ማቴዎስ ምዕራፍ 11
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ የሰራቸው ታላላቅ ተዓምራት ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነው የለወጡት። እግዚአብሔር ለመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ትልቅ ቦታ ይሰጣል።
First published on the 8th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ማቴዎስ 11፡1 ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።
በመጀመሪያው ምጻቱ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለአይሁድ ብቻ እንዲሰብኩ ላካቸው፤ ለአሕዛብ እንዲሰብኩ አልላካቸውም።
ማቴዎስ 10፡5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
6 ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
እግዚአብሔር ከአሕዛብ እና ከአይሁድ ጋር ለየብቻ ነው ሥራውን የሚሰራው።
ይህንን እውነት ባለ ሰባት ቅርንጫፉ መቅረዝ በበብሉይ ኪዳን ድንኳን ውስጥ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደሚወክል ማየት እንችላለን።
ይህ ባለ ሰባት ቅርንጫፍ መቅረዝ በቤተመቅደሱ ውስጥ ካለው 12 የገጽ ሕብስት የተለየ ነው፤ አስራ ሁለቱ የገጽ ሕብስት 12ቱን የእሥራኤል ነገዶች ይወክላሉ።
ዛሬ የአይሁድ ሕዝብ አይሁዳውያን ነን ይላሉ። የሚኖሩበትን ሃገር እሥራኤል ብለው ይቆጥራሉ፤ ደግሞም እሥራኤል የአባቶቻቸው ታሪካዊ ሃገር እንደሆነች ያምናሉ። እነዚህ በዚህ ዘመን የሚኖሩ አይሁዳውያን ምንጫቸው ጥንታዊ ነው።
ማቴዎስ 10፡5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
6 ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
ዳግም ምጻቱ እየተቃረበ ሲሄድ ኢየሱስ የመጨረሻውን ዘመን ነብይ የሚልከው ወደ አሕዛብ ብቻ ነው እንጂ ወደ አይሁዶች አይልከውም።
እግዚአብሔር ሙሽራይቱን በሰማያት ወደተዘጋጀው የሰርግ ግብዣ ከነጠቃት በኋላ ነው ወደ ጥንታዊ ሕዝቡ ወደ አይሁዶች የሚመለሰው።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ አይሁዳውያን እውነትን የሚሰሙበት ዕድል ነበራቸው። ብዙዎች ኢየሱስን እና ያስተማራቸውን ትምሕርቶች በደስታ ተቀብለው ነበር።
የአይሁድ መሪዎች ግን ኢየሱስን በሕዝቡ ላይ ለነበራቸው ክብር እና ስልጣን እንደ ስጋት አድርገው አዩት።
ዮሐንስ 11፡47 እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው፦ ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋልና።
48 እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ።
በተጨማሪ ኢየሱስ ለአይሁድ ሐይማኖታዊ ነጋዴዎችም ስጋት ሆኖባቸው ነበር።
ዮሐንስ 2፡14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
16 ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።
ይህ በአገልግሎቱ መጀመሪያ አካባቢ ነበረ፤ ኢየሱስም የገንዘብ ማካበቻ መንገዳቸውን በማውገዝ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እንዲጠሉት አደረገ።
የሐይማኖት መሪዎች በእግዚአብሔር ቃል በመነገድ ይተጋሉ።
ዛሬ የቤተክርስቲያን ዓለም ታላቅ የንግድ ማዕከል ሆኗል።
የሮማ ካቶሊክ ቫቲካን ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ካሉ ድርጅቶች ሁሉ አንደኛ ሃብታም ድርጅት ሆኗል።
ከዚያ በአገልግሎቱ መጨረሻ ላይም ኢየሱስ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።
ሉቃስ 19፡45 ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤
46 እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።
ኢየሱስ ቤተመቅደሱን ከገንዘብ ፍቅር ለማጽዳት የወሰደው ይህ ሁለተኛ እርምጃውን ሲያው አሁንስ አበዛው ብለው አሰቡ።
በዚያው ሳምንት ውስጥ ኢየሱስን ገደሉት።
የፓስተሩን የገቢ ምንጭ አትንካበት።
ኢየሱስ የመጀመሪም የመጨረሻም ነው። በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ገንዘብ ለዋጮቹን ከቤተመቅደስ አባረራቸው። በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ገንዘብ ለዋጮችን እንደገና በአገልግሎቱ መጨረሻ ላይ ከቤተመቅደስ አስወጣቸው።
ይህም ከአገልግሎቱ መጀመሪያ አስከ መጨረሻው ድረስ የእግዚአብሔርን ቃል መነገጃ ለሚያደርጉ ሰዎች ኢየሱስ ምንም ጊዜ እንዳልነበረው ያሳየናል።
ዛሬ በዘመናችን ያለው ትልቅ ችግር ቤተክርስቲያን የንግድ መናኸሪያ መሆኗ ነው።
ሃብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኛለው፤ አንዳችም አያስፈልገኝም። ቤተክርስቲያኖች እርማት እንደሚያስፈልጋቸው አይቀበሉም።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
የብልጽግና ወንጌል በዚህ ዘመን በተለይም በቴሌቪዥን በኩል ዓለምን ተቆጣጥሯል።
ብዙ ገንዘብ ባገኛችሁ ቁጥር ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ሕብረት ውስጥ የሆናችሁ እና እግዚአብሔርም እየባረካችሁ ይመስላችኋል።
ማቴዎስ 11፡2 ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦
ዮሐንስ ታላቅ ነብይ እና የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ጠራጊ ነበረ። ስለ ጋብቻ እና ስለ ፍቺ ማንንም ሳይፈራ እውነቱን ይናገር ነበር። ሕጋዊ ጋብቻ የሚፈርሰው በሞት ብቻ ነው። ዮሐንስ ሔሮድስን ለምን የወንድምህን ሚስት ታገባለህ ብሎ ገሰጸው። ሔሮድስም ዮሐንስ ፍቺ እና እንደገና ማግባት ስሕተት ነው ብሎ በድፍረት ስለተናገረ ወደ ወሕኒ ቤት ጣለው።
እውነትን መናገር በሰዎች ዘንድ ጥላቻን የማትረፍ ቅጣት ያስከትላል።
ዮሐንስ ታላቅ ነብይ ስለነበረ የተወሰኑ አማኞች የእርሱ ደቀመዛሙርት በመሆን ኢየሱስን በመከተል ፈንታ እርሱን ተከትለውት ነበር።
ለእነርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ ዮሐንስ የሚናገረው ቃል በልጦባቸዋል።
ማቴዎስ 11፡3 የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው።
ዮሐንስ መሲሁ መንግስቱን ወዲያው በምድር ላይ የሚመሰርት እና ሚሌንየም የሚባለው የ1,000 ዓመቱ ሰላም ቶሎ የሚጀምር መስሎታል።
ኢየሱስ ግን እንደዚያ ዓይነት ነገር እያደረገ አልነበረም።
ስለዚህ ዮሐንስ ወደ እግዚአብሔር ቃል በመመልከት ፈንታ ሁኔታዎችን በመመልከት ትልቅ ስሕተት ሰራ።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና ታላቁ መከራ መጀመሪያ እንደሚመጡ ዮሐንስ አላውቀም።
ታላቅ ነብይ ነበረ፤ ነገር ግን ሰውም ነበረ። ሰዎች ይሳሳታሉ።
ዮሐንስ እስር ቤት ውስጥ የተጣለው እንዴት ንጉስ ሔሮድስን ይገስጻል ተብሎ ነው። ዮሐንስ ላይ የተፈጸመበት ይህ ግፍ ነው ጥርት አድርጎ ማየት ይችል የነበረውን የንስር ዓይኑን እያደበዘዘበት የሄደው።
ዮሐንስ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን መጠራጠር ጀመረ። ከዚህም የተነሳ የነብዩ ደቀመዛሙርትም ኢየሱስን መጠራጠር ጀመሩ።
