ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 19



ኢየሱስ ሰኞ ዕለት ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አባረረ። ሐሙስ ዕለት ሞተ። የቤተክርስቲያን መሪዎችን በገንዘባቸው አትምጡባቸው።

First published on the 17th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022

ቀራጮች ብዙውን ጊዜ እንዲሰበስቡ ከታዘዙት ቀረጥ በላይ ያለምንም ርህራሄ ሕዝቡን በማስከፈል ለራሳቸው ትርፍ ገንዘብ እያገኙ ሃብታም የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ። ኢያሪኮ ውስጥ ዘኬዎስ የተባለ አንድ አጭር ቀራጭ ከብዙ ሕዝብ መካከል ኢየሱስን ለማየት ዛፍ ላይ ወጣ። ኢየሱስም ዘኬዎስን ከዛፍ ላይ እንዲወርድ ካለው በኋላ ወደ ዘኬዎስ ቤት አብሮ በመሄዱ ወደ ሐጥያተኛ ቤት በመሄዱ ሰዎችን ሁሉ አስደንግጧል።

ሉቃስ 19፡8 ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን፦ ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው።
9 ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤
10 የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።

ሃብታሙ ዘኬዎስ ከገንዘቡ ግማሹን በሙሉ ለድሆች ለመስጠት ወሰነ፤ ከሰዎች አላግባብ የወሰደውን ገንዘብም በአራት እጥፍ እንደሚመልስላቸው ቃል ገባ።

ሉቃስ እዚህ ክፍል ውስጥ የሚያሳየን ኢየሱስ በአንድ ሃብታም ሰው ላይ ያመጣበትን ተጽእኖ ነው፤ ይህም ተጽእኖ ሃብታሙ እውነተኛ ለመሆንና ሃብቱን ከድሆች ጋር ወዲያ ለመካፈል እንዲፈልግ አድርጎታል። ኢየሱስን ስንገናኘው ዓይናችንን ከራሳችን ላይ አንስተን ድሆችን እንድንመለከትና እንድናስባቸው ያደርገናል።

ሉቃስ አሁን ከበድ ያለ ትምሕርት ያስተምረናል። አንድ መኮንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለስ ወደ ሩቅ ሃገር ሄደ። ሲሄድም ንብረቱን እንዲያስተዳድሩለት ለሰራተኞች ትቶላቸው ሄደ። ሰዎቹ ግን መኮንኑን ስለጠሉት በላያቸው እንዲነግስ አልፈለጉም። ለያንዳንዱ ሰራተኞችም አንድ ምናን ሰጥቷቸው ሄደ።

ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ ለእኛ ሥፍራን ስለሚያዘጋጅበት ጊዜ ነበር የተናገረው። በሄደ ጊዜ ግን እኛን ክርስቲያኖችን ለዓለም የወንጌልን እውነት እንድሰብክ አደራ ሰጥቶን ነው የሄደው፤ ይህ ዓለም ግን እውነትን የሚጠላ እና ኢየሱስ እንዲነግስ የማይፈልግ ዓለም ነው።

ሉቃስ 19፡11 እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።

እነርሱ የፈለጉት ኢየሱስ ወዲያው ሮማውያን ገዢዎቻቸውን አስወግዶ በእሥራኤል ውስጥ ምድራዊ የአይሁድ መንግሥት እንዲመሰርትላቸው ነበር። በጥቂት ዓመታት ውስጥ ፖለቲካዊ መንግሥት እንዲመሰረትላቸው ፈልገዋል።

በጌታ መገለጥ የተነሳ ብዙ ግራ መጋባት ሆኗል። ኢየሱስ ግን የያዘው እቅድ መጀመሪያ ለሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ወደ ሩቅ ሃገር ሄዶ መቆየት ነው። ከዚያም በዳግም ምጻቱ ከሙታን ካስነሳንና የተዋረደው ሥጋችንን የራሱን ክቡር ሥጋ እንዲመስል ከለወጠው በኋላ ለእኛ ይገለጥልናል።

1ኛ ዮሐንስ 2፡28 አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።

እርሱ ቃሉ ነው። ወደ አዲስ ኪዳን እምነት የተመለሱ ሰዎች ብቻ ናቸው የሚለወጡት። የተቀሩት የዳኑ ክርስቲያኖች ሳይወሰዱ ወደ ኋላ መቅረታቸውን ሲያዩ ተከፋፍለው በቡድን ስለተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያናዊነት ያፍሩበታል።

