ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 18
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ባለጠጋው ወጣት ለሃብት ብሎ ኢየሱስን መከተል ተወ። ቤተሰብን ጨምሮ ሁሉን ትተው ኢየሱስን የሚከተሉ ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ።
First published on the 17th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022ኢየሱስ አንዲት ፍርድ እስኪፈረድላት ድረስ ዳኛውን ስጨቀጨቀች ሴትዮ ተናገረ። በስተመጨረሻም ዳኛው እንዲህ አለ፡-
ሉቃስ 18፡5 ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ።
6 ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።
7 እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
ስለዚህ ኢየሱስ አለመታከት ጥሩ ባሕርይ መሆኑን ይነግረናል።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል።
ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ እምነትን ያገኝ ይሆን? ብዙም አያገኝም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ጥቅሶች ሁሉ የሚያሳዝነው ጥቅስ ይህ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የቤተክርስቲያን ልማዶችና ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች ናቸው የሚያስደንቋቸው።
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ስለሚጸልዩ ሁለት ሰዎች ተናገረ።
ሉቃስ 18፡9 ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥
10 እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
11 ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
12 በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
እግዚአብሔር እኛ ምን ያህል መልካም እንደሆንን ስንነግረው መስማት አይፈልግም። እግዚአብሔር ሰው ራሱን በራሱ ሲያጸድቅ ምንም አይገርመውም።
ሉቃስ 18፡13 ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
14 እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።
እግዚአብሔር ጆሮውን ሰጥቶ የሚያደምጠን ሐጢያታችንን እና ድክመታችንን በግልጽ ስንናዘዝ ነው።
እግዚአብሔር አስተሳሰቡ ከእኛ ተቃራኒ ነው። እኛ በራሳችን መልካም ነን ብለን ካሰብን እግዚአብሔር ልካችንን ያሳየናል።
እኛ ደግሞ ምንም የማንጠቅም መሆናችንን ብንናዘዝ እግዚአብሔር እራሱ ይረዳናል።
ሉቃስ 18፡15 እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም አይተው ገሠጹአቸው።
16 ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ፦ ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
17 እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ።
በመጨረሻው ዘመን ልጆች ወደ አባቶቻቸው ሐዋርያዊ እምነት መመለስ አለባቸው። እኛ ልጆች የእግዚአብሔር ቃል ወደሆነው ወደ ኢየሱስ መመለስ አለብን። ትንሽ ልጅ አባቱ እንዲጠብቀው፣ እንዲመራውና የሚያስፈልገውን እንዲሰጠው ሙሉ በሙሉ ያምንበታል።
ትንሽ ልጅ የማንንም ወሬ መስማት አያስፈልገውም። ስለዚህ እኛ የመጨረሻው ዘመን ትንንሽ ልጆች እንደመሆናችን አባቶቻችን ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከጻፉልን ቃል ውጭ ሌላ አይነት ምሪት አያስፈልገንም።
ሉቃስ 18፡18 ከአለቆችም አንዱ፦ ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
19 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።
ሰዎች የመልካም እና የክፉ ድብልቅ ናቸው። እግዚአብሔር ብቻ ነው መልካም። ስለዚህ ኢየሱስን “መልካም” ብሎ በመጥራት ይህ ሰው ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን እየተናገረ ነው።
ይህ ሰው አሥርቱን ትዕዛዛት ጠብቋል።
ሉቃስ 18፡22 ኢየሱስም ይህን ሰምቶ፦ አንዲት ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
