ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ክፍል 2
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት በሩ ይዘጋባቸዋል። እነርሱም ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ። አስቀድሞ መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል እምቢ ብለው ነበር።
First published on the 13th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022በትንሳኤው እና ወደ ሰማይ በመሄዱ መካከል የኢየሱስ አገልግሎት ለደቀመዛሙርቱ ሚስጥር ነበረ። ምን እያደረገ እንደነበረ በውል አላወቁም።
አገልግሎቱ የወሰደው ጊዜ 40 ቀናት ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 1፡3 ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ።
የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንም ከሙታን ተነሱ።
ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
ከትንሳኤው በኋላ ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን ከተማ ውስጥ ለብዙዎች ታዩ።
ማቴዎስ 27፡54 የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ።
በዚህ የምድር መንቀጥቀጥ ጊዜ ልበ ደንዳኖቹ ሮማውያን እንኳ ሳይቀሩ ፈርተው እምነታቸውን መለወጥ ጀመሩ።
ይህ ትንሳኤ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን እንዴት ከሙታን እንደሚነሱ የሚያሳይ ምልክት ነው።
በዚያ ጊዜ ታላቅ የምድር መናወጥ ይሆናል።
ልበ ደንዳና የሆኑ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ቤተክርስቲያናቸው ብዙ እንዳታለሉዋቸው በዚያን ጊዜ ይገነዘባሉ፤ ከዚያም እምነታቸውን ያስተካክላሉ።
የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት ከተነሱ በኋላ ለብዙ ሰዎች ይታያሉ።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት በቤተክርስቲያናቸው እምነት የተነሳ ስተዋል፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኖች እንደ ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣ ፖፑ (እና ዊልያም ብራንሐም) የማይሳሳቱ ሰዎች ናቸው ወዘተ የሚሉ ብዙ የሮማ ካቶሊክ እምነቶችን ያራምዳሉ።
ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን ሲገለጡ በታላቅ የምድር መናወጥ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የተደናገጡት ሰነፍ ቆነጃጅት እምነታቸውን እንደገና ይፈትሻሉ። እምነታቸውን ለማስተካከል የ40 ቀናት ጊዜ ብቻ ይኖራቸዋል፤ በዚህም ሒደት ውስጥ ወደ ስሕተት የመሯቸው ፓስተሮች ሊያግዟቸው አይችሉም። ስለዚህ እንደ ምንም ብለው ወደ ልባሞቹ ቆነጃጅት ይሄዱና እርዳታ ይለምናሉ ምክንያቱም ልባሞቹ ቆነጃጅት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚችሉ ብቸኛ ሰዎች ናቸው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችን ማስረጃ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንዴት አድርገን መረዳት እንደምንችል እርሱ ራሱ እኛን ማስተማር መቻሉ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።
8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
ሙሽራይቱን ከሰነፎቹ ቆነጃጅት የሚለያት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ የምታውቅበት እውቀት ነው። የተለያዩ ጥቅሶችን ማገጣጠም የሚቻልበት ጥበብ በዚህም የእግዚአብሔርን ሃሳብ በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ማስተዋል የሚቻልበት ጥበብ ነው ሙሽራይቱን ከሰነፎቹ ቆነጃጅት የሚለያት።
ትንሳኤው ከተፈጸመ በኋላ ሰባቱ ነጎጓዶች በሕይወት ላለችው ለሙሽራይቱ ስጋዊ አካላቸውን እንዴት ወደ ዘላለማዊ አካል እንደሚለውጡ ያሳዩዋቸዋል። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሰባቱ ነጎድጓዶች ለሙሽራይቱ ወደ ሰማይ የምትነጠቅበትን እምነት ሊሰጧት የሚችሉት። አሁን በለበስነው በዚህ የስጋ እና ደም አካል ውስጥ ሆነን መነጠቅ አንችልም።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
ሙሽራይቱ መነቃቃትን ተለማምዳ አታውቅም። አያችሁ? መነቃቃት ሆኖ አያውቅም፤ ሙሽራይቱን ሊቀሰቅሳት የሚችል የእግዚአብሔር መገለጥ አልመጣም። አያችሁ? መነቃቃት እስኪመጣ እየጠበቅን ነን። ሙሽራይቱ እንድ ገና ከእንቅልፏ እንድትነቃ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ማሰማት አለባቸው። እርሱም መነቃቃትን ይልካል። ተስፋ ሰጥቶናል። እንግዲህ አሁን ልብ በሉ። በዚህ ሰዓት ሞታለች።
በአባልነት የታቀፋችሁባት ሜሴጅ ቤተክርስቲያን ለእግዚአብሔር ቅናት ያላት ይመስላችኋል። እውነታው ግን ቤተክርስቲያኒቱ ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ሆና በመንፈስ ሙት መሆኗ ነው።
ከእንቅልፏ እንድትባንን ቅስቀሳ ያስፈልጋታል።
ወንድም ብራንሐም ስለ “ሰባቱ የማይታወቁ ነጎድጓዶች” ተናግሯል።
ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደሆኑ የምታውቁ ከመሰላችሁ በጣም ተታልላችኋል ማለት ነው። ሰነፍ ቆነጃጅት ሆናችኋል።
ልብ በሉ። እኩለ ሌሊት ላይ ሁሉንም ሰነፎቹን ልባሞቹንም ቆነጃጅት የሚቀሰቅስ ድምጽ ይመጣል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም። አሆን፤ እውነት ነው። እኔም ደግሞ በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ እንዴት እንደምትዘጋጅ እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምትቀበል ይገለጥላታል። ምክንያቱም አሁን ባለን እምነት መነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ መጨመር ወደፊት መግፋት አለብን፤ ለመለኮታዊ ፈውስ እንኳ የሚበቃ እምነት የለንም።
ከመቅጽፈት የምንለወጥበት በቂ እምነት ሊኖረን ይገባል
ነገር ግን አስቡ፤ አሁን ይህንን እየጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ሌሎቹን ማለትም ሰባቱን ነጎድጓዶች ሊጽፍ ሲያስብ “አትጻፍ” አለው። ያየውን ሁሉ እንዲጽፍ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ባሰሙ ጊዜ እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- “እነዚህን አትጻፋቸው።” ሚስጥራት ናቸው። ምን እንደሆኑ እስከ አሁን ድረስ አናውቅም፤ ነገር ግን ኋላ በጊዜያቸው ይገለጣሉ ብዬ አምናለው። ሲገለጡም ቤተክርስቲያን ከዚህ ዓለም የምትወጣበት ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት እና ጸጋ ይሰጧታል። እስከዚያው ድረስ በተገለጠልን እን በተረዳነው እንመላለሳለን፤ ባለፉት ዘመናት ውስጥ ሁሉን አይተናል። የእግዚአብሔርን ሚስጥራት አይተናል። በመጨረሻው ዘመን ሙሽራይቱ እንዴት ባለ ታላቅ ክብር እንደምትሰበሰብ ተመልክተናል። ይህም ሁሉ ሆኖ ግን እስካሁንም ድረስ ልናውቅ የማንችለው ነገር አለ። ሌላ ነገር አለ። ነገር ግን እነዚህ ሚስጥራት መገለጥ ሲጀምሩ … እግዚአብሔር እንዲህ አለ፡- “ቆይ፤ አሁን አትጻፋቸው። ጥቂት ጠብቅ። በዚያ ቀን እኔ እገልጠዋለው፤ ስለዚህ አሁን አትጻፈው፤ ምክንያቱም የሚያነቡት ይንገዳገዱበታል። ተወው፤ አትጻፈው። (አያችሁ?) ነገር ግን በዚያ ቀን ሊገለጥ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኔ እገልጠዋለው።”
