ማርቆስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 – 12፡ ኢየሱስ እንደ ታላቅ አገልጋይ



ኢየሱስ ታላቁ አገልጋይ፤ ብርቱው በሬ ነው። ሸክማችንን የሚሸከምልንና ልክ ወደ በረሃ እንደሚለቀቀው ፍየል ሐጥያታችንን ተሸክሞልን የሄደው እርሱ ነው።

First published on the 3rd of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022

ሐጥያት በኤደን ገነት ውስጥ ተጀመረ።

ሔዋን ስለጸነሰች ነው የተቀጣችው። አርግዛ ነበር።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።

ሔዋን ማርያም እንድትሆን ነበር የታሰበችው። የተጠራችውም በድንግልና የሚወለደውን ልጅ ለመውለድ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ከእርሷ ይወለድና የሚሞትለት ሐጥያት ስለማይኖር ቅዱሳንን በሙሉ ከምድር አፈር ውስጥ ጠርቶ ያወጣቸው ነበር።

(ይህንን ሁሉ ኢየሱስ በትንሳኤ ቀን ያደርገዋል)።

ሔዋን ኢየሱስን ብትወልደው ኖሮ እርሱ ቅዱሳንን ከምድር አፈር በጠራቸው ጊዜ ምድር ላይ በቂ የሆነ ተፈላጊው የሰው ቁጥር ብቻ ይኖር ነበር። ተርፎ በሲኦል እንዲቃጠል የሚጣል ሰው አይኖርም ነበር።

አዳም እና ሚስቱ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ መንፈስ ነበሩ። (ሥጋዊ አካል የለበሱት ምዕራፍ 2 ውስጥ ነው)።

ስለዚህ ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር የፈለገው መንፈሳዊ በሆነ የመባዛት መንገድ እንዲባዙ ነው። ሔዋን ኢየሱስን በድንግልና ትወልደውና እርሱ ቅዱሳኑን በሙሉ ከአፈር ውስጥ ጠርቶ ያወጣቸዋል።

ዘፍጥረት 5፡1 የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤

እግዚአብሔር መንፈስ ነው። የሰው መንፈስ ብቻ ነው በእግዚአብሔር መልክ ሊፈጠር የሚችለው እንጂ የሰው አካሉ ወይም ሥጋው በእግዚአብሔር መልክ አይደለም።

መፍጠር ማለም ከምንም ነገር አንድ ነገር ማምጣት ነው። የሰው መንፈስ ብቻ ነው ከምንም ነገር የተፈጠረው። ሥጋችን ከአፈር ነው የተሰራው።

ዘፍጥረት 5፡2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው።

የሴት ባህርያት በሙሉ ወንድ ሆኖ በተፈጠረው በአዳም መንፈስ ውስጥ ነበሩ።

ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥

ፍሬው በውስጡ ዘር አለው።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ…

ኤልሳቤጥ ለማርያም እንዲህ አለች፡-

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ሕጻን ልጅ የማሕጸን ፍሬ ነው።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ስለዚህ አዳም እና ሴቲቱ በውስጡ የቃሉ ሙላት ያለው ልጅ (ፍሬ) እንዲወልዱ ታስቦ ነበር።

ይህም በሰው ጥረት ሊደረግ የሚችል ነገር አይደለም።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ሴቲቱን እስኪጸልላትና ክርስቶስን እንድትጸንስ እስከሚያደርጋት ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው።

እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ያሰበው ጽንስ ይህን ዓይነቱን ብቻ ነበረ።

በዚህ መንገድ ኢየሱስ ከሔዋን ቢወለድ ኖሮ ሲያድግ ቅዱሳኑን ሁሉ ከአፈር ውስጥ ጠርቶ ያወጣ ነበር።

ይህም ከትንሳኤ ጋር ተመሳሳይ ክስተት ይሆን ነበር፤ የሚለይበት አንድ ነገር ማንም አለመሞቱ ነው።

ነገር ግን የኤደን ገነት ለዘላለም ትኖር ዘንድ እያንዳንዱ ነገር በትክክል መደረግ ነበረበት። ሁሉም ፍጥረት ፍጹም መሆን ነበረበት። አንዳችም ስሕተት ቢቀላቀል ተቀባይነት የለውም።

ሔዋን ሐጥያት በሰራች ጊዜ በጥንቃቄ የተሰራ ከፍተኛ ኃይል የሚያመነጭ ሞተር ውስጥ አንድ ባልዲ ሙሉ ጠጠር እንደማፍሰስ ነበር የሆነው። ይህ ትልቅ አደጋ ነው። ፍጥረት በሙሉ ወደ ጥፋት ውስጥ ወደቀ።

እግዚአብሔርም “ብዙ ተባዙ” ብሎ የተናገረው ቃል ወደ “እጅግ አበዛለሁ” ሲለወጥ እናያለን።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤

ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት በኩል መውለድን መረጠች። ይህም ማለት እግዚአብሔርን የማያገለግሉ ስለዚህም ወደ መንግስተ ሰማይ የማይደርሱ ብዙዎች ይወለዳሉ ማለት ነው። የእግዚአብሔር የመጀመሪያ እቅድ አካል ያልነበሩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ከሴቶች ነው የሚወለዱት። ይህም በሰው ነጻ ፈቃድ የተነሳ የሚወለዱ ሰዎችን ቁጥር እጅግ ያበዛዋል።

በስተመጨረሻም ሐጥያት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።

ስለዚህ ማርቆስ ኢየሱስን መከራ የሚቀበል አገልጋይ አድርጎ ያቀርብልናል፤ እርሱም ወደ በረሃ የሚለቀቅ ፍየል ሲሆን ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል በመውረድ የሐጥያት አባት በሆነው በሰይጣን ላይ አራግፎ ይመለሳል።

በማርቆስ ወንጌል ውስጥ የኢየሱስ መወለድ እና የልጅነት እድሜው አልተጠቀሰም። አገልጋይ ስለሆነ አድጎ ትልቅ ሆኖ ለሥራ ተዘጋጅቶ ነው የምናገኘው።

ባርያን ወይም አገልጋይን የምንመዝነው በብቃቱና በትጋቱ እንጂ በውልደቱ አይደለም።

ሰይጣን ከመጀመሪያው ለሰራው ሐጥያት እግዚአብሔር የሰጠው ምላሽ ወንጌሉን በመላክ ነው።

ማርቆስ 1፡1 የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።

“የእግዚአብሔር ልጅ” ማለት የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጡ ያደረበት ኢየሱስ የሚባለው ሰው ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥

እግዚአብሔር ሥጋ እና አጥንት አይደለም። ስለዚህ ኢየሱስ የተባለው ሰው እግዚአብሔር አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር ወልድ” ብሎ አያውቅም።

ነገር ግን አንድ ሰው በውስጡ ያለውን ሁሉ ነው። የእግዚአብሔር ሙላት ሁሉ በኢየሱስ ውስጥ ስለነበረ ይህ ኢየሱስን እግዚአብሔር አድርጎታል።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ወንጌል አልነበረም። በብሉይ ኪዳን የነበረው በመቅደሱ ዙርያ የበሩ የሕግ ሥራዎች ብቻ ናቸው።

አሁን ግን አዲስ የማዳን እቅድ መጣ፤ እርሱም የጸጋ ወንጌል ነው።

ሐጥያት ኤድን ገነት ውስጥ ገባ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር አዳምን ስለ ሐጥያቱ ሲጠይቀው አዳም ማሳበቢያዎችን አቀረበ። የሰዎች ሁሉ ድካም ሌሎች ላይ ማሳበብ መፈለጋችን ነው። ጥፋታችንን በግልጽ ፊት ለፊት አምነን ለመቀበል አለመቻላችን ነው ትልቁ ድካማችን። ለድርጊታችን ተጠያቂ መሆን አንፈልግም።

አዳም የሰራው ትልቁ ስሕተት ጥፋቱን በመናዘዝ እና ይቅርታ በመጠየቅ ፈንታ ለሰራው ሥራ ማሳበቢያ መስጠት መፈለጉ ነው።

ሔዋን ሐጥያቷን ከመናዘዝ ይልቅ በእባቡ ማሳበብ ፈለገች።

ከዚያም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር እውነተኛ ሕብረት ማድረግ ከተፈለገ መጀመሪያ ሰዎች ሐጥያት መስራታቸውን ከልባቸው አምነው በመጸጸት ንሰሃ መግባት እንደሚያስፈልጋቸው ወሰነ። የትኛውም ዓይነት ማሳበቢያ ተቀባይነት የለውም።

