ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 9

ሉቃስ 9፡1 አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤
2 የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥
3 እንዲህም አላቸው፦ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ ሁለት እጀ ጠባብም አይሁንላችሁ።

ደቀመዛሙርት ድሃ ስለነበሩ በእምነት ነበር የሚኖሩት።

ሉቃስ 9፡4 በማናቸውም በምትገቡበት ቤት በዚያ ተቀመጡ ከዚያም ውጡ።
5 ማናቸውም የማይቀበሉአችሁ ቢሆኑ፥ ከዚያ ከተማ ወጥታችሁ ምስክር እንዲሆንባቸው ከእግራችሁ ትቢያ አራግፉ።
6 ወጥተውም ወንጌልን እየሰበኩና በስፍራው ሁሉ እየፈወሱ በየመንደሩ ያልፉ ነበር።

ንጉሥ ሔሮድስ መጥምቁ ዮሐንስን ገድሎ ስለነበረ አሁን ጨንቆታል። ኢየሱስ በአካባቢያቸው ሲያልፍ ክፉ ሰዎችም ጭምር ይጨንቃቸዋል።

ሉቃስ 9፡7 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም የተደረገውን ነገር ሁሉ ሰምቶ፥ አንዳንድ ሰዎች፦ ዮሐንስ ከሙታን ተነሣ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ ተገለጠ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይሉ ስለ ነበሩ አመነታ።
9 ሄሮድስም፦ ዮሐንስንስ እኔ ራሱን አስቈረጥሁት፤ ይህ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ማን ነው? አለ። ሊያየውም ይሻ ነበር።

በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የነበረውን መጥምቁ ዮሐንስን በመግደል ሔሮድስ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ የሚባለውን ሐጥያት ፈጸመ፤ ይህን ይቅር የማይባለው ሐጥያት ነው።

ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ለሔሮድስ አንዳችም አልተናገረም።

ኢየሱስ አሁን በምድረበዳ ውስጥ 5,000 ሰዎችን ሊያበላ አሰበ።

ሉቃስ 9፡13 እርሱ ግን፦ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸው። እነርሱም፦ ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን፥ ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም አሉት፤
14 አምስት ሺህ ሰዎች ያህሉ ነበርና። ለደቀ መዛሙርቱ፦ በየክፍሉ አምሳ አምሳውን አስቀምጡአቸው አላቸው።
15 እንዲህም አደረጉ ሁሉንም አስቀመጡአቸው።
16 አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረካቸው ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛርሙርቱ ሰጠ።

ይህ ተዓምር ወደፊት ሊመጡ ያላቸውን ሰባቱን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል።

ኢየሱስ ምግቡን ለደቀመዛሙርቱ ሰጠ። ደቀመዛሙርቱም ምግቡን በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡዋቸው።

ይህም የሚወክለው ኢየሱስ የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክን ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ይጽፉ ዘንድ ደቀመዛሙርቱን በመንፈስ ይመራቸዋል፤ በመጽሐፍቱ ውስጥ የተጻፉ ትምሕርቶችም በልዩ ልዩ ሥፍራ በተለያዩ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አማኝ ሆነው ወደተሰበሰቡ ሰዎች ሁሉ ይዳረሳሉ። ደቀመዛሙርቱ በቤተክርስቲያን ዘመን መጀመሪያ ላይ ከጸፉት መጽሐፍ ክርስቲያኖች ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ተምረዋል። የክርስትና መሰረቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው።

ስለእግዚአብሔር መማር የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ብቻ ነው።

የመጀመሪያዎቹ ሰባት መብሎችም ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክሉ ናቸው። ዓሳዎች በውሃ ውስጥ የሚዋኙ ፍጥረቶች እንደመሆናቸው በሦስተኛውና በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በነበረው ከባድ ስደት የተነሳ በድብቅ ውስጥ ለውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ቤተክርስቲያኖችን ይወክላሉ። እንጀራው ደግሞ ለሌሎቹ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮ ይወክላል።

ሉቃስ 9፡17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፥ ከእነርሱም የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ወሰዱ።

ደቀመዛሙርት 5,000 ሰዎችን ማብላታቸው በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ደቀመዛሙርቱ ልዩ ልዩ የክርስቲያን ቡድኖችን በአስተምሕሮዋቸው እንደሚያዳርሱ የሚያሳይ ነው። በስተመጨረሻ የሞቱ ክርስቲያኖች ከሙታን ይነሳሉ፤ ከዚያም ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ ክርስቲያኖች አብረውት ወደ መንግስተ ሰማይ ይሄዳሉ። ከዚያ በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወንጌሉ ወደ አሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገዶች ተመልሶ ይሄዳል። ሙሴ እና ኤልያስም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ባሉት የአስተምሕሮ ቁርስራሾች ሕዝቡን ይመግቡዋቸዋል። አይሁድም በስተመጨረሻ እምነታቸው ከአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች እምነት ጋር አንድ አይነት ይሆናል።

