ማቴዎስ ምዕራፍ 02. ሰብዓ ሰገል ወይም የጥበብ ሰዎች የሁለት ዓመት ሕጻን ልጅ ፍለጋ መጡ።



ታላቁ ፒራሚድና የዞድያክ ከዋክብት ስብስብ በአንድ ላይ የኢየሱስን ታሪክ ከመጀመሪያው ምጻቱ እስከ ዳግም ምጻቱ ድረስ ይተነብያሉ።

First published on the 5th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ ምዕራፍ 2

ማቴዎስ 2፡1 ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? … እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

የሔሮድስ ቤተሰብ የመጡት ከኤዶምያስ ነው፤ ኤዶምያስ ከይሁዳ በስተ ደቡብ የሚገኝ ግዛት ሲሆን ኢያሱ የተስፋይቱን ምድር ለእሥራኤል ባስወረሰ ጊዜ ከግዛቱ ውስጥ አላካተተውም። አይሁዳውያን ለአጭር ጊዜ ከግሪካዊው የሶርያ ገዥ ከአንቲዮከስ ኤፒፋነስ ነጻ በወጡ ጊዜ ኤዶምያስን ገዝተው ነበር። በዚያን ጊዜ ኤዶማውያን የአይሁዶችን ሐይማኖት ለመከተል ተገደዱ። አይሁዶች ግን ኢያሱ ካወረሳቸው ግዛት ወጥተው ኤዶምያስን በመቆጣጠራቸው ኋላ ተጸጽተዋል ምክንያቱም ከገዙዋቸው ነገስታት ሁሉ እጅግ ጨካኙ ሔሮድስ የመጣው ከኤዶምያስ ነው።

 

 

የሔሮድስ አባት አንቲፓተር ሮማዊውን ዩልየስ ቄሳስ ስለረዳው በሮማዊው ዘንድ ሞገስ አግኝቶ ሮማውያን እሥራኤልን በ63 ዓመተ ዓለም በተቆጣጠሩ ጊዜ ሹመት ተሰጥቶታል። ከዚያ በኋላ ሮም ሔሮድስን የይሁዳ አውራጃ ላይ ንጉስ አድርጋ ሾማዋለች።

ሔሮድስ የአይሁድ ትክክለኛ ንጉስ አለመሆኑን እራሱ ያውቀዋል። ሔሮድስ ከዳዊት የዘር ሐረግ የመጣ ሰው አይደለም።

ከዚህም የተነሳ ዙፋኑን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም አይሁዳዊ በከባድ ጥርጣሬ ነው የሚመለከተው። ሰው ሰራሽ በሆነው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ በነበረበት ዘመን ለስልጣኑ የሚያሰጋውን ሰው ሁሉ ያለ አንዳች ማመንታት ይገድል ነበር።

ሰብዓ ሰገል። እነዚህ እንግዶች ጥበበኞች ነበሩ። ጥበባቸውም ኢየሱስን እንዲፈልጉ አድርጓቸዋል።

በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጥበበኛ የምንቆጠረው ክርስቶስን እና ጥልቅ የሆነው ጥበቡን በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንፈልግ ብቻ ነው።

ማቴዎስ 2፡2 የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

በሙሴ ዘመን በለዓም ይህንን ትንቢት ተናግሮ ነበር።

ዘኁልቁ 24፡17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።

ሰብዓ ሰገል ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ኮከብ ባዩ ጊዜ አዳኙ መወለዱን አወቁ።

ማቴዎስ 2፡3 ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤

ሔሮድስ ተደናገጠ። የምስራቅ ሰዎች ኮከብ ተከትለው መጡ። ይህም ትንቢት የተነገረለት ኮከብ ነበረ።

ኮከቡ ተራ ኮከብ ሳይሆን ንጉስ መወለዱን የሚያበስር ኮከብ ነበር። ይህም ንጉስ የተቀባው በሰዎች አልነበረም። ሔሮድስ የውሸት ንጉስ መሆኑን የራሱ ልብ ያውቀዋል ምክንያቱም ሔሮድስን ዙፋን ላይ ያስቀመጡት ሮማውያን ናቸው። ይህም የሆነው እንደ እድል ዩልየስ ቄሳር ወደ ግብጽ እየሄደ ሳለ ችግር ሲገጥመው የሔሮድስ አባት ሊደርስለት በመቻሉ ነው። ይህም አጋጣሚ ለሮም ወዳጅነት በር ከፍቶለታል። ሔሮድስ አንድ ቀን ከዙፋኔ ላይ እወድቃለው በሚል ስጋት ውስጥ ስለነበረ የሚኖረው ስልጣኔን ይጋፋኛል ብሎ የጠረጠረውን ሁሉ ይገድል ነበር።

“ኢየሩሳሌም ሁሉ” ደነገጡ ማለት ከተማው በሙሉ የሰብዓ ሰገልን መምጣት ሰምተዋል ማለት ነው። የመጡት ሰብዓ ሰገል ሶስት ሰዎች ብቻ ቢሆኑ ኖሮ ከተማው በሙሉ ሊያውቅ አይችልም ነበር። ሶስት ብቻ ቢሆኑ ማንም አያስተውላቸውም።

ሌቦች እና ሽፍታዎች በመንገደኞች ላይ ጥቃት ይሰነዝሩ ነበር። አንዳንድ የታሪክ ምሑራን እንደሚናገሩት በዚያ ዘመን በቡድን መንገድ የሚሄዱ ሰዎች ሽፍታዎች እንዳይጠጉዋቸው በ150 የታጠቁ ተዋጊዎች ታጅበው ነበር የሚሄዱት። ሰብዓ ሰገል ስንት ሰዎች እንደነበሩ በውል አናውቅም ግን በዚያ ሽፍታ በሞላበት መንገዳቸው ላይ በሰላም ለመጓዝ በርከት ያሉ ሆነው እንደሚሄዱ ጥርጥር የለውም።

ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲደርሱ ከተማው በሙሉ ትኩረቱ ወደ እነርሱ ይሳብ ዘንድ በቂ ቁጥር ያላቸው ሆነው ነበር የመጡት።

ኮከቡ። ለሰዎች ሁሉ ጥያቄ የሆነባቸው ኮከቡ ነበር።

በሰማይ ላይ በሌሊት ከሚወጡት ከዋክብት መካከል ሁለት ዓመት ሙሉ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የሚሄድ ኮከብ የለም። ከዋክብት ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ለ6 ወራት ከሄዱ በኋላ ከምድር በስተጀርባ ጠፍተው ከስድስት ወራት በኋላ ነው የሚመለሱት። ተመልሰው ሲመጡ በምስራቅ በኩል ብቅ ይሉና ቢያንስ ለሶስት ወራት ከመንገደኞቹ በስተጀርባ ነው የሚሆኑት። ከዚያ ቀጥለው በድጋሚ ከመጥፋታቸው በፊት ለሶስት ወራት ብቻ ነው ከመንገደኞቹ ፊት ፊት የሚሄዱት። ስለዚህ ሰዎች ከምሥራቅ ተነስተው ወደ ምዕራብ መንገድ ቢጀምሩ የትኛውም ኮከብ ሊመራቸው የሚችለው በዓመት ለሶስት ወራት ብቻ ነው።

