ማቴዎስ ምዕራፍ 05፡1-24. የተራራው ስብከት ክፍል 1



ኢየሱስ ሰዎች ለመከተል ከሚችሉት በላይ ከፍ ያለ መርህ አስቀመጠ። ቸልተኝነት፣ ትዕቢት፣ እና ትምክሕት ይህን ተራራ ከመውጣት ሊያሰናክሉን ይችላሉ።

First published on the 6th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

የተራራው ስብከት።

ኢየሱስ ስብከቱን ከተራራ ላይ ሆኖ ሰበከ፤ ተራራ በፊታችን ተደቅኖ መንገድ የሚዘጋ ከፍ ያለ መሬት ነው።

ከዳንን ብቻ ሁሉ ነገር የሚያልቅ መስሎን ነበር። መዳናችን ወደ ሰማይ ለመግባት በቂ መሆኑ እውነት ነው።

ነገር ግን በዘላለማዊው የማይሞት አካል ውስጥ ሆነው (በቅርቡ) በሰማይ ወደሚደረገው የሰርግ እራት ግብዣ የሚታደሙ ልባም ቆነጃጅት አሉ፤ በአንጻሩ ደግሞ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ የሚገቡ ሰነፍ ቆነጃጅትም አሉ። እነዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱና ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልበልጥ ቤተክርስቲያንን የሚወዱ ሰዎች ዘላለማዊ አካላቸውን የሚያገኙት ከፍርድ ቀን ቀጥሎ 1,000 ካለፈ በኋላ ነው። ሁለቱም ወገኖች ቆነጃጅት ተብለዋል፤ ምክንያቱም ሁለቱም የዳኑ ክርስቲያኖች ናቸው፤ ቆነጃጅት ማለትም ንጹሆች ማለት ነው።

ነገር ግን በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ የሚያስተምረን ትምሕርት ከተፈጥሮአዊ አቅማችን አልፈን እንድንሄድ ያደርገናል። ሆኖም ወደ ሰማይ የሚነጠቁት የልባሞቹ ቆነጃጅት አካል መሆን ከፈለግን ይህንን ተራራ እንድንወጣ ይመክረናል።

በመሰረቱ ይህ ትምሕርት በሰው አቅም የማይቻል ነገር ነው።

እውነተኛ ክርስትና ማለት ይህ ነው።

እውነተኛ ክርስትና የክርስቶስ ሙሽራ ለመሆን የሚደረግ ከባድ ጥረት ነው።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ይህ መዳን ከሲኦል አይደለም። ምክንያቱም በሥራ ከሲኦል መዳን አንችልም።

በዚህ የቤተክርስቲያኖች ስሕተት በበዛበት፣ ኢየሱስ ከቤተክርስቲይን በር ውጭ በቆመበት አስፈሪ ዘመን ውስጥ እያንዳንዱ አማኝ የተወሰኑ የቤተክርስቲያን ትምሕርቶችን መጣል አለበት። ይህንን ሰው ፓስተሩም ጉባኤውም ይጠሉታል። ስለዚህ አንድን ሰው ሊያስፈራው የሚችለው በሰዎች የመገፋት እና በብዙዎች ስድብ እና የቃላት ጥቃት መካከል ለብቻ መቆሙ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ላይ የምንደርስበት መንገድ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ተቀባይነትን ማግኘት ለሚፈልጉ ለፈሪዎች የተዘጋጀ አይደለም።

ዕብራውያን 6፡1 ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥

ከሞተ የሐጥያት ሥራችን ንሰሃ መግባት እና በእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ማመን ወደ መንግስተ ሰማያት የምንገባበት መሰረቶች ናቸው።

መዳን በጣም ወሳኝ ነገር ነው፤ ነገር ግን ከመዳን በኋላ በኢየሱስ ዳግም ምጻት ጊዜ ወደ ሰማይ መነጠቅ ከፈለግን በክርስትና ሕይወት ውስጥ የማደግ ሌላ ሂደትም አለ።

መጀመሪያ መዳን አለብን። ከዚያ ደግሞ መቀደስ። ቀጥሎ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት። ያን ተከትሎ የሚያስፈልገን የ2,000 ዓመታት ዕድሜ ባለው የክርስቶስ አካል ውስጥ ቦታህን ማግኘት። (ይህ የመጨረሻው ደረጃ ከሁሉ በላይ አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ አሳሳች ነገር አለ።)

ልባሞቹ ቆነጃጅት ግን የክርስቶስ ሙሽራ ለመሆን ወደ ፍጻሜ እየገፉ ይሄዳሉ።

ይህ ግብ በክርስትና ሕይወታቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተሰጡትን ሰዎች ብቻ ነው የሚስባቸው።

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ የክርስቶስ ሙሽራ ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን እየተከተለች ትኖራለች።

የእግዚአብሔርን ሚስጥራት የመረዳት ከባድ ሥራ የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ግባቸው ነው። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ኢየሱስ እንዴት እንደሚያስብ መረዳት የሚችሉት። ነገር ግን ይህ ጥረት ከቤተክርስቲያን መሐይምነት እና ስሕተት ጋር የሚደረግ ጠንካራ ትግል ውስጥ ያስገባናል።

የፈለግነውን ያህል ብንታገል እንኳ ይህንን ተራራ በራሳችን ብርታት ልንወጣው አንችልም።

ይህ ተራራ በእኛ እና ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ በሚመሰረተው፣ ብዙውን ጊዜ ሚሌኒየም ተብሎ በሚጠራው የ1,000 ዓመት ሰላም በምድር ላይ በሚያመጣው በእግዚአብሔር መንግሥት መካከል እንደ ግድግዳ ሆኖ ይቆማል።

ሆኖም ግን የእግዚአብሔርን የሺህ ዓመት መንግሥት የወደፊቱ መኖሪያችን አድርገን ማየት ከፈለግን ከዚህ ኢየሱስ ቆሞ ከሰበከበት ተራራ አናት ላይ መውጣት አለብን።

ዳንኤል ይህንን መንግሥት ከአሕዛብ ምስል መፈራረስ ውስጥ የሚነሳ ታላቅ ተራራ አድርጎ ነው የተመለከተው።

 

 

ዳንኤል አራት የብሉይ ኪዳን ዘመን የአሕዛብ መንግሥታትን የሚወክል የአሕዛብ ምስል አየ።

የእነዚህ መንግሥታት አሕዛባዊ መንፈስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ ሲኖር ቆይቶ ከዚያ በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገባ። ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተነስቶ በልጆችዋ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ገባ።

በዚያ ዘመን መዳን የአይሁዶች ነበረ፤ ነገር ግን በቀራንዮ አይሁዶች ኢየሱስን እንደ ሰው ሲገፉት መዳን ከእነርሱ ወደ አሕዛብ ተሻገረና የአሕዛብ ምሱሉ እግር ውስጥ ገባ፤ ይህም እግር ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል።

 

 

ከእግሮቹ መጨረሻ ወይም ጫፍ ላይ ያሉት 10 ጣቶች በታላቁ መከራ ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሆኖ የሚነሳውን ፖፕ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ የሚያግዙትን አሥሩን ወታደራዊ አምባ ገነን መንግሥታት ይወክላሉ። ይህም አሕዛብ ኢየሱስን ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለመቀበላቸው የመጨረሻ ውጤት ነው። ቤተክርስቲያኖች፣ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ጨምሮ የ1769ኙ እትም ኪንግ ጄምስ ባይብል የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አያምኑም። ስለዚህ ኢየሱስ ትችት እንደ ወረደበት ወይም እንደተነቀፈው መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል።

ስለዚህ የጌታ ምጻት የአሕዛቡን ምስል እግሩ ላይ እንደሚመታው ድንጋይ ነው አመጣጡ።

 

 

ጌታ ኢየሱስ በምጻቱ ጊዜ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ሰዎች ከሙታን ያስነሳቸዋል። እነዚህ ሙታን በመንፈሳዊ እይታ ሲታዩ ጉልላት የሌለው ፒራሚድ ይመስላሉ። ይህች እንደ ፒራሚድ የምትመስል ሙሽራ በአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች እና በዓለም ውስጥ በሚገለጠውና የእግዚአብሔር ቃል ላይ በሚያፌዘው ቃሉን በሚቃወመው ዓለማዊ ሥርዓት እየተረገጠች ትቆያለች።

የጉልላቱ ድንጋይ የቤተክርስቲያን ግንበኞች የናቁት ድንጋይ ነው። ለዚህ ነው ቤተክርስቲያኖች የማይቀበሉዋችሁ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ሙሉ በሙሉ የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር አንቀበልም ብለው ከራሳቸው ውስን የሰዎች አስተሳሰብ እና መሐይምነት ጋር ተቀምጠው መቅረትን መርጠዋል።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ።

የተከፈተችዋን መጽሐፍ የያዘው ብርቱ መልአክ ማለትም ከአሕዛብ ለሆነችው ሙሽራ ሙሉ በሙሉ የተገለጠው መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ምድር ይወርድና በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ቅዱሳን ከሙታን ያስነሳቸዋል። እነርሱም ጉልላት የሌለው ኃያል መንፈሳዊ ፒራሚድ ይሆናሉ። ከሙታንም በተነሱ ጊዜ የጌታን መምጣት ይጠባበቃሉ ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው ሙሉ ለሆነችዋ ቤተክርስቲያን ራስ መሆን የሚችለው። ፒራሚዷን ሊወስዳት የሚመጣው የጉልላት ድንጋይ ሊወስዳት በመጣበት ጊዜ የአሕዛብን ዓለማዊ ሥርዓት ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ እንዲወድቁ በማድረግ ያጠፋቸዋል።

 

 

ጉልላቱ መንፈሳዊቷን ፒራሚድ ሙሉ ያደርጋታል፤ ከሙታን የተነሳችውን ሙሽራይቱን ቤተክርስቲያንም ወደ ሰማይ ይነጥቃታል።

በዚያው ጊዜ ደግሞ የጉልላት ድንጋዩ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰዎች እውቀት የተመሰረቱትን የአሕዛብ ስልጣኔዎችን ፈጭቶ አድቅቆ ያጠፋቸዋል።

