ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የሉቃስ ወንጌል የኢየሱስን ሰብዓዊ ገጽታ በሚገባ ያሳየናል።
ይህም እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ በደምብ ታይቷል፡- ያልተጠበቀ ነገር ሊሆን እንደሚችል ተምረናል።
አንዳችም የማሸነፍ ተስፋ ያልነበረው ትራምፕ ታሸንፋለች ተብላ ተስፋ የተጣለባትንና ተወዳጅዋን ሒላሪ ክሊንተንን በሰፊ ልዩነት አሸነፋት። ሒላሪ ለምርጫ ቅስቀሳ ከትራምፕ በአሥር እጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ ነበራት፤ ደግሞም የፓሪቲዋ መሪዎች እና የድምጽ አሰጣጥ ተንታኞች ሙሉ ድጋፍ ነበራት። ትራምፕ ግን ጋዜጦች፣ ቲቪዎች፣ ሬድዮዎችና ኢንተርኔት ሁሉ እንዲሁም የራሱ ፓርቲ መሪዎች ጭምር ሲያጣጥሉት ነበር። ትራምፕ ማሸነፉ የተሰማ ጊዜ ምድር በሙሉ ደነገጠች።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሊያሳየን የፈለገው ምንድነው? ይህ ስላለንበት ጊዜ ምን ያመለክተናል?
በምድር ሁሉ ላይ ድንጋጤን የሚፈጥር ሌላ ትራምፕ ደግሞ ሊሰማ ቀርቧል (trump የእንግሊዝኛው ትራምፕ የሚለው ቃል ትርጉሙ መለከት ማለት ነው)።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መለከቱ” የተጠቀሰው በ2000 ዓመታት የክርስትና ዘመን ውስጥ የሞቱ ክርስቲያኖች ከሙታን ከሚነሱበት ጊዜ ጋር ተያይዞ ነው። ከዚያ በኋላ በሕይወት ያሉት ክርስቲያኖች የምድር ስበት ሊጎትተው የማይችለውን የማይሞተውን አካል ለብሰው ይለወጡና ኢየሱስን በአየር ላይ ለመቀበል ይነጠቃሉ። ዛሬ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የማይመሰክርላቸውን ትምሕርቶች በማመን ወደ ምድር እየተጎተቱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ የሚያምኑ በጣም ጥቂቶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ የሚያምኑ ሰዎችን ደግሞ ብዙዎች ይንቁዋቸዋል፤ ያጥላሉዋቸዋል። ለእኛ ለሰው ዘሮች ወደ ላይ መሄድ ከተፈጥሯችን ጋር አየጣጣምም፤ ከዚህም የተነሳ ከመካከላችን ወደ ላይ የምንሄድ ጥቂቶች ነን።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
ከጌታ ኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት የሚከናወኑት የመጨረሻዎቹ ሁለት ክስተቶች ትንሳኤና የአካል መለወጥ ናቸው።
“ድምጽ” ማለት መልእክት ሲሆን ይህም መልእክት ዓላማው ልክ መጥምቁ ዮሐንስ እንዳደረገው ከደነዘዝንበት የቤተክርስቲያንና የሰዎች ልማድ እንዲሁም ከሰዎች አስተምህሮ አንቅቶን እምነታችን ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እንዲመለስ ማድረግ ነው።
የመላእክት አለቃ የተባለው በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰው ብርቱ መልአክ ነው። ይህም መልአክ ሲወርድ በታላቅ “ድምጽ” በባሕር እና በምድር ውስጥ የተቀበሩትን ሙታን ይቀሰቅሳቸዋል።
ከዚያ “መለከቱ” የሚነፋው አካላችን በሚለወጥበት ሰዓት ነው፤ ምክንያቱም “መለከቱ” ኢየሱስ ከሰማይ በሚወርድበት ጊዜ እርሱን እንድንቀበለው ወደ ላይ ወደ ሰማይ ጥሪ የሚያቀርብልን ድምጽ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መለከት ጦርነት ሊጀመር መሆኑን የሚያመለክት ማስጠንቀቂያ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 14፡8 ደግሞም መለከት የማይገለጥን ድምፅ ቢሰጥ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?
መንፈሳዊ ጦርነት። ቤተክርስቲያኖች በከፊል ከመጽሐፍ ቅዱስ ይሰብካሉ፤ በከፊል ደግሞ ከሰዎች ልማድ እና ከሰው ሰራሽ አስተምህሮዎች እየወሰዱ ይሰብካሉ። እንዲህ አይነቱ ስብከት ግልጽ ያልሆነ ድምጽ ነው። ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለብን።
ከትንሳኤው እና ከመለከቱ በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ ፍጥረታዊ ምልክት ይልካል። የሚልከው ፍጥረታዊ ምልክት ለምሳሌ በአሜሪካ ውስጥ እንደተደረገው ምርጫ ይሆናል፤ ይህም ዳግም ምጻቱ መቃረቡን እንድናስተውል ትኩረታችንን ለመሳብ ነው።
እና ማን ነው ለኢየሱስ ዳግም ምጻት ዝግጁ የሚሆነው? ብዙዎች ዝግጁ አይደሉም።
ሉቃስ 18፡8 … ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ጌታ በሚመጣበትም ጊዜ ብዙዎች የሚደነግጡበት ክስተት ይከሰታል፤ ሰው ሁሉ የሚያከብራቸው በቤተክርስቲያናቸው የተወደዱ ሰዎች ይቀሩና ተስፋ የሌላቸው የተባሉ ከቤተክርስቲያን ጋር ባለመስማማታቸው ሐሰተኛ ተብለው የተወገዙ (መጥፎ ሰዎች የተባሉ) የተናቁ ሰዎች ግን ከጌታ ጋር ይከብራሉ፤ በዚህም ብዙ ሰው ይደነግጣል። ልክ በአሜሪካ ምርጫ ጊዜ ተንታኞች እንደሳቱ ሁሉ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና አዋቂ የተባሉትም እንደሳቱ የዛኔ በግልጥ ይታወቃል።
የእግዚአብሔር አስተሳሰብ ከእኛ ከሰዎች አስተሳሰብ በጣም የተለየ ነው።
እንዲህ አይነቱ ነገር ሊከሰት ይችላልን?
