ማቴዎስ ምዕራፍ 24 የሚተረጎመው በራዕይ ምዕራፍ 6 መሰረት ነው - ክፍል 2
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የደመናው መታየት መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችላችሁ የመጀመሪያው እርምጃ እንደተጀመረ የሚያሳይ ምልክት ነው።
First published on the 10th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ማቴዎስ 24፡3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
ልብ በሉ። ደቀመዛሙርቱ ለጥያቄያቸው መልስ ፍለጋ ወደ ቃሉ መጡ። እኛም ለጥያቄያችን መልስ ለማግኘት ወደ ቃሉ መምጣት አለብን።
ይህ ጥቅስ በጣም ወሳኝ ነው።
ሶስት ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ጥያቄ 1. ይህ መች ነው የሚሆነው? በሌላ አነጋገር ቤተመቅደሱ መች ነው የሚፈርሰው?
ጥያቄ 2. የመምጣትህ ምልክቱ ምንድነው?
“ምልክቱ”። አንድ የታወቀ ምልክት።
ይህ ጉዳይ ወደ ወደ አራተኛው ማሕተም ይወስደናል። ይህም የንስሩ ዘመን ሲሆን በንስሩ ዘመን ውስጥ እውነት ለክርስቶስ ሙሽራ ይገለጥላትና ከታላቁ መከራ ያመልጣሉ፤ አለዚያም ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እውነትን አንቀበልም ብለው ልማዶቻቸውንና መሪዎቻቸውን በመከተል ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ። ይህ ጊዜ ልክ ሞት ታላቁን መከራ ለማስጀመር በፈረሱ እየጋለበ ከመግባቱ በፊት ነው። ሁላችንም አሁን በዝግጅት ላይ ነን፤ የምንዘጋጀውም ለበጉ ሰርግ አለዚያም ለአውሬው መምጣት። ወይ በሰማይ የሰርጉን እራት እንበላለን፤ ወይ ደግሞ የአርማጌዶን ጦርነት ላይ አሞራዎች ይበሉናል።
ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ መች እንደሚመጣ አልጠየቁም። የሚመጣበት ቀን ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ገብቷቸዋል።
ማንኛውም ክርስቲያን ጌታ መች እንደሚመጣ አውቃለው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ወይም ጌታ መች ነው ብሎ የሚጠይቅ ከሆነ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አይስማማም ማለት ነው። ስለዚህ ይህን ጥያቄ መጠየቅ ክልክል ነው፤ የሚጠይቅ ሰውም ስሕተት ውስጥ ገብቶ ከመስመር ወጥቷል። ከዚህም የባሰ ስሕተት ውስጥ የገባ ደግሞ ጌታ መጥቷል የሚል ሰው ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሰው ፈጽሞ ተሳስቷል።
ስለዚህ መንፈሳዊ መሆን ከፈለግን መጠየቅ የሚገባን የመምጣቱን ምልክት ብቻ ነው። ደቀመዛሙርቱም የጠየቁት ይህንኑ ነው።
ይህ ምልክት በጣም ወሳኝ ምልክት ነገር ግን ከመሆኑ በፊት ማንም ያልጠበቀው ምልክት ነው።
በዚህ ጥያቄ ውስጥ ያለው ሌላ ችግር ደግሞ የምልክት ጥያቄ መሆኑ ነው፤ ምልክት መጠየቅ የለብንም።
ማቴዎስ 16፡4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ።
ኢየሱስ ከሞት ተነስቷል። የትኛውም የሌላ ሐይማኖት መሪ ከሙታን አልነተሳም። ስለዚህ በየሳምንቱ እሁድ እግዚአብሔርን ለማምለክ እና ለማገልገል ስንሰበሰብ የምናስታውሰው ምልክት ትንሳኤውን ነው።
ኢየሱስ ስለ መምጣቱ ምልክት ሲጠይቁት ምን ብሎ መለሰ?
