ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 11
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የክርስትና ሕይወት ትልቁ ቁምነገሩ የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና ማድረግ ነው።
First published on the 4th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022ሉቃስ ይህንን ታዋቂ ጸሎት ሙሉ ቃሉን ጽፎልናል።
ሉቃስ 11፡2 አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
3 የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤
4 ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።
ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ሰው አድርጎ ነው የገለጸልን።
ሉቃስ ይህንን የጌታችንን ጸሎት ጽፎ ሳይጨርስ እዚህጋ ያቆመዋል፤ ምክንያቱም ይህ ክፍል እኛን ሰዎችን የሚመለከት ነው።
እግዚአብሔር በሰማያት ሆኖ በምድር የሚከናወነውን ነገር ሁሉ ከሰማያዊ እቅዱ ጋር አብሮ የሚሄድ እንዲያደርግልን እንፈልጋለን (እንጂ ከራስ ወዳድ ፍላጎቶቻችን ጋር እንዲሄድልን አይደለም)። እግዚአብሔር የምንበላውን ምግብ ሊሰጠንና በደላችንን ይቅር ሊለን ያስፈልገናል (እኛ ደግሞ በምላሹ የበደሉንን ይቅር እንላለን) እግዚአብሔር ከፈተና ሊጠብቀን ያስፈልገናል (ይህም እኛ ደካሞችና በቀላሉ በፈተና ልንወድቅ የምንችል መሆናችንን ያሳያል)። ስለዚህ ይህ ድንቅ ጸሎት ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ ልንደገፍ እንደሚያስፈልገን ያመለክታል።
ሉቃስ ሰውን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው አትኩሮ የጻፈው። ሉቃስ ሳይጽፈው የተወው የጸሎቱ የመጨረሻ ክፍል እግዚአብሔርን ብቻ የሚመለከት ነው፤ ምክንያቱም መንግሥትም፣ ኃይልም፣ ክብርም ለዘላለም የእግዚአብሔር ነው። (የእግዚአብሔር እቅድ ዘላለማዊ እንጂ እኛ ብዙውን ጊዜ ለምንጸልይባቸው ጊዜያዊ ጥቅሞች አይደለም።)
ሉቃስ የኢየሱስ ሰብዓዊነት ላይ ትኩረት አድርጎ ነው የጻፈው፤ በዚህም ከኢየሱስ ጋር እንዴት ሕብረት እንደምናደርግ ያስተምረናል።
እኛ ሰዎች ጸሎታችንን ፍሬያማ የምናደርገው እንዴት ነው?
ኢየሱስ እንዳለው እግዚአብሔር አንድ ነገር እንዲያደርግልን ስንጠይቀው ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌለው ሰው ነው መቅረብ ያለብን።
ሉቃስ 11፡9 እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
10 የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል።
13 እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?
እግዚአብሔር ጸሎትን በመልካም መንገድ ይመልሳል። ይህም ማለት የጠየቅነውን ባያደርግልን መጠየቅ የሌለብንን ነገር ጠይቀናል ማለት ነው፤ እርሱም ቢሰጠን ሊጎዳን የሚችል ነገር ነው የሚሆነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለጸሎታችን ሲመልስልን በሚያደርገው ውሳኔ በፍጹም ልባችን እርሱን መታመን አለብን።
አሁን ደግሞ ሉቃስ የሰዎችን ትልቅ ችግን ለይቶ ያሳየናል፤ ይህም ክፉ መናፍስት እንዲቆጣጠሩን መፍቀዳችን ነው።
ኢየሱስ አንድ ዲዳ የሆነ መናገር የማይችል ሰውን መረጠ።
ከዲዳው ሰውዬ ውስጥ ጋኔኑን ገስጾ አስወጣው። ከዚያ ሰውዬው አንደበቱ ተፈታና መናገር እንደቻለ ወዲያው ሕዝቡ ኢየሱስን አንተ ብኤል ዜቡል ወይም የአጋንንት አለቃ ነህ ብለው ከሰሱት።
ሉቃስ 11፡14 ዲዳውንም ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ ሕዝቡም ተደነቁ፤
17 እርሱ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁሉ ትጠፋለች፤ ቤትም በቤት ላይ ይወድቃል።
18 እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?
