ማቴዎስ ምዕራፍ 05፡25-48. የተራራው ስብከት ክፍል 2
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እግዚአብሔር ያስቀመጠልን መስፈርት በራሳችን አቅም ልንወጣው የማንችለው ነው። ፈተናዎች ለእኛ ጥሩ ናቸው። በፍጹም አታጉረምርሙ። እምነት ይኑራችሁ።
First published on the 7th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ማቴዎስ 5፡25 አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤
ከፍርድ ቤት እና ከክስ ጋር አትጠላለፉ በተለይም ከገንዘብ እዳ ጋር በተያያዘ። ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ውስጥ እንቅስቃሴህ በሙሉ አንተን ሊከሱህ እንዳይችሉ በማድረግ ይሁን።
ስሕተት ከሰራሁ ስሕተቴን ማመን እና የበደልኩትን ሰው በተቻለኝ መጠን ወዲያው ለመካስ መሞከር አለብኝ፤ አለዚያ ሰውዬው በኔ ላይ ያለውን አመኔታ ይተዋል ደግሞም በሰዎች ዘንድ ስሜን ያጠፋል። ብርሃኔ ተመልሶ እንዲበራ የጠፋውን ስሜን ማደስ አለብኝ። ብዙ ጥቅም ቀርቶብኝ ስሜ መልካም ሆኖ ቢቀርልኝ ይሻለኛል።
ስሕተት ሰርቶ ከዚያ በኋላ መካድ ወይም ማመካኛ ማቅረብ ወደ ፍርድ ቤት ተጎትቶ መወሰድን እና ኋላም እስር ቤት መግባትን ሊያስከትል ይችላል።
ይህ ቃል ሲኦልንም የሚገልጥ ማስጠንቀቂያ ነው። ከሐጥያታችን ንሰሃ ካልገባን፤ ሐጥያት አልሰራሁም ብለን ብንክድ ወይም ለሐጥያታችን ምክንያት ልናቀርብ የምንሞክር ከሆነ መጨረሻችን የሲኦል እስር ቤት ውስጥ መግባት ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ስለ ሐጥያታችን ይከሰናል፤ መንፈስ ቅዱስም ይወቅሰናል። ስለዚህ አሁኑኑ ጊዜ ሳለን ሐጥያታችንን እንናዘዝና የእግዚአብሔርን ይቅርታ እንቀበል። እስክትሞቱ ድረስ አትጠብቁ ምክንያቱም ከሞታችሁ በኋላ በእግዚአብሔር መንገድ መሄድ አትችሉም። የምንሄድበት መንገድ ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 14፡6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ማቴዎስ 5፡26 እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።
ከፍርድ ቤት ደጅ እንኳ አትለፉ። ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸውን ወደ ፍርድ ቤት መጎተት የለባቸውም። በገንዘብ ተጣልቶ በመካሰስ የክርስትናን ስም ከማበላሸት ገንዘብ ተወስዶብን ብንቀር ይሻለናል።
እስር ቤት ከገባን በኋላ ሙሉ ዋጋ እንከፍላለን፤ ይህም የምንከፍለው ሙሉ ዋጋ መጀመሪያ ተከስሰን ፍርድ ቤት ከመቅረባችን በፊት ክፈሉ ተብለን ከተጠየቅነብ ብዙ የሚበልጥ ዋጋ ነው።
ከሲኦል እስር ቤት ማንም ማምለጥ አይችልም። ሲኦል ውስጥ ሰዎች ስለ ሐጥያታቸው ሙሉውን ክፍያ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስኪከፍሉ ድረስ ይሰቃያሉ። ትንሽም ብትሆን ሳታስቀጣ የምታልፍ ሐጥያት የለችም። ሳንቲም ዋጋዋ ትንሽ ነው።
ከረጅም ጊዜ ስቃይ በኋላ ሁሉም ዋጋ ተከፍሎ ሲያበቃ ከዚያ በኋላ ነው ያ ሰው ከመኖር የሚደመሰሰው። ሐጥያተኞች እንደ ሐጥያታቸው መጠን የተለያየ የጊዜ ርዝመት ያለው ቅጣት ነው የሚቀጡት።
ማቴዎስ 5፡27 አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
ሚስት ያገባ ሰው ከሌላ ሴት ጋር ቢተኛ ነውር ነው።
ባል ያገባች ሴት ከሌላ ወንድ ጋር ብትተኛም ነውር ነው።
የጋብቻ ቃል ኪዳን የሚጀምረው ከእጮኝነት ነው። አንድ ሰው እና አንዲት ሴት ሊጋቡ ሲተጫጩ እንደ ባል እና ሚስት ሆነው አብረው መኖር ባይጀምሩም እንኳ እግዚአብሔር እጮኝነታቸውን የማይፈርስ ቃልኪዳን አድርጎ ነው የሚቆጥረው።
ማቴዎስ 1፡18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
ዮሴፍ እና ማርያም እጮኛሞች ነበሩ ነገር ግን አብረው መኖር አልጀመሩም።
ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን [በእንግሊዝኛ፡- ሚስትህን] ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
ገና በእጮኝነት ላይ ቢሆኑም እንኳ መልአኩ ማርያም የዮሴፍ ሚስት እንደ ሆነች አድርጎ ነው የተናገረው (በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው)።
ሊጋቡ የተማማሉበት ቃልኪዳን ጽኑና የማይሻር ነው።
2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
ሙሽራይቱ ለክርስቶስ ማለትም ለቃሉ ታጭታለች።
የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ትተን የአንድ ቤተክርስቲያን ፓስተር የሚለንን የምንሰማ ከሆነ ለባላችን፣ ማለትም ለቃሉ እየታዘዘን አይደለም።
ለቃሉ የማንታዘዝ ከሆነ ደግሞ መንፈሳዊ ዝሙት እየፈጸምን ነው።
ማቴዎስ 5፡28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።
አንዲት ሴት የወንዶችን ትኩረት ለመሳብ የሚያመች ልብስ ብትለብስ ከእርሷ ጋር ለመተኛት የተመኙ ወንዶች ሁሉ ዝሙት ይፈጽማሉ። ግን እርሷም ከእነርሱ እኩል ሐጥያተኛ ናት።
አንድ ሰር ከርታታ ዓይኖች ቢኖሩት እና በሥርዓቱ የለበሱ ሴቶችን ቢመኝ በዝሙት ሐጥያት ተጠያቂ የሚሆነው ሰውየው ብቻ ነው።
በመንፈሳዊ ገጽታ ስንመለከት ሰዎች የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችን ያያሉ፤ በልባቸው ግን መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ይላሉ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነትም ፈንታ ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችን ይወዳሉ፤ ለምሳሌ ሥላሴ፤ ስም የሌለው ባለ ሶስት አካል አምላክ፣ ስም የሌለው ጥምቀት በሶስት ማዕረጎች ማጥመቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይታወቀው የዲሴምበር 25 ክሪስማስ፣ የሮማውያን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን። ሰዎች ሰው ሰራሽ የሆኑ የስልጣን ተዋረዶች ያሉበትን ዲኖሚኔሽናዊ የቤተክርስቲያን መዋቅር በውስጡ ዓለማዊነት፣ ፖለቲካ፣ ከባዕድ እምነቶች የመጡ ትምሕርቶች እና ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተቀላቅለው እየቀረቡላቸው ያለ አንዳች ጥያቄ ዝም ብለው ይቀበላሉ። በሰዎች ትዕዛዝ የመመራት መንፈሳዊ ግልሙትና ቤተክርስቲያንን በገንዘብ አበልጽጓታል፤ ነገር ግን በዚህ ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሰነፎቹን ቆነጃጅት ወደ ታላቁ መከራ እየነዱዋቸው ነው።
በራሳችንን አስተሳሰብ እና በራሳችን አቅም መደገፍ እንደማንችል ኢየሱስ አብራርቶልናል።
ኤርምያስ 10፡23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም።
የራሳችን ተነሳሽነት እና ድንቅ ሃሳቦቻችን ሁሉ ዋጋ ቢስ ናቸው።
ኤርምያስ 17፡9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?