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
የጌታ ምጻት የመጀመሪያው ደረጃ መፈጸሙን ለማሳየት “ምልክቱ” መከሰት አለበት።
የኢየሱስ ምጻት በሶት ደረጃዎች ነው የሚፈጸመው።
ታላቅ ድምጽ። ይህ ድምጽ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የሚገልጥ እና ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንድትችል የሚያዘጋጃት መልእክት ነው።
ድምጽ። የመላእክት አለቃ ወይም በራዕይ ምዕራፍ 10 የተገለጸው ብርቱ መልአክ ሙታንን ለማስነሳት ይወርዳል።
መለከት። ኢየሱስ ሙሽራይቱን ነጥቆ ወደ ሰማይ ለመውሰድ በሚታይ አካል ተመልሶ ይመጣል።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ ወንድም ብራናሐም ታላቁ ድምጽ ወደፊት እንደሚሆን ሲጠባበቅ ነበር፤ ይህም ድምጽ ሙሽራይቱ እንድትዘጋጅ የሚያደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትና የመላእክት አለቃ ሙታንን የሚያስነሳበት ድምጽ ነው።
65-1127 ሰሜቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
በሕይወቱ መጨረሻ ላይ ወንድም ብራንሐም የመልአኩን መምጣት የሚያበስረውን “ታላቅ ድምጽ” ወደፊት እንደሚመጣ ይጠባበቅ ነበር።
“ታላቁ ድምጽ” ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመገለጥ መቀበሉ አይደለም። ሚስጥራቱን የተቀበለው ከ1947 እና 1965 መካከል ነው። ታላቁ ድምጽ ሙሽራይቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለራሷ ስትረዳ ነው።
የጌታ ምጻት የመጀመሪያ ደረጃ ምስጢራቱ የተገለጠ የእግዚአብሔር ቃል ሆነው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲወርዱ ነው የተፈጸመው።
ከክርስቶስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የምንተዋወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተከፍቶ መረዳት በቻልን ጊዜ እርሱ በቃሉ ውስጥ ሲገለጥልን ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶን መጠቀም አለብን። በወንድም ብራንሐም ንግግሮች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ መፍቻ ቁልፎችን እናገኛለን።
ሁለተኛው ደረጃ። ሚስጥራቱ ለሙሽራይቱ ከተገለጡላት በኋላ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር ይወርድና ሙታንን ያስነሳል። አሁን በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት የመጀመሪያውን ቤተክርስቲያን ዘመን ሙሽራ በትክክል እስኪመስሉ ድረስ ተለውጠዋልን?
ሶስተኛው ደረጃ። አካላችን ስጋችን ይለወጣል፤ መለከቱ ሲነፋ ሙሽራይቱ በሚታይ አካል የተገለጠውን ጌታ በአየር ላይ እድትቀበለው ጥሪ ያደርግላታል።
63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት
ምስጢራቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይወርዳሉ ከዚያም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነውን ሙሉ መገለጥ ይገልጣሉ።
… ማሕተሞቹ ሲፈቱ እን ሚስጥሩም ሲገለጥ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይወርዳል እርሱም መልእክተኛው ክርስቶስ እራሱ ነው፤ በራሱ ዙርያ ቀስተደመና ይሆናል፤ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር አድርጎ ይቆማል።
… አሁን ደግሞ በአስረኛው ምዕራፍ ተመልሶ ይመጣል የዚያን ጊዜ ሚስጥሩ ሁሉ ይፈጸማል ማሕተሞቹም ይፈታሉ፤ ከዚያ በኋላም ጊዜ እንደማይኖር ያውጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ሚስጥራቱ በሙሉ ይፈጸማሉ፤ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይገለጣል።”
ይህ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም የተገለጠው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ፎቶግራፍ ከተነሳ ከ17 ቀናት በኋላ ነው። መልአኩ ደግሞ እስከ አሁንም ስላልመጣ ገና ወደፊት ነው የሚመጣው። ስለዚህ ደመናው የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አልነበረም።
ሕያው የሆነችዋ ሙሽራ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ከተረዳች በኋላ በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ እንደተሰጠው የተስፋ ቃል የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ትንሳኤ ይፈጸማል።
64-0119 ሻሎም
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል የእውነት እንወደው እንደሆን ለማየት ክርስቶስ መጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ሆኖ ይወርዳል። ከኢየሱስ አስተሳሰብ ጋር የምንተዋወቀው በዚህ ነው። የእርሱ አስተሳሰብ ይመስጠናልን? የተገለጠውን የክርስቶስ ቃል ከሰዎች አመለካከት በላይ ከፍ አድርገን እንቀበላለን?
