ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ይናገራል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
በማቴዎስ 13 መሰረት የ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ በ7 የቤተክርስቲያን ዘመናት ተከፋፍሏል።
First published on the 8th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022በማቴዎስ ምዕራፍ 13 መሰረት የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ በ 7 የቤተክርስቲያን ዘመናት ተከፋፍሏል።
ማቴዎስ ምዕራፍ 12 ኢየሱስ ከአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች የገጠመውን ተቃውሞ ይጠቅሳል።
ምዕራፍ 13 የቤተክርስቲያን መሪዎች በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በዝርዝር ያሳያል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ነው።
የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች በሮማውያን ፖለቲካ ውስጥ ተጠላልፈው ነበር። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም እያደገች ስትሄድ በአውሮፓ ፖለቲካ ውስጥ ገባችበት። እረፍት የሌላቸው የአውሮፓ ሕዝብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወከሉት በባሕር ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤ ይህንንም ያደረገው በምድር (ጻድቃን) እን በባሕር ማለትም በሁከት እና በአመጽ ውስጥ ባሉት ሕዝብ መካከል ያለውን የማያቋርጥ ውጥረት ለማሳየት ነው።
ማቴዎስ 13፡1 በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤
ኢየሱስ ከቤት የወጣው የወደፊቱን የቤተክርስቲያንን እድገት ወደ አደባባይ እንደሚያወጣው በምልክት ለማሳየት ነው። ስሕተት ቤተክርስቲያንን እንዴት እንደጎዳት እና ተጽእኖ እንዳደረገባት ማየት እንድንችል ይፈልጋል።
የባሕር ዳርቻ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው። የባሕር ዳርቻ በምድር እና በባሕር መካከል የሚለይ መስመር ነው።
ባሕር አመጸኞችን እረፍት የሌላቸውን አዲስ ከመጣው ፋሽን፣ ብዙዎች ከተከተሉት አስተምሕሮ፣ እና ከፖለቲካው ሁሉ ጋር አብረው የሚባክኑ ሐጥያተኛ ሕዝቦችን ይወክላል። በባሕሩ ዳርቻ ያለው አሸዋ በነፋስ እና በተለያዩ የተፈጥሮ ኃይላት አማካኝነት ተሰባብሮ የደቀቀ ዓለት ነው። ክርስቶስ ማለትም ቃሉ ዓለታችን ነው። አማኞች ከክርስቶስ ነው ዳግም የሚወለዱት ስለዚህ የቃሉ (የመጽሐፍ ቅዱስ) አካል ሆነው ይኖራሉ። ዳግም በመወለድ ከመድሃኒታችን ዓለት ተቆርጠን መውጣት አለብን።
1ኛ ቆሮንቶስ 10፡4 ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
ስለዚህ በባሕሩ ዳርቻ ያለው አሸዋ ጻድቃንን ይወክላል። የባሕሩ ዳርቻ የባሕሩን ወሰን ይወክላል። እግዚአብሔር ባሕሩ (ሐጥያተኞች) ጻድቃንን ለማጥፋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከተመደበላቸው ድንበር (በባሕሩ ዳርቻ ካለው አሸዋ) እንዲያልፉ አይፈቅድም። ጻድቃን ክፉው አልፎ መሄድ የማይችለውን ድንበር ይወክላሉ።
የባሕር ሞገዶች ያለማቋረጥ በባሕሩ እና በአሸዋው ላይ ይፈስሳሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሞገድ በሄድ እስከሚችልበት ከፍታ ድረስ ይሄድና ወደ ውሃው ይመለሳል።
ስለዚህ የባሕሩ አሸዋ ሞገዶቹ ያለማቋረጥ የሚያደርጉበትን ድብደባ ተቋቁሞ ይኖራል። የባሕሩ ሞገዶች የባሕሩ አሸዋ ሁልጊዜ ንጹህ ሆኖ እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ኢየብ 26፡10 ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥
በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ።
ይህች ምድር የራሷ ገደቦች አላት። የምድር ቀን ርዝመቱ 24 ሰዓት ነው። ብርሃን እና ጨለማ ተራቸውን እየጠበቁ ስለሚፈራረቁ ሁለቱም የተገደበ ጊዜ አላቸው። የብሱ በባሕር ተገድቧል። ሕይወት በሞት ተገድቧል። በስተመጨረሻ ግን ብርሃን ጨለማን ለዘላለም ያጠፋዋል፤ ባሕርም አይኖርም። ሞት፣ ባሕር፣ እና ጨለማ ሌሊት በምድር ላይ ያሉ ችግሮችን የሚገልጡ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ ሁሉ ለእድገታችን አስፈላጊዎች ናቸው። ችግር፣ ሐዘን፣ ሐጥያት፣ ስሕተት፣ ዓለማዊነት፣ ወዘተ እኛን ለመፈተን፣ ለማበርታት፣ ለመቅጣት እና የምንጋደለው ባለጋራ እንዲኖረን ለማድረግ ይጠቅሙናል። ትግል የእድገት ሕግ ነው።
መሸነፍ እና መከራ የሰው ባሕርይ ጠንካራ ሆኖ ተቀርጾ የሚወጣባቸው ቦታዎች ናቸው። ከስሕተት ጋር ስናመቻምች ልፍስፍስ ሰዎችና የታላቁ መከራ ማገዶዎች ሆነን እንቀራለን። ስለዚህ የሚገጥመን ችግር እግዚአብሔር ከሕይወታችን የሚፈልገውን ቅርጽ የሚሰጠን ጊዜያዊ ሞረድ ወይም ቅርጽ ማውጫ ነው። ይህም ሁሉ እኛ በሕይወታችን ውስጥ ለራሳችን ከምንመኘው ነገር ሁሉ በላይ አስፈላጊ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 10፡13 ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
እግዚአብሔር እኛ ልንሸከም ከምንችለው በላይ እንድንፈተን አይፈቅድም።
ትልቅ መከራ ቢመጣ ለእኛ እንደ አድናቆት ነው። እግዚአብሔር ያንን ትልቅ መከራ ተቋቁመን አሸንፈን ማለፍ እንደምንችል ያምናል ማለት ነው።
ራዕይ 21፡1አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።
ፊተኛው ሰማይ ሚሌንየሙ ወይም የ1,000 ዓመቱ ሰላም ነው።
ታላቁ መከራ በአርማጌዶን ጦርነት ይጠናቀቃል፤ ከዚያ ወዲያ የሺህ ዓመቱ የሰላም መንግስት ይጀምራል። የሺህ ዓመቱ መንግስት ሲያበቃ የፍርድ ቀን ይጀምራል። የዚያን ጊዜ ባሕር እንደ ቦምብ ይፈነዳና የዚህ ሳይንሳዊ ዘመናችን በምድር ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶች ሙሉ በሙሉ ያስወግዳቸዋል፤ ቀጥሎም ባሕር እራሱ ይጠፋል። የምድር ላይኛ ንጣፍ ተቀጥሎ ይጠፋል፤ ነበልባሎቹም ወደላይ ወደ ሕዋ ውስጥ ሄደው የሰውን መንኩራኩሮች በሙሉ አቃጥለው ያጠፉዋቸዋል። በምድር ገጽ ላይ ባለው አመድ ላይ እግዚአብሔር አዲሲቷን ምድር ይሰራታል።
የፒራሚድ ቅርጽ ያለው ታላቅ ተራራ ከምድር እስከ ሕዋ ድረስ ይቆማል። ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በዚህ ተራራ ላይ ትወርዳለች። የዚህች ከተማ ራስ የዓለም ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ነው። ስለዚህ በዚህች ከተማ ለዘላለም ጨለማ አይኖርም።
ራዕይ 21፡5 በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥
ባሕር እና ጨለማ የማይኖሩበት ዘመን እየመጣ ነው።
ስሕተት እና ክፋት የተላኩበትን ዓላማ እስኪፈጽሙ ድረስ ብቻ ኖረው የሚጠፉ ነገሮች ናቸው።
ኢዮብ 14፡5 የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥
የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥
እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።
ማንም ቢሆን እግዚአብሔር ካበጀለት ዳርቻና ገደብ ማለፍ አይችልም።
የወደቀው የሰው ባህሪ ከፍጥረታዊ ስግብግብነቱና ራስወዳድነቱ መላቀቅ አለበት። እያንዳንዳችን እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ዳርቻ ውስጥ መንቀሳቀስን መልመድ አለብን። እነዚህ ዳርቻዎች እኛ እንዳንጠፋ የመጠበቅ አገልግሎት አላቸው።
ዳንኤል የግሪክ ንጉስ ታላቁ አሌግዛንደር ከምዕራብ ተነስቶ የምስራቅ ሃገሮችን እየገዛ እንደሚሄድ አውራ ፍየል ሆኖ በራዕይ አየው። አሌግዛንደር ብዕራቡን ለመግዛት የተነሳ ጊዜ ደግሞ ወደ ምዕራብ ዞሮ ይሄዳል። ራዕዩ ግን የተናገረው ከምዕራብ ተነስቶ እንደሚሄድ እንጂ ወደ ምዕራብ እንደሚሄድ አይደለም። ወደ ምዕራብ እሄዳለው ብሎ የጀመረ ጊዜ ባልታወቀ ምክንያት ሞተ። ይህም ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ እንዳንንቀሳቀስ የሚያሳየን ማስጠንቀቂያ ነው።
ሙሽራይቱ የእግዚአብሔር ቃል ዳርቻ አበጅቶላታል።
ዳንኤል 8፡5 እኔም ስመለከት፥ እነሆ፥ ከምዕራብ ወገን አንድ አውራ ፍየል በምድር ሁሉ ፊት ላይ ወጣ፥ ምድርንም አልነካም፤ ለፍየሉም በዓይኖቹ መካከል አንድ ታላቅ ቀንድ ነበረው።
በሰውነታችን ውስጥ እያንዳንዱ ሴል ወይም ሕዋስ በመጠኑ እና በአገልግሎቱ የተገደበ ነው። ካንሰር ማለት የተሰጠውን ገደብ ጥሶ የሚሄድ ሴል ማለት ነው፤ ከዚያም ለማደግ ብሎ ብቻ ያድጋል። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በተለያዩ ሰባት ዘመናት ውስጥ ክፋትና እና ስሕተትን እየተጠቀመ ይቀርጻታል፤ በስተመጨረሻም ክፋት ለዘላለም ይወገዳል። እስከዚያ ድረስ ቤተክርስቲያን በየዘመኑ የሚገጥማትን ስሕተት እየተቃወመች ማለፍ አለባት።
የባሕር ሞገድ ሁልጊዜ ቢመጣበትም በስፍራው የማይነቃነቀው የባሕር ዳርቻ ላይ ሆኖ በመስበክ ኢየሱስ ለወደቷ ቤተክርስቲያን በተሰጣት ገደብ ውስጥ እንድትቆይ መልእክት እያስተላለፈላት ነው፤ ይህም ገደብ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ደግሞም የባሕሩ ሞገድ ያለማቋረጥ በሙሽራይቱ (የባሕሩ ዳርቻ) ላይ እንደሚፈስስ እየተናገረ ነው፤ ሆኖም ሞገዱ ወደ ኋላው ይመለሳል የባሕሩ ዳርቻም ባለበት ጸንቶ ይቆማል።
ኤርምያስ 5፡22 በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።
እግዚአብሔር ለክፉው ገደብ ያበጅለታል። ክፉው እውነትን ፈጽሞ ሊያጠፋ አይችልም። አማኞች በስደት ምክንያት ሊበተኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እነርሱ ሲበተኑ እውነት አብሮአቸው በየሥፍራው ሁሉ ይሰራጫል። አማኞች በእምነታቸው ሊሰቱና ሊደክሙ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእነርሱ ቦታ ሌሎች ይነሳሉ።
ጨው መበስበስን ይገድባል። እግዚአብሔር ልጆቹን ለማዳን ብሎ የክፋትን ስርጭት ይገድበዋል። ክፋት እግዚአብሔር በፈቀደለት ቦይ ውስጥ ብቻ ነው መፍሰስ የሚችለው። እግዚአብሔር ከፈቀደለት ገደብ አልፎ መሄድም አይችልም።
(የሞንጎል ሰራዊት በወታድዊ መሪያቸው ሱቦዳይ አማካኝነት ራሺያንና ምስራቅ አውሮፓን ወረሩ። የሃጋሪ ጦር ሰራዊት ደምጥማጡ ጠፋ። ምዕራብ አውሮፓም በእነዚህ ወራሪዎች ስጋት ውስጥ ነበር ምክንያቱም ፖፑ ጀርመናዊውን የአውሮፓ ገዥ በመዋገት አቅሙን እያባከነ ነበር። ከዚያ በኋላ ኦጌዳይ የተባለው የጌንጂስ ካን ልጅ የነበረው የሞንጎል ንጉስ ካን ለ12 ዓመታ ብቻ ከነገሰ በኋላ በመጠጥ ብዛት ሞተ። ከዚያ በኋላ የኦጌዳይ ልጅ ጉዩክ ሰራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ ከአውሮፓ በመውጣት ወደ ሞንጎሊያ መለሳቸው፤ ምክንያቱም ሌላ አዲስ ንጉስ መሾም ያስፈልግ ነበር። በዚያ አሳሳቢ ወቅት አውሮፓ የዳነችው በሩቅ ሃገር ሞንጎሊያ ውስጥ አንድ ሰው በመሞቱ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ፈቃዱ አሸናፊ ይሆን ዘንድ ሁሉን እንደፈለገ ይቆጣጠራል።)
ኢሳይያስ 45፡7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
አሞጽ 3፡6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
በስዕል ውስጥ ጥልቀትን ወይም አድማስን ለመፍጠር ሰዓሊ ለጥላዎች ጠቆር ያሉ ቀለሞችን ለብርሃን ደግሞ ፈካ ያሉ ቀለሞችን ይጠቀማሉ። ብርሃን እን ጨለማ ሙሉ በሙሉ በሰዓሊው ቁጥጥር ስር ናቸው። እያንዳንዱ ጠቆር እና ፈካ ያለ ቀለም በስዕሉ ውስጥ የተሰጣቸውን ትክክለኛ ቦታ ይይዛሉ።
ፈካ ያለ ቀለም ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ ጨለም ካለ ቀለም አጠገብ ማድረግ ያስፈልጋል።
ልክ እንደዚሁ በጨለማ ኃይላት ከበድ ያለ ጥቃት እየተሰነዘረባቸው ያሉ ክርስቲያኖች መጨረሻቸው ደምቆ መታየት ነው። ለዚህ ነው ክፋት ወደሞላባቸው ጨለማ ሃገሮች ለመስበክ የሄዱ ሚሽነሪዎችን የምናከብራቸው። ብርሃናቸው በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ደምቆ ቦግ ብሎ በርቷል።
እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የባሕርይ ጥልቀትን ለመፍጠር በሕይወታቸን ላይ በጨለማ እና ፈካ ባሉ ቀለሞች ተጠቅሞ ስዕል ይስላል። ስለዚህ እኛን ለመቅረጽ መልካም እና ክፉ ሰዎች በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ አንደ መሳሪያ ያገለግላሉ። ሁለቱም ዓይነት ሰዎች ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ ናቸው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊት ክስተቶችን በተመለከተ ፍንጭ የሚሰጠን የትንቢት መጽሐፍ ነው።
ራዕይ 13፡1 በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ። አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
ይህ በጨለማው ዘመን ውስጥ በሁከት ሲኖሩ ከነበሩት የአውሮፓ ሕዝብ መካከል የሚነሳ ክፉ መንፈሳዊ አውሬ ነው።
ሰባቱ ራሶች የመጀመሪያዋ የሮም ከተማ የተመሰረተችባቸውን ሰባቱን ኮረብታዎች ይወክላሉ።
በድሮ ጊዜ ከተሞች በግምብ አጥር ይታጠሩ ነበር (ከታች ባለው ካርታ ላይ ቀዩን መስመር ተመልከቱ)።
የጁፒተር ቤተመቅደስ ያለበት ካፒቶላይን ኮረብታ የሮማ መንግስት ማዕከል ነው።
ካየሊያን ኮረብታ ላይ ደግሞ የላተራን ቤተመንግስት አለበት፤ እርሱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማዕከል ነው።
ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነዚህን ክፉ መናፍስት በመቆጣጠር በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሺ በላይ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎችን ገደለች።
እራሷን የቻለች ሃገር የሆነችው የቫቲካን ከተማ ከሰባቱ ኮረብታዎች አጠገብ ትታያለች፤ ይህም ቫቲካን ከተማ እንደ ቤተክርስቲያን በሰባቱ ኮረብታዎች ላይ የምትጋልብ አስመስሏታል።
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
ራዕይ ምዕራፍ 13 ዮሐንስ በባሕሩ ዳርቻ ቆሞ ይጀምራል። ለምን? የምዕራፍ 13 ማብቂያው የአውሬው ምልክት ሲሆን ይህም ምልክት ከሰው እና ከተሰጠው የ666 ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው። የባሕሩ አሸዋ ሊቆጠር አይችልም።
ይህም በባሕሩ አሸዋ የተመሰሉት ጻድቃን የአውሬውን ምልክት እንደማይቀበሉ ያሳያል ምክንያቱም ያ ምልክት እንደ ባሕር ሞገድ በሕዝቡ መካከል እየፈሰሰ ያልፋል፤ ባሕሩም ሐጥያተኞችን ይወክላል። በምድር ላይ ከየብስ የበለጠ ብዙ ብዙ ባሕር አለ። በተመሳሳይ መንገድ ከቅዱሳን ይልቅ በቁጥር የበለጡ ሐጥያተኞች አሉ።
ዘፍጥረት 32፡12 አንተም [ያዕቆብ]፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።
የአውሬው ምልክት በዓለም ውስጥ እንደ ሞገድ ያልፋል።
ራዕይ 13፡16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥
17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።
18 አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
ሚስጥራዊው ቁጥር 666 ነው።
ምን ማለት ነው?
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
ፍንጩን የምናገኘው ከዮሐንስ 6፡66 ነው።
ደቀመዛሙርቱ የእግዚአብሔርን ቃል ትተው ሄዱ።
የእግዚአብሔርን ቃል ትተን በራሳችን አስተሳሰብ ስንሄድ የአውሬውን ምልክት ተቀብለናል።
ማቴዎስ 15፡8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
የቤተክርስቲያን ሰዎች ያለባቸው ችግር ይህ ነው።
በብዙ ሕዝብ መካከል ሲሆኑ ደህንነት ይሰማቸዋል፤ ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባል መሆን በጣም ይፈልጋሉ።
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ትተው እየሄዱ እውነት የሚመስለውን የሰዎችን ወግ እና አስተምሕሮ ይቀበላሉ።
ዲሴምበር 25ን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጉ።
ማቴዎስ ምዕረፍ 2 ቁጥር 11 እንደሚለው ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ ገቡ እንጂ ወደ በረት ወይም ግርግም አልገቡም።
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ዮሴፍ እቤት ውስጥ አልነበረም። ኢየሱስ በግርግም ውስጥ የተኛ አራስ አልነበረም፤ በዚያ ሰዓት ኢየሱስ እቤት ውስጥ የሚኖር የሁለት ዓመት ልጅ ነበረ።
ሰብዓ ሰገልም ለኢየሱስ ስጦታ ሰጡ እንጂ እርስ በራሳቸው ስጦታዎችን አልተለዋወጡም።
እኛ በክሪስማስ በዓል ወቅት ተንጋግተን ወደ ገበያ ሄደን ለጓደኞቻችን እና ለቤተሰቦቻችን ስጦታ መግዛታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አንዳችም ተያያዥነት የለውም። ዲሴምበር 25 የክረምት አጋማሽ ነው። በዲሴምበር ወር ውስጥ እረኞች በሌሊት በጎቻቸውን ይዘው ሜዳ ላይ ሊሆኑ አይችሉም፤ ምክንያቱመ በቅዝቃዜው ይሞታሉ። በዚያ ወቅት ከባድ ብርድ እና ዝናብ አለዚይም ደግሞ በረዶ ይኖራል።
እረኞች ብቻ ናቸው ወደ በጎች ግርግም የሄዱት እንጂ ሰብዓ ሰገል አልሄዱም።
ሮማውያን ሕዝቡን በክረምቱ ውስጥ ግብር እንዲከፍሉ፤ ዮሴፍ እና ማርያምንም በረዶው ዘንቦ መንገድ መሄድ ከባድ እንዲሆን ባደረገበት ወቅት ያን ሁሉ መንገድ እንዲሄዱ ሊጠይቋቸው አይችሉም። የክሪስማስ ፖስት ካርዶችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።
ክሪስማስ የስግብግብነት እና ቁሳቁስ የመሰብሰብ ወንጌል ነው፤ ምክንያቱም ክሪስማስ የማቴዎስ ወንጌልም አይደለም የሉቃስ ወንጌልም አይደለም። ነገር ግን ብዙ ሰዎች በክሪስማስ ወቅት ገንዘብ ሲያወጡ ስለ ሐይማኖታቸው ያደረጉ መስሏቸው ብዙ አውጥተው ራሳቸውን ድሃ ያደርጋሉ። ከዚያ በኋላ ጥር ከወጪያቸው የሚያገግሙበት ደረቅ ወር ነው።
የክሪስማስ ወቅት በስሜት አስደሳች ቢሆንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ቀኑ እራሱ ከየት ነው የመጣው? በጣም ጎበዝ ፈረሰኛ የጦር ጀነራል የነበረው አረማዊው የሮማ ንጉስ ኦሬሊያን በሶስት ተከፋፍሎ የነበረውን የሮማ መንግስት አንድ አደረገው። ሶስቱን የተከፋፈሉ ግዛቶች ወደ አንድነት የማምጣቱን ሥራ በ274 ዓ.ም አጠናቀቀው፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ በመሄድ ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ የሶል ኢንቪክተስ የልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ፤ ይህም በዓል የሚከበረው የሮማ መንግስትን ወደ አንድነት መመለስ ለማሰብ ነበር። የፋርስ አምላክ ሚትራስ ልደቱ እንደዚሁ ዲሴምበር 25 ነበር። ስለዚህ ይህ ቀን እንደ ታላቅ በዓል በስፋት ተቀባይነት አገኘ (ማለትም አሕዛብ የሚጠጡበት እና እንደ ልባቸው የሚጨፍሩበት ታላቅ በዓል ሆነ)። ይህ ቀን በአሕዛብ ዘንድ በስፋት ተቀባይነት ያለው በዓል ከመሆኑ የተነሳ ክርስቲያኖችም ተሳቡበት። ይህ ቀን በጣም በስፋት ተቀባይነት ያገኘ የአሕዛብ በዓል እንደመሆኑ ብዙ ክርስቲያኖችም እየተሳቡበት ስለነበረ የበ350 ዓ.ም ልክ ፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ በ352 ዓ.ም ከመሞቱ በፊት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለክርስቲያኖች አማራጭ በዓል ፈጠረች። ዩልየስ የፀሃይ አምላክ ልደት የሚታሰብበትን ቀን ወስዶ የእግዚአብሔር ልጅ የልደት ቀን ብሎ ሰየመው። በዚህም የተነሳ ክርስትና ከአረማዊነት ጋር ተቀላቅሎ ቤተክርስቲያናዊነት ሆነ። ከተወሰኑ ክፍለ ዘመናት በኋላ አረማዊነት ከአውሮፓ ውስጥ ሲጠፋ የዲሴምበር 25 ካቶሊካዊ አከባበር ብቻ ሳይጠፋ ቀረ፤ እርሱም የክርስቶስ ልደት ተብሎ ተሰየመ። ለስሜታችን ቅርብ የሆነ የሰዎችን ልማድ ወይም አንድን ታላቅ ሰው ስለመከተል ወይም በአንድ ታላቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል መሆንን ክርስቶስን ማለትም ቃሉን ተከታይ ከመሆን የበለጠ ዋጋ እንሰጠዋለን። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉ ዝግጅቶች “ማስ” ተብለው ይጠራሉ፤ በአማርኛ ቅዳሴ እንደማለት ነው። ስለዚህ የክርስቶስ የልደት ቀን ብለው የሚያከብሩትን በዓል የክርስቶስ ማስ ይሉት ነበረ። ይህም በዓል ክሪስማስ የሚል ስም አገኘ። ከዚያ በኋላ ሰዎች ይህ በዓል ከኢየሱስ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር እንደሌለ ተረዱ። ከዚያ ወዲያ ክሪስማስ በዓል ውስጥ ክርስቶስ ተወገደና በዓሉ ኤክስ ማስ (X-mas) ሆኖ ቀረ።