23 እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ።
24 ኢየሱስም ብዙ እንዳዘነ አይቶ፦ ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል።
25 ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ሊገባ ይቀላል አለ።
ኢየሱስ በድጋሚ በምድር የመኖራችን ዓላማ ሐብት ማካበት አለመሆኑን በግልጽ ነናገረ። ሐብታሙ ሰውዬ ሐብቱን ትቶ መሄድ አልቻለም። ከእግዚአብሔር ይልቅ ሐብትን መረጠ።
ኢየሱስን በማስቀደም ብቻ ነው ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት የምንችለው። ሐብታሞች ገንዘባቸውን ያስቀድማሉ። ስለዚህ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዳይገቡ ገንዘብ እንቅፋት ይሆናባቸዋል። ስለዚህ እባካችሁን በብልጽግና ወንጌል አትታለሉ። የእግዚአብሔር እውነተኛ በረከቶች መንፈሳዊ ናቸው።
እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ያለው ዋነኛ ዓላም እኛን ወደ አዲስ ኪዳናዊው የሐዋርያት እምነት እንድንመለስ ማድረግ ነው።
ሉቃስ 18፡26 የሰሙትም፦ እንግዲህ ማን ሊድን ይችላል? አሉ።
27 እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ።
ስለዚህ ሊያድነን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ግን የሚያድነን እርሱን ስናስቀድመው ነው።
ጴጥሮስ ሁሉን ነገር ትቶ ኢየሱስን መከተል እንደሚያስፈልግ ይነግረናል።
ሉቃስ 18፡28 ጴጥሮስም፦ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ አለ።
29 እርሱም፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ቤትን ወይም ወላጆችን ወይም ወንድሞችን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን የተወ፥
30 በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም አላቸው።
ስለ እግዚአብሔር ብለን ቤተሰባችንን ትተን ለመሄድ ዝግጁ መሆን አለብን። እርሱ ከሁሉ በላይ የምንወደው ወዳጃችን ሊሆን ይገባል እንጂ ዝም ብሎ እንደ ተራ ጓደኛ የምንቆጥረው መሆን የለብንም።
እውነተኛው ሽልማታችን በሰማይ ውስጥ ነው ያለው። ነገር ግን በምድር እያለንም ሽልማት አለን። እዚህጋ በቁሳቁስ አንጻር ብቻ እንዳናስብ መጠንቀቅ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተጻፉት ሚስጥራት ዓይናችንን በመክፈት እግዚአብሔረ አስደናቂ መንፈሳዊ ሽልማትን ይሸልመናል። እኛ ግን ብዙውን ጊዜ ከመንፈሳዊ ሽልማት ይልቅ ቁሳቁስ እንመርጣለን። እግዚአብሔር እንደወደደ እንዲሸልመን ለእርሱ ብንተውለት ይሻለናል።
ሉቃስ አንድ ዓይነ ስውር እንዴት ዓይኑ እንደበራለት ይተርክልናል። ይህም እያንዳንዳችን እንዴት የውስጥ ዓይናችን በርቶ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በመገለጥ እንደምናገኝ የሚያመለክት ምሳሌ ነው።
ሉቃስ 18፡35 ወደ ኢያሪኮም በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
36 ሕዝብም ሲያልፍ ሰምቶ፦ ይህ ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀ።
37 እርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል ብለው አወሩለት።
38 እርሱም፦ የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ጮኸ።
39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።
የዳዊት ልጅ የሚለው መጠሪያ ኢየሱስ በሺ ዓመት መንግሥት ውስት ሲነግስ የሚታወቅበት ማዕረጉ ነው። ስለዚህ ዓይነ ስውሩ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ አረዳዱ ተሳስቷል፤ ስለዚህ ኢየሱስ ሊረዳው አልቻለም። ሰውየው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነ ነገር በማወቁ ኢየሱስ አልተገረመም። ሰውየው መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሳተ መንገድ በመረዳቱ ምክንያት ኢየሱስ ለሰውየው ጩኸት ጆሮ ሊሰጥ አልቻለም።
ሉቃስ 18፡40 ኢየሱስም ቆሞ ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። በቀረበም ጊዜ፦ ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? ብሎ ጠየቀው።