61-0806 የዳንኤል ሰባተኛ ሳምንት

በዚያ ፒራሚድ ላይ ጉልላት አላኖሩም ነበር። በሰው እጅ የተቀረጸ አልነበረም። የእግዚአብሔር እጅ ነው ያንን ድንጋይ ጠርቦ ያወጣው። ገብቷችኋል? ይህ ድንጋይ ሄዶ ምን አደረገ? ቀጥ ብሎ ሄዶ ምስሉን እግሩ ላይ መታው፤ ሰባብሮ በምድር ላይ እንደ ዱቄት ፈጨው። ሃሌሉያ። ያኔ ድንጋዩ በመጣ ጊዜ ምን ተፈጠረ? ቤተክርስቲያን በክብር ወደ ላይ በመነጠቅ ሄደች ምክንያቱም ድንጋዩ የአሕዛብ ዘመን እንዲያበቃ አደረገ። በዚያ ድንጋይ መምጣት አማካኝነት እግዚአብሔር የአሕዛብን ዘመን ወደ ፍጻሜ አመጣው።

እግዚአብሔር ስለ ዘመናዊው የሰዎች እውት የሚያስበው ይህንን ነው። ሙሉ በሙሉ የማይጠቅም የድንጋይ ስብርባሪ እንደሆነ ነው የሚያስበው።

 

 

የአሕዛብ ምስል መፈጨቱ እግዚአብሔር ከሰዎች ስልጣኔ እና ከሰዎች ቴክኖሎጂ አንዳችም ነገር አይፈልግም ማለት ነው። የእኛ እውቀት ብክለትን፣ መርዝን፣ ጎጂ ጨረሮችን፣ ጀርሞችን እና ቫይረሶችን፣ ቆሻሻ፣ ስግብግብነትን፣ ጉቦን፣ ራስ ወዳድነትን እና ግፈኝነትን አስከትሏል። ያለ ማቋረጥ የራሳችንን መብት ለማስከበር መፈለጋችን ለለኢየሱስ አዲሱ የሺህ ዓመት መንገስት የማንበቃ አድርጎናል።

የሰው እውቀት ወደ መንግሥቱ አያስገባንም።

በዚህ ሃሳብ ውስጥ ጥልቅ ትርጉም አለ።

ተራራውን መውጣት የምንፈልግ ከሆነ የግል እውቀታችን፣ ብርታታችን፣ እና ጥረታችን በሙሉ ተደምረው ምንም የማይጠቅሙ የጊዜ ብክነቶች ናቸው።

እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ነገር በጣም ከባድ ነው።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል የሚደረግ ከባድ ጦርነት ውስጥ አካል እንደሆንን ይገልጣል።

ይህም በግል መንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ የተሰጠን ክርስቲያኖች የመሆናችን ጉዳይ ብቻ አይደለም። ከዚያ በተጨማሪ አሁን ባለንበት በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ከሚገለጠው የእግዚአብሔር ቃል እውነት አንጻር የት እንደቆምን ማወቅ አለብን።

የተገለጠውን እውነት መረዳት እንችላለን ወይስ አንድ ሰው እውነትን ሊያስረዳን ሲሞክር የሚነግረንን አንቀበልም ብለን እንገፋዋለን?

እውነተኛው ጦርነት በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ነው ያለው፤ ጦርነቱም የሰውን አእምሮ ለማግኘት ነው።

ሰይጣን ከእኛ ይልቅ ኃይለኛ እና ጥበበኛ ነው። ስለዚህ በራሳችን ብርታት ልናሸንፈው አንችልም።

ስለዚህ ልናሸንፈው የምንችለው እግዚአብሔር እንዲዋጋልን ስንፈቅድ ብቻ ነው፤ ደግሞም በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መኖር አለብን እንጂ በራሳችን ምኞቶች መሰረት መኖር የለብንም።

በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደገፍ ያስፈልገናል።

የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ነው የሚያሸንፈው።

ዘጸአት 15፡6 አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤ አቤቱ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ።

ማቴዎስ 26፡64 ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።

ለዳግም ምጻት ለመዘጋጀት የሚያስችለን ብቸኛው ኃይል በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ኃይል ውስጥ መሆናችን ነው።

በቀኝ እጁ ውስጥ ሰባት ከዋክብት አሉ። እነዚህም ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተላኩ መልእክተኞች ናቸው። ስለዚህ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መዋቅር ውስጥ መግባትና መግጠም አለብን፤ ይህም ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ ግድ ይለናል።

ከቤተክርስቲያን ተክል ላይ መከር ሆና የምትታጨደው ሙሽራ መጀመሪያ በሐዋርያት አማካኝነት ከተተከለው የሙሽራዋ ዘር ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለባት። የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ዘመናት ወይም የቤተክርስቲያን ዘመናት አንድ ዓይነት ናቸው።

 

 

በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ብቻ ነው ተራራውን ለመውጣት መጀመር እና ከጌታ ምጻት እና ከእኛ መካከል የቆሙትን ግድግዳዎች ማለፍ የምንችለው።

እኛ ግን የአሁን ችግራችንን ብቻ የማየት ዝንባሌ ነው ያለን። እየተገለጠ ያለውን ጠለቅ ያለውን መንፈሳዊ እውነታ እንዳናስተውል ታውረናል፤ ይህም የተገለጠ እውነታ ዘመናችንን በሚያጋጥሙት ድሎች እና መሰናክሎች ውስጥ ይመራዋል።

እኛ አሁን በምንኖረው ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ሃላፊነት የግል ዓላማችንን እንድናሳካ መርዳት ይመስለናል። ነገር ግን ሕይወት የተሰጠን የእግዚአብሔርን ታላቅ እቅድ የማሳካት አካል እንድንሆን ነው። መጀመሪያ ግን የእግዚአብሔርን ታላቅ እቅድ መረዳት አለብን። እግዚአብሔር በ2,000 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የአሕዛብን ቤተክርስቲያን ሲገነባ ቆይቷል። እኛም በዚያ ታላቅ አካል ውስጥ ቦታችንን አግኝተን መያዝ አለብን።

የእግዚአብሔር ሃሳብ ከእኛ እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ እንቅስቃሴዎቹን መረዳት ለእኛ ከባድ ነው።

ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።

ይህም ማለት ስለ ምንም ነገር ብናማርት እግዚአብሔርን አንወደውም ማለት ነው።

መከራን እንደ መጥፎ ነገር ስንመለከተው እግዚአብሔር ለእኛ ያሰበውን ሃሳብና ዓላማ እንድንከተል አልጠራንም ማለታችን ነው። በዚህ ዓይነት አመለካከታችን የራሳችንን ዓላማ ብቻ እየተከተልን እና እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ጣልቃ ገብነት እየተቃወምን ነው።

የእግዚአብሔርን እውነት መውደድ መልመድ አለብን፤ እግዚአብሔር እያደረገ ስላለውም ነገር በፍጹም ማጉረምረም የለብንም። ይህ ለመማር ከባድ ትምሕርት ነው።

ፈተና ሲመጣብን የራሳችንን አስተሳሰብ እንድንለውጥ እና የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ እንድናገኝ ያደርገናል። እግዚአብሔር ነው መንገዱ፤ እርሱ ትክክለኛው የአስተሳሰብ መንገድ ነው።

ነፋስን የሚነፍስበትን መንገድ መለወጥ አንችልም፤ ነገር ግን የመርከባችንን ሸራ በትክክለኛው መንገድ በመወጠር ነፋሱን ተጠቅመን ወደምንፈልግበት አቅጣጫ መሄድ እንችላለን።

በዚሁ መንገድ የእግዚአብሔርን መንግሥት ማስቀደም እንችል ዘንድ አስተሳሰባችንን መለወጥ እንችላለን።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

34 ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።

ይህ ለእኛ ለሰዎች የሚቻል ነገር አይደለም። በራሳችን አስተሳሰብ ውስጥ ሁልጊዜ ስለ ወደፊቱ እናቅዳለን፤ የተሸለ ነገር ለወደፊት ማግኘት እንፈልጋለን።

የእውነት መጽሐፍ ቅዱስን መከተል ፍላጎት ይኖራችሁ እንደሆን ማወቅ የምትችሉት የተሻለ እና ይበልጥ አስደሳች እንዲሁም የሚስብ የሚመስለንን ነገር መተው ስንችል ነው።

ስለዚህ ሕይወት የእግዚአብሔርን ቃል ትታችሁ ብትሄዱ ምንም ችግር እንደሌለው እንዲመስላችሁ የሚያደርጉ አማራጮችን ዘወትር ታቀርብላችኋለች።

ለምሳሌ ከባድ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ለጊዜው ደስታ እንዲሰማቸው እና ጭንቀት ቀለል እንዲልላቸው ብለው ው መጠጥ ዘወር ይላሉ። ሆኖም ችግሮቻቸው እዚያው ባሉበት ይቀጥላሉ፤ ሰዎቹ ግን በችግራቸው ላይ ከአልኮል መጠጡ የተነሳ በማግስቱ ድባቴ እና ራስ ምታት የመሳሰሉ ችግሮችን በራሳቸው ላይ ይጨምራሉ፤ ከዚያም የባሰውን የአልኮል ሱሰኝነት ችግር ደርበው ይሸከማሉ።

 

 

የሸክላ እቃዎች በሚሰሩበት ሰዓት ለስላሳ ስለሆኑ ቅርጽ ለማስያዝ ያመቻሉ። የሸክላ እቃዎች የሚጠነክሩት ከእነርሱ በሚበልጥ ምድጃ ውስጥ ባለ የከሰል ፍም ውስጥ ነው። ስለዚህ የፈተናን፣ የትችትን እና የስደትን እሳት በያዙ ጠላቶች መካከል ተከብበን መኖር ያስፈልገናል፤ ይህም ያጠነክረንና ለአገልጋይነት ብቁ ያደርገናል።

