ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 3

መጥምቁ ዮሐንስ የኢየሱስ መንገድ ጠራጊ ነው።

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ወቅት በሐይማኖተኛ አይሁዳውያን ዘንድ የነበረው ሁኔታ በኢየሱስ ዳግም ምጻት ጊዜ የዳኑ ክርስቲያኖች መካከል ከሚሆነው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነበር።

ስለዚህ ዮሐንስ እንዲስተካከሉ ብሎ ለሕዝቡ የሚነግራቸውን የሰው ባሕርይ ችግሮች ሉቃስ ይጠቅሳቸዋል፤ እነዚህ ችግሮች እኛንም ይመለከታሉ።

ሉቃስ 3፡7 ስለዚህ ከእርሱ (ከመጥምቁ ዮሐንስ) ሊጠመቁ ለወጡት ሕዝብ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

ዮሐንስ ሐይማኖተኞቹን አይሁዳውያን ልክ ልካቸውን ይነግራቸዋል። እናንተ የእባብ ዘሮች፤ ወይም እባቦች የእፉኝት ልጆች ይላቸዋል። እፉኝቶች በአፋቸው ውስጥ መርዝ ያላቸው እባቦች ናቸው። መርዝ ማለት ማንኛውም ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቃረን እምነት ነው። ሲኦልን ብቻ ይፈራሉ እንጂ እግዚአብሔርን አይወዱም። የንሰሃ ፍሬ ስለማያፈሩ እግዚአብሔርን አለመውደዳቸው በሕይወታቸው ይገለጣል። የአብራሐም ዘር ስለሆኑ ብቻ ምንም የማይደርስባቸው መስሏቸዋል። ይህ የትምክሕት ምልክት ነው። እግዚአብሔር ምርጦቹን ሕዝቡን ትቶ ማንም ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ ብሎ ማይጠብቃቸውን የድንጋይ ልብ ያላቸውን ሰዎች እንደሚያስነሳ ዮሐንስ በመንገር ያስጠነቅቃቸዋል። ዛሬም በእኛ መካከል እንደ አይሁድ ሕዝብ አይነት አመለካከት አለ። የዳኑ ክርስቲያኖች ትምክሕት ይሞላቸውና በቤተክርስቲያን ውስጥ እስካሉ ድረስ ምንም እንደማይነካቸው ይሰማቸዋል፤ ነገር ግን እንዲህ ሁሉ ቸልተኛ የሚሆኑት በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች መካከል በሺ የሚቆጠር የተለያየ አይነት እርስ በርሱ የሚጋጭ እምነት እያለ ነው።

ሉቃስ ዮሐንስን በመጥቀስ እግዚአብሔር ሲሰራ ታላቅ እንደሆኑ የሚሰማቸውን ታዋቂ ሰዎች እንደማይቀበል ይናገራል። ተቀባይነት የማግኘት እድል የሌላቸውን ሰዎች መርጦ ያስነሳቸዋል። (ለዚህ አይነተኛ ማሳያ የሚሆነው ሰዎች የናቁት ያልተቀበሉት ትራምፕ በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ማሸነፉ ነው፤ በዚሁ ምርጫ ወቅት እርሱ አንዳችም የማሸነፍ ተስፋ ያልነበረው ሲሆን ሒላሪ ክሊንተን ደግሞ በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ነበረች። ትራም መልካም ሰው ነበር ለማለት አይደለም። እግዚአብሔር ግን ከፈለገ የድንጋይ ልብ ያለውን ሰው አስነስቶ ይጠቀምበታል።)

ሉቃስ 3፡8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን ማለትን አትጀምሩ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንዲችል እላችኋለሁና።