ስለዚህ ወንጌሉ የሚጀምረው ሰዎች ንሰሃ ሲገቡ እና እራሳቸውን ማዳን እንደማይችሉ ሲያውቁ ነው።

ይህም ሰዎች በሚመጣው አዳኝ እንዲያምኑ አስገደዳቸው።

ይህም አዳኝ ብቻ ነው ሐጥያትን ይቅር ማለት እና የእግዚአብሔርን መንግሥት መመስረት የሚችለው።

የእግዚአብሔር መንግሥት ትኩረቷን ያደረገችው በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ነው እንጂ አይሁዶች ሮማውያንን ከሃገራቸው ለማባረር በነበራቸው ፖለቲካዊ ፍላጎት ላይ አይደለም።

የእግዚአብሔር መንግሥት ትኩረቷ የአይሁድ መሪዎችን አእምሮ በተጸናወቱት የገንዘብ ፍቅር፣ የሥልጣን ጥማት ላይ አይደለም።

ማቴዎስ 3፡1-2 በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

እግዚአብሔር በምድረ በዳ አንድ ነብይ ላከ። በበረሃ ውስጥ ይህ ነብይ በብቸኝነት፤ ከሕዝብ ተገልሎ፤ የሕዝብን አድናቆት ሳይፈልግ ያድጋል። በምድረ በዳ ውስጥ አንዳችም ገንዘብ አይገኝም። ሰዎች ለግል ጥቅም ብለው እግዚአብሔርን ማገልገል ይፈልጋሉ፤ ይህም ትልቅ ስሕተት ነው።

“ይህንን ባደርግ እግዚአብሔር ይባርከኛል” ብለው ያስባሉ። ይህ የግል ጥቅም አሳዳጅነት ለእግዚአብሔር አጸያፊ ነው።

እግዚአብሔርን ማገልገል ያለብን ኢየሱስን ስለምንወደው ነው። እግዚአብሔርን የምናገለግለው መጽሐፍ ቅዱስን ስለምንወድ እና ሰዎችን ስለምንወድ ነው።

ኢዮብ 13፡15 እነሆ፥ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤

ኢየሱስ እንዲሞት የእግዚአብሔር እቅድ ከሆነ ኢዮብ በመሞት እንኳ ለመታዘዝ ዝግጁ ነበር። ኢዮብ ለመበልጸግ ብሎ አይደለም እግዚአብሔርን ያገለገለው። እንደውም ኢዮብ የነበረው ሃብት በሙሉ ከወደመበትም በኋላ እንኳ እግዚአብሔርን ማገልገል አላቆመም።

ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ የንሰሃን መሰረት በመጣል ወንጌሉን ጀመረው።

ዮሐንስ 1፡28 ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ።

ዮሐንስ በቤተራባ “የመሻገር ቤት” አካባቢ ምድረ በዳ ውስጥ መስበክ ጀመረ፤ ይህም ቦታ ኢያሱ የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገረበት ቦታ ነው።

 

 

ዮሐንስ ለራስ የመሞት ተምሳሌት ነው።

ንሰሃ ስንገባ ሐጥያታችን ወደ ኢየሱስ ይሻገራል፤ ለዚህ ነው የኢየሱስ መሞት ያስፈለገው።

ከዚያም የእርሱ ቅድስና ወደ እኛ ይሻገራል፤ ለዚህም ነው እኛ የዘላለም ሕይወት የምናገኘው።

የእውነት ንሰሃ ካልገባህ እና ለራስህ ካልሞትክ ከእግዚአብሔር ጋር ብዙ አትዘልቅም።

ትልቁ ሽግግር አይሁዶች ለመቀበል እምቢ ያሉት ወንጌሉ ነው፤፤ ከዚህም የተነሳ መዳንንም አንቀበልም እምቢ ብለዋል፤ መዳን ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ከአይሁድ ነበረ፤ በአዲስ ኪዳን ከአይሁድ ወደ አሕዛብ ተሻገረ።

 

 

ኢየሱስ የሞተ ጊዜ የሞትን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ሲኦል በመውረድ ሐጥያታችንን በሰይጣን ላይ አራገፈው። ከዚያ በኋላ የሞትን ወንዝ ተመልሶ መሻገሩንና ወደ ሕይወት መምጣቱን ለማሳየት ከሙታን ተነሳ። ስለዚህ የትንሳኤው በኩር እንደመሆኑ የሞትን ወንዝ አሻግሮን ወደ መንግስተ ሰማይ እንደሚያደርሰን ዋስትና ሰጥቶናል ምክንያቱም የሐጥያታችንን ዋጋ በሲኦል ውስጥ ከፍሎታል።

ከዚያም ሥጋችንን ከሙታን ማስነሳት ወይም በሕይወት ሳለን አካላችንን መለወጥ ለእርሱ ምንም ከባድ ሥራ አይሆንበትም፤ የዚያን ጊዜ ከዚህ ሟች ሕይወት እንወጣና ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ለመሻገር ከእርሱ ጋር በአየር ላይ እንነጠቃለን (በተለምዶ ይህንን ንጠቀት ይሉታል)።

ከኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ በኋላ ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን መሰረቱ። ቀራንዮ በዘፍጥረት ውስጥ የተነገረ የመጀመሪያ ትንቢት ነው።

ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

በናቡከደነጾር ሕልም ውስጥ ያለው ምስል ሰኮናው ወይም ተረከዙ መዳን ከአይሁድ ወደ አሕዛብ የሚሸጋገርበት ቦታ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ መዳናችን እርግጥ ይሆን ዘንድ የሰኮናውን ቦታ ወሰደ።

ሉቃስ 4፡8 ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።

ኢየሱስ እንቅስቃሴው በሙሉ ከተጻፈው ቃል ጋር ነበር።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ፍጹም መሆኑን ያምን ነበር፤ ስለዚህ ዲያብሎስን ለማባረር የእግዚአብሔርን ቃል ተጠቅሟል።

 

 

ሰይጣን እንደ እባብ ከኢየሱስ በስተኋላ በመምጣት ሰኮናው ላይ ይነድፈዋል፤ ለሦስት ቀናት ያህል ያቆስለዋል፤ በእነዚያ ሦስት ቀናትም ኢየሱስ መራመድ ስለማይችል መቃብር ውስጥ ተኝቶ ይቆያል። ለጊዜው ብቻ ተኝቶ ይቆይና ሳይበሰብስ በፊት በሦስት ቀን ውስጥ አሸንፎ ይነሳል።

ኢየሱስ መበስበስን አያውቅም። በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መበስበስም ሆነ ስሕተቶች የሉም። እርሾ ያልገባበት ቂጣ የሚወክለው ይህንን ነው። ስሕተት የሌለበት ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ።

ኢየሱስ ግን ሰይጣንን አናቱ ላይ ቀጠቀጠው፤ ከዚህም የተነሳ ሰይጣን በስተመጨረሻው መሞቱ አይቀርም።

ለጊዜው ሰይጣን አናቱ ላይ ካረፈበት ከባድ ምት የተነሳ ስለተጎዳ ሃሳቡን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ማሰብ ተስኖታል። ሁልጊዜ እውነት የሚመስሉ ስሕተቶችን ለመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ይሄዳል። በስተመጨረሻም 1769ኙ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ችግር አለበት ብሎ ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ከዚያም ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን አዘጋጀ፤ እነርሱም ቢሆኑ ፍጹም አለመሆናቸውን አልካደም። ይህ ዓይነቱ የተደበላለቀ በቤተክርስቲያን መሪዎች ስሕተት ተሞልተው የሚታበዩትን ሰዎች አስተሳሰብ ያስደስታል።

በስተመጨረሻም ቤተክርስቲያኖች ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የለም ብለው ወደ ማመን ይመጣሉ።

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ …

ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

በማርያም ማሕጸን ውስጥ ያደረው ጽንስ የሰው አባት የለውም። ስለዚህ ኢየሱስ የሴቲቱ ዘር ነው ምክንያቱም አንድም ሰው የእኔ ዘር ነው ማለት አይችልም። ይህ ዘር የዘላለም ሕይወት ዘር ነው።

የእባቡ ዘር የእስፐርም ሴል ነው (ከታች ተመልከቱ) እርሱም ከወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ የፍጥረታዊ ሕይወት ዘር ስለሆነ መሞት አለበት።

 

 

እግዚአብሔር እባቡን ረገመው፤ እርሱም ከፍጥረቱ ተንኮለኛ እና ከዝንጀሮዎች ይልቅ ወደ ሰው የቀረበ አጥቢ እንስሳ ነበረ። እግዚአብሔር እባቡን በደረቱ የሚሳብ እንስሳ እንዲሆን አድርጎ ለወጠው፤ እርሱም አሁን ያለው ቅርጽ የወንድን የመራቢያ ዘር ይመስላል።

ሰዎች ከሴት ሲወለዱ በሆዳቸው ላይ እምብርት የምንለውን ጠባሳ ይዘው ነው የሚወለዱት። ይህም በሰውነታችን ላይ የቀረው የአውሬው ምልክት ነው።

