ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 16



አይሁዶች ከእስራኤል በተሰደዱ ጊዜ በአሕዛብ ሃገራት ውስጥ በሕይወት ለመቆየት የንግድ ጥበባቸውን ተጠቅመዋል።

First published on the 14th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022

ሉቃስ አሁንም ስለ አንድ ሰው የሚናገር ምሳሌ ያቀርብልናል።

ይህ ምሳሌ ኢየሱስ ከሰጣቸው ምሳሌዎች ሁሉ ለመተርጎም ከባድ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ምሳሌ ውስጥ ኢየሱስ ጠማማ ሰውን ያመሰግናል።

ለምንድነው ይህን ያደረገው? ምክንያቱም ፈሪሳውያን እያዳመጡ ስለነበረና በሐይማኖር መሪነታቸው ተጠቅመው ገንዘብ መሰብሰብ ይወዱ ስለነበር ነው።

ሉቃስ 16፡14 ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።

ልክ እንደ ፈሪሳውያን ጠማማው መጋቢ የሥልጣን ቦታ ይዞ ነበር። አሁን ከሥራው ሊባረር ስለሆነ ከተባረረ በኋላ የሚጠጋበት ቦታ አስፈልጎታል።

ሉቃስ 16፡1 ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ፦ ይህ ሰው ያለህን ይበትናል ብለው ከሰሱት።
2 ጠርቶም፦ ይህ የምሰማብህ ምንድር ነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ አለው።
3 መጋቢውም በልቡ፦ ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፥ መለመንም አፍራለሁ።
4 ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ አለ።
5 የጌታውንም ባለ ዕዳዎች እያንዳንዳቸውን ጠርቶ የፊተኛውን፦ ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብህ? አለው።
6 እርሱም፦ መቶ ማድጋ ዘይት አለ። ደብዳቤህን እንካ ፈጥነህም ተቀምጠህ አምሳ ብለህ ጻፍ አለው።
7 በኋላም ሌላውን፦ አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ጫን ስንዴ አለ። ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ አለው።

እስቲ ይህን ምሳሌ በአይሁዳውያን ሕይወት እንፍታው።

አይሁዳውያን በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል እና የእግዚአብሔር መንፈስ መጋቢ ወይም ባለአደራ ነበሩ።

በቃልኪዳኑ ታቦት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ይዘዋል፤ ከውስጠኛው መጋረጃ በስተጀርባ ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ዘንድ ነበር። ከስንዴ ዳቦ ይጋገራል፤ ይህም የእግዚአብሔር ቃል ትምሕርት ምሳሌ ነው።

አይሁድ መሲሁን ስለተቃወሙ በእግዚአብሔር ዘንድ ከነበራቸው የከበረ ቦታና ከመንፈሱ እንዲሁም ከቃሉ ባለአደራነታቸው ሊሰረዙ ጊዜው ቀርቦ ነበር። ከዚያ በኋላ በሮማውያን አማካኝነት ከፓለስታይን ምድር ይባረራሉ። ስለዚህ ኢየሱስ በገንዘብ አበዳሪነትና በሃብት ሰብሳቢነት እንዲሰማሩ እየመከራቸው ነው ምክንያቱም በአሕዛብ መንግሥታት ውስጥ ተበትነው በሚኖሩበት ጊዜ መንግሥታቱን በገንዘብ በመደገፍ ተፈላጊ ሰዎች ይሆናሉ። በ70 ዓ.ም መቅደሱን አፍርሰው ኢየሩሳሌምን በሙሉ ከዘረፉ በኋላ ሮማውያን አይሁዶችን በዓለም ዙርያ በታተኑዋቸው፤ ከዚያም ቀጥለው በ135 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ከኢየሩሳሌም አስወጥተው ሰደዱዋቸው።

የእምነታቸው ማዕከል የነበረውን መቅደሳቸውን ካጡ በኋላ አይሁድ ለቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት የራሳቸውን በሕይወት የሚቆዩበትን ጽሑፍ ይጽፉ ነበር።

