ማቴዎስ ምዕራፍ 01. ክፍል 2. በስሞች ውስጥ የተገለጡ አስፈላጊ ትምሕርቶች



በስም ዝርዝሮች ውስጥ የተገለጠ ትምሕርት አለ። እግዚአብሔር በነገስታት የዘር ሃረግ ከሕይወት መጽሐፍ የተሰረዙ ውስጥ ክፉ ሰዎችንም ተጠቅሟል።

First published on the 4th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ያዕቆብ 12 ልጆች ነበሩት።

ማቴዎስ ግን የዘር ሃረጉን ሲቆጥር ከይሁዳ በመነሳት ነው ከዚያ ወዲያ የመጡትን ነገሥታት ታሪክ እስከ ኢየሱስ ድረስ የሚያሳየን።

በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ በመክፈቻው ላይ የምናገኘው ትምሕርት ይህ ነው።

ኢየሱስን ወደ ንግሥና የሚያመጡ ክስተቶች ብቻ ናቸው ዋጋ ያላቸው።

ይህ የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነበትም ምክንያት ይህ ነው፤ ምክንያቱም ከመክፈቻው ጀምሮ ኢየሱስ ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ደቀመዛሙርቱ በሙሉ አይሁዳውያን ነበሩ፤ እግዚአብሔር ግን ፊቱን ወደፊት ወደምትመሰረተው የአሕዛብ ቤተክርስቲያን እንደሚያዞር እያሰበ ነበር። ከዚህም የተነሳ አዲስ ኪዳን በዕብራይስጥ ሳይሆን በግሪክ ቋንቋ ነበር የተጻፈው።

 

 

ማቴዎስ 1፡3 ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡4 ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡5 ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡6 እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤

ነብያት አይሁዶችን እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ወዳዘጋጀላቸው እቅድ በሚመሩበት ዘመን ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ታላቅ ስራውን እየሰራ ነበር።

የመጀመሪያው ባለ አራት ማዕዘኑ የአይሁድ የመሰረት ድንጋይ አብራሐም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሴፍ መሆን ነበረባቸው።

ይህም እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለግለ ሰቦች ያዘጋጀውን እቅድ የሚወክል ነው፡- መጽደቅ፣ መቀደስ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ እና ልጁ በአባት እቅድ ውስጥ መግባቱ።

ዮሴፍ ግን የራሔል የበኩር ልጅ እንደመሆኑ እድል ፈንታው ድርብ ውርስ ነበረ።

ስለዚህ ሁለቱ ልጆቹ ኤፍሬም እና ምናሴ እያንዳንዳቸው በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ርስት ተቀብለዋል።

ኤፍሬም ግን ወደ ጣኦታት በዞረ ጊዜ እድል ፈንታውን አጥቷል።

ሆሴዕ 4፡17 ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ተወው።

ሌዊ ለክሕነት ተመረጠ። ስለዚህ ሌዊ በኤፍሬም ፈንታ ሊመረጥ ይገባው ነበር።

ነገር ግን ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ የክሕነት ልብሱን በመቀደዱ በሰራው ስሕተት የተነሳ ክሕነት ከሌዊ ቤት ተወሰደ።

ዘሌዋውያን 21፡10 በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ፤ ልብሱንም አይቅደድ።

ሊቀ ካሕናቱ ልብሱን መቅደድ አልተፈቀደለትም።

ቀያፋ ግን ኢየሱስን ጥያቄ እየጠየቀ በነበረበት ሰዓት ልብሱን ቀደደ።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።

ስለዚህ እግዚአብሔር የካሕናት ቤት የሆነውን የሌዊን ቤተሰብ አልመረጠም፤ የሌዊ ክሕነትም በአሳዛኝ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

እግዚአብሔር የይሁዳን ነገድ መረጠ።

ከይሁዳ ነገድ ውስጥ አንዳንድ ታላላቅ ሰዎች ተነስተዋል፤ እግዚአብሔር ግን ስለ ታላቅነታቸው አይደለም የመረጣቸው።

ከይሁዳ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ክፉ ሰዎች ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን የይሁዳን ነገድ መረጠ።

ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው የሰዎቹ መልካምነት አይደለም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ደም አማካኝነት የዳነው የመጀመሪያው ሰው አጠገቡ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የነበረ ወንጀለኛ ነው።

ይህ ወንጀለኛ ግን አስደናቂ መገለጥ አግኝቷል።

ይህ ሰው አጠገቡ ብዙ ተገርፎ ቆስሎ የተሰቀለው ሰው መሲሁ መሆኑን አውቋል። ማለትም እግዚአብሔር በሥጋ።

ይህ ወንጀለኛ ብዙ ተሰቃይቶ ተሰቅሎ ሊሞት እያጣጣረ ባለበት ሰዓት እውነትን መረዳት መቻሉ በጣም ያስደንቃል።

 

 

በጣኦት አምልኮ የተነሳ እግዚአብሔር ኤፍሬምን ለመሲሁ መምጫ እንዳይሆኑ ከለከላቸው። ከዚህም የተነሳ የዮሴፍ ተመራጭነት ቀረ።

መዝሙር 78፡67 የዮሴፍንም ድንኳን ተዋት፥ የኤፍሬምንም ወገን አልመረጠውም፤

ዮሴፍ አስደናቂ ሕይወት ነበር የኖረው፤ የልጅ ልጆቹ ግን ወደ ጣኦት አምልኮ ውስጥ ገቡ።

ስለዚህ ከታላቅ ሰው በተወለዱ ልጆች ብዙ መገረም የለብንም። ከታላቅ ሰው ዘር ቢወለዱም እንኳ የማይረቡ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ።

ከአባት ወደ ልጅ የሚተላፉ አገልግሎቶች ዓላማቸው ገንዘቡ ከቤተሰብ እንዳይወጣ ለማድረግ እንጂ ለዘመናችን የሚሆነውን የእግዚአብሔርን እውነት ለመረዳት አይደለም።

ኤፍሬም የበኩር ልጅ ሳይሆን የብኩርና ክብርን ማግኘቱ ከእርሱ የተወለዱ የልጅ ልጆቹን ጥሩ ሰዎች ሊያደርጋቸው አልቻለም።

ስኬት የራሱ የሆነ አደጋ አለው፤ ምክንያቱም ሊያስታብየንና እንዳናመሰግን ሊያደርገን ይችላል።

አንዲት ቤተክርስቲያን ስሕተትን እውነት አድርጋ ስትቀበል የገንዘብ ወዳጅ ትሆናለች፤ በዚህም ምክንያት እውነትን በመረዳት አቅም ሳይሆን በግብዝነት ትሞላለች።

ስለዚህ ዮሴፍ በአስደናቂ አገልግሎት ውስጥ ቢያልፍም እንኳ መሲሁ የሚወለድበት የዘር ሃረግ ሆኖ ለመመረጥ አልበቃም።

እግዚአብሔር በመረጠው ሰው ሕይወት ውስጥ አስደናቂ አገልግሎት ከተከናወነ በኋላ አገልግሎቱ በቤተሰቡ ውስጥ ክብሩን ጠብቆ እንደማይቀጥል ብዙ ጊዜ አይተናል።

ኤሊ ታላቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነበረ። ልጆቹ ግን እንደ እርሱ ታማኝ አገልጋዮች አልነበሩም።

1ኛ ሳሙኤል 2፡12 የዔሊም ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁም ነበር።

ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ነገድ ለአንድ ዓላማ ብቻ መረጠ።መሲሁ የሚወለደው ከይሁዳ ነገድ ነው።

መዝሙር 78፡68 የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ።

እግዚአብሔር ሊመርጠን የሚችለው የግል ፈቃዳችንን ለኢየሱስ አሳልፈን ስንሰጥ እና ሕይወታችንን እርሱ እንዲቆጣጠር ስንፈቅድለት ነው።

እግዚአብሔር የሚመርጠን ቃሉን ሙሉ በሙሉ ካመንን ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር እቅድ በጭራሽ ባላሰብነው መንገድ ሊመራን ይችላል።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም እንከን የሌለበት እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማመን አለብን።

መጽሐፍ ቅዱስን ማመን አለብን እንጂ በፍጹም የሚናገረውን ቃል ቸል ማለት፤ መለወጥ፤ ወይም መቃረን የለብንም።

ማቴዎስ ምዕራፍ 1 ውስጥ ከተጻፉት የስም ዝርዝሮች ምን ልንማር እንችላለን?

