ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የጠፋው በግ ተፈልጎ ይገኛል። የጠፋውም ሳንቲም ተፈልጎ ይገኛል። በንሰሃ የተመለሰው ምስጋና ቢስ ልጅ አባቱ ይቀበለዋል።
First published on the 12th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው ኢየሱስ የጠፉ ሰዎችን ፈልጎ ለማግኘትና ለማዳን የመጣ ሰው መሆኑን በማሳየት ላይ ነው።
ሉቃስ 15፡1 ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።
2 ፈሪሳውያንና ጻፎችም፦ ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ከሐጥያተኞች ጋር በመቀላቀሉና አብሮዋቸው ምግብ በመብላቱ ደንግጠዋል።
ስለዚህ ኢየሱስ እረኛ በመንጋ ውስጥ ያሉ በጎችን ከመንከባከብ የበለጠ ጊዜ የሚያጠፋው የጠፉ በጎችን በመፈለግ መሆኑን ነገራቸው (መንጋ ውስጥ ያሉት በጎች ምኩራብ ውስጥ የሚያመልኩት መልካሞቹ አይሁዶች ናቸው)።
ሉቃስ 15፡3 ይህንም ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል፦
4 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
5 ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤
6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦ የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።
7 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
አንድ ሐጥያተኛ ሲጠፋ እግዚአብሔር ያለውን አቅሙን ሁሉ አፍስሶ ያንን ሐጥያተኛ ለማዳን ይዘምታል።
አንዲት ሴት ዋጋ ያለው ነገር ቢጠፋባት መልሳ እስክታገኘው ድረስ በፍለጋ ብዙ ትለፋለታለች። የጠፋ ነፍስን ለማግኘት እና ወደ እግዚአብሔር መልሶ ለማምጣት ምን ያህል ከዚያ የበለጠ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል?
ሉቃስ 15፡8 ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
9 ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ፦ የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።
10 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።
ጠለቅ ያለ አተረጓጎም ሴት ቤተክርስቲያን መሆንዋን ያሳየናል።
ቤተክርስቲያን በአዲስ ኪዳን ተጀመረች፤ ነገር ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ ብዙዎቹን ሐዋርያዊ እውነቶች ጣለቻቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቤተክርስቲያን ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች ሁል ጊዜ የጠፋውን የሐዋርያት አስተምሕሮ በከፊልም ቢሆን መልሰው ለማግኘት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ቤተክርስቲያን ወደ ፊት ሊትገሰግስ የምትችለው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በመጠጋት ብቻ ነው።
ሐጥያት ማለት መጽሐፍ ቅዱስን አለማመን ነው። የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እውነቶችን እናገኝ ዘንድ መመለስ ታላቅ ደስታን የሚፈጥር ምክንያት ነው። ይህም እግዚአብሔር ከአለማመን እኛን በማውጣት እያዳነን ነው ማለት ነው።
እግዚአብሔር በእውነትና በመንፈስ ሊመለክ ነው የሚፈልገው።
ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
በዚህ በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ፍለጋችን በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን የመጀመሪያውን የእግዚአብሔር እውነት ለማግኘት ነው።
ከዚህ ቀጥሎ ሉቃስ በጣም ታዋቂ የሆነውን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ይነግረናል።
ሉቃስ ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ብለው የሚጀምሩ ምሳሌዎችን መርጦ ነው የጻፈው።
ሉቃስ 15፡11 እንዲህም አለ፦ አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።
12 ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።
13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።
ልጁ ከሰረ ገንዘቡን ሁሉ አጣ፤ ከዚያም ረሃብ መጣ፤ ጓደኞቹ የተባሉት ሁሉ ከዱት፤ እርሱም መጨረሻው አሳማዎችን መጠበቅና የአሳማዎችን ምግብ ተካፍሎ መብላት ሆነ።
ሉቃስ 15፡17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።
18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥
19 ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።
20 ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።
አባቱ ወደ ቤቱ ተቀብሎት ታላቅ ድግስ ደገሰለት።
ሉቃስ 15፡23 የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን፤
24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር።
ታላቅየው ወደ ቤት ሲመለስ ተበሳጨ፤ እንዲህም አለ፡- “እኔ አባቴን በታማኝነት አገልግያለሁ ግን እንዲህ አይነት ድግስ አልተደገሰልኝም። ግን ይህ በስባሳ ሐጥያተኛ ያለውን ሁሉ አባክኖ ሲመለስ የተካበደ ድግስ ይደገስለታል።”
ሉቃስ 15፡31 እርሱ ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፥ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤
32 ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለው።
ኢየሱስ ሐጥያተኛ ንሰሐ ሲገባ እና እግዚአብሔርን ሲያገለግል የሚፈጠረውን ደስታ ገለጠ።
ይህ እውነት ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲጀመር ያስቻለ እውነት ነው።
ለዚህ ምሳሌ ሁለተኛ ምክንያት አለ፡- የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የመጀመሪያ ቤት ነበረች። ከዚያም ክርስቲያኖች ቦታቸውን በጨለማ ዘመን ውስጥ አጡና በመንገድ ዳር ወደቁ። እያንዳንዱ ክርስቲያን ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የመጀመሪያ የሐዋርያት እምነት መመለስ እግዚአብሔር ሰማያዊ አባታችን ከእኛ የሚፈልገው እርምጃ መሆኑን በራሱ መወሰን አለበት፤ እንደዚህ አይነቱን ውሳኔ የሚያደርጉ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው በሰርጉ ግብዣ ላይ የሚገኙት።