ማቴዎስ ምዕራፍ 24 የሚተረጎመው በራዕይ ምዕራፍ 6 መሰረት ነው፤ ክፍል 3



ጽናት፤ በዘመን መጨረሻ የምትገኛዋ ሙሽራ ከባድ ሁኔታዎች ይገጥሟታል። አይሁዶች በ70 ዓ.ም የተፈጸመውን የኢየሩሳሌም መፍረስ እንዲያመልጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

First published on the 12th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ 24፡1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

2 እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።

3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ጥያቄ 1. መቅደሱ የሚፈርሰው መች ነው?

ጥያቄ 2. የመምጣትህ ምልክቱ ምንድነው?

ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ መች እንደሚመጣ አለመጠየቃቸውን ልብ በሉ። እኛም መጠየቅ የለብንም።

ጥያቄ 3. የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድነው?

 

 

ጥያቄ 3 ለመመለስ የሚከብድ ጥያቄ ነው።

ታላቁ የአርማጌዶን ጦርነት የዓለማችን ሥርዓት ፍጻሜ ነው (በስግብግብነት፣ በገንዘብ ፍቅር፣ በራስ ወዳድነት የተሞላው የበሰበሰው ስልጣኔያችን የሚያበቃበት) ከዚያ 1,000 ዓመታት ካለፉ በኋላ ግን የፍርድ ቀን ይመጣና አዲስ ምድር ከባሕር ውስጥ ብቅ ይላል። ስለዚህ ከእነዚህ ሁለት ክስተቶች መካከል የትኛውን ነው የዓለም ፍጻሜ ብለው ያሰቡት?

የአርማጌዶን ጦርነትን አስበው ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በዚያ ጊዜ ዮሐንስ ገና የራዕይ መጽሐፍን አልጻፈም ነበር። ስለዚህ የዚህ ዓለም የሐይማኖት፣ የፖለቲካ፣ እና የገንዘብ ፍቅር ስርዓት አብቅቶ ኢየሱስ ለ1,000 ዓመታት በምድር ላይ በሰላም የሚነግስበትን ጊዜ እያሰቡ ሊሆን ይችላል።

ኢየሱስ መልሱን ሊሰጣቸው ጀመረ።

ጥያቄ 1. መቅደሱ የሚፈርሰው መች ነው?

ኢየሱስ ቁርጥ ያለ ቀን አልሰጣቸውም። ይህ ለሁላችንም ማስጠንቀቂያ ነው። ቀኖችን አስልታችሁ ለማወቅ አትሞክሩ። ኢየሱስም ቀኑን ከመናገር ይልቅ ወደ ዋናው ቁምነገር በቀጥታ ይሄዳል እርሱም መጽሐፍ ቅዱስን አለማመን ነው። ስሕተቶች ሁሉ እና ሐጥያቶች ሁሉ ከዲያብሎስ ነው የሚመጡት። ስለዚህ ዲያብሎስ በማን በኩል ነው የሚሰራው?

ሰይጣን ትልቁ አሳሳች ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ቤተመቅደሱ መች እንደሚፈርስ ከመናገር ይልቅ ማን እንደሚያፈርሰው ይናገራል።

ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ይህ የመጀመሪያው ማሕተም ነው።

 

ነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በሚጋልበው የተመሰለው የሐይማኖት አሳሳች ክርስቲያኖችን ለመግዛት እና መጽሐፍ ቅዱስን ማመን ትተው የሰውን አመለካከትና የሰዎችን ልማዶች እንዲያምኑ ለማድረግ ይነሳል።

በሌላ አነጋገር እውነተኛ ክርስቲያኖችን የሚያስተው ታላቁ አሳሳች እርሱ ራሱ ነው የአይሁዶችንም ቤተመቅደስ የሚያፈርሰው።

ቤተመቅደሱን ያፈረሰው ማነው? በጄነራል ታይተስ መሪነት በ70 ዓ.ም የዘመተው የሮማውያን ሰራዊት ነው።

ስለዚህ የኢየሱስ መልስ ይህ ነው፡-

ቤተመቅደሱ መች እንደሚፈርስ መግለጥ አስፈላጊ አይደለም፤ ነገር ግን ቤተመቅደሱን ማን እንደሚያፈርሰው መግለጥ በጣም አስፈላጊ ነው።

አጥፊው ወይም ቤተመቅደሱን የሚያፈርሰው አካል የአይሁዶች ጠላት ብቻ አይደለም፤ የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ጠላትም ነው። ክርስቲያኖችን የሚያጠፋቸው መንፈሳዊ አሳሳች እራሱ ነው ቤተመቅደሱንም ያጠፋው። መንፈሱ የሚመጣው ከሮም ነው። አይሁዶችን ያጠፋቸው አጥፊ ክርስቲያኖችንም ያጠፋቸዋል። ሮማዊው አውሬ ሰዎችን ሁሉ የመጨቆንና የማጥፋት ፍላጎት አለው።

ወደር የሌለው የሮማውያን ጭካኔ እና ግፍ ከጊዜ በኋላ ቅርጹን ለውጦ በምድር ላይ ከተነሱ ነፍሰ ገዳዮች በአንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተመስሎ ይመጣል። በጨለማው ዘመን ውስጥ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ከአሥር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።

ኢየሱስ ጊዜው መች እንደሆነ ያልተናገረው ለምንድነው?

ምክንያቱም ድንጋይ በድንጋይ ላይ እየወደቀ ቤተመቅደሱ መፍረሱ እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዶች በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ተጨፍጭፈው ማለቃቸው በጣም አሰቃቂ ክስተት ስለነበረ ነው። ነገር ግን ያ ሁሉ እልቂት ከጊዜ በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቃዋሚዎቿን ለማፈን እና “አሕዛብን በሰይፍ ኃይል አስገድዳ ወደ ክርስትና ለመለወጥ” ከምትገድላቸው ሰዎች ብዛት ጋር ሲነጻጸር ከምንም የማይቆጠር ይሆናል።

በጣም የሚያሳዝነው ነገር በ70 ዓ.ም ከፈሰሰው የብዙ አይዶች ደም የበለጠ ኋላ ካቶሊክ መሆንን እምቢ የሚሉ ሰዎች ሞት እጅግ ይበዛል። ከ300 ዓ.ም እስከ 1600 የቤተክርስቲያን ታሪክ የተጻፈው በሰዎች ደም ነው፤ የዚያን ጊዜ አረማዊቷ ሮም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆና በመነሳት የሮማ ካቶሊክ ተከታይ አልሆንም ያለ ሰውን ሁሉ ትገድል ነበር። በዚያ ጊዜ ካቶሊክ ያልሆን ብዙ ሚሊዮን ሰዎች ተገድለዋል።

በብሉይ ኪዳን ዘመን አይሁዶች እንደ ሕዝብ ድነዋል።

አይሁዶች በቀራንዮ መሲሃቸውን አንቀበልም አሉ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ሕዝብ አድርጎ የነበረውን ቃልኪዳን አቋረጠ። ከዚያ ጊዜ በኋላ ልክ አሕዛብ በየግላቸው ኢየሱስን መቀበል እንዳለባቸው ሁሉ አይሁዶችም ኢየሱስን በግል መቀበል አለባቸው። ከዓመታት በኋላ በራሳቸው ሃገር ውስጥ የተቀሰቀሰ ስደት እና ደም መፋሰስ እንዲሁም የእሳት ቃጠሎ እና ልባቸው በጥላቻ የተሞሉ ሮማውያን በአንድነት ቤተመቅደሳቸውን አፍርሰውባቸዋል። እሥራኤልን ከመንፈሳዊው መድረክ ገፍትሮ ያስወጣት የሃገር ውስጥ መከራ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕዝቦቿ ያለቁበት ሰቆቃ ነው። በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አሕዛብ አዞረ።

በ1934 ሒትለር “ናይት ኦቭ ዘ ሎንግ ናይቭስ” ወይም የረጃጅሞቹ ቢላዎች ሌሊት በሚባል ቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎቹን ገደላቸው። ከዚያ በኋላ ይህ ነፍሰ ገዳይ ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ የ85% ጀርመናውያንን ድምጽ በማግኘት አሸነፈ። አይሁዶች በርባን የሚባል ነፍሰ ገዳይን መርጠው ኢየሱስን ገደሉት። ጀርመናውያን ደግሞ ሒትለር የተባለ ነፍሰ ገዳይ መረጡ። ከዚያ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሒትለር ፖላንድ ውስጥ ስድስት የጅምላ ጭፍጨፋ ማዕከሎችን በማዘጋጀት ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ገደለ። ሰው የዘራውን ያጭዳል።

