ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ክፍል 3



ማቴዎስ 25፡13 - የሰው ልጅ የሚመጣበትን ሰዓትና ቀን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።

First published on the 16th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ኢየሱሰ የተያዘው ማቴዎስ ምዕራፍ 26 ውስጥ ነው።

ሞቱ፣ ቀብሩ፣ እና ትንሳኤው የመጀመሪያ ምጻቱ ማጠናቀቂያ ናቸው።

ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ስለ ዘመን ፍጻሜ እና የቤተክርስቲያን ታሪክ ነው የሚናገረው ምክንያቱም ኢየሱስ እነዚህን ርዕሶች ከማቴዎስ ምዕራፍ 24 ጀምሮ አንስቷቸዋል።

የማቴዎስ ወንጌል የኢየሱስን የመጀመሪያ ምጻት በተመለከተ ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ ቀጣዮቹ ምዕራፎች ውስጥ ማቴዎስ ትኩረት ሰጥቶ የጻፈው ከዳግም ምጻቱ ፊት ቀድመው ስለሚከናወኑ የዘመን ፍጻሜ ክስተቶች ኢየሱስ የተናገራቸውን ቃሎች ነው።

ማቴዎስ ምዕራፍ 24 አይሁዶችንም አሕዛብንም በተመለከተ ወደፊት ስለሚሆኑ ክስተቶች የተነገረ ትንቢት ነው።

ማቴዎስ ኢየሱስን የይሁዳ አንበሳ፣ የአይሁድ እና የአሕዛብ ንጉስ አድርጎ ይገልጥልናል።

ማቴዎስ ምዕራፍ 24 የሚናገረው በብዛት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናትን ቢሆንም ስለ አይሁዶች ደግሞ ጥቂት ተናግሯል።

ማቴዎስ ኢየሱስ የአሕዛብም የአይሁድም ንጉስ መሆኑን ያሳያል።

በማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ በግልጽ ስለ አሕዛብ ቤተክርስቲያኖች በሚናገሩ ምሳሌዎች ውስጥ እዚህም እዚያም ስለ አይሁድ ጣል ጣል ተደርገው የተነገሩ ቃሎችን ማየት መቻል ያስፈልገናል።

 

ለምሳሌ ሊፈርስ ስለተቃረበው የአይሁዶች ቤተመቅደስ ሲናገር ማቴዎስ የሚከተለውን ብሏል።

ማቴዎስ 24፡2 እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።

በ70 ዓ.ም ይህ ትንቢት በሮማዊው ጀነራል ታይተስ አማካኝነት ተፈጽሟል። አሕዛቦቹ ሮማውያን ከተማይቱን ከበው ቤተመቅደሱን እና ከከመማይቱ ብዙውን ክፍል አፈራረሱ። የጥፋት እርኩሰት የተባሉት ሮማውያኑ ሰራዊት ናቸው። በከተማይቱ ዙርያ እስከ ሃያ ኪሎ ሜትር ድረስ ዛፎችን ቆርጠው ሃገሪቱን ምድረ በዳ አደረጓት።

ከዚያ በኋላ ይህ ሮማዊ አሕዛብ መንፈስ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስን እንደገና በመተርጎም እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚናገሩትን በመለወጥ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ሊያጠፋ ፈለገ። በቤተክርስቲያን ልማዶች ውስጥም እንደ ሥላሴ እና ክሪስማስ የመሳሰሉ የአሕዛብ ልማዶችን አስገብተዋል።

ከቤተክርስቲያኖች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጠፋ።

ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

የጥንቷ አሕዛብ ሮም ቤተመቅደሱን አፈረሰች፤ ከተሃድሶው በኋላ በፖፑ የምትተዳደረው ሮማ ካቶሊክ ደግሞ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ተጽእኖ አጠፋች። በአሁኑ ሰዓት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለበት ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው የሚያምኑ ፕሮቴስታንቶች በጣም ጥቂት ናቸው።

ማቴዎስ 24፡16 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥

ይህ በቀጥታ የሚናገረው ስለ አይሁዶች ነው። አይሁዶች በምድራቸው ላይ 1,100,000 ሕዝብ በታይተስ ሰራዊት ተጨፍጭፎ ካለቀ በኋላ ነበር ወጥተው የተበታተኑት። ሮማውያን ሊጨፈጭፏቸው ሲመጡ ቀድመው ያዩ ከኢየሩሳሌም ወጥተው በዙርያዋ ወዳሉ ተራሮች ለመሸሽ የአጭር ጊዜ ዕድል አግኝተዋል። የተቀሩት ተገደሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ በባርነት የተሸጡት 90,000 አይሁዶችን ተቀላቀሉ።

በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አይሁዶች ወደ ሃገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ፖላንድ ውስጥ በተዘጋጁ የሞት ካምፖች ውስጥ ሒትለር ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን ገድሏል።

“የእነዚያ ወራት መከራ” ተብሎ የተጻፈው በሒትለር የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በመለከተ ነው። ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታላቁ መከራ ምን ሊመስል እንደሚችል ፍንጭ ይሰጠናል።

ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች መሞታቸው ስድስተኛው ማሕተም ሲፈታ ስለሚመጣው ታላቅ መከራ ማስጠንቀቂያ እንድንቀበል ነው።

ስድስት ዋና ዋና የሞት ካምፖች ነበሩ፡- ሸልምኖ፣ ቢዩዤትስ፣ ሶቢቦር፣ ትሬብሊንካ፣ ማይዳኔክ እና ኦውሽዊትዝ-ቢርከናው።

ጦርነቱ ስድስት ዓመታት ነው የፈጀው።

ከዚህ ሁሉ አደጋ በኋላ በ1948 የዳዊት ኮከብ የተባለው ባለ ስድስት ጣቱ ኮበብ ሰንደቅ ዓላማ የሕዝቡ አዲስ ባንዲራ ሆኖ ተውለበለበ። ዳዊት ከ3,000 ዓመታት በፊት በእሥራ የነገሰ ንጉስ ነው።

ይህ ሰንደቅ ዓላማ እሥራኤል ዛሬ ካሉት ሃገሮች ሁሉ የበለጠ ጥንታዊ መሰረት ያላት ሃገር መሆኗን ያሳያል።

በአስገራሚ ሁኔታ የመጀመሪያው የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሆኖ ወደ ስልጣን የወጣው ሰው ራሱ ስሙ ከዳዊት ጋር አንድ ዓይነት ነው፤ ዴቪድ ቤን ጉሪዮን ይባላል።

እሥራኤል እንደገና እንደ ሕዝብ እንደ መንግስት ሆና የተነሳችው ከስድስት ቀናት ጦርነት በኋላ ሲሆን ጦርነቱን በድል የመራው ሰው ስሙ ሞሼ (ሙሴ) ዳያን ይባላል።

ሶስት የአረብ መንግስታትን ለስድስት ቀን ተዋግተው በሰባተኛው ቀን አረፉ። ከ3,500 ዓመታት በፊት ሙሴ ለአይሁድ ሕዝብ ስድስት ቀን ትሰራላችሁ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋላችሁ የሚል ትዕዛዝ ሰጥቷቸው ነበር። አሁንም ይህ መገጣጠም አስገራሚ ነው።

ስለዚህ ከ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ በኋላ እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች እየተመለሰ ነው። ስለዚህ በነዚህ የዘመን መጨረሻ ትንቢቶች ውስጥ አይሁዶች ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

ብርሃናችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው (እርሱም በፀሃይ ይመሰላል) ቤተክርስቲያንም (በጨረቃ ተመስላ) ታንጸባርቀዋለች። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ላይ አይሁዳውያን የተጨፈጨፉበት ጭፍጨፋ ሲያበቃ በጣም የተለያዩ ብዙ አዳዲስ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ታተሙ። ተርጓሚዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም አሉ፤ ሰዎችም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ፍጹም ብርሃን መመልከት ሲያቆሙ ብርሃኑ እየደበዘዘ ሄደ። ቤተክርስቲያን (በጨረቃ የምትመሰለው) ከዚያ ወዲህ በጣም ብዙ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከቶችን ማንጸባረቅ ጀመረች፤ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችም እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ስሕተት እና እርስ በራሱ የሚጋጭ ሃሳብ አለው ብለው እስኪያስቡ ድረስ ተታለሉ። ቤተክርስቲያንም ፍጹም እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ማንጸባረቅ አቆመች።

ሰይጣን ተግቶ ሲሰራ የቆየው ሥራ ዓላማው አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ማንበብ እንዲያቆሙ ወይም እንከን አለበት ብለው እንዲያስቡ ማድረግ ነው።

 

የአስሩ ቆነጃጅት ምሳሌ በሙሽራይቱ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑት ልባሞቹ ቆነጃጅት እና በሰነፎቹ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን የሚነቅፉ ቆነጃጅት መካከል ከጌታ ምጻት በፊት የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ያሳያል።

የእነዚህ ልዩነቶች መንስኤ ምን እንደሆነ መረዳት እንችል ዘንድ በዘመን መጨረሻ አካባቢ ያለውን ሁኔታ በሚገባ መረዳት ያስፈልገናል።

ሙሽራይቱ የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብባ መረዳት እንድትችል የሚበቃ ድምቀት ያለው መብራት ለመለኮስ የሚያገለግል በቂ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት አላት። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ግን የዳኑ እና በቅድስና የሚኖሩ ሰዎች ቢሆኑም እንኳ የተሰወሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ማየት አይችሉም።

 

ጌታ ከዘመን መጨረሻ ጋር የተናገረው ሌላ ምሳሌ በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ተጽፏል።

ሉቃስ ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን አሳይቶ ጽፏል። ስለዚህ እግዚአብሔር የሰውን ተፈጥሮ በስተመጨረሻ እንዴት እንደሚያይ ግልጽ መረዳት እናገኛለን። የዳኑ መልካም ክርስቲያኖች ወደ ጥንቱ የሐዋርያት እምነት የመመለስ ፍላጎት የላቸውም። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የማወቅ ፍላጎት የላቸውም።

ስለዚህ እግዚአብሔር ግፈኞችን ይጠቀማል፤ ምክንያቱም እነርሱ ብቻ ነው በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ጎርፍ የሚፈስሰውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ስሕተት ለመቃወም ድፍረት ያቸው።

ይህ አስገራሚ ምሳሌ የተነገረው ታላቅ የእራት ግብዣ ስላዘጋጀ ሰው ነው፤ ይህም ግብዣ የበጉን ሰርግ እራት ግብዣ ይወክላል። ይህ ምሳሌ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን አቋም እና በተለይም በዘመን መጨረሻ አካባቢ የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለማወቅ ምን ያህል ፍላጎት እንዳጡ ያመለክታል።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ግርግር ተከትለው እንደሚንቀሳቀሱ ሰዎች በፌስቡክ እና በትዊተር ተጠቃሚዎች ተጽእኖ በቀላሉ ይጠመዘዛሉ። ሕዝብ በብዛት ትክክል ነው ብሎ የተቀበለውን እነርሱም በቀላሉ ይቀበላሉ። ሳይንቲስቶች የኤቮልዩሽን ወይም አዝጋሚ ለውጥ እና ቢግ ባንግ በሚሉዋቸው ቲዎሪያቸው አማካኝነት ሰዎች ዘፍጥረት ውስጥ የተጻፈውን እንዳያምኑ ያደርጋሉ። ዓለም እና ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር እየራቁ ሲሄዱ ማሕበራዊ ሚድያዎች ይበልጥ በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ እየወደቁ ይሄዳሉ።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ይባላል። ሎዶቅያውያን እግዚአብሔርን ለማምለክ የራሳቸውን አስተሳሰብ ነው የሚከተሉት። ሎዶቅያ ማለት “የሕዝቡ መብት” ነው። ዛሬም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እግዚአብሔርን እነርሱ በፈለጉት በሚስማማቸው መንገድ የማገልገል መብት እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

እንደፈለጉት መልበስ እና የሚያስደስታቸውን ሁሉ ማድረግ እንደሚችሉ ያምናሉ።

ከዚህም የተነሳ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንከን የሌለው የእውነት ቃል አድርገው የሚቀበሉ ቤተክርስቲያኖች ቁጥራቸው ተመናምኗል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት፤ ደግሞም እርስ በራሱ ይጋጫል የሚል አነጋገር በጣም እየተለመደ መጥቷል።

እስቲ ምሳሌውን እንመልከት፡-

ሉቃስ 14፡16 እርሱ ግን እንዲህ አለው፦ አንድ ሰው ታላቅ እራት አድርጎ ብዙዎችን ጠራ፤

17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን፦ አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ።

እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለመግለጥ መልእክተኛ ነብይ ይልካል። ሚስጥራቱን በተማርን ጊዜ እምነታችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሚሆን ወደ ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንችላለን።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

የነብዩ አገልግሎት በዋነኛነት ለቤተክርስቲያን ስለነበረ የዳኑ ክርስቲያኖች በመጀመሪያ ወደ ሰርጉ የእራት ግብዣ ተጠርተዋል። የዳኑ ክርስቲያኖች ናቸው የነብዩን መጻሕፍት እና በድምጽ የተቀዱ መልእክቶች መጀመሪያ ሊያገኙ የሚችሉት። እግዚአብሔር አስቀድሞ ላልዳኑ ሰዎች ወደ ሰርጉ ጥሪ አይልክም፤ መጀመሪያ ለዳኑ ሰዎች ነው።

እግዚአብሔር ሰዎችን የሚጠራው በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ምንም ነገር አይቀበልም።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ በኩል ሲጠራቸው አጥርተው ይሰማሉ

መጽሐፍ ቅዱስ አድምጡ፤ በዚህ ዘመን የሚጠራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ መጽፍ ቅዱስ ነው።

ወንድም ብራንሐም በሚሰብክ ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው እያለ ይናገራል።

65-0429 የሙሽራይቱ አመራረጥ

የእግዚአብሔር ቃል ነው የክርስቶስን ሙሽራ የሚስባት።

… እውነተኛይቱ ሙሽራ ደግሞ ቃሉን በመጠበቅ የእግዚአብሔርን ትኩረት ትስባለች።

ልብ በሉ ቀላይ (በእግዚአብሔር ውስጥ ያለው) ቀላይን (በሰው ውስጥ ያለውን) ይጠራል።

የተገለጡት የቃሉ ሚስጥራት ሙሽራይቱን ይስቧታል። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ደግሞ ትኩረቱን ወደ ሙሽራይቱ ያደርጋል ምክንያቱም የተገለጠውን ቃል እንደ እውነት ይዘው በፍቅር ይጠብቁታል።