ሕይወት ሲያበቃ የሰው ሰውነት በመቃብር ውስጥ ይተኛል፤ መቃብሩም በምድር ላይ ጠባሳ ያመጣል።

በጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ውስጥ ከሴት የተወለዱ ሰዎች አእምሮዋቸው ባለበት በግምባራቸው ላይ የአውሬውን ምልክት በመቀበል የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ክርስቶስን አሳልፈው ሰጡት። ከእርሱ ይልቅ ነፍሰ ገዳይ የሆነውን በርባንን መረጡ።

ማርቆስ 15፡7 በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።

ልክ አይሁዶች ኢየሱስን አንቀበልም እንዳሉት ዛሬ ቤተክርስቲያኖች በ1769 የተጠናቀቀውን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንቀበልም ይሉታል።

ኢየሱስ ከሞቱ እና ከትንሳኤው በኋላ ከሲኦል ወደ መንግስተ ሰማያት ሲሻገር ወንጌሉም ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ተሻገረ።

ታለቁ አሳ አጥማጅ ጴጥሮስ አይሁዶችን በበዓለ ሃምሳ ዕለት አጠመደ፤ ከዚያም ሳምራውያንን (ሳምራውያን በከፊል አይሁድ በከፊል አሕዛብ ናቸው)፤ ቀጥሎ ደግሞ አሕዛብን፤ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል።

ጴጥሮስ የዮሐንስን ጥምቀት በኢየሱስ ስም በሆነው ጥምቀት ተክቶታል (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)።

ስለዚህ የዮሐንስ የውሃ ጥምቀት ተለውጧል ግን አብሮት የነበረው ንሰሃ አልቀረም።

ከዚያ በኋላ ድንኳን ሰፊው ጳውሎስ ሕግን እና ጸጋን በአንድ ላይ ሰፋ። እርሱም ክርስቶስ በውስጣችን በሕይወት ይኖር ዘንድ ለራሳችን መሞት እንዳለብን አብራራ።

እነዚህ የወንጌል እውነቶች በጨለማው ዘመን ጠፍተው ነበር።

ከዚያ በኋላ በመጨረሻዎቹ ሦስት የቤተክርስቲያን ዘመናት እውነት በተሃድሶ ተመልሳ መጣች። ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው ሐዋርያት ወደ መሰረቱት የአዲስ ኪዳን እምነት ትመለሳለች።

 

 

ራዕይ 14፡6 በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤

ይህ ለአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የተላከው መልአክ ወይም መልእክተኛ ጀርመኒ ውስጥ የተነሳው ማርቲን ሉተር ነው። እርሱም መዳን በኢየሱስ በማመን ብቻ ነው ብሎ ሰበከ። የዘላለም ወንጌል የተባለው ንሰሃ እና ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ማመን ነው።

ወንጌሉ የተጀመረው በመጥምቁ ዮሐንስ ነበረ፤ እርሱም ሕዝቡ ሊመጣ ባለው አዳኝ ያምኑ ዘንድ ስለ ንሰሃ ሰበከ። ወንጌሉ ሁልጊዜ በንሰሃ እና በኢየሱስ በማመን ነው የሚጀምረው። አዘውትሮ ቤተክርስቲያን መሄድ ክርስቲያን አያደርገንም።

ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ካመንን እውነተኛ ንሰሃ ክርስቲያን ያደርገናል።

ራዕይ 14፡8 ሌላም ሁለተኛ መልአክ፦ አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው።

ባቢሎን ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወይም ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ትተው በመሄድ እና የሰዎችን ልማድ በመከተል በአለማመን እና በመንፈሳዊ ውድቀተ ውስጥ ወድቀዋል።

መጠጣት፤ መዳራት፤ እነዚህን የመሳሰሉ ክፉ ልማዶች ተወግዘዋል። ይህ መልአክ ወይም መልእክተኛ ለስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እንግሊዝ ውስጥ ስለ ቅድስና በመስበክ የተነሳው ጆን ዌስሊ ነው።

ራዕይ 14፡9 ሦስተኛም መልአክ ተከተላቸው፥ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ፦ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥

በግምባር ማለት በአንጎል ወይም አእምሮ ማለት ነው።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን እስኪያምኑ ድረስ በአእምሮዋቸው ይስታሉ።

 

 

የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የሮማ ካቶሊክ አውሬ ምስሎች ናቸው።

ታላቅ ድምጽ።

ራዕይ 10፡7 ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥

አሜሪካ ውስጥ ከ1947 እስከ 1965 ያገለገለው ዊልያም ብራንሐም ወደ ጥንቶቹ ሐዋርያት አዲስ ኪዳናዊ እምነት እንመለስ ዘንድ ተሰውረው የቆዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ገለጦ አስተማረ።

ዊልያም ብራንሐምን የሚቃወሙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉ የሕዝባቸውን አእምሮ ይቆጣጠራሉ፤ ሕዝባቸውንም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን እንዲያምኑ ያስገድዷቸዋል። ከዚያም ሕዝቡ ለቤተክርስቲያናቸው እንደ ባሪያ ይሰራሉ። በዓለም ላይ አሁን ከ45,000 በላይ የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አሉ። አዳዲስ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚከተሉ ሰዎችን በኋላቸው ሰብስበው ባስከተሉ ቁጥር አዳዲስ ቤተክርስቲያኖች ይፈለፈላሉ።

62-0318 የመጀመሪያ ዘር በአፍ የተነገረው ቃል ነው፤ ክፍል 2

አሁን ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ትታ ሄደች፤ ከዚያም ሌላ ሰው አገባች እርሱም ፖፕ ይባላል፤ የራሱ የሆኑ ዶግማዎች አሉት። ስለዚህ አሁን በእርሷ ዘንድ ኢየሱስ የለም። በእርሷ ዘንድ ያለው ፖፑ ነው። አሁን በእኛ ዘንድ… ፕሮቴስታንቶች ኢየሱስን አላገኙትም። ፕሮቴስታንቶች ያላቸው ዲኖሚኔሽን ነው፤ እርሱም ለአውሬው የተዘጋጀለት ምስል ነው። ስለዚህ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ልጆቿን በቃል መውለድ አትችልም። እርሷ ራሷ ጋለሞታ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ ጋለሞታ ይላታል። “በእጇ ጽዋ ይዛለች፤ ከያዘችውም ጽዋ ለሕዝቧ አስተምሮ ትሰጣለች፤ አስተምሕሮዋም ጸያፍ ነገር ነው፤ የዝሙቷ እርኩሰት ነው።” ዝሙት ምንድነው? በእርኩሰት መኖር ማለት ነው። ለሕዝቧ የምታስተምረው አስተምሕሮ የዝሙቷ እርኩሰት ነው። “የምድር ነገስታትና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ በእርኩሰቷ ወይን ሰከሩ።” ተመልከቷቸው። ለዚህ ብለው አንቀው ይገድሏችኋል። ካቶሊኮች ብቻ አይምሰሉዋችሁ፤ ፕሮቴስታንቶችም ጭምር።

… ጴንጤ ቆስጤያዊ ቤተክርስቲያኖችም ከፕሮቴስታንቶች አይሻሉም፤ የሚዘሉ፣ የሚጮሁ፣ በልሳን የሚናገሩ ሰዎች ስብስብ ናቸው። እስቲ ተረጋጉ ብትሏቸው ከቤተክርስቲያናቸው ያባርሯችኋል። እግዚአብሔር እራሱ በመካከላቸው ወርዶ የሞተ ሰውን ቢያስነሳ እና እናንተ ግን ከእነርሱ ጋር ባትስማሙ የድርጅታቸው አባል ባትሆኑ ከቤተክርስቲያናቸው ያባርሯችኋል።

ወንጌል ከጀርመኒ ወደ እንግሊዝ እንዲሁም ወደ አሜሪካ ተዳረሰ።

ማቴዎስ 24፡27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤

 

 

ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች እንዲህ ብሎ አስጠነቀቃቸው።

የሐዋርያት ሥራ 20፡29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

የቤተክርስቲያን መሪዎች እራሳቸውን በጣም ታላቅ አድርገው በመቁጠር ሕዝብ እኛን ካልተከተለን ይላሉ።

ማርቆስ 1፡2 እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ … ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥

እግዚአብሔር በጥንት ዘመን ሚልክያስ 3፡1 እና ኢሳይያስ 40፡3 ነብያትን በመጠቀም ስለ ኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ትንቢት ተናግሯል።

