ማቴዎስ ምዕራፍ 24 የሚተረጎመው በራዕይ ምዕራፍ 6 መሰረት ነው



ክርስቶስ የተጻፈውን ቃል ለመግለጥ በሚስጥራቱ አማካኝነት ወደ ምድር ይወርዳል፤ ይህም ሙሽራይቱ የሚመጣውን ሰው ኢየሱስን ለመቀበል ዝግጁ እንድትሆን ነው።

First published on the 12th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ማቴዎስ 24፡25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።

ዛሬ ብንታለል ምንም ማመካኛ የለንም።

የመታለል አደጋ መኖሩንና እንዳንታለል ኢየሱስ አስቀድሞ አስጠንቅቆናል።

የዚህ ዘመን ትልቅ ስሕተት ወይም ስንፍና ሰዎች አስተዋዮች ወይም አዋቂዎች እንዲባሉ ፈልገው የሰው ንግግር ጥቅስ እየወሰዱ መፈላሰፋቸው ነው።

ብልጥ ወይም አዋቂ በመምሰል የዳነ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን ነው ከስሕተት የሚጠብቀን።

ተጠምዝዘው በተተረጎሙ የሰው ጥቅሶች አማካኝነት ከተዘጋጁ አስተምሕሮዎች ተጠንቀቁ።

ሮሜ 1፡22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ፌብሩዋሪ 2 ቀን 1963 ዓ.ም የታየው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ልክ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ (ከምሽቱ 12፡40) ነው የተገለጠው፤ ደመናውም እየታየ የቆየው ለ28 ደቂቃ ሲሆን በተፈጥሮ ደመናዎች ሊገኙ በማይችሉበት በ43 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ በሰሜናዊ አሪዞና ውስጥ ከሚገኘው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ነበር የታየው።

ከደመናው ስር ተራራም ሆነ ኮረብታ አልነበረም።

 

 

ይህ ፎቶ የተወሰደው ከታክሰን የጠፈር ምርምር ጣብያ ነው።

ለሳንሴት ፒክ ቅርብ የሆነው የታክሰን ከተማ ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቆ ነው የሚገኘው።

ትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሳንሴት ፒክ ከተማ አካባቢ አልታየም። ደመናው ፎቶግራፍ በተነሳበት ሰዓት ወንድም ብራንሐም ታክሰን ከተማ ውስጥ ነበረ፤ ስለ ደመናውም ምንም ነገር አላወቀም። እርሱ ስለ ደመናው ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ሰኔ ውስጥ ነው።

ደመናው ከታየ ከስምንት ቀናት በኋላ ደመናውን የሰሩት 7ቱ መላእክት ሰው ሳያያቸው ወንድም ብራንሐምን ሳንሴት ፕክ ከተማ ውስጥ ማርች 8 ቀን ጎበኙት። እነርሱም ወንድም ብራንሐም ወደ ጄፈርሰንቪል ከተማ ሄዶ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ይዘውለት እስኪመጡ ድረስ እንዲጠባበቅ አዘዙት።

ከማርች 18 ቀን ጀምሮ ሰባቱ መላእክት በተለያዩ ቀናት አንድ በአንድ እየጎበኙት የሠባቱን ማሕተሞች መገለጥ ሰጡት።

7ቱ መላእክት ሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ለጉብኝት ሲመጡ ደመና አልሰሩም።

 

 

ከዚህ በታች የምታዩት ፎቶግራፍ የተነሳው ከዊንስሎው ነው። ዊንስሎው ደመናዎቹ እየተንቀሳቀሱ ሳለ በሚያልፉበት መስመር ላይ ስለነበረ ሁለቱንም ደመናዎች ያሳያል።

ትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የተፈጠረው በሰባቱ መላእክት ክንፍ አማካኝነት ሲሆን ትንሹ ደመና ደግሞ ከቫንደንበርግ አየር ኃይል በዚያኑ ዕለት ከቀኑ 8፡52 ሰዓት ላይ ተወንጭፎ ሰማይ ላይ የፈነዳው ቶር የተባለ ሮኬት የፈጠረው ጭስ ነው።

 

 

ትልቁ ደመና የጌታ ምጻት ነው ብላችሁ ማመን የለባችሁም ምክንያቱም ደመናውን የሰሩት ሰባቱ መላእክት ከዚያ በኋላ በታላቁ የሶኖራን በረሃ ውስጥ በሚገኘው ሳንሴት ፒክ የሚባል ከተማ ሄደው ወንድም ብራንሐምን ጎብኝተዋል። ኢየሱስ ደግሞ በበረሃ ወይም በምድረበዳ አይመጣም።

ታላቁ ደመና የታየው በሳንሴት ፒክ ከተማ አልነበረም። የታየው በፍላግስታፍ ከተማ ነው።

 

 

ታላቁ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መምጣት ምልክት አልነበረም።

ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከአንድ ዓመት በኋላ ወንድም ብራንሐም የብርቱውን መልአክ መውረድ በተመለከተ ገና ወደ ፊት ሊፈጸም ያለ ክስተት መሆኑን እየተናገረ ነበር። መልአኩ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ሰዎች ለማስነሳት ይመጣል። ይህ ትንሳኤ በ963 አለመፈጸሙን እርግጠኞች ነን። ያ ጊዜ ከ60 ዓመታት በፊት አልፏል።

64-0119 ሻሎም

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ

 

“ስውር እልፍኞች።”

ፓሩሲያ የተባለ አስተምሕሮ ውስጥ ክርስቶስ በማይታይ መልኩ መጥቷል አሁን መገኘቱ ከእኛ ጋር ነው ብሎ ያስተምራል። ይህንን አትመኑ። የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስቶች ክርስቶስ “በመንፈሳዊ ሚስጥር እልፍኝ” ውስጥ ነው ያለው ይላሉ። ክርስቶስ በ1844 መጥቷል ብለው ያምናሉ። ይህንንም አትመኑ። ክርስቶስ ሲመጣ እጆቹ ላይ የተቸነከረበት ምልክት ያለው አካል ይዞ ነው የሚመጣው።

ማቴዎስ 28፡20 ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

ሐዋርያቱ ወዳስተማሩት ትምሕርት መመለስ አለብን።

ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መልክ እና በቃሉ አማካኝነት ሁልጊዜ ከቤተክርስቲያን ጋር እንደሚሆን ተናግሯል።

ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

ኢየሱስ ሁልጊዜ በቤተክርስቲያን መካከል ነው።

የቤተክርስቲያን ዘመን 1 በሐዋርያት ተጀመረ፤ የቤተክርስቲያንም መሰረት የእግዚአብሔር ቃል (ማለትም የኢየሱስ ሃሳብ) ነበረ።

በመጀመሪያዎቹ አራት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ ሐዋርያት ካስተማሩዋቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እየራቁ ሄዱ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ በተቻላቸው መጠን ወደ መጀመሪያው እውነት ለመመለስ የሞከሩ ሰዎች ነበሩ።

በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቆራጥ በሆነው የተሃድሶ መሪ ማርቲን ሉተር አማካኝነት ጀርመኒ ውስጥ የተጀመረው ተሃድሶ ቤተክርስቲያን ከሮማ ካቶሊክ ጭቅና እንድትላቀቅና ወደ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት እንድትመለስ አስችሏታል።

 

 

ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን እውነት ትታ በመሄድ (በራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ ወደተገለጸው) ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ወደቀች።

ከዚያ በኋላ ግን በራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ በተገለጸው መሰረት በሉተር በተጀመረው ተሃድሶ አማካኝነት ወደ እውነት ተመልሳለች።

በሁሉም ዘመን ውስጥ ግነ ኢየሱስ እውነተኛ አማኞችን ለመርዳት ሲል በቤተክርስቲያኖች መካከል ይገኝ ነበር።

ማቴዎስ 24፡27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤

ይህ የሚገልጸው ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ካስነሳው ተሃድሶ ጀምሮ የመጡትን የመጨረሻዎቹን ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው (አምስተኛው ዘመን ሳርዲስ ሲሆን ትርጉሙ ያመለጡ ሰዎች ነው)። ፕሮቴስታንቶች ከሮማ ካቶሊክ አመለጡ።

ከዚያ በኋላ እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ የቅድስና ተሃድሶ አስነሳ፤ ደግሞም የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ በመዘጋጀቱ ለታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን አስተዋጽኦ አደረገ። ይህም 6ኛው የፊልደልፊያ (የወንድማማች መዋደድ) ቤተክርስቲያን ዘመን ነው።

 

 

ወንጌሉ መሰበክ የተጀመረው በሐዋርያት አማካኝነት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ፓለስታይን ውስጥ ነው። (የተጀመረው ከላይ ባለው ካርታ ውስጥ ቀይ ነጥብ ያለበት ቦታ ነው።) በጨለማው ዘመን ውስጥ ብዙ እውነቶች ከጠፉ በኋላ የመዳን ወንጌል ወደ ምዕራብ ተሻግሮ ጀርመኒ ውስጥ ይኖር ወደነበረ ሉተር ወደተባለ ሰው (በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን) መጣ፤ ከእርሱ በኋላ እንግሊዝ ውስጥ ዌስሊ (በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን)፤ ቀጥሎ ደግሞ ለ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን አሜሪካ ውስጥ ጴንጤ ቆስጤያዊ እንቅስቃሴ እና ዊልያም ብራንሐም ተነሱ፤ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ይባላል (ትርጉሙ የሕዝቡ መብት ማለት ነው)። ቤተክርስቲያኖች (በሴቶች የተመሰሉት) እምነታቸውን እንደሚስማማቸው አድርገው ማበጀት እንደሚችሉ ያስባሉ (ለዚህ ነው ሴቶች ሜካፕ የሚጠቀሙት)።

