ማቴዎስ ምዕራፍ 01. ክፍል 1. የአይሁድም የአሕዛብም መሰረት የሆኑ አምስት ሰዎች። ቤተክርስቲያንን የሚገልጹ አራት ሴቶች



አምስት ሰዎች የአይሁዶችና የአሕዛብ ቤተክርስቲያን መሰረት ናቸው። አራት ሴቶች የወደፊቷን ቤተክርስቲያን ይገልጻሉ።

First published on the 4th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማቴዎስ ምዕራፍ 1

በራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት እናያለን።

አንበሳ። ጥጃ። ሰው። የሚበር ንስር።

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

 

አራቱ እንስሳት አራቱን ወንጌሎች ይወክላሉ።

ደግሞም ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ያሉትን የመጀመሪያዎቹን አራት ማሕተሞችም ይወክላሉ።

ማቴዎስ ኢየሱስን የይሁዳ ነገድ አንበሳ እንደሆነ አድርጎ ነው የሚያሳየን። አንበሳ የአራዊት ንጉስ ተብሎ ይታወቃል።

ስለዚህ ማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ታላቅ ንጉስ አድርጎ ያቀርብልናል።

እርሱ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሰረት ሊመለክ የሚፈልግ ንጉስ ነው። በሰው ሰራሽ ልማዶች መሰረት ሊመለክ አይፈልግም።

በራዕይ 6፡1-2 ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ማሕተም በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው የሚገልጸው፤ ነጩ ፈረስ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት የነበረውን ሐይማኖታዊ አታላይነትን የሮማ መንግሥት በቤተክርስቲያን ላይ ያስነሳውን ስደት ይወክላል፤ ይህም ዘመን በ312 ዓ.ም ነው የተጠናቀቀው።

የሰይጣን ዋነኛ ዓላማው እግዚአብሔርን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ መንገድ እንድናመልክ ማድረግ ነው። በሆነ መንገድ ከመጽሐፍ ቅዱስ መስመር ስንወጣ ሰይጣን በጣም ይደሰታል። 312 ዓ.ም ንጉስ ኮንስታንቲን ከእርሱ በፊት የነበረው ዲዮክሊቲያን የተባለው ንጉስ ያስነሳውን ግፍ የሞላበት ስደት እንዲቆም ያደረገበት ዓመት ነው።

ከ33 ዓ.ም እስከ 100 ዓ.ም ደግሞ ሐዋርያት እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ጽፈው ያስቀመጡበት ጊዜ ነው። 100 ዓ.ም ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት 27ቱን መጻሐፍት መርጦ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሆኑ በአንድ ላይ ጠረዛቸው።

አንበሳው በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ የመጀመሪያው እንስሳ እንደመሆኑ ኢየሱስን እንደ አይሁድ ንጉስም እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነትም ሆኖ ይወክለዋል።

ማቴዎስ የይሁዳ ነገሥታትን ሥርወ መንግስት ተከትሎ በዝርዝር ሲጽፍ መንፈሳዊ እውነት እና አንዳንድ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል መከተል ያልቻሉ ሰዎችም ላይ ትኩረት ያደርጋል።

 

 

ማቴዎስ 1፡1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

“የእከሌ ልጅ” ማለት ከዚያ ቤተሰብ የተወለደ ማለት ነው።

ኢየሱስ የነገስታት ንጉስ ነው። በእውነት ሊመለክ ይፈልጋል።

ዳዊት ከአይሁድ ነገስታት ሁሉ ታላቁ ንጉስ ነው። ስለዚህ የዳዊት ስም መጀመሪያ ላይ ነው የተጠቀሰው።

ከዳዊት በፊት አንድ ሺህ ዓመታት በላይ አስቀድሞ የተወለደው አብራሐም የመጀመሪያውን ታላቅ ንጉስ ፈት ለፊት አግኝቶታል፤ እርሱም መልከ ጼዴቅ ማለትም እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔር አንድ እጅ አፈር ውስጥ እስትንፋሱን እፍ ብሎ ለራሱ የሰው አካል አዘጋጀና ለአብራሐም ተገልጦ አናገረው።

አብራሐምን ካናገረ በኋላ እግዚአብሔር ያንን አካል ትቶ ሄደ። ያ አካልም ወደ አፈር ተመለሰና ከዚያ ወዲያ አልተገኘም።

ስለዚህ መልከ ጼዴቅ እናትም አባትም አልነበሩትም። ሕይወቱ ጅማሬ የለውም፤ ፍጻሜም የለውም። እግዚአብሔር የሥጋ አካል ለራሱ አዘጋጅቶ ለበሰው፤ ከዚያ በኋላ አወለቀው። ይህም ልክ ሰው ልብስ አንስቶ እንደሚለብስና ኋላ ደግሞ እንደሚያወልቅ ነው።

ዕብራውያን 7፡1 የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤

ዕብራውያን 7፡3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።

 

 

ማቴዎስ የነገስታት ዘር የሆኑ የ42 ትውልዶችን ስም ዝርዝር ጽፎልናል። በዚህ የትውልዶች ዝርዝር ውስጥ የነገስታት ስም ነው የተጻፈው፤ እነርሱም ከአብራሐም ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ይደርሳሉ።

ነገር ግን 13 ትውልዶች ሳይጠቀሱ ቀርተዋል ምክንያቱም የሉቃስ ወንጌል በዳዊት እና በዮሴፍ መካከል ተጨማሪ 13 ስሞችን ይጠቅሳል።

ተቺዎች ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት መኖሩን ያሳያል ይላሉ።

ስሕተት አይደለም። ማስጠንቀቂያ ነው።

13 ዓመጽን የሚያመለክት ቁጥር ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ዓመጽን የሚቀጣበት መንገድ ሰዎችን ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ በማስወገድ ነው።

ራዕይ ምዕራፍ 13 ውስጥ ሁለት ክፉ አውሬዎች (ኃይላት) እግዚአብሔር ላይ በዓመጽ ሲነሱ እናያቸዋለን፤ እነርሱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና አሜሪካ ናቸው። እነዚህ ሁለት ኃይላት በአንድነት ዓለም ሁሉ የአውሬውን ምልክት 666 እንዲቀበሉ ያደርጋሉ፤ ይህም ምልክት ትርጉም ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል፣ ኪንጅ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን መከተል ማቆም ነው። ዛሬ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚያምኑ ክርስቲያኖች በጣም ጥቂት ናቸው።

ዮሐንስ 6፡66 የሚገርም ምዕራፍ እና ቁጥር ነው፤ በውስጥ 666 ስላለው የአውሬው ምልክት ምን እንደሆነ ይነግረናል።

ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።

የአውሬው ምልክት ደቀመዛሙርት ኢየሱስን መከተል ትተው ሲመለሱ ማለት ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ዛሬ አስተማማኝ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

የአውሬው ምልክት በዚህ ዘመን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አቃቂር መፈለግ ነው።

 

 

ስለዚህ ስለ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩት ነገር በሙሉ ስለ ኢየሱስ የምትናገሩት ነገር ነው ማለት ነው።

የእግዚአብሔርን ሃሳብ የሚገልጥልን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ማለት የጀመራችሁ ጊዜ ኢየሱስን መተቸታችሁ ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው የሚገልጠው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

 

በተስፋይቱ ምድር ውስጥ የተጀመረው የመጀመሪያው ጦርነት የተካሄደው በነገስታት መካከል ነበር።

ዘፍጥረት 14፡4 አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዝተው ነበር፥ በአሥራ ሦስተኛውም ዓመት ዐመፁ።

ዓመጽ ከ13 ቁጥር ጋር ግንኙነት አለው።

ስለዚህ በማቴዎስ ምዕራፍ 1 ውስጥ ሳይጠቀሱ የታለፉት 13 ትውልዶች እግዚአብሔር ላይ ያመጹ ሰዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል አንድ ሰው ጅማሬው መልካም ነበረ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሕይወቱ መጨረሻ ያለውን እቅድ አልቀበል በማለቱ ፍጻሜው የማያምር ሆነ።

 

 

ስለዚህ ማቴዎስ ምዕራፍ 1 እግዚአብሔር በቃሉ ላይ የሚያምጹ ሰዎችን እንደማይታገስ በግልጽ ይነግረናል።

ብዙ ሰዎች የማቴዎስ ምዕራፍ 1ን የመጀመሪያ ክፍል ትኩረት ሰትተው አያጠኑትም ምክንያቱም ዝም ብሎ የማይጠቅም ረጅም የሰዎች ስም ዝርዝር ስለሚመስላቸው አይስባቸውም።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም ነገር ዋጋ አለው።