 

 

ኢየሩሳሌም ከደረሱ በኋላ ኮከቡ ጠፋ። የምናውቃቸው ተራ ኮከቦች በድንገት አይሰወሩም።

ኮከቡ እንደገና ብቅ ያለ ጊዜ ወደ ደቡብ ሄዶ ወደ ቤተልሔም መራቸው። ኮከቦች ወደ ደቡብ አይሄዱም።

ከዚያ በኋላ ኮከቡ ወደ አንድ ቤት አመለከታቸው (ወደ በረት አላመለከተም)። በሰማይ ላይ ካሉ ከዋክብት መካከል በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ቤት ላይ ነጥሎ ማመልከት የሚችል ኮከብ የለም።

ይህ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኮከብ ወደ ምድር ዝቅ ብሎ ከአንድ ቤት ጣራ በላይ ቀጥ ብሎ ቆመ። ሌሎች ከዋክብት እንዲህ አያደርጉም።

ስለዚህ የዚህ ሁሉ ነገር ትርጉሙ ኮከቡ ዛሬም ኢየሱስን እንድንፈልግ እና እንድናገኝ የሚመራን መንፈስ ቅዱስ መሆኑ ነው።

መንፈስ ቅዱስ በኮከብ መልክ ስለተገለጠ የሚመራቸው ማታ ማታ ብቻ ነበር። ይህም መንገዳቸውን በጣም አስቸጋሪና አደገኛ አድርጎባቸዋል። በማታ መንገድ መሄድ በጣም ከባድ ነው።

ክርስትና አልጋ በአልጋ የሆነ መንገድ አይደለም። ትጋት እና ጽናት ይጠይቃል።

 

 

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

መንፈስ ቅዱስ እውነትን ሊያሳየን የሚችል ብቸኛው የእውነት መሪያችን ነው።

ማቴዎስ 2፡4 የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።

የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እና ፖለቲከኞች በአንድነት አንዲሰባሰቡ አደረገ። እውነተኛው መሲህ ከመጣ ስልጣናቸውን እና አላግባብ የሚያገኙትን ገንዘብ እንደሚያጡ ፈርተዋል። ንጉሱ እና የሐይማኖት መሪዎች መሲሁን አልፈለጉትም። ወዲያው ቢሞት ደስ ይላቸው ነበር።

ይህም በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች ቅድመ እይታ ነበር።

በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሱት የሐይማኖታዊ አሳሳችነት ነጭ ፈረስ እና የፖለቲካዊ ኃይል ቀይ ፈረስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጻት በፊት አንድነት ይመሰርታሉ። ብዙ ገንዘብን እና አጋንንታዊ ሥራን የሚወክለው ጥቁሩ ፈረስ ቤተክርስቲያኖችን እየነዳ በዛሬው ዘመን በገንዘብ ፍቅር በሰከረው ዓለም ውስጥ ወደ አንድነት ይመራቸዋል።

ፖፑ ከልክ በላይ ፖለቲካ ውስጥ ይሳተፋል። ብዙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መሪዎችም ፖለቲካ ውስጥ ገብተዋል። ቤተክርስቲያኖች ትልቅ ንግድ ሆነዋል።

ማቴዎስ 2፡5 እነርሱም፦ … ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።

የሐይማኖት መሪዎች መልሱን አውቀዋል።

ማቴዎስ 2፡6 አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና… ።

የጠቀሱት ቃል ይህንን ትንቢት ነበረ።

ሚክያስ 5፡2 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።

መሲሁ ከቤተልሔም እንደሚመጣ እያወቁ ለምንድነው የሐይማኖት መሪዎች ወደ ቤተልሔም ሄደው ያልጠበቁት?

መልሱ ቀላል ነው። መቅደሱ ውስጥ የተቀመጡት ምግባረ ብልሹዎቹ ገንዘብ ለዋጮች ለሐይማኖት መሪዎች ብዙ ገንዘብ እየሰሩላቸው ነበር። ቤተልሔም ውስጥ ቤተመቅደስ ስላልነበረ እንደዚያ ዓይነት ገቢ አይገኝም ነበር። ሃብታም መሆን የፈለገ ሰው ኢየሩሳሌም ውስጥ መቅደሱ አካባቢ መቀመጥ አለበት፤ እዚያ በተቀመጠበት ቦታ ሆኖ መቅደሱ ውስጥ ከተገኘው ነውረኛ ረብ ወይም በግፍ ከተገኘ ገንዘብ ድርሻውን ይካፈላል።

ማቴዎስ 2፡7 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥

ሔሮድስ ተቀናቃኝ እንደመጣበትና ተቀናቃኙንም ሊያጠፋው እንደሚያስፈልግ ገብቶታል። መሲሁ ዕድሜው ስንነት ሊሆን እንደሚችል አጥንቶ ሔሮድስ በዚያ ዕድሜ እና ከዚያ ዕድሜ በታች ያሉ የአይሁድ ወንዶች ልጆችን በሙሉ ጨፍጭፎ ያጠፋቸዋል።

ሔሮድስ ከሰብዓ ሰገል ጋር ዝግ ስብሰባ አደረገ። ኮከቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገለጠ ጀምሮ ምን ያህል ዘመን እንዳለፈ ማወቅ ፈለገ። ኮከቡን ለስንት ዓመት ሲከተሉት እንደቆዩ ማወቁ ለእርሱ ይጠቅመዋል። ይህን ከነገሩት የመሲሁ ዕድሜ ስንት ዓመት እንደሚሆን መገመት ይችላል። ይህም ዕውቀት የትኞቹ ልጆች መገደል እንዳለባቸው ለመወሰን ይጠቅመዋል።

ማቴዎስ 2፡8 ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።

ገዥው ሔሮድስ ነው። ሕጻኑ ተፈልጎ እንዲገኝ ፈልጓል። ነገር ግን ስውር ተንኮሉ እዚህ ጋ ነው፡ ለሕጻኑ ሊሰግድለት የፈለገ አስመስሎ ሃሳቡ ግን በተቻለው መጠን ኢየሱስ ለማጥፋት ነበር።