ሰው እንደ መሆናችን አስተሳሰባችን ምን ያህል ክፉ መሆኑን አናውቅም።
ሃሳባችንን በራስ ወዳድነት፣ በስግብግብነት የተያዘ ስለሆነ ገንዘብ ማትረፍ እግዚአብሔር መምሰል እንደሆነ አድርገን የመቁጠር ዝንባሌ አለን።
ማቴዎስ 5፡29 ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።
ራሳችንን መግዛት በጣም ያስፈልገናል። ራሳችንን መግዛት የምንችለው ደግሞ ለራሳችን በመሞት ነው።
ቀኝ ዓይን የውስጥ ሃሳባችንን ወይም አመለካከታችንን ይወክላል።
ኢየሱስ በራሱ መንፈስ ቅዱስ ሊሞላን ይፈልጋል፤ በመንፈሱ ሲሞላንም በቃሉ ይመራናል፤ ከዚያ በኋላ እርሱ የሰጠንን ሥራ መስራትና ተልዕኮውን መፈጸም እንችላለን።
የውስጥ ሃሳቦቻችንን አውልቀን መጣል አለብን ምክንያቱም በሥጋ ምክንያት የረከሱ ናቸው።
ኢየሱስ አንድ ዓይነ ስውር ሰውዬን ፈወሰው፤ ሰውየውም ዓይኑ እንደበራ መጀመሪያ ሰዎች እንደ ዛፍ ሲሄዱ አየ።
በሌላ አነጋገር የሰዎችን መንፈስ አየ ማለት ነው፤ ይህም የሰዎቹን እውነተኛ ማንነት ያሳያል። ሰዎችን በትክክለኛው ዓይኑ ነበር ያያቸው። ይህ ሰውዬ በመንፈስ ነበረ ሰዎችን ያየው እንጂ በሥጋ አልነበረም። ያልዳነ ሰው ቅጠሎች እንደሌሉት የሞተ ዛፍ ሆኖ ነው የሚታየው።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን የግል አመለካከታችንን አውልቀን መጣል አለብን፤ ከዚያም ትክክለኛ በሆነው የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ልንተካው ይገባል። የግል አመለካከቶቻችን በኋላ ችግር ውስጥ ይከቱናል።
በዓለም ውስጥ የሚደረገውን ክፋት ለማየት እንድንጓጓ የሚያደርጉንን ፍጥረታዊ ፍላጎቶቻችንን ሙሉ በሙሉ እምቢ ማለት አለብን።
የቤተክርስቲያን ቡድኖች ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ማራኪ ናቸው፤ ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የጎደላቸው ናቸው፤ ከእነዚህ መራቅ አለብን።
አንዲትን ሴት አይቶ መመኘት መጥፎ ነገር ነው፤ ነገር ግን ውብ የሆኑትን የቤተክርስቲያን ስሕተቶች አይቶ መውደድ ደግሞ ከዚያም የባሰ ክፉ ነገር ነው።
ገንዘብ ለማትረፍ እና ዝነኛ ለመሆን መመኘት ነፍሳችን ምን ያህል እንደረከሰች ያሳያል።
በአእምሮዋችን ውስጥ ካሉት ኦፕቲክ ነርቮች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት አእምሮዋችን ለዓይናችን በሚያስተላልፈው ትዕዛዝ ውስጥ የሚሳተፉ ናቸው።
ከኦፕቲክ ነርቮቻችን 80 በመቶ የሚሆኑነት ሥራቸው ዓይናችን ለአእምሮዋችን ምን እንዳየ መንገር ነው።
ዓይን በራሱ ምንም ክፋት መስራት አይችልም።
ችግር የሚፈጠረው አእምሮዋችን ውስጥ ያሉ ሃሳቦች ለዓይናችን ምን ማየት እንዳለበት በሚናገሩበት ጊዜ ነው።
ፍጥረታዊ በሆነው ዓለም ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተንከራታች ዓይን ነው ወንዶች በስነ ሥርዓት ያለበሰች ሴትን በዓይናቸው ፈልገው እንዲያዩ የሚያደርጋቸው።
እግዚአብሔር የሥጋ ፍላጎትን የሚያሳድደውን ቀኝ ዓይን የሚመራውን ሃሳብ ነቅለን እንድንጥለው ነው የሚፈልገው፤ ምክንያቱም ይህ ሃሳብ ነው ክፉ ሃሳብን እንድንመርጥ እና ክፉ ነገርን የቤተክርስቲያንን ስሕተት ጨምሮ በማየት እንድንሳብ የሚያደርገን።
እነዚህ ክፉ ሃሳቦች ከአእምሮ ውስጥ ተነቅለው መውጣትና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይም በመንፈሳዊ ሃሳብ መተካት አለባቸው።
የዳነ ክርስቲያን በአእምሮው ውስጥ እርስ በርሳቸው የሚጣሉ ሁለት ውሾች አሉት፡ መልካም ውሻ እና ክፉ ውሻ።
አብዝቶ የሚቀልበው ውሻ ያሸንፋል።
ከቤታችን ውስጥ ቆሻሻ በጥንቃቄ ጠርገን እንደምናስወጣ ሁሉ ኢየሱስም ወደ ስሕተት መንገድ የሚመሩንን ክፉ ሃሳቦች ያለ አንዳችን ማመንታታ ነቅለን እንድንጥል ይፈልጋል።
መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። አእምሮዋችንን በመንፈሳዊ ሃሳቦች ይሞላዋል።
እግዚአብሔርን ለማወደስ እና ለማመስገን የተወሰነ ሰዓት ብንጠቀም ያ ብቻውን ሊጎዱን የሚችሉ ብዙ ሥራ ፈት ሃሳቦችን ነቅሎ ይጥልልናል።
ቀኝ ዓይናችንን ማለትን መጽሐፍ ቅዱስ የመረዳት ችሎታችንን እንዳናጣ እና በመልካም ነገር ላይ እንድናተኩር የሚረዱን ሶስት ሃሳቦች አሉ።
ይህ መሆን የሚችለው ግን ኢየሱስ ወደ ልባችን እንዲገባ ስንጋብዘው እና ለራሳችን፣ ለፍላጎታችን፣ ለችሎታችን በመሞት አእምሮዋችንን ሙሉ በሙሉ እርሱ እንዲቆጣጠር ስንፈቅድ ነው።
1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
17 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
18 በሁሉ አመስግኑ፤
ሁልጊዜ የሚደሰት፣ የሚያመሰግን እና አዘውትሮ የሚጸልይ አእምሮ ውስጥ ክፉ ሃሳቦች በቀላሉ መግባት ያስቸግራቸዋል።
ቀኝ ዓይን መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምንችልበትን መንፈሳዊ እይታ ይወክላል። ይህንን ቀኝ ዓይን በራሳችን ማሳደግ አንችልም። እንዲህ ዓይነቱን መንፈሳዊ የመረዳት አቅም ሊሰጠን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሲኖር ብቻ ነው።
በራሳችን ማሰብ የለብንም። ቀኝ ዓይናችንን ማጥፋት አለብን፤ ማለትም ሕይወታችንን የሚያበላሹ ራስ ወዳድ አስተሳሰቦቻችንን ማጥፋት አለብን። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በውስጣችን ሆኖ የራሱን ሃሳብ እንዲያስብ መፍቀድ አለብን፤ እርሱም በመንፈሱ አማካኝነት ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶችን ይሰጠናል። ይህ ብቻ ነው በትክክል ሊመራን የሚችለው።
60-0515 የተገፋው ንጉስ
ከዚያ በኋላ ጠላት እንደመጣ እና ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ታናሽ መንጋ መካከል ሾልኮ በመግባት የእያንዳንዱን ሰው ቀኝ ዓይን ነቅሎ ሊያወጣ እንደፈለገ እናውቃለን። ጠላት ሁልጊዜ ይህን ሊያደርግ ነው የሚፈልገው፤ ቢቻለው ሁለቱንም ዓይኖች ነቅሎ ማውጣት ይፈልጋል፤ ይህንም የሚያደርገው ሰዎች መንገዳቸውን ማየት እንዳይችሉ ነው። ሰይጣን ዛሬ በሁሉም ክርስቲያን ላይ ማድረግ የሚፈልገው ይህ ነው፡- መንፈሳዊ ዓይናቸውን አውልቆ መጣል ይፈልጋል። ከዚህም የተነሳ ዓይኑ የጠፋበት ክርስቲያ በአእምሮው የሚያውቀውን ብቻ እየተከተለ ይሄዳል እንጂ መንፈስ ቅዱስ ወዴት እንደሚመራው አያውቅም።
እስከ ዛሬ ድረስ ከተከናወኑ መንፈሳዊ ጦርነቶች ሁሉ ክርር ያለው ጦርነት የተካሄደው በሰው አእምሮ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን በሚያምነው በመንፈሳዊው ቀኝ ዓይን እና ክፉውን (ብዙውን ጊዜ) የሴቶችን ገላ፣ ገንዘብን፣ ዝናን በሚመኘውና የቤተክርስቲያንን ስሕተቶች በሚከተለው ፍጥረታዊ ቀኝ ዓይን መካከል ነው።
ሰይጣን መንፈሳዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ዓይናችንን ነቅሎ ሊያወጣ ይፈልጋል።
ከክርስቲያኖች መካከል የ1769ኙ እትም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የሌለበት ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው የሚሉ በቁጥር እምብዛም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ መረዳት ባለመቻላቸው አብዛኞቹ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ይላሉ።
ፀሃይ መጽሐፍ ቅዱስን ትወክላለች ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የምንሄድበትን መንገድ ያሳየናል።
“ፀሃይ ትጨልማለች” ሲባል ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ማመን ያቆማሉ ማለት ነው።
ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥
“ከዚያች ወራት መከራ” የሚለው ቃል ሒትለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን የገደለበትን ጊዜ ያመለክታል።
ከጦርነቱ በኋላ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን እያፈለቁ እንደ አሸን ፈሉ፤ በአሁኑ ሰዓትም 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች አሉ ምክንያቱም እያንዳንዱ ለራሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን አዘጋጅቶ ይከተላል። ሰው ሰራሽ ሃሳቦች እየበዙ በሄዱ ቁጥር የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን እየደበዘዘ ይሄዳል። የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሃይ እየጨለመ ነው።
