ማቴዎስ ምዕራፍ 06



ጊዜያዊ ከሆኑ ሁኔታዎቻችን ይልቅ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት ላይ ነው ትኩረታችንን ማድረግ ያለብን።

First published on the 7th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳትን አየ። እነርሱም አንበሳ፣ ጥጃ ወይም ትንሽዬ በሬ፣ ሰው፣ እና ንስር ናቸው።

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 … በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

እነዚህ አራት እንስሳት በሐዋርያት ሥራ ዙርያ ያሉትን አራቱን ወንጌሎች ይወክላሉ። የሐዋርያት ሥራ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት አማካኝነት የሰራቸውን ሥራዎች ነው የሚዘግበው።

 

 

እግዚአብሔር ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባት ሰስት እርምጃ ተራምዷል።

1. በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር እንደ አብ ሆኖ ከአይሁዶች በላይ ነበር።

2. እንደ ወልድ ወይም ልጅ እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር (አማኑኤል፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር) ነበር ምክንያቱም የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ በአካል ተገልጦ ይኖር ነበር (ቆላስይስ 2፡9)።

3. እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ለነበረው እቅድ የመጨረሻ ፍጸሜው እንደ መንፈስ ቅዱስ በአማኞቹ ውስጥ ሆኖ መኖሩ ነው።

በአማኞች ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነውጥ በሞላባቸው 2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በብዙ ሐይማኖታዊ አሳሳችነት፣ ፖለቲካው ውዥምብር እና ሰይጣን ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በገንዘብ ብዛት በሚፈታተንበት ጊዜ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ልጆች ይመራቸዋል።

ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ እና ዮሐንስ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉትን አራት ክቡር ዘበኛዎች ይወክላሉ፤ እነርሱመም አንበሳ፣ ጥጃ፣ ሰው፣ እና ንስር ናቸው።

እነርሱም ለቤተክርስቲያን እንዴት ማመን እንዳለባት እና በሰዎች የተፈጠሩ የቤተክርስቲያን ዲኖሚኔሽኖችን ሳይሆን የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት እንዴት መኖር እንዳለባት ያሳዩዋታል።

የመጀመሪያው ወንጌል ማቴዎስ የይሁዳ ነገድ አንበሳ የሆነውን ኢየሱስን የአንበሳነቱን መገለጫዎች ያሳየናል።

አንበሳ የአራዊት ሁሉ ንጉስ ነው።

ማቴዎስ የሚያስተምረን ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ እምነታችንን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንዳለበት ነው።

ንጉሱ በስልጣን ከሁሉ በላይ ነው።

ኢየሱስ ቃሉ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገለጣል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አስተሳሰብ ያሳየናል።

ዛሬ ኢየሱስ በምድር ላይ ቢኖር ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ብቻ ይናገር ነበር።

ስለዚህ ማቴዎስ የአይሁድ ንጉስ ሆኖ የተወለደውን ኢየሱስን ነው የሚያሳየን።

ማቴዎስ 2፡1 … እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ …

2 የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? … እያሉ … መጡ።

ይህ ሔሮድስን አስደንግጦታል። ሔሮድስ ከእስራኤል በስተደቡብ ከምትገኘው ኤዶምያስ ከምትባል ሃገር የመጣ ሰው ነው። አባቲ አንቲፓተር ለዩልየስ ቄሳር ብዙ ውለታ ውሏል፤ በዚህም ምክንያት ሔሮድስ በሮማውያን ገዥዎች አማካኝነት በአይሁዳውያን ላይ በግድ ንጉስ ተደርጎ ተሹሟል።

እርሱ እያለ እውነተኛው ንጉስ ደግሞ ተወለደ።

ሰው ያነገሰው የውሸት ንጉስ ሔሮድስ ኢየሱስን ሊያጠፋው ፈለገ ምክንያቱም ኢየሱስ እውነተኛው ቃል ነው።

ስለዚህ የኢየሱስ ሕይወት ኢየሱስ ትንቢትን በሙሉ በሚፈጽምበት ሰዓት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እና የሐይማኖት መሪዎችን ለመጥቀም በተፈጠሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የሰው ድርጅቶች እንዲሁም እምነቶች መካከል የሚደረግ የማያቋርት ግጭት ነው።

በአገልግሎቱ መጨረሻ ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ ኢየሱስን ማስገደል ግድ ሆነበት ምክንያቱም ኢየሱስ የአይሁድ ካሕናት እና የሐይማኖት መሪዎች ይዘውት ለነበረው ቦታ ስጋት ሆኖባቸው ነበር።

ስለዚህ ኢየሱስ የምድር ላይ ሕይወቱ በሙሉ በራሱ ማለትም በቃሉ እና ለራሳቸው ጥቅም (በተለይም ለገንዘብ እና ለስልጣን) በቆሙ የሐይማኖት መሪዎች መካከል የተደረገ መራራ ትግል ነበረ፤ ይህም የሆነው የሐይማኖት መሪዎች በሐይማኖታዊ ድርጅት ውስጥ የነበራቸው ቦታ ብዙ ገንዘብ ያስገኝላቸው ስለነበረ ነው።

ሊቀካሕናቱ ቀያፋ እንዲህ አለ፡-

ዮሐንስ 11፡48 እንዲሁ ብንተወው [ኢየሱስን] ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ።

ተራው ሕዝብ እድል ቢያገኝ በኢየሱስ ከማመን ወደ ኋላ እንደማይል ቀያፋ አውቋል። ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡ በኢየሱስ ላይ ያላቸውን እምነት ለማጥፋት ቆርጠው ተነሱ።

ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡ በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸውን እምነት ለማጥፋት ተግተው እየሰሩ ነው።

ዘመኑ አልፎበታል፤ ብዙ ስሕተቶች አሉበት፤ ደግሞም እርስ በርሱ ይጋጫል ይላሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ትክክል መሆኑን አይቀበሉም።

ቀያፋ በጣም ያሳሰበው የአይሁድ ሕዝብ መጥፋት ሳይሆን የራሱን የሊቀ ካሕናትነት ስልጣኑን ላለማጣት ነው የተጨነቀው።

ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ከሁሉ የበለጠው ክፋት ይመጣ የነበረው ከሐይማኖት መሪዎች ነው።

ይህ እውነት በደቀመዛሙርቱ መካከል እንኳ ሳይቀር ታይቷል፤ ለምሳሌ ሰይጣን ሐዋርያ እና የቤተክርስቲያን መሪ በሆነው ይሁዳ ውስጥ ገብቶ ነው ኢየሱስን የመግደል እቅዱን የፈጸመው።

ሉቃስ 22፡2 የካህናት አለቆችና ጻፎችም እንዴት እንዲያጠፉት ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።

3 ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤

4 ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ።

5 እነርሱም ደስ አላቸው፥ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ።

የሐይማኖት መሪዎች ውድቀት መንስኤው የገንዘብ ፍቅር ነው።

የሐይማኖት መሪዎች የቤተክርስቲያናቸውን አመለካከት እንዲለፈልጉ ነው ገንዘብ የሚከፈላቸው።

ኢየሱስን እንደ ንጉስ አድርጎ በማቅረብ ማቴዎስ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ስልጣን ሁሉ የኢየሱስ መሆን እንዳለበት ይናገራል።