ኢየሱስ ትናንትና፣ ዛሬ፣ ለዘላለምም ያው ነው (ዕብራውያን 13፡8)። ስለዚህ አይለወጥም።

ኢየሱስ ለዳግም ምጻቱ መንገድ ለመጥረግ የሚጠቀመው የዊልያም ብራንሐምን መልእክት ነው።

54-0515 ጥያቄዎችና መልሶች

እዚሁ የኦሃዮ ወንዝ ውስጥ የዛሬ ሃያ ሦስት ዓመት እየተጠመቅሁ ሳለ እንዲሁ ብሎ ነበር የተናገረው፤ ብዙዎቻችሁ የዚያን ዕለት ወንዙ አጠገብ ቆማችሁ ነበር፤ የዚያኔ ያ ብርሃን ያ መልአክ እዚያ ቦታ ላይ ወርዶ እንዲህ ነበር ያለው፡-

“መጥምቁ ዮሐንስ የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ጠራጊ ሆኖ ተልኮ እንደነበር ሁሉ ያንተ መልዕክት ደግሞ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።”

ትኩረት የተደረገው ወንድም ብራንሐም በሰበከው መልእክት ላይ እንጂ በሰውዬው ላይ አይደለም።

ማርቆስ 1፡3 የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ

በምድረ በዳ ውስጥ። ሕዝብ በማያየው ቦታ። ምኩራቦች አንቀበልህም ብለውት (ምኩራቦችን ዛሬ ቤተክርስቲያኖች እንላቸዋለን)፤ በእነዚህም ምኩራቦች ውስጥ ሰዎች ተደላድለው ተቀምጠው እግዚአብሔርን እያገለገልን ነን ብለው ራሳቸውን ያታልላሉ። ነገር ግን ለራሳቸው የሚስማማቸውን እምነት ለራሳቸው እያበጁ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስን እየተከተሉ አልነበሩም።

ዮሐንስ ምንም ነገር አላቀናም። ዮሐንስ አይሁዳውያን አይተው የማያውቁትን አዲስ የውሃ ጥምቀት አሳያቸው።

በተጨማሪም ዮሐንስ መሲሁን ለእሥራኤል ሊያስተዋውቅ ነው የመጣው። የመሲሁ መምጣት አዲስ ታሪካዊ ክስተት ነበረ።

ዮሐንስ ከመቅደሱ ወይም ከአይሁዳውያን የሐይማኖት መሪዎች ጋር ምንም ጉዳይ አልነበረውም። ይህም ማንም ያልሰማው ዓይነት ነገር ነው።

ዮሐንስ ከዘመኑ የቀደመ ሰው ነበረ። በመቅደሱ ውስጥ መስዋእት በማቅረብ የሚደረገው የአምልኮ ሥርዓት ጊዜው እያለፈበት መሆኑን አውቋል።

ማርቆስ 1፡4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

ምድረ በዳ። የብቸኝነት እና በጣም ከባድ የሆነ ቦታ። የእግዚአብሔርን ምሪት መከተል በሰዎች ዘንድ ዝነኛ አያደርግም።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማመን የሚፈልጉት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።

ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።

እኛ ግን እውነትን ፈልገን ማግኘት እና ለሰዎች ተቃውሞ ዝግጁ መሆን አለብን።

ማርቆስ 1፡5 የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፥ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

 

 

ከላይ ባለው ካርታ ውስጥ የይሁዳ አውራጃ አረንጓዴ ቀለም የተቀባው ቦታ ነው።

ዮሐንስ የሰዎችን ልማድ የማይከተል ሰዎችን ለማስደሰት የማይጨነቅ ሰው ነው። በዚያ አውራጃ የነበሩትን አይሁዶች አናወጣቸው። ከአንድም ሰው ገንዘብ አልጠየቀም፤ የሐይማኖት መሪዎችንም እባቦች ብሎ ዘለፋቸው፤ መርዛቸውም ትምሕርታቸው ነው። እነርሱም እሱ የማያመቻምች እውነተኛ ነብይ መሆኑን አውቀዋል።

ማርቆስ 1፡6 ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሀ ማርም ይበላ ነበር።

የግመል ጠጉር። ይህ ርካሽና በቀላሉ የሚገኝ ልብስ ነው ነገር ግን ጠንካራና ሸካራ ነው። በእርሱ ዘንድ የብልጽግና ወንጌል ቦታ የለውም።

አዳም እና ሔዋን ከኤደን ገነት ሲባረሩ የደም ነጠብጣብ ያለበት ቆዳ ለብሰው ነበር የወጡት። ከመጀመሪያው ሐጥያት በኋላ በወገባቸው ዙርያ የበለስ ቅጠል ለብሰው ነበር። እኛ ሁላችንም ሐጥያት የሰራንበትን የሰውነት ክፍል በደመነፍስ የመሸፈን ዝንባሌ አለን። እግዚአብሔር ይህንን ሰው ሰራሽ ከንቱ ሐይማኖት በእንስሳ ቆዳ ተክቶታል። የሔዋን ድንግልና የጠፋውና ደሟ የፈሰሰው በእባቡ አማካኝነት ነው፤ እርሱም ከእንስሳት ሁሉ ይልቅ ተንኮለኛና ከዝንጀሮዎች በላይ የሆነ ፍጡር ነበረ። ከዚያ በኋላ በሆዱ እየተሳበ እንዲሄድ ተረገመ። ምክንያቱም ሐጥያቱን በሰራ ጊዜ በሆዱ ተኝቶ ነው የሰራው።

እውነትን ከሐሰት ጋር ስለሚቀላቅል ልክ እንደ እባብ መንታ ምላስ አለው። መጥምቁ ዮሐንስ በአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ውስጥ የሚጠላባቸው ባሕርይ ይህ ነው። ሰው ሰራሽ ልማዶችን እና የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው ማስተማራቸውን አይወደውም። ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ እና ረቢዎች የሙሴ ሕግ አካል አልነበሩም። ሆኖም ግን እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውቅና የሌላቸው ሥልጣኖች እራሳቸውን ከፍ አድርገው የሐይማኖት መሪዎች ለመሆን በቅተዋል።

ስለዚህ ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸው ፖፕ፣ ካርዲናሎች፣ ሊቀ ጳጳሳት እና የቤተክርስቲያን መሪዎች አሉ።

ስለዚህ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ሕዝቡ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን እንዳይከተሉ አደረጉዋቸው። ልክ እንደ እባብ እነርሱም በአፋቸው ውስጥ የሐይማኖታዊ ስሕተት መርዝ ይዘዋል።

የመጀመሪያው ሐጥያት የተሰራው አንድ እንስሳ ንጹህ ደም ባፈሰሰ ጊዜ ነው። ስለዚህ ያንን ሐጥያት ለማስተስረይ የሌላ እንስሳ ደም ፈሰሰ። ከዚህም የተነሳ አዳም እና ሔዋን ወገባቸው ደም በነካው ቆዳ ተሸፍኖ ከኤደን ገነት ወጡ።

ዮሐንስ ግን አንድ አዲስ በግ የሐጥያትን ዋጋ ሊከፍል እንደሚመጣ ተረድቷል።

ሐጥያት ከተጀመረበት ከኤደን ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ዮሐንስ በወገቡ ላይ ቆዳ ለብሶ መጣ፤ ነገር ግን የሚመጣው በግ ሐጥያትን የሚያስተሰርይ ደም ከራሱ እንደሚያፈስ ያውቅ ነበር።

ከምግቦች መካከል ብቸኛው የማይበላሽ ምግብ ማር ነው። ዘላለማዊው ወንጌል ንሰሃ ነው። ንሰሃ ምንጊዜም አያረጅም፤ ዘመን አያልፍበትም። ሁልጊዜ ለሐጥያት ፍቱን መድሐኒት ነው።

አንበጦች በአጥፊነታቸው የተነሳ የአጋንንት ተምሳሌት ናቸው። ዮሐንስ በጥርሱ ዘነጣጠላቸው። ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎችን ግብዝነት ገነጣጥሎ ጣለው። በዘመኑ የነበሩ የሐይማኖት መሪዎችን እንደ እባቦች ነበር የቆጠራቸው። በእውነትም እባቦች፣ የእፉኝት ዘሮች። ለገንዘብ ብለው ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችን ያስተምሩ ነበር እንጂ እውነትን አልሰበኩም።

ማርቆስ 1፡7 ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።

ዮሐንስ የመጀመሪያው ምጻት አብሳሪ ወይም መንገድ ጠራጊ ነበረ። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የሚመጣው መሲህ ከእርሱ እጅግ በጣም የሚበልጥ እንደሚሆን ገብቶታል።

መንገድ ጠራጊውን ከኢየሱስ ጋር ማወዳደር በራሱ ትልቅ ስሕተት ነው።

“የጫማውን ጠፍር፤” ማለትም የጫማውነ ማሰሪያ።

ናቡከደነጾር በሕልሙ ያየው ምስል እግሮቹ የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ተምሳሌት ናቸው።

 

 

እግሮቹ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምሳሌ ናቸው።

እግር ማጠብ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት በቃሉ ውሃ የማጠብ ተምሳሌት ነው።