ሳይንቲስቶች በሰውነታችን ውስጥ ካለው ዲ.ኤን.ኤ ውስጥ የ5 በመቶውን ብቻ ነው ጥቅሙን የሚያውቁት፤ ስለዚህ ቀሪውን የዲ.ኤን.ኤ. “ኮተት” ይሉታል።

ነገር ግን በቅርብ የተደረገ ጥናት እንደ ገለጠው ቀሪው 95 በመቶ ዲ.ኤን.ኤ. የሚያስፈልገው ዲ.ኤን.ኤ በሕይወት እንዲኖር እና ራሱን ማባዛት እንዲችል ለማድረግ ነው።

በተመሳሳይ መንገድ በጦር ሰራዊት ውስጥ አንድ ወታደር በጦር ግምባር ላይ በርትቶ መዋጋት እንዲችል እቃ በማንቀሳቀስ፣ ማሽኖችን በመጠገን፣ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት በመስጠት፣ እቅድ በማውጣት የሚያግዙ 10 ሰዎች ከበስተኋላው አሉ። ቀሪው ሕዝብ የሰራዊቱ ኃይል ይህ አንድ ወታደር ይመስላቸዋል። ብዙውን ጊዜ ግን አንዱን ወታደር ስለሚያግዙት አስሩ ወሳኝ ሰዎች ምንም ወሬ አንሰማም።

በውትድርና ውስጥ ተዋጊዎቹ በጦር ሜዳ በሚያደርጉት ፍልሚያ ድል እንዲነሱ የሚበቋቸው አሰልቺውን የድጋፍ ሰጪ ሥራ የሚሰሩ ሰዎች ናቸው።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች እንደ አሰልቺ እና የማይጠቅሙ አድርገው የሚቆጥሯቸው ክፍሎች ቢኖሩ፤ እነዚህ ሰዎች የክርስቶስ ልብ እንደ ሌላቸው ያሳያል ምክንያቱም እነዚያን ክፍሎች ሁሉ የጻፋቸው ኢየሱስ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

 

 

ስለዚህ እስቲ 42 ትውልዶች የተጻፉበትን ይህንን ስም ዝርዝር በትኩረት እንመልከት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ስለ ምን እንደሚነግሩን መረዳት የምንችልበት “የንስር ዓይን” ካለን እያንዳንዱ ምዕራፍ አስፈላጊያችን እንደመሆኑ የሚያስተምረንን ትምሕርት መማር እንችላለን።

ይህ የ42 ትውልዶች ዝርዝር እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከአይሁዶች ጋር የነበረው ውል ምን እንደሚመስል ያሳየናል።

42 ወሳኝ ቁጥር ነው።

42 ወራት ከቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ እና ኢየሱስ ወደ አይሁዶች ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት በምድር ላይ የሚሆነው የታላቁ መከራ የጊዜ ርዝመት ነው።

ይህ በስሱ የሚያሳየን ፍንጭ አለ።

42 ትውልዶች በአይሁድ ታሪክ ውስጥ ከአብራሐም እስከ ኢየሱስ ያደርሱናል።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ዘወር ባለበት ዘመን ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እስኪጠናቀቁ ድርስ አይሁዶች ተቆርጠው ይወጣሉ።

ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲጠናቀቅ እግዚአብሔር 42 ወራት በሚፈጀው በታላቁ የመከራ ዘመን ውስጥ ወደ አይሁዶች ይመለስና 144,000ውን አይሁዳውያን ይቤዣቸዋል።

የወንዶች ስም በተጻፈት የ42 ትውልዶች ዝርዝር ውስጥ ለምድነው አራት ሴቶች የተጠቀሱት?

እነዚህ ሴቶች በኢየሱስ የዘር ሃረግ ውስጥ በመጠቀሳቸው ዝነኛ ሊሆኑ ችለዋል።

ትዕማር፣ ራኬብ፣ ሩት፣ እና ቤርሳቤህ።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

እነዚህ ሴቶች ቤተክርስቲያን በ2,000 ዓመታት ታሪኳ ውስጥ የምታልፍባቸውን አራት ደረጃዎች ያመለክታሉ።

 

 

እግዚአብሔር በእነዚህ አራት ሴቶች የተመሰለችውን ቤተክርስቲያንን በመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች ውስጥ እየመራ አሳለፋት፤ እነዚህ አራት ማሕተሞችም ስለ ቤተክርስቲያን ዘመናት ነው የሚናገሩት (ራዕይ 6፡1-7)።

ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 7 ቁጥሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

ከዚያ በኋላ ሞት ፈረስ ላይ ተቀምጦ በሚጋልብበት ጊዜ ታላቁ መከራ ይመጣል (ራዕይ 6፡8)። በዚህ አዲስ የመከራ ሥርዓት ውስጥ (8 አዲስ ሥርዓት ነው) ደም መፋሰስ እና ግፍ በሞላበት ሥርዓት ወቅት እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ይመለሳል።

የመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች እያንዳንዳቸው በሁለት በሁለት ቁጥሮች ነው የተጻፉት፤ ምክንያቱም በያንዳንዱ ማሕተም ውስጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የሚሰራው በሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ወስጥ ነው።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚወክለው በአንበሳ የተመሰለው የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዋርያቱ አማካኝነት ለመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የተሰጠው ቃል ነው።

ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።

ነጭ። ሐይማኖት። በዚህ ክፍል ደጋን ተጠቅሷል ቀስት ግን የለም። ይህ ቀልድ ነው። ሐይማኖታዊ አታላይነት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስትነሳ ሰው እና የሰው ሃሳብ በቤተክርስቲያን ላይ እንዲሰለጥኑ አድርጋለች። በስተመጨረሻም ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ማድረግ ጀመረ።

ይህ ፈረስ እና በላዩ ላይ የተቀመጠው ወዲያ ወዲህ ከሚቅበዘበዙ የአውሮፓ ነገዶች ባሕር ውስጥ የሚነሳውን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ያመለክታሉ።

ዘጸአት 15፡1 በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በፈርኦን እና በሰራዊቱ ውስጥ የነበረው ነፍሰ ገዳይ መንፈስ ነው።

ያ ክፉ መንፈስ እራሱ ፈርኦን ባሕር ውስጥ በሰጠመ ጊዜ እንደ ባሕር በሚናወጡ ሕዝቦች ውስጥ ገብቶ ባቢሎን፣ ፋርስ፣ ግሪክ፣ እና ሮምን ሁሉ እንዳጥለቀለቀ ዳንኤል ተከታትሎ አሳይቷል። ከዚያም አልፎ ወደ ትንሹ ቀንድ ማለትም ወደ ቫቲካን ከተማ ደርሷል። ቫቲካን በምድር ላይ ካሉ መንግስታት ሁሉ ትንሽዋ ናት። ስፋቷ አንድ ኪሎ ሜትር ካሬ ነው ፤ የቫቲካን ፓስፖርት ያላቸው ዜጎችም 150 ሰዎች ብቻ ናቸው። ወደ 650 የሚያህሉ የቫቲካን ሕዝቦች ሌላ ሃገር ውስጥ ስለሚኖሩ ሁለት ፓስፖርት ነው ያላቸው።

ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ራዕይ 6፡4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።

የሮማ ንጉስ ኮንስታንቲን በቤተክርስቲያኖች ላይ የሥላሴ አስተምሕሮ እንዲቀበሉ ጫና ካደረገ በኋላ ለፖፑ ሐይማኖታዊ ስልጣን ሰጠው።

ፖፑ እራሱ በፈጠራቸው አስተምሕሮዎች አማካኝነት ባርቤርያውያን ነገዶችን ሲገዛቸው የካቶሊክ ሐይማኖት ከፖለቲካዊ ኃይል ጋር አንድ በመሆን አውሮፓን ተቆጣጠረ። እነዚህ ነገዶች ግን የሮማ መንግስትን የገለበጡ ነገዶች ነበሩ።

በጨለማው ዘመን ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰዎችን የመግደል ዘመቻ ውስጥ ገባች።

የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ በሬ ተገለተ፤ ይህም በመከራ ውስጥ አገልግሎ ከዚያ በኋላ የሚታረድ እንስሳ ነው። ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ክርስቲያኖች እየተያዙ ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ተከለከለ።

“ሌላ ፈረስ” የተቀመጠበት ግን “ሌላ” አይደለም። ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ እራሱ ነው (ዲያብሎስ) በሁለት ፈረሶች ላይ ተቀምጦ የሚጋልበው፤ እነዚህም ሁለት ፈረሶች የሐይማኖት ማታለል እና ፖለቲካ ናቸው።

 

 

ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

ራዕይ 6፡6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።

“ስንዴ፣ ገብስ፣ እና ዘይት”። እነዚህ ሁሉ ዳቦ ለመጋገር የሚያስፈልጉ ዘሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ እንጀራችን ነው። ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት የሚለውን እውነት በተሃድሶ አመጣው። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ተተርጉሞ በ1604 እና በ1769 ዓ.ም ታርሞ ተጠናቀቀ። የተረጎሙት ምሑራን ፍጹም የተዋጣለት ትርጉም ነው ያዘጋጁት።

