮች የተሻለ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት እና አየር ኃይል እንዲኖራት አብቅቷታል።

ከኒውዮር አክሲዮን ገበያ ውስጥ አብዛኛው ገንዘብ የአይሁዶች በመሆኑ አሜሪካ ለእሥራኤል ከሁሉ የተሻሉ አውሮፕላኖቿን በመስጠት አይሁዶችን ለመደገፍ እንድትገደድ አድርጓታል። በአሁኑ ሰዓት የአይሁዶች አየር ኃይል ለተወሰኑ የአረብ ሃገሮች ከኢራን አየር ኃይል ጥቃት ጥበቃ ያደርጋል፤ ምክንያቱም ኢራን የአይሁዶችን አየር ኃይል በቀጥታ የመውጋት ፍላጎት የላትም። ይህም አገልግሎት በእሥራኤል እና በተወሰኑ የአረብ ሃገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን አድርጓል።

አይሁዶች ገንዘብ ማካበት ላይ ትኩረት ከማድረጋቸው የተነሳ አረቦች ሊያጠፉዋቸው ቢፈልጉም እንኳ ምድራቸውን ይዘው መቆየት ችለዋል።

አይሁዶች በእጃቸው ካለው ነገር ተነስተው ብዙ ገንዘብ በማትረፍ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ አንደኛ ናቸው።

ተላቁን ነብይ መሲሃቸውን ከገደሉ በኋላ 2,000 ዓመታት ሁሉ ገንዘብ በማትረፍ ተጠምደው ነው ያሳለፉት።

አሁን ደግሞ ኢየሱስ በአይሁዳውያን አማካኝነት ትርፍ ማግኘት የእኔ ተራ ነው ብሏል።

መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ተለይተው የተመረጡ 144,000 አይሁዶች አሉ።

አይሁዶች ለ2,000 አንቀበልህም ብለውታል። እርሱም በታላቁ መከራ ውስጥ ኢየሱስን እንደ መሲህ የሚቀበሉ 144,000 አይሁዶችን ለማዳን ተመልሶ ይመጣል።

ኢየሱስ በሙሽራይቱ ዙርያ ለጥበቃ እንደ ግምብ አጥር የሚቆሙ መንፈሳዊ ጃንደረባዎችን እየፈለገ ነው።

ይህን እውነት ለመረዳት ፍንጭ የምናገኘው ከሰማያዊቱ ከተማ ነው፤ ከተማይቱ በዙርያዋ ግምብ አጥር አላት፤ አጥሩም 144 ክንድ ከፍታ አለው።

ራዕይ 21፡17 ቅጥርዋንም ለካ፥ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ፥ እርሱም በመልአክ ልክ።

144 ጥበቃን የሚወክል ቁጥር ነው።

ማቴዎስ 19፡12 በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።

አይሁዶች ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው። አረቦች በቁጥር በጣም ቢበልጧቸውም እንኳ አራት ጊዜ በተከታታይ በጦርነት አሸንፈዋቸዋል።

የሙሽራይቱ አካላት ወደ አርማጌዶን ጦርነት በሚመጡ ሰዓት ጥበቃ ያደርጉላቸው ዘንድ ኢየሱስ ጠንካራ የሆኑ የአይሁድ ጦረኞችን ይፈልጋል።

ነገር ግን ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ነው ለ2,000 ዓመታት አንቀበልህም ብለው ልባቸውን ያደነደኑ አይሁዶችን ሊያድናቸውና ለሙሽራይቱ ታማኝ ጠባቂዎች አድርጎ ሊያሰማራቸው የሚችለው?

እግዚአብሔር አይሁዶችን በግለሰብ ደረጃ እንደማያናግራቸው ልብ በሉ።

እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ጉዳዩን ሲያከናውን እንደ ሕዝብ እያያቸው ነው የሚያከናውነው።

የአሕዛብ ቤተክርስቲያን የእርሱ ሙሽራ ናት፤ የአይሁድ ሕዝብ ግን አገልጋዮቹ ናቸው። እግዚአብሔር ደግሞ ለሙሽራይቱ ጠባቂ አገልጋዮች ይፈልጋል። እነዚህም ሰዎች ከሴት ጋር አንዳችም ንክኪ የሌላቸው ሰዎች ናቸው፤ ሴቶች የቤተክርስቲያኖች ምሳሌ ናቸው።