ጨረቃ የፀሃይን ብርሃን ነው የምታንጸባርቀው። ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ማንጸባረቅ አለባት።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ በማለት እና የሰው ጥቅሶችን ትርጓሜ ብቻ በማመን ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች (እና ሌሎች ቤተክርስቲያኖችም) የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማንጸባረቅ አቁመዋል። ሁላቸውም እንደተመቻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የፈለጉትን ይጨምሩበታል ያልፈለጉትን ይቀንሱበታል። ስለዚህ ጨረቃ (ማለትም ቤተክርስቲያን) መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማንጸባረቅ ትታለች።
ከዋክብት ማለት ሰባኪዎች ናቸው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ እንዲሰብኩ የተሰጣቸውን ሰማያዊ ጥሪያቸውን ትተው ወድቀዋል። ዛሬ ጥቅስ ወስደው ወደ ሰው ሰራሽ እምነት ይለውጡታል።
ማቴዎስ 5፡30 ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
ቀኝ እጅ የስልጣን ተምሳሌት ነው።
ማቴዎስ 26፡64 ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።
መጽሐፍ ቅዱስ በስተመጨረሻ ኢየሱስ ብቻ ስልጣን እንደሚኖረው ይናገራል።
ስልጣን ለመያዝ ብቁ የሆነ ሌላ ማንም የለም።
ስለዚህ ኢየሱስ በእኛ ውስጥ ሆኖ ስልጣኑን መግለጥ ይፈልጋል። እኛ ስልጣን በእጃችን ብንይዝ ታማኝ መሆን አንችልም።
ምክንያቱም ከኢየሱስ በቀር ስልጣን ሰዎችን ሁሉ ማበላሸት ይችላል።
በራሳችን ሕይወት ላይ የፈለግነውን ልናደርግ ስልጣን አለን። ይህም ስልጣናችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ አርቆ ስለሚወስደን ያበላሸናል።
ስለዚህ ለራሳችን መሞት እና ሕይወታችንን እግዚአብሔር እንዲገዛ መፍቀድ አለብን። ውሳኔዎቻችንን እርሱ ይወስንልን፤ የዚያን ጊዜ እኛ ጌቶች መሆናችን ይቀርና አገልጋዮች እንሆናለን።
ቀኝ እጅህን መቁረጥ ማለት የራስህን ሕይወት የመምራት ስልጣንህን ማጥፋት ነው።
ክፋት የሚጀምረው በሃሳብ ውስጥ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ለሥራ እጆችን ያንቀሳቅሳል።
በራሳችን ሕይወት ላይ እንዲሁም በሌሎች ሕይወት ላይ ስልጣን ሲኖረን ይህ ስልጣን እራሳችንን ያጠፋናል።
እግዚአብሔር እኛን ሰዎችን ሊያምነን አይችልም።
ኢዮብ 15፡15 እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤
እንኳን ለሌሎች ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚጠቅማቸው ይቅርና ለራሳችንም ምን እንደሚጠቅመን አናውቅም።
ሰዎች እራሳቸውን በሞባይል “ሰልፊ” ፎቶ ማንሳት በሚወዱበት በዚህ ዘመን ውስጥ ትልቁ ክፋት እራሳችንን ከፍ ከፍ ማድረግ ነው።
ገንዘብ ለማትረፍ እንስገበገባለን። የራሳችንን ክብር ከፍ ስለሚያደርግልን በሌሎች ሰዎች ላይ ስልጣንን መለማመድ እንፈልጋለን።
ሰባኪዎች ምዕመኑን ወደ ታች ይጫኑታል፤ ይህን የሚያደርጉት ከጉባኤው በላይ ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ፈልገው ነው።
ፓስተሮች በቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች ላይ መታየትና አድናቆት መቀበል ይፈልጋሉ፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለእነርሱ ተብሎ የተለየ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።
ማቴዎስ 23፡6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፣ በምኩራብም የከበሬታ ወንበር
ማቴዎስ 23፡7 በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
ዛሬ ደግሞ ፓስተር፣ ፓስተር ነው የሚባለው።
በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ በአንድ ባልታወቀ ምክንያት “ፓሰተር” የሚባለው ማዕረግ ብቻ ነው በሰው ስም ላይ የሚለጠፈው ሰውየው እራሱን ፓስተር ብሎ ከጠራ።
ቶማስ ብላችሁ ልትጠሩት አትችሉም (ስሙ ቶማስ ቢሆን) ፓስተር ቶማስ ብላችሁ መጥራት ግዴታችሁ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን “ፓስተር” የሚለው ማዕረግ ከማንም ስም ጋር አልተያያዘም።
“ፓስተሮች” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውሰጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ስድስት ጊዜ ተወግዟል።
ይህ ማዕረግ ጥሩ ስም የለውም።
ከፍ የማለት ፍላጎት እና በምዕመኑ እንዲሁም በጉባኤው ላይ ስልጣን መያዝ (ኒቆላዊነት) የፓስተሮችን አገልግሎት አበላሽቷል።
ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ ለማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰጠ መመሪያ አንድም ቦታ የለም።
ፓሰረተሩን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አልተፈቀደም።
ሮሜ 8፡13 እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።
መንፈስ ቅዱስ በአእምሮዋችን ውስጥ ያሉትን ክፉ መሻቶች መግደል አለበት። በተለይ ደግሞ እራሳችንን ከፍ የማድረግ ፍላጎታችንን፣ እኛ ከሌሎች ሰዎች እንሻላለን የሚለውን አስተሳሰባችንን ሊገድልልን ያስፈልገናል።
በክርስትና ውስጥ እርስ በርስ ከመወዳደር የሚበልጥ ክፉ ነገር የለም።
ከዚያ በኋላ ሌሎች ሰዎችን መቆጣጠርና ለእኛ ፈቃድ እንዲገዙ ማድረግ እንፈልጋለን። ይህ በጣም አደገኛ ልምምድ ነው።
ሰዎች የሚስቱት በሌሎች ሰዎች ላይ ስልጣንን ሲለማመዱ ነው።
የስልጣን ጥማት አንድ ፓስተር ጉባኤው ላይ ገዥ እንዲሆን የአምባ ገነንነት መንፈስን ያጋባበታል።
የዚህም ውጤት 45,000 ዓይነት ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች መፈጠራቸው ነው፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ፓስተር በራሱ አመለካከት መሰረት ጉባኤውን ይጨቁናል። እያንዳንዱ መሪ ከፍ የሚደረግበት ይህ የተከፋፈለ፣ የተቆራረሰ የቤተክርስቲያን አካል ኢየሱስን ከቤተክርስቲያን ውስጥ ገፍቶ አስወጥቶታል።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ
ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ጋር ከእንግዲህ አንዳችም ነገር አያደርግም። አሁን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን እየጠራ ነው። በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስልጣንን የተቆናጠጡ ግለሰቦች ያመጡት ጥፋት ይህን ያህል ነው።
ኢየሱስ እና መጥምቁ ዮሐንስ የአይሁድ ሕዝብን ወደ ስሕተት የመሩ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን ሲያናግሩ በትሕትና አናግረዋቸው አያውቁም። ዘመን አሁንም አልተለወጠም።
በ1906 የተጀመረው ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በስልጣን ፍቅር የተነሳ ብዙና ከፍተኛ ጥፋት ተሰርቷል።
ሌኒን ራሺያ ውስጥ በግፍ ወደ ስልጣን ሲወጣ ከአስር ሺ በላይ ሰዎችን ገድሏል። እስታሊን ወደ ስልጣን ሲወጣ ደግሞ በታላቅ ጭካኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል። ሒትለርን የተጸናወተው አጋንንታዊ የስልጣን ጥም 6 ሚሊዮን አይሁዳውያንን በጋዝ ቤት ውስጥ አፍኖ እንዲገድል እና አይሁድ ያልሆኑ ሌሎች 6 ሚሊዮን ሰዎችንም እንዲገድል አድርጎታል። ቻይና ውስጥ ማኦ ዜዶንግ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ገድሏል።
ሳይንቲስቶች የፍጥረት መሰረት የሆነው አተም ላይ ስልጣን ፈለጉ። ነገር ግን ይስ ስልጣን ጥፋትን የሚያስከትል ነበር፤ ምክንያቱም የአቶሚክ ቦምብ እንዲፈጠር አድርጓል። ሒሮሺማ ላይ የወደቀው የመጀመሪያው ቦምብ የሺማ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ እንዲወድም አድርጓል። ሁለተኛው ቦምብ ናጋሳኪ ላይ ነበር የወደቀው፤ ይህም ጃፓን ውስጥ ከፍተኛ የክርስቲያኖ ቁጥር የነበረበት ከተማ ነው። ይህን እያየን ራሳችንን ምሁር ብለን እንጠራለን?