በስተመጨረሻ እንደ እሳት ስለሚፋጁትና እግዚአብሔር ይጠቀምብን ዘንድ ብቁ ስለደረጉን የተቃውሞ እሳት ፍሞች እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።

ጠላቶቻችን ጠንካራ ሲያደርጉን እግዚአብሔር ይጠቀምብናል፤ ጠላቶቻችን ደግሞ ይወድቃሉ።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ሁለት ሥራ ይሰራል።

እኛን የክብር እቃዎች እንድንሆን ሲመርጠን በዙርያችን የሉትን ጠላቶቻችንን ደግሞ የውርደት እቃዎች እንዲሆኑ መርጧቸዋል። እግዚአብሔር እርሱን ለማገልገል የበቃን እቃዎች እንድንሆን መርጦናል።

ራዕይ 3፡18 ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ … ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።

የተቃውሞ እና የስደት እሳት ያስፈልገናል።

ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥

ኢየሱስ ወደ በረሃ እንደሚለቀቀው ፍየል ሆኖ ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወስዶ በሰይጣን ላይ ለማራገፍ ወደ ሲኦል በመውረዱ ምክንያት በሲኦል እሳት ውስጥ ስለ ማለፍ ሙሉ በሙሉ ያውቃል።

ዳንኤል ባየው ምስል ውስጥ እግሮቹ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ። ዳንኤል ባየው ምስል ውስጥ ያለው ሸክላ ሙሽራይቱን ይወክላል። ስለዚህ በእግሮቹ ውስጥ ያለው ሸክላ በእቶን እሳት ውስጥ ማለፉ አያስደንቅም።

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

ሸክላ ሰሪው ሸክላውን እንዴት አድርጎ እንደሚሰራው እና የክብር እቃ ይሆን ዘንድ እንዴት አድርጎ እንደሚያጠነክረው ያውቃል፤ ይህ የሚሳካው ግን እኛ የሚያቃጥሉትን ፍሞች እና ፍሞቹን የያዛቸው ትልቅ ምድጃ ላይ ካላመጽን ነው። ፍሞቹ የሚሰሩት አስቀድሞ የተሰጣቸውን ሥራ ብቻ ነው።

መልካም ባሕርይ፣ ትዕግስት፣ እና ጽናት ሊዳብሩ የሚችሉት በማያቋርጥ ትግል ውስጥ በከባድ መንገድ በማለፍ ነው።

እኛ ስንወለድ ጀምሮ ሐጥያተኞች ሆነን ነው የተወለድነው፤ ስለዚህ ሐጥያታችንን ይቅር ሊለን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ፍቅር መቅመስ ያስፈልገናል። በእጆቹ ላይ ያሉት ጠባሳዎች ሁልጊዜ እርሱ ስለ ሐጥያታችን የከፈለውን ዋጋ ያስታውሱናል። አዳኙ አስፈላጊያችን መሆኑን ስናውቅ በውስጣችን ያለው ትዕቢት ጥሎን ይሄዳል። ሐጥያት አጥፍቶን እንደ ነበር እና እኛም ወደ ሲኦል እየተንደረደርን እንደነበርን ስናውቅ ሐጥያት ለመስራት ያለን ፍላጎታችን ይለቀናል። ሐጥያት የሚያስከትላቸውን ሐዘን እና ብዙ አሳዛኝ መከራዎች እናውቅ ዘንድ በሐጥያት መወለድ አስፈልጎናል። ይህም ሐጥያት የሌለበትን ዓለም ለማየት እንድንመኝ ያደርገናል። እኛ እራሳችን ሐጥያታችን ይቅር ከተባለልን በኋላ በሌሎች ሰዎች ላይ የምንሰነዝረውን ትችት እንድንቀንስ እና ለሰዎች መልካም አዛኝ እንድንሆን ያደርገናል።

መከራ እና ስቃይ በራሳችን ወይም በሌላ ሰው ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ልባችን ኢየሱስን መደገፍ እስኪለምድ ድረስ በውስጣችን እምነትን ያሳድግልናል

በእርሱ ውስጥ ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለን እንጂ ከስጋ አንወለድም።

ፍጹም የሆነውን አካላችንን የምናገኘው በጌታ ምጻት ጊዜ ብቻ ነው። እስከዚያ ጊዜ ድረስ በራሳችን ብርታት የማናሸንፈው እንደ ተራራ ትልቅ የሆነ ትግል አለብን።

ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች እና የ2020 ዓ.ም ኮሮና ቫይረስ ምድር ኢየሱስ የሚነግሥበትን የ1,000 ዓመታት የሰላም መንግሥት ልትወልድ ስትቃረብ የመጡባት የወሊድ ምጥ ናቸው።

የመጨረሻው የወሊድ ምጥ የሚሆነው አርማጌዶን ነው።

 

 

ከዳንን በኋላ እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚጠብቅ ለማወቅ የተራራውን ስብከት እንመልከት።

ማቴዎስ 5፡1 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤

ሕዝቡ ወደ መንግስተ ሰማያት የሚያስገባውን መንገድ ማወቅ ፈልገዋል። ኢየሱስም መንገዱ ተራራ እንደመውጣት የሚመስል ከባድ ትግል መሆኑን አሳያቸው። ተራራ መውጣት ከባድ ሥራ ነው፤ ሆኖም ግን ከወጣን በኋላ የማናገኘው እይታ ድካማችን እንዳይቆጨን የሚያደርግ ነው።

ከዚያም እርሱ ተቀመጠ።

የትምሕርት አሰጣጥ ዘዴው እንደ ቲያትረኞች አይደለም። አንዳችም የሰውን ስሜት ለመቀስቀስ ሙከራ አላደረገም። ታላቁ መምሕር በትምሕርቱ ውስጥ ቁም ነገርን ብቻ ነበር የሚያካፍላቸው፤ አብዛኞቹ ተናጋሪዎች እጆቻቸውን በማወዛወዝና ወዲያ ወዲህ በመዝለል የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ የሚጠቀሙበትን ዘዴ አልተጠቀመም።

ማቴዎስ 5፡2 አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦

ሕዝቡ ሙሉ ትኩረታቸውን ሰጥተው ሲያዳምጡት ነበረ። ቃሉ ከአፉ ከመውጣቱ ከሰኮንድ በፊት አፉ መከፈቱን ሳይቀር አስተውለዋል።

ቃሎቹ ታላቅ ዋጋ ያላቸው እና በሰዎቹ አእምሮ ውስጥ ተቀርጸው የሚቀሩ ነበሩ። ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዴት ማሰብና አእምሮዋቸውን መጠቀም እንዳለባቸው እያስተማራቸው ነበር። ሲያስተምራቸው ስሜታቸውን እየቀሰቀሰ አልነበረም።

እነርሱ ሊሰሙ ከጠበቁት ፈጽሞ የተለየ ነገር ሊነግራቸው ነው።

ማቴዎስ 5፡3 በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ብፁዓን ማለት በውስጣቸው ደስተኛ የሆኑ ናቸው።

የእርሱ ጥበብ ከእኛ ጥበብ ፈጽሞ የተለየ ነው።

በመንፈስ ድሃ ማለት ሰዎች በገፉን እና በወደቅን ጊዜ የሚሰማን ስሜት ነው።

ነገር ግን ሰዎች ኢየሱስን መግፋታቸው አይቀሬ ስለሆነ እውነት በሰዎች ዘንድ እንደምትገፋ ማወቅ አለብን።

በሰዎች መገፋታችን ብዙውን ጊዜ በትክክለኛው መንገድ ላይ ለመሆናችን ምልክት ነው።

ሉቃስ 18፡13 ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።

ይህ ቀራጭ በመንፈስ ድሃ ነበረ። እራሱን ከፍ አላደረገም። ቀራጩ እራሱን ምንም ዋጋ እንደሌለው ምስኪን ሰው በመቁጠር ሙሉ በሙሉ እራሱን በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ጣለ።

የስኬቱም ሚስጥር ይህ ነው።

በራሱ እና በሥራው በግል ጥረቱ አልተመካም።

ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ምሕረት እና ጸጋ ላይ ነው የተደገፈው።

ሉቃስ 18፡14 እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።

ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ይህ የማይለወጥ ሕግ ነው።

ራስህን ከሌሎች በላይ ከፍ ከፍ ብታደርግ እግዚአብሔር ከከፍታህ ያወርድሃል።

ራስህን ዝቅ ብታደርግ እና ለራስህ ምንም ክብር ባትፈልግ እግዚአብሔር ከፍ ያደርግሃል።

እኛ ለራሳችን ከምናደርገው ተቃራኒውን ነው እግዚአብሔር የሚያደርግልን።

ስለዚህ የእግዚአብሔር አሰራር ከእኛ አስተሳሰብ ጋር አብሮ አይሄድም።

ብቸኛው መፍትሄ ለራሳችን መሞት እና ምሪትን ለማግኘት የእግዚአብሔርን ቃል መመርመር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ሊነግረን የሚችለው።

የራስህ ሃሳቦች እና የቤተክርስቲያንህ ሃሳቦች የሚያስተማምኑ አይደሉም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 … ዕለት ዕለት እሞታለሁ።

ሙታን ወይም እሬሳዎች ለራሳቸው አያስቡም፤ ደግሞም አያጉረመርሙም።

ለራሳችን ሞተናልን? ወይስ ለራሳችን መብት እንከራከራለን?