ስለዚህ በእያንዳንዱ ዘመን ተጨማሪ እውነት ሲገለጥ የወንጌሉ ብርሃን በዓለም ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሄደ።

የሰው ልጅ ማለት ኢየሱስ ሲሆን እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ስለዚህ የቃሉ (የብርሃን) መገለጥ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሄደ።

ሉተር ንሰሃ እንድንገባ ሲያስተምረን ዌስሊ ደግሞ በቅድስና እንድንኖርና ወጌልን እንድናሰራጭ አስተማረን። በጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መጣ። ዊልያም ብራንሐም ደግሞ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮ መለሰን።

የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን በዓለም ዙርያ በተሰራጨ ጊዜ እየደመቀ እየደመቀ በመሄዱ ኢየሱስ እንደ ሰው ልጅ ሆኖ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ በተገለጠው ቃሉ ሲመላለስ ልናየው ችለናል።

በመጨረሻዎቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ተገልጠውልናል። ኢየሱስን ዛሬ በአካል አናየውም፤ የምናየው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉት ሚስጥራት አማካኝነት ነው።

እግዚአብሔር ሰው ሆነ። ስለዚህ የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ብቁ የሆነው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው።

ኢየሱስን እና ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ማለትም ለሙሽራይቱ ያለውን እቅድ ማወቅ አለብን፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ የሚናገረው ስለ እርሱ ነው።

ፀሃይ ስትወጣ ከዋክብት እንደሚደበዝዙከኢየሱስ ጋር ሲወዳደሩ ሌሎች መሪዎች ሁሉ ይደበዝዛሉ።

በሰው ልጅ ብርሃን ውስጥ የምትመላለሱ ከሆኑ ሌላ ሰው ልትከተሉ አትችሉም። ሰውን የምትከተሉ ከሆነ ግን እስካሁን በጨለማ ትመላለሳላችሁ።

ማቴዎስ 24፡28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።

አሞራዎች ስጋ መብላት ይወዳሉ። ቤተክርስቲያኖች ግን የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል በሚንቁ ልማዶቻቸው ምክንያት ክርስቶስን እንደገና ይሰቅሉታል።

መጽሐፍ ቅዱስን አለመቀበል ክርስቶስን እንደገና መስቀል ማለት ነው።

ዕብራውያን 6፡6 በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።

ነገር ግን አሞራዎችን የሚስባቸው ይኸው ክርስቲያኖች አንቀበልም ብለው የጣሉት ቃል ነው፤ ምክንያቱም ያስተውሉ ዘንድ እግዚአብሔር ዓይናቸውን ያበራላቸዋል።

እውነተኛይቱ ሙሽራ ቤተክርስቲያን አጥብቃ የምትቃወማቸውን መገለጦች ማወቅ ትፈልጋለች።

በቅር የሚመጣው የአሕዛብን ምስል እግሩ ላይ የሚመታው እጅ ያልነካው ድንጋይ ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ሙሽራይቱን ከሙታን ይቀሰቅሳታል፤ ይህ ድንጋይ ምስሉን የሚመታበት ቦታ እውተኛይቱን ሙሽራ የሚወክለው ሸክላ እና ሰነፎቹን ወይም የተታለሉትን ቆነጃጅት ወይም የሮማካቶሊክን የሚወክለውን ብረት ነው። ሙሽራይቱን የሚያድናት ድንጋይ ቤተክርስቲያኖችን ያጠፋቸዋል። ስለዚህ ሙሽራይቱ በፍቅር የምትቀበለው የተገለጠ እውነት ለቤተክርስቲያኖች ስጋት ስለሆነ ይጠሉታል።

 

 

ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መገለጥ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ያስፈራቸዋል፤ ምክንያቱም አለማወቃቸውን ያጋልጥባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለማወቅ ብዙ ጥናት እንደሚጠይቅ ያውቃሉ፤ ይህም እንደ ብዙ ሥራ ያስፈራቸዋል። ይህ ፍራሃት ደግሞ የጠለቀውን እውነት የሚገልጡ ሰዎችን እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል። ከቁጣ ስር ሁልጊዜ ፍርሃት አለ።

ሰዎች አንበላም ብለው የጣሉዋቸውን ፍርፋሪዎች (እውነትን የሚወክሉትን) ነው ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲሰበስቡ ትዕዛዝ የሰጣቸው። በቀራንዮ አይሁዶች አንቀበልም ብለው የጣሉት የኢየሱስ ወንጌል በሐዋርያት አማካኝነት አዲስ ኪዳን ውስጥ ተጽፎ ለአሕዛብ ተሰጠ።

እነዚህ ሁኔታዎች ናቸው በአራተኛው ማሕተም ዘመን ማለቂያ አካባቢ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ጎልተው የሚታዩት።

ሰዎች አንቀበላችሁም ሲሉን ጸንተን መቆም አለብን።

ጸንተን ልንቃወመው የሚገባን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሕተት እንደ ጎርፍ በብዛት እየፈሰሰ ነው።

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ለመረዳት በዘመን መጨረሻ የተላከው ነብይ የዊልያም ብራንሐም መገለጦች ያስፈልጉናል።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

በራዕይ ምዕራፍ 6፡7 ውስጥ የተጠቀሰው በዙፋኑ ዙርያ ያለው አራተኛ እንስሳ ንስር ነው፤ ይህም ንስር የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለሙሽራይቱ በመግለጥ በሐዋርያት ወይም በአንበሳው ዘመን ወደነበረው እውነት ይመልሰናል። ንስሩ አስገራሚ የማየት ወይም የማስተዋል ችሎታ አለው።

 

 

ከዚያ በኋላ ሞት በፈረሱ ላይ እየጋለበ በሚመጣ ጊዜ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ታላቁ መከራ ተከትሎ ይመጣል።

ይህም ወደፊት የሚፈጸመው የአራተኛው ማሕተም ሁለተኛ አጋማሽ ተብሎ ተጠቅሷል።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

ይህም ዳንኤል የተናገረው ታላቅ መከራ ነው። ይህ መከራ በምድር ላይ ከመጡ መከራዎች ሁሉ እጅግ የከፋ መከራ ነው።

ዳንኤል 12፡1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።

 

በ1945 ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ ሒትለር 6 ሚሊዮን አይሁዶችን የገደለበትን አሰቃቂ ዘመን መለስ ብለን እንመልከት።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው

“ከዚያች ወራት መከራ በኋላ” የተባለው በአርማጌዶን ጦርነት መጨረሻ ላይ የሚመጣው ታላቁ መከራ አይደለም።

ይህ መከራ የሚናገረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጀርመኒ ውስጥ ኤይክማን ባደረገው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ውስጥ 6 ሚሊዮን አይሁዳውይን ስለተገደሉበት አነስተኛ መከራ ነው።

ጀርመኒ ውስጥ የተደረገው ጭፍጨዳ የአምስተኛው ማሕተም አካል ነው፤ እርሱም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አይሁዶች ላይ የሚደርስባቸውን ስደት ይወክላል።

ጀርመኒ ውስጥ የተደረገው ጭፍጨፋ ለሙሽራይቱ ዋናው ታላቅ መከራ ምን እንደሚል ቅድመ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል።

63-0323 ስድስተኛው ማሕተም

… አይሁዶች ቅድመ መከራ ዘመን ውስጥ አልፈዋል። በዚህ በቅርቡ በተደረገው የዓለም ጦርነት ውስጥ በሰው ሁሉ ተጠልተዋል። ጀርመኒ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን አይሁዶች ኤይክማን እየገደላቸው ብዙ ንጹሃን ሰዎች ሞተዋል፤ ያውም አይሁድ ስለሆኑ ብቻ እንጂ በሌላ በምንም ምክንያት አይደለም።

… አሁን ይህን ስሙ። ይህ ኢየሱስ በማቴዎስ 24፡29 እና 30 የተናገረው ነው። ከነዚያ የመከራ ወራት በኋላ።

ይህ መከራ፤ ይህ ቀላል መከራ፤ እነርሱ ያለፉበት መከራ

 

 

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

ይህ የሚፈጸመው በታላቁ መከራ ውስጥ ነው፤ ማለትም የተፈጥሮ ኡደት ሙሉ በሙሉ በሚቋረጥበት በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ነው።

የናዚ ጭፍጨፋ የታላቁ መከራ ምሳሌ ነው፤ ታላቁ መከራ ልክ እንደ ናዚ ጭፍጨፋ እጅግ ብዙ ሰዎች የሚገደሉበት ነውጠኛ ጊዜ ይሆናል፤ ከናዚ ጭፍጨፋ የሚብሰው ግን በዚያ ወቅት በተጨማሪ የተፈጥሮ ኡደቶች ሙሉ በሙሉ በመቋረጣቸው ነው።

የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ጭፍጨፋ በትኩረት የምንመለከተው ለምንድነው? የዓለም ሕዝብ ሁሉ እሥራኤልን ይጠላሉ። በተጨማሪም አንዳንድ የተሳሳቱ ክርስቲያኖችም እሥራኤልን ይጠላሉ። ሒትለር አይሁዳውያንን የገደለበት የመርዝ ጋዝ ቤቶች ግን በጣም ዘግናኝ ስለነበሩ የዓለም ሕዝብ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ለእሥራኤል አዝነውላቸው በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ በ1947 ዓ.ም ለእሥራኤል የመሮሪያ ሃገር እንዲሰጣት ወሰኑ። ስለዚህ በስተመጨረሻ አይሁዶች እሥራኤል ሃገራችን ናት ብለው ሲያውጁ ወዲያው ከዮርዳኖስ፣ ከሶርያ፣ ከሊባኖስ፣ ከግብጽ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከኢራቅ፣ እና ከየመን ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ጠላቶቻቸው በቁጥር እጅግ ቢበልጧቸውም እሥራኤላውያን በመለኮታዊ እርዳታ ሁሉንም አሸንፈው የተሰጣቸውን ሃገር መቆጣጠር ችለዋል።

ወደ እሥራኤል መመለሳቸው ኢየሱስ በታላቁ መከራ ዘመን ወደ አይሁዶች የሚመለስበትን መንገድ የሚጠርግ ክስተት ነው።

ፀሃይ መጨለሟ፣ ጨረቃ ወደ ደም መለወጧ፣ ከዋክብትም መውደቃቸው እግዚአብሔር ለእሥራኤል ጥበቃ ለማድረግ መለኮታዊ ኃይሉን ይጠቀማል ማለት ነው።

ጀርመኒ ውስጥ አይሁዳውያን ላይ የተደረገው ታናሽ ጭፍጨፋ አይሁዶች መኖሪያ ሃገራቸውን ለማግኘት የከፈሉት ከባድ ዋጋ ነው።

ከዚያ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወዲያ ስለ ታላቁ መከራ ይናገራል። አይሁዶች ወደ መኖሪያ ሃገራቸው የተመለሱበት ምክንያት በዋነኛው ታላቅ መከራ ወቅት መሲሃቸውን እንዲያገኙና ወደ እርሱ እንዲመለሱ ነው።

በታላቁ መከራ ወቅት ከአይሁድ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛዎቹ ይገደላሉ።

በ2020 ዓ.ም በተደረገው ቆጠራ 17 ሚሊዮን ያህል አይሁዳውያን መኖራቸው ተረጋግጧል።

ይህም 12 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በላይ አይሁዶች በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ ማለት ነው።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

ታላቁ መከራ እጅግ አስጨናቂ ከመሆኑ የተነሳ አይሁዶች ምንም የመትረፍ ተስፋ እንደሌላቸው ይገነዘባሉ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ይገለጥና ያድናቸዋል። ራሳቸውን ማዳን ባልቻሉበት ሰዓት ኢየሱስ ተገልጦ ሲያዩት በኃይሉ ታላቅነት ተደንቀው አዳኝ መሆኑን እውቅና በመስጠት ይቀበሉታል።

 

ትንቢት ብዙውን ጊዜ ድርብ ፍጻሜ አለው። በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ የምናየው ሁሉ በታላቁ መከራ ዘመን በአይሁዶች ላይ ምን እንደሚመጣባቸው የሚያሳይ ምልክት ነው።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

ይህ የተፈጸመው በናዚ የሞት ካምፕ ውስጥ ልክ 2ተኛው የዓለም ጦርነት እንደተጠናቀቀ ሲሆን እርሱ “ከዚያች ወራት መከራ በኋላ” የተባለው ጊዜ ነው።

“ፀሃይ ይጨልማል።” የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈሳዊ ብርሃናችን ምንጭ ነው። ስለዚህ በፀሃይ ይመሰላል።

የ1945ቱ ጦርነት እንዳበቃ ወዲያው በ1948 የዓለም ቤተክርስቲያኖች ምክር ቤት ተመሰረተ። ከዚያ በኋላ ምሑራን መጽሐፍ ቅዱስን እንደገና መተርጎም ጀሙ፤ ከዚህም የተነሳ የተለያዩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ብዛት ዛሬ በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 አልፏል። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ግድፈቶች አሉበት ብለው አዳዲስ የብራን ጽሑፎችን እየፈለጉ በመተርጎም ፍጹም ትክክል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት አይቻልም አሉ። ስለዚህ ዛሬ አብዛኛው ሰው (ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ብዙ አማኞችን ጨምሮ) ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ያምናል። ስለዚህ በእነርሱ ዓይን የእውነት ብርሃን ጨልሟል። ዛሬ በእነርሱ አመለካከት እውነት ማለት ከሰው ንግግር የተወሰደ ጥቅስ ነው። ይህ በጣም የሚያሳዝን ስሕተት ነው።

“ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም”። ቤተክርስቲያን ፀሃይ በጠለቀች ጊዜ የፀሃይን ብርሃን በማንጸባረቅ ለዓለም ብርሃን እንድታበራ ይጠበቅባታል። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ብርሃን ባለማንጸባረቅ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል ብርሃን ማንጸባረቅ ትታለች። የቤተክርስቲያን ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የሰውን ጥቅስ እና አመለካከት ማንጸባረቅ መርጠዋል። ከዚህም የተነሳ ዓለም ወደ ጨለማ ውስጥ እየወደቀች ናት።

የዓለም ብርሃን የሆነው ክርስቶስ ከየዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን እና ከሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ተገፍቶ ወጥቷል። ኢየሱስ ከቤተክርስቲያኖች ሁሉ በር ውጭ ቆሟል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ …

ኢየሱስ ጥሪውን የሚያቀርበው ለግለሰቦች ነው እንጂ ለማሕበር አይደለም።

ማንኛውም ከቤተክርስቲያን ጋር ለመቃረን የማይፈራ ግለሰብ ተጠርቷል።

“ከዋክብትም ሁሉ ከሰማይ ይወድቃሉ”።

ከዋክብቱ እነማን ናቸው? የአብራሐም ዘሮች ናቸው።

ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።

ሰማያዊውን ወንጌል የሚሰብኩ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሕዝቡ እንዲናገሩ ከተቀመጡበት ሥፍራቸው ይወድቃሉ። ትኩረታቸው ወርቅ፣ ክብር፣ እና ሴቶች (ገንዘብ፣ ዝና፣ እና ሴት መውደድ) ሲሆኑ በአገልግሎታቸውም ውስጥ ሰዎች መስማት የሚወዱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ልማድ እና ስሕተት ማስተማር ይወዳሉ።

 

 

ማቴዎስ 24፡29 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።

ይህ የተፈጥሮ ኡደቶች የሚቋረጡበት አስገራሚ ጊዜ ነው። በተፈጥሮ የማናውቃቸው ነገሮች ከአናታችን በላይ ሲሰሩ እናያቸዋለን። ይህም እግዚአብሔር ዕቅዱን ለማስፈጸም በመለኮታዊ ኃይሉ ጣልቃ ገብቶ እየተንቀሳቀሱ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው።

የአይሁዶች የመጨረሻ እንቅስቃሴ የተጀመረው ኤይክማን በመርዝ ጋዝ ቤቶቹ ውስጥ ከፈጸመባቸው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በኋላ በ1947 የተባበሩት መንግስታት ለአይሁዶች ከጥንቱ መኖሪያቸው የተወሰነ መሬት ቆርሰው ለመስጠት የወሰኑ ጊዜ ነበር።

በ1947 የእግዚአብሔር መልአክ ለወንድም ብራንሐም ተገለጠ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወንድም ብራንሐም ሙሽራይቱ ወደ ቀደመው የሐዋርያት እምነት መመለስ ትችል ዘንድ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገልጦ ማስተማር ጀመረ።

ዛሬም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ከታላቁ መከራ ለማምለጥ መዘጋጀት አለባት። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በትክክል ለመረዳት የሚያስፈልገው ቁልፍ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ማግኘት ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ለሙሽራይቱ ምልክት ይሆናለት ዘንድ አሁንም የተፈጥሮ ኡደቶችን ሊያቋርጥ ነው። ይህም ከጭንቅላታችን በላይ የሚከሰት መለኮታዊ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነገር ስለሆነ ልንቆጣጠረው አንችልም።

ይህ ምልክት እግዚአብሔር የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥራት ሊገልጥ መሆኑን የሚጠቁም በሰማይ ላይ የሚታይ ምልክት ነው።

ሚልክያስ 4፡4 ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።

5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።

ወንድም ብራንሐም ነፍሰ ገዳይ በሆነችዋ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምትሰራውን የኤልዛቤል መንፈስ ለመቃወም ነው የመጣው። የመጣበት ዓላማ ልባችንን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ነው።

