ማቴዎስ ምዕራፍ 03



መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን በሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ልዩ ሰው አድርጎ ነው ያስተዋወቀው።

First published on the 5th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ 2፡23 በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

ይህ የተጻፈ ትንቢት አይደለም። ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ትንቢት ነው።

ማቴዎስ 3፡1 በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ … በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

ቤተራባ “የመሻገሪያ ቦታ” ይባላል፤ እርሱም ኢያሱ የዮርዳኖስን ወንዝ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል በደረቅ ምድር የተሻገረበት ቦታ ነው። ኢያሱ ከተሻገረ በኋላ የደረሰበት የመጀመሪያ ከተማ ኢያሪኮ ነበር። የኢያሪኮ ትልቅ ግምብ አጥርም በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ፈረሰ።

የዮርዳኖስ ወንዝ ለእኔነት የመሞት ምልክት ነው።

 

 

ኢያሱ እኛ ለእኔነት ስንሞት በውስጣችን ገብቶ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው።

ኢየሱስ በቤተራባ አጠገብ ሊጠመቅ ከናዝሬት መጣ።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ስለሆነ አገልግሎቱን ለመጀመር፤ ትንቢቶችንም ለመፈጸም፤ የሐጥያትን ዋጋ ለመክፈል ከሰማያዊው ወደ ምድራዊው ዓለም ተሻገረ።

ከዚያ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ለሐጥያታችን ሞተ።

ሲሞት መንፈሱ ማለትም መንፈስ ቅዱስ ከምድራዊው ዓለም ተሻግሮ ወደ ሐጥያት መናገሻ ወደ ሲኦል እና ወደ አጋንንት መናኸሪያ መውረድ ይችላል። በሲኦል ውስጥ ያለው ግምብ አጥር ከኢያሪኮ ግምብ አጥር ይበልጥ ጠንካራ ነው። ኢየሱስ ግን ከኢያሱም የበለጠ ብርቱ ተዋጊ ነው። ኢየሱስ ሰይጣንን በራሱ በሰይጣን ግዛት ውስጥ ተዋግቶ አሸነፈው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን መዳን ለአይሁድ ሕዝብ ነበር የቀረበላቸው፤ ለአሕዛብ መንግስታት አልቀረበም ነበር፤ አሁን ግን ኢየሱስ ወደ ምድር የወረደ ጊዜ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መዳን ወደ አሕዛብ እንዲሻገር አደረገ።

የናቡከደነጾር ምስላ ከወገቡ በላይ ያለው አካል አሕዛብ የነበሩትን የባቢሎን፣ የፋርስ፣ የግሪክ፣ እና ሮም መንግስታት ይወክላል፤ እነዚህም አሕዛብ መንግስታት ወደ ይሁዲነት ካልገቡ በቀር ስለ እግዚአብሔር ማዳን የሚያውቁበት ምንም እድል አልነበራቸውም።

 

 

ዳንኤል ያየው አሕዛብ ምስል እግሮቹ የቤተክርስቲያንን የ2,000 ዓመታት ታሪክ ይወክላሉ። ቤተክርስቲያን በአሕዛብ መካከል የመዳንን ወንጌል አሰራጨች።

ኢየሱስ ከሙታን መነሳቱ ሰይጣን መሸነፉን ለራሱ ለሰይጣን መርዶ የሚያረዳ ታላቅ ክብር እና ድል ነው። ሰይጣን ለሞት የሚያበቃ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አከርካሪው እንደተሰበረ እንስሳ ሆነ፤ ነገር ግን የመጨረሻ ንዴቱን ለመወጣት ወደ እሳት ባሕር ውስጥ እስኪገባ ድረስ በእልህ አሁንም የቻለውን ያህል ጥፋት እያደረሰ ነው። ሰይጣን ተሸንፏል፤ ነገር ግን አሁንም አደገኛ እና አታላይ ነው። ሰይጣንን ማሸነፍ ከፈለግን አሁንም የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፈልገናል።

