ማቴዎስ 24፡45 ታማኝ እና ልባም ባሪያ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባሎቿ ከየአካባቢው የተገኙ ጥቂት ሰዎች ያሉበት ሕብረት ነበረ፤ የምትመራውም በአጥቢያ ሽማግሌዎች ስለሆነ አንድ ግለሰብ መሪ አይሆንም ነበር።
First published on the 12th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።
2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
ይህ የተደራጁ ቤተክርስቲያኖችን ካወገዘው ከወንድም ብራንሐም አገልግሎት በጣም ይመሳሰላል።
“የሰባተኛው መልአክ” ብርቱ ድምጽ!
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
“ውጡ”። ይህ ፍልሰት ነው።
“ሌላ ድምጽ”። ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ስሕተት መሆናቸውን ለሰዎች በውስጣቸው እየመተናገረ የሚያሳምናቸው የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት።
ቤተክርስቲያኖች ሁሉ? የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችም ጭምር?
አዎ። ምክንያቱም ኢየሱስ ስለ ሎዶቅያውያን ሲናገር ማንንም አላስቀረም።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
የተገለጠው ቃል ማለትም ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ይጣራል፤ ነገር ግን የሚጣራው ቤተክርስቲያንን ሳይሆን ግለሰቦችን ነው።
በዚህ ክሕደት ውስጥ የገባች ቤተክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ ወቀሳ ውስጥ ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ተካትተዋል።
ሶስተኛው ፍልሰት የሚደረገው ግለሰቦችን በአምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች ክሕነት ስር አስረው ከያዙ ከተደራጁ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ጠርቶ ለማስወጣት ነው። አምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች አሁን ተለውጠው ወደ አንድ ተጣምረው አንድ ሰው ብቻ ፓስተር የሚባል ስም ተሰጥቶት ብቻውን የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ተደርጓል። የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያን ፓስተሮች የጨለማውን ዘመን ጳጳሳት ተክተዋል። ፖፑ በጳጳሳት ሁሉ ላይ አለቃ ሆነ። ዛሬ ደግሞ ከፍ ያለ ስልጣን የተሰጠው ፓስተር (አንዳንድ ጊዜ ሐዋርያ ተብሎ የሚጠራ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በሌሎች ፓስተሮች ሁሉ ላይ አለቃ መሆን ይፈልጋል። ይህም የሮማ ካቶሊክ መንፈስ ነው።
65-0220 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ሥፍራ
አንድ ሰውዬ ከጥቂት ወራት በፊት ቴክሳስ ውስጥ አናግሮኝ ነበር። እንዲህ አለኝ፡- “አቶ ብራንሐም፤ ስምህ የእኛ ቤተክርስቲያን የአባላት መዝገብ ውስጥ ካልተጻፈ መንግስተ ሰማያት አትገባም።” ይህን አስባችሁ ታውቃላችሁ? እንዲህ ዓይነት ነገር ስትሰሙ በፍጹም አትመኑ። የሆነ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል ካልሆናችሁ በቀር ወደ መንግስተ ሰማያት የማትገቡ ይመስላቸዋል። እንደዚያ ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው። እንደዚያ ብሎ ማሰብ የክርስቶስ ተቃዋሚነት ነው። እኔ ደግሞ እንዲህ እላለው፡- ይህን ዓይነቱን መንፈስ የምታምኑ ከሆነ ጠፍታችኋል። ይህ ስለመጥፋታችሁ የሚያመለክት ግልጽ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም በዚህ አስተሳሰባችሁ የእግዚአብሔርን ሥራ ከንቱ ታደርጉታላችሁ። እግዚአብሔር በየትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስሙን አላኖረም። እግዚአብሔር ስሙን ያኖረው በልጂ በክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ያውም እርሱ እና ልጁ አንድ በሆኑ ጊዜ። እግዚአብሔርን ማምለኪያ ትክክለኛው ስፍራ ይህ ነው። ከዚህ ሌላ መሰረት ከዚህ ሌላ ዓለት የለም።
የጥንት ቤተክርስቲያኖች በሙሉ በሽማግሌዎች ነበር የሚመሩት፤ ከሽማግሌዎችም መካከል አንዳንዶቹ በአምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ በመሳተፍ ይሰብኩ ነበር።