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር ከፈለጉ ሰዎች ሁሉ ለኢየሱስ መገዛት አለባቸው።

ነገር ግን ስልጣንና ገንዘብ የሚወዱ መሪዎች ሰዎችን አሳስተው የሰው ተከታዮች ያደርጓቸዋል።

እነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት እስኪሞቱ ድረስ ብቻ ሲጠባበቁ ነበር። አብዛኞቹ ሐዋርያት እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ሞቱ።

“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ የኤርምያስ ትንቢት ውስጥ ስድስት ጊዜ በእግዚአብሔር ተወግዟል።

ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሰዎች አመራር እንዲህ ዓይነት አደጋ ነው ያለው።

ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ጠራቸውና በዚያ ከተማ ያለችዋን ቤተክርስቲየን በከተማይቱ ላሉት ሽማግሌዎች በአደራ ሰጠ እንጂ ለአንድ ግለሰብ አልሰጠም። ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመራ ብሎ አንድ ፓስተር መርጦ አልሾመም።

ጳውሎስ ለኤፌሶን ሽማግሌዎች እንዲህ ብሎ ተናገረ፡-

የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥

30 ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

ሰውን እንደ መሪ አድርጎ መከተል። በቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰራው ትልቅ ስሕተት ይህ ነው።

ሆኖም ግን በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ካለፉ ነውጦች ሁሉ በኋላ በስተመጨረሻ ኢየሱስ የንግስና ስልጣኑን በምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲሁም በሰማይም ጭምር ይገልጠዋል።

በወንጌሉ መጨረሻ ላይ ማቴዎስ እንዲህ ብሏል፡-

ማቴዎስ 28፡18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።

19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ … እያስተማራችኋቸው

ደቀመዛሙርቱ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ስልጣን ሁሉ የኢየሱስ ብቻ መሆኑን ለአሕዛብ ሁሉ እንዲያስተምሩ ነው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤

ስለዚህ ለደቀመዛሙርት የተሰጣቸው ሃላፊነት አዲስ ኪዳንን መጻፍ እና አማኞች ደግሞ መማር ያለባቸው ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

ምክንያቱም የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አስተሳሰብ ይነግረናል።

ብቸኛው ታላቅ ስልጣን የኢየሱስ ነው።

ኢየሱስ የተናገረውን ማንም ማሻሻል አይችልም።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

የኢየሱስ ልብ ወይም መንፈስ በውስጥህ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ታምናለህ እርሱን ብቻ ትናገራለህ።

ገላትያ 1፡8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

የትኛውም የሐይማኖት መሪ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል የሚለውጥ ከሆነ ከባድ ችግር ውስጥ ነው።

ስለዚህ ማቴዎስ የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ ታላቁ ንጉስ መሆኑን አስረግጦ ይነግረናል።

በዚህ መንገድ የመጀመሪያው ትምሕርታችን ሰዎች የራሳቸውን መልካም ሥራ ማወጅ እንደሌለባቸው ነው።

ለድሆች ብትሰጡ መልካም ሥራ ነው ነገር ግን ማንም እንዳያውቅ አድርጉ።

ማቴዎስ 6፡1 ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።

ምጽዋት ለድሆች በነጻ የሚሰጥ ገንዘብ ወይም ሌላ ዓይነት ስጦታ ነው።

ለድሆች ደግ ከሆናችሁ ሰዎች ወደናንት ይመለከታሉ፤ በናንተ ላይ ይደገፋሉ። ወደናንተ በሚመለከቱበት ሰዓት ዓይናቸውን ከኢየሱስ ላይ ያነሳሉ።

በስተመጨረሻ ማንኛውንም ቁሳቁስ እና ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የናንተ ተከታዮች ይሆናሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምረው ኢየሱስን መከተል ያቆማሉ።

ማቴዎስ 6፡2 እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

ሰዎች በሌሎች ሰዎች መወደስ ይወዳሉ። ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ምስጋና ለማግኘት ሲሉ ለተቸገሩ ሰዎች ደግ ሊሆኑላቸው ይችላሉ።

መልካም ሥራ በሰራህ ጊዜ “መለከትህን የምታስነፋ” ከሆነ የሰዎችን ትኩት ወደ ራስህ ትስባለህ።

ከእግዚአብሔር ዘንድ ሽልማት ወይም ዋጋ ማግኘት የምትችለው የሰዎችን ትኩረት ወደ ኢየሱስ የሳብክ እንደሆነ ነው።

ከሰዎች ፊት በተሰወርክ ጊዜ ብቻ ነው ትኩረታቸው ወደ ኢየሱስ እንዲሆን ማድረግ የምትችለው።

ይህ ዲጂታል የቴክኖሎጂ ዘመናችን በሁለት ቁጥሮች ነው የሚሰራው፤ እነርሱም 1 እና 0 ናቸው።

ስለዚህ በሕይወትህ ውስጥ 1 ቁጥር ማን መሆን እንዳለበት መወሰን አለብህ። እራስህ ወይም ኢየሱስ።

ኢየሱስ በሕይወታችን ቁጥር 1 ከሆነ ለእኛ የሚቀርልን ቁጥር 0 ብቻ ነው።

ነገር ግን በሕይወቴ ውስጥ እኔነት 1 ቁጥር ከሆነ ለኢየሱስ የሚቀርለት ቁጥር 0 ብቻ ነው።

ኢየሱስ የሁሉ ነገር ጌታ ካልሆነ የምንም ነገር ጌታ አይደለም።

በልብህ ውስጥ እርሱ ቁጥር “አንድ” ካልሆነ ትቶህ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርሱ የትኛውም ክፍል ውስጥ ሁለተኛው አካል ተብሎ አያውቅም።

 

 

ጳውሎስ በትክክል ብሎታል፡-

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 … ዕለት ዕለት እሞታለሁ።

የሰዎችን ትኩረት ወደ እሬሳ መሳብ አንችልም። እሬሳ ሰዎች እንዳያዩት ተደርጎ ነው የሚቀበረው።

እሬሳ ሰብዓዊ መብት የለውም። ያለው መብት መቀበር እና ከሰው እይታ መውጣት ብቻ ነው።

ለእራሳችን ከሞትን በሰዎች ዘንድ የመታየት ፍላጎት አይኖረንም።

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡-

ዮሐንስ 12፡32 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።

ኢየሱስን ብቻ ከፍ ብናደርገውና ስለ ራሳችን ባንናገር ሰዎችን ወደ እርሱ እንስባለን። በዚህ መንገድ ብቻ ነው የእግዚአብሔርን መንግስት ማገልገል የምንችለው፤ ማለትም ሰዎችን ወደ ኢየሱስ በማመልከት። ሰዎችን ወደ ራሳችን ማመልከት የለብንም።

ማቴዎስ 6፡3 አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤

ሰዎችን በገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ይህንን ድርጊትህን ሚስጥር አድርገህ ያዘው። ሰዎች ደግ መሆንህን ካወቁ ለራሳቸው ጥቅም ብለው ወዳጃቸው ያደርጉሃል፤ ይከተሉሃል። ሰዎች ሁልጊዜ ገብጋቦች ናቸው። ነገር ግን ወዳንተ በሚመለከቱ ሰዓት በኢየሱስ ላይ መደገፋቸውን ያቆማሉ።