የአብራሐም የወንድም ልጅ የሆነው ሎጥ ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ከአንዷ ሞአብ የተባለ ልጅ ወለደ።

ስለዚህ የሎጥ ልጅ ሞአብ ከይስሐቅ ጋር በተመሳሳይ ዘመን የኖረ ትውልድ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ወደ አይሁድ ማሕበር ተመልሶ መግባት የሚችለው ከ10ኛ ትውልድ በኋላ ነው።

ዘዳግም 23፡2 ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

3 አሞናዊና ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ለዘላለም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

ለዘላለም ማለት እስኪጠፉ ማለት ነው።

ከጋብቻ ውጭ የወመለድ ሐጥያት የሚወገደው ከ10ኛ ትውልድ በኋላ ነው።

እግዚአብሔር ይህን ያህል ነው ከጋብቻ ውጭ መውለድን የሚጠላው።

በዝሙትና በመዳራት ላለመኖር መጠንቀቅ አለብን፤ እግዚአብሔር በጣም ይጠላዋል።

ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብራሐም የ100 ዓመት ሰው ነበረ፤ ይህም ሰዶም ከጠፋች ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።

የይስሐቅ መወለድ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃል ኪዳን ስለገባ ነው።

ይስሐቅ አብራሐም በሥጋ የወለደው ዘሩ ነው።

ኢየሱስ ደግሞ የአብራሐም መንፈሳዊ ዘሩ ነው።

ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤

ከዚህ በታች ያለው ካርታ የተስፋይቱን ምድር እስከ ኤፍራጠስ ወንዝ ድረስ ያሳያል። ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ በሚመጣው በሺህ ዓመት የሰላም መንግሥት ዘመን አይሁዶች ይህንን ምድር ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩታል

 

 

አይሁዶች ዛሬ ከተስፋይቱ ምድር ከፊሉን ብቻ ነው የሚኖሩበት።

ነገር ግን ብዙዎቹ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የሚናገሩት ስለ ወደፊቱ ነው።

የአይሁድ ታሪክ ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ ያሉትን 2,300 የአይሁድ ዓመታት (ወይም እያንዳንዱ ዓመት 360 ቀን) ይሸፍናል፤ ይህም መንፈሳዊ ዘር የሆነው የኢየሱስ ሞት ድረስ የሚቆጠረው የፍጥረታዊው ዘር ዘመን ነው።

ቤተመቅደሱ በቀራንዮ ነጽቷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ታጥቧል።

ዳንኤል 8፡14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።

በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ሊወክል ይችላል።

ስለዚህ የአይሁድ ታሪክ ዋነኛ ክፍል ከይስሐቅ ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ድረስ ነው።

ሎጥ የአብራሐም የወንድሙ ልጅ ነው፤ ሞአብ ደግሞ ከሰዶም መጥፋት አንድ ዓመት በኋላ ከጋብቻ ውጭ የተወለደ ልጅ ነው።

ስለዚህ ይስሐቅ እና ሞአብ እድሜያቸው ተቀራራቢ ነበር።

ይስሐቅ።                    ሞአብ።

ያዕቆብ

ይሁዳ

ፋሬስ

ኤስሮም

አራም

አሚናዳብ

ነዓሶን

ሳልሞን                       ረአብ

ቦኤዝ                          ሩት።

 

 

ይስሐቅን የመጀመሪያ ትውልድ ብለን ብንቆጥር ቦኤዝ 10ኛ ትውልድ ነው። ሩት ደግሞ ከሞአብ 10ኛ ትውልድ ናት።

ስለዚህ ሩት ከጋብቻ ውጭ በመወለድ ከሚመጣው ነቀፋ ነጻ ናት።

ከዚህም የተነሳ ሩት ወደ አይሁድ ማሕበር መቀላቀል ትችላለች።

እግዚአብሔርም ያልተለመደ ነገር አደረገ።

በትውልዷ አይሁድ ያልሆነች አንዲትን ጻድቅ ሴት ወደ መሲሁ የትውልድ ሃረግ ውስጥ እንድትቀላቀል አደረገ።

ከዚህ ጠንከር ያለ ትምሕርት እንማራለን። እግዚአብሔር ለየትኛውም ሕዝብ ባለእዳ አይደለም። እርሱ ከፈለገ እናንተ ከማትወዱት ቡድን ውስጥ አንድን ሰው መምረጥ ይችላል።

የቦኤዝ አባት ሳልሞን ነበረ።

ሳልሞን ጋለሞታ የነበረችዋን የኢያሪኮ ሴት ረአብን አግብቶ ነበር። የሚገርመው ነገር ረአብም አይሁዳዊ አልነበረችም።

በዚህ መንገድ እግዚአብሔር አይሁዳዊ ካልሆኑ ሰዎችም ጋር ለመስራት መፍቀዱን እያሳየ ነበር። ሰዎቹ በሕይወታቸው መጀመሪያ ላይ ክፉ መንገድ ውስጥ የነበሩ ቢሆኑም እንኳ።

ነገር ግን እግዚአብሔር ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ ልጆችን በተመለከተ የነበረውን አቋም ለውጦ አያውቅም።

ከጋብቻ ውጭ የተወለደ ሰው እስከ ዘጠኝ ትውልድ ድረስ ወደ አይሁዶች እምነት ውስጥ መግባት አይፈቀድለትም። 10ኛ ትውልድ ላይ እስኪደርሱ ድረስ

 

 

ማቴዎስ የዘር ሐረጉን ከይሁዳ ይጀምረዋል፤ በዚህም መንገድ ወደፊት እስከ ኢየሱስ ድረስ ያለውን የነገሥታት ታሪክ ለመከታተል ያመቸዋል።

ቁም ነገሩ በዚህ ዝርዝር ውስጥ የትኞቹ ሰዎች አሉበት የሚለው ጥያቄ አይደለም።

ቁም ነገሩ ይህ የዘር ሐረግ የት ነው የሚያበቃው የሚለው ጥያቄ ነው፤ የሚያበቃውም በኢየሱስ ነው።

እምነታችን የሚመሰረተው በኢየሱስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ እንጂ በሆነ ቤተክርስቲያን መሪ አይደለም።

ዮሐንስ 12፡32 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።

ኢየሱስ ነው ከፍ ማለት ያለበት እንጁ አንድ ታላቅ ሰው አይደለም።

የመንፈሳዊ ስኬት ሚስጥር ወደ ክርስቶስ እርሱም እንደተሰቀለ መመልከት ነው።

የዚያን ጊዜ ማንም ሰው ከኢየሱስ ጋር መወዳደር እንደማይችል እናስተውላለን።

የይሁዳ የዘር ሐረግ በታላቅ ሰው ነው የሚጀምረው።

ነገር ግን ኢየሱስን አሳልፎ በሰጠው በአንድ ይሁዳ በሚባለው ሰው የተነሳ የዚህ ስም ታላቅነት ሊወድቅ ችሏል።

ዛሬ ይሁዳ ተብሎ መጠራት የሚፈልግ ሰው የለም።

የእግዚአብሔርን ቃል በመካድ ወይም በመቃረን እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን አልቀበልም በማለት አሳልፋችሁ ብትሰጠት ስማችህ ከእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ ይሰረዛል።

ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር ሐዋርያት እንኳ ቢሆኑ የገንዘብ ፍቅር የሚነዳቸው ከሆነ ታላቅ ጥፋትን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ነው።

የቤተክርስቲያን መሪ ወይም እንደ ይሁዳ ሐዋርያ መሆን አንድን ሰው ከመንፈሳዊ ስሕተተቶች ሊያድነው አይችልም።

አብራሐም ከመጀመሪያው እውነተኛ ንጉሥ ከመልከ ጼዴቅ ጋር ፊት ለፊት ተገናኘ።

እርሱ ለራሱ የሚሆን አካል ከአንድ እጅ አፈር የፈጠረ እግዚአብሔር ነበረ። እግዚአብሔር አብራሐምን አናግሮ ከዚያ በኋላ ወደ ሰማይ ሲመለስ ለብሶት የነበረውን ሥጋ ወደ አፈርነት መለሰው።

ጳውሎስ መልከ ጼዴቅን እንዴት እንደሚገልጠው ተመልከቱ።

ዕብራውያን 7፡3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።

መልከ ጼዴቅ አልተወለደም፤ ደግሞም አልሞተም።

ስለዚህ እግዚአብሔር እራሱ ነበረ፤ እርሱም ከአፈር በተሰራ አካል ውስጥ ሆኖ ምድርን ለጥቂት ጊዜ ጎብኝቷል።

ይህም ሥጋ ጊዜያዊ መሆኑን ያመለክታል። የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ዋናው ለዘላለም የሚኖረው።

ስለዚህ ማቴዎስ ክርስቶስን እንደ ንጉሥ፣ እንደ ይሁዳ ነገድ አንበሳ ሊያስተዋውቅ ከፈለገ ማቴዎስ የዘር ቆጠራውን የሚጀምረው እውነተኛውን ንጉሥ እግዚአብሔርን በሥጋ አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገናኘው ከአብራሐም ነው የሚጀምረው።

እግዚአብሔር ለራሱ የትልቅ ሰው አካል ፈጠረ።

ከዚያም ያ አካል እግዚአብሔር ተጠቅሞበት ሲያበቃ ወደ አፈርነት ተመለሰ።

ልክ እኛ ልብስ አንስተን እንደምንለብሰው እግዚአብሔርም በፈለገ ጊዜ ለራሱ አካል መፍጠር ይችላል።

ከዚያ ቀጥሎ እግዚአብሔር በኢየሱስ አካል ውስጥ እንደ ሕጻን ሆኖ ተወልዶ አድጎ ትልቅ ሰው ለመሆን አሰበ።

ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ … ስሙም … ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ …

ይህም እግዚአብሔር የእኛን ዓይነት ኑሮ በመኖር ዘመዳችን በመሆን ሊቤዠን ያሰበበት መንገድ ነው።

እንደዚህ ከተገለጠ ብቻ ነው ሐጥያት ያልነካው ሕይወቱን ስለ ሐጥያታችን ሊሰዋ የሚችለው።

ማቴዎስ በጽሑፉ እንዳደረገው ከአብራሐም ብንጀምር፡-

 

 