ኤርምያስ 33፡22 የሰማይን ሠራዊት መቍጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።
ሆሴዕ 2፡1 የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።
ስለዚህ የባሕሩ ዳርቻ ጻድቃንን ይወክላል፤ እነርሱም እንደ ባሕር አሸዋ ሊቆጠሩ አይችሉም ስለዚህ የአውሬውን ቁጥር ወይም ምልክቱን ሊቀበሉ አይችሉም። የአውሬውን ምልክት ከመቀበል ለማምለት ብቸኛው አማራጭ በእግዚአብሔር ቃል ጸንቶ መቆም ነው።
ማቴዎስ 13፡2 እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።
ሕዝቡ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። በባሕሩ ዳርቻ የነበሩ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መቅረብ ፈለጉ። ይህም የሚያሳየን ሙሽራይቱ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቃል መቅረብ እንደምትፈልግ ነው።
ኢየሱስ በመርከብ ላይ ተቀምጦ ነበር ስለዚህ ከባሕሩ በላይ (እረፍት ከሌለው ሕዝብ በላይ) እንጂ ባሕሩ ውስጥ አልነበረም። ዓሳ አጥማጆች ከባሕር ውስጥ ዓሳ አጥምደው ያወጣሉ ይህም የሰዎችን መዳን ያመለክታል። እነዚህ ሰዎች በባሕሩ ዳርቻ ቆመዋል፤ ስለዚህ ጻድቃንን ይወክላሉ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን እያደመጡት ናቸው። ጻድቅ የመሆን ቁልፉ የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ነው።
ኢየሱስ ተቀመጠ።
ስሜታዊ ሆኖ እየሮጠ ወይም እየዘለለ እጆቹን እያወራጨ አልነበረም።
ቁጭ ብሎ ረጋ ባለ ድምጽ እየተናገረ ነበር። ስብከቱ ውጤታማ የሆነው በሚያስተላልፈው መልእከት እንጂ ስሜት ለመቀስቀስ በሚደረግ ጥረት አይደለም።
ማቴዎስ 13፡3 በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው፦ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።
4 እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የጀመረው በእግዚአብሔር ቃል ስብከት ነው።
ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ወፎቹ ደግሞ ቃሉን የሚሰርቀውን ጠላት ይወክላሉ። ቃሉን ትተው በሰው ልማድ እና ፍልስፍና ይተኩታል።
5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፥
6 ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።
አንዳንዶች መልካም አጀማመር ይጀምራሉ ግን ልምምዳቸው ጥልቀት የለውም።
ፈተና ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ይተዋሉ።
7 ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።
አንዳንዶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያድጋሉ ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ይፈልጋሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ፈንታ የቤተክርስቲያንን ልማዶች እና አመለካከት እየጠጡ ነው የሚያድጉት። ስለዚህም መድረስ የሚጠበቅባቸው ቦታ አይደርሱም።
8 ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።
9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
መልካም መሬት ጥልቀት አለው። እያንዳንዱ ዘር የራሱን ሥሮች መዘርጋት እና የራሱን አቅም መግለጥ ይችላል። ይህም የሚሆነው በቤተክርስቲያን ስሕተት እና መሃይምነት የተነሳ ባለመገደቡ ነው።
ይህ ምሳሌ በሐዋርየት መሪነት ስር የነበረውን የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል። ሐዋርያት ዘሩን ዘርተዋል፤ ዘሩም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ዘሪው (ሰባኪው) አልተወቀሰም። የተወቀሱት መሬቶቹ ማለትም የሰሚዎቹ ልብ ናቸው።
ሐዋርያት የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መሰረት የሆነውን አዲስ ኪዳንን ጻፉ።
እኛም ሁልጊዜ እነርሱ በጻፉት መልእከት ጸንተን መቆም አለብን።
13፡9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
ይህ ቃል ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ተደግሞ ተነግሯል።
ራዕይ 3፡6 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
የዚህ ስብከት ቁልፍ መልእከት ይህ ቃል ነው። ኢየሱስ ስለ ሰባቱ የቤተክርሰቲያን ዘመናት እየተናገረ ነው፤ እነርሱም እርሱ ቃን ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ሲገልጠው ልብ ብለው ማድመጥ አለባቸው።
ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የመጀመሪያው ምሳሌ ረጅም ነበር፤ ማለትም ልክ እንደ ምሳሌው ርዝመት ሐዋርያቱ በመጀመሪያው ዘመን በነበሩ ሰዓት ብዙ የእግዚአብሔር ቃል ተሰብኳል። ወፎቹ ቃሉን ነጠቁ፤ ስለዚህ ጠላቶች ናቸው ማለት ነው። ሰባኪው (ጥሩ ሰብኳል ወይም የመስበክ ችሎታ የለውም ተብሎ) አልተነቀፈም። ነቀፋው በሙሉ የመጣው የመሬቱ ዓይነት ላይ ብቻ ነው እርሱም የሰሚዎችን ልብ ይወክላል። አንድ ሰው እውነትን ሲነግረኝ በደምብ አላብራራልኝም ብለህ አታማርር። ዘሩ የተዘራበት መንገድ ምንም ችግር የለበትም። ጉዳዩ በሙሉ ያለው ዘሩ በተዘራ ጊዜ ከወደቀበት አፈር (ልብ) ጋር ነው።
ማቴዎስ 13፡10 ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ? አሉት።
ኢየሱስ በምሳሌ ተናገረ፤ ሕዝቡም አልገባቸውም። ግን ሳይገባቸው ትተውት ሄዱ።
ደቀመዛሙርቱ ብቻ ናቸው ወደ እርሱ ተመልሰው በመምጣት ማብራሪያ የጠየቁት።
ዛሬ ቤተክርስቲያኖች መረዳት የማይችሉትን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያነባሉ። ነገር ግን መረዳት ያቃታቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ብዙም የማይጠቅም ዝርዝር እንደሆነ ቆጥረው ቸል ብለው ያልፉታል። ከዚህም የተነሳ መንፈሳዊ መሃይምነታቸውን ተሸክመው ይኖራሉ።