የሐይማኖት መሪዎች በዚህ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ ከእነርሱ ሃሳብ ጋር እንዲሄድላቸው ብለው እንደገና ይተረጉሙታል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካወረዱበት የትችት ናዳ የተነሳ ትሑት የሆኑ ክርስቲያኖች እንኳ በአተረጓጎሙ ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የለም እስከማለት ደርሰዋል። በእንግሊዝኛ ብቻ ከመቶ በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ስላሉ ሰዎች ሁሉም መጽሐፍ ቅዱስ እንከን እንዳለው እና ፍጹም ትክክል የሆነ አንድም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሌለ ያምናሉ። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች እግዚአብሔርን እናመልካለን እያሉ በሌላ ጎን ግን ሰዎች በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲጥሉ እያደረጉ ናቸው። ዛሬ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም ትክክል ነው ብለው የሚያምኑ ክርስቲያኖች በጣም ጥቂት ናቸው።

ማቴዎስ 2፡9 እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

በተጨማሪም ኮከብ ለመጨረሻው ዘመን የተላከውን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ መልእክተኛ ይወክላል። ይህ ዘመን ሎዶቅያውያን የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ የሚጽፉበትና ለራሳቸው የፈለጉትን ሐይማኖታዊ ትምሕርት የሚያበጁበት ነው። አሁን ቤተክርስቲያኖች ጽንስ ማቋረጥንና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መፍቀድ ጀምረዋል። ያልተጻፉትን ሰባቱን ነጎድጓዶች መተርጎም እንደሚችሉ ያምናሉ። ሰባቱ ማሕተሞች አስቀድመው ሳይገለጡ በፊት ተፈተዋል ብለው ያምናሉ።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

እግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን መልእክተኛ ማሕተሞቹን እስኪገልጣቸው ድረስ አይከፍታቸውም።

ማሕተሞቹ በእርግጥ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ሙሽራይቱ በራዕይ ምዕራፍ 4 ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ይከፈታሉ።

ስለዚህ በዚህ ግራ መጋባት በሞላበት ነውጠኛ ዘመን ውስጥ ሕዝቡ የፈለግነውን የማመን መብታችን ይከበር ብለው በተነሱበት ጊዜ እግዚአብሔር ወደ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ወደ ክርስቶስ የሞመራን ኮከብ ወይም መልእከተኛ ሊልክልን ያስፈልገናል።

ኢየሱስ ቃሉ ነው።

ሰብዓ ሰገል የሰሩት ስሕተት የአይሁድ የመቅደስ አምልኮ ማዕከል ወደሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው በዚያ የነበሩት የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር ለዘመናቸው የነበረው እቅድ ያውቃሉ ብለው መጠበቃቸው ነው። ስለዚህ የሰውን ንግግር ጥቅሶች ለመተርጎም በመሞከር ተጠላልፈው ቀርተዋል። ለምሳሌ የሰው ንግግር ጥቅስ ወስደው ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው ተረጎሙ። ደግሞም ብዙውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መተርጎም ወይም በትክክል ማብራራት እንኳ አይችሉም።

ስለዚህ ሰብዓ ሰገል የተቻላቸውን ያህል ጥሩ አማራጭ ተጠቅመው ውሳኔ አደረጉ። ቤተክርስቲያንን ትተው ሄዱ፤ ሰው የሾማቸውንም መሪዎች ከሰው ሰራሽ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎማቸው ጋር ትተው ሄዱ።

ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ከዚያ በኋላ ኮከቡ ማለትም የመጨረሻው ዘመን መልእክተኛ ንግግሮቹን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መሰረት ፈትሸው መከታተል ሲችሉ ወደ እግዚአብሔር ቃል ይመራቸዋል። የዚያን ጊዜ ኮከቡ ወይም መልእክተኛው ስለተናገረ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ስለተናገረ ያምናሉ።

የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ ምዕራፍ 9 - የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን

… እውነተኛ ነብይ ሁልጊዜ ሰዎችን ወደ ቃሉ መርቶ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው የሚያስተሳስራቸው እንጂ ሰዎች ነብዩን ወይም ንግግሩን እንዲፈሩ አያደርግም፤ ከዚያ ይልቅ ቃሉ የሚናገረውን እንዲፈሩ ነው የሚመክራቸው።

 

 

62-0318 በአፍ የተነገረው ቃል የመጀመሪያው ዘር ነው ክፍል 2

ለዚህ ነው ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ ልናያቸው የቻልነው። አሁን እነዚህ የተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ባይስማሙ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ባይገጥሙ ስሕተት ናቸው፤ ስሕተት ናቸው

64-0823 M ጥያቄዎችና መልሶች 1

ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ሰዎች ግን የሚቀበሉት እኔ ስለሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ነው። ለሚቀበሉ ሁሉ ነጻ ነው ምክንያቱም -- ዓለም ተፈርዶበታል።

ሰብዓ ሰገል በሕዝብ ብዛት የተጨናነቀውን ከተማ ከነሐይማኖት መሪዎች ጋር ትተው መሄዳቸው የመልዕክተኛውን ንግግር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አንጻር መረዳት አስቻላቸው። አንድ ሃሳብን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸን ማረጋገጥ እጅግ በጣም ደስተኞች ያደርገናል። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ የሚያመጣው መነቃቃት ነው።

ማቴዎስ 2፡10 ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።

የኮከቡ ወይም የመልእክተኛው አገልግሎት ወደ ፍጻሜው አስተዋይ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ቃል ማድረስ ነው።

ሰብዓ ሰገል ኮከቡ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ስላስቻላቸው ደስታቸው ገደብ አልነበረውም።

የዊልያም ብራንሐም መልእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ፈጽሞ የሚስማማ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝኖ ትክክለኛ ሆኖ መገኘቱን ሲያዩ እጅግ ተደስተዋል።

63-0323 ስድስተኛው ማሕተም

ለማንኛውም ነገር እጅግ በጣም ቅርብ በመሆናችን ልንታለል ወይም በግማሽ ልባችን ልናምን አንችልም። አስቀድሜ ማየት አለብኝ። ከዚያም ካየሁት በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ መገኘት አለበት። እስካሁን ድረስ እንዳየሁት በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት… ከመጀመሪያው ጀምሬ ይዤው ቆይቻለው፤ እናንተም እንደምታውቁት፤ በደምብ ተዋህዷል።

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ተብሎ መነገር አለበት ማለትም እኔ ስለማውቀው ብቻ እየተናገርኩ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የሚል ነው። ስለዚህ ቃሉ እንሆዋችሁ የሰጠኝ፤ እኔም ደግሞ ለእናተ አቀናብሬ አቀርበዋለው፤ ለእናንተም አሳያችኋለው፤ እናንተም ጭምር እግዚአብሔር እንዲህ ማለቱን ታውቁ ዘንድ። አያችሁ?