ይህም የሚመጣው ታላቅ መከራ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምልክት ነው። እንደ ሒትለር እና እስታሊን የመሳሰሉ ፍጥረታዊ ነፍሰ ገዳዮች በፍጥረታዊ እሥራኤል ላይ ነፍሰ ገዳይ አጋንንትን ሰደዱ።

እነዚህ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት በ70 ዓ.ም ሮማውያን አይሁዶችን እንዲጠሉ እና ኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲገድሏቸው ሲገፋፉ የነበሩ አጋንንት እራሳቸው ናቸው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ደግሞ እነዚሁ አጋንንት እጅግ የሚጠሉዋቸውን አይሁዶችን እንዲጨፈጭፏቸው የናዚዎችን ልብ አነሳሱ።

በጀርመናውያን የተደረገው የአይሁዶች ጭፍጨፋ የታላቁ መከራ ታናሽ ወንድም ነው። እግዚአብሔር በ33 ዓ.ም በቀራንዮ አይሁዶችን ተለይቶ ሄደ። በ70 ዓ.ም በአንድ ጊዜ እንደ ዶፍ በወረደ ሞት እና ጥፋት ውስጥ ቤተመቅደሱ ፈረሰ።

በ1900ዎቹ አካባቢ እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን መመለስ ጀመረ። ሰይጣንም ይህንን የእግዚአብሔር ወደ አይሁዶች መመለስ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ታላቅ ደም መፋሰስ አማካኝነት ሊያስቆም ሞከረ። በዓለም ላይ ከነበሩ አይሁዳውያን ውስጥ አንድ ሶስተኛዎቹ አለቁ። ከዚያ በኋላ በ1948 አይሁዶች ሃገራቸውን ከአረብ ሃገሮች ጋር ለአምስት አመታት መራራ ጦርነት ተዋግተው ነው ሃገራቸውን መልሰው የያዙት። አሁን አይሁዶች መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ ሊቀበሉት መጠባበቅ በሚችሉበት ሃገር ውስጥ ናቸው። እድሜ ለፐሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም አሁን የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን እውቅና አግኝታለች። የጎላን ኮረብታዎችም በትራምፕ አማካኝነት ለእሥራኤል ተመልሰዋል። እግዚአብሔር ከ2,000 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አይሁዶች እየተመለሰ ነው፤ ይህም ማለት ከአሕዛብ ፊቱን ዞር እያደረገ ነው።

ማቴዎስ 24፡5 ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።

የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ ነጭ ፈረስ እና በላዩ የተቀመጠው ነበር የታዩት፤ እርሱም የሐይማኖት አሳች ነው። ይህም የሚያመለክተው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አነሳስ ነው። ይህ የሐይማኖት እነ የፖለቲካ ጥምረት ካቶሊክ ያልሆኑ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ገድሏል። እያንዳንዱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር መንፈሳዊ ቤተመቅደስ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ነው። እግዚአብሔርም ይህንን መንፈሳዊ ቤተመቅደስ ለ2,000 ዓመታት ያህል ሲሰራው ቆይቷል። የእግዚአብሔር እውነተኛ ቤተመቅደስ ይህ ነው።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

የክርስቶስን መንፈሳዊ አካል ወይም ቤተመቅደስ ለማፍረስ ሮም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድላለች። ከዚያም በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ፈንታ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችን እና ልማዶች አምነው በመታለላቸው የተነሳ ተጨማሪ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጠፍተዋል፤ ከዚህም የተነሳ በቅንነት ቢኖሩም እንኳ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ አካል መሆን አልቻሉም። ሰው ሰራሽ ትዕዛዛት ማንንም ማዳን አይችሉም።

የቄሳሮቹ አረማዊ ሮም ኢየሩሳሌምን አጠፋች።

በካቶሊክ ጳጳሳት ስር ያለችው ሮም ደግሞ የሚቃወሙዋትንና መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን የሚሞክሩ ክርስቲያኖችን ያለማቋረጥ ለማጥፋት ስትሞክር ቆይታለች።

ሮም የተሳሳተ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ተመስርቶ የጸናባት የሐይማኖታዊ ስሕተት ማዕከል ናት። የፖፑ የመጀመሪያ ማዕረግ የሮም ጳጳስ የሚል ነበር። የፖፑ ሁለተኛው ማዕረግ Vicar of Christ (“ቪካር ኦቭ ክራይስት” ማለት በክርስቶስ ቦታ ማለት ነው) የሚል ሲሆን ይህም ማዕረግ ትልቅ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል።

በኤርምያስ ምዕራፍ 10 ውስጥ እንደተጠቀሰው አሕዛ እንደሚያመልኩበት ያጌጠ ዛፍ የገና ዛፍም የክሪስማስ ዛፍ በተባለ ጊዜ ተቀባይነት አገኘ። ይህም ተቀባይነት የተገኘው ክሪስማስ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመኖሩ እየታወቀ ነው። የዲሴምበር 25 ቀንም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

ኤርምያስ 10፡2 የአሕዛብን መንገድ አትማሩ …

3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።

4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ …

5 እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው …

ዛሬ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በቤታቸው እና በሱቆቻቸው ውስጥ የክሪስማስ ዛፍ አላቸው።

ክርስትና ከአረማዊነት ጋር ሙሉ በሙሉ በመጋባት አንድነት ፈጥሯል። ይህንን የተቀላቀለ “ክርስትና” ልንለው አይገባም። ክርስትና ሳይሆን ቤተክርስቲያናዊነት ነው።

ማቴዎስ 24፡6 ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ይህ ሁለተኛው ማሕተም ነው።

ለምንድነው የተጠቀሰው? ምክንያቱም ኢየሱስ ስሕተት ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት እንደገባ እንዲሁም ሰዎች ስሕተትን አራግፈው መጣል እስኪያቅታቸው ድረስ እንዴት ስር እንደሰደደ እየነገረን ነው። ፖለቲካ የስልጣን ጥማት ነው። ቤተክርስቲያን ወደ ፖለቲካ ውስጥ ገብታ በሰዎች ላይ ስልጣን በመያዝ ሱስ ተጠመደች።

መጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶች የመጣ ሐይማኖታዊ ስሕተት ነበረ።

ከዚያ በኋላ ግን ቤተክርስቲያን በፖለቲካዊ ስልጣን ውስጥ ገብታ ፖፑ በሕዝብ ላይ ያለው ስልጣን እንዲያድግ አደርጋለች። ከዚያ በኋላ ፖፑ የብዙ ሃገሮችን ጦር ሰራዊት ማዘዝ እና በእነርሱ አማካኝነት ካቶሊክ ያልሆኑ “መናፍቃንን” ማስገደል ቻለ። ፖለቲካ በሰይጣን ነው የሚመራው። ስለዚህ እውነት እየጠፋች ነበር።

ሮማዊው አውሬ የሚወክለው በሐይማኖት ተተቅመው እያሳቱ ፖለቲካዊ ስልጣንን ከዚያም ፖለቲካዊ ኃይልን የሚቆናጠጡ ሰዎችን ነው።

ፖለቲካ ዓላማው ለአንድ ቡድን መሪ ትልቅ ስልጣን ማስረከብ ነው። ፖለቲከኞች ፍላጎታቸው መግዛት እና መጨቆን ነው።

ከ366 – 384 ዓ.ም የሮም ጳጳስ የነበረው ዳማሰስ በ382 ዓ.ም የሮማ ገዥ በነበረው በአጎቱ በቴዎዶሲየስ አማካኝነት ፖንቲፍ የሚባለውን ማዕረግ ተቀበለ። ይህም ማዕረግ በአረማውያን ዘንድ ትልቅ ክብር ሰጠው ምክንያቱም የሮም ጳጳስ ሆኖ ለመመረጥ ብሎ ተከታዮቹ ወደ 300 መቶ የሚያህሉ የእርሱ ተፎካካሪዎች የነበሩ ሰዎችን እንዲገድሉለት አስደርጎ ነበር።

በአረማውያን ዘንድ ተወዳጅነት ለማግኘት ብለው የሮማ ጳጳሶች የአረማውያንን ልማዶችና እምነቶች ክርስቲያናዊ መልክ እየሰጡ ይቀበሉ ነበር። ክርስትናን ለአረማውያን አመቺ ለማድረግ ደግሞ የሮማ ቤተክርስቲያን አረማውያን እምነቶችን ክርስቲያናዊ ስም እየሰጠች ትቀበል ነበር።