አይሁዳውያን በየሃገሩ ከፍተኛውን የኃይል ሥፍራ ከያዙት ወገኖች ጋር በማበር የገንዘብ ያዥነት ብቃታቸውን በመጠቀም በየሃገሩ ተቀባይነትን ከማግኘታቸውም በላይ በሕይወት መቆየትም ችለዋል። አይሁዶች ትጋትን ከጥበብና ብልሃት ጋር በማዋሃድ ንግድ እና የባንክ ሥራን በማወቅ የተቀበላቸውን ሃገር ሁሉ ኢኮኖሚ ወይም ምጣኔ ሃብት በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

በ711 ዓ.ም ሙስሊም አረቦች እስፔይንን በተቆጣጠሩ ጊዜ አይሁዶች በገበያ ቦታ ሃብታም ሆነዋል፤ ደግሞም ወደ ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ሥፍራ ላይ ተሹመው ምክትል ገዢዎች በመሆን የእስፔይን ሙስሊም ንጉስ በሃብት እንዲከብር አድርገዋል። እነዚህ አይሁዶች የንግድ ጥበባቸውን በመጠቀም የቀረው አውሮፓ ሁሉ ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ በሚወድቅበት ጊዜ እስፔይን ግን ለ700 ዓመታት በእሥላማዊ ሥልጣኔና ዘመናዊ ትምሕርት እንድትደምቅ አድርገዋል። ስለዚህ አይሁዶች እስላማዊ ሃብት እንዲያድግ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

በ1066 ዊልያም ዘኮንከረር ብዙ የፍሬንች አይሁዶችን ወደ ሃገሩ በማስገባት ባንክ ቤቶች እንዲከፈቱ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ኢኮኖሚ በእነርሱ አማካኝነት እንዲገነባ አድርጓል። የኢንግላንድ አንግሎ ሳክሰን ቄስ በሰዓቱ ከአይሁዶች ጋር ሲነጻጸር መሃይምነቱ፣ ምግባረ ብልሹነቱና ስግብግብነቱ ተጋልጧል። ፊደል ያልቆጠሩ መሃይም እንግሊዛውያን በሰዓቱ ኢኮኖሚ የሚባል ነገር አልነበራቸውም።

አይሁዳውያን ሲመጡ ልዩ የሆኑ የተማሩ ነጋዴዎች እንዲፈጠሩ አደረጉ። አይሁዳዊ የባንክ ገዥዎችም በባንክ ቤታቸው አማካኝነት ታላላቅ መጠን ያላቸው ገንዘቦች እንዲንቀሳቀሱ አደረጉ። አይሁዳውያን ገንዘብን የሚወክል ማስታወሻ ወረቀት በማዘጋጀት በአውሮፓ ውስጥ ዓለም አቀፍ የባንክ ሥርዓት ዘረጉ። ደግሞም አይሁዳውያን በሞሃመዳኖች እና በክርስቲያኖች መካከል አገናኝ ሆነውም አገለገሉ።

የጨለማው ዘመን ፊውዳላዊ ሥርዓት ከበርቴዎችን ለውትድርና ለውግያ፣ ቄሶችን ለጸሎት፣ ባሪያዎችን ደግሞ እርሻ ለማረስ መድቧቸው ነበር። ስለዚህ የነጋዴ መደብ አልነበረም። ስለዚህ አይሁዶች ይህንን ክፍተት ሞሉት፤ ከዚህም የተነሳ ሌላው ሕዝብ ሁሉ ተጠቃ ሆነ።

አይሁዶች ከኢንግላንድ ተባርረው ነበር ግን ከ1648 በኋላ ኦሊቨር ክሮምዌል መልሶ ወደ ኢንግላንድ እንዲገቡ ጋበዛቸው፤ የእንግሊዝን ካፒታሊስት ኢኮኖሚያዊ እድገት ያፋጥኑ ዘንድ። በቤተመንግሥት አካባቢ የሚሰሩ አይሁዶች በገንዘብ አስተዳደር ብልሃታቸው የታወቁ ነበሩ፤ ንጉሡንም የሃብታም ከበርቴዎችን ተጽእኖ እንዴት እንደሚቋቋም ያሳዩት ነበር። ሌሎች አይሁዶች በአውሮፓ ዙርያ ታላላቅ የንግድ ድርጅቶችን ከፍተው አስፋፉ። ራሺያ ውስጥ ከ1762 እስከ 1796 ትገዛ የነበረችዋ ካትሪን ዘግሬት አዲስ በያዘችው ግዛት በፖላንድ ውስጥ ኢኮኖሚ ለማሳደግ የአይሁዶችን ድጋፍ ትፈልግ ነበረ።