ኮከቡን መልእክተኛ መከተላቸው ወደ ኢየሱስ ማለትም ወደ እግዚአብሔር ቃል አደረሳቸው።

ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

ወደ መኖሪያ ቤት ሄዱ እንጂ ወደ በረት አልሄዱም።

ትንሽዬ ልጅ አዩ እንጂ አራስ ሕጻን አላዩም።

ዮሴፍ እቤት ውስጥ አልነበረም።

ለኢየሱስ ሰገዱ። ይህ ትንሽ ልጅ የኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ መሆኑን ያስተውሉ ዘንድ ዓይናቸው በርቷል።

ኢየሱስ አድጎ ስለነበረ ሰዎቹ እየሰገዱለት እንደነበር አውቋል።

ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

የመጡት ሰብዓ ሰገል ሶስት አልነበሩም።

ነገር ግን ሶስት ስጦታ ሰጥተዋል።

ያቀረቡለት ስጦታ ስለ እርሱ ምን ብለው እንደሚያምኑ አሳይቶታል።

ወርቅ እግዚአብሔርን ይወክላል። እነርሱም እርሱ አማኑኤል ወይም እግዚአብሔር በሰዎች መካከል እንደ ሰው ሆኖ መገለጡን አምነዋል። የሚቤዠን ዘመዳችን።

እጣን የሚገኘው የዛፍን ግንድ በመውጋት ከግንዱ ውስጥ እንደ ዘይት የሚፈስስ ፈሳሽ ከፈሰሰ በኋላ ሲጠነክር ነው።

ኢየሱስ ሐጥያት የሌለበት ደሙ በግርፋት ቆዳው ሲሰነጠቅ ከውስጡ እስኪፈስስ ድረስ ይመለካል።

የሚቃጠል መስዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ስጋ መሰዊያ ላይ ሲቃጠል ከባድ ጠረን ይፈጥራል። ነገር ግን እሳቱ ላይ እጣን ስትጨምሩበት ደስ የሚያል መዓዛ ይሰጣል። ይህም ደስ የሚያሰኝ ሽታ መስዋዕቱ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል።

ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር በስጋ ሲገለጥ ነው። የመለኮት ሙላት በሰው ውስጥ ኖረ።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ከውጭ በኩል የተገለጠው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። በውስጡ ያለው መንፈስ ደግሞ እግዚአብሔር አብ ነው።

ሐጥያት የሌለበት ኢየሱስ የተባለው ሰው ሰዎች ይድኑ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መስዋእት ማቅረብ ነበረበት።

ስለ ሐጥያታችን ዋጋ ለመክፈል በእኛ ቦታ መሞት ነበረበት።

ከርቤ ደግሞ ሰው ከሞተ በኋላ አስከሬኑ ሽታ እንዳይፈጥር ከራሱ እስከ እግሩ የሚነሰነስበት ቅመም ነው።

ለኢየሱስ የምናቀርበው ነገር ስለ እርሱ ምን እንደምናስብ ያሳያል።

ጌታ ሙሉ በሙሉ የሆነ መታዘዛችንን ለእርሱ እንድናቀርብ ይፈልጋል።

እርሱ ሃሳባችንን እና እንቅስቃሴዎቻችንን ሁሉ መቆጣጠር ይችል ዘንድ ፈቃዳችንን ሁሉ ለእርሱ እንድናስረክብ ይፈልጋል።

ኢየሱስ በጌቴሴማኒ ውስጥ የጸለየውን ዓይነት ጸሎት ለመጸለይ መለማመድ ያስፈልገናል፤ የራሳችን ፈቃድ እንዲፈጸም ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም መጸለይ አለብን።

ማቴዎስ 26፡39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።

ወደ ሰብዓ ሰገል ስንመለስ ከሔሮድስ እንዲያመልጡ ማስጠንቀቂያ ሲቀበሉ እናገኛቸዋለን።

ማቴዎስ 2፡12 ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።

እግዚአብሔር ሰብዓ ሰገልን በሕልም ተናገራቸው።

ሰብዓ ሰገል ኢየሱስን ፊት ለፊት አግኝተውታል፤ ከዚህም የተነሳ ሕይወታቸው ተለውጧል።

እርሱን ለማግኘት አንድን መንገድ ተከትለው ሄደዋል፤ ካገኙት በኋላ ግን ሌላ የተለየ መንገድ ተከትለው ይሄዳሉ። በፊት በሄዱበት መንገድ ተመልሰው በድጋሚ አይሄዱበትም።

ኢየሱስ የሰውን ሕይወት ይለውጣል።

አንድ ጊዜ ኢየሱስን አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ በኋላ በተለየ መንገድ ላይ ስትሄድ ራስህን ታገኛለህ።

ማቴዎስ 2፡13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።

እግዚአብሔር ሁልጊዜ እውነትን ጠብቆ የሚያቆይበት የመሸሸጊያ ቦታ አለው።

የሮማ ካቶሊኮች አውሮፓ ውስጥ ፕሮቴስታንቶችን እየገደሉ ሳለ እግዚአብሔር ፕሮቴስታንቶችን ማሳቹሴትስ አሜሪካ ውስጥ ፕሊማውዝ ሮክ ወደሚባል ቦታ መራቸው። በዚያ ነጻነትን አገኙ። ከዚያ ወዲያ የትኛውም ፖፕ የትኛውም የእንግሊዝ ንጉስ ሊያሳድዳቸው አልቻለም።

ማቴዎስ 2፡14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና … ወደ ግብፅ ሄደ፥

በሌሊት መንገድ መሄድ አደገኛ ነበረ። ነገር ግን መንገድ አለመሄድ ደግሞ ይበልጥ አደገኛ ሆነ።

ክርስትና ለፈሪዎች አይሆንም። እውነት ሁልጊዜ አብሯት አደጋ አለ።

ሁልጊዜ የማይቋረጥ መንፈሳዊ ጦርነት አለ፤ ኢየሱስን የተቀበልክ ጊዜ ደግሞ የሰይጣን ጠላት ትሆናለህ፤ ስለዚህ ሰይጣን ሊያጠፋህ ሌት ተቀን ይጥራል።