ነገር ግን የስብከት አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ ሽማግሌዎች ከማይሰብኩት ሽማግሌዎች በላይ አልነበሩም። ሽማግሌዎች ሁሉ ስልጣናቸው እኩል ነበር።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
በኤፌሶን የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ለሁሉም የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት ናት። የኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ነበረ።
ጳውሎስ ይህችን ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች እጅ ነው አደራ ብሎ የሄደው። አንድም ፓስተር አልተጠቀሰም።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ … እኔ አውቃለሁ።
ሐዋርያቱ ከሞቱ በኋላ ወዲያው የስልጣን ጥማት ያላቸው ሰዎች ጳጳሳት ነን ብለው በቤተክርስቲያን ላይ መሰልጠን ጀመሩ። ጳጳሳቱ ራሳቸውን ከሕዝቡ በላይ ከፍ አደረጉ።
በሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል ይቆም የነበረው የብሉይ ኪዳኑ የክሕነት አገልግሎት በቀራንዮ መስቀል ላይ ጊዜው አብቅቷል።
አሁን እያንዳንዱ አማኝ ካሕን ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥
ከካሕን በላይ ሊቀካሕናት ብቻ እንጂ ሌላ ማንም የለም፤ ሊቀካሕናቱም ኢየሱስ ነው።
ዛሬ በክርስቲያኖች ላይ ማንም ሰው የበላይ መሆን አይችልም። የበላይ መሆን የሚፈልግ ሰው በኒቆላውያን መንፈስ እየተመላለሰ ነው።
“ኒቆ” ማለት በግሪክ “መጨቆን” ማለት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ እውቅና ያልሰጠው የሰባኪዎች ሕብረት ጉባኤውን ወይም ምዕመኑን ይጨቁናል።
በግ ሳር መብላት የሚችለው ታስሮ የቆመበት ቦታ ብቻ ነው።
እስከ 312 ዓ.ም ድረስ አማኞች በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ በትንንሽ ሕብረት ብቻ በሽማግሌዎች እየተመሩ ነበር የሚሰበሰቡት።
62-0601 ከኢየሱስ ጋር ወግኖ መቆም
እነዚያ የድሮ ሰዎች ሲወጡ አንዳንዴ ለስድስት ወይም ለስምንት ብቻ ሆነው በአንድነት ይወጡ እንደነበር ታውቃላችሁ? ጥቂት ሆነው ሃገሩን በሙሉ ያንቀጠቅጡ ነበር። አቂላ እና ጵርስቅላ ከአጵሎስ ጋር ሆነው ታላቅ መነቃቃት በሆነ ጊዜ በዚያ ሕብረት ውስጥ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ የተሰባሰቡት። አንድ ቤተክርስቲያን ሙሉ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ። ዛሬ ማታ እዚህ በተሰበሰብንበት ከእነርሱ በቁጥር አምስት፣ ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ እንበልጣለን።
ሮሜ 16፡5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
የመጨረሻዎቹ ሐዋርያት ከሞቱ ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ሁለት ዋና ዋና መዋቅራዊ ለውጦች ገቡ፡- መጀመሪያ ጳጳሱ እና ሽማግሌዎች መለያየታቸው እና ጳጳሱ የስልጣን ተዋረድ ውስጥ ቁንጮ ሆኖ መቀመጡ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በካሕናት (ሰባኪዎች) እና በምዕመናን መካከል ልዩነት መደረጉ ነው።
በ258 ዓ.ም የሞተው የካርቴጅ ጳጳስ ሳይፕሪያን ጳጳሳትን ከቀሩት የቤተክርስቲያን አባላት የተለዩ ሰዎች አድርጎ ከፍ አደረጋቸው።
እንጀራው እና የወይን ጠጁ የመዳን ምልክት መሆኑ ቀርቶ እንጀራውን መብላት እና በራሱ ለሕዝቡ መዳን ሆነ። ወይኑን የሚጠጣው ደግሞ ካሕኑ ብቻ እንዲሆን ተደረገ ይህም ካሕኑን ከቀረው ሕዝብ ለየት ለማድረግ ተብሎ ነው።
በዚህ መንገድ ቤተክርስቲያን የጨለማው ዘመን ውስጥ ገብታ ሞተች። ከሰዎች በላይ ከፍ በተደረጉ ጥቂት ሰዎች መመራት ጀመረች።
አንድ የቤተክርስቲየን መሪ ትኩረቱ በሙሉ በራሱ ዙርያ ሲሆን የራሱን ትንሽዬ መንግስት ይመሰርታል።
ማቴዎስ 24፡44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
ይህም በድጋሚ ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ያስታውሰናል።
“የሰው ልጅ”።
የሰው ልጅ የሚለው ቃል በዚህ ስም የሚጠረው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን ያመለክታል። እርሱም ኢየሱስ ነው።
ማቴዎስ 24፡45 እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?
