ማቴዎስ ምዕራፍ 02 - ሰብዓ ሰገል እና ኢየሱስ የሁለት ዓመት ልጅ በነበረ ሰዓት
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ሮም ልትገድለው ፈለገች። ሰብዓ ሰገል ያመጡለት ስጦታ ስለ እርሱ ምን እንደሚያስቡ ይገልጣል። ኢየሱስን ለማግኘት ከቤተክርስቲያን ውጡ።
First published on the 5th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ራዕይ 12፡1 ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።
ይህ አስደናቂ ራዕይ ነው። ሴቲቱ እሥራኤል ናት። ልክ እንደ ፀሃይ ብሉይ ኪዳን ለእሥራኤል ብርሃን እና ጽድቅ ሆኖ ይመራት ነበር፤ ሕጉ ደግሞ የፀሃይን ብርሃን በሌሊት እንደምታንጸባርቀው ጨረቃ ነበረ። ሕጉ እግዚአብሔር የሚያስበውን አስተሳሰብ ያስነጸባርቃል። አይሁዶች በሕጉ ላይ መቆም ይችላሉ ምክንያቱም አንድ ቀን መሲሁ መጥቶ ሕጉን ደመቅ አድርጎ እንደሚያበራላቸው ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሕጉን ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ መንገድ ይፈጽመዋል። ከዋክብቱ የእሥራኤል አሥራ ሁለት ነገዶች የተሰየሙባቸው አሥራ ሁለቱ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር እርሱን ያመልኩት ዘንድ አይሁዶችን ከአሕዛብ ነገዶች መካከል ለይቶ ጠራቸው።
ራዕይ 12፡2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።
ልጅ መውለድ በጣም ከባድ ነው።
እግዚአብሔር የመሲሁን ሕይወት ወደ እሥራኤል ሊያመጣ ባሰበ ጊዜ ሰይጣን ደግሞ ሞትን ለማምጣት በመፈለግ ምላሽ ሰጠ። በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል የማያቋርጠው ትግል እምነት እና አለማመን ነው።
ከመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነብይ ከሚልክያስ በኋላ እግዚአብሔር ለ400 ዓመታት ሳይናገር ቆይቶ ነበር።
እሥራኤልም መንፈሳዊ ድርቀት ውስጥ ገባች።
እሥራኤል በታላቁ አሌግዛንደር አማካኝነት በግሪኮች ተገዝታ ነበር። ሔለኒዝም የተባለው የግሪኮች ባሕል ለአይሁዳውያን የአኗኗር ዘይቤ ትልቅ ስጋት ነበረ።
ራዕይ 12፡3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥
ዘንዶው ሰይጣን ነው።
ሰይጣን ከገነባቸው መንግስታት ሁሉ በጉልበቱም በግፈኛነቱም አንደኛ የነበረው የሮማውያን መንግስት ነው።
ሮም የሰባቱ ኮረብቶች ከተማ በመሆኗ በሰባቱ ኮረብቶች ዙርያ ግምብ አጥር ከሰሩ በኋላ ዝነኛ ሆነች። በዚያ ዘመን አንድ ከተማ ለጥበቃ ሲባል በዙርያው ግምብ አጥር ያስፈልገው ነበር።
የሮማ መንግስት ማዕከል ሮም ውስጥ በኮፒቶሊን ኮረብታ ላይ የተሰራው የካፒቶሊነስ ቤተመቅደስ ነበረ።
ጣኦት አምላኪው የሮማ መንግስት በ476 ዓ.ም በባርቤሪያውያን እጅ ወደቀ። የሮማ መንግስት ከወደቀበት አመድ ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተነሳችና መናገሻዋን እስከ ዛሬ ድረስ በላተራን ቤተመንግስት እና በካየሊያን ኮረብታ ላይ በሚገኘው ባሲልካ (ትልቅ ቤተክርስቲያን) አደረገች።
እነዚህ ሰባት ኮረብታዎች የአውሬው ሰባት ራሶች ናቸው።
ፖፑ ወደ ስልጣን ሲወጣ የሮማውያን ነገስታትን ፈላጭ ቆራጭ መንፈስ ተሞላ፤ በጨለማው ዘመን ውስጥ ደግሞ ክርስቲያኖችን በሚገድለውን በሮማዊው ንጉስ በኔሮ መንፈስ ተሞላ።
ሰባቱ ዘውዶች የሚወክሉት የሮማ ሪፓብሊክን ያፈራረሰውን ከቤተሰቡ አምስት አባላትን የገደለውን ዩልየስ ቄሳር ነው፤ እርሱም ንጉስ ሆነ እርሱንም ተከትሎ ጨካኙ እና ግፈኛው ኔሮ ነገሰ። ሰባተኛው ሰው ጋልባ ነበረ፤ እርሱም በሰራዊቱ ድጋፍ የንጉስነትን ስልጣን ነጥቆ ነው የወሰደው።
ጣኦት አምላኪዋ ሮም ፈላጭ ቆራጭ መሪ እንዲሁም የባቢሎናውያን አረማዊ ሚስጢራት ፖንቲፍ እና በሥላሴ መልክ የሚታወቁት የግብጽ አማልክት ነበሯት። ቤተክርስቲያን እስከ ዛሬም ድረስ ሥላሴ ሚስጥር ነው ትላለች። ዲሴምበር 25 ቀን የሚከበረው የፀሃይ አምላክ ቀን ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገብቶ ክራይስትስ ማስ ወይም ክሪስማስ ሆነ። ይህም ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ልደት ቀን ተብሎ መከበር ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ክሪስማስን እንድናከብር አልተጠየቅንም። እነዚህ ሁሉ የኒቅያ ጉባኤ በ325 ዓ.ም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለውን ቃል ሥላሴን ሲቀበል ወደ ቤተክርስቲያን መግባት የጀመሩ ስሕተቶች ናቸው።