ሉቃስ 16፡8 ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።

ብሔራዊ ኢኮኖሚዎችን በመገንባት አንጻር የአይሁድ ካፒታሊዝም የክርስቲያን ቤተክርስቲያኖችን እጅግ በልጦ አደገ።

9 እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።

አይሁድ ኢየሱስን መሲሃቸው አድርገው ለዓለም አላስተዋወቁም። ነገር ግን ከሃገራቸው ተሰድደው በዓለም ዙርያ በተበተኑ ጊዜ የንግድ እና የባንክ ሥራ ክህሎታቸው በልዩ ልዩ ሃገሮች ውስጥ ተቀባይነት አስገኘላቸው።

በአይሁዶች ዘንድ ለማሕበረሰብ አገልግሎት መስጠት እንደ ግዴታ ነው የሚቆጠረው። አይሁዶች ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ ስለረዱዋቸው ሃገሮች በእነርሱ መኖር ብዙ ተጠቅመዋል።

10 ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።

አይሁዶች ከሃገራቸው ተሰድደው የወጡ ተንከራታቾች እንደመሆናቸው ለራሳቸው የሚደገፉበት አልነበራቸውም። ነገር ግን የገንዘብ አያያዝና የንግድ ጥበባቸውን በሚችሉት ያህል ተጠቅመውበታል። ደግሞም የግል ባንኮችንና ዓለም አቀፍ የባንክ አሰራሮችን በመዘርጋት የብዙ ሃገሮችን ምጣኔ ሃብት እንዲያድግ ድጋፍ አድርገዋል።

አይሁዳዊ የባንክ ገዥዎችና የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ብዙ ሃገሮችን ረድተዋል። የጀነራል ዌሊንግተን ጦር ሰራዊት እስፔይን ውስጥ በነበረ ጊዜ እንግሊዞች ፈረንሳይን እንዲያሸንፉ ለማገዝ አይሁዶች ብዙ ወርቅ ከኢንግላንድ ወደ እስፔይን በሰላም እንዲዘዋወር ረድተዋል።

አይሁዶች የገንዘብ አያያዝ ጥበባቸውን ተጠቅመው ብዙ ሃገሮችን መርዳታቸው ኋላ ለታላቅ ብድራት አብቅቷቸዋል -- እርሱም ወደ ራሳቸው ሃገር የሚመለሱበት ፈቃድ እንዲያገኙ።

በዚያው ጊዜ ውስጥ ግን እሥራኤልን ተቆጣጥረው የነበሩ ሕዝቦች የሃገሪቱን እምቅ ኃይል አላሳደጉም፤ ምክንያቱም እነርሱ አይሁዶችን በመጨቆንና በማሳደድ ተጠምደው ነበር። ብዙዎቹ እነዚህ ሕዝቦች ከታሪክ መዝገብ ውስጥ ጠፍተዋል።

ሮማውያን፣ የግሪክ ባይዛንታይኖች፣ ሳሳኒድስ፣ ክሩሴደሮች፣ ማምሉኮች፣ ቱርኮች፣ እና እንግሊዞች።

ቱርኮች እና እንግሊዞች ታላላቅ ግዛቶች ነበሩዋቸው፤ አሁን ግን አጥተዋቸዋል። አረቦች ፓለስታይን ውስጥ በድህነት ኖሩ፤ ያም ቦታ በረሃ እና እዳሪ መሬት ነበረ።

በስተመጨረሻ ግን አይሁድ ወደ እሥራኤል ተመልሰው ሲገቡ እዳሪ መሬት የነበረውን ሃገር አልምተውት በረሃን ወደ ገነት በመለወጥ በዓለም አንደኛ ሕዝብ ሆነዋል። ከራሳቸው ምድር ተባርረው በባዕድ ሃገሮች ለ2,000 ዓመታት ሁሉ ቆይተው ግን ተመልሰው ደግሞ በመምጣት ብቸኛ ሕዝብ ናቸው። ይህም በዓለም ታሪክ ብቸኛው የአንድ ሕዝብ ትንሳኤ ነው።

ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ በዓለም ዙርያ የነበሩ አይሁዳውያን እሥራኤል ውስጥ የሰፈሩ አይሁዳውያንን በብዙ ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች እና በብዙ የገንዘብ ስጦታ ድጋፍ አደረጉላቸው፤ ሰፋሪዎቹ አይሁዶችም ከቱርካውያን እጅ እዳሪ መሬቶችን እና ረግረግ ቦታዎችን በውድ ዋጋዎች ገዙ። ረግረግ ቦታዎች ላይ የተኛ ውሃ ወደ ሌላ ቦታ እየፈሰሰ እንዲሄድ አድርገው አጸዱ በረሃማ ቦታዎችንም ለእርሻ ምቹ የሆኑ ቦታዎች አደረጉዋቸው።

የኒውዮርክ ማዕከላዊ ገበያ ውስጥ የሚነግዱ አይሁዶችና አውሮፓ ውስጥ ሮዝስቻይልድ የተባሉ አይሁዳውያን ባንከሮች (በዓለም አንደኛ ሃብታም ቤተሰቦች) ለሃገሮች እና ለትልልቅ ዓለም አከፍ ኩባንያዎች ገንዘብ ያበድራሉ፤ ደግሞም የአሁኗን እሥራኤልም ይደግፋሉ። አይሁዳውያን የገንዘብ አጠቃቀምን ከማንም በላይ በማወቃቸው የዓለም ገንዘብና ኢኮኖሚ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሆነዋል። የገንዘብ አያያዝ ጥበባቸው ለ2,000 ዓመታት ያለማቋረጥ በደረሰባቸው ስደት ውስጥ ሳይጠፉ እንዲቆዩ አስችሏቸዋል።

በአሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ አይሁዳውያን እጅ ውስጥ ያለው ገንዘብ የእሥራኤል መንግሥት ጸንታ እንድትቆም ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል።

በ1948 እሥራኤል ነጻነቷን ስታውጅ ከአረቦች ጋር ሊገጥማት ስለሚችለው ጦርነት ጎልዳ ሜይር 2 ሚሊዮን ዶላር ለመለመን ወደ አሜሪካ ሄዶ ነበር። ጎልዳ 20 ሚሊዮን ዶላር ሰብስቦ ተመለሰ፤ ይህም ገንዘብ እስራኤልን በማዳን ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከ1941 – 1945 ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን በናዚ ጭፍጨፋ የመገደላቸው ግፍ ያስጨነቀው የተባበሩት መንግሥት መኖሪያ እንዲሆንላቸው በ1947 የሰጣቸው የእሥራኤል ምድር ለአይሁዳዊ ስደተኞች ዋነኛ መጠለያ ሆኗል።

እስታሊን ፕሬዚደንት በነበረበት ወቅት ራሺያ አይሁዳውያን በሃገራቸው መንግሥት እንዲመሰርቱ ዋነኛውን ሚና ተጫውታለች። ይህም እንግዳ ነገር ነበር ምክንያቱም እስታሊን አይሁዶችን በጣም የሚጠላ ሰው ነበር።

እግዚአብሔር ታላቅ እቅዱን ለመፈጸም የፈለገውን ሰው ይጠቀማል።

ሉቃስ 16፡11 እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?

የገንዘብ አያያዝ ጥበባቸውን ሌሎች ሃገሮችን ለመገንባት በማዋላቸው እግዚአብሔር ለአይሁዳውያን የራሳቸውን ሃገር እንዲገነቡ ፈቅዶላቸዋል፤ ይህም ሃገራቸው ራሳቸውን እየጠበቁ በሰላም መኖር የሚችሉበት ቦታ ነው። በቱርኮች እጅ የነበረውን ደረቅ እና እዳሪ የነበረ መሬት አረቦችም ተከራይተው በድህነት የኖሩበትን ሃገር አይሁዳውያን በገንዘብ አያያዝ ጥበባቸው በመጠቀም ሃገራቸውን በዓለም ላይ ካሉ ዋነኛ ኃያል አገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አብቅተዋል። በዚህ መንገድ አይሁዳውያን ብሔራዊ መኖሪያ ሃገራቸውን ከቱርኮች እጅ ገዝተው በንግድ ጥበባቸው በመጠቀም ዘመናዊ ሃገር ማድረግ ችለዋል፤ ቀሪውን መሬታቸውን ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት የፓለስታይን ምድር ለሁለት ተከፍሎ ሰማንያ በመቶ የሚሆነው በእንግሊዞች ጥበቃ ስር የነበረው ግዛት ለአረቦች እንዲሰጥ ቀሪው ግን ለአይሁዶች እንዲሰጥ ለተባለው ውሳኔ አንታዘዝም ካሉት አረቦች እጅ በጦርነት በማሸነፍ ነጥቀው የራሳቸው አድርገዋል።