ማቴዎስ 6፡4 በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።

ከሰዎች አንዳችም ጥቅም አገኛለው ብለህ ሳታስብ ሰዎችን እርዳቸው። በፍጹም ምስጋናም ዝናም አትፈልግ።

እግዚአብሔር በወደደው መንገድ እንዲባርክህ እንዲሸልምህ ሁሉን ለእርሱ ተውለት።

በሚስጥር መስጠትን እና በምላሹ ምንም ተስፋ አለማድረግን መለማመድ አለብን። የዚያን ጊዜ ብቻ ለራሳችን ጥቅም ለማግኘት ብለን ሳይሆን በእውነተኛ ፍቅር ሰጥተናል የምንባለው።

እግዚአብሔር የሰዎች የራስ ፈቃድ ውስጥ መስራት አይፈልግም።

እኔነት መሞት አለበት። “እኔነታችን” ለአገልግሎት ክፍያ ወይም ጥቅማጥቅም መጠየቅ የለበትም።

የእግዚአብሔር መንግስት አይነገድበትም።

ማቴዎስ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበረ።

ማቴዎስ ሰዎች በዓልም ውስጥ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሉ እንደሚነግዱ እንደሚሸጡና እንደሚገዙ ያውቃል። በንግድ ስራ ውስጥ ሁሉም ነገር የሚደረገው የራስን ጥቅም ከማስከበር አኳያ ነው። ገንዘብ የምናወጣው ካወጣነው ገንዘብ በላይ መልሰን ማትረፍ እንደምንችል አረጋግጠን ነው። የሮማ ግዛትን የሚገዛው የቄሳር መንግስት የሚሰራበት መርህ እንደዚህ ነበረ።

ኢየሱስ ደግሞ አዲሱን የእግዚአብሔር መንግስት እያስተዋወቀ ነበር። ይህም መንግስት በሮማውያውን ስግብግብነት ላይ ያልተመሰረተ ነበር።

ጳውሎስ እንዲህ አለ፡-

የሐዋርያት ሥራ 20፡35 እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።

የእግዚአብሔር መንግስር በእግዚአብሔር ፍቅር እና ለሰዎች በምንሰጠው ፍቅር ላይ የተመሰረተች ናት። የእግዚአብሔር መንግስር በራስ ወዳድነት ላይ የተመሰረተች አይደለችም።

የእግዚአብሔር መንግስት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ታስቀድማለች። የእኔነት ፈቃድ መሞት አለበት።

ጳውሎስ እግዚአብሔርን እያገለገለ ተገረፈ፤ መርከብ ተሰበረበት፤ በድንጋይ ተወገረ፤ ተዘረፈ፤ በእባብ ተነደፈ፤ ሌላም ዓይነት መከራ ተቀበለ።

ኢዮብ ከሚስቱ በቀር ሁሉን አጣ።

ሁለታቸውም እግዚአብሔርን ያገለገሉት ቁሳዊ ትርፍ ለማግኘት ብለው አልነበረም።

እንዲሁ እግዚአብሔርን ያገለግሉና እግዚአብሔርን በሕይወታቸው ያስቀድሙ ነበር። ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላቸውም እግዚአብሔርን ያገለገሉት ስለወደዱት ነው።

ማቴዎስ 6፡5 ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

ጸሎተኛ መሆናችንን ሰዎች ካወቁልን ደስ ስለሚለን በደምብ እንዲያውቁንና እንዲያደንቁን ብዙ ማስመሰል እንጀምራለን። ይህም የሰዎችን ትኩረት ወደ ራሳችን መሳብ ያስችለናል። በፍጹም ሰዎች እንዲያዩን መፈለግ የለብንም። የሰዎች ጉራ የእግዚአብሔር መንግስት አካል አይደለም።

ማቴዎስ 6፡6 አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።

ጸሎት በሚስጥር ነው መደረግ ያለበት። ሰዎችን በራሳችን መንፈሳዊነት ለማስገረም መሞከር የለብንም።

ሰዎች ባላዩን ቁጥር ይበልጥ ውጤታማ እንሆናለን።

እኛ የትኩረት ማዕከል ካልሆንን የሰዎች ትኩረት ይበልጥ ወደ ኢየሱስ የመሆኑ እድል ይጨምራል።

የእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ በሁሉ ነገር ቀዳሚው እግዚአብሔር ነው።

ማቴዎስ 6፡7 አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።

የተለመደ የተጻፈ ጸሎት በቃል መድገም ብዙም አይጠቅምም። ሌሎች ሰዎች የጸለዩትን ሸምድደን ስንደግመው እግዚአብሔር ምንም አይገረምብንም። በራሳችን ከልባችን እንድናናግረው ነው የሚፈልገው።

እግዚአብሔር በተዋበ ቋንቋ አይማረክም። ሃሳባችንን እና ፍላጎታችንን ሳንነግረው በፊት ያውቃል። እግዚአብሔር የሚፈልገው ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ሕብረት እንድናደርግ ነው።

እግዚአብሔር በእርሱ እና በእኛ መካከል የሆነ ሰው እንዲገባ አይፈልግም፤ ማንም ሰው በመካከላችን ጣልቃ ገብቶ እግዚአብሔርን እንዴት በጸሎት እንድናናግረው ሊያስተምረን አያስፈልገንም።

ማቴዎስ 6፡8 ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።

ስለ ጸሎት ሌሎች ሰዎች የነገሩንን ሃሳብ በሙሉ ከአእምሮዋችን ማስወጣት አለብን።

ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው ስንጸልይ የሚሰሙንን ሰዎች ለማስገረም መሆን የለበትም።

ወደ እግዚአብሔር ስንጸልይ ከልባችን የውስጣችንን እየተናገርን መጸለይ አለብን። ጸሎታችንን ሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ በሰማነው ዓይነት መንገድ ማድረግ የለብንም።

ከጨሌዎች የተሰራ መቁጠሪያ እየቆጠሩ ደጋግሞ “እመቤታችን ማርያም” እና “አባታችን ሆይ” እያሉ መጸለይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጸሎት አይደለም። ጸሎትን በአእምሮ ሸምድዶ መያዝ በቃላት እንከን የማይወጣለት ጸሎት ያስለምዳል ግን የሚጸልየው ሰው ልቡ ወይም ሃሳቡ ከጸሎቱ ጋር መሆኑ ቀርቶ ሌላ ሃሳብ ላይ እንዲባክን ያደርገዋል።

በቀቀኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጠቀሱም።

እግዚአብሔር የሌሎችን ሰዎች ጸሎት እንደ በቀቀን ቃል በቃል ደግመን እንድንጸለይ አይፈልግም።

እግዚአብሔር ጸሎታችን በአነጋገር ውበት ወይም በቃላት አጠቃቀም አይመዝንም።

በጸሎታችን ጊዜ ከሰው ዓይን ተሰውረን ስንጸልይ ትኩረታችን እራሳችን ላይ አይሆንም። የዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለመስራት ነጻነት ያገኛል።