ለስልጣን ባለን ፍቅር እና ምኞት እኛ ሰዎች አእምሮዋችን መሸከም ከሚችለው በላይ ተምረናል፤ ከዚህም የተነሳ ራስ ወዳድ ፍላጎቶቻችንን መቆጣጠር ተስኖናል።
ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግዛት ወይም ለማስተዳደር ብቁ አይደሉም፤ ለዚህም ነው የዓለማችን ሥርዓት በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት የሚጠፋውና በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም በታላቁ መከራ ዘመን ወደ ሲኦል የሚገቡት።
ማቴዎስ 5፡31 ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ።
አዳም እና ሔዋን አንድ ሰው እና አንድ ሚስት ብቻ ነበሩ። ሔዋን ኢየሱስን በድንግልና እንድትወልደው ነበር የተፈጠረችው።
እንስሳት ደግሞ አንድ ወንድ እንስሳ ከብዙ እንስት እንስሳት ጋር ግንኙነት እያደረገ ነበረ የሚራቡት።
ከእንስሳት ሁሉ ከፍ ባለ ደረጃ የተፈጠረው እባቡ ሔዋንን አሳታት። ከዚያ በኋላ ድንግልናዋን ስላጣች እግዚአብሔር ለኢየሱስ በድንግልና መወለድ የእርሷን ማሕጸን መጠቀም አልቻለም። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎች እንደ እንስሳ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን እያገባ የሚባዙበትን እና የብሉይ ኪዳን ትውልዶች የሚወለዱበትን ሥርዓት ፈቀደ።
አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን እንዲያገባ በሚፈቀድበት በብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድ ወንድ ሚስቱን መፍታት ይችላል፤ እርሷም ሌላ ሰው ማግባት ትችላለች።
ኢየሱስ ግን አንድ ሰው ብዙ ሴትን ማግባት ይችላል የሚለውን ሕግ ሻረውና ከመጀመሪያው አዳም እና ሔዋን ወደነበሩበት ሥርዓት እንድንመለስ አድርጓል። አንድ ሰው እና አንዲት ሚስት ብቻ።
ሐጥያት ወደ ዓለም የገባው ሔዋን ባሏ ላልሆነው ለእባቡ ድንግልናዋን ስለሰጠችው ነው።
ይህንን ጉዳይ ኢየሱስ ይበልጥ ጠበቅ አድርጎታል። አንዲት ሴት ከማግባቷ በፊት ድንግል ሆና መቆየት አለባት።
ስለዚህ አንድ ሰው የፈታትን ሴት ከባሏ ጋር የገባችው ቃልኪዳን ሳይፈርስ እንዳለ ማግባት አይፈቀድም።
ሮሜ 7፡2 ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።
የጋብቻ ቃልኪዳን ከሁለቱ ተጋቢዎች አንዳቸው እስኪሞቱ ድረስ የጸና ነው።
ማቴዎስ 5፡32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።
መዳራት ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ወሲብ ነው።
ሴት በሰውነቷ ውስጥ የድንግልና ምልክት ተሰጥቷታል ምክንያቱም እስክታገባ ድረስ እግዚአብሔር ድንግል እንድትሆን ይፈልጋል። ድንግል ካልሆነች ድንግል አለመሆኗን ለሚያገባት ሰው ቀድማ ማሳወቅ አለባት። አለበለዚያ ከእርሱ ጋር የምታደርገው ቃልኪዳን የውሸት ስለሆነ በሰውየው ላይ አይጸናም። ድንግል ነኝ ብላ ካታለለችው እርሷን ፈቶ ሌላ ሴት መርጦ የማግባት መብት አለው።
ነገር ግን በሕግ ያገባች ሴት ስትፋታ እና እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ስትጋባ ታመነዝራለች።
አንድ ሰው የተፈታች ሴት ካገባ አመንዝሯል።
አንዴ በሕግ ካገባችሁ በኋላ መፋታት እና ድጋሚ መጋባት አይፈቀድላችሁም።
ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።
ሴት ድንግል መሆኗ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
ዘዳግም 22፡23 ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥
24 ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
ከአንዲት ሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተኛ ሰው ዕድሜዋን በሙሉ በጥንቃቄ የጠበቀችውን ድንግልናዋን በማፍረስ ያስነውራታል። ድንግልናዋ ባሏን ራስ አድርጋ እንድትቀበለው ይረዳታል።
ከማግባቷ በፊት ሌላ ሰው ከእርሷ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ፈጽሞ ከሆነ ግን ባሏን ራስ አድርጋ ላትቀበል ትችላለች ምክንያቱም ድንግልናዋን አልሰጠችውም። በዚህ ምክንያት ለእርሱ ዝቅ ብላ ላትገዛ ትችላለች።
ብዙ ሰዎች በትዳራቸው ውስጥ እንዳዩት ያገቡዋት ሴት ድንግል ያልነበረች ከሆነች የአመጸኛነት ዝንባሌ አለባት። ስለዚህ ትዳራቸው ደስተኛ አይሆንም።
ማቴዎስ 5፡33 ደግሞ ለቀደሙት፦ በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ እንደተባለ ሰምታችኋል።
የጋብቻ መሃላ ከፈጸማችሁ ልትተብቁት ይገባል።
በትዳራችሁ ውስጥ መግባባት ቢያቅታችሁ እንኳ መሃላችሁን መጠበቅ አለባችሁ። ቢከብዳችሁ እንኳ ጠብቁት።
መሸነፍ የክርስትና አካል ነው። የመጨረሻው ድል እና ሽልማታችን በሰማይ ነው። ስለዚህ በምድር ሳለን አንድም ጊዜ አንሸነፍም ማለት አይደለም።
ስናሸንፍ ደስ ይለናል፤ ነገር ግን ባህርያችን የሚመዘነው በተሸነፍን ጊዜ ነው። የተሸነፍን ጊዜ ምን ዓይነት ባህርይ እናሳያለን?
