ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 17
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ተመለከተች። አንዱ ይወሰዳል አንዱ ይቀራል። ሁላችንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፤ ስለዚህ የበደሉዋችሁን ይቅር ለማለት ዝግጁ ሁኑ።
First published on the 14th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022ሉቃስ 17፡1 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤
እኛ ሰዎች በድርጊታችንም በእምነታችንም እንሳሳታለን። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን ትክክል እንደሆንን ይሰማናል፤ እርማት ለመቀበልም ዝግጁ አይደለንም። በራሳችን እውቀትና ማንነት ትምክህት ባናበዛ ኖሮ የምናምነው ምን እንደሆነ በጥንቃቄ እንመረምር ነበር፤ ግን አብዛኞቻችን እምነታችንን አንመረምርም። የቆዩ ሃሳቦቻችንን የሙጥኝ ብለን እንይዛለን እንጂ። የቤተክርስቲያናችን መሪዎች የሚሉንን አምነን ተመችቶን መኖር ለምደናል። ከዚህም የተነሳ ለራሳችን በራሳችን አእምሮ ማሰብን አልተለማመድንም።
ስለዚህ በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ እውቀት ይዘን እንኖራለን፤ የሳትን ጊዜ እግዚአብሔር ካልረዳን በስተቀር አደጋ ውስጥ ነን፤ ምክንያቱም በስሕተታችን ውስጥ ሆነን ትክክለኞች እንደሆንን እርግጠኝነት ስለሚሰማን እርማት መቀበል አንችልም። ትዕቢት ማለት ልንሳሳት አንችልም ብሎ ማመን ነው፤ ከትዕቢትም የተነሳ ከእኛ ቤተክርስቲያን ውጭ ሊያስተካክለን የሚችል ሰው የለም ብሎ ማሰብ ነው። በዚህ ዘመን 30,000 የሚያህሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ ግን ሁላቸውም እኛ ነን ትክክለኛ ብለው ያስባሉ። ከዚህም የተነሳ ብዙ ክርስቲያኖች ይታለላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ባለማወቃችንና ስለ ስህተታችን አንድ ቀን ከባድ ዋጋ እንከፍላለን። እስከዚያ ድረስ ግን ከእኛ ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ ሰው ሊያስተካክለን ሲሞክር እምቢ እንላለን። መንግሥታት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥትን እንዲቃወሙ ብለው ገንዘብ ይከፍላሉ፤ ቤተክርስቲያኖች ግን ይህን ለማድረግ የሚበቃ ማስተዋል የላቸውም። ለዚህ ነው ዓመታት እያለፉ እንኳ ክርስቲያኖች በእውቀታቸው ብዙም የማይጨምሩት።
ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ውስጥ የአሥር ዓመት ዋጋ ያለው ትምሕርትና እውቀት እንኳ የላቸውም። ያላቸው እውቀት የአንድ ዓመት ትምሕርት ለአሥር ዓመታት ተደጋግሞ ነው። በትንሽዬ የእውቀት ኩሬ ውስጥ እንዳለ እንቁራሪት በጣም ትንሽ የእውቀት ኩሬ ነው ያለን። ኩሬው ትንሽ ከሆነ በዚያ ትንሽ ኩሬ ውስጥ ትልቅ እንደሆነ እንደሚመስለው እንቁራሪት ነን።
ሉቃስ 17፡2 ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
የልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖች ቁጥር መብዛት የሚያሳየን ስሕተትም በቤተክርስቲያን ውስጥ የዛኑ ያህል መብዛቱን ነው። 30,000ዎቹ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እምነታቸውም የተለያየ ነው። ሰባኪዎች ያለምንም ፍርሃት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ የመጨረሻው ዘመን ልጆች ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሐዋርያዊ አባቶች ስሕተት ሰርተዋል የሚል ትምሕርት ተምረዋል። በሌላ አነጋገር የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ከጻፉት ሐዋርያት የተሻለ የምናውቅ መስሎናል ማለት ነው።
ከዚህም ሌላ ደግሞ የኤቮልዩሽን ወይም ዝግመተ ለውጥ ትምሕርት እውነት ነው፤ እኛም የመጣነው ከእንስሳት ነው ብለን ለልጆቻችን እናስተምራለን። ይህም በራሱ አምሳል በሰራን በእግዚአብሔር ላይ ከባድ ስድብ ነው። ሳይንቲስቶች የሰው እና የዝንጀሮን ዘር የሚያገናኘውን ነገር ለማግኘት ከ160 ዓመታት በላይ ሲፈልጉ ቆይተዋል። በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ቢጣሉም እንኳ ሁላቸውም የሚስማሙበት አንድ ነገር አለ፤ እርሱም፡- የጠፋው አገናኝ ነገር እስካሁንም እንደጠፋ ነው። አንድ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ንድፈ ሃሳብ ደግሞ ባልተገኘ ባልተጨበጠ ነገር ላይ ሊመሰረት አይችልም። ስለዚህ ኤቮልዩሽን ውሸት ነው።
ኤቮልዩሽን እንደሚለው ዝንጀሮ እራሱን ሰው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰው ራሱን “ዝንጀሮ” አደረገ ነው የሚለው። ማን ትክክል እንደሆነ እናንተ ወስኑ።
የዘፍጥረት መጽሐፍ ሳይንሳዊ እውቀት ከመዳበሩ በፊት በመሃይምነት ዘመን ስለ ቢግ ባንግ ያላወቁ ኋላ ቀር ሰዎች ስለ ፍጥረት አጀማመር ለማብራራት ያደረጉት ሙከራ ብለን ልጆቻችንን እናስተምራለን። ነገር ግን የቢግ ባንግን ንድፈ ሃሳብ ያፈለቁ እንደ አላን ጉት እን የኖቤል ሽልማት አሸናፊው እስቲቨን ዋይንበርግ የመሰሉ ታላላቅ ሳይንቲስቶች የራሳቸውን ንድፈ ሃሳብ ትተውታል። ቢግ ባንግ፣ ዳርክ ማተር እና ዳርክ ኤነርጂ ይገኛሉ ብሎ አልጠበቀም ነበር፤ አሁን ተገኝተዋል ግን ምን እንደሆኑ ሳይንቲስቶች አንዳች አያውቁም።