አንድ የታሪክ ምሑር እንደጻፈው፡- “የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ክርስትና የተነሳች አረማዊነት ናት”።

በ274 ዓ.ም በንጉስ ኦሬልያን አማካኝነት የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን ሆኖ የተደነገገው ዲሴምበር 25 ቀን የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ልደት ነው ተባለ። ይህም የተደረገው ኦሬልያን በጣም ክፉ የሆነ የክርስቲያኖች አሳዳጅ መሆኑ እየታወቀ ነው። ዲሴምበር 25ን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን አድርጎ ከመደንገጉ ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር የሮምን ጳጳስ የገደለው።

ኢሽታር የተባለችዋ ሴት አምላክ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ከእንቁላል ነው የተወለደችው ይባላል። ይህም የኢስተር ወይም የፋሲካ እንቁላል ተባለ።

የዳማሰስ ተተተኪ የነበረው ሲሪሺየስ የተባለው ጳጳስ (384 - 399) ፖፕ በሚባለው ማዕረግ ለመጠራት የመጀመሪያው ጳጳስ ነበረ።

ነገስታት የፖፑን አዋጆች ለማስፈጸም የጦር ሰራዊት ኃይላቸውን ይጠቀሙ ነበር።

በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።

 

 

ማቴዎስ 24፡7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥

ጦርነቶች መነሻቸው የወደቀው የሰው ተፈጥሮ ነው። ሐይማኖታዊ ጦርነቶች ደግሞ ክፋታቸው እጥፍ ድርብ ነው ምክንያቱም ሰዎች ሰውን በመግደላቸው እግዚአብሔርን ያገለገሉ ይመስላቸዋል። ቤተክርስቲያን ወደ ፖለቲካ ውስጥ ስትገባ ተቃዋሚዎቿን ገዳይ ሆና ተነሳች።

ጥይት መፈጠሩ ሰው ሰውን በአንድ ጊዜ በብዙ መግደል አስችሎታል። የጦር መሳሪያዎች እየተመረቱ የሞት ፋብሪካዎች እንዲከፈቱ አድርገዋል። የዓለም ታሪክ ማለቂያ በሌላቸው ጦርነቶች የተሞላ ነው።

ራብም… ይሆናል

ሦስተኛው ማሕተም በጥቁሩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው የሕይወትን እንጀራ በሚዛን የሚመዝንበት ነው።

ሕዝቡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የሚያስተምራቸው በማጣታቸው እውነትን ይራባሉ፤ በራባቸውም ጊዜ ማንኛውንም ያገኙትን መንፈሳዊ ምግብ ሁሉ አግበስብሰው ይበላሉ፤ ማንኛውንም ስሕተት ይቀበላሉ።

ከማርቲን ሉተር ተሃድሶ ጀምሮ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች መዳን በእምነት ብቻ የሚለውን ትምሕርት ይዘው ከመጡ በኋላ ወዲያው ከሉተር ሞት በኋላ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሃሳቦች ተሞልተዋል።

የጌታ እራት በቤተክርስቲያኖች በጠዋት ይቀርባል የጌታ ቁርስ ይመስል።

ጴጥሮስ ንሰሃ ግቡ ደግሞም ተጠመቁ አለ። በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ግን ሕጻናትን ማጥመቅ ተጀመረ፤ ሕጻናት ንሰሃ ሊገቡ እንደማይችሉ እየታወቀ።

ዲኖሚኔሽናዊነት የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ባይሆንም እንኳ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እያደገ ሄደ።

ቤተክርስቲያኖች ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ። ሰዎች በመሪነት ከጉባኤው በላይ ከፍ ተደረጉ። እያንዳንዱ መሪ የራሱን የግል አመለካከት በማራመዱ የተነሳ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የዳንኤል ሕልም ውስጥ እንዳለው ሃውልት እግሮች መጀመሪያ በሁለት ከዚያ በአስር ጣቶች ከዚያም በላይ እየተሰነጣጠቁ እየተከፋፈሉ ሄዱ። ቤተክርስቲያኖች በሰው አመለካከቶች እና ልማዶች እየተሞሉ ሄዱ ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትክክለኛነትን እየለቀቁ ሄዱ። የቤተክርስቲያን ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በጣም ተራቡ ተጠሙ።

ብዙ ጦርነቶች ገጠሮች ሁሉ ውስጥ ስለተዛመቱ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታዊ ረሃብም በብዙ ሃገሮች ውስጥ ተስፋፋ።

ቸነፈርም

አራተኛው ማሕተም። ይህ በ1906 አካባቢ የጀመረው 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።

ቸነፈሮች የበሽታ ወረርሽኞች ናቸው (ዓለም አቀፍ በሽታዎች)። ቸነፈሮች ብዙውን ጊዜ ሰውን ከመግደላቸው በፊት የቆዳውን መልክ እንደ እሬሳ እንዲገረጣ የሚያደርጉ በሽታዎች ናቸው። ብላክ ዴዝ የሚባለው እና የመሳሰሉ ወረርሽኞች ከአውሮፓ ሕዝብ አንድ አራተኛውን ያህል አጥፍተዋል። በሽታዎችን (እንደ ኤድስ እና ኢቦላ የመሳሰሉትን) ገዳይ የሚያደርጋቸው በሽታውን መጀመሪያ ያመጣው ጀርም ወይም ቫይረስ መልኩን መቀያየሩ ነው። ኤድስ ከ1960ዎቹ ጀምሮ በዓልም ዙርያ ተሰራጭቷል፤ እስከ ዛሬም 40 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል። በየዓመቱ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ሕዝብ በኤድስ ይሞታል። ደግነቱ ሳይንቲስቶች ኤድስ የሚያመጣውን ስቃይ በመጠኑ መቀነስ ችለዋል።

በ1918 እስፓኒሽ ፍሉ የተባለ የጉንፋን ዓይነት ከ65 ሚሊዮን እስከ 100 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎችን ከ1918 – 1920 በሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ገድሏል።

በ1918 ዓ.ም በምድር ላይ ሁለት ቢሊዮን ሕዝብ ነበሩ፤ ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በእስፓኒሽ ፍሉ ተይዘው ነበር።

ስለዚህ አራተኛው ማሕተም የተፈታው በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው፤ ማሕተሙ በተፈታ ጊዜም በሶስት ዓመታት ውስጥ በታሪክ በአንድ ጊዜ በበሽታ ምክንያት ከሞቱት ሕዝብ ሁሉ የበለጠ ሕዝብ አልቋል። ቢል ጌትስ ከሁሉ ነገር በላይ በጣም የሚፈራው እና ለመከላከልም ብዙ ገንዘብ በእርዳት የሚሰጥበት ዋና ምክንያት የገዳይ በሽታ አምጭ ቫይረስ በድንገት እንዳይሰራጭ እንደሆነ ይናገራል።

በ2020 ዓ.ም ኮቪድ-19 የተባለው የኮሮና በሽታ ቻይና ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ እስኪሆን ድረስ ተስፋፋና በአውሮፓ አልፎ አሜሪካ ገባ። የብዙ ሰዎች ጤና እና የሃገሮች ኢኮኖሚ ተጎዳ።

ሐመሩ ፈረስ የጥቁር፣ የቀይ እና የነጭ ድብልቅ ነው። እነዚህም ሶስቱ የክፋት ኃይላት በአንድነት በቤተክርስቲያን ውስጥ እየሰሩ ያሉት የሐይማኖታዊ አሳሳችነት፣ ፖለቲካዊ የስልጣን ብልግና፣ እና ከገንዘብ ፍቅር ጋር የተያያዘ አጋንንታዊ አሰራር ናቸው።

ዛሬ ትልቁ የስሕተት ምንጭ ምንድነው?

