ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 5
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ ከቀራጮችና ከሐጥያተኞች ጋር አብሮ በላ። ከቀራጮች አንዱን ሐዋርያ አድርጎ መረጠ፤ ለምጻምና ሽባ የሆነ ሰውን ፈወሰ።
First published on the 30th of March 2020 — Last updated on the 5th of November 2022በዚህ ምዕራፍ ሉቃስ የሚናገረው ደቀመዛሙርቱ በኢየሱስ መጠራታቸውን በተመለከተ ነው።
ሉቃስ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በማገልገል ውስጥ ሰዎች እንደ ሰው በምን አይነት መንገድ መመላለስ እንዳለባቸው ያሳየናል፤ ደግሞም እግዚአብሔር በእኛ በሰዎች መካከል እንደ ሰው የቤተክርስቲያን ዋና ራስ ሆኖ ተገልጦ እንዴት እንደተመላለሰም ያሳየናል።
ትምህርት 1፡ ኢየሱስ ሁል ጊዜ አደራረጉ ከእኛ አደራረግ የተለየ ነው።
እኛ ሰው እንደመሆናችን ነጻ ፈቃድ አለን፤ ነጻ ፈቃዳችን ግን በአጭር እድሜያችን ውስጥ የራስ ወዳድነት ፍላጎታችንን እንደፈለግን የምንፈጽምበት ጠባብ ሜዳ ነው። ንቁ የሆነው የአእምሮዋችን ክፍል በዚህ ጠባብ ሜዳ ውስጥ ነው የሚንቀሳቀሰው፤ እኛም ሁልጊዜ ይህንን የአእምሮዋችንን ክፍል ለማረጋጋት እየታገልን እንኖራለን።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ልክ እንደ ታላቅ መንፈሳዊ ወንዝ በማይታየው ዓለም ውስጥ በኃይል በመፍሰስ በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን ያተረማምሳል፤ ዓላማው ግን በእግዚአብሔር የረጅም ጊዜ የማዳን እቅድ ውስጥ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው። ወደዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ክልል ውስጥ ሆን ብለን አውቀን ልንገባ አንችልም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሃሳቡ ከእኛ ሃሳብ እጅግ የተለየ ነው። እግዚአብሔር ልክ እንደ ዮናስ እየገፋን ነው ወደዚህ ወደ ፈቃዱ ክልል ውስጥ የሚያስገባን፤ እኛም ሰላማችን ብለን የምናስበውንና ባለማወቅ ትልቅ ዋጋ የምንሰጠው ኑሮዋችንን ስለሚረብሽብን እየተነጫነጭን ነው ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የምንገባው።
ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
ሕዝቅኤል 3፡14 መንፈስ አንሥቶ አስወገደኝ፥ እኔም በምሬትና በመንፈሴ ሙቀት ሄድሁ፥ የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ በርትታ ነበር።
ለታላቁ ነብይ ሕዝቅኤል እግዚአብሔርን ማገልገል ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም።
ሉቃስ ምን እንደሚል እንመልከት።
ሉቃስ 5፡2 በባሕር ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ግን ከእነርሱ ውስጥ ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር።
3 ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደ ነበረች ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር።
ስምኦን (ኋላ ጴጥሮስ የተባለው) ጀልባው ውስጥ አልነበረም፤ እንደውም ሌሊቱን ሙሉ ዓሳ ለማጥመድ ሲታገል አድሮ አንድም ዓሳ ባለመያዙ ከመርከቡ ወርዶ መረቡን እያጠበ ነበር። ኢየሱስም መጣና ወደ ጴጥሮስ ባዶ ጀልባ ውስጥ ገባ።
በዚህ ሰዓት መረቡን ማጠቡ ትክክል አልነበረም ምክንያቱም ወዲያው ተመልሶ መረቡን ባሕር ውስጥ ሊጥለው ነው።
ኢየሱስ ስምኦንን መልሶ በራሱ አቅም ዓሳ ለማጥመድ ፈልጎ ወዳጣበት ባሕር ውስጥ ሊልከው ነው፤ ያውም ብዙ ከታገለ ብዙ ጥረት አድርጎ ከከሰረ በኋላ። ስምኦን ከብዙ ሙከራው በኋላ ተስፋ ቆርጦ ሙከራውን ትቷል።
ሉቃስ 5፡5 ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው።
ስምኦን ሌሊቱን በሙሉ ሲለፋ አድሮ እድሉን ሁሉ አሟጦ ከጨረሰና አንዳችም ዓሳ ሳያገኝ ካደረ በኋላ ምንም ማድረግ አልችልም ብሎ ተስፋ በቆረተበት ሰዓት ኢየሱስ መጣና ሊጠቀምበት አዘዘው። እኛ ግን እግዚአብሔር በችሎታችንና በጥበባችን የሚገረም ይመስለናል።
ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
ማድረግ ያለብን ነገር እግዚአብሔር ወደ ፈቃዱ ውስጥ እንዲያስገባንና ፍጹም በሆነው ፈቃዱ ውስጥ የራሱን ሥረሰ እንዲያሰራን መጸለይ ነው። ከዚያ ለኑሮ የሚያስፈልጉንን ነገሮች እራሱ ይጨምርልናል። የእርሱን ፈቃድ እንጂ የራሳችንን ፈቃድ መከተል የለብንም።