ሉቃስ 3፡9 አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።

የእግዚአብሔርን መስፈርት ካላሟላን የዳንን ክርስቲያኖች ብንሆንም እንኳ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ እንገባለን።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ምንም ሳያውቁ ግን በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ የሚሰማቸው እግዚአብሔር እንደጠራቸው እርግጠኛ የሆኑ የዳኑ ክርስቲያኖች ወደ ኋላ ቀርተው ታላቁ መከራ ውስጥ ሲወድቁ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሰው የጣላቸውን አንስቶ ማዳኑን ያሳያቸዋል።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ይህ በግልጽ ወደፊት እንደሚሆን ነው የተገለጸው። መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ኤልያስ ሆኖ መጥቷል፤ ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ቃል በተናገረ ጊዜ ዮሐንስ ሞቷል። ዮሐንስ ምንም ነገር አላቀናም። ዮሐንስ የውሃ ጥምቀትንና መሲሁን በማስተዋወቅ ሕጉን ገልብጦ ሄደ። ዛሬ ክርስቲያኖች ይድናሉ፤ ከዳኑ በኋላ ግን ግራ የሚያጋቡ የተለያዩ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ እምነቶች ውስጥ ተጠላልፈው ይቀራሉ። ስለዚህ ወደ አዲስ ኪዳኗ ቤተክርስቲያን እምነት የሚመልሰንና የሚያቀናን ሰው ያስፈልገናል። ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ ካልቻልን ከሲኦል እሳት ብንድንም እንኳ ወደ ታላቁ መከራ እሳት ውስጥ መግባታችን አይቀርም።

እኛ ክርስቲያኖች ለጌታ ዳግም ምጻት ምን ያህል ተዘጋጅተናል? እግዚአብሔር ወደ መጀመሪያዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ ይፈልጋል። ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ምን ያህል ተንቀሳቅሰናል? እምነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምሮ የሚያረጋግጥ ሰው ጠፍቷል። የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይምነት ማለትም አለማወቅ ደረጃው እንደ ወረርሽኝ ያህል ተስፋፍቷል። የዳኑ ክርስቲያኖች ከ30¸000 በላይ ከሚሆኑት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች የአንዱ አባል እስከሆኑ ድረስና አዘውትረው ቤተክርስቲያን እስከሄዱ ድረስ የመሪዎቻቸውን ንግግር እየጠቀሱ ከሌላው ሰው የበለጡና ምንም ችግር የማይገጥማቸው ይመሰላቸዋል። በጣም አሳዛኝ የሆነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስን የማወቅ ፍሬ በእኛ ዘንድ አለመገኘቱ ነው። መሃይምነታች በትዕቢታችን የተነሳ ጎልቶ ይታያል። ድነናል ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማወቅ የሚያስፈልገን አይመስለንም።

የመረጥነው ቤተክርስቲያን አዘውትረን እንሄዳለን፤ የቤተክርስቲያናችን መሪ ወይም ፓስተሩ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናል። ስለዚህ እኛ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ባናውቅም ስለዳንን ችግር የለም እያልን ራሳችንን እናታልላለን። ግን ታላቁ መከራ እየመጣ ነው፤ እኛም ልናመልጠው ከፈለግን በዘመናችን እየተከሰተ ያለውን ነገር ማወቅ አለብን።

ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ሰው በማስተዋወቅ መጥምቁ ዮሐንስ ለሰዎች የሰጠውን ምክር ጠቅሶልናል።

ሉቃስ 3፡10 ሕዝቡም፦ እንግዲህ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር።
11 መልሶም፦ ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር። (ለጋስ ሁኑ፤ ስጡ)
12 ቀራጮችም (ቀረጥ ሰብሳቢዎች) ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት።
13 ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው። (ስግብግብ አትሁኑ። ገንዘብ ላይ አታጭበርብሩ።)
14 ጭፍሮችም ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው። (ጨካኝ፣ ግፈኛ አትሁኑ። ፈርጠም በሉ ግን ፍትሃዊ ሁኑ፤ ሥራ ስላላችሁም ደስ ይበላችሁ፤ ተጨማ ደሞዝ አትጠይቁ።)