ትልቁ ስሕተት ምንጩ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወስዶ የራሳችንን ልማድ በተለይም ከአሕዛብ እና ከጣኦት አምልኮ የወሰድነውን ልማድ እንዲደግፍልን አመቻችተን መተርጎም ነው።

ለምሳሌ፡- ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች አዳም እና ሔዋን የዛፍ ፍሬ በሉ ብለው ያምናሉ፤ እና የኤደን ገነት ውስጥ ሔዋንን ያናገራት እባብ የእውነት ፍጥረታዊው እባብ ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን እባቦች መናገርም ሆነ ተከራክረው ሰውን ማሳመን አይችሉም። እባቡ በሰው እና በዝንጀሮ መካከል ያለ ከእንሳስት ሁሉ ከፍ ያለ እንስሳ ነበረ እንጂ የምናውቀው ዓይነት እባብ አልነበረም። እባቡ የምናውቀው ዓይነት እባብ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረውን እርግማን አብራርቶ አይነግረውም ነበር።

ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ኢየሱስ ዲሴምበር 25 ቀን ነው የተወለደው ብለው ያምናሉ፤ በተጨማሪም መፋታት እና እንደገና ማግባት ችግር የለውም ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር ሥላሴ ነው፤ ፓስተሩ ደግሞ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ብለው ያምናሉ። ከእነዚህ ሃሳቦች አንዳቸውም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም። እነዚህ ሁሉ መልካቸውን የለወጡ መንፈሳዊ ቫይረሶች ናቸው ስለዚህ የሰዎችን አእምሮ ከበከሉ በኋላ መኖራቸውን ለማየትም ሆነ ከሰው አእምሮ ውስጥ ለማስወጣት ያስቸግራሉ።

የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ሥፍራ

ከዘመኑ ምልክቶች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። የመሬት መንቀጥቀጦች እና ምድርን በውሃ የሚያጥለቀል የባሕር በታች የመሬት መንቀጥቀጦች አዘውትረው መከሰት ጀምረዋል። ይህ ሁሉ ወደ መጨረሻው የመቃረባችን ምልክት ነው። ይህ የመጨረሻው ዘመን ምልክት እንደመሆኑ መጠን ከዚህ በኋላ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የሚያደርሰውም ጥፋት እየበዛ ይሄዳል ብለን መተንበይ እንችላለን። ሎስአንጀለስን ትልቅ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያፈርሳት ጊዜ አሜሪካ በሙሉ ችግር ውስጥ ትገባለች፤ አሜሪካ የዓለምን ኢኮኖሚ ትልቁን ክፍል የያዘች ሃገር በመሆኗ ችግር ውስጥ ስትገባ የብዙ ሃገሮች ኢኮኖሚ አብሯት ይወድቃል።

 

 

ከላይ የቀረበው ካርታ ውስጥ ቀዩ መስመር ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚከሰትባቸውን ቦታዎች ያሳያል፤ መንቀጥቀጡ የሚከሰተውም በአሜሪካ ምዕራባዊ ዳርቻ ነው።

አረንጓዴው መስመር እየሰፋ ይሄዳል።

ሎስአንጀለስ አንድ ቀን ከባሕር በታች መስመጧ አይቀርም ምክንያቱም በባሕሩ እና የመሬት መንቀጥቀት በሚከሰትበት መስመር መካከል ነው የምትገኘው።

 

 

በ2014 ዓ.ም የመሬት መንቀጥቀት ቶሎ ቶሎ ይከሰት ነበር። እነዚህ የመሬት መንቀጥቀጦች ክስተታቸው መደበኛ ጊዜ እየጠበቀ የሚመጣ አይደለም። ነገር ግን መንቀጥቀጦቹ ምድር ኢየሱስ ለአንድ ሺ ዓመት በሰላም የሚገዛበትን መንግስት ለመውለድ የጀመረችው የምጥ ጣር እንደሆኑ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ።

“በልዩ ልዩ ሥፍራ” ማለት በተለያዩ ሃገሮች ውስጥ ማለት ነው። ከዓለም ዙርያ ከተለያዩ ቦታዎች የምድር መንቀጥቀጥ ዜና እንሰማለን። የምድር የላይኛው ንጣፍ እየተወጠረ ነው። የምንኖርባት ምድር ከእንግዲህ በኋላ አስተማማኝ አይደለችም። ከምድር የላይኛው ንጣፍ ስር ያሉ ዓለቶች እየተጨማደዱ ስለሆነ የምድር መንቀጥቀጦች እንደ ማስጠንቀቂያ ምልክት ይከሰታሉ። ጌታ እየመጣ ነው።

 

 

ማቴዎስ 24፡8 እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

ስሕተትን በሚያስፋፋው ፈረስ ላይ የተቀመጠው ጋላቢ የክርስቲያኖችን አእምሮ እንዴት በፍጥነት እንደተቆጣጠረ ኢየሱስ አሳይቶናል።

ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ታሪክ እስከ መጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ድረስ ምን እንደሚመስል አሳይቷል። እነዚህ ሁሉ ችግሮች ግን የምጣ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ኢየሱስ በትምሕርቱ ውስጥ እስከ አራተኛው ማሕተም የመጀመሪያ ቁጥር ድረስ አብራርቷል፤ እርሱም የንስሩ ዘመን ሲሆን ስሕተትን ለመከላከል የምንዘጋጅበት እንዲሁም ለጌታ ምጻት ዝግጁ ሆነን የምንቆምበት ዘመን ነው።

በምድር ላይ እንደ ቫይረስ በፍጥነት እየተዛሙቱ በአንድነት የሚመጡትን የክፋት እና የስሕተት ማዕበል መቋቋም እንችል ዘንድ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጦ ሊያስተምረን ይገባል።

ስለዚህ በዚህ ቃል አማካኝነት 2ኛውን ጥያቄ ይመልስልናል፡- የመምጣትህ ምልክቱ ምንድነው?

ከመልሱ እንደምንረዳው ከምጻቱ በፊት ብዙ ነውጦች ይከሰታሉ።

ነገር ግን ከዳግም ምጻቱ በፊት የሚከሰቱት ነውጦች የምጥ መጀመሪያ ተብለው ነው የተገለጹት።

ስለዚህ ነገሮች እየከበዱ ይሄዳሉ፤ ሰዎች ግን የችግሮቹ ምንጭ እና መንስኤ ምን እንደሆነ አያተውሉም። አሁን የምንኖርበት ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻው በታላቁ መከራ ሲሆን በዚህ መከራ ውስጥ የምጥ ጣሩ ይበልጥ እየከፋ ነው የሚሄደው።

ስለዚህ 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰዎች እውነትን እምቢ ብለው እየካዱ ነው የሚጠናቀቀው።

ልክ ጌታ ከመምጣቱ በፊት በምድር ላይ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ነው የሚመስሉት፡-

ማቴዎስ 24፡9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥

ክርስቲያኖች ያለማቋጥ ሲሰደዱ ቆይተዋል። 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በታላቅ ስደት ነው የተጀመረው፤ በ1915 ኦቶማን ቱርኮች ከ1 ሚሊዮን በላይ አርሜኒያውያን ክርስቲያኖችን ገድለዋል። ከዚያን ጊዜ በኋላ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የሚባለው ቃል ተወለደ። ዛሬ ከ40 በላይ በሚሆኑ ሃገሮች ውስጥ ክርስቲያኖች በሙስሊሞች ይሰደዳሉ፤ በአማካይም በወር 180 ክርስቲያኖች ስለ እምነታቸው ይሞታሉ። እንደ አይ.ኤስ.አይ.ኤስ የመሳሰሉ እስማላዊ ጽንፈኞች ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖችን ገድለዋል።

በተጨማሪ የሜሴጅ ተከታዮች ደግሞ ከእነርሱ ጋር የማይስማሙ ሰዎችን ያወግዛሉ። ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችም የሚቃረኑዋቸውን ሰዎች ያወግዛሉ። አለመቻቻል ነግሷል።

የሰው ንግግር ጥቅስ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተደርጎ በሚወሰድበት በዚህ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የሚከተሉ ሰዎች ያወግዟቸዋል። ሰዎች አሁን በአካል እየተገደሉ አይደሉም፤ ነገር ግን ስሕተትን የሚያጋልጡ ሰዎችን ስማቸውን ማጥፋት ከመግደል ያልተናነሰ ጸጥ ማሰኛ ዘዴ ነው።

ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በሐዋርያት ሥራ 2፡38 ውስጥ ጴጥሮስ እንዳዘዘው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ ከባድ ጥላቻን ይቀሰቅሳል። ቀጥሎ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚባለው ስም የእግዚአብሔር ስም ነው ብላችሁ ብትናገሩ የሥላሴ አማኞች ጭራሽም ሊያናግሯችሁ አይፈልጉም።

ማቴዎስ 24፡10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤

11 ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤

ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መሳሳታቸውን የሚያሳያቸውን ሰው ይጠላሉ። ከእንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ጋር ምንም ሕብረት አይፈልጉም።