አስሩ ቀንዶች በመጨረሻው ዘመን የሚነሱ እና ወታደራዊ ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ የሚሰጡ አስር ወታደራዎ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ናቸው። (ጋልባን አስታውሱ)። ይህም ፖፑ በታላቁ መከራ ዘመን ዓለምን እንዲመራ ያስችለዋል። ስሕተት ከቤተክርስቲያን ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የሚጠፋው በዚህ መንገድ ነው።
ራዕይ 12፡4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
ከዋክብት ከሰማይ የተወለዱ ሰዎችን የሚወክሉ ምልክቶች ናቸው። እግዚአብሔር ሰዎችን በሶስት ምድብ ነው የሚመለከታቸው። አይሁዶች፣ አሕዛብ፣ እና በከፊል አይሁድ በከፊል ደግሞ አሕዛብ የሆኑ ሳምራውያን። “ጅራቱ” ሰይጣን የሚናገረውን የውሸት ተረት ተረት የሚገልጽ ምልክት ነው። ስለዚህ ሰይጣን በሮም ተጠቅሞ አይሁዳውያን (ከሶስቱ ምድቦች አንዱ) ክርስቶስን እንዲሰቅሉና ከሕይወት መጽሐፍ እንዲደመሰሱ አስደረገ። በዚህ ምክንያት በቀራንዮ አይሁዳውያን ከሰማያዊ ሕይወት ተጎትተው ወደቁ።
ሮም እሥራኤልን በ63 ዓመተ ዓለም ገዛች፤ ስለዚህ ኢየሱስን ደግሞ ልክ ሲወለድ ልታጠፋው ተዘጋጅታ ነበር።
የሮም የመጀመሪያ መልእክተኛ እንደ አሻንጉሊት ንጉስ ያስቀመጡት ኤዶማዊው ንጉስ ሔሮድስ ነበር።
በሔሮድስ በኩል የተደረገው ሙከራ ሲከሽፍ ሮማዊውን የይዱዳ ገዥ ጴንጤናዊ ጲላጦስ ተጠቅመው ኢየሱስን ገደሉ።
እግዚአብሔር ለአብራሐም የተናገረውን ስሙ።
ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።
ስለዚህ የአይሁድ ሕዝብ መሲሁን ኢየሱስን ወልደዋል።
ራዕይ 12፡5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
የእሥራኤል ሕዝብ መነሻቸው ከክርስቶስ ልደት በፊት 2,400 ዓመታት ቀድሞ ከተጠራው ከአብራሐም ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በ33 ዓመቱ ሲሞት ዕድሜው ከአይሁድ ሕዝብ ዕድሜ ጋር ሲነጻጸር እንደ ሕጻን ልጅ ዕድሜ ነበር። ከአርማጌዶን ጦርነት የሚተርፉትን የአሕዛብ ወገኖች በሚሌንየሙ ወይም በ1,000 ዓመታቱ የሰላም ዘመን ውስጥ ኢየሱስ እራሱ ነው በብረት በትር የሚገዛቸው።
ስለዚህ ማቴዎስ ምዕራፍ 2 የሚጀምረው የአይሁድ ንጉስ ተብሎ በተቀመጠው በሔሮድስ የግድያ ዘመቻ ነው፤ እርሱም እውነተኛውን የአይሁድ ንጉስ ኢየሱስን መግደል ፈለገ። ሐሮድስ ኤዶማዊ እንጂ አይሁዳዊ አልነበረም። ስለዚህ ለእሥራኤል ባዕድ ነው።
የመጨረሻው ፖፕም ባዕድ ሰው ነው የሚሆነው እንጂ የሮማ ካቶሊክ ካርዲናል አይደለም። እንደምንም ብሎ በማታለል የፖፕነት ስልጣን ላይ ይወጣል።
ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።
እንደተለመደው በካርዲናሎች ጉባኤ ተመርጦ አይደለም ወደ ስልጣን የሚመጣው።
ማቴዎስ 2፡1 ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ … ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
አይሁዶች በመንፈስ ጠውልገው ደርቀው ነበር።
እግዚአብሔርን በራሳቸው ሰው ሰራሽ መንገድ ነበር የሚያመልኩት። ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ብዙ ርቀው መሄዳቸውን አላወቁም ነበር።
ኢሳይያስ 53፡2 በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤
ለእግዚአብሔር የነበራቸው ናፍቆት ጠፍቷል። ለሮማውያን ያላቸው ፖለቲካዊ ጥላቻ እና ለገንዘብ የነበራቸው ትልቅ ፍቅር ለእግዚአብሔር ቃል የነበራቸውን ቅናት ተክተዋል።
ንጉሳቸው የውሸት ንጉስ ነበረ። ሔሮድስ ከይሁዳ በስተደቡብ ከምትገኛው ከኤዶምያስ ነው የመጣው፤ ስለዚህ አይሁዳዊ አልነበረም። መቃእብያን ቤተሰቦች ግሪካዊ ገዥዎቻቸውን በመገልበጥ ፖለቲካዊ ስልጣን ያዙ። በስተመጨረሻም በ110 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነጻ የሆነች የአይሁድ ሕዝብ መንግስት ተመስርታ ነበር። በ125 ዓመተ ዓለም አካባቢ አይሁዶች በወታደራዊ ድላቸው በመደሰት ሄደው ኤዶምያስንም ገዙ፤ ኤዶምያስ ግን ከተሰጣቸው ከተስፋይቱ ምድር ድንበር ውጭ ነበር። በዚያም ኤዶማውያንን አስገድደው ወደ አይሁድ እምነት አመጧቸው።
አይሁዳውያን እግዚአብሔር በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ይሁዳ ደቡባዊ ድንበራቸው እንዲሆን አድርጎ ከሰጣቸው ግዛት አልፈው መሄዳቸው በጨካኙ ንጉሳቸው በሔሮድስ እጅ እንዲሰቃዩ አጋልጧቸዋል። በ63 ዓመተ ዓለም ሮም እሥራኤልን አሸንፋ ገዛቻት፤ ከዚያ በኋላ በ37 ዓ.ም የሮም መንግስት ምክር ቤት ሔሮድስ የአይሁዶች ንጉስ እንዲሆን ወሰነ።
አይሁዶች በሙሴ ሕግ ውስጥ ያልተጠቀሱ እንደ ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ እና ረቢ የተባሉ የሐይማኖት መሪዎች ነበሩዋቸው። ከዚህም የተነሳ ብዙ ጉዳት ሊያደርስባቸው የሚችል ሰው ሰራሽ የሐይማኖት ስርዓት ይከተሉ ነበር። የሐይማኖት መሪዎቻቸው መሲሃቸውን ኢየሱስን ለመቀበል እምቢ እንዲሉ በስተመጨረሻው በሮማውያን እጅ እንዲያስገድሉት ገፋፍተዋቸዋል። ከዚያ በኋላ በ70 ዓ.ም ሮማውያን አይሁዶችን አጠፉ።