“ታማኝ … ባሪያ”።
ታማኝ ባሪያ የሚለው ቃል ማንንም በተናጠል የሚጠቁም ስላልሆነ ስለ ማንም ሊሆን ይችላል።
ማንኛውም ታማኝ የሆነ ባሪያ ማለት ነው።
በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ታማኝ ሰዎች ነበሩ።
ቆላስይስ 1፡7 ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ ተማራችሁ፥ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው።
ቆላስይስ 4፡7 የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ ቲኪቆስ ኑሮዬን ሁሉ ያስታውቃችኋል፤
ቆላስይስ 4፡9 ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው፤ የዚህን ስፍራ ወሬ ሁሉ ያስታውቁአችኋል።
እግዚአብሔር እያንዳንዱን አስተዋይ እና ታማኝ ሰው በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሽማግሌ ሆኖ እንዲመራ ይጠቀምበታል።
የትኛውም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው ራስ መሆን የለበትም። የትኛውም ሰው የብዙ ቤተክርስቲያኖች ራስ መሆን የለበትም።
እያንዳንዱ አጥቢያ ጉባኤ በሽማግሌዎች ሕብረት መመራት አለበት እንጂ በግለሰብ መመራት የለበትም።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን። ዛሬ ግን መጥፎው ረብ ማለትም ገንዘብ በፓስተሩ ይሰበሰብና ከእርሱ ጋር ለሚስማሙ አጃቢዎቹ ይከፋፈላል።
አስራት ለፓስተሩ ነው የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የለም።
አጋቦስ ሊመጣ ስላለው ታላቅ ረሃብ ትንቢት ተናገረ። ደቀመዛሙርትም በይሁዳ ውስጥ ለነበሩ አማኞች ገንዘብ ሰብስበው ላኩ።
የሐዋርያት ሥራ 11፡29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤
የሐዋርያት ሥራ 11፡30 እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።
የተሰበሰበው ገንዘብ ለሽማግሌዎች ነበር የተሰጠው። ገንዘቡ እንዴት ባለ መንገድ አገልግሎት ላይ መዋል እንዳለበት ሽማግሌዎች ነበሩ ተወያይተው በአንድነት የሚወስኑት። ሽማግሌዎች ጉባኤውን ይመሩ እና ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ይቆጣጠሩ ነበር።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
የትኛውም ሽማግሌ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ብሎ አያስብም ነበር።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡4 የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል እያንዳንዱ ሽማግሌ ጌታ ሲመጣ ነው ሽልማቱን የሚቀበለው።
57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1
ከመጽፍ ቅዱስ ጠቅሳችሁ ማን እንደሚበልጥ አሳዩኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እና ከአጥቢያ ሽማግሌ ማን ይበልጣል?
እውነት ነው፤ ትክክል ነው፤ እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለራሱ ነጻ ሆኖ መቆም አለበት።
ዋነኛው ሃላፊነታቸው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባላት ቤተክርስቲያንን በአለቅነት የሚገዛ ፓስተር ወደሌለበት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አሰራር እንዲመለሱ ማድረግ ነው። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ከሆነ አሰራሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ማለት ነው።
ሮማዊው ጀነራል ታይተስ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን ባፈራረሰ ጊዜ አብዛኞቹ ሐዋርያት ሞተዋል። ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሰዎች ሁሉ በላይ ታላቅ ሆኖ የተሾመ ሰው አልነበረም። ከዚያ በኋላ ቀስ ብለው ኒቆላውያን እያንዳንዱን አጥቢያ ቤተክርስቲያን በራሳቸው ቁጥጥር ስር አደረጉ፤ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን አደረጉ። እግዚአብሔርም ይህንን ጠላ።
ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
የኒቆላውያን ስራ አንድ ሰውን ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ በማድረግ ሕዝቡን መጨቆን ነው።
ሰባተኛው መልአክ የመጣው የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር ለመግለጥ ነው።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ሁሉንም ነገር የሚያቀና ከሆነ እኛ ከዚህ በኋላ የሚቀጥል አገልግሎት መጠባበቅ አያስፈልገንም።
አማኞች እርስ በራሳቸውን መርዳት መቻላቸው ግልጽ ነው፤ ነገር ግን ጥገኛ የምንሆንበት በበላይነት የሚመራን አገልግሎት የለም።
እያንዳንዱ አጥቢያ ጉባኤ የወንድም ብራንሐም መገለጦች እውነት መሆናቸውን ለማረጋገጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ቢመረምራቸው ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ ይችላሉ።
ሰዎች ኢንተርኔትን መፈተሽ ወይም ልባቸው ወዳመዘነበት ሄደው እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሊታዘዙት የሚገባቸው አንድ ዓለም አቀፋዊ መሪ የለም።
ካቶሊኮች ለፖፑ ያላቸው አመለካከት እንዲህ ነው።
ብዙ ሰዎች ከኤልያስ በኋላ ተከትለን የምንመጣው ኤልሳእ እኛ ነን ወይም ስምንተኛው መልአክ ነን ብለዋል። ስለዚህ የኒቆላውያን መንፈስ ዛሬ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥም እየተንቀሳቀሰ ነው።