ሰይጣን የራሱን አጋንንት የሚያስወጣቸው ከሆነ መንግሥቱ እርስ በርሷ ተከፋፍላለችና ልትቆም አትችልም።
ኢየሱስ ከሰይጣን በላይ ብርቱ እንደሆነና በሰይጣን ላይ ስልጣን እንዳለው ተናገረ።
ስለዚህ ኢየሱስ ብኤል ዜቡል ወይም ዲያብሎስ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እርሱ ከዲያብሎስ የበለጠ ኃያል ነው።
በጨለማው መንግሥት ውስጥ አጋንንት ለዲያብሎስ ይታዘዛሉ። ስለዚህ በብርሃን ውስጥ ለመሆን እኛ ሰዎች ለኢየሱስ መገዛትና ለእርሱ መታዘዝ አለብን።
እርሱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሲፈጽም አብረነው ባንሆን ሃሳባችን ቅን ቢሆንም እንኳ ጥረታችን ከንቱ ነው የሚሆነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊሰበስብ የሚፈልገውን የእኛ ጥረት ይበትነዋል።
አጋንንት ከሰው ውስጥ ከወጣ ያ ነጻ የወጣው ሰው በትጋት እግዚአብሔርን ማገልገል አለበት። ያ ሰው መልሶ አጋንንቱን ወደ ውስጡ ቢያስገባ አጋንንቱ ከሌሎች ሰባት አጋንንት ጋር ሆኖ ነው የሚገባበት።
ለምንድነው ሰባት ሆነው የሚገቡት?
ሉቃስ 11፡24 ርኵስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባያገኝም፦ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤
አንድ ሰው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርቶች የሚመልሰን ነብይ እንዳለ ወደ ማወቅ ሲመጣ፤ በቡድን የተከፋፈሉት ቤተክርስቲያኖች መንፈስ ይለቀዋል፤ ምክንያቱም የቡድናዊነት መንፈስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አብሮ መቆም አይችልም።
ለምሳሌ ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ገቡ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ልታገኙ አትችሉም። (የገቡት ቤት ውስጥ ነው።) ደግሞም ለአራስ ሕጻን ልጅ ሰገዱ የሚልም ቃል የለም። (ከአራስነት አልፎ ነበር።) መጽሐፍ ቅዱስ ልደቱን እንድናስብ አላዘዘንም። ዲሴምበር 25 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቀን አይደለም። ክሪስማስ ወይም ገና የሚባል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። የገና ዛፍ ኢየሱስ ከተወለደበት በረት ጋር ምንም ዝምድና የለውም። (“ሳንታ” የሚለው ቃል ውስጠ “ን” ፊደልን ቦታዋን ብትቀይሩዋት “ሳታን” ማለትም ሰይጣን የሚል ቃል ይሰጣችኋል።) ስለዚህ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ሊከተል ቢፈልግ ቤተክርስቲያኖች ክሪስማስን ሲያከብሩ አብሮ ማክበር አይመቸውም።
ሉቃስ 11፡25 ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል።
መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመከተል ወስኖ ሰው ሰራሽ የሆኑ ልማዳዊ የቤተክርስቲያን ወጎችን የሚተው ሰው የጸድቃል፤ ይቀደሳል፤ ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ብቻ በመጠቀም ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ውሃ ጥምቀት፣ የቤተክርስቲያን ዘመናት፣ እና ስለ መጀመሪያው ሐጥያት እውነቱን እንዴት አድርጎ እንደሚያውቅ ይማራል።