የሰዎች ትኩረት ወደ እርሱ ሊሳብ የሚችለው እንዴት ነው? ሙሴን አስቡ።

ሙሴ ፍጥረታዊ ቁጥቋጦ ውስጥ እሳት ሲነድ አየ። ቁጥቋጦው አልተቃጠለም ስለዚህ እሳቱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ እሳት ነበረ። የሙሴ ምልክት የፍጥረታዊ (ቁጥቋጦ) እና የልዕለ ተፈጥሮአዊ (የእሳቱ) ቅልቅል ነበር። ልክ እንደዚሁ ዊልያም ብራንሐም ተፈጥሮአዊውን እና ልዕለ ተፈጥሮአዊውን በአንድነት የያዘ ምልክት ተሰጥቶታል።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከቀኑ 8፡52 ሰዓት ላይ ቶር አጄንዳ ዲ የተባለ በፈሳሽ ነዳጅ የተሞላ ሮኬት ከሌሎች ጠጣር ቲዮኮል ሮኬቶች ጋር ከቫንደንበርግ አየር ኃይል ጣብያ ተወንጭፎ በ27 ማይልስ ከፍታ ላይ ከካሊፎርኒያ የውቂያኖስ ጠረፍ አለፍ ብሎ ፈነዳ። ፍንዳታው አካባቢ የስብርባሪ እና የጭስ ቀለበት ተፈጠረ። በዚያ ከፍታ ላይ አየሩ በጣም ስስ ስለሆነ ጭሱ በጣም ሰፋ ብሎ በመበታተኑ ደመና ሊሰራ አልቻለም። ጭሱ በነፋስ እየተገፋ በሰሜን አሪዞና ወደሚገኘው ወደ ፍላግስታፍ ከተማ ሄደ። በዚያ ከፍታ ላይ ደመናዎች እንደሚበተኑ ሁሉ ይህም የደመና ቀለበት ቀስ በቀስ ተበትኖ ጠፋ። የጭሱ ደመና የታየው 12፡40 ሰዓት ላይ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ለጥቂት ደቂቃ ብቻ ነበር። ይህ የኖክቲሉሰንት (በሌሊት የሚታይ) ደመናዎች ባህርይ ነው። ነገር ግን ልክ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ሌላ ተለቅ ያለ ደመና ከመጀመሪያ ደመና ፊት ለፊት በ20 ማይልስ ርቀት ላይ ታየ። ይህኛው ደመና መጠነ ዙርያው 150 ማይልስ የሚያክል ትልቅ ደመና ነው። ይህኛው ደመና አልተበታተነም፤ ደግሞም ሳይንቲስቶች መንስኤውን ሊያውቁ አልቻሉም፤ ምክንያቱም ሮኬት ሲፈነዳ አንድ የጭስ ቀለበት ብቻ ነው የሚሰራው። ስለዚህ ትልቁ ደመና ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፤ ምክንያቱም የታወቁትን የፊዚክስ ሕጎቻችንን ሁሉ ጥሶ አልፏል፤ በዚያ ከፍታ ላይ ቀዝቅዞ ደመና ሊሰራ የሚችል የውሃ ትነት ወይም እንፋሎት አይገኝም።

ሙሴ የመጀመሪያውን ፍልሰት (የአይሁዶች ከግብጽ መውጣት) እንዲጀምር የተሰጠው ምልክት ፍጥረታዊ ቁጥቋጦ ከልዕለ ተፈጥሮአዊ እሳት ጋት ተደባልቆ ነበረ። ይህ ያልተለመደ ትዕይንት የሙሴን ትኩረት ሳበ።

በዚህ ሳይንሳዊ ዘመናችን ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር የሙሽራይቱን ትኩረት ለመሳብ ምልክት ሊሰጥ ወሰነ። የሁለቱ ደመናዎች ምልክት ዊልያም ብራንሐም በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፉትን የሰባቱን ማሕተሞች ቁልፍ ሚስጥራት ሊገልጥ ጊዜው መድረሱን እና ከገለጠው በኋላም መጽሐፍ ቅዱስን የምታምነዋ እውነተኛዋ ሙሽራ ከቤተክርስቲያን ስርዓት ውስጥ ፈልሳ እንድትወጣ የሚጠቁም ምልክት ነው።

ፍጥረታዊ ደመናዎች ከሚፈጠሩበት ከፍታ ከ42 ኪሎ ሜትር እስከ 65 ኪሎሜትር ድረስ ጎጂ የሆነውን የፀሃይ አልትራ ቫዮሌት ጨረር ኦዞን ከፀሃይ ውስጥ ሰብስቦ ወደ ምድር እንዳይመጣ ያስቀረዋል፤ በዚያም ከፍታ ላይ ሙቀቱ ስለሚበዛ የውሃ ጠብታዎች አይፈጠሩም። አንዳች ውሃ ቢገኝ እንኳ በትነት መልክ ነው የሚቀረው። በዚህ “ደመና ወይም የውሃ ጠብታ ሊፈጠር በማይችልበት ከፍታ ላይ” ሁለተ ደመናዎች ታዩ።

አንደኛው ከሰው ሰራሽ ፍንዳት የመጣ ጭስ ነበር። ይህኛውን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠት ይቻላል። ትልቁ ደመና ግን በመላእክት ክንፍ የተሰራ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ነው። አንድ ሮኬት ነው የፈነዳው ደመናዎቹ ግን ሁለት ናቸው። ስለዚህ ሁለተኛው ትልቁ ደመና በየትኛውም የሳይንስ ሕግ መሰረት ሊብራራ አይችልም።

 

 

የሰማይም ኃይላት ይናወጣሉ

የሕዋ ተፈጥሮአዊ ሕጎች በሙሉ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ። ስለ ሁለተኛው ትልቅ ደመና ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሊሰጡ አልቻሉም።

ይህም ደመና እግዚአብሔር ሰው ሰራሽ የሆነውን ጭስ ልዕል ተፈጥሮአዊ ከሆነው ታላቅ ደመና ጋር ምልክት እንዲሆነን ለእኛ መስጠቱ ነው።

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

የመላእክት ክንፍ የሰሩት ትልቁ ደመና በከፍታ ላይ ወይም በሰማያት ላይ የተሰጠ የሰው ልጅ ምልክት ነው።

63-0818 ምልክቱ እና የአንድነት ጊዜ

ከጥንቷ የቤተክርስቲያን ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛ የምናያቸውን ነገሮች ያዩ የሉም። ይህም ሊሆን የቻለው እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች የላከ ጊዜ እና በእርሱም ሰባት መላእክትን ልኮ ምልክት ሲሰጠን ነው። እነዚህም መላእክት ከሰማይ ወርደው በየቤተክርስቲያኑ በየዲኖሚኔሽኑ ተበታትኖ የነበረውን ቃል ሰብሰብ አድርገው አመጡልን፤ ካመጡልንም በኋላ መልሰው መንፈስ ቅዱስን ለማውረድ በእግዚአብሔር ቃል ማሰሪያ በአንድነት አሰሩልን

ሰባቱ መላእክት መጀመሪያ ምልክት እንዲሆን ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና በሰማያት ላይ ሰሩ።

ከዚያም ከ8 ቀናት በኋላ ወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች እንዲገልጥ ትዕዛዝ ሊሰጡት ወረዱ።

ወንድም ብራንሐም ሁለቱን ደመናዎች ከሁለት የእግዚአብሔር ቃል ክፍሎች ጋር አያይዞ ነው የሚናገረው።

1965-0718

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። ዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል።”

[ምልክቶስ፤ በኢዩኤል ትንቢት መሰረት በብዙ ቁጥር ነው]

እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የምድር መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ይታያል።

[በነጠላ ቁጥር የተጠቀሰው ምልክት ማቴዎስ ውስጥ የተጻፈው ትንቢት ነው። እርሱም ትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ነው።]

“በዚያ ቀን” ሉቃስ ውስጥ እንደተጻፈው “የሰው ልጅ እንደገና ራሱን ይገልጣል፤ ይገለጣል።” ዓለም ደግሞ እንደ ሰዶም እና ገሞራ ትሆናለች። ወየው ለዚያ ጊዜ!

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

በሰማይ ላይ የሚታየው ምልክት የሰው ልጅ መጽሐፍ ቅዱስን ውስጥ የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥራት በመግለጥ በእግዚአብሔር ቃል እራሱን የሚገልጥበት ነው።

ሙሽራይቱም በስተመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራቱ ተነበው ለማስተዋል የሚቻሉ መሆናቸውን ትገነዘባለች።

የኢዩኤል ትንቢትስ?

ኢዩኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።

“በሰማይ ድንቆችን (በብዙ ቁጥር) … የጢስም ጭጋግ”

ይህ የሰው ልጅ ምልክት (ነጠላ) ከሆነው ከዋነኛው ደመና የተለየ ነው።

ትንሸኛውም የጭስ ደመና ተመለከቱ። ልክ እንደ ሁለት የጭስ አምዶች የሚመስሉ ሁለት የጭስ መስመሮች ሰርቷል።

ስለዚህ የኢዩኤል ትንቢት እንዲፈጸም ጭስ መሄድ ከሚችልበት ከፍታ በላይ ከፍ ብሎ ላይ የሚፈነዳ ሮኬት አስፈልጓል።

ኢየሱስ ወደ ምድር የሚመለስበት ሂደት በሶስት ደረጃዎች ይከፈላል።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

1965-1127

ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ወንድም ብራንሐም የመጨረሻዎቹን ሚስጥራት በ1963 እና በ1965 ዓ.ም መካከል ገልጦ አስተማረ።

ይህ ግን ታላቁ ድምጽ አልነበረም፤ ምክንያቱም በ1965 ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ ወንድም ብራንሐም የድምጹን መምጣት እየተጠባበቀ ነበር።

“ድምጹ” መጣ የሚባለው ሙሽራይቱ ወንድም ብራንሐም ሲያስተምር የነበራቸውን እውነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ማረጋገጥ የቻለች ጊዜ ነው።