እስቲ ከጸሎቶች ሁሉ ታዋቂ የሆነውን ጸሎት እንመልከት።

ይህንን ጸሎት እንዳለ መደጋገም ይኖርብህ እንደሆን ወይም በጸሎትህ ውስጥ መካተት ያለባቸውን ነጥቦች የሚያሳይ መመሪያ እንደሆን አስበህ መወሰን አለብህ።

ኢየሱስ በዚህ ጸሎት ውስጥ የእግዚአብሔርን መንግስት እያስተዋወቀ ነው።

አንደኛ ነጥብ። የጸሎታችን ዋነኛው ትኩረት እግዚአብሔር እራሱ መሆን አለበት።

ጸሎት የምንፈልጋቸውን ነገሮች ዝርዝር ማቅረቢያ ብቻ መሆን የለበትም።

ማቴዎስ 6፡9 እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤

ልብ በሉ፤ እግዚአብሔር የሚኖረው በሰማይ ነው። ከእኛ በላይ ነው። ስለዚህ የእርሱን አስተሳሰብ አግኝተን መከተል ያስፈልገናል።

ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

ስለዚህ እያንዳንዱ ጸሎት የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ እንገልጥ ዘንድ እግዚአብሔር መንገዱን እንዲያሳየን በመጠየቅ መጀመር አለበት።

ከሁሉ ነገር በላይ የእግዚአብሔር ስም መመስገን እና መወደስ አለበት።

ቤተክርስቲያኖች ግን ሥላሴ የሚባል ሃሳብ አምጥተው የእግዚአብሔር ስም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ አድርገዋል። “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ፤ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጠ ስም የለም።

ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤

የሥላሴ አማኞች በሰማይ የሚኖሩት ሶስት ወንዶች በምድር ላይ ሁለት ሰዎችን ማለትም አዳምን እና ሔዋንን በመልካቸው እንደ ምሳሌያቸው ፈጠሩ ይሉናል። ይህ ግን ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ከሁለቱ ሰዎች አንዷ ሴት ናት።

 

 

የሥላሴ አማኞች አብን እና ኢየሱስን ሁለተ የተለያዩ አካላት አድርገው ይሰነጥቋቸዋል።

ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ የሚፈጥረውን ችግር ተመልከቱ።

ቆላስይስ 3፡17 እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

በዚህ መሰረት እግዚአብሔር እና አብ የተለያዩ አካላት ሊሆኑ ነው።

“በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ” ማለት ማንኛውንም ሐይማኖታዊ አገልግሎትና እንቅስቃሴ ይመለከታል። ሁሉም ነገር በኢየሱስ ስም መደረግ አለበት።

ስለዚህ ሁሉም ጸሎት በኢየሱስ ስም መቅረብ አለበት፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ነው።

ማቴዎስ 6፡10 መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤

በመጀመሪያ ደረጃ ትኩረት ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ መደረግ አለበት፤ እርሱም ከሁላችን በላይ ከፍ ብሎ የሚኖር አምላክ ስለሆነ ይቆጣጠረናል።

ሁለተኛ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ ማድረግ አለብን፤ ስሙም ኢየሱስ ነው።

ፊልጵስዩስ 2፡10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

ጸሎት በኢየሱስ ስም ሲቀርብ ኃይል አለው። እያንዳንዱ አጋንንት ለኢየሱስ ስም መገዛት አለበት።

ሶስተኛ ትኩረት የሚደረገው በእግዚአብሔር መንግስት ላይ ነው።

“መንግስትህ ትምጣ”። በስተመጨረሻ የእግዚአብሔር መንግስት ሁሉን ድል ታደርጋለች።

በእግዚአብሔር ዘንድ ነጥብ ማስቆጠር ከፈለግን ለእግዚአብሔር መንግስት መስራት አለብን።

ለመንግስቱ መስራት ደግሞ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ማወቅ ይጠይቃል።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

በምድር ላይ ያለነው የራሳችንን መንግስት ልንመሰረት ወይም ፍላጎታችንን ልናሳድድ አይደለም።

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የነበረው የሮማ መንግስት ከዚያ ወዲያ ዕድሜው ብዙ አልነበረም።

ከዚያ በኋላ ዓለምን ሁሉ ሊገዛ የቻለ መንግስት አልተነሳም።

ይህም እኛ ሰዎች ምን ያህል ብቃት እንደሚጎድለን ያሳያል።

ስለዚህ ስንጸልይ ትኩረታችን በእግዚአብሔር መንግስት ላይ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም በስተመጨረሻ በምድር ላይ ጸንቶ የሚኖረው የእግዚአብሔር መንግስት ነው።

አሁን ያለንበት ዘመን ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም የሎዶቅያውያን ዘመን ነው፤ በዚህም ዘመን ውስጥ በራዕይ ምዕራፍ 3 ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ እያንኳኳ መሆኑን ተናግሯል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በዘመናዊ ቤተክርስቲያኖቻችን አይገረምም። በቃሉ የሚገለጠው እግዚአብሔር አሁን በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሰዎች አይቀበሉትም።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

የጸሎታችን ትኩረት እግዚአብሔር በዚህ ዘመን መጨረሻ መስራት የሚፈልገው ስራ ላይ መሆን አለበት። ይህንም ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን ብዙ መመርመር ያስፈልጋል።

አንዴ ከዳንን በኋላ የእግዚአብሔርን እውነት ለማወቅ ቤተክርስቲያኖች ብዙም አይረዱንም።

“ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን”።

በሰማይ ውስጥ በራዕይ ምዕራፍ 4 እንደምናየው በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት አሉ።

 

 

አንበሳው ለጥንቷ ቤተክርስቲያን በሐዋርያት የተጻፈውን እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ይወክላል።

ጥጃው በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሶች እንዳይነበቡ በታገዱበት ዘመን እንዲሁም ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተገደሉበት ዘመን ውስጥ ወደ ትልቅ በሬነት አደገ። በሬ ለመስዋእት የሚታረድ እንስሳ ነው። በሬዎች ለጣፋጭ ስጋቸው ተብሎ ይታረዳሉ።

ሰውየው ደግሞ እግዚአብሔር የባረከውን የሰዎች አእምሮ ይወክላል፤ በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያን ሊመጣ ችሏል። ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት የሚለውን እውነት መልሶ አመጣ። 47ቱ ምሑራን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ተረጎሙ፤ ከዚያም በኋላ ለ150 ዓመታት በጥንቃቄ ተፈትሾ በትክክል መተርጎሙ በተረጋገጠ ጊዜ በ1769 ታተመ።

እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና ወንጌልን ስለማዳረስ ሰበከ፤ ከዚህም የተነሳ ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን ተጀመረ።

የንስሩ ክንፎች በአዙዛ እስትሪት፣ ሎሳንጀለስ አሜሪካ ውስጥ በ1906 የተቀጣጠለውን የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት ይወክላል። ከዚያም የንስሩ ታላቅ የማያት ችሎታ ደግሞ ለአሜሪካዊው ነብይ ዊልያም ብራንሐም የተሰጠውን ጥልቅ መረዳት ይወክላል፤ እርሱም ሙሽራይት ወደ ሐዋርያት አባቶችና ወደ አዲስ ኪዳን እምነት መመለስ ትችል ዘንድ በ1947 እን በ1965 መካከል የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገለጠ።