በጣም የሚያሳዝነው ግን እውነቱን መረዳት የጀመረ ሰው ከጊዜ በኋላ በፓስተሮች ተጽእኖ ስር ይሆንና መጽሐፍ ቅዱስን ማመን ይተዋል። ይህ ሰውም ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ቃል እና የኢየሱስ “አዲስ ስም” ማን እንደሆነ ይማራል። ይህ ሰው በተጨማሪም ኢየሱስ በ1963 ከፍላግስታፍ አሜሪካ በረሃ በላይ በታላቅ ደመና እንደመጣ (እንደተገለጠ) ይማራል። ይህ ከምድር በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የነበረ ደመና በምድርና በባሕር ላይ ሊቆም የወረደ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ነው ተብሎ ይታሰባል። የአደን ወቅት ገና ያልተከፈተ ቢሆንም እንኳ ደመናው ፎቶ በተነሳ ጊዜ ዊልያም ብራንሐም ከደመናው ስር እንዲሆን ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን የአደን ወቅት ገና ስላልተጀመረ እርሱ በዚያን እለት በአካባቢው ዝር እንኳ አላለም ነበር።
ተከታዮቹ እርሱ የተናገራቸውን ጥቅሶች ሰብስበው ደበላለቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጎን ጣሉ፤ ግምቶችና የአእምሮ ጨዋታዎች ውስጥ ገብተው ቀሩ። ደግሞም ከእነርሱ ጋር አልስማማ ብትሉ እና እነርሱ ከሚሉት የሚቃረኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብታሳዩዋቸው በጣም ይናደዱባችኋል። ነገርን ግን ዊልያም ብራንሐም ራሱ እነዚህኑ ሃሳቦቻቸውን የሚቃረኑ ብዙ ንግግሮች ተናግሯል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያልተደገፉትን እነዚህን ሃሳቦች አንድ ሰው ተቀብሎ ማመን በቻለ ጊዜ በቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ከነበረበት ጊዜ ይልቅ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ወድቋል ማለት ነው። ዊልያም ብራንሐም ሁልጊዜ ዓላማው እኛን ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሊመልሰን መሆኑን ተናግሯል፤ እነዚህ ሃሳቦች ሁሉ ግን በአዲስ ኪዳን ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ አልነበሩም።
የትኛዋም የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በፓስተር አልተገዛችም፤ ፓስተሩ(ሯ) ብቁ፣ ማራኪ ወይም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም እንኳ ቤተክርስቲያን በፓስተር አልተገዛችም።
ሉቃስ 11፡26 ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሌሎችን ሰባት አጋንንት ከእርሱ ጋር ይይዛል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል።
ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖችን የሚከተል ክርስቲያን ከዊልያም ብራንሐም ትምሕርቶች ውስጥ እውነትን እንደ አጋጣሚ ሊማር ይችላል።
ነገር ግን ከቡድናዊ ቤተክርስቲያን ከወጣና የተወሰኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን ከተማረ በኋላ በተንኮለኞች ጥበብ የተቀናበሩ የሰው ንግግር ጥቅሱች እውነት ናቸው ብሎ እስከሚያምን ድረስ ሊታለል ወይም ተጽእኖ ሊደረግበት ይችላል። በዚህም መንገድ (ጸንቶ እንዲቆም ሲጠበቅበት) መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለተኛ ጊዜ ይክዳል፤ ደግሞም የሰው ንግግር ጥቅሶችን መከተል ይጀምራል “ሜሴጅ ውስጥ ናቸው” ይላል። ይህን አይነቱን አደገኛ ስሕተት ወደ አእምሮው ውስጥ ካስገባ በኋላ ለዘመናችን የሚሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፈልጎ የማግኘት እድሉ እጅግ የመነመነ ነው።
እና “የሜሴጅ” አማኞች እንዴት ነው እንዲህ ሁሉ እርስ በርሱ የሚጣላ እምነት ውስጥ ሊገቡ የቻሉት?