ማቴዎስ 25፡28 ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤

አይሁድ አንድ መክሊት ነበራቸው። መክሊታቸውም ጌታ ወደ እነርሱ መምጣቱ ነበር። ይህንን መክሊት ቀበሩት፤ ከዚያም ጌታ መቀበሩን ሲያየ የጌታ አካል ተቀብሮ እንዲቀር ፈለጉና ሮማውያን መቃብሩን እንዲያሽጉላቸው ጠየቁ።

የመጀመሪያው የሐዋርያት ዘመን ውስጥ የነበረችው ቤተክርስቲያን በዘመኗ ሙሉውን እውነት ይዛ ነበረ። ስለዚህ ለሐዋርያቱ አምስት መክሊት ተሰጣቸው። የዘመን መጨረሻ ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ እውነት በመጨረሻው ዘመን ላለችው ቤተክርስቲያን ማቅረብ አለበት። በመጨረሻው ዘመን ያለችዋም ሙሽራ አምስት መክሊት ይኖራታል። ሙሽራይቱ ወደ ሙሉው እውነት በተመለሰች ጊዜ ከዚያ በኋላ ትንሳኤው ይፈጸማል።

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር ይወርድና ሙታንን ያስነሳል። በሕይወት ያለችው የመጨረሻ ዘመን ቤተክርስቲያን እንደ ዘር ከተዘራችህ ከመጀመሪያ ዘመን ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ዓይነት ትሆናለች።

64-0119 ሻሎም

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ስለዚህ የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትነ የጻፉት የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ሐዋርያት ውጤታማነታቸውን እጥፍ ድርብ ያደርጉታል ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን ልክ እነርሱን የሚመስሉ ሰዎችን ያፈራሉ። እነዚህም ልክ የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበረችውን ቤተክርስቲያን የሚመስሉ አማኞች ሙሉውን እውነት የያዙ ነው የሚሆኑት።

እግዚአብሔር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሙሉውን እውነት ለመረዳት ነው።

ስለዚህ ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን ከሙታን ተነስታ ከ7ኛው ዘመን ቤተክርስቲያን ሙሽራ ጋር በአንድነት ስትቆም የጌታን ተመልሶ መምጣት የሚወክለው መክሊት ለእነርሱ ይሰጣቸዋል።

በሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው የነበሩ ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ ጌታ ተመልሶ ሲመጣ እነርሱም አብረውን ይቆማሉ።

ነገር ግን ለጌታ መመለስ ዋነኛ መንስኤ የሚሆነው የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን እና የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን በእምነታቸው ፍጹም አንድ ዓይነት ሆነው መገኘታቸው ነው።

ማቴዎስ 19፡30 ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።

የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ዘመን ቅዱሳን ተመሳሳይ ናቸው ምክንያቱም እምነታቸው ፍጹም አንድ ዓይነት ነው።

ማቴዎስ 25፡29 ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያለችዋ ሙሽራ ጥልቅ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የሚኖራት ሲሆን ወንድም ብራንሐም ባስተማረው መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አማካኝት ብዙ ዝርዝር እውቀቶች ሲጨመሩላት የመረዳቷ ጥልቀት እየጨመረ ይሄዳል።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ቢድኑም እንኳ በተሳሳቱ ሃሳቦች አእምሮዋቸው አስተሳሰባቸው እየተበረዘ ሲሄድ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየራቁ ስለሚሄዱ የነበራቸው መሰረታዊ እውቀት ጭምር ይፈርስባቸዋል።

ለምሳሌ ወንድም ብራንሐም የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ነው ብለው በማመን ጀመሩ። ከዚያ በኋላ ግን የእርሱን ንግግሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ ተክተው ተቀበሉ፤ በዚህም እርሱ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው አሉ።

በ1870 ፖፑ አይሳሳትም ተብሎ ታወጀ። አሁን ደግሞ የሜሴጅ ተከታዮች ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የካቶሊክ መንፈስ ተቀብለው ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ፍጹም ሰው ነው ብለው አወጁ። ስለዚህ ከእውነት ርቀው ወደ ስሕተት ውስጥ እየተንሸራተቱ ናቸው። ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የሆነው እንከን የሌለበት እውነት መሆኑን ሊገልጥ ነው የመጣው። እርሱ እራሱ ፍጹም የማይሳሳት ሰው ለመሆን አይደለም የመጣው።