ፍላጎታችን ገንዘብ፣ ሴቶችን እና ዝና ከሆነ የራሳችንን ፈቃድ እየተከተልን ነው ማለት ነው። ለነገሩ እኛ ሰዎች የራሳችንን ምኞት እያሳደድን ሳለን በዚያ ውስጥ እግዚአብሔርን እያገለገልን ነን ብለን ራሳችንን ማሳት እንችልበታለን። ለራሳችን ገንዘብን ስናካብት ይህንን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የመሆን ምልክት አድርገን እስክንቆጥረው ድረስ ልንታለል እንችላለን።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡5 ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
ሉቃስ 5፡3 ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደ ነበረች ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር።
ኢየሱስ መጀመሪያ መርከቢቱን የተጠቀመው ሕዝቡን ለማስተማር ነው። ለዚህ ነው እርሱ ቅድሚያ የሚሰጠው። ከዚያ በኋላ እነ ጴጥሮስ የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ዓሳ ማጥመድ ይችልሉ።
ሉቃስ 5፡4 ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው።
5 ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው።
ኢየሱስ ያዘዘው ትዕዛዝ ማሰብ ለሚችል አእምሮ ሁሉ የማያስኬድ ቢሆንም ጴጥሮስ እሺ ብሎ ታዘዘ። ጴጥሮስ ልምድም ችሎታም ያለው ዓሳ አጥማጅ ነው፤ ግን አሁን ከዓሳ አጥማጅነ እውቀቱ ጋር ፈጽሞ የማይሄድ ትዕዛዝ ተሰጠው። ተፈጥሮዓዊ ችሎታው ያን ዕለት ዓሳ ማጥመድን እንዲተው አድርጎት ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ለብዙ ዓመታት ከተከማቸ ልምዱ ጋር የሚቃረን ቢሆንም እንኳ ኋላ ታላቅ በረከትን አምጥቶለታል።
6 ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ።
የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ ስኬትን አመጣ። ይህም በፊት አግኝቶ ከሚያውቀው ስኬት እጅግ የሚበልጥ ስኬት ነው።
ሉቃስ 5፡7 በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው ጠቀሱ፤ መጥተውም ሁለቱ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው።
8 ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው።
ይህ ታላቅ ስኬት ከስምኦን ችሎታ እና ብቃት ጋር የተያያዘ አልነበረም፤ ከዚህም የተነሳ የራሱ አቅመቢስነትና ዋጋቢስነት በጥልቀት አንዲሰማው አድርጎታል።
1 ቆሮንቶስ 1፡28 እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
29 ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።
እናንተ እና እኔ የእውነት ወደ እግዚአብሔር መገኘት ውስጥ እና ወደ ፈቃዱ ውስጥ ብንገባ እራሳችንን የማክበር ፍላጎት አይኖረንም።
ታላቅ ስኬትን ከተቀዳጀን በኋላ እንኳ ራሳችንን ምንም የማንጠቅም ሰዎች እንደሆንን አድርገን እንመለከታለን። ከኢየሱስ ጋር ስንነጻጸር እኛ ከምንም አንቆጠርም። እርሱ እኛን የሚጠቀምበት አንዳችም ምክንያት የለውም። ቢመርጠንም እንኳ ከጸጋው የተነሳ ብቻ ነው።
ስለዚህ አንዳችም የምንመካበት ምክንያት የለንም።
እግዚአብሔር የሚቸገርበት ትልቅ ችግር አንድ ሰውን የባረከ ጊዜ ሰውየው ራሱን እንደ ትልቅ አድርጎ በመቁጥር መመካት መጀመሩ ነው።
ሉቃስ 5፡9 ስላጠመዱት ዓሣ እርሱ (ስምኦን) ከእርሱ ጋርም የነበሩ ሁሉ ተደንቀዋልና፥
ኢየሱስ ለዚህ ታላቅ ስኬት ስለተጠቀመበት ጴጥሮስ በጣም ተገርሟል። ጓደኞቹና የሥራ አጋሮቹም በጣም ተገርመዋል። ኢየሱስም ከዚህ የተነሳ ደስ አለው። ሦስቱ ሰዎች ራሳቸውን እንደ ታላቅ ሰዎች አልቆጠሩም፤ ምክንያቱም ጴጥሮስ ራሱን ምንም እንደማይረባ ሲቆጥር አይተዋል። እነርሱም እግዚአብሔር በእነርሱ ስለተጠቀመ ብቻ ተደንቀዋል። ታላቅ ስኬት ተሳክቶላቸው ሳለ ካሳዩት ትሕትና የተነሳ ኢየሱስ መረጣቸው።
ስለዚህ እንደ ሰው ትክክለኛው አቋማችን ሊሆን የሚገባው ኢየሱስን እንደ ሁሉ በሁሉ ራሳችንን ግን ከእርሱ ጋር ስንነጻጸር ምንም አድርገን መቁጠር ነው።
በስኬታቸው ውስጥ ራሳቸውን ከሌሎች ሰዎች ጋር አላነጻጸሩም፤ ምክንያቱም ሁሉን ያደረገው ኢየሱስ እንጂ እነርሱ አልነበሩም።
በክርስትና ውስጥ ውድድር ማድረግ ወንጌሉ ላይ አስጸያፊ እድፈት የሚያመጣ ነገር ነው።
ሉቃስ 5፡10 እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ባልንጀሮች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦
አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ አለው።