አረቦቹ ይዘውት የነበረው ትልቅ ግዛት ትራንስጆርዳን የሚባል ሲሆን በዚህም ግዛት አረቦቹ በእንግሊዛውያን ጀነራሎች የሚመራ ጠንካራ ሰራዊት ነበራቸው። አረቦቹ የተባበሩት መንግሥታት ያስተላለፉትን ውሳኔ አልቀበል በማለት እሥራኤል ላይ ጦርነት አውጀው አይሁዳውያንን ከምድር ላይ ለማጥፋት ወሰኑ፤ በዚህም እንግሊዛውያን ተቆጣጥረውት የነበረውን የፓለስታይን ምድር አረቦቹ 100 በመቶ በእጃቸው ለማስገባት ፈለጉ።

አይሁዳውያን በጦርነቱ በማሸነፋቸው ስለእነርሱ የተነገረ ትንቢት ተፈጸመ (ትንቢቱ እውነት ነው)፤ ትንቢቱም የሚናገረው ወደ ምድራቸው እንደሚመለሱና እንደሚኖሩባት ነው።

አሞጽ 9፡15 በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥ ይላል አምላክህ እግዚአብሔር፡፡

ትልቁ ሃብታቸው መሲሁ ሲመጣ መጠባበቅ በሚችሉበት ሥፍራ በምድራቸው ውስጥ መሆናቸው ነው።

ሉቃስ 16፡12 በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?

አይሁዳውያን እንደ ባንከርነታቸው በሌሎች ሰዎች ገንዘብ ታማኝ ባይሆኑ ኖሮ የራሳቸውን መኖሪያ ሃገር ማን ይሰጣቸው ነበር?

አሁን ከብዙ ከባድ ጠላቶች ጋር ተዋግተው አሸንፈው ወደ ራሳቸው ሃገር ከተመለሱ በኋላ እግዚአብሔር ለዋነኛው መንፈሳዊ ዓላማቸው እያዘጋጃቸው ነው፤ ይህም ዓላማ በታላቁ መከራ ወቅት መሲሃቸውን መቀበል ነው። ይህም ለአይሁዳውያን እስከዛሬ ከተቀበሉት በረከት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ በረከት ነው።

መጋቢው የዘይቱን ግማሽ (50 በመቶ) መልሶ ሰጠ ነገር ግን ከስንዴው 20 በመቶ ብቻ ነው የመለሰው (ምክንያቱም ባለእዳው 80 በመቶ የስንዴ እዳ እንዳለበት አድርጎ እንዲጽፍ ነው የታዘዘው)።

አይሁዳውያን ለብሉይ ኪዳን ዘመን ብቻ የሚበቃ ያህል ነው የእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጣቸው፤ ያም ከእግዚአብሔር እቅድ ግማሹ (50 በመቶው) ነበር። ከዚያም በኋላ ሁሉን አጡ።

የ194ቱ የተባበሩት መንግሥታት በእንግሊዛውያን ጥበቃ ስር ከነበረው ግዛት 20 በመቶውን ብቻ ነው ያጸደቀላቸው። ቀሪውን ጦርነት የከፈቱባቸውን አረቦች በውጊያ በመግጠም ነው ያስለቀቁት።

ሉቃስ 16፡13 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ሃብትን ለማካበት ብለን መሥራት በቀላሉ የሕይወታችን ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ሊያጠምደን ይችላል፤ በዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገለጠው እውነት ከእግዚአብሔር መንግሥት ዓላማ ልንዘናጋ እንችላለን።

መጀመሪያ አይሁዶች ሃብት ላይ ትኩረት በማድረግ ሳይጠፉ ሊቆዩ ችለዋል፤ ይህም ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው መመለስ እንዲችሉ አብቅቷቸዋል።