ቤተክርስቲያን ያመነችበትና ነፍሷን የመገበችበትን ያንኑ ተመሳሳይ ትምሕርት ይመገባሉ።

ሉቃስ 9፡18 ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።
19 እነርሱም መልሰው፦ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይላሉ አሉት።

ሌሎች ሰዎች ምን ይላሉ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም መልስ ሰጡ። ሰዎች ሌሎች የተናገሩትን መጥቀስ ይወዳሉ። ነገር ግን አንድ ነገር ለራሳቸው ማመን በጣም ያስፈራቸዋል። ሰዎች ልክ እንደ ገደል ማሚቶ የሰማነውን የመድገም አባዜ አለብን።

ሉቃስ 9፡20 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።

እነርሱ ራሳቸው ምን እንደሚያስቡ ሲጠየቁ ጴጥሮስ ብቻ ነበር ስለ ኢየሱስ ማንነት የግል የሆነ መገለጥ ያገኘው። መልስ የሰጠውም እርሱ ብቻ ነበር።

ሉቃስ 9፡21 እርሱ ግን፦ … ለማንም ይህን እንዳይናገሩ አስጠንቅቆ አዘዘ።

ኢየሱስ ዝም እንዲሉ አዘዛቸው። አይሁድ ከእግዚአብሔር እውነት እየራቁ የነበሩበት ዘመን ነበር። ደቀመዛሙርት ደግሞ ቤተክርስቲያንን ሊጀምሩ ነበር። ለአይሁድ ሊያምኑ የማይችሉትን መንገር ምንም ጥቅም የለውም።

ሉቃስ 9፡21-22 እርሱ ግን፦ የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊጣል ሊገደልም በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ይገባዋል ብሎ ለማንም ይህን እንዳይናገሩ አስጠንቅቆ አዘዘ።

አይሁድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ መሆኑን ሊያምኑ ይቅርና ጭራሽ ሊገድሉት በዝግጅት ላይ ነበሩ።

ክርስቶስን የተቃወሙት የሐይማኖት መሪዎች እንደነበሩ አስተውሉ። ደግሞም ለዚሁ አላማ ሕዝቡንም አነሳስተዋል።

በአይሁድም ሆነ በቤተክርስቲያን ሕዝቡ የሚስቱት መሪዎችን ሲከተሉ ነው።

ሉቃስ 9፡23 ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።

ክርስቲያኖች ለእኔነት መሞት አለባቸው። እኔነት መሞት አለበት። መስቀሉ የሚወክለው መከራን ነው። ክርስቲያኖች ሰውን በፍጹም መከተል የለባቸውም፤ መከተል ያለባቸው ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ብቻ ነው። በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ካላየነው በስተቀር አንድንም ነገር ማመን የለብንም።

ሉቃስ 9፡24 ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል።

እግዚአብሔር ታላቅ ሃሳብ አለው፤ እርሱም በሰዎች ጉዳይ መካከል እንደ መንፈሳዊ ወንዝ የሚፈስስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

እያንዳንዳችን በራስ ወዳድነት የምንንቀሳቀስበት ትንንሽ የግል ፈቃድ ኩሬ አለን። በዚህ ትንሽ የግል ፈቃድ ኩሬያችን ውስጥ በመንቦጫረቅ ራሳችንን ጠብቀን ብናቆይ መንፈሳዊ ሞት እንሞታለን። የግል ፈቃዳችንን በመተው ለእኔነት ብንሞት ከዚያ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወንዝ ውስጥ እንገባለን፤ ይህም ወንዝ መሄድ ወደማንፈልግበትና ወደማናውቀው ቦታ ይዞን ይሄዳል። ነገር ግን የመዳን መንገድ በዚህ ወንዝ ውስጥ ብቻ ነው ያለው። ለእኔነት ካልሞትን እድሜያችንን ሁሉ ከወንዙ ለመውጣት በመታገል ብቻ እናባክናለን።

ሉቃስ 9፡25 ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ ራሱን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?

ሴቶች፤ ገንዘብ፤ ዝና። በዚህ ዓለም ውስጥ የምናተርፈው ሁሉ ጊዜያዊ ነው። ይዘን የምንሄደው ምንም ነገር የለም። መቃብር ውስጥ ካሉ እሬሳዎች ሁሉ የበለጠ ሃብታም እሬሳ መሆን ማንንም አያጽናናም።

ሉቃስ 9፡26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩ በአባቱና በቅዱሳን መላእክቱ ክብርም ሲመጣ በእርሱ ያፍርበታል።

ለእግዚአብሔር ቃል መቆም አለብን። ቤተክርስቲያኖች ወደ ባሕላዊ አስተሳሰቦች፣ ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችና ሌሎች ስሕተቶች ውስጥ ገብተዋል። እኛ ግን በተጻፈው ቃል ጸንተን መቆም አለብን፤ ይህም ማለት ከምትወዱት ቤተክርስቲያን ጋር አለመስማማት ይገጥማችኋል፤ ከምትወዱዋቸው የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በአስተሳሰብ ትጋጫላችሁ። እንዲህ አይነቱ መንገድ ለመከተል ቀላል አይደለም። ውሳኔው ግን የሚደረገው በሕይወታችሁ ማንን እንደምታስቀድሙ በመምረጥ ነው።