አዎን። ይህ እንደሚሆን ኢየሱስ አስጠንቅቆናል።
እንዲህ ብሏል፡-
ማቴዎስ 22፡2 መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።
3 የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም።
እግዚአብሔር መጀመሪያ ወደ ሰርጉ እራት ግብዣ የሚጠራው የዳኑ ክርስቲያኖችን ነው። ቅድሚያ ለእነርሱ ነው።
እነርሱ ግን ፍላጎት የላቸውም። እነርሱ በሕዝብ ዘንድ የተጨበጨበለትን የራሳቸውን ልማድና ትምሕርት ነው የሚፈልጉት። መስቀሉን ሳይሸከሙ ክብሩን ይፈልጋሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ተጣብቀው መኖር አይፈልጉም ምክንያቱም ያ ለእነርሱ ኋላ ቀርነትና ፋሽን ያለፈበት ነው።
ማቴዎስ 22፡4 ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ፦ የታደሙትን፦ እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ።
5 እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤
6 የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው ገደሉአቸውም።
ክርስቲያኖች እምነታቸውን በእግዚአብሔር ቃል መርምረው የማረጋገጥ ፍላጎት የላቸውም። ለመረዳት የከበዳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ “እንደማይጠቅም” አድርገው ያቃልሉታል ወይም ትተውት ያልፉታል።
ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያናቸው እንደሳተች የሚነግራቸውን ሰው ሁሉ ይጠላሉ። እምነታቸው ትክክል እንዳልሆነ የሚያሳያቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሁሉ ትተው ያልፋሉ። ሊያርሟቸው የሞከሩ ሰዎች ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ይደረግባቸዋል። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን እኔ ትክክል ነኝ ብሎ ያምናል። ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በራሳቸው ትክክለኛነት አስተሳሰብ እየተሟሟቁ መኖሩን ለምደውታል። በቤተክርስቲያኖች በር ላይ ያለው ማስታወቂያ እንዲህ ይላል፡- “ማንም እንዳይረብሸን፤ አለበለዚያ…”
ማቴዎስ 22፡8 በዚያን ጊዜ ባሮቹን፦ ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤ (ቤተክርስቲያናዊነትን የመረጡ የዳኑ ክርስቲያኖች፣ በብልጽግናና በሃብት የተባረኩ ክርስቲያኖች፣ ታላላቅ እና ዝነኛ የሆኑ የዳኑ ክርስቲያኖች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች)
ማቴዎስ 22፡9 እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ አለ። (መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የሚፈልጉና ሕዝብ የገፋቸው ሰዎች፣ ተስፋ የላቸውም የተባሉ፣ ድሃ እና መናፍቅ ተብለው የተወገዙ)
ማቴዎስ 22፡10 እነዚያም ባሮች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም (እንደ ተራምፕ ያሉትን) በጎዎችንም (እንደ ፔንስ ያሉትን። ፔንስ የሚለው ስም ከሃብታምነት ይልቅ ድህነትን ያመለክታል። በእንግሊዝ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን ፔንስ ነው፡- ፓውንድ፣ ሺሊንግ፣ ፔንስ) ሰበሰቡ፤ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት።
ስለዚህ የሉቃስ ወንጌል መስማት የማንፈልገውን ይነግረናል።
ለጌታ ምጻት መዘጋጀት የምንፈልግ ከሆነ መለወጥ ያስፈልገናል። የጌታ አመጣጡ ከምንጠብቀው ወይም ከምናስበው ውጭ ነው የሚሆነው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር በዙፋኑ ዙርያ አራት እንስሶች ወይም ሕያዋን ፍጥረታት አሉት፤ እነዚህም ሕያዋን ፍጥረታት ለአካሉ ማለትም ለቤተክርስቲያን እንደ ዘብ ጠባቂዎች ናቸው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
25 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ፣
ኢየሱስ ያዳናቸውና ለቃሉ እየተገዙ የኖሩ አማኞች ብቻ ናቸው የክርስቶስ መንፈሳዊ አካል የሚሆኑት፤ እነርሱም ሙሽራ ወይም ልባሞቹ ቆነጃጅት ይባላሉ።
የክርስትና ዋነኛው እውነት ይህ ነው። መዳን ያስፈልገናል፤ ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተጻፈው ቃል መገዛት አለብን።
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
ጥጃ ማለት ትንሽዬ በሬ ነው።
ብዙውን ጊዜ የሰማይን መንፈሳዊ ራዕይ በምድራዊ ቋንቋ መግለጽ ያስቸግራል፤ ግን ሕዝቅኤል የዮሐንስ ራዕይ ሳይጻፍ በፊት 600 ዓመታት ያህል ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመሳሳይ ራዕይ አይቶ ጽፏል።
ሕዝቅኤል 1፡10 የፊታቸው አምሳያ እንደ ሰው ፊት ነበረ፥ ለአራቱም በስተ ቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተ ግራቸውም እንደ ላም ፊት ነበራቸው፥ ለአራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።
ንስሩ ከሁላቸውም በላይ ይበርራል።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ዙፋን እርሱ በሚኖርበት ዳግመኛ በተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ልብ ውስጥ ነው።
የሰው ፍጥረታዊ ልብ ውስጥ ያሉት አራቱ ክፍሎች በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉት የአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት ምሳሌዎች ናቸው።
የቤተክርስቲያን (የክርስቶስ አካል) ጅማሬ ምን ይመስል እንደነበር እግዚአብሔር በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ገልጧል።
የአዲስ ኪዳን ዘመን በተጀመረበት ጊዜ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ አቋሟን ይዛ ነበር፤ ነገር ግን ለሰዎች አመራር መገዛት በጀመረች ጊዜ ትልቅ ስሕተት ሰራችና ወደ ጨለማ ዘመን ውስጥ እየተንሸራተተች ሄደች።
“መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ውስጥ ሆኖ በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሰራውን ሥራ” እንደ ጠባቂ ከብበው ከሚጠብቁት አራት ወንጌሎች ውስጥ አንዱ የሉቃስ ወንጌል ነው።
ደግሞም የሉቃስ ወንጌል ከእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ካሉት አራት እንስሶች አንዱን ይወክላል፤ እርሱም የሰው ፊት ነው።
ከዚህ የተነሳ ሉቃስ በወንጌሉ ውስጥ ክርስቶስን እንደ ፍጹም ሰው አድርጎ ያሳየናል፤ በተጨማሪም ሰብዓዊ ባሕርያችን እግዚአብሔርን ያስደስተውና መንግስቱንም በምድር ላይ ለማስፋት ያገለግል ዘንድ እንዴት ማመን እና መኖር እንዳለብን ያስተምረናል።
ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለነበረ እና ይቆጣጠራት ስለነበረ ብቻ ነው የሐዋርያት ሥራ ሊጻፍ የቻለው።
አራቱ ወንጌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ እምብርት ናቸው፤ ምክንያቱም ዘላለማዊ ሕይወታችን የተመሰረተው አራቱ ወንጌሎች ባስተላለፉልን የኢየሱስ ሕይወትና መስዋዕትነት መልእክት ላይ ነው።
አንበሳ የእንስሳት ሁሉ ንጉስ እንደመሆኑ ማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ንጉስ አድርጎ ነው የሚያሳየን። ማርቆስ ኢየሱስን ያለ መታከት እንደሚያገለግል አገልጋይ ወይም በሬ አድርጎ ያሳየናል። ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ፍጹም ሰው አድርጎ ያስተዋውቀናል። ዮሕንስ ደግሞ ኢየሱስን እግዚአብሔር በሰው አካል ውስጥ እንዳደረ አድርጎ ያቀርብልናል።