ሰባቱ ነጎድጓዶች መልእክታቸውን የሰማን ጊዜ ያንገዳግደናል።
በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ስለሚሆንብን ቶሎ ብለን መላመድ ያስፈልገናል።
በእጃችን ያሉትን ፍንጮን በመጠቀም የነጎድጓዶቹን መልእክት ለመረዳት በመሞከር ብዙውን ጊዜያችንን ማሳለፍ አለብን። ስለዚህ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ጋር ቁጭ ብሎ መሰረታዊ ስሕተቶቻቸውን ለመተንተን በቂ ጊዜ አይኖርም። እውነትን የማግኘት ዕድላቸውን መጠቀም ከመቻላቸው በፊት መጀመሪያ መሰረታዊ ስሕተቶቻቸውን ማስወገድ ያስፈልጋቸዋል። ሁለቱንም ማድረጊያ ጊዜ ደግሞ አይኖርም።
የትምሕርት ዝናብ በ1947 የወንድም ብራንሐም ስብከቶች በድምጽ ሲቀዱ ነው የተጀመረው። እኛም ሁሉጊዜ መማራችንን ስለምንቀጥል ይህ የትምሕርት ዝናብ እስከ ጌታ ምጻት ድረስ አይቋረጥም።
ኢዩኤል 2፡23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።
ስለዚህ የመከሩ ዝናብ ወይም ኋለኛው ዝናብ ከመጀመሪያው ዝናብ ወይም ከትምሕርት ዝናብ ጋር ይደራረባል።
ስለዚህ ለሙሽራይቱ የማይሞተውን አካል እንድትለብስ የሚያስችላት ኋለኛው ዝናብ የሚዘንበው ከትንሳኤ እና ከመነጠቅ መካከል በሚያልፉት 40 ቀናት ውስጥ ነው (በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ትነጠቃለች)።
ይህ ነውጠኛ እና ግራ የሚያጋባ ጊዜ ነው የሚሆነው።
የሙሽራይቱ አካላት ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች በሚሰሙ ጊዜ በመልእክታቸው ይንገዳገዳሉ።
ቤተክርስቲያን ተመላላሾቹ ሰነፍ ቆነጃጅት የተማሩትን ስሕተት ከአእምሮዋቸው ለማስወገድ እና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመማር በጥድፊያ ሲዋከቡ ካሉበት በንነው ይጠፋሉ። ስሕተታቸውን ማስወገድ እና እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር የመማሩ ሂደት ከ40 ቀናት በላይ ይፈጅባቸዋል።
ነገር ግን በዚያን ቀን የሚማሩት ያ ዕውቀት በታላቁ መከራ ውስጥ ለሚሰራጨው ስሕተት ያዘጋጃቸዋል። በዚህም መንገድ በቂ እውነት ተምረው ስለሚጠብቁ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ እና በመከራው ውስጥ በሚፈጸመው እልቂት እንዲሁም የደም መፋሰስ ውስጥ በሚያልፉ ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚ በሆነው ፖፕ እና በቤተክርስቲያኖች አይታለሉም። በዚያን ጊዜ የተበላሸውን የቤተክርስቲያኖች አሰራርና የተሳሳተ ትምሕርት በመቃወም ጸንተው ይቆማሉ፤ በዚህም ምክንያት ይገደላሉ። ይህ ዓይነቱ ወኔ ቀድሞ ቢኖራቸው ኖሮ፤ ዛሬውኑ በዘመናችን ፓስተሮቻቸውን ለመቃወም ድፍረት ቢያገኙ መልካም ነበር። ይህ ነው በግላቸው የሚጸጸቱበት ነገር። ማናችንም ብንሆን ተሞኝተን እንደነበረ መስማት አንፈልግም፤ በተለይም በምንወዳቸው እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው ብለን በምናምናቸው ሰዎች መታለላችንን መስማት አንፈልግም።
ከትንሳኤ በኋላ የሚመጣው ታላቅ ክስተት የሰባቱ ነጎድጓዶች መገለጥ ነው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች የተጠቀሱበትን ራዕይ ምዕራፍ 10 እንመልከት።
ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ብርቱው መልአክ ወደ ምድር ይወርድና ሙታንን ያስነሳል፤ ከዚያም በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ይነገራሉ።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ነገር ግን ይህ ከምድር አልመጣም። እርሱ የመጣው ከሰማይ ነው ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመዋል። ሚስጥሩም በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ዘመን አይኖርም” በዚያን ጊዜም ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።
መልአኩ ወደ ምድር የሚመጣው ሚስጥራቱ ስለተፈጸሙ እና የሙሽራይቱ አካላት ሚስጥራቱን ተረድተው ስለጨረሱ ነው።
መልአኩ የሚወርደው ሚስጥራቱን ለመግለጥ አይደለም።
ሙሽራይቱ የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ከተረዳች በኋላ ኢየሱስ እንደ መላእክት አለቃ ሆኖ ሙታንን ለማስነሳት ይወርዳል።
የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ሙታን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ተቀብረው ከቆዩበት ከምድር እና ከባሕር ውስጥ ሊያስነሳቸው ወደ ምድር ይወርዳል።
64-0119 ሻሎም
ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
የዚህ የመላእክት አለቃ ድምጽ ሙታንን ካስነሳቸው በኋላ ቀጥሎ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
ሙሽራይቱ መነቃቃትን ተለማምዳ አታውቅም። አያችሁ? መነቃቃት ሆኖ አያውቅም፤ ሙሽራይቱን ሊቀሰቅሳት የሚችል የእግዚአብሔር መገለጥ አልመጣም። አያችሁ? መነቃቃት እስኪመጣ እየጠበቅን ነን። ሙሽራይቱ እንድ ገና ከእንቅልፏ እንድትነቃ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ማሰማት አለባቸው። እርሱም መነቃቃትን ይልካል። ተስፋ ሰጥቶናል። እንግዲህ አሁን ልብ በሉ። በዚህ ሰዓት ሞታለች።
“ይልከዋል።” ይህ ቃል የሚናገረው ስለ ወደፊቱ ነው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት ሙሽራይቱን ለመቀስቀስ ነው፤ የሙሽራይቱ አካላት በቂ ዘይት ስላላቸው ተነስተው መብራታቸውን በማብራት ለመረዳት ከባድ የሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላት ብርሃን አብርተው ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት ይችላሉ።
መንፈስ ቅዱስ የሚያስፈልገን በዋነኛነት ለዚህ ዓላማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ያልተጻፉ ነገር ግን የተደበቁ ፍንጮችን ፈልገን ማግኘት አለብን።
የዚህ ዘመን ትልቁ ስሕተት ወንድም ብራንሐምን የማይሳሳተውና ፍጹሙ “የእግዚአብሔር ድምጽ” ነው ብሎ ከፍ ከፍ ማድረግ ነው።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስሙ እራሱ መለከት የሚል ትርጉም ያለው በመሆኑ “የእግዚአብሔር መለከት” ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ፍንጭ ይሰጠናል፤ ማለትም ወደ መጨረሻው ቀርበናል። እርሱ ፕሬዚዳንት መሆኑ መጨረሻው ስለ መቅረቡ ትልቅ ፍንጭ ነው።
በተለይም ደግሞ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና መስጠቱ ትልቅ ምልክት ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተነሱ መሪዎች መካከል ስለ ኢየሩሳሌም ጉዳይ የአረቦችን አክራሪነት በመቃወም ያለ ምንም ፍርሃት የተናገረ ብቸኛው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ነው።
የሜሴጅ ፓስተሮች ግን እርሱ የ2016ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደማያሸንፍ በልበ ሙሉነት ተንብየው ነበር። እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሃሳብ እንደማያውቁ በጣም ግልጽ ነው።