1ኛ ዮሐንስ 3፡2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ እውነተኛዎቹን አማኞች አዲስ አካል ያለብሳቸዋል።

12 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

ኢየሱስ ወደ ሩቅ ሃገር ስለሚሄደው መኮንን ይናገራል። ስለዚህ መኮንኑ ከመመለሱ በፊት ለረጅም ጊዜ ይቆያል ማለት ነው። ስለዚህ በጥድፊያ የሚፈጸም ነገር የለም። “ሩቅ ሃገር” የሚያመለክተው በስገብግብነት፣ በራስ ወዳድነትና በጥላቻ ከሚመሩት ምድራዊ መንግስታት የተለየ መንፈሳዊ መንግሥት በሺ ዓመቱ ዘመን እንደሚመሰረት ነው።

13 አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና፦ እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው።

ክርስቲያኖች ይኖሩበት ዘንድ አዲስ ኪዳን ተሰጥቷቸዋል። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከተጻፈው ቃል አንዳችም እንድንቀይር አልተነገረንም፤ የተነገረን ሐዋርያት የጻፉልንን እንዳለ እንድናምነውና ኢየሱስ እስኪመለስ ድረስ አጽንተን እንድንጠብቀው ነው። ክርስቲያኖች መንፈሳዊ እውነትን እና ሰዎች የሚድኑበትን ወንጌል ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ያካፍሉ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣቸው መሰረታዊ መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

14 የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና፦ ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ።

የዓለም ሕዝብ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ መገዛትን ይጠላሉ። በስተመጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስን የተወሰነ ክፍል የሚቀበሉ ቀሪውን ግን የማይቀበሉ ቤተክርስቲያኖች ብቅ ማለት ጀመሩ። ሰብዓዊ መብት የሚባል ሃሳብ መጣ፤ ሰዎችም ለምኞታችን እንደሚመቸን መኖር ይፈቀድልን ብለው አጥብቀው ጠየቁ። የሰውን ባሕርይ ገድበው የሚይዙ ብዙ ትዕዛዛት በሞሉበት መጽሐፍ ቅዱስ ለምን እንገዛለን ብለው ጠየቁ። ሰዎች እኛ የመጣነው ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከእንስሳት ነው ብለው ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ ንድፈ ሃሳቦችን ማዘጋጀት ጀመሩ።

አንድ መንስኤው ያልታወቀ “ቢግ ባንግ” ወይም ታላቅ ፍንዳታ የዓለም መፈጠር መጀመሪያ ነው የሚለውን ግምታዊ ሃሳብ ያመጡት ፈጣሪ ወይም እግዚአብሔር አያስፈልግም ለማለት ነው። ሰዎች እግዚአብሔር የለም ብለው ማሰብ የጀመሩ ጊዜ በሥነ ምግባራቸው ልቅ ለመሆንና የፈለጉትን አስጸያፊ እርኩሰት ለመፈጸም ኅሊናቸው ነጻ ሆነ።

የአረማውያን እምነቶችና ልማዶች በዘዴ ወደ ክርስትና አስተምሕሮ ውስጥ ሾልከው እንዲገቡ ተደረገ። ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ እና ሃብት የማሳደድ ፍላጎት ጋር ተጋባች። ከመቶ በላይ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን እውነት እንዲደበዝዝ አደረጉ። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማመን አስፈላጊ አይደለም ብለው ማሰብ ጀመሩ። ማቴዎስ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ብሎ ከጻፈ ሰዎች ግን ሲያነቡ ወደ በረት ውስጥ ገቡ ብለው ይለውጡታል። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር አልነገረንም፤ እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ “በላይ ስለምናውቅ” ልደቱን ከክርስትና በዓላት ሁሉ ታላቅ በዓል አድርገን እናከብረዋለን። እንዴት አይነት አስተዋዮች ነን? ለእግዚአብሔር ምን ማድረግ እንደምንፈልግ የምንነግረው እኛ ሆነናል። ከዚህም አልፈን መቼ ልናከብር እንደምንፈልግም ለእግዚአብሔር የምንነግረው እኛ ሆነናል፤ የምንፈልገውም ዲሴምበር 25 ቀን ነው።

