ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 13

በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ በሰዎች መካከል የተመላለሰ ፍጹም ሰው ሆኖ ነው የተገለጠው።

ሉቃስ በተጨማሪ እኛ ደግሞ ሰዎች እንደመሆናችን እንዴት ማመን፣ ማሰብ እና መመላለስ እንዳለብን ያስተምረናል።

ሉቃስ ወንጌልን ለአሕዛብ ለማድረስ ጥልቅ ፍላጎት ነበረው። ሉቃስ አይሁድ በኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት ወቅት የሰሩዋቸውን ብዙ ስሕተቶች ይጠቅስልናል ምክንያቱም እኛ አሕዛብ ክርስቲያኖች በኢየሱስ ዳግም ምጻት ጊዜ ተመሳሳይ ስሕተቶችን እንደምንሰራ ያውቃል። ለነገሩ ስንፍና እና አለማስተዋል የሰው ልጆችነት ውስጥ ለዘመናት የተጠናወቱ በሽታዎች ናቸው።

ስለዚህ ሉቃስ አይሆዶች የሰሩዋቸውን ስሕተቶች በመጠቆም ለእኛ ለክርስቲያኖች ስለ ቤተክርስቲያኖቻችን ስሕተቶች አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠን ነው የጻፈልን።

ሉቃስ ምዕራፍ 13

አሥራ ሦስት አመጽን የሚወክል ቁጥር ነው።

ዘፍጥረት 14፡4 አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዝተው ነበር፥ በአሥራ ሦስተኛውም ዓመት ዐመፁ።

ራዕይ ምዕራፍ 13 አስፈሪውና ኃይለኛው የሮማ ካቶሊክ አውሬ (ወይም የቤተክርስቲያን-የገንዘብና-የፖለቲካ ኃይል) እና ዓለምን የሚገዛው የአሜሪካ አውሬ (ወይም የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን-ፖለቲካዊ-ሳይንሳዊ-ወታደራዊና-የገንዘብ ኃይል) በምድር ላይ ሊሰለጥኑ እንደሚነሱና በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ እንደሚያምጹ እንዲሁም የአውሬውን ምልክት ይዘው እንደሚመጡ ይናገራል፤ የአውሬው ምልክት ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሐይማኖታዊ ሃሳቦች መሞላት ነው።

የሚከተሉት ጥቂት ነጥቦች ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል ፈቀቅ ማለታቸውን ያሳያሉ፡- ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ነገሮችን እንዲያምኑ ይማራሉ፤ ለምሳሌ ቢግ ባንግ እና ኤቮልዩሽን ወይም ዝግመተ ለውጥ። የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ። በስም የተከፋፈሉ ቤተክርስቲያኖች። ቀኖናዎች። ሲኖዶሶች። ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች፣ ፖፕ። ካሕናት ማግባት አይችሉም። አገልጋዮች የተገለበጠ ኮሌታ ያለው ልብስ መልበሳቸው። የፋሲካ እንቁላሎች። ጥንቸሎች። ጉልላት ያላቸው የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችና አናታቸው ላይ አውራ ዶሮ። ፑርጋቶሪ። የሁዳዴ ጾም። በመስቀል ምልክት ማማተብ። ለጸሎት የመቁጠሪያ ጨሌ መጠቀም። ወደ ቅዱሳን መጸለይ። አርብ አርብ ዓሳ መብላት። ትልልቅ ቤተመቅደሶችን ካቴድራሎችን መገንባት።

ክርስቲያኖች የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲያምኑ ይማራሉ ግን በዚያው ላይ የተወሰነ ሰው ሰራሽ እምነት በመጨመር እንዲስቱ ይደረጋሉ። ኢየሱስ በቤተልሔም በግርግም ውስጥ ተወለደ። ይህ እውነት ነው። ነገር ግን የተወለደበት ቀን ዲሴምበር 25 እና በጌጥ ያሸበረቀ የክሪስማስ ዛፍ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም። ዛፍ ከኢየሱስ መወለድ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም።

የአውሬው ምልክት ቀስ በቀስ ወደ አእምሮዋችን የሚገባው በዚህ መንገድ ነው። ቤተክርስቲያን በዘዴ አእምሮዋችን መልካም በሚመስሉ ሰው ሰራሽ ሃሳቦች እንዲሞላ አድርጋለች፤ እኛም ደግሞ ተስማምቶናል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትናንሽ ሃሳቦችን እንደ እውነት ከተቀበልን በኋላ ከዚያም ከበድ ያሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ በጣም የራቁ ሃሳቦችንም መቀበል እንጀምራለን። ምልክቱ በግምባራችን ላይ ነው።

ግምባራችን ውስጥ ያለው አንጎላችን ነው። አንጎላችን ውስጥ እናስባለን። ሃሳባችን በቡድናዊ ቤተክርስቲያናችን ተማርኮ በቤተክርስቲያናችን እምነት ተሞልቷል።

መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል ጸንቶ መኖር አስፈላጊነቱ ቀርቷል።

ስለዚህ ሉቃስ ምዕራፍ 13 አንዳንድ አይሁዶች በሮማውያን ላይ ያደረጉትን ያልተሳካ አመጽ በመጥቀስ ይጀምራል።

ሉቃስ 13፡1 በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት።

እነዚህ አይሁዳውያን በጨካኙ ሮማዊ ገዥ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ላይ አምጸዋል፤ እርሱም ደም አፍሳሽ ገዢ ነበር።
ጲላጦስ ጨካኞቹ የሮማ ወታደሮች ዓለም ሁሉ እንዲፈራቸው ያደረገውን ሰይፋቸውን በአይሁድ ላይ እንዲመዝዙ ለማድረግ ምንም አያመነታም። ሮም ማንኛውንም አመጽ እንደ ብረት በጠነከረ ጭካኔ ነበር የምትጨፈልቀው።

ሉቃስ 13፡2 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን?

የተገደሉት ከሌሎቹ አይሁዶች የከፉ ሐጥያተኞች አልነበሩም። የተሳሳተ ውሳኔ ብቻ አደረጉ እንጂ። የተሳሳቱት ነገር በሮም ላይ በማመጽ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ለማግኘት መሞከራቸው ነው። ነገር ግን ሮም እጅግ በጣም ኃይለኛ መንግሥት ስለነበረች የሮምን ኃይል የሚቋቋሙበት አቅም አልነበራቸውም። ደግሞም መሲሁን መጠበቅ እንዳለባቸው እንኳ አልተረዱም። እርሱ ብቻ ነው ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅ። ስለዚህ መሲሁን በትዕግስት መጠበቅ አቅቷቸው በራሳቸው ጉልበት ተነሱ፤ ጉልበታቸውም ከንቱ ነበር። ከዚህ ክስተት ጲላጦስ ደግሞ ተቃ

ዋሚዎችን መጨፍለቅ በጣም ውጤታማ የሆነ የአገዛዝ ስልት እንደሆነ ተማረ። ይህንኑ ስልት ኋላ በኢየሱስ ላይ ይጠቀምበታል።

ፋይሎ የተባለ የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የታሪክ ምሑር እንደሚለው ጲላጦስ እንደ ግለሰብ “እጅግ ቁጠኛና ተበቃይ” ሰው ነበረ። ስለዚህ በእርሱ ላይ ማመጽ በራስ ላይ የሞት ፍርድ መፍረድ ማለት ነበር።

