ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 4

ኢየሱስ በምድረ በዳ ለአርባ ቀን ጾመ። በሥው ደክሞ በነበረበት ሰዓት በዲያብሎስ ተፈተነ። ሰይጣንን ለማሸነፍ አንዳችም መለኮታዊ ስጦታዎች ወይም ኃይል አልተጠቀመም። ለቀረበለት ለያንዳንዱ ፈተና “… ተብሎ ተጽፏል” እያለ ከብሉይ ኪዳን ቃል እየጠቀሰ ነው ምላሽ የሰጠው።

እንደ ሰው ኢየሱስ ፈተናን የተቋቋመው በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል በመጽናት ነው። ራሱን መከላከያ ብቸኛ መሳሪያው ቃሉ ነበር።

ኢየሱስ ፍጹም የሆነ አርአያችን ስለሆነ እኛ ሰዎች እርሱ የሄደበትን መንገድ በጥንቃቄ መከተል አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን እንደተጻፈ ማወቅና በተጻፈው ቃል መጽናት አለብን። ከሰዎች አመለካከትና ከአባቶች ወግ ጋር ለመስማማት ብለን ከተጻፈው ቃል አልፈን መሄድ የለብንም።

ኢየሱስ ወደ ናዝሬት ሄዶ ምኩራብ ውስጥ ቆመ።

ሉቃስ 4፡17-19 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት (ለኢየሱስ)፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።

የመጨረሻው ቁጥር ላይ ሲደርስ እስከ ግማሹ አንብቦ አቆመ። ለምን?

ኢሳይያስ የተናገረው ሙሉው ቃል እንደሚከተለው ነው፡-

ኢሳይያስ 61፡2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤

ኢየሱስ በዚህ ቃል ውስጥ ድንቅ መገለጥ ሰጥቶናል። ኢሳይያስ ውስጥ ቁጥር ሁለት በመካከላቸው በ2,000 ዓመታት ስለሚራራቁ ሁለት ታላላቅ ክስተቶች ይናገራል።

“የተወደደችው የእግዚአብሔር ዓመት” ማለት የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ነው።

“አምላካችን የሚበቀልበት ቀን” ደግሞ ከኢየሱስ ዳግም ምጻትና ሙሽራዋ ከተነጠቀች በኋላ የሚመጣው ታላቁ መከራ ነው።

ስለዚህ የእውነትን ቃል ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል መተርጎም መቻል አለብን። እያንዳንዱ ቃል ስለምን እንደሚናገር ማወቅ አለብን።

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15 የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፡-

ማቴዎስ 17፡10 ደቀ መዛሙርቱም፦ እንግዲህ ጻፎች፦ ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ መሲኁ መሆኑን አውቀዋል። ነገር ግን ከኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት በፊት ኤልያስ ለምን እንዳልመጣ ማወቅ ፈልገዋል። በሌላ አነጋገር ደቀመዛሙርቱ የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ምን እንደነበረ ፈጽመው አልተረዱም። ስለዚህ እኛም መጠንቀቅ አለብን። እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ታላቅ የሆነ ሰው በዘመናችን ሊመጣ ይችላል፤ ነገር ግን ልክ ደቀመዛሙርቱ የመጥምቁ ዮሐንስን አገልግሎት እንዳላስተዋሉ እኛም በዘመናችን የሚገለጠውን ታላቅ መልእክተኛ የአገልግሎቱን ትርጉምና ዓላማ ላናስተውል እንችላለን።

ከዚያም ኢየሱስ ከዳግም ምጻቱ በፊት ስለሚገለጥ ኤልያስ ይናገራል። ይህም ነብይ የዳንነውን ክርስቲያኖች ወደ ትክክለኛው የወንጌል እውነት ይመልሰናል፤ ይህም ወንጌል በጨለማው ዘመን ውስጥ የጠፋው የመጀመሪያዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ነው።

ይህ ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ዮሐንስ ሙሉውን ወንጌል ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አላመጣም። የዮሐንስ አገልግሎት የወንጌል መጀመሪያ ነበረ ምክንያቱም እርሱ የውሃ ጥምቀትን በማስተዋወቅ መሲኁን ለእሥራኤል ለይቶ ማሳየት ነበረ ሥራው።

ማርቆስ 1፡1 የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።

2 እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ … ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የመጥምቁ ዮሐንስን አገልገሎት ጠቅሶ ይናገራል፤ ኢየሱስ በተናገረ ሰዓት የዮሐንስ አገልግሎት አልፏል።