(መጥምቁ ዮሐንስ ሰዎችን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በማጥመቅ የዚህን እውነት ቅምሻ አሳይቷል።)

የተጻፈው ቃል መገለጥ አእምሮዋችንን ለእውነት ይከፍተውና አለማመንን ከአእምሮዋችን ውስጥ አጥቦ ያስወጣዋል፤ ከዚያም ለቤተክርስቲያን ወይም ለአንድ ዲኖሚኔሽናዊ ድርጅት ከመስራት ነጻ አውጥቶን ለእግዚአብሔር መስራት ያስችለናል።

በተፈጥሮ እግሮች በጫማ ውስጥ ተደርገው ጫማዎቹን በማሰሪያ ይታሰራሉ።

በተጠላለፉት የጫማ ማሰሪያዎች ውስጥ አጮልቀን ስንመለከት ማየት የምንችለው የጫማውን ምላስ ነው። ስለዚህ የጴንጤ ቆስጤያዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ቦታ የሰጠው በልሳን (በምላስ) ለመናገር ልምምድ ነው፤ እርሱም በጣም ጠቃሚ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሲሆን ነገር ግን ከስጦታዎች ሁሉ ታናሹ ስጦታ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 12፡31 ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።

መጀመሪያ የተጠቀሱት ስጦታዎች ጥበብ እና እውቀት ናቸው።

የእውቀት ቃል ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወይም በቃሉ ውስጥ ያሉትን የቃል ተምሳሌቶች መረዳት ትችሉና የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በትክክል ለመተርጎም ብቃት ታገኛላችሁ ማለት ነው።

የጥበብ ቃል ደግሞ የሚያስፈልገው የተለያዩ ጥቅሶችን በማገናኘት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተያያዥ የሆኑ ሃሳቦችን እና እውነቶችን ተከታትሎ ለማጥናት ነው፤ ይህም ጠለቅ ያለ የመንፈሳዊ እውነት መገለጥ ላይ ያደርሳል።

የምስሉ እግሮች የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምሳሌ ከሆኑ ከሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ነው አንድ ነብይ መጥቶ የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ሚስጥር የሚገልጠው።

እነዚህም ሚስጥራት በራዕይ ምዕራድ 6 ጀምሮ በተጻፉት በሰባት ማሕተሞች ተዘግተው ነበር የቆዩት።

የማሕተሞቹን ሚስጥራት መግለጥ ወይም መፍታት የጌታን ጫማ ማሰሪያዎች ከመፍታት ጋር ተመሳሳይ ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ ማሕተሞቹን መፍታት የእርሱ አገልግሎት እንዳልነበረ ገብቶታል።

“ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ።”

ስለዚህ በመጨረሻው ዘመን ሌላ ኤልያስ መምጣት አለበት።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ይህ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞተ በኋላ ነው። ነገር ግን ወደፊት የመጨረሻውን ዘመን ልጆች ወደ አዲስ ኪዳናዊው የሐዋርያት አባቶች ትምሕርት የሚመልስ ሌላ ኤልያስ ይመጣል።

አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገለጠ። ነገር ግን እኛ ደግሞ እንደ ትንንሽ ልጆች እርሱ ያመጣውን መገለፅ በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረን ለራሳችን ማረጋገጥ አለብን። እርሱ ያስተማራቸውን መገለጦች በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት መርምረን የሰበከው ስብከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

ማቴዎስ 17፡12 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።

መጥምቁ ዮሐንስ መጣና ሄደ፤ አይሁዳውያን ግን የእርሱ አገልግሎት ዓላማ ምን እንደነበረ አልተረዱም።

ዊልያም ብራንሐምም መጣና ሄደ፤ ነገር ግን ሰዎች እርሱ ሲያገለግል እምነታቸውን እርሱ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጦ በማስተማር በገለጠላቸው እውነት ላይ እንዲመሰርቱ ሊረዳቸው መሆኑን ማንም አልተገነዘበም።

እርሱ የተናገራቸውን ንግግሮች እንደ ገደል ማሚቶ ደግሞ መናገር መቻል በቂ አይደለም። እርሱ ያስተማረው ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለባችው። ስለዚህ እምነታችሁ ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማሳየት መቻል ይጠበቅባችኋል።

እምነታችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ፈትናችሁ ማረጋገጥ የማትችሉ ከሆነ የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ምን እንደሆነ አልተረዳችሁም።

ወንድም ብራንሐም የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማሕተሞች ሚስጥር በገለጠ ጊዜ በመንፈስ በጌታ እግሮች ላይ ያለውን የጫማ ማሰሪያ ነው የፈታው፤ የጌታ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

ሰባተኛው ማሕተም አልተገለጠም ምክንያቱም ሰባተኛው ማሕተም የሚወክለው የኢየሱስን ዳግም ምጻት ሚስጥር ነው። ይህ በዓለማችን ውስጥ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሚስጥር ነው፤ ደግሞም በጣም ውስብስብ ሚስጥር ነው ምክንያቱም ከጊዜም ከስፍራም ሁሉ በላይ ነው። ስለዚህ ማንም ሰው ሚስጥሩ እስኪፈጸም ድረስ ሊያውቀው አይችልም።

አንድ ሰው በጊዜ እና በሥፍራ ተወስኖ በሚኖርበት ዘመን (እያረጀ ሲሄድ) በአካሉም ውስጥ ደም እስካለውና በሆዱም ላይ በተፈጥሮ ከመወለዱ የተነሳ እምብርት ባለው ጊዜ የ7ኛው ማሕተም አካል ሊሆን አይችልም። እምብርታችን በሰውነታችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ሲሆን ጌታ ቢዘገይ ይህ ምልክት እንድንሞት ያደርገናል።

የቃልኪዳኑን ታቦት ብትመለከቱት የምሕረት ዙፋኑ ከሁለት ኪሩቤሎች መካከል መሆኑን ታያላችሁ።

በቀራንዮ መስቀል ላይ የምሕረት ዙፋኑ የተገለጠው በአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ሲሆን እነርሱም በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ነው የሚገኙት።

ማርቆስ 1፡8 እኔ በውሃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።

አሁን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጓሜውን አግኝተናል። እርሱም መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መቻል ነው።

ዳንኤል 8፡27 እኔም ዳንኤል ተኛሁ፥ አያሌም ቀን ታመምሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ የንጉሡን ሥራ እሠራ ነበር፤ ስለ ራእዩም አደንቅ ነበር፥ የሚያስተውለው ግን አልነበረም።

ዳንኤል በዕብራይስጥ ቋንቋ የተነገሩትን ቃላት ያውቃቸዋል ነገር ግን ትርጉማቸው ምን እንደሆነ አላወቀም።

ኤርምያስ 5፡21 እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፥ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ ሕዝብ ሆይ፥ ይህን ስሙ።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃላትን ማንበብ ይችላሉ ግን ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት የሚችሉበት አውዳዊ እውቀት ወይም ስዕል የላቸውም። ስዕል መገለጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ ተያይዞ የሚገጣጠም የመረዳት ስዕል ያስፈልገናል።

ኢየሱስ በኤማውስ መንገድ ላይ ከሁለቱ ደቀመዛሙርት ጋር በተነጋገረ ጊዜ፡-

ሉቃስ 24፡27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።

ኢየሱስ መከራ የሚቀበል አገልጋይን ስዕል በቃላት ከሳለ በኋላ ይህንን ሃሳብ በብሉይ ኪዳን የነብያት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙ ቃላት ውስጥ አሳያቸው።

እነዚያን ጥቅሶች ሰብስቦ በማያያዝ አንድ ሙሉ ስዕል እንዲታይ ማድረግ ጥበብ ነው፤ እነዚህ ጥቅሶች የፈጠሩት “ስዕል” ደግሞ መረዳት ወይም “ማስተዋል” ነው። ይህ ሂደት በአጠቃላይ መገለጥ ይባላል።

እያንዳንዱ ጥቅስ በዚያ ስዕል ወይም አውድ ውስጥ ሲገጣጠም እነርሱ የጥቅሱን አውድ መረዳት ቻሉ።

ስለዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ እያንዳንዱ ጥቅስ ትክክለኛ እውቀት አገኙ።

ሐሰተኛ አስተማሪዎች የተለየ ስዕል ይስላሉ፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከሳሉት ስዕል ጋር ሙሉ በሙሉ የሚገጥሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት አይችሉም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ቃሎች እንዳላዩ ያልፋሉ ወይም ይለውጧቸዋል። በተጨማሪም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላት እና አባባሎችን በራሳቸው ፈጥረው ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ የሰባት ዓመታት መከራ፣ ፖፕ፣ ወዘተ።