ዮሐንስ 1፡28 ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ።

ማቴዎስ 3፡2 መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

አይሁዶች ኢየሱስን ቢቀበሉ ኖሮ የዛኔውኑ ከሰባት ዓመታት በኋላ ዓለምን በሙሉ ለ1,000 ዓመታት በሰላም እንዲገዙ እግዚአብሔር መንግስትን ይሰጣቸው ነበር። በኢየሩሳሌም ዙርያ የነበረው ቅጥር እንደገና እንዲሰራ ለነሕምያ ትዕዛዝ ከተሰጠው በኋላ 490 ዓመታት ብቻ እንደሚቀራቸው ዳንኤል ለአይሁዶች አስታውቆ ነበር። ኢየሱስ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ በመጣ ጊዜ የ29 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ዕድሜው 30 ዓመት ነበረ። ከዚያ በኋላ ለአይሁድ ከተነገራቸው ዓመታት የቀረው ሰባት ዓመት ብቻ ነበር።

 

ማቴዎስ 3፡3 በነቢዩ በኢሳይያስ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።

“ምድረበዳ” አስፈሪ ቃል ነው። አይሁዶች መሲሁ እስኪመጣ ድረስ ይጠባበቁ የነበሩ የእግዚአብሔር ሕዝብ ናቸው።

ምድረበዳ ግን ጭር ያለ ባዶ በረሃ ነው።

ስለዚህ ኢሳይያስ ለአይሁዳውያን መንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ መሆናቸውን እየነገራቸው ነበር። አይሁዳውያን በመንፈስ ድርቀት ውስጥ ወድቀው ነበር፤ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉ መሪዎቻቸውም በገንዘብ ፍቅር እና በስግብግብነት ተጠምደው ነበር።

ለሚመጣው መሲህ መዘጋጀት ቢፈልጉ በብዙ አቅጣጫ ለውጥ ይጠበቅባቸው ነበር።

በ2020 የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ለቤተክርስቲያን የማንቂያ ጥሪ ነው። በእግዚአብሔር አመለካከት የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያኖች ለመዘጋት እንጂ ሌላ ምንም ጥቅም የላቸውም። ቤተክርስቲያኖች የመጨረሻው ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ምን እንደሆነ ማሳየት አልቻሉም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ለጌታ ምጻት የሚያዘጋጃቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የመማር ዕድል አያገኙም። አእምሮዋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት (መዳን እና መልካም ሥራዎችን መስራት) እና በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የስሕተት ትምሕርቶች ተሞልተው ትኩስ ወይም በራድ ሳይሆኑ ለብ ብለው ይቀራሉ።

ማቴዎስ 3፡4 ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።

የግመል ጠጉር እና ጠፍር በጣም ጠንካራ ነገሮች ናቸው። ይህም ዮሐንስ የተበላሸውን የአይሁድ ሐይማኖታዊ ድርጅት ለብቻው መጋፈጥ የቻለ ብርቱ ተዋጊ መሆኑን ያመለክታል። ዮሐንስ ድሎት አይፈልግም፤ ማመቻመችም አያውቅም። የሐይማኖት መሪዎችን ሲያናግራቸው ተቅለስልሶ አያውቅም። እባቦች ብሎ ነበር የሚጠራቸው።

ዮሐንን የለበሰው ቀለል ያለ ልብስ እና የሚበላው ምግብ ካሕናቱ፣ ፈሪሳውያን፣ እና ሰዱቃውያን ከሚኖሩበት ቅጥ ያጣ ብልጽግና እና ቅብጠት በጣም የተለየ ነበር። እነርሱ እግዚአብሔርን መምሰል በገንዘብ መበልጸጊያ መስሏቸዋል (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡5)። የሰዎች ባሕሪ አሁንም አልተለወጠም። ዛሬ የክርስቶስን ዳግም ምጻት በምንጠባበቅበት ዘመንም እንደዚሁ ነው።

የበረሃ ማር ማለት በሰው ሰራሽ ዘዴዎች ያልተነካ ማር ማለት ነው። አንዳችም የሰው አመለካከት ያልተቀላቀለበት እውነት። ሰው ሰራሽ ልማድ የሌለበት። መጽሐፍ ቅዱስን በኪንግ ጄምስ ቨርዥን ውሰጥ እንደተጻፈው ብቻ ማመን። ያለ ምንም ማመቻመች የተጻፈውን ብቻ መናገር።

አንበጦች ከመቅሰፍት ጋር ነው የሚያያዙት። ራዕይ ምዕራፍ 9 ውስጥ ዘውድ የጫኑ አንበጦች ማለት የኮሮና አጋንንት ናቸው። በጣም አደገኞች ናቸው። በ2020 የመጣው ኮሮና ቫይረስ በማይክሮስኮፕ ሲታይ ዘውድ የጫነ ቫይረስ ይመስላል።