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወደ ራሱ ሊወስዳት በአየር ላይ ይነጥቃታል። በታላቁ መከራ ዘመንም ወንጌል ወደ አይሁዶች ይመለሳል፤ የንስሩ ሁለት ክንፎችም በዚያ ዘመን የሚመጡትን ሁለት ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስን ይወክላል። እነዚህ ነብያት እሥራኤልን ይጠብቃሉ፤ ደግሞም በራዕይ ምዕራፍ 11 እና 12 እንደተጻፈው አይሁዶችን ወደ መሲሁ መልሰው ይጠቁማሉ።

ስለዚህ ጸሎታችሁ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ትክክል እንዲገጥም በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ በሰማይ ውስጥ ያለውን ስርዓት መከተል አለበት።

ዛሬ የምንኖርበትን ዘመን ማወቅ አለብን፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልክቶችን እና የትንቢት ፍጻሜዎችንም መረዳት በጣም ያስፈልገናል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ማስረጃው ይህ ነው።

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችሁ ምልክቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳታችሁ ነው።

የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አንቀበልም ከምንል ወይም ትተን ከምናልፍ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብን። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በከፊል ስሕተት አለበት፣ አፈ ታሪክ ነው ወይም እርስ በርሱ ይጋጫል እያለ ማንም ሰው እንዲያታልለን መፍቀድ የለብንም።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት ብለን እስክናስብ ድረስ ከሰነፍን እኛም ከሰነፎቹ ቆነጃጅት እንደ አንዷ ሆነናል። ለዚህም ስንፍናችን በታላቁ መከራ ውስጥ ዋጋ እንከፍላለን።

አራተኛ በስተመጨረሻ ኢየሱስ ስለራሳችን ፍላጎት እንድንጸልይ ፈቅዶልናል።

አራት ቃላት ብቻ፡-

ማቴዎስ 6፡11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤

“የዕለት እንጀራ” ማለት ለዘመናችን ማለትም ለሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ነው።

በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የትጋ እንደቆምን ማወቅ ያስፈልገናል። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ምን ማድረግ እንዳለብን የምናውቀው።

የመጨረሻው መለከት ሲነፋ የሚሆነውን የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ እየተጠባበቅን ነን።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም

52 ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዘመኑ ምልክት ነው።

ትራምፕ ዓለም ሁሉ ፈርቶ ሳለ ያለ ምንም ፍርሐት ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ለመስጠት ቆራጥነት ያሳየ ድንቅ ሰው ነው። በዚህም ትንቢት ተፈጽሟል። እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች እየተመለሰ ነው።

የሜሴጅ ፓስተሮች ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ተላልፈዋል፤ ምክንያቱም ዶናልድ ትራምፕ የ2016ቱን ምርጫ አያሸንፍም ሲሉ ነበር። የሜሴጅ አማኞች ግን ዓይናቸው ከመታወሩ የተነሳ ይህንን ዓይነት የፈጠጠ ስሕተት ካዩ በኋላ እንኳ አልነቁም።

ፕሬዚዳንት ትራም እሥራኤልን ደግፎ ለመቆም ያሳየው ቆራጥነት እኛም የቤተክርስቲያንን ዓለም (የሜሴጅ ቡድኖችን ጨምሮ) በመቃወም ጸንተን ለመቆም ቆራጥነት ማሳየት እንዳለብን የሚያሳይ ምሳሌ ነው፤ ቤተክርስቲያኖች ዛሬ በኪንግ ጄምስ ቨርዥን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መሰረት ሃሳቦችን ፈትሾ ማረጋገጫ የማይገኝላቸውን ነገሮች ያምናሉ። ከቤተክርስቲያን መሪዎች እና ከሰው ሰራሽ አስተምሕሮዋቸው ጋር ለመቃረን ቆራጥ ሆነህ ከተነሳህ እነርሱ ቁጣቸውን እና የስድብ ናዳቸውን በአናትህ ላይ ያወርዱብሃል። ነገር ግን እምነትህን ከመጽሐፍ ቅዱስ እስካረጋገጥክ ድረስ ፕሬዚዳንት ትራም ባሳየው ዓይት ቆራትነት ጸንተህ መቆም አለብህ።

ስለዚህ ጌታ ሊመጣ ጊዜው እየቀረበ ስለሆነ አካላችንን እንዴት እንደምንለውጠው የሚያሳዩን ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ማስተዋል እንችል ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት መመርመር ማጥናት ያስፈልገናል።

በቃና ዘገሊላ ኢየሱስ ባደረገው የመጀመሪያው ተዓምር ወቅት ስድስት የውሃ ጋኖች እስከ አፋቸው ድረስ በውሃ ተሞልተው ነበር።

ከዚያም የማንንም ትኩረት ሳይስብ ኢየሱስ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ ለወጠው።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመረዳት አእምሮዋችንን በእግዚአብሔር ቃል ውሃ መሙላት አለብን።

ከዚያም ሙታን ከተነሱ በኋላ አሁን የተረዳናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ኢየሱስ ምን እየሰራ እንዳለ እናስተውል ዘንድ ይረዱናል፤ በዚህም መረዳት አማካኝነት ኢየሱስ ወደ ከበረ አካል ይለውጠናል።

የሜሴጅ ሰባኪዎች የትራምፕን መመረጥ እንደተቃወሙት እኛ ደግሞ የእግዚአብሔርን የመጨረሻ ሚስጥራዊ ስራ ስንቃወም ልንገኝ አንፈልግም።

በእርግጥ “የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ” የሚለውን ጸሎት አመካኝተን የራሳችንን ፍላጎት ለማሟላት ስለመጠየቅ እንደሚናገር ልንተረጉመው እንችላለን።

ይህ ጸሎት ግን አራት ቃላት ብቻ የያዘ እንደመሆኑ የግል ፍላጎታችንን በተመለከተ የምናቀርበው ጥያቄ በጣም ጥቂት መሆን እንደሚገባው ያመለክታል።

“የዕለት እንጀራችን”። ሕይወታችንን ለአንድ ቀን ብቻ ለማቆየት የሚበቃን ነገር ማለት ነው።

ይህ ስለ ድሎት አይደለም። የብልጽግና ወንጌል አይደለም።

ስንሞት ይዘን መሄድ የምንችለው ለሌሎች የሰጠነውን ብቻ ነው።

ማቴዎስ 6፡12 እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤

ከዚያም አምስተኛው ነጥብ ደግሞ ላቅ ያለ ዋጋ ያለው ጉዳይ ነው። ሐጥያተኝነታችንን ይመለከታል። ይቅርታ ያስፈልገናል።

የሌሎችን ሰዎች ድክመት እና ሐጥያት በማመልከት ብቻ እንጠመዳለን ምክንያቱም በዚህ ክፉ ዘመን ውስጥ እጅግ ብዙ ሐጥያት አለ። ነገር ግን መጀመሪያ በታማኝነት የራሳችንን ሐጥያት ማመን እንዳለበን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። ቅጠል ሰፍተው ሐጥያታቸውን ሊሸፍኑ እንደሞከሩት እንደ አዳም እና እንደ ሔዋን መሆን የለብንም (ቅጠሉ ሰው ሰራሽ ማመካኛዎችንና አስተምሕሮዎችን ይወክላል)። ንሰሃ መግባት አለብን።