ስለዚህ እግዚአብሔር ከዳኑ ክርስቲያኖች መካከል መጽሐፍ ቅዱስን እንከን የሌለው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል አድርገው የሚቀበሉ ሰዎችን እየፈለገ ነው።

ሉቃስ 14፡18 ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የፊተኛው፦ መሬት ገዝቼአለሁ ወጥቼም ላየው በግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው።

ነገር ግን ከዳኑ ክርስቲያኖች ውስጥ አንዳቸውም ለእግዚአብሔር ጥሪ መልስ መስጠት አይፈልጉም።

በማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ ከተጻፉት ምሳሌዎች ውስጥ በአምስተኛው ምሳሌ እንደተገለጸው ኢየሱስ የገዛው እርሻ ዓለም በሙሉ ነው። ኢየሱስ የሞተው የመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ መገለጥ ለክርስቲያኖች እንዲገለጥላቸው ነው።

ማቴዎስ 13፡44 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።

37 እርሻውም ዓለም ነው፤

ነገር ግን እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ሰው አንድ ቤተክርስቲያን መርጦ ይሄዳል፤ በዚህም ምክንያት እውቀቱ በሚሄድበት ቤተክርስቲያን መሃይምነት የተነሳ ተገድቦ ይቀራል። እነርሱም የሚገዙት ውስኑ እርሻ ይህ ነው። የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ያውቃሉ፤ ነገር ግን ጠለቅ ያሉትን ሚስጥራት አያውቁም፤ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ተጽእኖ የተገደበው እይታቸው ሚስጥራቱን ለመረዳት አያበቃቸውም።

ገንዘባችንን ያወጣንባቸው ነገሮች ላይ ጠበቅ ያለ ክትትል እናደርጋለን። ልባችን ያለበትን ጉዳይ ላይ በቀላሉ አንለቀውም። ነገር ግን ሰው እንደመሆናችን እውቀታችን እና ፍላጎታችን በምናውቀው ነገር ላይ የተወሰነ ነው።

ስለዚህ ውስን የሆነውን እውቀታችንን የእግዚአብሔር እውነታ አድርገን በመቁጠር ራሳችንን እናታልላለን።

በራሳችን የመረጥነውን የቤተክርስቲያን እርሻ በማሳደግ ብቻ እንጠመዳለን እንጂ ቃሉን ለማወቅ በማጥናት አይደለም።

እግዚአብሔር በቃሉ በኩል ነው እኛን የሚጠራን።

እግዚአብሔር የሚፈልገው ቃሉ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ እንድንታዘዝ ነው።

64-0719 የመለከቶች በዓል

ተመልከቱ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንጂ ሌላ ነገር የማታውቅ ቤተክርስቲያን ይህች ናት።

64-0719 የመለከት በዓል

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተጻፈው መሰረት ሚስጥሩ ሁሉ ሲፈጸም የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር በሙሉ ለሙሽራይቱ ይገለጥላታል። ልክ አይደል ወይ? ራዕይ 10።

…የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ በኩሉ ሲናገር አይተናል፤ ሰምተናል

62-0121 ዘርህ የጠላቱን ደጅ ይወርሳል

ከቃሉ ጋር ተጣበቁ፤ እናንተን የሚናገራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ እርሱ ነው።

62-0407 የምጻቱ ምልክቶች

እግዚአብሔር የጠራቸው ብቻ ናቸው የሚሰሙት። “በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ።” ይህ እውነት ነው። የእግዚአብሔርን ድምጽ ያውቃሉ። ድምጹ የሚናገረው ከቃሉ ውስጥ ነው።

 

60-0804 ንስር ጎጆዋን እንደምትበታትን

እውነቴን እነግራችኋለው፤ የእግዚአብሔርን ድምጽ፤ በውስጥ በልባችሁ የሚናገራችሁን ትንሽዬ የዝምታ ድምጽ ማዳመጥ ይጠቅማኋል። ድምጹ የሕዝቡን ትኩረት ይስባል።

… መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆኑን እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ የእኔ ድምጽ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው በመጽፍ ቅዱስ የሚናገረው

የእግዚአብሔር ሃሳብ የተገለጠው በቃሉ አማካኝነት መሆኑን መገንዘብ አለብን።

61-0108 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 3

“በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ።” የእግዚአብሔር ድምጽ ቃሉ ነው

64-0823 ጥያቄዎች እና መልሶች - 1

ቃሉን በሙላቱ የሚቀበሉ ሰዎች እኔ ስለ ሰበክሁት አይደለም የሚቀበሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ነው እንጂ። ቃሉን የሚቀበሉ ሰዎች ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃሉ መስክሮላቸዋል።

62-0318 የተነገረው ቃል እውነተኛው ዘር ነው - 2

አሁን እነዚህ የተናገርኳቸው ነገሮች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማሙ ከሆኑ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይገጥሙ ከሆኑ በሙሉ ስሕተት ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው እና ወንድም ብራንሐም በሚናገረው መካከል ልዩነት ካለ ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረው ነው።

 

63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው

መልእክቱን በሙሉ እመኑ። እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካልተጻፈ ግን አትመኑት።

መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም የወንድም ብራንሐም መገለጦች ትክክለኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ መቻል አለብን።

54-0302 የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ከሙታን መነሳት

መጽሐፍ ቅዱስ ነው በውስጡ ከተጻፉት ቃላት አንድ በአንድ እውነት የሆነው።

 

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው እውነት ስለሆነ ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እንድንርቅ የተቻለውን ያህል ጥረት ያደርጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ በራዕይ ምዕራፍ 3 የሰባተኛው መልአክ ድምጽ እንደሚመጣ ተስፋ ሰጥቶናል።

ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብላችሁ አትሳሳቱ። አዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም።

 

61-1119 ፍጹም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ

ኦህ፤ ከማንቆርቆሪያው ላይ ስለተከደነው ክዳን መከፈት እንናገር፤ አጋንንት ወዲያ ወዲህ ይዞራሉ፤ በክርስትና ስም የዲያብሎስ ኃይላት ይፈነጫሉ፤ ትምሕርት ብለው የሰዎችን ትዕዛዝ ያስተምራሉ፤ የስነመለኮት ኮሌጆች መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ትተዋል

አጋንንት መጽሐፍ ቅዱስን እንድንቃረን የተቻላቸውን ያህል ትግል ያደርጋሉ።

አንድ ነገር ደጋግመን ከሰማነው ሲቆይ እውነት እየመሰለን ይሄዳል።

ሰይጣን በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ያለንን ፍላጎት ያበረታታል። የቤተክርስቲያን ሰዎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን፤ ደግሞም ብንቃረናቸው እንዳያባርሩን እንፈራለን። የቤተክርስቲያን መሪን በቀላሉ እንፈራዋለን።

የቤተክርስቲያን መዋቅር መሪዎችን ይፈጥራል። መሪውም በመዋቅሩ ውስጥ የራሱን አመለካከት ይተክላል።

65-0220 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ስፍራ

ወደዚያ እነርሱ ወደሚሉት ቤተክርስቲያን ካልሄዳችሁ መንግስተ ሰማያት የማትገቡ ይመስላቸዋል። ይህ ስሕተት ነው። እንደዚህ ብሎ ማመን የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆን ነው። እኔም እንዲህ እላለው፡- እንዲህ ዓይነቱን መንፈስ ካመናችሁ ጠፍታችኋል።