ራዕይ 9፡7 የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤

እንደ ሰው ፊት። የአጋንንት አሰራር የሚሰራጨው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የሰው ስብከቶችና ሃሳቦች አማካኝነት ነው።

አንበጦች በመንጋ ነው የሚንቀሳቀሱት፤ ይህም የብዙሃኑን አመለካከት፣ አስተምሕሮ እና ሃሳብ ይወክላል። እነዚህ የብዙሃን አመለካከቶች እንደ መቅሰፍ ነው የሚሰራጩት። ለምንድነው እንደ በሽታ በፍጥነት የሚዛመቱት? ለብዙሃኑ ምኞት የሚመቹ ስለሆኑ ነው።

ይህ በመንጋ የሚንቀሳቀሰው ሰው ሰራሽ ስሕተት እየበረረ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ከወረደ በኋላ እንደ ባልጩት ድንጋይ ከጠነከረው ከመጥምቁ ዮሐንስ አገጭ ጋር ተጋጭቶ ተመለሰ። የሐንስ ይዞ ገነጣጠላቸው። ዮሐንስ ማፈግፈግ አያውቅም። ልክ እንደ አሜሪካ ወታደር ሲሸምቁበት ጥቃት በመሰንዘር ነው ምላሽ የሚሰጠው እንጂ ራሱን ለማዳን ከቁጥቋጦ ስር በመደበቅ አይደለም።

ለኑሮው የሚያስፈልጉት በጣም ጥቂት እና ቀላል ነገሮች ናቸው። ገንዘብ አይፈልግም ስለዚህ ሰይጣን እነርሱን የሚጠልፍበት ፈተና የለውም። ለግል ጥቅም አንዳችም ሳያስብ የእግዚአብሔር ቃል በትክክል ማወጅ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ስለነበረ በኢየሩሳሌም ዙርያ የነበረውን የይሁዳ አውራጃ በሙሉ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙርያ ያሉትን ሕዝብ ሁሉ አስደንቆ ነበር።

ዮሐንስ ከአይሁዶች ሁሉ ቀለል ያለ ሕይወት ነበር የሚኖረው። እነርሱ ከነበራቸው ገንዘብና ንብረት እርሱ ያለው በጣም ያንስ ነበር። ዮሐንስ ቆራጥነቱ እና ሐጥያትን ፊት ለፊት ማውገዙ ሁሉንም ያስፈራቸው ነበር። ሕዝቡ በታላቅ አድናቆት አደመጡት፤ የሐይማኖት መሪዎች በፍጥነት አፈገፈጉ። ገንዘባቸውን እና ክብራቸውን መተው ሲያስቡ አንገበገባቸው። በፍጹም አይደረግም አሉ።

ማቴዎስ 3፡5 ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤

ዮሐንስ አይሁዶች ላይ እንደ አውሎ ነፋስ ነው የመጣባቸው። ስንፍናቸውንና የተሳሳተ አመለካከታቸውን አጋለጠባቸው። ትምክሕታቸውን በአንድ ጊዜ አራቆተባቸው፤ አለማመናቸውንና ሐጥያታቸውንም ያለ ምንም ፍርሃት በግልጽ አወገዘ።

ማቴዎስ 3፡6 ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

ስለዚህ አይሁዶች ንሰሃ ከመግባት በቀር ምንም አማራጭ አልነበረባቸውም። በዮሐንስ የጽድቅ ቁጣ ተመቱ። ወዲያው እንደ ሙሴ ወይም እንደ ኤልያስ ያለ ሰው መነሳቱን አወቁ። እግዚአብሔር ያለ ጥርጥር ለአይሁዶች ነብይ አስነስቶላቸዋል።

እግዚአብሔር እኛ ትክክል መሆናችንን ሊነግረን ነብይ አያስነሳልንም። እግዚአብሔር ነብይ የሚያስነሳው ስለ ስሕተታችን ሊወቅሰን ነው።

ማቴዎስ 3፡7 ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

የሐይማኖት መሪዎችን በምን ዓይነት ንቀት እና ፌዝ እንዳናገራቸው ተመልከቱ። የሐይማኖት መሪዎች ከሕዝቡ በላይ ከፍ ከፍ ብለው ስለነበረ በትዕቢ የተነፉና ስለ ራሳቸው ከፍ ባለ ግምት የተሞሉ ትንንሽ አምባገነን ሰዎች ነበሩ።