ማቴዎስ 5፡34 እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ከቶ አትማሉ፤ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤
በጭራሽ አትማሉ። ሁልጊዜ እውነት የምትናገሩ ከሆነ እውነትን ለመናገር መማል አያስፈልጋችሁም።
ለእግዚአብሔር አክብሮት ይኑራችሁ። እውነት መናገሬን እግዚአብሔር ያውቃል አትበሉ።
እንደዚያ ብሉ መናገር ትርጉም የለውም፤ ምክንያቱም እናንተ ስለተናገራችሁት ነገር እግዚአብሔር ምን እንደሚል ሌላኛው ሰው የሚያውቀው ነገር የለም።
ማቴዎስ 5፡35 በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤
በፍጹም መሃላ የሚባል ነገር አትማሉ። በዙርያችሁ የምታዩት ነገር ሁሉ የተሰራው በእግዚአብሔር ነው። በመሃላ የተናገራችሁትን ቃል ልታፈርሱት ብትፈልጉ የማላችሁበት ነገር ሊያስቆማችሁ አይችልም።
ማቴዎስ 5፡36 በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና።
እውነትን ለመናገር መሃላ መማል ጊዜ ማባከን ነው። ውሸታሞች መሃላቸውን አያከብሩም፤ ስለዚህ ሲመቻቸው ይዋሻሉ። ታማኝ ሰዎች ሁልጊዜም እውነትን ይናገራሉ። ስለዚህ ምሎ መናገር ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም።
የጸጉራችንን ቀለም ምንም ልናደርገው አንችልም። ሰዎች የጸጉር ቀለም ሲጠቀሙ እየዋሹ ነው።
ሰዎቹ መልካቸውን አይደሉም።
ጸጉርህን ቀለም ከቀባኸው እግዚአብሔር ሲፈጥርህ በሰጠህ ደስተኛ አይደለህም ማለት ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6 ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤
እግዚአብሔር ሲፈጥርህ ባደረገህ ደስተኛ ካልሆንክ፤ በውኑ አንተ እግዚአብሔርን በመምሰል የምትኖር ሰው ነህን?
ማቴዎስ 5፡37 ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።
በሰዎች ዘንድ ሁልጊዜ እውነትን የሚናገር ሰው ተብለን መታወቅ አለብን። ስለዚህ “አዎ” ስንል ሁልጊዜ የእውነት አዎ ማለት አለብን።
“አይደለም” ስንልክ ሁልጊዜ የእውነታችንን አይደለም ማለት አለብን።
ማቴዎስ 5፡38 ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
ሕጉ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ዳኛ ለሁለት የተጣሉ ሰዎች እንዴት እንደሚፈርድ ማሳየት ነው። ነገር ግን ሁለት ሰዎች በግል ሕይወታቸው በደል ሲደርስባቸው ሕጉ እንደሚለው ማድረግ የለባቸውም።
ማቴዎስ 5፡39 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
ጉንጭ ላይ በጥፊ መመታት ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ነገር አይደለም።
ሌላኛውን ጉንጭ መስጠት ማለት በማይረቡ ትንንሽ ነገሮች ላይ ከፍ ያለውን መንገድ መሄድ ነው።
ማለትም ሲሰድቡን እና ሲያዋርዱን ምንም እንዳላረጉ ቆጥረን ማለፍ።
በሕይወት ውስጥ ድርጊት እና ምላሽ አለ።
አንድ ሰው ይመታሃል (ድርጊት) አንተም መልሰህ ትመታዋለህ (ምላሽ)። ይህ ማለት ደግሞ ሰውየው ተቆጣጥሮሃል ማለት ነው። ምክንያቱም እርሱ ያደረገው ነገር ያንተን እርምጃ ይወስነዋል።
ሐዋርያት ግን የጻፉት “የሐዋርያት ሥራ” የሚባል መጽሐፍ እንጂ “የሐዋርያት ምላሽ” የሚል አይደለም።
አንተ ተነስተህ ስትሰራ እግዚአብሔር ይቆጣጠርሃል። ሰዎች ላደረጉት ምላሽ የምትሰጥ ከሆንክ ግን ሰይጣን ይቆጣጠርሃል።
በምትሰጠው ምላሽ ጠላትህ ወደ ወደቀበት ዝቅታ አንተም ትወድቃለህ።
ማሸነፍ ዋናው ቁምነገር አይደለም።
በማን ቁጥጥር ውስጥ ነኝ የሚለው ነው ዋነኛው ነገር።
ማቴዎስ 5፡40 እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤
ደግሞም ልብስ ትልቅ ዋጋ ያለው ነገር አይደለም።
ለማይረባ ትናንሽ ነገር ሁሉ ፍርድ ቤት እየሄድን መጨቃጨቅ የለብንም። የሚጠይቁትን ብንሰጥ ከጠየቁንም በላይ ብንጨምርላቸው ይሻላል። ሰዎች ላደረጉብን ክፉ ነገር በመልካም ስንመልስላቸው በእነርሱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ እናደርጋለን። ክፉ ሲያደርጉባችሁ መልካም ካደረጋችሁላቸው ሰዎች በእናንተ ውስጥ የተለየ መንፈስ መኖሩን ያስተውላሉ።
ምሳሌ 25፡21 ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥ ቢጠማም ውኃ አጠጣው፤
22 ፍም በራሱ ላይ ትሰበስባለህና፥ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይመልስልሃልና።
ያንን ጠላት እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን ለመፈተን እና ለማስተካከል ነው። ለጠላትህ ደግ ብትሆንለት ከዚያ ወዲያ ላንተ ጠላት መሆኑን ትቶ ወዳጅህ ይሆናል።
ለተሰማን ስሜት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ እግዚአብሔር የተናገረንን ማድረግ ሕይወታችንን እግዚአብሔር እንዲመራ መፍቀዳችንን ያሳያል። ከዚያ ስለመታዘዛችን ሽልማት እንቀበላለን። በጠላቶቻችን ላይ የበቀል እርምጃ ወስደን ከመደሰት ይልቅ እግዚአብሔርን ማስደሰት በጣም ይበልጣል።
ማቴዎስ 5፡41 ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ።
ሰዎች ኢፍትሃዊ የሆኑ ሕጎችን ማክበር አስፈላጊ ነው ብለው አያምኑም።
ሁለት ኪሎ ሜትር ሁሉ ከመንገድህ ወጥተህ መሄድ ፍትሃዊ አይደለም። ነገር ግን የሮማውያን ሕግ ነበረ።
“ሁለተኛውን ምዕራፍ” መሄድ ማለት የተሰጠህ ትዕዛዝ ፍትሃዊ ባይሆንም እንኳ እንድታደርግ ከተጠየቅኸው በላይ ታደርጋለህ ማለት ነው።
ተጨማሪ በማድረግህ ለሰዎች የምታሳያቸው ነገር አንተ ከሁሉም የበላይ ለሆነ ኃይል እንደምትታዘዝ ነው። ሰዎችም በሕይወትህ ገዥ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን ያስተውላሉ።
በዚህም የተነሳ የሥነ ምግባር አርአያ ትሆናለህ።
አሕዛብ የሆኑት የግሪክ እስጦይኮችም ተመሳሳይ ሃሳብ ነበራቸው። “የግዳጅ አገልግሎት እንድትሰጥ ብትታዘዝ እና ወታደርም ቢይዝህ ወታደሩ የሚፈልገውን ያድርግ፤ አትቃወም፤ አታጉረምርም”። ኢየሱስ ይህንን ሕግ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ወስዶት ኢፍትሃዊ ትዕዛዝ ቢሰጥህ እንኳ በፈቃደኝነት ታዘዝ፤ ደግሞም ከተጠየቅኸው በላይ አድርግ።
