ማቴዎስ ምዕራፍ 04. አገልግሎት በመከራ እን በፈተና ሲጀመር
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ቀላል መንገድ የለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ይጠራና ለፈቃዱ ወዲያው እንዲታዘዙ ይጠይቃል። ምንም ሳናጉረመርም መከተል አለብን።
First published on the 6th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ማቴዎስ 4፡1 ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
ክርስትና ለልፍስፍሶች አይደለም። ክርስትና ውስጥ የፈተና እና የመከራ ጊዜም አለ።
የሰዎችን አእምሮ ለመቆጣጠር በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ጦርነት አለ። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን በዚህ ጦርነት ውስጥ ገብቶበታል። እግዚአብሔር አእምሮዋችን ውስጥ የቃሉን እምነት ለመትከል ይጋደላል። ሰይጣን ደግሞ በሰው ጥበብ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ አእምሮዋችን ውስጥ ለመትከል ይጋደላል። ስለዚህ ጦርነቱ የሰው ጥበብ በእግዚአብሔር ቃል ከተደገፈ እምነት ጋር የሚያደርገው ተጋድሎ ነው።
በውስጡ የሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ሰው የሆነውን ኢሱስን ከሕዝብ ራቅ አድርጎ ወደ ይሁዳ ምድረበዳ መራው። እኛ በዙርያችን ባሉ ክርስቲያኖች ተጽእኖ ስለምንንቀሳቀስ በራሳችን አእምሮ ረጋ ብለን ማሰብን አንማርም።
የክርስትና ሕይወት ጉዞዋችንን የምንጀምረው ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን በመቀበል እና ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ እርሱ ላይ በማድረግ ነው።
ከዚያ በኋለ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ስንል ፓስተሩን እና የቤተክርስቲያን እምነቶችን፣ ልማዶችን እንከተላለን።
በግል እምነት ቦታ “የቡድን አስተሳሰብ” ተተክቶ ቁጭ ይላል።
ከዚያ በኋላ እኛም በተመሳሳይ ቅርጽ እንደሚቆረጡ ብስኩቶች ቤተክርስቲያን ከሚመላለሱ ሰዎች አንዱን ሆነን እንቀራለን።
ስለዚህ ኢየሱስ በነጻነት ለራሱ ማሰብ የሚችል ሰው በመሆኑ በብዙ ትግል ነው የኖረው፤ ምክንያቱም ሰው ሁሉ አስተሳሰቡ ከእርሱ ተቃራኒ ነበር።
ከጾመ በኋላ በረሃብ ምክንያት ደከመ።
ስጋችን በደከመ ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መደገፍን እንማራለን።
ማቴዎስ 4፡2 አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
ረሃብ በስጋ ያደክመናል። የዚያን ጊዜ በራሳችን ብርታት መደገፍ አንችልም።
ሰይጣን ከሰማይ የወደቀበት ሐጥያት ትዕቢት እና የእኔነት ኩራት ነው።
1ኛ ዮሐንስ 2፡16 በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥
የአዳም ሙሽራ ሔዋን የወደቀችባቸው ፈተናዎች እነዚህ ናቸው።
ዘፍጥረት 3፡6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤
“ለመብላት ያማረ”። ለአእምሮ የሚሆን ምግብ። የስጋ አምሮት።
“ለአይን የሚያስጎመጅ”። የዓይን አምሮት።
“ለጥበብ መልካም እንደሆነ”። እኔ ከእንተ ይልቅ ጠቢብ ነኝ። የሕይወት ኩራት።
ኢየሱስን የገጠመው ፈታኝም ያው ሔዋንን የፈተናት ነው።
ማቴዎስ 4፡3 ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።