ከሐጥያት የሚያነጻው የኢየሱስ ደም በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈው አማኞችን ሕያው ስለሚያደርጋቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። የሐዋርያት ሥራ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዴት እንድትሆንለት እንደሚፈልግ ግልጽ የሆነ ምሳሌ ነው።
አራቱ ወንጌሎች ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት እንዴት አድርገን ከሰዎች ተጽዕኖ እንደምንጠብቀውና በሰዎች ሃሳብ ሳይሆን እንዴት በመንፈስ ቅዱስ እየተመራን እንደምንኖር ያስተምሩናል። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን እንድንታዘዝ በሚያደርገን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ፈንታ የሰዎችን ምሪት ተክተን እንድንኖር ይፈልጋል።
ቤተክርስቲያን በምታልፍባቸው ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በ2000 ዓመታት ታሪክ ውስጥ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች መካከል በአማኞች ውስጥ የዘላለም ሕይወትን ሊዘራ የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
የሉቃስ ወንጌልን የሚወክለው ሦስተኛው እንስሳ መንፈስ ቅዱስ ከ1517 ጀምሮ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ በተሃድሶ ዘመን ሲሰራበት የነበረውን የአሰራሩን ባሕርያት ይገልጻል። የእግዚአብሔር መንፈስ በጀርመኒ ውስጥ የማርቲን ሉተርን ሰብዓዊ ጥበብና ምሁርነት ባረኮ ተጠቀመበትና “ጻድቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል” የሚለው እውነት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለስ አደረገ። ክርስቲያኖች ከዚያ በኋላ ለመዳን ጥንታዊ የሃይማኖት ቁሳቁሶችን መታመን እና የሃጥያት ስርየትን በገንዘብ መግዛት ትተው ንሰሃ መግባት እና ማመን ብቻ እንደሚበቃቸው ተረዱ።
ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ የተባለውን ሰው ጥበቡን እና ምሁርነቱን በመጠቀም እርሱ ስለ ቅድስና፣ የወንድማማች መዋደድ፣ እና ወንጌልን ስለመስበክ በሰጠው ማብራሪያ አማካኝነት ቤተክርስቲያንን ወደ አዲስ ኪዳናዊ እምነት መለሳት። ይህም ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲመጣ መሰረት ጣለ፤ ያም ዘመን እግዚአብሔርን ለማገልገል ሰው እጅግ ታላቅ ጥረት ያደረገበት ዘመን ነበር። ያም ዘመን የተጠናቀቀው በካሊፎርንያ አሜሪካ ውስጥ የጴንጤቆስጤያዊ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መነቃቃት በ1906 ሲጀመር ነው።
በዚህ ዘመን ውስጥ የሰው ጥበብና ምሁራዊ ልቀት በእግዚአብሔር ቅባት ተባርኮ ስላገለገለ መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት የመጀመሪያ ቋንቋዎች ማለትም ከእብራይስጥ እና ከግሪክ ጽሁፎች በከፍተኛ ጥራትና ትክክለኛነት በ1611 ዓ.ም. ተተርጉሞ ኪንግ ጄምስ ባይብል የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ሊዘጋጅ ችሏል።
የቅጂ መብት ያልተመዘገበለት ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጄምስ ባይብል ነው። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በሙሉ የተርጓሚውን የግል አመለካከት እና የገቢ ምንጭ ለማስጠበቅ ተብሎ የቅጂ መብት እንዲኖራቸው ተደርጓል። ስለዚህ እነርሱ የሰው ቃሎች ናቸው።
“የሰው ፊት” የሚለው ቃል የሰውን “ራስ” እንድናስብ ያደርገናል።
የቤተክርስቲያን ራስ ማነው የሚለው ጥያቄ በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ እጅግ መሰረታዊ ችግር ያስከተለ ጥያቄ ነው።
የኪንግ ጄምስ ባይብል እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ መጠን ብቸኛው የትክክለኛ ክርስቲያናዊ አስተምሕሮ ምንጭ ወይም ራስ ነው። ትምሕርቱም ቀጥታ ከእግዚአብሔር አፍ የተወሰደ ቃል ነው።
ኪንግ ጄምስ ባይብን “Thus saith the Lord” ወይም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
መብራታቸውን ያበሩት ልባሞቹ ቆነጃጅት እውነተኛው ቃል ይገለጥ ዘንድ በኪንግ ጄምስ ባይብል ላይ ብርሃናቸውን ያበራሉ፤ እውነተኛውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ ያምናሉ።
ሌላኛው አማራጭ ካሉት ከመቶ የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የሚሻልህን በግምት መምረጥ ነው፤ እነዚህ ሁሉ ትርጉሞች በአተረጓጎማቸው አንዱ ከሌላው ይለያያሉ፤ በተጨማሪም በየጊዜው ማስተካከያ ይጨመርባቸዋል። ይህ ሁሉ ግራ ከማጋባት ውጭ ምንም ጥቅም የለውም።
በእውነተኛ ክርስትና ውስጥ የአስተምሕሮ መሰረት ተደርገው የሚወሰዱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ናቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ብቻ ናቸው የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አስረግጠው የሚነግሩን። (ሌላ ሃሳብ ወይም አመለካከት መቀበል የእናንተ ራስ ሰው እንዲሆን ያደርጋል።) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ብቻ የሚያምኑ አማኞች ራሳቸውን ክርስቲያን ብቻ ብለው ነው የሚጠሩት።
ሌላ ስም በጭራሽ አይፈልጉም ምክንያቱም ሚስት በባሏ ስም ብቻ ነው የምትጠራው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
ኤፌሶን 5፡24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በመቃወም የተነሱት ጀግናዎቹ የተሃድሶ ጀማሪዎች የሰሩት የመጀመሪያ ስሕተት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሥርዓት ተከትለው በቤተክርስቲያን ላይ ራስ እንዲሆን ሰውን መሾማቸው ነው። ይህ ሥርዓት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባለመሆኑ ምክንያት የሰውን ልማድ የሚከተሉ ቤተክርስቲያኖች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
ራስ ሆኖ የተሾመ ሰውን እንደ ፓስተር እያሉ መከተል መጨሻው አደጋ ነው። ከተሃድሶው ዘመን ወዲህ 30¸000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ተፈጥረዋል። ከሰው ተመርጠው የተሾሙ መሪዎች ማለቂያ የሌለው ልዩ ልዩ አስተምሕሮአዊ ስሕተቶችን ይዘው መጥተዋል። እኛ ግን መከተል ያለብን የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ ነው።
ሰዎች በራሳቸው ሃሳብ በመሰረቱት ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው (ፓስተር፣ ቄስ፣ ጳጳስ ወይም ሊቀ ጳጳስ) የቤተክርስቲያን ራስ ይሆናል፤ አባላትም ራሳቸውን በቤተክርስቲያናቸው እንቅስቃሴ ወይም በመሪያቸው ስም ይጠራሉ - ራሳቸውን ሉተራን፣ ሜተዲስት፣ ዌስሊያን፣ ባፕቲስት፣ ጴንጤቆስጤያዊ፣ ሜሴጅ አማኝ፣ ብራንሐማይት ወዘተ. ብለው ይጠራሉ።
ቤተክርስቲያን ይህንን ባለብዙ ራስ የሆነ የሰው አመራር ከመከተል እንድትመለስ ለማሳየት ሉቃስ ልንከተለው የሚገባን ፍጹም ሰው ኢየሱስ መሆኑን ይነግረናል።
ኢየሱስ እና ኢየሱስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ብቁ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻ ነው የሚታይ ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፊት።