ለሰላም ብለህ መሸከም የምትችለውን ጉዳት ሁሉ ተሸከም፤ በሚያሳስብህ ጉዳይ ሁሉ እንዲጠብቅህ ራስህን ለእግዚአብሔር ጥበቃ አደራ ስጥ። ይህን ሁሉ ጠቅለል አድርገን ስናየው ክርስቲያኖች ከመጣላት እና ጭቅጭቅ መራቅ አለባቸው ማለት ነው።
ማንም ሰው ሥጋ እና ደም እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ መቀበል አቅም የለውም ቢሉ ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግስት እንደማይወርሱ ማስታወስ ያስፈልገዋል፤ በትክክለኛው መርህ የሚመላለሱ ሰዎች ብዙ ሰላም እና ምቾት ያገኛሉ።
ሕይወት ፍትሃዊ ባልሆነች ጊዜ እንኳ እግዚአብሔርን ለማገልገል ዝግጁ መሆን አለብን።
ኢየሱስ ብዙ ኢፍትሃዊ የሆኑ ነገሮች ተደርገውበታል። ነገር ግን ሁሉንም ሳያጉረመርም ተቀብሏል።
ሮሜ 12፡19 ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
20 ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
21 ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
ለሚጠሉህ ሰዎች ደግ ሁንላቸው። የዚያን ጊዜ ግራ ይጋባሉ፤ ከዚያ በኋላ አስተሳሰባቸውን ይለውጣሉ።
ማቴዎስ 5፡42 ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል።
ለማጣት መዘጋጀት አለብን። ሰዎች ባላቸው ላይ መጨመር የተፈጥሮ ፍላጎታቸው እንደመሆኑ መጠን ይህ ለሰዎች በጣም ከባድ ትምሕርት ነው።
ኢየሱስ በገንዘቡ ለሚታመነው ሃብታም ሰውዬ የሰጠው ምክር በጣም ከባድ ምክር ነው።
ማቴዎስ 19፡21 ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
ወደ ሰማይ ይዘን መሄድ የምንችለው ብቸኛው ሃብት በምድር ሳለን ለሰዎች የምንሰጠው ብቻ ነው።
ማቴዎስ 5፡43 ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
ሰዎችን ጠላቶቻችን አድርገን መመልከት የለብንም። እያንዳንዱ ሰው የሚጫወተው የራሱ ሚና አለው።
ሒትለር በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ባደረገው የዘር ማጥፋት ዘመቻ 6 ሚሊዮን አይሁዳውያንን ገደለ።
ይህም ጭፍጨፋ በ1947 የተባበሩት መንግስታትን ባስደነገጠ ጊዜ ሁሉም ሃገሮች ለአይሁዶች ያላቸውን ጥላቻ ለጥቂት ጊዜ ትተው እሥራኤል ውስጥ ከተስፋይቱ ምድር ላይ ትንሽ መሬት እንዲሰጣቸው ተስማሙ። የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው ባይፈጸም ኖሮ ያ ውሳኔ አይደረግም ነበር።
ከዚያም ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፈው 5ኛው ማሕተም በ7ኛው የቤተክርስቲየን ዘመን ውስጥ ስለ እምነታቸው የተገደሉ አይሁዳውያን በሰማይ ውስጥ ነጭ ልብስ ይሰጣቸዋል ይላል። ስለዚያ ያ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በጭፍጨፋው ውስጥ የተገደሉት ሰዎች በሰማያት ቦታ እንዲያገኙ በሕይወት ለተረፉት ደግሞ በምድር ላይ ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ አስችሏል።
በዚህም ምክንያት ሒትለር በአይሁዶች ላይ ጥላቻውን በማፍሰሱ ውለታ አድርጎላቸዋል።
የድርጊት እና የምላሽ ሕግ አለ። ሒትለር 6 ሚሊዮን የሞቱ አይሁዳውያንን ወደ ሰማይ ገፍቶ አስገባቸው፤ በሕይወት የተረፉትን ደግሞ ገፍቶ ወደ እሥራኤል መንግስት ገፍቶ አስገባቸው። የዚህ ምላሽ ማለት እርሱ ደግሞ ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ይሄዳል ማለት ነው።
የእግዚአብሔር ጸጋ እናንተን ማዳኑ ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔር ጸጋ በአሰራሩ የሚጠሉዋችሁን ጠላቶቻችሁን ሁሉ ያካትታል፤ ጠላቶቻችሁ ሲገፉዋችሁ ሸካራውን ጎናችሁን ሞርደው በማጥፋት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንድትገቡ ያስገድዱዋችኋል።
ከዚህ የምናገኘው ትምሕርት፡- ጠላቶቻችሁ ሊጎዱዋችሁ ብለው በሚወስዱት እርምጃ ውስጥ ሳያውቁት እግዚአብሔር በዘላለማዊ እቅዱ ወዳሰበላችሁ ስፍራ እየገፉ ያስገቡዋችኋል፤ እግዚአብሔር በ7 የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሰራው ቤተመቅደስ ውስጥ ቦታችሁን ታገኛላችሁ።
ማቴዎስ 5፡44 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ … ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤
ወርቅ የሚጠራው ከውስጡ ቆሻሻዎች ሁሉ ተለቅመው እስኪወጡ ድረስ በመቀጥቀጥ ነው።
እግዚአብሔር እናንተን የሚቃወሙዋችሁ እና የሚጠሉ ሰዎች ይመድብባኋል፤ የእነዚህም ሰዎች ተቃውሞ እናንተን እንደ መዶሻ ቀጥቅጦ ትክክለኛ ቅርጽ ይሰጣችኋል።
መልካምነት ያለ ፈተና ጠርቶ ሊወጣ አይችልም፤ ምክንያቱም ያለ ጠላት ግጭት የለም፤ ያለ ጦርነት ያለ ትግል ድል የለም።
ፍጹም መልካምነት የሚመጣው ከጠንካራ ጠላት ጋር የከረረ ግጥሚያ ከተደረገ በኋላ ነው።
ትዕግስት የሚገለጠው ከቁጥጥራችን በላይ የሆነ መከራ ውስጥ ካለፍን በኋላ ነው።
አንድ ባሕርይ ሰው ላይ እንደ ኮፍያ ሊቀመጥበት አይችልም። መልካም ባህርይ ከሰውየው ውስጥ ተጨምቆ ነው የሚወጣው።
ምንም ጦርነት ከሌለ አንዳችም ድል የለም።
እምነት የሚያድገው እኛ በራሳችን ልንፈታው የማንችለው ችግር ሲገጥመን ነው።
ስለዚህ እንድናድግ ጠላት ያስፈልገናል።
ስለ ጠላቶችህ እግዚአብሔርን አመስግን።
ጠላቶችህ ሳያውቁት ብርቱ እና ስኬታማ ሰው ያደርጉሃል።
ማቴዎስ 5፡45 በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ … እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
እግዚአብሔር ክፉዎችንም ጥሩ ሰዎችንም ይባርካል።
መጥፎዎቹ ሰዎች መልካሞቹን ለመቅረጽ ያገለግላሉ። ከክፉ ወይም ከባለጋራችን ጋር በመታገል ነው መልካም ስነምግባር የምናዳብረው።
ማቴዎስ 5፡46 የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
የሚወዱን መውደድ ቀላል ነው። የሚወዱንን መውደድ ፈተና አይሆንብንም።
ማቴዎስ 5፡47 ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
አንድ ዓይነት ወፎች በቀላሉ አብረው ይሄዳሉ።
ነገር ግን ሰው የማይወዳቸውን ሰዎች እንጎበኛለን? ድሆችንና የወደቁትን፤ ከእኛ ጋር የማይስማሙትን ሰዎች እንጠይቃቸዋለን?