41 እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አይ ዘንድ ነው አለው።
ከዚያም ኢየሱስን “ጌታ” ብሎ ጠራው፤ ይህም ትክክል ነበር። ስለዚህ አሁን ኢየሱስ ሰውየውን ሊረዳው ችሏል።
ሉቃስ 18፡42 ኢየሱስም፦ እይ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።
43 በዚያን ጊዜም አየ፥ እግዚአብሔንም እያከበረ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
መንፈሳዊ ዓይን ያስፈልገናል -- እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን የማስተዋል ችሎታ ነው።
የዚህ ቃል ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን አጥርተን ማየት እንደሚያስፈልገንና ብዥ እንዳይልብን ነው። ዘፍጥረት ምዕራፍ 1ን ስታነብ የቢግ ባንግ ቲዎሪ የሚታይህ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚናገረው እውነት ታውረሃል ማለት ነው።
ቢግ ባንግ ቲዎሪ ፍጥረት የጀመረው በአንድ ታላቅ የብርሃን ብልጭታ እና ፍንዳታ አማካኝነት ነው ይላል። ይህ ዝም ብሎ ጭፍን ግምት ነው። የትኛውም ፍንዳታ ምንም ነገር ፈጥሮ አያውቅም።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን ፍጥረት በብርሃን ብልጭታ አይደለም የሚጀምረው።
ዘፍጥረት የሚጀምረው እግዚአብሔር መጀመሪያ ሰማይን እና ምድርን ሲፈጥር ነው። ሰማይንና ምድርን ሲፈጥር ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀ አልተጠቀሰም፤ ምክንያቱም ጊዜ መቆጠር ባልተጀመረበት በዘላለም ክልል ውስጥ ሆኖ ነበር እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራው። ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ እና ከዋክብት በመጀመሪያ ተፈጠሩ። ምድር በውሃ ተሸፍና ነበር፤ ይህም ውሃ ተነነና ጥቅጥቅ ያለ የደመና ሽፋን ፈጠረ። ከዚህ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ስር በጥልቅ ውሆች ፊት ላይ ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። ፀሃይዋ ጥቅጥቅ ካለው ደመና በላይ ነበረች።
የፀሃይዋ ብርሃን ምድር ላይ እንዳይደርስ ያደረጉት ደመናዎቹ ነበሩ። ከዚያም እግዚአብሔረ ሥራውን ቀጠለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “ብርሃን ይሁን”። እግዚአብሔር የተናገረው ቃል በምድር ዙርያ የነበረውን ጥቅጥቅ ደመና በታተነው፤ ስለዚህ የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር ፊት ሊደርስ ቻለ። ምድርም የፀሃይን የተዋበ ብርሃን ለመጀመሪያ ጊዜ አየች። ይህም የመጀመሪያው ቀን ማለትም እሁድ ሆነ፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር የሚሰራው ሥራ ከጊዜ ጋር አብሮ መሄድ ጀመረ።
ሰው ማለት አንድ ጭብጥ አፈር ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚሰራው ከምድር ጋር በሰራበት መንገድ ነው።
በመጀመሪያ እኛ በእናታቸን ማህጸን ውስጥ በውሃ እንከበባለን። ነገር ግን በነፍሳችን ዙርያ የአለማመን ጥቅጥቅ ደመና ከቦናል፤ ለዚህ ነው በሐጥያት የተወለድነው። ከዚያ ግን በሕይወታችን ውስጥ አንድ ቀን እግዚአብሔረ ተናገረ፤ ሲናገርም እኛ ሰምነት ካመንን እና ንሰሃ ከገባን በነፍሳችን ዙርያ ያለው አለማመን ይበተንና ለመጀመሪያ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃ ብርሃን ወደ ነፍሳችን ይደርሳል። ከዚያ በኋላ ነው ክብር በሞላው በእግዚአብሔር ልጅ ብርሃን ሐሴት ማድረግ እና እንዴት ያለ ድንቅ አዳኝ መሆኑን ማየት የምንችለው። ነገር ግን ከመወለዳችን ጀምሮ እርሱ በአዳኝነቱ እንደነበረ ነው። ነገር ግን እኛ እውነታው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠልን ንሰሃ የገባን ጊዜ ነው።
ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ ሆነን የምንኖርበት አዲሱ ሕይወታችን በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ውስጥ ስንመላለስ ተጀመረ።
የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ማየት መቻላችን ልክ እንደ ዓይነ ስውሩ ሰው በክርስቶስ ፊት ለመቆማችን ትልቅ ማረጋገጫ ነው፤ የማያምኑ ሰዎች ከነበርንበት አማኝ ወደ መሆን ሊለውጠን የሚችለውም ክርስቶስ ብቻ ነው።