ከዚያ በኋላ ብቻ ነው የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወይም ሊቀ መላእክት ወደ ምድር ወርዶ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ሰዎች በመላእክት አለቃ ድምጽ ከሞት ማስነሳት የሚችለው።

ይህም የጌታ ምጻት ሁለተኛው ደረጃ ነው የሚሆነው።

እስከ አሁን ድረስ የነጎድጓድ ድምጽ አለመምጣቱን ልብ በሉ። የነጎድጓዱ ድምጽ ራሱ ምን እንደሆነ አናውቅም።

የመጀመሪያው ማሕተም የእውነት ሲፈታ የነጎድጓድ ድምጽ ይሰማል።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ስለዚህ የመጀመሪያውን ማሕተም መገለጥ እናገኛለን።

ነገር ግን ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት የነጎድጓድ ድምጽ መምጣት አለበት

64-0119 ሻሎም

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ

ደመናው ፎቶ ከተነሳ ከአንድ ዓመት በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም ብርቱው መልአክ ገና ወደ ፊት እንደሚመጣ እየተጠባበቀ ነበር።

ስለዚህ ደመናው የመልአኩ መምጣት አልነበረም።

ትልቁ ደመና ምልክት እንዲሆን በ7 መላእክት ክንፍ ነበር የተሰራው።

ደመናው ከታየ ከስምንት ቀናት በኋላ ወንድም ብራንሐም የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ገልጦ እንዲያስተምር በ7ቱ መላእክት ትዕዛዝ ተሰጠው።

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ሲሰብክ የሚመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ሙሽራይቱ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት እንድትዘጋጅ ይረዳታል። ስለዚህ በዚህ ዘመን መጨረሻ ሙሽራይቱ የእነዚህን ጥቅል መገለጦች መረዳት ማግኘት ችላለች።

 

 

በደምብ አስተውሉ። ወንድም ብራንሐም የጻፈውን ታዋቂ መጽሐፍ “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” የሚል ርዕስ ነው የሰጠው።

“የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት” የሚል ርዕስ አልሰጠውም።

የማሕተሞቹ ሚስጥር መገለጥ እና የማሕተሞቹ መፈታት በጣም የተለያዩ ናቸው።

ሰባቱ ማሕተሞች በዝርዝር የሚፈቱትና የሚፈጸሙት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ሄዳ በራዕይ ምዕራፍ 5 በተጻፈው መሰረት በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ በተቀመጠች ጊዜ ነው።

1965 የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ - ምዕራፍ አንድ

እስከ ራዕይ 5፡6-8 (ይህ ክፍል በጊዜ ቅደም ተከተል ከራዕይ 4፡2-3 ተከትሎ የሚመጣ ነው) “በጉ” መጽሐፉን በዙፋኑ “ከተቀመጠው” እጅ ሲወስደው አናይም።

ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ዮሐንስ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ይሄዳል፤ ይህም ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል እንደምትነጠቅ ያመለክታል።

7ቱ ማሕተሞች ከተገለጡ በኋላ የተዘጋ ዚፕ እንደመክፈት ነው።

ይህን ተከትሎ ወዲያው ብዙ ጠለቅ ያሉ ሚስጥራት ለሙሽራይቱ ተገልጠውላታል። በነዚህ መገለጦች የተነሳ ሙሽራይቱ ብዙ ነገሮች ግልጽ ሲሆኑላት እና ስታውቅ ለቤተክርስቲያን መነጠቅ ዝግጁ ሆና መጠበቅ ትችላለች። ስለዚህ ሁለቱም ወገኖች ማለትም ሙሽራይቱም አይሁዶችም ለመጨረሻው ቀን መዘጋጀት ይችላሉ።

የ1963ቱ ታላቅ ደመና በሰማይ ላይ የተገለጠ የሰው ልጅ ምልክት ነው። ከ27 ማይልስ ከፍታ በታች በጭራሽ ፎቶ አልነተነሳም።

 

 

በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ሚስጥራት በእግዚአብሔር ቃል መልክ ወደ ምድር ይወርዳሉ፤ በዚህም ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እና ለጌታ አካላዊ ምጻት መዘጋጀት ትችላለች።

63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ

… ምስጢራቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሆነው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ሙሉ መገለጥ ለሰው ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ሚስጥር እና ሌላው ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል። ሚስጥራቱ በሙሉ፤ የእባቡ ዘር እና ሌላው ሊገለጥ ያለው ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል።

[ክርስቶስ በቃሉ ውስጥ ነው የሚገለጠው። መጽሐፍ ቅዱስ ከዚያ በኋላ የተገለጠ መጽሐፍ ይሆናል።]

ማሕተሞቹ ሲፈቱ እና ሚስጥራቱ ሲገለጡ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይወርዳል፤ መልእክተኛው ማለትም ክርስቶስ ይመጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ ያሳርፋርል፤ ከራሱም በላይ ቀስተደመና ይታያል።

[የማሕተሞቹ መፈታት እና የብርቱው መልአክ መውረድ ሊፈጸሙ የሚችሉት ከ1965 በኋላ ነው ምክንያቱም የዛኔ ነው የዚያኔ ነው ማሕተሞቹ የተፈቱትና የእግዚአብሔር ሚስጥር (ቃሉ) የተገለጠው]።

… አሁንም ወደ 10ኛው ምዕራፍ ተመልሶ ከሚመጣው ጊዜ በኋላ ሚስጥራቱ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይናገራል፤ ማሕተሞቹም ይፈታሉ ከዚያም በኋላ ዘመን እንደማይኖር ይታወጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ሁሉ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል”።

የመልአኩ መምጣት በዚያን ጊዜም ገና ወደ ፊት ነበረ። ደመናው ይህ መልእክት በወንድም ብራንሐም ከመቅረቡ ከ17 ቀናት በፊት ነበር ፎቶግራፍ የተነሳው።

 

 

በመጀመሪያው የኢየሱስ ምጻት ጊዜ በብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ቀን እና ወደ ሰማይ እርገት በተደረገበት ቀን መካከል 40 ቀናት አልፈዋል።

የክርስቶስ ምጻት የመጀመሪያው ደረጃ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለሙሽራይቱ መግለጥ ነው።

ይህ የመጀመሪያው ዝናብ ወይም ትምሕርት ነው።

የክርስቶስ ምጻት ሁለተኛው ደረጃ፡- ወደፊት ለሚሆነው ትንሳኤ ብርቱው መልአክ ወደ ምድር ይወርዳል።

ይህም የመጨረሻው የመከር ዝናብ እንዲዘንብ መንስኤ ይሆናል።

መከር ማለት ፍሬው ከተክሉ ላይ የሚለቀምበት ጊዜ ነው።

የሞቱ ቅዱሳን መጀመሪያ ከመቃብራቸው ውስጥ ይወጣሉ።

ከዚያም ሶስተኛው ደረጃ፤ የእግዚአብሔረ መለከት ሙሽራይቱን በሙሉ ከምድር ላይ ያነሳትና ጌታ ሲመጣ በአየር ላይ እንድትቀበለው ወደ ላይ ይነጥቃታል።

በዚህም የኋለኛው ዝናብ የተባለው የመከር ዝናብ ይጠናቀቃል።

 

 

ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ዘመን ምድር ላይ አትገኝም፤ ምክንያቱም ታላቁ መከራ የሚሆንበትን ሶስት ዓመት ከግማሽ በሰማይ የእራት ግብዣው ላይ ናት።

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እና ሙሽራይቱ በአርማጌዶን ጦርነት ለሶስተኛ ጊዜ ይመጣሉ።

ማቴዎስ 24፡30 … በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።

በዚያ ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ሰነፎቹን ቆነጃጅት እና ከአይሁድ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑትን ገድሎ ይጨርሳል።

ስለዚህ ኢየሱስ ለፍርድ ወደ ምድር ሲወርድ በደስታ ለመቀበል ምድር ላይ የሚጠባበቅ ሰው አይኖርም።

 

 

የ7ቱ ማሕተሞች መገለጥ ሙሽራይቱ በስተመጨረሻ ለጌታ ምጻት እንድትዘጋጅ የሚያበቃትን መገለጥ ይሰጣታል።

ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስን እንደተከፈተ መጽሐፍ ማንበብ በቻለች ጊዜ ቅዱሳን በሚስጥር በሚሆን መነጠቅ ወደ ሰማይ ተነጥቀው ይሄዳሉ፤ ይህም በዚህ ክፍል ያልተገለጸው ታላቅ ሚስጥር በመሆኑ ነው።

ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ትሄዳለች፤ የዚያን ጊዜም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወንጌል

144,000ዎቹ ጌታን ይቀበላሉ፤ ከዚያ በኋላ ይገደላሉ።

ከዚያ ቀጥሎ ኢየሱስ ለሶስተኛ ጊዜ ለአርማጌዶን ጦርነት ይመለሳል።

አሁን ትዕይንቱ በታላቁ መከራ ዘመን መጨረሻ ወደሚሆነው ወደ ኢየሱስ ሶስተኛ ምጻት ዘወር ይላል።

ይህ የሚሆነው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሰነፎቹን ቆነጃጅት ካጠፋቸውና 144,000ዎቹን አይሁዶች ከገደላቸው በኋላ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ለአርማጌዶን ጦርነት ሲመለስ የክርስቶስ ተቃዋሚ ተከታዮች በሙሉ ጉዳቸው እንደሚፈላ ያውቃሉ።

