ማርቆስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 13-45፡ ኢየሱስ እንደ ታላቅ አገልጋይ



በሙሉ ልቡ የተሰጠና ያለ እረፍት የሚሰራ አገልጋይ ከሕዝቡ ተለይቶ ወደ ምድረበዳ ሄዶ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻው የሚያሳልፈው ጊዜ ያስፈልገዋል።

First published on the 4th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ማርቆስ ኢየሱስን እንደ ትጉ ባሪያ ነው ያስተዋወቀው።

ባሪያዎች የሚፈልጉት የሚከፈላቸውን ገንዘብ እና የቋሚ ሥራ ዋስትና ነው። የሚሰሩት ሥራ መተዳደሪያቸው ነው። ደሞዝህ ስለ ሥራህ የሚከፈልህ ገንዘብ ነው። የምትሰራው በሥራህ አማካኝነት ለምታገኘው ገንዘብ ብለህ ነው።

ለእግዚአብሔር መስራት ጥሪ ነው።

የምትሰሩት በሥራ አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው።

እግዚአብሔር ሰዎችን የተለያየ ግብ መምታት እንዲችሉ ኃይል ይሰጣቸዋል፤ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ግቡ ሰዎች ለራሳቸው ካሰቡት የተለየ ነው።

ማርቆስ 1፡13 በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት።

የኢየሱስ አገልግሎት ጭር ባለው ምድረ በዳ ውስጥ የ40 ቀን ጾም በመጾም ነው የተጀመረው።

የዱር አራዊት ሊተናኮሉት ይችሉ ነበር።

ለመዘናጋት ጊዜ አልነበረውም፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ነቅቶ መቆየት ነበረበት።

ኢየሱስ ከጾሙ የተነሳ በሥጋ በተዳከመ ጊዜ ሰይጣን ሊፈትነው መጣበት፤ ይህንን ሰዓት ጠብቆ የመጣውም ዓይኖቹን ከእግዚአብሔር ጥሪ ላይ ዞር ለማድረግ ነው።

ኢየሱስ እራሱን ለመከላከል አንዳችም መለኮታዊ ኃይል አልተጠቀመም።

ለቀረበለት ፈተና ሁሉ የሰጠው መልስ “… ተብሎ ተጽፏል” የሚል ነበር።

እግዚአብሔርን ማገልገል ማለት በትክክል ምን እንደሆነ ይህ ያስረዳናል።

ኢየሱስ ምሪት ይቀበል የነበረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ቃል ነው።

ሔዋን ግን ምሪቷን የተቀበለችው ከእግዚአብሔር ቃል የተለየ ከሆነው እውነት ከሚመስል የሚያባብል የአታላይ ንግግር ነው።

እግዚአብሔር እኛን የሚያምነን ቃሉን ብቻ ስንከተል ነው።

ኢዮብ 4፡18 እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤

መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤

እግዚአብሔር ብዙውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደማናውቅ ያውቃል።

በተጨማሪ ደግሞ በሰዎች ተጽእኖ የተነሳ በቀላሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ፈቀቅ ልንል እንችላለን።

ስለዚህ እግዚአብሔር እኛ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ ጸንተን እንድንቆም ብዙ ይታገላል።

40ዎቹ ቀናት ሲጠናቀቁ መላእክት መጡና ኢየሱስን አገለገሉት።

አንዱ በክርስትና ውስጥ ያለው ሰዎች ማየት የማይችሉት ኃይል ይህ ነው። በሕይወታችን ውስጥ በሚገጥሙን ፈተናዎች መካከል በዓይን የማይታዩ ነገር ግን የሚረዱን መላእከት አሉ።

ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ልንሸነፍ አንችልም።

በማንኛውም ሰዓት አንድ ነገር ሲበላሽብን ወይም “አልሳካ ሲለን” እግዚአብሔር ጠልቶናል ማለት አይደለም፤ ሌላ መንገድ ሊያሳየን ነው እንጂ።

እኛ ችግር ወይም አለመሳካት ብለን የምንቆጥረው ነገር ሁሉ በሚያስጨንቅ ነገር ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥርዓት የምንማርበት መንገድ ነው።

ትምሕርት ቤት ውስጥ መጀመሪያ ትምሕርቱን እንማራለን፤ ከዚያ በኋላ ፈተና እንፈተናለን።

በመከራ በምንማርበት በእግዚአብሔር ትምሕርት ቤት ውስጥ ግን በመጀመሪያ በፈተና ውስጥ እናልፋለን፤ ከዚያ በኋላ ትምሕርቱን እንማራለን።

ነገር ግን በመከራችን ሁሉ ውስጥ የመላእክት እርዳታ እናገኛለን። ስለዚህ ተስፋ የምንቆርጥበት ምክንያት የለም።

አንድ በር ሲዘጋ የመልካም እድል መስኮት እኛ ያልጠበቅንበት ቦታ ይከፈትልናል።

ማርቆስ 1፡14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ … ወደ ገሊላ መጣ።

መጥምቁ ዮሐንስ ታላቅ ሰባኪ ነበረ።

ዮሐንስ ታላቅ ሰባኪ ከመሆኑ የተነሳ ከደቀመዛሙርቱ አንዳንዶች የእርሱ አገልግሎት ዓላማ እነርሱን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ሊመራቸው መሆኑን እንኳ አላወቁም።

ብዙ ሰዎች በመጥምቁ ዮሐንስ መንፈሳዊ ብርታት ከመገረማቸው የተነሳ የእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ዋነኛው ማዕከል ዮሐንስ መስሏቸው ነበር።