ይህ ከበድ ያለ ፈተና ነው።
ማቴዎስ 5፡48 እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ በእርግጠኛነት እኛ የማንችለውን ግብ እያሳየን ነው፤ ዓላማውም እንደማንችለው ተረድተን ትሁት እንድንሆን ነው።
ፍጹም መሆን ባይቻልም እንኳ ፍጹምነትን መከታተል ግን በጣም አስፈላጊ ነው።
በኢየሱስ የሚያምኑ እና የተገለጠውን ቃሉን የሚናፍቁ ለሁሉም ነገር በእርሱ ላይ ይደገፋሉ። በዚህ መንገድ ተስፋችንን እና እምነታችንን ሁሉ ፍጹም በሆነው በኢየሱስ ላይ እናደርጋለን።
ፍጹም የሆነው ኢየሱስ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠር ከማድረግ የበለጠ ምንም ልናመጣ አንችልም።
አብራሐም እና ኖኅ ፍጹም የተባሉት ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ስለታዘዙ ነው። የእግዚአብሔርን ፍጹም እቅድ በሙሉ ልባቸው አመኑ፤ ዕድሜያቸውንም በሙሉ የእግዚአብሔርን የልብ ሃሳብ ለመፈጸም ሰጡ።
ፍጹምነታቸው ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ማመናቸው እና ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር እቅድ መስማማታቸው ነው። በጭራሽ ከእግዚአብሔር ጋር ተከራክረው አያውቁም። አድርጉ ብሎ የነገራቸው ነገር ላይ አጉረምርመው አያውቁም።
ፍጽምናቸው በራሳቸው አልነበረም።
በሥራ ቦታ የሚገለጡ ፍጹምነቶች በሁለት ይመደባሉ። ከልክ በላይ ከፍ ያለ ውጤት በማምጣት ላይ ያተኩራሉ ወይም አንዳች እንኳ ስሕተት ባለመስራት ላይ ያተኩራሉ። ሁለቱም አካሄድ በራስ መመካት እና መኩራትን ያስከትላል፤ ይህም የሰይጣን የመጀመሪያው ሐጥያት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሐጥያት በክርስትና ውስጥ ለፉክክር በር ይከፍታል።
“ተመልከቱ እንዴት ያለ መልካምና ስኬታማ የተዋጣልኝ ክርስቲያን እንደሆንኩ”።
“ተመልከቱ ለእግዚአብሔር ምን እንደሰራሁለት”።
“የኔ ቤተክርስቲያን ከናንተ ቤተክርስቲያን ትበልጣለች”።
ኢየሱስ የተናገረው ፍጹምነት ይህን ዓይነት አይደለም።
የግል ውጤታማነት ላይ ትኩረት ማብዛት ሰውን በቀላሉ ከልክ ያለፈ ስር በመስራት እንዲጠመድ ያደርገዋል፤ ይህም ከድካም ብዛት ጭንቀት እና መሰላቸትን ያስከትላል።
ደግሞም በፍጹም መሳሳት አንፈልግም የሚሉ ከሰው ጋር አብረው ለመስራት የሚቸገሩ መሳሳትን የሚሸሹ ሰዎችም እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ ነው። ሙሉ ኃይላቸውን አንድ ሥራ ላይ ብቻ በማድረጋቸው ሌሎች ሥራዎቻቸውን ሳይሰሩ ይቀራሉ።
መካድ የማንችለው አንድ እውነት አለ፤ እርሱም የፈለግነውን ያህል ጥረት ብናደርግ እንኳ የማንጠቅም ባሪያዎች መሆናችን ነው።
ነገር ግን በትክክል ከምንሰራው ነገር ይልቅ የምናበላሸው እንደሚበልጥ ማመን አንፈልግም።
ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ ብዙም አይጠብቅም።
እንግዲህ በዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ እግዚአብሔር በጣም የሚያሳስበው ነገር ምንድነው?
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ይህም ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለመቻላችን ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መውደድ የሚገባንን ያህል አንወድም።
የምናውቀው አንድ ብቸኛ ፍጹምነት ኢየሱስ እራሱ እና የ1769ኙ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ሃሳብ ይገልጽልናል። ሰውን ከሃሳቡ መለየት አይቻልም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን የምትነቅፉ ከሆነ ኢየሱስን መንቀፋችሁ ነው።
ስለዚህ ፍጹም ለመሆን የመጀመሪያው እርምጃችን መሆን ያለበት መጽሐፍ ቅዱስን አለመንቀፍ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ነገር ሁሉ በሙሉ ልባችን ማመን አለብን፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ውስት ያልተጻፉ ነገሮችን በሙሉ እምቢ ማለት አለብን።
በዚህ መንገድ መንፈሳዊ አስተሳሰባችን ፍጹም ይሆናል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ ነው የምናምነውና የምንጠቅሰው።
የዚያን ጊዜ የራሳችንን ሕይወት ጉድለት እና ችግር ምን እንደሆነ በትክክል ለይተን እናውቃለን።
ጳውሎስ የተጠቀመው መፍትሄ በጣም ቀላል ነው።
ለራስህ ሙት፤ ከዚያ ወደ ክርስቶስ አካል ውስጥ ትገባለህ።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 … ዕለት ዕለት እሞታለሁ።
የራስህን ሃሳብ ይዘህ እየኖርክ የእግዚአብሔር አካል መሆን አትችልም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሃሳብ ለእኛ ለመረዳት ከአእምሮዋችን በላይ ነው።
ሮሜ 8፡1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
ለራስህ ስትሞት የዚያን ጊዜ ሕይወትህ ከአንተ ውስጥ ፈስሶ ይወጣል።
የዚያን ጊዜ ብቻ ነው በአንተ ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ መንቀሳቀስ የሚችለው።
ሮሜ 8፡2 በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።
በክርስቶስ ውስጥ ስንሆን ብቻ ነው የሕይወት መንፈስ የሚቆጣጠረን።
በዙርያችን ላሉ ነገሮች እና በዚህ ግዙዝ ዓለም ውስጥ ለሚያዘናጉ ነገሮች ሁሉ ስንሞት እግዚአብሔር ብቻ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረዋል።
እግዚአብሔር የማይወደው አንድ የሰው ድክመት አለ።
እርሱም ስለ ኑሮዋችን ማማረር እና የእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ እንከተለው ዘንድ ለእኛ በጣም ከባድ ነው ብሎ መተቸት ነው።
ዘኁልቁ 14፡36 ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው የተመለሱት ሰዎች ክፉ ወሬም ስለ ምድሪቱ እያወሩ በእርሱ ላይ ማኅበሩ ሁሉ እንዲያጕረመርሙ ያደረጉ፥
የእግዚአብሔር እቅድ ለእኛ አስቸጋሪ ወይም መስዋእትነት የሚጠይቅ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች ያጉረመርማሉ፤ ይነጫነጫሉ። ይህ በጣም አደገኛ ነው።
ዘኁልቁ 14፡37 ክፉ ወሬ ያወሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ።
እነዚህ ሰዎች የነበረባቸው ችግር አስተሳሰባቸው ውስጥ ነበር።
የገጠሙዋቸው ችግሮች ለመፍታት ከእነርሱ አቅም በላይ ነበሩ፤ ስለዚህ አምርረው አለቀሱ።
የገጠማቸውን ችግር እግዚአብሔር እንደሚፈታላቸው በእግዚአብሔር ላይ እምነት አልነበራቸውም።
እነርሱ ሃሳባቸውን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በተሰጣቸው ተስፋ ላይ በማድረግ ፈንታ ሃሳባቸውን በራሳቸው ብርታት ላይ ነበር ያደረጉት። እንደ እግዚአብሔር ማሰብን ወይም እግዚአብሔርን ማመንን አልተለማመዱም ነበር።
ፍጹምነት ማለት የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ መውደድ እና ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል እንኳ የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም መፈለግ ማለት ነው።
ስለ ችግሮቻችን ከመነጫነጭ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል መውደድ የፍጹምነት ዋነኛው ንጥረ ነገር ነው።
መነጫነጭ ማጉረምረም ስንተው ብቻ ነው በአስተሳሰባችን ፍጹማን መሆን የምንችለው።
የይሁዳ መልእክት የሚያጉረመርሙ ሰዎችን ያወግዛቸዋል።
ይሁዳ 1፡16 እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥
ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ይህ ማለት ከሚመጣው ታላቅ መከራ መዳን ነው።
እያንዳንዱ ሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች ይጠሉኛል ብሎ ከሚፈራ ይል የእግዚአብሔርን ቃል ይበልጥ መፍራት አለበት።
መንቀጥቀጥ አደጋ መኖሩን ያመለክታል። የሚከፈል ዋጋ አለ፤ የምንሸከመው መስቀል አለ።
የሐዋርያት ሥራ 14፡22 የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥
ብዙ መከራ።
ሮሜ 12፡12 በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
ምድራዊ መከራዎች እና ስደቶች በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን ያስተምሩናል። ከመከራ እንዲያድነን እግዚአብሔርን ነው የምንጠብቀው።
ፊልጵስዩስ 2፡13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።
በክርስቶስ ስንሆን ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረናል።
ስለዚህ በሚገጥመን ፈተና ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር እየመራን ነው።
ፊልጵስዩስ 2፡14 ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤
እግዚአብሔር የምናልፍበትን ፈተና እና የሚገጥሙንን ሁኔታዎች ሁሉ አቀናብሮዋቸው ጨርሷል።
መርከበኛ ባሕር ላይ ለምን ነፋስ ተነሳብኝ ብሎ ማጉረምረም አይችልም። ከነፋሱ ጋር ለመተባበር የሸራዎቹን አስተሳሰር መለወጥ አለበት።
እኛም ስለገጠሙን ሁኔታዎች ማልቀስ ወይም ማጉረምረም የለብንም። እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር እኛን ፍጹም ለማድረግ የሚሰራበት እቅድ አካል ናቸው።
ሐዘን ደስታችሁን የሚይዘው ጽዋ የሚቀረጽበት ስለታም ቢላዋ ነው።
ሐዘናችሁ በጣም ጥልቅ በሆነ መጠን ኢየሱስ ከሐዘን ሲያወጣችሁ የምትቀበሉትም ደስታ የዚያን ያህል ጥልቅ ደስታ ይሆናል።
ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ብርቱው መልአክ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው በምድር እና በባሕር ውስጥ የተቀበሩትን ሙታን ሊያስነሳ ይወርዳል።
64-0119 ሻሎም
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
ብርቱው መልአክ የሚወርደው የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ከተገለጡ በኋላ ብቻ ነው።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ከሰማይ ወርዶ ይመጣል ምክንያቱም ሚስጥራቱ በሙሉ ይፈጸማሉ። ሚስጥሩም በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ዘመናት አይሆኑም” ከዚያም ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።
ደግሞስ ለመነጠቅ የሚያስፈልገንን እምነት እንዴት እንደምናገኝ የሚያስተምረን ነገር ቢሆንስ? ይሆንን? እንሮጣለን፣ ከአጥሩ በላይ ዘለን እንሻገራለንን? ከዚያ በኋላ አንድ ነገር ይሆናል፤ ይህ ያረጀ የተዋረደ ሥጋችን ይለወጣል?