የሚስጥራቱ መገለጥ የእውነት ሊጀምር መሆኑን የሚያሳይ ትክክለኛ ምልክት (የሚታወቅ ምልክት) ያስፈልጋል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
የማሕተሞቹን መጽሐፍ ይወስደውና ማሕተሞቹን ፈቶ ሰባተኛውን መልአክ ይገልጠዋል፤ የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት ይህ ብቻ ማለትም የእግዚአብሔርን ሚስጥራት መቋጨት ነውና።
በወንድም ብራንሐም አገልግሎት ውስጥ ይገለጥ የነበረው ታላቅ መለኮታዊ ኃይል ዓላማው የሰዎችን ትኩረት መሳብ ነበረ።
የአገልግሎቱ ዋነኛ ዓላማ ግን የተቀሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለመፍታት ቁልፍ የሆኑትን ሰባቱን ማሕተሞች ለመግለጥ ነው።
የጌታ ምጻት ሊፈጸም የሚጀምረው ጌታ በሚስጥራቱ መፈታት አማካኝነት በቃሉ ሲገለጥ ነው።
1965-0718
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል።
ከዚያም በኋላ በሰማይ የሰው ልጅ ምልክት ይታያል።”
“በዚያ ቀን” በሉቃስ ወንጌል ውስጥ እንደተጻፈው “የሰው ልጅ እራሱን እንደገና ይገልጣል፤ እራሱ ይገለጣል።” በዚያ ጊዜ ዓለም ደግሞ ሰዶም እና ገሞራን ትመስላለች።
ክርስቶስ አሁን አማኞች ሲሰሙ መረዳት በሚችሉት ቃል ውስጥ ይገለጣል።
ማቴዎስ 24፡30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
ሰማያትን ከባቢ አየር እንላለን። ከባቢ አየር ግን ደመናዎቹ ያሉበት ቦታ ነው።
ስለዚህ አንድ ነገር በከባቢ አየር ውስጥ እጅግ በጣም ከፍ ብሎ ደመናዎች ሊፈጠሩ ከሚችሉበት ከፍታ በላይ አልፎ ታይቶ ፎቶግራፍ ተነሳ።
ደማነዎች ከ12 ማይልስ ከፍታ በላይ ሊፈጠሩ አይችሉም ምክንያቱም 99 በመቶ የሚሆነው ደመናዎች የሚፈጠሩበት የውሃ ትነት ከ12 ማይል ከፍታ በታች ነው የሚገኘው።
ሳይንስ ምንነቱን ሊገልጸው የማይችለው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሊፈጠር የሚችለው የከባቢ አየር ፊዚክስ ሕጎች ሲሻሩ ነው።
በሰሜን አሪዞና ከፍላግስታፍ ከተማ አጠገብ ልክ ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ሁለት ደመናዎች ለ28 ደቂቃ በ26 እስከ 30 ማይልስ ከፍታ ላይ ታይተው ነበር። የታዩትም ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነበር። ታናሹ ደመና ከታላቁ ደመና ኋላ በ20 ማይልስ ርቆ ነበር የታየው።
አንዱ ደመና በዚያኑ ዕለት ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው ከቫንደንበርግ አየር ኃይል የተወነጨፈ ሮኬት ተበላሽቶ ሲፈነዳ በታላቅ ከፍታ ላይ ፍንዳታው የፈጠረው ስብርባሪና ጭስ ነው።
ነገር ግን ከታክሰን የጠፈር ምርምር ጣቢያ ፎቶግራፍ የተነሳውን ትልቅ ደመና በተመለከተ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ማብራሪያ አልተገኘም።
ይህ ደመና የተፈጠረው በሰባት መላእክት ክንፍ ነበር።
ያን ዕለት መላእክቱ ያደረጉት ነገር እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች ለመግለጥ ሊጀምር መሆኑን ምልክት መስጠት ነበር።
በመጀመሪያው ትክክለኛ ፎቶግራፍ ውስጥ አንዳችም የሰው ፊት የሚመስል ነገር አለመኖሩን አስተውሉ።
ደግሞም ደመናት ታይቶ በቆየበት 28 ደቂቃ ውስጥም ሙሉ በሙሉ ጸጥታ ነበረ። ሰባቱ መላእክት ማንንም አላናገሩም። ወንድም ብራንሐም ደግሞ ደመናው ከተገለጠበት ቦታ 200 ማይልስ ርቀት ላይ ስለነበረ ስለ ደመናው አንዳችም አላወቀም።
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
ሁለቱ በ20 ማይልስ ተራርቀው የነበሩት ደመናዎች ከዊንስሎው ይታዩ ነበር ምክንያቱም ደመናዎቹ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሜሄዱበት መስመር በዊንስለው በኩል ያልፍ ነበር።
ከስምንት ቀናት በኋላ እነዚያው ሰባት መላእክት እራሳቸው ሳንሴት ፒክ አጠገብ ማርች 8 ቀን 1963 ወንድም ብራንሐምን ጎበኙት፤ ሥፍራውም ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይልስ ያህል ይርቃል።
መላእክቱ ሰማይ ላይ ደመናውን በሰሩበት ቀን እና ከወንድም ብራንሐም ጋር በበረሃማው ውስጥ ሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ በተገናኙበት ቀን መካክል የስምነት ቀናት እና የ200 ማይልስ ልዩነት አለ።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ደመናውን በራሳቸው የተጣመመ ትርጉም ሰጥተውት የጌታ ምጻት ነው ወይም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነው ብለው ተረጎሙት።
ሁለት ደመናዎች መታየታቸውን ሆን ብለው እንዳላወቁ አስመሰሉ።
መላእክቱ ወንድም ብራንሐምጋ በመጡ ዕለት ምንም ደመና አለመስራታቸውን ከሚያስፈልግ በላይ ትኩረት ሰጥተው ይከራከራሉ። ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው የተወሰኑ ወራት ካለፉ በኋላ መስማቱን እንዳላወቁ ያስመስላሉ። ለመከመሪያ ጊዜ ስለ ደመናዎቹ የተናገረው በሰኔ ወር 1963 ዓ.ም ነበር።
ሰባቱ መላእክት ፍላግስታፍ ከተማ ላይ ደመና በሰሩበት እና 7ቱ መላእክት ሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ ከወንድም ብራንሐም ጋር ውይይት ያደረጉበት ቀን መካከል ያሉትን 8 ቀናት አድበስብሰው ማለፍ ይፈልጋሉ።
ደግሞም ይህ ክስተት የተፈጸመው ታክሰን አሪዞና አጠገብ ያለው ሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ ሊሆን ይችላል ይላሉ ግን ውሸት ነው። ሳንሴት ፒክ የሚገኘው ታላቁ የሶኖራ በረሃ ውስጥ ነው።
ክርስቶስ በረሃ ውስጥ አይመጣም።
ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ ርቀት ከፍላግስታፍ በስተሰሜን የታየው የ1963ቱ ደመና እግዚአብሔር በወንድም ብራንሐም አማካኝነት ሰባቱን ማሕተሞች እንደሚገልጥ የሚያሳይ ምልክት ነበረ።
በፍላግስታፍ ከተማ ፌበሩዋሪ 28 ቀን 1963 ደመናውን የሰሩት 7ቱ መላእክት ክርስቶስን በቃሉ ውስጥ ለመግለጥ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ወደ ምድር ሊወርዱ ጊዜው መድረሱን ለማመልከት ለግማሽ ሰዓት ያህል ድምጽ የሌለው ምልክት ሲያሳዩ ነበር (ይህም የጌታን ምጻት ለሚያመለክተው ሰባተኛ ማሕተም ምልክት ነበረ)።
ከዚያ በኋላ እነዚሁ 7 መላእክት ከስምንት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ወርደው በሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ አነጋገሩት። በዚያም ወደ ጄፈርሰንቪል እንዲመለስ እና በዚያ ከተማ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ይዘውለት እንደሚወርዱ ነገሩት።
7ቱ መላእክት ይህን ያደረጉት ከማርች 17 እስከ ማርች 24 ድረስ በነበሩት ስምነት ቀናት ውስጥ ወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች በገለጠበት ወቅት ነው። እነዚህ ስብከቶች በመጽሐፍ ታትመው መጽሐፉ ዝነኛ ሆኗል።
ከዚያም የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቱ በተከፈተ ጊዜ የቀሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥረት በቀላሉ ማስተዋል ቻለ።
64-0719 የኢዮቤልዩ በዓል
ከዚያ በኋላ ወዲያው የእግዚአብሔር መላእክት ተገልጠው ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ነግረውኝ ወደ ጄፈርሰንቪል እንድመለስና ስለ ሰባቱ ማሕተሞች እንድሰብክ ትዕዛዘረ ሰጡኝ። በዚያም ከእግዚአብሔር መንፈስ የመጣ ሃሳብ ተናግሬ እንደሆን በንግግሬ ውስጥ ነው የሚገኘው። በዚያ የእግዚአብሔርን መልአክ በተገናኘንበት ሥፍራ መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ ሆነ። የዚያን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ተገለጠልንና የተሃድሶ መሪዎች ያልተረዱትን አዲስ እውነት በመገለጥ መረዳት ቻልን። እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ መገለጥ ነው፤ ለእኛ ሙሉ በሙሉ አዲስ ነው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ መገለጥ ነው። እርሱም ሁሌ የነበረው ቃል ነው። እኔም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላሁ፤ በመንፈስ ቅዱስ ተመራሁ።
የሜሴጅ አማኞች የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ከራሳቸው ከማሕተሞቹ መፈታት ጋር ባምታቱ ጊዜ ብዙ ነገር አደበላለቁ፤ ማሕተሞቹ የሚፈቱት እና በማሕተሞቹ ውስጥ የተገለጠው በሙሉ በዝርዝር የሚፈጸመው ግን ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመፍታት የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ በጣም ያስፈልግ ነበር።
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን በሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ሰው አስተዋወቀ።
ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመግለጥ ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መካከል እንደሚመላለስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ቃል አድርጎ አሳየን።
በእኛ ዘመን ኢየሱስ ስጋ እንደለበሰ ሰው ሆኖ አይደለም የሚገለጠው።
የሚገለጠው ሃሳቡን እና ሥራውን የሚያሳየውን የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል መረዳት በመቻላችን አማካኝነት ነው።
ሰዎች ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ይረሳሉ። ስለዚህ የተገለውን መጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ካልቻልን በቀር እውነተኛውን ኢየሱስ ማወቅ አንችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ሃሳብና ስራ ይነግረናል፤ ስለዚህ ለምጻቱ ዝግጁ መሆን እንድንችል የሚያስፈልገንን ያሳውቀናል።
ስለዚህ መጀመሪያ ሚስጥራቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ መውረድ አለባቸው።
ሰባቱ መላእክት የማሕተሞቹን መገለጥ ከማርች 17 እስከ ማርች 24 ድረስ ይዘው መጡ፤ እነዚህም መገለጦች የተቀሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለመረዳት እንደ ቁልፍ ያገለግላሉ።
63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት
… ሰባተኛው መልአክ ሚስጥሩን ማሰማት ሲጀምር እነዚህ ሰዎች ሁሉ ነካክተው የተዉትን ነገር ይቋጨዋል፤ ሚስጥራቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ይወርዳሉ፤ የእግዚአብሔርን መገለጥ በሙሉ ይገልጣሉ።
የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ የሚወርደው ሚስጥራቱ በሙሉ ከወረዱና ከተገለጡ በኋላ ነው።
ክርስቶስ መጀመሪያ የተገለጠውን ቃል ሆኖ ይወርዳል፤ ይህም ቃል በሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ አማካኝነት መውረድ ጀምሯል።
ክርስቶስ እኛ መረዳት በቻልነው ቃል አማካኝነት ነው የሚገለጥልን።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ የሚገልጠውን ማመን ትችላላችሁ?