በዚያ ጊዜ ገንዘብን አንደኛ እግዚአብሔርን ሁለተኛ አድርገው ነው የኖሩት።

ትኩረታቸው የገንዘብ ትርፍ ላይ ነበር።

በታላቁ መከራ ወቅት ግን ዝንባሌያቸው ይለወጣል። በዚያን ጊዜ መሲሁ ሊያድናቸው ሲመለስ ትኩረታች በአንደኛነት ወደ እግዚአብሔር ይዞራል።

ይህም ለውጥ የሚመጣው ከሁለቱ ነብያት ስብከት የተነሳ ነው (ሙሴ እና ኤልያስ)።

ሉቃስ 16፡15 እንዲህም አላቸው፦ ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።

አይሁዶች (እንዲሁም ሌሎቻችንም) ገንዘብ ማግኘት በምድር ላይ የመኖራችን ዋነኛ ዓላማ እንደሆነ ራሳችንን አሳምነናል። ሰዎች ሃብት ይገርማቸዋል። እግዚአብሔር ግን አስተያየቱ ከሰዎች ይለያል።

እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ ሊፈጽም የሚፈልገው መንፈሳዊ እቅድ አለው፤ ነገር ግን ገንዘብ መሰብሰብ የእግዚአብሔር እቅድ አይደለም።

አይሁዳውያን ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው እንደተመለሱት ሁሉ እግዚአብሔር የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት እንድትመለስ ይፈልጋል። ይህም እምነት ሙሴ እና ኤልያስ ለእሥራኤል ይዘውላት የሚሄዱት እምነት ነው።

ሉቃስ 16፡16 ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።

በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አይሁዳውያን በከባድ ፈተና እንዳለፉ ሁሉ ልክ እንደዚያው ክርስቲያኖችም የከባድ ፈተና ጊዜ ሊገጥማቸው ይችላል።

ሕጉ ለአዲስ ኪዳን እምነት ጥላ ነበረ። ኢየሱስ ደግሞ የጥላው አካል ነው። ነብያት የመሲሁን መምጣት በትንቢት ተናግረዋል። ዮሐንስ ከነብያት መካከል የመጨረሻው ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ በነበረበት ዘመን ኢየሱስ መሲሁ ሆኖ መጣ። አሁን እግዚአብሔር በማዳኑ በለወጣቸው ሰዎች ልብ ውስጥ መኖር ይፈልጋል። ግን ክርስቲያን መሆን ቀላል አይደለም። እያንዳንዱ ግለሰብ በሰው ሰራሽ ትምሕርቶች፣ በሐይማኖታዊ ወጎችና በመሪዎች አመለካከት ሳይታለል በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማገልገል ትልቅ ጥረት ማድረግ አለበት። ደግሞም በምድር ላይ የመኖራችን ዓላማ ሃብታም ለመሆን እንዳልሆነ መረዳትም ቀላል አይደለም። በተጨማሪ ደግሞ ማንም ሰው ወደ እውነት ለመጠጋት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ሰይጣን የቤተሰብ፣ የገንዘብ፣ የሥራ፣ እና የጤና ችግር በመፍጠር ጫና ያበዛበታል። እግዚአብሔር ለዘመናችን ባለው እቅድ ውስጥ ለመሳተፍ ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ መግፋትና መገስገስ ያስፈልጋችኋል።

ሉቃስ 16፡17 ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀላል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ነገር አንድ እንኳ ውሸት የለም። እያንዳንዱን ቃል ማመን አለብን። ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው የሚያምኑ። ብዙ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዱን ክፍል ይታዘዛሉ ሌላውን ክፍል ግን ቸል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለህ በፍጹም ማሰብ የለብህም። ደግሞም በፍጹም ሁለት ጥቅሶች ይጋጫሉ ብለህ ማመን የለብህም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማያስፈልግ ቃል አለ ብለህ በጭራሽ ማመን የለብህም።