ይህም ልክ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአሜሪካ ሕዝብ ፊት በመሆን እንደሚታወቀው ነው።
ስለዚህ ሉቃስ ትክክለኛው ሰብዓዊ ምሳሌያችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተለው ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን ያካፍለናል። ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር በሰው ሥጋ ውስጥ መገለጡ ነው።
ሉቃስ የኢየሱስ ሰብዓዊነት ላይ ያተኩራል፤ ኢየሱስ ትክክለኛው ሰው ነው።
የዮሐንስ ወንጌል ትኩረቱ በሰው አካል ውስጥ በክርስቶስ አድሮ የተገለጠው እግዚአብሔር ላይ ነው።
ሉቃስ 1፡76 ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ (መጥምቁ ዮሐንስ)፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፊት ነው። ሉቃስ ደግሞ ኢየሱስ ሰው እንደሆነ ይገልጥልናል።
ስለዚህ የሉቃስ ሰንደቅ ዓላማ የሰው ፊት ነው። ይህም የኢየሱስ ፊት ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ፊቱ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ። እኛ የቤተክርስቲያን መሪ የምንላቸው ሰዎች ሁሉ የክርስቶስ የአካሉ ብልት ከመሆን አያልፉም። እርሱ ራስ ነው፤ እኛ ደግሞ አካሉ ነን። የአካሉ ብልቶች ሁሉ በራስ ቁጥጥር ስር ናቸው።
ኢየሱስ ልክ እንደ እኛው አይነት ሰው ነው። ይህም ማለት እግዚአብሔር እንዴት ማሰብና መኖር እንዳለብን ሊያሳየን ብሎ ወደ እኛ ደረጃ ራሱን ዝቅ አደረገ ማለት ነው። ሰው እንደመሆናችን ወደ ቤተክርስቲያናችን መሪዎች መመልከት የለብንም (እነርሱ ብዙ ችግሮች ያሉባቸው ዕቃዎች ናቸው)፤ ነገር ግን ሰው እንዴት መሆን እንዳለበት የሚያሳየንን ፍጹሙን ምሳሌያችንን ኢየሱስን መመልከተ ነው ያለብን።
ሉቃስ ሐኪም ነበረ።
ቆላስይስ 4፡14 የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ፣
ከሌሎች ሰዎች በተሻለ ሰውን በደምብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሐኪም ነው። የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነና ቤተክርስቲያንም የክርስቶስ አካል ስለሆነች ሉቃስ በአጻጻፉ ወደ አሕዛብ ያደላል። በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን አካላት ከአሕዛብ የወጡ ሰዎች ናቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለአሕዛብ የሚራራውን ሉቃስን ለአሕዛብ ቤተክርስቲያን እንዲጽፍ መረጠው። ሉቃስ በተጨማሪ የሐዋርያት ሥራንም ጽፏል። የሐዋርያት ሥራ የመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ውስጥ በብዛት የተጻፈው ስለ ጳውሎስ ነው፤ እርሱም የአሕዛብ ሐዋርያ ነው፤ ምክንያቱም ባደረጋቸው ሦስት የወንጌል ስብከት ጉዞዎች አማካኝነት ለአሕዛብ ቤተክርስቲያን መመስረት መሰረት የጣለው እርሱ ነው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከተጻፉ መጽሐፎች ሁሉ ረጅሙ የሉቃስ ወንጌል ነው፤ ይህም ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚያልፉበትን 2000 ዓመታት ያህል ረጅም ዘመን የሚያመለክት ነው።
ገላትያ 2፡8 ለተገረዙት [ለአይሁድ] ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ [ለጳውሎስ] ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና።
ጳውሎስ የአሕዛብ ሐዋርያ ነበረ። ሉቃስ ደግሞ ጳውሎስ በአሕዛብ መካከል በተንቀሳቀሰበት ጊዜ ሁሉ ታማኝ አጋሩ ነበረ። ስለዚህ ሉቃስ ሁልጊዜ ከአሕዛብ ጋር ጠንከር ያለ የዝምድና ስሜት ነበረው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ።
በዚህ ቃል ውስጥ ጳውሎስ የሚናገረው ሉቃስ ለአሕዛብ በሚደረገው የወንጌል አገልግሎት ውስጥ የነበረውን ታማኝነት ነው።
ሉቃስ የኢየሱስ ሰውነት ላይ ስላተኮረ ስለ ኢየሱስም ስለ ዮሐንስም መወለድ በትኩረት ጠቅሷል። እያንዳንዱ ሰው ሕይወቱ የሚጀምረው ከሕጻንነት ነው። ስለዚህ ሉቃስ ሐኪም እንደመሆኑ ስለ ጽንስና ስለ መወለድ በዝርዝር ጽፏል።
የወንጌል ጠላቶች የኢየሱስን የዮሐንስንና የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ሕይወት በአጭር ሊቀጩ ይፈልጉ ነበር።
ብዙውን ጊዜ ወደ እርጅና ሳይደርሱ የሚሞቱ ሰዎች በሁለት የሕይወት ኡደት ውስጥ ያፋሉ፤ እነዚህም ልጅነትና ከዚያም አባትነት ናቸው።
ደቀመዛሙርትም በእነዚህ ሁለት ኡደቶች ውስጥ አልፈዋል። በወጣትነታቸው ሕጉን ለሚጠብቁ አይሁዳዊ ወላጆቻቸው ልጆች ነበሩ። ልጅ እንደመሆናቸው ከኢየሱስ እግር ስር ተምረዋል። ኢየሱስ ከሄደ በኋላ ደቀመዛሙርቱ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አባቶች ሆኑ፤ ቤተክርስቲያንም ሐዋርያት ብላ ነበር የምትጠራቸው።
ሉቃስ 1፡17 እርሱም [መጥምቁ ዮሐንስ] የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ [በጌታ ፊት] ይሄዳል።
ይህ ቃል ሉቃስ ውስጥ የተጠቀሰው በነብዩ ሚልክያስ ትንቢት ውስጥ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ምን ተብሎ ተጽፎ እንደነበር ለማሳየት ነበር።
የአባቶች “ልብ” ማለት አይሁድ በአምስት የተለያዩ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ተከፋፍለው ነበር ማለት ነው። ሁለቱ ዋነኛ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ምኩራቡን የተቆጣጠሩት ፈሪሳውያን እና መቅደሱን ያስተዳድሩ የነበሩት ሰዱቃውያን ናቸው። የሔሮድስ ወገን የሚባሉም ነበሩ (እነዚህ ከንጉስ ሔሮድስ ጋር ፖለቲካ ውስጥ የገቡ ናቸው)፣ ቀናተኞች (ጠላቶቻቸውን ለመግደል የማያመነቱ ሰዎች)፣ እና በ1946 ማለቂያ እና በ1947 መጀመሪያ ሙት ባሕር አጠገብ ቁምራን በተባለ አካባቢ የተገኙት ሰባቱ የብሉይ ኪዳን የብራና ጥቅልሎች እንደሚያመለክቱት የተባሉ ራሳቸውን ለይተው በምድረበዳ የሚኖሩ ኤሰን የሚባሉ ቡድኖችም ነበሩ። በ1949 እና በ1956 መካከል ቁምራን አካባቢ ተጨማሪ 930 የብራን ጥቅልሎች የተገኙ ሲሆን አብዛኞቹ የተሟሉ ጽሁፎች አይደሉም፤ አሥራ ሁለቱ ግን ጥንት እንደነበሩ ሳይቀደዱ ሳይሸራረፉ ደህና ሆነው ተገኝተዋል። እነዚህ የአርኬዎሎጂ ግኝቶች ብሉይ ኪዳን ትክክለኛ የአይሁድ ሕዝብ ታሪክ መሆኑን ማረጋገጫ ናቸው።
ይህም ኢየሱስ 5000 ሰዎችን እና 4000 ሰዎችን በተዓምር ባበላ ጊዜ የተሰበሰቡትን ሰባት መሶብ ቁርስራሾች እና 12 መሶብ ቁርስራሾች ያስታውሰናል።
በአይሁድ ቤተመቅደስ ውስጥ ባለ ሰባት መቅረዝ መብራት እና 12 ዳቦ ያለበት የገጽ ሕብስት ነበሩ፤ እነዚህም ሰባቱን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ዘመናት እና 12ቱን የብሉይ ኪዳን እሥራኤል ነገዶች የሚወክሉ ናቸው። በምድር ላይ የእግዚአብሔር ዋነኛ ትኩረቶች የአይሁድ ሕዝብ እና ቤተክርስቲያን ናቸው።
1947 ዓ.ም. ወሳኝ ዓመት ነው ምክንያቱም በዚያ ዓመት የተባበሩት መንግስታት በሁለት ድምጾች አብላጫ ለአይሁድ ሕዝብ እሥራኤል የምትባለዋን ሃገር ለመስጠት ወስነዋል። አይሁድን በሚጠላው እስታሊን ትመራ የነበረችውም ራሺያ ድንገት የአይሁዶች ደጋቢ በመሆን ለ18 ወራት ስትደግፋቸው ቆየች።
በ1948 ዓ.ም እሥራኤል በሮም ከተበተነችበት ከ135 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሷን መንግሥት አድርጋ አወጀች። አረቦቹ ወዲያው እሥራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱ።