ምክንያቱም በዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመናችን ውስጥ ካለፉት ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ተሰባስበው የተለቀቁ ተንኮለኛ አታላይ ክፉ መናፍስት አሉ።
ሰባት ክፉ መናፍስት የሚያመለክተው ከሰባት የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጣ አታላይ መንፈስን ነው።
ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ለመመለስ ከቡድናዊ ቤተክርስቲያን ከወጣህ በኋላ እንደገና የቡድናዊ ቤተክርስቲያን መንፈስ ተመልሶ ወደ ውስጥህ እንዲገባ አትፍቀድ። ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች ትምሕርቶቻቸውን እንዳይፋለሱ አድርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በስነሥርዓት አዛምደው አያስተምሩም።
በፓስተር የሚገዙ ቤተክርስቲያኖችና በዘመናዊ የሰው ንግግር ጥቅሶች እንዲሁም የጥቅሶች ትርጓሜዎች ላይ የተመሰረቱ አስተምሕሮዎች በፍጹም የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን አካል አልነበሩም።
እምነትህ ትክክለኛ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተጠቅመህ ማሳየት ካልቻልክ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲሰሩ ለነበሩ የስሕተት መናፍስት በር የሚከፍት ሰው ሰራሽ ሥርዓት እየተከተልክ ነህ ማለት ነው። እነዚህ በአንድነት የተቀናጁ መናፍስት እናንተ እና እኔ ልንቆጣጠራቸው ከምንችለው በላይ ተሸሎክላኪዎችና ተንኮለኞች ናቸው። ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ብቻ ነው ከእነዚህ አታላዮች ሊጠብቀን የሚችለው።
የ“ሜሴጅ” ቡድኖች ልክ እንደ ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በታማኝነት መከተል አቁመዋል። “የሜሴጅ” ቡድኖች ግን የሚያመካኙት የላቸውም። መጀመሪያ ልክ እንደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ የተመሰረተ እውነት እንዲያምኑ ተምረው ነበር።
ደግሞም ከዚህም በላይ የከፋው ነገር ግለሰቦች በ“ሜሴጅ” ቤተክርስቲያን ለመታቀፍ ብለው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲከተሉ የሚነግሩዋቸውን ሰዎች ሁሉ አጥብቀው ይቃወማሉ።
ከመጽሐፍ ቅዱስ የሆነውን እውነት በተቃወምክ ጊዜ ራስህን ከእግዚአብሔር ትለያለህ።
የኮምዩኒዝም ታሪክ እንደሚመሰክርልን ኮምዩኒስቶች ከሌኒን ትምሕርት በራቁ መጠን ለሌኒን ያላቸው አክብሮት ወደ አምልኮነት እስኪለወጥ ድረስ ነው የጨመረው።
ስለ “ሜሴጅ” ቤተክርስቲያኖችም ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል። ዊልያም ብራንሐም ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሊመልሰን ካደረገው ጥረት እየራቁ በሄዱ ቁጥር ዊልያም ብራንሐምን ከፍ ከፍ እያደረጉ ንግግሩቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ እስኪያከብሩ ደርሰዋል።
አሁን ደግሞ ሉቃስ የተወለድንበት ቤተሰብ በእግዚአብሔር ፊት አንዳችም ነጥብ እንደማያስቆጥርልን ይስረዳናል።
ሉቃስ 11፡27 ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦ የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው።
አንዲት ሴትዮ ማርያም ኢየሱስን የመሰለ ልጅ ስለወለደች የተባረከች ናት ብላ ጮኸች። ይህ አይነቱ አስተሳሰብ የኢየሱስ (ወይም የነብይ) ቤተሰብ ከሌለው ሰው የተሻለ ክብር አለው ይላል።