የሜሴጅ ሰባኪዎች የሰውን ጥቅሶች ልክ እንደ ቅጠል ልብስ ገጣጥመው በመስፋት ተጠምደዋል። ይህ ምንም አይጠቅማቸውም።

እምነታችን ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መገጣጠም መቻል አለብን።

ዘመናችንን ለሚወክለው ለመጨረሻው ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡-

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

እግዚአብሔር የሚወዳቸው እውነተኞቹ አማኞች ተግሳጽን ቅጣትን ለመቀበል ዝግጁዎች ናቸው።

ይህም ማለት የዛሬዋ የቤተክርስቲያን ዓለም ከእግዚአብሔር ሃሳብ በጣም ርቃ ሄዳለች ማለት ነው።

ንሰሃ መግባት ብቻ አይበቃንም። ንሰሃ ለመግባት መቅናት ያስፈልገናል።

ይህም ብዙ የተሳሳቱ ነገሮችን እያመንን እና እያደረግን መሆናችንን ያመለክታል።

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

ኢየሱስ ዛሬ በዘመናዊቷ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የለም።

የእግዚአብሔር ቃል በዲኖሚኔሽናዊ የእምነት መግለጫዎችና በሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ተገፍቶ ወጥቷል።

እስቲ ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ ፖፕ፣ ካርዲናል፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ኩዳዴ፣ የፋሲካ እንቁላሎችና ጥንቸሎች የሚሉ ቃላትን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጋችሁ አግኙ።

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ተመላላሾች እግዚአብሔር ፍጹም ትክክል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ሊሰጠን የሚችል አይመስላቸውም።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአተረጓጎም ስሕተቶች እና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ ብለው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይናገራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን ስተተቹ ኢየሱስንም መተቸታችሁ ነው። ይህ ደግሞ አደገኛ ነገር ነው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ማቴዎስ 6፡13 ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።

እኛ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን በሰው ብዛት ተከብበን ደህና የሆንን ይመስለናል፤ ልዩ መስህብ ያላቸውን የቤተክርስቲያን መሪዎችም መንገዱን ያሳዩናል ብለን እንተማመንባቸዋለን።

በዚህም አካሄዳችን መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ከማመናችን በፊት የቤተክርስቲያን መሪ የተናገረውን እናምናለን ማለት ነው።

ነገር ግን የአረማውያን ልማዶች፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎ፣ እና ትልልቅ የንግድ ስራዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ አጋንንታዊ አሰራር ቤተክርስቲያንን ወርረዋታል። ክፉው ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልኮ ገብቷል።

ሰዎች እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ይመስላቸዋል። ስለዚህ እግዘአብሔር እየመራቸው ይመስላቸውና የቤተክርስቲያን መሪያቸውን ተከትለው በሰይጣን ተንኮል ይታለላሉ።

ኢየሱስ ስለ መጨረሻው ዘመን ሲጠይቁት የሰጣቸው የመጀመሪያው መልስ እንዲህ የሚል ነው፡-

ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ይህ የዘመናችን ክፋት ነው። ማሳሳት።

ስሕተት የሚመጣው ቤተክርስቲያንን ከተቆጣጠሩዋት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች ነው።

ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች አሉ። ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። የቤተክርስቲያን ዓለም መንፈሳዊ አረንቋ ሆኗል።

ቤተክርስቲያን ወደ እውነት ሁሉ የምንሄድበትን መንገድ የምናገኝባት ሰላማዊ ቦታ ትሆናለች ብለን ስንጠብቅ በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በከፊል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነች ወጥመድ ሆናብናለች። ሔዋን በአንድ መገለጥ ብቻ ተሳሳተችና ተፈረደባት።

በከፊል ትክክል በከፊል ደግሞ ስሕተት የሆኑ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ለስሕተታቸው ዋጋ ይከፍላሉ፤ የቤተክርስቲያን ስሕተቶች ደግሞ በጣም ብዙ ናቸው ምክንያቱም እግዚአብሔር ያለንበት የቤተክርስቲያን ዘመን ዕውር መሆኑን ተናግሯል።

ከዚያም ኢየሱስ ይህንን ጸሎት መንግስት የቤተክርስቲያን ወይም የሆነ የአንድ ሰው ሳትሆን የእግዚአብሔር እንደሆነች በማወጅ ይቋጨዋል።

እውነትን ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ብቻ ታገኙታላችሁ።

ከመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ነገር የሚናገር ሰው ሁሉ እውነትን እየተናገረ አይደለም።

ሰውን ከተከተልን ጉድ እንሆናለን፤ ስለዚህ ትኩረታችን በእግዚአብሔር ላይ ብቻ መሆን አለበት። ኃይል እና ክብር ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ናቸው።

ኢየሱስ ቀጥሎ የተናገረው ነገር ስለ ጸሎት አንኳር ሃሳብ ይገልጥልናል።

ይህም ሐጥያተኝነታችን እና ይቅርታ እንደሚያስፈልገን ነው።

ማቴዎስ 6፡14 ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤

እግዚአብሔር ይቅር የሚለን ሌሎች ሰዎችን ይቅር ባልንበት መጠን ብቻ ነው።

ሰዎች በእኛ ላይ የሰሩትን ሐጥያት እኛ ከሰራነው ሐጥያት በላይ አጉልተን ነው የምናየው።

ስለዚህ እኛ ራሳችን ማየት ከምንችለው በላይ ብዙ ሐጥያት ነው እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የሚያየው።

ማቴዎስ 6፡15 ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።

ሌሎች ሰዎችን ይቅር ማለት እንደማንችል የሚሰማን ከሆነ እግዚአብሔር እኛን ይቅር አላለንም ማለት ነው።

እኔ ምሕረት የማይገባኝ ሳለሁ እግዚአብሔር በጸጋው እኔን በነጻ ይቅር እንዳለኝ ሙሉ በሙሉ ከገባኝ እኔም የበደለኝን ሌላ ሰው ሙሉ በሙሉ ይቅር ማለት እችላለው፤ ሰውየው ይቅርታ የማይገባው ቢሆንም እንኳን።

ማንም ሰው ይቅርታ ይገባኛል ብሎ መጠየቅ አይችልም።

በነጻ የሚሰጥ የሐጥያት ይቅርታ በየትኛውም ዓይነት ክፍያ ሆነ በሐጥያተኛው መልካም ሥራ አማካኝነት ሊገኝ አይችልም።

ማቴዎስ 6፡16 ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

እግዚአብሔር እኛ ወደ ራሳችን ትኩረት እንድንስብ አይፈልግም። ስለዚህ እግዚአብሔርን ማገልገል ቀላል አይደለም።

ሐይማኖታዊ አስመሳይነትን መከተል የለብንም።

ማቴዎስ 6፡17-18 አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።

ተቃራኒውን አድርግ። መጾም ከባድ ነው ግን ደስተኛ ምሰል እንጂ ሐዘንተኛ መስለህ አትታይ።

ማቴዎስ 6፡18 አንተ ግን ስትጦም፣ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባተህም በግልጥ ይከፍልሃል።