ስለዚህ ዮሐንስ ከአካባቢው መወገድ ነበረበት።

ከሁሉ ለተሻለው ነገር ጠላቱ መልካም ነገር ነው።

ዮሐንስ እጅግ የተዋጣለት ነብይ ስለነበረ ሰዎች እርሱ ክርስቶስ መስሏቸው ነበር።

ሰዎች ነብይ ሲያዩ በቀላሉ ወደ መለኮት ደረጃ ከፍ ያደርጉታል።

ዮሐንስ ወህኒ ቤት በገባ ጊዜ ብቻ ነው ሰዎች ዓይናቸውን ከእርሱ ላይ አንስተው ኢየሱስ ላይ ትኩረት ማድረግ የቻሉት።

ነብይ የሚላከው የኢየሱስን መንገድ ለመጥረግ ነው። ሰዎች ግን በቀላሉ በነብዩ ተማርከው ዮሐንስ የሚሰብከውን መሲሁን ግን ይረሱታል።

ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔርን ቃል ሊገልጥ መጣ፤ ሰዎች ግን በቀላሉ የእርሱን ንግግሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ ያደርጋሉ።

ይህ የሰዎች መሰረታዊ ድክመት ነው።

ዮሐንስ 5፡35 እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፥ እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ።

የዮሐንስ አገልግሎት እጅግ በጣም ደማቅ ስለነበረ ከዮሐንስ ደቀመዛሙርት አንዳንዶች ከዮሐንስ ይልቅ የሚደምቀውን ብርሃን ኢየሱስን ማየት እስከማይችሉ ድረስ ዓይናቸው ታውሮ ነበር።

ዮሐንስ ይህንን ጉዳይ በሚገባ ገልጦ ተናግሯል።

ዮሐንስ 3፡30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።

ይህ ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ የሚጠቅም ምክር ነው።

ለእኔነት መሞት አለብን። የራስ ፈቃድን በሙሉ ከሕይወታችን ማስወገድ እና በመንፈስ ቅዱስ መመላት ያስፈልገናል።

የዛኔ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ በመስራት ፈቃዱን መፈጸም ይችላል።

ማርቆስ 1፡15 ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ የሚጠቅም ቁልፍ ሃሳብ፡-

ጊዜው አሁን ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በደጅ ናት።

የቤተክርስቲያን መንግሥት አላልንም። ዲኖሚኔሽናዊ ፕሮግራምም አይደለም። የሰባኪ የግል ፍላጎትም አይደለም። የእግዚአብሔር መንግሥት ነው እንጂ።

ዛሬ እግዚአብሔር እንድንጋደል የሚፈልገው ጥንት ቅዱሳን ለተቀበሏት እምነት ነው።

ይሁዳ 1፡3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ዘመን ወደነበረው እምነት መመለስ አለብን።

ልክ እንደ አዲስ ኪዳን አማኞች መሆን አለብን።

 

 

ኢየሱስ የተጠመቀው በቤተራባ ከተማ አጠገብ በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ነው።

ኢየሱስ ከመከራው ወይም በምድረ በዳ ከተፈተነው ፈተና በኋላ ወደ ሰሜን ራቅ ብሎ ከገሊላ ባሕር አካባቢ ነበር የሄደው (የገሊላ አካባቢ ካርታው ውስጥ በአረንጓዴ ቀለም የተቀባው ሥፍራ ነው)።

ይህም አካላዊ ብርታቱን ያሳያል። እሥራኤልን ከጫፍ እስከ ጫፍ በእግሩ አቋርጧል።

ማርቆስ ኢየሱስን እንደ ታታሪ አገልጋይ ነው የሚያስተዋውቀን። ስንፍና በእርሱ ዘንድ ከቶ አይታወቅም። ሁልጊዜ በውስጡ በሚኖረው በእግዚአብሔር መንፈስ እየተነዳ ነው የሚንቀሳቀሰው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

“ወዲያው”። አንዲት ደቂቃ እንኳ አያባክንም።

“መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው”። የሚቆጣጠረው እግዚአብሔር ነው።

ከውጭ ያለው ሰብዓዊው ሰው ሙሉ በሙሉ በውስጡ ለሚኖረው መለኮታዊ መንፈስ እየታዘዘ ነው የሚመላለሰው።

ማርቆስ 1፡12 ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።

የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ ሰው እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠረው መፍቀድ አለበት።

እግዚአብሔርን ማገልገል ከፈለግን ትጋትን እና ጠንክሮ መስራትን መውደድ አለብን።

ከዚያ በተጨማሪ በመንገዳችን ላይ የሚገጥሙንን መከራዎች እና ፈተናዎች የምንቋቋምበት መንፈሳዊ ጥንካሬ ያስፈልገናል።

ማርቆስ 1፡16 በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።

“ሲያልፍ”። ማርቆስ በሥራና በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ሰውን እያሳየን ነው።

ኢየሱስ ተግተው የሚሰሩ ሰዎችን ይፈልጋል። ስምኦን እና እንድሪያስ መረባቸውን ባሕር ውስጥ በመጣል በሥራ ተጠምደው ነበር። ኢየሱስ ከሥራ እረፍት ወጥተው እየተዝናኑ የነበሩ ሰዎችን አይደለም የፈለገው።

ማርቆስ 1፡17 ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

ኢየሱስ ተከተሉኝ አላቸው።

ሰዎችን አጥማጅ የምትሆኑበት ብቸኛው መንገድ የኢየሱስን ምሪት በመከተል ነው።

ማርቆስ 1፡18 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

ቁልፉ ቃል “ወዲያውም” የሚለው ነው።

ጴጥሮስ እና እንድሪያስ በፍጥነት እና ያለማመንታት ወደ ሥራ የሚገቡ ዓይነት ሰዎች ናቸው።

ለሥራ በተጠሩ ጊዜ ስለ ደሞዝ መደራደር ውስጥ አልገቡም። ለራሳቸው ገንዘብ ማትረፍ ዋነኛው ዓላማቸው አልነበረም።

እግዚአብሔር በጠራቸው ጊዜ ያለምንም ክርክር ተከተሉት።

እግዚአብሔርን የማገልገል መሰረቱ እርሱን ማመን ነው።

ሮቤል በፈጸመው ነውር የተነሳ ብኩርናውን አጣ።

የልጅ ልጆቹ ከበጎቻቸው መካከል ተቀምጠው ለረጅም ጊዜ ልባቸውን ይመረምራሉ። በጣም ብልጣ ማመካኛ አዘጋጅተው ራሳቸውን አገለሉ፤ ውጊያውን ደግሞ ለሌሎች ትተው ሄዱ።

መሳፍንት 5፡16 መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት

በበጎች ጕረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?

በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ።

ኢየሱስ የፈለገው እንዲህ ዓይነት ደቀመዛሙርት አይደለም።

ማርቆስ 1፡19 ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።

እነዚህ ደግሞ ሌሎች ትጉህ ሰራተኞች ናቸው። መረቦች ጥገና ያስፈልጋቸዋል።

ዓሳ ከማጥመድ ሥራ ውስጥ ምንም የማያዝናናው ሥራ መረብ ጥገና ነው።

ሆኖም ይህ ሥራ ሃላፊነትን የሚቀበሉ ሰዎች መሆናቸውን ያሳያል። መረብ መጠገን በእጅ የሚሰራ አሰልቺ ሥራ ነው፤ ነገር ግን ቀጣዩ ዓሳ የማጥመድ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የግድ መሰራት አለበት። መረቡ የተቀደደበት ቦታ ዓሳዎች ሾልከው እንዲያመልጡ ያደርጋል። እነዚህ ሰዎች ጠንቃቃ እና በሥራ ላይ ታማኝ ናቸው። ይህም ለአገልጋይነት አስፈላጊ ባሕርይ ነው።

ማርቆስ 1፡20 ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።

“ወዲያውም”። እነዚህ ሰዎች ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ፈጣኖች ናቸው።

የእግዚአብሔርን ጥሪ ከቤተሰባቸው ኑሮ የበለጠ ቦታ ሰጥተውታል። በቤተሰባቸው ውስጥ በሚሰሩት ንግድ አባታቸው የገቢ ዋስትናቸው ነበረ። እነርሱ ግን ገንዘብ ማትረፍ የሚችሉበትን ንግድ ትተው ሄዱ።

የተቀጠሩት ሰራተኞች ግን ከእነርሱ አባት ጋር ቀሩ ምክንያቱም ትኩረታቸው ደሞዛቸው ላይ ነው።

እግዚአብሔርን የምናገለግለው ለገንዘብ ብለን እንዳልሆነ ማርቆስ በግልጽ ይነግረናል።

እነዚህ አራት ሰዎች ብዙ ገንዘብ ሊያገኙ የሚችሉበትን ንግድ ነው ትተው የሄዱት።

ዓሳ አጥማጅነት ሙያቸውም የገቢ ምንጫቸውም ነበር። ነገር ግን ከሚያውቁት ብቸኛ ሙያቸው ተለይተው ሄዱ።

እኛ ግን ኢየሱስን ለመከተል የገቢ ምንጫችንን ትተን ለመሄድ ዝግጁ ነን?

ኢዮብ ስኬታማ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሚያስብሉ መስፈርቶችን በጌታ ፊት አስቀምጦ ተወ።

ኢዮብ 13፡15 እነሆ፥ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤

አገልጋይ ወይም ባሪያ ጌታው ያዘዘውን ብቻ ይከተላል እንጂ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ጥያቄ አይጠይቅም።

ማርቆስ 1፡21 ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።

“ወዲያውም” የሚለው ቃል አሁንም ተጠቅሷል።

ኢየሱስ አንዴም እንኳ አያመነታም። ሁልጊዜ መስራት ያለበትን ያውቅ ስለነበረ ፈጽሞ ጊዜ አያባክንም።

ማርቆስ 1፡22 እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።

ጻፎች የተለያዩ አመለካከቶችን የመሰንዘር ዝንባሌ አላቸው።

ብዙ ባጠኑ ቁጥር ብዙ አስተያየት የመስጠት ችሎታ አዳብረዋል።

የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ግን በጉም በድንግዝግዝ ውስጥ ጥላቸውን ማሳደድ ብቻ ነው።

“ይህ ሊሆን ይችላል ወይም ያ ሊሆን ይችላል” የሚለው መላ ምታቸው ሰዎችን ግራ ከማጋባት በስተቀር ምንም አልጠቀማቸውም።

ኢየሱስ ግን ንግግሩ ቀጥተኛ ነው።

እያንዳንዱ ቃሉ ግልጽ ትርጉም አለው። ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ሁሉም ሰው እነዚያ ቃላት ምን ማለት እንደሆኑ በእርግጠኝነት አውቀዋል።

ማርቆስ 1፡23 በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ፤

አንድ እርኩስ መንፈስ ድምጹን አውጥቶ ተናገረና “እባክህ አታጥፋን” አለ።

ማርቆስ 1፡24 እርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ።

ዘፍጥረት ውስጥ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፡- “ሰውን እንፍጠር”።

እንፍጠር የሚለው ቃል ለምን የግድ ሦስት መንፈሶችን ይገልጣል እንላለን?

ሰውን በመፍጠር ውስጥ ሶስት መንፈሶች ወይም ሶስት አካላት ተሳትፈውበት ከሆነ ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈው እንግዳ ሁኔታ ጋር እንፋጠጣለን።

 

 

በሰማይ የሚኖሩ ሦስት ሰዎች አንድ ወንድ እና አንዲት ሴትን ይፈጥራሉ፤ ከዚያ “በመልካችን” ፈጠርን ይላሉ።

ይህ ሃሳብ አንድ ከባድ ችግር አለበት።

መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ ስም አልተሰጠውም።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር አብ አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም። ስሙ በእንግሊዝኛ ፊደላት JHWH ወይም JHVH ሲሆን ምን ተብሎ እንደሚነበብ ማንም በትክክል አያውቅም። ስለዚህ ያህዌ የሚለው ስም በእነዚህ ፊደሎች ላይ አናባቢ በመጨመር ነው የተፈጠረው፤ ስለዚህ የእርሱ ስም አይደለም። ስለዚህ አብ ስም የለውም።

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ብሎ አይናገርም። የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ የኖረበት ሰው ነው። ስለዚህ ኢየሱስ የሚባለው ስም የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ነው።