ሰባኪዎች የሰውን ንግግሮች ይገጣጥማሉ፤ ንግግሮቹን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈተሽ ሲገባቸው። ሰዎች መሪዎቻቸውን መከተል ይወዳሉ ምክንያቱም እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሾ የማረጋገጡን ከባድ ስራ መስራት አይወዱም።

የሜሴጅ ሰባኪዎች ስለ አንዲት አሜሪካ ላይ ስለምትቀመጥ ቆንጅዬ ነገር ግን ጨካኝ ሴት (የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልትሆን ትችላለች) የተነገረውን ንግግር አጣምመው ተረጎሙ። ሲተረጉሙም ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ማለት ነው አሉ። እርሷ ግን አላሸነፈችም። በተሳሳተ መረዳት የተተረጎሙ ጥቅሶች ላይ የተመሰረተ ትንቢት መጨረሻው ይህ ነው።

12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።

ብዙ ሰዎች የተሳሳተ ነገር ስለሚያደርጉ (በሐጥያት መኖር እና ገላን አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ መልበስ) ሰዎች ችግር የለውም ይላሉ።

ዓመፃ ማለት ሰዎች ስሕተት እየሰሩ መሆናቸውን እያወቁ መስራታቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው።

ሰዎች በጥቂት የሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ የተመሰረቱ አስተምሕሮዎችን ያምናሉ። ይህም በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት አለው።

ስለዚህ የአንድን አስተምሕሮ ትክክለኛነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገጣጠም ብቻ ለማሳየት የሚሞክር ሰው ብዙዎች ይገፉታል። አንድን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ተከተለ ብሎ መግፋት ስሕተት መሆኑን ያውቃሉ፤ ግን እያወቁ እንደዚያ ዓይቱን ሰው ይገፉታል፤ ይህንንም የሚያደርጉት በቤተክርስቲያናቸው አባልነት ተመችቷቸው ለመኖር ብለው ነው። ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ከመሞከር እና አስተምሕሮዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሾ ለማረጋገጥ ከመሞከር በጣም ይቀልላል።

13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

ይህንን የሚናገረው ስለ ግለሰብ ነው እንጂ ስለ ቤተክርሰቲያን ወይም ስለ ቡድን አይደለም።

ከታላቁ መከራ የሚድኑት ግለሰቦች ናቸው።

ነገር ግን እስከ መጨረሻው መጽናት አለብን። ቀላል ወይም አልጋ በአልጋ የሆነ መንገድ የለም።

ፊልጵስዩስ 2፡12 በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ይህ መዳን ከሲኦል አይደለም። ራሳችሁን ከሲኦል ማዳን አትችሉም።

ይህ መዳን ከታላቁ መከራ ነው። ከታላቁ መከራ ለመዳን ከቤተክርስቲያናችሁ በተለይም ደግሞ ከቤተክርስቲያናችሁ መሪዎች ጋር መቃረን አለባችሁ። ይህን የማድረግ ወኔ አላችሁን?

ማቴዎስ 24፡14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።

ወንጌሉ በዓለም ዙርያ ሁሉ መዳረስ አለበት። ሚሽነሪዎች ትልቅ ሥራ ሰርተዋል። የሬድዮ እን የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በአየር ሞገዶች በዓለም ዙርያ ሁሉ ተሰራጭተዋል። አሁን ደግሞ ከበፊቱ የበለጠ ብዙ መረዳ በኢንተርኔት ወይም በመረጃ መረብ አማካኝነት መለዋወጥ ተችሏል።

ኢንተርኔት ወንጌልን በዓለም ሁሉ ማሰራጨት አስችሏል።

በአሁኔ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞባይል ስልክ አላቸው፤ ስለዚህ አንድ ሰው አጠገቡ ያሉ ሰዎች እውነትን ባይፈልጉ እንኳ እርሱ ግን ሞባይል ስልክ ከያዘ እውነተን በዌብሳይት ወይም በድረ ገጽ ላይ ማንበብ ይችላል

አሁን አዲስ የመጣ ዙም የሚባል የኢንተርኔት ፕሮግራም ደግሞ ጥቂት ሰዎች በዓለም ላይ በተለያየ ቦታ ተበታትነው ቢገኙም እንኳ በቡድን ሃሳብ እንዲለዋወጡ እና መጽሐፍ ቅዱስን እንዲወያዩ ያስችላል።

“በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።”

ይህ ለሶስተኛው ጥያቄ መልስ ነው።

አራተኛው ማሕተም በሁለት ቁጥሮች ነው የተገለጸው። የመጀመሪያው ቁጥር (ራዕይ 6፡7) የንስሩን ዘመን የሚያሳይ ሲሆን እርሱም ታላቁን መከራ ለማምለጥ ማወቅ የሚያስፈልገንን ነገር ይገልጥልናል።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም የሚጠቀሙ ሰዎች ለጌታ ምጻት ዝግጁ ሆነው ይገኛሉ። ከዚያ በኋላ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ። በዚህም መንገድ ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ አማካኝነት በዓለም ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ታመልጣለች።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

ይህ ሁለተኛው ጥቅስ (ራዕይ 6፡8) ሞት ታላቁን መከራ ለማምጣት እየጋለበ ሲገባ ያሳያል።

ሞት መግባት የሚችለው ሕይወት ለቆ ሲወጣ ብቻ ነው።

ስለዚህ ከዳኑ ክርስቲያኖች ውስጥ አብዛኞቹ ልክ እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ፤ በንስሩ አማካኝነት የመጣውን የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የሚሰሙ ጥቂት ልባም ቆነጃጅት ብቻ ናቸው ከመከራው የሚያመልጡት። ሰነፎቹ ቆነጃጅት መጨሻቸው ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ሲሆን ይህም መከራ የሚያበቃው በአርማጌዶን ጦርነት ነው። አርማጌዶን የዚህ ዓለም ስርዓት ማብቂያ ነው።

ማቴዎስ 24፡14 “በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።”

ታላቁ መከራ የዘመናችን ስልጣኔ እና የዚህ ዓለም ስርዓት ማብቃታቸውን በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሚጠፉበት ወቅት ነው።

ስለዚህ የዚህ ዓለም መጨረሻው ከጌታ ምጻት ሶስት ዓመት ተኩል በኋላ ነው የሚሆነው።

በዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና ውስጥ በተከበብንበት በዚህ ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኝ መሆን ምን ያህል ከባድ መሆኑን ኢየሱስ አስረድቶናል። ታላቁን መከራ ማምለጥ ከፈለግን ልንጠነቀቃቸው የሚያስፈልገንን ዋና ዋና ስሕተቶች ጠቁሞናል።

ከታላቁ መከራ እንዴት ማምለጥ እንደሚችሉ ምክር ከሰጠ በኋላ ኢየሱስ ተመልሶ ስለ ቤተመቅደሱ መፍረስ ይናገራል። ለአይሁዶች በኢየሩሳሌም ሮማውያን ቤተመቅደሱን ሲያፈርሱ ስለሚከሰተው ስደት አስመልክቶ እንዴት ማምለጥ እንደሚችሉ ምሪት ይሰጣቸዋል። ያ ጊዜ ለአይሁዶች ከባድ ጊዜ ስለሚሆንባቸው ኢየሱስ አስፈላጊውን ምክር ሰጥቷቸዋል።

ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

“አንባቢው ያስተውል” የሚሉት ቃላት የጥፋት እርኩሰት በመጣ ጊዜ ለማስተዋል ቀላል እንዳልሆነ ያመለክታሉ።

ወንድም ብራንሐም እንደሚለው ዛሬ የኦማር መስጊድ በቤተመቅደሱ ቦታ ላይ ቆሟል (የኦማር ሙስሊም የሚባል የለም)። ኢየሱስ የጥፋት እርኩሰት ብሎ ይጠራዋል።

የኦማር መስጊድ ከቤተመቅደሱ ቦታ 500 ሜትር ራቅ ብሎ ነው የቆመው። ዶም ኦቭ ዘሮክ የሚባለው ሕንጻ ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ መሃል ላይ ነው ያለው።

61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 2

… ጥፋት የሚያስከትለው እርኩሰት(የኦማር ሙስሊም መስጊድ ቤተመቅደሱን ባፈረሱበት ቀን በቤተመቅደሱ ቦታ ሲቆሙ)…

በ70 ዓ.ም ታይተስ ቤተመቅደሱን አቃለጠ። ከዚያ በኋላ በ692 ዓ.ም ነው ሙስሊሞቹ ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለውን መስጊድ የሰሩት።