ፍጥረታዊ የሆነው አካላዊ ግኡዝ ዓለማችንን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ከሆነው ከንፈሳዊው የሰማይ ዓለም የሚለይ ግድግዳ አለ።
65-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያመጣውም
አዎን የሞት “ሰራዊት” ከመገስገስ የሚያግደው የለም፤ ድንበርን ሁሉ ጥሶ ያልፋል። በፍጥረታዊው እና በመንፈሳዊው መካከል ይዘላል፤ ወደ እግዚአብሔር እቅፍ፤ ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ውስጥ ዘልቆ ይገባል። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።
መጀመሪያ የእግዚአብሔር ምስጢራት ወደ ወንድም ብራንሐም መውረድ አለባቸው፤ ከዚያ በኋላ እርሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ይገልጣቸዋል።
የዚያን ጊዜ ብቻ ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ መውረድ የሚችለው።
ስለዚህ ሁለት ምጻቶች አሉ።
የሚስጥራቱ ምጻት እና ከዚያ በኋላ ደግሞ የዚያ ብርቱ መልአክ ምጻት።
63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት
… ምስጢሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይወርዳል፤ በእግዚአብሔር ቃል መልክ ይመጣና የእግዚአብሔርን ሙሉ መገለጥ ይሰጠናል።
ማሕተሞቹ ሲፈቱ እና ሚስጥራቱ ሲገለጡ መልአኩ ይወርዳል፣ መልእክተኛው፣ ክርስቶስ ይመጣል፤ እግሮቹን በባሕር እና በምድር ላይ አድርጎ ይቆማል፤ ከራሱ በላይ ቀስተ ደመና ይታያል።
አሁን ልብ በሉ ይህ ሰባተኛ መልአክ በዚህ ምጻት ጊዜ በምድር ላይ ነው።
“ይህ ምጻት” አንድ ምጻት ነው። ሁለት ምጻት አይደለም።
የትኛው ምጻት? የምስጢራቱ ምጻት ወይስ የመልአኩ ምጻት?
… አሁን ደግሞ በ10ኛው ምዕራፍ ከመጪው ጊዜ በኋላ ተመልሶ ይመጣል፤ የዚያን ጊዜ ሚስጥር ሁሉ ይፈጸማል፤ የዚያን ጊዜ ማሕተሞች ሁሉ ይፈታሉ፤ ከዚያ በኋላ ዘላለማዊነት ውስጥ እንገባለን። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም ይገለጣል።”
ሚስጥራቱ ከመገለጣቸው በፊት መልአኩ ወደ ምድር መውረድና ሙታንን ማስነሳት አይችልም። ሚስጥራቱ በወንድም ብራንሐም አገልግሎት መጨረሻ ላይ ብቻ ነው የተገለጡት።
ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ወንድም ብራንሐም ብርቱው መልአክ ወርዶ ሙታንን ሲያስነሳ ድምጹን ለመስማት እየተጠባበቀ ነበር።
65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ከእግዚአብሔር የሚወርዱትን ሚስጥራት ለመቀበል በምድር ላይ መሆን ነበረበት።
በዚያውም የተጻፉጽን ሚስጥራጽ በመግለጥ መጽሐፉን መክፈት ችሏል።
ስለዚህ ብራንሐም መልአኩ ሙታንን ለማስነሳት ወደ ምድር በሚወርድበት ሰዓት ምድር ላይ መሆን አላስፈለገውም።
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
በሙሽራይቱ አካል ውስጥ ያሉ አማኞች በሙሉ የተገለጠውን ቃል መረዳት መቻል አለባቸው ምክንያቱም መልአኩ የሚመለሰው መጽሐፉ ለእነርሱ ከተከፈተላቸው በኋላ ብቻ ነው።
ራዕይ 10፡10 ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።
ዮሐንስ እንደ አንድ ግለሰብ ነው የሚንቀሳቀሰው።
የተጻፈውን ቃል ይበላዋል፤ በሆዱም ያብላላዋል ደግሞም ትርጉሙን ያስተውለዋል ምክንያቱም ወንድም ብራንሐም (ሰባተኘው መልአክ) የዚህም መጽሐፍ መገለጥ አምጥቷል።
በሆዱ ውስጥ መራራ ሆኖበታል ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚቃወሙ ሰዎች እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉትን ሰዎች የሚያሳድዱ ብዙዎች ናቸው።
ነገር ግን በአፉ ውስጥ ጣፋጭ ምስክርነት ነበረ ምክንያቱም ኢየሱስ ከመከራ ሁሉ አድኖታል።
ሰዎች የ1769ኙ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም አይደለም፤ ስሕተት አለበት ስለዚህ ንጹህ የእግዚአብሔር ድምጽ አይደለም ብለው ይከራከራሉ።
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
መጽሐፍ ቅዱስን አድምጡ፤ በዚህ ዘመን እናንተን የሚጠራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ እርሱ ነው።
63-1226 የቤተክርስቲያን ሥርዓት
አንድ ፍጹም የሆነ መመሪያ ያስፈልገናል፤ ለእኔ ፍጹም የሆነው መመሪያዬ ደግሞ ቃሉ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
65-0429 የሙሽራይቱ መመረጥ
ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እወዳለው ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። መሆኑን ደግሞ አምናለው። ደግሞም ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምናለው።
አስተሳሰባችን ፍጹም የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እውነት መሆኑን ስናምን እና ጥልቅ የሆኑትን ሚስጥራት እውነት መማር ስንወድ ነው።
ፍጹም የሆነው እረፍታችን የሚመጣው የሚገጥሙንን ፈተናዎች አንዳችም ያለማጉረምረም እስክንቀበል ድረስ ሕይወታችን በክርስቶስ ውስጥ ሲሰወር ነው። የሚሆንብን ነገር ሁሉ ለመልካም እንደሚሆን በእምነት እናስተውላለን። ስለዚህ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር አደራ እንሰጣለን።
ፍጹምነታችን በራሳችን ሥራ አይደለም።
የእኛ ፍጹምነት የሚገለጠው ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እና እግዚአብሔር ለዘመናችን ያዘጋጀውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ስናምን እንዲሁም የሕይወታችንን መከራዎች እግዚአብሔር እንደሚቆጣጠራቸው ስናምን ነው።
እምነታችን ፍጹም ሊሆን የሚችለው ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር መሆኑን በሙሉ ልባችን ስናምን ነው።
እምነታችን ፍጹም የሚሆነው ኢየሱስን ከነገር ሁሉ ከፈተና በዚህ ሕይወት ውስጥ ከሚገጥሙን ፈተናዎች ሁሉ በላይ ከፍ ስናደርገው ነው።