ዮሐንስን በእግዚአብሔር ቃል ማረም ነበረባቸው፤ እነርሱ ግን ባለማወቃቸው ነብይን ለማረም መሞከር ሐጥያት መሰላቸው።
በኢየሱስ ማመናቸውን ለማቆም ተዘጋጅተው ነበረ፤ ምክንያቱም በዮሐንስ ንግግር ጥቅስ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ነበር፤ ይህም ስሕተት ነው።
የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ዋነኛውን ነጥብ ስትዋል። ዮሐንስ የመጣው ወደ ኢየሱስ ሊመራቸው ነበር። ዮሐንስ የመጣው ኢየሱስን ለመተካት አልነበረም።
ቀጣዩ ጥቅስ የዮሐንስ አገልግሎት በደቀመዛሙርቱ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚገባው ያስረዳል።
ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
ዮሐንስ ተልእኮው ከሰዎች መካከል ኢየሱስ የትኛው ሰው እንደሆነ ለይቶ ማሳየት ነው።
ዊልያም ብራንሐም ተልእኮው በከባዶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ በተሰወሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት አማካኝነት ኢየሱስን ገልጦ ማሳየት ነው።
ዮሐንስ 1፡36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
ዮሐንስ ክብርን ለራሱ አልወሰደም። ዮሐንስ ወደ እግዚአብሔር ቃል ማለትም ወደ ኢየሱስ ነው ሰዎችን ያመለከተው።
ዮሐንስ 1፡37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
በተገለጠው ቃል አማካኝነት እምነታችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ እያጸናችሁ ኢየሱስን ስትከተሉ የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ወንድም ብራንሐም ምን እየተናገረ እንደነበረ ተረድታችኋል ማለት የሚቻለው።
ዮሐንስ 1፡41 ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ።
ሌሎች ሰዎች ዮሐንስ ሲናገር ሰምተዋል ግን አልተረዱትም፤ ስለዚህ ዮሐንስ የተናገረውን ሰምተው ቀሩ እንጂ ኢየሱስን አልተከተሉም።
እንድርያስ በማስተዋል ነበር የሰማው። የዮሐንስ አገልግሎት ሰዎች ኢየሱስን እንዲከተሉ ማስተማር መሆኑን ገብቶታል።
እምነታችሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ድረስ ማሳየት ካልቻላችሁ ወንድም ብራንሐም ሲናገር አልሰማችሁም።
ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል ከእንድሪያስ በቀር ማንም የኢየሱስ ደቀመዝሙር አልሆነም።
ስለዚህ የሁለተኛው መንገድ ጠራጊ የወንድም ብራንሐም ጓደኛ እና ተከታይ መሆን የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል የሆነው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት እንደምትሆኑ ዋስትና አይሰጥም።
የወንድም ብራንሐምን መገለጦች ከሰሙ በኋላ ኢየሱስ በተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ተመልክተው የኢየሱስ ተከታዮች ወደ መሆን የሚሸጋገሩ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው።
ማቴዎስ 11፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤
የእግዚአብሔር ቃል ማለትም ኢየሱስ ለመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት ዮሐንስን ወደ እግዚአብሔር ቃል በማመልከት እንዲያርሙት ስልጣን ሰጣቸው። ዮሐንስ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመመልከት ፈንታ ምንም መንግስት ያለመመስረቱን ሁኔት በመመልከቱ ተሳስቷል።
ስለዚህ የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ጠራጊ የነበረው ታላቅ ነብይ እንኳ ስሕተት ሊሰራ ይችላል።
ኢየሱስ የመጥምቁ ዮሐንስን እና የደቀመዛሙርቱን ስሕተት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማመልከት ብቻ ነው ያረመው።
ኢሳይያስ 35፡5 በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።
6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈጸሙን አመለከተ። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ይመሰክር ነበር።
ማቴዎስ 11፡5 ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤
ወንድም ብራንሐምም ስለ አገልግሎቱ ትክክለኛነት ምስክር ይሆን ዘንድ ደቀመዛሙርቱን ወደ ተገለጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ማመልከት አለበት።
64-0614 አፈንጋጩ ወገን
መልአኩ እንዲህ ብሎ ነው ነው የተናገረኝ፡- “ሕዝቡ እንዲያምኑህ አድርግ።”
እኔም የእግዚአብሔርን ቃል ብንገር “እኔን እመኑኝ” ብዬ ሳይሆን “ቃሉን እመኑ” ብዬ ነው የምናገረው።
63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው
መልእክቱን በሙሉ። እመኑ እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ባታገኙት ግን አትመኑ።
ወንድም ብራንሐምም አገልግሎቱ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክት ነበር። መገለጦቹን ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥ ነበር።
64-0823 ጥያቄዎች እና መልሶች - 1
ቃሉን በሙላቱ የሚቀበሉ ሰዎች እኔ ስለ ሰበክሁት አይደለም የሚቀበሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ነው እንጂ። ቃሉን የሚቀበሉ ሰዎች ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃሉ መስክሮላቸዋል።
62-0318 የተነገረው ቃል የመጀመሪያው ዘር ነው - ክፍል 2
እንግዲህ እነዚህ የተናገርኳቸው ነገሮች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ባይስማሙ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ባይገጥሙ በሙሉ ስሕተት ናቸው።
መጥምቁ ዮሐንስ ሰው የሆነውን ኢየሱስ ለሕዝብ አሳይቱ ሕዝቡ ኢየሱስን እንዲከተሉ ነገራቸው እንጂ እራሱን እንዲከተሉ አላላቸውም።
ወንድም ብራንሐም ተከታዮቹን በተገለጠው ቃል አማካኝነት ወደ ኢየሱስ መርቷል። ከዚያም በኋላ የተገለጠውን ቃል እንድንከተል ነው ያስተማረን እንጂ ዊልያም ብራንሐምን እንድንከተል አይደለም።
ማቴዎስ 11፡6 በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ሲገስጻቸው የማይሰናከሉ ሰዎች ብጹአን ናቸው።
ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከሰው ንግግር ጥቅስ ጋር ሲጋጭ ብዙ የሜሴጅ አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ትተው የሰውን ንግግር ጥቅስ ይዘው ይቀጥላሉ።
ይህ የተሳሳተ አቋም ነው።
የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን በመከተልና እርሱን በማድመጥ ፈንታ እንዴት ትተውት እንደሄዱ ተመልከቱ።
የሜሴጅ ተከታዮችም ዛሬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የሰውን ንግግር ጥቅስ ይመርጣሉ።
ማቴዎስ 11፡7 እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን?