ሉቃስ ሰውን የሚመለከቱ እለታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፤ ደግሞም እንደ ሰው ያለብንን ትልቅ ድክመት ማለትም ራስ ወዳድነታችንንና ስግብግብነታችንን አጉልቶ ያሳየናል። የአይሁድ ጥያቄዎች በብዛት ከገንዘብና ከንብረት ጋር የተያያዙ ነበሩ። ዛሬም ክርስቲያኖች ዋነኛ ትኩረታቸው ገንዘብና ንብረት ነው። ከዚያም ሉቃስ ዮሐንስ የሰጣቸውን መድሐኒት ይነግረናል። ለድሆች ስጡ። ደሞዛችሁ እንዲበቃችሁ ኑሮዋችሁን ቀለል አድርጉ። በስልጣን ሥፍራ ብትቀመጡ ደግ ሁኑ፤ በቅንነት አስተዳድሩ። በስልጣን ወንበር የተቀመጣችሁት ሕዝብን እንድትረዱ እንጂ እንድትጨቁኑ አይደለም፤ ራሳችሁን ለማበልጸግም አይደለም።

ሉቃስ 3፡19 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ ገሠጸው፥
20 ይህን ደግሞ ከሁሉ በላይ ጨምሮ ዮሐንስን በወኅኒ አገባው።

ጋብቻ እና ፍቺ ከጥንትም ጀምሮ እስከ ዛሬም በሰዎች መካከል ትልቅ ጉዳይ ነው።

ሚልክያስ 2፡16 መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥

“መፋታት” የትዳር መፍረስ ነው። እግዚአብሔር መፋታትን ይጠላል።

ማቴዎስ 19፡6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።

በሕግ የተጋቡ ባልና ሚስትን ማንም ማፋታት አይችልም። የጋብቻ ቃል ኪዳን ሞት እስኪለየን ድረስ ነው።

ስለዚህ ማንም ሰው የትዳር አጋሩን መፍታት አይችልም ወይም የፈታት ሚስት የፈታችው ባል በሕይወት ሳሉ እንደገና ማግባት አይችሉም፤ ምክንያቱም ቃለ መሃላው ሞት እስኪለየን የሚል ነው።

ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤

ማርቆስ 10፡12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።

ስለዚህ መፋታትና በድጋሚ ማግባት ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው።

ነገር ግን አንዲት ሴት ስታገባ ድንግል መሆን አለባት። ከማግበቷ በፊት ዝሙት ፈጽማ ከሆነ እና ይህንንም ለሚያገባት ሰው ቀድማ ባትነግረው የጋብቻ ቃል ኪዳንዋ የውሸት ይሆናል፤ በሚያገባት ሰውዬ ላይም አይጸናም።

ድንግል አለመሆንዋን ባወቀ ጊዜ ከፈለገ ወዲያው ፈቷት ሌላ ድንግል ሴት ማግባት ይችላል፤ ምክንያቱም የጋብቻ ቃልኪዳናቸው ዋጋ ቢስ ነው፤ የውሸት ቃልኪዳን ነው። ይህ ከተጋቡ በኋላ የሚፈጸምን ዝሙት አይመለከትም፤ ምክንያቱም በሕግ ተጋብተዋልና ሕጋዊ ጋብቻ ቃልኪዳኑ የሚጸናው እስከ ሞት ድረስ ነው። የጋብቻ ቃልኪዳን “በደጉም ሆነ በክፉው ጊዜ” የጸና ነው። ስለዚህ ዝሙት ደግሞ “ክፉው” ጊዜ ነው። ሆኖም ቃልኪዳኑን ዋጋ ቢስ አያደርገውም። ባል ወይም ሚስት ታማኝ ባይሆኑም እንኳ የጋብቻ ቃልኪዳን ሳይሻር ይጸናል። ስለዚህ ስለ ማመንዘር ብሎ ማንም መፍታት ወይም ድጋሚ ማግባት አይችልም።

ማቴዎስ 5፡32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት (ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ወሲብ) ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።