በ1949 እሥራኤሎች በሰባት የአረብ መንግስታት በመደገፍ ሊወጉዋቸውን የመጡትን አምስት የአረብ ጦር ሰራዊቶች ድል ነሱዋቸው።
በ1956 በሌላ ጦርነት ግብጽን ሲና ውስጥ አሸነፉዋት፤ ደግሞም በ1967 በስድስት ቀን ጦርነት አረቦችን ድራሻቸውን አጠፉዋቸው።
ግልጽ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ወደ እሥራኤል መመለሱን አሳየ። የቁምራን ብራናዎች ልክ እሥራኤል ከ1800 ዓመታት ስደት በኋላ ሕዝብ ሆና በተመሰረተችበት ጊዜ ነበር የተገኙት።
በ1946 ዓ.ም አንድ መልአክ አሜሪካ ውስጥ ለዊልያም ብራንሐም ተገለጠለት፤ በዚህም የተጀመረው ታላቅ አገልግሎት በመለኮታዊ ፈውስ እና መናፍስትን በመለየት ስጦታ ታጅቦ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ ውስጥ በፔንቴኮስታሎች መካከል ታላቅ መነቃቃትን አስከትሏል። በ1960ዎቹ ውስጥ የኦራል ሮበርትስ ፔንቲኮስታል አገልግሎት ድርጅት ብቻ የነጻውን (በኮምዩኒስቶች ያልተገዛውን) ዓለም አንድ አራተኛው የሚሆነውን አሥራት የሚሰበስብበት ጊዜ ነበረ።
በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር በፔንቲኮስታል ቤተክርስቲያኖች ውስጥ መለኮታዊ ኃይሉ በብዛት እንዲገለጥ አድርጓል።
ፔንቲኮስታል ያልሆኑትም ቤተክርስቲያኖች በዚያ ጊዜ ወንጌልን በማሰራጨት ትልቅ ስኬት አግኝተዋል፤ በተለይም በወንጌል ስርጭት ስኬት ግምባር ቀደም ከነበሩት ውስጥ ቢሊ ግራሐም ተጠቃሽ ነበር።
ስለዚህ እግዚአብሔር በፔንቲኮስታል መነቃቃትና በአስደናቂው የዊልያም ብራንሐም የማስተማር አገልግሎት አማካኘነት አሜሪካ ውስጥ መለኮታዊ ስጦታዎቹን ይገልጥ ነበር። በዚያኑ ጊዜ እግዚአብሔር እሥራኤልን እንደገና እንደ ሕዝብ ሲመሰርታቸው ነበር፤ በተመሰረቱም ጊዜ የዳዊትን ባለ ሥድስት ጣት ኮከብ ከዓለም ሁሉ ጥንታዊ ባንድራ ምልክታቸው አድርገው ተነሱ።
ነገር ግን በ1950ዎቹ መጨረሻ አካባቢ አስተዋይ የነበረው የአሜሪካ ፕሬዚደንት አይዝንአወር ማስተዋል ጠፍቶበት በቬትናም ውስጥ በሙሉ ስለ አንድነት ጉዳይ ነጻ በሆነ ምርጫ ድምጽ እንዲሰጥ በማድረግ ፈንታ በሰሜን ቬትናም የነበሩትን ኮምዩኒስቶች ለመቃወም 700 የጦር አማካሪዎችን ወደ ደቡብ ቬትናም ላከ። ከዚያ በኋላ ካቶሊክ የሆነው ፕሬዚደንት ኬኔዲ በ1960ዎቹ መጀመሪያ 15¸000 ተጨማሪ የጦር አማካሪዎችን ወደ ደቡብ ቬትናም በመላክ ከአይዝንአወር ስሕተት የባሰ ስሕተት ሰራ፤ እርሱ የላካቸው አማካሪዎች የተላኩት አምባገነኑን ካቶሊካዊ የደቡብ ቬትናም ፕሬዚደንት ዲየም ለመደገፍ ነበር። ነገር ግን ሐይማኖትና ፖለቲካ ተቆራኝተው ሲሰሩ ለመልካም ዓላማ የታሰበ እርምጃ ሁሉ ያልታሰበ እልቂትና ሞትን የሚያስከትል ክፉ ውጤትን ይወልዳል። ከዚያ በኋላ በ1965 ፕሬዚደንት ጆንሰን ጦርነቱ እንዲቀጥል በማድረጉ ታላቅ ስሕተትን ሰርቷል፤ የታሪክ ምሑራንም ከዚያ ቀጥሎ የነበሩትን 15 ዓመታት አሜሪካ ራሷን ለመግደል የሞከረችባቸው ዓመታት ናቸው ይላሉ። የአሜሪካ ጦር ሠራዊት በጦር ሜዳ ተሸንፎ አያውቅም ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ ሦስት ፕሬዚደንቶች የተከተሉት የጦርነት መርህ ቆረጥነት የጎደለው በመሆኑ በብዙ ሰንካላ ውሳኔዎች ጦርነቱ ያልተፈለገ ኪሳራ የሚያስከትል እንዲሆን አድርገዋል።
ፕሬዚደንት ኒክሰን በጥበብ አሜሪካ ከቬትናም ጦርነት እንድትላቀቅ አደረገ፤ አሜሪካም ማገገም ቻለች፤ ነገር ግን ፔንቲኮስታል ቤተክርስቲያኖች ከሃያ ዓመታት በፊት የነበራቸውን መንፈሳዊ ነጽዕኖ ይዘው መቀጠል አልቻሉም።
በዚያኑ ጊዜ የቤተክርስቲያን ዓለም ግራ በተጋቡ የሐይማኖት መሪዎች አማካኝነት መሰነጣጠቅና መከፋፈሉን ቀጠለ፤ እስከ 2016 ዓ.ም ተከፋፍለው 30¸000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እስኪሆኑ ደረሱ። በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ክርስትና ጠፍቶ በቀና አመለካከትና ዝም ብሎ ብሩህ ተስፋን ብቻ በሚያርገበግብ ቡድናዊ ሥርዓት ተተክቷል። በዘመናችን ሐይማኖታዊ ግራ መጋባት የተነሳ ብዙ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ከጥፋት መጠለያ እናገኛለን በማለት ተሞኝተዋል። በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን ወጎችና ልማዶች እንዲሁም የሰዎች ትምሕርት “በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል የማመንን” ቦታ ተክተዋል። ኢየሱስ ከቤተክርስቲያኖቻችን ተገፍቶ ወጥቷል። ከውጭ ቆሞ የቤተክርስቲያንን በር ያንኳኳል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት ሰዎች ትልቁ ናፍቆታቸው ከፍ ባሉት የቤተክርስቲያን መሪዎች ዘንድ እውቅና እና ክብር ማግኘት ሆኗል።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
በመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን የአይሁድም ሐይማኖት ተከፋፍሎ ነበር፤ ግን መከፋፈሉ እንደ ዛሬው የቤተክርስቲያን መከፋፈል የከፋ አልነበረም። ዮሐንስም የተሰጠው ትልቅ ፈታኝ ሥራ የተከፋፈሉትን የአባቶች ልብ እና የልጆች ልብ ወደ አንድነት ማምጣት ነበረ።
ሉቃስ 1፡17 እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
እነዚህ የተለያዩ ቡድኖች ሁሉ የሙሴን ሕግ በየራሳቸው መንገድ ይተረጉሙ ነበር። እያንዳንዱ ቡድን ትክክል እንደሆኑ ያስቡ ነበር ግን ሁላቸውም ስሕተት ውስጥ ነበሩ።
እያንዳንዱ ሐይማኖታዊ ቡድን ራሱን ከፍ ከማድረጉ የተነሳ ዮሐንስ የተጋፈጠውን ፈተና ሊወጣ የቻለው ሁላቸውንም በአንድ ላይ የእፉኝት ልጆች ብሎ በመጥራት ነበር። እንዲህም ብሎ በመናገሩ እርሱ ሲሰብክ ሊሰሙ የመጡትን የአይሁድ ሕዝብ በሙሉ በአንድነት አውግዟል።
ሉቃስ 3፡7 ስለዚህ ከእርሱ [መጥምቁ ዮሐንስ] ሊጠመቁ ለወጡት ሕዝብ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
እባብ መንታ ምላስ አለው። አንድ ጎኑ እውነት ሲሆን ሌላኛው ጎኑ ሐሰት ነው። ዛሬ ቤተክርስቲያኖች በከፊል እውነትን ይሰብካሉ (ኢየሱስ ለሐጥያታችን ሞቶልናል) በከፊል ደግሞ ሐሰትን ይሰብካሉ። (ለምሳሌ ኢየሱስ በዲሴምበር 25 ነው የተወለደው፤ ሲወለድ ደግሞ ግርግሙ አካባቢ በአጋጣሚ በጌጣ ጌጥ ያሸበረቀ ዛፍ ነበረ። እነዚህ ሃሳቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ ናቸው። ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ ገብተው ነው ሕጻኑን ኢየሱስን ያዩት፤ እንጂ በግርግም ውስጥ የተወለደውን አራስ አይደለም ያገኙት። ሌላስ ቤተክርስቲያኖቻችን ያስተማሩን ውሸት ምንድነው? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን ክሪስማስ ወይም ገና የሚባለውን ቃል የሚቃወም ክርስቲያን አንድ እንኳ የለም።
ክሪስማስ የሚለውን ስም መጠቀም የተጀመረው በ350 ዓ.ም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ነው፤ ክሪስማስን ቸል የሚል ሰው ሁሉ ልክ እንደ ቤተክርስቲያን ትልቅ የንግድ ትርፍ ያመልጠዋል።)
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
(በዚህ ክፍል ውስጥ ዮሴፍ አልተጠቀሰም። ሰብዓ ሰገል መንፈሳዊ ሰዎች ነበሩ። እግዚአብሔር መንፈሳዊ አባታቸው ለሁለት ዓመታት ማታማታ በኮከብ መልክ በመንፈሱ ሲመራቸው ነበር፤ ኮከቡንም ከእነርሱ በስተቀር ማንም አላየውም። ደግሞም እግዚአብሔር እነዚህ በመንፈስ እየተመሩ የመጡ የምሥራቅ ጠቢባን የሰማዩ አባታቸውን በሕጻን ልጅ መልክ ተገልጦ ሊያመልኩት በመጡ ጊዜ የኢየሱስ ሰብአዊ “አባት” ተብሎ የሚቆጠረው ዮሴፍ በቦታው እንዳይገኝ አረደገ።)
ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
እነዚህ ሰዎች ጠቢባን የሆኑት ስለተማሩ አይደለም። ጠቢብ የሆኑት ኢየሱስን ይፈልጉ ስለነበር ነው። እናንተስ ጠቢብ ናችሁ?