እግዚአብሔርም እኛ ራሳችን በመረጥነው መንገድ ስናመልከው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እየለወጥን ራሳችንን ክርስቲያን ብለን ስንጠራ በጣም ሳይገረምብንና ሳያደንቀን አይቀርም። ኤርምያስ ምዕራፍ 10 ዛፍ ቆርጠን በወርቅና በብር እንዳናስጌጠው ይነግረናል፤ እኛ ግን ከቃሉ በላይ አውቀናል። የክሪስማስ ዛፎቻችንን የማይወዳቸው የለም።

ኤርምያስ ይህን ማድረግ የለብንም ብሎናል። ኤርምያስ ደግሞ ማን ሆኖ ነው ማድረግ የሌለብንን የሚነግረን። እኛ ዘመናዊ ሰዎች ብልሆች ነን።

ኤርምያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና።

(የከዋክብት ትንበያ - ኮከቦችህ የወደፊት እጣ ፈንታህን ይገልጣሉ። ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን ያምናሉ።)

3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

ስለዚህ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው ሄደዋል፤ እንደ በፊት ለመጽሐፍ ቅዱስም መገዛት ትተናል። “ነጻ” ወጥተናል።
ነገር ግን በስተመጨረሻ ኢየሱስ ሲመለስ ይጠይቀናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ሲመሰርታት በሰጠን የአዲስ ኪዳን እውነትና ትምሕርት ምን እንዳደረግንበት ይጠይቀናል።

መከሩን ፍለጋ ተመልሶ ይመጣል። በመጨረሻ የሚታጨደው ፍሬ መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ አይነት ነው፤ ማለትም በመጀመሪያ መቶ ዓመት ውስጥ አዲስ ኪዳን ከተጻፈበት እውነት ጋር ተመሳሳይ ነው።

ሉቃስ 19፡15 መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ።
16 የፊተኛውም ደርሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው።
17 እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።

ይህ ባሪያ ብዙ ሰዎችን ወደ አዲስ ኪዳን እምነት እንዲመለሱ ረድቷል ስለዚህ በሺ ዓመት መንግስት ውስጥ ብዙ ከተሞችን ይገዛል።

18 ሁለተኛውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው።
19 ይህንም ደግሞ፦ አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው።

ይህኛው ባሪያ ደግሞ ጥቂቶችን ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ትምሕርት አንዲመለሱ ረድቷል፤ ስለዚህ በጥቂቱም ቢሆን ታማኝነት ስላሳየ የመጀመሪያውን ባሪያ ያህል ባይሆንም በሺ ዓመት መንግስት ውስጥ በተወሰኑ ከተሞች ላይ ስልጣን ይሰጠዋል።

ሉቃስ 19፡20 ሌላውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤

ጌታ ሆይ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ይፈጽምና እኛን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት ይመልሰን ዘንድ ለሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ እንዲሆን ነብይ ልከህ ነበር። ቤተክርስቲያኖች ግን ከመልእክቱ ጋር አልተስማሙም፤ ስለዚህ እንዳላስቀይማቸውና እኔንም እንዳይጠሉኝ ያገኘሁዋቸውን የእውነት መገለጦች በሙሉ ምሳ ሰዓት ጠረጴዛ ላይ በሚነጠፈው ጨርቅ ጠቅልዬ አስቀምጫቸዋለው። በዚህ መንገድ ቤተክርስቲያኖች የእኔን ምሳ ፈንታ እንዳይከለክሉኝ ማድረግ ችያለው፤ ደግሞም መስማት የሚፈልጉትን ነግሬያቸዋለው።

ሉቃስ 19፡21 ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው።

ጨካኝ ሰው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ብቻ ጸንታችሁ ኑሩ። ይህ ባሪያ ግን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንደማይወዱ ገብቶታል።

ጌታ ከዘመኑ የቤተክርስቲያን ውስጥ መዝናኛ እና ዲስኮ ሙዚቃ ጋር አያመቻምችም። ጌታ ሰዎች በአንድ ስም እንዲጠመቁ ካዘዘ በኋላ በሦስት ማዕረጎች አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ የሚደረገውን ጥምቀት አይቀበለውም። የጌታ ሐዋርያት የእግዚአብሔር ስም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ነግረውናል። እኛ ግን እውነቱ ይህ መሆኑን ደፍረን ብንናገር ሐዋርያት ወዳስተማሩት ወደ አዲስ ኪዳን እውነት መመለስ የማይፈልጉት ቤተክርስቲያኖች ይጠሉናል።