ማቴዎስ 5፡4 የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መፅናናትን ያገኛሉና።

ሐዘን ያጣነው ነገር እንዳለ ያመለክታል።

ወዳጅ ዘመድ ሲሞት የሚፈጠረው የእጦት ስሜት ለክርስቲያን በጣም ከባድ ነው።

ማጣት በክርስትና ውስጥ እምነታችን ላይ ከሚመጡ ፈተናዎች ውስጥ ከባዱ ፈተና ነው።

1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6 ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤

የደረሰብን እጦት ምንም ያህል ከባድ ቢሆን በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ረክቶ መኖርን መለማመድ አለብን።

ይህም ከሰው ችሎታ በላይ ነው።

ተስፋ በቆረጠው አእምሮዋችን ውስጥ ተረጋግተን መኖር የሚያስችለን የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው።

በጣም የምንወደው እና የሚያስፈልገን ሰው በሞት ሲለየን ሐዘኑ ወደ ኢየሱስ እቅፍ ውስጥ እንድንገባ ይገፋናል። ከሁሉም ቦታ ይልቅ ሰላም የምንሆነው በክርስቶስ እቅፍ ውስጥ ነው። ሰው እንደመሆናችን የራሳችንን ሐዘን ማጥፋት አንችልም። ኢየሱስ ብቻ ነው ሐዘናችንን የሚያስረሳን።

ማቴዎስ 5፡5 የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።

የዋሆች በጸጥታ ለእግዚአብሔር የሚገዙ ሰዎች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች ሲሰድቡዋቸው መልሰው አይሳደቡም፤ ዝም ይላሉ ወይም ለስለስ ያለ መልስ ይሰጣሉ።

እነዚህ ሰዎች በትዕግስታቸው ነፍሳቸውን ያድናሉ፤ ሌላ ነገር ማዳን ቢያቅታቸውም ነፍሳቸውን ግን ያድናሉ።

ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።

የዋህነት ማለት ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራስን ማስገዛት ነው።

እርሱ ጠርቶኛልና ወደ የትም ቢመራኝ በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢያሳልፈኝ እንኳ እከተለዋለው።

የዋህነት ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የመከተል ፍላጎት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የመመራት ፍላጎት ነው። ሌሎች ሰዎች በሚሉት መሄድ አይደለም።

ማቴዎስ 5፡6 ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።

አንዳንድ ሰዎች ሳይበሉ ሳይጠጡ ተርበውና ተጠምተው ይኖራሉ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን መንግሥት ጉዳይ አስቀድመው የሥጋ ፍላጎታቸውን ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣሉ።

እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሔር ሳይታዘዙ ከመኖር ይልቅ ያለ ምግብ መኖርን ይመርጣሉ።

ምግብ እና ውሃ ለኑሮ አስፈላጊ መሰረታዊ ነገሮች ናቸው። የእነዚህ ሰዎች የመሰጠታቸው መጠን ግን እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ እግዚአብሔርን ለመፈለግ እና ለመከተል ብለው እነዚህን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንኳ ሳይቀር ወደ ጎን ትተዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለመረዳት ጥልቅ የሆነ ፍላጎት። ይህ እውነተኛ መብል ነው።

ከኢየሱስ ጋር ጠለቅ ያለ ሕብረት ለማድረግ ጠንካራ ፍላጎት ማሳየት። ይህ እውነተኛ መጠጥ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እና የእግዚአብሔርን መንፈስ ለማወቅ አጥብቆ መናፈቅ። የራበው ሰው ምግብን አጥብቆ የሚፈልገውን ያህል።

ማቴዎስ 5፡7 የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።

የዘራኸውን ታጭዳለህ።

ወንጀለኞች ዋጋቸውን ሲያገኙ ማየት እና ፍትህ ሲሰፍን ማየት ደስ ይለናል። የበደለንን ሰው እድል ስናገኝ መበቀል እንፈልጋለን።

በሐሳባችን ውስጥ በፊት የደረሱብን በደሎች ቶሎ ተፍቀው አይወጡም።

አሁን ግን አዲስ መንገድ መጥቷል።

የበደላችሁ ሰው ምሕረት የማይገባው ቢሆንም እንኳ ይቅር በሉት፤ ምሕረት አድርጉለት።

እኛ ምሕረት የማይገባን ሆነን ሳለ እግዚአብሔር ከሐጥያታችን እንዲያድነን ስንጠይቀው በምሕረቱ ላይ ተደግፈን ነው።

እኛም ለሌሎች እንዲሁ ምሕረት ማድረግ አለብን። ምንም በቢድሉን እንኳ መማር አለብን።

 

 

ማቴዎስ 18፡21 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።

22 ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።

በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመት የሚል ትርጉም አለው።

ላባ ለያዕቆብ እንዲህ አለው፡-

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

አይሁዶች እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ 70 ሳምንታት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል። ይህም 70 x 7 ቀናት ማለት ነው።

ዳንኤል 9፡24 … በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።

ስለዚህ “ሰባ ጊዜ ሰባት” ማለት እስከ ዘመን ፍጻሜ ማለት ነው።

በሌላ አነጋገር የሚበድለንን ሰው ይቅር ማለታችንን ማቆም የለብንም ማለት ነው።

ታድያ መጨረሻው እስካሁን ለምን አልመጣም?

ምክንያቱም ልክ አይሁዶቹ መሲሁን በገደሉ ጊዜ እግዚአብሔር ዓመታቱን መቁጠር አቆመ።

እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘወር አለና የቀረችዋን ግማሽ ሱባኤ ወይም ሳምንት ወደ ፊት ወደ ዓለም ፍጻሜ አርቆ ገፋት።

 

 

ዳንኤል 9፡27 እርሱም [እግዚአብሔር] ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል [ከአብራሐም ጋር የገባውን]፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።

ኢየሱስ ለሶስት ዓመት ተኩል አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ በቀራንዮ ተሰቀለ። ይህም ለሰዎች ሁሉ መዳንን አመጣ። ከዚያ በኋላ የአይሁዶች መስዋእቶች በሙሉ ዋጋቸውን ስላጡ ተቋረጡ።

ነገር ግን ያች የመጨረሻዋ የአይሁዶች 7 ዓመት ትፈጸም ዘንድ የቀረ ሦስት ዓመት ተኩል አለ።

ማቴዎስ 5፡8 ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

ልብ የሚወክለው ፍላጎቶቻችንን እና ስሜቶቻችንን ነው።

ራስ ወዳድነት። እኔ እኔ ብቻ ማለት። ስግብግብነት። ታላቅ ለመሆን መፈለግ። ጥላቻ። ምኞት። ሰዎችን የመግዛት ፍላጎት።

ሰዎች እነዚህን ክፋቶች ከልባቸው ማስወጣት አይችሉም።

ሁልጊዜ የግል ጉዳዮች በልባችን ውስጥ ቦታ ይይዛሉ።

እግዚአብሔር ሃሳባችንን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር በመፍቀድ ብቻ ን የልብ ንጽሕና እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው።

ነገር ግን ስንቶቻችን ነን እርሱ ይህንን እንዲያደርግ የምንፈቅደው?

ለራሳችን መሞት ብንችል ብቻ ብዙ ነገር ይስተካከል ነበር።

 

 

ማቴዎስ 5፡9 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።

አስተራራቂዎች ሙሉ በሙሉ ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋቸዋል። በሚያስተራርቁ ጊዜ የሁለቱንም ወገኖች ፍላጎት እኩል ማዳመጥ አለባቸው። በፍጹም ሳያዳሉ ማስታረቅ መቻል የራሳችንን ሚዛን የሳተ አመለካከትና ሃሳብ ወደ ጎን መተው አለብን ማለት ነው። ሁሉም ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል ነው መወሰን ያለበት።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በእሥራኤል ላይ ግልጽ የሆነ አድሎ በመፈጸሙ ምክንያት የብዙ ሃገሮችን አክብሮት አጥቷል።

እኛ ሰዎች የቤተሰባችንን ፍላጎት ወይም የማሕበረሰባችንን (ወይም የብሔራችንን) የሃገራችንን ፍላጎት ማስቀደም እንወዳለን።

ለምሳሌ ናይጄርያ 200 ያህል የተለያዩ ብሔሮች አሏት። ግጭቶችን በመፍታት ጊዜ ለእያንዳንዱ የሚያስደስት ነገር ማድረግ እጅግ በጣም ከባድ ነው።

እኛ እራሳችን ሰላማዊ በሆንን መጠን ልዩ ልዩ የሆኑት ማሕበረሰቦቻችንም ተባባሪዎች ይሆናሉ።

ነገር ግን በሎዶቅያ ዘመን ሎዶቅያ ማለት “የሕዝቡ መብት” እንደመሆኑ እያንዳንዱ ማሕበረሰብ ወይም ቤተሰብ ወይም ግለሰብ የራሱን መብት እንዲከበርለት አጥብቆ መጠየቅ ያበዛል፤ ይህም ግጭቶችን ይቀሰቅሳል።

የዛሬ ዜና ሁከትና ብጥብጥ ሙስና እና ግፍ ይበዛበታል፤ ይህም ዘመናችን ከእግዚአብሔር የሰላማዊነት መርህ ምን ያህል እንደወደቀ ያስረዳል።

በዚህ ዘመን የአሜሪካ ባሕል በሁሉም ሕዝብ ላይ ገዥ ባሕል ሆኗል። የአሜሪካ ባሕል ያማረኝን ሁሉ ማግኘት አለብኝ ማለትን እና ራስ ወዳድነትን የሚያበረታታ ባሕል ነው። በዚህም ምክንያት የሰዎች ማንነት ባላቸው ገንዘብና ንብረት ነው የሚወሰነው እንጂ በሥራቸው መሆኑ ቀርቷል። ይህ ዓይነቱ ራስ ወዳድነት ማሕበረሰብ ውስጥ መከፋፈልን ይፈጥራል። ሰለዚህ ለነጻነት ያለን አመለካከት ከሌሎች ሰዎች ላይ ነጥቀን ለራሳችን ጥቅም ማግኘት ሆኗል። ይህ ዓይነቱ አካሄድ መጨረሻው ግጭት፤ ብጥብጥ እና ኪሳራ ነው።

አሁን የተፈጠረው ነገር በማሕበራዊ ሚድያ አማካኝነት አመጸኛ ሰዎች በሕዝብ ላይ ገዥ የሆኑበት ነው። በሌላ ወገን ደግሞ የእኛ ቤተክርስቲያን የምትለው ብቻ ነው ትክክል ብሎ ሌሎች አመለካከቶችን ቸል ማለት ነው።