ሰይጣን እንዲህ ነው የሚሰራው። እርሱን እንድታገለግሉት ካባበላችሁ በኋላ ተመልሶ ያጠፋችኋል።
ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት፣ እርስ በርስ የሚጋጩ ሃሳቦች አሉበት፣ አፈ ታሪኮች እና የተሳሳተ አተረጓጎም አለበት በማለት የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን ይገፉታል።
ነገር ግን ኢየሱስ በሚያስበው ሃሳብ እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ምክንያቱም ቃሉ የሃሳቡ መግለጫ ነው። አንድ ሰው በማንነቱ እና በአስተሳሰቡ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ስለዚህ ስለ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩት እና ስለ ኢየሱስ የምታስቡት አንድ ነው።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት አለበት በማለቷ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ለእርሷ ራስ እንዳይሆን እምቢ እያለች ነው። ዛሬ ፓስተሮች የቤተክርስቲያን ራስ ነን ይላሉ። ለቤተክርስቲያንም መጽሐፍ ቅዱስ የትጋ ችግር እንዳለበት ይነግሯታል። ፓስተሮች የኢየሱስን ቃል ሊያርሙ እየሞከሩ ነው። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው። ስለዚህ በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ እግዚአብሔር ሕጻኑን ኢየሱስን የሚያመልኩ ሰዎችን ለማግኘት ከእሥራኤል ውጭ ሲፈልግ ነበር። እነዚህ ሰዎች ጠቢባን ነበሩ፤ ስለተማሩ ሳይሆን ኢየሱስን እየፈለጉ ስለነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስን የምንፈልግበት መጠን እውነተኛውን ጥበባችንን ያንጸባርቃል። ጠቢብ የሆኑ ሰዎች ኢየሱስን ይፈልጉታል።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም እንከን የሌለው ፍጹም ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለማወቅ ጥበብ ይጠይቃል።
ማቴዎስ 2፡2 እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ … መጡ።
ኢየሱስ የአይሁድ ንጉስ ሆኖ ነው የተወለደው።
እንዲህ መወለዱ እውነተኛው የአይሁድ ንጉስ እንዲሆን አድርጎታል።
ሔሮድስ እውነተኛ ንጉስ ስላልነበረ የኢየሱስ መወለድ አስደንግጦታል። ሔሮድስ አይሁድ አይደለም ደግሞም ከነገስታት የዘር ሐረግ አልተወለደም። ሔሮድስ ሮማውያን በዙፋን ያስቀመጡት አሻንጉሊት ነበረ። ሮማውያን ሔሮድስ ለእነርሱ እስከተገዛ እና አይሁዳውያንን ለሮማውያን እስካስገዛ ድረስ ንጉስ የሚለውን ማዕረግ ለጥፈውለታል።
ይህም ልክ የዚህ ዘመን ፕሮቴስታንት ፓስተሮች ቤተክርስቲያኖቻቸውን እንደ ሥላሴ እና ክሪስማስ ለመሳሰሉ የሮማ ካቶሊክ አስተምሕሮዎች እንደሚያስገዙ ማለት ነው።
አይሁዶች በመንፈሳዊ ድርቀት ውስጥ ስለነበሩ የዘመኑን ምልክት ለይተው መረዳት አልቻሉም።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን በኮከብ የተመሰለው መሲህ ከእሥራኤል ዘንድ የንጉስ በትር ይዞ እንደሚገዛ ተናግሮ ነበር።
ዘኁልቁ 24፡17 … ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥
ሰብዓ ሰገልን ለሁለት ዓመት ያለማቋረጥ ማታ ማታ ሲመራ የነበረው ኮከብ ፍጥረታዊ ኮከብ አልነበረም ወይም የፕላኔቶች በአንድነት መሰብሰብም አልነበረም።
ኮከቡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሰብዓ ሰገልን ወደ ክርስቶስ እንዲመራ የተሰራ ኮከብ ነበረ።
ዛሬም ሰዎች ጠቢብ ሆነው ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ መፈለግ ቢጀምሩ በተመሳሳይ መንገድ መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ ይመራቸዋል
ሰብዓ ሰገል የተጓዙበት መንገድ አደጋ የሞላበት ነበረ፤ እነርሱ ግን አንድ ዓላማ ብቻ ነበራቸው፤ እርሱም ኢየሱስን ማምለክ ነበረ።
ክርስቲያኖች ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያናቸው ዝና ብለው መስራት የለባቸውም። ኢየሱስን የአምልኮዋቸው ዋና ትኩረት ለማድረግ እርሱን ብቻ መፈለግ አለባቸው።
እግዚአብሔር ክብሩን ከማንም ጋር አይጋራም። ኢየሱስ አማኑኤል እንደመሆኑ እግዚአብሔር በስጋ ከእኛ ጋር ሆኗል ማለት ነው። የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ በስጋ አድሯል።