ሰዎች የራሳቸውን አገልግሎት ሲያሞግሱ መኖር የለባቸውም።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤
ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል እንድርያስ ብቻ ነው የኢየሱስ ደቀመዝሙር የሆነው።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐምን መከተል በስተመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስን ስለመከተላችሁ ዋስትና ሊሆን አይችልም።
በተለይ ደግሞ የቤተክርስቲያናችሁ ራስ ፓስተር ከሆነ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ ስላልሆነ መጽሐፍ ቅዱስን የምትከተሉ አትሆኑም።
ሁላችንም በእምነታችን ውስጥ ብዙ ስሕተቶችን የሰራን ፍጹማን ያልሆንን ሰዎች ነን።
ስለዚህ እነዚህ ራሳቸው ከፍ የሚያደርጉ ሰዎች ከፍ በሚያደርጉዋቸው ሰዎች ዘንድ ሁሉ ስሕተትን ያሰራጫሉ።
እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የራሳቸውን ከፍ ያለ ፓስተር ብቻ ያዳምጣሉ።
በዚህም ምክንያት ከቤተክርስቲያናቸው ውጭ ከሆነ ሰው እውነቱን የመስማት እድላቸው የመነመነ ነው።
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ግን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው የቆመው። ከእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውጭ። ምክንያቱም የትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ መኖሩን አልተናገረም።
በእምነታቸው የሚለያዩ ብዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ከዚህም የተነሳ በመካከላቸው ብዙ ስሕተቶች ይሰራጫሉ። ሆኖም ግን እያንዳንዱ ሜሴጅ ቤተክርስቲያን ሙሉውን እውነት አግኝተናል ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።
ግልጽ ከሆኑ ስሕተቶቻቸው ጥቂቶቹ፡-
የሰባት ዓመታት መከራ የሚባለው ስሕተት ከዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ወደ ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ተላልፏል።
የክርስቶስ ተቃዋሚ ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ለ7 ዓመታት ቃልኪዳን ያደርጋል ከዚያም በሰባቱ ዓመታት እኩሌታ ወይም 3.5 ዓመት ላይ ቃልኪዳኑን ያፈርሳል ይላሉ።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤
ቃልኪዳኑ ይጸናል እንጂ አይደረግም።
የጸና ቃልኪዳን ሊፈርስ አይችልም።
ገላትያ 3፡15 ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም።
እግዚአብሔር በዘፍጥረት ምዕራፍ 15 የእንስሳት መስዋእት በመጠቀም ከአብራሐም ጋር ቃልኪዳኑን አድርጓል።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦
ከዚያ በኋላ ቃልኪዳኑ በቀራንዮ በተደረገው የመጨረሻ መስዋእት ጸንቷል ወይም ተረጋግጧል፤ ማረጋገጫውም ከ3½ አገልግሎት በኋላ የተፈጸመው የኢየሱስ ሞት ነው። የኢየሱስ መስዋእትነት የእንስሳት መስዋእት እና የቤተመቅደስ ቁርባን በሙሉ እንዲያበቃ አድርጓል።
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ … አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል
ከዚህም የተነሳ አሁን የ3½ ዓመት መከራ ብቻ ነው የሚቀረው።
ሌላው ትልቅ ስሕተት ደግሞ አንድ ሰው አግብቶ መፍታት እና ከፈታ በኋላ እንደገና ማግባት ይችላል የሚሉት ነው፤ በተለይም በዕድሜ ወጣት የሆነች ሴትን ማግባት ይችላል።
አንድ ሰው እና አንድ ሴት በሕግ ከተጋቡ በኋላ መፋታትም ሆነ ከፍቺ በኋላ እንደገና ማግባት አይፈቀድም።
ሴትየዋ ድንግል መሆን አለባት። ድንግል ካልሆነች ከጋብቻቸው በፊት መናገር አለባት፤ ከሰርጋቸው በፊት ካልተናገረች መሃላዋ የውሸት ነው።
ባሏ ድንግል አለመሆኗን ባየ ጊዜ ከፈለገ ወዲያው ሊፈታት መብት አለው። መሃላዋ የውሸት ስለሆነ በእርሱ ላይ አይጸናበትም፤ ስለዚህ ሌላ ሴት ፈልጎ ማግባት ይችላል። ይቅርታ ካደረገላት ግን የጋብቻ ቃልኪዳናቸው ጽኑ ይሆናል።
መዳራት ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ወሲብ ነው። ወንድም ቢሆን ሴትም ከጋብቻ በፊት መዳራት አይችሉም።
1ኛ ቀሮንቶስ 7፡2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።
ድንግል ያልሆነች ሴት ከጋብቻ በፊት ድንግል አለመሆኗን ካልተናገረች ባሏ እርሷን መፍታት ይችላል። ሔዋን ወደ አዳም በመጣች ጊዜ ድንግል አልነበረችም። እግዚአብሔር ሰርግን ለመሰረዝ የሚቀበለው ብቸኛ ምክንያት ሴቲቱ ድንግል አለመሆኗን ነው። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሰውየው ሌላ ሴት ማግባት የሚችለው ያውም የሚያገባት ሴት ድንግል ከሆነች።
ሰው ድጋሚ ማግባት የሚችለው በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት በዚህ ምክንያት ብቻ ነው።
ነገር ግን ሙሽራይቱ ድንግል አለመሆኗን ሳያውቅ ቢቀር እርሷ ከዚያ በፊት በሌላ ሰው ድንግልናዋ የተወሰደ መሆኑን ሳያውቅ ቢቀር፤ ካገባት በኋላ ቢያውቅ እርሷ እርሱ ራስ እንዲሆናት ራሷን ዝቅ አድርጋ ለእርሱ ብታቀርብ እርሱ ይቅር ሊላት እና ሚስቱ አድርጎ ሊቀበላት መብት አለው፤ የጋብቻ ቃልኪዳናቸውም እስከ ሞት ድረስ የጸና ይሆናል።
ማቴዎስ 19፡9 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው።
በሌሎች ጉዳዮች ሁሉ መፋታት እና እንደገና መጋባት በዝሙት መኖር ነው።
ሮሜ 7፡1 ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?