ይህ አታላይነት ነው።

ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤

በመጨረሻ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስን ዋነኛ ትልቅ ስዕል ላለማወቃችን ምንም ማሳበቢያ አይኖንም። እግዚአብሔር ሚስጥራትን ይገልጥልንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በትልቁ ስዕል ውስጥ መገጣጠም እንድንችል ይጠብቅብናል።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ አንድ ብርቱ መልአክ የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ ለትንሳኤ ወደ ምድር ይወርዳል። ሚስጥራቱ ተገልጠዋል ምክንያቱም መጽሐፉ አሁን ክፍት ነው።

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

ደመናው ከታየበት አንድ ዓመት በኋላ በ1964 ወንድም ብራንሐም የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ እንደሚወርድ እና ሙታንን እንደሚያስነሳ ገና እየተጠባበቀ ነበር። ስለዚህ በ1963 የተገለጠው ደመና የራዕይ ምዕራፍ አሥር መልአክ አልነበረም።

1964-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ወደ ምድር መውረዱ ሙታንን ለማስነሳት ነው።

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው የነበሩ ቅዱሳን በሙሉ በምድር ወይም ባሕር ውስጥ ተቀብረዋል።

መጽሐፉ ተከፍቷል። የተገለጠውን ቃል የሚያምኑ ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ለዚህ ነው “ታናሽ” መጽሐፍ የተባለው።

ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።

በመጨረሻ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሆኑት። የቤተክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሳይጠቅሱ ሰዎችን የእነርሱን አስተሳሰብ እንዲከተሉ አስፈራርተውም ቢሆን ያሳምኗቸዋል።

ማቴዎስ 9፡37 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤

ትክክለኛነታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተረጋገጡ ትምሕርቶችን የሚያስተምሩ በጣም ጥቂቶች ናቸው።

ማቴዎስ 25፡23 ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

ወንድም ብራንሐም ያስተማረው ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ታማኝ መሆን። የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን እምነቷ ከመጀመሪያው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እምነት ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን እንዳለበት ለማመን ታማኝ መሆን።

እንደዚህ ታማኝ ስንሆን ብቻ ነው በ1,000ው ዓመት የሰላም መንግስት ውስጥ ለመንገስ ብቁ የምንሆነው።

ሉቃስ 12፡31 ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።

በመጨረሻው ዘመን ውስጥ የሺውን ዓመት መንግስት የሚወርሱት ታናሽ መንጋ የተባሉት አማኞች ናቸው ምክንያቱም እነርሱ አንድ ግለሰብን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው የሚያስቀድሙት።

ገላቲያ 5፡8 ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል።

በጣም ጠንቃቃ መሆን አለብን ምክንያቱም ትንሽ ስሕተት ትልቅ ውጤቶችን ሊያስከትል ይችላል፤ ደግሞም የምናምነው ውስጥ ሁሉ ተዛምቶ እምነታችንን በሙሉ ሊያበላሽብን ይችላል።

ማቴዎስ 24፡37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።

በኖህ ዘመን ስምነት ሰዎች ብቻ ነበሩ የዳኑት። ወደ ሰማይ የተነጠቀው ደግሞ አንድ ሄኖክ ብቻ ነው። ስለዚህ ለጌታ ዳግም ምጻትም ብዙ ሰዎች ዝግጁ የሚሆኑ አይመስልም።

ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር በመካከላቸው አንዳችም ልዩነት ሊገኝ እስከማይችል ድረስ ተመሳሳይ መሆን አለበት። ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ይህንን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የመመለስ ተሃድሶ ለማከናወን ጥቂቶች ብቻ ናቸው የሚመረጡት።

ማቴዎስ 22፡14 የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

ብዙዎች ስለ ወንድም ብራንሐም መልእክቶች ያውቃሉ ነገር ግን በአንዳንድ መሪዎች በመታለላቸው የእርሱን ንግግሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ አድርገው ያያሉ። ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶች ወደ ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልከው ገብተዋል።

እርሱ ያስተማራቸውን ትምሕርቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ እና ትምሕርቶቹ ትክክለኞች መሆናቸውን እንዲያዩ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የተመረጡት። እርሱ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተመሰረተ ማንኛውም ንግግር ትኩረት ሊሰጠው አይገባም።

በ30 ማይል ከፍታ ላይ የታየው የ1963ቱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የጌታ ዳግም ምጻት ነው ተብሎ ነበር፤ ከዚያም ሌላ ደግሞ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ ነው ተብሎም ነበረ።

ወንድም ብራንሐም ደመናው ከታየ ጥቂት ወራት እስኪያልፉ ድረስ እንኳ ስለ ደመናው አልሰማም ነበር። እርሱ ባለማወቅ ማርች 8 ቀን 1963 ሳንሴት ፒክ የተባለ ቦታ አጠገብ ከእርሱ ጋር ሲነጋጉ የነበሩ ሰባት መላእክት ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ ደመናው የተፈጠረ መሰለው። መላእክቱ በእርግጥ ሲሄዱ ደመና የፈጠሩት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከሳንሴት ፒክ 200 ማይል ርቆ የሚገኝ ፍላግስታፍ የተባለ ከተማ አጠገብ ነው። ዮሐንስ በራዕይ ባየው መልአክ እና በደመናው መካከል ምንም ተመሳሳይነት የለም።

መልአኩ ይህን የሚመስል ነው።

 

 

ደመናው ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን ፎቶ የሚመስል ነው።

 

 

በራዕይ ውስጥ ያለው መልአክ እንደ ፀሃይ የሚያበራ ፊት ያለው ነው።

ደመናው ከምድር 30 ማይል ያህል ከፍታ ላይ ቆይቷል ግን አልወረደም።

 

 

ወንድም ፔሪ ግሪን የፎቶውን ነገቲቭ ያወጣ ጊዜ (ከላይ እንደምታዩት) የዚያኔ ብቻ ነው ደመናው ውስጥ ፊት የሚመስል ምስል በስሱ ብቅ ያለው።

1965-0718

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል ከዚያ በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል።”

በስተመጨረሻ በ1965 ወንድም ብራንሐም ደመናው በሰማይ ላይ የሚታየው የሰው ልጅ ምልክት ነው አለ።

በሕይወቱ የመጨረሻ ወር ውስጥ በ1965 ወንድም ብራንሐም እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሙታንን የሚያስነሳውን የመላእክት አለቃ ድምጽ እየተጠባበቀ ነበር።

1965-1127

ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ታላቁ ድምጽ የተባለው ዊልያም ብራንሐም ሚስጥራትን ሲገልት ያስተማረበት ድምጽ አልነበረም።ታላቁ ድምጽ ሙሽራይቱ እራሷ እነዚያን ሚስጥራት ከመጽሐፍ ቅዱስ መግለጥ የቻለች ጊዜ ነው።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

“በታላቅ ድምጽ ጮኸ”። ኢየሱስ አላዛርን ከሙታን ከማስነሳቱ በፊት በታላቅ ድምጽ ጮኋል።

ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

የአንበሳው ድምጽ የሚሰማው ኢየሱስ እንደ መላእክት አለቃ ሙታንን ሲያስነሳ ነው። ይህም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው የተቀበሩትን ቅዱሳኑን ሊሰበስብ የሚመጣው የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ “በጮኸ ጊዜ” የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ተነስተዋል።

ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

“በታላቅ ድምጽ ጮኸ” እና “በጮኸ ጊዜ” ሁለቱም ከትንሳኤ ጋር የተያያዙ ቃላት ናቸው።

ስለዚህ በራዕይ 10፡3 የተገለጠው የመላእክት አለቃ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳንን ከሙታን ሲያስነሳ እናያለን።

“በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጎድጓዶች በድምጻቸው ተናገሩ።”

ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት ከትንሳኤ በኋላ ነው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ለመነጠቅ የሚያስፈልግ እምነት ይሰጡናል።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ከዚያ በኋላ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ያልተገለጡ ሰባት ነጎድጓዶች ይመጣሉ። አዎን። ደግሞም በእነዚያም ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ የምትነጠቅበት እምነት ይገለጣል፤ ምክንያቱም አሁን ባለንበት ሁኔታ ልንነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ ጨምረን ልንሄድ የሚገባን ነገር አለ። ለመለኮታዊ ፈውስ የሚያስፈልግ በቂ እምነት መለማመድ እንኳ አቅቶናል። ከመቅጽበት የምንለወጥበትና ከዚህ ምድር ላይ ተነጥቀን የምንሄድበት በቂ እምነት ያስፈልገናል።

በአዲስ የማይሞት አካል ውስጥ ከሆናችሁ ብቻ ነው መነጠቅ የምትችሉት። ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች አካላችን እንዴት እንደሚለወጥ ይነግሩናል።

ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ታላቅ ሚስጥር ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ አልተጻፉም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውረዋል።

የተገለጡ ጊዜ እጅግ በጣም እንግዳ ይሆኑብናል፤ እኛም መልእክታቸውን ስንሰማ እንንገዳገዳለን።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ነገር ግን አስቡ፤ አሁን ይህንን እየጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ሌሎቹን ማለትም ሰባቱን ነጎድጓዶች ሊጽፍ ሲያስብ “አታስብ” አለው።

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፡- “ለጊዜው አትጻፈው። ቆይ አንዴ። በዚያን ቀን እራሴ እገልጠዋለው። አሁን አትጻፈው ዮሐንስ ምክንያቱም ሲሰሙት ያንገዳግዳቸዋል። ለአሁን ተወው። ነገር ግን በዚያ ቀን እንዲገለጥ ሲያስፈልግ እገልጠዋለው።”

ነገሮች እየተወሳሰቡ ይሄዳሉ፤ ነውጦችም እየበዙ ይሄዳሉ። በየትኛውም የሰው ጥበብ ላይ መደገፍ አንችልም። በዘመናችን የሚከሰቱ ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ በመጽሐፍ ቅዱስ እየመረመርን ልንተረጉማቸው ያስፈልገናል።

ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዶናልድ ትራምፕ የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የማያሸንፍ መስሏቸው ነበር ምክንያቱም መጥፎ ሰው ስለነበረ ነው። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን እውቅና እሰጣለው አለ።

የዘመን መጨረሻ ላይ የተነሳው ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጧል፤ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እሥራኤል የሚመልስበት ሰዓት እየደረሰ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በሃሳቡ ውስጥ የነበረው ትልቅ ስዕል ይህ ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች ግን ዶናልድ ትራምፕ በግሉ የሚሰራቸው ስሕተቶች ላይ ትኩት አድርገው ተዘናግተው ነበር። በቁጥር 1.4 ቢሊዮን የሚሆኑ ሙስሊሞችን ተጋፍጦ መቆም ትልቅ ድፍረት ይጠይቃል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደግሞ ብዙ ድፍረት አለው።

በተመሳሳይ መንገድ ሙሽራይቱም የዊልያም ብራንሐምን ንግግሮች ወስዳ በመጽሐፍ ቅዱስ እንድትመዝነው ድፍረት ያስፈልጋታል።

ራዕይ 10፡5 በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥

6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ ወደ ፊት አይዘገይም፥… አለ።

ዘመን ያበቃል። ጊዜ የሚያመጣቸው ለውጦች እንድናረጅና እንድንሞት ያደርጋሉ።

ጊዜ የሚያበቃው ወደ ዘላለማዊነት ውስጥ ስንገባ ነው።

አልበር አይንሽታይን ጊዜ እና ሥፍራ እርስ በርሳቸው የተቆራኙ ናቸው ብሏል።

ስለዚህ ከባለ 4 ገጽታ ጊዜ መውጣት የምትችሉት ከባለ 3 ገጽታ ሥፍራ ስትወጡ ብቻ ነው። ለዚህም ከላይኛው ዓለም የሚመጣው አዲስ የማይሞት አካል ያስፈልገናል።

በጌታ ዳግም ምጻት ጊዜ ሙሽራይቱ ወደ ላይኛው ዓለም ተነጥቃ ትሄዳለች።

መጽሐፉ የተከፈተው መች ነው?

ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

“ይፈጸማል?” ይህ የሚናገረው ስለ ወንድም ብራንሐም አይደለም፤ እርሱ ምን ሊገልጥ እንደተላከ አውቋል።

ይህ የሚናገረው የወንድም ብራንሐምን ትምሕርቶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መልሳ በመውሰድ እውነቱን አጣርታ የምታምነውን ሙሽራ በተመለከተ ነው፤ እንደዚህ ስናደርግ እምነታችን ከጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት ጋር አንድ ይሆናል።

ከ1966 ወዲህ የሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ውስጥ ኖረናል። የእርሱ ስብከቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች ትርጉም እናውቅ ዘንድ በቂ መረዳት ይሰጡናል። እምነታችን ትክክለኛ መሆኑን ከዘፍጥረት ጀምረን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ ጥቅሶች አማካኝነት ተከታትለን እስከ ራዕይ ድረስ ባሉት መጽሐፎች መሰረት ማረጋገጥ አለብን።

“ይፈጸማል”። ወንድም ብራንሐም ሚስጥሮችን ገልጧል፤ ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ ለምንድነው የእግዚአብሔር ሚስጥር “ይፈጸማል” የሚለው? ወንድም ብራንሐም ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር ጠንቅቆ አውቋል። ሚስጥራቱ ተገልጠውለታል።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በሰባተኛው መልአክ ዘመን ማለትም ከ1947 እስከ 1965 አላለም። ይህ እርሱ ሲሰብክ እና ሚስጥራቱን ሲገልጥ የቆየበት ዘመን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ነው።

ስለዚህ ድምጹ የሚሰማበት ዘመን ከ1966 ጀምሮ ያሉት ዓመታት ናቸው። እነዚህን ሚስጥራት ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረን ማጣራት አለብን።

ራዕይ 10፡8 ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና፦ ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ ሲል ሰማሁ።

የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ ብቻ አይደለም።

ሌላኛውንም ድምጽ ከሰማይ መስማት አለብን። እርሱም የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ነው።

ለወንድም ብራንሐም በ1965 ወደተገለጠለት ወደተከፈተው መጽሐፍ ማለትም ወደ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንድንሄድ ይመራናል፤ ነገር ግን ለሙሽራይቱ ገና አልተገለጠላትም።

በሌላ አነጋገር ወንድም ብራንሐም የሰበከውን ስብከት ሰምተን ሃሳቦቹ እውነተኛ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ማረጋገጥ አለብን። ይህን የምናደርገው ኢየሱስ በኤማውስ መንገድ ላይ እየሄዱ ለነበሩ ደቀመዛሙርት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በመጠቀም ማንነቱን እንዳረጋገጠላቸው ነው።

2ኛ ቆሮንቶስ 13፡1 ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።

ቢያንስ ሁለት ምስክሮች ያስፈልጉናል። የነብዩ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተፈትሾ መረጋገጥ አለበት።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችን ማስረጃው መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት እርሱ እንዲመራን መፍቀድ መቻላችን ነው።

2ኛ ቆሮንቶስ 3፡6 እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምን እንደሚናገር ሚስጥሩ ሳይገለጥልን ፊደሉን ማንበብ ብቻ ብዙም ጥቅም የለውም።

ማቴዎስ 5፡18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

የብሉይ ኪዳን ሕግ እያንዳንዱ ገጽታው የሚያመለክተው ጥልቅ መንፈሳዊ እውነት አለ። ፍጥረታዊው ሕግ እና ሥርዓቶቹ አሁን ቀርተዋል ግን ጠለቅ ያለ ፍጻሜ አላቸው።

ለምሳሌ፡-

ዘሌዋውያን 19፡19 … ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።

የተልባ እግር የተባለው ጨርቅ የቅዱሳንን ጽድቅ ያመለክታል።

የበግ ጸጉር የሚያመለክተው ዳኞች በራሳቸው ላይ የሚያጠልቁትን ጸጉራም ኮፍያ ነው።

የበግ ጸጉር እና የተልባ እግር አለመቀላቀል አሁን ጠለቅ ያለ ፍጻሜ ስላገኘ ይህንን ሕግ እንደ ወረደ መፈጸም አይተበቅብንም።

የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ቅዱሳን በፍርድ ቀን ሊፈረድባቸው አይሄዱም። እነርሱ ራሳቸው ይፈርዳሉ እንጂ።

ጻድቃን ወደ ፍርድ አለመምጣታቸው በተጨማሪ የቀረው ዓለም በሙሉ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወደ ፍርድ ሲገቡ ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ስለመነጠቋ ያመለክታል።

1ኛ ቆሮንቶስ 6፡2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን?

