ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 12
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የእግዚአብሔርን መንግስት በሕይወታችን ውስጥ ካስቀደምን እግዚአብሔር ደግሞ የሚያስፈልገንን ይሞላልናል።
First published on the 6th of April 2020 — Last updated on the 5th of November 2022እጅግ ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ። ኢየሱስም ሕዝቡን ስለሚያስቱዋቸው የሐይማኖት መሪዎቻቸው በተመለከተ አስጠነቀቃቸው።
ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎችን አጥብቆ ይቃወማቸው ነበር።
ሉቃስ 12፡1 በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።
ግብዝነት አስመሳይነት ነው። ሰባኪዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው የምንሰብከው ይላሉ፤ ግን እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ አያሳዩም። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የሚያምኑ ሰዎችን አጥብቀው ይቃወማሉ። ሰባኪዎች በአፋቸው እግዚአብሔርን እንወዳለን ይላሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አስተማርን ብለው ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን ነው የሚያቀርቡት።
ማቴዎስ 15፡8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
ሰዎች የራሳቸውን እምነት ሲፈጥሩ ሙሉ በሙሉ ጊዜ ማባከን ብቻ ነው ውጤቱ። “በከንቱ” ማለት ያለ ምንም ዋጋ እና ያለ ምንም እርባና ጥቅም የሌለው ማለት ነው።
ሰው “የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ” ከጊዜ በኋላ “የእግዚአብሔር ድምጽ” አድርጎ ለውጦታል። ሰዎች ዘወትር እውነትን ይበርዙታል።
ሰባኪዎች ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ መግባታቸውን ማመን በጣም ያስፈራቸዋል። የ80 ዓመት እድሜ ያላት እድሜ ልኳን የቤተክርስቲያን አባል ሆና የኖረች ሴትዮ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ መግባታቸውን ሰምታ እንደማታውቅ ተናግራለች። ሌላ ሴትዮ ደግሞ አንድ ሰውዬ ሰብዓ ሰገል እቤት ውስጥ መግባታቸውን ስለተናገረ ብቻ ሲኦል ግባ ብሎ ረገመችው። ይሄ ሰውዬ የሰራው ትልቅ ሐጥያት ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ስለሆነ ሰውየውን እንድረግመው እግዚአብሔር ተናግሮኛል አለች። በዚሁ ርዕስ ላይ ጥያቄ ሲቀርብለት እስር ቤት ውስጥ እያገለገለ የነበረ ሰባኪ መጽሐፍ ቅዱስን ሳይከፍት ድምጹን ከፍ አድርጎ “የኔ መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ ገብተዋል ነው የሚለው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ ተከፍቶ ሲነበብለት በቁጣ አፍጥጦ ተመለከተና ምንም ሳይናገር ጸጥ ብሎ ወጣና ሄደ።
ለምንድነው ብዙ ሰዎች ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ መግባታቸውን የሚክዱት? ሊደብቁ የሚፈልጉት ነገር ምንድነው?