ሉቃስ 11፡28 እርሱ ግን፦ አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።
ኢየሱስ ግን እንዲህ አላት፡- “የለም፤ ማንም ሰው በቤተሰባዊ ዝምድና ምክንያት መንፈሳዊ በረከት ሊያገኝ አይችልም።”
የእውነት የተባረኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሰምተው በቃሉ እምነት የሚጸኑ ሰዎች ናቸው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚኖሩ ሰዎች፤ ደግሞም ከመጽሐፍ ቅዱ ብቻ የሚሰብኩ ሰዎች፤ መጽሐፍ ቅዱስንም የማይቃረኑ ሰዎች የተባረኩት እነርሱ ናቸው።
ኢየሱስ ለክፉው ዓለም የሚደረግለት ምልክት የእርሱ ከሙታን መነሳት ብቻ ነው ብሎ ተናገረ።
የኢየሱስ ትንሳኤ በዓለም ላይ ከተከሰቱ ክስተቶች ሁሉ ይበልጥ አስደናቂ ክስተት ነው። የመጨረሻው ጠላታችን ሞት ነው። ከመቃብር በመውጣት ሞትን ያሸነፈ አንድም የሐይማኖት መሪ የለም። የኢየሱስ ትንሳኤ ልዩ ክስተት ነው።
ከትንሳኤው ጋር ሊፎካከር የሚችል ሐይማኖት የለም። ሐጥያተኞች ትንሳኤው ምንም የማይደንቃቸው ከሆነ ሌላ ሊያሳምናቸው የሚችል ምንም ምልክት የለም።
ሉቃስ 11፡31 ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።
የሳባ ንግሥት እግዚአብሔር ለሰሎሞን የሰጠውን ጥበብ ለመስማት ከነበራት ጥማት የተነሳ የሰሃራ በረሃን አቋርጣ ሳትሄድ አትቀርም። ያለጥርጥር እውነትን ለማግኘት ትልቅ ጥረት አድርጋለች።
ስለዚህ ከዚህ የምንረዳው የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ለማግኘት ይበልጥ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልገን ነው። በተደላደለ ወንበር ተቀምጦ በቤተክርስቲያን ሙዚቃ መዝናናት፤ ማንም ሰው የተለየ ሃሳብ እንዲያስብ የማይፈቀድለት ቦታ መቀመጥ ኢየሱስ እውነትን ለማግኘት ዋጋ የሚያስከፍል ከባድ መንገድ ብሎ የተናገረለት አይደለም።
ሉቃስ 11፡32 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
በዘመናት ውስጥ ነነዌ በክፋትዋ አንደኛ ከተማ ነበረች። ነገር ግን የነነዌ ሰዎች ንሰሀ ገቡ።
ዳጎን የሚባለውን የዓሳ አምላክ ያመልኩ ነበር። ዓሳ ነባሪ ዮናስን ዋጠውና ከሦስት ቀናት በኋላ በባሕር ዳርቻ ተፋው። አረማውያኑ ተገረሙ። ዮናስ ተውጦ ስለነበረ ሦስት ቀን ሙሉ እንደሞተ ተቆጥሮ ነበር። አረማውያኑ የሚያመልኩት የዓሳ አምላክ ወደ ውሃ ዳር እየዋኘ መጥቶ ዮናስን በተፋው ጊዜ አምላካቸውን ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ በመገረም አዩ። ትውከቱን ትኩረት ሳያደርጉበት ከዓሳው አምላካቸው አፍ የወጣ ነብይ ሲመጣላቸው በደስታ ተቀበሉት። ይህም ከሙታን እንደመነሳት ነበር። ከዚያ በፊት እንደዚያ ያለ ነገር አረማውያኑ አይተው አያውቁም ነበር። ከዚያ በኋላም ሁለተኛ እንደዚያ ያለ ነገር አላዩም። ስለዚህ ዮናስ ሲናገር አደመጡ። የዚህ ተዓምር ወሬ በነነዌ ውሰጥ ተሰራጨ፤ ሕዝቡም የዮናስን መልእክት ሰምተው ንሰሃ ገቡ። ይህ “ከሙታን የተነሳ” ነብይ በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ በታላቅነቱ የታወቀውን መንፈሳዊ ተሃድሶ መሪ ሆነ፤ በዚህ ተሃድሶ ውስጥ 120,000 ክፉ አረማውያን ንሰሃ ገቡ።
ለሦስት ቀን በዓሳ ተውጦ ለነበረ ሰው እንደዚያ አይነት አክብሮት የሞላው ምላሽ ከሰጡ ኢየሱስ ደግሞ የማያምኑ ሰዎች ሐሙስ እለት ሞቶ እሁድ እለት ከመቃብር በወጣበት በትንሳኤው ከዚያም በላይ እንዲገረሙ ይጠብቅባቸዋል። ይህም ሞት እና ትንሳኤ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ የተደረገ ድንቅ ነው።
ከዚህ ውጭ ሌላ ምልክት አያስፈልገንም?