ወይን። በመገለጥ የሚመጣ መነቃቃት። የጆን ዌስሊ የቅድስና መገለጥ እና ተከትሎት የመጣው ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመቻ።

ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ የምሑራንን አእምሮ ባረከውና መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል እንዲተረጉሙ አበቃቸው፤ ከዚህም የተነሳ የቅድስና እና የመዳን እውነት ተገልጦ ወንጌሉ ለአሕዛብ ሃገሮች ሊዳረስ ችሏል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰዎችን ስለ ሐይማኖታቸው ገንዘብ ታስከፍላቸው ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል ለንግድ ተጠቀሙበት። የስርየት ወረቀት ይሸጥ ነበር፤ ይህንን ወረቀት የገዛ ሰው ሐጥያቱ ይቅር ይባልለታል ይላሉ። ሰዎችም ከፑርጋቶሪ ለመውጣት ገንዘብ ይከፍላሉ።

ገንዘብ ለማጋበስ የሚደረገውን ሩጫ ፐሮቴስታንቶችም ተከትለውት ሄደዋል። ለዚህም ብለው ሰዎችን በቤተክርስቲያናቸው ሥርዓት አስረው ያስቀምጧቸዋል። ሥላሴ በሚሉት አስተምሕሮ የተነሳ ሥላሴ የሆነው አምላክ ስም ባይኖረውም እንኳ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ግን ተገልጠዋል። ለሶስት አካላት አንድ ስም መስጠት አይቻልም።

የትልቅ ገንዘብ አጋንንታዊ አሰራር ግን ቀስ ብሎ ወደ ቤተክርስቲያን እየገባ ነበር።

የመጀመሪያው ጋላቢ ነው በሶስቱም ፈረሶች ላይ የተቀመጠው። ፈረስ ኃይልን ይወክላል።

 

 

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

አራተኛው እንስሳ አርቆ ማየት የሚችል ንስር ነው።

አሜሪካ ውስጥ ከ1945 – 1965 ዊልያም ብራንሐም የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ሚስጥራት ገለጠ።

(7ቱ ነጎድጓዶች የተናገሩት ነገር፣ 7ኛው ማሕተም፣ እና የኢየሱስ አዲስ ስም አልተገለጡም፤ ምክንያቱም እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም።)

ስለዚህ አሁን ቤተክርስቲያኖች የሚሰናከሉባቸውን ከባድ ጥቅሶች ማብራራት መቻል አለብን። ነገር ግን 7ቱ መለከቶች እና 7ቱ ጽዋዎች ምን እንደሆኑ ማብራራት አንችልም ምክንያቱም የእነዚህ ሚስጥር የሚገለጠው በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ በሁለቱ ነብያት ማለትም በሙሴ እና በኤልያስ ነው።

ሙሽራይቱ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ አትገባም።

 

 

የሐይማኖት አታላይነት የመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲጠቀለሉ አደረገ።

ነጩ ፈረስ በሶስተኛው እና በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመናትም ውስጥ ለ1,200 ዓመታት ያህል ሮም በአውሮፓ ውስጥ ፖለቲካዊ ኃይሏን እያጠናከረች በሄደች ቁጥር ግልቢያውን ቀጠለ። እነዚህ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ብቻ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ርዝመት ወደ 60 በመቶ ያህሉን ፈጅተዋል። ለዚህ ነው በሰማይ ውስጥ ያለው ሁለተኛው እንስሳ ጥጃ የሆነው። ጥጃ ትንሽዬ በሬ ነው። ግልገል ሆኖ ነው የጀመረው ምክንያቱም ከፊቱ በጣም ብዙ የሞት እና የጥፋት ዓመታት ነበሩ፤ በእነዚህ ሁሉ ውስጥ አልፎ ሉተር በ1520 ዓ.ም የክፉውን ኃይል ሰብሮ ተሃድሶ እስካመጣበት ጊዜ ድረስ ሳይጠፋ መቆየት ነበረበት።

ቀጥሎ ደግሞ ቤተክርስቲያን በገንዘብ እና በቁሳቁስ ትርፍ ዓይኖቿ ታውረው መንፈሳዊ ጥሪዋን እስክትረሳ ድረስ ሁለት ሌሎች ዘመናት አለፉ። በዚሁ ዘመን ውስጥ ፖለቲካ እና የሐይማኖት አታላይነት በፈረሳቸው ላይ ተቀምጠው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲጋልቡ ቆዩ።

ነጩ የሐይማኖት አታላይነት፣ ቀዩ የፖለቲካ ኃይል፣ እና ጥቁሩ የገንዘብ ብዛት ጋር የሚሰራው አጋንንታዊ ኃይል በንስሩ እይታ ቢጋለጡም እንኳ (ማለትም በዘመን መጨረሻ ነብይ በዊልያም ብራንሐም ትምሕርት ቢጋለጡም እንኳ) ቤተክርስቲያን ውስጥ መጋለባቸውን አላቆምሙ፤ 7ኛው ቁጥር ላይ መጋለጣቸውን እናነባለን፤ ይህም ቁጥር 7ኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።

“የአራተኛውን እንስሳ ድምጽ ሰማሁ”።

ወንድም ብራንሐም ስብከቶቹን በቴፕ እና በመጻሕፍት ቀድቶ አስቀምጧል።

እርሱም ከ1965 ጀምሮ ከምድር ተሰናበተ፤ ከ1966 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” ውስጥ እየኖርን አለን።

ስብከቶቹ በድምጽ ተቀድተው ስለተቀመጡልን አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምን እንደሚናገር ማየት እንችላለን።

የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምን እንደሚናገር ማየት ከቻልን ንስሮች ነን ማለት ነው።

 

 

ቁጥር 8 ላይ ታላቁ መከራ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ መናፍስት በአንድነት ሆነው እሬሳ የሚመስለውን ሐመር ፈረስ ይሆናሉ፤ እነርሱም በአንድነት ወደ ሰይጣንነት ሲለወጡ ሰይጣን እንደ ሞት ሆኖ ለመጨረሻ ጊዜ እየጋለበ ይንቀሳቀሳል።

ስለዚህ አሁን የምንኖርበት ዘመን የታላቁ መከራ ዋዜማ ነው፤ በዚህም ጊዜ በሎዶቅያውያን የገንዘብ እና የቁሳቁስ ትርፍ የተገዙት የክርስቶስ ተቃዋሚ መናፍስት ከሐይማኖታዊ ስሕተት እና ከፖለቲካዊ ኃይል ጋር ተጣምረው በመስራት በሽተኛ ፈረስ ለመፍጠር እየተሯሯጡ ናቸው።

 

 

በማቴዎስ ምዕራፍ አንድ ውስጥ የተጠቀሱት አራት ሴቶች ቤተክርስቲያንን በተለያዩ ዘመናት ውስጥ ይወክሏታል፤ ከእነዚህ ሴቶች ምን እንማራለን?

ከነዚህ ሴቶች አንዷ እንደ ጋለሞታ ነበረች። ሁለተኛዋ ጋለሞታ ነበረች። ሶስተኛዋ ጻድቅ ሴት ነበረች፤ ነገር ግን አይሁዳዊ አልነበረችም። አራተኛዋ በአደባባይ እርቃኗን ገላዋን ታጠበችና ዝሙት ፈጸመች። ሆኖም ግን አራቱም የመሲሁ ቅድመ አያቶች ሆነዋል።

ሰዎች በመልካም ሥራቸው እንደሚድኑ ሲያስቡ ከእግዚአብሔር መንገድ ይተላለፋሉ።

ማቴዎስ 1፡3 ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡5 ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤

ማቴዎስ 1፡6 እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት [ከቤርሳቤህ] ሰሎሞንን ወለደ፤

ትዕማር። 1ኛ እና 2ኛ የቤተክርስቲያን ዘመን።

ራኬብ። 3ኛ እና 4ኛ የቤተክርስቲያን ዘመን። እነዚህ ደግሞ ታላቂቱ ጋለሞታ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ እንደ ኤልዛቤል ሆና አውሮፓን በሙሉ አስጨንቃ የገዛችበት ዘመናት ናቸው።

“ፖርኖክራሲ”። ይህ የታሪክ ምሑራን ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሰጡዋት ስም ነው ምክንያቱም ከ904 ዓ.ም እስከ 963 ድረስ የነበሩት የካሊክ ጳጳሳት ምግባረ ብልሹ ከመሆናቸው የተነሳ ከጋለሞታዎች ጋር ይማግጡ ነበር።

