ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ክፍል 1



የ10 ቆነጃጅት ምሳሌ። ሁላቸውም በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ አንቀላፍተዋል። “ውጡ” የሚል ጩኸት ሲሰሙ ሁሉም ከቤተክርስቲያን ይወጣሉ።

First published on the 13th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።

አሥር ቁጥር የመጨረሻውን ዘመን የሚያመለክት ትርጉም ያለው ቁጥር ነው።

በአስር ቁጥር ላይ የተመሰረተውን ዘመናዊውን የክብደት የርዝመት እና ሌሎች መለኪያዎች በ1800 አካባቢ ለዓለም ያስተዋወቁት ፈረንሳዮች ናቸው።

ለምሳሌ፡ 1 ሴንቲሜትር = 10 ሚሊሜትር ነው።

ይህ ለአሰራር በጣም አመቺ ዘዴ ነው፤ ነገር ግን የተገኘው በጣም ዘግይቶ በሰው ታሪክ ማብቂያ አካባቢ ነው።

ናቡከደነጾር የአሕዛብን ታሪክ በአንድ ሰው ሃውልት መልክ በሕልም አየ። የሸክላው እግር (ከካቶሊክ ውጭ የሆኑ ቤተክርስቲያኖች) እና ብረቱ (የሮማ ካቶሊክ) ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

 

 

እግሮቹ መጨረሻቸው በአሥር ጣቶች ነው፤ አምስት ጣቶች በቀኝ እግር እና አምት ጣቶች በግራ እግር። ይህም ከአንድ በላይ ትርጉም አለው።

ሸክላው የዳኑ ክርስቲያኖችን ይወክላል። በአስሩ ጣቶች ውስጥ ያለው ሸክላ በምሳሌው ውስጥ ያሉትን አስር ቆነጃጅት ይወክላል።

አስሩ ጣቶች የዘመን መጨረሻን እንደሚወክሉ ግልጽ ነው።

ስለዚህ አምስቱ ልባም ቆነጃጅት እና አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት በዘመን መጨረሻ የሚኖሩትን የዳኑ ክርስቲያኖች ይወክላሉ። ቆነጃጅት ወይም ድንግሎች ንጹህ ሴቶች ናቸው፤ ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የዳኑ ቅዱሳን ሰዎችን ይወክላሉ።

 

 

በአስሩ ጣቶች ውስጥ ያሉት የብረት ስብርባሪዎች የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ዓለምን እንዲገዛ ለማስቻል ወታደራዊ ኃይላቸውን እና ስልጣናቸውን የሚያስረክቡትን አስር ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ይወክላሉ።

ሒትለር እና እስታሊን ሕዝቡ እንዲታዘዙዋቸው ማስገደድ የቻሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በመግደል ነው።

በመጨረሻው ፖፕ የሚገዙት አስር ፈላጭ ቆራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰዎችን በብዙ ቁጥር ጨፍጭፈው ይገድላሉ። እነዚህ መሪዎች ሰዎችን እንደማይጠቅሙ የፋብሪካ እቃዎች በመቁጠር ያለምንም ሃሳብ ሲገድሉ የሚመሩበት ስርዓት ማሕበራዊ ምሕንድስና ይባላል።

ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።

 

 

ይህ ራዕይ የሮማ ካቶሊክ ቫቲካን ከተማን ይወክላል፤ ይህችም ከተማ የተቆረቆረችው ሮም በመጀመሪያ በተመሰረተችባቸው ሰባቱ ተራራዎች አጠገብ ነው።

 

 

የካፒቶላይን ተራራ የአረማዊው የሮማ ግዛት ዋነኛ ማዕከል ነበረ። ባርቤርያውያን ካጠፉት በኋላ ያ አረማዊ መንፈስ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሞት አንሰራርቶ መናገሻውን የካኤልያን ተራራ ላይ ባለው በላተራን ባሲልካ (ትልቅ ቤተክርስቲያን) ውስጥ አደረገ።

ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

“እንደ ነገሥታት” ሥልጣንን ይቀበላሉ። ዘውድ የጫኑ ነገሥታት አይደሉም ነገር ግን እንደ ነገስታት ስልጣን ይሰጣቸዋል። ስለዚህ አምባገነኖች ናቸው ማለት ነው።

ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

“ሥልጣን” ማለት ወታደራዊ ኃይላቸው ነው።

“አንድ ልብ”። እነዚህ ሁሉ በስተመጨረሻ በሚመጣው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ሥልጣን ስር ይሆናሉ።

አምስቱ ልባም ቆነጃጅት ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ስለሚያገኙ በጌታ ምጻት ጊዜ ዘላለማዊው አካላቸውን ይለብሳሉ። አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት ግን ወደ ኋላ ይቀሩና ዘላለማዊ አካላቸውን የ1,000 ዓመቱ የሰላም መንግስት ካለፈ በኋላ ይቀበላሉ።

 

የአሕዛብ ምሱሉ ሁለት የብረት እግሮች የሮማ መንግስትን ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ ግዛቶች የሚያመለክቱ ናቸው። ስለዚህ አስሩ የእግር ጣቶችም በስተመጨረሻ ለፖፑ ስልጣን እጅ የሚሰጡትን አምስት የምስራቅ አምባ ገነን መሪዎች እና አምስት የምዕራብ አምባ ገነን መሪዎች ይወክላሉ። በነውጠኛ ዘመናት ውስጥ ሰዎች አምባገነን መሪዎችን ለመቀበል ፈቃደኞች ይሆናሉ።

አሜሪካውያን የጦር ሰራዊታቸውን ወደ ሌላ የዓለም ክፍል ለማንቀሳቀስ ስድስት ወራት ያህል ይፈጅባቸዋል።

ስለዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ፖፕ የአስሩን አምባገነን መሪዎች ጦር ሰራዊት መጠቀሙ ጊዜ ይቆጥብለታል፤ ምክንያቱም እነዚህ መሪዎች ወታደሮቻቸው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ ስለሚገኙ መንቀሳቀስ አያስፈልጋቸውም።

ይህም በስተመጨረሻ በእምነትም ሆነ በፖለቲካ ውስጥ ብዙ ነውጥ እና አለመረጋጋት እንደሚመጣ ያሳያል።

በ2020 ዓ.ም በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንደ ቻይና፣ ቬትናም፣ እና ካምቦዲያ ያሉ አምባገነን መንግስታት ወረርሽኙን ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ ዴሞክራሲያዊ መንግስታት የተሻለ በቁጥጥር ስር ማድረግ መቻላቸውን አሳይተዋል። ወደፊት ብዙ ነገሮች ከዚህ ይበልጥ ሲበላሹ ሕዝቡ ሥራ ሊሰጣቸው የሚችል አምባገነን መሪ ከተነሳ በቀላሉ ይቀበሉታል። ጀርመኖች ልክ እንደዚሁ ነው ከ1929ኙ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ውድቀት በኋላ በቀላሉ ሒትለርን የተቀበሉት። በዚያው ዓመት ሙሶሊኒ የቫቲካንን ከተማ ራሷን እንደቻለች መንግስት ወይም ሃገር አድርጎ የተቀበላት፤ ይህንንም በማድረጉ የቫቲካን ከተማ (በምድር ላይ ከሁሉ ትንሽዋ ሃገር በመሆን) የዳንኤል ትንቢት ውስጥ የተጠቀሰውን ታናሽ ቀንድ መሆን ችላለች።

የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች መምሕራኑ በደምብ እንደማያስቡ፤ በብዙ እንደ ሳቱ እና መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸውን ትምሕርቶች እንደተቀበሉ ያሳያሉ፤ ለምሳሌ ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ የሰባት ዓመታት መከራ፤ አይሁዳውያን ከፍልስጤማውያን ጋር ቃልኪዳን ሲያደርጉ ታላቁ መከራ ይጀመራል፤ ጌታ በ1963 ተመልሶ መጥቷል፤ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወርዷል፤ ዊልያም ብራንሐም ፍጹም የማይሳሳተው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው።

በዚህ ሁሉ ስሕተት ውስጥ እውነተኛዋ ሙሽራ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በኢንተርኔት ፈልጋ ማገኘት አለባት።

ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ የተጻፉት ሰባቱ ምሳሌዎች ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው የሚናገሩት። ሰባተኛው ምሳሌ እርፍት በሌለው የሕዝብ ባሕር ውስጥ ስለሚያልፍ መረብ ይናገራል። ይህም እግዚአብሔር በየሥፍራው የተበታተኑ ግለሰቦችን ለመሰብሰብ የቃሉን እውነት በመረጃ መረብ ማለትም በኢንተርኔት አማካኝነት ያሰራጫል ማለት ነው። እግዚአብሔር የሚጠራቸው በራሳቸው አእምሮ ማሰብ የሚችሉትን ጥቂት ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች በፓስተሩ አመለካከት መገዛት የማይፈልጉ ናቸው።

በየስፍራው ተበታትነው ያሉ ግለሰቦች በ ZOOM የኢንተርኔት ኮንፈረንስ በመጠቀም መሰብሰብ እና በአንድነት ሕብረት ማድረግ ይችላሉ።

ማቴዎስ 13፡47 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤

“መረብ”። የመረጃ መረብ ወይም ኢንተርኔት።

“ባሕር”። ዕረፍት ያጣ የዓለም ሕዝብ።

መጽሐፍ ቅዱስን የሚያኑት ልባሞቹ ቆነጃጅት ወይም እውነተኛዋ ሙሽራ ወደ ሰርጉ እራት ተነጥቃ ትሄዳለች።

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አቃቂር የሚያወጡት ሰነፍ ቆነጃጃት ቤተክርስቲያኖች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

 

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንዲገለጥልን ብርሃን ያስፈልገናል፤ የዚያን ጊዜ ቃሉን በመረዳት ማንበብ እንችላለን።

ሙሽራይቱ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንከን የሌለው የእግዚአብሔር ቃል አድርጋ ትቀበላለች። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ማስተካከያ አያስፈልገውም።

 

59-0628 ጥያቄዎችና መልሶች

“ድንግል” የሚለው ቃል ትርጉሙ “የተቀደሰ (ይህን በፊት ታውቁ ነበር?) ቅዱስ፣ ንጹህ፣ የተለየ ማለት ነው።”