ይህንን ትምሕርት አንድ እርምጃ ወደፊት ልናየው እንችላለን።

አንድ ችግር ሲገጥመን በአደባባይ ወዮ በማለት ለሰው ሁሉ ማወጅ የለብንም።

ከዚያ ይልቅ አስፈላጊ የሆነ የአቅጣጫ ለውጥ አድርገነው በመቁጠር እግዚአብሔር አንድ ዋጋ ያለው ነገር እንዲያስተምረን እድል መስጠት አለብን።

ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።

እግዚአብሔርን የመውደዳችን ምልክቱ በመከራ ውስጥ መደሰት ነው። መከራ ለእኛ መልካም ያደርግልናል። መከራ እግዚአብሔር እንደ እኛ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ራሱ ፈቃድ እኛን የሚጠራበት መንገድ ነው።

ይህ ቀላል ፈተና አይደለም።

ማቴዎስ 6፡19 ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤

የእግዚአብሔር መንግስት የብልጽግና አስተምሕሮ አይደለችም።

የእግዚአብሔር መንግስት ሃብታም መሆኛ አይደለችም።

ሃብትህ በበዛ መጠን ስለ ሃብትህ ጭንቀትህም እየበዛ ይሄዳል።

ንብረት እንክብካቤ ይፈልጋል። ሃብት ከገበያ ዋጋ ጋር ይዋዥቃል። ሌቦች ሃብታሞችን ይከታተሉዋቸዋል።

ማቴዎስ 6፡20 ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤

ምሳሌ 19፡17 ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥

በመቃብርህ ውስጥ ካንተ ጋር ይዘህ የምትሄደው ሃብት ለድሆች በነጻ የሰጠሃቸው ስጦታ ነው።

ማቴዎስ 6፡21 መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።

ልብህ በቁሳቁስ ሃብት እና የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መረዳት በሚያስችልህ የተከፈተ ዓይን መካከል መምረጥ አለበት።

ከሁለቱ የትኛው ይበልጥብሃል? ገንዘብ እና ዝና ወይስ የመጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መገለጥ?

ማቴዎስ 6፡22 የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤

ብርሃን ወደ ዓይን ውስጥ ይገባል። የምናነበውን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ማመን ያለብን። መንፈሳዊ ዓይናችን ጤናማ መሆን አለበት።

በልባችን ውስጥ ቦታ መስጠት ያለብን ለአንድ ሰው ብቻ እርሱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ይህም ማለት አንድ ብቻ ፍጹም መጽሐፍ ቅዱስ አለ ማለት ነው፤ እርሱም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን።

መጽሐፍ ቅዱስን ስናምን እና ስንጠቅስ በእውነተኛ አማኞች የተገነባው የጌታ አካል በብርሃን ይጥለቀለቃል።

ማቴዎስ 6፡23 ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!

ሔዋን የዛፍ ፍሬ በላች፤ ሥላሴ፤ የገና በዓልን ማክበር፤ ዲሴምበር 25፤ ሰባቱ የመከራ ዓመታት፤ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ በ1963 በተገለጠው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና መልክ ወደ ምድር ወርዷል የሚሉ እና የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች አእምሮዋችሁ ውስጥ ሲሞሉ እነዚህ ስሕተቶች ብዙ እውነቶችን ማየት እንዳትችሉ ዓይኖቻችሁን ያሳውራሉ። ከዚህም የተነሳ በሰዎች አመለካከት እና ወጎች በፈጠሩት ጨለማ ውስጥ ትመላለሳላችሁ።

መምረጥ ያስፈልጋችኋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት ኢየሱስን ተከተሉ አለዚያ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶቻቸውን እና ስሕተቶቻቸውን በሚከተሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተወዳጅ ሆናችሁ ኑሩ።

ምርጫው የናንተው ነው።

ነገር ግን አንዴ እምነታችሁን በስሕተቶች ላይ መመስረት ከጀመራችሁ፤ ይበልጥ እየሳታችሁ ትሄዳላችሁ።

ከዚያም የባሰው ክፉ ነገር ደግሞ እውነትን ስሕተት ነው በማለት ታወግዛላችሁ።

ማቴዎስ 6፡24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።

በሕይወቴ ውስጥ ማንን አስቀድማለው? እግዚአብሔር ወይስ የዚህ ዓለም ስኬት?

በዚህ ዓለም ስኬት ላይ ስታተኩሩ እግዚአብሔር ከሕይወታችሁ ይወጣል። [እኔነት 1፤ እግዚአብሔር 0]

እግዚአብሔር ላይ ስታተኩሩ ለቁሳቁሳዊ ስኬት ያላችሁ ትኩረት ይቀንሳል። [እኔነት 0፤ እግዚአብሔር 1]

በሕይወታችሁ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው ማነው? እግዚአብሔር ወይስ እኔነት?

ማቴዎስ 6፡25 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?

የእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የምንኖረው አኗኗር እግዚአብሔርን ዛሬውኑ በማገልገል እና ለኑሮዋችን የሚያስፈልገንን እግዚአብሔር ነገ እንዲሰጠን እርሱን በማመን ነው።

አንተ ሰው በመሆንህ ብቻ ከሚያስፈልግህ ምግብ እና ልብስ ትበልጣለህ።

ማቴዎስ 6፡26 ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

ወፎች በየዕለቱ ምግብ ፍለጋ ይበርራሉ። ወፎች መዝራት እና ማጨድ አያስፈልጋቸውም።

እግዚአብሔር በየዕለቱ ወፎች ምግባቸውን የሚያገኙበት ተፈጥሮአዊ ኡደትን አዘጋጅቷል።

እግዚአብሔርን በመንግስቱ ውስጥ ለሚያገለግሉት ሰዎችም እግዚአብሔር እንደዚሁ የሚያስፈልጋቸውን የሚያገኙበት ሥርዓት አበጅቷል ምክንያቱም ሰዎች ከወፎች የሚበልጥ ዋጋ አላቸው።

ማቴዎስ 6፡27 ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?

እኛ ራሳችንን እንደ አዋቂ እንቆጥራለን። ነገር ግን ይህ አስተሳሰባችን አያሳድገንም።

እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን የተወሰነ ቁመጥ ብቻ ማደግ የሚችል አካል ውስጥ አስቀምጦናል። የእኛ አካላዊ እድገት ሳይንስ ሊያውቀውም ሆነ ሊያደርገው የማይችለው ተዓምር ነው።

አንድ ሰው እንዲያድግ ማድረግ እጅግ ውስብስብ ሥራ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው እንዲያድግ ማድረግ ከቻለ እንግዲያውስ ለእያንዳንዱ ሰው ምግብ እና ልብስ ማዘጋጀት ለእግዚአብሔር በጣም ቀላል ሥራ ነው።

ግን በቁመታችሁ መደሰት አለባችሁ።

ሴቶች ረጅም ለመምሰል ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ ማድረግ የለባቸውም።

ሴቶች ፋሽን ተከታይ ለመምሰል ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ማድረግ የለባቸውም። ይህ ራስን ከፍ ማድረግ ነው።

እርሱም የሮማ ካቶሊክ መንፈስ ነው።

 

 

የኢጣልያ ካርታ አንዲት ሱሪ የለበሰችና ታኮ ጫማ ያደረገች ሴትን ይመስላል። ሁለቱም ስሕተት ናቸው።

 

 

የሲሲሊ ደሴት (ቀይ ቀለም የተቀባው) ዳንኤል በናቡከደነጾር ሕልም ውስጥ ያየው የአሕዛብ ምስል እግሩን ሊመታ የሚመጣውን ድንጋይ ይመስላል።

ይህ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ነው።

ኢየሱስ የዚህን ዓለም ሥርዓት ሊያጠፋው እየመጣ ነው።

ማቴዎስ 6፡28 ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤

ሰዎች ሁልጊዜ ስለ ልብሳቸው ይጨነቃሉ። እግዚአብሔር ግን አበቦችን እንኳ አስውቦ ያለብሳል። ታድያ እግዚአብሔር እኛንስ መንከባከብ ያቅተዋል?