የሰው አስተሳሰብ በምድር ላይ ሰላምን አላመጣም።

የሚያሳዝነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉ ሰዎች የሚሰማቸው አጥተዋል።

ማቴዎስ 5፡10 ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ሰይጣን እውነትን ይጠላል። ሰይጣን ሰው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን እንዲተው ይፈልጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አብራሐም ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

ሮሜ 4፡5 … እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

ጽድቃችን መልካም ሥራችን አይደለም፤ ጽድቃችን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ያለን እምነት ነው።

ኢሳይያስ 64፡6 ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤

መልካም ሥራዎቻችን እንኳን በእግዚአብሔር ዓይን ሲታዩ ንጹህ አይደሉም። ለዚህ ነው በሥራ መዳን የማንችለው።

ዛሬ ግን ተነስታችሁ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹምና ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል ነው ብላችሁ ብትናገሩ ፍጹም ትክክል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የለም የሚሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ያወግዙዋችኋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም ጥቅም ላይ የዋሉትን ጥንታዊ ጽሑፎች ይተቻሉ፤ የተርጓሚዎቹንም እወቀት ያጣጥላሉ። ምን ማለታቸው ነው፤ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ሊሰጠን አይችልም እያሉ ነው። ስሕተታቸው ምን ያህል ርቆ እንደሄደ አስተውሉ። እግዚአብሔር ማድረግ የማይችለው ነገር አግኝተናል ይላሉ።

እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ሊሰጠን አልቻለም።

በሌላ በኩል ደግሞ የሜሴጅ ሰባኪዎች የወንድም ብራንሐም ንግግሮች በሙሉ የእምነታችን መሰረት ናቸው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት በወንድም ብራንሐም ንግግሮች በመጠቀም ፈንታ መጽሐፍ ቅዱስን በወንድም ብራንሐም ንግግሮች ይተካሉ። ወንድም ብራንሐም የማይሳሳት ሰው ነው መልእክቶቹም (ስብከቶቹም) አንዳች ስሕተት የለባቸውም ይላሉ።

62-1007 የበሩ መክፈቻ

… በጣም ብዙ ውሸቶችን ሰምታችኋል፤ እኔ ምንም እንደማልሳሳት ተወርቷል፤ ደግሞም ሌሎችንም ውሸቶች ሰምታችኋል።

መጽሐፍ ቅዱስን ትቶ መሄድ መንፈሳዊ ምድረ በዳ ውስጥ እንደሚከተን ነብዩ ዳንኤል አስጠንቅቆናል።

ወንድም ብራንሐም የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ነበረ። በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ ቃል አልተገባልንም።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም “የእግዚአብሔር ድምጽ ነው” ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው አነጋገር ነው።

የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

64-0719 የኢዮቤልዩ በዓል

ጌታ ሆይ አሁን በሕይወት ያለን ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ድምጽ በቃሉ ውስጥ ሲናገረን መስማታችንን እና ማየታችንን እናስተውል ዘንድ ፈቃድህ ይሁንልን፤

65-1204 መነጠቅ

በክርስቶስ ከሆናችሁ በዚህ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በሙሉ ታምኑታላችሁ።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው ትክክለኛ የእምነት መሰረት ነው ብለው የሚቀበሉ ሰዎችን የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ አይቀበሉዋቸውም። የእነዚህ ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን ይነቀፋሉ፤ ስማቸው ይጠፋል፤ ይሰደባሉ።

ይህም የሚያስተምረን ሽልማታችን በምድር ሳይሆን በሰማይ መሆኑን ነው። ለጊዜው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን እያመንን የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶቸን እያገጣጠምን እውነትን በመረዳት መኖራችንን እንቀጥላለን።

ማቴዎስ 5፡11 ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

ተራራውን መውጣት በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ አያደርጋችሁም።

ሰዎች ያሳድዷችኋል፤ ይጠሉዋችኋል። ቢቻላቸው ሊጎዱዋችሁ ሁሉ ይፈልጋሉ። በብዙ የሃሳት ወሬዎች ስማችሁን ያጠፋሉ።

የሚያሳዝነው ነገር ሲቀወሙዋችሁ የሚቃወሙት እናንተን አይደለም። እነርሱን የሚያንገሸግሻቸው ስትናገሩ የምትጠቅሱት መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

በጥንቃቄ የተገነባው ሰው ሰራሽ እምነታቸው ውስጥ ያሉትን ስሕተቶች መጽሐፍ ቅዱስ ያጋልጥባቸዋል።

እነዚያ ስሕተቶች ሲጋለጡ ኩራታቸው ይተነፍሳል።

ማቴዎስ 5፡12 ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

መከራ እና ስደት የቤተክርስቲያን ታሪክ አካል ሆነው ቆይተዋል።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ታላቅ መልእከተኛ ሆኖ የተላከው ቅዱስ ጳውሎስ ምን እንደደረሰበት ተመልከቱ።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡24 አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ።

25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።

26 ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፤

27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።

በጨለማው ዘመን ውስጥ ካቶሊክ መሆን አንፈልግም ያሉ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።

ማቴዎስ 5፡13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።

ጨው ሥጋ እንዳይበሰብስ ይከላከላል። ሥጋ አስተምሕሮን ይወክላል። ትክክለኛ አስተምሕሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ከፍ አድርጎ መኖር ነው።

ብዙ ችግር እና መከራ ቢደርስባቸውም እንኳ ክርስቲያኖች ለዓለም ትልቅ አርአያ ሆነው መታየት አለባቸው። በሌብነት እና በክፋት ውስጥ ባለመሳተፍ ክርስቲያኖች በማሕበረሰብ ውስጥ ያለው ክፋት እንደ ልቡ እንደዳይንሰራፋ ማዕቀብ ያደርጉበታል። ስለዚህ ክርስቲያኖች ክፋት እንዳይስፋፋ ገደብ ያበጃሉ። ክርስቲያኖች በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገሮችን በሙሉ ላለመቀበል ውሳኔ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ክርስቲያኖች ተወዳጅነት ወይም ተቀባይነት ለማግኘት ብለው ከሚሰክሩ፣ ከሚያጨሱ፣ ከሚሳደቡ እና በፖርኖግራፊ ከተጠመዱ ሰዎች ጋር አብረው ቢውሉ እነርሱ የሚያደርጉትን ሁሉ ቢያደርጉ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ዋጋዋን አጥታለች ማለት ነው። የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ተብሎ ስሕተትን እንደ እውነት መቀበልም ዋጋ የሌለው ድርጊት ነው።

ስብከት ሁልጊዜ ተደላድለው የተቀመጡትን ከምቾታቸው የሚያስነሳ መሆን አለበት። ክርስትና የመጣው ዓለማዊነትን ለማበረታት እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶችን ለመደገፍ አይደለም።

መጥምቁ ዮሐንስ በሰበከበት ጊዜ ሁሉ ሰዎች ሐጥያተኝነታቸው ተሰምቷቸው ንሰሃ ይገቡ ነበር።

ማቴዎስ 5፡14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

ብርሃናችን ምንጩ ክርስቶስ እና ቃሉ ነው። እኛ የራሳችን የሆነ ብርሃን የለንም፤ ስለዚህ የክርስቶስን ብርሃን ማለትም ቃሉን ነው የምናንጸባርቀው።

በተራራ ላይ ያለች ከተማ የሚለው ቃል በተራራ ላይ ከተማ ለመስራት የሚጠይቀውን ዳገት የመውጣት ትግል ያመለክታል። ክርስቲያኖች ኑሮ የሚያመጣባቸውን ትግል በትዕግስት የመታገል ምሳሌ በመሆን የክርስቶስን ሕይወት ማንጸባረቅ አለባቸው።

ከተራራ ጫፍ ላይ መሆን ከተማይቱ በዙርያዋ ካሉ ሃገሮች ይበልጥ ከፍ ያለ መገለጥ እንደምታገኝ ያመለክታል።

ዙርያችሁ ምንም ያህል መጥፎ፣ የማይመች ወይም አስቸጋሪ ቢሆን እንኳ ከዚህ ሁሉ ችግር በላይ ከፍ በማለት ሰይጣን በምድር ላይ ያመጣውን ክፋት ሁሉ እግዚአብሔር ልጆቹን በመርዳት አሸንፈው ለመኖር እንደሚያስችላቸው ማሳየት አለባችሁ።

እግዚአብሔር በሁኔታዎች ሁሉ ከሰይጣን በላይ ኃይለኛ መሆኑን ለሰይጣን ማሳየት ይፈልጋል።

ኢየሱሰ አንድም ጊዜ አጉረምርሞ አያውቅም። ኢየሱስ የራሱን ሰብዓዊ ፈቃድ በውስጡ ለሚኖረው ለልዕለ ተፈጥሮአዊው የእግዚአብሔር ፈቃድ አስገዝቶ ነው የኖረው።

ሉቃስ 22፡42 ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።

እኛ ማልቀስ እና የሰው ልብ እንዲራራልን ማድረግ እንፈልጋለን። ነገር ግን በገጠመን ችግር እያለቀስነ መንከባለል ተራራ ለመውጣት አያበቃንም።

ሁል ጊዜ ዓይናችንን ከራሳችን ምኞቶች ላይ አንስተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማየት አለብን።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የስኬት ሚስጥር ይህ ነው። እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ አብዝቶ እንዲኖር በፈቀድን ቁጥር ሕይወት የምታመጣብንን ተግዳሮት ሁሉ ማሸነፍ እንችላለን። ብርታታችን የሚመጣው ከላይ ነው።

የእግዚአብሔር ተራራ ላይ ያለው አስተሳሰብ እኛ ከለመድነው አስተሳሰብ የተለየ ነው።

ጠላቶቻችሁን ውደዱ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው። አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።