ግብጽ የዓለማዊነት ምሳሌ ናት።

ስለዚህ ኢየሱስ የሕጻንነት ዘመኑን በዓለማዊ ሰፈር አሳልፏል ግን ከስነምግባር መርሁ አልወረደም።

እግዚአብሔር ምድርን በአዳም ሐጥያት ምክንያት ከረገማት በኋላ የምድር ገጽታ ተለውጧል።

ሆኖም ግን የመጀመሪያዋ ኤደን አሁን ግብጽ ውስጥ የነበረች ይመስላል።

65-0829 የሰይጣን ኤደን

በስተመጨረሻ ሁሉን ሰርቶ ሲያጠናቅቅ… እኛም ደግሞ ተሰርቶ በተጠናቀቀው ማዕከል ውስጥ ገባን፤ ያም ሥፍራ ከኤደን በስተ ምስራቅ የሚገኘው የኤደን የአትክልት ሥፍራ ወይም ገነት ነበር። እግዚአብሔር የዓለምን ማዕከል በኤደን ገነት ግብጽ ውስጥ አደረገ፤ ማዕከሉም ከአትክልት ሥፍራው በስተምስራቅ ነበረ።

ቀጣዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ግብጽን ከእግዚአብሔር ገነት ጋር ያያይዛል፤ ይህም የኤደን ገነት ነው።

ዘፍጥረት 13፡10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።

ስለዚህ ኤደን ግብጽ ውስጥ ከነበረች ሁሉም ነገር ግብጽ ውስጥ ነው የጀመረው።

ስለዚህ ኢየሱስ ሐጥያትን ለማጥፋት የመጣበትን ተልዕኮ የጀመረው ሐጥያት መጀመሪያ ወደተጠነሰሰበት ቦታ በመሄድ ነው።

ደግሞም ግብጽ ውስጥ ስለ ኢየሱስ የሚመሰክር ምስክርም ነበረ፤ እርሱም ታላቁ ፒራሚድ ነው።

ይህ ታላቅ ፒራሚድ ሰዎች ከሰሩዋቸው የግንባታ ስራዎች ሁሉ ታላቅ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ ይመዝናል (የቻይናን ግምብ ካልቆጠርን)።

አናቱ ላይ ጉልላት የለውም።

ፒራሚድ አናቱ ጠፍጣፋ ሆኖ ሙሉ የሚያደርገውን ጉልላት የሚጠብቅ ከሆነ የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጻት የምጥጠብቀዋን ቤተክርስቲያን ወይም ሙሽራይቱን ይወክላል።

 

 

ታላቁ ፒራሚድ ውስጡ ክፍሎች ያሉት ብቸኛው ፒራሚድ ነው።

በምስሉ ላይ የምታዩት ቀዩ ክፍል የንጉሱ እልፍኝ የሚባል ሲሆን ውስጡ ባዶ የእሬሳ ሳጥን አለው።

ባዶው ሳጥን በቀጥታ የሚያመለክተው የኢየሱስን የመጀመሪያ ምጻት ነው።

ስለዚህ ታላቁ ፒራሚድ ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ይመሰክራል፤ እነዚህም ሰባት ዘመናት የአዲስ ኪዳን አማኞች ከኢየሱስ የመጀመሪያ እና ዳግም ምጻት መካከል በምድር የሚያሳልፉዋቸው ዘመናት ናቸው።

ኢሳያስ ግብጽ ውስጥ ስላለው ምስክር፣ መሰዊያ እና አምድ በተመለከተ ይናገራል። ይህም በመሃሏ እና በድንበሯ ነው።

በዚህ ካርታ ውስጥ ሰማያዊው ቀለም ሜዲተራንያን ባሕርን ይወክላል።

 

 

ታላቁ ፒራሚድ (ሮዙ አራት ማዕዘን) በካይሮ ከተማ ዳርቻ ጊዛ የሚባል አካባቢ ይገኛል።

ታችኛው የግብጽ ግዛት የናይል ደልታ (በቀይ ቀለም የተመለከተው) ወደ ሜዲተራንያን ባሕር ከመግባቱ በፊት ግማሽ ክብ ቅርጽ ይሰራል። ታላቁ ፒራሚድ ከዚህ ክበብ መሃከል ላይ ነው የተሰራው።

ታላቁ ፒራሚድ የናይል ደልታ መነሻ ላይ እንደመሆኑ የናይል ደልታ (ዙርያውን በቀይ መስመር የተመለከተው ታችኛው ግብጽ) እና የቀረው የግብጽ ግዛት ወይም የላይኛው ግብጽ ድንበር መሃል ላይ ነው የቆመው።

ኢሳይያስ 19፡19 በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔር ዓምድ ይሆናል።

ኢሳይያስ 19፡20 ይህም ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉና፥ እርሱም መድኃኒትንና ኃያልን ሰድዶ ያድናቸዋልና።

ሙሴ አይሁዶችን ከግብጻውያን ጨቋኞቻቸው ነጻ ሊያወጣቸው መጣ።

ከዚያ በኋላ ከሙሴ የሚበልጠው ኢየሱስ ከአለማመናችን እና ከሐጥያታችን ጭቆና ነጻ ሊያወጣን መጣ።

ስለዚህ ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት አስቀድሞ በሔኖክ የተሰራው ታላቁ ፒራሚድ ለኢየሱስ የመጀመሪያ እና ዳግም ምጻት ምስክር ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።

ከዚያም ኢየሱስ ወደ ግብጽ በሄደ ጊዜ ወደ ፒራሚዱ መጣ።

ይህም ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆነው የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነፍሳቸውን በትዕግስታቸው እንደሚያድኑ ያስረዳል። አንድ ቀን ኢየሱስ በክብር ይመጣል፤ በመጣም ጊዜ ከእርሱ ጋር በአየር ላይ ይሆኑ ዘንድ ለቃሉ ታማኝ የሆኑትን ከምድር ይነጥቃቸዋል።

 

 

53-0403 የሐጥያት ክፋት ወይም ጭካኔ እና ሐጥያትን ከሕይወታችን ለማስወገድ ያስከፈለው ዋጋ

ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ በሰማያት ላይ በዞዲያክ ነበር የተጻፈው። ከድንግሊቱ ይጀምራል፤ ጌታ የመጣው ከድንግል በመወለድ ነው። የሚጠናቀቀው ደግሞ በሊዮ ማለትም በአንበሳው ነው፤ ይህም ዳግም ምጻቱን ያመለክታል። እርሱም የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ጽፏል።

ሁለተኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በሔኖክ ሲሆን ከተጻፈ በኋለ በፒራሚድ ውስጥ ተቀምጧል።

ከዚያም ሶስተኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ ሲሆን እርሱም ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

በከዋክብት መካከል የተጻፈው ወንጌል 12ቱ የዞዲያክ ምልክቶች ናቸው።

ዞዲያክ ፀሃይ በሕዋ ውስጥ የምትሄድበትን ምሕዋር የሚያመለክቱ 12 የከዋክብት ስብስብ ናቸው።

አስትሮሎጀሮች እነዚህን የዞዲያክ ምልክቶች አላግባብ ተጠቅመው ጠንቋይ ለመሆን ሞከሩ።

ዞዲያክ ከየትኛው ምልክት እንደሚጀምር አያውቁም።

 