ጌታ ምንም የማያመቻምች መምሕር ነው፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈውን ሥላሴ የሚል ቃል አይቀበለውም። ይህም ቤተክርስቲያኖችን ያበሳጫቸዋል። ስለዚህ ሦስተኛው ባሪያ ማንንም አላስቆጣም፤ የአዲስ ኪዳንን መሰረታዊ እውነቶችም ለማንም አልተናገረም።

ሉቃስ 19፡22 እርሱም፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ …

እግዚአብሔር ጨካኝ ነው። እግዚአብሔር ለብዙ ዓመታት በአይሁድ ዘንድ የሰለጠነውን ሳውል የተባለ ታላቅ ፈሪሳዊ ወስዶ ወደ ጳውሎስ ለውጦት ታላቅ ክርስቲያንና የፈሪሳውያን ቀንደኛ ጠላት አደረገው። ዲያብሎስም ስላልቻለ አልፈልግም አልጫወትም ብሎ አኮረፈ።

እግዚአብሔር ጨካኝ ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማርቲን ሉተርን አንደኛ የቤተክርስቲያኒቱ ምሁር መነኩሴ እንዲሆን አሰለጠነችው፤ ከዚያ ግን እግዚአብሔር ከእጃቸው ወሰደውና ያሳደገችውን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ከነሥርዓቷ እንዲገዳደደራት አስናሳው።

ዲያብሎስ አሁንም ከማኩረፍ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻለም።

እግዚአብሔር ጨካኝ ነው። ንጉሥ ሔንሪ ስምንተኛው ሥድስት ጌዜ ሚስት ያገባ እና ሁለቱን ሚስቶቹን የገደለ ክፉ ሰው ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሚስቱን ፈትቶ እንደገና ማግባት ከለከለችው፤ ይህም ትክክለኛ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ) ውሳኔ ነበር። ስለዚህ ሔንሪ ሚስት እየፈታ ለማግባት እንዲችል ፈልጎ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወጣ፤ በዚያውም እንግሊዝን የፕሮቴስታንት ሃገር አደረጋት።

ይህ ክፉ ንጉሥ በንዴት የወሰደው እርምጃ እንግሊዝን ፕሮቴስታንት ሃገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም ምክንያት ሆነ። ሰይጣን አሁንም አጉረመረመ።

ሒትለር አይሆዶችን ስለጠላቸውና ሊያጠፋቸው ስለፈለገ ከእነርሱ ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑትን ገደላቸው። ይህም ለጥቂት ጊዜ ዓለም በሙሉ ለአይሁዳውያን እንዲያዝናላቸው ስላደረገ በ1947 የተባበሩት መንግሥታት ለአይሁድ ሕዝብ ፓለስታይን ውስጥ ሃገር እንዲሰጣቸው በድምጽ ብልጫ ውሳኔ አስተላለፈ። ሒትለር ያደረገው ክፋት አይሁዳውያን ሃገር እንዲያገኙ ምክንያት ሆነ። ሒትለርም ሰይጣንም በአንድነት አኮረፉ።

ስለዚህ እግዚአብሔር መልካሙንም ይሁን ክፉውን ነገር ዓላማውን ለመፈጸም ይጠቀምበታል።

እግዚአብሔር ጨካኝ ነው። እግዚአብሔረ ሕይወታችንን በራሱ መንገድ ነው መምራት የሚፈልገው። እግዚአብሔር የእኛን አመለካከት የማዳመጥም ሆነ ከእኛ ጋር የመደራደር ፍላጎት የለውም። እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጀው የዘመን መጨረሻ እቅድ አለው። እኛ ደግሞ ለሃሳቡ ታዛዥ ካልሆንን በቀር አንዳችም አንጠቅመውም።

ሉቃስ 19፡22-23 ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው።

ገንዘቡ ወደ ባንክ ቢገባ ኖሮ ሌላ ሰው ነግዶ ያተርፍበት ነበር። እራሱ አንዳችም ሊሰራ ዝግጁ ካልሆነ ለምን ሰዎችን ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ ለመርዳት የሚተጋ ሰውን አልደገፈም?

እዚህ ክፍል ውስጥ ሉቃስ ሊያሳየን የፈለገው አንድ ጠንካራ የእግዚአብሔር መርህ አለ።

ዓለምም ይህንን መርህ ታውቀዋለች፡- “የማትጠቀምበትን ነገር ታጣዋለህ”።

ይህ በመንፈሳዊ ቋንቋ ምን ማለት ነው?