ይህም መጥፋታችሁን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ያደረገውን መሻር ነው።

እግዚአብሔር በየትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስሙን አላኖረም። እግዚአብሔር ስሙን ያኖረው በልጂ በክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ያውም እርሱ እና ልጁ አንድ በሆኑ ጊዜ። እግዚአብሔርን ማምለኪያ ትክክለኛው ስፍራ ይህ ነው። ከዚህ ሌላ መሰረት ከዚህ ሌላ ዓለት የለም።

63-0707 ክሱ

… የሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽኖችን እና ቀኖናዎችን እውነተኛነቱ ከተረጋገጠለት ከእግዚአብሔር ቃል በላይ ይወዳሉ።

… እርሱ ቃሉ ነው፤ እነርሱም ቃሉን አንቀበልም አሉ። እንዲያመልጣችሁ የማልፈልገው አንዱ ዋና ነጥብ ይህ ነው፤ እንዲያመልጣችሁ አልፈልግም። እርሱ ቃሉ ነው፤ እርሱን አንቀበልም ባሉ ጊዜ ቃሉን ጭምር ነው አንቀበልም ያሉት። አንቀበልህም ብለው ከገፉት በኋላ በስተመጨረሻ ሰቀሉት። ዛሬም ይህንኑ ነው ያደረጉት፤ የእግዚአብሔርን ቃል አንቀበልም ብለው የራሳቸውን አስተምሕሮ ተቀብለዋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም አሰራር በይፋ በጉባኤያቸው ፊት ሰቅለውታል። በደለኞች ናቸው፤ ስለዚህም በኢየሱስ ስም ከስሻቸዋለው።

… አዎን በአስተምህሮዋቸው አማካኝነት እነደገና ይሰቅሉታል።

… አስተምሕሮዋቸው እና ልማዶቻቸው ከእግዚአብሔር ቃል ርቀው እንዲሄዱ አድርገዋቸዋል።

… ይህ አዲሱ ቀራንዮ ቤተክርስቲያን ናት፤ መቸም ቤተክርስቲያን ብለው ይጠሯታል፤ የተቀደሰች ሥፍራ፣ መድረክ፣ የካቶሎክ መሰዊያ፣ ምስባክ ብለው ይጠሯታል። ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ፕሬስቢተሪያን፣ ሉተራን፣ ፔንቲኮስታል፣ ከሁሉ በላይ የተቀደሱ ሥፍራዎች፤ እነዚህ ናቸው ከባድ ውጋት የሚወጉት። አዲሶቹ ቀራንዮዎች! ቀራንዮ ዛሬ የት ነው? በተቀደሱት ሥፍራዎች ውስጥ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ።

የት ነው እርሱ የተሰቀለው? ፓስተሮች ናቸው የሰቀሉት። እናንተ ግብዞች

… ጎኑን በጦር የተወጋው የት ነው? የት ነበር የተወጋው? ቀራንዮ። ዛሬስ የት ሆኖ ነው እየተወጋ ያለው? በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ

ወንድም ብራንሐም አስጠንቅቆናል።

 

ዋነኛው ስሕተት የሚመጣው መድረክ ላይ ቆመው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን ከሚናገሩ ፓስተሮች ነው።

 

እኛ ግን የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን የሚናገሩትን ንግግር እና የቤተክርስቲያን ልማዶችን መከተል እናበዛለን።

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት አክብሩ ብሎ አልነገረንም፤ እኛ ግን የዓመቱ ታላቅ በዓል አድርገነዋል። ሁሉንም ነገር በራሳችን መንገድ ማድረግ መርጠናል። መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ብሎ በቁምነገር የሚጠይቅ ማነው? “እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ” የማለት ግዴታ ያለብን ይመስለናል፤ ነገር ግን ይህ ልማድ መጽሐፍ ቅዱስ አይደግፈውም።

ክርስትና በቤተክርስቲያኖች መካከል በሚደረግ ፉክክር የተሞላ ሲሆን ገበያ ቦታ ላይ በግድ ግዙ ለማለት የሚደረገውን ዓይነት ጭቅጨቃ ይሆናል። ከፓስተራችሁ ጋር አንድ ጊዜ ብቻ ተቃረኑ እና ከዚያ ወዲያ በቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድ ጊዜ ተቀባይነታችሁ ሲወድቅ ታያላችሁ።

ተደላድላ የተቀመጠችዋ ቤተክርስቲያን በብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሃሳቦች የተሞላች የጊዜ ማሳለፊያ እና መዝናኛ ቦታ ትሆናለች፤ ከዚህም የተነሳ ሕዝቦቿ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን ይተዋሉ።

እግዚአብሔርም ከሐይማኖት ውጭ ይሆናል፤ ስሙም ይረሳል።

በሥላሴ መለኮት ውስጥ ላሉት ሶስት አካላት አንድ ስም ፈልጉላቸው።

ፓስተሩ ሻይ የሚጠጣ ደግ ሰው (ወይም ሴት) ነው፤ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ባለማወቃቸው እንዲሞቃቸውና ተደላድለው እንዲቀመጡ፤ እውነቱን ፈልገው እንዳያገኙ ያባብላቸዋል።

እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን በድንዛዜ ውስጥ ነው ያለው።

ጭፍን የሆነ ፍርሃት ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ጥያቄ እንዳይጠይቁ አፍኖ ይዟቸዋል። ወዲያው ሕዝቡ እንደ ባሪያ ዓይነት እውቀት የጎደለው እንዲሁም መሪዎችን የሚፈራ ደካማ አቋም ይይዛሉ።

ሙሽራይቱ ግን ከምቾት ይልቅ ጽናት እና ብርታትን ትመርጣለች። ከሚያዝናናት ነገር ይልቅ ትክክል እና እውነት የሆነውን ነገር ትመርጣለች።

 

ሉቃስ 14፡19 ሌላውም፦ አምስት ጥምድ በሬዎች ገዝቼአለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው።

በምድራዊ ጉዳዮቼ ላይ ተጠምጃለው ስለዚህ ጊዜ የለኝም። ገንዘብ እንዳያመልጠኝ።

ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በዙፋኑ ዙርያ አራት እንስሳት አሉ።

ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

 

አምስት። ይህ ቁጥር የእግዚአብሔርን ጸጋ ይወክላል። ይህም ለእኛ የሚደረግልን ሰማያዊ ጥበቃ ነው።

አንበሳው በመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት የተሰበከውን እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል።

በሬው ደግሞ የሥላሴ ትምሕርት በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን በጉልበት ሰብሮ በገባ ጊዜ ቀስ በቀስ እየደበዘዘ የጠፋውን የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል።

ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ እየጠለቀች ስትገባ ብዙ ተጨማሪ እውነቶች እየጠፉ ሄዱ።

ይህ ሰው አምስት ጥማድ በሬዎች አሉት።

አምስት ጸጋን የሚወክል ቁጥር ነው። ስለዚህ ይህ ሰው አምኖ በጸጋው ድኗል።

ነገር ግን ሰውየው የተጠመደው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሳይሆን ከቤተክርስቲያኑ ጋር ነው።

አምስት ጥማድ በሬዎች የሚለው ቃል ሰውየው በዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየኖረ ሳለ የጣላቸውን እውነቶች ያመለክታል።

ከዚህ በታች የተጻፉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ስሕተቶችን ተመልከቱ፡-

ሥላሴ። ክሪስማስ። ዲሴምበር 25። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው። የሰባት ዓመታት መከራ። የ1963ቱ ደመና የጌታ ምጻት ነበር። የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር ወርዷል። ለሙሽራይቱ በቀር ከእንግዲህ ምሕረት የለም። ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳተው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች ተናግረዋል።