የዓለማችን 96 በመቶው ዳርክ ማተር እና ዳርክ ኤነርጂ ነው። ስለዚህ ከዓለማችን እጅግ ብዙውን ክፍል ምን እንደሆነ ሳይንቲስቶች መግለጽ አይችሉም። ሳይንቲስቶች እናውቃለን ብለው የሚያስቡትን ያህል አያውቁም፤ ምክንያቱም ከሳይንቲስቶች መካከል ብዙ ያውቃሉ የተባሉት ስለ ዓለማችን አመጣጥ ፈተና ቢፈተኑ አራት ከመቶ ብቻ ነው መመለስ የሚችሉት። 4 አመቶ ደግሞ ማለፊያ ማርክ አጠገብ እንኳ አይደርስም። ስለ አንድ የትምሕርት አይነት 4 በመቶ ብቻ የሚያውቅ ሰው ደግሞ አውቃለው ብሎ አፉን ባይከፍት ይሻላል።
አንድ ቀን ስለ ውሸተኛው ሳይንሳዊ እውቀታችን ከባድ ዋጋ መክፈላችን አይቀርም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡20 ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤
በዘመን መጨረሻ ያለነው ክርስቲያኖች የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትን ወደ ጻፉት ሐዋርያዊ አባቶች እምነት መመለስ ያለብን መንፈሳዊ ልጆች ነን። ዘንድ ዘር ከተዘራ በኋላ ተክል ይበቅልና በተለያዩ ደረጃዎች ያድጋል፤ ከዚያ በኋላ ግን በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የተዘራውን አይነት ዘር ያፈራል። የዚያን ጊዜ የመከር ወቅት ይመጣል። ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ስትመለስ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል።
አንድ ሰው ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት የሚነቅፉ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እውነትን ወደ ቤተክርስቲያን ሊመልስ የጀመረውን ሥራ እየተቃወሙ ነው። መመለስ ያቃታቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ምንም አይጠቅምም በማለት አለማወቃቸውን ለመሸፋገን የሚሞክሩ ክርስቲያኖች ሌሎች ሰዎች በእውቀታቸው ወደ ፊት እንዳይገሰግሱ እንቅፋት ይሆናሉ።
ሁላችንም ጥያቄዎች መጠየቅ እና መልስ መፈለግ አለብን። አለዚያ መንፈሳዊ ልጆች አይደለንም።
ሉቃስ 17፡3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፦ ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።
አንድ ክርስቲያን ቢሳሳት ገስጸው፤ ግን ንሰሃ ሲገባ ደግሞ ይቅር በለው።
ሁላችንም የተሳሳተ እምነት አለን፤ ደግሞም ትክክል ያልሆኑ ነገሮች እናደርጋለን። ሁላችንም ደግሞ ንሰሃ ለመግባት መቅናት አለብን።
ሁላችንም መማር፤ የተማርነውን ስሕተት ከአእምሮዋችን ማስወጣትና እንደገና መማር አለብን። ሁላችንም እናውቃለን ብለን ከምናስበው በጣም ያነሰ ነው የምናውቀው፤ ምክንያቱም በቤተክርስቲያኖች ልማዳዊ ትምሕርት በቀላሉ ተታልለናል። እንደዚያ ባይሆን ማቴዎስ ምዕራፍ ሁለት በግልጽ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ብሎ እየተናገረ ስለምን ወደ በረት ገቡ ብለን እናምናለን። ደግሞም አራስ አይደለም ያዩት የሁለት ዓመት ሕጻን እንጂ። ሁላችንም ጥርት ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ እናገኝ ዘንድ የዓይን ኩል እንዲሰጠን መጸለይ ያስፈልገናል።
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ሉቃስ 17፡4 በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።
ሁላችንም እንደምንሳሳትና ለመመለስ ንሰሃ ለመግባት መቅናት እንዳለብን ነው ሉቃስ እየነገረን ያለው። ስለዚህ ብዙ ስሕተት የሰሩ ሰዎች ንሰሃ ቢገቡ ስሕተቶቻቸውን አትቁጠሩባቸው። በዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመናችን ውስጥ ሁላችንም ከምንገምተው በላይ በጣም ብዙ ስሕተቶች አሉብን፤ ከምናስበውም በላይ መሃይም ነን። በቀን ሰባት ጊዜ ማለት በሰባት ቁጥር ውስጥ ካለው ሚስጥር ጋር የተያያዘ ነው፤ እርሱም የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ስሕተቶች ሁሉ ተሰብስበው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ተለቀዋል ማለት ነው። ከዘመናት ሁሉ አሳሳች በሆነ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነው። ነገር ግን ሞኝነታችን ምንም አያስፈልገንም ብለን ስለምናምን እርማት አያስፈልገንም ብለን ማሰባችን ነው።
ሉቃስ 17፡5 ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት።
6 ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።
እምነት ያስፈልገናል። እምነታችን ማደግ አለበት። እምነት የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት ነው። እምነት የማይቻል ነገርን ማድረግ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሆኑን መማር አለብን፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውንም ማመን አለብን። ይህ ብቻ ነው የእምነት መሰረት። እምነታችንን ለማሳደግ መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ እያወቅን መሄድ አለብን።
በዚህ ክፍል ሉቃስ የሚያሳየን ከኢየሱስ ጋር ስንነጻጸር ከምንም የማንቆጠር መሆናችንን ነው።
ኢየሱስ እንደተናገረው በገንዘብ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ ሥራውን ይሰራል፤ ነገር ግን ጌታዬ ያመሰግነኛል፤ ሽርጉድ ይልልኛል ብሎ መጠበቅ አይችልም።
ሉቃስ 17፡7 ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?
8 የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን?
9 ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?