እባቦች አፋቸው ውስጥ መርዝ አላቸው። ይህም መርዝ ሰባኪዎች የሚሰብኩት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምሕሮ ነው።

የ2020 ኮሮና ቫይረስ የሚያመለክተው ይህንኑ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖችን ለመዝጋት ተጠቅሞበታል። ኮሮና ቫይረስ እግዚአብሔር ስለ ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶችን እና የግል አመለካከታቸውን ስለሚያራምዱ የቤተክርስቲያን መሪዎች ምን እንደሚያስብ ያሳያል።

ማቴዎስ 3፡8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤

ንሰሃ ገብቻለው ካልክ ለንሰሃ የሚመጥን ፍሬ አሳይ።

ከልቡ ንሰሃ የገባ ሰው ነብይ በመጣ ጊዜ ወዲያው ነብይነቱን ያስተውላል።

ማቴዎስ 21፡26 ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ።

ዮሐንስ በዘመኑ የነበሩ የሐይማኖት መሪዎችን አወገዘ፤ ሕዝቡ ግን ከውግዘቱ አሻግረው በማየት እርሱ ነብይ መሆኑን ተረዱ።

ዛሬም ደግሞ የእውነት ንሰሃ የገባ ሰው ዊልያም ብራንሐም ነብይ መሆኑን ያውቃል። ንሰሃ የገቡ ሰዎች መጠንቀቅና መዋጋት ያለባቸው ቤተክርስቲያኖቻቸው እና ፓስተሮቻቸው በውሸት ሃሳባቸውን እንዳያስለውጧቸው ነው።

ንሰሃ መግባት ማለት ኢየሱስን ማግኘት ነው።

ኢየሱስ ግን ከሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ማለትም ከመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ውጭ ነው።

ማቴዎስ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ

ኢየሱስ እየፈለገ ያለው ቡድኖችን ሳይሆን ግለሰቦችን ነው።

ስለዚህ ግለሰቦች ኢየሱስን የሚያገኙበት ብቸኛው መንገድ እግዚአብሔር በ2020 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ቤተክርስቲያኖችን ሲዘጋ ነው (2020 ማለት ጥርት ያለ እይታ ነው) ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች እና ሁሉም ድርጅቶች በተዘጉበት ግለሰቦች እቤታቸው ሲቀመጡ ኢንተርኔትን ፈትሸው እውነትን ማግኘት ይችላሉ። በዚህም መንገድ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሆነው ከሚሰሙዋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ስሕተቶች ያመልጣሉ።

ማቴዎስ 3፡9 በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና፦ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።

ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ዛሬ ድነናል ብለው ይኩራራሉ፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን በምትነጠቅ ጊዜ ወደ ሰማይ ተነጥቀን እንሄዳለን ብለው ያምናሉ።

ስለዚህ እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት (ቆነጃጅት ንጹሃን የዳኑ ሰዎች ናቸው) በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ተሰብስበው እየተሟሟቁ ለመጨረሻው ዘመን የመጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ቸል ይላሉ። ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው፤ በተለይም ራዕይ፣ ዳንኤል፣ እና ዘፍጥረትን መረዳት አይችሉም።

ነገር ግን ለሰነፍ ቤተክርስቲያኖች ምንም ቦታ የማይሰጡ እንደ ድንጋይ የጠነከረ ልብ ያላቸው ሐጥያተኞች ከቤተክርስቲያን ውጭ አሉ። እግዚአብሔር ተነስቶ እነዚህን አከራካሪ ወንበዴዎች ያድናቸዋል፤ ምክንያቱም እነርሱ ብቻ ናቸው ያለ ምንም ፍርሃት ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የመቆም ድፍረት የሚኖራቸው። እነርሱ ብቻ ናቸው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ሲገለጥላቸው በፍቅር የሚቀበሉት።

ስለ እውነት ለመቆም እንደ ዮሐንስ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ለመቃወም የሚበቃ ድፍረት ያስፈልጋችኋል።

ኢሳይያስ 9፡2 በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ የቤተክርስቲያን ካድሬዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሚቀኑ የቤተክርስቲያን ተቺዎች ይተካሉ።

መሳሳታችሁን ስለዚህም በጨለማ ውስጥ መሆናችሁን ካወቃችሁ የዚያን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን ብርሃን ማየት ትችላላችሁ።