ኢየሱስ ራሱን ከሞት ካስነሳ እኛን መኩታን ለማስነሳት ምንም አይቸገርም።
ከነሥጋው ከሙታን መነሳቱን ካላመንን ከነነዌ ሰዎች የባስን ክፉዎች ነን፤ እነርሱን ዮናስ ባደረገው የትንሳኤ ጥላ በሆነ ምልክት አምነዋል።
ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎችን በቁጣ ማውገዝ ጀመረ።
ሉቃስ እዚህጋ አንድ አሳዛኝ ማስታወሻ አስቀምጧል። የሐይማኖት መሪዎች ጥሩ ሰዎች ናቸው፤ ቅኖችና የተቸገረ ሰውን ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ መሪ ሰዎች የእርሱን አመለካከት እንዲከተሉ ያደርጋል። በአሁኑ ሰዓት ከ30,000 በላይ የተለያዩ ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎች ጥሩ ሰዎች ናቸው፤ እውነትን የምትፈልጉ ከሆነ ግን ምንም ሊረዱዋችሁ አይችሉም።
ሉቃስ 11፡37 ይህንንም ሲናገር አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምሳ ይበላ ዘንድ ለመነው ገብቶም ተቀመጠ።
38 ከምሳም በፊት አስቀድሞ እንዳልታጠበ ባየው ጊዜ ፈሪሳዊው ተደነቀ።
የቤተክርስቲያን መሪዎች ሽክ ብለው ነው የሚለብሱት፤ ውድ መኪኖችን ይነዳሉ፤ በተሸለሙ ውድ ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ። ማራኪዎችና ሰውን ወዳጆች ይመስላሉ። በውጭ ሲታዩ ውብ ናቸው።
ነገር ግን በቡድናዊ ቤተክርስቲያኖቻቸው ውስጥ የሚያስተምሩትን ትምሕርታቸውን ብትመረምሩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ አይደሉም። ስለዚህ ነው ኢየሱስ የሚያወግዛቸው።
ሉቃስ 11፡39 ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል፡፡
ኢየሱስ እንደተናገረው የሐይማኖት መሪዎች ውጪያቸውን በሐይማኖታዊ ስርዓት፣ በሙዚቃ፣ እና በማራኪ ስብከት ያሳምራሉ፤ በውስጣቸው የሞላው ግን ክፋትና ስግብግብነት ነው። የጥንቷን ቤተክርስቲያን እምነት አያንጸባርቁም። የጥንቷን ቤተክርስቲያን እምነት ቢከተሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካላቸው ስልጣን ይባረራሉ። የሚያምር አፕል ግምጥ ስታደርጉ ውስጡ ግን የበሰበሰ ሆኖ አጋጥሟችሁ ያውቃል?
ኢየሱስ ስለ ሐይማኖት መሪዎች የተናገረው ይህንን ነው።
ሉቃስ 11፡42 ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከጤና አዳም ከአትክልትም ሁሉ አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ ስለምትተላለፉ፥ ወዮላችሁ፤ ነገር ግን ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉት ይገባችሁ ነበር።
መሪዎች እንደ አስራት ስለመክፈል የመሳሰሉ ጥቃቅን ሥርዓቶች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ለመጽሐፍ ቅዱስና እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለማሳየት አንዳችም ፍቅር የላቸውም። ሕዝቡ ክሪስማስ ወይም የገና በዓልን ይወዳሉ፤ ስለዚህ ሰባኪዎች ተወዳጅነታቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለውን ቀን እና ዛፍ ደግፈው ያስተምራሉ። ለአየሱስ ሦስት ስጦታዎችን ይዘው የመጡት ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ አለመግባታቸውን በጭራሽ ገልጠው አይናገሩም። ሁለት ዓመታ ካለፈ በኋላ መጥተው እቤት ውስጥ ነው የገቡት። ሕዝቡ ግን ስጦታዎቹን ይወዳሉ፤ ስለዚህ የቡድናዊ ቤተክርስቲያናት ሰባኪዎች ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ገቡ ብለው በማስተማር ተወዳጅነታቸውን ያስጠብቃሉ። ስለ እውነት ግድ አይላቸውም። ግድ የሚላቸው ሕዝቡን ማስደሰት ነው።