የአይሁዶቹ አመጽ ስኬታማ የሆነበት ነገር ቢኖር የጲላጦስን ጨካኝና ክፉ ባህርይ ማጋለጥ ሲሆን ኋላ ንጹህ ሰው የነበረውን ኢየሱስን ለምን ይሰቀል ዘንድ እንደፈረደበት ለማስተዋል ይረዳናል። ጲላጦስ ልቡ እውነተኛ ንጉሳቸው ኢየሱስ ላይ ወዳመጹት የአይሁድ አምባጓሮ ፈጣሪ ሕዝብ አድልቷል፤ ምክንያቱም እነርሱ ልባቸው በሐይማኖት መሪዎቻቸው ክፉ ምክር ተሞልቶ ሰክሯል። ሆኖም ግን ሕዝቡ በዚያው ሳምንት መጀመሪያ ኢየሱስ በሆሳዕና ዕለት አህያ ላይ ተቀምጦ ሲመጣ በጥሩ አቀባበል ተቀብለውት ነበር። የሰው ባሕርይ በቀላሉ ተለዋዋጭ ነው። አይሁድ ሲታለሉ የሐይማኖት መሪዎቻቸውን ሰሙ። የሐይማኖት መሪዎች ስለ ሐይማኖታዊ ሥርዓታቸው ለመሟገት ብለው ከሚሰብኩት ስብከት በላይ አደገኛ ክፉ ነገር የለም። በእውነት ላይ በሚያደርጉት አመጽ አይሁዶች ኢየሱስ፣ ማለትም ቃሉ፣ እንዲፈረድበት አደረጉ።

ሉቃስ 13፡3 እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ።

አይሁድ በኢየሱስ ላይ አመጹ፤ ከዚያም ገፉትና በ33 ዓ.ም ገደሉት።

ከዚያ አለማመናቸውና አስፈሪ ሐጢያታቸው እንዲሁም ከውጤቱ የሚያመልጡ መስሏቸው ነበር።

ግን አይሁድ በ66 ዓ.ም በሮማ መንግሥት ላይ አመጹ። ከአራት ዓመታት በኋላ ማለትም በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል የንጉስ ቬስፓሲያን ልጅ ወይም ልዑል ታይተስ ኢየሩሳሌምን ከበበና መቅደሱን አፈረሰ፤ ከተማይቱንም አወደማት። በዚያ የጥፋት ወቅት 1¸100¸000 አይሁዳውያን ተገድለው ወይም በበሽታና በረሃብ አልቀዋል።

አይሁድ ከዚያም በኋላ ከ115 – 117 ዓ.ም በንጉስ ትራጃን ላይ አመጹበት፤ በብዙ የጦር ሜዳዎችም ላይ ተሸንፈው ተገደሉ። በ132 ዓ.ም አይሁድ ለሦስተኛ በሮማ መንግሥት ላይ ጊዜ አመጹ። በስተመጨረሻ የሮማ ገዥ ሐድሪያን በ135 ዓ.ም አሸንፏቸው ከኢየሩሳሌም አባረራቸውና ኢየሩሳሌምን አዲስ የሮማ ከተማ አድርጎ ገንብቶ ኤሊያ ካፒቶሊና የሚል ስም አወጣላት። አይሁድ በዓለም ዙሪያ ተበታትነው ለ2000 ዓመታት ያለማቋረጥ ብዙ ስደት እና ጭፍጨፋ ደረሰባቸው። ይህም በአይሁድ ሕዝብ ላይ ሲደረግ የነበረ ጭፍጨፋ በስተመጨረሻ ጣራውን የነካው ከ1941 – 1945 ሒትለር ፖላንድ ውስጥ ባዘጋጃቸው በጋዝ ማፈኛ ክፍሎች ውስጥ ስድስት ሚሊዮን አይሆዶች በተገደሉ ጊዜ ነው። ከዚያ በኋላ እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው ወደ ፓለስታይን ተመልሰው እንዲገቡ በ1948 በተፈቀደላቸው ጊዜ በአረቦች በተከፈቱባባቸው አራት ጦርነቶችና ከጋዛ እንዲሁም ከሊባኖስ በኩል በትናንሽ ታጣቂ ቡድኖች አማካኝነት ያለማቋረጥ በሚደረግባቸው ብዙ ጥቃቶች ውስጥ አልፈዋል፤ ደግሞም በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶች ተተኩሰውባቸዋል፤ ብዙ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብም ፈንድቶባቸዋል። ከዚህም የተነሳ በዘመናት ውስጥ የሞቱ አይሁድ ቁጥር እያሻቀበ ሄዷል።

ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት ያለ ጥርጥር ተፈጽመዋል።

ሉቃስ 13፡4 ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤
5 ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።

ኢየሱስ በድጋሚ እጅግ ብዙ አይሁዶች እንደሚሞቱ ያስጠነቅቃል። የሞቱት አሥራ ስምንት አይሁድ ከሌሎች አይሁዶች ሁሉ በላይ ክፉዎች ሆነው አይለም። ለእኛ እነዚህ በአጋጣሚ የሞቱ ሰዎች ይመስሉናል፤ በሰዎች አመለካከት ሞት በአጋጣሚ መልካሙንም ክፉውንም አይሁድ ይዞት የሚሄድ ይመስላል። እነዚህ ሰዎች ክፉ ነገር እያደረጉ አልነበሩም፤ በማይሆን ሰዓት መሆን የሌለባቸው ቦታ ተገኙ እንጂ። አይሁዶች ኢየሱስን እንደ መሲሃቸው አድርገው ለመቀበል እምቢ ስላሉ ከዚያ የተነሳ በመንፈስ መገኘት የሌለባቸው ቦታ ነበሩ፤ ደግሞም በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ በተለያዩ ሕዝቦች የሚነሳ ጥላቻ አይሁዶችን በኢየሱስ ላይ ስላመጹበት አመጽ ከባድ ዋጋ እንዲከፍሉ አድርጓቸዋል። በታሪክ ውስጥ ከሁሉም ሕዝብ በላይ ምንም ርህራሄ የሌለው ጥቃት እና ስደት የደረሰባቸው አይሁዶች ናቸው።

ሉቃስ 13፡6 ይህንም ምሳሌ አለ፦ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው፥ ፍሬም ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም።

የበለስ ዛፍ በእግዚአብሔር ዘንድ የአይሁድ ሕዝብን ትወክላለች። ኢየሱስ ወደ አይሁድ ሕዝብ መጣ፤ እነርሱ ግን አንዳችም በእርሱ የማመን የእምነት ፍሬ አላፈሩም። እርሱ በጣም ቀለል ባለ መንገድ ስለመጣ በተስፋ የተነገራቸው መሲህ እርሱ መሆኑን ማመን አልቻሉም። አመጹበት፤ ደግሞም ይገደልልን አሉ።

ሉቃስ 13፡7 የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፦ እነሆ፥ ከዚህች በለስ ፍሬ ልፈልግ ሦስት ዓመት እየመጣሁ ምንም አላገኘሁም፤ ቍረጣት፤ ስለ ምን ደግሞ መሬቱን ታጐሳቍላለች? አለው።

ቀራንዮ አይሁድ ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ አልቀበል ማለታቸውን ያሳያል። እግዚአብሔር የሮማውያን ሰራዊትን ልኮ መቅደሱንና ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እያሰበ ነበር።