58-1012 የቤተክርስቲያን በድንገትና በሚስጥር መነጠቅ

“ድንግል” የሚለው ቃል “ንጹሕነትን” ያሳያል። ሁላቸውም ጥሩ ሰዎች ነበሩ፤ ሁላቸውም ድንግል ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ዕቃዎች። ነገር ግን በመብራታቸው ውስጥ ዘይት የነበራቸው ብቻ ገቡ። ሌሎቹ ግን በውጭ ቀሩ። ሁሉም ቆነጃጅት ወይም ድንግል ነበሩ፤ ምንም እንከን ልታወጡላቸው አትችሉም። ሁላቸውም በጌታ ምጻት ያምኑ ነበር፤ እርሱ ሲመጣ ሊቀበሉት በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ግን ከመካከላቸው የተወሰኑቱ ዘይታቸው አልቆ መብራታቸው ጠፋባቸው።

እናንተ እንደዚያ አትሁኑ። ሁልጊዜ በመብራታችሁ ውስጥ ዘይት ይኑራችሁ። ዘይት መንፈስ ወይም መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ውስጥ እንዲጠፋ አታድርጉ። ፍቅራችሁ እየቀዘቀዘ ሲሄድ ሲሰማችሁ፤ ለክርስቶስ ያላችሁ ቅናት እየበረደ ሲሄድባችሁ የማያልቅ የዘይት ምንጭ ወዳለው ወደ እርሱ ሄዳችሁ እንደገና የመንፈስ ቅዱስን ሙላት ግዙ።

መግዛት ማለት ዋጋ ትከፍላላችሁ ማለት ነው።

የምትከፍሉት ዋጋ ምን እንደሆነ ማወቅ ከፈለጋችሁ በቤተክርስቲያን ዘንድ መገፋት እና መወገዝ ነው።

59-0628 ጥያቄዎችና መልሶች

ዕቃዎቹ… የብሉይ ኪዳን ድንኳን ውስጥ መሰውያው ዕቃዎችን ሁሉ ይቀድሳቸዋል፤ ከዚያም ዕቃዎቹ ለአገልግሎት ተለይተው ይቀመጣሉ። በተሞሉ ጊዜ ለአገልግሎት ዝግጁ ናቸው።

… ልብ በ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘይት የምን ምሳሌ ነው? ልትነግሩኝ ትችላላችሁ? [ጉባኤው “መንፈስ ቅዱስ” በማለት ይመልሳሉ።] መንፈስ ቅዱስ። ንጹህ እና የተቀደሳችሁ ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ላይኖር ይችላል። መንጻትን ብቻ ነጽታችኋል።

አሁን ተመልከቱ። አሁን ይህን ጠርሙስ ልወስደው ነው። ይህ ጠርሙስ መጀመሪያ ከቤት ውጭ ወድቆ በቆሻሻ ተሞልቷል። ከወደቀበት ሳነሳው ይህ መጽደቅ ይባላል፤ “ይህንን ሐጥያተኛ ልጠቀምበት ነው።” ልጠቀምበት ብፈልግ ቀጥዬ የማደርገው ነገር ጠርሙሱን ማንጻት ነው። ከዚያ ካነጻሁት በኋላ ምን አደርገዋለው? እቀድሰዋለው። “መቀደስ” የሚለው ቃል በትርጉሙ “ማንጻት” ከሚለው ጋር አንድ ነው ስለዚህ ቅዱስ ማድረግ ነው። “መቀደስ” የሚለው ቃል “ማንጻት እና ለአገልግሎት መለየት” ነው።

ቃሉ እንደሚለው “ስለ ጽድቅ የሚራቡ እና የሚጠሙ ብጹዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና” ማለትም ለአገልግሎት ይመረጣሉ።

 

ንሰሃ በገባህና በዳንክ ጊዜ ለመዳን የሚሰጥህ የመንፈስ ቅዱስ መጠን አለ።

ከዚያ በኋላ ልብህን ለማንጻት እና በቅድስና እንድትኖር ለማስቻል መንፈስ ቅዱስ እንደገና ይሰጥሃል።

እንግዲህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምንድነው?

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

መንፈስ ቅዱስ ከሚሰራቸው ሥራዎች ሁሉ ከባዱ ሥራ ይህ ነው። መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት አንብበን መረዳት እንችል ዘንድ አስተሳሰባችንን ያሳድገዋል።

በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይህ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የተደረገው።

በአንበሳው ዘመን ማለትም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተከሏት።

በስተመጨረሻ በ1903 አሜሪካውያኑ ወንድማማቾች የመጀመሪያውን አውሮፕላን ሰርተው የበረሩ ጊዜ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም የሚበርረው የንስር ዘመን ውስጥ የመጨረሻው ዘመን ነብይ አማኞችን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ ጀመረ። እርሱም ከ1965 ጀምሮ ከዚህ ዓለም ተሰናበተ፤ ነገር ግን በድምጽ የተቀረጹ መልእክቶቹ እስከ ዛሬ ድረስ የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት አድርገን መረዳት እንደምንችል ያስተምሩናል። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የምንማርበት ወቅት የቀደመው ዝናብ ወይም የትምሕርት ዝናብ ይባላል።

ይህ እውነት ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ባሉት በአራቱ እንስሳት አማካኝነት ተገልጧል።

ራዕይ4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

 

ሙሽራይቱን በአንበሳው ዘመን ወደ ነበረችው ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እና በሐዋርያት አገልግሎት አማካኝነት ወደተሰጣት የእግዚአብሔር ቃል እውነት ሊመልሳት የሚችለው ልዩ የማየት ችሎታ ያለው ንሥሩ ብቻ ነው።

በጥጃው ዘመን ማለትም በጨለማው ዘመን ውስጥ እውነት ጠፍታ ነበር። ከአራቱ እንስሳት ውስጥ በሰው የተወከለው ዘመን ደግሞ እንደ ሉተር እና ዌስሊ የመሳሰሉ ሰዎችን ጥበብ የሚገልጽ ነው፤ እነዚህ ሰዎች መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እና በቅድስና የመኖርን ትምሕርት ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው አምጥተዋል። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ጥልቅ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት አልተረዱም። ጠለቅ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚሰጥራት ያለ መለኮታዊ ጥበብ ሊገለጡ አይችሉም፤ ምክንያቱም የሰው ጥበብ እነዚህን ሚስጥራት በትክክል ሊተረጉማቸው አይችልም።

ሚስጥራቱን በትክክል ለመረዳት መጀመሪያ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ አፈታት መሰረት መጣል ያስፈልጋል፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ዝርዝር ሃሳብ በዚህ መሰረት ላይ ይገጥማል።

ኖህ መርከቡን በሰራ ጊዜ መጀመሪያ የመርከቡን የታችኛ መሰረት አዘጋጀ፤ ከዚያ በኋላ የመርከቡ ግርግዳዎች እና ሌሎች ክፍሎች ሁሉ ስፋቱ፣ ከፍታው፣ ጥልቀቱ ሁሉ በመሰረቱ ላይ ይጋጠማል። ይህን ማድረግ የሚችለው ከእግዚአብሔር መልእክት የተቀበለ ነብይ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ የኖህ ልጆች በመርከቡ መሰረት ላይ ጣውላዎችን በሚስማር እየመቱ ገጣጠሙ። እነርሱ የሰሩት ሥራ ኖህ ባዘጋጀላቸው መሰረት ላይ ዝርዝሮችን መግጠም ብቻ ነው። ወንድም ብራንሐም ዋነኞቹን መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አሳይቶናል። የእኛ ሥራ እርሱ ባስቀመጠልን የሚስጥራት መሰረት ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች እያመጣን መገጣጠም ነው።

ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ሚስጥራት በመጨረሻው ዘመን ብቻ ነው የሚገለጡት።

ስለዚህ አሁን የምንኖርበት ዘመን በጣም ወሳኝ ዘመን ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለዳንኤል በግልጽ የነገረው ስለዚህ ዘመን ነው።

የመጨረሻውን ዘመን ሚስጥራት መረዳት እኛ ከምናስበው በላይ በጣም አስፈላጊ ነው።

እነዚህን ሚስጥራት መግለጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ አለው። ለዚህ ነው ለዘመኑ መጨረሻ መንፈሱን በንስር መልክ ሊገልጥ ተስፋ የሰጠን።

የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለመውደድ ራሳችንን ማለማመድ አለብን።

ስለዚህ ከዳንን እና ከተቀደስን በኋላ የቀደመ አስተሳሰባችንን አፈራርሶ፤ የቀደመውን ተሳሳተ መረዳታችንን ሰርዞ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ትከተለው በነበረው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ለመተካት ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይጠይቃል።

2ኛ ተሰሎንቄ 2፡10 ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።

መዳን ወደ መንግስተ ሰማያት ያስገባናል ግን የሙሽራይቱ አካል አያደርገንም።

በቅድስና መኖር ከሕሊናችን ኩነኔ ነጻ ያወጣናል ግን የሙሽራይቱ አካል አያደርገንም።

ኢየሱስ የሚፈልገው የእርሱን ሃሳብ በአድናቆት የሚከተሉ ሰዎችን ነው፤ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚወዱ ሰዎችን ነው።

ኢየሱስ ለሰዎች ያለውን እቅድ የሚወዱ ሰዎችን ይፈልጋል።

 

የመንፈስ ቅዱስን ተጨማሪ ጣልቃ ገብነት የሚፈልጉ ሶስት የሎዶዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ባሕርያት አሉ።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

18 ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።

“በእሳት የነጠረውን ወርቅ ግዛ”። መንፈስ ቅዱስ ስደትን፣ መሰደብን፣ መገፋትን ለመቋቋም የሚያስችል ብቃት ሊሰጠን ያስፈልገናል። በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ባገኙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሃሳቦች ግፊት ሲደረግብን ለመቋቋም ኃይል ሊሰጠን ያስፈልገናል። ከቤተክርስቲያን እና ከፓስተሩ ጋር ለመቃረን አቅም ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመሆን ፍላጎት ስላለን በመንጻት ሂደት ውስጥ ማለፍ ያስፈልገናል። ስለዚህ በውስጣችን ያሉትን ቆሻሻዎች አቃጥሎ የሚያወጣውን እና እምነታችንን የሚያጠራውን የመከራ እሳት የምንታገስበት አቅም ያስፈልገናል። አቅም እና መልካም ባሕርይ የሚቀረጹት በሽንፈት እን በመከራ ውስጥ ነው። ይህም አቅም ስለ እውነት ብሎ ሲደበደቡ የመታገስ ብቃት ነው።