ንጉስ ሔሮድስ የወንድሙ ሚስት ባሏን እንድትፈታ አደረገና እራሱ አገባት። ይህ በጣም ታዋቂ የፍቺ እና እንደገና የማግባት ክስተት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ሔሮድስን ገሰጸውና ይህንን እውነት ስለመስበኩ ወዲያው ወደ እስር ቤት ተጣለ።

ሉቃስ ይህንን የሚጠቅሰው ለምንድነው? ምክንያቱም ፍቺ እና እንደገና ጋብቻ በኢየሱስ ዳግም ምጻት ጊዜ ትልቅ ሐጢያት ሆኖ ስለሚገለጥ ነው። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ላይ እያመቻመቹ ናቸው፤ ፍቺ እና ድጋሚ ጋብቻን መፍቀድ ጀምረዋል።

የተጋቡ ጥንዶች ከፈለጉ መፋታት ይችላሉ፤ ግን ከተፋቱ በኋላ ላጤ ሆነው መቅረት አለባቸው።

ወንዶችም ሴቶችም እግዚአብሔር ለጋብቻ ያስቀመጠውን መርህ የመጣስ ምኞታቸው ማቆሚያ የለውም።

ኔልሰን ሮክፌለር በ1962 ሚስቱን ከፈታ በኋላ በ1963 ሌላ ሚስት አገባ። እንዲህ በማድረጉ የተነሳ ብዙ ባለትዳር ሴቶች ድምጻቸውን አልሰጥ ስላሉት በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውስጥ ሦስት ጊዜ ለመወዳደር ቢሞክርም እንኳ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆን አልቻለም። በዚያን ጊዜ አሜሪካኖች ጋብቻ እስከ ሞት ድረስ መሆኑን ያምኑበት ነበር።

በ1980 ግን ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት ያገባው ሮናልድ ሬገን ፕሬዚደንት ሆኖ ተመረጠ።

ሁለት ጊዜ ፈቶ ሦስት ጊዜ ያገባው ዶናልድ ትራምፕ በ2016 ፕሬዚደንት ሆነ። ለአሜሪካኖች በአሁኑ ዘመን ፊቺ እና ድጋሚ ጋብቻ ትልቅ ነገር አይደለም።

አሁን ይህንን ቤተክርስቲያኖቻችን የሚታገሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ባሕርይ መጥምቁ ዮሐንስ ተገልጦ ቢያወግዘው አሁንም የሐይማኖት ቤት ባዘጋጀው እሥር ቤት ውስጥ ይቆለፍበታል።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ ስሕተት ውስጥ እየዘቀጥን እንገኛለን፤ እግዚአብሔርም ምንም የማይለን ይመስለናል። ግን ኋላ ይጠይቀናል።

ሉቃስ 3፡20 ይህን ደግሞ ከሁሉ በላይ ጨምሮ ዮሐንስን በወኅኒ አገባው።
21 ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥
22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

በዚህ ቃል ውስጥ አንድ ወሳኝ ነገር ተጽፏል።

ሉቃስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እና ስለ ስብከቱ በጥልቀት ይነግረናል። የዮሐንስ አገልግሎት በኢየሱስ መጠመቅ ከፍታው ላይ ከደረሰ በኋላ ግን ሉቃስ ሁለተኛ የዮሐንስን ስም አይጠቅስም። ለምን? ከኢየሱስ ስም ጋር ሲነጻጸር የዮሐንስ ስም ለመጠቀስ የሚበቃ አይደለም።

ሆኖም ዮሐንስ ከታላላቅ ነብያት አንዱ ነበር። እርሱ መሲሁን ያስተዋወቀ መልእክተኛ ነብይ ነው።

ሉቃስ ክስተቶቹን በቅደም ተከተላቸው አይደለም የመዘገባቸው። ዮሐንስ በእስር ቤት ስለመግባቱ ይጠቅሳል፤ ይህም ስለ ዮሐንስ ማውራትን ለማቆም ጥሩ ምክንያት ይሆነዋል። ከዚያም ሉቃስ በጊዜ ወደ ኋላ በመመለስ የኢየሱስን መጠመቅ ይጠቅሳል፤ በዚህም ውስጥ የዮሐንስን ስም አይጠቅስም።