ኢየሱስ መልኩ ያንጸባረቀበት የመገለጥ ተራራ ላይ መገኘት የሰባተኛውን ቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ይወክላል። የጌታ ምጻት ሁለት ክስተቶች ይቀድሙታል። መጀመሪያ በክርስቶስ ሆነው የሞቱት ይነሳሉ። እነዚህ ሰዎች ከሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ የተውጣጡ ናቸው። ከዚያም በሕይወት ያሉት አማኞች ወደ አዲስ አካል ይለወጣሉ። ከዚያ ሁሉም ጌታ ሲመጣ ለመቀበል በአየር ላይ ይነጠቁና በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ እራት ግብዣ ለመታደም ይሄዳሉ።

ከዚያም ሁለት ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ በታላቁ መከራ ውስጥ ወንጌልን ለአይሁድ ይሰብካሉ።

ሉቃስ 9፡27 እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከሚቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።

ሦስት ደቀመዛሙርት የጌታ ምጻት ምን እንደሚመስል በመገለጥ ተራራ ላይ አይተዋል።

ሉቃስ 9፡28 ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

ሰባት ቀናት አለፉ፤ ይህም ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደሚፈጸሙ ያመለክታል። ስምንተኛው ቀን (8 አዲስ ሥርዓትን የሚወክል ቁጥር ነው) የታላቁን መከራ ጅማሬ ይወክላል። “ያህል” የሚለው ቃል ቁርጥ ያለ ጊዜን አያመለክትም፤ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ዘመን ማለቂያ እና በታላቁ መከራ መጀመሪያ መካከል ርዝመቱ በውል ያልታወቀ የሽግግር ጊዜ ይኖራል።

ሉቃስ 9፡29 ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ለውጥ ተከሰተ። ይህም የሞቱ ቅዱሳን በማይሞት አካል እንደሚነሱ እና በሕይወት ያለችዋ ቤተክርስቲያን ወደማይሞት አካል እንደምትለወጥ ያሳያል።

ኢየሱስ ማንም ሰው ሊወዳደረው በማይችል አንጸባራቂ ክብር ያበራል። ይህም የሆነው ከሰው ሁሉ ይልቅ በክብር እጅግ እንደሚበልጥ ለማሳየት ነው፤ ስለዚህ እርሱን ሊወዳደረው የሚችል ሰው የለም።

ሉቃስ 9፡30 እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤

ፊት ላይ ያበራው ክብር ከሁለቱ ነብያት በድምቀት እጅግ ይበልጥ ነበር፤ ምክንያቱም ሁለቱ ነብያት ሰዎች ናቸው። ኢየሱስ ከሰው እጅግ አብዝቶ ይበልጣል። በዚያ ሰዓት በውስጡ የነበረው ከተፈጥሮ በላይ የሆነው አምላክ ነው ከውስጡ ሆኖ በማብራት ውጭውን የለወጠው።

ሙሴ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳንን ከሙታን መነሳት ይወክላል፤ ምክንያቱም እርሱ ሞቶ ነበር።

ኤልያስ ግን አልሞተም፤ ስለዚህ በዳግም ምጻት ጊዜ በሕይወት እያለችዋ አካሏ የሚለወጥላትን ቤተክርስቲያን ይወክላል።

ነገር ግን የኤልያስ መንፈስ በአሕዛብ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ተመልሶ በመምጣት ሁሉንም ነገር በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደተጻፈው አድርጎ እንደሚያስተካክል ተስፋ ተሰጥቷል።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

መጥምቁ ዮሐንስ በኤልያስ መንፈስ ነበር የመጣው። ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ቃል በተናገረበት ጊዜ ዮሐንስ ሞቷል። ስለዚህ ከመጥምቁ ዮሐንስ በኋላ ገና ወደ ፊት ስለሚፈጸም ትንቢት ነው ይህ ቃል የተነገረው።

ስለዚህ በመጨረሻ የመጨረሻውን ዘመን አማኞች ወደ መጀመሪያዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያ እምነት የሚመልስ የኤልያስ አይነት አገልግሎት ይኖራል፤ የአዲስ ኪዳን እምነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍቶ ነበርና። ይህ ተሃድሶ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ለሚደረገው የቤተክርስቲያን መነጠቅ አማኞች እንዲዘጋጁ ይረዳቸዋል።

ሉቃስ 9፡31 በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

ሙሴ እና ኤልያስ በክብር ተገልጠዋል ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ሞት ለመናገር ነበር የተገለጡት። (እንደ ክርስቲያን ትልቁ ክብራችን ለእኔነት ስንሞት ነው።) የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ውስጥ ትልቁ ክስተት ቀራንዮ ነው፤ ይህም ለአሕዛብና ለአይሁድ መዳንን አምጥቷል፤ በዚያውም በክብር ለሚሆነው ለዳግም ምጻቱ መንገድ ጠርጓል።

ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ሙሴ እና ኤልያስ ወንጌልን ለአይሁድ ሕዝብ ይዘው ይሄዳሉ። በዚያም ጊዜ 144,000 አይሁድ ኢየሱስን መሲሁ እርሱ ነው ብለው ይቀበሉትና ይሞታሉ።

ስለዚህ በዚህ በመገለጥ ተራራ ላይ በሆነው ክስተት ውስጥ የጌታ ምጻት በግልጽ ተተርኳል።

ሉቃስ 9፡32 ነገር ግን ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

የአሥሩ ቆነጃጅት ምሳሌ፡- ሁላቸውም ንጹሃን ሴቶች ናቸው -- የዳኑ የክርስቲያን ቤተክርስቲያኖች። ነገር ግን ሁላቸውም ከሰርጉ ሰዓት በፊት ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ነበር። ድምጽ ሲሰሙ ከእንቅልፍ ባነኑ -- ያባነናቸው ድምጽ ቤተክርስቲያንን ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያዊ አባቶች እምነት የሚመልሰው የኤልያስ ድምጽ ነው።

ከዚያም ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ስትነጠቅ እነዚህ ሁለት ነብያት (ሙሴ እና ኤልያስ) በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ 144,000ውን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጻት ለማዘጋጀት ወንጌልን ወደ አይሁድ ሕዝብ ይዘው ይሄዳሉ።

ሉቃስ 9፡33 ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

በዚህ ሰዓት ጴጥሮስን ሥላሴያዊ መንፈስ ያዘው። የሰዎች ትልቅ ድክመታቸው እግዚአብሔር የተጠቀመባቸውን ዝነኛ ሰዎች ከፍ ከፍ ማድረግ ነው። ይህ የብዙ ሕዝብ ስሕተት ነው። ተመልከቱ ጴጥሮስ ምን እንዳደረገ፤ ሁለት ታላላቅ ሰዎችን ከኢየሱስ ጋር በተመሳሳይ ደረጃ መደባቸው።

ሌላው ጴጥሮስን የያዘው መንፈስ ደግሞ የቤተክርስቲያን መንፈስ ነው። ጴጥሮስ ታዋቂ በሆነ የእግዚአብሔር ሰው ስም ዳስ ወይም ቤተክርስቲያን ሊሰራ ፈለገ። የሉተራን ዳስ ወይም ቤተክርስቲያን። ዌስሊያን ዳስ ወይም ቤተክርስቲያን። ይህ በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያንን በ30,000 ልዩ ልዩ ቡድኖች የከፋፈለ የመከፋፈል መንፈስ ነው።

ብዙ የሜሴጅ አማኞች የዊልያም ብራንሐምን ንግግር ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እኩል ይቀበላሉ። አንዳዶች እንደውም ከእርሱ ንግግር የተወሰዱትን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚበልጥ ሥፍራ ይሰጡዋቸዋል።

እምነታችሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አመሳክራችሁ ትክክል መሆናችሁን ካላረጋገጣችሁ ከእነዚህ የሰው ጥቅሶች መገለጥ ልታገኙ አትችሉም።

ጴጥሮስ የሰራው ታላቅ ስሕተት ለኢየሱስ ምክር መስጠቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረንን ማመን ብቻ እንጂ ልናሻሽለው መሞከር የለብንም። እግዚአብሔር የእኛን ሐሳብ ወይም ምክር አይፈልግም።

ሉቃስ 9፡34 ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።

ደመና ወረደና በተራራው ላይ የነበረውን ትዕይንት ሙሉ በሙሉ ደመሰሰው፤ ይህም የጴጥሮስ ሃሳብ መደምሰሱን ያመለክታል። ሦስቱ ደቀመዛሙርትም ፈሩ፤ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ስንሆን ሊኖረን የሚገባንን ትክክለኛ አቋም ያሳያል። በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት ስንሆን ከመናገር ይልቅ ለማዳመጥ ዝግጁ እንሆናለን።

በተራራ ላይ የሚወርድ ደመና እንደ ከባድ ጉም ስለሚመጣ በዚያ ውስጥ የቆመ ሰው አቅጣጫ ሁሉ ይጠፋበታል። እኛ ክርስቲያኖች አንድን ሰው ከክርስቶስ ጋር እኩል ልናደርገው ስንሞክር የሚደርስብን ይህ ነው። ሙሴ፣ ኤልያስ፣ ወይም ዊልያም ብራንሐም ከኢየሱስ ጋር እኩል ሊሆን ይችላል ብሎ መናገር በአለማመን ጉም ውስጥ መጥፋታችንን ያመለክታል።

ሉቃስ 9፡35 ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

በመጨረሻው ዘመን የሚናገረን ማንኛውም ድምጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ይገልጥልናል። መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ኢየሱስ በተጻፈው ቃል መልክ ሲገለጥ ማለት ነው። እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።

“ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” የሚናገራቸውን ቃሎች ሁሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት እውነት ሲገለጥ ከምናገኘው ትምሕርት ጋር አብሮ የሚስማማልንን ብቻ ነው ማመን ያብን።

የሰው ንግግር ጥቅሶች ተናጋሪው በትክክል በተናገረበት ጊዜ ብቻ ወደ እውነት ያመለክታሉ። እውነት እራሱ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው። ይህም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምስክርነት ሲቆምና አንዳችም ግጭት ሳይገኝበት ሲቀር ነው።

ኢሳይያስ 28፡13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።

የትኛውም ስሕተት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሆነ ቦታ ይጋጫል እንጂ ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ጋር ሊስማማ አይችልም። የዘመናችን ትልቅ አሳሳች ዘመቻ የሜሴጅ ሰባኪዎች ትምሕርታቸውን በሰው ጥቅሶች አስደግፈው ማቅረባቸው ነው።

ሃሳባቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈው የማያቀርቡት ለምንድነው? ምክንያቱም ሃሳቦቻቸው ስሕተት ስለሆኑና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለማይገኙ ነው። ሃሳቦቻቸውን አብዝተው ከመውደዳቸውና አስተዋዮች ተደርገው መቆጠርን በጣም ስለሚሰዱ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጎን ገፋ አድርገው ሲተዉ በደስታ ነው።

ለምሳሌ ብዙ “የሜሴጅ” ሰባኪዎች የኢየሱስን አዲስ ስም እናውቃለን ይሉዋችሁዋል። የተለያዩ ሰባኪዎች “አዲስ ስሞችን” ፈጥረዋል፤ ስለዚህ አዲሱ ስም በምታናግሩት ሰው ይወሰናል።

ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አዲስ ስም ማንም እንደማያውቀው ይናገራል።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ማንም አያውቅም ያለውን ነው “የሜሴጅ” ሰባኪዎች እናውቃለን የሚሉት ነው።

ለእኛ የሚቀርልን ማስጠንቀቂያ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው የእውነት መመዘኛችን ነው።

ሙሴ እና ኤልያስ ሁለቱ ታላላቅ ነብያት ቢሆኑም እንኳ ከኢየሱስ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም።

የዊልያም ብራንሐም ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል ሊጠቀሱ ይችላሉ የሚሉት “የሜሴጅ” ሰባኪዎች ሕዝቡን ከማታለልም በላይ ዊልያም ብራንሐም ያስተማረውን ትምሕርት እያጣመሙ ናቸው።

ማንኛውም ሰው ያመጣልን መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተመርምሮ ሲታይ ብቻ ነው ትክክለኝነቱ የሚረጋገጠው።

ሦስቱ ታላላቅ ደቀመዛሙርቱ በራሳቸው ልክ እንደ እኛው ምንም የማያውቁ ሰዎች ናቸው። የሰው አመለካከት ከንቱ ነው። በኢየሱስ ፊት ማንም ሰው ዝነኛ መሆን አይችልም።

በዚህ ዲጂታል ዘመን ውስጥ ሁለት ቁጥሮች ብቻ አሉ፤ እነርሱም 1 እና 0 ናቸው። በዚህ የዲጂታል መረጃ ዘመን መሰረት ኢየሱስ አንድ ቁጥር ሲሆን ሌላው ሰው ሁሉ ዜሮ ነው።

አንተ የትኛው ቁጥር ነህ?

ሉቃስ 9፡36 ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።

ድምጽ ተናገረ። ደመናው ሄደ። ከዚያ ኢየሱስ ብቻ ቀረ። ከኢየሱስ ጋር የሚወዳደር ማንም የለም። እርሱ ብቻ ነው የሚያድነን።

የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ ሰምተህ ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እያገናኘህ በምታነብበት ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ኢየሱስን ብቻ ታየዋለህ፤ እርሱ ብቻ በክብር ይገለጥልሃል።

ሦስቱ ታላላቅ ደቀመዛሙርት በጸጥታ ተዋጡ። ከራሳቸው ያመጡት አስተዋጽኦ በሙሉ ወደ ታላቅ ስሕተት ውስጥ የሚያስገባ በር ብቻ ነው። በዚያ ሰዓት በጣም አስፈላጊ ትምሕርት ወስደዋል፤ ይህም ኢየሱስ የተናገረውን ብቻ ማስተላለፍ እንዳለባቸው እንጂ የራሳቸውን አመለካከት አይደለም። ከዚያ በኋላ ነው አዲስ ኪዳንን ለመጻፍ ብቁ የሚሆኑት።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን አንድ መሪ ብቻ አላት፡- እርሱም ኢየሱስ ነው። አንድ የእምነት መግለጫ ብቻ አላት፡- ኢየሱስ። አንድ መጽሐፍ፡- መጽሐፍ ቅዱስ።