እኛ ሰዎች ለገጠሙን ችግሮች አስቸኳይ ጊዜያዊ መፍትሄ የመፈለግ ዝንባሌ አለን።
ነገር ግን ስጋን ወይም አካልን ለመገንባት የሚያስፈልገው ምግብ ነፍስን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ምግብ ማለትም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በአስፈላጊነቱ እኩል አይደለም
ኢየሱስ በድርጊቱ እያስተላለፈ የነበረው መልእክት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ነገር በጭራሽ ስላለማድረግ ነው።
በእርሱ አመለካከት መንፈሱ እና ቃሉ ከስጋ የበለጠ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል።
ማቴዎስ 4፡4 እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
የስጋ አምሮት። ረሃብ። በተለይም ለአርባ ቀናት ሁሉ ምግብ ሳይበላ ለቆየ ሰው።
ማቴዎስ 4፡5 ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦
የዓይን አምሮት። ይህ ማለት ሰዎች ሁሉ ሊያዩ እና ሊያደንቁ የሚችሉት አስገራሚ ተዓምር በመስራት ኃይል መግለጥ ነው።
ሰዎች መታየት ይፈልጋሉ። የሕዝብ ሁሉ ትኩረት ወደ እነርሱ እንዲሆን ይፈልጋሉ። በሰዎች ዓይን ውስጥ መግባት እና ሰዎች እንዲያደንቋቸው ይፈልጋሉ።
ዝነኛነት መሰረቱ የሰዎች ሁሉ ዓይን በእኔ ላይ መሆኑ ነው። በአደባባይ ተገልጦ መታየት። ሰው ሁሉ አስገራሚ ነገር ሳደርግ አየኝ።
ማቴዎስ 4፡6 መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
ማቴዎስ 4፡7 ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።
ተዓምራት በማድረግ የሰዎችን አድናቆት ለማግኘት ብለን እግዚአብሔር እንዲረዳን መጸለይ የለብንም። በጉራ ለማውራት የምንችልበት ብቃት እንዲኖረን ብለን አደጋን መፈለግ የለብንም።
የራሳችንን ራስ ወዳድ ዓላማ ለማስፈጸም ብለን የእግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ የለብንም።
የእግዚአብሔርን ምሪት መጠየቅና እርሱ የሚነግረንን ማድረግ አለብን እንጂ ሰዎችን ለማስደነቅ ብለን እራሳችን የምንፈልገውን ማድረግ የለብንም።
ማቴዎስ 4፡8 ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦
ስለ ገንዘብ መመካት። ክብር፣ ሃብት፣ አድናቆት፣ ዝና፣ እና ከፍ ያለ ቦታ።
ዓለም ሊሰጠን የሚችለው ሃብት እና በሰዎች ላይ ገዥ መሆን ብቻ ነው። ግን ይሁ ሁሉ እንደ ቅዠት ነው። የዚህ ዓለም መንግስታት ሁሉ የአርማጌዶን ጦርነት ሲመጣ በጦርነቱ ሊጠፉ ተወስኖባቸዋል።
ፖለቲካዊ ስልጣን ግቡ እራስን ማበልጸግ ነው። ፖለቲካ ለራስ ወዳድነታችን እና የራስ ክብር ፈላጊነታችን የሚሆን የጥቂት ጊዜ ክብር ነው። ከዚያ ግን መጨረሻው ከሞት ወዲያ ከእግዚአብሔር መለየት ስለሆነ አስፈሪ ነው። ይህን ያህል ዋጋ ሊከፈልለት የሚገባው አይደለም። ለጊዚያዊ ደስታ ተብሎ ሕይወትን ማጣት ተገቢ አይደለም።
ማቴዎስ 4፡9 ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ማንንም ማምለክ ትልቅ ስሕተት ነው።
የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ የመጨረሻው ፖፕ የመሆንን ስልጣን ነጥቆ ይወስዳል ምክንያቱም ፖፑ ቢካሪየስ ክሪስቲ ይባላል፤ ትርጉሙም በክርስቶስ ቦታ ማለት ነው።
እራሱን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለማወዳደር የሚሞክር ማንኛውም ሰው ወይም እራሱንም ሆነ ሌላ ሰውን ቢአየሱስ ቦታ የሚያስቀምጥ ሰው ሙሉ በሙሉ ተሳስቷል።