አብራሐም

ይስሐቅ

ያዕቆብ

ይሁዳ

ፋሬስ

ኤስሮም

አራም

አሚናዳብ

ነዓሶን

ሳልሞን

ቦኤዝ

ኦቤድ

እሰይ

ዳዊት

ዳዊት ከአብራሐም 14ኛው ትውልድ ነው።

ይህም ያዕቆብ ለሊያ ብሎ 7 ዓመት፣ ለራሔል ደግሞ 7 ዓመት እንደሰራ ያስታውሰናል።

ሊያ እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር ያሳለፋቸውን ሰባት ዘመናት ትወክላለች።

አብራሐም። ዮሴፍ። ሙሴ። ኤልያስ። እዝራ። ነኅምያ። መጥምቁ ዮሐንስ። እነዚህ የአይሁድ ታሪክ ውስጥ ያለፉ ሰባት ታላላቅ ሰዎች ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ቁጥራቸው ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር ይገጣጠማል።

ኤፌሶን። አብራሐም የቀደመች ፍቅሩ የሆነችዋን ሳራን ሶስት ጊዜ ትቷት ነበር። በዚህ ሂደትም ውስጥ እስማኤልን እና አረቦችን ወለደ፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁዶች ጎን ውስጥ ዋነኛ ውጋት ሆነው ቀሩ። ድሮ የሰራናቸው ስሕተቶች እየመጡ ይቆነጥጡናል።

ራዕይ 2፡4 ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።

ኒቆላውያን። ይህ አሰራር አንድ ሰውን ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ በማድረግ በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል እንዲቆም፤ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን መሾም ነው። ሰው መሪ ሲሆን ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን ወጥቶ በደጅ ይቆማል።

ሰምርኔስ። ዮሴፍ እስር ቤት ገባ።

ራዕይ 2፡10 “እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥”

ጴርጋሞን። በለዓም፣ የሙሴ ጠላት በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ተጠቅሷል።

ራዕይ 2፡14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።

ትያጥሮን። ኤልዛቤል በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በጨለማው ዘመን ውስጥ ተጠቅሳለች።

ራዕይ 2፡20 ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤

ሰርዴስ። ዕዝራ መዝገቡን ወደ ቤተመቅደሱ መለሰው። ይህም ሉተር በእምነት መዳን የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ማምጣቱን ይወክላል።

ፊላደልፊያ:- ነኅምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አድሶ ከተማይቱን ብርቱ አደረጋት። ፊላደልፊያ የወንድማማች መዋደድ ብርታት ነው፤ እርሱም ከቅድስና እና ከወንጌል አገልግሎት ጋር ተጣምሮ ወርቃማውን የሚሽነሪ ወይም ወንጌልን ለዓለም የማዳረስ ዘመን አስጀመረ።

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ወቅት መጥምቁ ዮሐንስ የሐይማኖት መሪዎችን እባቦች ብሎ አወገዛቸው።

ማቴዎስ 3፡7 ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

ነገሮች አሁንም አልተለወጡም። የመጨረሻዋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዕውር እና ለብ ያለች፤ ጌታ የሚተፋት ቤተክርስቲያን ተብላ መገለጧ አይገርምም (እነዚህ ቤተክርስቲያኖች የራሳቸውን ሃሳብ ነው የሚያምኑት)።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተገፍቶ ወጥቷል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ቤተክርስቲያኖችም አንፈልግህም ብለውታል።

ኢየሱስም ጥሪውን የሚያቀርበው ለግለሰቦች እንጂ ለቡድኖች አይደለም።

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

የያዕቆብ ሚስቶች ወደ ነበሩት ወደ ሊያ እና ወደ ራሔል እንመለስ።

ራሔል ሰባቱን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት ትወክላለች።

ስለዚህ 14 ቁጥር የብሉይ ኪዳኑን የአይሁድ ሕዝብ እንዲሁም የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን የሚወክል ቁጥር ነው።

14 ቁጥር ኢየሱስ የአይሁድም የአሕዛብ ቤተክርስቲያንም ንጉስ መሆኑን ያመለክታል።

አይሁዶች የዕብራይስጥ ፊደሎችን እንደ ቁጥርም ጭምር አድርገው ይጠቀሙባቸዋል።

D =4 and V= 6

የዕብራይስጥ ፊደሎች አናባቢዎች አልነበሩዋቸውም።

ስለዚህ ዳዊት DAVID ብለው ለመጻፍ DVD ብለው ነበር የሚጽፉት።

ስለዚህ DVD = 4 + 6 + 4 = 14

ዳዊት ከአብራሐም ጀምሮ 14ኛው ትውልድ ሆኖ፤ ደግሞም 14 ቁጥር 7ቱን የአይሁድ ዘመናት እና 7ቱን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክል እንደመሆኑ ማቴዎስ የአይሁድ ነገሥታትን 14 ነገስታት ባሉዋቸው ሁለት ቡድኖች ከፍሎ ነው የጻፋቸው።

ይህም ማለት ትውልዶችን በ14 ከፋፍሎ ማስቀመጡ ዋናውን መልእክት ማለትም አይሁድ እና የአሕዛብ አማኞችን ለመግለጽ ብሎ ነው።

ማቴዎስ ከዳዊት ይጀምርና ንጉስ ኢኮንያንን ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሄደው 14ኛ ንጉስ አድርጎ ይመዘግባል።

ማቴዎስ 1፡11 አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።

 

 

ማቴዎስ የመዘገባቸው የነገሥታት ስም ዝርዝር ኢዮራም ላይ እስኪደርስ ድረስ በመጽሐፈ ነገሥት እና በመጽሐፈ ዜና ውስጥ የተቀመጠውን ዝርዝር ነው የሚከተለው።

ማቴዎስ 1፡6 እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡7 ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡8 አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤

ይህ የስም ዝርዝር ኢዮራም፣ ከዚያ አካዝያስ፣ ኢዮአስ፣ አሜስያስ፣ ከዚያም ኦዝያን መሆን ነበረበት።

ለእኛ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን አካዝያስ፣ ኢዮአስ፣ እና አሜስያስ ከስም ዝርዝሩ ውስጥ ተወግደዋል።

ከእነርሱ ምን መማር እንችላለን?

 

 

በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ዜና ውስጥ የአይሁድ ነገሥታትን ስም ዝርዝር ስንመለከት በዳዊት እና በኢኮንያን መካከል ማቴዎስ ስድስት ነገሥታትን ሳይጠቅስ አልፏል።

ይህ የሚያስፈራ ሃሳብ ነው። ስድስት ሰዎች ጭራሽም ኖረው የማያውቁ ይመስል የማቴዎስ መጽሐፍ ውስጥ ስማቸው ተሰርዟል።

ይህ እግዚአብሔር ለአምስተኛዋ ቤተክርስቲያን ለሰርዴስ (ያመለጡ ሰዎች) የሰጣት ማስጠንቀቂያ ነው፤ የዚህች ቤተክርስቲያን ስም ተሃድሶን ያመለክታል።

ራዕይ 3፡4 ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፥ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።

5 ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።

ሰዎች እግዚአብሔርን እንከተላለን እያሉ ነገር ግን ከቃሉ ሲያፈነግጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያለውን ሕብረት ያቋርጣል። ስማቸው ይሰረዛል። ለእነዚህ ዓይነት ሰዎች በሰማይ ስፍራ አይገኝላቸውም።

ማቴዎስ 1፡8 … ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤

3 ሰዎች ጎድለዋል፡- አካዝያስ፣ ኢዮአስ፣ እና አሜስያስ።

ኢዮራም የጎቶሊያ ባል ነበረ፤ እርሷም የአካብ እና የኤልዛቤል ልጅ ነበረች።

ኢዮራም ክፉ ነገር አደረገ። ይህም የሰራው ክፉ ነገር በእሥራኤል ውስጥ ከሁሉ በላይ ክፉ ንጉሥ እና ክፉ ንግስት የነበሩትን የአካብ እና የኤልዛቤል ልጅ የሆነችዋን አታሊያን ማግባቱ ነው።

2ኛ ነገሥት 8፡18 የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።

1ኛ ነገሥት 20፡25 በእግዚአብሔር ፊት ክፋት ለመሥራት ራሱን እንደ ሸጠ፥ ሚስቱም ኤልዛቤል እንደ ነዳችው፥ እንደ አክዓብ ያለ ሰው አልነበረም።

ሰዎች በቤተክርስቲያኖቻቸው አነሳሽነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን ያምናሉ።

በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ቤተክርስቲያኖች እንደ ፈለጉ እምነታቸውን በራሳቸው መንገድ ሲተረጉሙ እና ሲፈጥሩ ምንም አለመፍራታቸው ነው።

ምንም ሳያፍሩ የራሳቸውን ሃሳብ እየፈጠሩ ይከተላሉ። የሰው ሞኝነት እና በቀላሉ ለመታለል የተጋለጠ መሆኑ በጣም ይገርመናል። ሰዎች ራሳቸውን በማታለል ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሊቀሩ ይችላሉ።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡ ኢየሱስ ይገደልልን ብለው እንዲጠይቁ አነሳሱዋቸው።

የኤልዛቤል ሴት ልጅ ምሕረት የሌላት ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ ናት።

ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

“የጋለሞታዎች እናት”። እናት ከሆነችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፕሮቴስታንት ልጆቿ ተወለዱ፤ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምሕርቶችን ተከተሉ፤ ለምሳሌ፡- ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ እሁድ የሰንበት ቀን ነው፣ የፋሲካ የጥንቸል እንቁላሎች፣ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው፤ እንዲሁም የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ መናገር አለመቻል።