እነ ጴጥሮስ የሰለጠኑ ዓሳ አጥማጆች ነበሩ፤ ነገር ግን አሁን ለተጠሩበት የላቀ አገልግሎት ማለትም ሰዎችን ለኢየሱስ የማጥመድ አገልግሎት ውስጥ የእነርሱ ዓሳ የማጥመድ ልምድ ምንም ጥቅም አልነበረውም።
11 ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።
የመጀመሪያው እርምጃቸው የገንዘብ ስኬት ፍላጎትን ፈጽሞ ጥሎ መሄድ ነበር።
ዓሳ ይዘው የማያውቁትን መጠን ያህል ይዘዋል።
ያንን ሁሉ የያዙትን ዓሳ ቢሸጡት መጋዘን ሁሉ የሚሞላ ገንዘብ ያመጣላቸው ነበር፤ ግን ያን ሁሉ ትተው ሄዱ። ይህ የብልጽግና ወንጌል አይደለም።
ትክክለኛ የኢየሱስ ተከታይ እግዚአብሔርን የሚያገለግለው ገንዘብ ለማግኘት ብሎ አይደለም።
ማቴዎስ 6፡24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ መሆናችንን የምናውቀው እንዴት ነው? በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መሆናችንን የምናውቀው እግዚአብሔርን የምናገለግልበት ምክንያት ከገንዘብ ፍላጎት የራቀ ሲሆን ነው። እውነተኛ ክርስቲያን አስቀድሞ እግዚአብሔርን ያገለግላል፤ ከዚያ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ይሰጠው ዘንድ ሙሉ በሙሉ ሃሳቡን በእግዚአብሔር ላይ ይጥላል። እግዚአብሔርን የምናገለግለው ስለምንወደውና በታላቅ እቅዱ ውስጥ መሆን ስለምንፈልግ ነው። ቢዚህ ዓለም ውስጥ ስኬታማ መሆን አለመሆናችን ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ጉዳይ ነው።
የምናገለግልበት ዋና ምክንያት የገንዘብ ፍላጎት ሆኖ ሳለ እግዚአብሔርን እናገለግላለን ማለት በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ አይደለንም ማለት ነው።
አንድ ለምጻም ወደ ኢየሱስ መጣ (ለምጽ ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ በሽታ ነው) ከዚያ ብትፈቅድ ልታድነኝ ትችላለህ አለው።
ሉቃስ 5፡13 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።
ሉቃስ ሐኪም እንደመሆኑ በዚህ ተዓምር ተገርሟል።
ሉቃስ 5፡14 እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን፦ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው።
ኢየሱስም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው።
ይህም መንፈሳዊ ስጦታን የተቀበሉ ሰዎች እግዚአብሔር በሰጣቸው ኃይል የተነሳ ለሚያገለግሉት አገልግሎት ምንም አይነት የሕዝብ እውቅና እና ዝና መፈለግ እንደሌለባቸው ነው። ዝና ለሰዎች ጥሩ ነገር አይደለም። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ሰዎች በተለይም ከተሳካላቸው ራሳቸውን በመለኮታዎ ኃይል በሚደረግ ድንቅ ሥራ አማካኝነት ታዋቂ ማድረግ ይፈልጋሉ። እንደዚህ ግን መሆን የለባቸውም። ወደ ራሳችን ትኩረት መሳብ የለብንም።
ሉቃስ 5፡15 ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤
የዚህ ፈውስ ዝና እጅግ ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ሳበ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ግን የግል ፈቃዳቸው እንዲፈጸምላቸው የፈለጉ ሰዎች ስለሆኑ ኢየሱስ በእነርሱ ተከብቦ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ነጻነት አጣ። ዝና ያመጣው ጣጣ ኢየሱስ በሰዎቹ ፈቃድና ምኞት ቁጥጥር ውስጥ ተወስኖ እንዲቆይ ማድረግ ነበር። ነገር ግን በቀኑ ውስጥ ምን እንደሚደረግ የሚወስነው ኢየሱስ እንጂ ሕዝቡ አይደሉም።
16 ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር።
ትምሕርት 2፡ ከሕዝብ ውዳሴ ርቆ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል
ደቀመዛሙርቱ ሊማሩ ያስፈለጋቸው ሁለተኛው ቁምነገር ከሕዝብ ውዳሴ ፈቀቅ ማለትን ነው፤ ምክንያቱም የሕዝብ አድናቆትን መቀበል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ትተው አድናቆት የሚሰጡዋቸውን ሰዎች ፍላጎት በመፈጸም እንዲጠመዱ ያደርጋቸዋል።
ሰዎች ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል ሲገለጥ ያስደንቃቸዋል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ኃይሉን ሊገልጥበት የተጠቀመበት ሰው እርሱን ዝነኛ ከሚያደርገው የሰዎች አድናቆት ፈቀቅ ማለት አለበት። ምድረበዳ ሰዎች የሌሉበት ጸጥ ያለ ሥፍራ ነው። ምድረበዳ ውስጥ ዝና የለም ምክንያቱም ምድረበዳ ውስጥ ሰዎች የሉም። ስለዚህ ከሰዎች አድናቆት ፈቀቅ ማለትን መማር አለብን (ሰዎች እንደመሆናችን ብንወደውም) ከዚያም እግዚአብሔር ምሪት እንዲሰጠን በጸሎት ውስጥ መሆን አለብን። ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ ማንኛውም ዋጋ ያለው ስኬት በእርሱ እጅ ብቻ መሆኑን እንዳንረሳ ያደርገናል፤ ስለዚህም ምስጋና እና አድናቆት የሚገባው እርሱ ብቻ ነው እንጂ እኛ አይደለንም። በሕይወታችን ውስጥ ለምንወስደው ቀጣይ እርምጃ የእግዚአብሔርን ፍጹም ፈቃድ የምናገኝበት መንገድ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እና መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ነው።