ማቴዎስ 6፡29 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።

ማቴዎስ 6፡30 እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?

ሳር ብዙም ሳይቆይ ከብቶች ቢበሉትም እንኳ ወይም በእሳት ቢቃጠልም የራሱ የሆነ ውበት አለው። እግዚአብሔር ሳርን እና ተክሎችን ለማኖር የተፈጥሮ ኡደቶችን አስተካክሎ እንደሚጠብቅ ሁሉ በመንግስቱ ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎችን ፍላጎትም ለመሙላት እንዲሁ ይተጋል።

ዛሬ ባለን ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ለማገልገል መትጋት አለብን።

ለነገ የሚያስፈልገንን እግዚአብሔር ይሞላልናል።

ማቴዎስ 6፡31 እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤

ስለ ራስ ፍላጎት በማሰብ መጠመድ ሁልጊዜ እንደ ምግብ፣ መጠጥ፣ እና ልብስ በመሳሰሉ ፍላጎቶች ላይ መጨነቅ ነው። የአለባበስ ፋሽኖች ወዲያው ተለውጠው ገላን አጋልጦ የሚያሳይ ዓለማዊ አለባበስ ይሆናሉ። ይህም ትኩረት ወደ ራስ ለመሳብ ነው።

ዋነኛው ትኩረታችን በራሳችን ቁሳቁሳዊ ፍላጎቶች ላይ መሆን የለበትም። የራሳችን ፍላጎት ላይ ትኩረት ማድረግ ወደ መንፈሳዊ ፍጻሜያችን ከሚያደርሰን መንገድ ያስወጣናል።

ማቴዎስ 6፡32 ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።

መብል፣ መጠጥ፣ ልብስ።

የሃሳባችንና የጸሎታችን ዋነኛ ርዕስ ይህ ከሆነ እኛ በኑሮዋችን ከአሕዛብ በምንም አንበልጥም ማለት ነው።

ከዚሁ ሁሉ ይልቅ ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጦች ላይ ትኩረት ብናደርግ ነው የሚሻለን።

እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ባሰበው ታላቅ እቅድ ውስጥ ቦታችንን ስለማግኘት ማሰብ አለብን።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

የስኬታማ ጸሎት ሚስጥር ይህ ነው።

ሃሳባችን በራሳችን ፍላጎቶች ላይ መጠመድ የለበትም።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈተም መቅናት አለብን።

በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ትኩረት ማድረግ እና የእኛን ሕይወት እርሱ እንዲመራ እንዲሁም እኛ ምን እንደሚያስፈልገን እራሱ አውቁ እንዲሰጠን መተው አለብን።

ማቴዎስ 6፡34 ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።

ይህ ዘመናዊ ጊዜ ክፉ ነው።

እያንዳንዱ ቀን ክፉ ነው፤ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ በብዛት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱን ማመን እየተዉ ናቸው። ስለዚህ ስለ ነገ መጨነቅ አያዋጣንም፤ ምክንያቱም ስለ ነገ መጨነቅ ዛሬ ብዙ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን እንድናደርግ ይገፋፋናል። ስለ ወደፊቱ መተንበይ አንችልም ስለዚህ በእያንዳንዱ ዕለት እግዚአብሔርን ማገልገል አለብን።

እኛ አናውቅም እንጂ ዛሬ የምናምናቸውና የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች ስሕተት ናቸው።

በዘመን መጨረሻ እግዚአብሔር ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሲናገር እንዲህ ይላል።

ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

ቤተክርስቲያን በገንዘብ እጅግ በልጽጋለች፤ ስለዚህ ስለ ሃብቷ መኩራራት ትችላለች።

ነገር ግን ክርስቲያኖች በምን ዓይነት ደካማ መንፈሳዊነትና የአለማመን ሕይወት ውስጥ እንዳሉ እንኳ አያውቁም።

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ትክክል መሆኑን እንኳ ማመን አቅቷቸዋል።

ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳታይ ዓይኗ ታውሯል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን እየቀያየሩ ወደ ጥልቅ ጨለማ ውስጥ እየገቡ ናቸው።

የያዙዋቸው አዳዲስ ትርጉሞች የተሻሻሉ ናቸው ይላሉ፤ መልሰው ደግሞ ፍጹም አይደሉም ብለው ይናገራሉ።

ቤተክርስቲያን ፍጹም ትክክል ባልሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ነው እምነቷን የመሰረተችው። በጣም ተጭበርብራለች።

ስለዚህ የወደፊት ሕልውናቸውን ለመጠበቅ የቆሙበት መሰረት ጽኑ አይደለም።

ይህች ዓለም በአስፈሪ ፍጥነት እየተለወጠች ነው።

የወደፊቱ ዘመን እኛ በጠበቅነው መንገድ አይሄድም።

የሜሴጅ ፓስተሮች በ2016 ስለተደረገው የትራምፕ ምርጭ እንዴት እንደተሳሳቱ አስቡ። ከእነዚያ ፓስተሮች አንዳንዶቻቸው ኢየሱስ በ1977 ይመለሳል ብለው ነበር። ሌሎቹ ደግሞ ኢየሱስ በ1963 መጥቷል ብለው ነበር።

እኛ ሰዎች ለመማር የዘገየን ነን።

ትንበያዎቻችን በጣም ቀላል፤ የገሃዱ ዓለም እውነታ ግን በጣም ውስብስብ ነው።

በዓለም ላይ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ እንኳን ብዙ የምናውቀው ነገር የለም።

እግዚአብሔር ነገ ከመጽሐፍ ቅዱ አዲስ ነገር ያስተምረናል፤ እኛም ለመቀበል ልባችንን ዝግጁ ማድረግ ያስፈልገናል።

እኛ ሁሉን አናውቅም።

ስለዚህ ብዙ መማር ያለብን ነገር አለ።

ከዚያ በኋላም ተጨማሪ ብዙ መማር የሚያስፈልገን አለ።

ስለዚህ አብዝተን ንሰሃ ብንገባ እና መሳሳታችንን ብናምን የተሻለ ይሆናል።

የ2020 ዓ.ም ኮሮና ቫይረስ ቤተክርስቲያኖች እንዲዘጉ አድርጓል። ይህም እግዚአብሔር ስለ ቤተክርስቲያኖቻችን ምን እንደሚያስብ ይገልጣል። ለመዘጋት ብቻ የሚበቁ ሆነዋል።

ስለዚህ እቤታችን መቀመጥ እና ይበልጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለብን እንጂ ቤተክርስቲያናዊ መሆን የለብንም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23