የእግዚአብሔር ድምጽ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስንም እንደማያውቁ በጣም ግልጽ ነው።
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ በኩል ሲጠራቸው በግልጽ ይሰማሉ
… የእግዚአብሔር ድምጽ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዘመን ሲጠራችሁ ልብ ብላችሁ አድምጡ።
ዕድሜ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ አይሁዳውያን በይፋ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ወደ ጥንታዊቷ ዋናከተማቸው ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ችለዋል፤ በዚያችም ከተማ መሲሁ ወደ እነርሱ ይመጣል።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ዓ.ም ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና በሰጠ ጊዜ ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈው ትንቢት መፈጸሙን ተመልከቱ።
በዚህ ቃል ውስጥ እግዚአብሔር ተበታትነው የነበሩትን የአይሁድ ሕዝብ መልሶ እንደሚሰበስባቸውና የእሥራኤል ዋና ከተማ ወደሆነችው ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚያመጣቸው ተስፋ ይሰጣል።
ዘካርያስ 8፡7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፤
8 አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ትደግፍ የነበረችው ከተማ ሰዶም ከመጥፋቷ በፊት ሶስት መልእክተኞች ወደ አብራሐም መጡ።
ጴንጤቆስጤያዊ ወዳልሆኑት ቤተክርስቲያኖች ቢሊ ግራሐም ተላከ፤ ወደ ጴንጤቆስጤያዊ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ ኦራል ሮበርትስ ተላከ፤ ወደ ሙሽራይቱ ደግሞ ዊልያም ብራንሐም ተላከ።
እነርሱ ከሄዱ በኋላ እሳቱ ወደቀ። ከሶስቱ የመጨረሻውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው ወንጌል ሰባኪ ቢሊ ግራሐም ከዚህ ምድር ተለይቶ ሄዷል። ይህም የመጨረሻው ዘመን ላይ ለመሆናችን ተጨማሪ ምልክት ነው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ምን እንደሚፈጠር አናውቅም፤ ምክንያቱም ስለ እነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዝርዝር አልተጻፈም።
ነገር ግን ለጌታ ምጻት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንዳለብን የሚመሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍንጮች አሉ። ልባሞቹ ቆነጃጅት ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው የሚያጠኑት እነዚህን በግልጽ ያልተጻፉ ነገር ግን በሆነ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውረው የሚገኙ ሚስጥራት ፈልገው ለማግኘት በመሞከር ነው። ከዚህም የተነሳ ለሰነፎቹ ቆነጃጅት መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን የሚያስተምሩበት ጊዜ አይኖራቸውም።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ቃሉ መጥቷል። እነዚህ ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ሲያልቁ “በውስጣችህ የተጻፈው መጽሐፍ” ያን ጊዜ ይፈጸማል። እስቲ ደግሜ ላንብበውና ሁላችሁም ሰምታችሁ እርግጠኛ ሁኑ። አሁን ተመልከቱ።
… እነዚህ ማሕተሞች ከመጽሐፉ በጀርባ በኩል ነው ያሉት። “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በተሰማ ጊዜ በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉት ሚስጥራት በሙሉ ይፈጸማሉ።”
ወንድም ብራንሐም ማድረግ የሚችለው ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል እንድትነጠቅ የሚያስችሏትን የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገልጦ ማስተማር ብቻ ነው።
ራዕይ 10፡7 … ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ያለብን አሁን ነው።
የሜሴጅ ሰባኪዎች በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ትራምፕን እየተቃወሙ እንደተናገሩ በዚህም እግዚአብሔርን እንደተቃወሙ ሁሉ እኛም ያልተለመዱትን የሰባቱን ነጎድጓዶች ክስተት እንዳንቃወም ከአሁኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆን መዘጋጀት አለብን።
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
መጽሐፉ ተከፍቷል።
ሚስጥራቱ በሙሉ ለሙሽራይቱ አካላት ተገልጠዋል። በዚህ ዘመን እየተፈጸመ ያለው ነገር ይህ ነው። ግለሰቦች የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል እውነት ለማግኘት ኢንተርኔትን እየበረበሩ ነው።
እያንዳንዱ የሙሽራይቱ አካል የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከተረዳ በኋላ ብቻ ነው ኢየሱስ እንደ መላእከት አለቃ ሆኖ የሚወርደው።
ብርቱው መልአክ ሲወርድ እግሮቹ በምድር እና በባሕር ላይ ነው የሚቆሙት ምክንያቱም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ ቅዱሳን የተቀበሩት በምድር እና በባሕር ውስጥ ነው።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
ደመቅ ባለ ቀለም የተጻፉት (ሁለቱም) ሐረጎች ሁለቱም የመልአኩን ድርጊት የሚገልጹ ሲሆኑ ከትንሳኤ ጋር የተያያዙ ናቸው።
ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።
በመስቀል ላይ ሆኖ ሐሙስ ዕለት “በጮኸ ጊዜ” የሚለው ቃል የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ከመነሳታቸው ጋር የተያያዘ ነው፤ ይህም ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሳ ወዲያው ተፈጽሟል።
ልብ በሉ። ኢየሱስ የሞተው ሐሙስ ዕለት ነው ምክንያቱም በመቃብር ውስጥ ያደረው ሶስት ሌሊት ነው።
እሑድ ጠዋት ከሙታን ተነሳ። የአይሁድ ቀኖች የሚጀምሩት ከቀደመው ቀን ምሽት ሆኖ የሚጠናቀቁት ደግሞ በፀሃይ መጥለቂያ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ሐሙስ ማታ ወደ መቃብር ገባ፤ አርብ ማታ እና ቅዳሜ ማታ በመቃብር ውስጥ ቆየ።
ማቴዎስ 12፡40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
በተጨማሪ በዘጸአት ምዕራፍ 12 የተጠቀሰው የፋሲካ በግ በ10ኛው ቀን ተመርጦ በ14ኛው ቀን ነው የሚታረደው። ኢየሱስ የተመረጠው ሕዝብ ባለበት የሆሳእና ዕለት እሑድ ነው፤ ያም ከወሩ 10ኛው ቀን ነው። ስለዚህ የሞተው በ14ኛው ቀን ሲሆን እርሱም ቀን ሐሙስ ነው።
ዘጸአት 12፡3 ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።
6 በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።
ክርስቶስ በሆሳዕና ቀን ተመረጠና ወደ እግዚአብሔር አብ ቤት ወደ ቤተመቅደሱ ተወሰደ።
ይህ የተደረገው በ10ኛው ቀን ነው።
ከዚያ ቀጥሎ 14ኛው ቀን የፋሲካው በግ የሚታረድበት ዕለት ሐሙስ ነበረ።
በቀጣዩ ቀን አርብ እለት ታላቅ ቀን ወይም ዓመታዊ ሰንበት ነበረ፤ እርሱም የፋሲካ በዓል ይባላል። ቀኑ የጀመረው ሐሙስ ዕለት ወደ ማታ ፀሃይ ስትጠልቅ ነው። ለአይሁዶች አርብ የሚጀምረው መች ነው?