አንድ የሚያስፈራኝ ሃሳብ አለ፡- እርሱም በተለያዩ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ውስጥ ታቅፈው የነበሩትን የአይሁድ ሕዝብ ዮሐንስ “እናንተ የእፉኝት ልጆች” ወይ መርዛማ እባቦች ብሎ መጥራቱ ነው። ዮሐንስ በእኛ ዘመን ተመልሶ ቢመጣ በቡድን ተከፋፍለው የተለያዩትን ቤተክርስቲያኖቻችንን በፍጥነት “ንሰሐ ለመግባት እንድንቀና” ነው የሚመክረን። በቡድን የተከፋፈሉት ቤተክርስቲያኖቻችን ሁሉ በየራሳቸው ትክክለኛ እንደሆኑ ያምናሉ። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ልዩነት ውስጥ ሁላቸውም ትክክል ሊሆኑ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። የሚያስፈራው ሁሉም ቤተክርስቲያኖቻችን የተሳሳቱ ሆነው ቢገኙስ የሚለው ሃሳብ ነው። ዮሐንስ በነበረበት ዘመን የነበሩ ቡድኖች አንዳቸውም ትክክለኛ እንዳልነበሩ ልብ በሉ።
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ጌታ በመጀመሪያው ምጻቱ ከመገለጡ በፊት በነብዩ ሚልክያስ ትንቢት ተነግሮ ነበር (400 ዓመታት ያህል ቀድሞ)።
የአባቶች “ልብ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር መጠቀሱ የዮሐንስ አገልግሎት ስኬታማ እንደነበረ ያመለክታል፤ ምክንያቱም ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ የመለሳቸው አይሁድ በሙሉ የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አምነዋል። እነዚህ በእድሜ የገፉ አይሁዳውያን ከተመለሱ በኋላ በአንድነት ሆነው በአንድ ልብ ኢየሱስን ብቻ አገልግለዋል። በተለያዩ ቡድኖች የተከፋፈሉትን የአይሁድ ሐይማኖታዊ ጎራዎችን ማለትም ፈሪሳውያንን፣ ሰዱቃውያንን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ትተው የአዲስ ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምሕርት ብቻ የሚከለቱ ክርስቲያኖች ሆነዋል።
ሉቃስ ሐኪም እንደመሆኑ በአጻጻፉም ጠንቃቃ ስለሆነ ዮሐንስ የሚልክያስን ትንቢት በከፊል ብቻ እንደፈጸመው አመልክቶናል። መጥምቁ ዮሐንስ ሕጉን እንጠብቃለን ብለው የሚያስቡት የአይሁድ አባቶች ወደ ልጆቻቸው ባይመለሱ ማለትም በኢየሱስ በማመን የኢየሱስ እና የደቀመዛሙርቱን ትውልድ ባይመስሉና መሲሁን ባይቀበሉ አመጸኞች መሆናቸውን ነግሯቸዋል። እነዚህ ልጆች ጥበብም በእግዚአብሔር ዓይን ጽድቅም ምን እንደሆነ ገብቷቸዋል።
ከዚያ እነዚሁ ልጆች አድገው ለመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አባቶች ይሆናሉ፤ የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍትም ይጽፋሉ።
ከጊዜ በኋላ ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳንን እምነት በመጣል ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ትወድቃለች፤ ከዚያም ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ በተሃድሶ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት መመለስ አለባት። ይህም ተሃድሶ በታላቁ የተሃድሶ መሪ በማርቲን ሉተር አማካኝነት በ1517 ይጀመርና በ1800ዎቹ ውስጥ እጅግ የተዋጣለት የወንጌል ስርጭትን ባስጀመረው ወንጌላዊ በጆን ዌስሊ አማካኝነት ይቀጥላል። ከዚያ በኋላ ታላቁ የፔንቲኮስታል መነቃቃት ሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ በአዙዛ እስትሪት ተጀመረ፤ እርሱም የጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ መነሻ ነበረ። በመንፈስ ቅዱስ መገኘት በተፈጠረው ነጻነት የተነሳ የተለያዩ ቡድኖች በአንድነት ማገልገል ቻሉ። አፕሪል 9 ቀን 1906 ዓ.ም በአንድ የጸሎት ሕብረት ተጀምሮ እስከ 1915 ድረስ ዘልቆ ነበር። በ1917 ይህ ፔንቲኮስታል እንቅስቃሴ ሰው ሰራሽ በሆኑ የቤተክርስቲያን ቡድኖችና በሰው አመራሮች አማካኝነት በመከፋፈሉ ተጽእኖውን ሊያጣ ችሏል። በዚያ ዓመት ራሺያ ውስጥ የኮምዩኒዝም አብዮት በሌኒን መሪነት ተቀሰቀሰ፤ እግዚአብሔርም አንድ ቀን ምዕራባውያን በመንፈሱ እና በቃሉ አማካኝነት የሚገለጠውን የእግዚአብሔርን መሪነት እምቢ ስለማለታቸውና በሰው መሪዎች እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተምህሮዎች ስለመተካታቸው ሊቀጣቸው የቅጣት መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበት ዘንድ ይህንን ክፉ የኮምዩኒስት ሥርዓት አሳደገው። በተመሳሳይ መንገድ ከክርስቶስ ልደት 606 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር አይሁድን በተጻፈው ቃሉ ስላለመጽናታቸው ለመቅጣት ባቢሎንን አስነስቶ ነበር። በ1919 - 1920 እግዚአብሔር እስፓኒሽ ፍሉ የተባለ የጉንፋን ወረርሽኝ ላከ፤ ይህም በሽታ ቢል ጌትስ እንደገመተው 65 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል፤ ይህ ቁጥር ከ1914 - 1918 የተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከገደላቸው 20 ሚሊዮን ሰዎች በብዙ ይበልጣል።
የሰው ዘር በሙሉ የመንፈስ ቅዱስን መሪነት እምቢ ብሎ የሰውን መሪነት ስለመምረጡ ከባድ ዋጋ ከፍሏል።
ሚልክያስ 4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ከዚያም ለመጨረሻው ዘመን የሚሆን ሌላ የኤልያስ አገልግሎት እንደሚኖር በትንቢት ተነግሯል፤ ይህም አገልግሎት የሚሆነው ታላቁ መከራ ከመምጣቱ በፊት ነው። በዚያን ጊዜ እኛ ከመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያንና ከሐዋርያት በ1900 ዓመታት ርቀን የተወለድን “ልጆች” ሐዋርያዊ አባቶች ወዳስተማሩት አዲስ ኪዳናዊ ትምሕርቶች ተመለሱ የሚል መልእክት ይመጣልናል። ለዚህ የመጨረሻ ዘመን አገልግሎት አጽንኦት ለመስጠት ምድር በእርግማን ትመታለች፤ ግን ይህ እርግማን በታላቁ መከራ ጊዜ ለሚመጣው እርግማን እንደ ቅምሻ ነው የሚሆነው። እርግማን በሰዎች ላይ የሚመጣ ከባድ ችግር እና ቶሎ የማይጠፋ ነው። ይህ እርግማን በ1945 በሒሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ የወደቀው የአተም ቦምብ ነው፤ የቦምቡ ሬዲዮ አክቲቭ ጨረር ቶሎ ሳይጠፋ በመቆየቱ ቦምቦ ከተጣለበት ጊዜ በኋላ ለብዙ ዓመታት ጉዳት ማስከተሉን ቀጥሏል። ያም ክስተት እንደ መጥምቁ ዮሐንስ አይነት ለኢየሱስ ዳግም ምጻት የሚያዘጋጀን ነብይ ሊነሳ መሆኑን የሚጠቁመን ምልክት ነው፤ ይህም ነብይ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት የሚያዘጋጀን ወደ ጥንቱ የሐዋርያት የአዲስ ኪዳን ትምሕርት እንድንመለስ በማድረግ ነው። ሐዋርያት አባቶች ወዳስተማሩት የአዲስ ኪዳን እምነት ባንመለስ በታላቁ መከራ ወቅት በብዙ የራሺያ ኑክሊየር ቦምብ ናዳ ውስጥ ልንደበደብ ነው። ይህ ለአሜሪካ የመጨረሻውን ዘመን ነብይ አልቀበል ስለማለቷ የሚጠብቃት የመጨረሻ እጣ ፈንታዋ ነው። የሰሜን ንጉስ የተባለችዋን ሃገር ራሺያ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