የመጨረሻው ዘመን ነብይ ያመጣቸውን መገለጦች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን እንድንመረምር ትክክል መሆናቸውን በቃሉ አስተያይተን እንድናረጋገጥ ነገረን።

ሉቃስ 19፡24 በዚያም ቆመው የነበሩትን፦ ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው።
ሉቃስ 19፡25 እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት።
ሉቃስ 19፡26 እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል።

እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መረዳትና መገለጥ ሰጥቷችሁ ከሆነ፤ እናንተም ለተገለጠላችሁ እውነት ምላሽ ብትሰጡና ሌሎችንም ልትረዱበት በትሞክሩ እግዚአብሔር ደግሞ ለእናንተ ተጨማሪ መገለጥ ይሰጣችኋል።

ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ እውነት ገልጦላችሁ ምንም ባታደርጉበት እግዚአብሔር ያንን መገለጥ ይወስድባችሁና በፊት ከነበራችሁበት ስሕተት የባሰ የጠለቀ ስሕተት ውስጥ ይተዋችኋል።

ከዚያም እግዚአብሔር ምስጢሩን ለሚያስተውሉ ሰዎች ይበልጥ ተጨማሪ መረዳትን ይሰጣቸዋል።

ሉቃስ 19፡27 ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።

መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ዋነኛ መመሪያቸው የማይቆጥሩ የዳኑ ክርስቲያኖች፤ ደግሞም ሐዋርያት በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን ወደተከተሉት እምነት የማይመለሱ የዛሬ ክርስቲያኖች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይሞታሉ። ለምን? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታቸው እንዲነግስ አይፈቅዱም።

ሉቃስ 19፡28 ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር።

በመጀመሪያው ምጻቱ የኢየሱስ ትኩረት ለፋሲካ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድና ለአይሁድ እንዲሁም ለአሕዛብ ሐጥያት መሞት ነበር።

በዳግም ምጻቱ ደግሞ ኢየሱስ ትኩረቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያንን አስወግዶ ኢየሩሳሌም ላይ በድጋሚ ትኩረት በማድረግ አይሁዶችን ወደ ምድራቸው ወደ እሥራእል መልሶ በማስገባት በዚያ እራሱን ለእነርሱ መሲህ መሆኑን መግለጥ ነው።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጠናቀቂያው ሲቃረብ የዓለም ክስተቶች በሙሉ በእሥራኤል ዙርያ ያጠነጥናሉ። ከ1941 እስከ 1945 በጀርመኒ አማካኝነት ፖላንድ ውስጥ የተደረገው የሥድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን ጭፍጨፋ ዓለም ሁሉ በደለኝነት እንዲሰማት ከማድረጉ የተነሳ የተባበሩት መንግሥታት በፓለስታይን ምድር ውስጥ ለአይሁዳውያን ሃገር ሊሰጣቸው ተገድዷል። አረቦች ይህንን ውሳኔ በመቃወም አይሁዳውያንን ከምድር ላይ ለማጥፋትና የእሥራኤልን ምድር ለራሳቸው ለመውሰድ አራት ጊዜ ጦርነት አወጁባቸው። እግዚአብሔር አይሁዳውያን በጦርነቶቹ ድል እንዲያደርጉ ረዳቸው፤ እነርሱም በወታደራዊ ኃይል የነበራቸውን ትንሽዬ ሃገር አሰፉ። ሶርያ፣ ጋዛ ውስጥ ያለው ሃማስ፣ እና ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሂዝቦላ በእሥራኤል ላይ በመተባበር ጠንካራ ተቃዋሚዋ ሆነው ተነሱ። እግዚአብሔርም በሶርያ ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲነሳ ስላደረገ ጦርነቱ እጅግ ከመክበዱ የተነሳ የሶርያ ፕሬዚዳንት አሳድ በጦርነቱ ውስጥ ይረዱት ዘንድ ሂዝቦላዎችን ለመናቸው። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ታላላቅ የእሥራኤል ጠላቶች ለብዙ ዓመታት በአሰቃቂ ጦርነት ውስጥ ተጠምደው ቀሩ። ከዚህም የተነሳ እሥራኤል ላይ ትንኮሳ ለማድረግ ጊዜ ስላጡ እሥራኤል በሰላም ኖረች።