ሼክስፒር እንዳለው በቤተክርስቲያን ውስጥ “የሆነ የተበላሸ ነገር አለ”።
ሉቃስ 12፡4 ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ።
አሸባሪዎችና የሐይማኖት አክራሪዎች ሊገድሉን ይችላሉ። እነዚህ ጥሩ ሰዎች አይደሉም። በእነርሱ እጅ መሞት ከባድ ነገር ነው፤ ግን የነፍሳችሁ የመጨረሻ እጣ ፈንታ ላይ አንዳችም ተጽእኖ የለውም።
ሉቃስ 12፡5 እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እርሱን ፍሩ።
የሐይማኖት መሪዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ትምሕርት ያስተምሩዋችኋል። “ሥላሴ”፣ “አንድ አምላክ በሦስት አካላት”፣ “አንድ በሦስት”፣ “የመለኮት ሁለተኛው አካል”፣ “እግዚአብሔር ወልድ”፣ “ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው”፣ “እረኛው ፓስተሩ ነው”፣ “አሥራት የሚገባው ለፓስተሩ ነው”፣ “ኢየሱስ የተወለደው ዲሴምበር 25 (ወይም ታሕሳስ 29) ቀን ነው”፣ “የጌታን ልደት አክብሩ”፣ “ሰብዓ ሰገል ሕጻኑን ኢየሱስን ለማየት ወደ በረት ውስጥ ገቡ”፣ “ሴቶች ቢሰብኩ ችግር የለውም”፣ “ጽንስ ማቋረጥ ተፈቅዷል”፣ “የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ችግር የለውም” እና የመሳሰሉ ትምሕርቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም።
እነዚህ የዘመናዊ “ክርስትና” የጀርባ አጥንት የሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተፋቱ የትምሕርት አይነቶች ዘርዝረን ብንጽፋቸው አያልቁም።
ብዙ ሰዎች ያመኑበትን ስሕተት እውነት ነው ብለህ እያመንክ ብትሞት የነፍስ እጣ ፈንታ ምንድነው የሚሆነው? ጳውሎስ እና ሐዋርያቱ በመጀመሪያ ካስተማሩት ትምሕርት ርቀህ የሄድከው ለምንድነው? እነ ጳውሎስ እነዚህን ትምሕርቶች አስተምረው አያውቁም።
ይህን ሁሉ ስሕተት የሚያስተምር ማነው? የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን ናቸዋ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን የምናስተምር መልካም ሰዎች ነን ስለሚሉ በሥጋ ላይገድሉህ ይችላሉ። ነገር ግን ነፍስህ ለሲኦል አደጋ እንድትጋለጥ ያደርጓታል፤ ይህ ደግሞ በሥጋ ከመግደልም የከፋ ነው።
እግዚአብሔር ስለ እኛ ሁሉን ያውቃል፤ ደግሞ ቤተክርስቲያን ጣል ጣል ብታደርገንም እርሱ ይንከባከበናል።
ሉቃስ 12፡7 ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲያስ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።
የቤተክርስቲያን ወግ ጫና እያደረገብን ሳለ ተቋቁመን ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ስንል መቆም እንችላለን? የቤተክርስቲያን መሪዎቻችንን ትምሕርት ለመጠርጠርና በእነርሱ ዘንድ ተወዳጅነታችንን ለማጣት ወኔው አለን?
ሉቃስ 12፡8 እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤
የቤተክርስቲያን መሪዎች ሲያፈጥጡብንና የቤተክርስቲያን አባላት ሲገፉን ፈርተን እጅ በመስጠት ከስሕተታቸው ጋር አብረን ተጎትተን እንሄዳለን?
ሉቃስ 12፡9 በሰውም ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል።
10 በሰው ልጅም ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ ግን አይሰረይለትም።
መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ሲገልጥና የቤተክርስቲያን አባላት እንዲሁም መሪዎች የቤተክርስቲያን ወጎቻቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ እነዚህን ክርስቲያኖች ሰይጣኖች ናችሁ ሲሉዋቸው የዛን ጊዜ ቀዩን መስመር እያቋረጡ ናቸው።
ሉቃስ 12፡11 ወደ ምኵራቦችና ወደ መኳንንቶችም ወደ ገዢዎችም ሲጐትቱአችሁ፥ እንዴት ወይም ምን እንድትመልሱ ወይም እንድትናገሩ አትጨነቁ፤
12 መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና።
እውነት ሁልጊዜም ተቃውሞ ይገጥማታል ሁሌም ትሰደዳለች። ስለዚህ ተጠንቀቅ፤ ከተሰበከው ስብከት ሁሉ ጋር እየተስማማህ ሰውን ሁሉ ለማስደሰት ተመችቶህ የምትኖርበት የቤተክርስቲያን ሕይወት እውነትን የመከተልህ ማስረጃ አይሆንም።
ሉቃስ 12፡15 የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው።
ዛሬ የእግዚአብሔር በረከት ምልክት አድርገን የምንቆጥረው ሃብትን ነው። ይህ ግን አደገኛ ስሕተት ነው። ይህንን መንገድ ተከትለህ አትሂድ።
ገንዘብህን እያጣህም ቢሆን እግዚአብሔርን ለመከተል ዝግጁ ነህ?