ኢሳይያስ 42፡8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ሰብዓ ሰገል እጅግ ትልቅ ጥበብ ነው የተሰጣቸው፤ አለዚያ ሕጻኑ ኢየሱስ የኃያሉ እግዚአብሔር በሰው አካል ውስጥ መገለጥ መሆኑን ሊያስተውሉ ባልቻሉ ነበር።
ጥበበኛ ሰዎች ይህንን ሚስጥር መረዳት ይችላሉ። በዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ፓስተሮች የተታለሉ ሰዎች ይህንን ሚስጥር መረዳት አይችሉም።
ስለዚህ ዛሬ ክርስቲያኖች ልባም ቆነጃጅት ወይም ሰነፍ ቆነጃጅት ተብለው ይከፈላሉ።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።
ድንግል ሴት ንጹህ ሴት ስለሆነች የዳኑ ክርስቲያኖችን ትወክላለች።
አንዳንድ ሰዎች በቂ ጥበብ ስለሚያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር ያስተውላሉ።
ሌሎች ግን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ምን ማለት እንደሆኑ ባናውቅም ችግር የለውም እስኪሉ ድረስ ተጃጅለዋል።
ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበሩ አይሁዶች መሲሁ የት እንደተወለደ ባያውቁም ችግር እንደሌለ አስበዋል።
ማቴዎስ 2፡3 ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
ዘመኑ አደገኛ ነበረ። ወንበዴዎች በመንገዶች ዳር እና ዳር ያሉ ኮረብታዎች ላይ ሆነው ያደፍጡ ነበረ።
ለዚህ ነው ኢየሱስ በመንገድ እየሄደ ሳለ በወንበዴዎች ተይዞ ተደብድቦ ስለተዘረፈው አይሁዳዊ በምሳሌ የተናገረው።
አንዳንድ የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት በዚያ ዘመን መንገድ መሄድ የፈለገ ሰው ወንበዴዎች ሳያጠቁት በሰላም መሄድ ከፈለገ ቢያንስ 150 የታጠቁ ሰዎች ሊያጅቡት ያስፈልጋል። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የታጠቁ ሰዎች እና አሽከሮቻቸው ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ትልቅ ትኩረት ስበዋል።
አይሁዳውያን በሮማውያን ጭቆና ስር ቆይተው ከእግዚአብሔር በጣም በመራቃቸው አዲሱ ንጉሳቸው መወለዱን ሲሰሙ ከመደሰት ይልቅ ተደናግጠዋል።
ሰው ሰራሽ በሆነው ሐይማኖታቸው በልጽገዋል። ተደላድለውና ተመችቷቸው ከሚኖሩበት ሐይማኖታዊ አቋማቸው የሚያናውጣቸውን አይፈልጉም ነበር።
ማቴዎስ 2፡4 የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
ሔሮድስ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች መሲሁ የት እንደሚወለድ እንዲነግሩት ጠየቀ። የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር እነርሱን ትቶ አልፎ ከሩቅ ከምሥራቅ ለመጡ ሰዎች የመሲሁን መወለድ መግለጡ ትንሽም ጥያቄ አልፈጠረባቸውም፤ ይህም ምን ያህል እንደ ደነዘዙ ያሳያል።
ስለዚህ በኢየሱስ ዳግም ምጻትም የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን በሙሉ ከመጽፍ ቅዱስ ብዙ ርቀው ነው የሚገኙት፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ ሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽናዊ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ) የቤተክርስቲያን ሃሳቦችን ይከተላሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ቃላት እና አባባሎች ተሞልተዋል፤ ለምሳሌ ሥላሴ፣ ዲሴምበር 25፣ ኢየሱስ የመለኮት አካል ነው፣ የመለኮት የመጀመሪያው አካል፣ የመለኮት ሁለተኛው አካል፣ የመለኮት ሶስተኛው አካል፣ የሰባት ዓመታት መከራ እና የመሳሰሉት። አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው አይልም። የትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አስራቱ የፓስተሩ ነው አይልም።
ስለዚህ ልክ አይሁዶች ከ2,000 ዓመታት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት ወቅት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ ሥርዓት እንዳበጁ ሁሉ እኛም ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት የራሳችንን ሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች አበጅተናል።
ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየመራ የሚያደርሰን ኮከብ ያስፈልገናል።
ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት የሚመልሰን ነብይ ያስፈልገናል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