የሰዎችን አድናቆት ማዳመጥ ወደ እውነት መንገድ አይመራንም።
ክርስቲያን አንዴ ዝነኛ ከሆነ በኋላ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ሳይሆን ለሕዝቡ ፍላጎትና ጥያቄ ምላሽ መስጠት ግዴታ ይሆንበታል።
ቀጣዩ ትዕይንት ደግሞ ኢየሱስ በሕዝብ ብዛት ተከብቦ ባለበት ቀጥታ እርሱን ለማግኘት ጥረት ያደረጉ ሰዎች ያሉበት ነው። አሁንም ይህ ዝና ያመጣው መዘዝ ነው። በጣም ትንንሽ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች ኢየሱስን በቆመበት ቤት ውስጥ ስለከበቡት ከበድ ያለ ጥያቄ ያለው ሰው ወደ እርሱ መጠጋት አልቻለም። በስተመጨረሻም የቤቱን ጣራ ገንጥለው በገመድ ሰውየውን ወደ ኢየሱስ አጠገብ አወረዱት።
ሉቃስ 5፡18 እነሆም፥ አንድ ሽባ በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አግብተውም በፊቱ ሊያኖሩት ይሹ ነበር።
19 ስለ ሕዝቡም ብዛት እንዴት አድርገው እንዲያገቡት ሲያቅታቸው፥ ወደ ሰገነቱ ወጡ የጣራውንም ጡብ አሳልፈው በመካከል በኢየሱስ ፊት ከነአልጋው አወረዱት።
20 እምነታቸውንም አይቶ፦ አንተ ሰው፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
እንደ ሰው ከዚህ የምንማረው ትምሕርት ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ለማቅረብ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ነው። እርሱ ብቻ ነው ሊያድናቸውና ሊፈውሳቸው የሚችለው። የእኛ ሥራ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ፊት ማቅረብ ነው።
በሽታ የሐጥያት ውጤት ነው። ሐጥያት ባይኖር ኖሮ በሽታም አይኖርም ነበር። እግዚአብሔር ብቻ ነው ሐጢያትን ይቅር ሊል የሚችለው። ስለዚህ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ እግዚአብሔር መሆኑን አሳይቷል። ኢየሱስ የሰውየውን ሐጢያት ይቅር አለው፤ የሰውየውም ሽባነት ተለይቶት ሄደ። የበሽታው ለቆት መሄድ ሐጥያቱ ለመሰረዩ የሚታይ ምልክት ነበር።
ነገር ግን ይህ ተዓምር ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው።
ሽባ ሰው ለሸክም ይከብዳል። ሽባውን በገመድ ቀስ ብሎ መሬት ላይ ሳይወድቅ ማውረድ የአራት ሰዎችን ጉልበት ይጠይቃል፤
እያንዳንዳቸውም ሰውየው የተኛበትን ቃሬዛ አንድ አንድ ማዕዘን መያዝ አለባቸው። ሰውየው ለራሱ ምንም የማድረግ አቅም የለውም።
ልክ እንደዚሁ እኛ ሰዎች ከሐጢያታችንና ከአለማመናችን የተነሳ ለራሳችን አንዳችም ማድረግ የማንችል አቅመቢሶች ነን። አራቱ የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ እና የዮሐንስ ወንጌሎች የሚናገሩትን ብናምን መንፈሳዊ ቃሬዛ ይሆኑልናል (እምነታችን የሚገነባበትን የአስተሳሰብ መሰረት ያበጁልናል) ይህም ልክ ሽባው ሰውየ እንደተኛበት ቃሬዛ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ያወርደናል።
ዋነኛው ሐጢያታችን አለማመን ነው። ከዚህም ሐጢያት ይቅርታ የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል በሆነው በኢየሱስ ፊት ብቻ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ስንቀጥል አለማመናችን ከእኛ እየተወገደ ስለሚሄድ ሐጢያታችንም ለቆን ይጠፋል። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው መሰረት መመላለስ አለብን።
ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ አንድ ቀራጭ ወይም ግብር ሰብሳቢ እንዲከተለው ጠራው። ስሙም ሌዊ ነበር። ቀራጮች ማንም አይወዳቸውም ነበር። እንደ ሰው ስናስበው ሉቃስ ሰውየውን ሌዊ በሚባለው ስሙ በመጥቀስ ከክፉ ዓይን ሊጋርደው የፈለገ ይመስላል። ከዚያ በኋላ በሌላኛው ማቴዎስ በተባለ ስሙ ነበር የተጠራው። ይህም ሰው ኋላ የመጀመሪያውን ወንጌል የማቴዎስ ወንጌል በመጻፍ ዝነኛ ሆነ። ሉቃስ እርሱን ሌዊ ብሎ በመጥቀስ ከቀደመው አሳፋሪ ሕይወቱ ሊሸሽገው ሙከራ እያደረገ ይሆናል፤ ምክንያቱም በጊዜው የበነሩ ማቴዎስ በሚባለው ስሙ የሚያውቁት ሰዎች ሌዊ የሚለውን ስም ሲያዩ ሌላ ሰው ሊመስላቸው ይችላል።