ማናቸውም ቢሆኑ የክርስቶስን ሶስተኛ ምጻት ማየት ስለማይፈልጉ የክርስቶስ ተቃዋሚ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ የገቡ የዳኑ ክርስቲያኖችን ሁሉ ገድሎ ጨርሷል ማለት ነው።

ስለዚህ ወደ ታላቁ መከራ አለመግባታችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

ማቴዎስ 24፡31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።

መላእክት፤ በብዙ ቁጥር።

እነርሱም ለአይሁድ ሕዝብ የተላኩ ሁለቱ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው።

እነርሱም የሚላኩት በታላቁ መከራ ዘመን ወደ ክርስቶስ የሚመለሱትን 144,000 አይሁዳውያን ይዘው ለመውጣት ነው። ይህ የታላቁ መከራ ወቅት እንደመሆኑ ነፋስ ግጭትን እና ጦርነትን ነው የሚያመለክተው።

እነዚህ ሰዎች በታላቁ መከራ ዘመን ዳግመኛ የተወለዱ ነፍሳት ናቸው። ይህም ስድስተኛው ማሕተም ነው።

 

 

አሁን ደግሞ የክርስቶስ ሁለተኛ ምጻት ስለሆነው ስለ ሰባተኛው ማሕተም መስማት አለብን።

ማቴዎስ 24፡32 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

ኢየሱስ ግን እንዲሁ የሚናገርበትን ርዕስ ቀየረ።

ኢየሱስ ሰባተኛውን ማሕተም ባለመጥቀስ ምንም የማናውቀው ሚስጥር መሆኑን ያስገነዝበናል። ጌታ መች እንደሚመለስ አስልቶ ለማወቅም ሆነ ለመገመት የሚሞክር ሰው ሁሉ በከንቱ እየደከመ ነው።

 

 

የበለስ ዛፍ የእሥራኤል ተምሳሌት ናት። እሥራኤል ሕዝብ የሆነችበት ሰዓት ሕዝብ መሆኗ ስለ ጊዜው የሚጠቁም ታላቅ ምልክት ነው።

ሰዎች በ1948 እሥራኤል ሕዝብ ናት ብለው አወጁ።

እግዚአብሔር ግን እሥራኤል ሕዝብ ናት ብሎ ያወጀው መች እንደሆነ ማናችንም አናውቅም።

አሁን ግን እሥራኤል ወደ ምድራቸው ስለተመለሱ መመለሳቸው የጌታ ምጻት ቅርብ መሆኑን ያመለክታል።

እሥራኤል የእግዚአብሔር ሰዓት አመልካች ናት። ለአይሁዳውያን ጸልዩ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ሲሰጥ ወኔ የሚጠይቅ ነገር ነው ያደረገው።

ማቴዎስ 24፡33 እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።

34 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።

35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

 

ማቴዎስ 24፡36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።

ሰባተኛው ማሕተም በአጭሩ ሲየጌታ ዳግም ምጻት ነው። እርሱም መች እንደሚሆን የሚያውቅ አንድም ሰው የለም።

ማቴዎስ 24፡37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።

38 በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥

39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ከጌታ ምጻት እና ከታላቁ መከራ በፊት ወደሆነው ወደ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ተመልሰናል።

ልክ በኖህ ዘመን እንደሆነው ሁሉ ሰዎች ትኩረታቸውን ተድላ እና ደስታ ላይ አድርገዋል። ትኩረታቸው ጋብቻ ላይ ነው። ሰዎች ይጋባሉ፤ ልጅ ይወልዳሉ። በ2020 የዓለም ሕዝብ ብዛት ወደ 8 ቢሊዮን ደርሷል። በ12 ዓመቱ ምድራችን ላይ አንድ ቢሊዮን ሰዎች እየተጨመሩ ነው። ስለዚህ ጋብቻ ላይ ትልቅ ትኩረት እንዳደረግን ያስታውቃል። ይህም የዘመኑ ሌላ ምልክት ነው።

 

ማቴዎስ 24፡40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል።

41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።

በጌታ ምጻት ጊዜ ተነጥቆ መሄድ የግል ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር የሚወስደው የተዘጋጀውን ሰው ነው። አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ ነበረ (እየሰራ ወይም እየሰበከ) አንድ ሴት ደግሞ በወፍጮ እህል እየፈጨች ነበር (ዳቦ ለመጋገር ዱቄት እያዘጋጀች ወይም ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር እንደ ሕይወት እንጀራ ይበሉት ዘንድ መረዳት በሚችሉበት መንገድ እያስተማረች)።

እነዚህ ሁሉ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ለሚሆነው ለአራተኛው ማሕተም ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው። ከዚያ በኋላ እውነተኛዋ ሙሽራ ቀጥ ብላ ወደ ሰባተኛው ማሕተም ውስጥ ትገባለች፤ እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።

ይህም ቃል በድጋሚ የሚያሳስበን ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ነው።

 

 

ማቴዎስ 24፡43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።

ሁልጊዜ አስተምሕሮዋችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እየፈተሽን ያለማቋረጥ ንቁ መሆን አለብን። ሁልጊዜ ንቁ መሆንና እራሳችንን መመርመር እንጂ ሁሉን እንዳጠናቀቀ ሰው እፎይ ማለት እና መዘናጋት የለብንም።

የልባችን አቋም በማንኛውም ሰዓት ልንሳሳት እንደምንችል በማሰብ ለመማር ዝግጁ መሆን ነው ያለበት።

አንድ ሰው መሳሳታችንን ካሳየን ስለ እርማቱ ማመስገን እንጂ መቆጣት ወይም መናደድ የለብንም።

ማቴዎስ 24፡44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

ይህም ቃል በድጋሚ የሚያስገነዝበን ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ነው።

“የሰው ልጅ”።

ይህ አነጋገር ስለ አንድ ሰው ብቻ እንደሚናገር ይገልጻል። እርሱም ኢየሱስ ነው።

 

 

ማቴዎስ 24፡45 እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?

“ታማኝ … ባሪያ”።

በዚህ ቃል ውስጥባሪያ በነጠላ ቁጥር መጠቀሱ ቃሉ የትኛውምን ሰው በተለይ የሚያመለክት አለመሆኑን ያሳያል።

ስለዚህ ይህ ማንኛውም ታማኝ የሆነው ሰውን ይመለከታል።

ቆላስይስ 1፡7 ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ ተማራችሁ፥ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው።

ቆላስይስ 4፡7 የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ ቲኪቆስ ኑሮዬን ሁሉ ያስታውቃችኋል፤

ቆላስይስ 4፡9 ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው፤ የዚህን ስፍራ ወሬ ሁሉ ያስታውቁአችኋል።

 

እግዚአብሔር እያንዳንዱን ታማኝና ልባም ሰው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መሪ አድርጎ ይጠቀማል።

 

የትኛዋም አጥቢያ ቤተክርስቲያን አንድ ግልሰብ ራስ ሊሆናት አይገባም። የትኛውም ሰው የብዙ ቤተክርስቲያኖች ራስ መሆን አይገባውም። ይህ የካቶሊክ ስርዓት ነው።

እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የምትመራው በአጥቢያዋ ሽማግሌዎች እንጂ በአንድ ግለሰብ አይደለም።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን። መጥፎውን ረብ ወይም ገንዘብ ፓሰተሩ ይሰበስብና ለእርሱ ታማኝ ከሆኑ ሰዎች ታማኝነታቸውን ለመግዛት ይጠቀምበታል።

አስራት የፓስተሩ ነው የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤

1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።

ጌታ ሲመጣ በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያገለግል የነበረ ሽማግሌ ይሸለማል።

57-0908

ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው መሰረት ለአንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከሽማግሌ የሚበልጥ አገልጋይ ካለ አሳዩኝ

ይህ እውነት ነው፤ ወገኖች እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ራሷን ችላ በነጻነት መኖር አለባት።

የሽማግሌዎች ሃላፊነት እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ጉባኤዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተዳዳሪ እንዲሆን የተሾመ ፓስተር ወደ ሌለባት ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ሥርዓት እንዲመለሱ ማድረግ ነው። የቤተክርስቲያን ራስ ፓስተሩ ከሆነ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት አይደለም።

ሮማዊው ጀነራል ታይተስ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን ባጠፋ ጊዜ አብዛኞቹ ሐዋርያት ሞተዋል። ስለዚህ የትኛዋም ቤተክርስቲያን የሌሎች አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች የበላይ አልነበረችም። ከዚያ በኋላ ኒቆላውያን ቀስ በቀስ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖችን መቆጣጠር ጀመሩ፤ ከዚያም አንድን ሰው የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ከፍ አደረጉ። እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ይጠላል።

ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

የኒቆላውያን ሥራ አንድን ሰው ከፍ በማድረግ በጉባኤው ወይም በምዕመናን ላይ ገዥ እንዲሆን መሾም ነው።

ሰባተኛው መልአክ የመጣው የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለመግለጥ ነው።

 

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ሁሉን ነገር ካቀና እኛ ከዚያ ቀጥሎ ምንም የምናገለግለው አገልግሎት አይኖረንም።