ማርቆስ 1፡25 ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።

26 ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ።

ሰውየው እርኩስ መንፈስ ለቆት ሲወጣ በጣም ተሰቃይቷል። አጋንንት በጣም አደገኞች ናቸው።

ይህ ጋኔን በሐይማኖታዊ ስብሰባ ውስጥ ነው የተገኘው።

ቤተክርስቲያኖችስ ውስጥ ስንት አጋንንት ሾልከው ገብተዋል።

ማርቆስ 1፡27 ሁሉም፦ ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው? ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ ያውቃል አጋንንትም ይታዘዙለታል።

ማርቆስ 1፡28 ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ።

መለኮታዊ ኃይል የሚገለጥበት አገልግሎት ወዲያው ትኩረት ይስባል።

ማርቆስ 1፡29 ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።

“ወዲያውም”። አሁንም ጊዜ ማባከን የሚባል ነገር የለም።

ስምኦን ኋላ ጴጥሮስ የሚል ስም ተሰጠው።

እኛ በደምብ የምናውቀው ኋላ በተሰጠው ስሙ ነው።

ማርቆስ 3፡16 ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤

የካቶሊክ ጳጳሳት ብዙውን ጊዜ አዲስ የክርስትና ስም ይቀበላሉ።

ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበር ይላሉ። ነገር ግን ጴጥሮስ ኋላ የተሰጠው ስሙ እንጂ የመጀመሪያው ስሙ አይደለም።

የሮማ ጳጳስ ከ400 ዓ.ም በፊት ፖፕ ተብሎ ይጠራ እንደነበረ የሚያስረዳ አንዳችም ማስረጃ አላገኘሁም። ስለዚህ ጴጥሮስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን ፖፕ የሚባል ማዕረግ ያለው አገልጋይ አይታወቅም።

ፖፕ ሚስት ማግባት አይፈቀድለትም። ጴጥሮስ ግን ሚስት ነበረው።

ጴጥሮስ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጠመቀ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)። የካቶሊክ ጳጳሳት ግን በኢየሱስ ስም አያጠምቁም።

ስለዚህ ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበረ ማለት ስሕተት ነው።

በሮም ለነበሩት ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ ውስጥ ጳውሎስ 27 ሰዎችን በስም ጠቅሶ ሰላምታ ያቀርባል፤ ነገር ግን ጴጥሮስን አይጠቅሰውም። ስለዚህ ጴጥሮስ ሮም ውስጥ አልነበረም።

የሐዋርያት ሥራ ውስት ሉቃስ ጳውሎስን እየተከተለ ጳውሎስ ሮም ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኖ እስከሚታሰርና እስከሚገደል ድረስ አብሮት ይዞራል። አሁንም ጴጥሮስ አልተጠቀሰም።

ፖፑ በተጨማሪ ፖንቲፍ ተብሎም ይጠራል፤ ፖንቲፍ ተብሎ መጠራቱ እርሱን የባቢሎናውያን ሚስጥር ሊቀካሕናት ያደርገዋል።

ጴጥሮስ በዚያ ማዕረግ ተጠርቶ አያውቅም።

ጴጥሮስ ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች መልእክት ጻፈ። ለአንድ ግለሰብ መሪ አልጻፈም።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

ጴጥሮስ እራሱ ሽማግሌ ሆኖ ለሽማግሌዎች ጻፈ፣ በዚህ እርሱ ከእነርሱ እንደማይበልጥ አሳይቷል። እራሱን ሐዋርያ ብሎ በመጥራት ከሽማግሌዎች የበላይ ነኝ ለማለት እንኳ አልሞከረም።

ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት እንድትመራ ነው የፈለገው።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

ሽማግሌዎች ናቸው መንጋውን በእግዚአብሔር ቃል መመገብ ያለባቸው እንጂ ፓስተሩ ወይም ፖፕ አይደለም።

ደግሞ “ለመጥፎ ረብ” ብለውም አይደለም።

ነገር ግን ቫቲካን በምድር ላይ አንደኛ ሃብታም ድርጅት ናት።

ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም የተቻላቸውን ያህል ሃብታም ለመሆን ጥረት እያደረጉ ናቸው።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤

የትኛውም ሰው ቢሆን የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አይችልም።

ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ ሦስቱ ዋነኞቹ ደቀመዛሙርት ናቸው። እንድሪያስ የጴጥሮስ ወንድም ነው።

ማርቆስ 1፡30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።

ጴጥሮስ ሚስት ነበረችው። ይህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መጥቀስ ያስፈለገው ለምንድነው?

ማርቆስ ኢየሱስን ታላቅ አገልጋይ አድርጎ ነው የሚያሳየን። ስለዚህ ክርስቲያኖችም እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል እንዳለባቸው ማወቅ ይፈልጋሉ።

አረማዊው የሮማ መንግስት ሲፈራርስ የሮማ አረማዊነት መንፈስ ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገባና ቤተክርስቲያኒቱ ሮምን በተቆጣጠሩት ባርቤሪያውያን ነገዶች ላይ በስልጣን እንድትነሳ አስቻላት።

አረማውያኑ ፔትር ሮማ በሚባል ታላቅ አስተማሪ አለ የሚል እምነት ነበራቸው።

ይህም ሰው አንድ ቀን መጥቶ የአሕዛብ አማልክትን ሚስጥር ይገልጥልናል ብለው ይጠባበቁ ነበር።

ፔትር ማለት ተርጓሚ ነው። ሮማ ደግሞ ዝነኛ ማለት ነው።

ስለዚህ ጴጥሮስ የሮም ጳጳስ ወይም ፖፕ ነው በማለት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን “የሮማው ጴጥሮስ” “ፔትር ሮማ” ነው ልትል ትችላለች። ባርቤሪያኖችም ተገርመው የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አመኑ። በተለይም ደግሞ የሮም ጳጳሳት የጴጥሮስ ተተኪ ነን ሲሉ ሙሉ በሙሉ ተቀበሉዋቸው።