ሰውየው በሬዎቹን “ሊፈትን” ይሄዳል። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እነዚህን ሐሰተኛ አስተምሕሮዎች ትክክል ናቸው ብለው በክርክር ፈትነው ለማረጋገጥ እንደሞከሩ ናቸው፤ ክርክራቸውም ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም።

ሉቃስ 14፡20 ሌላውም፦ ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው።

ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። እኔ ከቤተክርስቲያን ጋር ተጋብቻለው። ቤተክርስቲያኔ የምትለኝን አደርጋለው። ቤተክርስቲያኔ የምትለኝን አምናለው። እግዚአብሔርን የማገለግለው ቤተክርስቲያኔ ባዘዘችኝ መንገድ ነው። ይህም ለእኔ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው ይበልጥብኛል። ቤተክርስቲያኔ ውስጥ እስከኖርኩ ድረስ ክፉ አይደርስብኝም።

59-0628 በዓለም የተታለለች ቤተክርስቲያን

ትልቅ የሙዚቃ ባንድ ከሌለ እና ሞቅ ያለ ሙዚቃና የጭፈራ አጀብ ከሌለ የጥንቱን ከነፍስ የሆነ የደስታ እምባ የሚያመጣውን፣ መለኮታዊ ፈውስ ይዞ የሚመጣውን፣ የሐዋርያትን ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን የሚመልሰውን፣ ከሙታን የተነሳውንና የዚህ ዘመን መሲህ የሆነውን ክርስቶስን የሚገልጠውን ወንጌል አይፈልጉትም።

63-0112 ተጽእኖ

ይህም ደግሞ ስሕተት ነው። ከዚያም እንጮሃለን፤ እንደንሳለን፤ በልሳን እንናገራለን። ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ክብር በእኛ ላይ ነው እንላለን። ከዚያ በኋላ ነው ይህን ወደመሰለ ነገር የምንሄደው? አንድ ከባድ ችግር አለ ማለት ነው።

ልብ በሉ፤ እኔም እራሴ በእነዚህ ነገሮች አምናለው፤ በመጮህ፣ በልሳን በመናገር፣ እና በመንፈስ በመደነስ አምናለው።

ነገር ግን ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነት የማይቀበለውን ነገር እንዴት ሊታገሰው ይችላል? በቃሉ ውስጥ እንዲሁ ብሎ ተናግሯል። ሴቶቻችን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ለወሲብ የሚቀሰቅስ አለባበስ ይለብሳሉ። ከመድረክ ላይ ደግሞ ማንም ይህን በተመለከተ ተናግሮ አያውቅም። እንዲህም ሆኖ እንጮሃለን፤ እንዘላለን፤ በልሳን እንናገራለን። ለዚህ ነው ይህ ፔንቲኮስታል የተባለ ታላቅ እንቅስቃሴ ወዴትም ፈቀቅ ማለት ያልቻለው፤ በውስጡ አንዳችም ቅንነት የለበትም። ስሜት ብቻ ሆኖ ቀርቷል።

59-0412E ኤልያስ ሆይ ምን ሰማህ

… ትክክለኛና የተሟላ የሆለዊድ መዝናኛ ቡድን ከብዙ የመዝናኛ ፕሮግራም ጋር ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። የአሜሪካ ሕዝብ መዝናናት ይፈልጋል። እውነተኛውን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አይፈልጉም።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ባሉበት ቆመው መቅረት እንጂ መንቀሳቀስን ወደፊት መሄድን አያውቁም። ስለዚህ ተደላድለው ተኝተዋል፤ አንቀላፍተዋል። እንደዚህ በእንቅልፍ ውስጥ ለመቅረት እውር መሆን ይጠይቃል። ሕይወት ሰዎች በጣሏቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ውስጥ ሲቀጥል ሕዝቡ በሌላ ነገር አእምሮዋቸው እንዲጠመድ አድርገው ያስቀሯቸዋል። ሰባኪዎች እውነትን እና ልቦለድን አጠላልፈው ቀባብተው በማቅረብ እውቀትን የማጥፋት ልዩ ችሎታ አላቸው። ሰነፎቹ ቆነጃጅት የዛሬውንና የአሁኑን የግል ፍላጎታቸውን ብቻ ነው የሚያሳድዱት፤ በአንጻሩ ሙሽራይቱ ግን በእግዚአብሔር የረጅም ጊዜ እቅድ እና በፍጻሜው ላይ ታተኩራለች።

የሙሽራይቱ ትኩረት ትንሽ ሆና ግን በየዘመኑ የሚገጥማትን ፈተና ለመቋቋም ዝግኙ መሆን ነው።

ዓለም ሁሉ በድንገት በኮሮና ቫይረስ በተመታበት በዚህ ሰዓት ውስብስብ የሆኑ ሚስጥራት በታላቅ ፍጥነት እየተገለጡ ናቸው። በዓለም ላይ የሚመጡ ክስተቶች መሄድ በሚገባን በትክክለኛ መንገድ እንድንሄድ እያስገደዱን ናቸው። ቤተክርስቲያኖች ሳይቀሩ ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸው ተዘግተው ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔርን እየተናገረን ያለው ምንድነው?

ዓለምን በጥላቻ በተሞላችበት ሰዓት ሙሽራይቱ ብቻዋን መቆምን መልመድ አለባት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ነገር ሲነሳ ልባችን አብሮ መነሳት አለበት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ድር እና ማግ የተዘረጉ እውነቶች አንድ ላይ ተሰባስበው የቃሉን ሸማ መስራት አለባቸው፤ ይህም በእምነት የምንቀበለው የጽድቅ መጎናጸፊያችን ነው። እግዚአብሔርም የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታደርገው እንደነበረው ወደየቤታችን ተመልሰን ሕብረት እንድንጀምር ያደርገናል። ይህም በየቤታችን ተዘግተን የ ZOOM ቴክኖሎጂ ስንጠቀም መሆነ ይችላል።

እውነት ልክ በውሃ ላይ እንደሚንሳፈፍ የበረዶ ስባሪ አንድ አስረኛው ከላይ ይታያል ዘጠኝ አስረኛው ግን ከውሃው ወለል በታች ተደብቋል። ቤተክርስቲያኖች የሚያሳዩን እውነት ጎደሎ እና ጥልቀት የሌለው ነው።

ያለፈ ክብር እና ድንቅ ነገር ለዛሬ ምግብ አይሆንም። ትናንት ባለፈው ነፋስ ኃይል መንቀሳቀስ የሚችል መርከብ የለም።

ዛሬ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ እንደሚፈልግ እናውቃለን ወይ?