61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 2

የኦማር ሙስሊም ትክክል ነበር… በቤተመቅደሱ ቦታ ሰርተውት እስከዛሬ ድረስ በዚያ ቦታ ቆሟል።

ዶም ኦቭ ዘሮክ ከዚህ በታች ባለው ፎቶ ውስጥ በአረንጓዴ መስመር ክብ የተሳለበት ቦታ ነው። ዶም ኦፍ ዘሮክ መስጊድ አይደለም።

ከበታቹ ያለው በቀይ ቀለም አራት ማዕዘን ምልክት የተደረገበት ሕንጻ አል-አቅሳ መስጊድ ሲሆን የተሰራው በ705 ዓ.ም ነው።

በሁለቱ ሕንጻዎች ዙርያ ያለው ትልቅ አራት ማዕዘን ግድግዳ የመጀመሪያው ቤተመቅደስ የቆመበት ቦታ ከሆነ ዶም ኦቭ ዘሮክ ቤተመቅደሱ መጀመሪያ ተሰርቶ የነበረበት ቦታ ሊሆን ይችላል (አንዳንድ ሰዎች ግን ይህ ቦታ የመጀመሪያው የቤተመቅደሱ ስፍራ ሊሆን አይችልም ብለው ይከራከራሉ፤ ምክንያቱም ለመስዋእት የሚቀርቡትን እንስሳት ማጠቢያ የሚሆን የውሃ ምንጭ በአካባቢው የለም)። ሮክ ወይም ዓለቱ የመጀመሪያው ቤተመቅደስ የቆመበት ትልቅ መሰረት ነው ተብሎ ይታመናል።

 

 

ቀጣዩ ካርታ ከዶም ኦቭ ዘሮክ በስተግራ 500 ርቀት ላይ የኦማር መስጊድ ያለበትን ቦታ ያሳያል።

 

 

ስለዚህ ሙስሊሞች ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ለረጅም ዘመን እውነት እንዳይሰበክ በማድረግ ስፍራውን ኦና አድርገውታል።

የአረብ ሕዝቦችም ለረጅም ዘመናት የአይሁድ ሕዝብ ላይ ስደት እና ጥቃት ሰንዝረዋል።

ነገር ግን ሙስሊሞች የቤተመቅደሱን ስፍራ ከመቆጣጠራቸው ብዙ ዓመታት በፊት ሮማውያን ቀድመው በስፍራው ተገኝተዋል።

ቤተመቅደሱን በእሳት ካቃጠሉ በኋላ በ70 ዓ.ም ድንጋዮቹን ፈነቃቅለወዋል። ከዚያ በኋላ ቤተመቅደሱ በፈረሰበት ስፍራ በ136 ዓ.ም ጁፒተር ለተባለው ጣኦታቸው ቤተመቅደስ ሰርተውለታል። ስለዚህ ሮምም የጥፋት እርኩሰት ናት ምክንያቱም ቤተመቅደሱ በነበረበት ስፍራ ላይ ጥፋት አድርሳለች።

የጥፋት አንዱ ትርጉም ወደየትም የማያደርስ መንገድ ማለት ነው። ወደ መንግስተ ሰማያት እየሄድኩ ነው ብላችሁ ስታስቡ ከቆያችሁ በኋላ በስተመጨረሻ ወደዚያ እየሄዳችሁ እንዳልነበረ ስታውቁ ከዚያ የበለጠ ጥፋት የለም። ስለዚህ በአረማውያን ስርዓቶች እና እምነቶች ላይ የተመሰረቱት የሮማ ካቶሊክ አስተምሕሮዎች (የባቢሎን ሚስጥሮች) ወደ ማርያም መጸለይን የመሳሰሉ ከንቱ ተስፋዎችን በመስጠት የተከታዮቻቸውን እምነት ጥፋት አድርገዋል። ካሊኮች ለብዙ መቶ ዓመታት በመታለላቸው የሞቱ ዘመዶቻቸውን ከፑርጋቶሪ ለማስወጣት ለቤተክርስቲያን ገንዘብ ሲከፍሉ ኖረዋል። በዚህ መንገድ የተሰበሰቡ ገንዘቦች በ1567 ዓ.ም ከመቋረጣቸው በፊት ሲስቲን ቻፕል እና የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያንን ሰርተዋል። ነገር ግን በ2000 ዓ.ም ፖፕ ጆን ፖውል ዳግማዊ ድሆችን ለመርዳት በርከት ያለ ገንዘብ ለሚከፍሉ ሰዎች የስርየት ክፍያ በድጋሚ ፈቅዷል።

መንፈሳዊ ጥፋት ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሃሳቦችን እንደ እውነት አድርጎ ለሕዝብ ማስተማር ነው።

“በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥”

ምንድነው መረዳት ያለብን?

እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱስ። እግዚአብሔር በቤተመቅደሱ ውስጥ በነበረ ጊዜ ቤተመቅደሱ የተቀደሰ ስፍራ ነበረ። የእግዚአብሔር መገኘት ኢየሩሳሌምን ቅድስት ከተማ ፓለስታይንን ቅዱስ ምድር አድርጎ ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ሲሞት እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ትቶ ሄደ፤ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የነበረው መጋረጃም ተቀደደ። ከዚያ በኋላ ሮማውያን ቤተመቅደሱን አፈረሱት። ስለዚህ ኢየሱስ ቃሉን እየነገራቸው በነበረ ሰዓት ቤተመቅደሱ ቅዱስ ስፍራ እንደነበረ መረዳት አለብን፤ ከዚያ በኋላ ግን ስለፈረሰ እግዚአብሔር በውስጡ መኖር ትቷል።

በጴንጤ ቆስጤ ዕለት እግዚአብሔር ወርዶ በሰዎች ልብ ውስጥ መኖር ጀምሯል። ስለዚህ አሁን እግዚአብሔር በልባቸው ውስጥ የሚኖርባቸው ሰዎች ቅዱስ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ ላት ትኩረት ማድረግ ትቶ አሁን ትኩረቱ የተቀደሱ ሰዎች ልብ ላይ ነው።

ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ኢየሱስ በሰማይ በአራት እንስሳት ተከብቦ እንደሚኖር ተገልጧል።

 

 

ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

በሰው ልብ ውስጥ ያሉት አራት ክፍሎች በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉትን አራት እንስሳት ይወክላሉ።

ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ ተመችቶት የሚኖረው ንሰሃ በገቡ ሰዎች ልብ ውስጥ ነው።

 

 

ነገር ግን ጥፋት የሚያመጣው እርኩሰት ምን እንደሆነ ለመረዳት ማወቅ ያለብን ተጨማሪ ነገር አለ።

ሮማውያን ኢየሩሳሌም ከማጥፋታቸው እና ቤተመቅደሱን ከማፍረሳቸው በፊት ቤተመቅደሱ በአይሁድ ቀነናውያን እና በአይሁድ ወንበዴዎች ተወርሶ ረክሶ ነበር፤ እነዚህ ሰዎች በሕጉ መሰረት ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ መግባት አልተፈቀደላቸውም። ተራው ሕዝብ ወደ ቤተመቅደሱ ውስጥ ለመግባት ይፈራሉ። ስለዚህ ቀነናውያን እየወጡ የአይሁድ ሕዝብን ዘርፈው ገድለው ሲመለሱ ቤተመቅደሱን እንደ መሸሸጊያቸው ተጠቀሙበት። ቀነናውያኑ ሊቀ ካሕናቱን ገደሉ። ሕዝቡ ከኢየሩሳሌም ፈጥነው መምለጥ ነበረባቸው፤ ምክንያቱም ቀነናውያን ከኢየሩሳሌም የሚያስወጡ መንገዶች ላይ ሁሉ ጥበቃ መድበው ለመውጣት የሚሞክሩ ሰዎችን ይገድሉ ነበር። ማንም ከከተማው እንዳይወጣ ቀነናውያን የከተማይቱን ደጆች ዘጉ። ሮማውያን የኢየሩሳሌምን ግንብ አጥር አፍርሰው ወደ ከተማይቱ ከመግባታቸው በፊት የአይሁድ ቀነናውያን እና ወንበዴዎች አስቀድመው ቤተመቅደሱን አረከሱት፤ በዚህም መንፈሳዊ ጥፋት አመጡበት፤ ሮማውያን ሲገቡ ግን ቤተመቅደሱ ላይ የግድግዳ ጥፋት ብቻ ነው ያደረሱበት። ስለዚህ የመጀመሪያውዎቹ የጥፋት እርኩሰት ቀነናውያን ናቸው ምክንያቱም ወደ ውስጡ እንዲገቡ ያልተፈቀደላቸው ቤተመቅደስ ውስጥ ገብተዋል። ከዚያ በኋላ ሮማውያንም በኢየሩሳሌም ከተማ ዙርያ አጥር ሲገነቡ እና ከተማይቱን ሲከብቡ የጥፋት እርኩሰት የመሆኑን ሚና እነርሱም ተጫውተውታል። ከዚያ በኋላ ሊያመልጥ የሞከረ አይሁዳዊ ሲያገኙ በመስቀል እየሰቀሉ ይገድሉ ነበር። ከዚያ በኋላ በስተመጨረሻ በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሱን አፈራረሱትና የባር ኮክባ አመጽ ሲያበቃ በ136 ዓ.ም ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ ጁፒተር ካፒቶሊነስ ለተባለው ጣኦታቸው ቤተመቅደስ ሰሩለት።