14ኛው ቀን የመዘጋጀት ቀን ስለሆነ የበግ ጠቦት የሚታረድበት ጊዜ ነው።
ከዚያም በ15ኛው ቀን የፋሲካ በግ ይበላሉ።
ዮሐንስ 19፡31 አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።
ከዚያ በኋላ መደበኛው ሰንበት ይመጣል።
ዘጸአት 12፡46 በአንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ፤ አጥንትም አትስበሩበት።
አይሁዶች ከፋሲካው በግ ውስጥ አንድም አጥንት እንዲሰብሩ አይፈቀድላቸውም።
መስቀል ላይ የተሰቀሉት ሰዎች የእግራቸው አጥንት ተሰብሯል፤ ይህም የተደረገው በፍጥነት እንዲሞቱ ተብሎ ነው።
ዮሐንስ 19፡33 ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤
ስለዚህ ኢየሱስ የፋሲካ በግ ነው።
ቤተክርስቲያኖች በክሪስማስ ቀንም ተሳስተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዲሴምበር 25 የሚባል ቀን የለም።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የጌታን ልደት እንድናከብር አልተጠየቅንም።
ፖፑ ሊያታልለን አይችልም ያለው ማነው? በጣም ጠንቃቃ እና ንቁ መሆን አለብን።
ከሙታን የተነሱ ቅዱሳን ክሪስማስን ባለማክበራቸው ታዝንባቸዋለህን? የስቅለት አርብን ባለማክበራቸውስ?
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
የመላእክት አለቃ ድምጽ (ኢየሱስ በመልአክ መልክ ሲገለጥ) ሙታንን ያስነሳቸዋል ቤተክርስቲያንንም ይቀሰቅሳታል። ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ፍንጮችን መከተል የሚችሉት።
እነዚያን ፍንጮች ለመከተል የሚያበቃ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ይኖረን ይሆን?
ሰባቱ ነጎድጓዶች የሚሰጡንን ፍንጮች ሳናውቅ እንዳንተላለፍ በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ሊኖረን ያስፈልጋል።
7ቱ ነጎድጓዶች ትንሳኤው ከመፈጸሙ በፊት ሊታወቁ የማይችሉ ሚስጥራት ናቸው።
ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።
ነጎድጓዶቹ ስለተናገሩት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አልተጻፈም።
63-0324
….መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ነገር ግን እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ሰባት ድምጽ ያሰማሉ፤ ድምጻቸውንም ባሰሙ ጊዜ የጊዜውን ታላቅ መገለጥ ይገልጣሉ።
…. አሁን በዚህ ሰባተኛው ማሕተም በሚፈታበት ሰዓት ካስተዋላችሁ ይህ ሶስት እጥፍ ሚስጥር ነው። ይህን ተናግሬያለው … ወደፊትም እናገራለው፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር ነው።
በሰማያት ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጣሉ። ይህም የሚፈጸመው ልክ በክርስቶስ መምጫ ሰዓት ነው ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሰው የእርሱን መምጫ ሰዓት አያውቅም ብሎ ተናግሯል።
7ቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት በመጨረሻው ሰዓት ብርቱው መልአክ ወደ ምድር ከመጣ በኋላ ነው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ነገር አውቃለው ብላችሁ ብታስቡ ተታላችኋል ማለት ነው።
63-0324 ሰባተኛው ማሕተም
እንግዲህ ከዚህ ማሕተም ስር ያለው ታላቅ ሚስጥር ምን እንደሆነ አላውቅም። እኔ አላውቅም። ላየውም አልቻልኩም። ምን እንደሆነ ተገልጦ አላነበብኩትም። ምን እንደሆነ ምን እንደሚል አላውቅም። ነገር ግን የማውቀው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም የሚናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች መሆናቸውን እና ተራ በተራ በአንድነት ሁሉም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ታላቅ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነው።
ይህንንም ባየሁ ጊዜ ትርጓሜውን ለማወቅ ፈለግሁ፤ እርሱም እዚያው ነበረ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም። ይህ ነው እውነቱ ወዳጆች ሆይ። አያችሁ? እነዚህ ሚስጥራት ሊገለጡ ጊዜው አልደረሰም፤ ነገር ግን በጣም እየቀረበ ነው። አያችሁ? በጣም እየቀረበ ነው።
… ነገር ግን የማውቀው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም የሚናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች መሆናቸውን እና ተራ በተራ በአንድነት ሁሉም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ታላቅ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነው።
ይህንንም ባየሁ ጊዜ ትርጓሜውን ለማወቅ ፈለግሁ፤ እርሱም እዚያው ነበረ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም። … ደግሞም አንድ ልተረጉም የማልችለው ነገር አለ ምክንያቱም የተነገረው በማይታወቅ ቋንቋ ነው።
ይህ በማይታወቅ ቋንቋ የተነገረ ነገር ነው። ምን እንደሆነ በውል አናውቅም።
63-0324 ሰባተኛው ማሕተም
“መች ነው የሚሆነው ወንድም ብራንሐም?” እኔ የት አውቅና። አላውቅም … ያ ማሕተም ሚስጥር የሆነበት አንዱ ምክንያት እስካሁን አለመፈታቱ ነው፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ከዚያም በኋላ ማንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ አልተጻፈም። ስለዚህ ወደ መጨረሻው ዘመን ቀርበናል፤ መጨረሻው ላይ ነን።
“ማንም ምንም የሚያውቀው ነገር የለም”። ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን እናውቃለን በሚሉ ሰዎች አትታለሉ።
… እርሱም ያንን ሰባተኛ ማሕተም ፈታ። ነገር ግን አያችሁ፤ የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም። ነገር ግን እርሱ ራሱ ማንም አያውቅም ብሎ እንደ ተናገረው እንደ ምጻቱ ቀን ማንም ሊያውቀው አይችልም፤ ስለነዚህ ሰባት ነጎድጓዶችም ማንም ሊያውቅ አይችልም። ስለዚህ እንደምታዩት የተያያዘ ነው።
ልብ በሉ። ሰባተኛው ማሕተም የጌታን ምጻት ነው የሚወክለው፤ ስለዚህ ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም ልናውቅ አንችልም። ዝምታ ብቻ ነው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች የጌታን ምጻት ይገልጣሉ፤ ስለዚህ ስለ እነርሱም ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