ኢየሱስን ትቶ ሄዶ ወደ ዮሐንስ መመለስ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ሊያደርግ ካሰበው ሃሳብ ተቃራኒ ነው።
ስለ ሁለቱ እነዚህ ሁለት ደቀመዛሙርት ሁለተኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ አናገኝም።
ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አውጥቶን የተገለጠውን ቃል እንድናምን አድርጎናል። አሁን ደግሞ ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተለይተው እየሄዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን እንዲቀበሉ እያደረጉዋቸው ነው። ለምሳሌ፡-
“ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ተናግረዋል”።
“የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ ወርዷል”።
“የ1963ቱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የጌታ ምጻት ነው”።
“ወንድም ብራንሐም ትክክለኛውና የማይሳሳተው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው”።
እስቲ እነዚህ ሃሳቦች በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ እውነት መሆናቸውን አሳዩ። አትችሉም።
ወንድም ብራንሐም ከላይ እንደተጻፈው ብሎ ተናግሮ አያውቅም።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ክርስቲያኖች በእነዚህ ሃሳቦች አያምኑም ነበር፤ እኛም ደግሞ የጥንት አባቶች ልጆች እንደመሆናችን ወደ እነርሱ እምነት መመለስ አለብን።
ማቴዎስ 11፡8 ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።
ዮሐንስ ከባድ ስሕተት ነበር የሰራው።
ዮሐንስ ለሰራው ስሕተት ኢየሱስ ወዲያው ማስተካከያ ሰጠ፤ ነገር ግን የሰራውን ስሕተት አመካኝቶ ዮሐንስን ሐሰተኛ ነብይ ብሎ አልፈረጀውም።
እንደውም ኢየሱስ ለዮሐንስ መሲሁን ለአጭር ጊዜ በአስደናቂ አገልግሎት ለማስተዋወቅ ብሎ ሕይወቱን በሙሉ መስዋእት አድርጎ ለሰጠው ጀግና አገልጋይ አድናቆቱን ገልጧል።
ዮሐንስ በአገልግሎቱ ዘመን የኖረው ኑሮ ቤተክርስቲያኖች የልብስ ፋሽን እየተከተሉ በምቾትና በዝነጣ የሚኖሩትን የድሎት ኑሮ አልነበረም።
ማቴዎስ 11፡9 ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።
ነብያት ስለ መሲሁ መምጣት ትንቢት ተናግረዋል።
ዮሐንስም እንደ ነብይ የመሲሁን መምጣት ተንብዮአል። ነገር ግን ዮሐንስ ከነብያት ሁሉ ታላቅ ነብይ የሆነው ሌሎቹ ነብያት ትንቢት ተናግረው ብቻ ሲቀሩ እርሱ ግን መሲሁን እራሱን በአካል በተገለጠ ጊዜ ማስተዋወቅ በመቻሉ ነው
ዮሐንስ የመጀመሪያው ምጻት መንገድ ጠራጊ ነበረ። ይህም ትልቅ ሃላፊነት ነው።
ማቴዎስ 11፡10 እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።
ዮሐንስ የመሲሁ መምጣት መንገድ ጠራጊ ከመሆኑም በላይ የሚያስደንቀው ነገር ደግሞ ስለ ዮሐንስ አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ትንቢት መናገሩ ነው።
ብዙዎቹ ነብያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢት አልተነገረላቸውም።
ማቴዎስ 11፡11 እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።
ስለ ዮሐንስ ግን ትንቢት ተነግሯል። ዮሐንስም መሲሁን በስጋ አይቶታል። ስለዚህ ዮሐንስ የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነብይ ነበረ። እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን መጋረጃ በቀደደ ጊዜ የብሉይ ኪዳን ቃልኪዳን በቀራንዮ ላይ አበቃ።
ነገር ግን ከኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ በኋላ የዳኑ እና በመንፈስ የተሞሉ ብቻ ናቸው የኢየሱስ ሙሽራ አካል መሆን የሚችሉት። የአንድ ሰው ሚስት ከሰዎች ሁሉ ወደ ሰውየው የምትቀርብ ሴት ነች።
ስለዚህ በሙሽራይቱ አካል ውስጥ ከሁሉ ታናሽ የሆነ ሰው እንኳ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ይቀርባል።
ማቴዎስ 11፡12 ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የሚመሰክርላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የላቸውም። ስለዚህ ሔሮድስ ፖለቲካዊ ኃይል እና ግፍ በመጠቀም ነው መጽሐፍ ቅዱስ የመሰከረለትን ዮሐንስን ወደ እስር ቤት የጣለው። ግፍ መስራት ተስፋ የቆረጠ ሰዎች የመጨረሻ እርምጃቸው ነው።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችም ሮማዊው ገዥ ጴንጤናዊው ጲላጦስ ኢየሱስን በአሰቃቂ ሞት እንዲገድል ኃይል ተጠቅመው አስገደዱት።
ማቴዎስ 11፡13 ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤
ስለ ምንድነው ትንቢት የተናገሩት? በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ውስጥ ዋነኛው ስለነበረው ስለ መሲሁ ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 1፡11 በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
የእያንዳንዱ ነብይ ሕይወት የክርስቶስን አገልግሎት በከፊል የሚያሳይ ነበረ።
ዳዊት ንጉስ እንዲሆን ተቀብቶ ነበር፤ ነገር ግን የነገሰው ጠላቱ ሳኦል ከሞተ በኋላ ነው።
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ንጉስ እንዲሆን ተቀብቶ ነበር፤ ነገር ግን ሮማዊው አውሬ ዋነኛው የእውነት ጠላት በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ ከጠፋ በኋላ በሺው ዓመት መንግስት ነው የሚነግሰው።
ትንቢት ሁሉ ለምንድነው እስከ ዮሐንስ ድረስ የተተነበየው?