ሉቃስ ልክ እንደ እርሱ ወንጌል የጻፈውን ሰው ከለላ ሊያደርግለት በመሞከሩ ሰብዓዊነቱን ገልጧል። ይህ ደስ የሚል ሰብዓዊ ርህራሄ ነው። ደግሞም በሰዎች ውስጥ ያለ መልካም ባሕሪያቸው ላይ ትኩረት እንድናደርግና ያለፉ ስሕተቶቻቸውን ንሰሃ የገቡበትን ስሕተቶቻቸውን እንድንተውላቸው ያስተምረናል።
ሉቃስ 5፡27 ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሌዊ የሚባል ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ ተመለከተና፦ ተከተለኝ አለው።
28 ሁሉንም ተወ፤ ተነሥቶም ተከተለው።
29 ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፤ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩ ከቀራጮችና ከሌሎች ሰዎች ብዙ ሕዝብ ነበሩ።
ከሰዎች አስጨንቆ የተቻለውን ያህል የቀረጥ ገንዘብ ይሰበስብ የነበረው ቀራጭ በማጭበርበር አግኝቶ የነበረውን ገንዘብ ሁሉ ትቶ ኢየሱስን ተከተለ። ኢየሱስን መከተል ሰዎች ገንዘብን እንዲንቁ አስችሏቸዋል።
ከዚያም ሌላ ትልቅ ድግስ በማዘጋጀት በለጋስነት ሰዎችን ለማብላትና ለማጠጣት ገንዘብ አወጣ። ይህም ስለ ገንዘብ የነበረው አመለካከት ሙሉ በሙሉ መለወጡን ያመለክታል። ከገንዘብ ይልቅ ለእግዚአብሔር መገዛትን መረጠ። ኢየሱስ ሰዎችን እንዲህ ነው የሚለውጣቸው። ሕይወታቸውን በሙሉ ይቀይረዋል።
እኛ ሰዎች ኢየሱስን ስንከተለው በሕይወታችን ላይ ይህን የመሰለ ለውጥ ነው የሚያመጣው። በሕይወትህ የሚገለጠው የለውጥ መጠን ምን ያህል ኢየሱስን እንደተከተልከው ይገልጣል። እስካሁን ድረስ ኢየሱስን ከማወቃችን በፊት የነበርነውን ያህል ስግብግብ ነን?
ሉቃስ 5፡30 ፈሪሳውያንና ጻፎቻቸውም በደቀ መዛሙርቱ ላይ፦ ስለ ምን ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ትበላላችሁ ትጠጡማላችሁ? ብለው አንጐራጐሩ።
31 ኢየሱስም መልሶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤
32 ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።
ክርስቲያኖች በቀላሉ ከቡድናቸው ውጭ የሆኑ ሰዎችን የማግለል ዝንባሌ ይኖራቸዋል፤ በተለይም ሌሎቹ ሰዎች ሐጢያተኞች ከሆኑ ወይም በአመለካከታቸው ከእነርሱ ጋር የማይስማሙ ከሆኑ።
ነገር ግን ሕመምተኞች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ሐጥያተኞችም እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የአስተምሕሮ ስሕተት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ምንጊዜም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለመርዳት ዝግጁ መሆን አለብን።
ስለዚህ ክርስትና አባላት ላልሆኑ ሰዎች ጥቅም የተቋቋመ ሕብረት መሆኑን እንማራለን።
ሉቃስ 5፡36 ደግሞም ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ የአዲስ ልብስ እራፊ ባረጀ ልብስ ላይ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱን ይቀደዋል ደግሞም አዲስ እራፊ ለአሮጌው አይስማማውም።
መዝሙር 104፡2 ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፤
ሰዎችን በትክክል አናያቸውም። ብዙውን ጊዜ የምናየው የለበሱትን ልብስ ነው። እግዚአብሔር ራሱን በቃሉ ብርሐን ውስት ይሸፍናል፤ ይህም የቃሉ ፍቺ ወይም ሰዎች በቀላሉ የማያገኙት የተሰወረ መልዕክቱ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ፍቺ ሲያበራልን እግዚአብሔርን በደምብ ማየት እንችላለን።
1ኛ ዮሐንስ 1፡5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ራሱንም የሚገልጠው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃሉን እያበራልን ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡16 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤
ዓይናችንን ቃሉ ላይ በማድረግ እግዚአብሔር እንዲገልጥልን እንጠባበቃለን፤ ይህንም የምናደርገው “ብርሃኑን ማየት እንድንችልና” መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ እንድናስተውል ነው።
በ1517 ዓ.ም ማርቲን ሉተር ጻድቅ በእምነት በሕይወት እንደሚኖር በገለጠ ጊዜ ይህ የተገለጠ ብርሃን ለሐጥያት ስርየት ገንዘብ መክፈል፣ ፑርጋቶሪ፣ የጥንት ቅዱሳን ሃውልቶችንና የቅዱሳን አጽሞችን ማክበር የመሳሰሉ የሮማ ካቶሊክ ልማዶችን ብትንትናቸውን አወጣ።