ስለዚህ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ውስጥ በአባልነት መቀላቀል ወይም መጋባት ማለት አንድ ሰው ከሲኦል ቢድንም እንኳ አስፈሪ በሆነው ታላቁ መከራ ውስጥ ሊሞት እየተነዳ መሆኑን ያሳያል። በሴት የተመሰሉት ቤተክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን የመረዳት ችሎታችንን ይገድሉብናል።

የዳኑ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ወደ እራት የጋበዛቸውን ሃብታም ሰው ምሳሌ አስቡ። ኢየሱስ የዳኑ ሰዎችን ብቻ ነው ወደ ሰርጉ እራት የሚጋብዛቸው።

ሉቃስ 14፡16 ተጋብዘው የነበሩ የዳኑ ሰዎች ሁሉ ግብዣውን አልተቀበሉም ምክንያቱም ማናቸውም እርሱ የጠየቃቸውን ማድረግ አልፈለጉም። ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ እንድንከተል ይፈልጋል፤ ምክንያቱም ወደ ሰርጉ የእራት ግብዣ የምንሄድበት መንገድ ጠባቡ የመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ ነው። ነገር ግን የዳኑ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ አማራጭ መንገድ ነበራቸው፤ አማራጮቻቸውም እነርሱ መከተል የፈለጉዋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ናቸው፤ ለምሳሌ፡- ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ሃላፊ ነው፣ እሁድ የሰንበት ቀን ነው።

ሌላኛው ማሰናከያ ደግሞ ሚስት ማግባት ነው። የቤተክርስቲያን አባል መሆን ምክንያቱም ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።

ሉቃስ 14፡20 ሌላውም፦ ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው።

ሚስትየው ወይም ቤተክርስቲያን ሐብታሙ ሰው ከጠየቃቸው ነገር ሌላ እንዲያደርጉ ትጠይቃቸዋለች። ስለዚህ ቤተክርስቲያናቸው አንድ ፓስተር ወይም ሐዋርያ ይኖራታል እርሱም ሰዎች ምን ማመን እንዳለባቸው ይነግራቸዋል። ይህ ዓይነቱ መሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉትን ሰባቱን ነጎድጓዶች ሊገልጥላቸው ይቃጣዋል። እነርሱም የማያስተውሉ ከመሆናቸው የተነሳ የሚነግራቸውን ያምናሉ።

የሜሴጅ ተከታዮች የአንድ ታሪካዊ ክስተት ትንቢታዊ መገለጥን ከክስተቱ ለይተው ማየት አይችሉም።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

የሚሆነው ነገር በገሃዱ ዓለም ከመሆኑ በፊት አስቀድሞ መገለጥ አለበት።

ወንድም ብራንሐም የመጣው የስድስቱን ማሕተሞች መፈታት ለመግለጥ ነው። ከዚያም ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ በሄደች ጊዜ በጉ ስድስቱን ማሕተሞች ይፈታቸውና በዝርዝር ይገልጣቸዋል።

62-0601 ከኢየሱስ ጋር መቆም

እነዚያ ጥንታዊ ሰዎች በወጡ ጊዜ አንዳንዴ ለስድስት ወይም ለስምንት ብቻ ሆነው ይሄዱ እንደነበር ታውቃላችሁ? ሆኖም ግን አገሩን በሙሉ አናወጡት። መቸም ታውቃላችሁ፤ አቂላ እና ጵርስቅላ ባሉበት አጵሎስ ታላቅ መነቃቃት ባስነሳ ጊዜ የተሰበሰቡት ሰዎች ስድስት ወይም ስምንት ብቻ ነበሩ። ያ ቤተክርስቲያን በሙሉ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ነው የነበሩት። አሁን እዚህ በተሰበሰብንበት ከእነርሱ በስድስት ወይም ሰባት እጥፍፍ ብዙ ሰዎች አለን።

ስለዚህ በሽማግሌዎች ትመራ የነበረችው ትንሽ ቤተክርስቲያን ሰዎች ሁሉ ደህንነታቸው የሚረጋገጥባት ቦታ ነበረች፤ ነገር ግን የሕዝቦቿ ቁጥር በዝቶ ትልቅ ቤተክርስቲያን ስትሆን የስሕተት ወጥመድ እና ሰዎች በሰው እየተመሩ መንፈሳዊ እስረኛ የሚሆኑባት ቤት ሆነች።

የ2019 ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ወጥቶ መሰራጨት ሲጀምር የመጀመሪያዋ ተጠቂ ከታላላቅ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ትልቅ ቤተክርስቲያን ያላት ደቡብ ኮርያ ነበረች። በ2020 ዓ.ም ቤተክርስቲያኒቱ የሞት ወጥመድ ስለሆነች ተዘጋች። እግዚአብሔር ምን እየነገረን ነው?

ከዚያ በኋላ ሃብታሙ ሰውዬ አስደንጋጭ ነገር ተናገረ።

ሉቃስ 14፡24 እላችኋለሁና፥ ከታደሙት ከእነዚያ ሰዎች አንድ ስንኳ እራቴን አይቀምስም አለው።

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ባለመረዳታቸው ምክንያት የዳኑ ክርስቲያኖች ወደ ሰርጉ ግብዣ ሳይሆን ወደ ታላቁ መከራ እየገሰገሱ ናቸው።

አንዳንድ ጊዜ እውነት ተመልሶ እስኪገለጥ ድረስ ሶስት ትውልዶች ሁሉ ሊያልፉ እንደሚችሉ እግዚአብሔር ተናግሯል።

ይህን እውነት በጠፉት ሶስት ነገስታት አማካኝነት መረዳት እንችላለን።

ዘፍጥረት 15፡16 በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ፤ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና።

ከኢዮራም በኋላ ሶስት ትውልዶች ሲጠፉ እናያለን፡- እነርሱም አካዝያስ፣ ኢዮአስ፣ እና አሜስያስ ናቸው።

አራተኛው ትውልድ ኦዝያን ተመልሶ ወደ ተሃድሶ መጣ። የኦዝያን ሌላኛው ስሙ አዛርያ ነው።

መጥፎ ሚስት በማግባቱ (በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመራት ይልቅ በሰዎች የምትመራ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል በመሆን) ኢዮራም አካዝያስ የተባለ መጥፎ ልጅ ወለደ። ይህ ልጅ መጽሐፍ ቅዱስን የመከተል ፍላጎት አልነበረውም።

2ኛ ነገሥት 8፡27 [አካዝያስም] በአክዓብም ቤት መንገድ ሄደ፥ እንደ አክዓብም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ ለአክዓብ ቤት አማች ነበረና።

ከአካዝያስ ምን እንማራለን? ልጆች በወላጆቻቸው እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ተጽእኖ ስር ስለሚያድጉ በቀላሉ የወላጆቻቸውን ትውልድ ስሕተት ተከትለው ይሄዳሉ።

ከዚህም የተነሳ አካዝያስ ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተደመሰሰ።

ስለዚህ ወላጆቻችሁ እና ዘመዶቻችሁ ምን እንደሚያምኑ በጥንቃቄ መርምሩ። እውነት ወደ ፊት ትገሰግሳለች። ወላጆች ብዙውን ጊዜ በትናንት እውነት ያምናሉ፤ ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር የት እንዳለ ማወቅ ተስኗቸዋል።

እግዚአብሔር ለሚሴጅ ተከታዮች እውነትን ያውቁ እንደሆን ፈተና ላከባቸው። ወላጆች ወይም የቀደመው ትውልድ ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው ያምኑ ነበር ምክንያቱም ወንድም ብራንሐም ወደፊት አንድ ቀን ቆንጅዬ ግን ጨካኝ የሆነች ሴት አሜሪካን ትመራለች ብሎ የተናገረውን ትንቢት አሳስተው ተረድተዋል። ይህ ራዕይ ተጽፎ ተቀምጧል፤ እነርሱም ስተዋል። ሒላሪ ክሊንተን በምርጫው ተሸነፈች፤ የሚሴጅ ተከታዮች ቀደምት ትውልድም ተሳሳቱ። እንግዲህ እነዚህ የሚሴጅ ሰባኪዎች ናቸው ያልተጻፉትን 7 ነጎድጓዶች እና በዝምታ የተዘጋውን ሰባተኛ ማሕተም ሚስጥር ፍቺ አግኝተናል የሚሉት።

ቀጣዩ ትውልድ ኢዮአስ ነበረ።

ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ጥሩ ጅማሬ ጀምረው ኋላ ወደ ስሕተት ሊወድቁ እንደሚችሉ የሚያሳይ አስፈሪ ምሳሌ ይህ ሰው ነው።

ኢዮአስ በወጣትነቱ መልካም አድርጎ ነበር፤ አያቱ ጎቶልያ የሰራችውን ክፉ ሥራ ሁሉ አስወግዷል።

ስለዚህ ሁሉ ሰላም መስሎ ነበር፤ ግን ይህ አሳሳች ነገር ነው።

ኢዮአስ በትክክለኛው መንገድ የቆመው ካሕኑ ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ሰዓት ነው።

2ኛ ዜና 24፡2 በካህኑም በዮዳሄ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ።

ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ኢዮአስ ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ እንዲያደርጉበት በመፍቀዱ ወደ ተሳሳተ መንገድ ሊገባ ችሏል።