ነገር ግን ትክክል እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እርማትን አትፈልጉም፤ ከዚህም የተነሳ ብርሃንን ማየት አትችሉም።

ማቴዎስ 3፡10 አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።

መጥምቁ ዮሐንስ ፍጹም ቆራጥ ነበረ። ማመቻመች የሚባል ነገር በጭራሽ አያውቅም። የዛፍ ግንድ ስትቆርጡ የእንጨት ስንጣሪዎች በየአቅጣጫው ይፈናጠራሉ። ዮሐንስ ብዙዎችን አስቆጣ። ሆኖም ግን በአድማጮቹ ነፍስ ውስጥ ሊጠፋ የማይችል የዕሳት ምልክት አደረገ። ግልጽ የሆነ ምርጫ አስቀመጠላቸው፡- ተመለሱ አለዚያ ትጠፋላችሁ።

ማቴዎስ 3፡11 እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤

ዮሐንስ በውሃ አጠመቀ። ይህ ለአይሁዶች አዲስ ሥርዓት በመሆኑ አስደንግጧቸዋል። መጠመቅ ለእነርሱ አዲስ ነበር።

የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ለአይሁድ ሕዝብ በዚህ መንገድ ነበር የተነገራቸው።

የኢየሱስ ዳግም ምጻት ለቤተክርስቲያኖች የሚነገራቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚደረግ የውሃ ጥምቀት ነው።

ሁሉን እናውቃለን ብለው ለሚያስቡ በሥላሴ እምነት ለተጠመዱ ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖችና ለአባሎቻቸው ይህ እውነት ትልቅ ሐይማኖታዊ ድንጋጤ ይፈጥርባቸዋል።

ኢየሱስ ሰዎችን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል፤ ይህም ከሁሉም የበለጠ የጥምቀት ዓይነት ነው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምታሰራጨው ስሕተት የሰዎችን አእምሮ እየተቆጣጠረ ቢሄድም መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን የሚያስፈልገውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ይገልጣል።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያለችዋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አለባት። የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን በሐዋርያት የተመሰረተችው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የነበራት ዓይነት እምነት ሊኖራት ይገባል።

የሚታጨደው ዘር መጀመሪያ ላይ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ነው።

 

 

ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጫማ ይናገራል።

ጫማ እግሮችን ይሸፍናል።

ጫማዎች በማሰሪያ ስለሚታሰሩ እግሮችን ሙሉ በሙሉ ከእይታ ይሰውራሉ። በዚህም ምክንያት ዮሐንስ ለእርሱ የተሰጠው አገልግሎት ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር እንደማይያያዝ ገብቶታል።

ዳንኤል ያየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ የምስሉ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ መዳን ለአይሁድ ነበር፤ ስለዚህ መዳን ከአሕዛብ መንግስታት ውጭ ነበር።

 

 

ዮሐንስ ታላቅ ለውጥ ሊሆን ጊዜው እንደቀረበ ገብቶታል። ነገር ግን መዳን ከአይሁድ ዘንድ ወጥቶ ወደ አሕዛብ ሊሄድ መሆኑን አልተረዳም። የብረቱ እግሮች የሚወክሉት ጣኦት አምላኪዎቹን ሮማውያንን ነው። በእግር ውስጥ የነበሩት የብረት ስብርባሪዎች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናቸው። ሸክላው ወይም እርጥቡ ጭቃ ሙሽራይቱን ይወክላል፤ ምክንያቱም ከአሕዛብ ምሱሉ ውስጥ ሕይወት ያለው ተክል ሊያድግበት የሚችለው ክፍል ሸክላው ብቻ ነው። ዘር በእርጥብ ሸክላ አፈር ውስጥ ማደግ ይችላል።

ዮሐንስ ሊመጡ ስለነበሩት ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት አንዳችም አላወቀም። በዚህም ምክንያት ከኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት በፊት ጫማውን መሸከም አልችልም አለ።