ማቴዎስ 4፡10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
እግዚአብሔር ብቻ ነው አምላክ።
የሆነ ሰው በእግዚአብሔር ቦታ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ክርክር ውስጥ እንኳ አትግቡ።
እንደዚህ ብሎ የሚከራከራችሁን ሰው ከአጠገቤ ሂድ ብላችሁ ተለዩት ምክንያቱም ካዳመጣችሁት የሚያሳስት መንፈስ አለው። ማንም ሰው በመለኮት ውስጥ ጣልቃ ሊገባ አይችልም።
ማቴዎስ 4፡11 ያን ጊዜ ዲያብሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።
መላእክት በመንፈሳዊው ክልል ውስጥ ሰው ሳያያቸው ነው ስራቸውን የሚያከናውኑት። ነገር ግን በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ የሚሰሩት እኛን ለመርዳት ነው። እኛ ከምናስበው በላይ እጅግ ብዙ እኛን ሊረዱ የሚችሉ መላእክት አሉ። አንድ አማኝ እነዚህ የማይታዩ የመላእክት ሰራዊት እንደ ጋሻ ይጠብቁታል።
ኢየሱስ ሰይጣንን ያሸነፈው መለኮታዊ ኃይሉን በመጠቀም አይደለም።
ሰይጣንን ያሸነፈው የረቀቀ የግሪክ ፍልስፍና ተጠይቆ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ትምሕርት ወስዶ አይደለም።
ኢየሱስ ያደረገው ነገር ለእያንዳንዱ ጥያቂ አስፈላጊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መጥቀስ ብቻ ነው።
ይህ ለእኛ ምሳሌያችን ነው።
በሕይወታችን ለሚገጥመን ለእያንዳንዱ ጥያቄ ተስማሚ መልስ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እናገኛለን። ሕይወት ለሚያመጣብን ጥያቄ ሁሉ ትክክለኛው መልስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው ቃል ነው።
ይህም እምነት ይባላል። እምነት ማለት ቤተክርስቲያን ወይም ጓደኞቻችን የሚሉትን ትተን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃ ስንቆም ነው።
ማቴዎስ 4፡12 ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።
ዮሐንስ ታላቅ ነብይ ነው። ሕዝቡን ወደ ኢየሱስ በመጠቆም አገልግሏል።
ስለዚህ አሁን ዮሐንስ መድረኩን ለቆ እንዲወርድ ጊዜው ደረሰ።
ሰዎች ያለባቸው ችግር አንድ ታላቅ ነብይ ሲያገኙ በአገልግሎቱ በጣም ከመደነቃቸው የተነሳ ነብዩ እግዚአብሔር እራሱ እንደሆነ ይመስል ነብዩን ወደ መለኮት ደረጃ ከፍ ማድረጋቸው ነው።
ነብዩ ከፊታቸው ዘወር ባለ ጊዜ ሕዝቡ ኢየሱስ ላይ ትኩረት ማድረግ ይችላሉ፤ ነብዩም ደግሞ ይህንኑ እንዲያደርጉ ነው ሲነግራቸው የነበረው።
ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በገለጠ ጊዜ እኛ መከተል ያለብን የተገለጠውን መጽሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ ነብዩን እና ከነብዩ ንግግሮች የተወሰዱ ጥቅሶችን አይደለም።
ነብዩ ወደ እግዚአብሔር ቃል ይጠቁማል። ነብዩ የእግዚአብሔርን ቃል ሊተካ አይመጣም።
ማቴዎስ 4፡13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።
አዲስ ኪዳን ግሪክኛ ስሞችን ሲጠቀም ብሉይ ኪዳን ደግሞ ዕብራይስጥ ስሞችን ይጠቀማል።
የንፍታሌም እና የዛብሎን ነገዶች የኖሩባቸው እስከ ገሊላ ባሕር የሚደርሱ ግዛቶች በኋላ ገሊላ በሚባለው አውራጃ ውስጥ ተካትተዋል።
ማቴዎስ 4፡14-15 በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ … የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።