 

ምልክቶቹ መነሻም መጨረሻም በሌለበት ክብ መስመር ላይ ናቸው፤ ስለዚህ ከየትጋ እንደሚጀምር ማንም ሰው መገመት ይችላል።

ነገር ግን በየ2,000 ዓመቱ ክረምት ካለፈ በኋላ የጸደይ ምልክት ይለወጣል።

ይህም በምስራቅ በኩል መጋቢት 21 አካባቢ ልክ ፀሃይ ከመውጣቷ በፊት የሚታየው የከዋክብት ስብስብ ነው።

ከ4,000 ዓመታት በፊት ባቢሎን ውስጥ የጸደይ ምልክት ኤሪስ ወይም አውራው በግ ነበረ። የኮከብ ትንበያ ላይ የሚሰሩት አስትሮሎጀሮች ኤሪስ የጸደይ ምልክት ነው ይላሉ። ነገር ግን በኤክዊኖክ (ወይም መሬት በሌሎች ፕላኔቶች ስበት ምክንያት በዛቢያዋ ላይ ባለችበት በመዋለልዋ) የጸደዩ ምልክት ከኤሪስ ወደ አኳሪየስ ተዛውሯል። አኳሪየስ ከጎርጓዳ ሰሃን ውስጥ ውሃ የሚያፈስሰው ውሃ ተሸካሚ ነው። ስለዚህ ሁሉም ምልክቶች ለአስትሮሎጀሮች ከቦታቸው ተዛንፈውባቸዋል።

 

 

ሔኖክ ግን ለዚህ እንቆቅልሽ መፍቻ የሚሆን ፍንጭ ትቶልናል።

ሔኖክ ከፒራሚዱ አጠገብ የእስፊንክስ ሐውልት ቀርጾ አስቀምጧል። ይህም በምድር ሁሉ ላይ ከተሰሩ ሰው ሰራሽ ሐውልቶች ትልቁ ነው።

ይህ ሐውልት የዞዲያክ ምልክት የሚጀምርበትን ሚስጥር ይዟል።

እስፊንክስ ከላዩ የሰው ጭንቅላት አለው፤ ጺም ስለሌለው የሴት ፊት ነው፤ የቀረው አካሏ ደግሞ የአንበሳ ነው።

 

 

ሴቲቱ ቨርጎ ወይም ድንግል ትባላለች። ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ ከድንግል ሴት የተወለደ ወንድ ልጅ ሆኖ ነው የመጣው።

የዞዲያክ ምልክቶችን ተከትለን ስንሄድ የመጨረሻው ምልክት ሊዮ ወይም አንበሳው ነው። ኢየሱስ በዳግም ምጻቱ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ሆኖ ነው የሚመጣው።

መዝሙር 19፡1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።

4 በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥

5 እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።

 

 

ፀሐይ በ12ቱ የዞዲያክ ምልክቶች ውስጥ ታልፋለች፤ ይህም ኡደቷ ብርቱ ሰው የሆነው ኢየሱስ ሞትን አሸንፎ ሙሽራይቱን ሊወስዳት እስኪመጣ ድረስ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እንደሚያልፍ ያመለክታል።

ኢየሱስ ሙሽራይቱን ፍለጋ የሚመጣው ሙሽራ ነው።

ለባቢሎናውያን “ዞዲያክ” የሚለው ቃል “የሕያዋን ፍጥረታት ኡደት” የሚል ትርጉም አለው።

ለእነርሱ ችግር የሆነባቸው ግን ሚዛን ወይም ሊብራ የሚባለው ምልክት ነው።

ይህ ምልክት በግራ እና በቀኝ በክብደት እኩል ሆነው የሚቆዩ ሚዛኖችን ይመስላል።

ነገር ግን የሚዛኑ ሰሃኖች ሕይወት ያላቸው ነገሮች አይደሉም።

ስለዚህ የባቢሎን ካሕናት ግራ ተጋቡ። ይህንን ሚስጥር ሊፈቱት አልቻሉም።

የሔኖክ እስፊንክስ የዞዲያክ ኡደት መነሻው በድግልና የተወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መሆኑን እና እርሱም ሙሽራይቱን እንደሚፈልግ ያመለክታል።

ቀጣዩ ምልክት ደግሞ ሊብራ ሚዛኑ አይሁዶች አመዛዝነው ማንን እንደሚመርጡ መወሰን እንደሚጠበቅባቸው ያሳያል። የሞት ሰው የሆነውን ነፍሰ ገዳዩን በርባንን ወይም የሕይወት ራስ የሆነውን ኢየሱስን ከሁለቱ አንዱን ይመርጣሉ።

ሰው እንደመሆናቸው ዝንባሌያው ሞትን ወደ መምረጥ ነው።

ቀጣዩ ምልክት እስኮርፒዮ ሲሆን ይህም የሞት መውጊያ ያለው ጊንጥ ነው።

ኢየሱስ በቀራንዮ ሞትን፣ ሲኦልን እና መቃብርን ባሸነፈ ጊዜ ይህ የሞት መውጊያ ተሰብሯል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡55 ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ?

የሞት መውጊያ በቀራንዮ ተሰብሯል። ንሰሐ የሚገቡ ሐጥያተኞች አሁን ከሐጥያት ነጻ ሆነው በመሞት ከሲኦል እሳት ማምለጥ ይችላሉ።

ቀጣዩ ምልክት ቀስተኛው ሳጂታሪየስ ነው።

ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ የሚገለጠው ቀስተኛ ሲሆን እርሱም ደጋን ይዟል ግን ቀስት የለውም። ይህም አሳሳች መሆኑን ይጠቁማል። ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር ኃይለኛው የሮማ ካቶሊክ ፈረስ ላይ ይቀመጣል። ነጩ ፈረስ የሐይማኖት አሳሳችነት ምልክት ነው። የካቶሊክ ሊቀ ጳጳሳት በ860 ዓ.ም ከፖፕ ኒኮላስ ጀምሮ ለ1,000 እስከ ፖፕ ፖውል 6ኛው 1963 ዓ.ም ድረስ በራሳቸው ላይ ዘውድ ጭነዋል።

በ1963 ወንድም ብራንሐም ከሰባቱ ማሕተሞች ስድስቱን ገልጦ አስተሯል፤ ያም ደማቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ፖፑን እና ካቶሊካዊውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኬኔዲን ገድሏቸዋል። ፖፕ ፖውል በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ከማየቱ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ አውልቋል።

በሰማያት ላይ ያሉት ከዋክብት እና ከድንጋይ የተሰራው ፒራሚድ የወንጌሉን እና የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ታሪክ ይናገራሉ።

 

 