የኢየሱስ ጫማ ላይ የነበሩት የጫማ ማሰሪያዎች በዮሐንስ ዘመን ሊገለጡ የማይችሉ የሰባቱ ማሕተሞች ሚስጥራት ነበሩ።

በ1906 ሎሳንጀለስ ውስጥ በአዙዛ ጎዳና ጴንጤቆስጤያዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ መጣ። ጴንጤቆስጤያዊ ቤተክርስቲያኖች በሰባት ማሕተሞች ከታሸጉት የጫማ ማሰሪያዎች አልፈው ለማየት ሞከሩ፤ ነገር ግን ከጫማዎቹ ምላሶች ባሻገር ምንም ማየት አልቻሉም። ከእነርሱ ተሰውሮ ስልነበረ እና ስላልታወቀላቸው ሌላ ምንም ነገር ማየት አልቻሉም። ስለዚህ በማይታወቁ ልሳናት በመናገር በርትተው ተገኙ።

ነገር ግን ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት ዊልያም ብራንሐም ከሰባቱ ማሕተሞች ስድስቱን የመግለጥ ተልዕኮ ተቀብሎ መጣ። ሰባተኛው ማሕተም ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ስለዚህ ወንድም ብራንሐም እነዚያን ጫማዎች የማውለቅ እንዲሁም እግሮቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት እንዴት እንደሚገልጡ የማሳየት አገልግሎት ተሰጠው።

ይህም መገለጥ እግር የማጠብ ስነ ሥርዓቱ ምን እንደሆነ ለማብራራት ይጠቅማል። ትርጉሙ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በቃሉ ውሃ መታጠባቸው ነው።

አይሁዶች አሕዛብን ይንቁ ስለነበረ በሰዓቱ እግር የማጠብ ትርጉም አልገባውም። በኋላ ግን አሕዛብ በቆርኔሌዎስ ቤት ውስጥ ሲድኑ ጴጥሮስ ወንጌል ወደ አሕዛብ እየሄደ መሆኑን አስተዋለ።

ኋላ ደግሞ ጳውሎስ ስለሚመጡት ዘመናት በመናገር ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የነበረውን መገለጥ አካፈለ። ይህንን እውነት የተናገረበትን ዓረፍተ ነገር ሰባተኛው ቁጥር ላይ በመጻፍ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ስለመኖራቸው ፍንጭ ሰጠ።

ኤፌሶን 2፡7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ፤

መጥምቁ ዮሐንስ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ነው ያስተላለፈው። እንደ ስንዴ ነዶ እንሰበሰባለን፤ ወይ ደግሞ እንደ ገለባ እንቃጠላለን። እመኑ አለዚያ ትጠፋላችሁ።

ማቴዎስ 3፡12 መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።

እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚያምኑትን የስንዴ ፍሬዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ሃሳቦችን ከሚያምኑ ገለባዎች ይለያቸዋል። ይህ ታላቅ የማጥራት ስራ ይጠይቃል፤ ምክንያቱም ስሕተት የሆነ ሃሳብን ከሰው አእምሮ ውስጥ ማስወጣት በጣም ከባድ ነው። ነገር ግን እንደ ሥላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እን ክሪስማስ በመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌሉ ሃሳቦች አእምሮዋቸውን የተሞሉ ሰዎች መጨረሻቸው ወደ ታላቁ መከራ እሳት ውስጥ መግባት ነው። ንሰሃ ያልገቡ እና ኢየሱስን የግል አዳኛቸው አድርገው ያልተቀበሉ ሰዎች መጨረሻቸው የእሳት ባሕር ውስጥ መግባት ነው።

ነገር ግን ስንዴው ከገለባው መለየት ስላለበት እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን በመከራ እሳት ውስጥ ያልፋል።

የሐዋርያት ሥራ 14፡22 የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን … ተመለሱ።

ክርስትና ለልፍስፍሶች አይደለም። እያንዳንዱ ዘመን በተለያዩ መከራዎች ውስጥ ያልፋል።

የመጨረሻው የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያሉ ቤተክርስቲያኖች ለዘመን መጨረሻ የተሰጡትን የሚስጥራት መገለጦች አንቀበልም ይላሉ። ከዚያም በኋላ በዘመኑ ማለቂያ ላይ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይጣላሉ።

ማቴዎስ 3፡13 ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።

ኢየሱስ እሥራኤልን በሰሜን ካለው ከገሊላ (የገሊላ ባሕር ካለበት በግራ በኩል) እስከ ቤተራባ ድረስ (ከሙት ባሕር በላይ) በርዝመቷ ሄዶባታል።

 

 

ስለዚህ ኢየሱስ ለጥምቀት ትልቅ ቦታ ሰጥቷል።

ስለዚህ እኛም ለውሃ ጥምቀት ትልቅ ቦታ መስጠት አለብን።

ኢየሱስ በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ስለመጠመቅ ሲናገር ያ ስም ማን እንደሆነ ለማወቅ መጠየቅ አለብን።