ጋለሞታዋ ራኬብ እንድትድን የኢያሪኮ ግምብ መፍረስ ነበረበት። ሰው ሰራሽ የሆኑት የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽናዊ ሥርዓቶች መፍረስ አለባቸው፤ ሲፈርሱም በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የታሰሩ ሰዎች ነጻ ወጥተው ይድናሉ።

ራኬብ ጋለሞታ መሆንዋ ቤተክርስቲያን የእርኩሰት ዝቅጠት ውስጥ የገባችበትን ዘመን ቁልጭ አድርጎ ለማሳየት ያመቻል።

ራኬብ ቀይ ገመድ ነበራት፤ እርሱም የኢየሱስን ደም ይወክላል፤ የዚህ ቀይ ገመድ ተምሳሌትነት ሐጥያተኞችን ከጥልቁ ጉድጓድ ጎትቶ እንደሚያወጣ የነፍስ አድን ገመድ ነው።

ነገር ግን አንድ ቁልፍ ነገር እንማራለን። አንድ ሰው ምንም ያህል በሐጥያት የተጨማለቀ ቢሆን እንኳ የኢየሱስ ደም አጥቦ ያነጻዋል። ክርስቶስ ሐጥያተኞችን ሊያድን ነው የመጣው እንጂ ጻድቃንን ፍለጋ አይደለም።

ራዕይ 1፡6 ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ [ለኢየሱስ ክርስቶስ]

ራኬብ ሁለት ሰላዮችን በቤቷ ሸሸገች፤ ደበቀች፤ ይህም ሰዎች ሁሉ አውጥተው ሊጥሉ የሚገልጓቸውን የተገለጡትን ሁለቱን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳንን ይወክላሉ። እነዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ወንድም ብራንሐም ባዘጋጃቸው የስብከት ቴፖች ተገልጠዋል።

ራኬብ እነዚያ ሁለት ሰላዮች የነገሩዋትን አደረገች፤ ከዚህም የተናሳ ዳነች። ከዚያ በኋላ የኢየሱስ የዘር ሃረግ ውስጥ ተቀላቀለች።

የወደፊት ስኬታችን አስተማማኝ መሰረት የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ መታዘዝ ነው።

ሩት። 5ኛ እና 6ኛ የቤተክርስቲያን ዘመናት።

ሩት በቦኤዝ እርሻ ላይ የስንዴ ቃርሚያ በምትለቅምበት ሰዓት ታላቅ ስም አትርፋለች።

5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እውነት መልሶ በማምጣት እና እጹብ ድንቅ የሆነውን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ከ1604 እስከ 1769 ድረስ አዘጋጅቶ በማጠናቀቅ ታላቅ ስም ያገኘ ዘመን ነው።

6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመንም ታላቅ ክብር የነበረው ዘመን ነው ምክንያቱም በዚያ ዘመን ጆን ዌስሊ የቅድስና ተሃድሶ አምጥቷል። ሩት በመልካም ሥነ ምግባሯ ትታወቃለች። ከዚያ በኋላ ሚሽነሪዎች በዓለም ሁሉ ወዳለው የወንጌል እርሻ በመሄድ አሕዛብን በወንጌል በመለወጥ አድነዋል።

ንሰሃ እና ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ መቀበል ብዙ ሐጥያተኞችን ቅዱሳን እንዲሆኑ ለውጧቸዋል።

ሩት ታላቅ ስም ነበራት ግን አይሁዳዊ አልነበረችም። ሩት አይሁዳዊ ለመሆን እምቷን የለወጠች ሞዓባዊ ናት።

 

 

ቤርሳቤህ። 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን።

“የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ዘመን፤ ይህ ማለት ቤተክርስቲያኒቱ የእግዚአብሔር አይደለችም ማለት ነው። ይህ ጨለማ እና እጅግ አደገኛ አታላይ ዘመን ነው።

ሎዶቅያ ማለት የሕዝቡ መብት ማለት ነው። ለምሳሌ በአደባባይ እርቃን ሆኖ ገላ የመታጠብ መብት። ከዚያ በኋላ ከንጉስ ዳዊት ጋር ዝሙት ፈጸመች።

ልክ ዛሬ ወንዶች እና ሴቶች አንድ ላይ እንደሚኖሩት ማለት ነው። የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻዎች። ዝሙት። መፋታት እና እንደገና መጋባት። እንዲህ ይላሉ፡- ምን ችግር አለው?

ሁሉም ሰው የፈለግሁትን የማድረግ መብት አለኝ ይላል።

 

 

ራኬብ፣ ሩት፣ እና ቤርሳቤህ ባህርያቸው ከሚወክሏቸው የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር ይገጣጠማል።

ቤርሳቤህ በስም አልተጠቀሰችም። ዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ስም በሌለው ሥላሴ ተጠምዳለች። ለሶስት አካላት አንድ ስም መስጠት አይቻልም። ስለዚህ ቤተክርስቲያንም ሶስት አካላት በሆነው ባሏ ስም ስለምትጠራ እርሷም ስም ሊኖራት አይችልም። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያኖች የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ስም ያወጣሉ። ለራሳችን ስም ለማውጣት መብት አለን (ብለው ያስባሉ)።

ቤርሳቤህ አራተኛዋ ሴት ናት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን በአራተኛው ማሕተም ውስጥ ያለችበትን ሁኔታ ታመለክታለች።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

አራተኛው እንስሳ ድንቅ የማየት ችሎታ ያለው ንስር ነው።

ቁጥር 7 ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ያመለክታል፤ ይህም እንደ ንስር የማየት ችሎታ ያለው ነብይ ዘመን ሲሆን እርሱም የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያኖች እስኪገፉት ድረስ ሲያገለግል ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንድንከተል አስጠንቅቆናል።

የቤተክርስቲያን ተምሳሌት የሆነችዋ ቤርሳቤህ ትኩረቷን ያደረገችው ውበት እና እርቃን ገላዋን ማሳየት ላይ ነው፤ ልክ እንደ ዛሬዋ ቤተክርስቲያን። የቤተክርስቲያን ሴቶች ገላቸውን አጋልጦ የሚያሳይ የተለያየ ቅድ ያለው ልብስ ለብሰው ይመጣሉ። ገላን የሚያሳዩ ከስስ ጨርቆች የሚሰሩ ልብሶች፣ እጅጌ የሌላቸው ቲሸርቶች፣ አጭር ቀሚሶች እና ጡታቸውን የሚያሳዩ ቀሚሶችን ይለብሳሉ።

ሴቶች መገዛት አለባቸው፤ ዛሬ ግን የበላይነታቸውን ለማሳየት ሱሪ ይለብሳሉ።

1965-0801 በትንቢት የተገለጡ ታሪካዊ ክስተቶች

እነዚህን ወንዶች ልጆች ስናያቸው ልክ እንደ ሴቶች ልጆች ይመስላሉ፣ አለባበሳቸው እነደነሱ ነው፤ ሴቶቹን ደግሞ ተመልከቱ እንደ ወንዶች ለመሆን ሲሞክሩ፤ ትልልቅ ሰዎችን እና ሴቶችን ደግሞ ተመልከቱ በዚህ ጠማማ ዘመን ውስጥ፤ የወሲብ ስሜት ቀስቃሽነት የጣኦት አምልኮ ምልክት ሆኗል። ወንጌል ወደ አንድ ጎን ተገፍቷል፤ በቦታው እርቃን ሆኖ መታየት በሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነግሷል። ኦ እግዚአብሔር ሆይ፣ ምን ዓይነት ሰዓት ነው! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና፤ ራስህን ግለጥልን። በኢየሱስ ስም እንጸልያለን።

 

 

“የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” መሰረታዊ ችግር ሕዝቡ የፈለጉትን ሁሉ ማድረጋቸው ነው። መቸም ዘመኑ የሕዝቡ መብት የሚከበርበት ዘመን ነው። የግብረ ሰዶማውያን መብት። ጽንስ የማስወረድ መብት። ድራም የተባለው የሙዚቃ መሳሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ ባይጠቀስም እንኳ እግዚአብሔርን በድራም ምት ማምለክ።

65-0711 አሳፋሪ ነገር

… የአፍሪካ ጫካ ውስጥ የዱር አራዊትን ለማየት የሄዱ ጎብኚዎች የኤልቪስ ፕሬስሊ፣ የፓት ቡን እና የሮክ ኤንደ ሮል ዘፋኞችን ሙዚቃ ለመስማት ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ሬድዮዎች ይዘው ይሄዳሉ። የሃገሪቱ ነዋሪዎች ደግሞ ሲደንሱ ለማየት ራሳቸውን ሲንጡና ወገባቸውን ሲያውረገርጉ ቆመው ይመለከቱዋቸዋል…