በአሁኑ ሰዓት 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች እንዲሁም ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖ እውነትን የሚፈልግ ሰው መውጣት ከማይችልበት መንፈሳዊ አረንቋ ውስጥ ይገባል።
ማቴዎስ 2፡5 እነርሱም፦ … ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።
የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች መሲሁ በቤተልሔም እንደሚወለድ አውቀዋል፤ ነገር ግን መንፈሳዊ ዓይኖቻቸው ታውረው ስለነበረ በተወለደ ጊዜ መወለዱን አላወቁም።
በቤተልሔም እንደሚወለድ ካወቁ እነርሱ ራሳቸው ለምንድነው በቤተልሔም ሆነው ያልተጠባበቁት? መልሱ ግልጽ ነው። ብዙ ገንዘብ ማግኘት የሚችሉት በታላቋ ሐይማኖታዊ ማዕከላቸው በኢየሩሳሌም ከተማ ነበረ።
የዛሬ ቤተክርስቲያኖችም የብልጽግና ወንጌል በማስተማር እንደ መጠመዳቸው ትልቁ ትኩረታቸው ገንዘብ ሆኗል።
ቤተክርስቲያን ገንዘብ ወዳድ ሆናለች። ሙሽራይቱ ግን ነብይ ትፈልጋለች።
ማቴዎስ 2፡6 አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና
ተራ ከሆኑት ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ይመጣል።
ለአይሁዶች ቤተመቅደሱ እንደ ዛሬዎቹ ትልልቅ ቤተክርስቲያኖች ነበር። ነገር ግን ወደዚያ ታላቅ ቤተመቅደስ የሚጎርፉ ሕዝብ ስለተወለደው መሲህ አንዳችም አላወቁም።
ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ ሰብዓ ሰገል ከመምጣታቸው ከሁለት ዓመት በፊት በኢየሩሳሌም የነበሩ ታላላቅ የሐይማኖት መሪዎች በድጋሚ ታልፈው መወለዱ የተገለጠው ልብሳቸውን እንኳ ላላጠቡ እረኞች ነበር። እረኞቹ በምሽት የሚወለዱትን የበግ ግልገሎች ለማዋለድ ከቤት ውጭ ነበሩ። ልብሳቸውን ያላጠቡ እረኞች ብቻ ናቸው በሚሸት ግርግም ውስጥ ምንም ሳይሰማቸው እንደ ቤት መቀመጥ የሚችሉት። እየሮጡ ላብ በላብ ሆነው ጠረናቸው እየሸተተ ወደ ግርግሙ ደረሱ። በግርግም ውስጥ የሚገኘው ብቸኛው መጠቅለያ ጨርቅ በላብ የተነከረ የበሬውን አንገት ቀንበሩ እንዳይልጠው በበሬ ትከሻ ላይ ከቀንበሩ ስር የሚደረግ አሮጌ ጆንያ ብቻ ነበር።
ኢየሱስ በዚያ ላብ በነካው ጨርቅ ነበር የተጠቀለለው። ማንም የማያውቃቸው እረኞች ላብ በላብ በሆነው ክንዳቸው አቀፉት።
በአዳም ላይ የተነገረው እርግማን “በላብህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ” የሚል ነበር። ደግሞም እሾህም በእርግማኑ ውስጥ ተጠቅሷል።
ስለዚህ ኢየሱስ ከአዳም ሐጥያት ነጻ ሊያወጣን መጣ።
ኢየሱስ በሕይወቱ መጀመሪያ ላብ በነካው ጆንያ ተጠቀለለ፤ በሕወቱ መጨረሻ ደግሞ የእሾህ አክሊል በግምባሩ ላይ ተደፋ።
ይህንን የምናገኘው ከሉቃስ ወንጌል ነው።
ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ፍጹሙ ሰው አድርጎ ነው የሚገልጥልን።
ኢየሱስ በድህነት ተወለደ፤ ሰው በማያውቀው ሰፈር አደገ፤ ካደገም በኋላ የሐይማኖት መሪዎች ሁልጊዜ ያሳድዱት ነበር። እንደዚህም ሆኖ ግን የሐጥያተኞች ወዳጅና አጽናኝ እርሱ ነበረ፤ የበሽተኞች እና ሰው ያገለላቸው ሰዎች ወዳጅ፤ እንዲሁም በመስቀል ላይ በከባድ ስቃይ ሆኖ ሊሞት ለሚያጣጥረው ወንበዴም ወደ እርሱ በተመለከተ ጊዜ በመጨረሻው ሰዓት መጽናናት የመጣለት ከኢየሱስ ነበረ። በመስቀሉ ላይ ሆኖ ሌባው ያልጠበቀውን ወዳጅ አገኘ። ተስፋ የቆረጡ ሐጥያተኞች በሞሉበት ዓለም ውስጥ እንደ ኢየሱስ ያለ አጽናኝ ከየት ይገኛል።
ማቴዎስ ግን ስለ ኢየሱስ የተለየ መገለጥ ነው የሰጠን፤ እንደ ታላቅ ንጉስ አድርጎ ገልጦልናል።
ነገስታት በሚሸቱ ግርግሞች ውስጥ አይወለዱም። ስለዚህ ማቴዎስ ኢየሱስ የተወለደበትን ቦታ ትቶ መንፈስ ቅዱስ ሰብዓ ሰገልን እንዴት ለሁለት ዓመታት በፊታቸው እንደ ኮከብ እየተገለጠ እንደመራቸው ይጽፍልናል።
ማቴዎስ 2፡7 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥
ሔሮድስ ኮከቡ የኢየሱስን መወለድ እንደሚያመለክት አውቋል። ስለዚህ ለምን ያህል ጊዜ ኮከቡን ሲከተሉ እንደነበሩ በቁምነገር ጠየቀ። ኢየሱስን ለመግደል ፈለገ፤ ስለዚህ እርሱን አገኛለው ብሎ በእርሱ ዕድሜ የሆኑ ሕጻናትን በሙሉ ገደለ። ለዚሁ ብሎ ነው ኢየሱስ ዕድሜው ስንት እንደሆነ ማወቅ የፈለገው። ኢየሱስ በዚያ ጊዜ ዕድሜው ሁለት ከሆነ ሔሮድስ እርሱን ለመግደል የሁለት ዓመት እና ከዚያ በታች ዕድሜ የሆኑ ሕጻናትን ሁሉ መግደል አለበት። ይህም የአካባቢውን ሕጻናት ሁሉ ጨፍጭፎ እንዳይጨርስ ያደርገዋል።
ሔሮድስ ሕጻናትን ማስገደሉ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አውቋል። ስለዚህ የሚገድላቸው ሕጻናት በጣም እንዲበዙ አልፈለገም።
ማቴዎስ 2፡8 ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።
የዚህ የውሸት ንጉስ ውሸትነቱ ሲጋለጥ ተመልከቱ። ሔሮድስ ኢየሱስን ሊገድለው እንጂ ሊያመልከው አልፈለገም።