11 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ቸልተኛ የሆነ አንባቢ እንዳይገባው ተደርጎ ነው። አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ዳግመኛ ከተወለደ በኋላ ብቻ ነው የውስጥ ዓይኖቹ በብርሃን ተሞልተው ጥቅሶችን ከጥቅሶች ጋር እያገናኘ እውነቱ ላይ ሊደርስበት የሚችለው።
እግዚአብሔርም ደግሞ በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔርን ሚስጥር የሚገልጥ መልእክተኛ መላክ አለበት።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ይህ መልአክ ወይም መልእክተኛም ነብይ ነው። ማለትም መልእክተኛው ሰው ነው እንጂ እንደ መልአኩ ገብርኤል ዓይነት ልዕለ ተፈጥሮአዊ መልእክተኛ አይደለም። ስለዚህ እግዚአብሔር ማን የመሆኑን ሚስጥር እን በ2,000 ዓመታት ውስጥ የማዳን እቅዱ ምን እንደሚመስል የሚያስተምረን እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ዓይነት በመንፈስ የተሞላ ነብይ ያስፈልገናል።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሮማውያን በንጉስ ኔሮ አማካኝነት ክርስቲያኖችን ማሳደድ የጀመሩበት ጊዜ ነበረ፤ ኔሮ የሮምን ከተማ እንደገና ለመገንባት ብሎ ካቃጠላት በኋላ ከተማይቱን ያቃጠሏት ክርስቲያኖች ናቸው በማለት ብዙዎቹን ገደላቸው። ክርስቲያኖችም በሚስጥር እና በጥቂት ሰዎች ቡድን ሆነው መሰብሰብ ግድ ሆነባቸው። ክርስቲያኖች ለአመራር ወደ ሐዋርያቱ ይመለከቱ ነበር፤ በዚያም ዘመን ሐዋርያት ያመጡት ተጽእኖ እንዲሁም የጽሑፍ መልእክቶቻቸው ሐዋርያው ዮሐንስ በ100 ዓ.ም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ በየስፍራው ተዳርሶ ነበር።
ዓላማቸውም ትልልቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎች መገንባት አልነበረም።
የሐዋርያት ሥራ 8፡4 የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ።
የአይሁዳውያን ቤተመቅደስ በ70 ዓ.ም መፍረሱ ግልጽ የሆነ ክርስቲያናዊ የአምልኮ ማዕከል እንዳይኖር አድርጓል።
በየግለሰቡ ቤት ወይም መሰብሰቢያ በተገኘበት ቦታ ወይም ቤት በሌለበት ሜዳ ላይ ይደረጉ ለነበሩ ስብሰባዎች ልዩ የሆነ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አያስፈልጋቸውም ነበር።
(The Pilgrim Church በ E H Broadbent ገጽ 3)
ነገር ግን ቀስ በቀስ የሰው ጥበብ መጽሐፍ ቅዱስን በማመን መመራትን እየተካው መጣ።
ጀስቲን ማርተር (100 – 165 ዓ.ም) የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ከግሪክ ፍልስፍና አንጻር መተርጎም ጀመረ። ደግሞም በወልድ እና የሁሉ ፈጣሪ እንዲሁም ብቸኛው እውነተኛ አምላክ በሆነው በአብ መካከል አንዳንድ ልዩነቶችን ማሳየት ጀመረ። ክርስቶስን “እውነተኛው አንዱ አምላክ” ብሎ አይጠራውም ነበር። በጀስቲን ማርተር አመለካከት መለኮታዊው ሎጎስ (ቃል) የሆነው ክርስቶስ ከአብ የተነጠለ ሌላ አምላክ ነው። ጀስቲን እንዲህ ብሎ ያብራራል፡- “ሌላ ስል በፈቃድ የተለየ ሳይሆን በቁጥር የተለየ ማለቴ ነው።” ጀስቲን ከነበረው ተጽእኖ እና ታላቅ ዝና የተነሳ የሰው አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስን እየተካው ሄደ።
ከዚያ ወዲያ ከካርቴጅ ሰሜን አፍሪካ እንደ ተርቱልያን (160 – 220 ዓ.ም) ያሉ ሰዎች ዝነኞች ሆኑና ሰዎችን በኋላቸው ማስከተል ጀመሩ። የነዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች የተባሉ ሰዎች አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስን መተካት ጀመረ። ሰዎችም ሐዋርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጻፉትን ብቻ በመጥቀስ ፈንታ የንግግር ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ቃላት መጥቀሱ ጀመሩ። የሥላሴ አስተምሮ መጀመሪያ ያስተማረው ጸሐፊ ተርቱልያን ነበረ። ስለ አብ፣ ስለ ወልድ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ “እነዚህ ሶስቱ አንድ ማንነት አላቸው ግን አንድ አካል አይደሉም” ብሎ ጻፈ። “ሥላሴ” የሚለው ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ አይደለም ግን ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ግድ የላቸውም።
ሰዎች አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው ይላሉ (ባህሪ ግን ምን ማለት እንደሆ እንጃ)። “ባህሪ” የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።
ብልጥ ሰዎች ሕዝቡን መቆጣጠር ጀመሩ።
ይህ አንድ ቅዱስ ሰውን ከምዕመናን በላይ ከፍ ማድረግ የኒቆላዊነት ሥርዓት ነው።
ብዙ አማኞች ወደ ክርስትና ሲመጡ ክርስትናን የተሻለ መዋቅር ያለው ድርጅት ለማድረግ ተብሎ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ መመሪያዎች ተዘጋጁ። ቀስ በቀስ ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሽማግሌዎች አስተዳደር እየራቁ ሄዱና የግለሰብን መሪነት ተቀበሉ።
እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች አመራር ሳይሆን በግለሰብ ቁጥጥር ስር በወደቀ ጊዜ ብዙም ሳይቆይ ጳጳስ የሚለው ቃል ትርጉሙ ተለውጥ የአንድ አካባቢ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ሃላፊ ወደ መሆን ተለወጠ። የሮማ መንግስት በየአካባቢው የአንድ ግዛት አስተዳዳሪ እንዲሆኑ የተሾሙ ፖለቲካዊ መሪዎች ነበሩት። ይህ አሰራር በቤተክርስቲያንም ተኮረጀና የቤተክርስቲያን ሰዎች የአንድ አካባቢ ቤተክርስቲያኖችን እንዲመሩ ሹመት ተቀበሉ። እነዚህ ስልጣኖች ብዙ ገንዘብ የሚያስገኙ የገንዘብ እና የስልጣን ጥማት የነበራቸው ሰዎች ለዚሁ ብለው አንዳችም ሳያፍሩ መወዳደር ጀመሩ።
ለድርጅታዊ መዋቅር ቅልጥፍና ተብሎ በመሪነት ቦታ የሚቀመጥ አንድ ግለሰብ ያስፈልጋል ተባለ።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን እየሰፋች ስትሄድ የየከተሞቹን መሪዎች የሚቆጣጠር ካርዲናል አስፈላጊ ነው ተብሎ ተሾመ። የመጨረሻውም ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ ፖፕ መሰየም ሆነ። እጅግ በጣም የተዋጣለት መዋቅር ያለው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ድርጅት ተመሰረተ በዓለምም ዙርያ ተስፋፋ። ኒቆላዊነት (ኒቆ = መግዛት፣ ማለትም ምዕመናንን መግዛት) በእግዚአብሔር እና በምዕመናን (ተራው ሕዝብ) መካከል የአሮን ዓይነት ክሕነት ማስገባት እስከዛሬ ድረስ የማይጠፋ ልማድ ሆኖ ቀረ። እንደ ሰው አመለካከት ይህ አሰራር እግዚአብሔርን ለማገልገል መልካም መንገድ ይመስላል፤ እግዚአብሔር ግን ሥርዓቱን አጥብቆ ይጠላዋል።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