ይህ ዓይነቱ መገለጥ ሊመጣ የሚችለው ከላይ ብቻ ነው።

እንደዚህ ዓይነቱን ሕይወት መኖር ወደ ተራራው ለሚወጣ ክርስቲያን ከፍ ያለ የሥነ ምግባር ዓለም ውስጥ መኖር ያስችለዋል።

ማቴዎስ 5፡15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

የድሮ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቲዎዶር ሩዚቬልት እንዲህ ብሎ ነበር፡- “ተግዳሮት የሌለበት ሥራ የለም። ነገር ግን ባለመሳካት ውስጥ ሆኖ ጥረትን መቀጠል በራሱ ስኬት ነው። ጥረትን መቀጠል ሽንፈትንም ሆነ ድልን የማያውቁ እጃቸውን አጣጥፈው ከሚቀመጡ ሰዎች የተሻለ ኑሮ ነው።”

በቤተክርስቲያን ውሰጥ ያሉት ሰነፍ ቆነጃጅት በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚጓጉ ሰዎች ናቸው። ከአስተምሕሮ ጋር በተያያዘ በሚመጡ ጥያቄዎች ላይ ከመነጋገር ሸሽተው ከብዙሃኑ ጋር መስማማትን ይመርጣሉ። ቤተክርስቲያናቸው የምታስተምራቸውን ስሕተት ለመቃወም ይፈራሉ፤ ከቤተክርስቲያንም እንዳይባረሩ በጣም ይሰጋሉ። ስለዚህ የራሳቸውን ምቾትና ደህንነት ለመጠበቅ ይተጋሉ፤ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት ለመግለጥ አንዳችም ሚና አይጫወቱም።

ትችቶች እና ስደት ቢበዙባትም እንኳ ሙሽራይቱ የተገለጠውን እውነት ይዛ መቆም አለባት። ሙሽራይቱ ይህንን በማድረጓ ቤተክርስቲያኖች ቸል ብለው የጣሉት ጠለቅ ያለ እውነት መኖሩን እንዳይረሱ ታደርጋቸዋለች።

ይህን በማርደጓም ይጠሏታል፤ ይንቋታል።

ማቴዎስ 5፡16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።

ምንም ነገር ቢደርስብህ የእግዚአብሔርን ቃል እያበራህ ኑር።

እግዚአብሔር እኛ ከምናውቀውም ይበልጥ ጠለቅ ያለ እቅዱን እያዘጋጀ ነው። ዋናው ነገር የእግዚአብሔር መንግሥት እንጂ የእኛ የግል ሕይወት አይደለም።

መልካም ሥራዎች አያድኑንም ነገር ግን እውነቱ እንዳይነቀፍ እና ዋጋ እንዳያጣ መልካም ሥራዎችን እንድንሰራ እግዚአብሔር ይፈልግብናል።

ማቴዎስ 6፡10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤

እገዚአብሔር ዘመናችንን ከፊታችን ላለው ከጌታ ምጻት እና ተከትሎት ለሚመጣው ታላቅ መከራ እያዘጋጀ ባለበት በዚህ ጊዜ የግል ሕይወታችንን ከእኛ ለሚበልጠው ለእግዚአብሔር እቅድ ማስገዛት አለብን።

ሒትለር ባደረገው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ውስት ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን ሞተዋል። የዓለም ሕዝቦች ለአይሁዳውያን እንዲያዝኑ እና ከተስፋይቱ ምድር ላይ በከፊል ተቆርሶ ይሰጣቸው ዘንድ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚያስፈልገው ዋጋ ይህ መሆኑን አላወቁም ነበር። ከዚያ በኋላ በ1948ቱ የነጻነት ጦርነት ብዙ አይሁዳውያን ሞቱ። ነገር ግን ተዓምረዊ በሆነ መንገድ አረቦችን አሸነፉ፤ የያዙትን የተስፋይቱን ምድር ማስፋት የሚችሉበትም ብቸኛው መንገድ ያ ነበር። ከዚያ በኋላ በጣም ስኬታማ የሆነውን የስድስት ቀን ጦርነት በ1967 በማድረግ ከተስፋይቱ ምድራቸው አብዛኛውን መልሰው ተቆጣጠሩ። ነገር ግን ከመስገብገባቸው የተነሳ ለአብራሐም ያልተሰጠውን የሲና በረሃ ጨምረው ወሰዱ።

በ1973 አይሁዶች በራሳቸው መመካታቸውን ያለ ልክ ሲያበዙ ባልተዘጋጁበት ከባድ ጥቃት ደረሰባቸው። ሪቻርድ ኒክሰን የአየር ኃይል ሰራዊትን በመጠቀም ድጋፍ አደረገላቸው። እነርሱም ግብጽን እና ሶሪያን አሸነፉ፤ ነገር ግን የሲናን በረሃ ለግብጽ መልሰው ለመስጠት ስምምነት አደረጉ። ኒክሰን በዎተርጌት ቅሌት የተነሳ ከስልጣኑ ለመውረድ ተገደደ። እግዚአብሔር “መጥፎ ሰው” የተባለውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ተጠቅሞ እሥራኤልን አዳነ። እሥራኤልን የማዳን ዓላማ ኒክሰን ካለበት ስነምግባራዊ ጉድለት የሚበልጥ ቦታ ተሰጥቶታል። እግዚአብሔር ዓላማውን ለመፈጸም ሁልጊዜ መልካሞቹን ሰዎች ብቻ አይደለም የሚጠቀመው። ኒክሰን ግን እሥራኤልን ለመርዳት በተነሳ ጊዜ የራሺያዎችን እና የአረቦችን ተቃውሞ ለመቋቋም ድፍረት ነበረው።

እሥራኤሎች የሲናን በረሃ ለግብጽ እንዲያስረክቡ በማድረግ እግዚአብሔር በስተ ደቡብ በኩል ከሰጣቸው የተስፋይቱ ምድር ድንበር እንዳያልፉ አደረጋቸው።

በቅርቡ “መልካም ሰዎች” ተብለው የሚቆጠሩት ፕሬዚዳንቶች ኢየሩሳሌምን የእሥራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እውቅና ለመስጠት የአረቦችን ቁጣ ፈርተው አፈግፍገዋል። እግዚአብሔርም ሌላ “መጥፎ” የተባለ ሰው ማለትም ዶናልድ ትራምፕ የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ባልተጠበቀ መንገድ እንዲያሸንፍ አድርጎ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና እንዲሰጥ አድርጎታል።

ትንቢት የሚፈጸምበት ሰማያዊው የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰዎችን ድካም እና ጉድለት ሁሉ አልፎ ይሄዳል። እግዚአብሔር ለቃሉ የሚቆሙ በጥፎ ሰዎችን ድፍረታቸውን ይወደዋል፤ እንደዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች እግዚአብሔር ዓለምን ለመቃወም እና ለቃሉ እውነት ለመቆም ከሚፈሩ መልካም ሰዎች የበለጠ ይወዳቸዋል።

ሙሴ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ ግን ደግሞ ፈርኦንን ለመጋፈጥ ያልፈራ ሰውም ነበረ። እግዚአብሔር ዛሬም ቆራጥ ሰዎችን ይፈልጋል።

እግዚአብሔር አሁን ትልቁ ሃሳቡ ለመሲሁ ዳግም ምጻት የተስፋይቱን ምድር ማዘጋጀት ነው።

ስለዚህ ከእያንዳንዱ አይሁዳዊ የግል ሕይወት በላይ እግዚአብሔር አይሁዳውያን ሁሉ ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው የሚመለሱበትን ታላቅ እቅድ ሲያዘጋጅ ነበር፤ እነርሱም በትንቢት እንደተነገረው በተስፋይቱ ምድራቸው ሆነው መሲሃቸውን ይገናኙታል። ይህ እኛ ሁላችንም በግል ጉዳዮቻችን ስለምንጠመድ የምንረሳውና ሳናይ የምናልፈው የትልቁ እቅድ አካል ነው።

ማቴዎስ 5፡17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።

የብሉይ ኪዳን ሕግ እና ነብያት ልክ እን ቢራቢሮ እጭ ሆነው ቆይተው በአዲስ ኪዳን ዘመን አድገው ቆንጅዬ ቢራቢሮ ሆነው ተገልጠዋል።

ሕጉ እና ነብያት በብዙ ምሳሌዎች እና ጥላዎች የተሞሉ ነበሩ፤ እነዚህም ጥላዎች ሁሉ ወደ ኢየሱስ እና ወደ ሰባቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ነው ሲያመለክቱ የኖሩት።

በሕጉ ውስጥ የእሥራኤልን ሐጥያት እንዲያስወግዱ ሁለት ፍየሎች ይመረጡ ነበር። አንደኛው ፍየል የሐጥያታቸውን ዋጋ ለመክፈል ይታረዳል፤ ሁለተኛው የሚለቀቀው ፍየል ደግሞ ሐጥያታቸውን ተሸክሞ ሁለተኛ ተመልሶ መምጣት ወደማይችልበት በረሃ ውስጥ ይለቀቅና እየዞረ ይጠፋል።

ይህ ሥርዓት ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሳኤው ጊዜ የሚያደርገውን አገልግሎት የሚያሳይ ጥላ ነበረ። ኢየሱስ ሞተና ተመልሶ ተነሳ። ፍየሎች ግን ሞተው መነሳት ስለማይችሉ ነው ሁለት ፍየሎች ያስፈለጉት።

ኢየሱስ የሁለቱንም ፍየሎች አገልግሎት ፈጽሟል።

ኢየሱስ ሞተና በቀራንዮ የሐጥያታችንን ዋጋ ለመክፈል ደሙን አፈሰሰ። ከዚያም እንደሚለቀቀው ፍየል ሐጥያታችንን ከእኛ አርቆ ይዞ በመሄድ ሲኦል ውስጥ በሰይጣን ላይ አራገፈው።

ስለዚህ የኢየሱስ ሕይወት በሕጉ ውስጥ ያሉትን ምሳሌዎች እና ጥላዎች ሁሉ ወደ ፍጻሜ አምጥቷቸዋል።

ማቴዎስ 5፡18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

በሕጉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ዝርዝር ነገር ትርጉም አለው፤ ፍጻሜም አለው።