ማቴዎስ 17፡12 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።
13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል እንተርጉም።

ኢየሱስ መጀመሪያ ወደፊት ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት ስለሚገለጠው ኤልያስ ተናገረ።

ከዚያ በኋላ ደግሞ ከኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት በፊት ስለተገለጠው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ተናገረ።

እነዚህም በኤልያስ መንፈስ እና ኃይል የሚደረጉ ሁለት የተለያዩ አገልግሎቶች ሲሆኑ በመካከላቸውም የ2,000 ዓመታት ክፍተት አለ።

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
“የእግዚአብሔር ቀን” ታላቁ መከራ ነው።

6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል እንተርጉም። ሁለት የተለያዩ አገልግሎቶች አሉ። እግዚአብሔር የተሳሳቱ እምነቶችን መልካም ወደሆኑ ወደ ትክክለኛ እምነቶች ይለውጣቸዋል።

የመጀመሪያው የተሳሳቱትን አባቶች እውነትን ወደተረዱት ልጆች መመለስ ነው።

ከዚያ በኋላ የሚመጣው ሌላ አገልግሎት ደግሞ የተሳሳቱትን ልጆች እውነትን ወደያዙት አባቶች መመለስ ነው።

ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ትክክለኛውን እውነት ያወቁት ልጆች ኢየሱስ እና የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ነበሩ።

ዮሐንስ ስሕተት ውስጥ የነበሩትን የአይሁድ አባቶች እውነትን ወዳወቁት ልጆቻቸው ማለትም ወደ ኢየሱስ እና ወደ ደቀመዛሙርቱ መለሳቸው።

ኢየሱስ ከሄደ በኋላ ደቀመዛሙርቱ አድገው ለጥንቷ ቤተክርስቲያን መልካም ሐዋርያዊ አባቶች ሆነዋል።

ከዚያ ወዲያ ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያን እውነት ጠፋባት።

ዛሬ 30,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እንደመኖራቸው መጠን ሐዋርያዊ አባቶች በአስቆረቱ ይሁዳ ቦታ የተተካው ሐዋርያው ጳውሎስን ጨምሮ ያምኑት ወደነበረው የአዲስ ኪዳን ትክክለኛው ትምሕርትና እውነት መመለስ ያለብን የሳትነው ልጆች እኛ ነን።

በዚህ በተከፋፈሉ ቤተክርስቲያኖች ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ወደእኛ መልሶ የሚያመጣ ኤልያስ ያስፈልገናል።

ከመጀመሪያው ምጻትና ከዳግም ምጻት በፊት ከሚገለጡት ኤልያሶች መካከል ቤተክርስቲያን በሰባት ደረጃዎች ውስጥ አልፋለች (ነጭ ብርሃን በቀስተደመና ውስጥ በሰባት የተለያዩ ቀለሞች ይከፋፈላል)። በነዚህ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን በአብዛኛው የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ነው የምትሆነው።

ቤተክርስቲያን የተጀመረች ጊዜ በብዛት በአይሁድ አማኞች ነው የተጀመረችው፤ ግን ከዚያ ወዲያ በብዛት አሕዛብ ያሉባት ቤተክርስቲያን ሆነች።

ለዚህ እውነት አጽንኦት ለመስጠት ወደ አሕዛብ የሚያመዝነው ሉቃስ ኢየሱስ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን እቅዱን ለመፈጸም የተጠቀመባቸውን ሁለት ከአሕዛብ ወገን ስለሆኑ ሰዎች መናገሩን ይጠቅሳል።

ሉቃስ 4፡25 ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤
26 ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።

ሲዶና የአሕዛብ ግዛት ነበረች።

ሉቃስ 4፡27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።

ሶርያ የአሕዛብ አገር ነበረች።

ስለዚህ ኤልያስም ኤልሳዕም (የኤልያስን መንፈስ እጥፍ የተቀበለው) አሕዛብን አገልግለዋል። ስለዚህ ከታላቁ መከራ በፊት የሚመጣው ኤልያስ ለመጨረሻው ዘመን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ነብይ ሆኖ መምጣቱ እንግዳ ነገር አይደለም።

ሉቃስ 4፡28 በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥
29 ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤
30 እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