ስለዚህ መንፈስ ነው። ደግሞ መንፈሱ አሜሪካ ውስጥ ብቻ አይደለም፤ ይህ መንፈስ በዓለም ዙርያ ሁሉ ራሱን አሰራጭቷል፤ ከዚያም ወደ አርማጌዶን ጦርነት ያዘምታቸዋል።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ደምበኞች በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ስለሚደረገው ነገር ሁሉ ቸልተኛ መሆናቸው እንዲሁም ስለ እምነታቸው የፈለጉትን ትምሕርት እየጨመሩ መሄዳቸው ወደ ስሕተት ጉድጓድ ውስጥ ምን ያህል ጠልቀው እየወደቁ መሆናቸውን በግልጽ የሚያመላክት ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የስሕተት ትምሕርቶቻቸውን ለመደገፍ የሚጠቀሙት መከራከሪያ ብዙ ሰዎችን ያሞኛል።

ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ የሆነ አክብሮት እና ፍርሃት የላቸውም።

ዳዊት በዚያ ጊዜ እንደ ወታደራዊ መሪ ችግር ያለበት ሰው ነበር። ይህም የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ጥሩ ባልሆነ አመራር ስር መሆኗን ያሳያል። ሰራዊቱ ጦርሜዳ ላይ እየተዋጋ ሳለ መሪያቸው ዳዊት ግን እቤት ተቀምጦ ነበር። ሥራ ፈት አእምሮ የሰይጣን ምሽግ ነው።

ዳዊት ቤርሳቤህ የተባለችዋን ሴት ራቁቷን ሆና አያት። በራዕይ 3፡17 የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን “ራቁቷን” ስለሆነች ተገስጻለች። ዳዊት እና ቤርሳቤህ ማድረግ የፈለጉትን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ግድ አልነበራቸውም። ከዚያ በኋላ ንጹህ የሆነውን ሰው ለመግደል ዝግጅት ተደረገ። ዛሬ በየዓመቱ ጽንስ በማቋረጥ ምክንያት 50 ሚሊዮን ንጹህ ሕጻናት ይገደላሉ። ሕዝቡ የዚህን ወንጀል ክፋት ማየት እንዳይችሉ “ታውረዋል”። ዛሬ በቤተክርስቲያን ሰባኪዎች ዘንድ ምን ያህል ወሲባዊ ቅሌት እየታየ ነው?

የመጀመሪያው ልጅ ሞተ፤ ዳዊት እና ቤርሳቤህም ታላቅ “ሐዘን እና ቁዘማ” ሆነባቸው።

ይህም በ1906 በአዙዛ እስትሪት በሎሳንጀለስ ከተማ የተጀመረውን ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት ያመለክታል፤ ይህ መነቃቃት ከ1917 ጀምሮ በሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽኖች አማካኝነት ሊያደራጁትና ሊቆጣጠሩት ሲሞክሩ ቀስ በቀስ ሞተ። በሥላሴ ማመናቸው አብዛኞቹ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅን እምቢ እንዲሉ አደረጋቸው። የተገለጠውን እውነት መቀበል አቅቷቸው በዚያ ዘመን የነበሩ ቤተክርስቲያኖች ዓይናቸው እያየ ራሺያ ውስጥ በሌኒን ከዚያ በእስታሊን አማካኝነት ኮምዩኒዝም ተነስቶ አደገ። ጴንጤ ቆስጤያዊ ቤተክርስቲያኖች ባያውቁትም እንኳ (“አታውቅም”) ራሺያ በታላቁ መከራ ዘመን በኑክሊየር ኃይል አሜሪካን ለማጥፋት እየተዘጋጀች ነው።

ቤርሳቤህ ቀጥላ የወለደችው ልጅ ሰሎሞን ነው፤ እርሱም እውነተኛው ንጉስ ነው። ይህም ልጆች ለጌታ ምጻት ለመዘጋጀት ይረዳቸው ዘንድ ወደ ሐዋርያዊ አባቶቻቸው የሚመለሱበትን የመጨረሻውን ዘመን ያመላክታል። ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻው ዘመን ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ይችሉ ዘንድ ሊረዳቸው የመጽሐፍ ቅዱን ሚስጥራት ገለጠ። የተደራጁት ቤተክርስቲያኖች ግን እነዚህን የተገለጡ እውነቶች ማየት እንዳይችሉ ታውረው ቀሩ።

ሰሎሞን ታላቅ ንጉስ ነበረ ነገር ግን ውድቀቱ የመጣው በሴቶች እና በገንዘብ ነበር።

ይህ ለዛሬዎቹ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ ነው፤ ምክንያቱም እውቀት የላቸውም፤ ደግሞም ገንዘብ የእግዚአብሔር በረከት ነው ብለው ራሳቸውን ያሞኛሉ።

ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

የቤርሳቤህ ባል ኦርዮን ጻድቅ ሰው ነበረ።

ቤርሳቤህ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ኦርዮን ደግሞ የሕጉ ምሳሌ ነው። ቤርሳቤህ ከሕጉ ጋር የተጋባች ጊዜ ልጅ መውለድ ሕይወትን ማምጣት አልቻለችም። ስለዚህ ከኦርዮን ጋር ተጋብታ በነበረችበት ሰዓት የጸነሰችው ዘር ሞተ።

ከዚያ ኦርዮን ጦርነቱ በኃይል በተጧጧፈበት ግምባር ላይ ተገደለ። ከሐጥያት ጋር በሚደረገው እውነተኛ ጦርነት ውስጥ ሕጉ መሞት አለበት። መልካም ሥራዎች ሊያድኑን አይችሉም። በኢየሱስ ሥራ ብቻ ስናምነት ጸጋ ብቻ ነው ሊያድነን የሚችለው።

ኦርዮን መሞቱ ቤርሳቤህ ከእርሱ ጋር ከነበራት ጋብቻ ነጻ እንድትወጣ አደረጋት። ከሕጉ ነጻ ከወጣች በኋላ ሰሎሞንን ወለደች እርሱም የዳዊት ልጅ ነው።

ሙሽራይቱ ከአለማመን እና ከሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ልማዶች እንዲሁም ከሰው ሰራሽ ሕጎች ነጻ መውጣት ያስፈልጋታል፤ ከዚያ በኋላ ነው የዳዊል ልጅ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጻት መውለድ የምትችለው።

 

 

ቀጥሎ ደግሞ ትዕማርን እናያለን፤ እርሷም አዲስ ሕይወት ለመጀመር ወደ አባቷ ወደ ይሁዳ ተመልሳ ሄደች።

ትዕማር የይሁዳን ልጅ አግብታ ስለነበረ የይሁዳ ልጅ ትባላለች።

በትዕማር የተወከለችው የጥንቷ ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ዕለት ከሰማይ ሲወርድባቸው ከእግዚአብሔር አብ በቀጥታ ከሰማይ የዘላለም ሕይወትን ተቀብላለች።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳንን ተቀበለች፤ እርሱም ቀጥታ በእግዚአብሔር እስትንፋስ የተጻፈ መጽሐፍ ነው።

ሃሳቦቹን ከሰው አልሰሙም ከሰው አልተቀበሉም።

እንደውም ጳውሎስ የሰበከላቸውን መልእክት እንኳ ሳይቀር እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው አረጋግጠዋል።

የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።

ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግመኛ ስለተወለዱ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ ነበር የሚያምኑት።

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እራሱ እንጂ ሌላ አይደለም።

የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያስቀምጥ እርሱ የሕጻኑ አባት ነው።

ማቴዎስ 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።

እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐንስ 4፡24) በባህርዩም ቅዱስ ነው። ስለዚህ “ቅዱስ መንፈስ” እግዚአብሔርን በትክክል የሚገልጽ መጠሪያ ነው።

ይሁዳ ሶስት የማይረቡ ልጆች ሥላሴዎች ነበሩት፤ ሶስታቸውም አዲስ ሕይወት ወደ ምድር አላመጡም፤ በክፋታቸው፣ ለሞተ ወንድማቸው ዘር ለማቆም እምቢ ብለው እግዚአብሔር ላይ በማመጽ ልጆች ሳይወልዱ ቀሩ፤ ወይም ደግሞ ከስንፍናቸውና ከቸልተኝነታቸው የተነሳ ሚስት ሳያገቡ ቀሩ።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ምሳሌ የሆነችው ትዕማር ከነዚህ ሶስት ወንዶች ልጅ አልወለደችም።

ነገር ግን ትልቅ ራዕይ ነበራት።

ከይሁዳ ወንዶች ልጆች ሁለቱ ሞተዋል፤ ሶስተኛው ደግሞ የማግባት ፍላጎት አልነበረውም። ከዚህ የተነሳ የይሁዳ ንጉሳዊ ዘር ሊጠፋ ነበር፤ መሲሁም ላይመጣ ነበር።