ስለዚህ ሉቃስ ምን እየነገረን ነው? ሰው እንደመሆናችን ኢየሱስ ስለሞተልን ዋጋ አለን፤ ነገር ግን አንዳችም ጥቅም የለንም። ለእግዚአብሔር እናደርግለታለን ብለን የምናስበውን ማንኛውንም ነገር እግዚአብሔር ድንጋዮችን ተጠቅሞ ወይም የማይፈለጉ ሰዎችን ተጠቅሞ ማድረግ ይችላል ከፈለገ። ስለዚህ ማናችንም የታላቅነት ወይም የተፈላጊነት ስሜት ሊሰማን አይገባም።

ብዙ ክርስቲያኖች ዛሬ አስተሳሰባቸው ዘቅጦ ለራሳቸው አድናቆት ያላቸውና በሌሎች ዘንድ አድናቆት ለማግኘት የተራቡ ሰዎች ሆነው ቀርተዋል።

ሉቃስ በሚያሳየን እውነታ ግን ከኢየሱስ ጋር ስንነጻጸር ከዜሮ እንኳ አንበልጥም።

ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ መላእክት እግዚአብሔርን እያከበሩ ሲዘምሩ የሰሙት እረኞች በስም ሊጠቀሱ የሚበቁ ስላልነበሩ ስማቸው ማን እንደሆነ አልተጻፈም። ኢየሱስ የተጠመቀም ጊዜ በዘመኑ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ በስም አልተጠቀሰም።

ሰው በሆነው በኢየሱስ ፊት ከእርሱ ጋር ሲነጻጸር ሰው ሁሉ ከምንም አይቆጠርም።

በዚህ ዲጂታል የኢንፎርሜሽን ዘመን ሁለት ቁጥሮች አሉ፤ እነርሱም አንድ እና ዜሮ ናቸው።

እነዚህ ሁለት ቁጥሮች ዓለማችንን እንደ ጎርፍ ለሚያጥለቀልቀው የመረጃ ብዛት መሰረት ናቸው።

ኢየሱስ አንድ ቁጥር ሲሆን ከእርሱ ጋር ሲወዳደሩ ሰዎች ሁሉ ዜሮ ናቸው።

ሉቃስ ይህ የመንፈሳዊ እውቀታችን ሁሉ መሰረት እንዲሆን ይፈልጋል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 … ዕለት ዕለት እሞታለሁ።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ታላቅ ሐዋርያ ጳውሎስ ሁልቀን ዜሮ ለመሆን ነበር ትግሉ። ይህም የስኬቱ ሚስጥር ነበር።

ዜሮዎች የሆንን እኛ ከኢየሱስ ኋላ ብንሰለፍ እርሱም ከፊታችን ሆኖ ራስ ቢሆን ከዚያ በኋላ የሚጨመር ዜሮ ሁሉ ከፊት ባለው አንድ የተነሳ ዋጋው ከፍ ይላል። ለምሳሌ 1 000 000 ከ 100 የሚበልጥ ዋጋ አለው።

የአውሬውን ምልክት መቀበል የለብንም፤ የአውሬው ምልክት በ666 ነው የተወከለው።

ዜሮ ብቸኛው መቆጠር የማይችል ቁጥር ነው። የትኛውም ቁጥር ዜሮ ሲደመርበት ወደ 666 ሊጠጋ አይችልም።

ስለዚህ ጨረቃ የፀሃይን ብርሃን ብቻ እንደምታንጸባርቀው እኛም “… ተብሎ ተጽፏል” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ብቻ ነው ማንጸባረቅ ያለብን። የራሳችን አመለካከት ዋጋው ዜሮ ነው። እንደ 1 ሊቆጠር የሚችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው ብቻ ነው።

የአውሬው ምልክት ማለት የሰዎች አእምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፈ በሰው ወግ፣ ልማድና አመለካከት ሲሞላ ማለት ነው።