ወደ ግብጽ እና ወደ ዮሴፍ እንመለስ።

ማቴዎስ 2፡15 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

ዮሴፍ ግብጽ ውስጥ ሳለ ከመጠበቅ በቀር ምን ማድረግ አልቻለም።

ወደ እሥራኤል የሚመለስበትን ትክክለኛ ጊዜ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነበር።

ከእግዚአብሔር ቀድመን ለመሮጥ መሞከር የለብንም።

አንድ ትንቢት ድርብ ፍጻሜ ሊኖረው ይችላል።

የእሥራኤል ሕዝብ ከግብጽ ሲወጣ ሕዝቡ በሙሉ አንድ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተቆጥሮ ነበር የወጣው። ይህም አይሁዶች ከግብጽ የወጡበት የመጀመሪያው አይሁዶች ፍልሰት ነበር።

ቀጥሎ ኢየሱስም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ከግብጽ ወጣ። ሁለተኛው ፍልሰት ደግሞ ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት የሐይማኖት ስርዓት የወጣችበት ነው። ቤተክርስቲያን ጥላው የወጣችው ይሁዲነት የማይጠቅሙ የሐይማኖት ሥርዓቶች እና ገንዘብ አላግባብ በማግኘት ጥማት የተሞላ ልማድ ነበረ።

ማቴዎስ 2፡16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

ሔሮድስ በቁጣ ነደደ። ሰብዓ ሰገል ለሁለት ዓመት በመንገድ ሲጓዙ ቆይተዋል። ይህንን መረጃ ሔሮድስ ከእነርሱ በጥንቃቄ ጠይቆ ነው የተረዳው። ስለዚህ መሲሁን ለማጥፋት በማሰብ በጥንቃቄ አስልቶ የሁለት ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ሕጻናትን በሙሉ ገደለ። ሰው እንደመሆናችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አናስተውልም። አንዳንዶች መሞት አለባቸው፤ አንዳንዶች ደግሞ መኖር።

ነገር ግን ከዚህ ሕይወት በኋላ ለአማኞች የዘላለም ሕይወት አለ።

የዚያን ጊዜ የምድር ቆይታችን አጭርም ይሁን ረጅም አንዳች ልዩነት እንደማይፈጥር እናውቃለን።

ልዩነትን የሚያመጣው እግዚአብሔርን መታዘዛችን ወይም አለመታዘዛችን ነው።

ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ብለው የሞቱ ሰዎች ከሞት በኋላ ባለው ሕይወት ውስጥ ብዙ ሽልማት ይጠብቃቸዋል።

ራዕይ 2፡13 የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።

እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሙ እንዲመዘገብ ከማድረጉ ውጭ ታሪክ ስለ አንቲጳስ አንዳችም አልጻፈም።

አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃል ተገድሏል። ይህም የሚያሳዝን ይመስላል። ነገር ግን ስሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊመዘገብ መቻሉ ታላቅ ክብር ነው።

አንቲጳስ ቶሎ ነው የሞተው ነገር ግን ለዘላለም ስናደንቀው እንኖራለን። አንዳችም የሚጸጸትበት ነገር የለውም።

መሞት የሚያሳዝን ነገር በሆንም ስለ እግዚአብሔር መሞት ግን ጥቅም ነው

ፊልጵስዩስ 1፡21 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።

 

 

ማቴዎስ 2፡17 ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ … የተባለው ተፈጸመ።

ኤርምያስ 31፡15 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።

ማቴዎስ 2፡18 ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።

ራሔል የሞተችው ቢንያም ሲወለድ ነው።

ራማ በቢንያም ግዛት ውስጥ የሚገኝ ከተማ ሲሆን ሔሮድስ ሕጻናት ልጆችን በጭካኔ የገደለበት ቦታ ነው። ራሔል የቢንያም እናት እንደመሆኗ ከቢንያም ነገድ ለተወለዱ ልጆች ሁሉ እናት ናት።

ያለ ዕድሜ መሞት ምን ማለት እንደሆነ ራሔል አይታዋለች።

ሕይወት የሆነው መሲህ መምጣቱ ሞት የሆነው ዲያብሎስ ክፉ ድንጋጤ ፈጥሮበታል።

ሐሰተኛና ሰው ሰራሽ ንጉስ የሆነው ሔሮድስ እውነተኛ የሆነውን ንጉስ ኢየሱስን ለማጥፋት ብሎ ወንድ ሕጻናትን ጨፈጨፈ።

ወደ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ስንቃረብ የግል ምርጫን እንደግፋለን በሚሉ ፖለቲከኞች አማካኝነት በፈቃደኝነት ጽንስ በማቋረጥ በየዓመቱ 60 ሚሊዮን ሕጻናት ከመወለዳቸው በፊት ሲገደሉ እያየን ነው። አሁንም በድጋሚ ሰይጣን ሕጻናት እንዲገደሉ ግፊት እያደረገ ነው።

በመጀመሪያው ፍልሰት አይሁዶች ከግብጽ ወጡ። በዚያን ጊዜ ፈርኦን የአይሁድ ወንድ ልጆች በሙሉ እንዲገደሉ ትዕዛዝ አወጣ።

በሁለተኛው ፍልሰት ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት ወጣች። በዚያ ጊዜ ደግሞ ሔሮድስ የአይሁድ ወንዶች ልጆች እንዲገደሉ ትዕዛዛ ሰጠ። ሞት ልጆችን በላቸው።

ሶስተኛው ፍልሰት የሚሆነው ልጆች በጴንጤ ቆስጤ ዕለት ወደተጀመረው ወደ አዲስ ኪዳን አባቶች እምነት ሲመለሱ ነው።

የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ይህንን ፍልሰት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ እምነቶች አማካኝነት ትቃወመዋለች፤ በዚህም ድርጊቷ በዘመን መጨረሻ ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው እንዲሞቱ እየገፋቻቸው ናት።

 

 

ማቴዎስ 2፡19 ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦

እግዚአብሔር ሕልም ተጠቅሞ ለዮሴፍ ተናገረ። ከዮሴፍ የሚጠበቅ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ጊዜው ደርሷል አሁን ተነስተህ ሂድ እስኪለው ድረስ መጠበቅ ብቻ ነው።

ከዚህ ትልቅ ትምሕርት እንማራለን።

ማቴዎስ 2፡20 የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።

አደገኛ ጠላቶች እውነትን ይቃወማሉ። እግዚአብሔር ግን እነዚያን ጠላቶች ሞት እስከሚያስወግዳቸው ድረስ የራሱን ሕዝብ እንዴት አድርጎ እንደሚሸሽግ ያውቅበታል። ከዚያ በኋላ የእውነት እርምጃ ይቀጥላል።

ሰይጣን ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ የሚሰነዝረው ጥቃት በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የጥቂት ጊዜ ዝምታ ነው።