“ነጭ ልብስ”። የእግዚአብሔር ጽድቅ። ሰባተኛው ዘመን ስለ ምድራዊ ኪሳራችንም ሆነ ስኬታችን ሳይሆን ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት መመለሳችን መሆኑን መረዳት ነው። በቤተክርስቲያን አባልነታችን ወቅት የተቀበልናቸውን ብዙ አለማመን እና የተሳሳቱ አስተምሕሮዎች ሁሉ አራግፈን መጣል አለብን። ስሕተታችንን ለማጽደቅ መሞከር ትተን ለመታረም ፈቃደኛ እና ዝግጁ መሆን አለብን። በትዕቢት የተሞላው ፊኛችን ተበስቶ መተንፈስ አለበት። ይህም እንዲሆን እኛ ብዙ መቅናት እና ንሰሃ መግባት ይጠበቅብናል። ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናትን በሚሸፍነው የእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ እና ትንሽዬ ክፍል ነን። በቃሉ ውስጥ ከሚፈስሰው የእግዚአብሔር የሕይወት ወንዝ ጋር መስማማት አለብን እንጂ ከቤተክርስቲያናችን ትንሽ የአመለካከት ኩሬ ጋር አይደለም። 45,000 ዓይነት የቤተክርስቲያን ኩሬዎች አሉ።

 

 

ስለ ወደፊቱ ምንም እንድንወስን አልተሰጠንም ምክንያቱም በስተመጨረሻ የሚታጨደው ዘር መጀመሪያ በሐዋርያቱ አማካኝነት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተዘራውን ዘር መምሰል እንዳለበት ተወስኗል። ስለዚህ የመጀመሪያ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነቷ ምን ይመስል እንደነበረ ለማወቅ በትጋት መመርመር አለብን፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ቃል መለወጥም ሆነ ቸል ማለት የለብንም።

“ዓይናችንን ኩል መቀባት” የሚያስፈልገን የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ እውነቶች በጥልቀት ማየት እንድንችል እና ለዳግም ምጻት ለመዘጋጀት የሚረዱንን ከባድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለመረዳት እንድንችል ነው። ይህ እውነትን ምን ያህል እንደምንወድ የሚታወቅበት እውነተኛ ፈተና ነው ምክንያቱም ቤተክርስቲያኖች እነዚህን ጠለቅ ያሉ እውነቶች ይነቅፋሉ ለመቀበልም እምቢ ይላሉ። ስለዚህ በእያንዳንዱ እርምጃችን ተቃውሞ ይገጥመናል፤ እኛ ግን በእያንዳንዱ እርምጃችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለብን። ሁልጊዜ ጥያቄ መጠየቅ እና መልስ መፈለግ አለብን። ስሕተት ልንሰራ የምንችለው ትክክለኛውን ጥያቄ የምንጠይቅበት ጥበብ ሲጎድለን ነው። ስሕተት በሰራን ቁጥር ልብ ብለን ካደመጥን ከስሕተታችን ትምሕርት እንማራለን። መሃንዲሶች አደጋ ከደረሰ በኋላ አደጋውን በመመርመር ብዙ ይማራሉ ምክንያቱም አደጋው በምን ምክንያት እንደመጣ ያያሉ። እኛም ከስሕተታችን እንማራለን።

 

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

ጠለቅ ያሉ እውነቶችን መረዳት እንድንችል እግዚአብሔር ስለ ተሳሳቱ እምነቶችችን ሊገስጸን ይገባል፤ ከዚያም በኋላ ከፊታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች ዝግጁ እንሆን ዘንድ ሊቀጣንና ሊገርፈን ያስፈልገናል። ይህ ቀላል መንገድ አይደለም።

 

ለመዳን እና በቅድስና ለመኖር የምንቀበለው የመንፈስ ቅዱስ መጠን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመግለጥ የሚበቃ አይደለም።

የተገለጠውን እውነት ማየት እንችል ዘንድ ብዙ የዓይን ኩል ያስፈልገናል።

እውነትን ከመረዳት የሚያግዱንን ብዙ የተሳሳቱ ሃሳቦች እንጥል ዘንድ እኛን ለመገሰጽ ብዙ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል።

ከዚያም እኛን ለመቅጣትና ለማቃናትም ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገናል ምክንያቱም እኛ የቤተክርስቲያን አባል መሆን ስለምንፈልግ በቀላሉ በቤተክርስቲያን እና በዓለማዊ ልማዶች እንሳባለን። ሰዎች እንዳይገፉን ደግሞ በጣም ስለምንፈራ ከቤተክርስቲያን ፓስተሮች ጋር መከራከርም በጣም እንፈራለን። አቅም ይጎድለናል። ከቤተክርስቲያን መባረር በጣም እንፈራለን። ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ የመሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን ባይኖረውም እንኳ እንፈራዋለን።

 

ለመዳን አንድ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገናል፤ በቅድስና ለመኖር ደግሞ ሌላ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገናል።

ይህም ሁለት መጠን ማለት ነው።

በዚህ ብቻ ከቆምን ከሰነፎቹ ቆነጃጅት መካከል እንቆጠራለን። እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ከሆንን በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በደስታ ማገልገል እንችላለን ግን ሰዎች ለመረዳት የሚከብዷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቸል እያልን እንኖራለን።

 

መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ መረዳት ከፈለግን ተጨማሪ ሶስት የመንፈስ ቅዱስ መጠን መቀበል ያስፈልገናል።

አንድ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ከፓስተሩ ጋር ለመቃረን ያስፈልገናል።

ሌላ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ደግሞ የተገለጠውን ቃል ማየት እንድንችል ዓይናችን ይበራ ዘንድ ያስፈልገናል።

ከዚያም ሌላ የመንፈስ ቅዱስ መጠን የሚያስፈልገን ደግሞ የራሳችንን እምነቶች ለመመርመር የሚያስችለን ጥበብ ይኖረን ዘንድ እና ብዙዎቹን ስሕተቶቻችንን ለማመን የሚያበቃን ትሕትና ይኖረን ዘንድ ነው።

ይህም ማለት የሙሽራይቱ አካል መሆን ከፈለግን በአጠቃላይ አምስት የመንፈስ ቅዱስ መጠን ያስፈልገናል።

 

ብልጥ ሰዎች የሌሎች ሰዎችን እምነት ይመረምራሉ።

ልባም ሰው ብቻ ነው የራሱን እምነት የሚመረምረው።

በዚህ ሂደት ውስጥ እንማራለን፤ የቀደመ የተሳሳተ እውቀታችንን እንጥላለን፤ እንደገና እንማራለን።

ዛሬ ቶሎ ቶሎ ስራ በምንቀያይርበት ዘመን ውስጥ የሚያስፈልገን አቋም ይህ ዓይነት ነው።

ደግሞም እንዲህ ዓይነቱ አቋም ብቻ ነው መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን ለመረዳት እስክንችል ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን የተከፈተ መጽሐፍ የሚያደርግልን።

ዳንኤል 12፡10 ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ።

“የሚነጹት” በእግዚአብሔር እጅ ተቀጥቅጠው ብዙ ስንፍና ሲራገፍላቸው ነው።

“ያነጡማል” ወይም ነጭ ይሆናሉ የሚለው ከራሳችን በጣም የሚበልጠው የእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ አካል ስንሆን ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር ካልተረዳን እና በውስጡ ስፍራችንን እስካላገኘን ድረስ ልባሞቹ ቆነጃጅት ልንሆን አንችልም።

“ይነጥሩማል”። አስተሳሰባችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ሃሳቦች መንጻት አለበት። በስሕተት እና በመገፋት እቶን እሳት ውስጥ እንፈተናለን። በዓለም ላይ 45,000 ዓይነት መልካም የሚመስሉ ሁላቸውም ግን ሊያስቱን የተዘጋጁ ቤተክርስቲያኖች አሉ።

ሙሽራይቱ ተጠንቅቃ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር ካልተጣበቀች በቀር ቤተክርስቲያኖች ሙሽራይቱን ለማሳሳት ያዘጋጁት ብዙ የሚያደናግሩ የስሕተት ትምሕርቶች አሏቸው።

እግዚአብሔር ግን እስከ መጨረሻው ድረስ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንዲችሉ መንገዱን ክፍት አድርጎላቸዋል። ሆኖም አዘውትረው የሚጠይቁ እና እምነታቸውን የሚፈትሹ ሰዎች ናቸው ወደ መረዳት የሚመጡት።

የተቀሩት በሙሉ በተደላደሉ የቤተክርስቲያን ቡድኖቻቸው ውስጥ ሆነው እንቅልፋቸውን ይተኛሉ።

ማቴዎስ 25፡2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።

በመጀመሪያው የባቢሎን አሕዛብ ዘመን መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ጣት ግርግዳ ላይ ጻፈች።

ዳንኤል 5፡27 ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው።

በአሕዛብ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር የሎዶቅያውያንን ቤተክርስቲያን ይመዝንና ቀልለው ያገኛቸዋል። እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳችም መልካም ነገር አልተናገረም።

እያንዳንዱ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል መሰረት መመዘን አለበት።

ሰነፎቹ ወይም የተታለሉት ቆነጃጅት ፓስተሮቻቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት አላስተማሯቸውም።

ለምን? ምክንያቱም ፓስተሮች እጅግ መሃይም ከመሆናቸው የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት አያውቁም፤ ደግሞም ለመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ዕድል አይሰጡም ምክንያቱም ፓስተሮች ሁሉን አዋቂ የቤተክርስቲያን ራስ ሆነው መታየት ይፈልጋሉ። ሰው የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት አይደለም።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ …

ከዚህ የተነሳ የዘመን መጨረሻ ክስተቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር መተንተን አይችሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው እጅግ አናሳ ነው። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በተለይም የዳንኤል ትንቢት እና የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የተጻፈውን መረዳት አይችሉም።

ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር አያሸንፍም፤ ሒላሪ ክሊንተን ታሸንፈዋለች ብለው ሲተነብዩ የነበሩ የሜሴጅ ፓስተሮች ከእግዚአብሔር ሃሳብ ምን ያህል ርቀው መሄዳቸውን ያሳያል።

እነዚህን ሰዎች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ የሚያስገባቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውጭ ማሰብና መናገር እንዲሁም በሰው ንግግር ጥቅሶች መጠመዳቸው ነው።

60-1204 በፍጥሞና የታየው ራዕይ

ልብ ብላችሁ ብታዩ አምስት ሰነፍ ቆነጃጅት እና አምስት ልባም ቆነጃጅት ነበሩ፤ እነዚህ ቆነጃጅት ሁሉ አንድ ዓይነት ሴቶች ናቸው። ነገር ግን ስለ ምርጫ ስናስብ እግዚአብሔር ሙሽራይቱን ከዓለም መፈጠር በፊት አስቀድሞ መርጧታል፤ በሙሽራይቱ አካል ውስጥ የሚሆኑትን ሰዎች ከዓለም መፈጠር በፊት በታረደው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ስማቸውን ጽፏል፤ ዓለም ገና ሳይጀምር በፊት እግዚአብሔር በአእምሮው ውስጥ አስቀድሞ ወስኗቸዋል።

… ስለዚህ አሁን ብቸኛው የእውነት ማረጋገጫ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መምጣት ነው፤

ሙሽራይቱም ሆነች ሰነፎቹ ቆነጃጅት በሙሉ ንጹህና ታማኝ ሰዎች ናቸው።

ነገር ግን በዚህ የውሸት ዜና በብዛት በሚሰራጭበት ዘመን ውስጥ ሙሽራይቱ ብቻ ናት የእውነትን መረጃ የመሰብሰብና እውቀቷን የማሳደግ ፍላጎት ያላት። ሙሽራይቱ ብቻ ናት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ከባድ ጥቅሶች ለመረዳት፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሁሉ በአንድ ላይ ለማገጣጠም፤ ወንድም ብራንሐም ያስተማራቸውን ትምሕርቶች ሁሉ እንዴት ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ፈትሸን መግለጥ እንደምንችል ለማወቅ ፍላጎት ያላት። ሙሽራይቱ ብቻ ናት መጽሐፍ ቅዱስን ብቸኛ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል አድርጋ የምትቀበል፤ ስለዚህ እያንዳንዱን ቃል እና ነጥብ ሁሉ ታምናለች። አንድም ነገር አትጠራጠርም።

የሙሽራይቱ አካላት የግል ድክመት ቢኖርባቸውም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ከልባቸው ያምናሉ። በሌላ አነጋገር ልክ ኢየሱስን ፍጹም የሆነ አዳኝ አድርገው እንደሚመለከቱ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስንም ፍጹም እና የእምነታቸው ምንጭ አድርገው ይመለከታሉ።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማንኛውም መንገድ የምትነቅፉ ከሆነ ኢየሱስን መንቀፋችሁ ነው። ይህም ስሕተት ነው።

ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ወሬዎችን ሁሉ ለይታ መጣል አለባት። የዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ቁልፍ ነጥብ ላይ ትኩረት መስጠት ትችላለች። የሕይወት ወንዝ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መሆኑን በመረዳት ሙሽራይቱ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየገጣጠመች እውነቱን ወደ ማወቅ ትመጣለች እንጂ የጥቅስ ኩሬዎች ውስጥ አትምቦጫረቅም።

ወንድም ብራንሐም ስሕተት ከሰራ ሙሽራይቱ ስሕተቱን አርማ በትክክል ካስተማረው ትምሕርት ጋር መንገዷን ትቀጥላለች። የሙሽራይቱ አካላት ስሕተትን ትክክል ነው እያሉ በመደገፍ ጊዜያቸውን አያባክኑም። ግሪኮች ስሕተትን በመደገፍ የተዋጣላቸው ነበሩ። ለዚህ ነው የግሪክ ቋንቋ በ325 ዓ.ም ከተደረገው ከኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን አሰናክሎ ላስቀራት የሥላሴ አስተምሕሮ በር የከፈተው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኘው ሥላሴ የተባለው ቃል ወደ ቤተክርስቲያን ከገባ ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ መውደቅ ጀመረች። ስሕተትን መደገፍ እውነትን መካድ ነው።

 

 

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ያለባቸው ችግር በራሳቸው ከመተማመናቸው የተነሳ እሳሳት ይሆን ብለው አለመጠየቃቸው ነው። በእውነት ፈንታ ፕሮፓጋንዳ ተከትለዋል።

የዮሐንስ ራዕይ በግሪክ አፖካሊፕስ ይበላል፤ ትርጉሙም መገለጥ ማለት ነው።

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይበልጥ እየተማርን ስንሄድ ጥቅሶቹን እርስ በራሳቸው ማገጣጠም እየለመድን እንሄዳለን፤ ከዚያም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ በግልጽ ማየት እንችላለን።

 

ስምህ በመጽሐፍ ውስጥ ከተጻፈ ያንን መጽሐፍ ለማንበብ ትልቅ ፍላጎት ያድርብሃል።

የበጉ የሕይወት መጽሐፍ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በጣም የምትወደው ከሆነ ስምህ በሕይወት የተጻፈ መሆኑን የሚያሳየው ምልክት መጽሐፍ ቅዱስን መውደድህ ነው።

አንድ ቀን ስምህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትጋ ተሰውሮ እንደተቀመጠ እግዚአብሔር ያሳይሃል።

ማቴዎስ 25፡3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ሁለት ችግር አለባቸው።

በመብራታቸው ውስጥ ለመዳን እና በቅድስና ለመኖር የሚበቃ ዘይት ብቻ ነው የነበራቸው። በቸልተኛ ቤተክርስቲያኖቻቸው ውስጥ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ መረዳት አስፈላጊ መሆኑ አልታያቸውም ነበር። ሲኖሩ የቆዩት በሰው ጥቅሶችና በሰው አመለካከቶች ነበር። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያናቸው ትክክል ስለመሆንዋ እና እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ሊገናኙ ዝግጁ የሆኑ መሰላቸው።

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ ለመረዳት ያስችላቸው ዘንድ የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ እገዛ እንደሚያስፈልጋለቸው አልተሰማቸውም።

ሮሜ 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።

አንዳንድ ሰዎች እውነተኛ አማኞች ባይሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን በሆነ መንገድ እንዲያገለግሉት ይቀባቸዋል።

ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

“ሐሰተኛ ክርስቶሶች”።

ማቴዎስ 24፡24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።

ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነው። ቅባቱ ትክክለኛ ነው ስለዚህ ተዓምራትን ማድረግ ይችላል፤ ነገር ግን በነፍሳቸው ውስጥ የሚበቅለው ዘር ትክክለኛ አይደለም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል አይደለም። ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን ያምናሉ።

ከበድ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አንብበው ለመረዳት የሚያስፈልገው መንፈሳዊ ብርሃን የላቸውም።

ማቴዎስ 24፡25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።

እነዚህ ሐሰተኛ ክርስቶሶች እንዴት ነው የሚያስቱን?

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 በሳንሴት ፒክ አሪዞና የተከሰተው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የጌታ ምጻት ነው ብለው እየተናገሩ ነው የሚያስቱን።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ኢየሱስ በበረሃ አይመጣም። ሳንሴት ፒክ የሚገኘው ታላቁ የሶኖራን በረሃ ውስጥ ነው።

 

 

በመላእክቱ ክንፍ የተፈጠረው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የታየው በሳንሴት ፒክ አልነበረም። ደመናው ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ለ28 ደቂቃ ብቻ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ሰሜን ታይቶ ፎቶግራፍ ተነስቷል፤ ይህም ቦታ ደግሞ በረሃ ውስጥ አይደለም።

ይህ ሁሉ የሚያሳየን ፓስተሮች ሰው የተናገረውን ሲጠቅሱ ምን ያህል እንደሚምታታባቸው ነው።

ወንድም ብራንሐም ደመናው የጌታ ምጻት ነው ብሎ አያውቅም።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ይታለላሉ ምክንያቱም ምንጩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልሆነ ሐሰተኛ ወሬ ያሰራጫሉ።

የሜሴጅ ተከታዮች ለዓመታት ሲያምኑበት የቆዩትን ፎቶ ከዚህ በታች ተመልከቱ።

 

 

ደመናው ፎቶግራፍ የተነሳበት ቦታ ከፍላግስታፍ በስተ ሰሜን ሲሆን ይህም ቦታ ከሳንሴት ፒክ በ200 ማይልስ ይርቃል። ስለዚህ ደመናው ከሳንሴት ፒክ ከተማ በላይ አልታየም። ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከስምንት ቀናት በኋላ መላእክቱ በሳንሴት ፒክ ከተማ ወንድም ብራንሐምን ጎበኙ።

 

በአስሩ ቆነጃጅት ምሳሌ ውስጥ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ትልቅ ስሕተት ሰርተዋል። ያለ ምንም ዝግጅት እንደነበሩ ሆነው ሄዱ።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት የሆነ አንድ ቤተክርስቲያን አባላት በመሆናቸው ብቻ ለጌታ ምጻት ዝግጁ እንደሆኑ እንዲሰማቸው አድርገው ያታለሉዋቸው ፓስተሮቻቸው ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስን ስላለማወቃቸው ምንም ግድ አልነበራቸውም።

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ስለሚያስፈልጋቸው ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ መጠን ምንም አያውቁም ነበር።

ዘይት እየተቃጠለ ብርሃን ይሰጣል።

ጥልቅ የሆኑትን የመጽሐፍ ሚስጥራት አንብቦ ለመረዳት እንዲያስችለን ብርሃን ይሰጠን ዘንድ የምናነደው በቂ ዘይት ሊኖረን ይገባል።

ቆነጃጅቱ መጽሐፍ ቅዱስ የተከፈተ መጽሐፍ እስኪሆንላቸው ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች መረዳት ይችሉ ዘንድ የሚያበራላቸው ብዙ ዘይት ያስፈልጋቸው ነበር።