10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
ይህ በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ቁልፍ ጥቅስ ነው።
ሰው እንደመሆናችን እግዚአብሔርን ስናገለግል ከእግዚአብሔር አንዳችም ምስጋና መጠበቅ የለብንም።
እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ መስራትና መንገዳችንን መምራት ይፈልጋል። ስለዚህ አንዳች መልካም ነገር ብንሰራ እግዚአብሔር ነው በእኛ ውስጥ ሆኖ መልካም ሥራ የሰራው፤ ስለዚህ ምንም አይነት ምስጋና አይገባንም። ምሳሌ እንጠቀም ከተባለ፤ እኛ እንደ መኪና ስንሆን እግዚአብሔር ደግሞ እንደ አሽከርካሪ ነው።
በመኪና አንድ ቦታ ሄዳችሁ ከመኪናው ስትወርዱ መኪናውን አመስግናችሁታል?
በእግዚአብሔር መስፈሪያ ስንሰፈር ሚዛን እንኳ አንደፋም። ለእግዚአብሔር እንቅፋት እንጂ ረዳት ልንሆንለት አንችልም።
ለእግዚአብሔር ምንም እንደማንጠቅም አስቡ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን በመታገሱ የሚያገኘው አንዳች ትርፍ የለም፤ ይልቁንም በእኛ የተነሳ ብዙ እየከሰረ ነው። በትክክል ከምንሰራው ይልቅ በመንግሥት ውስጥ የምናደርሰው ጥፋት ይበልጣል።
ይህ የብዙዎችን ትዕቢት ያስተነፍሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
የተወሰኑ መልካም ነገሮችን ለእግዚአብሔር አድርጌያለው ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። አድርጋችሁም ይሆናል። በእግዚአብሔር እይታ ግን ከሰራችሁለት መልካም ነገር የራሳችሁን ፍላጎት በማሳደድና የተሳሳተ እምነታችሁን በማሰራጨት ያበላሻችሁበት ይበልጣል። ይህ በሙሉ ሲደመር ውጤቱ ከምናደርገው መልካም ነገር የምንሰራው ስሕተት እንደሚበልጥ ያሳያል። ለዚህ ነው ምንም ትርፍ የማናመጣው። ለዚህ ነው የሚያቀናን የሚያስተካክለን ነብይ የሚያስፈልገን።
አሥር ለምጻሞች ወደ ኢየሱስ ቀረቡ፤ እርሱም ፈወሳቸው። ነገር ግን አንዱ ብቻ ነው ሊያመሰግን ተመልሶ የመጣው።
ሉቃስ ሰዎች በተፈጥሮዋችን ምስጋና ቢስ መሆናችንን በአጽንኦት ያሳየናል። እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር በአጋጣሚ እንደሆነልን ይመስል ዝም ብለን እናልፋለን።
ብዙ እናማርራለን ግን ብዙም አናመሰግንም።
ሉቃስ 17፡15 እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥
16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።
ወደ አሕዛብ የሚያዘነብለው ሉቃስ ኢየሱስን ሊያመሰግን ተመልሶ የመጣው ሰው አይሁዳዊ አለመሆኑን በማሳየት አይሁዶችን ጠንከር አድርጎ ይገስጻል።
ሉቃስ 17፡17 ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ?
18 ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም አለ።
የተወደዱት አይሁዶች የተጠበቀባቸውን እንዳላደረጉ ሉቃስ ያሳያል። ነገር ግን አይሁዶች የሚንቁት እንግዳ የሆነ ሰው ብቻ ነው ኢየሱስን ያስደሰተው።
19 እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።
ሉቃስ 17፡20 ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤
የእግዚአብሔር መንግሥት መኖሯን የሚያመለክት ውጫዊና የሚታይ አንዳችም ምልክት የለም። ስለዚህ በዓይን የሚታይ ሃብታቸውንና የተድላ ኑሮዋቸውን የእግዚአብሔር በረከት ማስረጃ አድርገው የሚቆጥሩ ክርስቲያኖች ራሳቸውን እያታለሉ ነው። በምድራችን አንደኛ ሃብታም የሆኑ ሰዎች ክርስቲያኖች አይደሉም።
ከሁሉም የሚበልጥ ትልቅ ቤተክርስቲያን ሕንጻ መስራት ለዓይን ያስደንቃል። ነገር ግን በዓይን የሚታይ ስለሆነ ቤተክርስቲያኑ ትክክለኛ ወይም የእግዚአብሔር መንግሥት አካል ስለመሆኑ ማረጋገጫ መሆን አይችልም።
ሉቃስ 17፡21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።
የእግዚአብሔር መንግሥት በዓይን አትታይም። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንግስት ፖለቲካዊ ስኬት ወይም ሃብት ማከማቸት አይደለችም፤ ከፍ ያለ ሥልጣን መያዝም አይደለችም።
የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት እግዚአብሔር በሰው ልብ ውስጥ ሲኖርና ለእኔነታችን እንድንሞት ሲያደርገን ነው።
እኛ በራሳችን ሕይወት ላይ ባለን ሥልጣን እየቀነስን ስንሄድ ብቻ ነው እርሱ በእኛ ሕይወት ላይ ያለው ሥልጣን እየጨመረ የሚሄደው።
እኛ እየደከምን ስንሄድ እርሱ እየበረታ ይሄዳል። የእግዚአብሔረ መንግሥት ማለት እግዚአብሔር ፈቃዳችንን በራሱ ፈቃድ እንዲተካልን የምናደርገው ውስጣዊ ትግል ነው። እኛ እየጠፋን ስንሄድ እርሱ እየጎላ ይሄዳል።
የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት በግልጽ አነጋገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እያመኑ መኖር ነው።
በምድር ላይ የትኛውም ልዩ ቦታ ላይ መሆን አያስፈልጋችሁም። የእግዚአብሔር መንግሥት በአንድ የተመረጠ አካባቢ አትገለጥም። ወደ አንድ ልዩ ቦታ መሄድ አያስፈልጋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስን ማመን ብቻ ይበቃችኋል። ሥፍራችሁን የምታገኙት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው። እግዚአብሔርን ከራሳችሁ ውጭ የሆነ ቦታ ፍለጋ አትሂዱ። ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት የሚከፈተው በውስጣችሁ ነው። አስተሳሰባችሁ መለወጥ አለበት። ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ሕብረት በአእምሮዋችሁ ውስጥ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ አእምሮዋችሁም ለማሰብ የአንጎላችሁን ሴሎች የሚጠቀም መንፈስ ነው።