8 እርሱ ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት።

ግን መጀመሪያ ተጨማሪ እድል ሊሰጣቸው ፈለገ። በዚህም ምክንያት የእሥራኤል ዛፍ ከመቆረጥ ተረፈች። አይሁዶችን በማጥፋት ፈንታ እግዚአብሔር ሐዋርያትን መጀመሪያ ለአይሁዶች እንዲሰብኩ ላካቸው፤ መሲሁን በመግደል ትልቅ ሐጥያት ቢሰሩም በወንጌሉ ሊያድናቸው ፈለገ።

9 ወደ ፊትም ብታፈራ፥ ደኅና ነው፤ ያለዚያ ግን ትቈርጣታለህ አለው።

ኢየሱስ ለአይሁድ ሰበከ፤ እነርሱ ግን እምቢ አሉ። የመጀመሪያው እድል አለፋቸው። ከገደሉትም በኋላ እንኳ ኢየሱስ ወደ እነርሱ ሄደው ይሰብኩ ዘንድ ደቀመዛሙርቱን ላከ፤ በዚህም ሌላ እድል ሰጣቸው።

ነገር ግን ብዙዎቹ አይሁዶች ወንጌሉን አልቀበልም አሉ። በዚህም ሁለተኛ እድላቸውን እምቢ አሉ።

የአዲስ ኪዳን ታላቅ ሐዋርያ ጳውሎስ ነበረ። እርሱንም ጭምር አይሁዶች አንሰማህም አሉ።

የሐዋርያት ሥራ 13፡46 ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው፦ የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘላለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።

ሉቃስ የአይሁዶችን አመጽ ሊነግረን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ አሥራ ሦስተኛ ምዕራፍን እንደ መረጠ ልብ በሉ። ይህም አመጽ አይሁዶች ወንጌልን የገፉበትና ጳውሎስም እነርሱን ትቶ ወደ አሕዛብ ዘወር ለማለት የተገደደበት ነው።

ስለዚህ በመቅደሱ አምልኮ ማዕከልነት የተመሰረተው የአይሁድ ዛፍ ሊቆረጥ ጊዜው ደረሰ፤ ምክንያቱም ለሁለተኛ በተሰጠው እድልም እንኳ በኢየሱስ ማለትም በእግዚአብሔር የማመንን ፍሬ አላፈራም አለ።

ገላትያ 5፡22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።

የዚያን ጊዜ አይሁድ እንደ ሕዝብ በተጨማሪ የየዋሕነትና የሰላምን ፍሬ አንፈልግም ብለው ጣሉ፤ በሮማ መንግሥት ላይ ለአራት ዓመታት ምርር ያለ አመጽ በማስነሳታቸው በሮማዊው ጀነራል ታይተስ አማካኝነት በ70 ዓ.ም ተጨፍጭፈዋል፤ በኢየሩሳሌም የነበረው መቅደሳቸውም ፈርሷል።

ይህ ለእኛም ማስጠንቀቂያ ነው። በዚህ ባለንበት የመጨረሻ የሎዶቅያ ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል አልቀበል ማለቷ በታላቁ መከራ ውስጥ እንድትወድቅ ያደርጋታል። ስለዚህ በአደገኛ ዘመን ነው የምንኖረው።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን [በእንግሊዝኛ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ነው የሚለው] መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

ቤተክርስቲያኖቻችን ዛሬ ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ያለው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከበር ውጭ መቆሙንና ሊገባ እየፈለገ መሆኑን ያሳየናል። ማን ትክክል እንሆነ መምረጥ አለባችሁ።

ከዚያ በመቀጠል ሉቃስ በአይሁድ እና በኢየሱስ መካከል ስለተከሰተ አንድ ክስተት ይነግረናል፤ ይህም ክስተት ለአሕዛብ ቤተክርስቲያን የሚናገረው ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው። ሉቃስ እኛ አሕዛቦች ከአይሁዶች ስሕተት እንድንማር ይፈልጋል፤ አለዚያ የአሕዛብ ቤተክርስቲያንም አዲስ ኪዳንን ባለማመኗ በታላቁ መከራ ውስጥ ከባድ ስደትና ሞት ይገጥማታል
ሴት የክርስቶስ ሙሽራ ለሆነችዋ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

ከዚያም ኢየሱስ አንዲት የጎበጠች ሴትን (ይህች ሴት የጎበጠችና ትፈወስ ዘንድ የኢየሱስ ኃይል የሚያስፈልጋትን ቤተክርስቲያን ትወክላለች) በቅዳሜ ቀን ፈወሳትና በሰንበት ሥራ ሰርተሃል ተብሎ ተከሰሰ።

ሉቃስ 13፡12 ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤
13 ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
14 የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ።
15 ጌታም መልሶ፦ እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን?

ሴትየዋ በፊት ወደነበራት ጤና መመለሷን የሐይማኖት መሪዎች ተቃወሙ።

ዛሬ ቤተክርስቲያን በአዲስ ኪዳን መጀመሪያ ዘመን ላይ ወደነበረችበት መመለሷን የሚቃወሙት የሐይማኖት መሪዎች ናቸው።

በኢየሱስ (በእግዚአብሔር ቃል) ላይ የሚመጣው ተቃውሞ ከጉባኤ መሪዎች ዘንድ መሆኑን ልብ በሉ። ዛሬ ምኩራቡን ቤተክርስቲያን ብለን እንጠራዋለን። መሪውም ፓስተሩ ነው።

ኢየሱስ የምኩራቡን መሪ በመንቀፍ ጠንከር ያለ ትችት ሰነዘረበት። የሐይማኖት መሪውን ግብዝ ነህ አለው። በቅዳሜ እንስሳት ውሃ እንዲጠጡ ይዘሃቸው ትሄዳለህ። አንዲት ሴትስ የሚፈውሰውን የሕይወት ውሄ እንድትጠጣ ለምን አይፈቀድላትም?

ሉቃስ 13፡16 ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው።
17 ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።

ሕዝቡ ኢየሱስን ይወዱታል፤ የሐይማኖት ተቋማት ግን አጥብቀው ይቃወሙታል።

የሐይማኖት መሪው ኢየሱስን ተቃወመ ምክንያቱም ኢየሱስ ለሐይማኖታዊ ድርጅቶች አደጋ ነበረ።

በመጀመሪያው ምጻቱ ኢየሱስ የአይሁዶችን የሐይማኖት መሪዎች እንደተቃወመ ልብ በሉ።

በዳግም ምጻቱስ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ምንድነው የሚላቸው?

ሉቃስ ከዚህ በመቀጠል ቤተክርስቲያንን የሚመለከት ትንቢት ይገልጥልናል። 2000 ዓመታት የሚፈጀው የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት የተከፋፈለ ነው። የቤተክርስቲያን ዘመናት አንድ በአንድ ሲገለጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች የተቻላቸውን ያህል ሕዝቡን ከኢየሱስ ማለትም ከእግዚአብሔር ቃል ለማለያየት ጥረት አድርገዋል። እንዴት አድርገው ነው የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡ ከተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ፊታቸውን ዘወር አድርገው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነውን ክፍል ብቻ አምነው የቀረውን እምቢ እንዲሉ ያደረጓቸው?