ልጆች የማወቅ ፍላጎታቸው ማለቂያ ስለሌለው ያለማቋረጥ ጥያቄ ይጠይቃሉ። ወላጆችም ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልስ ስለሌላቸው ይበሰላቻሉ፤ መልስ ለመፈለግ ትጋት ስለሌላቸው ከስንፍናቸው የተነሳ የልጆችን ጥያቄና የማወቅ ጉጉት ምንም እንደማይጠቅም ነገር ቸል በማለት ያፍናሉ። በስተመጨረሻም ልጆች ፍላጎታቸው እየጠፋ ይሄዳል።
ዛሬ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን የማወቅ ጉጉት የላቸውም። አመንዝራለች የተባለችዋ ሴትዮ በድንጋይ እንድትወገር ሲጠይቁት ኢየሱስ ለምን በጣቱ መሬት ላይ እንደጻፈ ብትጠይቋቸው ለምንድነው ብለው ለማሰብ እንኳ ፍላጎት የላቸውም። ለምን እንደሆን አያውቁም፤ ለማወቅም አይፈልጉም። ልክ እንደ ወላጆች አይነት ባሕርይ ነው ያላቸው። ከዚያ በኋላ ቢያውቁም ምንም እንደማይጠቅማቸው ይናገራሉ።
ስለዚህ የዛሬዎቹ ክርስቲያኖች እንደ ልጆች የማወቅ ጉጉት ስለሌላቸው የአዲስ ኪዳን መጽሐፎችን ወደ ጻፉት ሐዋርያት አባቶች የመመለስ ዝንባሌ የላቸውም።
ያላችሁበት ቤተክርስቲያን መመለስ የማትችለውን ጥያቄ ስትጠየቁ የማወቅ ፍላጎታችሁ ሊቀሰቀስና ከቡድናችሁ ውጭ መልስ ፍለጋ ልትነሳሱ ይገባል። አንዴ ከቤተክርስቲያናችሁ ውጭ ከወጣችሁ በኋላ እውነተኛውን ቃል ኢየሱስን የማግኘት እድል ይኖራችኋል፤ ምክንያቱም እርሱ ቆሞ ያለው ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ነው።
ሉቃስ እንደ ሐኪም የማርያምን እና የኤልሳቤጥን እርግዝና ከመጀመሪያው በዝርዝር መዝግቦ ጽፏል።
ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ጸንሳ ስድስት ወር በሞላት ጊዜ ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስን ጸንሳ ነበር።
ሉቃስ 1፡35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
ሉቃስ 1፡36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
ከዚያ ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጎበኝና በእርሷ ዘንድ ለመቀመጥ ሄደች። የስድስት ወር ጽንስ ማሕጸን ውስጥ በዙርያው ውሃ ይከብበዋል። ስለዚህ ማርያም ለእግዚአብሔር ነብይ ለዮሐንስ በእናቱ ማሕጸን ውሃ ውስጥ ሳለ የእግዚአብሔርን ቃል (ኢየሱስን) ይዛለት መጣች።
ማርያም እንዲህ አለች፡-
ሉቃስ 1፡52 ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
53 የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
ሉቃስ ስለ በኢየሱስ ሰብዓዊነት ላይ በማተኮር እግዚአብሔር በሰዎች መካከል እንዴት እንደሚሰራ በአጽንኦት ያሳያል።
እግዚአብሔር በሰው ዘንድ የተናቁትን ከፍ ያደርጋል፤ ከፍ ያሉትንም ዝቅ ያደርጋቸዋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር በሰዎች መካከል የሚያደርገው ነገር ከምንጠብቀው ፍጹም የተለየ ነው።
ሃብታሞች ገንዘብ ስላላቸው በምድር ላይ ድሎትን መግዛት ይችላሉ፤ ነገር ግን መንፈሳዊ ባዶነት ውስጥ ስለሆኑ በሰማያት ብዙም ቦታ አይኖራቸውም። እግዚአብሔርም ዝንባሌው እነርሱን ከመጥራት ይልቅ ባዶዋቸውን መስደድ ነው።
ሉቃስ 1፡56 ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
የሐንስ ሊወለድ የሚችለው በማሕጸን ውስጥ ያለው ውሃ ሲፈስስ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ሁለተኛ በውሃ ውስጥ አይሆንም። ስለዚህ ማርያም ተመልሳ ስትሄድ ቃሉም ትቶት ሄደ። ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ዮሐንስ ተመልሶ ውሃ ውስጥ ገባ። በዚያን ጊዜ ሰዎችን ሊያጠምቅ በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ ነበር። የዛኔ ኢየሱስ በድጋሚ ወደ ዮሐንስ መጣ። ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በውሃ ውስጥ ወዳለ ነብይ ይመጣል። ይህም የሚያሳየን እውነተኛ ነብይ ሁልጊዜ በቃሉ ውሃ ውስጥ እንደሚቆይ ነው።
ኤፌሶን 5፡26 … በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ [ክርስቶስ] ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
የነብይ አገልግሎት የእግዚአብሔርን ቃል ለእኛ ማስተማር ነው። የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ማመንና መታዘዝ ሕይወታችንን ለማንጻት ይረዳናል።
ማርያም ዮሴፍን ልታገባ ስትመለስ የሦስት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች።
ስለዚህ ዮሴፍ የኢየሱስ አባት አለመሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነበረ። ከዚህም የተነሳ ማርያም ከዝሙት እንደጸነሰች ተብሎ የሚወራባትን የሐሰት ወሬ ተሸክማ ትኖር ነበር። ማርያምም ኢየሱስም ይህንን ነቀፋ ተሸክመው ኖረዋል።
ከኢየሱስ ጋር በተከራከሩ ጊዜ አይሁድ ከዝሙት አልተወለድንም ይሉ ነበር።
ዮሐንስ 8፡41 … እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት።
ይህን በማለታቸው እርሱ ከዝሙት እንደተወለደ በሽሙር መናገራቸው ነበር።
ስለዚህ ሉቃስ ሰው ሲያምን ራሱን ለስም አጥፊዎችና ለነቃፊዎች እንደሚያጋልት በግልጽ አሳይቷል። ከክርስትና አደጋዎች አንዱ ይህ ነው።
ከዚያም መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ።
ሉቃስ 1፡59 በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ።
እናቱ ግን መልሳ፦ አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
ሉቃስ ሐኪም እንደመሆኑ የመገረዝን ጉዳይ እንኳ ሳይጠቅስ አላለፈም። አይሁድ ሕጻኑን ዘካርያስ ብለው (በአባቱ ስም) ሊጠሩት ፈለጉ፤ እርሱም የአባቱን ፈለግ ተከትሎ ካሕን ይሆን ይመስል። ነገር ግን ያ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም። ሕጻኑ ባደገ ጊዜ የአባቱ ትውልድ የሆኑትን የአይሁድ አባቶች ፈጽሞ የሚቃወም ሰው ነው የሚሆነው። በዚያ ጊዜ የነበሩትን በእድሜ የገፉትን የአባቱን እኩዮች ወደ ልጆቻቸው ይመልሳቸዋል። ስለዚህ ሕጻኑ የተለየ ስም አስፈልጎታል።