ሉቃስ 17፡22 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ልታዩ የምትመኙበት ወራት ይመጣል አታዩትምም።
“የሰው ልጅ” የሚለው አነጋገር ነብይን ያመለክታል። የመጨረሻውን ዘመን ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያ ዘመን ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ የሚመልስ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ነብይ ያስፈልጋል። ደቀመዛሙርቱም ይህንን ክስተት የማየት እድል አይኖራቸውም ምክንያቱም የሚሆነው እነርሱ ከኖሩበት ዘመን ሁለት ሺ ዓመታት ያህል አልፎ ነው። ነገር ግን እነርሱ የአዲስ ኪዳንን መሰረት ጥለው ያልፋሉ፤ ኋላ የሚመጣውም ነብይ እነርሱ ወደ መሰረቱት መሰረት ነው የሚመልሰን።
ሉቃስ 17፡23 እነርሱም፦ እነሆ በዚህ፥ ወይም፦ እነሆ በዚያ ይሉአችኋል፤ አትሂዱ አትከተሉአቸውም።
ነገር ግን እንድትከተሉዋቸው ወይን የሆነ ሰውን እንድትከተሉ ብለው የሚሯሯጡ አማኞችን ተከትላችሁ አትሂዱ።
እግዚአብሔር በአሪዞና በረሃ ውስጥ እንደ ታላቅ ደመና ሆኖ አይመጣም። ስለዚህ አሪዞና ውስጥ መገኘት አያስፈልጋችሁም።
በመጨረሻው ዘመን የሚነሳው ነብይ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጨመር አይችልም - የእርሱ ድርሻ አስቀድሞ የተጻፈውን ቃል መግለጥ ብቻ ነው።
ስለዚህ የነብዩን ንግግሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደሚበልጡ ወይም እኩል እንደሚሆኑ አድርጋችሁ አትቁጠሩ። በመጽሐፍ ቅዱስ ወደ ተጻፈው ቃል ሊያመለክታችሁ ብቻ ነው የሚችለው። ስለዚህ ሰውን አትከተሉ። ነብዩ የሚያሳያችሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ብቻ ተከተሉ። አንድ ሰው የሚናገረውን ቃል ትክክለኛ መሆኑን በተናገረበት ርዕስ ላይ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መርምራችሁ ካረጋገጣችሁ በኋላ ብቻ ነው ማመን ያለባችሁ።
በመጨረሻው ዘመን ዓለም ሁሉ በኢንተርኔት እየተገናኘች ናት። በኢንተርኔት ላይ ከሚሰራጩት ስሕተቶች ሁሉ መካከል ሰዎች እውነትን ሊያገኙ የሚችሉባቸው አንዳንድ ዌብ ሳይቶች አሉ። ስለዚህ ግለሰቦች የትም ቦታ ሆነው እውነትን መማር ይችላሉ። ለጌታ ምጻት እንድንዘጋጅ የሚያስፈልገንን መረጃ በሙሉ ሞባይሎች እና ኮምፒዩተሮች ዳውንሎድ ማድረግ ወይም ማውረድ ይችላሉ። የዚህን ዘመን ታዋቂ ነገር ግን የተሳሳተ ትምሕርት የሚያስተምሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተደገፉ ትምሕርቶችን የሚያጋልጡ ዌብ ሳይቶች አሉ።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ የሚያስፈልጋችሁን ከኢንተርኔት ማግኘት ትችላላችሁ።
ትክክለኛ የእውነት ትምሕርት የሚገኝባቸው ዌብ ሳይቶች አሉ።
ደግሞም ጥያቄዎቻችሁን የምትልኩባቸውና መልሶችን የምታገኙባቸው ዌብ ሳይቶችም አሉ።
ስሕተት የሚጋለጥባቸው ዌብ ሳይቶች አሉ።
እንደ ግለሰብ በግላችሁ የምትፈልጉትን መረጃ ሁሉ ከኢንተርኔት ማግኘት ትችላላችሁ።
በምሕዋር ውስጥ ካሉት ሳተላይቶች የሚዘንብ የኤሌክትሪክ “ዝናብ” አለ። በዚያ ውስጥ የቀደመውን ዝናብ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ማግኘት ትችላላችሁ፤ እርሱም ኢየሱስ ሙሽራውን ለሚወስድበት ጊዜ ማለትም ለኋለኛው ወይም ለመከር ዝናብ እንድትዘጋጁ ይረዳችኋል፤ ሙሽራይቱም መጽሐፍ ቅዱስን የምታምነዋ ቤተክርስቲያን ናት።
ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር አያስፈልጋችሁም።
እውነትን እኔ ብቻ ይዣለሁ ማለት የሚችል ግለሰብ ወይም ቤተክርስቲያን የለም።
እንደ ማንኛውም ሌላ ሰው ወይም ቡድን በሞባይላችሁ ወይም በኮምፒዩተራችሁ የፈለጋችሁትን ያህል እውነተኛ መረጃ ዳውንሎድ ማድረግ ትችላላችሁ። ነገር ግን እውነትን ተግታችሁ መፈለግ ይኖርባችኋል፤ እግዚአብሔርም ይመራችኋል።
ሉቃስ 17፡24 መብረቅ በርቆ ከሰማይ በታች ካለ ከአንድ አገር ከሰማይ በታች ወዳለው ወደ ሌላ አገር እንደሚያበራ፥ የሰው ልጅ በቀኑ እንዲህ ይሆናል።
መብረቅ ተንቀሳቃሽ ብርሃን ነው።
ቃየን ወደ ምሥራቅ ሄደ በዚያም አጋንንታዊ አሰራር (የምሥራቅ ነገሥታት) ተመሰረተ። አሁን ደግሞ እነዚህ አጋንንታዊ ሰራዊት ሊያስቱን ወደ ምዕራቡ ዓለም እየዘመቱ ናቸው።
ዘፍጥረት 4፡16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፤ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ።
ራዕይ 16፡12 ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።
13 ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤
14 ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።
ኤፍራጠስ የተስፋይቱ ምድር ድንበር ነው። የወንዙ መድረቅ የሚያመለክተው የቃሉ ወንዝ በደረቀ ጊዜ ለአጋንንታዊ አሰራር መንገድ እንደሚከፈት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ትተን ስንሄድ ዲያብሎስ ይቆጣጠረናል ማለት ነው።