ኢየሱስ ሁለት ምሳሌዎችን በመጠቀም ሊመጡ ስላሉት ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት አስደናቂ ትንቢት ይናገራል።

በማቴዎስ ምዕራፍ አሥራ ሦስት ውስጥ ሰባት ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል። (አሁንም 13 ቁጥር።) እያንዳንዱ ምሳሌ አንድ የቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል። ከእነዚህ ምሳሌዎች ውስጥ ሁለቱን ብቻ ነው የሚጠቅሳቸው፤ ማለትም ሦስተኛውን እና አራተኛውን። ሦስተኛውና አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመኖች ከ312 ዓ.ም እስከ 1517 ዓ.ም የዘለቀውን የጨለማውን ዘመን ይወክላሉ፤ ያም ጊዜ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን የተቆጣጠረችበት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያመጸችበትና ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን በእጃቸው እንዳይገባ ያገደችበት ዘመን ነበረ። ብቸኛው ማንበብ የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስ በላቲን ቋንቋ የተጻፈው ሲሆን ሕዝቡ ደግሞ ላቲን ማንበብ አይችሉም ነበር። ቤተክርስቲያን ዊልያም ቲንዴልን ገደለች፤ የጆን ዊክሊፍን አጥንት ደግሞ ቆፍራ በማውጣት አቃጠለች፤ ይህን ያደረገችው እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሕዝቡ ማንበብ ወደሚችሉት ቋንቋ ስለተረጎሙ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚደረገው ይህ አመጽ እንዴት እንደሚጀምር ይገልጻል።

አይሁዶች በኢየሱስ ላይ ሰው እንደመሆኑ አመጹበት። ቤተክርስቲያን ደግሞ በኢየሱስ ላእ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ አመጸችበት።

ይህ ምሳሌ በ312 ዓ.ም ጀምሮ በ600 ዓ.ም ስለተጠናቀቀው ስለ ሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።

ሉቃስ 13፡18 እርሱም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች፥ በምንስ አስመስላታለሁ?
19 ሰው ወስዶ በአትክልቱ የጣላትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች፥ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ሰፈሩ አለ።

የሰናፍጭ ቅንጣት እንክብካቤ ሲደረግላት መጠነኛ ቁመት ያለው ዛፍ ሆና የምታድግ ትንሽዬ ዘር ናት።

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖች በጣም ትልቅ እንዲሆኑ አስቦ አያውቅም።

ለዚህ ነው በጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሰዎች በየቤቱ ይሰባሰቡ የነበሩት። የዛን ጊዜ አንድ ሰው ትልቅ ጉባኤን የመግዛት እድል አልነበረውም።

ሮሜ 16፡5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

ፊሊሞና 1፡2 ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤

ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።

ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ልንመለስ ከፈለግን ይህንን እውነት ልብ ማለት አለብን።

ሕዝቡ እንጂ ሕንጻው ቤተክርስቲያን እንዳልተባለ አስተውሉ። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን እንደሄዱ አይናገርም። ሕዝቡ ራሳቸው ቤተክርስቲያን ነበሩ።

መጀመሪያ ክርስቲያኖች ጥቂት ሆነው ነበር የሚሰባሰቡት ምክንያቱም ሮማውያን ሊገሏቸው ይፈልጓቸው ነበር። ከ64 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 312 ዓ.ም ባሉት ዓመታት መካከል የሮማ ነገሥታት በክርስቲያኖች ላይ አሥር ከባድ ስደቶችን በማስነሳት 3 ሚሊዮን ያህል ክርስቲያኖችን ገድለዋል። [እነዚህን ከባድ ስደቶች ካስነሱ የሮማ ነገሥታት አንዱ ኦውሬሊያን ሲሆን ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ የሶል ኢንቪክተስ (የማይሸነፈው ፀሃይ) ልደት ቀን ነው ብሎ ያወጀውም እርሱ ነው። ይህም ቀን ሮም ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የፀሃይ አምላክ ልደትም የክርስቶስ ልደትም ተብሎ በፋይሎካሊያን ካላንደር በ354 ዓ.ም ተጠቅሷል። የፀሃይ አምላክ ልደት ቀን የአከባበር ሥነ ሥርዓት በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተኮርጆ የእግዚአብሔርን ልጅ ልደት ለማክበርም እንዲያገለግል ተደረገ፤ ይህም የባእድ አምልኮ ውስጥ የነበሩዋቸውን ስጦታ የመለዋወጥና ዛፍን የማስጌጥ ልማዶቻቸውን ወደ ክርስትና ይዘው መምጣት አስችሏቸዋል። ይህንን የአሕዛብ በዓል ማክበር ያስጀመረው ሰው ጨካኝ የክርስቲያኖች አሳዳጅና ነፍሰ ገዳይ እንደነበረ አትርሱ።]

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ትስፋፋ የነበረው በመበታተንና በስደት ስለነበረ በጥቂት ሰዎች ቡድን ነበር የምትሰበሰበው፤ ያውም በሰዎች ቤት ውስጥ። በይፋ በሕዝብ አዳራሽ ወይም “በቤተክርስቲያን” ቢሰበሰቡ የሮማ ወታደሮች ይዘዋቸው ይገድሉዋቸው ነበር። በቻይና ውስጥ ኮምዩኒስቶች ክርስቲያኖች ላይ ስደት እያስነሱ የእምነት ነጻነት በሌለበት ቤተክርስቲያን የተስፋፋችበት መንገድ አሁንም የምትንቀሳቀስበት መንገድ የቤት ውስጥ ቤተክርስቲያን ነው።

በ312 ኮንስታንቲን የተባለው ንጉሥ ክርስቲያኖችን ማሳደድ እንዲቆም አደረገ፤ ክርስቲያኖችም በሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ መሰብሰብ ጀመሩ፤ መሰብሰቢያዎቹም በስሕተት ቤተክርስቲያን ተብለው ተጠሩ። ቤተክርስቲያን የአማኞች አንድነት እንጂ የሚሰበሰቡበት አዳራሽ አይደለም። ጉባኤውም በቁጥር እጅግ እየበዛ ሄደ። አንዳንዴ ክርስቲያኖች ትልልቆቹን የአሕዛብ ቤተመቅደሶች መውረስ ጀመሩ። የሰናፍጭ ቅንጣት ያለቁጥጥር በጣም ሲያድግ ነው ትልቅ ዛፍ የሚሆነው፤ ይህም ከሰናፍጭ ባሕርይ ጋር አብሮ አይሄድም። ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ማደግ ማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ሃሳቦችን ተቀብሎ ማስተናገድ ነው። ትልቅ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የሰው አስተሳሰቦችን አመራሮችን፣ ሰው ሰራሽ ሥርዓቶችን እና የሥልጣን ተዋረዶችን፣ ወጎችና ልማዶችን ተቀብሎ ያስተናግዳል። የሰው አስተሳሰቦች ገዢ ይሆናሉ። በዚያ ዘመን ክርስትና ከሮማውያን ባእድ አምልኮ እና ከፖለቲካ ጋር መዋሃድ ጀመረ። የአሕዛብ ቤተመቅደሶች የሚተዳደሩት በካሕን ነበር፤ ከዚያ በኋላ ቆይቶ ፓስተሮች ቦታውን ተረከቡ።

መጽሐፍ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ራስ ፓስተር ነው ብሎ አያውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ እረኛ ፓስተር ነው አይልም። ፓስተር የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው። ዛሬ ግን ፓስተሮች የቤተክርስቲያን ራስ የመሆንን ስልጣን ነጥቀው ይዘዋል። ከዚያም ምክትል ፓስተሮች፣ ረዳት ፓስተሮች፣ የሰንበት ትምሕርት ቤት ተቀጣጣሪዎች፣ ፓስተሮችን የሚቆጣጠሩ ቄሶች፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ የከተማ እና የአውራጃ አስተዳዳሪዎች፣ ካርዲናሎች እና ፖፕ ድረስ የሚደርሱ የስልጣን ተዋረዶች ተመሰረቱ። ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን የሥልጣን ተዋረዶች በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል እንጂ በሙሉ አይደለም። ይህ አይነቱ የቤተክርስቲያን አወቃቀር የሮማ መንግሥት ፖለቲካዊ መዋቅር ኩረጃ ነው።