1963-11-10 በወኅኒ ያሉ ነፍሳት
ሰባተኛው ማሕተም ወደ ምድር ተመልሶ እንዲመጣ ያደርገዋል።
ሰባተኛው ማሕተም ሚስጥራዊ የሆነውን የጌታን ምጻት ነው የሚወክለው። ይህ የዓለም ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ነው።
1964-07-19 የመለከት በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም እርሱም ምጻቱ ነው። የጌታ ምጻት ነው።
ሰባተኛው ማሕተም እስከ ጌታ ምጻት ድረስ ሊፈታ አይችልም።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
እንደምታውቁት ስድስቱን ማሕተሞች ማቴዎስ 24 ውስጥ ካለው ቃል ጋር ስናነጻጽራቸው ሰባተኛው ማሕተም ሳይጠቀስ እንደታለፈ እናስተውላለን። ክርስቶስ እንደተናገረው እግዚአብሔረ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ መላእክት እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ነው ሳይጻፍም የቀረው። ይህ ጉዳይ ጸጥ ተብሏል፤ ምንም ነገር አልተፈጸመም። መላእክትም አያውቁትም፤ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ነገር ግን እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ሰባት ድምጽ ያሰማሉ፤ በዚያን ጊዜም ታላቅ መገለጥን ይገልጣሉ።
… አሁን ስድስተኛው ማሕተም እንደተፈታልን እናያለን፤ እናየዋለን፤ ደግሞም ሰባተኛው ማሕተም ደግሞ ያ የተቀጠረለት ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ለሕዝብ ሊገለጥ እንደማይችል እናውቃለን።
የሜሴጅ ፓስተሮች በውጭ ያለው ሕዝብ ብቻ ነው የማያውቀው ብለው ይናገራሉ። ሙሽራይቱ ግን ታውቃለች ይላሉ።
63-1110 በወኅኒ ውስጥ ያሉ ነፍሳት
ልብ በሉ፤ ሰባቱ ማሕተሞች ተጠናቅቀዋል፤ እነዚያም ሰባቱ እውነትን በገለጡ ጊዜ…
ከእነርሱ አንዳቸውንም እንድናውቅ አልፈቀደልንም። ሰባቱ ማሕተሞች በተገለጡ ጊዜ ማነው ተገኝቶ የሰማ? ሁላችሁም የነበራችሁ ይመስለኛል። አያችሁ፤ ሰባተኛውን ማሕተም ግን እርሱ አልፈቀደም።
በዚህ ስብከት ውስጥ ሙሽራይቱ እንኳ ሰባተኛውን ማሕተም እንደማታውቀው ወንድም ብራንሐም ግልጽ አድርጓል።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
…ሰባቱኛው ማሕተም ሳይጠቀስ እንደታለፈ እናስተውላለን። ክርስቶስ እንደተናገረው እግዚአብሔረ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ መላእክት እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ነው ሳይጻፍም የቀረው። ይህ ጉዳይ ጸጥ ተብሏል፤ ምንም ነገር አልተፈጸመም። መላእክትም አያውቁትም፤ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም።
… አሁን አናውቀውም ደግሞም እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ አይታወቅም፤ ነገር በዚያ ቀን ይገለጣል፤ እንዲገለጥ በተወሰነበት በዚያ ሰዓት ይገለጣል።
ማንኛውም ድምጽ አውጥቶ የተነገረ ነገር ሁሉ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል። ስለዚህ ሕዝብ በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ተካትቷል።
“ሕዝብ” ማለት ወንድም ብራንሐም ሲናገር የሰማ ማንኛውም ሰው ነው።
… እንግዲህ ይህ ሰባተኛው ማሕተም ነው። ከሁሉም ነገር የተለየ ነገር ነው። እኛም ደግሞ… እኛም አናውቀውም፤ ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም ምክንያቱም እንዲገለጥ አልተፈቀደም።
ወንድም ብራንሐም የተናገረው ነገር በሙሉ ለሕዝብ ክፍት ነው። እኛም እርሱ የተናገረውን ስናዳምጥ የሕዝቡ አካል ነን።
65-0725 በዘመን መጨረሻ ላይ የተቀቡት
“በዚያ በተወሰነው ቀን የሰው ልጅ ይገለጣል።” ራዕይ 10፡1 እስከ 7 እቤታችሁ ስትገቡ አንብቡት፤ “የሰባተኛው መልአክ መልእክት እና የማሕተሞቹ መፈታት።” ይህ ምንድነው? መልአኩ የሰው ልጅ አይደለም፤ ነገር ግን መልእክተኛው የሰውን ልጅ እየገለጠው ነው። አሁን ለይታችሁ ማየት ቻላችሁ? ለእናንተ ከባድ የሚመስላችሁ ይህ ነው፤ አያችሁ። የሰው ልጅ እራሱ ሳይሆን ሰባተኛው መልአክ፤ ሰባተኛው መልእክተኛ ነው የሰው ልጅን ለሕዝብ የሚገልጠው ፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ተመልሶ ዘር ሆኗልና አሁን እንደ በፊቱ በስጋ ዓይን አይታይም።
ወንድም ብራንሐም ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ እንዴት እንሚመላለስ በማሳየት የሰው ልጅ መሆኑን ገልጦልናል። ስለዚህ ሕዝቡ ማለት እኛ ነን።
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ስጋ እንደለበሰ ሰው ለሕዝቡ ገለጠላቸው።
ወንድም ብራንሐም ኢየሱስን እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል አድርጎ ለእኛ ይገልጥልናል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ዛሬ ቢገለጥልን የእግዚአብሔርን ቃል ተረድተናል ማለት ነው።
ለዚህ ነው መልአኩ በእጁ የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ የወረደው።
የሙሽራይቱ አካላት በስተመጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለራሳቸው ያስተውላሉ።
ወንድም ብራንሐም ስለተናገረ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ነው።
64-0614 አፈንጋጩ ኳስ
መልአኩ የነገረኝ ይህ ነው፡- “ሕዝቡ እንዲያምኑህ አድርግ።”
እኔ የእግዚአብሔርን ቃል ብናገር እኔ ስለተናገርኩ “እኔን እመኑኝ” አልልም “ቃሉን እመኑ”።
የማያምኑ ሰዎች የሚገለጠውን ሃሳብ መከታተል ይችላሉ ነገር ግን መገለጡን ሊያስተውሉ አይችሉም። ሙሽራይቱ ብቻ ናት የመጨረሻው ዘመን ነብይ የሕዝቡን የልብ ሃሳብ እና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ሲገልጥ መረዳት የቻለችው።
ወንድም ብራንሐም የሰዎችን የልብ ሃሳብ የመግለጥ ስጦታ ስለነበረው የልባቸውን ሃሳብ ለራሳቸው ገልጦላቸዋል።
ይህ ስጦታው በተጨማሪ የእግዚአብሔርንም ሃሳብ እና ጥልቅ ሚስጥር ከመጽሐፍ ቅዱስ መግለጥ እንደሚችል ማረጋገጫ ሆኗል።
ከዚህ በኋላ ሙሽራይቱ ወንድም ብራንሐም ያስተማራትን መገለጦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መከታተል እና እምነቷን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተጠቅማ ማረጋገጥ መቻል አለባት። እምነቷን ለማረጋገጥ የሰው ንግግር ጥቅሶችን መጠቀም አያስፈልጋትም።
ዘመን የሚያበቃው መች ነው?