2 ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።
ሕጋዊ ጋብቻ እስከ ሞት ድረስ ጽኑ ነው።
ባልየው በሕይወት ባለበት ዘመን ሁሉ ሴቲቱ በጋብቻ ቃልኪዳን ታስራለች።
ይህ ቃልኪዳን በሰውየውም ላይ እስከ ሞት ድረስ ጽኑ ነው።
ሌላው ትልቅ ስሕተት ሰው በራሱ ትዳር ላይ ዝሙት ሊፈጽም አይችልም የሚሉት ነው።
ያገባ ሰው ካላገባች ሴት ጋር መተኛት ይችላል ይላሉ። ይህ ግን የፈጠጠ ስሕተት ነው።
በጣም መጥፎ ስሐተት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 6፡18 ከዝሙት ሽሹ።
መዳራት ማለት ያላገባ ሰው ወሲብ ሲፈጽም ነው።
ብሉይ ኪዳን ሕግ ለእንስሳት የሚፈቀደውን ከአንድ በላይ ማግባት ለሰዎች የፈቀደው ሔዋን እንስሳውን እባቡን ሰምታ ስለሳተች ነው።
በቀራንዮ ግን ከአንድ በላይ ማግባት አቁሟል። ከዚያ በኋላ ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት ትክክለኛ መንገድ ተመልሰዋል። አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ብቻ።
ማቴዎስ 19፡8 እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።
መፋታት አስቀያሚ ነገር ነው። የልብ ጥንካሬን ያሳያል።
አሁን የምንፋታ ከሆነ ወደፊት ለምንጠራበት የበጉ ሰርግ እራት ግብዣ መዘጋጀት አንችልም።
ኢየሱስ የሚፈልገው አዳም እና ሚስቱ በመጀመሪያ እንደነበሩት እንድንሆን ነው የሚፈልገው። ፍቺ የለም። እርስ በርሳቸው የተጋቡ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ብቻ። ሌላ ሶስተኛ ሰው የለም።
61-0806 የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ
የአሜሪካ የፍቺ ፍርድ ቤቶች የዓለም ሃገራት ፍርድ ቤቶች ሁሉ ከሚያስተናግዱት የበለጠ ፍቺ ያስተናግዳሉ፤ ያውም በሴቶች ጥያቄ። ሃገራችን ውስጥ በመንገድ ላይ በአደባባይ ሴተኛ አዳሪነት ከሚፈጸምባቸው ከኢጣልያ እና ከፈረንሳይ በላይ ስነምግባር ወድቋል። የእነርሱን ሴተኛ አዳሪዎች ናቸው ዝሙት የሚፈጽሙት፤ በእኛ ዘንድ ግን ያገቡ ሴቶች በአንድ ጊዜ ከተለያዩ ወንዶች ጋር መተኛታቸው እንዲሁም ያገቡ ወንዶች ከተለያዩ ሴቶች ጋር መተኛታቸው ነው። ብዙ ሚስት ማግባት በሚፈቀድባቸው ሃገሮች ውስጥ በጣም የተሻሉ ናቸው። እንደዚህም ሆኖ ግን ብዙ ሚስት ማግባት ስሕተት መሆኑን እናውቃለን።
የሜሴጅ ፓስተሮች አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ለመግለጥ በመፈላሰፍ ተጠምደዋል።
የወንድም ብራንሐም አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት ለመጨረስ ነበረ።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
የሚያቀርባቸውን የመልእክት ዓይነት ተመልከቱ፤ “በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን በሙሉ ማጠናቀቅ”። ሰባተኛው መልአክ ያልተጠናቀቁትን ሚስጥራት በሙሉ ወደ መቋጫ እያመጣቸው ነው። ሰባተኛው መልአክ የተበታተኑትን ይሰበስባቸውና ሚስጥራቱን ሁሉ ያጠናቅቃል መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህንኑ ነው። “የተጻፈውን የመጽሐፍ ሚስጥር ያጠናቅቀዋል”።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን 7ቱ ነጎጓዶች ምን እንዳሉ ወይም የጌታ ምጻት መች እንደሚሆን እና የመሳሰሉ ያልተጻፉ ሚስጥራት ላይ ለመስበክ አትሞክርም ነበረ።
63-0324 ሰባተኛው ማሕተም
እንግዲህ ከዚህ ማሕተም ስር ያለው ታላቅ ሚስጥር ምን እንደሆነ አላውቅም። እኔ አላውቅም። ላየውም አልቻልኩም። ምን እንደሆነ ተገልጦ አላነበብኩትም። ምን እንደሆነ ምን እንደሚል አላውቅም። ነገር ግን የማውቀው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም የሚናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች መሆናቸውን እና ተራ በተራ በአንድነት ሁሉም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ታላቅ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነው።
ይህንንም ባየሁ ጊዜ ትርጓሜውን ለማወቅ ፈለግሁ፤ እርሱም እዚያው ነበረ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም። ይህ ነው እውነቱ ወዳጆች ሆይ። አያችሁ? እነዚህ ሚስጥራት ሊገለጡ ጊዜው አልደረሰም፤ ነገር ግን በጣም እየቀረበ ነው። አያችሁ? በጣም እየቀረበ ነው።
… ነገር ግን የማውቀው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም የሚናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች መሆናቸውን እና ተራ በተራ በአንድነት ሁሉም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ታላቅ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነው።
ይህንንም ባየሁ ጊዜ ትርጓሜውን ለማወቅ ፈለግሁ፤ እርሱም እዚያው ነበረ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም። … ደግሞም አንድ ልተረጉም የማልችለው ነገር አለ ምክንያቱም የተነገረው በማይታወቅ ቋንቋ ነው።