ከዚያም በኋላ የራዕይ ምእራፍ 10 ብርቱ መልአክ ሙታንን ለማስነሳት ይወርዳል።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
… ሰባተኛው መልአክ ድምሱን በሚያሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥራት በሙሉ በድምጹ አማካኝነት ይፈጸማሉ ይጠናቀቃሉ። ከተፈጸመ በኋላ ደግሞ ብርቱው መልአክ ወደ ምድር ይወርዳል እርሱም ክርስቶስ ነው።
ብርቱው መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ሊመጣ የሚችለው ወንድም ብራንሐም ሚስጥራቱን ከገለጠ በኋላ ብቻ ነው።
ወንድም ብራንሐም ዲሴምበር 1965 ዓ.ም ውስጥ ሚስጥራቱን ገልጦ ጨረሰ። በዚያው ወር ሞተ።
ሚስጥራቱን ሁሉ ገልጦ ለመጨረስ ሰባተኛው መልእክተኛ መጀመሪያ 7ቱን ማሕተሞች መግለጥ አለበት። ይህም ክርስቶስን በቃሉ ውስጥ መግለጥ ነው።
ከዚያ በኋላ መልአኩ ይወርድና ሙሽራዋ የማይሞተውን አካሏን በምትለብስበት ሰዓት ዘመን እንዲያበቃ ያደርጋል።
ነገር ግን 7ቱን ማሕተሞች ከማሳየቱ በፊት እግዚአብሔር በሰማይ ላይ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና አሳየ፤ እርሱም በቃሉ ውስጥ ሊገለጥ ላለው የሰው ልጅ ምልክት ነበረ።
64-0112 ሻሎም
በሰባተኛው ሰዓት ግን እነዚህ ሚስጥራት ቡሉ ይጠናቀቁ ዘንድ ሰባተኛው መልእክተኛ ይመጣል። አያችሁ? ሰባተኛው የምድር መልአክ፤ ይህ እንደሚመጣ የተነገረለት መልእክተኛ በምድር ላይ ነበር። መልአክ ማለት “መልእክተኛ” ነው።
ከዚያም በኋላ ቀጥሎ ሌላ መልአክ ሲወርድ አየ፤ ይህ ግን እዚህ መልእከት የተሰጠው ምድራዊው መልአክ አይደለም፤ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ወረደ፤ በራሱም ላይ ቀስተደመና ነበረው፤ እርሱም እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ አድርጎ ለዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው ማለ እንዲህ ሲል፡- “ከእንግዲህ በኋላ ዘመን አይኖርም።” አያችሁ?
ነገር ግን እነዚያን ሰባት ማሕተሞች ከመፍታቱ በፊት በመጀመሪያ በሰማያት ውስጥ ነው የገለጣቸው።
በዚያን ቀን አሜሪካ እና ሜክሲኮ ውስጥ ፎቶግራፍ አነሱዋቸው። ፎቶግራፉ እስካሁን ድረስ ላይፍ መጽሔት ውስጥ አለ፤ እነርሱም ምን ማለት እንደሆነ አላወቁም።
ነገር ግን በምድር ላይ ከመፈጸሙ በፊት በሰማያት ያውጀዋል። እርሱ ሁልጊዜ እንደዚህ ነው አደራረጉ። በመጀመሪያ ምልክቶቹን በሰማያት ላይ ያሳያል።
64-0719 የኢዮቤልዩ በዓል
ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም፤ ይህን ታውቃላችሁ። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።
64-0816 ቃሉን ማረጋገጥ
ሰባተኛው መልአክ የተላከው የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር እንዲገልጥ ነው። ሁሉም ሚስጥር በሰው ልጅ ውስጥ ነው የሚጠቀለለው፤ የአካሉን ሙላት ለመግለጥ የእርሱ የጊዜ ሙላት ወደ ቃሉ ሙላት መጥቷል። ያም ቃሉ ነው፤ እርሱም በአፍ የተነገረው ቃል ሲሆን የተጻፈውን ቃል ይገልጠዋል።
ሰባተኛው ማሕተም የኢየሱስን ዳግም ምጻት ያመለክታል። በዚህም ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አናውቅም፤ ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም።