ሉቃስ 12፡16 ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት።
ይህ ሃብታም ሰው ያመረተውን እህል በሙሉ የሚያከማችበት ተለቅ ያሉ ጎተራዎች ለመስራት አሰበ። ለብዙ ዓመታት አስተማማኝ የሆነ የገንዘብ መጠን አከማችቷል። ስለዚህ አሁን ተኝቶ አረፍ ብሎ መብላት መጠጣትና መዝናናት ይችላል። ነገር ግን የዛኑ ሌሊት ሞተ፤ ሞኝ መሆኑም ተጋለጠ።
ሉቃስ 12፡21 ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።
የእግዚአብሔር መዝገብ ወይም ሃብት እውነት ነው። እውነትን እመን እውነትን ተከተል፤ የዛኔ በሰማያት ቤት ታገኛለህ። ይህ ነው እውነተኛው ሃብት። ነፍስህን ማቆሚያ በሌለው ሃብት የማከማቸት ምኞት ከምትሞላት ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ።
ማቴዎስ 19፡24 ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።
ገንዘብህ በበዛ ቁጥር ወደ መንግስተ ሰማያት መግባትም ከባድ እየሆነብህ ይሄዳል።
ለቁሳዊ ፍላጎታችን መጨነቅ አያስፈልገንም። ለገንዘብ የምንጨነቅ ከሆነ ማድረግ የማይገባንን ብዙ ክፉ ነገር እያደረግን ያለ ጊዜያችን ወደ መቃብር እንፈጥናለን (ለምሳሌ ግብር ላለመክፈል እናጭበረብራለን፤ ከሥራ ላይ ደግሞ እንሰርቃለን)።
ሉቃስ 12፡22 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።
30 ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል።
ክርስቲያን ሆነህ ሳለ ትልቁ ፍላጎትህ ኑሮን ለማሸነፍ ከሆነ ካላመኑ ሰዎች በምንም አትሻልም፤ ምክንያቱም እነርሱም የሚጨነቁት ለዚሁ ነው።
ሉቃስ 12፡31 ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
ከሁሉ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማመን እና ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ላይ ትኩረት አድርግ። በሕይወት ስንኖር ዋናው ዓላማችን ይህ ነው መሆን ያለበት። የእግዚአብሔርን ምሪት ተከተል፤ ምሪቱ ወዴት እንደሚያደርስህ ባይገባህም ተከተለውና ከዚያ የፈለገውን እንዲጨምርልህ ለእርሱ ተውለት። አንዳንድ ነገሮችን ከአንተ ዘንድ ሲያስወግድ አታጉረምርም። ላንተ መልካም የሚሆነው ምን እንደሆነ እርሱ ያውቃል እንጂ አንተ አይደለህም የምታውቀው።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
“ታናሽ መንጋ” -- በስተመጨረሻ በእውነተኛው መንገድ ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖች በጣም ጥቂት ነው የሚሆኑት። ስለዚህ በሕዝብ ብዛትና በዝነኛነት አትታለል።
ትልቁ ሽልማታችን የሚሆነው በሰማያት የተዘጋጀልን መኖሪያ ቤት ነው። ይህንን ሽልማት በተመለከተ እግዚአብሔርን ከመከተልና ከመታዘዝ ውጭ ምንም ልናደርግ አንችልም፤ ምክንያቱም ሊሰጠን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። ስለዚህ ትልቁን ሽልማት ይሰጠናል ብለን የምንጠብቀው ከሆነ በምድር ላይም ለመኖር የሚያስፈልገንን እንደሚሰጠን የማናምነው ለምንድነው? ስለዚህ ያስፈልጉናል የምንላቸውን ቁሳቁሶች ለምንድነው ተግተን የምንሯሯጥላቸው?