ዘንዶው ዲያብሎስ ነው። አውሬው ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣንን በአንድነት የያዘው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነው። ሃሰተኛው ነብይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የሃሰተኛ ሃይማኖት ነብይ ነው፤ እርሱም የካቶሊክ ፖፕ ነው። እነዚህ ሦስቱ ተባብረው ነው የሥላሴ ትምሕርትን የፈጠሩት። ዛሬ ቤተክርስቲያኖችን ወደ አንድነት የማምጣትን ትልቅ መንፈሳዊ ተዓምር እየሰራ ያለው ዋነኛ አስተምሕሮ ሥላሴ ነው። ከሥላሴ ትምሕርት በቀር ቤተክርስቲያኖች የሚስማሙበት ሌላ ብዙም ነገር የለም። ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በሮም መሪነት ወደ አንድነት ሲመጡ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ። የዳኑ ግን ሳይነጠቁ የሚቀሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይሞታሉ። በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ የዳኑት ክርስቲያኖች ሁሉ ከጠፉ በኋላ ክርስቶስ ለአርማጌዶን ጦርነት ይመጣል።
በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን በኢየሱስ እና በሐዋርያት አማካኝነት በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ተገልጧል።
ከዚህ የቃል ብርሃን አብዛኛው በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍቷል።
ከጨለማው ዘመን በኋላ ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር በጸጋ እና በእምነት ብቻ ስለመዳን የሚናገረውን የየእውነት ብርሃን መልሶ አምጥቷል። ይህም በእምነት መጽደቅ ይባላል። ከዚያም የወንጌል ብርሃን ወደ ምዕራብ ሄዶ ኢንግላንድ ሲደርስ ጆን ዌስሊ ለክርስቲያኖች የቅድስና እና የወንጌል ሰባኪነትን እውነቶች ገለጠላቸው። ይህም የቅድስና ትምሕርት ይባላል። ከዚያም እንደገና ወደ ምዕራብ በመሄድ የወንጌል ብርሃን ወደ አሜሪካ ተሻገረ፤ በዚያም በፔንቲኮስታል መነቃቃት አማካኝነት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ስጦታዎች ገለጠ። ከዚያም አሜሪካ ውስጥ ይህ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ማለትም ቃሉን በሚገልጥ ትንቢታዊ የትምሕርት አገልግሎት ወደ ፍጻሜ ይመጣል ምክንያቱም አሜሪካ የምዕራብ ጥግ ናት። የዚህም የተገለጠ ቃል ብርሃን ልክ እንደመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ብርሃን ይሆናል። “የሰው ልጅ” የሚለው ስያሜ ክርስቶስ በትንቢታዊ አገልግሎት በመጠቀም የሚገለጥበትን አገልግሎት ነው የሚያመለክተው፤ ይህም አገልግሎ የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያ ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት ይመልሳታል።
እግዚአብሔርን በመንፈስም በመጽሐፍ ቅዱስ እውነትም እውነትም ማምለክን መማር የግድ ያስፈልገናል።
ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
ሉቃስ 17፡25 አስቀድሞ ግን ብዙ መከራ እንዲቀበል ከዚህም ትውልድ እንዲጣል ይገባዋል።
ነገር ግን እውነት ያለ መገፋትና ያለ መከራ ልትጸና አትችልም። አይሁዶች እውነትን ገፍተዋል፤ ኢየሱስንም ገድለዋል። በቀራንዮ ለኢየሱስ ብሎ የተሟገተ አንድም ሰው አልነበረም፤ ያም የመጀመሪያ ምጻቱ ነበረ።
ስለዚህ የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያንም የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ብትገፋው አያስደንቅም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ብቻ ነው ወደ መጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት ልንመለስ የምንችለው።
ሉቃስ 17፡26 በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።
ኖኅ በሚሰብክበት ጊዜ ስለ ስብከቱ የቆመለት ሰው አልነበረም። ሁሉም ሰው ስብከቱ አልቀበል አለው። በምድር ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ስምንት ሰዎች ብቻ ወደ መርከቢቱ ገብተው ዳኑ። ይህም ስለ መጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን የሚያሳይ አስፈሪ ተምሳሌት ነው። በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው ከጥፋት የሚያመልጡት።
ስለዚህ ከኖኅ ዘመን ጋር ሲነጻጸር የመጨረሻው ዘመን ትንቢታዊ ወይም “የሰው ልጅ” አገልግሎት ፍጻሜው ላይ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምን ሰው ላይገኝ ይችላል። በምድሪቱ ላይ የሚበዙት በሰው ንግግር ላይ የተመሰረቱ ሰው ሰራሽ ትምሕርቶችና የቤተክርስቲያን ወጎች ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የሚያምን ማነው? በጣም ጥቂቶች።
ከዚያም ታላቁ መከራ እንደ ደራሽ ውሃ ይመጣል። በዚህ ጊዜ ግን ውሃ ሳይሆን እሳት ነው የሚመጣው። የኑክሊየር ቦምብ በብዛት ተሰርቶ አልቆ በመጠባበቅ ላይ ነው።