እነርሱ ግን በነበሩበት ሁኔታ ተደላድለው ስለነበረ ስለ ወደፊቱ ምንም ዝግጅት አላደረጉም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት የሚያስቸግሩትን ክፍሎች ለማብራራት ምን ያህል ከባድ መሆኑን አልተገነዘቡም ምክንያቱም እነዚህን አስቸጋሪ ክፍሎች ሙሉ ለሙሉ ቸል ብለው ያልፏቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ከመቻላችን በፊት መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል ሊመራን እንደሚያስፈልግ አላወቁም።

ከዚህም የተነሳ መንፈስ ቅዱስን በትንሽ መጠን ከተቀበሉ በኋላ ዝም ብለው መኖራቸውን ቀጠሉ። የተቀበሉት የመንፈስ ቅዱስ መጠን ለመዳን እና በቅድስና ለመኖር የሚበቃ ብቻ ነበረ።

ድንገት ችግር ቢገጥማቸው የሚያልፉበት ተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ አልያዙም። ጠለቅ ያለ መረዳትን ለመቀበል የሚሆን ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር አልበራቸውም።

ልክ እንደዚህ ዘመን ተማሪዎች ዝቅተኛውን የማለፊያ ነጥብ ካገኘን ለማለፍ ይበቃናል ብለው ነበር የሚኖሩት።

በዝግጅታቸው ውስጥ ከባድ ስሕተት መስራታቸውን የሚገነዘቡት ቆይተው በጣም ከረፈደባቸው በኋላ ነው።

 

ማቴዎስ 25፡4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።

ልባሞቹ ቆነጃጅት ያለን እውቀት ይበቃናል ብለው አልተቀመጡም።

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ለመረዳት ያለማቋረጥ ይመረምሩ ነበር።

ይህ ጠለቅ ያለ መረዳት የሚመጣው ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ።

ልባሞቹ ቆነጃጅት የሚፈልጉት ከጌታ ጋር ጠበቅ ያለ የግል ሕብረት ለማድረግ ነው፤ ከዚህም ዓይነት ሕብረት የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታቸው እየጨመረ ይሄዳል።

መዳን እና በቅድስና መኖር በቂ አይደሉም። እነዚህ ቆነጃጅት መብራቶቻቸው በመዳን እና በቅድስና ይበሩ ነበር። ነገር ግን እንደ ማንኛውም በማስተዋል እንደሚያቅድ ሰው በሕይወታቸው ውስጥ ሁል ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ እየተሞሉ ይኖሩ ነበር። ለወደፊት ለሚያጋጥማቸው ድንገተኛ አደጋ ብለው መጠባበቂያ ሁሉ ተሞልተዋል።

ቀጥሎ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከልባቸው ይኖሩበታል።

ፊልጵስዩስ 2፡12 በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችሁ ማደግ አለበት ብለው አያምኑም፤ ምክንያቱም እውቀቱን ለማሳደግ ማንም ፍላጎት የለውም።

ከልባቸው የሚከታተሉት የሰው ንግግር ጥቅሶችን ነው።

ሙሽራይቱ ግን ወደ እግዚአብሔር ትመለከታለች እንጂ ቤተክርስቲያን ወደሚመላለሱ ሰዎች አስተሳሰብ አትመለከትም። ስለዚህ ወደ ፊት ሙሽራይቱ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት እንደሚያስፈልገን ታውቃለች፤ ያም ደግሞ ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ይጠይቃል። ከዚህም የተነሳ ሙሽራይቱ የተቻላትን ያህል ትፍር ዘይት ታስቀምጣለች።

በስተመጨረሻ በደምብ የደመቀ ብርሃን ለማብራት ብዙ ዘይት ያስፈልገናል፤ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን የተሰወሩ ሚስጥራት ለመግለጥ ይጠቅማል። አስቀድሞ ማቀድ ለወደፊት ስኬት አስፈላጊ ነው።

በሰው ውስጥ ያለው ጥልቅ በእግዚአብሔር ውስጥ ወዳለው ጥልቅ ይጣራል።

ይህም ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ በቅርበት መሄድ እና የልቡን ሃሳብ ይበልጥ ለማወቅ ይረዳል። ሙሽራይቱ የእግዚአብሔርን እቅድ ትወዳለች፤ ደግሞም እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ ለመረዳት ከሰው አእምሮ በላይ የሆነውን ሃሳቡን ውስን በሆነ መንገድ በምሳሌዎች የሚገልጥበትን አገላለጥ በአድናቆት ትመለከታለች።

ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

አሁኑኑ ጊዜ ሳለን የምንችለውን ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ከእግዚአብሔር መማድ አለብን።

ይህን ማድረግ የምነችለው ደግሞ የወንድም ብራንሐምን መገለጦች በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረን በማጥናት ብቻ ነው።

62-0531 በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ያለው ግጭት

ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ላከ፤ ያም እርሱ ራሱ ነው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “ገና ጥቂት ዘመን አለ፤ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ ምክንያቱም እስከ ዓለም ፍጻሜ እኔ በእናንተ ውስጥ ከእናንተ ጋር እሆናለው።”

አሁን አሁን አሁን ተመልከቱ። ኢየሱስ አስቀድሞ አውቆታል ስለዚህ ቃሉን ለማጽናት መንፈስ ቅዱስን ላከ። ኦ! ገብቷችኋል? [ጉባኤው “አሜን” አሉ።] አያችሁ? “ለማጽናት፤” ማለትም መታመኛቸውን በቃሉ ላይ ላደረጉ ሰዎች “እርሱ ቃሉ መሆኑን ለማጽናት።” አያችሁ?

እነርሱን ግን እዚያው ተዋቸው። በሥርዓቱ ላይ ይስቃሉ። “አብደዋል ይላሉ።”

ኢየሱስ ግን መንፈስ ቅዱስን የላከው ማለትም እራሱን በቃሉ ለሚታመኑ ሰዎች ብሎ ነው፤ ልክ ለአብራሐም እንዳሳየው በቃሉ ለሚታመኑ ሰዎች ዛሬም እርሱ ራሱ ቃሉ መሆኑን ያጸናላቸዋል። በትክክለኛ ሥፍራ መቆማችሁን አረጋግጡ።

ነገር ግን እናምናለን ብለው የሚናገሩ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ። አንዱ “እንግዲህ ቤተክርስቲያን ማለት እኛ ነን” ይላል። ሌላው ደግሞ “ቤተክርስቲያን እኛ ነን” ይላል።

[ሙሽራይቱም ሰነፎቹ ቆነጃጅትም ቤተክርስቲያን እኛ ነን ይላሉ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ቤተክርስቲያን እኛ ነን ትላለች። ስለዚህ ሰዎች ስለ ራሳቸው ቤተክርስቲያን እያደነቁ የሚያወሩትን መስማት ምንም አይጠቅምም።]

… ሰይጣን ግን ከእኛ በላይ ብልጥ ነው። ይህን በደምብ እናውቃለን። ሰይጣን ከየትኛውም ሰው በላይ ብልጥ መሆኑን እናውቃለን። በራሳችሁ ጥበብ እናሸንፈዋለን ብላችሁ እንዳትሞክሩ። ምክንያቱም በራሳችሁ አትችሉትም።

ኢየሱስ ይህንን ያወቃል፤ ስለዚህ ለቤተክርስቲያን ከሰይጣን ተንኮል የምታመልጥበትን መሸሸጊያ ላከላት። መንፈስ ቅዱስን ላከላት።

ቤተክርስቲያንም ብልጥ ነኝ አትልም። አምናለው ብቻ ይላሉ እንጂ።

 

በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያለው ትልቁ አደጋ ፓስተሮች የሰውን ንግግር ሰነጣጥቀው በመገጣጠማቸው ራሳቸውን አስተዋይ አድርገው በመቁጠራቸው ጠቢብ እንደሆኑ አድርገው ማሰባቸው ነው።

ትልቁ ጥማታቸው እራሳቸውን “ብልህ” አድርገው ማስጠራት ነው።

ነገር ግን ማንም ሰው ብልህ ስለሆነ አልዳነም።

 

ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

የመጨረሻው ዘመን ፈተና ትዕግስት ነው። ኢየሱስ ከመምጣት ዘገየ።

በመጨረሻ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ልባሞችም ሰነፎችም እንቅልፋቸውን ተኙ። ደግሞም ዕውር ተብለው ተጠርተዋል።

ነገር ግን ሁሉም ቤተክርስቲያኖች እራሳቸውን ዝግጁ እና ንቁ እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ።

ማንም ግድ የለውም። ሁሉም በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ በማሰብ ይመካሉ፤ እርማት ወይም ትምሕርት እንደሚያስፈልጋቸው አያስቡም።

የትኞቹም ቤተክርስቲያኖች ተሳስተው እንደሆን አያሳስባቸውም።

ከዚህ በታች የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቤተክርስቲያኖችንም ምንም አላሳሰባቸውም።

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

45,000 ዓይነት ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች በሞሎሉበት ምድር ላይ በጣም ብዙ ስሕተት ይኖራል።

ብዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ጅል የሚመስሉ አስተምሕሮዎችን ለራሳቸው አበጅተዋል።

ለምሳሌ፡- “ጌታ እንደ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሆኖ በ1963 መጥቷል”።

ይህ ከሆነ 60 ዓመታት ቢያልፉ እስከ ዛሬ ምንም ነገር አልተፈጠረም።

ይህ ዓይነቱ እምነት ወንድም ብራንሐም ስለ ጌታ ምጻት የተናገረውን ብዙ ነገር ባለማስተዋል የመጣ ነው።

ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አምስት ወራት በፊት እንኳ የጌታን መምጣት ገና ሲጠባበቅ ነበረ።

65-0725 በተራራው ላይ ያለው መስሕብ ምንድነው

ብፕሬስኮት አሪዞና ተራሮች ውስጥ ላለው ወንድም ሊዮ መርሲየ እና ለወገኖቹ እዚያው ሆነው የጌታን ምጻት በሚጠባበቁበት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። በታክሰን ውስጥ ሆነው ዛሬ ማታ ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ሂውስተን ቴክሳስ ውስጥ ሆነው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ቺካጎ ውስጥ ሆነው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። በምስራቅም ደግሞ ኒው ዮርክ እና ኮኔቲከት በታላቅ ጉባኤ ተሰብሰበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁ ሰላምታ እንልክላቸዋለን። እነርሱ ሁሉ ወደዚህ ቢመጡ የሚቀመጡበት ቦታ አይገኝም፤ ስለዚህ መልእክታችንን በስልክ ነው የምንልክላቸው። ለወንድም ጁንየር ጃክሰን እና በክላርክስቪል ለተሰበሰቡ ወገኖቹ ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ለወንድም ራድል እና ለወገኖቹም የጌታን ምጻት እየተጠባበቁ ባሉበት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። እኛ ደግሞ በዚህ ተሰብስበን የጌታን ምጻት እየተጠባበቅን ነን