ይህ የተለመደ የሰዎች ባሕርይ ነው። አይሁዶች በጣም ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ መስሏቸዋል። እግዚአብሔር ለአሕዛብም መልካምን ሊያደርግ እንደሚችል ሲሰሙ አይሁዶች ቁጣ ሞልቶባቸው ኢየሱስን ሊገድሉት ተነሱ።

በድጋሚ እግዚአብሔር ራሳቸውን እንደተወደዱ አድርገው ከሚቆጥሩ ሰዎች (አይሁዳውያን) ፊቱን ዘወር አደርጎ የተጠሉ ተብለው ወደተቆጠሩት አሕዛብ አይሁዶች ወደማይቀበሉዋቸው ዘንድ ፊቱን መለሰ።

ዛሬ ቤተክርስቲያንም ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ነች። ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው ሲባልና አሁን ደግሞ በጥንታዊቷ የተስፋ ምድራቸው መልሶ እየመሰረታቸው ወዳሉት ወደ አይሁዶች ሊመለስ ነው ሲባል ክርስቲያኖች ይናደዳሉ (ምክንያቱም በእኛ በጣም የሚደነቅብን ይመስለናል)። የዳኑ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን አባልነታቸው ተመክተው በጣም ቸልተኛ ሆነው መኖርን ተላምደዋል። ከዚህም የተነሳ መሳሳታቸውን የሚነግራቸውን ሰው ለመስማት እንኳ ዝግጁ አይደሉም። እነዚህ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ ሁላቸውም እርስ በእርሳቸው በትምሕርታቸው ይቃረናሉ። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እጅግ ብዙ ስሕተት አለ።

ሉቃስ ሐኪም እንደመሆኑ ድንቅ መድሐኒት ያሳየናል።

ሉቃስ 4፡38 በምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት።
39 በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው።

በዚህ ቃል ውስጥ ሉቃስ ወደፊት የምትነሳዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምትሰራውን ስሕተት ይነግረናል።

ስምዖን ጴጥሮስ ሚስት ነበረችው። የሮማ ካቶሊኮች ግን እርሱ “የመጀመሪያው ፖፕ” ነበረ ይላሉ። ታድያ የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ለምንድነው ሚስት የማያገቡት? ይህ ሥርዓታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር በግልጽ የሚጋጭ ነው።

ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበረ ይላሉ እርሱ ግን በኢየሱስ ስም ነው ያጠመቀው። ካቶሊኮች የእነርሱ ፖፕ የማይሳሳት ሰው ነው ይላሉ፤ ከሆነ ሁሉም ፖፕ ከጴጥሮስ ጋር መስማማት አለበት።

ስለዚህ የካቶሊክ ፖፕ ልክ ጴጥሮስ ባጠመቀበት መንገድ ነው ማጥመቅ ያለበት።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
40 በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና፦ ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ ብሎ መከራቸው።

የዛሬዎቹ የካቶሊክ ፖፕ ለምንድነው “የመጀመሪያው ፖፕ” ጴጥሮስ ባጠመቀበት መንገድ የማያጠምቁት?

የእኛም ትውልድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፉ እንግዳ ሃሳቦች የሚያምን “ጠማማ ትውልድ” ነው።

ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፎች ለጴጥሮስ ሰጥቶታል፤ ጴጥሮስም ንሰሐ እንድንገባ በመንገር እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድንጠመቅ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታንም እንድንቀበል በማስተማር የመንግሥተ ሰማያትን በር ከፈተልን። ይህ ትዕዛዝ እግዚአብሔር የሚጠራቸውን ሁሉ ይመለከታል። እኛም ይህንን ሥርዓት የመለወጥ ሥልጣን የለንም።

አንድ አምላክ አለ። እርሱም ሦስት ማዕረጎች አሉት፡- አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ። ነገር ግን እግዚአብሔር በሰዎች ዘንድ የሚጠራበት ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

አዲስ ኪዳን የተጀመረው የእግዚአብሔር መንፈስ ሰው በሆነው በኢየሱስ አካል ውስጥ ራሱን ሲገልጥ ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።

እግዚአብሔር አዲሱን ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው ሰብዓዊ ስሙን ከተቀበለ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ እንኳ እግዚአብሔርን በብሉይ ኪዳን ውስጥ በሚታወቅበት ያሕዌ በሚባለው ስሙ አይጠራውም።

ስለዚህ የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳኑ ያሕዌ ነው።