ክርስቶስ በቃሉ መገለጥ መልክ መጥቷል፤ ይህንንም ያደረገው መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና አንብባችሁም መረዳት እንድትችሉ ነው።
65-0718 የጊዜው መንፈሳዊ ምግብ
አሁን ይህንን የመጨረሻው ነብይ ከተናገረው ጋር አስተያዩ፡- “እነሆ ነብዩ ኤልያስን እልክላችኋለው፤ እርሱም የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።” አያችሁ? ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመልሳቸው መልእክት፤ በዚያም ቀን የሰው ልጅ እራሱን ይገልጣል። በዚያም የመጨረሻው ቤተክርስቲያን ዘመን በሚታወጅበት ቀን በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ሚስጥራት መገለጥ አለባቸው። ሰባቱ ማሕተሞች ይፈታሉ። የእነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያኖች ሚስጥራት እና ብዙ ነገሮች፤ ምን እንደተደረገ እና እንዴት እንደተደረገ ሁሉ ይገለጣል።
ነገር ግን የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ገና አልወረደም።
ይህ መልአክ በወረደ ጊዜ በትንሳኤ ሙታንን ሁሉ ያስነሳቸዋል።
ከዚያም በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሙሽራይቱ አዲሱን የማይሞት አካሏን እንድትቀበል ይመራታል።
ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሙሽራይቱ መነጠቅ የምትችልበትን እምነት የምትቀበለው። በዚህ አሁን በምንኖርበት አካል ውስጥ ሆነን ልንነጠቅ አንችልም።
የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ጌታ ኢየሱስ ወደ አየር ላይ ሊነጥቀን የሚመጣው።
ሰዎች ኢየሱስ የ1963ቱን ደመና ሆኖ መጥቷል ይላሉ፤ በዚህም ምክንያት የምሕረት ዘምን አብቅቷል፤ ስለዚህ የጌታ እራት መውሰድ የለብንም ብለው ይናገራሉ።
ልክ ቫይረስ መልኩን እየቀያየረ እንደሚኖር ሁሉ ስሕተት መልኩን በመለዋወት መጽሐፍ ቅዱስንም ይለውጠዋል።
ማቴዎስ ምዕራፍ 24 ውስጥ ኢየሱስ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለቂያ አካባቢ ከታላቁ መከራ ከሚያድነን ዳግም ምጻት በፊት ሰዎች ባሕርያቸው ምን እንደሚመስል ገልጧል።
ነገር ግን ከዚያም በላይ በዘመን መጨረሻ የሚታዩ ሁኔታዎችን ሲገልጽ ብዙውን ጊዜ የተጠቀመው ከታላቁ መከራ መምለጥ እንችል ዘንደ አስተሳሰባችን እና ባሕሪያችን ምን መምሰል እንዳለበት ለማስረዳት ነው።
ደመናው ፎቶግራፍ በተነሳበት ጊዜ ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው ምንም እንደማያውቅ አትርሱ።
ደመናው በፍላግስታፍ ከተማ በታየበት ሰዓት ወንድም ብራንሐም ከፍላግስታፍ 200 ማይልስ በስተደቡብ ርቆ የሚገኝ ታክሰን የተባለ ከተማ ውስጥ ነበረ።
እርሱ ራሱ ቀኖቹ እንዴት እንደተምታቱበት ተመልከቱ።
63-0601 ኑ ተከተሉኝ
እኔም ስመለከት እነዚያ መላእክት በዚያ ነበሩ፤ በግልጽ ይታያሉ፤ በዚያ ስዕል ውስጥ እንደሆኑ ይመስል ቁልጭ ብለው ይታያሉ። አያችሁ? ምን እንደሆን ለማየት ተመለከትኩኝ፤ ይህም የሆነው እኔ እዚያ ከነበርኩት ሁለት ቀናት በፊት ወይም ሁለት ቀናት በኋላ ነበር። የት እንደነበረ ተመለከትኩ። “ከፍላግስታፍ በስተ ሰሜን ምስራቅ ወይም ከፍላግስታፍ በታች ባለው በፕሬስኮት”። ያው እዚያ እኛ የነበርንበት ከተማ ነው፤ ብቻ እናንተም እዩ።