ምክንያቱም ዮሐንስ በመጣ ጊዜ ኢየሱስም ስለመጣ ነው።
ሕጉ አበቃ፤ የእንስሳት መስዋእትም አቆመ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ሰዓት መጋረጃውን ቀድዶታል። የትኛውም የእንስሳት መስዋእት ከኢየሱስ ታላቅ መስዋእት ጋር ሊወዳደር አይችልም።
ከቀራንዮ በኋላ አዲስ የጸጋ ቃልኪዳን መጥቷል፤ እርሱም አዲስ ኪዳን ነው።
የአዲስ ኪዳን ቋንቋ ግሪክ የብሉይ ኪዳኑን ቋንቋ ዕብራይስጥን ተክቷል።
ከዚያ በኋላ በ1604 እና በ1769 መካከል የእንግሊዝኛው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ግሪክኛን ተክቷል፤ በዚህም ምክንያት ሚሽነሪዎች ወይም የወንጌል ሰባኪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋን በዓለም ዙርያ አስፋፍተዋል።
አሜሪካኖች ኢንተርኔትን ፈጥረው እንግሊዝኛን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አስፋፍተዋል።
ማቴዎስ 11፡14 ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።
ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ሲመሰክር ዮሐንስ የኤልያስ መንፈስ አለው ብሏል።
ኤልያስ እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷልን? የት?
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
ኢየሱስ ሲናገር ይህ ትንቢት በመጥምቁ ዮሐንስ መምጣት ተፈጽሟል አለ።
ነገር ግን እዚህ ጉዳይ ውስጥ አንድ እንግዳ ነገር አለ። ኤልያስ የሚመጣው ከታላቁ መከራ፣ ታላቁ የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን ምድርን ከማቃጠሉ በፊት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ግን ከታላቁ መከራ 2,000 ዓመታት ቀድሞ መጣ።
ወደፊት ከብዙ ዓመታት በኋላ ስለሚከሰት ነገር መናገር ለምን አስፈለገ?
ሚልክያስ 4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ይህም ሌላ እንግዳ ቃል ነው። ዮሐንስ የዚህን ጥቅስ የመጀመሪያ ግማሽ ብቻ ነው የፈጸመው።
“እርግማን” ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነገር ነው። እርሱም ለረጅም ጊዜ ጉዳቱ ቶሎ የማይጠፋ የአቶሚክ ወይም ኑክሊየር ቦምብ ጨረር ነው። በምጥምቁ ዮሐንስ ዘመን እንደዚህ ዓይነት ነገር አልተከሰተም።
ሉቃስ 1፡17 እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
አባቶች ማለት በእድሜ የገፉት የአይሁድ ትውልድ ናቸው። ልጆቻቸው ደግሞ ወጣቱ ትውልድ፣ ኢየሱስ እና ሐዋርያት ናቸው። በእድሜ የገፉት አይሁድ ዓመጸኞች ነበሩ፤ ኢየሱስ ስለ መሲሁ የተነገሩ ትንቢቶችን እንዴት እንደፈጸመ ማየትም አልቻሉም። ከኢየሱስ የተማሩት ወጣት ሐዋርያት ግን በቀራንዮ ኢየሱስ እንዴት ትክክለኛ መስዋእት እንደሆነ ማስተዋል ችለዋል። መስዋእቱ እንዴት የሐጥያትን ዋጋ እንደከፈለ፤ እንዲሁም ያ መስዋእት እንዴት ሕጉን ወደ ፍጻሜ አምጥቶ የጸጋውን ወንጌል እንዳስጀመረ መረዳት ችለዋል።
ሚልክያስ ከተናገረው ትንቢት ውስጥ ግን ሁለተኛው ግማሽ አልተፈጸመም።
ሚልክያስ 4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ወጣት የነበሩት ሐዋርያት አድገው የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች ሆኑ። እኛ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም በጨመረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን የምንኖር አማኞች ደግሞ ልጆች ስለሆንን ወደ ጥንቷ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ አለብን።
ሐዋርያቱ በአዲስ ኪዳን መጻሐፍት አማካኝነት እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ዘር ተከሉ።
ዘሩ በጨለማው ዘመን ውስጥ ተቀብሮ ሞተ።
ከዚያ በኋላ የተሃድሶው ቡቃያ በማርቲን ሉተር ዘመን አቆጠቆጠ።
የቅድስና እና የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ በቡቃያው ላይ እንደ አበባ አብቦ በዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት አማካኝነት የዘላለምን ሕይወት እስከ ምድር ዳርቻ ሁሉ በማዳረስ ፈካ።
መከር የሚሰበሰበው ዘሩ ከተክሉ ላይ ታጭዶ ሲወሰድ ነው።
ሙሽራይቱ ከዚህ ምድር ላይ ተለይታ የምትሄደው ጌታ በአየር ላይ ለመቀበል በምትነጠቅበት ጊዜ ብቻ ነው።
ይህ የሚፈጸመው የሚታጨደው ዘር መጀመሪያ በሐዋርያት ከተዘራው የእግዚአብሔር ቃል ዘር ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ብቻ ነው።
ይህ እንዴት ነው ሊሆን የሚችለው?
ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይኖራሉ፤ በእነዚህም ዘመናት ውስጥ የመጀመሪያው እውነት ይጠፋና ኋላ በመጨረሻው ዘመን ተመልሶ ይመጣል።
ማቴዎስ 17፡10 ደቀ መዛሙርቱም፦ እንግዲህ ጻፎች፦ ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
ጻፎች የሚልክያስን ትንቢት ጽፈው አስቀምጠዋል። ሚልክያስ ከመሲሁ በፊት ኤልያስ እንደሚመጣ ተናግሯል።
ስለዚህ የመጥምቁ ዮሐንስን መምጣት ትርጉም ያልተረዱት ደቀመዛሙርት እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- “መሲሁ መጥቶ ኤልያስ ግን ለምንድነው ያልመጣው?”