የሰሎሞን ልጅ በነገሰበት ዘመን የተስፋይቱ ምድር ይሁዳ እና እሥራኤል ተብላ ተከፋፍላለች። አሶራውያን እሥራኤልን በ721 ዓመተ ዓለም ቶቆጣጠሩ፤ ከዚያ በኋላ እሥራኤል በአሕዛብ ስትገዛ ቆይታለች። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እሥራኤላውያን ተበታትነው ቀርተዋል እንጂ ወደ እሥራኤል አልተመለሱም። ይሁዳ በ606 ዓመተ ዓለም በናቡከደነጾር ተማረከች፤ ናቡከደነጾር የማረካቸው አይሁዳውያንም በ536 ዓመተ ዓለም በቂሮስ አማካኝነት በነጻ ተለቀቁ። እነርሱም ቤተመቅደሱን መልሰው ለመገንባት ወደ ይሁዳ ተመልሰው ሄዱ። አይሁዳውያንን ወደ ይሁዳ እንደ ማግኔት የሳባቸው በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ላይ የተገነባው ቤተመቅደስ ነው። ክርስቲያኖች ከእምነታቸው ወደ ኋላ ቢያፈገፍጉ በነፍሳቸው ውስጥ የተተከለው የእግዚአብሔር ቃል ንሰሃ እስኪገቡ እና ወደ እግዚአብሔር እስኪመለሱ ድረስ እረፍት የሌላቸው ሐጥያተኞች ያደርጋቸዋል።
በነፍሳቸው ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል ዋጋ የማይሰጡ ክርስቲያኖች፤ መጽሐፍ ቅዱስን ትልቅ ቦታ የማይሰጡት ክርስቲያኖች ከእምነታቸው ወደ ኋላ ባፈገፈጉ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የመመለስ ዝንባሌ የላቸውም። በነፍሳችን ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ወደ ክርስቶስ መልሶ የሚስበን ማግኔት ነው።
ማቴዎስ 4፡16 በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው
ሐጥያት እና አለማመን ጨለማ ነው። ኢየሱስ በመጣ ጊዜ እርሱ የእውነት ብርሃን ነበረ። ብርሃን ደምቆ የሞታየው በጨለማ ሰፈር ውስጥ ነው።
ጥላ የሚፈጠረው ብርሃን በሌለበት ቦታ ነው። ብርሃን ሲመጣ ግን ጥላው ስፍራውን ትቶ ይሸሻል።
ሰይጣን ጥላ ነው። ሰይጣን ስራውን የሚሰራው ብርሃን በሌለበት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ብትጠቅሱት እና ብትኖሩበት ሰይጣን ከእናንተ አካባቢ ጥሎ ይሸሻል።
ሞት ጥላ ነው። ሞት ክፉ ነገር ይመስላል፤ ለዳነ ክርስቲያን ግን ክፉ ነገር አይደለም። ለዳነ ሰው ሞት ማለት ወደተሻለ ስፍራ ወደ ሰማይ የሚዘዋወርበት የተከፈተ በር ነው።
መዳናችንን ያመጣልን የኢየሱስ ሞት የእኛን ሞት ተስፋ ቢስ እና አሳዛኝ ክስተት ከመሆን ተለውጦ ወደ ተሻለ ተስፋ የምንሻገርበት ልምምድ እንዲሆን አድርጎታል።
ዮሐንስ 1፡47 ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው።
ናዝሬት መጥፎ ስም የነበራት ከተማ ነበረች። ናዝሬት ውስጥ ሐጥያት ያለ ገደብ ተስፋፍቶ ነበር። ሆኖም ግን ለተወሰኑ ዓመታት ኢየሱስ በእዝያ ነበር የኖረው።
ማቴዎስ 4፡17 ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።
የወንጌሉ የመጀመሪያ እርምጃ ንሰሃ መግባት ነው። ይህ ሁልጊዜም አይለወጥም። ከኢየሱስ ጋር ያለን የሕይወት ልምምድ የሚጀምረው ከልባችን ንሰሃ ስንገባ ነው።
ራዕይ 14፡6-11 ስለ ሶስት መላእክት ወይም መልእክተኞች ይናገራል።
እነዚህ ሰዎች በመጨረሻዎቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እውነትን መልሰው የማስተማር ሃላፊነት አለባቸው።
እነርሱም የጀርመኒው ማርቲን ሉተር፣ የእንግሊዙ ጆን ዌስሊ፣ እና የአሜሪካው ዊልያም ብራንሐም ናቸው።
የመጀመሪያው መልአክ ማርቲን ሉተር ነው።