ሉቃስ 17፡28 እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤
29 ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ።
አሁንም በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ካመለጡበት ዘመን ጋር አስፈሪ የሆነ ንጽጽር እናገኛለን። ሦስት ሰዎች ብቻ ከሰዶም ወጥተው ሄዱ። እነርሱም ሎጥና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ናቸው። ስለዚህ ከዚያ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ለሚመጣው ለታላቁ መከራ ምሳሌ ከሆነው እሳት የዳነ አልነበረም።
እሳት ከላይ ከሰማይ ወረደ። ወደ ፊት በሚመጣው መከራ አውሮፕላኖች ከአየሩ ላይ ወደ ምድር የኑክሊያር ቦምብ ይጥላሉ። አሕጉሮችን አቋርጠው የሚሄዱ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ብዙ ኑክልየር ቦምብ ከላይ ያዘንባሉ። እነዚህም በፍንዳታቸውና በሚፈጥሩት የእሳት ሞገድ እጅግ ሰፊ ቦታን መሸፈን እንዲችሉ ከመሬት ሦስት ወይም አምስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ሳሉ ይፈነዳሉ። ቀጥታ የእሳት ዝናብ ያዘንባሉ። ከቤተክርስቲያን መነጠቅ ወደ ኋላ የሚቀሩ የዳኑ ክርስቲያኖች በሙሉ በታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ።
ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
የዳኑ ክርስቲያኖች ማለትም እንቅልፍ የተኙት ቆነጃጅት ለአውሬው ምስል መስገድን እምቢ ይላሉ። ከዚያም ይገደላሉ።
ይህ በምእራፍ 13 ውስጥ የተጠቀሰው ሁለተኛው አውሬ ነው። የመጀመሪያው አውሬ (ኃይል) ዓለምን የተቆጣጠረው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነው። ከላይ በወንድ ጾታ የተጠቀሰው አካል ባለፈው ምዕተ ዓመት (በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን) ዓለምን በወታደራዊና በኢኮኖሚ ኃይል ሊገዛ የተነሳው የአሜሪካ ፖለቲካዊ አውሬ ወይም ኃይል ነው። የዚህ አሜሪካዊ አውሬ ኃይሉ በገንዘብ ራሱን ማጠናከሩ ነው። በዓለም ላይ ካሉ የሙሉ ጊዜ ያላቸው ክርስቲያኖች መካከል ዘጠና በመቶ የሚሆኑት አሜሪካ ውስጥ ናቸው።
የአሜሪካ ገንዘብ በዓለም ዙርያ ያሉ ቤተክርስቲያኖችን ይረዳል። ይህ ገንዘብ ነው ሐይማኖታዊ ተቋማት በሕይወት እንዲቆዩ ተግተው የሚሰሩ ሰዎችን የሚደግፋቸው።
በታላቁ መከራ ውስጥ ዓለምን የሚቆጣጠረው አውሬ የብዙ ዲኖሚኔሽኖች መፍለቂያ የሆነው የሮማ ካቶሊክ ነው። የአውሬው ምስል ማለት ፕሮቴስታንት እና ዲኖሚኔሽናል ያልሆኑት በፖለቲካ ውስጥ እና ገንዘብ በማካበት የሮምን ምሳሌነት የሚከተሉ ቤተክርስቲያኖች ናቸው። ገንዘብን ተከትሎ የሄደውን ይሁዳን አስታውሱ።
ቤተክርስቲያኖች ንሰሃ ስለገባን እና ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስለተቀበልን ከታላቁ መከራ እናመልጣለን ብለው በማሰባቸው በጣም ተሳስተዋል። በፍጹም እንደዚያ አይደለም። ንሰሃ መግባት ከሲኦል ነው የሚያድነን። ልባም ቆነጃጅትና እንቅልፋም ቆነጃጅት ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ንጹህ ሴቶች የሚወክሉት የዳኑ ክርስቲያኖችን ነው። ነገር ግን ሙሽራውን ኢየሱስን ሲመጣ የተቀበሉት ልባሞቹ ቆነጃጅት ብቻ ነበሩ። እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት ከሲኦል ድነዋል፤ ነገር ግን በታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ።
ምን ያህል ልባም ናችሁ?
ከእምነታችሁ ውስጥ ምን ያህሉን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በመጠቀም ትክክል መሆኑን ማሳየት ትችላላችሁ?
በጣም ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ገልጠው ማሳየት የሚችሉት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች ማብራራት የማይችሉት በጣም ብዙ ነገር አለ።
አዳም እና ሔዋን ተመሳሳይ ሐጥያት ነው የሰሩት። እግዚአብሔር ለአዳም እንዲህ አለ፡- “ይህን ስላደረግህ ቅጣትህ ይህ ነው …”።
ለሔዋን ግን ስለ ቅጣቷ ምንም ማብራሪያ አልሰጠም። “ይህን ስላደረግሽ” አላላትም። ለምንድነው ያላላት?
ሁለቱም የሰሩት ሐጥያት ተመሳሳይ ሆኖ የደረሰባቸው ቅጣት ግን ይለያያል። ለምን?
ሁሉንም ዛፎች እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ነው የፈጠራቸው፤ ደግሞ ሁሉም መልካም ናቸው ብሏል። ታዲያ አንድ ክፉ ዛፍ ኤደን ውስጥ ከየት ተገኘ?
ማቴዎስ የኢየሱስን የዘር ሃረግ ከዳዊት ጀምሮ እስከ ዮሴፍ ዘርዝሮ መዝግቧል። ሉቃስም የኢየሱስን የዘር ሃረግ ይዘረዝራል ግን የተለዩ ስሞችን ከመጠቀሙ በተጨማሪ በዮሴፍና በዳዊት መካከል ተጨማሪ 13 ትውልዶችን ጨምሮበታል - ለምን?
የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ሰባት ቤተክርስቲያኖች በከተሞቻቸው ስም ተጠቅሰዋል። ሥድስቱ በተለመደ ስማቸው ነው የተጠቀሱት። የጴርጋሞን ከተማ ግን ጴርጋሞስ ተብላ ነው የተጠቀሰችው ይህም የከተማይቱ ግሪክኛ ስሟ ነው [በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው]። ሌሎቹ ሥድስት ከተሞች የተለመዱ ስሞቻቸው ብቻ ሲኖሩዋቸው ይህችኛዋ ቤተክርስቲያን ብቻ ለምን የግሪክኛ ስም ኖራት?
የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ የማናውቀው ነገር እያለ ዝም ብለን ተቀምጠናል። ይህንን ለማስተካከል የመጨረሻ ዘመን ነብይ ያስፈልገናል።
በጣም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የለን መስሎን ከመታበያችን የተነሳ ማንም እንዲረዳን የሚያስፈልገን አይመስለንም።
ነገር ግን ትዕቢት ሲበዛ መሃይምነትን እያባባሰ ይሄዳል።
ሉቃስ 17፡30 የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።
የመጨረሻው ዘመን ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ሲገልጥ እርሱ የሚያስተምረውን ትምሕርት ትክክል መሆኑን ሄደው መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመርና ጥቅሶችን በማገናኘት ለማረጋገጥ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የሚሞክሩት። ይህንን የሚያደርጉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የዘመናችንን ስሕተቶችን እና ክፋቶችን ለማቃጠል ከሚመጣው እሳታዊ መከራ የሚያመልጡት።
የክርስትና ትልቁ ጠላቱ በዲኖሚኔሽን የተከፋፈለ “ቤተክርስቲያናዊነት” ነው። ሰዎች እንዲህ ማለት ይወዳሉ፡- “እኔ የዚህ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ፤ ቤተክርስቲያኔ የምትለኝን አምናለው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ነገር ከተናገረች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ትቼ ቤተክርስቲያኔ የነገረችኝን አምናለው፤ ሁሉም ቤተክርስቲያኖች እንደዚሁ ነው የሚያደርጉት።”
“የቤተክርስቲያናዊነት” አመለካከት ይህ ነው። ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ስሕተቶችን ለይተን ማየት እንዳንችል የሚያደርግ ጥልቅ የሆነ ስሜታዊ ተቃውሞ ነው። እንደዚህ አይነት ችግር መኖሩን መቀበል አንፈልግም። የለመድናቸውን ስሕተቶቻችንን አጥብቀን ስለያዝን አለማወቃችንን መገንዘብ አልቻልንም።
ሉቃስ 17፡31 በዚያም ቀን በሰገነት ያለ በቤቱ ያለውን ዕቃ ሊወስድ አይውረድ፥ እንዲሁም በእርሻ ያለ ወደ ኋላው አይመለስ።
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርቲያን በር ውጭ ቆሞ ያንኳኳል። መላዋ ቤተክርስቲያን ሳትሆን ግለሰቦች ብቻ በራቸውን ከፍተው እንዲያስገቡት ይጠይቃል። ሉቃስ ከዚህ ዘመን “ቤተክርስቲያናዊነት” ስለሚያመልጥ ግለሰብ ይናገራል። በቤቱ ሰገነት ላይ በመቆሙ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት ሌሎቹ ማየት ከሚችሉት የበለጠ አርቆ አሻግሮ ያያል። ወይም በእርሻ ውስጥ ያለ ሰው ማለትም በወንጌል ስራ ውስጥ የተሰማራ ሰውም ከሌሎች የበለጠ ማየት ይችላል። በድርጅት ውስጥ ያሉትን ስሕተቶች አይቶ አንድ ግለሰብ ሰው ሰራሽ ከሆኑት አስተሳሰቦችና አስተምሕሮዎች ማምለጥ አለበት።
እኛም እንደ ግለሰቦች ከቤተክርስቲያኖቻችን ስሜታዊ አመለካከቶችና ልማዳዊ አስተሳሰቦች ማምለጥ አለብን። የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሰዓት ላይ መገኘት እንችላለን ከፈለግን ነገር ግን ያስተማሩንን ሰው ሰራሽ ትምሕርት በሙሉ ወደ ኋላ እንጥለዋለን። ወደ ኋላችሁ ጣሉትና ቤተክርስቲያን ያስተማረቻችሁን ልማዳዊ ሃሳቦችና አመለካከቶች እርግፍ አድርጋችሁ ተዉ። ከአንድ ቤተክርስቲያን ፓስተር ጋር እድሜ ልካችሁን ተስማምታችሁ አትችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እውነትን መያዙን ካወቃችሁ በኋላ ከሰዎች ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል አድርጋችሁ አትቆጥሩም። አንድ ግለሰብን መከተል እየሰለቻችሁ ይሄዳል ምክንያቱም በዚያ መንገድ እምነታችሁ ትክክለኛው መሆኑን ማረጋጥ አትችሉም። ከዚያ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ቃል ብቻ በማመን እንድትኖሩ የሚነግራችሁን ሰው መተቸት ታቆማላችሁ።
በፓስተር ከሚገዛ አንድ ጉባኤ ወጥታችሁ በፓስተር ወደሚገዛ ሌላ ጉባኤ መሄድ ችግራችሁን አይፈታላችሁም። ምክንያቱም ይህ አንድ ስሕተት ትቶ ወደ ሌላ ስሕተት መግባት ብቻ ነው የሚሆነው። የቤተክርስቲያኖቻችን አደረጃጀትም ሆነ የሚሰጡን ትምሕርቶች በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን መርህ የሚከተሉ አይደሉም።
“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው። ስለዚህ የፓስተሩ አገልግሎት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሌሎች አገልግሎቶች ሁሉ የበላይ የነበረ አገልግሎት አይደለም ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፓስተር ማለት እረኛ ነው የሚል ቃል አንድም ጊዜ አልተጻፈም። ፓስተሮች የበጎች እረኛ ነን ይላሉ። ፓስተሮች የበጎች እረኛ ከሆኑ ከሌሎች አማኞች የተለዩና የሚበልጡ ፍጡራን ሆነዋል ማለት ነው። ሰው ከእንስሳት ሁላ እጅግ አብዝቶ ይበልጣል። ነገር ግን አንድ ሰውን ከሌሎች ሰዎች በላይ ከፍ አድርጎ የሚያይ ሥርዓት ኒቆላዊነት ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ኒቆላዊነትን ይጠላል።
ሉቃስ 17፡32 የሎጥን ሚስት አስቡአት።
የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ዞር ብላ ንብረቷን ተመለከተች። ኑሮዋን ሙሉ በሙሉ እንደ አዲስ መጀመር ስለፈራች ከቀደመ አስተሳሰቧ አልተላቀቀችም ነበር። ቀድሞ ወደነበረችበት መመለስ አማራት።