ዛፍ በቁመቱ ውስጥ በተለያዩ ከፍታዎች ላይ ቅርንጫፎች አሉት። ሰዎች እግዚአብሔርን ያገለገሉ እየመሰላቸው በቤተክርስቲያን ውስጥ በስልጣን እያደጉ ይሄዳሉ። ነገር ግን የሚያገለግሉት የቤተክርስቲያንን መዋቅር ብቻ ነው።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን ትልቅ እየሆነች ስትሄድ በእነዚህ አይነት ሰዎች እና በእነርሱም አመለካከት ትተዳደራለች።

አሞራዎች ማለት ምን ማለት ነው?

ዘፍጥረት 15፡11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።

ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እያደረገ ሳለ አብራሐም አሞራዎችን አባረረ። ስለዚህ አሞራዎች የጠላት ምሳሌ ናቸው።

ግን በትልቅ ሐይማኖታዊ መዋቅሮች ውስጥ ለ“አሞራ” አገልጋዮች ከሕዝቡ በላይ ከፍ ብለው የሚቀመጡበት ምቹ ቦታ አለ። እነርሱም ከፍ ባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተቀምጠው በሙሉ ጊዜያቸው ጉባኤውን ይበሉታል። ይህ የኒቆላውያን ሥርዓት ነው፤ ማለትም ታላላቆቹ የሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡን ጨቁነው ይገዛሉ፤ ሕዝቡም የቤተክርስቲያን አባል ሆነው መቀጠል የሚችሉት ለመሪዎች ያለ ምንም ጥያቄ እስከታዘዙ ድረስ መሆኑን ያውቃሉ። እግዚአብሔር የኒቆላውያንን ሥራ ይጠላል። የኒቆላውያን ሥራ ማለት አንድ ሰውን ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ ነው። ስለዚህ አሁን ጠላት ትልልቆቹን የቤተክርስቲያን ድርጅቶች ይገዛቸዋል። ይህ በጣም የተዋጣለት አታላይነት ነው።

ይህ አይነቱ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ፈውስ በሚያስፈልጋት በድካም መንፈስ በታሰረችዋ ሴት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወከለው።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ድካም ያለባት ሴት በጨለማውን ዘመን ውስጥ በመንፈሳዊ ድካም ታስራ የነበችውን ቤተክርስቲያን ትወክላለች። በጨለማው ዘመን የቤተክርስቲያን ኃይል ምንጩ ፖለቲካ እና የባእድ ሐይማኖቶች እምነት ነበር። ፖለቲካ እና ሐይማኖት ሲጣመሩ የሞት ታናሽ ወንድም ነው የሚሆኑት። በጨለማው ዘመን ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በመቃወማቸው እና ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር የጀመረውን ተሃድሶ ለማፈን ተብሎ በተደረገው ጸረ ተሃድሶ ዘመቻ 68 ሚሊዮን ሰዎች ተገድለዋል።

እግዚአብሔር በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ለሦስተኛዋ ቤተክርስቲያን ምን እንደሚል ተመልከቱ።

ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

ኒቆላውያን። ምዕመናኑን ጨቁኖ የሚገዛ አንድ ቅዱስ ሰውን ከፍ አድርጎ መሾም። ፖፑ ዋነኛ ሐይማኖታዊ አምባገነን ነው። ፓስተሮችም የእርሱን ምሳሌነት በመከተል እንደ ራሳቸው ሃሳብ ጉባኤውን ይገዛሉ። ጉባኤው ለዚህ አምባገነናዊ አገዛዝ በመገዛት የሚገዛቸውን የፓስተሩን መንፈስ ይከተላሉ። እንዲህ አይነቱ ቦታ ውስጥ መቀመጥ ለክርስቲያን መልካም አይደለም።

የሰው አመራር የሰውን ሥርዓቶችና ወጎች እንዲሁም የተዛቡ የሰው አመለካከቶች በሕዝብ ላይ ይጭናል። አንድ ፓስተር ሚስቱን ፈቶ ሌላ ቢያገባ ብዙ ሰዎች ወደርሱ ቤተክርስቲያን ይጎርፋሉ፤ ምክንያቱም እነርሱም ለመፋታትና እንደገና ለማግባት ፈቃድ ያገኛሉ። አንድ ፓስተር መጠጣትንና ማጨስን ከፈቀደ ጉባኤውም እርሱን ተከትለው ይጠጣሉ፤ ያጨሳሉ።

ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን መሪያቸው ሊሳሳት ይችላል ብለው አያስቡም። መጽሐፍ ቅዱስን ከሚከተሉት ይበልጥ መሪዎቻቸውን ይከተላሉ። እግዚአብሔር በሰው ሰራሽ ሕጎች፣ እምነቶችና መዋቅሮች አማካኝነት መሪዎች ራሳቸውን ከጉባኤው በላይ ከፍ ያደረጉበትን የቤተክርስቲያን ሥርዓት ይጠላዋል።

በተለይም እግዚአብሔር የሚጠላው ነገር ፓስተሩ አሥራት በሙሉ ለእኔ ይገባኛል ሲል ነው። ይህም የቤተክርስቲያን መሪ መሆንን ሰው የሚፈልገው ለምን እንደሆነ ያስታውቃል፡- ለገንዘብና፣ በሰዎች ላይ ሥልጣን ለማግኘት። ይሁዳም ገንዘብ ተከትሎ ነው የሄደው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሰበከ (የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት መንፈስ ቅዱስ በግለሰቦች ልብ እና አእምሮ ውስጥ ሲሰራ ማለት ነው) የሰዎች አመራር ግን ታላቅ የቤተክርስቲያን መዋቅርን አበጀ፤ በዚህም መዋቅር ውስጥ ሰዎች የሥልጣን ተዋረድን በማበጀት፤ መማክርትን መስርተው ኢየሱስ የደነገጋቸውን ትዕዛዛት ሁሉ ለራሳቸው ብዙ ተከታዮች ለማፍራት ሲሉ ሻሩ። ስለዚህ ኢየሱስ ያወገዘው የብሉይ ኪዳን ክህነት ስርዓት በካሊክ ቤተክርስቲያን የጓሮ በር በኩል ሾልኮ በመግባት ቤተክርስቲያን እንድታድግ አደረገ።