64-0409 የክርስቶስ መገለጥ በዘመናት ሁሉ
ተመልከቱ፤ አሁን አንድ ሰው በእጆቹ ላይ የችንካር ጠባሳ ሰውነቱ ላይ ቁስሎች እና ፊቱ ላይ ደም እያሳየን ቢገባስ? ማንኛውም ግብዝ ሰው ይህን ሊያደርግ ይችላል። ደግሞ አስተውሉ፤ ኢየሱስ እንደዚህ ሆኖ አይመጣም። ሲመጣ ከዚያ በኋላ ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም። እርሱ ሲመጣ ጊዜ ያበቃል።
ግን ደግሞ እርሱ ሲመጣ እርሱ መሆኑን እንዴት ልታውቁ ትችላላችሁ? የምታውቁት እርሱ ራሱን በመንፈሱ ስለሚገልጥ ነው፤ ምልክቱም በውስጣችሁ የሚኖረው የእርሱ ሕይወት ነው። “እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎቼ ናችሁ።”
የሆነ ነገር ማወቃችሁን እውነትን እንዳወቃችሁ አድርጋችሁ በመቁጠር አትሳሳቱ።
ለትንሳኤ ወደ ምድር ስለሙወርደው መልአክ ታውቃላችሁ።
ግን መልአኩ ወደ ምድር ወርዷል ማለት አይደለም።
ራዕይ 10፡6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ ወደ ፊት አይዘገይም።
ገዜ የሚባለው ነገር የሚያበቃላችሁ ዘላለማዊውን አካላችሁን ስትለብሱ ብቻ ነው።
ነጎድጓዶቹ የሚያመጡት ውጤት ይህ ነው።
ማለትም እኛ አዲሱን አካል እንድንቀበል ያስችሉናል።
አንዴ ያንን የተለወጠ አካል ከለበስን በኋላ ብቻ ነው ልንነጠቅ የምንችለው።
አሁን በለበስንበት ስጋ ውስጥ ሆነን መነጠቅ አንችልም ምክንያቱም ይህ አካል ውስጡ ደም አለው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
አዲሱ አካላችሁ ውስጡ ደም አይኖረውም። በደም ስራችሁ ውስጥ የሚዘዋወረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ለዚህ ነው የማታረጁት እና የማትታመሙት እንዲሁም የማትሞቱት።
አዲሱ አካላችሁ አስደናቂ ችሎታዎች ይኖሩታል።
2ኛ ሳሙኤል 22፡30 በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።
63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያመጣውም
ኦ የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉ ሰዎች ምንኛ አስደናቂ እንደሚሆኑ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ! እንዲህ ይላል፡- “በሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ ቅጥሩንም ይዘላሉ።” አዎ፤ የሞት ሰራዊት ሊይዛቸው አይችልም፤ በመካከሉ ሮጣ ታልፋለች። በፍጥረታዊው እና በልዕለ ተፈጥሮአዊው መካከል ያለውን “ግድግዳ” ዘላው ታልፈዋለች፤ ከዚያም ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ትገባለች። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው በጣም እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።
ያልዳነ ሰው ሞቶ ከአካሉ ሲወጣ የአጋንንት ሰራዊት መንፈሱን ወስደው ወደ ሲኦል ሊጥሉት ተሰልፈው ይጠብቃሉ።
እናንተ ግን የማይሞተውን አካላችሁን ልትለብሱ ከአሁኑ ስጋችሁ ስትለያዩ እነዚያ ሁሉ አጋንንት መንገዳችሁን ሊዘጉ ቢሞክሩ እንኳ በመካከላቸው ሮጣችሁ ማለፍ ትችላላችሁ።
በዚያ አዲስ አካል ውስጥ ዘላለማዊነትን ተላብሳችሁ ከዘላለማዊው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ዓለም የሚለየንን የጊዜ ግድግዳ ዘላችሁ ማለፍ ትችላላችሁ።
ይህም የሚሆነው በአየር ላይ ሲመጣ እንቀበለው ዘንድ ኢየሱስ በሚነጥቀን ጊዜ ነው።
ማቴዎስ 25፡10 ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
“በሩ ተዘጋ”።
በኖህ ዘመን የመርከቡን በር የዘጋው እግዚአብሔር ነው።
በሎጥ ቤት ውስጥ ደግሞ ሁለቱን በሮች የዘጉት መላእክት ናቸው። ያንን ተከትሎ ከሰማይ እሳት ዘነበ።
በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ፓስተሮች የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ክርስቶስን በር ዘግተው ከቤተክርስቲያን አስወጡት። በዚህም መንገድ ሰነፎቹን ቆነጃጅት የራሳቸው አመለካከት እስረኛ አድርገው አስቀሯቸው። የአስራት ገንዘብም ከቤተክርስቲያናቸው እንዳይወጣ ቁጥጥር አደረጉ።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር ስለሆኑ የቤተክርስቲያን ፓስተሮች በአሁኑ ጊዜ ምን እየተከናወነ እንዳለ አንዳችም አያውቁም። ስለዚህ እነርሱም ሆነ ጉባኤያቸው እውነትን የማግኘት ተስፋ የላቸውም። ልማዳዊ የቤተክርስቲያን ስሕተቶቻቸው የነጎድጓዶቹ ሚስጥር እንዳይገለጥላቸው ይከለክላቸዋል።
በተጨማሪ ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተሉ ሰዎችን ያለማቋረጥ አውግዘዋል፤ ተችተዋል፤ ገፍተዋል። በዚህም የተነሳ ወደ እውነት የሚያስገባው በር ተዘግቶባቸዋል። ይህም የሆነባቸው እውነትን ከቤተክርስቲያናቸው አውጥተው ስለጣሉ እንዲሁም እውነት ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንዳይገባ በራቸውን ጥርቅም አድርገው ስለ ዘጉ ነው። ማንኛውም የቤተክርስቲያንን በር ለመክፈትና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስገባት የሞከረ የቤተክርስቲያን አባል ከቤተክርስቲያን ይባረራል። ይህ ሕዝቡን ለመሪው ታዛዥ እና ፈሪ ማደረጊያ ዘዴ ነው። አምባገነን የፖለቲካ መሪዎችም አሰራራቸው እንደዚሁ ነው።
ፖፑ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው ፈላጭ ቆራጭ መሪ ነው።
አንድ ሰው ብቻ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ የሚመራበትን አሰራር የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ፓስተሮች እናታቸው ከሆነችው ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኮርጀዋል።
በመብራቶቹ ውስጥ በሚነደው እሳት የተመሰለው መንፈስ ቅዱስ ዓላማው መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን ለመረዳት የሚበቃ ብርሃን መስጠት ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች ከትንሳኤ በኋላ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት ሊሰጧት ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ልባሞቹ ቆነጃጅት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አገጣጥመው የተሰወረውን የሰባቱን ነጎድጓዶች ሚስጥር ማግኘት ይችላሉ።
ይህ የመጨረሻው የመከር ዝናብ ወይም ኋለኛው ዝናብ ነው፤ በዚህ ዝናብ ወቅት እነዚህ መገለጦች አማኞችን ከምድር አንስተው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ይነጥቋቸዋል። መከር የሚባለው ከሞተው ተክል ላይ ፍሬው ተለቅሞ ሲሰበሰብ ነው።
ያ የወደፊት ኋለኛ ዝናብ ከመምጣቱ አስቀድሞ የመጀመሪያው ዝናብ ወይም የትምሕርት ዝናብ መምጣት አለበት።
ይህ የትምሕርት ዝናብ የጀመረው ወንድም ብራንሐም ከ1947 እስከ 1965 ድረስ መገለጦቹን በቴፕ ሲቀዳ ነው።
መገለጦቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ እየመረመርን በማረጋገጥ አሁኑኑ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት መማር ያስፈልገናል። ስለዚህ የትምሕርት ዝናብ “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” ውስጥ እርሱ ከሄደ በኋላ እንኳ ይቀጥላል። በድምጽ ተቀድተው የተቀመጡት ስብከቶቹ እስከ ዛሬ ድረስ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል እንዴት አድርገን እንደምንረዳ ያስተምሩናል።
ስለዚህ የትምሕርቱ ዝናብ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ እኛም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ተጨማሪ እየተማርን እንኖራለን። ሒደቱ አይቋረጥም።
ከትንሳኤው በኋላ በመከሩ ዝናብ ውስጥ እንገባለን ምክንያቱም የሞቱ ቅዱሳን ከመቃብር ውስጥ ይወጣሉ። ከዚያ በኋላ በቂ ጊዜ ስለማይኖር ማወቅ የሚያስፈልጋችሁን አሁኑኑ ማወቅ አለባችሁ። ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ወዲያው ያበቃል።
ከሙታን የተነሱ ቅዱሳን በሚያናግሯችሁ ጊዜ እነርሱ የሚናገሩትን እንድታስተውሉ ይጠብቃሉ። የምትናገሩት ንግግር ከእነርሱ ጋር ካልተስማማ ንግግራችሁ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት መካከል መሆናችሁን ያጋልጥባችኋል።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት የተመሰሉት ሜዳ ላይ ደርቆ በሚቀረው አገዳ እና በጠወለገ ተክል ነው፤ ይህም ከመከር በኋላ ሜዳ ላይ ስለሚቀር ኋላ አውሬው መጥቶ ይበላዋል፤ ከአውሬው የተረፈውም በታላቁ መከራ እሳት ውስጥ ይቃጠላል።