ራዕይ 19፡8 … ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

ዳንኤል 7፡9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ …

10 … ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።

ስለዚህ ሕጉ ከፍ ከፍ ይደረጋል። ሕጉ ከእንግዲህ በሥጋ ስለሚከናወኑ ድርጊቶች የሚያመለክት ሳይሆን ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ትርጉም የሚሰጥ መልእክት ሆኗል።

ፍጥረታዊ የሆነው የፋሲካ በግ በቀራንዮ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ በተሰዋው በኢየሱስ ሞት ፍጻሜ አግኝቷል።

ኢሳይያስ 42፡21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።

ዘሪ ሊዘራ ወጣ በሚለው ምሳሌ ውስጥ መልካሙ መሬት አንድ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለመረዳት ያለውን ችሎታ ያሳያል።

ማቴዎስ 13፡23 በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።

ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን በተዓምራት ባበላ ጊዜ ሰዎች አንበላም ብለው የመለሱት ቁርስራሽ መጠኑ ለምን 12 መሶብ እንደሆነ ደቀመዛሙርቱ እንዲያስተውሉ ፈልጓል።

ማቴዎስ 16፡9 ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

ኢየሱስ 4,000 ሰዎችን ባበላ ጊዜ ሰዎችን አንበላም ብለው የመለሱት ቁርስራሽ ለምን 7 መሶብ ሙሉ እንደሆነ ደቀመዛሙርቱ እንዲያስተውሉ ፈልጓል።

ማቴዎስ 16፡10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

የፈሪሳውያን ትምሕርት እንደ እርሾ ነበረ፤ ስለዚህ በዘመኑ የነበሩ አይሁዶችን ያቦካቸዋል፤ ማለትም የኢየሱስን ወንጌል እንዳይቀበሉ ያደርጋቸዋል።

ከዚያም በኋላ ደቀመዛሙርቱ ሕዝቡ አንቀበልም ብለው የጣሉትን የወንጌል ቁርስራሽ ሰብስበው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አድርገው ለሁለት ወገኖች ያቀርቡታል፤ እነዚህም ሁለት ወገኖች በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን እና 144,000ው መሲሃቸውን በሚቀበሉበት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሚገኙት 12 የእሥራኤል ነገዶች ናቸው።

12 እና 7 በብሉይ ኪዳን ቤተመቅደስ ውስጥ የምናገኛቸው ሁለት ቁጥሮች ናቸው።

 

 

ባለ 7 ቅርንጫፉ መቅረዝ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚበራውን የወንጌሉን ብርሃን ይወክላል።

12ቱ የእሥራኤል ነገዶች የተመሰሉት በ12ቱ እንጀራዎች ወይም የገጹ ሕብስት ነው፤ እነዚህም እንጀራዎች በቅዱሱ ሥፍራ ነው የሚበሉት። ለዚህ ነው አይሁዶች መሲሁን ለመገናኘት ወደ እሥራኤል እየተመለሱ ያሉት።

ኢየሱስ የዳኑ ሰዎች ሁሉ ራስ ነው፤ እነርሱ ደግሞ የእርሱ አካል ናቸው።

ራስ ከአካል ጋር የሚገናኘው በአከርካሪ ወይም በጀርባ አጥንት ነው። ከአንገት ጀምሮ የመጀመሪያዎቹ አጥንቶች ወደ ታች ሲቆጠሩ 7 ናቸው። ከዚያ ቀጥሎ ያሉት 12 አጥንቶች ከጎድን ጋር የተያያዙ ናቸው።

 

 

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛነት በሦስተኛ ደረጃ የሚመሰክረው ተፈጥሮ ነው።

ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሙሉ የሚፈጽምበት ቦታና ሰዓት ላይ ደረሰ።

ማርቆስ 1፡9 በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።

ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? አንዳችም ሐጥያት አለነበረበትም።

2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።

ኢየሱስ የሐጥያት መስዋእታችን ነው። የሐጥያታችንን ዋጋ በሙሉ ለመክፈል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከዚያም እንደሚለቀቀው ፍየል ሐጥያታችንን ተሸክሞ ከእኛ አርቆ ወስዶ ሐጥያተኞች በሚቃጠሉበት ቦታ ሲኦል ውስጥ አራገፈው። እርሱ እራሱ ግን ፍጹም ስለነበረ ሐጥያታችንን በዲያብሎስ ላይ ለማራገፍ በሲኦል እሳት ነበልባሎች መካከል እየተራመደ ቢሄድም አልተቃጠለም።

ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥

ስለዚህ ሰው መተንፈስ በማይችልበት ሁኔታ ከውሃ ስር መስመጥ ሥጋው ያረፈበትን መቃብር ያመለክታል፤ በዚያኑ ሰዓት መንፈሱ ሲኦል ውስጥ ገብቶ ድል እያደረገ ነበረ። ከእርሱ ውስጥ የወጣው ቅዱስ መንፈስ የሚቃጠል መስዋእታችን ነው። ቅዱሱ መንፈስ ሐጥያታችንን ተሸክሞ በእኛ ፈንታ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ነገር ግን ፍጹም ቅዱስ ስለነበረ በሲኦል ውስጥ ያሉ አጋንንትም ሆነ የሲኦል እሳት ሊነኩትም ሊያቃጥሉትም አልቻሉም። ስለዚህ ሲኦል ውስጥ በገባ ጊዜ ሐጥያታችንን ሁሉ የሐጥያት አባት በሆነው በሰይጣን ላይ አራገፈው።

ከሞተ በኋላ በመንፈሱ ሆኖ ነው ወደ ሲኦል የወረደው።

ከዚያም ኢየሱስ በሰይጣን፣ በሞት፣ በሲኦል እና በመቃብር ላይ ድልን ተጎናጽፎ ከሙታን ተነሳ።

ማርቆስ 1፡10 ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና፦ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥

ከውሃው ውስጥ መውጣቱ ከሙታን የመነሳቱ ተምሳሌት ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የመለኮት ሙላት ማለት በሰውነቱ ውስጥ ያደረው የእግዚአብሔር መንፈስ በሙሉ ነው። ነገር ግን ልክ የአንድ ሰው ምስል ሰውየው ከቆመበት ቦታ ውጭ በዓለም ዙርያ በቲቪ የትም መታየት እንደሚችል ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስም በአንድ ጊዜ የትም ቦታ መገኘት ይችላል።

የእግዚአብሔር በግ (ሰው የሆነው ኢየሱስ) በእርግብ መልክ ባረፈበት በታላቁ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅባት ነው የተመራው።

ይህ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። እግዚአብሔር ይመራን ዘንድ በውስጣችን በሚኖረውና በሚቀባን በእግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንፈስ ነው መመራት ያለብን።

ማርቆስ 1፡11 በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።

ክርስቲያኖች ድምጹ የመጣው “ከእግዚአብሔር አብ” ነው ይላሉ። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ውስጥም ሆነ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወንጌሎች ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ አንድ ጊዜ እንኳ ተልተጻፈም።

የኢየሱስ አባት ማነው?

የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያስቀምጥ ሰው ለተጸነሰው ሕጻን አባቱ ነው።

ማቴዎስ 1፡18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

20 … የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።

ኢየሱስ የተባለውን ሰው “የምወደው ልጄ” ብሎ የተናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው።

ኢየሱስ በሰውነቱ የነበረው ስኬት ሚስጥሩ ያለ አንዳች ማንገራገር ለእግዚአብሔር መንፈስ መታዘዙ ነው፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጡ አድሯል፤ ከላይም ደግሞ ቀብቶታል።

ማርቆስ በ11 ቁጥሮች ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስን የይሁዳን አውራጃ እንዳንቀጠቀጠ እና ኢየሱስን እንዳጠመቀ ታላቅ የእግዚአብሔር ባሪያ ያስተዋውቃል። ይህ ሰው በኃይል የተሞላ ሰው ነበረ። ይሁዳ ላይ እንደ መንፈሳዊ አውሎ ነፋስ ነው የወረደባት።

የታላቅ ባሪያ ወይም አገልጋይ ባሕርያት ብቁ ሆኖ መገኘት፣ በኃይል መሞላት እና የተሰጠውን ሥራ ጠንቅቆ ማወቅ ናቸው።

ማርቆስ ቀጥሎ ከዮሐንስም የሚበልጥ ታላቅ አገልጋይ አስተዋውቆናል። ይህም ታላቅ አገልጋይ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ለራሱ እረፍትና ድሎት ያልፈለገ ታታሪ የሥራ ሰው ነበር። ግቡ ምን እንደሆነ በማወቅ እራሱን ሳይቆጥብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በትጋት አከናውኗል።

ማርቆስ 1፡12 ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።

“ወዲያው”። በኢየሱስ ዘንድ ስንፍና ዳተኛነት አልነበረም። ሁልጊዜ የሥራ ሰው ነበረ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ የእኛ የግል ፈቃድ አይደለም።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰዎች መካከል ነጥሎ ከታዋቂነትና ዝነኝነት ነጥሎ ወደ ምድረበዳ ሲመራው በመታዘዝ ምሳሌ ትቶልናል።

እኛ ሰዎች ምቾት ሲበዛብን አናድግም።

በደረቅ ምድረ በዳ ውስጥ ምንም ምቾት የለም።

የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዎችን ቀርጾ አስተካክሎ ለፈቃዱ እሺ ብለው እንዲገዙ የሚለውጣቸው በምድረ በዳ ውስጥ ነው።

ከፊታችን ከባድ ጉዞ ይጠብቀናል። ክርስትና ለልፍስፍሶች አይደለም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23