 

ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም የጌታ ምጻት ገና ወደ ፊት እንደሚሆን እየተጠባበቀ ነበር።

1964-07-19 የመለከት በዓል

ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም፤ ይህ ታውቃላችሁ አይደል። ሰባተኛው መለከት የጌታ ምጻት ነው።

ወንድም ብራንሐም በሕይወቱ ሳለ ጌታ መጥቷል ብሎ አያውቅም።

 

ሌላኛው ትልቅ ስሕተት ደግሞ ይህ ነው፡-

“የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወንድም ብራንሐም በሕይወት ሳለ መጥቷል።”

መልአኩ ግን መጥቶ ቢሆን እንኳ ላለፉት ስልሳ ዓመታት ምንም የሚታይ ነገር አላደረገም።

ይህ መልአክ ወደ ምድር በሚወርድበት ጊዜ ሙታንን ያስነሳል።

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ወንድም ብራንሐም ይህንን የተናገረው ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።

ስዚህ ደመናው መልአኩ አለመሆኑ ግልጽ ነው።

የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ገና አልተፈጸመም። ስለዚህ መልአኩ በወንድም ብራንሐም የሕይወት ዘመን ውስጥ አልመጣም ማለት ነው።

 

የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች የሚያምኑት ሌላው አሳዛኝ ስሕተት ይህ ነው፡-

“ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ተናግረዋል”።

ወንድም ብራንሐም እንዲህ ብሎ አላስተማረም።

 

ሌላው ስሕተት ደግሞ ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት የመለኮት አካል ነው ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብሎ ሰውየውን ወደ አምላክነት ከፍ ማድረግ ነው።

61-0611 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 1

በዚህም ምክንያት አገልግሎቴን ላቆም ነው ብዬ ለመናገር ተገድጃለው ምክንያቱም በሕዝቡ መካከል እንዲህ ዓይነት ውሳኔ እንዳደርግ የሚገፋፋ ነገር ሰምቻለው፤ እርሱም “ወንድም” ወይም “አገልጋይ” ከመሆን ተራ አውጥተው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እያሉ ስለ እኔ እስከ ማውራት ደርሰዋል፤ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ካሉኝ … የክርስቶስ ተቃዋሚ ሊያደርጉኝ ነው።

61-0611 ራዕይ ምዕራፍ 5 - 1

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ ዓይነት ደብዳቤዎች ደርሰውኛል፤ ከልዩ ልዩ ስፍራዎች ብዙ ስልክ ተደውሎልኛል፤ አንተ ክርስቶስ ነህ እያሉ ይጠይቁኛል። ወንድሞች ይህ አስነዋሪ፣ መጥፎ የሰይጣን ውሸት ነው።

 

ማቴዎስ 25፡6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

ታላቅ የማንቂያ ጥሪ እየመጣ ነው።

“በእኩለ ሌሊት”። ይህ በጊዜ ውስጥ ቁርጥ ያለ ቅጽበታዊ ሰዓት ነው እንጂ በብዙ ረጃጅም ዓመታት ውስጥ የሚፈጸም ነገር አይደለም።

በዘመናት ውስጥ አንድ ቀን የሆነ ወሳኝ ሰዓት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ታላቅ አደጋ ይሆናል። የሚሆነውም ነገር ሰው ሁሉ ከሚጠብቀው የተለየ ነገር ነው።

“ውካታ” የሚለው ቃል የሚያስጨንቅ ነገር እንደሚመጣ ያመለክታል።

“ውጡ”። የዚያን ጊዜ ሰዎች የትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ቢሆኑ አይጠቅማቸውም። መውጣት አለባቸው።

የምንጠባበቀው ቀጣዩ ታላቅ ክስተት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳንን ትንሳኤ ነው።

የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ በምድር መንቀጥቀጥ ታጅቦ ተፈጽሟል።

ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

የመላእክት አለቃ ድምጽ (ማለትም ኢየሱስ በመልአክ መልክ የሚገለጥበት ድምጽ) ቤተክርስቲያንን ያነቃታል ሙታንንም ያስነሳቸዋል። ነገር ግን ፍንጩን መከተል የሚችሉት መጽሐፍ ቅዱስን በበቂ የሚያውቁት ብቻ ናቸው።

የ2020 ኮሮና ቫይረስ ቤተክርስቲያኖች እንዲዘጉ በማድረግ አስደንግጧቸዋል።

በማቴዎስ 25፡6 የተጠቀሰው “ሁካታ” ከዚህም የሚበልጥ አስደንጋጭ ነገር ወደ ቤተክርስቲያን እንደሚመጣ ያመለክታል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች በስተመጨረሻ የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው እንደማያዋጡዋቸው ይገባቸዋል።

ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው በመሪነት ቦታቸው ላይ ተቀምጠው ማንቀላፋታቸውን ያያሉ።

61-0806 የዳንኤል ሰባኛው ሳምንት

ዳንኤል ምዕራፍ 12 ውስጥ ምን ብሎ እንደተናገረ ታስታውሳላችሁ፡- “በመጨረሻው ቀናት ጠቢባን ያስተውላሉ”? ለጠቢባን ተሰጥቷቸዋል።

የጥበብ መንፈስ ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚመጣው ለቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ አማካኝነት ሊያሳውቃት ነው - ለቤተክርስቲያን በምን ዓይነት ዘመን ውስጥ እንደምንኖር ሊገልጥላት ነው። ልክ ገብርኤል ወደ ዳንኤል እንደመጣ መንፈስ ቅዱስም በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ እነዚህን ታላቅ፣ ጥልቅ ሚስጥራት ሊገልጥ ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣል። አሁን ገብቷችኋል?

“መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት” በመጨረሻው ዘመን ክስተቶች መካከል በተስፋ የተሰጠው ለልባሞቹ ቆነጃጅት ነው።

ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን በአካል ሲመላለሱ በሚናገሩት ንግግር ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ ይናገራሉ።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችም የእነርሱን ንግግር መረዳት አይችሉም።

ይህም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ታላቅ ችግር እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ ያነቃቸዋል።

65-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛው ሥፍራ

በመካከላችሁ ቃሉ ብቻ እንጂ አንዳችም እርሾ አይገኝ፤ በሰማያዊ ሥፍራ፣ በበሩ እርሱ ስሙን ባኖረበት ሥፍራ ተቀምጣችኋል፡- ክርስቶስ ኢየሱስ።

እውነተኛዋ ሙሽራ ሁሉንም ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ አረጋግጣ ማየት ትፈልጋለች።

እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያረጋገጡ የእውነተኛዋ ሙሽራ አካላት ብቻ ናቸው ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን ሲናገሩ መረዳት የሚችሉት።

62-0422 የሙሽራይቱ ዛፍ መታደስ

ያ መልአክ ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ ነገር ቢናገር የእግዚአብሔር መልአክ ሊሆን አይችልም።

የትኛውም መልአክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር መናገር አይፈቀድለትም።

ይህም ሰባተኛው መልአክ የሆነውን ወንድም ብራንሐም ይጨምራል።

64-0719 የመለከት በዓል

በውስጥ ያለን ሁሉ ያለንን እንቁጠር፤ ያየነውን እና የእግዚአብሔርን ድምጽ በቃሉ ውስጥ መስማታችንን፤

መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ሰዓት ብቻ ነው እግዚአብሔር ለእኛ እየተናገረ መሆኑን እርግጠኛ መሆን የምንችለው።

64-0719 የመለከት በዓል

ይህች ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንጂ ሌላ ምንም የማታውቅ ናት። የቤተክርስቲያን ስርዓትና አወቃቀር ምንም ይሁን ምን አንዳችም አያውቁም። ለእነርሱ እንግዳ ነገር ነው። እነርሱ እርሱን እና እርሱን ብቻ ነው የሚያውቁት።

ወንድም ብራንሐም የተናገራቸውን ቃላት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስዳችሁ ፈትሻችሁ አረጋግጡ።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ አማካኝነት ሲጠራቸው በግልጽ መስማት ይቻላሉና

… ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም የእግዚአብሔር ድምጽ ሲጠራችሁ ስሙ።

 

ማቴዎስ 25፡8 ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።

 

በመብራታቸው ውስጥ ለመዳን እና ለመቀደስ የሚበቃ ዘይት ነበራቸው። ነገር ግን በመብራታቸው ውስጥ ያለው ነበልባል የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለማየት የሚበቃ ብርሃን አልሰጣቸውም።

ከዚህም የተነሳ ጠለቅ ያሉትን ሚስጥራት መገለጥ ቸል ብለዋል።

ሚስጥራቱን ለመረዳት ከፈለጉ የዊልያም ብራንሐምን ትምሕርቶች ማዳመጥ አለባቸው።

ነገር ግን ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ምንም እገዛ የሚያስፈልጋቸው አልመሰላቸውም፤ ስለዚህ ለወንድም ብራንሐም ትኩረት አልሰጡም።

ከዚህም የተነሳ በጣም ከበድ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ሲገጥሙዋቸው ብዙ ቤተክርስቲያኖች ሚስጥራቱን ለማብራራት አቅም የላቸውም።

ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያሉ ሰዎች ጠለቅ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መፍታት ባይችሉም እንኳ በራሳቸው በጣም ረክተው እየኖሩ ናቸው።

ፓስተሮቻቸው በደምብ አደርገው አደንዝዘዋቸዋል።

ሰነፍ ሰዎች ነቅተው አይጠባበቁም። የሚሰሙትን ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ አይመዝኑም።

ሙሽራይቱ ግን “ማወቅ አለብን” ትላለች።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ደግሞ “ማወቅ አለብን እንዴ?” ይላሉ።

ነውጠኞቹ የዘመን ፍጻሜ ክስተቶች እየተባባሱ ሲሄዱ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ከመንገዳቸው ብዙ መውጣቸውን ማየት ይጀምራሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳታቸውን ብንመለከት ምንም ብርሃን አላገኙም።