ከዚያ በኋላ ኢየሩሳሌም በ638 ዓ.ም በተቆጣጠሩ ጊዜ የጥፋት እርኩሰት የሆኑነት ሙስሊሞች ናቸው። ካሊፍ ኦማር ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ ላይ ትንሽዬ የጸሎት ቤት ሰራ፤ ቀጥለው ደግሞ በ691 – 692 ዓ.ም ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ነው ብለው በገመቱት ስፍራ ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለውን መስጊዳቸውን ሰሩበት።

ሶርያ ውስጥ በ2011 የተጀመረው የሙስሊሞች የእርስ በርስ ጦርነት በዚህ ፎቶ ውስጥ ማየት እንደምትችሉት እጅግ ብዙ ጥፋት አስከትሏል። እስካሁን ድረስ ሰላም እናመጣለን ብለው በራሳቸው ላይ ጥፋትን በማድረስ በትንቢት ውስጥ የተሰጣቸውን ድርሻ እየፈጸሙ ናቸው።

 

 

ማቴዎስ 24፡16 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥

17 በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥

18 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

19 በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።

20 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤

በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ለአይሁዶች ነበር የሚናገረው።

አይሁዶች መጀመሪያ ከአይሁድ ቀነናውያውን እና ከአይሁድ ወንበዴዎች ማምለጥ ያስፈልጋቸዋል፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ከሁሉ በላይ አደገኛ ከሆኑት ኢየሩሳሌምን በ70 ዓ.ም ከሚከብቧት የሮማውያን ሰራዊት ማምለጥ ያስፈልጋቸዋል።

አይሁዶች በሰንበት ማለትም በቅዳሜ መንገድ መሄድ አይፈቀድላቸውም። በክረምት ደግሞ ከባድ ብርድ አለ።

ስለዚህ ኢየሱስ በክረምት መሃል በታሕስስ 25 አካባቢ አይደለም የተወለደው፤ ምክንያቱም በዚያ በሚንቀጠቅጥ ብርድ እረኞች ከቤት ውጭ ሜዳ ላይ አይገኙም።

ያ ዘመን አስቸጋሪ ጊዜ ነበር። በ66 ዓ.ም በጀነራል ቬስፓሲያን መሪነት ሮማውያን በእሥራኤል ላይ ጥቃት ሰነዘሩ። ኢየሩሳሌምን መክበብ ሲጀምሩ በሰኔ ወር 68 ዓ.ም ንጉስ ኔሮ ሞተ። ቬስፓሲያን ከአዲሱ ንጉስ ከጋልባ ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ ውጊያውን አቋረጠ፤ አዲሱ ንጉስ ግን ስለ እሥራኤል እውቀት ስላልነበረው ቬስፓሲያን ላቀረበው ፈቃድ ትኩረት አልሰጠም። ጋልባ ከ7 ወራት በኋላ ተገደለ፤ ቀጣዩ ንጉስ ኦርቶ ደግሞ ከ3 ወራት በላይ አልቆየም። በዚህ ወቅት ሮማውያን እሥራኤል ውስጥ ምንም አላደረጉም።

በዚያው ጊዜ ቀነናውያን በቤተመቅደሱ ውስጥ ገብተው እየኖሩ የከተማውን ሕዝብ ይዘርፉና ይገድሉ ነበር፤ ደግሞም ከከተማው ማንም እንዲወጣ አይፈቅዱም ነበር። ሮማውያን ደግሞ ኢየሩሳሌምን ለማጥቃት ፈቃድ እስኪያገኙ ድረስ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል እየተጠባበቁ ነበር።

ኔሮ ከሞተ በኋላ ሶስት ነገስታት ቶሎ ቶሎ በጥቂት ወራት ውስጥ አለፉ። ከዚያ በኋላ የቬስፓሲያን ወታደሮች ቬስፓሲያንን ንጉስ አድርገው ሲሾሙት ቬስፓሲያን ዙፋኑ ላይ ለመቀመጥ ወደ ሮም ተመለሰና ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት እንዲሰነዝር ታይተስ የተባለውን ልጁን ሃላፊነት ሰጠው። ስለዚህ ሮማውያን በድጋሚ ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ከተማው ውስጥ ያሉ ሰዎች በብርቱ ከተማይቱን ለመከላከል ተዘጋጅተው ስለነበረ ሮማውያን ከተማይቱን ከብበው በማስራብ እጅ እንዲሰጡ ሊያስገድዱዋቸው ሞከሩ።

ብዙ ክርስቲያኖች በ68 ዓ.ም ሮማውያን ሲመጡ ባዩዋቸው ጊዜ ኢየሱስ የተናገራቸውን ቃል አስታውሰው በፍጥነት ከኢየሩሳሌም ሸሽተው ወጡ። ያኔ ሮማውያን ምንም አላደረጉም ምክንያቱም ኔሮ ሞቶ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ማንም እንዳያመልጥ ቀነናውያን የከተማይቱን በሮች ዘጉ። ስለዚህ ሰዎች ቶሎ ካላመለጡ ከተማይቱ ውስጥ ቀርተው መሞታቸው ነው። በ70 ዓ.ም ሮማውያን ተመልሰው መጡ። ቀነናውያን በከተማይቱ ቅጥር ውስጥ ተቀመጡ። ሮማውያን በከተማይቱ ዙርያ የጭቃ አጥር ከመስራታቸው በፊት የማምለጥ ዕድል ነበር ግን መሞከሩ በጣም አደገኛ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን የትኛውም አይሁዳዊ ማምለጥ አልቻለም፤ 1,100,000 አይሁዳውያን አለቁ።

የኢየሩሳሌም መጥፋት በታሪክ ውስጥ ከተመዘገቡ ዘግናኝ እልቂቶች አንዱ ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ በእስታሊንግራድ በተደረገው ፍልሚያ 1,200,000 ያህል ራሺያኖች ሞተዋል። ከኢየሩሳሌም እልቂት ወዲያ በአንድ ከተማ ይህን ያህል ብዙ ሕዝብ በአንድ ጊዜ የረገፈበት ሌላ ከተማ ይኖር እንደሆን አላውቅም። ስለዚህ አይሁዶች በከተማቸው ውስጥ በተደረገው የ70 ዓ.ም እልቂትና ሰቆቃ አምስተኛውን ማሕተም ጀምረውታል፤ ይህም የመጣባቸው መሲሁን አንቀበልም በማለታቸው ነው። ከዚያ ቀጥሎ 2,000 ያህል ዓመታት ካለፉ በኋላ በታላቁ መከራ ውስጥ አይሁዶች ወደ ወንጌሉ በመመለስ መሲሁን ይቀበሉታል።

ማቴዎስ 24፡21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።

ታላቁ መከራ አይሁዶች የሚመለሱበት እና ኢየሱስን የሚቀበሉበት ዘመን ነው። እርሱ አይሁዶችን ከታላቁ መከራ እንዲያመልጡ ሊመክራቸው አይችልም ምክንያቱም እነርሱ የታላቁን መከራ ሰቆቃ ካላዩ እና በተፈጥሮ ላይ ስልጣን ያላቸውን የሁለቱን ነብያት ኃይል ካላዩ በቀር አይሰሙም፤ ስለዚህ ሁለቱ ነብያት ናቸው አይሁዶችን ወደ ኢየሱስ የሚመልሷቸው።

ነገር ግን ይህ ታላቅ መከራ ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ የሰቆቃ ዘመን ነው የሚሆነው።