ትምሕት 1፡ ወሳኙ አጀማመርህ አይደለም። አጨራረስህ ነው እንጂ።

ትምሕርት 2፡ በራስህ አእምሮ ማሰብ አለብህ። በአንድ መልካም ሰው የምትመራ ከሆንክና እርሱ የሚልህን እየሰማህ የምትደግም ብቻ ከሆንክ ብዙም አይጠቅምህም። አንድ ቀን ያ መልካም ሰው ሲሞት ሌላ ሰው ይመጣና አስተሳሰብህን ይቆጣጠረዋል፤ እንተም ያ ሌላ ሰው ያለውን እደገምክ ትከተለዋለህ። ይህም በቀቀን ያደርግሃል፤ ማለትም ያንተ ብቃት ሌሎች ሰዎች የተናገሩትን መኮረጅ ብቻ ሆኖ ይቀራል።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለራስህ ማመን አለብህ እንጂ የሆነ ሰው እውነት ነው ብሎ ሲናገር ስለሰማህ አይደለም።

ወንድም ብራንሐም የተናገረውን ከሰማህ በኋላ ሃሳቡን ወስደህ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች መሰረት ፈትሸህ ማረጋገጥ ያስፈልግሃል። ከዚያ በኋላ ታምናልህ፤ ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ስለተናገረ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ነው።

1965-0725 የተቀቡት በመጨረሻው ቀን

ስለዚህ ይህ እውነት መሆኑን ለማወቅ በቃሉ ፈትሸን ማረጋገጥ እንችላለን፤ እንጂ በሆነ ሰው ሃሳብ ወይም በሆነ ሰው ቲዎሪ አይደለም።

ይህ ሰው ማንም ቢሆን ማን ግድ የለኝም፤ እኔም ልሁን ሌላ። “እንደ ሕጉ እና እንደ ነብያቱ ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም።” አያችሁ? መጽሐፍ ቅዱ ያለው ይህንን ነው። “እግዚአብሔር ብቻ እውነተኛ ይሁን፤ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ይሁን” ማንም ይሁን ማን።

አንድ ታላቅ ሰው ሥፍራውን ለቆ ሲሄድ እርሱን እንተካለን ብለው የሚያስመስሉ ብዙ አታላዮች ይነሳሉ።

2ኛ ዜና 24፡17 ዮዳሄም ከሞተ በኋላ የይሁዳ አለቆች ገብተው ለንጉሡ እጅ ነሡ፤ ንጉሡም እሺ አላቸው።

ኢዮአስ ለራሱ ማሰብን አልተለማመደም። ዮዳሄ የነገረውን ብቻ ነበር የሚከተለው። አንድ ትልቅ ሰው እውነትን ሲናገር ስለ ሰማ እውነትን እንደ ገደል ማሚቶ መድገም ኢዮአስን አማኝ አላደረገውም።

ኢዮአስ በእምነቱ የራሱ የሆነ የልብ እርግጠኝነት አልነበረውም፤ ከዚህም የተነሳ ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ወዲያው ከእምነቱ ተዳክሞ ወደቀ።

ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ኢዮአስ መሪ የሌለው መርከብ ሆኖ ቀረ።

የሰዎች አመለካከት እንደ ነፋስ እየነዳው እድሜውን በሙሉ ሲፍገመገም ኖረ።

ለዚህ ነው ቤተክርስቲያኖች ከሕንጻቸው አናት ላይ የነፋስ ጠቋሚ የዶሮ ምስል አስቀርጸው የሚያኖሩት። ዶሮው ነፋስ ወደነፈሰበት አቅጣጫ እየዞረ ያመለክታል።

 

 

2ኛ ዜና 24፡18 የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ።

19 ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።

የሜሴጅ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እምነታቸውን በወንድም ብራንሐም ጥቅሶች ላይ እንዲመሰርቱ ካስተማሩዋቸው በኋላ እነዚህን ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፎ ሊያሳያቸው የሚሞክር ሰውን በጭራሽ አይሰሙም።

እነዚህ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ ለሰው ንግግር የበለጠ ዋጋ ይሰጣሉ።

2ኛ ዜና 24፡20 የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆመና፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካምም አይሆንላችሁም፤ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል አላቸው።

21 ተማማሉበትም በንጉሡም ትእዛዝ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።

“በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ” ማለት ቤተ መቅደሱ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስቀምጡበት ቦታ ነው።

የእግዚአብሔርን ቃል የሚነግራቸውን ሰው ይህን ያህል ነበር የሚጠሉት።

ጥቅሶችን ሲተረጉሙ ቢሳሳቱም እንኳ (ለምሳሌ ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን ምርጫ ታሸንፋለች ብለው) የሚሴጅ ተከታዮች እስከ አሁንም ድረስ የእግዚአብሔርን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ መከተል የሚፈልግ ሰውን ስም ያጠፋሉ።

“ሰባተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ማወቅ አትችሉም። ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ ወይም እነዚህ ነጎድጓዶች ምን እንደሆኑ ማወቅ አትችሉም። የኢየሱስን አዲስ ስም ማወቅ አትችሉም።” ለምን? ምክንያቱም እነዚህ ሚስጥራት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም።

ነገር ግን እነዚህን ሚስጥራት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በቃላት ይወገራሉ ይሰደባሉ።

አንድን እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መሰረት ማረጋገጥ አሁን በሜሴጅ ተከታዮች ዘንድ ዋጋ አጥቷል።

ወንድም ብራንሐም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ እንድናምን አስጠንቅቆናል።

ኢዮአስ የሚለው ስም ደስ የሚል ስም ነው። ትርጉም “በያህዌ የተሰጠ” ማለት ነው። ነገር ግን የእርሱ ውድቀት መነሻው ገንዘብ ነበረ። ኢዮአስ የቤተመቅደሱን ሃብት ሰበሰበ፤ ልክ የዛሬ ፓስተሮች አስራቱን በሙሉ ለራሳቸው እንደሚሰበስቡት።

ኢዮአስ የሰበሰበውን ገንዘብ እውነትን ለማሰራጨት አልተጠቀመበትም።

ያ ሁሉ ገንዘብ ወደ ጠላት እጅ ገባ።

2ኛ ነገሥት 12፡19 የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ [የኢዮአስ ስም ትርጉሙ “በያህዌ የተሰጠ” ነው] አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፥ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።

ከጠላት ጥቂት ሰዎች ብቻ መጥተው በቁጥር ብዙ የነበሩትን አይሁዳውያን አሸነፉዋቸው።

2ኛ ዜና 24፡24 የሶርያውያንም ሠራዊት ቍጥር ጥቂት ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር ታላቅን ሠራዊት አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ስለ ነበረ ነው። እነርሱም በኢዮአስ ላይ ፍርድ ፈረዱበት።

ጥቂት የሜሴጅ ፓስተሮች ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የታየውንና አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ፎቶግራፍ የተነሳውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ከወንድም ብራንሐም ጋር ተነጋግረው ወደ ሰማይ የተመለሱት መላእከት ናቸው ብለው እንግዳ የሆነ ሃሳብ አመጡ፤ መላእክቱ ግን ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡት ከስምንት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ሳንሴት ፒክ የሚባል ከተማ አካባቢ ነው። ሳንሴት ፒክ ደግሞ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተደቡብ 200 ማይልስ ርቀት ላይ የሚገኝ ከተማ ነው።

 

 

ቀኑ አልተገጣጠመም። ቦታውም አልተገጣጠመም።

ደመናው ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ እየሄደ ነበር። ወደ ዊንስሎው አካባቢ ሲደርስ ፎቶ በተነሳ ጊዜ ሁለት ደመናዎች ይታዩ ነበረ። እነዚህም ትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና እና ትንሹ ደግሞ ከሮኬት ፍንዳታ በኋላ የተፈጠረው ጭስ እና የብረታ ብረት ስብርባሪ ናቸው።

ደመናውን ፎቶ ያነሳው የጠፈር ተመራማሪ ጄምስ ማክዶናልድ ደመናው ምን እንደሆነ ሊገባው እንዳልቻለ ተናግሯል ምክንያቱም ሁለት ደመናዎች ነበሩ አብረው የታዩት።

 

 

ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ እውነታዎችን ቸል በማለት ከሳንሴት ፒክ ተነስተው የሄዱት ሰባት መላእከት የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ሙታንን ለማስነሳት መውረዱ ነው ተብሎ ተተረጎመ። ይህም ከምድር በላይ 42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ የታየው ደመና ከፍጥረታዊ ደመናዎች በላይ ከፍ ብሎ የታየው ደመና በአንዳንድ ሰዎች አተረጓጎም የጌታ ምጻት ወይም የብርቱው መልአክ መውረድ ነው ተባለ። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ብዙዎቹ የሜሴጅ ተከታዮች ይህንን እውነት ነው ብለው መቀበላቸው ነው።

1964-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ። በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ቆዩ፤ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ቆዩ።

መልአኩ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ ሙታንን ያስነሳቸዋል።

ይህ “ሻሎም” በሚል ርዕስ የቀረበው መልእክት ደመናው ፎቶ ከተነሳ ከአንድ ዓመት በኋላ ነበር የተሰበከው፤ በዚያን ጊዜም ወንድም ብራንሐም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ገና ወደፊት ይመጣል ብሎ እየተጠባበቀ ነበር። ስለዚህ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር ደመናው መልአኩ አለመሆኑን ነው።