አንድ ሃሳብ ለእኛ ለሰዎች ምንም ያህል መልካም ቢመስለን ሃሳቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆነ ከእግዚአብሔር ይነጥለናል።
የሆነ ሰው የተናገራቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ካመንን እውነተኛ ክርስቲያኖች አይደለንም። አምልኮዋችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሕተት የተሞላ ከሆነ ኢየሱስ አምልኮዋችንን አይቀበለውም። የምናከልከው በከንቱ ነው፤ ስለዚህ ጊዜያችንን እያባከንን ነው።
እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት እውነቱን እንድናምን ነው የሚፈልገው።
ማቴዎስ 13፡12 ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
ይህ ጥቅስ ለሙሽራይቱ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ቃል ሲሆን ለሰነፎቹ ቆነጃጅት ግን አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን እውነተኛ ምሳሌዎች እና መልእክቶች ካመንክ እግዚአብሔር ያለቋረጥ ጥልቅ እውነቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ይገልጥልሃል። ከዚህ በፊት ለመረዳት አስቸግረውህ የነበሩ ጥቅሶች ሁሉ ይገለጡልሃል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ እውነቶችን እያበራልህ ይሄዳል። ይህም ልምምድ እንደሚፈስስ የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው። እየተደጋገመ ያለማቋረጥ ይፈስሳል። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት የሰውን ንግግር ጥቅሶች እናነብ ነበር። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታችን መስመር ከያዘ በኋላ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እየተገለጡልን ይሄዳሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎች መረዳታቸው በብዙ እየጨመረ ይሄዳል።
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በሰዎች አተረጓጎም የሚተኩ ሰዎች ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እውነተኛነታቸው በማይመሰክርላቸው ጥቅሶች መካከል ተዘፍቀው ይቀራሉ፤ ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታቸው አንድ ቦታ ታስሮ ይቀራል። በተሳሳተ መንገድ በተተረጎሙ ጥቅሶች ላይ እምነታቸውን እየገነቡ በሄዱ ቁጥር መጽሐፍ ቅዱስ ከዓይናቸው እየራቀ ይሄዳል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በደምብ ያውቋቸው የነበሩ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ጭምር ይጠፉባቸዋል ምክንያቱም እነዚያ ጥቅሶች ከተጣመሙ መረዳቶቻቸው ጋር አይገጥሙላቸውም።
በስተመጨረሻ “እከሌ እንዲህ ብሏል” የሚለው አባባል “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል” የሚለውን ይተካዋል።
የሰው ንግግር ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ቦታ ሲይዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ዋነኛ መታወቂያቸው መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ይሆናል።
የሰው ንግግር እየወሰዱ የሚሰብኩ ሰባኪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው እየቀነሰ ይሄዳል።
ማቴዎስ 13፡13 ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።
ስለዚህ ኢየሱስ በምልክቶች እና በምሳሌዎች ነው የሚያስተምረው። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞችን ከሌሎች ሰዎች መካከል አጥርቶ ይለያቸዋል። የዚያኔ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው የሚስጥር መገለጥ ብቻ ነው ምሳሌዎችን ግልጽ የሚያደርጋቸው። በሰው ንግግር ጥቅሶች እና በሰው አመለካከት የሚደገፉ ሰዎች የምሳሌዎችን ትርጉም ማግኘት አይችሉም።
ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ በግሪኮች ፍልስፍና (በሰዎች አመለካከት) መሰረት እንዲተረጎም አልፈለገም፤ ደግሞም እንደ “ሥላሴ” የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላትን ተጠቅመን እውነትን ለማብራራት እንድንሞክርም አልፈለገም። ሰዎች ግን መጽሐፍ ቅዱስን ካነበቡ በኋላ የሰውን ጥበብ እና አመለካከት በመጠቀም መረዳታቸውን ያዛባሉ፤ የሰዎች አመለካከት ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በሌላ ክፍል ውስጥ ካሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አንጻር ለመተርጎም አስተዋጽኦ የላቸውም።
ማቴዎስ 13፡14 መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።
ኢሳይያስ የሰዎች አመለካከት ጥልቀት እንደሌለው እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን እውነቶች መረዳት ካለማወቃችን ጋር የመረዳት አቅማችንን እንደሚቀንሰው አስጠንቅቋል።
ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ማስተዋል ይባላል፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊ ቋንቋ ደግሞ “ቀኝ ዓይንህ” ይባላል።
ነገር ግን ይህ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ መረዳት ወይም “ቀኝ ዓይን” እንዲበራልን ከፈለግን ከየትኛውም የሰው አመለካከት እና ከየትኛውም የሰው ሥነ ጽሑፍ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን መውደድ አለብን።
ከዚያም ደግሞ የምንሰማውን ነገር በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማነጻጸር እና ጠለቅ ያለ መረዳት ማግኘት እንችላለን። ደግሞም ይህንን መረዳታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ብቻ አረጋግጠን ማጽናት መቻል አለብን።
15 በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ከባድ ሥራ ነው። ብዙ ሰዎች ለማጥናት ይሰንፋሉ።
ለመረዳት ከባድ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስን ለመረዳት መሞከር ያንን ጥቅስ ለማብራራት የሚያስፈልጉ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሁሉ ማወቅ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ጊዜ የሚፈጅ ሥራ ነው። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ መማር ጊዜ ይወስዳል።