ማቴዎስ 3፡14 ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።

ዮሐንስ ይህ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር በስጋ መሆኑን አውቋል። ዮሐንስ ከኢየሱስ እንደሚያንስ ስለዚህም እርሱን ለማጥመቅ ብቁ እንዳልሆነ ገብቶታል። ኢየሱስ ሐጥያት ሰርቶ አያውቀም። የዮሐንስ ጥምቀት ደግሞ የንሰሐ ጥምቀት ነበረ።

ማቴዎስ 3፡15 ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።

ጽድቅ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የእግዚአብሔር በግ ከመታረዱ በፊት መታጠብ አለበት።

2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።

ማቴዎስ 3፡16 ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤

መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሱ ውስጥ አልገባም፤ ነገር ግን በላዩ ላይ የሚታይ ቅባት ሆኖ አረፈበት።

ይህ ክስተት እግዚአብሔር ኢየሱስን የቀባበት ሰዓት ነው።

የሐዋርያት ሥራ 10፡38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥

የመጀመሪያው ሊቀ ካሕናት አሮን በነብዩ በሙሴ አማካኝነት ታጥቦ ተቀብቷል።

ዘጸአት 40፡12 አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ።

13 የተቀደሰውንም ልብስ አሮንን ታለብሰዋለህ፤ በክህነትም ያገለግለኝ ዘንድ ቀብተህ ትቀድሰዋለህ።

ኢየሱስ የመጨረሻውና ዋነኛው ሊቀካሕናት በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በመጥምቁ ዮሐንስ አማካኝነት ታጥቦ ወንዙ ውስጥ በቆመበት ሰዓት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተቀብቷል።

ዳዊት በነብዩ ሳሙኤል እጅ ንጉስ ሆኖ ተቀብቷል፤ ነገር ግን የነገሰው ጠላቱ ሳኦል ከሞተ በኋላ ነው።

ኢየሱስ የዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ንጉስ ሆኖ ተቀብቷል፤ ነገር ግን የሚነግሰው ጠላት በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ ከጠፋ በኋላ ነው።

 

 

ማቴዎስ 3፡17 እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

ድምጽ ከሰማይ መጣ። ይህም እግዚአብሔር አብ ስለ ልጁ የተናገረበት ድምጽ ነው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያኖር ሰው የሕጻኑ አባት ነው።

ስለዚህ በማርያም ማሕጸን ውስጥ ሕይወት እንዲጸነስ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ሰው ለሆነው ለኢየሱስ አባቱ ነው።

1ኛ. መንፈስ ቅዱስ እና አብ አንድ ናቸው። ሰው የሆነው ኢየሱስ ሁለት አባቶች ሊኖሩት አይችልም።

እግዚአብሔር ሰው በሆነው በኢየሱስ ደስ የተሰኘው ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ስለተገዛ ነው።

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃል የለም።

መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ወልድ” ወይም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” አይልም።

ኢየሱስ እንደ ሰው እግዚአብሔር መሆን አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰው አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ነው።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥

ዘኁልቁ 23፡19 … እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥

ስለዚህ ሰው የሆነው ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ምን ማለት ነው?

ይህም የመለኮት ሙላት የሚኖርበትና የሚሰራበት ሰው ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

እግዚአብሔር አብ በሙላቱ በኢየሱስ ውስጥ ከኖረ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ነው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ቅዱስ መንፈስ ነው።

ስለዚህ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ይህም እውነት የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ውስጥ በጴጥሮስ አንደበት ተረጋግጧል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ሐጥያት የሚሰረየው ሐጥያተኛው በመጠመቁ አይደለም። ሐጥያት የሚሰረየው ሐጥያተኛው ንሰሃ በመግባቱ ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ንሰሐ ከጥምቀት መቅደም አለበት። ስለዚህ ሕጻናትን ማጥመቅ አይቻልም።

የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ አድሯል፤ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

እኛ የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች እና ሴቶች ልጆች የምንሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ሲኖርና ሲቆጣጠረን ብቻ ነው።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው፤ ነገር ግን በስጋው አይደለም እግዚአብሔር የሆነው፤ የመለኮት ሙላት በእርሱ ውስጥ ስላደረ ነው እንጂ።

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23