መጥምቁ ዮሐንስ በዚያን ጊዜ መጥቶ አልፏል። ይህን ጥያቄ በጠየቁ ሰዓት ዮሐንስ ሞቶ ነበር።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ኢየሱስ ግን ገና ወደፊት ሊፈጸም ስላለው ክስተት ነበር የሚናገረው።
ነገር ግን የሚልክያስ ትንቢት ግማሹ ገና አለመፈጸሙን በመረዳት ኢየሱስ ወደፊት በዘመን ፍጻሜ ወደ ሐዋርያዊ አባቶች ስለሚመለሰው የልጆች ልብ እየተናገረ ነበር፤ ይህም በዘመን መጨረሻ ላይ ነው የሚሆነው።
ኢየሱስ ወደፊት የተሰወሩትን የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለመግለጥ ስለሚመጣው ኤልያስ እየተናገረ ነበር። በዘመን መጨረሻ የሚነሳው ኤልያስ ሚስጥራትን ሲገልጥ ለሙሽራይቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የመረዳት አቅም ይሰጣታል።
ይህም የሚሆነው ወደፊት ነው።
ቀጥሎ ደግሞ ኢሱስ ስላለፈው የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ተናግሯል።
ስለዚህ ይህ የሚልክያስ ትንቢት የሚፈጸመው በሁለት ሰዎች አማካኝነት ነው።
ማቴዎስ 17፡12 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።
13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።
ዮሐንስ እውነትን ስለሰበከ ነው የተገደለው። የአይሁድ ሕዝብ መሪዎች ዮሐንስ ከሚልክያስ ትንቢት የመጀመሪያውን ክፍል እንደፈጸመ አላስተዋሉም።
ደቀመዛሙርት እንኳ ሳይቀሩ ይህ አልገባቸውም ነበር።
ማቴዎስ 11፡15 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
ይህ ቃል ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ተደግሞ ተነግሯል።
ራዕይ 2፡7 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደሚመጡ እና በእነዚህም ዘመናት ውስጥ መጀመሪያ የነበረው እውነት በመሃል ጠፍቶ ከዚያ ተመልሶ እንደሚመጣ ነግሮናል።
እግዚአብሔር ለአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ዘመን ያለው ሙሉ እቅድ እና ዓላማ ይህ ነው።
ወንድም ብራንሐም የመጨረሻው ዘመን ኤልያስ እንደመሆኑ ወደ ሐዋርያት አስተምሕሮ ሊመልሰን ይገባል።
ማቴዎስ 11፡16 ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ።
በአይሁድም ሆነ በክርስቲያኖች ዘንድ የሐይማኖተኛ ሰዎች ድክመት እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል እንዳለባቸው በራሳቸው አእምሮ መወሰናቸው ነው። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረነውን የራሳቸውን ሰው ሰራሽ እምነት በሕዝብ ዘንድ ያሰራጫሉ።
እግዚአብሔር ለስሜታቸውና ለግል አመለካከታቸው ደስ ብሎት ምላሽ የሚሰጥ ይመስላቸዋል።
ለነገሮች ባላቸው አመለካከት እግዚአብሔር የሚስማማ ይመስላቸዋል።
ማቴዎስ 11፡17 እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል።
እውነት ተለውጣ ከእነርሱ አስተሳሰብ፤ ማለትም ከስሜታዊ አቋማቸው ጋር አብራ እንድትሄድ ይፈልጋሉ።
እኛ ደስተኞች ከሆንን እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ደስተኛ ማድረግ አለበት።
እኛ ካዘንን ሰው ሁሉ ማዘን አለበት።
ማቴዎስ 11፡18 ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት።
መጥምቁ ዮሐንስ ከምቾት እና ከስጋዊ ድሎት የራቀ ሕይወት ነበር የኖረው። ስለዚህ ደባሪ፣ ደስታ የማይወድ ክፉ ሰው አድርገው ቆጠሩት።
ማቴዎስ 11፡19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።
ኢየሱስ ደግሞ ከዮሐንስ ይልቅ ቀለል ያለ ሕይወት ኖረ። ኢየሱስ ወይን ጠጣ፤ ከሰዎችም ጋር እንጀራ አብሮ በላ። ሆኖም የዮሐንስን ቁጥብ ሕይወት ካዩ በኋላ የኢየሱስን አኗኗር ይሻላል ብለው በመቀበል ፈንታ እርሱን ደግሞ በላተኛ እና ጠጪ ብለው ነቀፉት።
ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ ምንም ልዩነት አልነበረውም። እግዚአብሔር ምንም ያድርግ ምን እነዚህ ሐይማኖተኞች ከማጉረምረም እና እግዚአብሔርን ከመቃወም አይመለሱም።
በአጭሩ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን መቀበል አልፈለጉም።
በቤተክርስቲያናቸው በለመዱት ምቹ ልማዳቸውና ባሕላቸው ውስጥ ተደላድለው ተኝተው መቅረት ነው የፈለጉት።
ማቴዎስ 11፡20 በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦
ተዓምራዊ ኃይል ሲገለጥ አብሮት የሚመጣው ችግር ይህ ነው። በከተማ ውስጥ ያሉ ብዙ ሕዝብ ልብ ብለውም አያዩትም።
የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጆች የተረዱት ነገር አለ፤ እርሱም ውበት ትኩረትን እንደሚስብ ነገር ግን ይዞ መቆየት እንደማይችል ነው።
ተዓምራዊ ኃይልም ተመሳሳይ ውጤት ነው ያለው። ለጥቂት ጊዜ የሰዎችን ትኩረት ይስባል ስሜታቸውንም ይቀሰቅሳል። ነገር ግን በብዙ ሰዎች ላይ ዘላቂ ውጤት የለውም።
ማቴዎስ 11፡21 ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።
ኮራዚን እና ቤተሳይዳ ከገሊላ ባሕር አጠገብ ናቸው።
ኮራዚን የተጠቀሰችው ኢየሱስ ወዮልሽ ብሎ ፍርድ በተናገረባት ጊዜ ብቻ ነው።
ኮራዚን ማለት “ሚስጥራት” ነው።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ የኮራዚን ከተማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ ለሰራቸው ተዓምራት ትኩረት አልሰጡም።
በኢየሱስ ዳግም ምጻት ጊዜ ደግሞ ሕዝቡ በዊልያም ብራንሐም ለሚቀርብላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት መገለጥ ትኩረት አይሰጡም።
ቤተሳይዳ “የአደን ቤት” ማለት ነው።
የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ቸል በማለት እንዲሁም ሌሎችንም የተገለጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ቸል በማለት ቤተክርስቲያኖች ወደ መጀመሪያው ዘመን የሐዋርያት እምነት መመለስ አልቻሉም።
በዚህም ምክንያት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሐይማኖታዊ አታላይነትን በሚወክለው ነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ለሚመጣው ለክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ጥቃት ተጋልጠዋል።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ደጋን አለው ቀስት ግን የለውም። ይህም አታላይነትን ይገልጻል።
ይህ የተደራጀ ሐይማኖት መንፈስ ሕዝቡን ተቆጣጥሯል፤ ደግሞም በዲኖሚኔሽን የተከፋፈሉ መንፈሳዊ ቤቶችን በመክፈት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተሳሰባቸውንና እምነታውን ይከተሉ ዘንድ የሰዎችን ነፍስ እያደኑ ይለቅማሉ።