ይህንን ለመከላከል ትዕማር እንደ መጥፎ ሴት ሆና ሄደች፤ ራሷን እንደ ጋለሞት እንድትመስል መልኳን ለውጣ ይሁዳን አማለለችው፤ ይህን ያደረገችው የሕይወትን ዘር ከይሁዳ ከራሱ ለማግኘት ብላ ነው።

የራሷን ስም አደጋ ላይ በመጣልና በራሷ ላይ የሞት አደጋ በማምጣት ትዕማር የመሲሁን የዘር ሃረግ ለማዳን ቆርጣ ተነሳች።

ሊመጣ ያለውን መሲህ ዘር እንዳይጠፋ ብላ ትዕማር መንፈሳዊ ጉዳይን ከራሷ ደህንነትም ይልቅ ቅድሚያ ቦታ ሰጥታ ነበር።

ከእግዚአብሔር ከራሱ በመጣው የዘላለም ሕይወት የተሞላችው ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን በአረማዊው የሮማ መንግስት እንደ ክፉ ተቆጥራ ነበር።

በሮማ ግዛት ውስጥ የተፈጠረ ችግር ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ ይሳበብ ነበር። አረማዊ የሆኑት ሮማውያን ክርስቲያኖችን በጭካኔ መሞት እንዳለባቸው አስጸያፊ ነገር ይቆጥሩዋቸው ነበር።

በክርስቲያኖች ላይ ቢያን አስር ጊዜ ስደት ተነስቶባቸዋል፤ አንድ የታሪክ ምሑር እንደሚለው በክርስቲያኖች ላይ ከ64 ዓ.ም እስከ 312 ዓ.ም በተደረጉ ስደቶች 3 ሚሊዮን ያህል ክርስቲያኖች ተገድለዋል። በ64 ዓ.ም በሮም ከተማ ከተነሳው ትልቅ እሳት አደጋ በኋላ ኔሮ ክርስቲያኖችን መግደል ጀመረ።

ነገር ግን የሰማእታት ደም እንደ ማዳበሪያ ሆኖ የእግዚአብሔር ቃል በይስፍራው እንዲባዛ አደረገ።

ትዕማር ከአባቷ ከይሁዳ ሶስት ምልክቶች ጠየቀች።

ቀለበት፣ አምባር፣ እና በትር። በትር ሰው ተደግፎ የሚሄድበት እንጨት ነው።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር አብ ሶስት ነገሮች ጠየቀች።

በመጀመሪያ ሰብዓዊ ስሙን ጠየቀች፤ የእርሱ ሙሽራ ትሆን ዘንድ። እርሱ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ወደ ሞት ቢመራቸውም እንኳ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ለእርሱ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ የመገዛትን መብት ጠየቀች።

የጥንት ክርስቲያኖች ቃሉን ሙሉ ለሙሉ ሲታዘዙ ይደግፋቸው ዘንድ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የቃሉን እና የመንፈሱን ሙሉ ድጋፍ ጠየቁ።

ቀለበቱ የሰርግ ምልክት ነው፤ በዚህም ሙሽራዋ የባሉዋን ስም ትቀበላለች።

ሥላሴ ለቤተክርስቲያን የሰርግ ቀለበት የለውም ምክንያቱም ሥላሴ ሶሰት አካላት ላሉት አምላክ አንድ ስም የለውም። ሶስት ማዕረጎች ብቻ አሉት። “በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ አንዳችም አያውቁም።

አይሁዶች ሙሴን በተከተሉ ጊዜ ከእርሱ ጋር ይተባበሩ ዘንድ በቀይ ባሕር ውስጥ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው እየሰጡ ተጠመቁ።

ሙሴ ለአይሁዶች ሕይወት የሰጠ ስም ነው፤ ይህ ስም ብርቱ ጠላቶቻቸውንና የግብጻውያንን ሰረገሎች ድምጥማጣቸውን አጥፍቷል።

1ኛ ቆሮንቶስ 10፡2 ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤

በኢየሱስ ስም መጠመቅ ለጥንቷ ቤተክርስቲያን የዘላለም ሕይወት ሰጣት፤ ምክንያቱም ይህ ጥምቀት በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ አንዱ እርምጃ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም የዘላለም ሕይወት ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ግብጻውያን በፈርኦን ስም ተከትለው ወደ ቀይ ባሕር ውስጥ ገቡ፤ ፈርኦን የማዕረግ መጠሪያ ነው።

ስለዚህ ሞቱ።

ጥምቀት በሶስት ማዕረጎች ሲደረግ በስም አልተደረገም። የማዕረግ መጠሪያ ወደ ኢየሱስ መምጫ መንገድ አይሆንም ምክንያቱም ኢየሱስ ስም አለው።

ስለዚህ በሁለቱ የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያለፈችዋ ጥንታዊት ቤተክርስቲያን በሥላሴ አላመነችም።

የሥላሴ ትምሕርት በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ነው በቤተክርስቲያን ላይ በግድ የተጫነባት።

በጥምቀት ላይ የሚተቀሙዋቸው አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ የተባሉ ማዕረጎች ቤተክርስቲያንን ወደ ሞት እና ወደ ጨለማው ዘመን ይዘዋት ገቡ።

የሥላሴ ትምሕርትን በቤተክርስቲያን ላይ ለመጫን ተብሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል።

ዛሬ በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ንሰሃ በመግባታቸው የተነሳ ከሲኦል ሊድኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ወደ ታላቁ መከራ ገብተው ሊሞቱ ተሰልፈዋል ምክንያቱም በሶስት ማዕረጎች ነው ሰዎችን የሚያጠምቋቸው።

በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ሥላሴ ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችሉት ሚስጥር መሆኑን ይናገራሉ።

እንደዚህ የሚሉት በዘመን መጨረሻ የመጣውን ነብይ የዊልያም ብራንሐምን ትምሕርት ስለማይቀበሉ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰባተኛው መልአክ (ወይም መልእክት) ሚስጥሩን በሚገልጥበት ጊዜ ይህ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይጠናቀቃል ብሎ ተናግሯል

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

የእግዚአብሔር ሚስጥር ለሰዎች ሁሉ የሚገለጠው ሥላሴን ወደ ጎን ትተው ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር መሆኑን ሲረዱ ነው።

ራዕይ 1፡1 … በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ …

8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።

በሥላሴ እስካመናችሁ ድረስ የእግዚአብሔር ሚስጥር አይጠናቀቅም።

ትዕማር የይሁዳን አምባር መያዝ ፈለገች፤ አምባር በድሮ ጊዜ እስረኞች የሚታሰሩበትን የእጅ ካቴና ያመለክታል። ትዕማር የአባቷ የይሁዳ እሥረኛ መሆን ፈለገች። መሲሁ በይሁዳ የዘር ሐረግ ብቻ እንደሚመጣ አውቃለች።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር አብ እሥረኛ መሆን ፈለገች እንጂ የሆነ የአንድ ቤተክርስቲያን ወይም የራሱን አመለካከት የሚሰብክ የቤተክርስቲያን መሪ እሥረኛ መሆን አልፈለገችም።

ኤፌሶን 3፡1 ስለዚህም አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ የክርስቶስ ኢየሱስ እስር የሆንሁ እኔ ጳውሎስ …

የኢየሱስ እስረኛ መሆን የእግዚአብሔር እስረኛ ያደርግሃል ምክንያቱም አብ ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ ውስጥ ነው የሚኖረው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

አሕዛብን መርዳት የምንችለው ለተገለጠው ለኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እስረኛ ሲሆኑ ነው።

ዊልያም ብራንሐም የመጣው የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ለመግለጥ ነው እንጂ ከእርሱ ንግግር በተወሰዱ ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመተካት አይደለም።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር አብ ሰብዓዊ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ጥርት ባለ መገለጥ አማካኝነት ተረድታለች።

ትዕማር በተጨማሪ የአባቷን በትር ፈልጋለች።

መጽሐፍ ቅዱስ እኛን የሚያጸናን እና የሚደግፈን በትር ነው።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

የራሳችንን ደህንነት መፈለግ ሁለተኛ ጉዳይ ነው። ይህንንም ለእግዚአብሔር መተው አለብን።

ዋነኛውና የመጀመሪያው ጉዳያችን መሆን ያለበት በተገለጠው ቃል ላይ የተመሰረተው የእግዚአብሔር መንግስት እንዲሰፋ ማገዝ ነው።

ዘዳግም 28፡2 የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል።

በረከቶች ቢከተሉንና ቢደርሱብን መጀመሪያም ከኋላችን ነበሩ፤ እኛ አላየናቸውም ትኩረትም አላደረግንባቸውም ማለት ነው።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኞች እግዚአብሔር እራሱ መልካም ነው ብሎ ያሰበውን እንዲያደርግላቸው ሁሉን ለእርሱ ትተው ነበር።