ሉቃስ 12፡34 መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
የሰዎች ችግር ዓይኖቻችን በማይታዩ መንፈሳዊ ነገሮች ላይ በማድረግ ፈንታ በሚታዩ ፍጥረታዊ ነገሮች ላይ ማድረጋችን ነው። በዓይን የሚታይ ነገርን እንደ ሃብት እንቆጥራለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የማሰብ ችሎታችንን እንዲለውጠው ብንፈቅድ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኝ መገለጥ በምድራችን ላይ ካለ ከማንኛውም ነገር ሁሉ እንደሚበልጥ እናስተውላለን።
ሉቃስ 12፡35 ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
2ኛ ሳሙኤል 20፡8 … ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፥ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፥ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ …
መታጠቂያ በሰው ወገብ ዙርያ የሚጠመጠም ጨርቅ ሆኖ የሰይፉን ሰገባ ወገቡ ላይ አጥብቆ የሚይዝ ነው።
ኤፌሶን 6፡14 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥…
እውነት በሰው ወገብ ውስጥ ካለ ሕይወት ጋር ነው የሚዛመደው።
በዚህ የእውነት መታጠቂያ አማካኝነት ነው የእግዚአብሔርን ቃል ሰይፍ አጥብቀን የምናስረው፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል በእኛ ዘንድ ያለው ብቸኛው እውነት ነው።
ኤፌሶን 6፡17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ወገባችን ሕይወት የሚፈልቅበት ምንጭ ነው።
የዘላለም ሕይወት የሚመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
መዝሙር 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
ኢሳይያስ 8፡20 ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም።
ለእኛ ያለን ብርሃን የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
2ኛ ጴጥሮስ 1፡19 ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ብቻ ነው ሊመራን የሚችለው። ከዚያ ውጭ ሁሉም ነገር ጨለማ ነው።
ብርሃናችን የሚበራው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ስንጠቅስ፤ ለሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ስንነግራቸው ብቻ ነው።
ሉቃስ 12፡40 እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
ከዳግም ምጻት ጋር የተያያዘ ነገር በሙሉ እኛ ይሆናል ብለን ከምናስበው በጣም የተለየ ነው የሚሆነው።
ሉቃስ 12፡42 ጌታም አለ፦ እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?
“ምግባቸውን በጊዜው”። በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ለዛሬ የት መሆን እንዳለብን ማወቅ ያስፈልገናል። ለዚህም ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንድንችል ዊልያም ብራንሐም ያስተማረንን ትምሕርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መሰረት ፈትነን አረጋግጠን መቀበል አለብን። ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ፍጹም የማይሳሳት መሪያችን መሆኑን መቀበል አለብን።
ከተገለጠው ከተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣበቅ አለብን። ከዚያ ውጭ ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች ላይ ትንታኔ ማድረግ አይጠቅመንም።
ሉቃስ 12፡43 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው።
44 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
ወንድም ብራንሐም ያስተማረን ትምሕርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሊሰጥ የሚችል ትምሕርት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። ለዚህ ዘመን እግዚአብሔር ያለው እቅድ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ እመኑ።