ሐጥያተኛው ሔሮድስ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችም ኢየሱስን ለማግኘት ሊረዱት እንደማይችሉ አውቋል። ምክንያቱም የትጋ እንደተወለደ በትክክል አያውቁም። ከዚያም በላይ የሐይማኖት መሪዎቹ መሲሁን የማግኘት ፍላጎትም አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም አንዳቸውም ተነስተው ወደ ቤተልሔም አልሄዱም። ልክ እንደዚሁ ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች እውነተኛይቱን ቤተክርስቲያን (ሙሽራይቱን) የሚመሩበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ማግኘት አይችሉም።
ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ነው ይላሉ።
ኢየሱስ ግን አባቱ ማለትም በእርሱ ውስጥ የሚኖረው ልዕለ ተፈጥሮአዊው መንፈስ ከእርሱ እንደሚበልጥ ነው የተናገረው ምክንያቱም ኢየሱስ ስጋ እና አጥንት ያለው ሰው ነበረ። መንፈሳችሁ አካላችሁን ይቆጣጠራል ስለዚህ ከአካላችሁ ይበልጣል። ዮሐንስ 14፡28 … ከእኔ አብ ይበልጣል።
ማቴዎስ 2፡9 እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው የሚመራው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
14 እርሱ ያከብረኛል፥
ኢየሩሳሌም ዋነኛዋ ማዕከል ናት።
በአይሁድ ሐይማኖት ማዕከል በኢየሩሳሌም ተቀምጠው ሳሉ ይመራቸው የነበረው ኮከብ ጠፋባቸው። ታላላቅ ቤተክርስቲያኖች እና የቤተክርስቲያን ቡድኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ሚስጥራት መረዳት የላቸውም።
አንድ ሰው የእነርሱ አባል ከሆነ በኋላ ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ደግሞም የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንደሚያስፈልጋትም አያውቅም።
ዘሩ መከር ሆኖ የሚታጨደው በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ሆኖ ሲገኝ ነው።
ሰብዓ ሰገል ከሐይማኖት ማዕከል ራቅ ባሉ ጊዜ ብቻ ነው ይመራቸው የነበረው ኮከብ በድጋሚ የተገለጠላቸው። ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ ልማዶቻቸው እውነትን ያጨልማሉ።
ሶስት አካላት ባሉት ሥላሴ አምላክ በማመን እግዚአብሔር ስም እንዳይኖረው አድርገዋል። ለሶስት ሰዎች አንድ ስም መስጠት አይቻልም። ሥላሴ የሆነው አምላክ ስም የለውም።
ይህ አሳዛኝ ጉዳይ ታዋቂ በሆነው ጥቅሳቸው ጀርባ ተደብቆ ይገኛል፡- በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም።
ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።
ማቴዎስ 2፡10 ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
ኮከብ መሪ ወይም መልእክተኛ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ኮከብ ነበረ፤ አይሁድን (የዚያ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ከነበሩት) ከቤተመቅደሳቸው እና ከምኩራባቸው አርቆ በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ ወደ ኢየሱስ መርቷቸዋል።
ለዚህ ነው ዮሐንስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎችን ከሚያስተምሩ ከቤተመቅደስ እና ከምኩራቦች ርቆ በምድረበዳ የሰበከው።
ኢየሱስ እጅግ በጣም የተቆጣበት ብቸኛው ጊዜ ገንዘብ ለዋጮችን እየገረፈ ከቤተመቅደስ ባስወጣ ጊዜ ነበር።
ኢየሱስ ወደ ከዘመናዊ ቤተክርስቲያኖቻችን ወደ አንዳቸው ቢመጣ ብላችሁ አስቡ።
ይህን ስናስብ ራዕይ ምዕራፍ ሶስት ከመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል ማለቱ ጥያቄ አይፈጥርብንም።
ስለዚህ ዛሬ ኮከብ ወይም ነብይ ያስፈልገናል - እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ውስጥ የተሰወረውን ኢሱስን እንድናገኘው የሚመራን መልእክተኛ ያስፈልገናል።
የዚያን ጊዜ ኢየሱስን በኤደን ገነት ውስጥ እንደተተከለ የሕይወት ዛፍ ማየት እንችላለን። ከዚያ በኋላ የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደነበረ እና ሔዋን ስለማርገዟ ለምን እንደተቀጣች መረዳት እና ማብራራት እንችላለን።
ሔዋን ጸንሳ ነበር።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ [በእንግሊዝኛው KJV መጽሐፍ ቅዱስ ጽንስሽን አበዛለው ይላል]
እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ጊዜ “ብዙ ተባዙ” ብቻ ነበር ያለው፤ በዚህ ክፍል ውስጥ ግን “እጅግ አበዛለው” ይላል።
ስለዚህ ምንድነው የተለወጠው?
ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥
ከውድቀት በፊት “ብዙ ተባዙ” የተባለው ከውድቀት በኋላ ለምን “እጅግ አበዛለው” እንደተባለ መረዳት አለብን።
ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበሩ የሐይማኖት መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እንዳልተረዱ ሁሉ የቤተክርስቲያን መሪዎችም መረዳት አይችሉም።
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ይህ ለንጉስ የሚገባ ስጦታ ነው።
ስጦታው የመጣለት በሚሸት ግርግም ውስጥ ባለበት ሰዓት ሳይሆን እቤት ውስጥ በሆነበት ሰዓት ነው።
ደግሞ ሰብዓ ሰገል በመጡ ሰዓት ኢየሱስ አራስ ሕጻን ሳይሆን ትንሽ ልጅ እንደነበረ ልብ በሉ።
ሲመጡ ማርያም ቤት ውስጥ ነበረች፤ ዮሴፍ ግን አልተጠቀሰም።
ዮሴፍ የኢየሱስ አባት አይደለም።
የኢየሱስ አባት መንፈስ ቅዱስ ነው።
በአንዴት ሴት ማሕጸን ውስጥ የሕይወትን ዘር የሚያኖር ሁሉ የሕጻኑ አባት ነው።
ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።
አስተውላችሁ እንደሆነ “እግዚአብሔር አብ” ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሶ አያውቅም።
“እግዚአብሔር ወልድ” እና “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ አልተጠቀሱም።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር በአንድ ትንሽ የሁለት ዓመት ልጅ ውስጥ ሊኖር ወደ ምድር መውረዱን አላወቁም።
እነዚህ ከሩቅ የመጡ ሰዎች ግን አስተዋዮች ጥበበኞች ስለነበሩ አውቀዋል።
እነርሱም ኢየሱስን አመለኩ።
ኢየሱስ በስጋ የእግዚአብሔር መገለጥ ባይሆን ኖሮ እርሱን ማምለካቸው ስሕተት ይሆን ነበር።
ከተሳሳቱ ደግሞ ጠቢባን አይደሉም።
ነገር ግን ሰዎቹ ጠቢባን ነበሩ። እነርሱ ግን ኢየሱስን ማምለካቸው ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል።
ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ መሆኑን ማመን አቅቷቸዋል።
ስለዚህ ኢየሱስ የመለኮት ሁለተኛው አካል በመሆኑ በመለኮት ውስጥ ነው እያሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን ይናገራሉ።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
“ሁለተኛው የመለኮት አካል” መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አይደለም።
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ለኢየሱስ ያቀረቡለት ስጦታ ስለ ኢየሱስ ምን እንደሚያስቡ ለራሱ ለኢየሱስ ይነግረዋል።
ወርቅ። ይህ እግዚአብሔርን የሚወክል ስጦታ ነው። እነርሱም ኢየሱስ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን አምነዋል።
እጣን። ይህ ከዛፍ ግንድ ላይ የሚገኝ ወፍራም ፈሳሽ ነው። እሳት ውስጥ ሲጨምሩት ደስ የሚል ሽታ ይሰጣል። የከብት ስጋ መስዋእት ሲቃጠል መጥፎ ሽታ ይፈጥራል። ስጋው በሚቃጠል ጊዜ እሳቱ ላይ እጣን ሲጨመርበት መጥፎውን ሽታ አስወግዶ ለመስዋእቱ መልካም መዓዛ ስለሚሰጠው ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል።
ከርቤ። ይህ ደግሞ ሙታን አካላቸው እንዳይበሰብስ ማድረጊዜ ቅመም ነው።
ስለዚህ ሰብዓ ሰገል ለኢየሱስ ምን እያሉ ነበር?
አንተ በሰው አካል ውስጥ የምትኖር የእግዚአብሔር መንፈስ ነህ። ስለዚህ አንተ እግዚአብሔር በስጋ ነህ።
የሐጥያት ስርየት የሚደረገው በሞት ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ ግን መሞት አይችልም።
ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው መስዋእት ለማቅረብ ነው።
እርሱ የመጣው ለመሞት ነው።
ሞት ማለት የመንፈስ ከስጋ መለየት ነው።
መንፈሱም ከስጋው ከተለየ በኋላ ሐጥያታችንን ወደ ሲኦል ይዞ በመውረድ ሰይጣን ላይ ማራገፍ ይችላል።
ይህም ሰው ከሐጥያት ነጻ መሆን የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ነው።
ማቴዎስ 2፡12 ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
ወደ ኢየሱስ በአንድ መንገድ ከመጡ በኋላ የሆነ ነገር ተፈጠረ። ስለዚህ ወደ ሃገራቸው በሌላ መንገድ ተመልሰው ሄዱ።
ንሰሃ የመግባታችሁ ማረጋገጫ ኢየሱስን ወደ ልባችሁ ውስጥ በተቀበላችሁ ጊዜ አካሄዳችሁና መንገዳችሁ መለወጡ እንዲሁም የተለወጠ ሕይወት መኖራችሁ ነው። ሰዎችም በሕይወታችሁ የመጣውን ለውጥ ማየት ይችላሉ።
በሕይወታችሁ ውስጥ ምንም እውነተኛ ለውጥ ከሌለ ኢየሱስን አላገኛችሁትም ማለት ነው። ስለዚህ ራሳችሁን እያታለላችሁ ናችሁ።
ኢየሱስን ከማግኘታችሁ በፊት የነበረው ሕይወታችሁ ምንም ይሁን ምን እርሱን ካገኛችሁ በኋላ ሕይወታችሁ የግድ ይለወጣል።
ማቴዎስ 2፡13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።
እግዚአብሔር ሕይወትን ሲያመጣ ሰይጣን ሞትን በማምጣት ምላሽ ይሰጣል።
ማቴዎስ 2፡14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና … ወደ ግብፅ ሄደ፥
ሌላም የሌሊት ጉዞ። በጨለማ መንገድ መሄድ አደጋ አለው።
ማቴዎስ 2፡15 ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።
ይህ የመጀመሪያውን ፍልሰት ያስታውሰናል።
ሙሴ አይሁዶችን ከግብጽ አወጣቸው። ነገር ግን ያለ ዋጋ አይደለም። ፈርኦን የአይሁዶችን ወንዶች ልጆች ሁሉ ሊገድል ሞከረ።
ሁለተኛውን ፍልሰት የመራው ኢየሱስ ነው።
ቤተክርስቲያን ከአይሁዶች ማሕበር እየወጣች ነበርየዛኔም ሔሮድስ ሕጻናትን በገደለ ጊዜ ሞት በሕጻናት ላይ መጣ።
ዛሬ ደግሞ እኛ በሶስተኛው ፍልሰት ውስጥ ነን።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችዋ ሙሽራ (ልባሞቹ ቆነጃጅት) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ትወጣለች። አሁንም በድጋሚ ሕጻናት እየተገደሉ ናቸው። በዓለም ዙርያ በዓመት ከ30 እስከ 40 ሚሊዮን ሕጻናት በውርጃ ይገደላሉ።
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ በልባችን ውስጥ ሆኖ ከቤተክርስቲያኖች እንድንወጣ እየተናገረን ነው።
ማቴዎስ 2፡16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ለምንድነው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያም የሚያንሱትን ያስገደለው?