… እርሱም ያንን ሰባተኛ ማሕተም ፈታ። ነገር ግን አያችሁ፤ የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም። ነገር ግን እርሱ ራሱ ማንም አያውቅም ብሎ እንደ ተናገረው እንደ ምጻቱ ቀን ማንም ሊያውቀው አይችልም፤ ስለነዚህ ሰባት ነጎድጓዶችም ማንም ሊያውቅ አይችልም። ስለዚህ እንደምታዩት የተያያዘ ነው።
ትርጓሜው የተጻፈው በማይታወቅ ልሳን ነው። ስለዚህ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ምንም አናውቅም።
64-0614 የእግዚአብሔር መገለጥ
እርሱም እንዲህ አለ፡- “ያው እንግዲህ እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች፤ አያችሁ፤ እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ማስተጋባታቸው፤ ይህ መገለጥ ለሆነ አይሰጠውምን?”
እኔም እንዲህ ብዬ መልስኩ፡- “በፍጹም፤ የለም፤ ይህማ በቃሉ ላይ አንዳች መጨመር ነው።”
ማንም ሰው ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ለማብራራት በድንገት አስደናቂ ሃሳብ ወይም መገለጥ ይዞ ሊመጣ አይችልም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን ቃል ብቻ ነው የሰበከችው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2 ቃሉን ስበክ፥
ማቴዎስ 24፡46 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤
“ያ ባሪያ”። የትም የሚኖር ማንኛውም ሽማግሌ ጥቅሶችን ወስዶ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ እውነትን በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ተጠቅሞ ማጣራት ይችላል።
ማንኛውም ሽማግሌ የ1769ኙ እትም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እስካመነ ድረስ ታማኝ ባሪያ ነው።
47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
የምንኖርበት የንስር ዘመን ውስጥ ሃላፊነታችን ከዊልያም ብራንሐም መልእክቶች ውስጥ መገለጦችን ማግኘት እና ትምሕርቶቹን በመጽሐፍ ቅዱስ መዝነን አጣርተን ለመቀበል መትጋት ነው። ትምሕርቱ ትክክል መሆኑን ወደ ወንድም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች ሳንመለስ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ ማጣራት መቻል አለብን።
በአጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚያገለግል ልባም ባሪያ ሁሉ ይህን ለማድረግ ነው የሚጥረው።
በአሁኑ የኢንተርኔት ዘመን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ማለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተበታትነው የሚኖሩ ግልሰቦች ሕብረት ሊሆንም ይችላል፤ ምክንያቱም የZOOM ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሕብረት ማድረግ ይችላሉ ደግሞም ከዌብሳይቶች መማር ይችላሉ።
ማቴዎስ 24፡48 ያ ክፉ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥
49 ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥
በራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ የተጠቀሰችዋ ታላቂቱ ጋለሞታ ሰክራለች። ልክ እንደዚሁ የሜሴጅ ፓስተሮች የሮም ቤተክርስቲያን ከጠመቀችው የአስተምሕሮ ጽዋ ጠጥተው በቤተክርስቲያን ላይ ራስ ነን ይላሉ። ልክ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካሕናት በራሳቸው ቤተክርስቲያን ላይ ራስ ነን እንደሚሉት ሁሉ የሜሴጅ ፓስተሮችም የቤተክርስቲያን ራስ ነን ይላሉ። ሕዝቡን በጭቆና ይገዛሉ፤ ሁሉም ሰው እሺ ብሎ እንዲታዘዝላቸውና የተሳሳተ እምነታቸውን እንዲከተል ደግሞ የሚቃወማቸውን ሰው ሁሉ ያወግዛሉ። እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት ስለማይችሉ ሁል ጊዜ ከሰው ንግግር በሰበሰቧቸው ጥቅሶች ላይ ጥገኞች ናቸው። አንድን ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ መርምራችሁ ስተቀበሉ ብቻ ነው ከሕይወት ወንዝ የምትጠጡት።
ማቴዎስ 24፡50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥
ይህም ቃል በድጋሚ የሚያሳስበን የጌታን ምጻት የሚወክለው ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ነው።
ማቴዎስ 24፡51 ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
ፓስተሮች ለራሳቸው ክብር መስጠት ይወዳሉ። ቤተክርስቲያን ላይ ገዥ ሆነው ይቀመጣሉ። ሕዝቡ እነርሱ ካወቁት ውጭ ምንም እንዳያውቅ ያፍኑታል፤ ከዚህም የተነሳ ጉባኤው ፓስተሩ እውቀት ባጣበት ጉዳዮች ላይ መሃይም ሆነው ይቀራሉ። እነዚህ ጨቋኝ መሪዎች መጨረሻቸው ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።
ፓስተሮች እረኞች ነን ይለሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እረኛው ፓስተሩ ነው አይልም።
መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ነው አይልም።
“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ ስለዚህ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ምንም ስልጣን የለውም።
መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሮችን ስድስት ጊዜ ያወግዛቸዋል።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።
ኤርምያስ 2፡8 … ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥
ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥
ፓስተሮች ከሚሰሯቸው ስሕተቶች መካከል የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።
በሕዝብ ላይ ስልጣን መያዝ ባለ ስልጣኑን እንደሚያባልገው ግልጽ ነው።
የቤተክርስቲያን አመራር እንደገና በጥንቃቄ መፈተሸ አለበት።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
“ፓስተሮች” ወይም መጋቢዎች በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ብቻ ነው።
በዚህም ጥቅስ ውስጥ ከአምስት አገልጋዮች መካከል በአራተኛ ደረጃ ላይ ነው የተጠቀሱት። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አለቃ ለመሆን ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የላቸውም። ይህንን ስልጣን በጉልበታቸው ቀምተው ነው የያዙት።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሲመሰርታት ስለ ፓስተሮች አንዳችም አልተናገረም።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
የሜሴጅ መገለጦችን ከእግዚአብሔር ቃል ለማረጋገጥ የመጽፍ ቅዱስ አስተማሪ ካልሆነ በቀር ሌላ ሰው አይችልም።
ቤተክርስቲያንን መምራት ያለበት ማነው?
በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ጅማሬ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን መምራት ያለባቸው ሽማግሌዎች ናቸው ብሏል።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ መጨረሻ አካባቢ ቅዱስ ጴጥሮስም ተመሳሳይ ነገር ነው የተናገረው።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በሚገዙ ፓስተሮች አይገረምም።
ፓስተር የራሱ የሆኑ ውሱንነቶች አሉት። አንድ ፓስተር የራሱ የሆኑ ጠንካራ ጎኖች አሉት፤ እነዚህም ጥሩ ናቸው፤ ደግሞም ደካማ ጎኖች አሉት፤ ደካማ ጎኖቹ ደግሞ ሰዎች እውነትን ለማወቅ በሚደርጉት ጉዞ ያደናቅፋለቸዋል። አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ሽማግሌዎችን ይሾማሉ፤ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ ፓስተሩ የሚፈቅዳቸው ሰዎች መሆን አለባቸው፤ ስለዚ ሽማግሌዎቹ የፓስተሩ ደጋፊዎች ሆነው ይቀራሉ። ቤተክርስቲያኖች አንድ ሰው የሁሉ ገዥ የሚሆንበትን የካቶሊክ አሰራር ስለተቀበሉ ፓስተሩ በሕዝቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በሽማግሌዎችም ላይ አለቃ ነው።
በአንድ ሰው ስልጣን ተጨቁና በምትኖር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማግኘት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ ነው። በስሕተት በተዋቀረ መዋቅር ውስጥ ሙሉ እውነት ሊገኝ አይችልም።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች መኖራቸውም ራሱ ስሕተት ቤተክርስቲያንን የሚቆጣጠርበት የመጨረሻ ዘመን መቅረቡን አመላካች ነው።
እግዚአብሔር እኛ ስለምንኖርበት ስለ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ምን እንዳለ ሁልጊዜ አስቡ፡-
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
ለብ ያለ ማለት በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በከፊል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን አለመቀበል ነው።
ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣው ቃሉ ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች በሚያምኑት ብዙ ትምሕርት ውስጥ ቃሉ አለመኖሩ በእግዚአብሔር አፍ ውስጥ አለመኖራቸውን ያሳያል። እግዚአብሔር በከፊል ትክክል በከፊል ደግሞ ስሕተት ሆነን አይደለም የሚቀበለን። ሙሉ በሙሉ ትክክል የሆኑ ትምሕርቶችን ፈልገን እንድናገኝ ይፈልጋል። በሌላ አነጋገር ስሕተታችንን ለማረም ፈቃደኛ መሆን አለብን። ለመማር ዝግጁዎች መሆን አለብን። ለመማር ፍላጎት ሊኖረን ይገባል።
ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
ጨለማ የሚባል ራሱን የቻለ “ነገር” የለም። ጨለማ የብርሃን አለመኖር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆን ብርሃን ማጣት ነው። ይህም ጨለማ ውስጥ ይከተናል። በጨለማ ውስጥ የሚመላለስ ሰው ሁሉ ዕውር ነው ምክንያቱም የሚሄድበትን መንገድ ማየት አይችልም። በቤተክርስቲያናችን ትምሕርቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫ አለመኖሩ በር የሆነውን ኢየሱስን ብርሃናችንን ፍለጋ በጨለማ ውስጥ እየተመላለስን መሆናችንን ያመለክታል።
ዘፍጥረት 19፡10 ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።