አንድ ዝነኛ ሰው በምታደንቁበት ጊዜ ይህንን እውነት አትርሱ። ዓይናችሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘወር ባደረጋችሁ ጊዜ እንደ ጴጥሮስ ዓለምን እያጥለቀለቀ ባለው አሳሳች ሐይማኖታዊ ማዕበል ውስጠ ትሰምጣላችሁ።

በዘመናችን የሲኦል ጉድጓድ ተከፍቷል፤ ከዚህም ጉድጓድ ውስጥ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ አሳሳች መናፍስት በአንድነት በመውጣት የዘመን መጨረሻ ላይ የቆመችዋን ሙሽራ ሊያታልሉ ተዘጋጅተዋል። እነዚህ ተንኮለኛ፣ አታላይ፣ አማላይ መናፍስት (የዘመን መጨረሻ “መልእክት” የሚባሉ ብዙ ልዩ ልዩ ትምሕርቶች አሉ) ነገር ግን ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ሁሉም ዓይናችሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንድታነሱ ማድረጋቸው ነው። ከዚያ በኋላ እምነታችሁ ትክክል መሆን አለመሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምራችሁ ማረጋገጥ ያቅታችኋል። ለዚህ ነው የእምነት ጋሻ የሚያስፈልገን። እምነት የሚመጣው ቃሉን በመስማት ብቻ ነው።

ዊልያም ብራንሐም “የእግዚአብሔር ድምጽ” ነው ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። ለእርሱ አገልግሎት እንዲህ አይነቱን ስያሜ መስጠት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። እርሱ የተባለው “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ነው። ስለዚህ የሚያደናግሩን የእርሱ መጽሐፍ አሳታሚዎች ናቸው።

ይህ የመገለጥ ተራራ ትዕይንት የሚገልጠው የቤተክርስቲያን ዘመናትን የመጨረሻ ቀን ነው፤ ለአይሁድም መንገር ያላስፈለገው በዘመናቸው ይህንን ቢሰሙ ምንም ትርጉም ስለማይሰጣቸው ነው።

አንድ ሰው አጋንንት ያደረበትን ዲዳ ልጁን ይዞ ወደ ኢየሱስ መጣ።

ሉቃስ 9፡40 ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፥ አልቻሉምም።
41 ኢየሱስም መልሶ፦ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው አለ።
42 ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው።
43 ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥

ኢየሱስ ታላቅ ኃይልን ከገለጠ በኋላ ለደቀመዛሙርቱ እንደሚገደል ነገራቸው። ኢየሱስ የሚገደለው ኃይል ስላጣ አልነበረም፤ የእርሱ መሞት ሰዎች ያላወቁት የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ስላለበት እንጂ።

ስለዚህ ነገሮች ሲበላሹ እግዚአብሔር እኛ ከምናውቀው በተለየ መንገድ ስራውን እየሰራ መሆኑን መገንዘብ አለብን።

ከዚያ ሃሳባችን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ወደመሆን ሲመጣ ምንም ነገር እንዳልተበላሸ እናስተውላለን። እግዚአብሔር ሊሰራ የፈለገበት መንገድ መሆኑን እንረዳለን።

እግዚአብሔር ታላቅ ኃይል አለው፤ ነገር ግን ኃይሉን በሰው ድካም ውስጥ ሊደብቀው ይችላል። ነገር ግን አትሳቱ። ሥራውን ያውቃል። ለዚህ ነው ዲያብሎስ ሁልጊዜ ግራ የሚጋባው።

ሉቃስ 9፡44 ለደቀ መዛሙርቱ፦ የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሮአችሁ አኑሩ አለ።
45 እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፥ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ፈሩ።

ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ ታላቅ ኃይሉን ሲገልጥ ያያሉ። ግን በቀራንዮ መስቀል ላይ በሚሆንበት ጊዜ ኃይሉን ብዙ መከራ በተቀበለ በሰው ሥጋ ውስጥ እንደሚደብቀውና ደካማ መስሎ እንደሚታይ አላወቁም።

ደቀመዛሙርቱ ስውር የሆነው የእግዚአብሔር እቅድ እየተፈጸመ ሲገለጥ ሊያዩ አልቻሉም።

መሲሁ በሕይወቱ መጨረሻ የደረሰበት መከራ ሰውን ሁሉ ግራ አጋብቷል። በቀራንዮ ምን እየተደረገ እንደነበር አንድም የተረዳ ሰው አልነበረም። ስለዚህ ከዚህ እኛ የምንወስደው ማስጠንቀቂያ በዳግም ምጻት ወቅት ነገሮች እኛ ሰዎች ከምንጠብቃቸው ፍጹም በተለየ መንገድ እንደሚከናወኑ ነው።

ከዚህ የተነሳ ሰዎች ቤተክርስቲያንን ለመምራት ብቁ አይደሉም፤ ምክንያቱም እኛ ሰዎች የተሰወረው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ አናውቅም።

እኛ ማድረግ የምንችለው አንድ ነገር ቢኖር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣበቅ ነው፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ አንድም ነገር ማመን ወይም ማድረግ የለብንም።

ቀጥሎ መውሰድ ያለብንን እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻውን ሊያሳየን ይችላል።