አማኞች እርስ በራሳቸውን መርዳት ይችላሉ፤ ሆኖም ግን ከሁላችን በላይ እንደ ጥላ የሚሆን አገልግሎት የለም።

እያንዳንዱ አጥቢያ ጉባኤ ለራሱ መልእክቱን ቢያጠና ሁላቸውም ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን መመለስ ይችላሉ።

ሰዎች እግዚአብሔር በመራቸው ጊዜ ሁሉ እርዳት ለመጠየቅ ነጻ ናቸው፤ ነገር ግን አንድ ሊከተሉትና ሊታዘዙት የሚገባ ዓለም አቀፍ መሪ የለም።

ካቶሊኮች ፖፑን እንደዚያ ነው የሚያዩት።

ብዙ ሰዎች እኔ ከኤልያስ በኋላ የተነሳሁ ኤልሳእ ወይም ስምንተኛው መልአክ ነኝ ብለዋል። ስለዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እስካሁንም ድረስ የኒቆላውያን መንፈስ እየሰራ ነው።

ሰዎች የራሳቸውን አገልግሎት አብዝተው ማድነቅ የለባቸውም።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤

ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል እንድሪያስ ብቻ ነው የኢየሱስ ደቀመዝሙር የሆነው።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐምን ተከተላችሁ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ስለመከተላችሁ ዋስትና አይሆንም።

በተለይ ደግሞ የቤተክርስቲያናችሁ ራስ ፓስተር ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን እየተከተላችሁ አይደለማችሁም።

 

ስለዚህ እነዚህ ራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉ ሰዎች ለሌሎች ራሳቸውን ከፍ ለሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ ስሕተታቸውን ያከፋፍላሉ።

እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምዕመናን ፓስተራቸውን ብቻ ነው የሚሰሙት። ይህም ከቤተክርስቲያን ውጭ እውነቱን የመስማት እድላቸውን ይቀንሰዋል።

በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ነው የቆመው። ከሁሉም ቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል። ምክንያቱም በደጅ ቆሜ ሲል የትኛውንም ቤተክርስቲያን ለይቶ አልተናገረም።

በእምነታቸው የሚለያዩ ብዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ከዚህም የተነሳ ብዙ ስሕተት በሕዝብ መካከል ይሰራጫል። ሆኖም ግን እያንዳንዱ የሜሴጅ ቤተክርስቲያን እውነቱን የያዝን እኛ ነን ይላሉ።

ጉልህ ከሆኑ ስሕተቶቻቸቸው በጥቂቱ፡-

የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ከዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ከወሰዱዋቸው ስሕተቶች አንዱ የሰባት ዓመት ታላቅ መከራ ትምሕርት ነው።

የክርስቶስ ተቃዋሚ ለ7 ዓመታት ከአይሁዶች ጋር ኪዳን ይፈጽማል ከዚያም በ3 እስከ 5 ዓመታት ውስጥ ኪዳኑን ያፈርሳል ይላሉ።

ዳንዔል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤

ቃልኪዳን አያደርግም፤ ያጸናል እንጂ።

የጸና ቃልኪዳን ሊፈርስ አይችልም።

ገላትያ 3፡15 ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም።

እግዚአብሔር የእንስሳት መስዋእቶችን በመጠቀም ዘፍጥረት ምዕራፍ 15 ውስጥ ከአብራሐም ጋር ቃል ኪዳን ገባ።

ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦

ይህ ቃልኪዳን ኋላ በቀራንዮ ከ3½ ዓመታት በኋላ በኢየሱስ ሞት በተደረገው የመጨረሻ መስዋእት አማካኝነት ጸና። ይህም ታላቅ መስዋእት በቤተመቅደሱ ውስጥ የሚቀርቡ የእንስሳት መስዋእቶች በሙሉ እንዲቀሩ አድርጓል።

ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል

ከዚህም የተነሳ የ3½ ዓመታት መከራ ብቻ ነው የሚቀረው።

 

ሌላው ትልቅ ስሕተት አንድ ሰው ሚስቱን ከፈታ በኋላ እንደገና ሌላ ወጣት ሴት ማግባት ይችላል የሚችለው አስተሳሰብ ነው።

አንድ ሰው እና አንዲት ሴት በሕግ ከተጋቡ በኋላ መፋታት እና በድጋሚ ማግባት አይችሉም።

ሴቲቱ ድንግል መሆን አለባት። ድንግል ካልሆነችና ከሰርጓ በፊት ድንግል አለመሆኗን ካላሳወቀች የጋብቻ መሃላዋ የውሸት ነው።

ባሏ ድንግል አለመሆኗን ባወቀ ጊዜ ከፈለገ ሊፈታት መብት አለው። መሃላዋ የውሸት ስለሆነ በእርሱ ላይ አስገዳጅ አይሆንም፤ ስለዚህም ሌላ ለማግባት ነጻ ነው። ይቅር ካላት ግን የጋብቻ መሃላቸው ሊጸና ይችላል።

ሮሜ 7፡1 ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?

2 ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።

ሕጋዊ መሃላ እስከ ሞት ድረስ አይሻርም።

አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት ባለበት ዘመን ሁሉ የጋብቻ ሕግ ያስራታል።

ይህ ሕግ በሰውየውም ላይ እስኪት ድረስ ይሰራበታል።

በጣም የሚያሳዝነው ስሕተት አንድ ሰው በትዳሩ ላይ ዝሙት ሊፈጽም አይችልም የሚለው ወሬ ነው።

ይህ አባባል ያገባ ሰው ከላጤ ወይም ካላገባች ሴት ጋር መተኛት ይችላል የሚል ነው። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 6፡18 ከዝሙት ሽሹ።

መዳራት ማለት ያላገባ ሰው ወሲባዊ ግንኙነት ሲፈጽም ነው።

በአሁኑ ሰዓት የሜሴጅ ፓስተሮች ዋነኛ ስራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሚስጥራትን መተንተን ሆኗል።

የወንድም ብራንሐም አገልግሎት በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት ማጠናቀቅ ነበረ።

62-1230

ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

የሚያቀርባቸውን የመልእክት ዓይነት ተመልከቱ፤ “በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን በሙሉ ማጠናቀቅ”። ሰባተኛው መልአክ ያልተጠናቀቁትን ሚስጥራት በሙሉ ወደ መቋጫ እያመጣቸው ነው። ሰባተኛው መልአክ የተበታተኑትን ይሰበስባቸውና ሚስጥራቱን ሁሉ ያጠናቅቃል መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህንኑ ነው። “የተጻፈውን የመጽሐፍ ሚስጥር ያጠናቅቀዋል”።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን እንደ 7ቱ ነጎድጓዶች እና የጌታ ምጻት መች እንደሚሆን የመሳሰሉ ያልተጻፉ ሚስጥራትን በተመለከተ ልታስተምር አልሞከረችም።

64-0614 የእግዚአብሔር መገለጥ

እርሱም እንዲህ አለ፡- “ያው እንግዲህ እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች፤ አያችሁ፤ እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ማስተጋባታቸው፤ ይህ መገለጥ ለሆነ አይሰጠውምን?

እኔም እንዲህ ብዬ መልስኩ፡- “በፍጹም፤ የለም፤ ይህማ በቃሉ ላይ አንዳች መጨመር ነው።”

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን ቃል ነው የሰበከችው።

2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2 ቃሉን ስበክ፥

 

ማቴዎስ 24፡46 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤

47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

በንስሩ ዘመን ውስጥ የምንኖር አማኞች በዊልያም ብራንሐም የቀረቡ መልእክቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት አረጋግጠን መቀበል እንችላለን። ከዚያ በኋላ አስተምሕሮውን ወደ ወንድም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች ሳንመለስ ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መዝነን ማረጋገጥ መቻል አለብን።

ማቴዎስ 24፡48 ያ ክፉ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥

49 ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥

ራዕይ 17 ውስጥ ያለችዋ ታላቂቱ ጋለሞታ ጠጥታ ሰክራለች። ስለዚህ የሜሴጅ ፓስተሮች ከሮም ዲኖሚኔሽናዊ ጽዋ ጠጥተው እነርሱም የቤተክርስቲያን ራስ ነን ይላሉ። ልክ እንደ ካቶሊክ ቄሶች እነርሱም የቤተክርስቲያን ራስ ነን ይላሉ። በሕዝቡ ላይ ራሳቸውን ባለ ስልጣን አድርገው በጭቆና ይገዙዋቸዋል፤ ሕዝቡን በማስፈራራት ለመግዛት እንዲሁም ለእነርሱ ፈቃድ እንዲታዘዙ እና እምነታቸውን እንዲከተሉ ብለው የሚቃወሙዋቸውን ሁሉ በጥብቅ ያወግዛሉ። እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት ስለማይችሉ በሰበሰቡት የሰው ንግግር ጥቅሶች ነው የሚደገፉት። ከሕይወት ወንዝ መካፈል የምትችሉት የምትማሩትን ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ መርምራችሁ ስታረጋግጡ ነው።

ማቴዎስ 24፡50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥

ይህም ቃል ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን በድጋሚ ይነግረናል።

ማቴዎስ 24፡51 ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ፓስተሮች ታላቅነትን ይወዳሉ። ቤተክርስቲያንን ይመራሉ። ፓስተሮች ሕዝቡ ከእነርሱ እውቀት በላይ እንዳያውቅ ይገድቡታል፤ ከዚህም የተነሳ ፓስተሩ በማያውቃቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ጉባኤው መሃይም ሆኖ ይቀራል። ሕዝብን የሚጨቁኑ መሪዎች መጨረሻቸው ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።