ዶናልድ ትራምፕ ካልተጠበቀ ቦታ ተነስቶ የ2016 የአሜሪካ ፕሪዚዳንታዊ ምርጫ አሸነፈ። ሊያሸንፍ የቻለውም በእሥራኤል ውስጥ የነበው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲዛወር በማድረጉና ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና በመስጠቱ ነው።

እሥራኤልን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። እሥራኤል ያለንበተን ዘመን እንድናውቅ የምትረዳን የእግዚአብሔር የግርግዳ ሰዓት ወይም ምልክት ናት።

እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን ለመመለስ ስላሰበ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ለመንጠቅ እየተዘጋጀ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

ለ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይደረግ የነበረው የጦፈ ፍልምያ “ትራምፕ” የተባለው ስም ለብዙ ወራት በዜና ማሰራጫዎች ላይ እንዲታይ አድርጓል። ትራምፕ ብዙ ስሕተቶችን ሰርቷል፤ በምርጫ ዘመቻዎች ውስጥ በተደረጉ ክርክሮችም ብዙ ጊዜ በሒላሪ ክሊንተን ተሸንፏል።

ግን ትራምፕ (የስሙ ትርጉም በእንግሊዝኛ መለከት ማለት ነው) በሙታን ትንሳኤ ጊዜ የሚነፋውን የእግዚአብሔር መለከት ይወክላል።
አረቦች አጥብቀው ቢቃወሙም እንኳ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን ድጋፍ ማድረግ ይፈልጋል። ስለዚህ ወደ ሥልጣን በመውጣት እርሱ ለዚህ አይበቃብ ሲሉ ያጣጥሉት የነበሩትን ኤክስፐርቶች ጉድ አሰኝቷቸዋል። ተወዳጅዋ ሒላሪ ክሊንተን ተሸነፈች።

ይህ ለቤተክርስቲያኖች የማንቂያ ጥሪ ነው። የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነው።

ዛሬ በምድራችን ያሉ 30,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖች ስለዳኑ ሁላቸውም እግዚአብሔር ከሌላው አብልጦ የሚወዳቸው ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን ሁላቸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መመራትን እምቢ ይላሉ። ስለዚህ ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ ሙታን ሁሉ ሲነሱ ታላላቆቹ ቤተክርስቲያኖች ወደ ሰርጉ ሳይጋበዙ ሲቀሩ “ታናሽ መንጋ” የሆኑት ሰው የናቃቸው አማኞች ሐዋርያት ወዳስተማሩት የአዲስ ኪዳን እምነት በመመለሳቸው በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ ግብዣ ይሄዳሉ።

ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።

ከዚያም ኢየሱስ ፈጽሞ ባልተጠበቀ መንገድ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።

ደቀመዛሙርቱንም ወደ አንዲት በስም ያልተጠቀሰች በሰዎችም ዘንድ ትልቅ ሥፍራ ያልተሰጣት መንደር እንዲሄዱ ነገራቸው።

ከዚያም የአህያ ውርንጭላ ይዘው እንዲመጡ አላቸው። የአህያይቱ ባለቤቶች ምንም ያወቁት ነገር የለም፤ ነገር ግን አህያይቱን እንውሰድ ሲሉዋቸው እሺ አሉ። አህያይቱም ኢየሱስን ተሸክማ ወደ ከተማ ገባች፤ ከተማይቱ ግን ለኢየሱስ መምጣት አልተዘጋጀችም ነበር።

ሕዝቡ ኢየሱስን በድንገት ሲያዩት ተደሰቱ። የሐይማኖት መሪዎች ግን ተቃወሙት።

ሉቃስ 19፡29 ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና፦
30 በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፥ ፈትታችሁም አምጡት።
31 ማንም፦ ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው።
32 የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።
33 እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ፦ ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም
34 እነርሱም፦ ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ።
35 ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።
36 ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።
37 ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው፤
38 በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።
39 ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ፦ መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት።
40 መልሶም፦ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።

አሁንም ፈሪሳውያን ማለትም የሐይማኖት መሪዎች ናቸው ኢየሱስ ቃሉ የሚያደርገውን ሲቃወሙ የነበሩት።

ዛሬ ደግሞ የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው ሰው ሰራሽ ትምሕርቶችንና የቤተክርስቲያን ወጎችን በማስተማር አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይከተሉ የሚያደርጉት።

ክርስትና “በቤተክርስቲያናዊነት” ተተክቷል። ሰዎች “እኔ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔ የምትለኝን አምናለው” ይላሉ።