በ1315 ዓ.ም ፖፑ በራሱ ላይ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ጫነ፤ ይህም ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ የሰማይ፣ የምድር፣ እና አጋንንት የሚኖሩበት ታችኛው የፑርጋቶሪ ዓለም ሁሉ ገዥ አደረገው።
ነፍሳትን የምትለቅመው ዋነኛዋ ቤተክርስቲያን መገኛዋ ቫቲካን ሲሆን ይህች የካቶሊክ መናገሻ በዓለም ዙርያ 1.4 ቢሊዮን ሮማ ካቶሊኮችን ትገዛለች።
እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ፖፕ ሌላውን ፖፕ እየተካው የመጣው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጀምሮ በመጣው የስልጣነ ሽግግር ነው ይላሉ፤ በዚህም ምክንያት የፖፕ መተካካት በምድር ላይ ረጅሙ የስልጣን ሽግግር ለመሆን በቅቷል።
ከስሕተቶቻቸው ሁሉ ትልቁ ስሕተት ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት ዓለት ጴጥሮስ ነው ማለታቸው ነው።
ከዚያም ከጴጥሮስ ጀምሮ አንድ ፖፕ ሌላውን ፖፕ እየተካ እስከ ዛሬ ደርሷል ይላሉ።
ነገር ግን የሮም ጳጳስ ፖፕ ተብሎ የተጠራውና የጴጥሮስ ተተኪ መባል የተጀመረው በ400 ዓ.ም ነበር።
የአንድ ፖፕ በሌላ ፖፕ መተካካት የክርስቶስ ተቃዋሚን የሚወክለው ነጭ ፈረሰኛ በማሳሳት የሚያደርገው ግስገሳ መፈጸሙን ያመለክታል።
በ754 ዓ.ም ፖፕ እስቲቨን ዳግማዊ በሐሰት ስልጣን አለኝ ብሎ ፔፒን የተባለውን ሰው የፍራንኮች ንጉስ አድርጎ ሾመው፤ ይህን ያደረገው ፔፒን ሎምባርዶችን በጦርነት አሸንፎ ከግዛታቸው ላይ የተወሰነውን ለፖፑ እንዲሰጠው ተስማምተው ነው። ከዚያም ፖፑ ለፔፒን እንዲህ ብሎ ቃል ገባለት፡- ስትሞት ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር ይከፍትልሃል። ይህን በማለቱ ጴጥሮስን የመንግስተ ሰማያት በር ጠባቂ አደረገው። ይህም ድርጊት ፖፑን በባርቤሪያውያን ነገዶች ላይ ትልቅ ስልጣን አጎናጸፈው፤ ስለዚህ ንጉስ የሚሾምላቸው እና የመንግስተ ሰማያትን በር የሚያስከፍትላቸው እርሱ ስለሆነ ለእርሱ ጥበቃ ያደርጉለታል ደግሞም ያገለግሉታል።
ፖለቲካ ሁልጊዜ ጦርነት እና ደም መፋሰስ አያጣውም።
በጨለማው ዘመን ውስጥ ፖፑ አውሮፓን በሙሉ ሊገዛ በተነሳ ጊዜ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትም ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ትንሽ ቀረው።
ራዕይ 6፡4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
ይህ ሌላ ፈረስ ነው፤ ፈረሰኛው ግን ሌላ አይደለም። የመጀመሪያው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፈረሰኛ እራሱ የቤተክርስቲያንን ሐይማኖታዊ አታላይነት እና የፖለቲካ ግፍ በአንድነት ይዞ ይንቀሳቀስ ጀመር። ይህም ለቤተክርስቲያን ተቃዋሚዎቿን የመግደል ስልጣን ሰጣት።
ማቴዎስ 11፡22 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።
ጢሮስ እና ሲዶና የአሕዛብ ከተሞች ነበሩ ግን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የመካድ ሐጥያትን አልፈጸሙም።
ጢሮስ ማለት ዓለት ነው።
ካቶሊኮች ግን ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት ዓለት ጴጥሮስ ነው ቢሉም እንኳ ብዙ ሰዎችን እውነትን ከማግኘት አሰናክለው አስቀርተዋል።
ሲዶና ማለት ማደን ማለት ነው።
አሕዛብ ነፍሳትን እያደኑ ይይዙ ነበር።
እውነተን በሐሰት የሚለውጡ እና ተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራ የሚገፉ ቤተክርስቲያኖች ግን እውነትን ካልተቀበሉት አሕዛብ ይበልጥ የከፋ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች በሐዋርያት ዘመን የነበሩ እውነትን መልሰው የሚያመጡልንን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ አንቀበልም ብለው ገፍተዋቸዋል። ስለዚህ ስም የሌለው ሥላሴ የመሳሰሉ አስተምሕሮዎችን ይዘው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መበረዛቸውን ይቀጥላሉ።
ማቴዎስ 11፡23 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
ኢየሱስ ከናዝሬት ወጥቶ ከዚያ በቅፍርናሆም ኖረ። በዚያም ከተማ ብዙ ተዓምራት አደረገ።
የሚያሳዝነው ነገር የተደረጉት ተዓምራት በሰዎቹ ውስጥ ዘላቂ እምነት አለመፍጠራቸው ነው። ጊዜ ሲያልፍ ሰዎች ያዩትን ተዓምራት ረሱ።
ቅፍርናሆም ማለት “በጸጸት የተጠበቀች” ማለት ነው።
በመሰረቱ ንሰሐ በመግባባት መጽናናትን እናገኛለን። ከተማይቱ ግን ንሰሐ በመግባት ፈንታ ራሷን ከፍ ማድረግ መረጠች።
ከዚያ ዘመን በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ ከተማይቱ ጠፍታ ቀርታለች። እንደውም የነበረችበት ቦታ እንኳ የት እንደነበረ አጨቃጫቂ ነው።
ማቴዎስ 11፡24 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል።
በድጋሚ እንደተነገረው ቅፍርናሆም የእግዚአብሔርን ኃይል ያየች ከተማ ናት፤ ነገር ግን እራሷን የመንግስተሰማይ ደጅ አድርጋ ከፍ ከፍ አደረገች።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስልጣን የተቀበልኩት ከቅዱስ ጴጥሮስ ነው በማለት የመንግስተ ሰማይ መግቢያ ነኝ ብላ እራሷን ከፍ አድርጋለች፤ የመንግስተ ሰማይ መግቢያ ቁልፍ ያለው ብቸኛው ቅዱስ ሰው ጴጥሮስ ነው ይላሉ።
በ1302 Unam Sanctam የተባለውን ሕጋቸውን አጸደቁ፤ ትርጉሙ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም ማለት ነው። ለሮማው ፖፕ በመገዛት ብቻ ነው መዳን የሚቻለው እያሉ ያስተምራሉ።
የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ያንኑ ተመሳሳይ መንፈስ ተቀብለዋል። ከቤተክርስቲያናቸው ከወጣህ ጠፍተሃል ይሉሃል። በእነርሱ ቤት ያች ቤተክርስቲያናቸው ከፍ ያለችው የመንግስተ ሰማያት መንገድ መሆኗ ነው።
65-0220 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ስፍራ
እንዲህ ይላሉ። ሰዎች እኔጋ መጥተው እንዲህ ብለውኝ ያውቃሉ፤ ለምሳሌ አንድ ሰውዬ ከጥቂት ወራት በፊት ቴክሳስ ውስጥ አናግሮኝ ነበር። እንዲህ አለኝ፡- “አቶ ብራንሐም፤ ስምህ የእኛ ቤተክርስቲያን የአባላት መዝገብ ውስጥ ካልተጻፈ መንግስተ ሰማያት አትገባም።” ይህን አስባችሁ ታውቃላችሁ? እንዲህ ዓይነት ነገር ስትሰሙ በፍጹም አትመኑ። የሆነ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል ካልሆናችሁ በቀር ወደ መንግስተ ሰማያት የማትገቡ ይመስላቸዋል። እንደዚያ ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው። እንደዚያ ብሎ ማሰብ የክርስቶስ ተቃዋሚነት ነው። እኔ ደግሞ እንዲህ እላለው፡- ይህን ዓይነቱን መንፈስ የምታምኑ ከሆነ ጠፍታችኋል። ይህ ስለመጥፋታችሁ የሚያመለክት ግልጽ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም በዚህ አስተሳሰባችሁ የእግዚአብሔርን ሥራ ከንቱ ታደርጉታላችሁ። እግዚአብሔር በየትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስሙን አላኖረም። እግዚአብሔር ስሙን ያኖረው በልጂ በክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ያውም እርሱ እና ልጁ አንድ በሆኑ ጊዜ። እግዚአብሔርን ማምለኪያ ትክክለኛው ስፍራ ይህ ነው። ከዚህ ሌላ መሰረት ከዚህ ሌላ ዓለት የለም።