11 በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ።
በሎጥም ዘመን ተመሳሳይ ነገር ነው የሆነው። በሰዶም የነበሩ ግብረ ሰዶማውያን በጨለማ በዳበሳ በሩን ይፈልጉ ነበር፤ በሩ ግን ተዘግቶ ነበር።
ሉቃስ 17፡28 እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤
ሁሉ ነገር ሰላም በመሰላቸው ሰዓት ድንገት በሩ ተዘጋ።
ሉቃስ 17፡26 በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።
አሁንም ሁሉ ሰላም ይመስል ነበር ግን እግዚአብሔር በሩን ዘጋው።
ዘፍጥረት 7፡16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት።
ወደ ኖህ መርከብ የሚያስገባው በር አንድ ብቻ ነበር፤ እርሱንም እግዚአብሔር ዘጋው።
ወደ ሰማይ መግቢያ በር ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 10፡7 ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
በኖህም ዘመን በሎጥም ዘመን በሩ ተዘጋ።
ስለዚህ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የዘመን መጨረሻ መቅረቡን የሚያመለክት ዋነኛ ምልክት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚቻልበትን የመረዳት በር እግዚአብሔር መዝጋቱ ነው።
ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ብዙ ጉዳዮችን ማብራራት አይችሉም፤ ደግሞም ከትምሕርቶቻቸውም ብዙዎቹን ትክክል መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አይችሉም።
ወደ እውነት የሚያስገባው በር በዘመን መጨረሻ እየተዘጋ መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው?
ሉቃስ 13፡24 በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።
25 ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላችኋል።
26 በዚያን ጊዜም፦ በፊትህ በላን ጠጣንም በአደባባያችንም አስተማርህ ልትሉ ትጀምራላችሁ፤
(ብዙ ውዳሴ እና አምልኮ)
27 እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል።
(ስሕተትን እያወቁ ማድረጋቸው)
28 አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
(ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ)።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ መቆሙን በግልጽ ያሳያል። የተዘጋውን በር እያንኳኳ ነው።
ስለዚህ በሩ ተዘግቷል፤ እርሱ ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች ድምጹን እንዲሰሙ ለማድረግ እየሞከረ ነው፤ እርሱ ቃሉ ስለሆነ ድምጹ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ይህ ቃል በመጨረሻው ዘመን አማኞች በጣም ጥቂት እንደሚሆኑ ያሳያል።
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
እምነታችሁ ጥንካሬው የምታምኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ያህል ብቻ ነው የሚሆነው።
እነዚህ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች እንደሚናገሩት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ የሚችሉት።
በቤተክርስቲያናችሁ ያሉ ሰዎች ሁሉ ግድየለሽ ቢሆኑም እንኳ እናንተ ግን እምነታቸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከሚያጸኑት ሰዎች መካከል ሁኑ። መዳን ከብዙሃኑ ጋር በመቀላቀል አይደለም። በእርሻ ውስጥ እና በወፍጮ ከነበሩት ውስጥ አንድ አንድ ብቻ ነው የወሰደው።
ቆም ብለን እንድናስብ የሚያደርግ ነገር ነው።
ከጥፋት ውሃ በፊት ሔኖክ የተባለ አንድ ሰው ብቻ ሳይሞት ወደ ሰማይ ተነጥቋል። ዛሬ ደግሞ ሙሽራይቱ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ወደ ሰማይ ለመነጠቅ መዘጋጀት አለባት። ስለዚህ በሕይወት ያለችዋም ሙሽራ ሞትን አታይም። የጥፋት ውሃ እኛ ከምንኖርበት ዘመን ጋር ከተነጻጸረ የሚነጠቁ ሰዎች በቁጥር ብዙ አይሆኑም።
የመጨረሻ ዘመን ስለመቅረቡ ሌላ ምልክት ደግሞ በእምነታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች በጣም ጥቂት መሆናቸው ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እና በትጋት ለማጥናት ጊዜ የሚሰጡ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው። ለምን? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ካጠኑ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነታቸው ይቀንሳል።
ይህ የግዴለሽነት ዝንባሌ የመጨረሻው ዘመን ምልክት እና ሰዎች ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸውን ፍላጎት የሚያቀዘቅዝ ባህርይ ነው።
ስለዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ ፈንታ የምንኖርበት ሁኔታ እንዲቆጣጠረን እንፈቅዳለን ማለት ነው።
ማቴዎስ 15፡8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።