ሉቃስ 19፡41 ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥
42 እንዲህ እያለ፦ ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል።

አለማመን ኢየሱስን ያስለቅሰዋል። ኢየሱስ የሚደሰተው ሰዎች በቃሉ ሲያምኑ ብቻ ነው።

መሲሁ መጥቷል፤ እሥራኤልም ኢየሱስ ለአንድ ሺ ዓመት በምድር ላይ በሰላም ወደሚነግሥበት ዘመን ተቃርባ ጫፍ ላይ ደርሳ ነበር። ነገር ግን አይሁድ በሐይማኖት መሪዎቻቸው ስብከት ታውረው ነበር። አይሁድ ታማኝነታቸውን ለምኩራቦቻቸው፣ ለመቅደሳቸውና ለሐይማኖት መሪዎቻቸው ሰጥተዋል። የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ ላይ ከፈረዱበት ሕዝቡም እነርሱን ተከትለው ይፈርዱበታል። የሰው አመራር ከንቱነቱ ይህን ይመስላል።

በተመሳሳይ መንገድ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አለብን የሚሉ ሰዎችን ቢያወግዙ የቤተክርስቲያን አባላትም እነርሱን ተከትለው ያወግዛሉ። ልክ እንደ አይሁዳውያን የዛሬ ቤተክርስቲያኖችም መዳንን እና መልካም ሥራዎችን ቢቀበሉም እንኳ ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ መመራትን ግን እሺ አይሉም። ነፍሳቸው ከሲኦል ቢድንም እንኳ ሥጋቸው ግን በታላቁ መከራ ውስጥ ገብቶ ሊጠፋ ተዘጋጅቷል።

ሉቃስ 19፡43 ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤
44 አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና።

በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል ታይተስ ኢየሩሳሌም ላይ ዘመተባት። ሮማውያን በኢየሩሳሌም ዙርያ ታላቅ ቅጥር ሰርተው መሸጉባት፤ ከዚያም የተነሳ አንድ ሰው ሊያመልጥ አልቻለም። 1,100,000 አይሁውያን ሕጻናትና አዋቂዎች አለቁ። መቅደሱም ተቃጥሎ ወደመ። ከተማይቱ ፈራረሰች፤ ባዶዋንም ቀረች። አይሁድ ኢየሱስ በመካከላቸው የመገኘቱ ሚስጥር ምን እንደሆነ አልገባቸውም። ከሰሩት ስሕተት ሁሉ ትልቁ ስሕተታቸው እርሱን አልቀበል ማለታቸው ነበር። እርሱ በመካከላቸው ነበር ግን ማን እንደሆነ አላወቁም።

የመጨረሻው ዘመን ነብይ የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያና ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳናዊ እምነት መመለስ እንደሚያስፈልጋት ይህን ሚስጥር ገልጧል። ቤተክርስቲያን ግን ያለንበት ዘመን ምን እንደሆነ እንኳ አልገነዘበችም። ስለዚህ የቆዩበትን የቤተክርስቲያን ወግ ቀጥለውበታል። እርሱ በተጻፈው ቃሉ አማካኝነት በመካከላችን መሆኑን እንኳ ልብ አላልንም።

ሉቃስ 19፡45 ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤
46 እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።

ኢየሱስ ቤተክረስቲያኖች ወደ ፊት ታላላቅ የገንዘብ መከማቻዎች እንደሚሆኑ ይህም ለክርስትና ማፈሪያ እንደሚሆን አስቀድሞ ተረድቷል። ኢየሱስ ሐይማኖትን ለሃብት ማከማቻ አድርገው የሚጠቀሙ ሰዎችን ይጠላል። አገጫቸውን የሥጋ መረቅ ውስጥ የነከሩ ወፋፍራም የሐይማኖት ቅልቦች በጣም ያስቆጡታል። ነገር ግን የወርቅ እና የብልጽግና አምልኮ የዛሬዋን የቤተክርስቲያን ዓለም አጥለቅልቋል።

ማቴዎስ 19፡23 ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።

ሰማይ ውስጥ ሃብታም ሰባኪዎችና ፓስተሮች አይኖሩም። ጉባኤው በሃብት በጣም በበለጠገ መጠን ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የዛኑ ያህል ከባድ ይሆንበታል።

ሉቃስ 19፡47 ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ ታላላቆችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፥