ሰዎች የሚጠመዱበት ሌላ ታላቅ ስሕተት ምን እንደሆነ ሉቃስ ገልጦልናል።

ሉቃስ 9፡46 ከእነርሱም ማን እንዲበልጥ ክርክር ተነሣባቸው።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ መርገሞች ሁሉ ትልቁ ይህ ነው። እርሱም ሰውን ከፍ የማድረግ ፍላጎት ነው። ከዚያም የባሰው መርገም ደግሞ ራስን ከፍ የማድረግ ፍላጎት ነው። ክርስትና ውድድር በሚሆንበት ጊዜ ሰው በትእቢት ተሞልቶ ራሱን ከሌሎች ሁሉ የተሻለ አድርጎ በመቁጠር “እኔ ከሁላችሁም እበልጣለው” ይላል። ይህም ራስን ከፍ የማድረግ አደገኛ መርዝ ነው። ራስ ወዳድ ሰዎች ይህ ይመቻቸዋል።

ከሌሎች እንበልጣለን ብለው የሚያስቡ ክርስቲያኖች ሌሎችን እንደራሳቸው ለማድረግ ያስተምራሉ፤ ከዚህም የተነሳ የሚያመጡዋቸው ሰዎች በእነርሱ መልክ እና አምሳል ይሆናል። ራሳቸውን ማባዛት ነው የሚፈልጉት።

ሉቃስ 9፡47 ኢየሱስም የልባቸውን አሳብ አውቆ ሕፃንን ያዘ፤ በአጠገቡም አቁሞ
48 ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና አላቸው።

“ከሁሉ ታላቅ ማነው?” ለሚለው ጥያቄ ለመስጠት ኢየሱስ አንድ ሕጻን ልጅ በመካከላቸው አቆመ። ሕጻን ልጅ ግን ትልልቅ ሰዎችን አይበልጥም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የምትመሰረተው “በታላቅ” ሰው ላይ አይደለም። በቤተክርስቲያን ውስጥ ለታላቅ ሰው ተብሎ የተዘጋጀ ሥፍራ የለም። ሕጻን ልጆች ታላቅ ነኝ አይሉም፤ ምክንያቱም ሕጻናት ሁልጊዜ የማወቅ ፍላጎት ስላላቸው ብዙ ጥያቄ ይጠይቃሉ፤ የሚጠይቁትም ብዙ እንደማያውቁ ስለሚያውቁ እና ለማወቅም በጣም ስለሚጓጉ ነው። ለዚህ ነው ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ የሰጠን። መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ብዙ እንደማናውቅ እያሳየን ነው። ከማስተማር ይልቅ ለመማር መጓጓት አለብን። በሰውነታችን ላይ ሁለት ዓይን እና ሁለት ጆሮ ሲኖርን አፍ ግን አንድ ብቻ ነው ያለን። ይህም ከምናስተምር ይልቅ ብዙ መማር እንደሚያስፈልገን ያሳየናል።

ስለዚህ የምናስበውን ያህል አስተዋዮች አይደለንም። በመንፈሳዊነት ከሌሎች እበልጣለሁ ብሎ ማሰብ ክርስቲያናዊ ባሕርይ አይለም።

ከክርስቲያኖች ሁሉ ታናሽ የሆነው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነው። እኛ ታናሽ የሆነውን ክርስቲያን ከፍ የማድረግ ዝንባሌ የለንም፤ ይህም ከሰዎች መካከል ከፍ ያለ ወይም ታላቅ የሆነ መሪ እንደሌለ ነው የሚያመለክተው። ክርስቶስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ። በቃሉ ሲናገር እርሱን ብቻ ነው መስማት ያለብን። በትሕትና ለቃሉ መታዘዝ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ታላቅነት ይቆጠራል።

እነዚህ ደቀመዛሙርት ለታላቅነት ሲፎካከሩ የእነርሱ አደገኛ ጠላት የነበረው ሳውል የተባለ ፈሪሳዊ የቤተክርስቲያንን መሰረት በመትከል አንጻር ከሁላቸውም ሊበልጣቸው እንደሚችል አላወቁም። ሳውልም ኋላ ስሙ ጳውሎስ ተብሎ ይቀየራል።

አሁንም ስለ ራሳቸው በማሰብ ደቀመዛሙርቱ ፈጽሞ በተሳሳተ መንገድ ላይ ቆሙ።

ሉቃስ “የኛ ቤተክርስቲያን ናት ትክክለኛ” እያሉ በቤተክርስቲያን የመከፋፈልን መንፈስ ይቃወማል።

ፍጹም ትክክለኛ ነኝ ማለት የምትችል ቤተክርስቲያን ልትኖር አትችልም።

ሉቃስ 9፡49 ዮሐንስም መልሶ፦ አቤቱ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው አለው።
50 ኢየሱስ ግን፦ የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት አለው።

የአስተምሕሮ ልዩነት በቤተክርስቲያኖች መካካል ቢኖርም እንኳ መለኮታዊ ኃይል በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ይገለጣል።