ስለዚህ ሉቃስ ሰው እግዚአብሔርን ሊያገለግል ቢፈልግና ወላጆቹ የእግዚአብሔርን ቃል የማይከተሉ ከሆኑ ከወላጆቹ ጋር ላለመስማማት ፈቃደኛ መሆን እንደሚያስፈልገው አስረግጦ ይናገራል። እውነት ከቤተሰብም ትበልጣለች።
ሉቃስ 14፡26 [ኢየሱስ እንዲህ አለ] ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ሉቃስ 180 ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።
መጥምቁ ዮሐንስ እውነትን ማወቅ ስላስፈለገው በዘመኑ ከነበሩ የሐይማኖት መሪዎች ተጽእኖ ርቆ በምድረበዳ አደገ።
በመካከላቸው ቢያድግ ኖሮ ወደ ስሕተት ብቻ ነው ሊመሩት የሚችሉት። ስለዚህ ከእነርሱ ተለይቶ ማደግ የግድ አስፈለገው።
ዮሐንስ በዘመኑ ከነበሩት የሐይማኖት ቡድኖች ከአንዳቸውም ጋር አልተቀላቀለም። ለዚህ ነው እግዚአብሔር በእርሱ ላይ እምነት የጣለበት።
የአይሁድ ልጆች ክሕነት ውስጥ ወይም የእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ መግባት የሚችሉት እድሜያቸው ሰላሳ ሲሞላ ብቻ ነበር።
ዘኁልቁ 4፡1 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
2 ከሌዊ ልጆች መካከል በየወገናቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች የቀዓትን ልጆች ድምር ውሰድ፤
3 ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በመገናኛው ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትደምራለህ።
ካሕናት የሚመረጡት ከሌዊ ነገድ ነበር። እግዚአብሔርንም ከሰላሳ ዓመታቸው እስከ ሃምሳ ዓመታቸው ድረስ ለሃያ ዓመታት ያገለግላሉ። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊት እድሜያቸው ሰላሳ እስኪሞላ ጠብቀዋል። ዮሐንስ እድሜው ከኢየሱስ በስድስት ወር ይበልጣል። ኢየሱስ ሰላሳ ዓመት በሞላው ጊዜ ዮሐንስ ለስድስት ወራት ሲሰብክ ቆይቷል።
ሉቃስ 3፡21 ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ
ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር
መጥምቁ ዮሐንስ ሰላሳ ዓመት ሲሞላው በቤተመቅደሱ ውስጥ የሚደረገው የክሕነት አገልግሎት ብዙ ስሕተት ውስጥ ጠልቆ መግባቱን ለአይሁድ ሕዝብ ያሳያቸው ዘንድ ማጥመቅ ጀመረ። የአይሁድ ሕዝብም የሐይማኖት መሪዎቻቸው ለክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት ሊያዘጋጁዋቸው እንዳልቻሉ መገንዘብ ነበረባቸው። አይሁድ በመቅደሳቸው ወይም በምኩራባቸው ይተማመኑ ነበር፤ ስለዚህ መቅደሳቸው ወይም ምኩራባቸው እስካለ ድረስ ሊስቱ እንደማይችሉ ያስባሉ። ያም ትልቅ አለማስተዋል ነበር። ስለዚህ ኢየሱስን አንቀበልም አሉ፤ የሮማ ጦር ሠራዊት በ70 ዓ.ም በታይተስ መሪነት መቅደሱን ባፈረሰ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁድ ተገደሉ።
ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ መቆሙ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ክርስቲያኖች ለመቀበል እምቢ ማለታቸውን ያሳያል። ስለዳንን ብቻ የተለያዩት የቤተክርስቲያኖቻችንን እምነቶች እየተከተልን ምንም የማይደርስብን ይመስለናል። ነገር ግን ታላቁ መከራ እንደ ደራሽ ውሃ በድንገት ሲመጣብን ይህ የሞኝነት አስተሳሰባችን በአንድ ጊዜ ተንዶ ይወድቃል።
(ለዚህ ነው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሌላ መጥምቁ ዮሐንስ የሚያስፈልገው፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች ቃሉን ገፍተው ከቤተክርስቲያን አስወጥተውታል። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ይላል። ማንም ሰው ሁለት ራስ ሊኖረው አይችልም፤ ስለዚህ ኢየሱስ ቦታ አጥቷል። ከዚህ የተነሳ የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን ለኢየሱስ ዳግም ምጻት ሊያዘጋጁን አይችሉም። ዛሬ የቤተክርስቲያን አባላት እምነታቸውን የመሰርቱት በሰዎች አመለካከት እና ልማድ ላይ ነው፤ ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን በመጥቀስ እምነታችሁ ትክክል መሆኑን አሳዩ ሲባሉ በጣም ይፈራሉ። ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር እንደምንም እየተደነባበሩ መሪያቸው የተናገረውን ወይም እንደተናገረ የመሰላቸውን መጥቀስ ነው።)
ለአይሁድ በጣም ከባድ የሆነባቸው ጉዳይ የመጥምቁ ዮሐንስ፣ የኢየሱስ እና የደቀመዛሙርቱ አዲስ ወጣት ትውልድ በዘመኑ ተቀባይነት ከነበረው የሐይማኖት ሥርዓት ውጭ ቢሆኑም እንኳ የእውነት እግዚአብሔርን እያገለገሉ መሆናቸው ነበር። እነርሱም በዘመኑ ከነበሩት የአይሁድ የሐይማኖት ቡድኖች ከአንዳቸውም ወገን አልነበሩም።
ከሐይማኖት ቡድኖች ውጭ የነበሩት ብቻ ናቸው እውነትን ያገኙት።
[ዛሬም እኛን ተመሳሳይ ችግር ነው ያጋጠመን። ቤተክርስቲያኖቻችንን እግዚአብሔር ሲያያቸው እውር ነው የሚላቸው፤ ደግሞም ከሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ውጭ እንደቆመም ተናግሯል (ሎዶቅያ ማለት “የሕዝቡ መብት” ነው) ደግሞም ሎዶቅያ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።]
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 … ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ሰዎች ብዙ ከሆኑ ከብዛታቸው የተነሳ ከክፉ የሚጠበቁ ይመስላቸዋል። ነገር ግን የቤተክርስቲያን መሪዎች እግዚአብሔር ዛሬ ምን እያደረገ እንዳለ አያውቁም፤ ምክንያቱም በጨለማ ውስጥ መንገዱን እየፈለገ እንደሚንገዳገድ እውር ሰው ሁላቸውም በተለያየ አቅጣጫ ተበታትነው እየሄዱ ናቸው።
ማቴዎስ 15፡14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።
ተጠንቀቁ። በዚህ ዘመን “ጉድጓዱ” ማለት ታላቁ መከራ ነው። የዳኑ እና ወደ ሰርጉ ድግስ እየሄድን ነው ብለው ለሚያስቡ ክርስቲያኖች ይህ አስደንጋጭ እውነታ ነው፤ ምክንያቱም በታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው በጣም አስጨናቂ ወደ ሆነ ሞት ሲወርዱ ራሳቸውን ያገኛሉ።
“እንዴት ይህን ያህል ልንሳሳት ቻልን?” ብለው ያለቅሳሉ፤ ልክ በ2016 ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውስጥ ካሸነፈ በኋላ የቲቪና የሬድዮ ዜና ተንታኞች እንዳሉት።
መጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያኖቻችን እውር እንደሆኑ ይነግረናል፤ እኛ ግን እናያለን እንላለን። ማን ትክክል እንደሆነ ጊዜ ይፈርዳል። የሚያሳዝነው ግን ትክክለኞቹ እኛ አለመሆናችን ነው።