ማቴዎስ 25፡30 የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ነገር ግን የዛሬዎቹም አይሁዶች እስከ አሁን ድረስ መሲሁን ስለ መግደላቸው የሚከፍሉት ዋጋ አለ።

መዳንን ለማግገኝ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

ከአይሁዶች ሁለተ ሶስተኛ የሚሆኑቱ በክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ እና ነፍሰ ገዳይ ሰራዊቱ እጅ ይገደላሉ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ 144,000ዎቹን የተመረጡ አይሁድ ለማዳን ይመለሳል። አይሁዳውያን በቃ ጠፋን ባሉበት ሰዓት አንዳችም የመዳን ተስፋ ባጡበት ሰዓት ኢየሱስ በአስደናቂ ክብር እና ኃይል ተገልጦ ሲያድናቸው እርሱ መሲሁ መሆኑን ያሳምናቸዋል።

አይሁዶች ከክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ጋር የኢኮኖሚ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ ምክንያቱም ፖፑ የአይሁዶችን አክሲዮን ገንዘብ ይፈልጋል። ፖፑ ይህንን ቃልኪዳን ያፈርስና አይሁዶች የኢንቨስትመንት ገንዘባቸውን በሙሉ አጥተው ኪሳራ ውስጥ እንዲወድቁ ያደርጋል። ፍጥረታዊ ገንዘብ የሆነውን “መክሊታቸውን” ማጣታቸው ሌላ አማራጮችን ሁሉ አጥተው ለመንፈሳዊ “መክሊት” ወደ ኢየሱስ እንዲጮሁ ያደርጋቸዋል፤ እርሱም ይመጣና 144,000ዎቹን ያድናቸዋል።

በዚህ ዘግናኝ የእልቂት ወቅት አይሁዶች ኢየሱስ መጥቶ እነርሱን ማዳኑ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባሉ።

አይሁዶች ኢየሱስ ንጉሳቸው መሆኑን መቀበል እንዲችሉ የታላቁ መከራ ሰቆቃ ያስፈልጋቸዋል።

ነገር ግን ከእነርሱ መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ካለቁ በኋላ ነው የቀሩት ሕዝብ ይህንን እውነት የሚገነዘቡት።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

አይሁዶች ከጴንጤናዊ ጲላጦስ ምን እንደጠየቁ አስታውሱ?

ማቴዎስ 27፡25 ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ።

ስለዚህ አይሁዶች ስለ ሐጥያታቸው የፈሰሰውን የመሲሁን ደም አንቀበልም ብለው ለሐጥያታቸው በራሳቸው ደም መክፈልን መረጡ።

ከዚህም የተነሳ መዳናቸውን በራሳቸው ደም ለመግዛት ተገደዱ።

ይህም ምሕረት የተፈቀደላቸው እግዚአብሔር አሳውሯቸው ስለነበረ ነው። ኢየሱስ የመጣበት አመጣጥ በታላቅ ትሕትና እና በብዙ ይቅር ባይነት ነው። በተጨማሪ ደግሞ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ሃሳብ ስላልነበረው ሮማውያን ላይ አንዳችም ጥላቻ የለውም። ይህም አይሁዳውያን እርሱን መቀበል እንዲከብዳቸው አደረገ፤ በተለይም ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ ሲያባርር። ይህ ድርጊቱ በሐይማኖት መሪዎች ዘንድ አሁንስ አበዛው የሚያስብል ነበር። ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ ካባረረ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው ይዘው የገደሉት።

ስለ ኢየሱስ የሰሙት የመጨረሻው ወሬ ሞቶ መቀበሩን ነው ምክንያቱም በትንሳኤው ለማመን እምቢ ብለዋል።

ሮሜ 11፡25 ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤

እግዚአብሔር አይሁዶችን አሳወራቸው። ስለዚህ አይሁዶች ማመካኛ አላቸው።

እግዚአብሔር ግን የሚያድናቸው ስለ እምነታቸው ከተገደሉ ብቻ ነው።

እነርሱ መሲሁን ገድለዋል፤ ስለዚህ እነርሱም መገደል ይጠብቃቸዋል።

ራዕይ 6፡9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።

እነርሱ ያመኑት ብሉይ ኪዳንን ነው፤ ስለ ምስክርነታቸውም ሞተዋል እንጂ ስለ ኢየሱስ ምስክርነት አይደለም የሞቱት።

በሰማያት ያለው የሰማእታት መሰዊያ የተገደሉ አይሁዶች ማረፊያ ነው።

10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።

እነርሱ በቀል ይፈልጋሉ፤ ምክንያቱም አይሁድ ናቸው። ክርስቲያኖች ግን የገደሉዋቸውን ሰዎች ይቅር ይላሉ።

ይህ ጊዜ ልክ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው። እነዚህ አይሁዶች ወደ ምድር ተመልሰው ለ2,000 ዓመታት ሲያሳድዳቸው የቆየውን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ድምጥማጡን ማጥፋት ይፈልጋሉ።