የዊልያም ብራንሐም ልክ ቤኪ “Return to Sunset” በሚል ርዕስ በጻፈችው መጣጥፍ እንዳለችው ብራንሐም ሳንሴት ፒክ ከተማ የደረሰው ማርች 6 ቀን 1963 ነው። መጀመሪያው ስለ “ፍጹምነት” ማርች 4 ቀን 1963 ዓ.ም ሰብኮ ነበር፤ ይህም ቦታ ከታክሰን በ1,000 ማይልስ ያህል ርቆ በሚገኘው በሂውስተን ቴክሳስ ነበር።
ደመናው የታየው ፌብሩዋሪ 28 ቀን ነው። ያም ቀን ከማርች 6 ሁለት በፊት አልነበረም፤ ደግሞም ሁለት ቀን በኋላም አልነበረም።
63-0324 ሰባተኛው ማሕተም
(ከ16 ቀናት በኋላ። መላእክቱ ከጎበኙት ከሁለት ሳምንታት በኋላ)
ልብ በሉ፤ ደግሞ ሶስት ምስክሮች እዚሁ ተቀምጠዋል፤ ከአንድ ሳምንት በፊት (አንድ ሳምንት ከጥቂት ቀናት በፊት) ወደ ሜክሲኮ ድንበር አካባቢ ከሁለት ወንድሞች ጋር ነበርን በዚያም ከሱሪዬ እግር ላይ የተጣበቁ ጨጎጊቶችን እየለቀምኩ ነበር፤ ከዚያም ተራሮቹን ሲደመስሳቸው ትንሽ ብቻ እስኪቀረው ድረስ ታላቅ ነፋስ ይነፍ ጀመር።
ይህ ስብከት የቀረበው ማርች 24 ቀን ነበር። አንድ ሳምንት ከጥቂት ቀናት ከተባለ ወደ 10 ቀናት ያህል ይሆናል። የጫካ አሳማ የሚታደንበት ወቅት ግን ከማርች 1 እስከ ማርች 10 ቀን ድረስ ነው። ስለዚህ ማርች 8 ቀን የተገለጡለት መላእክት ከ16 ቀናት በፊት ማለትም ከአንድ ሳምንት በላይ ነው የተገለጡለት።
ስለዚህ እባካችሁ እውነታውን በተጨባጭ ማስረጃ ሳታረጋግጡ ሰው የተናገረውን ቃል አትጥቀሱ።
ወንድም ብራንሐም ደመናውን ጭራሽም አላየም ነበር፤ ስለዚህ ስለ ደመናው ሶስት የተለያዩ ግምቶች ነበሩት።
ደመናው ሳንሴት ፒክ አካባቢ የተፈጠረና እርሱ ደግሞ ከደመናው በታች ቆሞ እንደነበረ ገመተ።
ይህም ጥሩ ግምት አይደለም፤ ምክንያቱም ፌብሩዋሪ 28 ቀን የአደን ወቅት ከመጀመሩ በፊት ነበረ።
መላእክቱ ሲወርዱ ደመናውን የሰሩ መሰለው።
ሌላ ጊዜ ደግሞ መላእክቱ ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ ደመናውን የሰሩ መሰለው።
አሁንም በሌላ ጊዜ የገመተው ግምት ደግሞ ደመናውን የሰሩት መላእክት ከምድር 30 ማይል ከፍታ ለይ ተንሳፍፈው የቆዩ መሰለው።
ሶስት የተለያዩ ግምቶች። ያለ ምንም ጥርጥራ ያላየውን ነገር በተመለከተ ግምቱን እየተናገረ ነበር።
63-0628 ጌታ ሆይ አንድ ጊዜ ብቻ
አሁን ሳይንስ ፎቶ አንስቶታል፤ ፎቶውን በአሶሼትድ ፕሬስ ዜና ላይ አይታችሁታል። ምን እንደሆነ አላወቁም። ከምድር ሃያ ስድስት ማይልስ ከፍታ ላይ የሚንሳፈፍ ደመና ብቻ ነው የመሰላቸው።
ደመናው በአየር ላይ እየተንሳፈፈ ነበረ። ይህ እውነት ነው። ልክ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ በታየበት 28 ደቂቃ ውስጥ የነበረበት ከፍታ አልተለወጠም።
63-0630 ሕይወታችሁ ለወንጌሉ የሚመጥን ነውን?
ከምድር ወደ ላይ ትነት የማይገኝበት ቦታ ከአስራ አምስት ማይልስ ከፍታ በላይ ነው ብለን እናስብ። ይህ ግን ሃያ ስድስት ማይልስ ከፍታ ሆኖ ደመናው ቀኑን ሙሉ በዚያ ተንሳፎ ቆየ። አያችሁ? ምን እንደሆነ አያውቁም። እግዚአብሔር ይመስገን እኛ ግን እናውቃለን።
በፍጹም። ደመናው ቀኑን ሙሉ አልታየም። ከ26 – 30 ማይልስ በሚሆን ከፍታ አየሩ በጣም ስስ እና ሞለኪዩሎቹም በጣም ተራርቀው የተበታተኑ ስለሆኑ በቀን ከሚታየው ደማቅ ሰማይ ጋር ደመናው ሊታይ አይችልም። ሊታይ የሚችለው ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ሰማዩ ሲጠቁር ለ28 ደቂቃ ብቻ ነው።
65-0725 በተራራው ላይ ያለው መስህብ ምንድነው?