አንድ ጨቋኝ መሪ በቤተክርስቲያን ላይ ከተሾመ ቤተክርስቲያንን በተዋጣለት መንገድ ማሳደግ ይችላል።

ቀጣዩ ምሳሌ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ አራተኛው ምሳሌ ነው፤ እርሱም አራተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል፤ ያም የጨለማው ዘመን ኃይል ከ600 ዓ.ም እስከ 1517 ዓ.ም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የነበረበት ጊዜ ሲሆን ሉተር ተሃድሶ የጀመረው የዛኔ ነው። በዚያ ዘመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኃይሏ በአውሮፓ ላይ በከፍተኛ ደረጃ የበረታበት ጊዜ ነው። ከዚያ በኋላ በ1348-49 ብላክ ዴዝ የሚባለው ወረርሽኝ የአውሮፓን ሕዝብ ቁጥር በእጅጉ ስለቀነሰው ታላላቅ የመሬት ባለንብረቶች ማለትም ከበርቴዎችና ቤተክርስቲያን ሃብታቸውንና በሕዝቡ ላይ የነበራቸውን ስልጣን በተወሰነ ደረጃ አጥተዋል። የነጋዴዎች መደብ በኃይል እየበረታ መጣና ከዚያ ወዲያ ሕዝቡ ቤተክርስቲያን የምታደርጋቸውን ክፉ ሥራዎች መቃወም ጀመሩ። ነገር ግን የሥላሴ ትምሕርት በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ቦታ ይዞ በመቆየቱ የተሃድሶ መሪዎች እንኳ ጥያቄ ሊያነሱበት አላሰቡም። በ1553 ጆን ካልቪን የተባለው የፕሮቴስታንት ተሃድሶ መሪ በሥላሴ አላምንም ብሏል ብሎ ማይክል ሰርቬተስ የተባላ ፕሮቴስታንት እስፔይናዊ ዶክተርን በአደባባይ በእሳት አቃጥሎ ገደለው።

ሉቃስ 13፡20 ደግሞም፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን አስመስላታለሁ?
21 ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች አለ።

ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ አውሮፓን በሙሉ በጭቆና ገዝታለች።

አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ትያጥሮን ይባላል፤ ትርጓሜውም “ጨቋኝ ሴት” ማለት ነው።

በዚህም የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-

ራዕይ 2፡20 ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤

ኤልዛቤል። በብሉይ ኪዳን ከተጠቀሱ ሴቶች ሁሉ በክፋቷ አንደኛ ናት። እርሷም የጨለማው ዘመን ገዥ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እስካሁን የተቀረጹ ምስሎችን ማለትም ጣኦታትን ለአምልኮ ትጠቀማለች።

በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ጫና በማድረግ ያስፋፋችው አስተምሕሮ ምንድነው?

እንጀራ የሚጋገርበትን ዱቄት ወሰደች፤ ይህም የአስተምሕሮ ተምሳሌት ነው። ኢየሱስ ማለትም ቃሉ የሕይወት እንጀራ ነው። ከዚያም እርሾ ወስዳ ዱቄቱ ውስጥ ደባለቀችው፤ ከዚህም የተነሳ እርሾው ስለተደበቀ በግልጽ አይታይም። እርሾ ሊጥ ውስጥ ሲገባ ከመበስበሱ የተነሳ ከውስጡ በሚያወጣው ካርቦን ዳይኦክሳይድ አየር የተነሳ ሊጡን ኩፍ ያደርገውና ያፋፋዋል። ኩፍ ማለቱ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ትዕቢት ያመለክታል፤ እነርሱም በራሳቸው ብቃት ይተማመናሉ፤ የአባሎቻቸውም ብዛት ልክ ሊጡ ኩፍ እንደሚለው እየበዛ ይሄዳል።

ነገር ግን የአባላጥ በቁጥር መብዛት መንስኤው የእርሾው መበስበስ ነው። ይህም ጥሩ ተምሳሌት አይደለም።

ቤተክርስቲያን ከውጭ ሲያዩዋት መልካም ትመስላለች ከውስጧ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ አስተሳሰቦች የተነሳ በስብሳለች።

ሉቃስ 11፡39 ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል፡፡

ልክ በጨለማው ዘመን የካቶሊክ ቄሶች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪዎች እንደነበሩት ፈሪሳውያን የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ነበሩ።

ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ ተሳስተሻል የሚላት ተቀናቃኝ በሌለበት ለዘጠኝ መቶ ዓመታት በሕዝብ ልብ ውስጥ የተከለችው ክፉ ትምሕርት ምንድነው?

እርሾው በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ ነው የተደበቀው። ቤተክርስቲያን ሥላሴ የሚባል አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስውር በመሆነ መንገድ ደብቃ ስላስገባች ሰዎች በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሊያዩ አልቻሉም።

የሥላሴን ጽንሰ ሃሳብ ለማስረዳት ተብሎ የሚጠቀሙዋቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።

“ሥላሴ” የሚለው ቃል እራሱም ሆነ “በመለኮት ውስጥ ያሉ ሦስት አካል” የሚለው አገላለጽ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። “አንድነት በሦስትነት”። “ሦስትነት በአንድነት”። “አንድ አምላክ በሦስት አካላት”። “የመለኮት ሁለተኛው አካል”። “አብና ወልድ አንድ ባሕሪ ናቸው”። “እግዚአብሔር ወልድ”። “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ”። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ለምን “የእግዚአብሔር ልጅ” እንደሚል ነገር ግን በጭራሽ “እግዚአብሔር ወልድ” እንደማይል ቢጠየቁ መመለስ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔር መንፈስ” ይላል ግን በጭራሽ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” አይልም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ 16 ጊዜ “እግዚአብሔር አብ” ይላል። የተደበቀው እርሾ ይህ ነው። ቤተክርስቲያን የሥላሴን ጽንሰ ሃሳብ ከጥንት አረማውያን ባቢሎኖችና ከግብጾች ተውሳ አመጣችውና ይህ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በስውር ተገልጧል ለማለት የግሪክ ፍልስፍና ተጠቀመች (አንድ በሦስት እና ሦስት በአንድ)። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነቡ ሲያደርጉ የነበሩት ለዚህ ነው።

ስለዚህ ከብዙ ዓመታት በኋለ ሰዎች ከቤተክርስቲያን የሰሙትን ሁሉ ማመን ለመደባቸው። ይህ ልማድ እስከዛሬም ድረስ ቀጥሏል።

ንጉስ ኮንስታንቲን በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ሰዎች እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች እንዲያምኑባቸውና የሥላሴ ትምሕርትን እውነት አድርገው እንዲቀበሉ አስገደደ። ይህም የተደረገው ክርስቲያኖች እና አረማውያን በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስር ወደ አንድነት እንዲመጡ ተብሎ ነው። ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የሥላሴ ትምሕርት ከተቀበሉ በኋላ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ማንኛውንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶችን ለመቀበል አእምሮዋቸውን ክፍት አደረጉ፤ ከእነዚህም ውስጥ ለምሳሌ መዳን ከፈለጋችሁ ለሮማ ፖፕ ራሳችሁን ማስገዛት አለባችሁ የሚለው እምነት ተጠቃሽ ነው።

ሌላው ደግሞ በገንዘብ የሐጥያት ስርየትን የመግዛት እምነት ነው። ከዚያ ወዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማመን አስፈላጊነቱ ሁሉ ተረሳ።

ከዚያም የእግዚአብሔር ስም ተረሳ። ሦስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። አንድ ክርስቲያንን የእግዚአብሔር ስም ማን እንደሆነ ጠይቁትና እንዴት እንደሚደናገር ታያላችሁ። ሦስት የተለያዩ አካላትን በሃሳባቸው ስለሚያዩ የአንድ እግዚአብሔር ስም ሲባል አይመጣላቸውም። ስለዚህ ሦስት የማዕረግ መጠሪያዎች የእግዚአብሔር ስም ናቸው ብለው እስኪያምኑ ድረስ ተታልለዋል።

“በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” እያሉ መናገር ለምዶባቸዋል፤ ነገር ግን የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩዋችሁ አይችሉም።