11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።

አምስተኛ ማሕተም። አምስት ጸጋን የሚወክል ቁጥር ነው። እነዚህን የተገደሉ አይሁዶች እግዚአብሔር በጸጋ ነው ያዳናቸው።

እነዚህ አይሁዳውያን ሰማእቶች ጥቂት ጊዜ እንደጠብቁ ተነገራቸው። 144,000ውን አይሁዶች ለመጥራት የሚያስፈልግ የ3½ ዓመታት መከራ አለ። ከዚያ በኋላ እነዚህ አይሁዶች ይገደሉና ከሙታን ተነስተው በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ ለሙሽራይቱ ጥበቃ ያደርጋሉ።

 

ማቴዎስ ምዕራፍ 25 የሚጠናቀቀው ኢየሱስ ወደ ፊት ስለሚሆነው የፍርድ ቀን እየተናገረ ሳለ ነው።

ማቴዎስ 25፡31 የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤

ይህ የፍርድ ቀን ነው። የ1,000 ዓመቱ የሰላም ዘመን ኢየሱስ በምድር ላይ በነገሰ ጊዜ ይጠናቀቃል።

አጠቃላዩ ትንሳኤም ያልፋል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ሰዎች እግዚአብሔር በጎች እንደሆኑ ቆጥሮ የዘላለም ሕይወት እንደሚሰጣቸው ተስፋ በማድረግ በፊቱ ይቆማሉ።

ወደ መንግስተ ሰማያት መግባታቸውን እርግጠኛ መሆን የሚችሉት ሰነፎቹ ቆነጃጅት ብቻ ናቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ድነዋል።

ኢየሱስን እንደ አዳኝ ስለተቀበሉ መንግስተ ሰማያት መግባታቸውን አረጋግጠዋል።

በቤተክርስቲያናቸው አማካኝነት ብዙ ስለተታለሉ የሙሽራይቱ አካል ከመሆን ጎደሉ እንጂ መዳኑንስ ድነዋል።

ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተሰባሰቡት የሙሽራይቱ አካላት እና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የማይሞተውን አካላቸውን ለብሰዋል። ስለዚህ በፍርድ ቀን ለፍርድ አይቀርቡም።

ነገር ግን የተታለሉት ወይም ሰነፎቹ ቆነጃጅት ለፍርድ ይቀርባሉ።

ማቴዎስ 25፡32 አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥

በጎቹ ወደ መንግስተ ሰማያት ሲገቡ ፍየሎቹ ግን ወደ እሳት ባሕር ይገባሉ።

ማቴዎስ 25፡33 በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።

34 ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።

35 ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥

36 ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።

ኢየሱስ አስደናቂ ነገር ተናግሯል። ለሙሽራይቱ አካላት ደግነት አሳይተው ቢሆን ኖሮ፤ ይምራቸው ነበር።

ማቴዎስ 25፡37 ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?

38 እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?

39 ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?

40 ንጉሡም መልሶ፡- እውነት እላችኋለው፣ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

ይህንን ደግነት የፈጸሙት ምንም ሳያውቁ ነው። ሙሽራይቱን እየረዱ መሆናቸውን አላወቁም።

እንዲሁ በመከራ ውስጥ የነበረ ሰው ሲያዩ ከልባቸው አዝነው ለመርዳት መሞከራቸው ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ደግነት ዋጋ አለው።

ማቴዎስ 25፡41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።

“የዘላለም እሳት”። ዘላለማዊ እሳት አይደለም።

ዘላለም የሚለው ቃል መጀመሪያ እና ማቆምያ የሌለውን ዘመን ያመለክታል።

የእሳት ባሕር ዘላለማዊ ከሆነ ሐጥያተኞች በእሳት ባሕር ውስጥ ለመቆየት የዘላለም ሕይወት ሊኖራቸው ያስፈልጋል። ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የክርስቶስ ሕይወት እንደመሆኑ ከእሳት ባሕር የሚያድነን የእርሱ ዘላለማዊ ሕይወት ነው።