እነዚያ የሜሴጅ ተከታዮች ጥቅሶችን በተሳሳተ መረዳት ተረድተዋል። የረሱት ነገር አለ፤ እርሱም ወንድም ብራንሐም በጭራሽም ደመናውን አለማየቱን ነው፤ ስለዚህ እርሱ ደመናው ምን ይመስል እንደነበር በሃሳቡ ብቻ ነው ለማወቅ የሞከረው። ሰባቱ መላእክት ደመና መስራታቸውን አውቋል ግን እርሱ ደመናው በተፈጠረበት ቦታ አልነበረም (ሳንሴት ፒክ የሚባል ቦታ ነው እርሱ የነበረው) ደግሞም ደመናው በተፈጠረበት ዕለት አልነበረም (ማርች 8 ቀን 1963)። ደመናው ፎቶ የተነሳው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ሰሜን ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነው። በዚያ ጊዜ እነዚህን ዝርዝር እውነታዎች የተከታተለ አልነበረም።

የሜሴጅ ተከታዮች ስለ ነጎድጓዶቹ ባላቸው ልዩ ልዩ መረዳት የተነሳ በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለዋል። ከእነርሱ መካከል የተለያየ ትርጓሜ ይዘው የሚነሱ ብልጥ ሰዎች አሉ፤ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ሃሳብ ይዘው ይነሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሌለ ሃሳብ መንፈሳዊ ቫይረስ ነው። መንፈሳዊ በሽታ ያመጣል። እንደዚህ ዓይነቱ ሃሳብ ለእውነትነቱ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት አይሰጠውም።

2ኛ ዜና 24፡25 ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታምሞ ነበር፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ዮዳሄ ልጅ ተበቅለው ተማማሉበት፥ በአልጋውም ላይ ገደሉት፥ ሞተም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።

ኢዮአስ አጀማመሩ መልካም ነበር ነገር ግን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍን ለራሱ ማመን አልቻለም።

ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎች በሚሉት ላይ ነበር የሚደገፈው። ታላቁ ዮዳሄ በሞተ እና ከአጠገቡ ዞር ባለ ጊዜ የመሪዎች ባሕርይ እየወደቀ ሄዶ በስተመጨረሻ ኢዮxስ ወደ ስሕተት ሊገባ ችሏል። እርሱም በስተመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉ ሰዎችን ገደለ። ከዚያ በኋላ ኢዮአስ አሳዛኝ ሞት ሞተ። ስሙም ከሕይወት መጽሐፍ ተሰረዘ።

ስለዚህ አሁንም እንጠንቀቅ። መልካም ጅማሬ ለመልካም ፍጻሜ ዋስትና አይሰጥም።

ኢየሱስ ሌሎች ሰዎች የተናገሩትን እንደ ገደል ማሚቶ በሚደግሙ ሰዎች አይገረምም።

በራሱ የሚያስብ ሰውን ኢየሱስ እንዴት እንደሚያደንቅ ተመልከቱ።

ስምኦን ጴጥሮስ ሕዝቡን ተከትሎ የሚሄድ ሰው አልነበረም።

ማቴዎስ 16፡13 ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ እንደ ገደል ማሚቶ የሰሙትን እንዲደግሙ ነበር የጠየቃቸው። ደቀመዛሙርቱም ወዲያው መልስ ሰጡ፤ ምክንያቱም ሰዎች የተናገሩትን ሰምቶ መድገም በጣም ቀላል ነው። ብዙ ሰዎች ካመኑበት ትክክል ነው ብሎ የማሰብ ዝንባሌ በብዙዎች ዘንድ አለ።

ማቴዎስ 16፡14 እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።

ከዚያም ኢየሱስ ወደ ዋናው ጥያቄ መጣ። እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ? በራሳችሁ እግር ቁሙ።

ማቴዎስ 16፡15 እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።

በዚህ ጊዜ ታላቅ ጸጥታ ሰፈነ። ልክ እንደ እኛ እነርሱም በራሳቸው አእምሮ አያስቡም ነበር። እኛም ምን ማሰብ እንዳለብን ሌሎች ሰዎች እየነገሩን መከተል ለምደናል።

ከዚያ በኋላ ወኔ ያለው አንድ ሰው ብቻ ተናገረ።

ማቴዎስ 16፡16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

ጴጥሮስ። ኢየሱስ ማን ስለመሆኑ ጴጥሮስ በግሉ መገለጥ አግኝቷል። እግዚአብሔር እራሱ በልጁ ውስጥ፤ በእግዚአብሔር ሰብዓዊ አካል ውስጥ።

ማቴዎስ 16፡17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

ይህንን እውነት ለጴጥሮስ የነገረው ሰው አልነበረም። ጴጥሮስ እራሱ ኢየሱስን አይቶት ነው ኢየሱስ የእግዚአብሔር በስጋ መገለጥ መሆኑን የተረዳው።

ማቴዎስ 16፡18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።

ዓለቱ የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። ይህ መገለጥ በአእምሮዋችሁ ውስጥ በእግዚአብሔር ኃይል ተቀርጾ መቀመጥ አለበት። ሰው ስለነገራችሁ አይደለም። ይህንን መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ተከታትላችሁ በማየት እውነት መሆኑን ማወቅ አለባችሁ ምክንያቱም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ ጋር ይገጣጠማል።

ማቴዎስ 16፡19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ የከፈተው ቁልፍ የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ንሰሃ። የውሃ ጥምቀት በኢየሱስ ስም። መንፈስ ቅዱስን መቀበል።

መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ መከተል በሰማይ ደጅ ውስጥ የማለፍ ውጤት ነው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ እርሱ የሰማይ መግቢያ ወይም በር ነው።

ከእንግዲህ መግቢያ ሆኖ እንዳያገለግል ጴጥሮስ ያሰረው ወይም የዘጋው የሰማይ በር የትኛው ነው?

የዮሐንስ የውሃ ጥምቀት አስፈላጊነቱ አብቅቷል ምክንያቱም የዮሐንስ ጥምቀት የሚደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልነበረም።

ስለዚህ የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት አስፈላጊነቱን አጥቷል።

በኢየሱስ ስመ ያልተደረገ ማንኛውም የውሃ ጥምቀት ዋጋ የለውም።

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው።

የሥላሴ አማኞች ግን ያ ስም ማን እንደሆነ አያውቁም።

ስለዚህ ባለማወቅ ኢየሱስ የተናገረውን ይደግማሉ እንዲህ ብለው፡- “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም”።

ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ አንዳችም አያውቁም።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በሕብረት “በቡድን ተባብረው ካሰቡት” ሃሳብ ይልቅ በጴጥሮስ የግል መገለጥ የተገረመው ለምንድነው?

ምክንያቱም የባህሪ ሳይንቲስቶች አጥንተው በደረሱበት መሰረት ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁት የሌሎችን ሰዎች ሃሳብ ተመስጠው የመከታተል ዝንባሌ አላቸው።

አብዛኞቻችን ምን ማድረግ እንዳለብን እርግጠኛ ባልሆንን ጊዜ “ሌሎች ሰዎች የሚያስቡትንና የሚያደርጉትን” አይተን ለትክክለኛ ባሕሪ እንደ መመሪያ እንጠቀምበታለን።

ይህንንም የምናደርገው በራሳችን አእምሮ ለማሰብ ስለምንሰንፍ እና ከሰዎች ጋር መቃረን በጣም ስለሚያስፈራን ነው። ትክክለኛ ለመሆናችን ዋነኛ ማረጋገጫ የምናገኘው የቡድኑ አካል በመሆን ነው።

ለብቻችን መቆም እንፈራለን ምክንያቱም ለብቻው የሚቆም ሚስማር እርሱ ነው ብዙ ጊዜ በመዶሻ አናቱን የሚደበደበው።

ኢየሱስ የፈለገው የማይፈሩ ሰዎችን ማየት ነው።

እርሱ የፈለገው ከብዙሃኑ ሕዝብ ለመለየት እና እውነትን ለመናገር አለመፍራትን ነው። በሰዎች መገፋትን ሳይፈሩ የመቀበልን ድፍረት ነው የፈለገው። ጴጥሮስ እንደዚያ ዓይነቱ ወኔ ነበረው። ደግሞም በበዓለ ሃምሳ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፊት ቆሞ ወንጌልን ሲሰብክም እንደዚያ ዓይነቱ ድፍረት ያስፈልገዋል።

ቀጥሎ ደግሞ ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የተወገደ ሌላም ዓይነት ሰው አለ።

አሜስያስ። የኢዮአስ ልጅ።

አሜስያስ ብዙ መልካም ነገሮችን አድርጓል፤ ነገር ግን የተወሰኑ የተሳሳቱ እምነቶችን ለማስተካከል ድፍረት አጣ።

ልክ ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ይመስላል።

ብዙ ነገሮችን በትክክል ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ፓስተሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገሮችን ሲያስተምር ከፓስተሩ ጋር ለመቃረን ይፈራሉ።

ስለዚህ ይድናሉ፤ መልካም ሥራዎችን ይሰራሉ ነገር ግን ሥላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ ክሪስማስ፣ እና ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ መቁጠር የመሳሰሉ ስሕተቶችን ይቀበላሉ።

2ኛ ነገሥት 14፡3 [አሜስያስ] በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮአስ እንዳደረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላደረገም።