የጌታ ሐዋርያት ሁልጊዜ ሰዎችን በኢየሱስ ስም ነው ያጠመቁት፤ ምክንያቱም የመለኮት ሙላት በእርሱ ውስጥ ነው ያለው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ይህም ስም የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው።

ቤተክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ስም እንዲረሳ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ኢየሱስ ክርስቶስን የሥላሴ ሁለተኛው አካል በማለት ክብሩን ቀንሰዋል፤ ደግሞም የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብለው በማጥመቃቸው ተሳስተዋል ይላሉ። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች የቀድሞዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ወደነበረችበት እምነት መመለስ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሐዋርያት የተሳሳቱትን ስሕተት እናስተካክላን ብለው ያምናሉ። ቤተክርስቲያኖች እንደሚያስቡት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መስተካከል ያለበት ስሕተት አለ፤ ከዚህም የተነሳ ለእነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት አይደለም። ይህም ለወደፊት ትልቅ አደጋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብሎ ማመን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ማመጽ ነው።

አይሁድ በተጠመዱበት ስሕተት እና ኋላም ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን በምትጠመድበት ስሕተት የተነሳ ብዙ ሰዎች እንደማይድኑ ሉቃስ አስቀድሞ ይጠቁማል።

ሉቃስ አይሁዳውያን እና መሪዎቻቸው የሚሰሩዋቸውን ስሕተቶች በግልጽ ያሳየናል ምክንያቱም የእነርሱ ስሕተት ቤተክርስቲያን እና መሪዎቿ ከሚሰሩዋቸው ስሕተቶች ጋር አንድ አይነት ናቸው።

በመሰረቱ አይሁድም ሆነ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጸንቶ መኖር የሚችል አይመስልም።

ሁላቸውም ለአእምሮ ማራኪና ሰው ሰራሽ ወደሆኑ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወዳልተጻፉ ሃሳቦች እየተሳቡ መሄድን ይወዳሉ።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ የሰውን ልማድና አስተሳሰብ አብልጠን እንወዳለን።

ሳንታ የመጣው ከየት ነው? “ን” የተባለውን ፊደል ከመሃል አውጥተን ወደ መጨረሻ ስናመጣው “ሳታን” ወይም ሰይጣን የሚል ቃል እናገኛለን።

ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።

ክሪስማስን ማክበር ማለት ጳውሎስ እንደተናገረው ዳግመኛ ባሪያ መሆን ነው። ቀኖችንና በዓላትን ማክበር ጳውሎስ ሕዝቡን ለመርዳት የደከመውን ድካም ከንቱ እንዳያደርግበት ፈርቷል።

25ኛ ቀን። 12ኛ ወር። የገና ወይም የክሪስማስ በዓል። በየዓመቱ የሚከበር የኢየሱስ የልደት ቀን።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የኢየሱስን ልደት እንድናስብም ሆነ እንድናከብር አንድም ጊዜ አልታዘዝንም።

አሕዛብ ግን የቤተክርስቲያን ልማዶቻቸውንና በዓላቶቻቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ይወዳሉ።

በጨለማው ዘመን ውስጥ እኛን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለማለያየት ነው የተዘራው ዘር በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ታላቅ ፍሬ እያፈራ ነው።

ዛሬ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል በሚሞክሩ ጥቂት ሰዎች ላይ ያምጹባቸዋል።

ሉቃስ 13፡22 ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ከተማዎችንና መንደሮችን እያስተማረ ያልፍ ነበር።
23 አንድ ሰውም፦ ጌታ ሆይ፥ የሚድኑ ጥቂቶች ናቸውን? አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፦
24 በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።

“የጠበበው” ደጅ ቀጭን የውሃ መውረጃ ነው። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ እኛ ሰዎች የምናምነው እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የማረጋገጥ ፍላጎታችን ጠፍቷል። ከዚህም የተነሳ በቃሉ ውሃ ውስጥ አንቆይም።

ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት…

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ባመናችሁ ጊዜ ወዲያው ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚያስገባው ቀጭኑ የውሃ መንገድ ወጥታችኋል።

በፍጹም ልብ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል በዚህ ዘመን ለክርስቲያኖች ትልቅ ቁምነገር መሆኑ ስለቀረ ወደፊት እንደ ደራሽ ውሃ ጠራርጎ ሊወስደን እየመጣ ካለው ከታላቁ መከራ ብዙ ክርስቲያኖች አይድኑም፤ ይህም እግዚአብሔር ወደ ቀጭኑ የውሃ መንገድ ማለትም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የተመለሱትን ጥቂች ክርስቲያኖችን ወደ አየር ላይ ነጥቆ ካልወሰደ በቀር።

ከሲኦል መዳናችን ከታላቁ መከራ ለመዳናችን ዋስትና አይሆንም። ሁለቱ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው።

ሉቃስ 13፡25 ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላችኋል።

ሉቃስ 13፡26 በዚያን ጊዜም፦ በፊትህ በላን ጠጣንም በአደባባያችንም አስተማርህ ልትሉ ትጀምራላችሁ፤
እነዚህ ወደ እርሱ የሚጮሁት የዳኑ ክርስቲያኖች ናቸው።

ሉቃስ 13፡27 እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል።

አመጸኝነት ማለት ማድረግ የሌለብንን ነገር እያወቅን ማድረግ ነው። እግዚአብሔር የየተራቀቀ የሰው አስተሳሰብና ወግ ምንም አያስደንቀውም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ አንዳች ነገር ካመንን እግዚአብሔር ዳግም ምጻቱን በተመለከተ ከእኛ ዘንድ አንዳች ጉዳይ አይኖረውም።

ክርስቶስን የግል አዳኛችን አድርገን መቀበል ከሲኦል ያድነናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በመኖር ከታላቁ መከራ መዳንም አለብን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ እንዲሆኑት የሚፈልገው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ክርስቲያኖችን ብቻ ነው። የክርስቶስ ሙሽራ በስሙ መጠራት አለባት። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ አለብን። በስሙ የምንጠራበት ሌላ መንገድ የለም።

ሉቃስ 13፡28 አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

የዳኑ ክርስቲያኖች ለሙሽራይቱ መነጠቅ አለመብቃታቸውን ሲያዩ ለማመን እንኳ ይቸግራቸዋል። አለመነጠቃቸው በስሕተት ምክንያት ነው ብለው መከራከራቸውም አይቀርም። የተወዳጅዋ ሒላሪ ክሊንተን በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አለማሸነፏን ሲያዩ ማመን አልቻሉም። ከትራምፕ የበለጠ ሦስት ሚሊዮን የምርጫ ድምጽ ልታገኝ ትንሽ ነበር የቀራት። ድምጾቹ ድጋሚ እንዲቆጠሩ ተጠየቀ ግን ድጋሚ መቁጠሩ ምንም ለውጥ አላመጣም። ሰው ሁሉ የናቀውና ተንታኞቹ በፍጹም ያልጠበቁት ትራምፕ አሸነፈ። የምንሰማ ከሆነ ይህ ክስተት ለዘመናችን ትልቅ ምልክት ነው። የዳኑት ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚመቻቸውን ብቻ እየመረጡ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ወደ ኋላ ሲቀሩ ይደነግጣሉ፤ ኩራታቸውም እሾህ እንደወጋው ፊኛ ተነፍሶ ኩምሽሽ ይላል። ሰው የጣላቸው ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ክርስቲያኖች ግን ይነጠቃሉ። ወደፊት ቤተክርስቲያኖችን ታላቅ ድንጋጤ ይጠብቃቸዋል። አሁን በሰው ዘንድ ተወዳጆች ናቸው፤ ኋላ ግን ተጎጂዎች ይሆናሉ።