ስለዚህ ቀለል የሚለው አማራጭ ሰዎች የተናገሩዋቸውን ቃላት መገጣጠም እና ላይ ላዩን የሆነ መልስ መቀበል ነው።
ሰነፍ ሰዎች ቴሌቪዥን እና ቪዲዮ ይመርጣሉ ምክንያቱም እነዚህ ይበልጥ አዝናኝ ናቸው። ነገር ግን ከቴሌቪዥን እና ከሬድዮ የሚገኘው መረዳት ጥልቀት የለውም።
ኢየሱስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቅድሚያ የማይሰጥ ሰው በሙሽራይቱ አካል ውስጥ እንዲሆን አይፈልግም። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም ስሕተት የሌለበት አድርገን የማንቀበል ከሆነ ኢየሱስም እኛን አይፈልገንም። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው የእውነት መመሪያችን ነው።
ስለዚህ ሰዎችን የሚያዝናኑ ሰባኪዎችና የሰው ንግግር መጥቀስ የሚወዱ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል የማይቀበሉ ሰዎችን ያዘናጉዋቸዋል።
ማቴዎስ 13፡16 የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።
ደቀመዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ሆነው ቆዩ። ሐዋርያት እንደመሆናቸው ከእግዚአብሔር ቃል መለየት አይፈልጉም። ጳውሎስ ወደ አቴንስ የሄደው ከግሪኮቹ ፍልስፍና ለመማር ሳይሆን እነርሱን ለክርስትና ለመለወጥ ነው። ሐዋርያት ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ የፋሲካ ጥንቸል እና እንቁላሎች፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናል፣ ፖፕ የመሳሰሉ ቃላትን ተጠቅመው አያውቁም። “ቤተክርስቲያን” የሚለውን ቃል አንድን ሕንጻ ለመግለጽ አልተጠቀሙበትም። ክርስቶስ በበረሃ ውስጥ እንደ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሆኖ ይመጣል ብለው አላመኑም።
ሳንሴት ፒክ አሪዞና ውስጥ ባለው የሶኖራን ትልቅ በረሃ ውስጥ ነው የሚገኘው።
ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
ማቴዎስ 13፡17 እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
ይህ ጥቅስ የሚነግረን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መገለጥ ምን ያህል በአክብሮት መመልከት እንዳለብን ነው።
ይህንን መረዳት እግዚአብሔር ከብሉይ ኪዳን ነብያት ሁሉ ሰውሯል።
ደቀመዛሙርት ይህ ሚስጥር ለእነርሱ መገለጡ ለእነርሱ ታላቅ ክብር ነው።
ይሁዳ ግን ገንዘብ እስካገኘ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን አሳልፎ መስጠት ላይ አተኮረ።
ዘመናዊ ሰባኪዎች ለስብከታቸው ገንዘብ ይከፈላቸዋል። በሰው ዘንድ ተወዳጅ ሆነው ለመቆየት የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን መካድ ግድ ይሆንባቸዋል።
ለምሳሌ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል አንድም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ነገር ግን ፓስተሮችን የሚያወግዙ ስድስት ጥቅሶች አሉ።
የመጀመሪያውን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ ኢየሱስ ቀጥሎ ያደረገው ነገር ፍቺውን ለሐዋርያት መግለጥ ነው።
ይህም ኢየሱስ ለሐዋርያቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እየገለጠላቸው እንደነበረ ያመለክታል። እነርሱ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ሙሉ በሆነው እውነት ላይ የመትከል ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ስለነበረ እውነትን መረዳት ያስፈልጋቸዋል። የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ጽንሰ ሃሳብ አይሁዶች ያልተረዱት ነገር ግን በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የታሰበ ሚስጥር ነበረ።
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ ይህንን ጥልቅ እውነት ያስተውሉ ዘንድ ዓይኖቻቸውን እየከፈተ ነበር።
አንድ ምዕራፍ ሙሉ ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሊጻፍ መቻሉ ይህ አስተምሕሮ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን ያመለክታል።
ቅዱስ ጳውሎስ ምን እንዳለ ተመልከቱ።
ኤፌሶን 2፡7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥
ጳውሎስ ወደፊት የሚመጡ ዘመናት መኖራቸውን አውቋል።
ይህንንም ሃሳብ ቁጥር 7 ላይ በመጻፍ ስለ ምን እየተናገረ መሆኑን ፍንጭ ይሰጣል።
ሰባት ዘመናት ይመጣሉ ማለት ነው።
ኢየሱስ የሰጠው ማብራሪያ የጥንቷ ቤተክርስቲያን እውነትን መረዳቷን ያመለክታል፤ ይህም የሆነው በሐዋርያቱ አገልግሎት ምክንያት ነው።
ማቴዎስ 13፡18 እንግዲህ እናንተ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
19 የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።
ወፎቹ በክፉው ተመስለዋል፤ እርሱም ዲያብሎስ ነው። እርሱ አመጣጡ በተለያየ መንገድ ቢቀያይረውም ሁልጊዜ ዓላማው አንድ ነው፤ ያውም መጽሐፍ ቅዱስን እንዳናምን ማድረግ ነው። እምነትህን ለማስረዳት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት ከተጠቀምክ በተሳሳተ መንገድ ላይ እየሄድክ ነህ።
ማቴዎስ 13፡20 በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤
21 ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፥ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።
ላይ ላዩን ብቻ የሚያምኑ ክርስቲያኖች እውነትን የሚፈልጉት የሚያመጣላቸው ጥቅም ሲኖር ብቻ ነው።
ማንኛውም ፈተና፣ በሰው ዘንድ ተቀባይነት ማጣት ወይም መስዋእትነት በእነርሱ ዘንድ ቦታ የላቸውም።
የተድላ እና የቀላል ኑሮ ወንጌልን ብቻ ነው የሚያምኑት።
የብልጽግና አስተምሕሮ።
ማቴዎስ 13፡22 በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል።
ይህ ወንጌል የታዋቂነት እና የስግብግብነት ወንጌል ነው። እግዚአብሔርን የማገለግለው ከቤተሰቦች እና ከጓደኞቼ ጋር በራሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። በራሴ መንገድ ገንዘብ የማገኝበትን ሥራ እየሰራሁና የግል ፍላጎቴን እያሳደድኩ እግዚአብሔርን አገለግላለው (ራስ ወዳድነት እና አጭበርባሪነት “ቢዝነስ” ነው የሚባሉት)።