እነዚህ አሮጌ አስተሳሰቦች በእምነት መጽደቅ ከሚለው አዲስ አስተሳሰብ ጋር ሊጋጠሙ አልቻሉም። ስለዚህ ሉተር ካቶሊኮች በሃሳቡ አልስማማ ስላሉ ከእነርሱ መለየት ግድ ሆነበት። እግዚአብሔር አዲስ ብርሃን በገለጠ ቁጥር ቀድመው የነበሩ ቤተክርስቲያኖች ይቃወሙታል። ከመቀበል ይልቅ ያረጁ የተሳሳቱ ሃሳቦቻቸውን መደገፍ ይፈልጋሉ፤ ከዚህም የተነሳ የግድ አዲስ እንቅስቃሴ ይጀመራል።
ሉቃስ 5፡37 ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳል፥ እርሱም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል።
ወይን የመገለጥን መነቃቃት ያመለክታል። በ1900ዎቹ በተጀመረው የጴንጤቆስጤያዊ መነቃቃት አማካኝነት መንፈሳዊ ስጦታዎች ተመልሰው መምጣታቸው በጊዜ የነበሩ ቤተክርስቲያኖች ሊሸከሙ የሚችሉት ነገር አልነበረም። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች በሰው ስርዓት ውስጥ ያለውን ሰላምና ሰው ሰራሽ ቁጥጥር በጣም የሚወዱ ነበሩ። የመንፈስ ነጻነት ግን በልማዳዊ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ውስጥ ታፍኖ መቅረት አይችልም። ስለዚህ ፔንቲኮስታሎች ከቀድሞዎቹ ቤተክርስቲያኖች መለየት ግድ ሆነባቸው።
38 አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።
ፔንቲኮስታል አማኞች በመካከላቸው ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ለመጠበቅ ሲሉ ከቀድሞዎቹ ቤተክርስቲያኖች ተለይተው አዲስ እንቅስቃሴ መጀመር ግድ ሆነባቸው።
39 አሮጌ የወይን ጠጅ ሲጠጣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤ አሮጌው ይጣፍጣል ይላልና።
የፔንቲኮስታሎች እንቅስቃሴ በመካከላቸው ከሚገለጠው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የተነሳ በጣም አስደናቂ ነበር። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚለውን ሃሳብ ያመጡት እነርሱ ናቸው፤ ይህም ቤተክርስቲያንን ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመጀመሪያ የሐዋርያት ትምሕርት ከመመለስ አንጻር ትልቅ እርምጃ ነበር።
ነገር ግን ትልቁ የፔንቲኮስታሎች ድክመት መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ላይ ነበር።
ትንቢት፣ የሁለት ሺ ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ እና የመጀመሪያውን ሐጢያት በተመለከተ ፔንቲኮስታል ካልሆኑት ቤተክርስቲያኖች በምንም አይሻሉም ነበር። የመጀመሪያውን ሐጥያት እና የራዕይ መጽሐፍን ፔንቲኮስታሎቹ የሚተረጉሙዋቸው ልክ እንደ ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች እስኮፊልድ እና ላርኪን የተባሉ መምሕራን ከ1925 በፊት ባሳተሙዋቸው መጻሕፍት መሰረት ነበር።
ሳይንሳዊ እውቀታችን በ1925 በነበረበት ቢቀርት ምን ያህል ኋላ ቀር እንደምንሆን አስቡ። በጣም መሃይሞች እንሆን ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችንም እንደዚያው።
በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ አቅጣጫ ፔንቲኮስታሎች ከሌሎች ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ቀድመው በንሥር ክንፍ በረሩ። የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን በመረዳት ግን ፔንቲኮስታሎችም ልክ እንደ ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች ምንም ጥልቀት አልነበራቸውም። ብዥ ያለው እይታቸው በአስደናቂ ሁኔታ አጥርቶ በዝርዝር በሚመለከተው የንሥር ዓይን ሊወከል አይችልም።
ፔንቲኮስታሎች የንሥር ክንፍ ቢኖራቸውም ግን የበቀቀን ዓይን ነው ያላቸው። በቀቀኖች ሌሎች ያሉትን ሰምተው መድገም ብቻ ነው የሚያውቁት።
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢራትን ስላለማወቃቸው ሁሌ የሚሰጡት ምላሽ “አስፈላጊ አይደለም” የሚል ነው።
እውነቱ ግን ያ አይደለም። ማለት የፈለጉት እንዲህ ነው፡- “አንዳችም አላውቅም፤ ፍላጎትም የለኝም”።
ፔንቲኮስታሎች እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ለምን ንሰሃ እንዲገቡ እንዳልነገራቸው አያውቁም። ሌላ ጊዜ ሁሉ ግን እግዚአብሔር ሰዎች ሐጥያት ወደ ሰሩበት ቦታ ሲመጣ ንሰሐ ግቡ ይላል። ፍርዱን የሚልከው ምሕረቱን አልቀበል ካሉ ብቻ ነው። ዮንስ በነነዌ ከተማ የነበሩትን ክፉ ሰዎች ንሰሃ እንዲገቡ ነገራቸው። ንሰሃ ሲገቡም እግዚአብሔር ይቅር አላቸው። ታድያ ለአዳምና ለሔዋን ለምንድነው ንሰሃ ግቡ ያላላቸው?