ጠለቅ ያሉ እውነቶችን ሲገለጡ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ይቆጣሉ። አለማወቃቸው እንዳይጋለጥባቸው ይፈራሉ። በአስተምሕሮ ላይ በሚደረግ ክርክር ውስጥ ማሸነፍ አደጋው ከቤተክርስቲያን ዘንድ ጥላቻን እና አለመፈለግን ማትረፍ ነው።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት የሚማሩት ከፌስቡክ ነው። በታሪክ ውስጥ ከተነሱ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ትልቁ ፌስቡክ ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ እየተስፋፋ በሄደ መጠን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እየጠቀሱ መከራከር ቀርቷል። አምባገነንነት የሚመሰረተው ሰዎች በጋራ በሚዋሹት ውሸት እና በሚያሰራጯቸው የተሳሳቱ መረጃዎች አማካኝነት ነው። በዚህ መንገድ ፓስተሮች አምባገነን መሪዎች ይሆናሉ።

ስሕተትን እውነት ብለው የሚደግፉ ሰዎች ሁሉ በጋለ ስሜት እና በቁጣ ነው የሚናገሩት። አመለካከታቸውን የሚደግፍ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት ስለማይችሉ በጣም ስሜታዊ ይሆናሉ።

ከወገኖች የሚደረግባቸው ግፊት ሰዎች በቡድን እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፤ ይህም አንድ ሰው በብዙሃኑ ተጽእኖ ስር የመውደቁ ምልክት ነው።

ማስረጃ በሌለበት አመለካከታችን ያለ ድጋፍ ብቻውን ይቀራል።

ጥበብ የጎደላቸውና ዋጋቢስ የሆኑ የዘመኑ ቤተክርስቲያን ውሳኔዎች የእግዚአብሔርን ቃል ከበራቸው ገፍተው አስወጥተዋል።

ቤተክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ያልተጠቀሰበት የንግግር ብዛት ጥበብ ይመስላቸዋል።

ነገር ግን ሁልጊዜ የተሳሳተ መረጃ ወደ ተሳሳተ ውጤት ነው የሚያመራው።

ኢየሱስ ለሕዝቡ ሲናገር እርሱን የተከተሉት ተዓምራት ስላዩ ሳይሆን እንጀራ በነጻ ስለበሉ ነው አላቸው። ምድራዊ ትፍር መፈለግ እንደሌለባቸው ነገራቸው። ከዚያ ይልቅ ከፍ ባሉ መንፈሳዊ እሴቶች ላይ የተመሰረት ሕይወት መፈለግ እንዳለባቸው ነገራቸው።

የሥላሴ ትምሕርት በተንኮል የተቀናበረ አሳሳች ትምሕርት ነው። ሰዎች ሥላሴ ምን እንደሆን በትክክል መረዳት ባይችሉም እንኳ በጣም አስተዋይ የሆኑ እንዲመስላቸው ያደርጋቸዋል።

ጥሩ ስነምግባር የሚገኘው ንቁ ከሆኑ ሰዎች ነው። ሁልጊዜ አስተሳሰባችን እምነታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አብሮ የሚሄድ እንዲሆን ነቅተን መጠበቅ አለብን።

ሙሽራይቱ ለሌሎች ሰዎች የማይገጣጠሙ ከሚመስሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ የሃሳብ ዝምድናዎችን ማየት መቻል እና ጥልቅ እውነቶችን ማግኘት መቻል አለባት።

ዶናልድ ትራምፕ እንደባለጌ ሰው ይነቀፍ ነበር፤ ነገር ግን 1.2 ቢሊዮን ሙስሊሞችን ሳይፈራ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ሰጥቷል።

በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የትኛው ነው? የሰውየው ባለጌነት ወይስ ስለ አይሁድ የተነገረ ትንቢት መፈጸሙ?

የትራምፕ የግል ባሕርይ ግድፈቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ዕቅድ እና ፍጻሜውን ማየት አልቻሉም።

ወደ መጨረሻው ዘመን እየተቃረብን ስንሄድ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ትቶ እየሄደ ነው።

የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የማያውቁት መልካሞቹ የዳኑ ሰነፍ ቆነጃጅት ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ሊገቡ እየተንደረደሩ ናቸው።

በዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ትኩረት አይሁዶችን ወደ እሥራኤል ምድር መልሶ ማምጣት እና ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንድትችል ማድረግ ነው።

ይህንን ዓላማ የሚደግፍ ማንኛውም ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

እግዚአብሔር የተገለጠው ቃሉን መረዳት እንድንችል ይፈልጋል፤ አለዚያ እርሱ ሊፈጽም የሚፈልገው አላማ እንዳይፈጸም እንቅፋት እንሆናለን።

የሰው ንግግር ጥቅስ አሳስተው በመተርጎም በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሒላሪ ታሸንፋለች ብለው ትራምፕን ሲያወግዙ የነበሩ የሜሴጅ ፓስተሮች እግዚአብሔርን እናገለግላለን ብለው የእግዚአብሔርን እቅድ እየተቃወሙ ነበር።

ሉቃስ 14፡21 ባሪያውም ደርሶ ይህን ለጌታው ነገረው፦ በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ ባሪያውን፦ ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች ፈጥነህ ውጣ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ አግባ አለው።

ወንድም ብራንሐም ቤተክርስቲያኖች እርሱ የሚያስተምረውን መገለጥ ቢቃወሙም እንኳ አስደናቂ የፈውስ አገልግሎቶችን አድርጓል።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የዳኑ ክርስቲያኖች ከቃሉ ጋር ጸንተው አይቆዩም።

ከዚህም የተነሳ ሰው የገፋቸውን ሁሉ እግዚአብሔር ይጠራቸዋል። የተሰበሩትን ሁሉ ወደራሱ ይሰበስባል።

ለቤተክርስቲያን የገቢ እድገት አስተዋጽኦ የማያደርጉትን ሁሉ እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፤ ቤተክርስቲያን ግን ትኩረቷን የአባላት ብዛት እና ገንዘብ ላይ አድርጋለች።

ልክ እንደ ሩት እግዚአብሔር የማይፈለጉትን ቃርሚያዎች እየሰበሰበ ነው።

በዚህ የቁስ ዓለም ውስጥ ምንም ነገር ማበርከት የማይችሉትን እርሱ ይፈልጋቸዋል።

ቤተክርስቲያን ሃብታም ሰዎችን እየፈለገች ነው፤ እግዚአብሔር ግን ድሆችን እና የተገፉትን እየፈለገ ነው።

በትላልቅ እና በስኬታማ ቤተክርስቲያኖች አትታለሉ። የጌታ ምጻት ሲደርስ እነርሱን ያልፋቸዋል።

በየቤታቸው ሆነው ሕብረት የሚያደርጉትን ድሆች እና በሰው የተገፉትን ፈልጉ።

ጳውሎስ ስለ ሎዶቅያ ይናገርና ከዚያ በኋላ በቤት ውስጥ ስላለች ቤተክርስቲያን ይጠቅሳል።

ኮሮና ቫይረስ ሰዎች በቤታቸው ተቀምጠው የቤተክርስቲያን አገልግሎቶችን በኢንተርኔት እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።

ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።

እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ያለነውን ሎዶቅያውያን በየቤታችን ተቀምጠን የቤተክርስቲያን አገልግሎት እንድናደርግ እያስገደደን ነው።

በቤት ውስጥ ስላሉ ቤተክርስቲያኖች ተጨማሪ ፍንጭ የምናገኘው ጳውሎስ ለፊሊሞና በጻፈው መልእክት ውስጥ ነው።

ፊሊሞና 1፡1 የክርስቶስ ኢየሱስ እስር ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥

2 ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤

 

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ስሞች ውስጥ የተሰወረ ሚስጥር አለ።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ነበረች።

ይህንን የመጻሕፍት ዝርዝር ተመልከቱ፡-

 

ኤፌሶን

ፊልጵስዩስ

ቆላስይስ

ተሰሎንቄ

ጢሞቴዎስ

ቲቶ

ፊሊሞና

ዕብራውያን

 