ፓስተሮች እረኞች ነን ይላሉ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እረኛ ፓስተር ነው አይልም።

መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው አይልም።

“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ ስለዚህ ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን የለውም።

መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሮችን ስድስት ጊዜ ያወግዛቸዋል።

ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

ኤርምያስ 2፡8 ካህናቱም … ዐመፁብኝ፥

ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።

ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥

ፓስተሮች ብዙውን ጊዜ የሚሰሩዋቸው ስሕተቶች እነዚህ ናቸው። ሰዎች ስልጣን ሲይዙ ስልጣን እንደሚያበላሻቸው የታወቀ ነው።

የቤተክርስቲያን አመራር እንደገና ታይቶ መታረም ያስፈልገዋል።

ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤

አዲስ ኪዳን ወስጥ ፓስተሮች ወይም “መጋቢዎች” የተጠቀሱበት ብቸኛ ጥቅስ ይህ ነው።

በዚህም ጥቅስ ውስጥ ከአምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ በአራተኛ ደረጃ ላይ ነው የተጠቀሱት። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መሆን የሚችሉበት ማስረጃ የላቸውም። ያንን ስልጣን በጉልበት ተናጥቀው ነው የወሰዱት።

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሲመሰርት ፓስተሮች ጭራሽም አልጠቀሳቸውም።

1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።

ቤተክርስቲያንን መምራት ያለበት ማነው?

በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን መምራት ያለባቸው ሽማግሌዎች ናቸው ብሏል።

የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ መጨረሻ አካባቢ ቅዱስ ጴጥሮስ ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

 

ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

እግዚአብሔር ሰዎችን በሚገዙ ፓስተሮች አይደነቅም።

ፓስተሩ የራሱ የሆኑ ውሱንነቶች አሉበት። ፓስተር የራሱ ጥንካሬዎች ይኖሩታል፤ በተጨማሪም የራሱ ድክመቶችና የማያውቃቸው ነገሮች ስላሉ እነዚህ ድክመቶች ሕዝቡ እውነትን በመፈለግ ሂደት ውስጥ የሚሄዱትን እርምጃ ያጓትታሉ። አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ሽማግሌዎችን ይመድባሉ፤ ነገር ግን ሽማግሌዎች መጀመሪያ የፓስተሩን አዎንታ ማግኘት ስላለባቸው ከተሸሙ በኋላ የፓስተሩ አገልጋዮች ሆነው ይቀራሉ። ቤተክርስቲያኖች አንድ ሰው ከፍ ብሎ የሚገዛበትን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስለተቀበሉ ሽማግሌዎችም ጭምር ለፓስተሩ ተገዢዎች ይሆናሉ።

 

በአንድ ሰው ስልጣን ስር በምትገዛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማግኘት ከባድ ነው ምክንያቱም የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ ነው። በስሕተት ላይ በተመሰረተ መዋቅር ውስጥ እውነት በሙላት ልትገለጥ አትችልም።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ ገዥ መሆን በራሱ ስሕተት ቤተክርስቲያንን የሚወርርበት የመጨረሻው ዘመን አመላካች ነው።

 

ሁልጊዜ እግዚአብሔር ስላለንበት ሰባተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን የተናገረው አስቡ፡-

ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

ለብ ያለ ማለት በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በከፊል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ባለመከተል ማለት ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር አፍ ይመጣል። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች በሚያምኑት አብዛኛው እምነታቸው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ አለመኖሩ በአፉ ቃል ውስጥ አለመሆናቸውን ያመለክታል። እግዚአብሔር በከፊል ትክክል በከፊል ደግሞ ስሕተት ሆነን አይቀበለንም። ሙሉ በሙሉ ትክክል የሆኑ አስተምሕሮዎችን እንድንፈልግ ይጠብቅብናል። በሌላ አነጋገር ለመታረም ፈቃደኞች መሆን አለብን። ለመማር ዝግጁዎች መሆን አለብን። ለመማር ፍላጎት ሊኖረን ይገባል።

 

ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

 

እራሱን የቻለ ጨለማ የተባለ “ነገር” የለም። ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን አለማመን ብርሃን ማጣት ነው። ይህም ጨለማ ውስጥ ይከተናል። በጨለማ ውስጥ የሚኖር ሁሉ መንገዱን ስለማያይ ዕውር ነው። የቤተክርስቲያናችን አስተምሕሮዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ ከሌላቸው ብርሃናችን የሆነውን ኢየሱስን በሩን ፍለጋ በጨለማ ውስጥ በዳበሳ እየሄድን ነው ማለት ነው።

ዘፍጥረት 19፡10 ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።

11 በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ።

በሎጥም ዘመን ተመሳሳይ ነገር ሆነ። በሰዶም ውስጥ የነበሩ ግብረ ሰዶማውያን ለመግባት በሩን በጨለማ ውስጥ ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን በሩ ተዘጋ።

ሉቃስ 17፡28 እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤

ሁሉ ሰላም ይመስል በነበረ ጊዜ በሩ ተዘጋ።

ሉቃስ 17፡26 በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።

ስለዚህ ሁሉ ነገር ሰላም ይመስል ነበር፤ ነገር ግን የዛኔም እግዚአብሔር በሩን ዘጋው።

ዘፍጥረት 7፡16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት።

ወደ መርከቡ መግቢያ አንድ በር ብቻ ነበረ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ዘጋው።

ኢየሱስ የሰማይ መግቢያ በር ነው።

ዮሐንስ 10፡7 ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።

በኖህ ዘመን እንዲሁም በሎጥም ዘመን በሩ ተዘግቶ ነበር።

ስለዚህ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የዘመን መጨረሻ የመቅረቡ ትልቁ አመላካች እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳትን በር መዝጋቱ ነው።

ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ብዙ ጉዳዮችን ማብራራት አይችሉም፤ ደግሞም አብዛኞቹን ትምሕርቶቻቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትክክል መሆናቸውን አሳይተው ማረጋገጥ አይችሉም።

በዘመን መጨረሻ ወደ እውነት የሚያስገባው በር እየተዘጋ መሆኑን እንዴት እናውቃለን?

ሉቃስ 13፡24 በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።

25 ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላችኋል።

26 በዚያን ጊዜም፦ በፊትህ በላን ጠጣንም በአደባባያችንም አስተማርህ ልትሉ ትጀምራላችሁ፤

(የምስጋና እና የአምልኮ ብዛት)

በአደባባያችንም አስተማርህ።

27 እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል።

(እያወቁ ጥፋት የሚሰሩ ሰዎች)

28 አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

(ወደ ታላቁ መከራ)

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ደጅ ውጭ መቆሙን በግልጽ ያሳያል። የተዘጋውን በር እያንኳኳ ነው።

ስለዚህ በሩ ተዘግቷል፤ እርሱ ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች ድምጹን እንዲሰሙ እየተናገረ ነው፤ እሱም ቃሉ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ይህ ቃል የሚያሳየን በመጨረሻው ዘመን የሚያምኑ ሰዎች በቁጥር በጣም ጥቂት እንደሚሆኑ ነው።

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

እምነታችሁ የሚበረታው በውስጣሁ ባስቀመጣችሁት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መጠን ነው።

እነዚህ ሁለት ጥቅሶች የሚናገሩት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃነት አስደግፈው ማረጋገጥ እንደሚችሉ ነው።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ባይስማሙ እንኳ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚያረጋግጡ ሰዎች አንዳቸውን መሆን አስፈላጊ ነው። የምንድነው ብዙሃኑን በመከተል አይደለም። በሜዳ ላይ እህል ሲፈጩ ከነበሩት መካከል አንዷ ብቻ ናት የተወሰደችው።

ይህ ማስጠንቀቂያ ነው።

ከጥፋት ውሃ በፊት ሔኖክ ብቻ ነው ሳይሞት ወደ ሰማይ የተነጠቀው። ዛሬ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ለመነጠቅ መዘጋጀት አለባት። ስለዚህ በሕይወት ያለችው ሙሽራይቱም ሞትን አታይም። የጥፋት ውሃ ከዘመናችን ጋር የሚነጻጸር ከሆነ አሁንም የሚድኑ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ አይሆንም።

ስለዚህ የዘመኑ መጨረሻ ስለ መቃረቡ የሚያመለክተው ሌላ ምልክት በእምነታቸው ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥራቸው በጣም አነስተኛ መሆኑ ነው።

 

መጽሐፍ ቅዱስን በቁም ነገር አጥንተው የሚያምኑ እና የሚከተሉ ሰዎች ቁጥራቸው እየቀነሰ ነው። ለምን? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና ብለው ሲያስቡ ብዙ ሰዎች እንደማያጠኑ እና እንደማያምኑ ያያሉ።

የዘመኑ መጨረሻ ላይ የተለቀቀው የግድ የለሽነት ባህሪ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ያላቸውን የጋለ ፍላጎት አቀዝቅዞታል፤ ብዙዎችም ፍላጎታቸው ጠፍቷል።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ከሚቆጣጠረን ይልቅ የምንኖርበት ሁኔታ እንዲቆጣጠረን እየፈቀድን ነው።

ማቴዎስ 15፡8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23