የዳኑ እና በቅድስና የሚኖሩ ሰዎች ለመረዳት ከባድ በሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እስካሁንም ግራ ይጋባሉ።

መዳን እና በቅድስና መኖር ብቻ የሚበቃ መስሏቸዋል።

የእግዚአብሔርን ቃል ሚስጥራት ለመረዳት የሚበቃ ብርሃን እንዲኖራችሁ ብትፈልጉ በመብራታችሁ ውስጥ እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ባላችሁ ፍቅር ውስጥ ተጨማሪ ዘይት ያስፈልጋችኋል።

2ኛ ተሰሎንቄ 2፡10 ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ …

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ከመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ቤተክርስቲያንን ወደዱ፤ ስለዚህ ከታላቁ መከራ አያመልጡም።

ከቤተክርስቲያናቸው ጋር ለመቆየት ብለው ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን የገለጠበትን ትምሕርት ቸል አሉ።

ትልቁ ስሕተታቸውም ይህ ነው።

ለእውነት ፍቅር ስለሌላቸው የግል መገለጥ መብራታቸው አንብበው መረዳት የሚያስችላቸውን ብርሃን በመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ላይ ሊያበራላቸው አልቻለም።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳትን በተመለከተ የቤተክርስቲያናቸው ብርሃን ጠፍቷል።

በሥላሴ እና በሰባት ዓመታት መከራ ካመኑ በኋላ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት መረዳት አይችሉም፤ የመጨረሻውን ዘመን ትንቢትም መረዳት አይችሉም።

የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ትርጉማቸው ምን እንደሆነ አያውቁም። እስከ መጨረሻው ድረስ ጥሩ የቤተክርስቲያን አባላት ሆነው ይቆያሉ፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳትም እንደማያስፈልጋቸው እያሰቡ ይኖራሉ። የቤተክርስቲያን ፓስተሮቻቸው የሰዎችን አመለከካትና ሰው ሰራች ልማዶችን አስተምረዋቸዋል።

የቤተክርስቲያን ፓስተሮች ጠለቅ ላሉት ሚስጥራት በራቸውን ዘግተዋል፤ በዚህ ምክንያት ነው ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ የሆነው። ለዚህ ነው የቤተክርስቲያን አባላት የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው ዝቅተኛ ሊሆን የቻለው።

መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ በቤተክርስቲያኖች እንደ ወረርሽኝ በሽታ ተስፋፍቷል።

ወደ ፊት የሚመጣ አንድ አስደንጋጭ ክስተት ከቤተክርስቲያናቸው መውጣት እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል።

አንድ ቀን ኢየሱስ ውብ ከሆነው ቤተክርስቲያናቸው በር ውጭ መሆኑን ሲያውቁ ይደነግጣሉ።

ብቻቸውን ሲወጡ ብቸኛው መሪያቸው የሚሆነው የተጻፈው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ኢየሱስን በትክክል ለማወቅ እንዲሁም ከሙታን የነተሱትን ቅዱሳን ንግግር ለመረዳት ይችሉ ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አለባቸው። ነገር ግን እነርሱ ዕድሜያቸውን ያሳለፉት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን በመንቀፍ እና ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ መመራት አለብን የሚሉ ቤተክርስቲያን የጠላቻቸውን ሰዎች በመተቸት ነው።

በዚያን ጊዜ ግን እውነትን ለማግኘት ወደነዚህ ቤተክርስቲያን “ወዳባረረቻቸው” ሰዎች መምጣት ይኖርባቸዋል።

የሰነፎቹን ቆነጃጅት አስተሳሰብ ለመለወጥ ወደፊት የሚመጣው አንድ ክስተት ምን ያህል ታላቅ እና አስደንጋጭ መሆን እንደሚያስፈልገው ማሰብ በራሱ አስገራሚ ነው። አመለካከታቸው እውነትን ሙሉ በሙሉ መቃወም የነበረ ሲሆን ወደ ፊት ግን እውነትን ለማወቅ ወደ መለመን ይለወጣል።

ምን እንደሚፈጠር ለጊዜው ባናውቅም ግን ዓለምን ሁሉ የሚያንቀጠቅጥ ታላቅ ነገር እንደሚሆን እናስባለን።

ነውጥ የሞላበት እና ግራ የሚያጋባ ጊዜ ይሆናል። ትንሳኤው በታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ታጅቦ ነው የሚመጣው።

የዚያን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃቸውን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስን የተጻፉ ጥቅሶች ለመረዳት መታወራቸውን በድንገት ይገነዘባሉ። የመጽሐፍ ቅዱስን ጠለቅ ጥቅሶች ጠለቅ ያለ ትርጉም ከመረዳት አንጻር መዳን እና መቀደስ ምንም ማለት አይደሉም።

ስለዚህ መብራታቸው ሳይጠፋ እንዲቆይ የሚረዳቸውን ተጨማሪ ዘይት በብርቱ ፈለጉ፤ መጽፍ ቅዱስን በራሳቸው አንብበው ለመረዳት በበቂ ድምቀት የመጽሐፍ ቅዱሳቸው ጥቅሶች ላይ የሚያበራ ብርሃን ፈለጉ።

ከሙሽራይቱ ዘንድ እርዳታ እና መገለጥ ለመኑ።

ማቴዎስ 25፡9 ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።

“መግዛት” ማለት ዋጋ መክፈል ነው። የሚከፈለውም ዋጋ በሰዎች ዘንድ አለመፈለግ ወይም መገፋት ነው። ዋጋው የሰዎች ፌዝ እና ስደት ነው።

ባሕር ዳርቻ ላይ መርከቦችን ለመመራት የተተከለ መብራት የሚያበራው ብርሃን በአንድ ቦታ ለብዙ ጊዜ አይቆይም።

በብርሃን ውስጥ መሆን ከፈለግን እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሲያበራልን መንቀሳቀስ አለብን።

እግዚአብሔር ከሉተር ጋር ጀርመኒ ውስጥ ነበረ ነገር ግን በጆን ዌስሊ ዘመን ደግሞ ወደ ኢንግላንድ ሄደ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ከወንድም ብራንሐም ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ ሄደ።

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እውነት እንዴት ከቦታ ወደ ቦታ እንደተዘዋወረች ተመልከቱ።

ከታች ያለው ካርት 7ቱ መልእክተኞች የኖሩባቸውን ሃገሮች ያሳያል።

የመጨረሻው እንቅስቃሴ የሚሆነው ከአሜሪካ ተነስቶ በታላቁ መከራ ዘመን ሁለቱን ነብያት ለመጥራት እንደገና ወደ እሥራኤል ነው።

 

 

እግዚአብሔር ከ1947 እስከ 1965 አሜሪካ ውስጥ ከወንድም ብራንሐም ጋር ነበረ።

ነገር ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ እንቅስቃሴውን አያቆምም? ስለዚህ እግዚአብሔር ዛሬ የት ነው?

ለእኔነት ስንሞት ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለብን፤ ምክንያቱም የራሳችን አመለካከቶች እና ልማዶች ከንቱ ናቸው። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እን በእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ ውስጥ ሥፍራችንን የምናገኘው።

እያንዳንዱ ግለሰብ በእግዚአብሔር መንፈሳዊ አካል ውስጥ የራሱን ሥፍራ ማወቅ አለበት፤ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ አካል ላለፉት 2,000 ዓመታት ቤተክርስቲያን ሆና ቆይታለች። አካሄዳችን ከጥንቷ የመጀመሪያ ዘመን ቤተክርስቲያን ጋር በአንድ መስመር ውስጥ ለመግባት መሆን አለበት።

ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ከአዲስ ኪዳን ትንሳኤ በኋላ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ማወቅ አለብን።

ትኩረታችንን ሁሉ የነጎድጓዶቹን ቃል ትርጉም ማግኘት ላይ ማድረግ አለብን፤ ምክንያቱም ከእነርሱ የምንማረው ነገር አለ።

በሆነ መንገድ እንዴት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንደሚገለጡ ማየት መቻል አለብን።

ሙሽራይቱ ጊዜዋን ሁሉ የምትሰጠው ከተሰወሩት ፍንጮች ለመማር በመሞከር ነው።

የሙሽራይቱ አካላት የሆኑ ሰዎች ሁሉ አካላቸው እንዴት ወደማይሞት አካል እንደሚለወጥ የሚያሳየቸውን መገለጥ ለመያዝ ሚስጥሩን መረዳት አለባቸው። በተለወጠው አካላቸው ውስጥ ከገቡ በኋላ ብቻ ነው ለመነጠቅ የሚሆነውን እምነት መቀበል የሚችሉት። አሁን በምንኖርበት አካል ውስጥ ሆነን መነጠቅ አንችልም።

ሙሽራይቱ በተገለጠው ቃል ውስጥ ኢየሱስን እንዴት ልታውቀው እንደምትችል መማር አለባት። ስለዚህ እነርሱ ብቻ ናቸው እርሱ እንዴት እንደሚያስብ የሚያውቁት።

ሙሽራይቱ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ አለባት። የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ ሙሽራይቱ ብቻ ናት ከእነርሱ እምነት ጋር መስማማት የምትችለው።

ወንድም ብራንሐም የመጨረሻውን ዘመን ልጆች ወደ ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ አለበት።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

64-0726 ዘመናችሁንና መልእክቱን ማስተዋል

የሰባተኛው መልአክ መልእክት የማሕተሞቹን ሚስጥር መግለጥ ነው፤ በአሥራ አንደኛው ሰዓት የመጡትን አሕዛብ ሰራተኞች ደሞዛቸውን በመጀመሪያው ሰዓት ከመጡት ሰራተኞች እኩል እንዲቀበሉ መጥራት ነው።

በአስራ አንደኛው ሰዓት የመጡት ሰራተኞች ከሁሉ መጨረሻ መጥተው ከመጀመሪያው ሰዓት ጀምሮ ሲሰሩ ከዋሉት እኩል ክፍያ መቀበላቸው ኢፍትሃዊ ይመስላል።

ነገር ግን የተሰጣቸው ክፍያ የእግዚአብሔር ሚስጥራት መገለጥ ነው።

እግዚአብሔር በስራ ስላሳለፍናቸው ሰዓታት አይደለም የሚያስበው። የሰዓታቱ ብዛት የሰው ጥረት ነው፤ እኛ ደግሞ በሥራ መዳን አንችልም።

እግዚአብሔር ከቁም ነገር የሚቆጥርልን የአስተሳሰባችንን ጥራት እና ማስተዋላችንን ነው።

የእግዚአብሔር ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲገለጥልን እርሱ የሚያስብበትን መንገድ መረዳት እንችላለንን?