ሳይንቲስቶች ከዲ.ኤን.ኤያችን ውስጥ 95 በመቶው ምን እንደሚሰራ አያውቁም፤ ግን አእምሮ ያላቸው ሳይንቲስቶች አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት 95 በመቶው የማይጠቅም ነው ብለው የሚያስቡ አይደሉም፤ ዘጠና አምስት በመቶው ምን እንደሚሰራ ያልታወቀው በአሁኑ ሰዓት ካለንበት ያለማወቅ ደረጃ የተነሳ ነው። ወደፊት አንድ ቀን ተጨማሪ እውቀት እናገኛለን። ለጊዜ ግን ሥራ እንዳለው እናውቃለን፤ ስለዚህ ሥራው ምን እንደሆነ እስክናውቅ ድረስ ፍለጋችንን ምርምራችንን እንቀጥላለን።

ልክ እንደዚሁ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው። ለጊዜው ባይገባህም ፍለጋህን ቀጥል፤ ሌሎችንም ለማዳመጥ ዝግጁ ሁን።

መልሱን ፍለጋ ተግተህ ብትቀጥል አንድ ቀን መልሱ ይገለጥልሃል።

2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 … የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

ትምሕርት እውነትን ያስተምረናል። ተግሣጽ ምን እንደተሳሳትን ያሳየናል። ማቅናት መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሳተ መንገድ ስንተረጉመው ወይም በትክክል ያልተረዳነው ጊዜ ያርመናል። ጽድቅ ደግሞ የተሻልን ሰዎች እንድንሆን ያደርገናል።

ከዚህ ቀጥሎ ሉቃስ ቤተክርስቲያኖች ከሚሰሩዋቸው ስሕተቶች መካከል ትልቁን ስሕተት ያሳየናል።

ሉቃስ 16፡18 ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፥ ከባልዋም የተፈታችውን የሚያገባ ያመነዝራል።

የትዳር ጓደኛ በሕይወት ሳለ መፋታት ወይም እንደገና ማግባት የሚባል ነገር የለም። የጋብቻ መሃላ የሚጸናው “ሞት እኪለየን ድረስ” ነው። ይህ መሃላ አንዴ በሕጋዊ መንገድ ከተፈጸመ በኋላ ምንም ነገር ሊያፈርሰው አይችልም።

ቤተክርስቲያኖች በዚህ ዘመን ከዓለም ጋር በማመቻመች በዓለም ዘንድ ተወዳጅ ሆነው ለመገኘት ሲሉ ትልቅ ስሕተት ሰርተዋል።

በድጋሚ አገቡ የተባሉ ጥንዶች ሁሉ በዝሙት የሚኖሩ ጥንዶች ናቸው። ለዚህም ሐጥያታቸው በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል።

በድጋሚ ያጋቡዋቸው የሐይማኖት መሪዎችም በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል። በዚያ ቀን ለማናቸውም ነገሮች መልካም አይሆኑላቸውም።

ያዕቆብ 4፡4 አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።

ቀጣዩ ስለ ሃብታም ሰው እና ስለ አንድ ድሃ ሰው የሚናገረው ምሳሌ ሰማይ ውስጥ ሁሉም ነገር በምድር ከምናየው ተገላቢጦሽ መሆኑን ያሳያል።

ሉቃስ 16፡19 ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር።
20 አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥
21 ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር።
22 ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ።
23 በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።

ሃብታሙ ሰውዬ ልክ ከሞተ በኋላ ወዲያው በድንገት ሐይማኖተኛ ሆነ፤ ስለዚህ አሁን ከድሃው ሰው ጋር አብሮ መሆን ፈለገ። ግን ጊዜ በጣም አልፎበታል፤ ረፍዶበታል።

ምንም መውጫ መንገድ የለም። አንዴ መስመሩን አቋርጧል።

ከዚያ በኋላ አንድ ሰው ከሙታን ተነስቶ ሄዶ ወንድሞቹን እንዲያስጠነቅቅለት ለመነ። አሁን ደግሞ በድንገት ወንጌላዊ ሆነ። ነገር ግን ለዚህም ረፍዶበታል።

ሉቃስ 16፡29 አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው።
30 እርሱም፦ አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ።
31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

ይህ በጣም አስፈሪ ማሳሰቢያ ነው። የጥንቷን ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳናዊ እውነቶች አሁን ማመን ካልቻልን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ከሙታን ተነስታ ብናያት እንኳ ትምሕርቶችዋን ማመን አንችልም። ምክንያቱም ከሙታን ከተነሳችም በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው የምትነግረን። ስለዚህ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጋር አብረን ወደ ሰማይ አንነጠቅም።

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23