ራዕይ 14፡6 በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤
ሉተር ስለ ጽድቅ ሰበከ። መዳን ንሰሃ በመግባት ነው እንጂ መልካም ስራዎችን በመስራት አይደለም ብሎ አስተማረ።
የዘላለም ወንጌል ማለት ይህ ነው።
ይህ ወንጌል የተጀመረው ስለ ንሰሃ ይሰብ በነበረው በመጥምቁ ዮሐንስ ነው። ንሰሃ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁልጊዜም ይሰበክ ነበር፤ የተቋረጠው ቤተክርስቲያን ይህ እወነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ሲጠፋባት ነው። ከዚያም ሉተር ተሃድሶውን ሲጀምር ንሰሃ በመግባት መዳን የሚባለውን ትምሕርት ተመልሶ እንዲመጣ አደረገ።
ማቴዎስ 4፡18 በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
ኢየሱስ ትጉህ ሰራተኞችን ነው ወደ ራሱ የጠራው። የነዚህ ሰዎች መተዳደሪያ ስራ ዓሳ ለማጥመድ ወደ ባሕር ውስጥ መረብ መጣል ነበረ። በመንፈሳዊው ስራቸው ደግሞ ወንጌሉን በመናገር እረፍት የሌለው የብዙ ሕዝብ ባሕር ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል እየሰበኩ እንደ መረብ ይጥላሉ።
ጴጥሮስ ከመስበክ በተጨማሪ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጽፎ በማስቀመጥ የወንጌልን መረብ ወደ ባሕር ውስጥ ጣለ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እስከ ዛሬም በዓለም ዙርያ እየተንቀሳቀሰ ቃሉን ለማመን ፈቃደኛ የሆኑትን እንዲድኑ የተመረጡ ነፍሳት ይይዛል።
ማቴዎስ 4፡19 እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
ደቀመዝሙር የመሆን ሚስጥር፡- ኢየሱስን መከተል እና የራስህን ፈቃድ አለማድረግ ነው።
ማቴዎስ 4፡20 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
ጴጥሮስ እና እንድሪያስ ጥሪው ሲደርሳቸው ወዲያው ምላሽ ሰጡ። የያዙትን ስራ ትተው ወዲያ ተከተሉ። ለራሳችን ምን ያህል ገንዘብ እናገኛለን የሚል ሃሳብም አልነበራቸውም። ምን ጥምቅ እንደሚገኝ አልጠየቁም። ያዋጣናል ወይስ አያዋጣንም ብለው እንኳ አልተደራደሩም። ጴጥሮስ ስለ ወንጌል ለመሞት እንኳ ዝግጁ ነበረ። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለወንጌል የተሰጠ ሰው ነበረ። ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍለው እንኳ ከማገልገል ወደ ኋላ አይልም።
ማቴዎስ 4፡21 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
ያዕቆብ እና ዮሐንስ ጠንቃቆች እና የቤተሰባቸውን ንግድ በትጋት የሚሰሩ ሰዎች ናቸው። ዓሳ በማያጠምዱበት ሰዓት እንደ ሰነፍ ዝም ብለው አይቀመጡም። ዓሳ በማያጠምዱ ሰዓት የሚያጠምዱበትን መረብ እየጠገኑ ይውላሉ። መረቡን መጠገን በጣም አስፈላጊ ስራ ነው። መረቡ ውስጥ ቀዳዳ ካለ ዓሳዎች እንዲያመልጡ ያደርጋል።
ማቴዎስ 4፡22 እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።
ኢየሱስ በጠራቸው ጊዜ ወዲያው ምላሽ ሰጡ። ሲከተሉም ስለ ጡረታ አልጠየቁም፤ ስለ ጤና ኢንሹራንስ እና ስለ ዓመት እረፍት አልጠየቁም። እንዲሁ ተከትለው ሄዱ። ምንም ነገር ቢያስፈልጋቸው እግዚአብሔር ያቀርብላቸዋል። እነርሱ የእግዚአብሔርን ስራ በትጋት ለመስራት ወስነዋል ምክንያቱም እግዚአብሔር የእነርሱን ጉዳይ እንደሚሞላላቸው አምነዋል። ቤተሰብን የማስተዳደር ጉዳይ እንኳ በእነርሱ ዘንድ ወንጌልን ከመስበክ ይበልጥ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ነገር አልተቆጠረም።