አውሬው ሰዎች አንድ ከፍ ያለ ሰውን እንደ እግዚአብሔር እንዲያመልኩ የሚያደርግ መንፈስ ነው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ ፖፑ በተጨማሪ አውሬው ተብሎ ይጠራል።

 

 

የካቶሊክ ጳጳሳት ወደ ኋላ ሲቆጠሩ እስከ ጴጥሮስ ይደርሳሉ ማለት ከመጀመሪያውም ጀምሮ “ፖፕ” ነበረ ማለት ነው ይላሉ።

ፖፑ ይሞታል፤ ስለዚህ “የለም”።

“ነገር ግን እንዳለ ሲየዩ”። በካርዲናሎች መማክርት ጉባኤ አማካኝነት አዲስ ፖፕ ይመረጣል።

ራዕይ 17፡8 … አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ

ይህ የካቶሊክ ጳጳሳት የሥልጣን መተካካትን ያሳያል። በዓለም ላይ ከነገሱ ሥርወ መንግስታት በዘመን ርዝመቱ አንደኛ ነው።

ስለዚህ ማርቆስ ጴጥሮስ ሚስት ያገባ ሰው መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ይነግረናል፤ ይህም የካቶሊክ ቄሶች ሚስት አለማግባታቸው ስሕተት መሆኑን ያሳያል።

1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡1 መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤

ይህ አደገኛ አጋንንታዊ ትምሕርት ነው።

1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2 በውሸተኞች ግብዝነት … በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፤

መጽሐፍ ቅዱስን ፊት ለፊት እየተቃረኑ እንኳ መሳሳታቸውን አያምኑም።

1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡3 መጋባትን ይከለክላሉ፥

ለጳጳሳት እና ለካሕናት ወይም ለቄሶች ሚስት ማግባት እንደማይፈቀድላቸው መንገር የአጋንንት ትምሕርት ነው። ሆኖም ግን ይህ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ያገኘ ትምሕርት ነው።

በዚህም ትምሕርታቸው እግዚአብሔርን ያገለገሉ ይመስላቸዋል፤ ግን ይህ ትምሕርት የመጣው ከሰይጣን ነው።

ይህም አጋንንት ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው ለመግባታቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው። በጣም የሚያስፈራ እውነት።

ልክ አይሁዶች በምኩራቦቻቸው ውስጥ አጋንንት እንደሚቀመጥ ማለት ነው።

እስቲ ኢየሱስ የጴጥሮስን አማች ወደ ፈወሰበት ትዕይንት እንመለስ።

ማርቆስ 1፡31 ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።

ኢየሱስ የጴጥሮስን አማች በፈወሰ ጊዜ ሴትየዋ ወዲያው ተነስታ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱ የሚበላና የሚጠጣ ነገር ማዘጋጀት ጀመረች።

ኢየሱስ እራሱ የማይደክም የማይታክት ሰራተኛ ነበረ።

ደግሞም ሌሎች እርሱን እና ሌሎችንም እንዲያገለግሉ የሚያነቃቃ አርአያ ሆኖላቸዋል። ሰዎች ወደ ኢየሱስ በመጡ ቁጥር ወዲያው ልባቸው ለሌሎች የሚጠቅም ነገር በማድረግ ፍላጎት ይሞላል። በሆነ መንገድ ሰዎችን ማገልገል ይፈልጋሉ።

ኢየሱስ ታላቁ አገልጋይ በመልካም ምሳሌነቱ ሌሎችንም ለአገልግሎት አነሳስቷል።

ማርቆስ 1፡32 ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

ሕዝቡ መሰብሰብ ጀመሩ። ኢየሱስ ሥራ ላይ ሲውል የሥራ ሰዓት ፀሃይ በመጥለቋ አያበቃም። ሲመሽ የከተማው ሕዝብ በሙሉ በጴጥሮስ ቤት ደጅ ላይ ተሰበሰቡ። ዋናው ሥራ የሚጀምረውም የዛኔ ነው።

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ቤተክርስቲያንን ከይሁዲነት ውስጥ አውጥቶ ለራሱ ይለያት ዘንድ ሊሞትላት በመጣበት ወቅት በአይሁዳውያን መካከል የአጋንንት እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ነበረ።

ስለዚህ ኢየሱስ ሙሽራይቱን ከቤተክርስቲያን መካከል አውጥቶ ሊወስዳት ዳግም በሚመለስበት ጊዜም ተመሳሳይ ነገር በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እንደሚሆን ማወቅ እንችላለን።

ማርቆስ 1፡33 ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር።

ኢየሱስ የነበረበት የሥራ ጫና ብዛት እና እርሱም ያን ሁሉ የከተማ ሕዝብ ሳይደክም በማገልገል ያሳየው ብርታት እጅግ አስደናቂ ነው።

የከተማው ሕዝብ ሁሉ የእርሱን እርዳታ በፈለገበት ሰዓት ሳይታክት ማገልገሉን ለመቀጠል የሚያስፈልገው አካላዊ ብርታት ብቻ አስደናቂ ነው።

ሰዓቱ በጣም እየመሸ ቢሄድም እንኳ እርሱ ግን ምንም የድካም ምልክት አላሳየም።

ሕዝቡ ኢየሱስ ተቀምጦ በነበረበት ቤት በር ላይ ተሰበሰቡ።

ይህም በጣም ተገቢ ነው ምክንያቱም እርሱ የሰማይ ደጅ ነው።

ነገር ግን የሰዎች ሁሉ ጎልቶ የሚታየው ትልቁ ድክመታችን ለአካላዊ እና ለሥጋዊ ችግራችን መፍትሄ ለመፈለግ ቅድሚያ መስጠታችን ነው።

ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መንፈሳዊ ነገሮችን የመማር ፍላጎታችን ዝቅተኛ ነው።

ውስጣችን ቢፈተሽ ፍላጎታችን ቀዳሚው ምርጫችን ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ ሃብት፣ እና ፈውስ እንጂ ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚገኘውን ጥበብ እና ማስተዋል አይደለም የምንፈልገው።