በሙሉ ልባቸው እግዚአብሔርን እያገለገሉ እርሱ በፈቀደው መንገድ እንዲባርካቸው ሁሉን ለእርሱ ይተዉለት ነበር።

ልክ እንደ ትዕማር የጥንቷ ቤተክርስቲያንም መንፈሳዊ ፍላጎቷን ከስጋዊ ፍላጎቷ በላይ ትልቅ ቦታ ሰጥታዋለች።

ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ መጥፎ ወንጀል ሰርተዋል ተብለው ቢከሰሱ እና ቢሞቱ እንኳ ወደሚሞቱበት ቦታ ያለ ምንም ፍርሃት ይሄዱ ነበር።

የሚበሉትንና የሚለብሱትን እንዲሰጣቸው ሙሉ በሙሉ እምነታቸውን እግዚአብሔር ላይ ጥለዋል፤ ትኩረታቸውን ደግሞ ሙሉ በሙሉ እርሱን በማገልገልና የተጻፈውን ቃሉን በመታዘዝ ላይ አድርገዋል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡44 ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤

45 ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።

በዚህም ምክንያት እነዚህ የጥንት ክርስቲያኖች ከዛሬዋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን በብዙ ቀድማ ሄዳለች፤ ዛሬ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖች ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ስላላቸው የገንዘብ ብዛት ማውራት ይወዳሉ።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን አንድ ፍላጎት ብቻ ነበራት፤ እርሱም ሰማያዊውን አባት ለማገልገል ነው። የዚያን ጊዜ ክርስቲያኖች በምድር ላይ የራሳቸውን መንግስት የመገንባት አጀንዳ አልነበራቸውም።

 

 

ማቴዎስ 1፡2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤

ማቴዎስ ከአብራሐም የሚጀምረው ለምንድነው?

ምክንያቱም አብራሐም (መጀመሪያ አብራም የነበረው) ከካራን የመጣ ሰው ሲሆን የመጀመሪያው ዕብራዊ “ነበረ” (ዕብራዊ ማለት “ተሻገረ” ማለት ነው፤ ምክንያቱም አብራሐም ከካራን ተነስቶ ሲሄድ አንድ ማይል ስፋት ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ ከነከብቶቹ እና ከነበጎቹ ተሻግሮ ነው ወደ ተስፋይቱ ምድር መጥቶ የሰፈረው)። ይህም መሻገር ታላቅ ድል በመሆኑ የከነዓን ሕዝብ (በተስፋይቱ ምድር ላይ የነበሩት) አብራሐምን በትኩረት እንዲመለከቱት አድጓቸዋል።

 

 

እኛ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ከሐጥያት ሕይወት ወደ ጽድቅ ሕይወት እንድንሻገር ይጠበቅብናል። ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ መሆኑን ማየት አለባቸው።

ከአብራሐም የአይሁድ ሕዝብ ተወለደ።

እግዚአብሔር አብራሐምን ጠራው፤ በዚህም ምክንያት አይሁዶች የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝቦች ሆኑ።

ኢየሱስ የአይሁድ ንጉስ ተብሎ ነው የተሰቀለው። የአይሁድ ሕዝብ ዋነኛ አስፈላጊነት ኢየሱስ የእነርሱ የወደፊት ንጉስ ሆኖ መወለዱ ነው።

ይህንን የሙሴ ሃውልት ተመልከቱ። ከእግሩ በታች አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው መሰረት አለ።

 

 

የመጀመሪያዎቹ አራት አባቶች (አብራሐም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሴፍ) በፎቶው ላይ በቀይ ቀለም እንደተሰመረው መስመር ባለ አራት ማዕዘን መሰረት ናቸው፤ በእነርሱም ላይ እግዚአብሔር ነብያቱን በመጠቀም የአይሁድን ሕዝብ እንደ አንድ አካል መስርቷል።

ኢየሱስ ከአብራሐም ወዲያ ከ2,000 በኋላ ይወለድና የዚህ አይሁዳዊ አካል ራስ ይሆናል።

አይሁዶች ግን አንቀበልህም አሉት። ከዚህም የተነሳ አይሁዳዊው አካል ራስ የሚሆንለትን አልተቀበለም።

ለዚህ ነው መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን የተቆረጠው። የዮሐንስ አስከሬን የአይሁድ ሕዝብ ራስ ሊሆንለት ከመጣው ከኢየሱስ መለየታቸውን ያመለክታል።

 

 

አይሁዶች ኢየሱስን በገደሉ ጊዜ ከ2,000 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው ሕዝባቸው ከላይ እንደምታዩት ፎቶ ነው የሆነው።

ራስ የሌለው ሃውልት ትክክል አይደለም።

ኢየሱስ ከሙታን በተነሳ ጊዜ ከራሱ ዙርያ ተጠቅልሎ የነበረው መገነዣ ጨርቅ ሰውነቱ ከተጠቀለለበት ጨርቅ ተለይቶ ነበር የተገኘው።

ይህም በሞት አማካኝነት ከአይሁዶች መለየቱን ያመለክታል። ኢየሱስ የአይሁዶች ራስ ነው። እነርሱ ግን ገደሉት።

ዮሐንስ 20፡6 ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ፤ የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥

ዮሐንስ 20፡7 ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።

ይህም ሕያው የሆነው ክርስቶስ አንድ ቀን አይሁዳዊ አካሎቹን ከራሱ ጋር አንድ እንደሚያደርጋቸው ነው። ምክንያቱም ሕያው የሆነው አካሉ ከራሱ ጋር ተጋጥሟል።

ኢየሱስ ይህንን ያከናወነው ከራሱ ትንሳኤ በኋላ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን በማስነሳት ነው። አንድ ቀን በቅርቡ በታላቁ መከራ ውስጥ 144,000 አይሁዳውያንን የራሱ አካል ያደርጋቸዋል።

ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

አይሁዶች በቀራንዮ አንቀበልህም ካሉት በኋላ ኢየሱሰ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ወደ አሕዛብ ዘወር አለ፤ ይህንንም ያደረገው 2,000 ዓመታት በሚፈጁት በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ለራሱ ቤተክርስቲያንን ለማዘጋጀት ነው።

ነገር ግን ቤተክርስቲያንም የምትቆምበት አራት ማዕዘን ያሉት የመሰረት ድንጋይ አስፈልጓት ነበር።

ማቴዎስ፣ ማርቆስመ ሉቃስ፣ እና ዮሐንስ። አራቱ ወንጌሎች።

ዮሐንስ (ንስር)

ሉቃስ (ሰው)

 

 

ማቴዎስ (አንበሳ)

ማርቆስ (ጥጃ)

ከዚያም ኢየሱስ በቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት ውስጥ የቤተክርስቲያን አካሉን ገነባ። የዛሬዎቹ እውነተኛ አማኞች የዚህ አካል አንገት ናቸው። በቅርቡ ኢየሱስ ራስ ለመሆን ይመለሳል።

ከዚያ በኋላ ከሙታን የተነሳችዋ ሙሽራ የኢየሱስ እውነተኛ አካል ትሆናለች፤ ይህ የሚሆነው ግን እውነተኞቹ አማኞች ሙሉ በሙሉ ራስ ለሆነው ለኢየሱስ ከተገዙ ነው።

ኢየሱስ ሃሳቦቹን እና መመሪያዎቹን ፍጹም በሆነው ቃሉ ማለትም በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ይገልጥልናል።

በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ስሕተት እንኳ አለ የሚል ክርስቲያን የሙሽራይቱ አካል መሆን አይችልም።

ሙሽራይቱ ለባሏ ማለትም ለቃሉ ትታዘዛለች።

በዳግም ምጻት ጊዜ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ራስ የሆነውን ኢየሱስን ተቀብላ ሙሉ ትሆናለች።

 

 

ለአይሁድ አማኞችን አካል የሚወክለውን የመሰረት ድንጋዩን እንመልከት (ቀዩን መስመር ማለት ነው)።

ዮሴፍ

(ፍጹምነት)

ያዕቆብ (ጸጋ)

 

 

አብራሐም

(እምነት)

ይስሐቅ (ፍቅር)

አብራሐም ታላቅ እምነት ነበረው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከሙታን መልሶ ያስነሳልኛል ብሎ በማመን ይስሐቅን ለመግደል ተዘጋጅቶ ነበር።

ዘፍጥረት 22፡5 አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን።

አብራሐም ይስሐቅን ለመግደል ቆርጦ ነበር። ነገር ግን ቢገድለውም እንኳ ይስሐቅ ተመልሶ ከሙታን እንደሚነሳ አውቋል። አብራሐም እምነቱ ይህን ያህል ስለነበረ ይስሐቅ ቢሞት እንኳ እግዚአብሔር መልሶ ያስነሳለታል።