ዘሮቹ ከተክሉ ላይ ከተለቀሙ በኋላ ከብቶቹ (የሜዳ አራዊት) በእርሻው ላይ ተፈተው ይለቀቃሉ፤ የደረቁትን አገዳዎች ሁሉ ይበሏቸዋል።
ይህ የሚያሳዝን ነገር ነው።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት ነፍሳቸውን ስለ ጌታ አሳልፈው የመስጠት ድፍረት ይኖራቸዋል ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን የሚገለጠው የቤተክርስቲያን ዘግናኝ ስሕተት ብዛት ያስደነግጣቸዋል። የዚያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ፍጥጥ ያለ ስሕተት እና ግፍ አካል ከመሆን መሞት እንደሚሻላቸው አስበው ነፍሳቸውን መስጠት ይመርጣሉ።
በዛሬው ዓለም ውስጥ ግን የትምሕርት ስሕተት በጣም ግልጽ ባልሆነበት እና ቤተክርስቲያኖች ሁሉ መልካም በሚመስሉበት ጊዜ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ እየተሞኙ ናቸው። ሁል ጊዜ ነቅተው ለመጠበቅ የሚያስፈልግ ብርታት የላቸውም። በቀላሉ ሊታለሉ እንደሚችሉ እንኳ አያውቁምና በጣም ቸልተኞች ይሆናሉ። እምነታቸውንም በጥንቃቄ አይመረምሩም፤ ቤተክርስቲያናቸው በትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ እየሄደች እንደሆንም አያጣሩም። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ፓስተራቸው ስሕተትን እያስተማራቸው እንደሆነ እያወቁ እንኳ ጥያቄ ለማንሳት ድፍረት የላቸውም። ተደላድለው ከኖሩበት ከቤተክርስቲያናቸው ሕብረት እንዳይባረሩም ይፈራሉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ መልካም ሰው የሚያዩት ፓስተራቸው ሊሳሳት ይችላል ብለው አያምኑም። ለእነርሱ ሁሉ ነገር በፓስተራቸው ዙርያ ነው የሚያጠነጥነው። ፓስተራቸው በጣም ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን ቢያራምድም እንኳ ለእነርሱ ግን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ እመነት ጀግና መስሎ ነው የሚታያቸው።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት ሰውን እስከሚከተሉ ድረስ አእምሮዋቸው ደንዝዟል። ለእነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው። እነርሱ እንደሚያስቡት ፓስተሩን ነው ሁልጊዜ መታዘዝ ያለባቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል እየተናገራቸው ከሚመራቸው ከማይታየው እግዚአብሔር ይበልጥ ገዝፎ የሚታያቸው በዓይናቸው በምድር ላይ የሚያዩት መሪ ነው።
ነገር ግን ይህ ሁሉ ወደ ንጥቀት በሚያደርሰውና በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚጠናቀቀው በኋለኛው ዝናብ ወቅት መለወጥ ይጀምራል።
የዚያን ጊዜ ፓስተራቸው እና ቤተክርስቲያናቸው ምን ዓይነት እንደሆኑ ሲያዩ፤ ፓስተሮቻቸውም ምንም ግንዛቤ እንደሌላቸው ሲያዩ የዚያን ጊዜ ጠለቅ ያሉ መልሶችን መፈለግ ይጀምራሉ።
አንድ ጊዜ ታላቁ መከራ ውስጥ ከገቡ በኋላ ጉዳዩ በጣም እየተካረረ ይሄዳል። የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ሰነፎቹን ቆነጃጅት ለማጥፋት ይነሳል። እነርሱም በዚያን ጊዜ በታላቅ ቆራጥነት ይነሳሉ። ነገር ግን ሰዓቱ በጣም ይረፍድባቸዋል።
ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ስለዳኑ የተታለሉት ቆነጃጅት ወይም ሰነፎቹ ቆነጃጅት መንግስተ ሰማያት መግባታቸው አይቀርም፤ ሆኖም ግን የሙሽራይቱ አካል አይሆኑም። 1,000ውን ዓመት በክርስቶስ ሆነው ከሞቱት ጋር ያሳልፉና በፍርድ ቀን ከሙታን ይነሳሉ። ከዚያ በኋላ ይድናሉ። ይህም ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ ጠመዝማዛ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም ቀጥተኛውን እና ጠባቡን መንገድ ለመከተል እድሉ በነበራቸው ጊዜ አልተጠቀሙበትም።
ማቴዎስ 7፡13 በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
ከብሮድዌይ እና ከሆሊውድ ምርቶች የተነሳ አሜሪካ በዓለም ላይ የመዝናኛ ገበያውን እየመራች ትገኛለች።
ድራም የሚባል የሙዚቃ መሳሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጠቀሰም፤ ነገር ግን በዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ለመዝናኛነት የሚያቀለግለው የድራም ምት ነው።
63-0711 ማፈር
ድሮ ድሮ የአፍሪካ ጫካዎች ውስጥ አውሮፓውያን ለአደን ሽርሽር ሲሄዱ የኤልቪስ ፕሬስሊ እና የፓት ቡን ዘፈኖችን እንዲሁም የሮክ ኤን ሮል ሙዚቃዎችን ለማዳመጥ ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ሬድዮዎች ተሸክመው ይሄዱ ነበር። አፍሪካውያኑም ፈረንጆቹ ሲደንሱ ጭንቅላታቸውን ሲንጡ ለማየት ይሰበሰቡ ነበር። አያችሁ፤ ነገር ግን እነርሱ እንደ ፓት ቡን እና እንደ ኤልቪስ ፕሬስሊ እና እንደ ሪኪ ኔልሰን አሜሪካውያን አይደሉም። ይሁዳዎችም አይደሉም፤ ነገር ግን … ያው መንፈስ ነው። ደግሞም መንፈሱ አሜሪካ ውስጥ ብቻ አይደለም፤ ሰዎችን ሁሉ ሰብስቦ ወደ አርማጌዶን ጥርነት ሊያዘምት መንፈሱ እራሱን በዓለም ዙርያ ሁሉ አሰራጭቷል። ምንም ይሁኑ ምን እንደዚያው ነው አኳኋናቸው… ከየትም ሃገር ይሁኑ ከአፍሪካ፣ ከሕንድ ያ ብልግናቸው በምድር ሁሉ ተዳርሷል፤ የተዳረሰውም አንድ ሰው ስለጀመረው ብቻ ነው።
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
እውነተኛው መንገድ ሕዝብ የሚወደው መንገድ አይደለም።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ የተታለሉ ሰዎች ቤተክርስቲያን ከምታባርራቸው ይልቅ የተገለጠውን ቃል አለመቀበልን መረጡ።
“ማወቅ አለብን እንዴ?” ይላሉ።
የሙሽራይቱ አካልት ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነትን ከማግኘት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ ስላስበለጡ ከቤተክርስቲያን መባረርን መረጡ።
እነርሱም “ማወቅ አለብን” ይላሉ።
ማቴዎስ 25፡11 በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
12 እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
ከእንቅልፋቸው በባነኑ ጊዜ ሰዓቱ ረፍዶባቸው ነበር። እነርሱ ሲነቁ ጌታ መጥቶ ሄዷል።
የቀደመው ዝናብ የትምሕርት ዝናብ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ሚስጥር ይፈጽማል፤ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል በመረዳት እንድናነበው ያስችለናል።
ዛሬ ግን ቤተክርስቲያኖች የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ትተው እየሄዱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሆን የሰዎችን ድምጽ ያዳምጣሉ።
ዮሐንስ 10፡26 እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
ኢየሱስ ብቻ ነው ድምጹን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደምጡ ሰዎችን የሚያውቃቸው።
ፓስተሮች እረኞች ነን ይላሉ።
የትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እረኛው ፓስተሩ ነው አይልም።
እረኛ ሰው ነው፤ ሰው ስለሆነም ከበጎች እጅግ አብዝቶ ይበልጣል።
የትኛውም ፓስተር ከሰዎች አይበልጥም።
አንድን ቅዱስ ሰው ከሕዝብ በላይ ከፍ ማድረግ፤ ይህ ኒቆላዊነት ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ … ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
ሁሉም ክርስቲያኖች ካሕናት ናቸው። ካሕናት ሁሉ እኩል ናቸው። ሊቀካሕናቱ ማለትም ኢየሱስ ብቻ ነው ከካሕናት የሚበልጠው።
ስለዚህ ክርስቲያኖች በሙሉ እኩል ናቸው።
እረኛ የሆነው ሰው ኢየሱስ ብቻ ነው።
መዝሙር 23፡1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንድናዳምጥ ነው የሚያደርገን።
ማቴዎስ 25፡13 ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
በዓለም ላይ የሚከሰቱ ነገሮችን በትክክል ለመረዳት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመልከት አለብን። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ስሕተቶችን ለመለየት መጽሐፍ ቅዱስን መመልከት አለብን።
የዘመን መጨረሻ ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር ቃል ፍላጎት አጥተዋል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን በዚህ ፍላጎት ማጣት ውስጥ ሁሉ አሳልፎን ቃሉን እንድንሰማ ይረዳናል፤ ይመራናል።
በሩ የመዘጋቱ ትርጉም ምንድነው?