ሰዶም ሰዎችን ግብረ ሰዶማዊነት አስለመደች። ይህም ነውር ነው።
ነገር ግን የሰዎችን እምነት በመበረዝ አንድ ቤተክርስቲያን ወይም የቤተክርስቲያን መሪ ወይም ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ሰማይ ሊያስገባችሁ ይችላል ማለት የባሰ ነውር ነው።
ኢየሱስ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚበርዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም ከሚሉ ሰዎች ይልቅ ሐጥታቸው የከፋ ነው።
ራዕይ 3፡15 በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በሙሉ አንቀበልም ብላችሁ ቀዝቃዛ ሰዎች ወይም የለየለት አሕዛብ ሁኑ።
ወይ ደግሞ ትኩስ በመሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በሙሉ ፍጹም እውነት አድርጋችሁ እመኑ።
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
የትኩስ እና የበራድ ድብልቅ። የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ማመን እና የተወሰኑትን አለመቀበል። እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመለወጥ መበረዝ።
ብዙ ክርስቲያኖች ዛሬ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት ብለው ያምናሉ። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የሌለበት ፍጹም ትክክል መሆኑን አያምኑም።
ለመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነት ክፉ አመለካከት ሊኖረን አይገባም።
የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር አፍ ነው የሚወጣው። ስለዚህ በቃሉ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ካልን እርሱ ደግሞ ተጸይፎን ከአፉ አውጥቶ ይተፋናል።
ማቴዎስ 11፡25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤
የሰው ጥበብ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መግለጥም ሆነ ማብራራት አይችልም።
በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተምረው ዲግሪ የጫኑ ሰዎችም ሆኑ በስነ መለኮት ትምሕርት ቤቶች ዲግሪ የተመረቁ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መረዳት አይችሉም።
ሕጻናት ወደዚህ ዓለም ተወልደው ሲመጡ ስለዚህ ዓለም ለማወቅ አእምሮዋቸው የተከፈተና ዝግጁ ነው። ስለዚህ ወላጆቻቸው የሚሉትንና የሚያደርጉትን ይኮርጃሉ።
ልክ እንደዚሁ በዘመን መጨረሻ ላይ ያሉ መንፈሳዊ ልጆችም አዲስ ኪዳንን ወደ ጻፉ ሐዋርያዊ አባቶቻቸው በሚመለሱበት ጊዜ እነርሱ የተናገሩትንና ያደረጉትን በመከተል ነው የሚመለሱት።
እውነተኛዋ ሙሽራ ከሐዋርያዊ አባቶች ለመማር እና እምነታቸውን ለመከተል ዝግጁ ናት።
ማቴዎስ 11፡26 አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
ሁሉም ነገር ከእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ጋር መጋጠም አለበት።
የእውነተኛው ቃል ዘር በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከተተከለ በኋላ በጨለማው ዘመን ውስጥ ሞቶ ተቀበረ።
ከዚያ በኋላ በሉተር ተሃድሶ ጊዜ እንደገና አቆጠቆጠ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዘሩ አድጎ መጀመሪያ የተዘራውን ዓይነት ፍሬ ለመከር እስከሚያፈራ ድረስ እግዚአብሔር እየተንከባከበው ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፉ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው የክርስቶስ ሙሽራ አካል የሚሆኑት።
በ2,000 ዓመቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ኢየሱስ ሙሽራይቱን ለራሱ እያዘጋጃት ነው። ኢየሱስ ሙሽራይቱን ወደ ራሱ ወደ ሰማይ ነጥቆ ሊወስዳት ይናፍቃል፤ ከዚያ በኋላ ሰባቱን ማሕተም ይፈታና በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ስለተከናወነው ነገር ሁሉ በጥልቀት ያስረዳታል።
መጀመሪያ ግን ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት የተወሰነ መረዳት ወይም መገለጥ ሰጥቷታል።
በዚህም መንገድ እግዚአብሔር ከእርሱ አስተሳሰብ ጋር ማን እንደተስማማ እና እቅዶቹን ማን በፍቅር እንደተቀበለ ይለያል።
የዊልያም ብራንሐምን መገለጦች ትክክለኛነት መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ መርምሮ ማረጋገጥ የሙሽራይቱ አካሎች ከሌሎች ሰዎች የሚለዩበት ማጣሪያ ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ሙሽራይቱ ደግሞ የሙሽራው አካል ናት።
ስለዚህ ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው የምታምነው።
ሌሎቹ የዳኑ ነገር ግን ከቤተክርስቲያናቸው ልማድ እና አመለካከት ጋር የታሰሩ ክርስቲያኖች የበጉ ሰርግ እራት ግብዣ ከሚያመልጣቸው ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ጋር ሕብረት የሚያደርጉት።
ማቴዎስ 11፡27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
እግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ውስጥ በአካል የሚኖረው ወሰን የሌለው ታላቅ መንፈስ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ኢየሱስ በሰውነቱ እግዚአብሔር አይደለም። ኢየሱስ እግዚአብሔር የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ውስጥ በአካል ስለሚኖር ነው።
ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር መሆኑን ካልተገነዘብን በቀር እግዚአብሔርን አብንም ሆነ የእግዚአብሔርን ልጅ መረዳት ወይም ማወቅ አንችልም።
የእግዚአብሔር ልጅ አካሉ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከኖሩ ክርስቲያኖች የተሰራ መሆኑን ካልተገነዘብን በቀር የእግዚአብሔርን ልጅ በትክክል ልናውቀው አንችልም።