የተከተሉት ኢየሱስን እንጂ አባታቸውን አልተከተሉም።
ስለ ወንጌል በመሞት የመጀመሪያ የሆነው ሐዋርያ ያዕቆብ ነው። ሐዋርያቱ በተጠሩ ጊዜ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ለሚጥል አገልግሎት ነው እሺ ብለው የታዘዙት። እነርሱ የሚያሳስባቸው ብቸኛው ነገር ኢየሱስን መከተል ነው። በሕይወት መኖር ወይም መሞት ለእነርሱ ቀዳሚ አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም። እነርሱን በጣም የሚያስደስታቸው ነገር ለእግዚአብሔር መንግስት አንድ ቁም ነገር መስራት ነው። ለማገልገል ጽኑ ፍላጎት ነበራቸው።
ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
የእኛ ኃላፊነት እግዚአብሔርንና የመንግስቱን ጉዳይ ማስቀደም ነው፤ ይህንንም ማድረግ የምንችለው ኢየሱስን እና ቃሉን ከተከተልን ነው። ለግል ጥቅማችን መጨነቅ የለብንም፤ ከዚያ ይልቅ የሚያስፈልገንን ነገር እግዚአብሔር እንዲጨምርልን በእርሱ መታመን ያዋጣናል።
ማቴዎስ 4፡23 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።
የኢየሱስ አገልግሎት በውስጡ ብዙ አስደናቂ ታላላቅ ተዓምራት እና ጠንከር ያሉ እውነቶችን ማስተማር በአንድነት ነው። ሕዝቡ አስደናቂ ተዓምራቱን ይመርጣሉ ምክንያቱም ተዓምራቱ የሰዎችን ትኩረት ይስባሉ። ነገር ግን በዋነኝነት የተዓምራቱ ዓላማ ሰዎች ስብከቱን እንዲያደምጡ ትኩረታቸውን ወደ ስብከቱ ለመሳብ ነው። ይህም እነርሱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት ቢፈልጉ እግዚአብሔር ከእነርሱ ምን እንደሚጠብቅ ያሳውቃቸዋል።
ማቴዎስ 4፡24 ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም።
የእግዚአብሔር ኃይል መፈወስ የማይችለው በሽታ ወይም ማስወጣት የማይችለው አጋንንት አልነበረም።
ማቴዎስ 4፡25 ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
አይሁዶች ርቀትንና አቅጣጫን የሚለኩት ከቤተመቅደሱ በመነሳት ነው። ስለዚህ “ከዮርዳኖስ ማዶ” ማለት ከዮርዳኖስ ወንዝ በሌላኛው ዳርቻ ማለት ነው።
ስለዚህ የኢየሱስ አገልግሎት በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አይሁዳውያንን ሁሉ ትኩረት ስቧል። የቀሩት ሳምራውያን ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም የአሕዛብ እና የአይሁድ ክልሶች ናቸው።
ማቴዎስ 10፡5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
6 ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
ኢየሱስ አገልግሎቱን ያከናወነው የአብራሐም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ ልጆች በሆኑን በአይሁዳውያን መካከል ብቻ ነው
በተስፋይቱ ምድር የነበሩ አይሁዶችን ሁሉ በመሳብ ኢየሱስ ወዲያም በአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ልብ ውስጥ ጠላትነትን እያጫረ ነበር፤ እነርሱ በራሳቸው የታላቅነት ስሜትና ትዕቢት የተሞሉ ሰዎች ነበሩ።
በኢየሱስ ሕይወት የመጨረሻው ሳምንት ውስት የሐይማኖት መሪዎች የሕዝቡን አእምሮ ጠምዝዘው ኢየሱስ ላይ ጠላት እንዲሆኑ ማድረግ ችለዋል።
የቤተክርስቲያን መሪዎች እቅማቸው ይህን ያህል ነው፤ እነርሱም በገንዘባቸው ።