ፔንቲኮስታሎች ሔዋን የዛፉን ፍሬ ስትበላ የተጀመረውን ሐጥያት ለማስወገድ እግዚአብሔር ለምን የእንስሳ ደም የግድ ያስፈልጋል እንዳለ አያውቁም።
ሔዋን ለምን በጽንስ ብዛት እንደተቀጣች ማብራራት አይችሉም። ለነገሩ እንድትበዛ እና ምድርን እንድትሞላ ተነግሯታል፤ ይህም ብዙ ልጆችን መውለድ ይጠይቃል። ወይስ ያልተረዳነው ነገር ይኖር ይሆን?
ሔዋን የዛፍ ፍሬ በመብቷ ለምን ስትወልድ በጭንቅ እንዲሆን እንደተፈረደባት ማብራራት አይችሉም።
ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
እግዚአብሔር እባቡንና አዳምን ሲያናግረው “ምክንያቱም” [በልተሃልና] የሚል ቃል በመጠቀሙ ስሕተት እንደሰሩ አስረድቷቸዋል።
ከዚያም ቀጣቸው። ለሔዋን ግን እግዚአብሔር ምን ጥፋት እንደሰራች አላብራራላትም። ሔዋንን ሲያናግራት “ምክንያቱም” የሚል ቃል አልተጠቀመም። የቅጣቷን ምክንያት ሳይነግራት ቅጣቷን ብቻ አስታወቃት። ፔንቲኮስታሎች ይህ ለምን እንደሆነ ማብራራት አይችሉም።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
ልብ በሉ። በዚህ ንግግር ውስጥ “ምክንያቱም” የሚል ቃል የለም።
በቅጣቷ ውስጥ ፈቃዷ ወደ ባሏ መሆኑ ለምን ተካተተበት? ባሏን የምትወድ ሴት ሁሉ ፈቃዷ ወደ ባሏ አይደለምን?
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ለባሎቻቸው መገዛትን ይቃወማሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የመገዛት ሃላፊነት አይወዱትም። በዚህ “ሰልፊ” ፎቶ በምንነሳበት ዘመን ያሉ ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አይወዱም። እኩልነትን እንደ መብታቸው አድርገው ይጠይቃሉ። “ሎዶቅያ” ማለት “የሕዝቡ መብት” ነው። ይህ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የእውርነትና የክሕደት ዘመን ነው።
ልብ በሉ። እግዚአብሔር ለእንስሳ ሲናገር “ይህን ስላደረግህ” በማለት የቅጣቱን ምክንያት ያብራራለታል።
ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
እግዚአብሔር እባቡን በደረቱ የሚሳብ እንስሳ እንዲሆን አድርጎ ቀጣው። እባቡ ከመረገሙ በፊት በሰውና በዝንጀሮ መካከል ሳይንቲስቶች ፈልገው ያጡት መገናኛ መስመር ነበረ። እባቡ ማሰብ፣ መናገርና ቃላትን ሰምቶ መረዳት ችሎታ ነበረው። አሁን ግን እባብ እነዚህን ሁሉ ማድረግ አይችልም።
ስለዚህ እግዚአብሔር በአዳም እና በእባቡ ላይ የወሰነውን ቅጣት ከነ ምክንያቱ ነገራቸው፤ የሴቲቱን ቅጣት ግን ምክንያቱን አልነገራትም።
ስለዚህ ሴቲቱ ምን ጥፋት እንደሰራች በጭራሽ መረዳት ባለመቻሏ ከእንስሳ በታች ነበር የተቆጠረችው። ለዚህ ነው ሴቶች እንደ ላም ወይም እንደ ሴት ውሻ በእንስሳ ሲመስሏቸው በጣም የሚበሳጩት።
አዳምም ሔዋንም ከአንድ ዛፍ አንድ ፍሬ ነው የበሉት። ግን ለምንድነው እግዚአብሔር ለአዳም የሰራውን ጥፋት የገለጠለት ለሔዋን ግን የሰራችውን ጥፋት ገልጦ ያልነገራት?