የእውነት መመዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ስጦታ የሚወዱ ሰዎች ስሜትና ስግብግብነት አይደለም የእውነት መመዘኛው።
ሉቃስ 11፡43 እናንተ ፈሪሳውያን፥ በምኵራብ የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ።
የሐይማኖት መሪዎች በሰዎች ፊት የሚታዩበትንና በሰዎች አእምሮ ውስጠ ክብር የሚያገኙበት ፊት ለፊት ያለውን ወንበር ላይ መቀመጥ ይወዳሉ። ፓስተሮች በአደባባይ ፓስተር ተብለው ሰላምታ መቀበልን ይወዳሉ። ስለዚህ ስታገኙዋቸው “እከሌ” ብላችሁ ስማቸውን ብቻ በመጥራት ሰላም ልትሏቸው አትችሉም፤ የግድ “ፓስተር እከሌ” ማለት አለባችሁ።
ኢየሱስ ግን በዚህ ተገርሞ አያውቅም።
ሉቃስ 11፡44 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበት የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።
ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎች የሚራመዱ እሬሳዎች ናቸው አለ። የተደበቁ መቃብሮች ናቸው። ስለዚህ ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደ ሞት ነው የሚወስዷቸው። እንደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ካልተመራችሁ ብትድኑም እንኳ ወደ ታላቁ መከራ ለመግባት መንገድ ጀምራችኋል። ኢየሱስን እንደ አዳኝ መቀበል ከሲኦል ያድናችኋል። ከታላቁ መከራ ለመዳን ግን እግዚአብሔርን በመንፈስ እና በእውነት ማገልገል ያስፈልጋል።
ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
እግዚአብሔር የቃሉን እውነት ሲገልጥ ሰዎች መሃይም ሆነው ለመቅረት ምንም ማመካኛ የላቸውም። እውነትን ሳናውቅ የምንቀረው መጽሐፍ ቅዱስን ከምንወደው በላይ የቤተክርስቲያናችንን ወጎችና ሰው ሰራሽ ትምሕርቶች የምንወድ ከሆነ ብቻ ነው።
ለነብያቶቻቸው ያማሩ ያጌጡ መቃብሮችን ሰሩላቸው፤ ነገር ግን ነብያቶቻቸውን የገደሉት እራሳቸው ናቸው።
የሐይማኖት መሪዎች ስልጣናቸውን፣ ተጽእኖዋቸውንና፣ ገንዘብ ለማግኘት ያላቸውን እድል ማጣት አልፈለጉም።
እውነትንም ደግሞ አልፈለጉም።
ሉቃስ 11፡53-54 ይህንም ሲናገራቸው፥ ጻፎችና ፈሪሳውያን በአፉ የተናገረውን ሊነጥቁ ሲያደቡ፥ እጅግ ይቃወሙና ስለ ብዙ ነገር እንዲናገር ያነሣሡ ጀመር።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ማለትም ቃሉ እንዲሞት ፈለጉ።
የሐይማኖት መሪዎች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሕብረት አልነበራቸውም።
በተወሰነ መንገድ ስናየው የሐይማኖት መሪዎች በሴፕቴምበት 11 ኒውዮርክ መንትያ ሕንጻዎች ላይ አውሮፕላን ጠልፈው በማጋጨት ሕዝቡን እንደጨረሱ ጠላፊዎች ናቸው። ሕዝቡ ወንበሮቻቸው ላይ ተረጋግተው በመቀመጥ አብራሪዎቹ በሰላም መሬት ላይ ያሳርፉናል ብለው ሲጠባበቁ ነበር። ግን በድንገት ሞቱ። ይህ ለሁላችንም አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው። ክርስቲያኖች ወደ ፍጻሜያቸው እንዲያደርሱዋቸው ፓሰተሮቻቸውን ተስፋ የሚያደርጉ ተሳፋሪዎች መሆን የለባቸውም። እንቅልፍ የተኙትን አሥር ቆነጃጅት አስቡ።
ፊልጵስዩስ 2፡12 ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
የጳውሎስን ትምሕርቶች መታዘዝ አለብን። ንሰሃ መግባት ከሲኦል ያድነናል። ያሉብን ሌሎች አደጋዎችስ ምንድናቸው? በቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ካሉት ስሕተቶች መዳን አለብን። መሪዎቻችን ወደ ታላቁ መከራ ይዘውን እየሄዱ ሳለ በሰው ሰራሽ ትምሕርቶችና ወጎች ተደላድለን ከተቀመጥንበትና ሞቆን ከተኛንበት እንቅልፍ መንቃትና መዳን አለብን።
ክርስቲያኖች ለኢየሱስ ዳግም ምጻት ዝግጁ ካልሆኑ በታላቁ መከራ ውስጥ ድንገተኛ ሞት ይሞታሉ።