ሉቃስ ፍጹም ሰው የሆነው የኢየሱስን የዘር ሐረግ መዝግቧል፤ የዘር ሃረጉም የመጀመሪያው ፍጹም ሰው እስከነበረው እስከ አዳም ይደርሳል።

አዳም ግን ወደቀ፤ ይህም ማለት ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደመሆኑ በፍጹምነት ሊኖር ይጠበቅበታል፤ ግን ይህም ብቻ ሳይሆን አዳም በውድቀቱ በኤደን ገነት ውስጥ ሳለ ያበላሸውን ነገር ሁሉ ኢየሱስ ማስተካከል እና ሁላችንን መዋጀት አለበት።

ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አይደለም። ዮሴፍ የኢየሱስ አባት አለመሆኑን ማርያም ስታገባው የሦስት ወር ነፍሰ ጡር መሆንዋ ማረጋገጫ ነው። ዮሴፍ የነገስታት ዘር ነው ምክንያቱም የትውልድ ሃረጉ የሰሎሞን አባት ከነበረው ከንጉስ ዳዊት ወገን ነው።

ነገር ግን ይህ የነገሥታት የዘር ሃረግ በንጉሥ ኢኮንያን ሐጥያት ምክንያት ተቋርጧል።

ኤርምያስ 22፡24 እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ እነቅልህ ነበር፥ ይላል እግዚአብሔር፤

ኤርምያስ 22፡28 በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?

ኤርምያስ 22፡30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።

እግዚአብሔር የኢኮንያን የልጅ ልጆች በዙፋን እንደማይቀመጡ ተናግሯል። ስለዚህ ዮሴፍ የኢኮንያ የልጅ ልጅ ልጅ ስለሆነ ሊነግስ አልቻለም።

ሉቃስ ይህንን የሰው ችግር በግልጽ ይጠቅሰዋል። የንጉሥ ሰሎሞን የልጅ ልጆች ከንጉሥ ኢኮንያን ጀምሮ ከንጉሥነት ከተቆረጡ ኢየሱስ እንዴት የአይሁድ ንጉሥ መሆን ይችላል? ይህ ጥያቄ ሉቃስ የኢየሱስን የትውልድ ሃረግ በማርያም በኩል በዳዊት የመጀመሪያ ልጅ በናታን በኩል አድርጎ እንዲቆጥር አድርጎታል።

ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥

ኤሊ የማርያም አባት ነበረ። ዮሴፍ ማርያምን ስላገባ እና ኢየሱስን ያሳድግ ስለነበረ ሰው ሁሉ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ የነበረ መሰለው።

ሉቃስ 3፡31 የዮናን ልጅ፥ የኤልያቄም ልጅ፥ የሜልያ ልጅ፥ የማይናን ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥ የናታን ልጅ፥ የዳዊት ልጅ፥

ይህ የትውልድ ሃረግ በኢኮንያን ላይ ከመጣው እርግማን ነጻ ነው፤ ምክንያቱም ይህኛው ሃረግ ከሰሎሞን የዘር ሃረግ የተለየ ነው።

ዮሴፍ ኢየሱስን የማደጎ ልጅ አድርጎ አልተቀበለውም። እንደዚያ ቢቀበለው ኖሮ ኢየሱስ ሊነግሥ ይችል ነበር (የዮሴፍ የማደጎ ልጅ ተብሎ)። ኢየሱስም ደግሞ ከእርግማን ነጻ ነበረ፤ ምክንያቱም የማርያም ልጅ ስለሆነ እና ከዮሴፍ አብራክ ስላልተወለደ። በማደጎ የሚያድግ ልጅ በቤት ከተወለደ ልጅ ጋር እኩል ክብር እና እኩል መብቶች አሉት።

ለዚህ ነው ማርያም ሳታገባ የመጸነሷን ነቀፋ ሁሉ በትዕግሥት የተሸከመችው። ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑን ማሳየት ነበረባት። ኢየሱስ የዮሴፍ የማደጎ ልጅ ነበር።