ምክንያቱም ሰብዓ ሰገል ኮከቡን እየተከተሉ በመንገድ ያሳለፉት ጊዜ ሁለት ዓመት ያህል ስለነበረ ነው።
ኮከቡ ማታ ማታ ብቻ ነበር ብቅ የሚለው። ስለዚህ በሌሊት ቀስ ብለው መሄድ ነበረባቸው። መንገዳቸው በጣም ረጅም እና በአደጋ የተሞላ ነበረ። ክርስትና ለልፍስፍሶች አይደለም።
ኢየሱስን ማግኘት እና መከተል ከፈለጋችሁ መንገዱ ከባድ ነው።
ማቴዎስ 2፡17 ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ … የተባለው ተፈጸመ።
ማቴዎስ 2፡18 … ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና… ።
ራማ የሚለው ቃል ትርጉሙ ከፍታ ነው።
“ከፍታ” ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ማለት ነው። ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ዋጋ ያስከፍላል። እርሱም እምባ እና ሐዘን ነው።
ወደ እግዚአብሔር በቀረባችሁ ቁጥር የሰይጣን ኢላማ ውስጥ ትገባላችሁ።
አይሁዳውያን ሕጻናት ተገደሉ።
እናቶች ሊጽናኑ አልቻሉም።
ራሔል ማለት የበግ ግልገል የምትወልድ “እናት በግ” ማለት ነው።
ኢየሱስ ሐጥያት የሌለበት ንጹሁ የእግዚአብሔር በፍ ለመሞት ነው የመጣው። ለዚህ ዓይነቱ ጊዜ ነው የተወለደው። የሰብዓ ሰገል ስጦታ ይህንን ግልጽ ያደርጋል።
ሌሎቹ ሕጻናት ንጹሐን የሚሆኑት ሕጻናት ሳሉ ብቻ ነው። ስለዚህ እነርሱም ንጹሐን ሕጻናት እያሉ መሞት ነበረባቸው። የሞቱበት ቀን ለዚያ ቀን ነው የተወለዱት።
በሶስተኛው ፍልሰት ወቅት የመጨረሻው ዘመን ሕጻናት ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት መመለስ አለባቸው።
በውርጃ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት ሳይወለዱ ይሞታሉ።
እግዚአብሔር የጥንቷን ቤተክርስቲያን ሕይወት መልሶ ለማምጣት መስራት ሲጀምር ሰይጣን ደግሞ ለመግደል ይነሳል።
ነገር ግን ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ነው የሚከናወነው።
ማቴዎስ 2፡19 ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦
ሔሮድስ ኢየሱስን ለመግደል በብርቱ ፈልጎ ነገር ግን መግደል አልቻለም። በስተመጨረሻ ስጋው በስብሶ በትል ተበልቶ ቀፋፊ አሟሟት ሞተ። ስለዚህ እውነትን ለማጥፋት ያደረጋቸው ሙከራዎች በሙሉ አልተሳኩም።
በዓለም ላይ ያሉ አረቦች በሙሉ ቢተባበሩ እንኳ አይሁዶችን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባትና በታላቁ መከራ ጊዜ በዚያ ሆነው መሲሃቸውን ከማግኘት ሊያግዷቸው አይችሉም።
የዓለም ክስተቶች አደገኛ ቢሆኑና ሁከት ቢበዛባቸውም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገር ሁሉ አንድ በአንድ ይፈጸማል።
ማቴዎስ 2፡20 የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
21 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።
22 በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤
ይሁዳ ውስጥ የተቀመጠ ክፉ ንጉስ ዮሴፍ ወደ ናዝሬት እንዴሄድ ምክንያት ሆነ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሕዝቡን እርሱ ወደፈለገበት ቦታ እንዲሄዱ ለመምራት መጥፎ ሰዎችን እንኳ ሊጠቀም ይችላል።
መልካምም ክፉውም ሁለቱም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር ናቸው።
ነገር ግን መልካሙ ብቻ ነው ሽልማት የሚያገኘው።
ክርስቲያኖች ከማያምኑ ሰዎች አይሻሉም። ክርስቲያኖች የተሻለ ተስፋ ያላቸው የእግዚአብሔርን ጸጋ ስለሚያውቁ ነው።
ሐጥያተኞችም አማኞችን ለመቅረጽና ለማስተካከል የተሰጣቸውን ሚና መጫወት አለባቸው።
እግዚአብሔር ጸጋውን ስላሳየህ አመስግነው፤ ለሚያጉላሉህና ለሚያሳድዱህ ሐጥያተኞች ግን እዘንላቸው። የተሰጣቸውን ድርሻ እየተወጡ ነው፤ መጨረሻቸው ግን አስጨናቂ ነው የሚሆነው።
ማቴዎስ 2፡23 በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።
ጊዜው በጣም አደገኛ ነገር ግን በትንቢት የተነገረለት ዘመን መቋጫ ነበረ፤ ተቃውሞ እና አደጋዎች ቢበዙም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትንቢት የተነገረ ነገር ሁሉ ይፈጸማል።