ማርቆስ 1፡34 በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።

ኢየሱስ በአጋንንት እና በበሽታዎች ላይ ታላቅ ኃይል ነበረው።

እንደ ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን የመሳሰሉ የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን ይክዱታል፤ ይቃወሙታል። እርሱ ማን እንደሆነም አላወቁም።

አጋንንት ግን እርሱ ማን መሆኑን በትክክል አውቀዋል።

ኢየሱስ አጋንንት ስለ እርሱ እንዲያወሩ አልፈለገም።

በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም ይሳደባሉ።

ሁልጊዜ በኢየሱስ ስም ይራገማሉ።

እነርሱ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ እና ስሙ ማን እንደሆነ ያውቃሉ።

የቤተክርስቲያን መሪዎች በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ይናገራሉ።

ነገር ግን ስሙ ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።

በሥላሴ ውስጥ ላሉት ሦስት አካላት አንድ ስም ማምጣት አይችሉም።

 

 

ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች የእግዚአብሔርን ስም አያውቁም።

ማንም ሰው አጋንንትን በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ አይገስጽም ምክንያቱም አጋንንት ይህ የእግዚአብሔር ስም አለመሆኑን ያውቃሉ።

ስለዚህ ዛሬም ታሪክ እራሱን ይደግማል። አጋንንት ኢየሱስ የሚለው ስም የእግዚአብሔር ስም መሆኑን ያውቃሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ግን የእግዚአብሔር ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።

ባለማወቅ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የተባሉት ሦስት ማዕረጎች ስም ናቸው ይላሉ።

ማርቆስ 1፡35 ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።

ከተማይቱን ሁሉ ማስተናገድ በጣም ብዙ ሰዓት ሳይፈጅ አይቀርም።

የመጨረሻው በሽተኛ ከተፈወሰ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ደክሟቸው እንቅልፋቸውን ተኙ።

ኢየሱስ ግን ጥቂት ሰዓት ብቻ እንቅልፍ ከተኛ በኋላ በሌሊት ተነስቶ ለብቻው ሊጸልይ ወደ ምድረ በዳ መሄድ ችሏል። ብርታቱ በጣም አስገራሚ ነው።

ከእርሱ እኩል ለመንቀሳቀስ መሞከር መቸም ለደቀመዛሙርቱ በጣም አድካሚ ሳይሆንባቸው አልቀረም።

ከተወሰነ ሰዓት በኋላ ደቀመዛሙርቱ ከእንቅልፍ ነቅተው እርሱ የሄደበትን መንገድ ተከትለው ወደ ምድረ በዳ ወጡ።

የጌታን መንገድ ተከትሎ መሄድ፤ ይህ ትልቅ ትምሕርት ነው።

ማርቆስ 1፡36 ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት፥

ደቀመዛሙርቱ ነገሮችን በተለየ እይታ ማየት አስፈልጓቸው ነበር።

ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

እግዚአብሔርን ማገልገል ከፈለጋችሁ ነገሮችን እርሱ በሚያይበት መንገድ ለማየት መለማመድ አለባችሁ።

ሌሎች ሰዎችን መኮረጅ የለባችሁም።

ሌሎችን ቤተክርስቲያኖች መኮረጅ የለባችሁም።

እግዚአብሔር ነገሮች እንዴት እንዲደረጉ እንደሚፈልግ መጽሐፍ ቅዱስን መርምረን ማጥናት አለብን።

ደግሞም እግዚአብሔር ነገሮችን እኛ ማድረግ ከምንፈልገው በተለየ መንገድ ማድረግ እንደሚፈልግ ሁልጊዜ ማስታወስ አለብን።

ማርቆስ 1፡37 ባገኙትም ጊዜ፦ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት።

ደቀመዛሙርቱ በጣም ብዙ ሕዝብ በኢየሱስ አገልግሎት ምክንያት በመሰብሰቡ ኢየሱስ የሚደሰት መስሏቸዋል።

እርሱ ግን ይህ የሕዝብ ብዛት ነው ብቸኝነትን እንዲፈልግ ያደረገው።

ይህን የሰዎች ችግር ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።

ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ሲያገኙት ያወቁትን ሊነግሩት ፈለጉ።

(እርሱ ቀድሞ ያላወቀውን ነገር ያወቁ ይመስል።)

ነገር ግን ጸጥ ብለው እርሱ የሚነግራቸውን ለማዳመጥ ቢጠባበቁ ነበር የሚሻላቸው።

የሕዝብ መብዛት እግዚአብሔር እንደተገረመ አያመለክትም።

በመጨረሻው በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሞ ይታያል።

ከውጭ ቆሞ እርሱን ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰቦችን ይጠራቸዋል።

እግዚአብሔር የሚፈልገው ግለሰቦችን እንጂ ሕዝብን አይደለም።

ሰዎች ግን የሕዝብ ብዛት በጣም ያስገርማቸዋል።

የሕዝብ መብዛት ደግሞ ሰዎችን የማስደሰት ጫና እና ብዙሃኑን የመከተል ጫና ይፈጥራል።

ሕዝቡ ምንም ያስቡ ምን ከሕዝቡ ጋር መስማማት እና መመሳል ለሁላችንም ቀላል ነው።

ሰዎች ፍላጎታቸውን በመናገር አገልጋይን ከማስጨነቃቸው ብዛት አገልጋይ ከእግዚአብሔር ምሪት ለመቀበል ጊዜ ሊያጣ ይችላል።

የምናያቸውና የምንሰማቸው ሰዎች ጫና ይፈጥሩብናል። ሰዎችን ለማስደሰት የምንጨነቅ ከሆነ በሰዎች ዘንድ ያለን ተወዳጅነት ደስ ስለሚለን ከሃሳባቸው ለመቃረን መፍራት እንጀምራለን።