ኤፌሶን የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን የምትወክል ከሆነ ፊሊሞና ደግሞ ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።

ስለዚህ ፊሊሞና በቤቱ ውስጥ ስላለች ቤተክርስቲያን መናገሩ አስደናቂ ነው።

ከዚህም በላይ ደግሞ ከሰባተኛው (በፊሊሞና ከተወከለው) የቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ ወንጌሉ በታላቁ መከራ ውስጥ 144,000ውን አይሁዳውያን ለይቶ ለማውጣት ወደ ዕብራውያን ይመለሳል።

ይህም እውነት በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ከተጻፉት ከመጀመሪያዎቹ ስምንት ቁጥሮች ጋር በትክክል ይገጥማል።

 

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን

ሁለተኛው የቤተክርስቲያነ ዘመን። አንበሳው ሐይማኖታዊ አሳሳችነትን ከሚወክለው ነጭ ፈረስ ጋላቢ ጋር ይፋለማል።

ሶስተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን።

አራተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን። በሬው የፖለቲካ ኃይልን ከሚወክለው የቀይ ፈረስ ጋላቢ ጋር ይፋለማል።

አምስተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን።

ስድስተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን። ሰው የታላቅ ገንዘብ አጋንንታዊ አሰራርን ከሚወክለው የጥቁር ፈረስ ጋላቢ ጋር ይፋለማል።

ሰባተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን። የፈረሱ ቀለማት ይዋሃዳሉ። በንስር የተመሰለው ነብይ ይናገራል።

ታላቁ መከራ። ከሶስት የተዋሃዱ ቀለሞች የተፈጠረ ሐመር ፈረስ። የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ እንደ ሞት ሆኖ በፈረሱ እየጋለበ ይመጣል። ሞት መግባት የሚችለው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ በተነጠቀች ጊዜ ሕይወት (መንፈስ ቅዱስ) ምድርን ለቅቆ ከሄደ በኋላ ብቻ ነው።

 

ሉቃስ 14፡22 ባሪያውም፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፥ ገናም ስፍራ አለ አለው።

በተገለጠው ቃሉ መሰረት ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት እምቢ በማለት በታላላቆቹ የበለጸጉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያሉት ሰነፍ ቆነጃጅት ወደ በጉ የሰርግ እራት ግብዣ አይደርሱም።

ስለዚህ ለሌሎች የሚበቃ ቦታ ይኖራል።

ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን አዲስ ስርዓት ያበጃል።

ሉቃስ 14፡23 ጌታውም ባሪያውን፦ ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤

የመጨረሻው ዘመን ሚስጥራት ሲገለጡ ለሙሽራይቱ አካላት እጅግ አስደናቂ ስለሚሆን ተራ የሆኑ የቤተክርስቲያን ትምሕርቶችን ሁሉ እርግፍ አድርገው ጥለው በታላቅ ኃይል ወደ ተገለጠው ቃል እየተሳቡ ይመጣሉ።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችውን እውነት ለማመን ልባቸውን ያዘጋጃሉ፤ ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስት የነበሩ አማኞች ከሙታን ሲነሱ ከእነርሱ ጋር በቀላሉ መግባባት ይችላሉ። የሙሽራይቱ አካላት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት እንዲፈልጉ ከውስጣቸው የሆነ ነገር ይገፋፋቸዋል። በውስጣቸው የሆነ ነገር እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማወቅ እንዲፈልጉ ያነሳሳቸዋል።

አማራጮች ሲጠፉ የመጣብን ቀውስ ተባብሷል ማለት ነው።

በስተመጨረሻ የሙሽራይቱ አካላት በሁኔታዎች የተነሳ ከራሳቸው ሃሳብ ተቃራኒ የሆነ ውሳኤ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥመን የኑሮ ቀውስ ሌላ ጊዜ ልንሄድበት ከምናስበው መንገድ ያስወጣናል።

“ግድ በላቸው።” ይህ የሚያመለክተው በተከታታይ የተለያዩ ቀውሶች ሊገጥሙን እንደሚችሉ ነው።

በ2020 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከቤት መውጣት ስለተከለከለ ክርስቲያኖች ቤታቸውን እንደ ቤተክርስቲያን አድርገው እንዲጠቀሙ አስገድዷቸዋል።

የጥንት ቤተክርስቲያን አማኞች በቤት ውስጥ ነበር የሚሰበሰቡት።

ዊኪፔዲያ፡- ለመጀመሪያ ጊዜ በጥናት የተገኘ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን ሕንጻ በ233 እና 256 መካከል ሲሆን እርሱም መኖሪያ ቤት ነው።

ይህም የጥንቷ ቤተክርስቲያን መሰብሰቢያዋ መኖሪያ ቤት መሆኑን ያሳያል።

የዚህ ዘመን ትኩረት ግን እየተለወጠ በመምጣቱ በትልልቅ ቤተክርስቲያን ሕንጻዎች ውስጥ እንደ ከብት ከሚሰባሰቡ ብዙ ሰዎች አንጻር በኢንተርኔት የሚሰበሰቡ ግለሰቦች እየተገለሉ ናቸው። ትንንሽ በመኖሪያ ቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕብረቶች በአባሎቻቸው መካከል ጠበቅ ያለ ቅርበት አላቸው። በዚህ ዘመን በኢንተርኔት አማካኝነት ትንንሽ ሕብረቶች እና ግለሰቦች በዓለም ዙርያ ሆነው መተባበር ይችላሉ።

ልማዳዊ የሆኑ የቤተክርስቲያን ፖሊሲዎች ዘመን አልፎባቸዋል። ፓስተሩ እንደ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እያስተማረ ሰው ሁሉ በእኔ ሃሳብ የግድ ካልተስማማ ይላል። ቤተክርስቲያን ተመላላሾች የሚሰሙት ስብከት በቤተክርስቲያኒቱ ፍላጎት መሰረት የተቀረጹ ጎደሎ እውነቶችን ነው። ሕይወት ሊኖረው የሚገባውን ባሕርይ በሙሉ ያሟላሉ ግን ቤተክርስቲያን በዘመን መጨረሻ ምን ማመን እና ምን ማድረግ እንዳለባት አያውቁም። የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት እስካሁን ግራ ያጋቧቸዋል፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ባስተማረቻቸው መሰረት ሚስጥራቱን ማወቅ ምንም አይጠቅምም ብለው ያስባሉ።

ቤተክርስቲያኖች ዲኖሚኔሽናዊ ፖሊስ አዘጋጅተዋል። ስለዚህ ከእነርሱ የተለየ ሃሳብ ያሰበ አባል ወዮለት።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ዋና ሃሳባቸው ደረቅ ትርፋቸውነ መታቀፍ ነው። መንፈሳዊ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች አያዩም፤ ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትንም መረዳት አይችሉም። ከመሪው ጋር የሚስማማውን ቡድን ጥበቃ ያደርጉለታል ነገር ግን በሃሳባቸው የማይስማማውን ግለሰብ ይገፉታል። በሃላፊነት ቦታ የተቀመጡ ሰዎች ራሳቸውን ፓስተር ብለው ይጠራሉ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ርቀው ይሄዳሉ፤ ይህንንም ስልጣን ልክ እንደ ጥንታዊ ንግስና በቤተሰብ ከአባት ወደ ልጅ በማስተላለፍ በቤተክርስቲያን ያገኙት ገንዘብ ከአንድ ቤተሰብ እጅ እንዳይወጣ በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።

ኤልያስ ልጅ ነበረውን? ኤልሳእ ልጅ ነበረውን? መጥምቁ ዮሐንስ ልጅ ነበረውን? ልጆች ከመች ወዲህ ነው የስልጣን ተረካቢ የተደረጉት?