ሉቃስ 12፡45 ያ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥
47 የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤
የ“ሜሴጅ” ሰባኪዎች ሰዎች ላይ በትጋት ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን ይጭኑባቸዋል። ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል የሚፈልጉ አፈንጋጮችን ያወግዙዋቸዋል፤ ይዝቱባቸዋል። ቁጠኛ ያልሆኑ ፓስተሮች ረጋ ብለው ፈገግታ ያሳያሉ፤ ነገር ግን በአምባገነንነት ይገዛሉ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ፓስተር የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አልሆነም። ዛሬ ሕዝቡን የሚገዙት ሰው ሰራሽ ትምሕርቶችና የቤተክርስቲያን ወጎች ናቸው። ብትታዘዙ ታዘዙ አለዚያ የሚሉ ዛቻዎችም አሉባቸው።
ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመለስ እንዳለብን እያወቁ የሰው ንግግር ጥቅስና የጥቅስ ትርጓሜዎችን እየተመገቡ የሚኖሩ “የሜሴጅ” ሰባኪዎች ትልቅ አደጋ ውስጥ ናቸው። ወደ አዲስ ኪዳን እምነት እንድንመለስ የተደረገልንን ጥሩ እምቢ ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎችም በታላቁ መከራ ውስጥ ይወድቃሉ።
ሉቃስ 12፡48 ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።
ብዙ እውቀት የሌላቸው የቡድናዊ ቤተክርስቲያን ሰባኪዎች በጥቂቱ ይቀጣሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር ዓይናችንን ከከፈተ፤ ከእኛ ብዙ ይጠብቃል። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለተናገሩት ቃል ሰብካ አታውቅም፤ አዲሱ የኢየሱስ ስም ማን እንደሆነ ለመግለጥም አልሞከረችም፤ ወይም ጌታ እንደ ታላቅ ደመና ሆኖ መጥቷልም አላለችም - እግዚአብሔር ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እንድንመለስ ይፈልጋል። ደግሞ የጥቷ ቤተክርስቲያን አማኞች የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ እንደ ታላቅ ደመና ሆኖ ወርዷል ብለውም አላመኑም (ያ ደመና ከምድር 42 ኪሎሜትር ከፍ ብሎ የታየ ነበር)። የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምትስበሰበው በቤት ውስጥ ብቻ ነበር፤ የሚመራት ፓስተርም አልነበራትም። አዲስ ኪዳን ውስጥ አሥራት ለፓስተሮች እንደሚሰጥ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።
አዳዲስ የቤተክርስቲያን ሃሳቦች ሁልጊዜ መልካቸውን መቀያየራቸውን ይቀጥላሉ። ስለዚህ ሁልጊዜ እነርሱን ተከታትሎ መያዙ ከባድ ነው።
ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መመለስ ይቀላል፤ ምክንያቱም በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ መርሆች አይለዋወጡም ነበር።
ስለዚህ “የሜሴጅ” ሰባኪዎች በታላቁ መከራ ውስጥ ከበድ ያለ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስን መከተል እንዳለባቸው ያውቃሉ ግን ሰዎች ደግሞ የሰው ንግግር ጥቅሶችን ስለሚፈልጉ ብለው መጽሐፍ ቅዱስን ትተው ጥቅሶችን ማስተማር ቀጠሉ። የሜሴጅ ተከታዮች ሰው እንዲመራቸው ፈለጉ። ልክ አሮን በሲና ተራራ ላይ እንዳደረገው ፓሰተሩ ለሕዝቡ የተበከለ የወርቅ ጥጃ ስሕተት አቀረበላቸው።
ይህም ሰባኪዎችን ሃብታም አደረጋቸው፤ ግን የሜሴጅ አማኞች የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን አማኞች ካመኑበት እምነት በጣም ርቀው ሄደዋል።
ሉቃስ 12፡50 ነገር ግን የምጠመቃት ጥምቀት አለችኝ፥ እስክትፈጸምም ድረስ እንዴት እጨነቃለሁ?
ጥምቀት የሞት ምሳሌ ነው። ኢየሱስ እስከሞት ድረስ የታመነ ነበር። እንደዚህ ያለ ብርታት አለን?
ሉቃስ 12፡51 በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ።
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በቤተሰብ መካከል መለያየትን ያመጣል። ለመሆኑ የቤተሰብ አባላትን እንኳ ለመቃረን የሚበቃ ወኔ አለን?