ቤተ መቅደሱ በመስቀል ቅርጽ ነበር የተሰራው።

 

 

“ንሰሃ ግቡ” የሚለው ትዕዛዝ መሰዊያው ላይ ነው፤ ያም ኢየሱስ ለሐጥያታችን ሞቶ ወደ ሲኦል የወረደበት ነው።

“በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ” የሚለው ትዕዛዝ ደግሞ ከመታጠቢያ ሰን ጋር ነው የተያያዘው፤ ይህም የውሃ ጥምቀትን ያመለክታል።

“የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ትቀበላላችሁ” የሚለው ቃል በቤተመቅደሱ ውስጥ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ጋር የተያያዘ ነው። በዚያም ስፍራ የ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምሳሌ የሆነውን ባለ ሰባት መብራቱን መቅረዝ እናያለን። 12ቱ የገጹ ሕብስት የተባሉት እንጀራዎች በታላቁ መከራ ዘመን የሚኖሩት ከ12 የእሥራኤል ነገዶች የተወጣጡት 144,000ው አይሁዳውያን ናቸው። ሕብስቱ የሚበላው በቅደሱ ስፍራ ነው። ስለዚህ አይሁዶች መሲሁን ለመገናኘት ወደ ተስፋይቱ ምድር መመለስ አለባቸው።

ቅድስተ ቅዱሳኑ እግዚአብሔር ይኖር የነበረበት ስፍራ ነው። በዚያ የሙሴ ሕግ ነበረ። እግዚአብሔር የሚኖረው በቃሉ ውስጥ ነው። እርዚአብሔር ቃሉን ይገልጥልን እና በውስጣችን ሕያው ያደርገው ዘንድ በሰው ልብ ውስጥ መኖር ይፈልጋል።

“መስቀል” ልብን ለአራት ቦታ ይከፍላል።

 

 

አራት ወንጌሎች የኢየሱስን ሕይወት እስከ መስቀሉ ድረስ ያሳዩናል።

ሕጉ ውስጥ የተጻፈ ነገር በሙሉ ጥልቅ ትርጉም አለው።

ማቴዎስ 5፡19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።

የሕጉን አንድ ክፍል እንኳ ብናፋልስ ችግር ውስጥ ነን ምክንያቱም አብሮት ያለውን ሚስጥራዊ ትርጉምን ጭምር እየካድን ነን።

ክርስቲያኖች መረዳት ያቃታቸውን ጥቅስ እንደ አላስፈላጊ “ዝርዝር” በማየት ትተው ያልፋሉ። በዚህ ድርጊታቸው ግን መሃይምነታቸውን እያሳዩ ነው፤ እነዚያ ጥቅሶች ምን ማለት እንደሆኑ አያውቁም፤ ምን ማለት እንደሆኑ የማወቅ ፍላጎትም የላቸውም።

መጥምቁ ዮሐንስ ሰው እንደመሆኑ ኢየሱስን ለማጥቅ ፈርቶ ነበር። ግን ወዲያ የመስዋእቱ በግ ለመስዋእት ከመቅረቡ በፊት መታጠብ እንደሚያስፈልገው አስተዋለ።

2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም [ሰሎሞን] አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።

አዲስ ኪዳንን በደምብ ስናውቀው ወዲያ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች በሙሉ በአዲስ ኪዳን ውስጥ መፈጸማቸውን እናስተውላለን።

በ2ኛ ነገሥት 5፡14 ከአሕዛብ ወገን የሆነው ሶርያዊው ንዕማን ከለምጽ ለመንጻጽ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እንዲል ታዘዘ። ለምጽ የሐጥያት ምሳሌ ነው። የአሕዛብ ቤተክርስቲያን 7 የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ማለፍ እና ከሐጥያት እንዲሁም ከአለማመን እንድትነጻ በቃሉ ውሃ መታጠብ አለባት።

ዘሌዋውያን 19፡19 ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህ ከሌላ ዓይነት ጋር አይደባለቅ፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።

ሱፍ እና የተልባ እግር ስለ ፍርድ እና ስለ ጽድቅ ነው የሚያመለክቱት፤ ሁለቱ ደግሞ አይቀላቀሉም።

ዳንኤል 7፡9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።

ዳኞች በራሳቸው ላይ የሚያደርጉት ጸጉር ከሱፍ የተሰራ ነው። የእኛ ዳኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህ ዳኛ ለዘመናችን የተገለጠውን እውነት ማወቅ እንዳለብን ይናገረናል። ምንም ማመካኛ የለንም።

 

 

የራስ መሸፈኛ መገዛትን ያመለክታል። በራስ ላይ የሚደረገው የሱፍ ጸጉር ዳኛው ለሃገሪቱ ሕግ ዝቅ ብሎ መገዛቱን ያመለክታል።

በፍርድ ቀን የሚሰየመው ዳኛ ለእግዚአብሔር ቃል መገዛት አለበት።

ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ እርሱ ብቻ ነው ዳኛ መሆን የሚችለው።

ዮሐንስ 5፡22 … ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።

ኢየሱስ ዳኛችን ነው። ነገር ግን ጠበቃችንም ኢየሱስ ነው፤ ምክንያቱም ለሐጥያታችን ሞቶልናል፤ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የተገለጠውን ቃሉን እናስተውል ዘንድ ዓይናችንን ሊያበራልን እየታገለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ተገልጦልን ሙሉውን እውነት ብናስተውለውና ብናምነው የታላቁን መከራ ፍርድ እናመልጣለን።

ስለ አብራሐም እንዲህ ተብሏል፡-

ሮሜ 4፡5 ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

አብራሐም ጻድቅ ለመሆን ምንም ሥራ አልሰራም። አብራሐም የሐጥያትን ዋጋ ለመክፈል እና ሐጥያተኛውን ለማጽደቅ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን አመነ።

ይህ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ የሆነ እምነት ጽድቅ ሆኖ ተቆጠ።

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

ብቸኛው ትክክለኛ እምነታችን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማመን ነው።

እውነተኛው ጽድቃችን በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ማመናችን ነው።

እኛ ተመችቶን አባል ሆነን ከምንኖርበት ቤተክርስቲያን ትምሕርት ጋር ስለተቃረነ ብለን የእግዚአብሔርን ቃል እንጥላለን?

ቤተክርስቲያን የምታስተምረንን ትምሕርት ትክክለኛነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አለመቻሏን እያየን ማመናችን ጽድቅ አይደለም፤ እምነትም አይደለም። እንዲሁ በሞኝነትና በምኞት መዋለል ነው።

የተልባ እግር የሚወክለው ጽድቅን ነው።

ራዕይ 19፡8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

ሕጉ የተልባ እግር (ጽድቅ) እና ሱፍ (ፍርድ) በአንድ ላይ መስለበስ አትችሉም ይላል።

በሌላ አነጋገር ጻድቃን የሆኑት ቅዱሳን ማለትም ሙሽራይቱ በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል የሚያምኑ ሕዝቦች ወደ ታላቁ መከራ ፍርድ ውስጥ አይገቡም።

 

 

ማቴዎስ 5፡20 እላችኋለሁና፦ ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።

ጻፎች እና ፈሪሳውያን ንጹሕ እና ቅዱስ ሕይወት ይኖሩ ነበር፤ ይህም ጻድቅ የሚያደርጋቸው መስሏቸዋል።

ነገር ግን እውነተኛው ጽድቅ በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሰረተ እምነት ነው። ጻፎች እና ፈሪሳውያን በእግዚአብሔር ቃል ማመን አልቻሉም ምክንያቱም የአይሁዳውያን ጻድቅ መሪዎች አድርገው ራሳቸውን በሾሙበት ሹመታቸው ይመኩ ነበር።

በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ እምነት ነው እውነተኛው ጽድቃችን። እግዚአብሔር በዘመናችን የሚፈልገው ይህን ነው።

መልካም ሕይወት መኖር ጽድቅ ይመስላል ግን አይደለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች፣ ብዙ ሙስሊሞች፣ ብዙ ሒንዱዎች መልካም ሕይወት ይኖራሉ። ሆኖም ግን በመልካም ሥራዎቻችን አንድንም።

ጻድቅ ሰው እንደ ፈሪሳውያን ንጹህ እና የተከበረ ሕይወት ይኖራል። ነገር ግን ከተከበረ ሕይወትም በላይ ያለፈ ነገር ያስፈልገዋል። ምክንያቱም ትክክለኛ ጽድቅ ከቤተክርስቲያን ባርነት በሙሉ ነጻ መሆን እና በዘመንህ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ማመን መቻል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ማመን እስካልቻልክ ጊዜ ድረስ መልካም ሕይወት መኖር ትርጉም የለውም፤ በተለይም ደግሞ የቤተክርስቲያኔን አስተምሕሮ ይቃረናል ብለህ የተገለጠውን እውነት የምትክድ ከሆነ።

ማቴዎስ 5፡21 ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።

ሰውን መግደል ከባድ ሐጥያት ነው። ይህ ለማንም ግልጽ ነው።

ነገር ግን የሰውን ስም ማጥፋትስ? በአስተሳሰባቸው ከአንተ ጋር የማይስማሙ ሰዎችን ስም ማጥፋት።

ይህም ከባድ ሐጥያት ነው።

አስተምሕሮውን መቃወም መልመድ አለብን እንጂ አስተምሕሮውን የሚያራምደውን ሰው አይደለም የምንቃወመው።

የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ትልቁ ድክመቷ ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን ትምሕርቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆናቸውን ማሳየት የሚችሉ ሰዎችን መጥላታቸው ነው። ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ከቤተክርስቲያናቸው ጋር ፍቅር ስለያዛቸው ፓስተሮቻቸውን ብቻ ይከተላሉ። ከሚያምኑት ጋር የሚቃረን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስን ሁሉ ይጥላሉ። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቆ የሚያምነውን እና ከስሕተታቸው ሊያርማቸው የሚሞክረውን ሰው ያወግዙታል። ለዚህ ነው የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ ዛሬ ከቤተክርስቲያን ደጅ ውጭ የቆመው።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