ማቴዎስ 13፡23 በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።
ከአራቱ ዘሮች አንዱ ብቻ ነው በመልካም መሬት ላይ የወደቀው። ሶስቱ ፍሬ አላፈሩም። አንድ ከሶስት ጋር ሲነጻጸር።
አንድ አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር በሶስት አካላት ከሆነበት ሥላሴ ጋር ሲነጻጸር።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም አካባቢ ተጠናቀቀ፤ በዚያም ጊዜ የሐዋርያት ተጽእኖ እየቀነሰ ሲመጣ ብልጣ ብልጥ ሰዎች በብልጠታቸው የቤተክርስቲያንን አመራር ተቆጣጠሩ። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን የሚመራት ጳጳስ የግድ ይኑራት ተባለ። ይህም አሰራር ከመጀመሪያው ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት ትመራ የነበረበትን አሰራር ተካው።
ጳውሎስ ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት እንድትሆን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በኤፌሶን እንዴት እንደተከላት ተመልከቱ።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ጳውሎስ በኤፌሶን ያሉትን ምዕመናን እንዲመግቡ ለሽማግሌዎች ነው ሃላፊነት የሰጣቸው።
ፓስተሩን በሃላፊነት ቦታ አላስቀመጠውም።
ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ተብሎ አያውቅም።
የሐዋርያት ሥራ 20፡29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ … እኔ አውቃለሁ።
ጳውሎስ በ68 ዓ.ም አረማዊ በሆነው ሮማዊ ንጉስ በኔሮ እጅ ተገድሎ ነው የሞተው።
ከ70 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 120 ዓ.ም ድረስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የጸጥታ ዘመን ነው ምክንያቱም በዚያ ዘመን ውስጥ የተጻፈ መጽሐፍም ይሁን ደብዳቤም የለም።
ብዙ መረጃ የምናገኘው ከአይሬንየስ ነው እርሱ ግን በ130 ዓ.ም ነው የተወለደው። የተወለደበትም ዓ.ም በትክክል አይታወቅም።
ሊጽፍ በጀመረ ጊዜ የ30 ሰው ነው ብንል የጀመረው በ160 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ከ70 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 120 ዓ.ም ድረስ ስላሉት ዓመታት የምናውቀው በስማ በለው ብቻ ነው። በዚህ የተጻፉ መረጃዎች ባልነበሩበት ጊዜ ውስጥ ጴጥሮስ የሞተው ሮም ውስጥ ነው የሚል አፈታሪክ ተፈጠረ። ይህ እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ የታሪክ ሰነድ የለም። በነዚያ የጸጥታ ዓመታት ውስጥ ቀስ በቀስ አንድ ጳጳስ የአንድ ከተማ ቤተክርስቲያን ራስ መሆን ጀመረ።
ጳውሎስ ሾልከው ስለሚገቡ ተኩላዎች ተናግሮ ነበር። ይህም አዲስ አይነት የቤተክርስቲያን መሪ ነው።
ይህም መሪ ሁሉም ሰው እኔን ይከተለኝ የሚል መሪ ነው።
ጳጳስ ማለት ሽማግሌ ማለት ብቻ ነው። ነገር ግን ቀጥሎ ደግሞ እኔ ብቻ ነኝ መሪ ማለት ጀመረ። ከዚያ በኋላ ደግሞ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ አለ።
የሐዋርያት ሥራ 20፡30 ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
1965 የሰባቱ ቤተክርስቲያናት ማብራሪያ
ምዕራፍ 5 - ኒቆላውያን
እውነታው ይህ ነው፡- “ሽማግሌ የሚለው ቃል ሰውየውን ሲያመለክት፣ “ጳጳስ” የሚለው ቃ ግን የዚያኑ ሰው የሥራ ድርሻ ያመለክታል። ሽማግሌው ሰውየው ነው። ጳጳስ የሰውየው የሥራ ድርሻ ነው። “ሽማግሌ” የሚለው ቃል በፊትም ሁሌም የሚያመለክተው ሰውየው በጌታ ቤት ለብዙ ዓመታታ መቆየቱን ነው። ሰውየው ሽማግሌ የሚሆነው ስለተመረጠ ወይም ስለተሾመ አይደለም፤ ነገር ግን ከሌሎቹ አማኞች በእድሜ ስለሚበልጥ ነው። በደምብ የሰለጠነ፣ የበሰለ፣ የተማረ፣ በረጅም ጊዜ የክርስትና ሕይወት ልምዱ የተነሳ በባሕርዩ አስተማማኝ ሰው እንጂ አዲስ አማኝ አይደለም። ጳጳሳቱ ግን የጳውሎስን መልእክት አልተከተሉም፤ ከዚያ ይልቅ ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20 ውስጥ ሽማግሌዎችን ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን የጠራበትን ጊዜ ጠቀሱ። ቁጥር 17 “ሽማግላች” ተጠሩ ይልና በቁጥር 28 ደግሞ እነዚሁ ሽማግሌዎች ተቆጣጣሪዎች (ጳጳሳት) ተብለዋል። እነዚህ ጳጳሳት (ፖለቲካዊ አስተሳሰብ እና የስልጣን ጥማት እንደነበራቸው አንጥራጠርም) ጳውሎስ ጳጳሳት ወይም ተቆጣጣሪ ሲል ከአካባቢው በራሱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሽማግሌነት ከሚያገለግለው ሰው በስልጣን የሚበልጡ ማለቱ ነው ብለው እንደ ራሳቸው ፍላጎት ትርጉም ሰጡት። በእነርሱ አመለካከት ሽማግሌ በብዙ የአጥቢያ ሽማግሌዎች ወይም መሪዎች ላይ ከፍ ያለ ስልጣን ያለው ሰው ማለት ሆነ። እንዲህ ዓይነቱ ጽንሰ ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ ታሪካዊ አይደለም፤ ሆኖም ግን ፖሊካርፕን የመሰለ ሰው እንኳ ሳይቀር በዚህ አመለካከት ተሳበ።
በ70 ዓ.ም አብዛኞቹ ሐዋርያት ሞተው የጥንቷ ቤተክርስቲያን ተመስርታ ነበር።
ሐዋርያው ዮሐንስ በ100 ዓ.ም አካባቢ ሲሞት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠረዙትን 27 መጻሕፍት ከሰበሰበ በኋላ ነው የሞተው። የትኞቹ መጻሕፍት በአዲስ ኪዳን ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ለመወሰን የሚያበቃ መንፈሳዊነት የነበረው ዮሐንስ ብቻ ነበረ።
በመቅረዙ ላይ የመሃለኛው መብራት የተለኮሰው መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ዕለት የመጣ ጊዜ ነው።
እስከ 100 ዓ.ም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፈው ተጠናቅቀው በሐዋርያው ዮሐንስ አማካኝነት ተጠርዘዋል።
ቤተክርስቲያን የሚጠበቅባት የሐዋርያትን አስተምሕሮ ጸንታ መከተል እና ይህንኑ አስተምሕሮ በዓለም ዙርያ ማሰራጨት ብቻ ነበር።
ነገር ግን እንደዚያ አላደረገችም።
ጳውሎስ እና ሐዋርያት ዲያብሎስ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይጠጋ አድርገው ነበር፤ የጥንቷንም ቤተክርስቲያን ከስሕተት ጠብቀዋታል።
ከሞቱ በኋላ ግን ስልጣን የሚፈልጉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ይሁን ይላል ብለው መጽሐፍ ቅዱስን ለግል ፍላጎታቸው መጠምዘዝ ጀመሩ።
ወደ ጨለማው ዘመን እየተንሸራተቱ መግባት የጀመሩበት መንገድም የተከፈተው አንድ ሰው ራሱን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ ሲሾም ነው።
ኒቆላውያን።
ይህ እግዚአብሔር የሚጠላው መንፈስ ነው።