ሉቃስ 12፡53 አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በልጅዋ ላይ ልጅዋም በእናትዋ ላይ፥ አማት በምራትዋ ላይ ምራትም በአማትዋ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።
ሉቃስ 12፡54 ደግሞም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ ደመና ከምዕራብ ሲወጣ ባያችሁ ጊዜ፥ ወዲያው፦ ዝናብ ይመጣል ትላላችሁ፥ እንዲሁም ይሆናል፤
በ1963 ደመና ለመፍጥር የሚሆን እርጠበት በሌለበት ርቀት ታላቅ ደመና በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ከአሜሪካ ምዕራባዊ ዳርቻ ካሊፎርኒያ ተነስቶ ወደ ምስራቅ በማቋረጥ ወደ ኒው ሜክሲኮ ውስጥ ወዳለው ፍላግስታፍ አሪዞና ሄደ።
ከሳምንት በኋላ ሰባት መላእክት ወደ ዊልያም ብራንሐም መጡና የሰባቱ ማሕተሞች መፈታትን አስመልክቶ እንዲሰብክ አዘዙት። እነዚህ መገለጦች ብዙዎቹን ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት እንዲችል ረዱት።
በመገለጦቹ የተነሳ የቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች ስሕተት ስለተጋለጠ መንፈሳዊ ውጊያ ተጀመረ። ነፋሳት ጦርነትን ይወክላሉ፤ ስለዚህ ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች የተገለጡት ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶች ላይ ጥቃት ሰነዘሩባቸው።
የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ከእግዚአብሔር ቃል የመጣ የመንፈሳዊ በረከት ዝናብ ነበር፤ ይህም መገለጥ ዊልያም ብራንሐም የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን የመጀመሪያ ትምሕርቶች መልሶ እንዲያመጣቸው አስችሎታል።
አንዳንድ አማኞች ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ ፈለጉ። ሌሎች ደግሞ አልፈለጉም።
ሉቃስ 12፡55 በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ፦ ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል።
ከእስራኤል በስተ ደቡብ ሞቃት የሆነው የሲና በረሃ አለ። ከደቡብ ነፋስ ወደ እሥራኤል ሲነፍስ በበረሃው ሞቃት አሸዋ ላይ ይነፍስና አየሩ ይሞቃል። በመንፈሳዊ ቋንቋ ይህ የስደትን ቃጠሎ ይወክላል። ቤተክርስቲያናት ዊልያም ብራንሐምን አወገዙት። የእርሱን ትምሕርቶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደው የሚመረምሩ ሰዎች የሰውን ንግግር ጥቅስ በሚከተሉ ነገር ግን አስፈላጊዎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አገናኝተው በማያመዛዝኑ ሰዎች ተወገዙ። በስተመጨረሻ ታላቁ መከራ ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ያልተመለሱ ክርስቲያኖችን በሙሉ ያሳድዳቸዋል።
ሉቃስ 12፡56 እናንት ግብዞች፥ የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፥ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው?
በመጨረሻው ዘመን ውስጥ መሆናችንን የሚያመለክቱ ዋና ዋና የዓለማችንን ክስተቶች ማወቅና ትርጉማቸውን መለየት መቻል ያስፈልገናል።
የዘመኑን ምልክት ለመለየት እንቸገራለን። በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ የፍርድ ቤት ክርክሮችን እንኳ ስሕተታችንን ካለመቀበል የተነሳ መፍታት ያቅተናል።
ሉቃስ 12፡57 ራሳችሁ ደግሞ ጽድቅን የማትፈርዱ ስለ ምን ነው?
58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ እንድትታረቅ ትጋ።
59 እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ግማሽ ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ከቶ አትወጣም።
ኢየሱስ ሰዎች ስሕተታቸውን አምነው ስላለመቀበላቸው በጣም ያዝናል። በእስተምሕሮዋችን መሳሳታችንን መቀበል ያቅተናል። በሥራ እንኳ መሳሳታችንን በቀላሉ አናምንም።
ለስሕተት ግትር ብሎ መቆም የዳኑ ክርስቲያኖች ወደ ታላቁ መከራ የሚገቡበት ዋነኛው ምክንያት ነው።