ያን በሚያህል ከፍታ ላይ ጭጋግ ወይም ጉም ወይም ምንም ነገር ሊኖር አይችልም። “ምንድነው ያመጣው? የት ነው ያለው?” ያ ክብ ቅርጽ ያለው ሰማይ ላይ የታየው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ግራ አጋብቷቸዋል።
እውነት ነው። ደመናው ሰማይ ላይ ለ28 ደቂቃ እየተንሳፈፈ ቆይቷል።
63-0623 በፈረሰው ቅጥር ቦታ መቆም
እኔ በዚያ ጊዜ ደመናውን ፎቶግራፍ እያነሱ እንደነበረ አላወቅሁም፤ ሳይንቲስቶቹ ግን መላእክቱ ከሰማይ መልእክቱን ሊያቀብሉኝ እየወረዱ በነበረ ሰዓት ፎቶ እያነሱ ነበር።
… የደመናውን ፒራሚድ ታያላችሁ? እኔ ልክ ከዚህ ስር ቆሜ ነበር።
ይህ እንኳ እውነት አይደለም። ተሳስቷል። ደመናው መላእክቱ ወደ እርሱ ከመምጣታቸው 8 ቀን በፊት ነው የታየው። እርሱም ደግሞ ከደመናው ስር አልቆመም። መላእክቱ ወደ እርሱ ሲወርዱ ደመና አልሰሩም።
65-0718 የወቅቱ መንፈሳዊ ምግብ
… እኔ እና ወንድም ጂን ኖርማን ወደ ላይ በተመለሱ ጊዜ እዚያ ቆመን ነበር። እነርሱም ፎቶ አነሱት ግን እስከ ዛሬ ድረስ ምን እንደሆነ አያውቁም።
ይህም እውነት አይደለም። ይህ የሆነው ደመናው ከተፈጠረ ከ8 ቀናት በኋላ ነበር። መላእክቱ ወደ ላይ ሲወጡ ደመና አልሰሩም።
ደመናው ላይ የነበረው ሃሳብ ሲለዋወጥ ተመልከቱ። ደመናው የተፈጠረው መላእክቱ ሲወርዱ ይሁን ሲወጡ እርግጠኛ አልነበረም።
ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ደመናውን የጌታ ምጻት ነው አላለም።
ደመናው የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነውም አላለም።
ደመናውን በሰማያት ላይ የታየ የሰው ልጅ ምልክት ነው ብሏል።
64-0112 ሻሎም
አሁንም ፎቶው ላይፍ መጽሔት ውስጥ አለ፤ እስካሁንም ግራ አጋብቷቸዋል። እርሱ ግን በምድር ላይ ከማድረጉ በፊት በሰማያት ውስጥ ያውጀዋል። በመጀመሪያ ምልክቶቹን በሰማያት ያሳያል።
65-0718 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይፈጽሙ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
… ከዚያ በኋላ በሰማይ ላይ የሰው ልጅ ምልክት ይታያል።”
ደመናው ትርጉሙ ይህ ነው።
ክርስቶስ እኛ መረዳት የምንችለው የተገለጠ ቃል ሆኖ እንደሚወርድ የሚያሳይ በሰማይ ላይ የተገለጠ ምልክት ነው።
የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሐዋርያት እምነት ይመልሰናል፤ በዚያውም በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሞቱት ቅዱሳን ከሙታን ለሚነሱበት ትንሳኤ ያዘጋጀናል። ይህም የሚፈጸም ያ ብርቱ መልአክ ከሙታን ሊያስነሳቸው ሲወርድ ነው።
ከዚያም በስተመጨረሻ ክርስቶስ ከራሱ ጋር ወደ ላይ ሊነጥቀን በሚታይ አካል ይመጣል።
ከልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ጋር የተያያዙ ችግሮች የተፈጠሩት ወንድም ብራንሐም ላይ ትኩረት በመደረጉ ነው።
ትኩረት መደረግ ያለበት እርሱ ላይ ሳይሆን ያመጣው መልእክት ላይ ነው፤ ይህ መልእክት መሽራዋ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንድትችል የእግዚአብሔርን ቃል ይገልጥላታል።
61-0316 ቤተክርስቲያን በጸጋ ፈንታ ሕግን መምረጧ
በነበርኩበት ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ አለኝ፡- “መጥምቁ ዮሐንስ ለመጀመሪያው የክርስቶስ ምጻት መንገድ ሊጠርግ እንደመጣው ሁሉ ያንተ መልእክት ደግሞ ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።”
ራዕይ 10፡7 በሰባተኛው መልአክ ዘመን አይልም። ያ ዘመን ከ1947 እስከ 1965 ነው።
ቃሉ የሚለው ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ነው።
ወንድም ብራንሐም በ1965 ዓ.ም ሞተ።
ከ1966 ጀምሮ በቴፕ ተቀርጾ በተቀመጠው ድምጹ መመራጽ አለብን ምክንያቱም በድምጽ በተቀዱት መልእክቶቹ አማካኝነት የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር እንድናስተውል ያግዘናል።
ቀጥሎ የምታዩት ምስል የሐሰት ዜና ነው።
ወንድም ብራንሐም “ክርስቶስ ሳንሴት ተራራ አጠገብ ተገለጠ” አላለም። ደመናውም በጭራሽ ከሳንሴት ተራራ አጠገብ አልነበረም።
በተጨማሪም ወንድም ብራንሐም “ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል” አላለም።
ከተሞኙት ወይም ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ወገን አትሁኑ።