4 ነገር ግን በኮረብቶቹ ላይ ያሉት መስገጃዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶች ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋና ያጥን ነበር።

አሜስያን ሙሉ በሙሉ አካሄዱን አላጸዳም። አሜስያስ እግዚአብሔርን አገልግሏል፤ ነገር ግን የጣኦት አምልኮ የሚደረግባቸውን የኮረብታ መስገጃዎች አላስወገዳቸውም።

ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ብለን ስሕተቶችን እያየን እንዳላየን እናልፋለን። በልባችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቦታ የሚሻሙትን የወሲብ፣ የገንዘብ፣ እና የዝና ጣኦታት ታግሰን ዝም እንላቸዋልን።

የኮረብታ መስገጃዎች። ሰው ሁሉ አፉን ከፍቶ ለመናገር የሚፈራቸው የቤተክርስቲያን ስሕተቶች ናቸው።

ልክ እንደ ሴት ልብስ።

በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተን ለመኖር ስንል ስሕተት የሆኑ ነገሮችን ታግሰን እናልፋለን።

ከዚህም የባሰው ነገር ደግሞ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ላለማጣት ብለን ትክክል የሆኑ ነገሮችን እናወግዛለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት ሊያርመን የሞከረ ሰውን ሁሉ እናወግዛለን።

ኢዮራም አባት እንደመሆኑ ጎቶሊያ የተባለች ሴትን አገባ፤ የእርሷም አለማመን ቀጣዮቹን ሶስት ትውልዶች አበላሻቸው።

ዘጸአት 34፡7 እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።

ቀጥሎ ኦዝያን ከመጠቀሱ በፊት ከኢዮራም በኋላ ሶስት ትውልዶች ይጠፋሉ። ይህ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ነው።

አካዝያስ፣ ኢዮአስ፣ እና አሜስያስ ከሕይወት መጽሐፍ ተወግደዋል።

እግዚአብሔርን ማገልገል ከፈለግን መንገዳችንን ማጽዳት አለብን።

እግዚአብሔርን ካገለገልን እስከ መጨረሻው መጽናት አለብን።

በሰዎች ላይ መደገፍ የለብህም። በሰው ከተደገፍን የተደገፍንበት ሰው ዞር ሲል እንወድቃለን።

ደግሞም እኛ የተከተልነው ሰው በራሳችን አእምሮ እንዳናስብ ያደርገናል።

ማቴዎስ 1፡9 ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡10 አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡11 አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።

ከኢዮስያስ በኋላም ሦስት ስሞች ተሰርዘዋል። እነዚህ ሦስቱም የኢዮስያስ ልጆች ናቸው።

2ኛ ነገሥት 23፡25 እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ በፍጹምም ነፍሱ በፍጹምም ኃይሉ ወደ እግዚአብሔርም የተመለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእርሱ አስቀድሞ አልነበረም፤ እንደ እርሱም ያለ ንጉሥ ከእርሱ በኋላ አልተነሣም።

ኢዮስያስ ትልቅ ንጉስ ነበረ ነገር ግን በጦር ሜዳ የግብጽን ንጉሥ ሊቃወም ሞከረ።

ወደ መጊዶ ጦር ሜዳ ሄደ።

የታሪክ ምሑራን የጽሑፍ ማስረጃ ያገኙለት የመጀመሪያው ጦርነት ይህ ነው።

በተጨማሪም መጊዶ የመጨረሻው ጦርነት የሚካሄድበት አርማጌዶን የሚባለው ቦታ ነው። ይህም ብዙ ደም መፋሰስ የሚሆንበት ጦርነት ነው።

ስለዚህ ኢዮስያስ በጦር ሜዳ ሞተ። እርሱን ለመሰለ ታላቅ ንጉሥ ይህ አሳዛኝ ፍጻሜ ነው።

2ኛ ነገሥት 23፡29 በእርሱም ዘመን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።

ምንም ያህል ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን ብናገለግል እንኳ ለማድረግ ለምናቅደው ሁሉ የእርሱን ምሪት መፈለግ አለብን። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ ስንወጣ ትልቅ ዋጋ እንከፍላለን።

2ኛ ነገሥት 23፡30 የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወሰዱት፥ ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት።

መልካም አባት የግድ መልካም ልጅ ይወልዳልን?

አይወልድም።

የኢዮስያስ ልጆች ክፉዎች ነበሩ።

የመጀመሪያ ልጁ ኢዮአካዝ ነበረ።

2ኛ ነገሥት 23፡31 ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ፦

የግብጹ ፈርኦን ኢየአካዝን በሶርያ ከተማ ውስጥ አሰረው፤ ከዚያ በኋላ ወደ ግብጽ ወደሰው፤ ኢዮአካዝም ግብጽ ውስጥ ሞተ።

ግብጽ የዓለም ምሳሌ ናት።

ልክ እንደ ኢዮአካዝ በዓለማዊ አለባበስ እና በሌሎች ዓለማዊ ባሕርያት በቀላሉ ተማርከን እስረኞች እንሆናለን።

2ኛ ነገሥት 23፡32 [ኢዮአካዝ] አባቶቹም እንዳደረጉ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

ቀጣዩ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም ነው። ፈርኦን የኤልያቄምን ስም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው።

ግብጽ እና ባቢሎን የሰዎችን ስም የመለወጥ ልምድ አላቸው።

ስምህን የሚያስለውጥህ ሰው በአንተ ላይ የተወሰነ ኃይል ወይም ስልጣን ይኖረዋል፤ ምክንያቱም ስምህን ሲለውጠው እሺ ብለህ ተቀብለኸዋል።

የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ሹመት ሲቀበል ስሙ እንደሚለወጥ አስተውሉ። ይህ የባቢሎናውያን ሚስጥራት ተጽእኖ ነው።

ኢዮአቄም ለ11 ዓመታት ነገሰ፤ ከዚያ በኋላ ናቡከደነጾር ገደለው።

2ኛ ነገሥት 23፡37 አባቶቹም እንዳደረጉ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

2ኛ ነገሥት 24፡6 ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

ኢዮአካዝ፣ ኢዮአቄም፣ እና ሴዴቅያስ የታላቁ ንጉሥ የኢዮስያስ የማይረቡ ልጆች ሆነው ቀሩ።

እነዚህ ሶስቱ ማቴዎስ በጻፈው የዘር ሃረግ ውስጥ ስማቸው አልተካተተም።

ከዚህ የምናገኘው ትምሕርት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ካደረግን እግዚአብሔር ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንደሚሰርዘን ነው።

ስማችን ሲሰረዝ ፈጽሞ እንዳልተፈጠርን እንሆናለን።

ከኢዮስያስ የማይረቡ ልጆች መካከል ኢኮንያን ብቻ ነው በምርኮ ወደ ባቢሎን የሄደው።

ይህ የሆነው ግን ለአንድ ልዩ ምክንያት ነው።

ከኢዮስያስ ልጆች መካከል ኢዮአቄም የተባለው ብቻ ኢቆንያንን ይወልድ ዘንድ ሌሎቹን የማይረቡ ልጆች በሙሉ ማስወገድ አስፈላጊ ስለነበረ ነው።

የነገሥታት ዘር ሆነው ከተወለዱት መካከል ኢቆንያን ብቻ ነበር በሕይወት የተረፈው፤ ነገር ግን ኢቆንያን ደግሞ ንግሥና ሊያገኝ አልቻለም።

ኤርምያስ 22፡28 በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?

ኤርምያስ 22፡30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።

ከኢኮንያን የተወለደ ሰው ቢኖር በፍጹም ንጉሥ መሆን አይችልም።

2ኛ ነገሥት 24፡8 ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአሥራ ስምንት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ

2ኛ ነገሥት 24፡9 አባቱም እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

2ኛ ነገሥት 24፡15 [ናቡከደነፆር] ዮአኮንንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ

ከዚህ በታች በቀይ ቀለም የተጻፉት ስሞች በማቴዎስ የዘር ሐረግ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።

 

 

2ኛ ነገሥት 24፡17 የባቢሎንም ንጉሥ የዮአኪንን አጎት ማታንያን በእርሱ ፋንታ አነገሠ፥ ስሙንም ሴዴቅያስ ብሎ ለወጠው።

የኢኮንያን አጎት ሴዴቅያስ ለ11 ዓመታት ያህል ነገሰ፤ ከዚያ በኋላ በባቢሎን ምርኮ ተወሰደ።

2ኛ ነገሥት 25፡7 የሴዴቅያስንም ልጆች በፊቱ ገደሉአቸው፤ የሴዴቅያስንም ዓይኖች አወጡ፥ በሰንሰለትም አሰሩት፥ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።

የሴዴቅያስ ልጆችና የልጅ ልጆች በሙሉ ተገደሉ።

በምርኮ ሃገር ውስጥ በሕይወት የተረፉት የኢቆንያን ልጆች ብቻ ነበሩ።

ማቴዎስ 1፡11 አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።

ኢቆንያን የኢዮስያስ የልጅ ልጅ ነው።

ኢዮአካዝ፣ ኢዮአቄም፣ እና ሴዴቅያስ ሶስቱ የኢዮስያስ ክፉ ልጆች ጠፍተዋል።

ኢዮስያስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። ብዙውን ጊዜ የመልካም ሰዎች ልጆች ክፉ ሆነው ሊያድጉ ይችላሉ።