ባለፉት 2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያሉትን የተወሳሰቡ ጉዳዮች በትክክል መረዳት የሚችለው የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። የዚህ ታላቅ እቅድ ዝርዝሮች እኛ መረዳት ከምንችለው በላይ ናቸው።
በ2,000 ዓመታት ውስጥ የነበረችው ቤተክርስቲያን ናት የክርስቶስ አካል የምትሆነው።
በዚህም ምክንያት ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።
በተጨማሪም ክርስቶስ የቤተክርስቲያን አዳኝ ነው ምክንያቱም እኛን ከእርሱ ሌላ ሊያድነን የሚችል የለም።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚካተቱትን ሰዎች በሙሉ የሚያውቀው እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለውን ሃሳብና እቅድ መረዳት የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።
በ2020 ዓ.ም የተነሳው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያሳየው በዓለማችን ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ነገሮች በፍጥረታዊ ዓይናችን ተመልክተን ለመረዳት ምን ያህል እንደሚከብዱ ያሳየናል።
ይህም በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እየተከሰተ ያለው ነገር ለእኛ ለሰዎች መረዳት ከምንችለው በላይ በጣም ጥቅልቅ እና የተወሳሰበ መሆኑን ያስገነዝበናል።
ስለዚህ ከታላቁ መከራ እንድናመልጥ እና ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ሕብረት ውስጥ እንድንሆን ምን ማድረግ አለብን?
ፊልጵስዩስ 2፡12 ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጳውሎስ በሕይወት ሳለ ለጳውሎስ ትታዘዝ ነበር።
እኛ ደግሞ ጳውሎስ በምድር በሌለበትም ሰዓት እንኳ ለጳውሎስ መታዘዝ አለብን።
“በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ”።
ይህ ከሲኦል ስለ መዳን አይደለም የሚናገረው። በስራ መዳን አንችልም።
ይህ ቃል የሚናገረው በምናደርገው እና በምንናገረው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆን ከሚመጣው ታላቅ መከራ ስለ ማምለጥ ነው።
መሸሸጊያችን የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ኢየሱስ ነው፤ ስለዚህ እርሱን መፈለግ እን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ እርሱን መከተል አለብን።
ማቴዎስ 11፡28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
እርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ስለተገለጠ ሁላችንንም ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይጠራናል።
የወንድም ብራንሐም ትክክለኛ አገልግሎቱ ይህ ነበረ። አገልግሎቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት አማካኝነት የኢየሱስን እውነት መግለጥ ነው።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ማሕተሞቹን ይወስዳቸውና ይፈታቸዋል፤ ከዚያም ለሰባተኛው መልአክ ያሳየዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሚስጥራት መግለጥ የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት ነው። ስለዚህ አሁን የቤተክርስቲያን ዘመናትን ሁሉ በማየት በታሪክ ጭምር ይህንን እውነት እናረጋግጣለን።
የእግዚአብሔርን ሚስጥር መረዳት ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ማወቅን ያጠቃልላል።
ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከአይሁዳውያን በላይ አባት ወይም አብ ሆኖ የተገለጠው አምላክ ነው።
ኢየሱስ በአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ከአይሁዳውያን ጋር አብሮ የነበረው ወልድ ነው።
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
ኢየሱስ አሁን ደግሞ በእያንዳንዱ ዳግመኛ በተወለደ ክርስቲያን ውስጥ በተወሰነ መጠን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ዮሐንስ 14፡17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
በቅዱሳን ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቀስ በቀስ የኢየሱስን አካል ወይም ድንኳን ገንብቷል።
ውጤታማ ልንሆን የምንችልበት ብቸኛው ስራ በዘመናችን መንፈሳዊ አካሉን ለመገንባት መተባበር ነው።
ከሐጥያት ያረፍንበት እረፍታችን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው፤ እርሱም ሊያሳርፈን የሚችለው ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራን ከፈቀድንለት ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ማቴዎስ 11፡29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ከኢየሱስ ጋር አብረን መጠመድ አለብን አንጂ ከሆነ ሰው ወይም ቤተክርስቲያን ጋር አይደለም የምንጠመደው።
በኢየሱስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመራ ከአለማመን እና ከሐጥያት እውነተኛ እረፍት እናርፋለን።
ኢየሱስ ግን የዋህ እና ትሑት ነው።
ስለዚህ ከእርሱ ጋር በአንድ ቀምበር ከተጠመድን እኛም የዋህ እና ትሑት እንሆናለን።
ትዕቢት እና ኩራት ቦታ የላቸውም።
ሁሉን እናውቃለን የሚሉ ሰዎችም በጌታ ዘንድ ቦታ የላቸውም። ከሰዎች ለመብለጥ የሚፈልጉ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም።
ማቴዎስ 11፡30 ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።
ከኢየሱስ ጋር አብሮ መጠመድ ማለት የሸክማችንን ብዙውን እርሱ ይሸከማል ማለት ነው። እኛ እንድንሸከም የሚተውልን ትንሽ ሸክም ከባድ አይደለም።
ኢየሱስ የገለጠልን እውነት የትኛውም ዓይን ሕግን ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረት ለሰዎች አስጨናቂ ሸክም እንደሚሆን ነው።
ሕግን ለመጠበቅ መሞከር በሰዎች ላይ ከባድ “የጭቆና ቀምበር” ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም የትኛውንም ያህል ሕግን ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረት በእኛ ሐጥያተኝነት እና በእግዚአብሔር ቅድስና መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት አይችልም።