ሉቃስ 13፡29 ከምሥራቅና ከምዕራብም ከሰሜንና ከደቡብም ይመጣሉ፥ በእግዚአብሔርም መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ።

በሙታን ትንሳኤ ጊዜ በሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ይነሳሉ።

ሉቃስ 13፡30 እነሆም፥ ከኋለኞች ፊተኞች የሚሆኑ አሉ፥ ከፊተኞችም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።

በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚታጨደው የበቆሎው ወይም የስንዴው እህል በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ከተዘራው ዘር ጋር አንድ አይነት መሆን አለበት። ስለዚህ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በአስተምሕሮ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለበት። በሌላ አነጋገር በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ያምኑበት የነበረውና ኋላ በጨለማው ዘመን የጠፋው የሐዋርያቱ የአዲስ ኪዳን አስተምሕሮ የእውነት ተመልሶ ሊመጣና ሊያንሰራራ የሚችለው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው።

መከሩ ውስጥ ለመታጨድ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ካመነችው እምነት ጋር በአንድ አይነት መስመር መጓዝ አለብን። የክርስቲያን ቤተክርስቲያኖች እግዚአብሔር በማዳን እቅዱ ውስጥ እንዲህ አይነት መንገድ እንዳለው ፈጽመው አይውቁም።

ሉቃስ 13፡31 በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት።

ንጉሥ ሔሮድስ የሚወክለው ፖለቲካዊ ሥርዓትን ነው። ኢየሱስ ለሔሮድስ አንድም ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ አያውቅም፤ ስለዚህ ሐይማኖት እና ፖለቲካ መደባለቅ እንደሌለባቸው አሳይቶናል። ይህም ቤተክርስቲያን ኋላ የረሳችው አስፈላጊ ትምሕርት ነው። የሮማ ነገሥታት ሦስት ሚሊዮን ክርስቲያኖችን ገድለዋል። በ312 ዓ.ም ንጉሥ ኮንስታንቲን በክርስቲያኖች ላይ የሚደረገውን ግድያ አስቆመ።

ክርስቲያኖችም ለዚህ ውለታው ሊያመሰግኑት ፈልገው ፖለቲከኛ መሆኑን እያወቁ በቤተክርስቲያን ላይ ሥልጣን እንዲኖረው አድርገው ተቀበሉት። እርሱም በ325 ዓ.ም ያዘጋጀውን የኒቅያ ጉባኤ ተጠቅሞ ክርስቲያኖችን የሥላሴ ትምሕርት እንዲቀበሉ አስገደዳቸው፤ እነዚሁ ክርስቲያኖች ናቸው ኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሆኑት። ዛሬ ለመረዳት በሚከብዱን ምክንያቶች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን ተቀበለችና በአንድ መቶ ዓመታት ውስጥ የሮማ ነገሥታት ይገድሏት የነበረችዋ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እራሷ በሥላሴ ትምሕርት የማያምኑትን ሰዎች ሁሉ እያሳደደች የመግደል ፖሊሲ አውጥታ መከተል ጀመረች።

ሉቃስ 13፡32 እንዲህም አላቸው፦ ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ፦ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፥ በሦስተኛውም ቀን እፈጸማለሁ በሉአት።

ኢየሱስ ከፖለቲከኛው ከሔሮድስ ጋር አንዳችም ሕብረት አልነበረውም። ቀበሮ ብልጣ ብልጥ ተንኮለኛ እንስሳ ነው። የፖለቲከኞችም እርግማን ይኸው ነው፤ ወደ ፖለቲካ ሲገቡ ተንኮለኞች ይሆናሉ። ጲላጦስ ወደ ሔሮድስ ሲልከው ኢየሱስ ሔሮድስን አንድ ቃል እንኳ ለማናገር እምቢ አለ። ከዚህ ምሳሌ በመውሰድ የቤተክርስቲያን መሪዎች ፈጽመው ከፖለቲካ መራቅ አለባቸው።

ሉቃስ 13፡33 ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ ያስፈልገኛል።

አይሁዳዊው የፖለቲካ መሪ ሔሮድስ እስከ ቀራንዮ መስቀል ድረስ የነበረውን የእግዚአብሔር እቅድ ማደናቀፍ አልቻለም። ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ነብያት የተገደሉባት ከተማ ነበረች። ኢየሩሳሌም ከከተሞች ሁሉ ቅድስት ከተማ። ነገር ግን ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል እርሱም የሞተው በኢየሩሳሌም።

ሉቃስ 13፡34 ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፥ እናንተም አልወደዳችሁም።

ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ተቀምጦ (በታላቅ ትሕትና) የመጣውን ኢየሱስን ተቀበለችው፤ እርሱም ለሕዝቡ የዘላለም ሕይወትን ሰጠ፤ የሕዝቡ የሐይማኖት መሪዎች ግን እምቢ አሉት፤ ከተማይቱንም የሞት ከተማ አደረጓት።

በተመሳሳይ መንገድ ቅዳሳን ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ቤተክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር እምቢ ብለው ይገድሉታል፤ ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን በደስታ ያምናሉ። ከዚያም የባሰ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የሚያምኑትን ደግሞ ያወግዛሉ። እውነተኛው ደህንነታችን ያለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። ቤተክርስቲያኖች ግን መጽሐፍ ቅዱስን አይፈልጉትም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የሰውን ወግ ይመርጣሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ ልባቸው መከተል የሚፈልጉ ሰዎች ላይ ትችት ለመሰንዘር አንደኛ ማነው? ቤተክርስቲያኖች ናቸው። ሰዎች ቤተክርስቲያናቸው የምትላቸውን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን አይፈልጉም። ቤተክርስቲያናዊነት (እኔ የእከሌ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ ማለት) ቤተክርስቲያንን (እኔ የክርስቶስና የቤተክርስቲያን ነኝ የሚለውን አቋም) ተክቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ሉቃስ 13፡35 እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁም፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።

የአይሁድ “ቤት” ቤተመቅደሱ ነበር። ከዚያ ጊዜ በኋላ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ኢየሱስን ያዩት በእግዚአብሔር ስም እንደሚመጣ ንጉስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲገባ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ወዲያ አሳልፈው ሰጥተውት ይገድሉታል። በዚህም መንገድ ኢየሱስን መግፋታቸው ኋላ ታይተስ መቅደሳቸውን እንዲያፈርስ መንገድ አዘጋጀለት። ታይተስ መቅደሱን ሙሉ በሙሉ አወደመው።

መሲኁን አግኝተው ሲመጣ በደስታ ተቀበሉት፤ ግን ከዚያ ወዲያ መሪዎቻቸው መሲኁን እንዲገፉት ነገሩዋቸው፤ እነርሱም ባለማስተዋል ገፉት። ከዚያም እነርሱ እንዲሁም መሪዎቻቸው መቅደሱና ከተማቸው ሲወድሙባቸው ዋጋቸውን አገኙ። ኢየሩሳሌምም በፈረሰች ጊዜ 1,100,000 አይሁዶች ሞቱ። ኢየሱስን መግፋት ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ለማመን እምቢ ማለት አሳዛኝ ውጤቶችን ያስከትላል።