ቀድሞ የሰው አገዛዝና የሰው አመራር ደስ ይለን ነበር። ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ካልሆኑ እምነቶች ማምለጥ ከፈለግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ጸንተን መቆም አለብን። የቤተክርስቲያን መሪዎች ስሕተት ሲሰብኩ እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጸንተን መቆም አለብን፤ አለዚያ እንደ ሎጥ ሚስት መንፈሳዊ ሞት እንሞታለን። ሴት የምትወክለው ቤተክርስቲያንን ነው። ከተወሰኑ ስሕተቶች ልታመልጥ ሞከረች፤ ነገር ግን ይዛ ልትቆይ የምትፈልጋቸውን ስሕተቶች አስባ ወደ ኋላ ተመለከተች።
ሉቃስ 17፡33 ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል።
ሊጠቅሙህ የሚችሉ የተወሰኑ እውነቶችን በሚያስተምር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕብረት እያደረክ መቆየት ትችላለህ፤ ነገር ግን በየትኛውም የቤተክርስቲያን ቡድን ውስጥ ሙሉውን እውነት አታገኘውም። ጠለቅ ያለ እውነትን ለማግኘት ከቤተክርስቲያን መዋቅር ውጭ በራስህ መፈለግ አለብህ። ከሰባኪዎች ስሕተት እን ከመጀመሪያ እምነትህ ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እንዳትችል ካደረጉህ ቤተክርስቲያኖች ጋር ለመስማማት መሞከር በብርድ ወቅት እሳት ዳር እንደተቀመጠ ሰው ደስ እንዲልህና እንዲሞቅህ ሊያደርግህ ይችላል፤ ግን ሳታውቀው በታላቁ መከራ ውስጥ ወደሚጠብቅህ ሞት እየሄድክ ነህ።
ከእኛ ጋር አልተስማማህም ብለው ቢያወግዙህ ይሻልሃል። ቤተክርስቲያን የገፋቻቸው ናቸው ከታላቁ መከራ የሚያመልጡት።
ኢየሱስ በቤተክርስቲያን መነጠቅ ጊዜ የሚነጠቁት በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ በአጽንኦት ተናግሯል። የመነጠቅ ጊዜም ባላሰብንበት ቀን በድንገት ነው የሚሆነው። በንግግሩ ውስጥ በቀን ሦስት የተለያዩ ጊዜዎችን ጠቅሷል፡- እርነሱም የእንቅልፍ ሰዓት፣ ምግብ የሚዘጋጅበት ሰዓት፣ እና እርሻ ውስጥ ሥራ የሚሰራበት ሰዓት ናቸው።
በማንኛውም ጊዜ ከቀን ውስጥ ሦስት የተለያዩ ሰዓቶች ሲጠቀሱ ሦስት የተለዩ የዓለም ክፍሎችን ነው የሚያመለክቱት። በዚህ ምሳሌ መሰረት ግለሰቦች ብቻ ናቸው የሚሄዱት እንጂ ቡድኖች አይደሉም። ከሦስት የተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከእያንዳንዳቸው አንድ ግለሰብ ብቻ ይወሰዳል። ይህንን ስናስብ የሚወሰዱት ሰዎች በጣም ብዙ እንደማይሆኑ እናስተውላለን። ብዙ ሰዎች ሳይወሰዱ ስለሚቀሩ በጣም ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።
ሉቃስ 17፡34 እላችኋለሁ፥ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።
35 ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች ሁለተኛይቱም ትቀራለች።
36 ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።
37 መልሰውም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው? አሉት። እርሱም፦ ሥጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ አላቸው።
የጌታ አካላ መንፈሳዊ ምግባችን የሆነውን የተገለጠውን መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎችና ሴቶች ያሉባት እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ናት። ንሥሮች ከርቀት ጥቃቅኑን ነገር አጉልቶ የሚያሳይ ጥርት ያለ እይታ አላቸው። ክርስቶስ ቃሉ ነው። እርሱ የሕይወት እንጀራ ነው።
የጌታ አካል የሆነችዋ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን በእንጀራ ወይም በምግብ የተመሰለውን የጌታን ሥጋ ማለትም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርቶችን በመብላት ነው በሕይወት የምትኖረው። ስለዚህ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን የምታምነዋ ቤተክርስቲያን ናት።
ስለዚህ ከሚመጣው ቁጣ ተነጥቀን እናመልጥ ዘንድ የት መሆን አለብን? በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን እና የምናምነውን እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መርምረን ማረጋገጥ አለብን።
ዮሐንስ 6፡51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፡23 ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤
24 ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
መንፈሳዊ ንሥሮች የእግዚአብሔርን ቃል አጥርተው ያያሉ። ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ሲጠየቁ መጽሐፍ ቅዱስን ያለማወቅ መሃይምነታቸውን ሸፋፍነው ለማለፍ ብለው ጥያቄዎችን አያስፈልጉም እያሉ ወደ ጎን አይገፉም። እንቅልፋቸውን የተኙት ቆነጃጅት መግለጥ የማይችሏቸውን ምስጢሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መግለጥ ይችላሉ። መቅረዛቸው የዘይት መብራት ስላለው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር ይገልጥላቸዋል። ዘይት የሌላቸው መቅረዞች መብራት አይሰጡም፤ ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ትርጉም አያሳዩም። ስለዚህ ብዙ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን መመለስ የማይችሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች በመቅረዞቻቸው ውስጥ መብራት የላቸውም። ከዚህም የተነሳ ልባሞቹን ቆነጃጅት ለዳግም ምጻት ማዘጋጀትና መምራት አይችሉም፤ ነገር ግን እንቅልፋሞቹን ቆነጃጅት በእንቅልፋቸው ማስቀረት ይችላሉ።
ንሥሮች ስለታም መንቆር አላቸው በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ሥጋ መዘነጣጠልና ለመብላት እንዲያመች (ለመረዳት) በትንንሹ መክተፍ ይችላሉ።
ንሥሮች በተጨማሪ ከፍ ብለው መብረር ይችላሉ፤ ይህም የቤተክርስቲያንን መነጠቅ ያመለክታል።