ማቴዎስ 2፡21 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።

ስለዚህ ኢየሱስ የሁለት ዓመት ሕጻን ሆኖ ከእሥራኤል ምድር ሸሽቶ ሌላ ቦታ አድጎ ተመለሰ።

ሔሮድስ በጭካኔው ያስነሳው ስደት ብዙ መከራ አስከትሏል ግን ኢየሱስን ሊገድለው አልቻለም።

የሔሮድስ ጨካኝ ልጅ አርኬላዎስ በይሁዳ ገዥ ስለነበረ ዮሴፍ ወደ ሰሜን አልፎ በገሊላ ወዳለችው ናዝሬት እንዲሄድ ግድ ሆነበት።

ኢየሱስ ደግሞ እስከ ጉልምስና ድረስ ማደግ የነበረበት በናዝሬት ነበረ።

ስለዚህ ሔሮድስ ያስነሳቸው ጨካኝ ስደቶች ለእኛ አሳዛኝ ቢመስሉም እንኳ አንዳቸውም የእግዚአብሔርን እቅድ ሊያሰናክሉ አልቻሉም።

ዮሴፍ ወደ ናዝሬት ሊሄድ መገደዱ ለእግዚአብሔር እቅድ ምቹ አጋጣሚ ነበር። በሌላ አነጋገር ዲያብሎስም እንኳ ሳይቀር ሳይወድ በግዱ ለእግዚአብሔር ይታዘዛል። ሰይጣን ግን ለአገልግሎቱ አንዳችም ዋጋ አያገኝም።

ስለዚህ የሰይጣንን ጥቃቶች መፍራት የለብንም። ልክ የባሕሩ ዳርቻ ለውሃው እንቅስቃሴ ገደብ እንደሚያበጅለት ሁሉ እግዚአብሔርም ሰይጣን ማድረስ ለሚችለው ጥፋት ገደብ ያበጅለታል።

ማቴዎስ 2፡22 በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤

የገሊላ ከተማ በእሥራኤል ሰሜናዊ ግዛት ውስጥ ከገሊላ ባሕር አጠገብ ነበረ።

 

 

ማቴዎስ 2፡23 በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

ናዝራዊ ማለት ከናዝሬት የመጣ ሰው ነው።

ነገር ግን እንደዚያ ተብሎ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፈ ትንቢት የለም።

ተጠራጣሪዎች ይህንን ነጥብ ይዘው መጽሐፍ ቅዱስን ለመተቸት ይጠቀሙበታል፤ ነገር ግን አንዳንድ ትንቢቶች በቃል የተነገሩ ብቻ እንጂ ያልተጻፉ መሆናቸውን ስለማያውቁ ነው።

መሲሁ ናዝራዊ ይሆናል የሚለው ትንቢት በቃል ብቻ የተነገረ ትንቢት ነው።

ይህ ትንቢት ዘመኑ ደርሶ እስከሚፈጸም ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ በአፍ ብቻ እየተነገረ ነው የደረሰው።

በዚህ መንገድ አይሁዶች ከናዝሬት አንድ ነብይ ይመጣ ዘንድ እንዳለው ተረድተዋል።

ኢየሱስ ሰው እንደመሆኑ ለሕዝቡ ባሳያቸው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል እርሱ ነብይ መሆኑን ገልጦላቸዋል።

አይሁዶች ኢየሱስን ከናዝሬት ከተማ ጋር ማያያዝ ለምደዋል፤ ያም ትልቅ ሰው እስኪሆን ድረስ ያደገበት ቦታ ነው።

ስለዚህ ከናዝሬት የመጣ ነብይ እንደመሆኑ ስለ እርሱ በቃል ብቻ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ተረድተዋል።

ማቴዎስ 21፡11 ሕዝቡም፦ ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።

አይሁዶችን ከናዝሬት ስለሚመጣው ናዝራዊ ነብይ በቃል ብቻ የተነገረውን ይህንን ትንቢት በደምብ ያውቁት ነበር።

 

 

ሌላም ያልተጻፈ ትንቢት አስቡ።

ሐጌ እና ዘካርያስ ቤተመቅደሱ ከፈረሰ በኋላ በ536 ዓመተ ዓለም እንደገና ሊሰራ በተጀመረበት ጊዜ ነበር ትንቢት የተናገሩት።

ዕዝራ 5፡1 ነብያቱም ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእሥራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።

የቤተመቅደሱ መሰረቶች በ536 ዓመተ ዓለም ተጣሉ፤ ከዚያም በኋላ አይሁዶች ለ17 ዓመታት ግንባታውን አቋርጠዋል፤ ግንባታውን የቀጠሉት በንጉስ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት ማለትም በ520 ዓመተ ዓለም ነበር።

ከዚያ በኋላ ቤተመቅደሱን በአራት ዓመታት ውስጥ ሰርተው በ516 ዓመተ ዓለም አጠናቀቁ።

 

 

ዕዝራ 4፡24 በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ቀረ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተጓጐለ።

ሐጌ 2፡10 በዳርዮስም በሁለተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦

ትንቢተ ሐጌ ሁለት ምዕራፍ ብቻ ነው ያለው።

ሁለተኛው ምዕራፉ በንጉስ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት (520 ዓመተ ዓለም) ላይ ነው የሚጀምረው፤ ያም የመቅደሱ ግንባታ እንደገና የተጀመረበት ዓመት ነው።

ሐጌ ግን እስከ ንጉስ ዳርዮስ ዘመነ መንግስት ስድስተኛው (516 ዓመተ ዓለም) ዓመት የቤተመቅደሱ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለአራት ዓመታት ትንቢት ሲናገር ቆይቷል።

ዕዝራ 6፡14 የአይሁድም ሽማግሌዎች በነቢዩ በሐጌና በአዶ ልጅ በዘካርያስ ትንቢት ሠሩ ተከናወነላቸውም። እንደ እስራኤልም አምላክ ትእዛዝ፥ እንደ ፋርስም ነገሥታት እንደ ቂሮስና እንደ ዳርዮስ እንደ አርጤክስስም ትእዛዝ ሠርተው ፈጸሙ።

ዕዝራ 6፡15 ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ።

ስለዚህ ሐጌ ከዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በኋላ የተናገራቸው ትንቢቶች አልተጻፉም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ትንቢቶች ቢጻፉም ያልተጻፉ ትንቢቶችም አሉ።

1ኛ ሳሙኤል 10፡10 [ሳኦል] ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።

ሳኦል ትንቢቶቹን በአፉ ተናግሯል፤ ግን የተናገራቸው ትንቢቶች አልተጻፉም።

አንዳንድ ትንቢቶች በሰዎች አፍ ብቻ ነው ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉት።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23