ከዚህም የተነሳ መጨረሻችን እግዚአብሔርን ሳይሆን የሰዎችን ፈቃድ ማገልገል ሆኖ ይቀራል።

አብዛኞቹ ሰዎች ኢየሱስ የተከተሉት ከእርሱ ለሚያገኙዋቸው ጥቅሞች ብለው ነው።

በተለይም ከፈውስ እና ጤና ጋር የተያያዙ ጥቅሞች እና ነጻ ምግብ ፈልገው ነው የሚከተሉት።

ከብዙ ሰዎች በጣም ብዙ የአገልግሎት ጥያቄዎች ሲመጡ ከአገልጋዮች ሁሉ ታታሪ የሆነ አገልጋይ እንኳ ከሥራ ብዛት ሊደክምና ሊዝል ይችላል። ልትረዱት የሞከራችሁት የአንድ ሰው ጥያቄ ብቻ እንኳን ከአቅማችሁ በላይ ብዙ ሊሆንባችሁ ይችላል።

ሰዎችን መርዳት ያልተጠበቀ ውጤት ሊያመጣ ይችላል። መጀመሪያ ስለረዳችኋቸው ያመሰግኗችኋል።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የተቀበሉትን እርዳት ከቁም ነገር አለመቁጠር ቀላል ይሆንላቸዋል።

ከዚያ በኋላ ጥያቄያቸውን ሁሉ መመለስ ሲያቅታችሁ በእናንተ ላይ መቆጣት ይጀምራሉ። የጎደለባቸውን ሲያዩ በፊት የተደረገላቸውንና የሞላላቸውን ወዲያው ይረሱታል። ምስጋና ይጠፋባቸዋል። ሰዎች ሁልጊዜ አመስጋኝ ሆነው መቆየት አይችሉም።

የሰዎች ወዳጅነትና ታማኝነት የሚዘልቀው በነጻ የሚያገኙዋቸው ጥቅሞች እስካሉ ድረስ ብቻ ነው።

ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ማስከተልን የስኬት ምልክት አድርጎ አያየውም።

ማርቆስ 1፡38 እርሱም፦ በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው።

ኢየሱስ በዝነኛነት ተገርሞ አያውቅም።

ሕዝቡ ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ እርሱ ለብቻው ፈቀቅ ይላል።

የሆሳዕና እሁድ ዕለት ሲዘምሩለት የነበሩት ሕዝብ እራሳቸው ደግሞ በቀጣዩ ሐሙስ ሰቀሉት።

የፋሲካ በግ በ10ኛው ቀን ተመርጦ በ14ኛው ቀን ነው የሚታረደው።

ኢየሱስ በሆሳዕና እሁድ ዕለት ተመረጠ፤ ያም 10ኛው ቀን ነው። ከዚያ በኋላ 14ኛ ቀን ሐሙስ እርሱ የሞተበት ቀን ነው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ የሞተው አርብ ዕለት ነው ትላለች። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለተጻፈ “ጉድ ፍራይዴይ” የሚባል ፈሊጥ አላቸው። ፕሮቴስታንቶችም መጽሐፍ ቅዱስን በመከተል ፈንታ ካቶሊኮችን ተከትለዋል።

በአራት ቀናት ውስጥ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የአይሁድ ሕዝብን ልብ ቀይረውት ለኢየሱስ በምስጋና እና በአድናቆት ሲጮሁ የነበሩትን ሕዝብ ይገደል ብለው እንዲጮሁ አደረጉዋቸው።

ይህም በመጀመሪያው የኢየሱስ ምጻት ወቅት አጋንንት ሕዝቡን ምን ያህል እንደተቆጣጠሩዋቸው ያስረዳል።

ስለዚህ ኢየሱስ ሙሽራይቱን ሊወስድ በሚመለስበት ጊዜ የቤተክርስቲያን ሁኔታ ምን ሊመስል ይችላል?

ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ሰዎች በይፋ ማጋባት ጀምራለች። ይህ ግብረ ሰዶማዊነት ነው።

እሳት ከሰማይ ወርዶ ሰዶምን አቃጥሏል።

ታላላቆቹ ሃገራት በማንኛውም ሰዓት ከሰማይ መውረድ የሚችል የሚሳኤል እና የኑክሊየር ቦምብ አላቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነትን ያወግዛል።

ሮሜ 1፡24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤

25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።

28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤

ኢየሱስ በእግሩ እየተመላለሰ በገሊላ አውራጃ ውስጥ ሁሉ ሰበከ።

ስለዚህ በዚህ በመክፈቻ ምዕራፍ ውስጥ ማርቆስ ኢየሱስ ያለ እረፍትና ያለመታከት ሲሰራ ሲያገለግል ያሳያል። ከእርሱ በላይ ማንም ሊተጋ አይችልም።

ኢየሱስ በመንፈስ የተሞላ አገልጋይ ምን እንደሚመስል ትልቅ አርአያ ትቶልናል።

ማርቆስ 1፡39 በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።

ይህ አስፈሪ ሃሳብ ነው። እነዚያ ሁሉ አጋንንት በአምልኮ ሥፍራ ነበር የተከማቹት።

ታሪክ እራሱን ይደግማል። ስለዚህ ይህ ስለ ዛሬዎቹ ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖቻችን ምን ይነግረናል?

ማርቆስ 1፡40 ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና፦ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።

ለምጽ ከበሽታዎች ሁሉ ክፉ በሽታ ነው።

ይህ ሰው እራሱን ዝቅ አድርጎ ነው እርዳታ የሚለምነው፤ ምክንያቱም በጣም ከባድ ችግር ውስጥ ነበር።

የነበረበት አስጨናቂ ችግር ወደ ኢየሱስ እንዲሄድ ገፋፋው።

የዚያኑ ጊዜ የሐይማኖት መሪዎች የተደላደለ ኑሮዋቸውን እየኖሩ ኢየሱስን ሐሰተኛ ብለው ዋጋ ሊያሳጡት ይተጉ ነበር።

ስለዚህ በጣም አስጨናቂ ችግሮች ወደ እግዚአብሔር ቃል እንደሚገፉን ማየት እንችላለን፤ ይህም የተሻልን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ያደርገናል።

ከሰዎች መካከል በሙሉ እራስን በመስጠት ስለማገልገል ስናስብ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ቅዱስ ጳውሎስ ነው።