ኢየሱስ እያንኳኳ ያለው የሐጥያተኛውን ልብ ደጅ ሳይሆን ኢየሱስ የሚያንኳኳው የቤተክርስቲያንን በር ነው።

ማቴዎስ 5፡22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።

በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሥላሴን አስተምሕሮ የማይቀበሉ ሰዎችን የሚያወግዝ ጨካኝ ልብ በዝቷል።

ወንድም ብራንሐምን የማይሳሳት፣ የእግዚአብሔር ድምጽ እያሉ በመጥራት ከአምላክ እኩል እስኪሆን ድረስ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ የሜሴጅ ተከታዮች የ1963ቱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የጌታ ምጻት ወይም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ አይደለም የሚሉ ሰዎችን ይጠሉዋቸዋል፤ ይኮንኑዋቸዋል ያወግዙዋቸውማል።

ሮሜ 2፡1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።

በሃሳባቸው የማይስማሙትን የሚተቹ እና የሚያወግዙ ክርስቲያኖች እራሳቸውን እየተቹ እና እራሳቸውን እያወገዙ ነው።

ስለ አስተምሕሮ በተከራከርክ ጊዜ የምትናደድ ከሆነ ሃሳብህን ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳይተህ ማስረዳት አቅቶሃል ማለት ነው።

ስለዚህ አስተምሕሮ ላይ ያለህ እውቀት ባህርይህ ውስጥ እንዳለው ችግር ሁሉ ችግር አለበት ማለት ነው።

አስተምሕሮዋቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ማሳየት አለመቻል ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ንዴተኛ እና ቁጠኛ ያደርጋቸዋል። በተለይም ደግሞ መመለስ የማይችሉትን ጥያቄ ሲጠይቋቸው።

ለምሳሌ በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎቸ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ ከተጠየቁ ይናደዳሉ ወይም ጥያቄውን ሸሽተው ርዕስ ይቀይራሉ። እንደምንም ብለው ዝም ሊያሰኙህ ይሞክራሉ። ለሶስት አካላት የሚሆን አንድ ስም ማግኘት አለመቻላቸውን በማመን ፈንታ ጠፍተሃል ብለው አንተን ሊያስፈራሩህ ይፈልጋሉ።

የቃላት ጨዋታ ውስጥ ይገቡና ኤል፣ ኤላህ፣ ወይም ኤሎሂም ስሞች ናቸው ይላሉ ነገር ግን እነዚህ ቃላት በሙሉ እግዚአብሔር ተብለው ነው የተተረጎሙት። “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል ደግሞ የእግዚአብሔር ስም አይደለም።

ቀጥለው ደግሞ “ጄሆቫ” ነው ሊሉ ይፈልጋሉ፤ እርሱ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም አይደለም፤ ምክንያቱም ዕብራይስጥ አናባቢዎች አልነበሩትም። ትክክለኛው ቃል JHVH ነው፤ እርሱም ደግሞ ሊነበብ ስለማይችል እንደ ስም ልንጠቀመው አንችልም።

ከዚያ በኋላ የሚሉት ሲያጡና ተስፋ ሲቆርጡ “ጌታ” የእግዚአብሔር ስም ነው የሚል የቃላት ጨዋታ ውስጥ ይገባሉ።

እግዚአብሔር “ጌታ” ወይም በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “the Lord” ነው። በእንግሊዝኛ the የምትባለዋ ቃል ከስሞች ጋር አትቀጠልም።

ለምሳሌ “the Jesus” ወይም “the David” አንልም።

ስለዚህ “ጌታ” ልክ እንደ “ነብይ” ማዕረግ ነው። ለምሳሌ “ነብዩ ዮናስ” እንላለን።

ተስፋ ሲቆርጡ “እኔ እኔ ነኝ” ወይም “I AM THAT I AM” የእግዚአብሔር ስም ነው ይላሉ። ያ ግን ስም አይደለም፤ ዘላለማዊነትን የሚገልጽ ንግግር ነው እንጂ።

የሚከተሉትን ጥቅሶች ሳይጠቅሱ ያልፋሉ፡-

ዘጸአት 34፡14 ስሙ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ቅንዓት ያለው አምላክ ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ።

እነርሱ ራሳቸው ቀናተኛ የሚለው ቃል ስም አለመሆኑን ያምናሉ። ቀናተኛ የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር ባህርያት ውስጥ አንዱን ነው የሚገልጸው። እግዚአብሔር ማንም ተነስቶ ከእርሱ ጋር እኩል እንዲሆን አይፈልግም።

የሶምሶን ወላጆች አንድ መልአክ አዩ፤ ኋላ እግዚአብሔር መሆኑን አወቁ። ስሙ ማን እንደሆነ ጠየቁት።

መሳፍንት 13፡18 የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው።

የእግዚአብሔር ስም ሚስጥር ነበረ፤ የተገለጠውም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ተብሎ ነው።

በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ለምን ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ እንዳልተጻፈ ማብራራት አይችሉም፤ ደግሞም “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሙሉ ለምን እንደማይገኝ ማብራራት አይችሉም።

እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስሙን እንዳልገለጠ ለማመን ያስፈራቸዋል።

ስለዚህ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔርን ስም ማግኘት አይችሉም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሙሉ ብትፈትሹ አንድም ቦታ የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ አታገኙትም።

የሥላሴ አማኞች ስሙ “ጌታ” ነው ይላሉ፤ ግን ያ ደግሞ ማዕረግ እንጂ ስም አይደለም።

ስለዚህ በሥላሴ ውስጥ ወልድ ብቻ ነው ስም ያለው፤ ስሙም ኢየሱስ ነው።

ነገር ግን አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር ወልድ አልተባለም”። ይህም ለምን እንደሆነ የሥላሴ አማኞች ማብራራት አይችሉም።

እነዚህ ቃላት ሁሉ ስሞች አለመሆናቸው ማረጋገጫው ሰዎችን ሲያጠምቁ ከእነዚህ ማዕረጎች ውስጥ አንዳቸውንም አለመጠቀማቸው ነው።

ዝም ብለው “በአብ፣ በወልድና፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም” የሚሉትን ቃላት ይደጋግማሉ እንጂ ያ ስማ ማን እንደሆነ የሚያውቁት ነገር የለም። በቃል ተሸምድዶ የሚደገም ፎርሙላ መያዝ የማስተዋልና የመረዳት ጉድለትን ያንጸባርቃል።

ከዚያም ቀጥሎ ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስ ስም ለምን ሶስት ጊዜ በውሃ ጥምቀት ውስጥ እንደተጠቀሰ ማብራራት አይችሉም። ሁልጊዜም ደግሞ የትኛው ኢየሱስ መሆኑን ለማመልከት አንድ ማዕረግ አብሮት ይጠቀሳል ምክንያቱም ዛሬ ኢየሱስ በሚለው ስም የሚጠሩ የተለያዩ ሰዎች አሉ።

ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ሲባል እየተጠራ ያለው ስም የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ መሆኑ ያስታውቃል።

“ክርስቶስ” ስም አይደለም። ክርስቶስ “የተቀባው” የሚል ትርጉም ያለው ማዕረግ ነው።

እነርሱ ግን ሊንቁህ ይፈልጋሉ ምክንያቱም “ሁሉም ቤተክርስቲያኖች በሥላሴ ያምናሉ” ስለዚህ እጅግ ደካማ የሆነውን የሥላሴ ክርክራቸውን መቃወም አይፈቅዱልህም። ክርክር ላይ መሸነፋቸውን እያወቁ ሲመጡ ወደ ቁጣ እና ወደ ስድብ ውስጥ ይገባሉ።

“ጨርቃም” ንቀትን የሚገልጽ ቃል ነው።

“” የሚያዋርድ ስድብ ነው።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ከዚያ በኋላ ያንን ሰው ሊደበድቡትም ይፈልጋሉ ምክንያቱም ሥላሴ ነው ብለው ለሚያምኑት አምላክ ስም ሊያገኙለት አይችሉም።

“እግዚአብሔር ወልድ” እና “አንድ አምላክ በሦስት አካላት” የሚሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላትን ይጠቀማሉ።

ቆላስይስ 2፡9 የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ በአካል ተገልጦ ይኖራል ለምን እንደሚል ማብራራት አይችሉም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በመለኮት ውስጥ ነው ብለው ያምናሉ።

ሐሳባቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረዳት ሲያቅታቸው ሰውን መናቅ እና ማጥላላት የሚችሉ መስሎ ይሰማቸዋል። ከዚያም ሰዎች አቋማቸውን እንዲለውጡ ለማስገደድ ብለው መሳደብ እና ማዋረድ ይጀምራሉ።

ነገር ግን ስለ አስተምሕሮ መወያየት ያለባቸው ከዚህ በታች የተጠቀሰው ቃል እንደሚለው ነው። ሆኖም ይህን የሚያደርግ ብዙም ሰው የለም።

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡24 የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።

25 ደግሞም፦ ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና … ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።

ትሑት ካልሆንን በቀር ከአንድ ሰው ጋር ስለ አስተምሕሮ መወያየት አንችልም።

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡26 ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።

ማቴዎስ 5፡23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥

24 በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።

አስተምሕሮ ላይ በተደረገ ክርክር ውስጥ ክርስቲያን ወንድምህን ብትሰድበው እና ብታዋርደው ወደ እግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ለመግባት ብቁ መሆን አትችልም። ትልልቅ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ቢኖሩህ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ አትችልም። ስለ እግዚአብሔር ብለህ የሚገርሙ መስዋእትነቶችን ብትከፍል እንኳ አይቻልም።

በአስተምሕሮ ላይ አለመስማማት ቢኖር በአክብሮት እና ረጋ ባለ መንፈስ ነው ውይይት መደረግ ያለበት።

ሌሎች ላይ የምታደርገውን ነገር ነው እግዚአብሔርም አንተ ላይ የሚያደርግብህ።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23