48 የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።

ተራው ሕዝብ ኢየሱስን ይወዱታል፤ መጽሐፍ ቅዱስን ለማመንም ዝግጁ ናቸው።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ደግሞ ዋነኛ የተጠመዱበት ሃሳብ ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ መሆንን ፈጽሞ ማጥፋት ነው።

ሰዎች ከመጀመሪያው እንዲስቱ ለማድረግ ብለው ከመቶ በላይ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን አዘጋጅተዋል። ሰባኪዎች በቀላሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ለማለት ይደፍራሉ። ብዙ ቤተክርስቲያኖች ዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ትክክል አይደለም ብለው ለማስተማር የቢግ ባንግ ንድፈ ሃሳብን ይጠቀማሉ። ይህ ንድፈ ሃሳብ ግን የዓለማችንን 96 በመቶ የሚሸፍነውን ዳርክ ማተር እና ዳርክ ኤንጂ ምን እንደሆ አንዳች እንኳ አይገልጽም። ስለዚህ የግኡዙን ዓለም ዘጠና ስድስት በመቶ እውነታ በብዛት ቸል ብሎ የሚያልፍ ንድፈ ሃሳብ እንደመሆኑ የሚረባ ንድፈ ሃሳብ አይደለም።

ቤተክርስቲያኖች የኤቮልዩሽን ወይም የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሃሳብን ያስፋፋሉ፤ እርሱም ሰዎች የመጡት ከእንስሳት ነው የሚል ሃሳብ ነው። ከዚያ ሰው ለምን እንደ እንስሳ ይሆናል ብለው ያማርራሉ። በኤቮልዩሽን ማመናቸው አስተዋይ ያደረጋቸው ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር መልክ እንደመፈጠሩ መጠን ሰው ከእንስሳ ነው ማለት ለእግዚአብሔር ትልቅ ስድብ ነው። አዳማ ሐጥያተ ከመስራቱ በፊት ሞት አልነበረም። ስለዚህ ሐጥያት ከመምጣቱ በፊት እንስሳት ለሚሊዮን ዓመታት ይሞቱ ነበር ማለቱ ትርጉም አይሰጥም። ሞት ለሐጥያት የመጣ ቅጣት ነው።

በኖህ የጥፋት ውሃ የተነሳ ፎሲል ወይም ቅሪተ አካሎች ሊፈጠሩ የቻሉት ዘጠኝ ኪሎሜትር ያህል ጥልቀት ባለው ተራሮችን በሸፈነው ውሃ ክብደት ሲደፈጠጡ ነው። ዛሬ ግን አንዳችም ቅሪተ አካል ሊፈጠር አይችልም፤ ሳይንቲስቶች ላብራቶሪ ውስጥ ሊፈጥሩ ሲሞክሩ እንኳ አይፈጠርም። ለምን? ገና ወደ ቅሪተ አካልነት ከመለወጣቸው በፊት ባክቴሪያ እና ሌሎች ሕዋሳት ቀድመው ያበሰብሷቸዋል። በእድሜው ከሁሉም ጥንታዊ የሆነው ቅሪተ አካል ትራይሎባይት ነው፤ ነገር ግን ትራይሎባይት ራሱ የተገኘው በሰው የጫማ ዱካ ቅሪተ አካል ውስጥ ነው፤ ያገኘውም በ1968 ዊልያም ሜይስተር የተባለ ሰው ደልታ ዩታህ አጠገብ አሜሪካ ውስጥ ነው። ስለዚህ ቅሪተ አካሎች የሚሊዮን ዓመታት እድሜ የላቸውም።

ልክ እንደ “ክሪስማስ” እና “ዲሴምበር 25” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ የማይገኙ ቢሆኑም እንኳ እንደ “ሥላሴ” “አንድ አምላክ በሦስት አካላት” እና “የሥላሴ ሁለተኛው አካል” የተባሉ ባዕድ ቃላት የቤተክርስቲያን እምነት ውስጥ ተካትተዋል። ቤተክርስቲያኖች እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች እውነት አድርገው መቀበልን ከመላመዳቸው የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ብቸኛው የእውነት መመሪያቸው አድርገው መቁጠር ትተዋል።

በዚህ መንገድ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማራራቅ ተሳክቶላቸዋል። ሰብዓ ሰገል ኢየሱስን ለማየት ወደ በረት ውስጥ ገቡ ብለህ ካመንክ የቤተክርስቲያን መሪዎች በስራቸው ተሳክቶላቸዋል፤ ምክንያቱም አንተ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማመን ትተሃል።

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23