የእግዚአብሔር ኃይል በእኛ ቤተክርስቲያን ብቻ ነው የሚገለጠው ማለት የሚችል ቡድን የለም።

ሮሜ 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።

ቤተክርስቲያኖች “ከሁሉ የተሻለ ቤተክርስቲያን” ለመሆን ወይም “እውነት የበራልን ብቻ ቤተክርስቲያን እኛ ነን” ለማለት ብለው በዙርያቸው በሚገነቡት አጥር እግዚአብሔር አይወሰንም።

የእግዚአብሔር ስጦታና ኃይል በተገለጠበት ሁሉ በአክብሮት ልንቀበል ያስፈልገናል።

እያንዳንዱ ክርስቲያን እግዚአብሔር አንድ ቤተክርስቲያን ካበጀችውና ከተስማማችበት መንገድ ውጭ ሊንቀሳቀስ እንደሚችል መገንዘብ አለበት።

ሉቃስ ተቃዋሚዎቻችንን አውግዘን እንድናጠፋ አይመክረንም።

በአንድ መንደር ውስጥ የነበሩ ሳምራውያን ኢየሱስን አንቀበልም አሉ።

ሉቃስ 9፡54 ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት።
55 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤
56 የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

በ2,000 ዓመታት ውስጥ የተለወጠ ነገር የለም። ክርስቲያኖች እስካሁንም ሰዎች በሃሳባቸው አልስማማ ሲሉዋቸው ይናደዳሉ።

ክርስቲያኖች እስካሁንም እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቻቸውን እንደሚያጠፋላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። በአስተምሕሮ ላይ ያለመስማማት መብት አለን፤ ግን ማንም ሰው ስለተሳሳተ እንዲጠፋ መመኘት የለብንም። እንደዚያ የምናስብ ከሆንን በውስጣችን የተሳሳተ መንፈስ አለ ማለት ነው።

የካንተርበሪ ሊቀጳጳስ በቅርቡ እግዚአብሔር የለም እያለ የሚናገረውና የቤተክርስቲያን ቀንደኛ ተቃዋሚ ተቺ የሆነው ሪቻርድ ዳውኪንስ ከበሽታ እንዲፈወስ ሲጸልይለት ነበር። ሌሎች እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች ሊቀጳጳሱ ለዚህ ሰው በመጸለዩ ተገርመው ጸሎቱ ከልብ ይሆን ብለው ሲጠይቁ ነበር። ጸሎቱ ከልብ ነበር። ይህ ሊቀጳጳስ ለሌሎቻችን ጥሩ ምሳሌ ነው የተወልን። ከአንድ ሰው ጋር በሃሳብ መቃረን ካስፈለገህ ተቃረን ነገር ግን በሰውነቱ አክብረው። የካንተርበሪ ሊቀጳጳስ ስለ ወሰደው እርምጃ ልናደንቀው ይገባናል። ሪቻርድ ዳውኪንስም ጤናው ስለተመለሰለት እንኳን ደስ አለው። እያንዳንዱ ሰው በጤና የመኖር መብት አለው።

እንደ ቤተክርስቲያን ድክመታችንን የሚያሳዩን ተቺዎች ያስፈልጉናል። ስሕተቶቻችንን ሲያሳዩን እየታረምን ብቻ ነው ልንለወጥ የምንችለው። ዓለም ከወደቀችበት ቀውስ አንጻር ስንመለከተው ቤተክርስቲያኖቻችን በሙሉ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። ዓለማውያን ሲነቅፉን ነቅተን እንድንኖር ያደርጉናል፤ ይህም በሰው ሰራሽ እምነታችን ውስጥ ሞቆን ተመችቶን እንቅልፍ ከመተኛት ይሻለናል።

ለእኛ ለሰዎች ኢየሱስን መከተል ቀላል እንዳልሆነ ሉቃስ በአጽንኦት ያመለክታል። ክርስቲያን መሆን የአልጋ በአልጋ መንገድ አይደለም።

ሉቃስ 9፡57 እነርሱም በመንገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው።
58 ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።
59 ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ።
60 ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው።
61 ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ።
62 ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።

ከሁሉ በፊት ለወንጌሉ ትኩረት መስጠት አለብን። ለእንቅልፍ የሚመች ቦታ ላይኖር ይችላል። የቤተሰብ ሃዘንና ቀብር ላይ የመገኘት ወይም የስንብት ጌዜ ላይ የመገኘት ሃላፊነት እንኳ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ የምንሰጠውን ቅድሚያ ቦታ ሊይዙብን አይገባም።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ስንገባ በፊት በግላችን ልንሄድ በማንመርጠው መንገድ ያስኬደናል።

ኢየሱስን ራስ አድርገን ስንቀበል መንገዳችን ወዴት እንደሚያመራ የመወሰን መብታችንን አሳልፈን ሰጥተናል። አካል ራስ ያዘዘውን ይፈጽማል እንጂ ማድረግ የፈለገውን ለራስ ሊነግረው አይችልም።