በተከፈተው በር ማለትም በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ማንኛውንም ሰው ይቀበለዋል።
እግዚአብሔር በሩን ሲዘጋ ግን ሁሉንም ሰው በውጭ ያስቀረዋል።
እግዚአብሔር አንድ ቦታ ላይ ቀይ መስመር ያሰምራል፤ ከዚያ በኋላ ቃሉን ባንከተል ጉዳችን ፈላ።
ማቴዎስ 25፡11 በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
አስተሳሰባቸው ላይ ተጽእኖ የሚያደርገውን የሥላሴ መንፈስ ልብ ብላችሁ እዩ።
እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር ወልድ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ይመስሏቸዋል፤ ስለዚህ ሁለቱን በየግል ለየብቻ ማናገር የሚያስፈልግ ይመስላቸዋል። “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመኖሩን አላወቁም፤ የሰዎች ሃሳብና ፈጠራ ብቻ ነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም።
“እግዚአብሔር አብ” ተብሎ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለምን እንዳልተጻፈ ማብራራትም አይችሉም።
61-0723 እግዚአብሔርን በተሳሳተ መንገድ መረዳት
ከአስሩ ቆነጃጅት አምስቱ ጠፍተዋልን?
ስለ “አምስቱ ቆነጃጅት”፤ አምስት ልባሞች እና አምስት ሰነፍ ቆነጃጅት በተመለከተ ጥያቄዎችን እንደሚጠይቁ አውቃለው። ባላፈው ከዮሐንስ ራዕይ እየተማርን በነበረ ጊዜ ከእኛ ጋር ብትሆኑ ኖሮ ከአስር ቆነጃጅት መካከል አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት እንዳልጠፉ ትሰሙ ነበር። ባይጠፉም ግን ወደ ሰርጉ እራት ግብዣ መግባት አልተፈቀደላቸውም፤ በዚያ ፈንታ ስደት ይደርስባቸዋል፤ ሰማእት ሆነው ያልፋሉ፤ በስተመጨረሻም ሁሉም ሰው በሚነሳበት ትንሳኤ ይነሳሉ። እነዚህ ሰዎች ናቸው በጎች እና ፍየሎች ተብለው የሚለዩት። (ገባችሁ?) እነዚህ በፍርድ ፊት ይቆማሉ።
… ስለዚህ አልጠፉም፤ ነገር ግን የሙሽራይቱ አካል አይሆኑም። በሁለተኛው ትንሳኤ ይነሳሉ ነገር ግን የሙሽራይቱ አካል አይሆኑም፤ ከሙታን ሲነሱም የተሰጣቸውን ብርሃን ከያዙበትን እና ከተጠቀሙበት አጠቃቀም አንጻር ይፈረድባቸዋል። ይህም ፍርድ የክርስቶስ ነው። ቢፈረድባቸውም እንኳ አይጠፉም።
ማቴዎስ 25፡12 እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
53-0729 ጥያቄዎች እና መልሶች በዘፍጥረት ላይ
በዚያን ጊዜም መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ሊጸልዩ ሞከሩ ነገር ግን የአሕዛብ ዘመን አብቅቶ ስደቱ ጀምሮ ነበር። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ልቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ተጥለዋል።” በሁለተኛው ትንሳኤ ግን ከፍየሎች ተለይተው የሚቆሙ በጎች ይኖራሉ፤ ነገር ግን ሙሽራይቱ ወይም የተመረጡት ለዚህ ፍርድ አይቀርቡም። እነዚህ ሁሉ የተቀሩት የሴቲቱ ዘር ናቸው።
ቅሬታዎች ምንድናቸው? ተቆርጠው የቀሩ ክፍሎች ናቸው። ገብቷችኋል? ልብስ ለማሰፋት ስታስቡ ከትልቅ ጨርቅ ላይ በልካችሁ ይቆረጥና ይዘጋጃል። ልብሱን የምታሰፉበት ዲዛይን ምርጫው የናንተው ነው። እግዚአብሔርም የራሱን ዕቅድ ዲዛይን ማድረግ ምርጫው የራሱ ነው፤ ስለዚህ በመረጠው መንገድ ቀርጾ ያዘጋጀዋል። ግልጽ ነው? ጨርቁ ልብስ ሆኖ ሲሰፋ ተቆርጦ የሚቀረው ቁራጭ ጨርቅም ልብስ ከሚሰፋበት ጨርቅ እኩል ጨርቅ ነው፤ አንድ ዓይነት ነው። አይደል ወይ? ነገር ግን የእግዚአብሔር ምርጫ ነው። እግዚአብሔር ነው ቤተክርስቲያንን የሚመርጣት፤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን አስቀድሞ ይወስናታል፤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት እንደምትሆን አስቀድሞ ያሰበው ሃሳብ አለው፤ ስለዚህ ያችን ቤተክርስቲያን ከዓለም ለይቶ ያወጣታል። የቀሩት ሕዝብ በታላቁ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ በምድር ይቀራሉ።
… የተመረጡት ወደ ላይ ተነጥቀው ሲሄዱ ቅሬታዎቹ ግን በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ያልፉ ዘንድ እዚሁ ይቆያሉ። በዚያም ዘመን መጨረሻ የሚያልፉበትን መከራ ሲያዩ ሰማእት ሆነው ነፍሳቸውን መስጠት አለባቸው።