ጳውሎስ እግዚአብሔርን ያገለገለው አንዳችም የግል ጥቅም ፈልጎ አይደለም።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡23 የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ።

24 አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ።

25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።

26 ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፤

27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።

28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።

የማያቋርጡ መከራዎችና ፈተናዎች።

ቅዱስ ጳውሎስ ማገልገል ማለት መከራን መቀበል መሆኑ ገብቶታል።

የሐዋርያት ሥራ 20፡24 የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።

1ኛ ተሰሎንቄ 3፡3 በዚህ መከራ ማንም እንዳይናውጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።

ኢዮብ 2፡10 ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን? አላት።

እግዚአብሔርን ማገልገል ከባድ ሥራ ነው። ክብር እና መከራ ሁለቱም ከእርሱ ዘንድ ይመጣሉ።

ማርቆስ 1፡41 ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።

42 በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።

43 በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አወጣው፤

44 ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው።

ኢየሱስ ታላቅ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል እያሳየ ነበረ ነገር ግን እዩልኝ እዩልኝ እያለ አልነበረም።

ለተፈወሰው ሰውዬ ስለ ፈውሱ እንዳያወራ ነገረው።

አንድ ለምጻም በተፈወሰ ጊዜ ፈውሱ ይረጋገጥለት ዘንድ ሄዶ እራሱን ለካሕን ማሳየት አለበት።

ነገር ግን ሰዎች በመለኮታዊ ተዓምር በጣም ይሳባሉ።

እኛ ሰዎች ስንባል ሁልጊዜ የግል ጥቅም እና ትርፍ ፈላጊዎች ነን፤ መለኮታዊ ፈውስ ደግሞ ትልቅ ትርፍ ያመጣል።

ስለዚህ ሕዝቡ የግል ጥቅማቸውን ፍለጋ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የወንጌሉን እውነት የመረዳትና የማመን ጥልቅ የሆነ ፍላጎት የላቸውም።

ዝነኛ መሆን ሌላኛው መዘዙ ዝነኛ መሆን በሚፈልጉ ነገር ግን ዝነኛ የሚያደርጋቸው ብቃት በሌላቸው ሰዎች ዘንድ ከባድ ቅናት መቀስቀሱ ነው።

አንድ ሰው አድናቆት ባገኘ ቁጥር በሐይማኖት መሪዎች መካከል ብዙ ተቃውሞ ይነሳበታል። ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎች አድናቆት የተሰጠውን ሰው ለመቃወም እና ስሙን ለማጥፋት ተግተው መስራት ይጀምራሉ።

እያንዳንዱ ፓስተር ለራሱ ቤተክርስቲያን ራስ መሆንና ዋነኛው የሚስጥራት ገላጭ መሆን ይፈልጋል። ልክ ሳኦል እያደገ በመጣው በዳዊት ዝና መቅናት እንደጀመረ በሥልጣን ላይ ያሉ መሪዎች ሁሉ ክብራቸውንና ዝናቸውን ለማስጠበቅ ነቅተው ይዋጋሉ።

የተፈወሰው ለምጻም ስለ ኢየሱስ ፈዋሽነት በማውራት ኢየሱስን ያገለገለው መስሎት ነበር።

ይህ ድርጊት ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይፈጽሙ እግዚአብሔርን ለማገልገል የመሞከር ምሳሌ ነው።

አንድ ድርጊት ትክክል ስለሚመስል ትክክል ነው ማለት አይደለም።

የተፈወሰው ለምጻም ለኢየሱስ ቢታዘዝ እና ጸጥ ቢል መልካም ነበር።

ስለዚህ እግዚአብሔርን በማገልገል ውጤታማ መሆን ከፈለግን የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ አመለካከት ተቃራኒ በሚመስል ሰዓት እንኳ ቃን መታዘዝ አለብን።

ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።

ድርጊቶቻችን ብዙውን ከመልካም ነገር ይልቅ ጊዜ እኛ ያላሰብነውን ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

ለምጻሙ ሰውዬ ከተፈወሰ በኋላ የኢየሱስን ዝና አወራ፤ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ መግባት ሳይችል ቀረ። ስለዚህ የተፈወሰው ለምጻም ምስክርነቱ ኢየሱስን አላገዘውም።

ማርቆስ 1፡45 እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፥ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፥ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ታዋቂነት ለታዋቂው ሰው ምንም ጥቅም አያስገኝም። እጅግ ብዙ ሰዎች ከዚህ ተዓምረኛ ሰው የሚፈልጉት ፈውስ እና ሌሎች ጥቅሞችን ነው።

ኢየሱስ ከእነርሱ ተለይቶ ወደማይመች ቦታ ወደ ምድረ በዳ ሄደ ነገር ግን ችግርተኛው ሕዝብ እርሱን ፍለጋ ተከትለውት ወደዚያ ሄዱ።

ኢየሱስ ትጉህ አገልጋይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የገጠመው ትልቁ ችግር ይህ ነው። ከከተማው ውስጥ በብዛት እየመጡ ያጨናነቁት ሳያንሳቸው ወደ ምድረበዳ ሁሉ ተከትለውት ይሄዳሉ። ኢየሱስም ሕይወቱ በሙሉ ያለማቋረጥ በመስጠት እና እራሱን በመሰዋት ስለተሞላ እረፍት ሊያገኝ አልቻለም።

ኢየሱስ ብቻውን ተቀምጦ እፎይ የሚልበት ቦታ እና ጊዜ አላገኘም፤ እራሱንም ሆነ አብረውት የሚሰሩትን ሰዎች ጉልበት ለማደስ የሚሆን ጊዜ አላገኘም።

እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ልክ እንደዚህ ሁልጊዜ ለራሱ ለመሞት መፈለግ አለበት።

ሕዝቡ ለስሜታችሁ ግድ የላቸውም።

ስለዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ በራሱ ስሜት መመራት የለበትም።

ሁሉንም ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ማየትን መልመድ ያስፈልገናል።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23