ደግሞም በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ሚስጥራቱ የሚገለጡት በመጨረሻ ብቻ ነው።

የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ እንወዳለንን?

ሁልጊዜ ከተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እየተማርን መኖር እንፈልጋለንን? የእግዚአብሔር ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መከታተል እንፈልጋለንን?

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

የመጀመሪያውን ማሕተም ይፈታውና ሰባተኛውን መልአክ ይገልጠዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሚስጥራት ወደ ፍጻሜ ማምጣት ብቻ ነው የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት።

ወንድም ብራንሐም አስደናቂ አገልግሎት አገልግሏል። ግን በጣም ወሳኙ ነገር የዘመን መጨረሻ ሚስጥራትን መረዳቱ ነው።

የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለመረዳት የሚያስችል ቁልፍ ይሰጠናል።

 

አነጋገራችሁ ማንነታችሁን ያጋልጣል።

በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የተማራችሁት ትምሕርት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳታችሁ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።

የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ከሙታን ተነስተው አነጋገራችሁን ሲሰሙ ወደ እነርሱ እምነት ተመልሳችሁ መሆኑን አለመሆኑን ከአነጋገራችሁ ወዲያው ያውቁባችኋል።

ጴጥሮስ የገሊላ ሰው መሆኑን ሊክድ ሞክሮ ነበር። ኢየሱስ የተያዘበት ሰዓት አስፈሪ ነበረ።

ማቴዎስ 26፡73 ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፦ አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት።

ነገር ግን ጴጥሮስ በአነጋገሩ ተያዘ።

ስለተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የምትናገሩት ነገር በየትኛው ጎራ መሆናችሁን ያጋልጣል፤ ከሙሽራይቱ ወይም ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ወገን መሆናችሁ በንግግራችሁ ያስታውቃል።

የመጨረሻው ዘመን በጣም ነውጠኛ ይሆናል። ቤተክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል ሊያጠፉ እየሞከሩ በመሆኑ አስፈሪ ዘመን ይሆናል። ንግግራችን እውነትን ማወቃችን ወይም አለማወቃችንን ይገልጣል።

“የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” “የእግዚአብሔር ድምጽ” አይደለም።

ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብሎ መናገር ትልቅ ስሕተት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እርሱን “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ብሎ ነው የሚገልጠው።

የትኛውንም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርሱ ከተናገረው በላይ አጋነን መግለጽ የለብንም።

ቆላስይስ 2፡18 ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ።

መልአክን ማምለክ (ወንድም ብራንሐም ሰባተኛው መልአክ ነበረ) ሰዎች በቀላሉ የሚወድቁበት ስሕተት ነው።

ባለ ራዕዩ ዮሐንስ እንኳ ሳይቀር ይህንን ስሕተት ሰርቷል።

ስለዚህ እንዳታደርጉት ተጠንቀቁ።

ራዕይ 19፡10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ … አለኝ።

ከሶስት ምዕራፎች በኋላ ተመልሶ ተመሳሳይ ነገር ሲያደርግ እናገኘዋለን።

ራዕይ 22፡8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።

9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

ስለ ምስጢራቱ ያስተማረንን መልአክ ማምለክ ትልቅ ስሕተት ነው። ማምለክ ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ ነው።

ወንድም ብራንሐም እግዚአብሔር አይደለም። ስለዚህ እርሱን የእግዚአብሔር ድምጽ በማለት ከፍ ከፍ አታድርጉት።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም። ተስፋ የተሰጠን የሰባተኛው መልአክ ድምጽ እንደሚመጣ ነው።

የኢየሱስን ሃሳብ የሚገልጥልን የእግዚአብሔር ድምጽ የ1769ኙ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

64-0719 የመለከት በዓል

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተጻፈው መሰረት ሚስጥሩ ሁሉ ሲፈጸም የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር በሙሉ ለሙሽራይቱ ይገለጥላታል። ልክ አይደል ወይ? ራዕይ 10።

የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ በኩሉ ሲናገረን አይተናል፤ ሰምተንማል።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ ውስጥ ሲጠራቸው በግልጽ መስማት ይችላሉና

መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም የእግዚአብሔርን ድምጽ ዛሬ ሲጠራችሁ አድምጡ።

64-0614

መልአኩ የነገረኝ ይህንን ነው “ሰዎች እንዲያምኑህ አድርጋቸው።”

እኔም የእግዚአብሔርን ቃል ብናገር “እመኑኝ” ብዬ አይደለም የምናገረው፤ “ቃሉን እመኑ” ብዬ እንጂ።

ወንድም ብራንሐምን እንድታምኑ ማንም አይጠይቃችሁም።

እንድታምኑ የተጠየቃችሁት እርሱ ያብራራውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው።

64-0823 ጥያቄዎች እና መልሶች - 1

ቃሉን በሙላቱ መቀበል የሚችሉ ሰዎች እኔ ስለተናገርኩት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ነው የሚቀበሉት። የሚቀበሉት ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃ አስቀድሞ ተናግሯል።

አንድ ነገር የምታምኑት ወንድም ብራንሐም ስለተናገረ ከሆነ በእውነት ላይ ባላችሁ አቋም ተሳስታችኋል። እርሱ የተናገረውን ማመን ያለባችሁ እርሱ የተናገረው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ መሆኑን ካረጋገጣችሁ በኋላ ብቻ ነው።

65-0725 በዘመን መጨረሻ ላይ የተቀቡት

እላችኋለው ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ እምነትን ያገኝ ይሆን?

ይህ ጥያቄ ነው። አሁን ላሳያችሁ የምፈልገው ራዕይ ምዕራፍ 10 ነው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እናየዋለን፤ ቀጥሎ ሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንመለከታለን። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል።” የምንጠይቀው ጥያቄ ይህ ነው፡- በዚህ ተከትለን ብንሄድ አሁን ይፈጸማልን?

“የሚያስፈልገውን እምነት አገኛለውን?”

ሚልክያስ 4 በዚህ ሰዓት ይፈጸማልን

“የልጆች እምነት ወደ አባቶች ወደ መጀመሪያው ወደ ቃሉ ይመለሳልን?” አያችሁ?

 

በስተመጨረሻ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ቤተክርስቲያን የነገረቻቸውን ክርስቶስን ማግኘት ያቅታቸዋል።

61-0424 በታሪክ ሁሉ መካከል የተሰማ ታላቅ ዜና

አሁን መልእክቱ ይህ ነው፤ እርሱ ከፊታችን ቀድሞን ይወጣል። ከኋላችን መቃብር ውስጥ አይደለም እርሱ ያለው፤ ነገር ግን መንገድን እየከፈተልን ከፊታችን ነው የሚሄደው። እኛም እርሱን እያየን መከተል እንጂ መቃብር እያየን ወደ ኋላ መሄድ የለብንም፤ ይልቁንም እርሱ መሪያችን ስለሆን እርሱ ወደሚመራን ማየት ነው ያለብን። እርሱን መከተል አለብን እንጂ ወደ መቃብር መመልከት የለብንም።

ያን ዕለት ጠዋት ማርያም ግራ የተጋባችዋን ቤተክርስቲያን ወክላለች። በሚገባ ወክላለች ምክንያቱም ያን ዕለት እርሷ ልክ የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ያለችበት ስሜት ውስጥ ነበረች። ኢየሱስም “ማርያም ለምን ታለቅሺያለሽ?” ብሎ ሲናገራት በሰማችው ጊዜ ምን ብላ መለሰች?

እንዲህ አለች፡- “ጌታዬን ወስደውታል፤ ምን እንዳደረጉትም አላውቅም።” ዛሬ ቤተክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ ይህን የሚመስል ነው። “ጌታዬን ወስደውታል፤ እኔም የት ላገኘው እንደምችል አላውቅም። ሕብረታቸው ውስጥ ሁሉ ለመገኘት ሞክሬያለው። የውሃ ጥምቀታቸውን ሁሉ ሞክሬያለው። ከሜተዲስቶች፣ ባፕቲስቶች፣ ፕሬስቢተሪያኖች፣ ፔንቲኮስታሎች፣ ካቶሊኮች እና ከሌሎቹም ሁሉ ጋር ሕብረት አድርጌያለው ግን ላገኛቸው አልቻልኩም። መጽሐፍ ቅዱስ እርሱ ትናንትናም፣ ዛሬም፣ ለዘላለምም ያው ነው ካለ የሆነ ቦታ መኖር አለበት። ካልሞተ ሕያው መሆን አለበት። በአንድ ጊዜ ሙትም ሕያውም መሆን አይችልም።” ስለዚህ ማርያም ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ በትክክል ታሳየናለች፤ “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳደረጉት -- ወይም ምን እንዳደረጉት አላውቅም።”

ትንሳኤው በሚሆንበት ጊዜ ጌታህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት መቻል አለብህ።

ቤተክርስቲያኖች ግን ትልቁ ችግራቸውን የሚጋፈጡት የዛኔ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን ማመን በጣም ተላምደዋል።

በትንሳኤው ሰዓት ሰዎች በቤተክርስቲያን በተማሩት ስሕተታቸው በጣም ሥር ከመስደዳቸው የተነሳ አስተሳሰባቸውን መለወጥ ያቅታቸዋል።

ሙታን ተነስተው ሲናገሩዋቸው እንኳ አይሰሙም።

አብራሐም በሲኦል ውስጥ ካለው ከሃብታሙ ሰውዬ ጋር እያወራ ነበር።

ሉቃስ 16፡31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ፕሮፓጋንዳ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ከፓስተሮቻቸው ስሕተት ጋር አስሮ ያስቀራቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል የማታምኑ ከሆነ ከሙታን የተነሱ ሰዎች መጥተው የሚናገሩትን መልእክት መረዳት አትችሉም።

ደግሞም አታምኗቸውም።

ከዚያም የጌታ ምጻት ያመልጣችኋል።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23