አብራሐም በትንሳኤ በማመኑ የእምነት አባት ሆነ።

ከሁሉ በላይ የምንፈራው ጠላታችን ሞት ነው። ነገር ግን ትንሳኤው ከሞት ነጻ ያወጣናል። ስለዚህ የመጨረሻው ድል አድራጊ ትንሳኤ ነው።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል። ስለዚህ አብራሐም ዘሩ (ልጁ) ቢሞት እግዚአብሔር ከሙታን እንደሚያስነሳው አውቋል።

ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤

ይስሐቅ የአብራሐም ዘር ወይም ልጅ ነው።

ነገር ግን የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር ክርስቶስ ነው።

ለዚህ ነው ማቴዎስ ክርስቶስን የአብራሐም ልጅ ያለው።

ኢየሱስ ብቻ ነው ሰዎችን ከሙታን ማስነሳት የሚችለው።

 

 

ይስሐቅ እና ርብቃ ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ አላቸው። ርብቃ አይታው የማታቀውን ሰው ወደደችው፤ ነገር ግን ሳታየው በፊት ስለ እርሱ ከታማኝ ባሪያ ሰምታለች።

እግዚአብሔር ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን እንደ ሰባተኛ መልአክ አድርጎ አንድ መልእክተኛ ላከ እርሱም አሜሪካዊው ዊልያም ብራንሐም ነው፤ የተላከውም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እንዲገልጥ ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ስለዚህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ መስማት ትችላለህ፤ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ትክክለኛ እውነት መሆኑን በማወቅ ልትወደው ትችላለህ።

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ ልባችን ከመውደዳችን የተነሳ አንዳች እንከን የሌለበት ፍጹም መጽሐፍ ቅዱስ አድርገን ነው የምንቀበለው።

ርብቃ ከቤቷ ወደ ይስሐቅ የወሰዳትን ግመል ውሃ አጠጣችው። ወንድም ብራንሐም ከመጽሐፍ ቅዱስ ገልጦ ያሳየንን በትክክል መረዳት እንድንችል ሊመራን የሚችለውን መንፈስ ቅዱስን ነው የምናምነው። ወደ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ተመርተን ልንሄድ የምንችለው መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ብቻ ነው።

ስለ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩት በሙሉ ስለ ኢየሱስ የምትናገሩት ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ቃሉ ነው።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን በማንኛውም መንገድ ከተቸኸው ኢየሱስን መተቸትህ መሆኑን አትርሳው። የምትተቸው ከሆነ አትወደውም ማለት ነው።

ያዕቆብ አታላይ ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርን አግኝቶ ከታገለው በኋላ ግን ተለወጠ። አረማመዱ እንኳ ሳይቀር ተቀየረ።

እግዚአብሔረ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት የሚከብዱ ጥቅሶችን ትርጉም እስኪሰጠን ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር መታገል አለብን። የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብበን በመረዳት ብቻ ነው በዛሬው ዓለም ውስጥ የትጋ እንዳለን ማወቅ እና ለጌታ ምጻት ተዘጋጅተን መጠበቅ የምንችለው።

ያዕቆብን የለወጠው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።

ክርስቶስን የሚወክለው ያዕቆብ ለታላቅየው ለሊያ 7 ዓመታት ሰራ (ይህም ሰባቱን የአይሁድ ዘመናት ይወክላል)። ከዚያ በኋላ ሰባት ዓመታት ለራሐየል ሰራ (ይህ 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት) ስለሚያመለክት የተወከለው በታናሽየው እሕት በራሔል ነው። ይህም እግዚአብሔር አሕዛብ ለሆንነው ሕዝብ ያሳየን ጸጋ ነው።

ዮሴፍ ፍጹም የሆነ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። ዮሴፍ በአባቱ ዘንድ ተወዳጅ በወንድሞቹ ግን የተጠላ ሰው ነበር። ከጠጅ አሳላፊ ጋር በእስር ቤት ተጥሎ ነበር፤ ጠጅ አሳላፊው በሕይወት ኖረ፤ አብሮት የታሰረው ዳቦ ጋጋሪ ግን ተገደለ።

ኢየሱስ እራሱ በመሰረተው የጌታ እራት (ወይም የሕብረት ጊዜ) ከወይን እና ከሕብስት ጋር ነው እራት የተደረገው፤ ሕብስቱንም በሞት የተቆረሰውን የራሱን አካል ለመግለጥ ቆረሰው።

ዮሴፍ በነገሰ ጊዜ ግብጽን አዳነ። ኢየሱስ አማኞቹን አድኗል።

ዮሴፍ ባለፈበት መንገድ ያየው ሁሉ ይሰግድለት ነበር። ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል።

በመሰረት ድንጋዩ አራተኛ ማዕዘን ላይ እንደገና ለውጥ እናያለን፤ ይህም ዮሴፍ በታናሽ ልጁ በኤፍሬም በተተካበት ጊዜ ነው።

ሮቤል የሊያ የበኩር ልጅ ስለነበረ ብኩርናው ድርብ የሆነው ርስት የእርሱ ነበር።

ነገር ግን በሰራው ሐጥያት ምክንያት ብኩርናውን አጣ።

1ኛ ቆሮንቶስ 7፡1 ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው።

አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ካልተጋቡ እርስ በራሳቸው የመነካካት መብት የላቸውም።

ዮሴፍ የራሔል የበኩር ልጅ ነበረ፤ እርሱም ብኩርና ስለተቀበለ ከተስፋይቱ ምድር ውስጥ ሁለት ግዛት ርስት ተደርጎ ተሰጠው፤ ይህም ለሁለቱ ልጆቹ ለምናሴ እና ለኤፍሬም ነው።

ነገር ግን ያዕቆብ እጆቹን አጠላልፎ ስለጫነባቸው ብኩርናው ለታናሽየው ልጅ ለኤፍሬም ተሰጠ።

እግዚአብሔር መጀመሪያ አይሁዶችን የራሱ ሕዝብ አድርጎ መረጣቸው፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ በራንዮ ወደ አሕዛብ ተሻገረ።

 

 

መዳን ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ምስል እግር መሻገሩ የዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ተገልጧል።

ስለዚህ ኤፍሬም ዮሴፍን ተክቶታል።

ኤፍሬም

(ብኩርና)

ያዕቆብ (ጸጋ)

 

 

አብራሐም

(እምነት)

ይስሐቅ (ፍቅር)

ኤፍሬም ግን ኋላ በጣኦት አምልኮ ተጠላልፎ ይወድቃል።

ሆሴዕ 4፡17 ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ተወው።

ስለዚህ የኤፍሬም ነገድ ከእግዚአብሔር የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ወጥቶ ተጣለ።

ዮሴፍ ግን ፍጹም የሆነው የክርስቶስ ጥላ ነበረ።

ስለዚህ ፍጹምነት በመሰረት ድንጋዩ አራተኛ ማዕዘን ላይ በሆነ መንገድ መታየት አለበት።

ነገር ግን ብቸኛው ፍጹምነት የሚገኝበት ሰው ኢየሱስ ነው፤ እርሱም የአይሁድ ንጉስ ሆኖ ነው የሚመጣው።

ስለዚህ የኤፍሬም ቦታ በይሁዳ ተወስዷል ምክንያቱም ይሁዳ ነገስታት የሚመጡበት ነገድ ነው።

የአይሁድ ነገስታት ብዙ ስሕተቶችን ሰርተዋል፤ ነገር ግን በስተመጨረሻ ፍጹም የሆነው ንጉስ ከእነርሱ ተወለደ፤ እርሱም ኢየሱስ ነው።

ከኤፍሬም እና ከሌሎች ነገስታት በተለየ መልኩ ኢየሱስ አንዳችም ስሕተት አይሰራም። ኢየሱስ ፍጹም ነው።

ይሁዳ

(ነገስታት)

ያዕቆብ (ጸጋ)

 

 

አብራሐም

(እምነት)

ይስሐቅ (ፍቅር)

የብሉይ ኪዳን የመሰረት ድንጋይ በዚህ መልክ ተጣለ።

በዚህ የመሰረት ድንጋይ ላይ እግዚአብሔር ነብያቱን በመጠቀም እሥራኤሎችን እየመራ የብሉይ ኪዳንን ሃውልት ወይም የአይሁድ አማኞችን አካል መገንባት ችሏል።

ነብያቱም ስለ መሲሁ የወደፊቱ ንጉስ እርሱ እንደሚሆን ትንቢት ተናገሩ። እርሱም የብሉይ ኪዳን አይሁድ አማኞች ራስ ነው።

ስለዚህ ማቴዎስ በጽሑፉ ውስጥ በአይሁድ ነገስታት ላይ ትኩረት ያደርጋል ምክንያቱም ይህ የዘር ሐረግ በውስጡ ብዙ ስሕተት የሰሩ ሰዎች ቢኖሩበትም እንኳን ፍጹም የሆነውን የነገስታት ንጉስ ይወልዳል።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23