ፔንቲኮስታሎች ይህንን ጥያቄ መመለስ አይችሉም።
ስለዚህ የጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትንና መንፈሳዊ ስጦታዎችን መልሶ በማስተዋወቅ አስደናቂ ሥራ ሰርቷል።
ነገር ግን ልክ እንደ ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ስለ መጀመሪያው ሐጢያት እና ብዙ ርዕሶች ላይ መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ አልቻሉም፤ በተለይም የሁለት ሺ ዓመቱን የቤተክርስቲያን ታሪክ በተመለከተ የተነገረውን ትንቢት መተርጎም አልቻሉም።
ስለዚህ የእርሱ አዲስ ወይን የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራትን በመግለጥ በኩል ብዙም አስገራሚ አልነበረም።
ፔንቲኮስት ታላቅ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ ለሚገለጠው የትምሕርት አገልግሎት መነሻ መንገድ ጠራጊ ነበረ (የመጀመሪያው ዝናብ ወይም የትምሕርት ዝናብ) እርሱም እግዚአብሔር የኋለኛውን ዝናብ ወይም የመከሩን ዝናብ ከመላኩ በፊት የእግዚአብሔር ቃልን ምስጢራት የሚፈታ የትምሕርት ዝናብ ነው።
ፔንቲኮስት የእግዚአብሔርን ሚስጥር የሚገልጠውን የመጨረሻ ዘመን ነብይ ሊሰጠን አልቻለም።
ይህም ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የቀደሙ ትምሕርቶች እና የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት መገለጦች መልሶ የሚወስደን ነብይ ነው። ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ልናገኝ የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ መረዳት በቻልን ቁጥር ሊመጣ ካለው ታላቅ መከራ የማምለጥ ዋስትናችን ይጨምራል። ደግሞም ለጌታ ምጻትም ይበልጥ እንዘጋጃለን።
ዛሬ ቤተክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ አይፈልጉም። የሚፈልጉት የሰው ንግግር እንዲጠቀስላቸውና ጥቅስ እንዲተረጎምላቸው ነው።
አንድም ቤተክርስቲያን መሳሳቷን የሚነግራት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ አትፈልግም።
ማንም መለወጥ አይፈልግም። ለውጥ ግን የግድ ያስፈልገናል።
ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
ጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ እግዚአብሔርን በመንፈስ ማምለክ የሚባለውን ልምምድ ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። አሁን ግን እግዚብሔርን በእውነት ማምለክንም መማር አለብን፤ ከዚያ በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጠት እንችላለን።
የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በትክክል መተርጎም የምንችለው ከጥቅሱ ጋር በተያያዙ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ብቻ ነው። የመጨረሻው ዘመን ነብይ ምንም ቢያስተምር መገለጦቹን በሙሉ ትክክል መሆናቸውን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈተሽ አለብን እንጂ ከራሱ አፍ በተጠቀሱ ንግግሮች አማካኝነት አይደለም።
ነብይ የተናገረው ንግግር ሲጠቀስልን ንግግሩን ብቻ ወስደን ብናምን ትልቅ ስሕተት ውስጥ ገብተናል።
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል ከቤተክርስቲያን በር ውጭ መቆሙ “በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች” ውስጥ መገለጥ መሰረቱ በሰው ንግግር ጥቅሶችና በነዚህ ጥቅሶች ትርጓሜዎች ላይ መመስረቱን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አለመሆኑን ያመለክታል።
ማንም ሰው ሁለት ራስ ሊኖረው አይችልም። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ በሆነ ጊዜ ኢየሱስ የግድ ወደ ውጭ ወጥቶ ይቆማል።
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በዚህ ዘመን ከቤተክርስቲያን ውጭ እንደሆነ ይናገራል። ስለዚህ “የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን” ጨምሮ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ከባድ ችግር ውስጥ ናቸው፤ ነገር ግን ችግር ውስጥ መሆናቸውን “አያውቁም” ምክንያቱም “አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም” ብለው ስለሚያስቡ እርማት አይቀበሉም። እርማት ያስፈልገናል ብለውም አያስቡም። እውር ስለሆኑ የራሳቸውን ጥፋት ማየት አይችሉም።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ በጣም አሳዛኝ ቃል ነው።
ቤተክርስቲያኒቱ የሳተች ቤተክርስቲያን ናት ግን ሃብትን በማሳደድ ስለተሳካላት በስሕተቷ ተመችቷት ተደላድላ ተቀምጣለች።
ኢየሱስ ግን መግቢያ አጥቶ በውጭ ቆሟል። ሲወለድ በእንግዶች ማረፊያ ውስጥ ለእርሱ ቦታ አልነበረም፤ በቤተክርስቲያን የመጨረሻ ዘመንም ለእርሱ ሥፍራ የለም።
1ኛ ቆሮንቶስ 16፡22 ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።
“ማራናታ” ማለት “ጌታችን መጥቷል” ማለት ነው።
“አናቴማ” ማለት “በታላቅ እርግማን ማሰር” ማለት ነው።
ልክ በፉኩሺማ ጃፓን፣ ቼርኖቢል ዩክሬይን ከኑክልየር የመጣ ሬድዮአክቲቭ ጨረር፣ እና በሒሮሺማ እና ናጋሳኪ በተባሉ የጃፓን ከተሞች የወደቀው የአተም ቦምብ ተጽእኖዎች ሳይጠፉ ለረጅም ጊዜ እስካሁን እንደቆዩት ሁሉ እርግማንም ለረጅም ጊዜ ተጽዕኖው ሳይጠፋ ይቆያል።
የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን የማንወደውና የማንከተለው ከሆነ እርሱ ሲመጣ የዳኑ ክርስቲያኖች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ በዚያ በታላቅ መከራ ወቅት የዳኑ ክርስቲያኖች ዓለምን ሁሉ በሚያዳርሰው የኑክሊየር እልቂት ውስጥ ታስረው ይቀራሉ። የኑክሊያር ቦምብ መፈንዳት ሲጀምር ሕይወት በምድር ላይ ሲኦል ይሆናል።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡10 የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
ታላቁ መከራ ከመጣ በኋላ ሞት እና ሲኦል ለመጨረሻ ጊዜ ተከታትለው ይመጣሉ። እርግጠኛ ነኝ እዚያ ውስጥ መግባት አትፈልጉም።