ይሁዳ 1፡7 … በዘላለም እሳት እየተቀጡ

እሳቱ ሕይወት የለውም። እሳቱ መበቀል አይችልም።

ዕብራውያን 12፡29 አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።

እሳቱ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ነው በሐጥያት ላይ የበቀል እርምጃ የሚወስደው።

እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ዘላለማዊ እሳት ነው።

የእግዚአብሔር ፍርድ ዘላለማዊ ነው። አንድን ሰው ወደ እሳት ባሕር እንዲገባ ከፈረደበት በኋላ ያ ፍርድ ሊለወጥ አይችልም። ሰውየው ለዘላለም ባይኖርም እንኳ ለዘላለም የተኮነነ ሆኖ ይቀራል።

ሚልክያስ 4፡1 እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡

ሰዎች በእሳት ባሕር ውስጥ ለተወሰነባቸው ዘመን ያህል ይቃጠላሉ፤ የሚቃጠሉበት ጊዜ ርዝመት እንደ ሐጥያታቸው ይወሰናል። በጣም ክፉ የሆኑ ሐጥያተኞች ረዘም ላለ ጊዜ ይቃጠላሉ።

ነገር ግን የቅጣት ዘመናቸው ሲያልቅ ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ይጠፋሉ። ከዚያ በኋላ አይኖሩም።

ኢሳይያስ 66፡24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።

“እሳታቸውም አይጠፋም”። ይህ የሚገልጸው የእሳት ባሕርን ነው። ነበልባሎቹ በምንም ዓይነት ዘዴ ሊጠፉ አይችሉም። ነገር ግን የመጨረሻው ሐጥያተኛ በእሳት ባሕር ውስጥ የተወሰነበትን ቅጣት ተቀብሎ ሲጨርስ እግዚአብሔር ቃል ይናገርና የእሳት ባሕር ይጠፋል፤ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ምንም አገልግሎት የለውም።

የሰዎችን ስቃይ ለማቅለል ተብሎ እሳቱን ማጥፋት አይቻልም። በስተመጨረሻ ግን ከሁሉ የሚረዝመው ቅጣት ሲጠናቀቅ ከረጅም በጣም ረጅም ጊዜ በኋላ የእሳቱ ነበልባሎች በሙሉ ስራቸውን ጨርሰው ይጠፋሉ።

ማቴዎስ 25፡42 ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥

ኢየሱስ በዚህ ክፍል የሚናገረው ቀለል ያሉ የሰብዓዊ ርህራሄ ድርጊቶችን በተመለከተ ነው።

ማቴዎስ 25፡43 ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።

የሙሽራይቱ አካላት በሕይወት ሳሉ ፍየሎቹ እነርሱን ማውገዝ ነበር የወሰዱት እርምጃ። ፍልስፍናቸው እውነትን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ነበር።

ለዚህ ነው ለሙሽራይቱ መሰረታዊ የሆነ ሰብዓዊ ርህራሄ እንኳ ማሳየት ያልቻሉት።

ማቴዎስ 25፡44 እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።

45 ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።

አሁንም ይህ በጣም ቀላል ፈተና ነው። እግዚአብሔር ንሰሃ የማይገቡትን ሐጥያተኞች ይመለከትና አንድ የመጨረሻ ዕድል ይሰጣቸዋል። ከሙሽራዬ አካላት ለአንዳቸው እንኳ ደግነት አሳይተሃልን?

እነዚህ ሰዎች ለዚህ ጥያቂ የሚመልሱት መልስ አሉታዊ ሲሆን ሰብዓዊ ርሕራሄ የሌላቸው ስለሆኑ ይፈረድባቸዋል።

ሙሽራይቱ ላይ የሚያፌዙ እና የሚያሳድዷት ሁሉ በድርጊታቸው ይጸጸታሉ።

ጠላቶቻችሁ በጣም ከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ።

ማቴዎስ 25፡46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

እባካችሁ አስተውሉ። ቅጣቱ ዘላለማዊ ነው። በጣም ረጅም ጊዜ ነው ነገር ግን በስተመጨረሻ ያበቃል።

ሽልማቱ ግን የዘላለም ነው። ፍጻሜ ወይም ማቆምያ የለውም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23