ጥሩ ሰው ልጆቹን ሊያድን አይችልም።

ማቴዎስ 1፡12 ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤

ቀጥሎ እዚህ ግቡ የማይባሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር እናገኛለን። ማቴዎስ ስማቸውን ባይዘረዝር ኖሮ ላናውቃቸውም እንችል ነበር።

ከተዘረዘሩት 14 ስሞች መካከል ኢኮንያን፣ ዮሴፍ፣ እና ኢየሱስን ብቻ ነው በሰሩት ስራ ምክንያት የምናውቃቸው።

ይህ ስም ዝርዝር የያዘው ምንም ታሪክ ያልሰሩ መታሰቢያ የሌላቸውን ሰዎች ስም ነው። ሆኖም ግን ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ ተቆጥሮ በሚያድግበት ጊዜ ከነገሥታት ዘር የመጣ መሆኑን ለማስረዳት አስፈላጊ ናቸው።

እነዚህ የማይታወቁ ሰዎች ኢየሱስን በዘር ሐረግ ከንጉሥ ዳዊት ጋር ያያይዙታል፤ ይህም ለኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ የመሆን መብትን ይሰጠዋል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ በማይታወቁ እና እዚህ ግቡ በማይባሉ ሰዎች አማካኝነት ፈቃዱን ይፈጽማል።

የጌታ ወደ እሥራኤል መምጣቱ እየተቃረበ በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር ፈጽሞ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎችን እየተጠቀመ ነበር።

የማርያም ባል ዮሴፍ በታሪክ ውስጥ ታዋቂ ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምሪት ታዛዥ ነበረ።

ዮሴፍ ለእኛ ጥሩ ምሳሌያችን ነው።

ፓስተሮች በጣም አስተዋይ ስለሆኑ እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው ይመስላቸዋል።

ግን አይደለም።

በጣም ብዙ ሰዎች በኢቆንያን ሐጥያት ምክንያት ከንጉሥነት ቢወገዱም እንኳ የንጉስነትን ደም በደም ስራቸው ውስጥ ይዘው ኖረዋል።

ስለነዚህ ሰዎች ታሪክ አንዳችም አይነግረንም። ማንም ሳይውቃቸው ኖረው አለፉ። ማንም ያላወቃቸው ማንም ያላደነቃቸው ነገር ግን ንጉሥ ዳዊትን ከኢየሱስ ጋር ለማያያዝ ያገለገሉ ሰዎች ሆነዋል።

ማቴዎስ 1፡13 ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤

14 አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤

15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤

16 ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።

ማቴዎስ 1፡17 እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።

እነዚህ የመጨረሻዎቹ 14 ሰዎች ከንጉሳውያን ሹመት ውስጥ የተቆረጡት ለምንድነው?

በኢቆንያን ሐጥያት ምክንያት ነው።

ኢዮስያስ ከወለዳቸው ሶስት ልጆች መካከል ኢቆንያን ብቻ ነበር ልጆች የወለደው፤ ልጆቹም ሆኑ የልጅ ልጆቹ ሊነግሱ አልቻሉም።

 

 

በስጋ የተወለደ አይሁዳዊ የእሥራኤል ንጉሥ ሊሆን አይችልም።

(ስለዚህ ኤዶማዊው ሔሮድስ (አይሁዳዊ ያልሆነ ሰው) የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ የተሾመው በሮማውያን ነው)።

ይህም መቃዕቢያኖች የሰሩት ስሕተት ነው። መቃዕቢያኖች ሶሪያውያንን ከእሥራኤል ውስጥ አባረሩ፤ ይህም መልካም ነበር። በዚህ ስኬታቸው ከመደሰታቸው ብዛት ኤዶማውያንን አሸንፈው ገዙዋቸውና እንደ አይሁዳውያን እንዲኖሩ አስገደዱዋቸው። ይህም ትልቅ ስሕተት ነበረ፤ ምክንያቱም ኤዶምያስ ከሙት ባሕር በስተ ደበቡብ በመሆኗ የአብራሐም የተስፋ ምድር አካል አልነበረችም። ሔሮድስ በሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዳውያንን ገደለ።

ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ድንበር ውጭ መውጣት የለባቸውም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ከወጣን ሞት እና ጥፋት ሲመጣብን አትገረሙ።

የኢቆንያንን ልጆችና የልጅ ልጆች ተረግመዋል።

በኢቆንያን ዘሮች ላይ የተደረገውን እርግማን ለማለፍ በድንግልና መወለድ ይጠይቃል።

ማቴዎስ 1፡18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ነበር። በእጮኝነት ኪዳን ውስጥ ነበሩ ግን አብረው እየኖሩ አልነበሩም። ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ግንኙነት አልፈጸሙም። ማርያም በድንግልና የሚወለደውን ኢየሱስን ለመውለድ ድንግል ሆና መቆየት ነበረባት።

እጮኝነታቸው የማይፈርስ እጮኝነት ነበረ። እጮንነት በዚያን ጊዜ ሊፈርስ እና ከሌላ ሰው ጋር አዲስ እጮኝነት ሊፈጸም የሚችልበት አልነበረም። እጮኝነት ውስጥ የገባ ሰው እጮኛው ለሆነችው ሴት ባሏ ተደርጎ ይቆጠር ነበር።

ማቴዎስ 1፡19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።

“በስውር ሊተዋት” የሚለው ቃል ሊፈታት ማለት ነው። የእጮኝነትን ኪዳን ማፍረስ መፋታት ነው።

አዲስ ኪዳን ውስጥ መፋታት እና እንደገና መጋባት አይፈቀድም ምክንያቱም የሕጋዊ ጋበቻ ቃልኪዳን እስከ ሞት ድረስ የጸና ነው።

ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤

12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

ዮሴፍ እና ማርያም ተጫጭተው ነበር። አብረው መኖር አልጀመሩም። ሆኖም በእግዚአብሔር ዓይን ግን ማርያም የዮሴፍ ሚስት ነበረች።

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።

በሴት ማሕጸን ውስጥ የሕይወትን ዘር ያስቀመጠ ሰው የሕጻኑ አባት ነው።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ የተጻፈ ቃል አናገኝም።

እግዚአብሔር እግዚአብሔር አብ ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር በውስጡ የሚያድርበት “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚሆን ፍጹም ሰው ሲገኝ ብቻ ነው። ኢየሱስ ብቻ ነው ይህን ሰው ሊሆን የሚችለው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ስለዚህ እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ በሰው ስም ተጠርቷል።

ማቴዎስ 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።

ከኢኮንያ እስከ ኢየሱስ ድረስ የዘር ሃረግ ውስጥ የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ ግን እዚህ ግቡ የሚባሉ ሰዎች አይደሉም።

ስለዚህ የሰው ጥረት እና ዝና በእግዚአብሔር ዘንድ አንዳችም ዋጋ የለውም። ዋጋ ያለው ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል መፈጸም ብቻ ነው።

ማቴዎስ 1፡22-23 በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

እግዚአብሔር ይህንን ትልቅ እውነት ለዮሴፍ በሕልም ገለጠለት።

ዮሴፍ በእንቅልፍ ውስጥ ስለነበረ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር አልቻለም።

ለእግዚአብሔር ጥሩ ምላሽ መስጠት የምንችለው ሙሉ በሙሉ ለቃሉ በመታዘዝ ነው። ከእርሱ ጋር አንዳችም ነገር መከራከር የለብንም።

ማቴዎስ 1፡24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤

25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

“የበኩር ልጇ።” ዮሴፍ የኢየሱስ አባት ተብሎ አልተጠቀሰም።

ማርያም ዮሴፍን ከማግባቷ በፊት ነበር የጸነሰችው። ከዚህም የተነሳ ከጋብቻ ውጭ ልጅ እንደተወለደ አስበው ሰዎች በማርያም እና በኢየሱስ ላይ የሚሰነዝሩት ነቀፋ ነበረ።

እውነት ሁልጊዜ ዋጋ ታስከፍላለች። ይህም ዋጋ በሰዎች ዘንድ ነቀፋን መቀበል ነው።

እግዚአብሔር ለሰዎች ባሰበው የማዳን እቅድ ውስጥ መግባት ድፍረት ይጠይቃል።

ከጋብቻ ውጭ የተወለደ ተብሎ መነቀፉ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑን ያስረዳል።

ይህም እውነት ኢየሱስ ከኢኮንያን እርግማን ነጻ መሆኑን ስለሚያረጋግጥ በጣም አስፈላጊ ነው።

ከዚህም የተነሳ ማርያም የተነሳባትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ሁሉ ተቀብላ ኖራለች። ክርስትና ለልፍስፍሶች አይደለም።

ዮሴፍ ኢየሱስን እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ለማሳደግ ሲቀበለው በዚያን ጊዜ ኢየሱስ የዮሴፍን ውርስ አግኝቷል።

የዮሴፍ ውርስ ንጉስ የመሆንን መብት ያካትታል፤ ምክንያቱም ዮሴፍ ከንጉሳዊ ቤተሰብ የተወለደ ሰው ነው።

በስጋ በቀጥታ የዮሴፍ ዘር አለመሆን ደግሞ ኢየሱስ ከኢኮንያ ትውልድ ወይም ዘር ውስጥ እንዳይቆጠር ያደርገዋል።

ስለዚህ የኢኮንያን እርግማን ኢየሱስን አልነካውም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23