ስለዚህ ኢየሱስ አሁን ትኩረቱን የመለሰው በራዕይ 6፡7 ላይ ወዳለው አራተኛው ማሕተም ወደ ንስሩ ነው።

ይህ በአራተኛው ማሕተም ጊዜ የሚገለጠው 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው፤ እርሱም 4ኛውን ማሕተም ወደ ፍጻሜ ከሚያመጣው ከታላቁ መከራ በፊት ነው የሚሆነው።

ማቴዎስ 24፡22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።

ኢየሱስ ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ያሳጥረዋል። አለማመን፣ የሰዎች አመለካከት፣ የአረማውያን ልማዶች፣ እና የወንድም ብራንሐምን መልእክት ማጣመም እጅግ በስፋት ስለሚሰራጭ ወደ ታላቁ መከራ ከመግባት የሚድን ሰው አይኖርም።

ምክንያቱም ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የሚያምንና የሚታዘዝ አንድም ሰው አያገኝም።

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

 

ኢየሱስ ስለ ታላቁ መከራ ጠቅሶ ከተናገረ በኋላ ከታላቁ መከራ ለማምለት ምን ዓይነት ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልገን ይመክረናል።

አይሁዶች በ70 ዓ.ም ከሚፈጸመው ታላቅ እልቂት እንዴት እንደሚያመልጡ ነግሯቸዋል፤ የሚያመልጡት ከኢየሩሳሌም ከተማ ሮጠው በመውጣት ነው። ቀነናውያን እና ወንበዴዎች ቤተመቅደሱን እየዘረፉ ሳለ አንዳንድ አይሁዶች ወጥተው ሄዱ። ነገር ግን ቀነናውያን ይሸሹ የነበሩ ሰዎችን ወዲያው ተከትለው በመሄድ ይገልድሏቸዋል። ስለዚህ ሰዎቹ ሲሸሹ በፍጥነት መሸሽ አለባቸው፤ ይህም ለእርጉዝ ሴቶች ከባድ ነበረ።

አሁን ደግሞ ኢየሱስ ከበፊቱ የኢየሩሳሌም እልቂት ይበልጥ የከፋ የሚሆነውን የታላቁን መከራ እልቂት እንዴት እንደምናመልጥ ይነግረናል።

ነገሮች ሁሉ ይበልጥ እየከፉ ይሄዳሉ ስሕተትም በሥፍራ ሁሉ ስለሚሰራጭ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኝ ክርስቲያን መሆን ወደፊት በጣም ከባድ እየሆነ ይሄዳል።

በ2017 ዓ.ም በተደረገ ጥናት በዓለም ላይ 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች መኖራቸው ተረጋግጧል። መጽሐፍ ቅዱስም ከመቶ በሚበልጡ የተለያዩ ትርጉሞች ተተርጉሟል፤ እነዚህ ትርጉሞች ሁሉ በሃሳብ ይለያያሉ። ቤተክርስቲያኖች በሰው ማለትም በፓስተሮች ይተዳደራሉ፤ በዚህም ምክንያት በፓስተሮቻቸው መሃይምነት የተነሳ እውቀታቸው ውሱን ይሆናል።

ስለዚህ አንድ ሰው እውነትን ማግኘት የሚችለው እንዴት ነው? እውነትን ማግኘት በጣም ከባድ እየሆነ ነው።

አንድ ሰው የሚያገኛት እያንዳንዷ የእውነት ፍንጣቂ በቤተክርስቲያኖች ዘንድ ውግዘት እየወረደባት ነው።

የሜሴጅ አማኞች የሰሙትን ትምሕርት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደው አይፈትሹትም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመርመር ይልቅ የሰሙትን ንግግር በራሳቸው እንደፈለጉ ይጠመዝዙትና እውነት ነው ብለው የሙጥኝ ይዘውት ይኖራሉ።

ከዚያ በኋላ ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብለው እርሱን እንደ አምላክ ከፍ በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ የእርሱን ንግግር ጥቅሶች ይተካሉ።

እርሱ እውቀቱ ፍጹም ስለሆነ ሊሳሳት አይችልም ይላሉ።

ይህ ዓይነቱ አነጋገር የሮማ ካቶሊኮች ስለ ፖፑ የሚሉት ነው። እያንዳንዱ የሜሴጅ ቤተክርስቲያን ወይም ሌላ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን እውነትን የያዝን ብቸኛ ቤተክርስቲያን እኛ ነን፤ ከሌላ ቦታ ምንም ትምሕርት አያስፈልገንም ይላሉ። ሁሉም እነርሱ ብቻ እውነትን ሙሉ በሙሉ እንዳወቁ ስለሚያስቡ ከማንም እርዳታ አይቀበሉም።

እውነትን ማወቅ ብቻ ነው አንድን ሰው ከታላቁ መከራ ሊያድነው የሚችለው፤ ነገር ግን ለአዲስ አማኝ እውነትን ማግኘት በጣም ከባድ ይሆንበታል። ስለዚህ አሁንም የሰውን አመለካከት የማይፈልጉ፤ አንድ ፓስተርም ራስ እንዲሆንላቸው የማይፈልጉ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማመን የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች ሳሉ እግዚአብሔር ዘመናችንን ማሳጠር ይኖርበታል። ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች በአሁኑ ዘመን ብዙ አይደሉም።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ

ስለዚህ የትኛውም ፓስተር፣ ጳጳስ፣ ወይም ፖፕ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ማለት አይችልም።

ማቴዎስ 24፡23 በዚያን ጊዜ ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም፦ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

ሰዎች ክርስቶስ መጥቷል ይላሉ። እንደዚህ ሲሉዋችሁ አትመኑ። ክርስቶስን ለማግኘት የሆነ ቦታ መሄድ የለባችሁም።

ሰዎች የትም ቢሆኑ ኢየሱስ በልባቸው ውስጥ ለመኖር ፈቃደኛ ነው።

እምነት ካላችሁ ኢየሱስ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ እንደመጣው ሁሉ ወደናንተም ይመጣል፤ ደቀመዛሙርቱን ወዳሉበት ሄዶ እንዳገኛቸው እናንተም ባላችሁበት እርሱ ወደናንተ ይመጣል።

24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።

ሐሰተኛ ክርስቶሶች። በዘመን መጨረሻ ሐሰተኛ የተቀቡ ሰዎች። በሰዎቹ ላይ ያለው ቅባት እውነተኛ ነው፤ ነገር ግን በውስጣቸው ያለው ዘር የእግዚአብሔር ቃል አይደለም።

መንፈሳዊ ስጦታዎች እና ጥሪዎች ጸጸት የለባቸውም።

ይሁዳ፣ በለዓም፣ ኢያኔስ እና ኢያንበሬስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ተዓምራት ማድረግ እና ትንቢት መናገር የሚችሉ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ሁላቸውም ክፉ ሰዎች ነበሩ።

ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

ተዓምራት ማድረግ መቻል አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በመልካም ሕብረት ውስጥ መሆኑን አያመለክትም።

ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ሕብረት ውስጥ የምትሆኑነት የእግዚአብሔር ቃል ዘር በነፍሳችሁ ውስጥ ከተተከለ ብቻ ነው።

ነፍሳችሁ እንደ አትክልት ስፍራ ነው፤ ውሃ ሊያጠጣው የሚችለውም መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።

በነፍሳችሁ ውስጥ የተዘራው ማንኛውም ዓይነት ዘር የመንፈስ ቅዱስ ውሃ በፈሰሰበት ጊዜ ይበቅላል።

ስለዚህ በነፍሳችሁ ውስጥ የምታምኑት እና ውሃ የምታጠጡት ዘር የእግዚአብሔር ቃል ብቻ መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ።

ሮሜ 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።

ስለዚህ አንድ ሰው በፍጹም የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ በመታዘዝ የማይጸና ከሆነ ተዓምራት ማድረግ ምንም ትርጉም የለውም።

የምትሰሙትን ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መርምሩ፤ አለበለዚያ ትታለላላችሁ።

እያንዳንዱን እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈትሹ፤ በአንድ ወይም በሁለት ጥቅስ ላይ ብቻ እምነታችሁን አትመስርቱ፤ ወይም ደግሞ ከሰው ንግግር በተወሰደ ጥቅስ ላይ አትመስርቱ።

25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።

ብዙዎች የሚስቱባቸው ቁልፍ ስሕተቶች ምን እንደሆኑ አስቀድሞ ተነግሮናል።

ስለዚህ ብንታለል እራሳችንን እንጂ ማንንም መውቀስ አንችልም።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23