ሰዎች የራሳቸውን ሃሳብ ጥቅስ ውስጥ አስገብተው ያነባሉ።

የተደጋገሙ ስሕተቶቻችንን ሳናውተውል ማለፍ በጣም ለምዶብናል።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች በግብዝነትና በትዕቢት ታውረዋል።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ሥራ ሲገባ የተገፉትንና የተጣሉትን ብቁ አይደላችሁም የተባሉትን ይጠራል። እነዚህ ሰዎች በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ አይገጥሙም ምክንያቱም ፓስተሩ የሚለውን ሁሉ ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም። እነዚህ ሰዎች አይፈለጉም ምክንያቱም ፓስተሩን ለመቃወም ደፍረዋል።

የዘመኑ ምልክት ይህ ነው። ሰባኪዎች ትራምፕ ባለጌ ሰው ስለሆነ አይመረጥም ብለው ነበር። በዘመናቸው የተሰጣቸውን ምልክት አላስተዋሉም። እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ መልካም ሰዎች ፈቀቅ ብሏል። በቤተክርስቲያናዊ ልማዳቸው ታስረዋል።

አሁን እግዚአብሔር እንደ ትራምፕ የመሳሰሉ ለሰው ወግ ግድ የሌላቸውን ሰዎች ጠርቶ እየተጠቀመባቸው ነው ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የሰውን አመለካከት አይፈሩም።

እግዚአብሔር የሚፈልገው የማይፈሩ ሰዎችን ነው።

የክርስትና ተሃድሶ ምዕራፍ አውሮፓ ውስጥ ለፍርሃት እምቢ ብሎ በተነሳው በማርቲን ሉተር አማካኝነት ተጀምሮ በጆን ዌስሊ ወደ እንግሊዝ ተሰራጨ። እውነት እንድታንሰራራ ጥረት በማድረግ ጀርመኒ እና እንግሊዝ ዓለምን መርተዋል። ብርቱ የሆኑ ሚሽነሪ የወንጌል ሰባኪዎች ወንጌልን በዓለም ሁሉ አሰራጩ።

የተባበሩት መንግስታት በዲሴምበር 2017 ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ትሁን በሚለው ጥያቄ ላይ ድምጽ ሲሰጡ 9 ሃገሮች ብቻ ሃሳቡን ሲደግፉ 128 ሃገሮች የተቃውሞ ድምጽ ሰጥተዋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወም ሃሳብ መልካም ከሆኑን የምዕራብ አውሮፓ ክርስቲያን ሃገሮች እንዲሁም ከካናዳ ጭምር ድጋፍ አግኝቷል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ቁራንን መረጡ።

ይህ ጊዜው ምን እንደሚመስል የሚጠቁም አስፈሪ ምልክት ነው። ነገር ግን ሰዎች ባለጌ ብለው የሚቆጥሩት አንድ ስርዓት አልበኛ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ሊጠቀምበት የቻለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ባለጌ የተባለውን ሰው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንዲሆን መረጠው።

መልካም ስነ ምግባር አላቸው የተባሉ ፕሬዚዳንቶች እን ክሊንተን፣ ጆርጅ ቡሽ፣ ኦባማ ሁሉ 1.2 ቢሊዮን አረቦችን ፈሩ። ስለዚህ ጨዋ ለመምሰል ብለው ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና አልሰጡም።

እግዚአብሔር ግን ስለ አይሁዳውያን የተነገረው ትንቢት መፈጸሚያ ጊዜው ደርሷል ብሎ ወሰነ።

በእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ውስጥ የትንቢት መፈጸም ሁልጊዜም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

ስለዚህ የብዙ ሰዎችን አመለካከት ጥሶ እግዚአብሔር አንድ ባለጌ የተባለ ሰው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲያሸነፍ ሁኔታዎችን አመቻቸ።

ከዚህም የተነሳ ዛሬ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ሆናለች፤ የጎላን ኮረብታዎችም በእሥራኤል ቁጥጥር ስር ሆነዋል።

ባለጌ ስለተባሉ ሰዎች እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

ሉቃስ 14፡24 እላችኋለሁና፥ ከታደሙት ከእነዚያ ሰዎች አንድ ስንኳ እራቴን አይቀምስም አለው።

ይህ በጣም አስደንጋጭ አነጋገር ነው።

የዳኑ መልካም ክርስቲያኖች ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ያልተረዱ ሁሉ ለሰርጉ የእራት ግብዣ አይጋበዙም።

ክሊንተን፣ ቡሽ፣ እና ኦባማ መልካም ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ምንም መንፈሳዊ ማስተዋል አልነበራቸውም። እየኖሩበት የነበረውን ዘመን አልተረዱም። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆን ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ክብር አጣጥመውታል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈጸም ፍላጎት አልነበራቸውም። አረቦችን ላለማስቆጣት በጣም ፈርተው ነበር።

እሥራኤልን ለአይሁዳውያን የመስጠት የእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ መሳተፍ አልቻሉም፤ ስለዚህ የስልጣን ዘመናቸውን ጨርሰው ዘወር አሉ።

የሚያስፈራው ይህ ነው። የዳኑ ጥሩ የሆኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ለመኖር ፈቃደኛ ያልሆኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተጥለዋል። ከነቤተክርስቲያናቸው በታላቁ መከራ ውስጥ ይጠፋሉ። በክርስቶስ ሆነው ከሞቱት ጋር በአንድነት ይቆዩና ከ1,000 ዓመታት በኋላ ይነሳሉ። በፍርድ ቀን የሚጠብቃቸውን ውርደት ይዋረዳሉ ነገር ግን አምነው ስለ ዳኑ ወደ ጥፋት አይገቡም።

የቤተክርስቲያን ልማዶች እና የመሪዎች ንግግር ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተሳሰብ ያላቸውን የዳኑ ሰዎች አእምሮ ተቆጣጥሯቸዋል።

ክርስቲያኖች አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሉት ቃላት የእግዚአብሔር ስም እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ። ሶስት የማዕረግ መጠሪያዎች እንዴት የአንድ አምላክ ስም ይሆናሉ? ይህ አለማወቅ ነው።

ስለዚህ ሥላሴ ነው ብለው ለሚያስቡት አምላካቸው የሚሆን ስም የላቸውም።

ይህ ምሳሌ በመጨረሻው ዘመን የሚታዩ ሁኔታዎችን ይገልጻል።

የሚገጥሙን ሁኔታዎች ሁሉ ያልተለመዱ እና ያልተጠበቁ ናቸው። በቤተክርስቲያን አግዳሚ ወንበሮች ላይ ተቀምጠን በተደላደልን ጊዜ ሲሞቀን ማሰብ እንደለመድነው ዓይነት ነገር አይደለም የሚሆነው።

ማቴዎስ 25፡13 ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።

በድጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። ስለ ጌታ ምጻት ምንም አናውቅም።

ባልታሰበ ሰዓት ነው ጌታ የሚመጣው።

ቤተክርስቲያን ውስጥ ተደላድለን እንቅልፍ ከምንተኛ ከቤተክርስቲያን ውጭ በእግሮቻችን ጣቶች ጫድ ቆመን መጠባበቅ አለብን።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23