ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው - በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10

ኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ ላይ 70 ሰዎችን ጨመረና ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።

ሁልጊዜም ብዙ ሥራ አለ። ስንፍና የክርስቲያን ባሕርይ አይደለም።

ሉቃስ 10፡1 ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው።
2 አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዴህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።
3 ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።
4 ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።
5 ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ።
7 በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።

ደቀመዛሙርት ባዶ እጃቸውን ወጡ። የወንጌል አገልግሎት የገንዘብ ድጋፍ አይፈልግም። በየቤቱ ሰዎችን ለመጠየቅ ብለው አይዞሩም።

በአንዳንድ ከተሞች ውስጥ እየሰበኩ በሽተኞችን ይፈውሳሉ በሌሎች ከተሞች ውስጥ ደግሞ ይሰደዳሉ።

በኋላ እውነትን አንቀበልም ያሉትን ከተሞች እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።

ሉቃስ 10፡17 ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።
18 እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።

ክርስቲያኖች ሁልጊዜ መለኮታዊ ኃይል ሲገለጥ ያስገርማቸዋል።

ኢየሱስ ግን ከመጀመሪያው ሰይጣንን ከሰማያት ወርውሮ እንደጣለው ነገራቸው። ስለዚህ ኢየሱስ በሰይጣን ላይ ኃይል አለው።

ሉቃስ 10፡19 እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።
20 ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።

ኢየሱስ የራሱን ኃይል ለደቀመዛሙርት ሰጣቸው፤ ይህም አስደናቂ ነገር ነው። ነገር ግን ስኬታችን ማንም ሊያየው በማይችለው ሥፍራ በሰማያት ነው የሚጻፍልን እንጂ በምድር በምናያቸው ነገሮች መካከል አይደለም።

ይሁዳም ጭምር ይህ ኃይል እንደነበረው አስታውሱ፤ ነገር ግን እርሱ በስተመጨረሻው ገንዘብን ወደ ማሳደድ ዘወር ባለ ጊዜ ይህ ኃይል ምንም አልጠቀመውም።

ሉቃስ 10፡21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።

የሰው ብልሃት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች ሊገልጥ አይችልም። በመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ዓመታትን ማሳለፍ እውነትን ለመግለጥ አያበቃም። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የራሱ የሆነ የማሰልጠኛ ማእከል አለው፤ የሚያስተምሩትም አስተምሕሮ ከሌላው ቤተክርስቲያን የተለየ ትምሕርት ነው። ስለዚህ የማናቸው ማሰልጠኛ ነው ትክክለኛውን እውነት የያዘው? ሁላቸውም እውነተና ሊሆኑ ይችላሉ?

እግዚአብሔር እውነትን የሚገልጠው ፍጹም ላልተጠበቁ ሰዎች ነው።

ዓይኖቻችን በዓይን ኩል እንዲቀቡ መጸለይ አለብን። አለዚያ ትክክለኛውን እውነት ማየት አንችልም።

ሉቃስ ስለ ሰው ባሕርይ ሁለት ነጥቦችን ያብራራል፡-

የእውነት እርዳታ የሚያስፈልገውን ሰው ለመርዳት ሁሌ ዝግጁ ሁን፤ ነገር ግን መልካም ሥራዎች የእግዚአብሔር ቃል ከመስማት እንደማይበልጡ አስታውስ።

ኢየሱስ በመንገድ ላይ ተዘርፎ ተደብድቦ ስለ ወደቀ የሌላ ብሔር ሰው እና እርሱን ስለ ረዳው ደግ ሳምራዊ አንድ ምሳሌ ተናገረ፤ ሳምራዊውም የራሱን ገንዘብ አውጥቶ በመክፈል ሰውየውን አሳከመው።

ይህ ሳምራዊ መልካም ባልንጀራ ነው፤ ምክንያቱም ከአንድ ዘር በስተቀር ሌላ ዘር አያውቅም፤ ያውም የሰው ዘር ነው። ሰዎች እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ የዘር፣ የቀለም፣ የጎሳ ድንበሮች ሁሉ ይፈርሳሉ።

በአንድ መንደር ውስጥ ሁለት እሕትማማቾች ነበሩ። አንዷ ለደቀ መዛሙርቱ ምግብ ስታዘጋጅ ሌላኛዋ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ታዳምጥ ነበር።

ማርያም ከዚየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ትምሕርቱን ታዳምጥ ነበር።

ማርታ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱን ምግብ በማብላትና እቃ በማጠብ ተጠምዳለች። ከዚያም ማርያም በዚህ ሥራ ውስጥ ለምንድነው የማትረዳኝ ብላ ቅሬታ አቀረበች።

ለእኛ ለሰዎች ከሁለት ማርታ የምትሻል ነው የሚመስለን፤ ምክንያቱም ሌሎች ሰዎችን ምግብ ለማብላት ሥራ በትጋት ሰርታለች።

ሰዎችን ማብላት ማጠጣት በጣም አስፈላጊ አገልግሎት ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች ምግብ ካልበሉ መኖር አይችሉም።

ግን ተመልሰው ወዲያው ይራባሉ። ኢየሱስ ደግሞ ቁጭ ብሎ ነፍስ በእግዚአብሔር ቃል መመገብ እንጀራ ከመብላትም ይበልጣል አለ።

የዛኔ ለሌሎች የምታካፍሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ይኖራችኋል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ደግሞ ጥቅሙ ለዘላለም ነው። እንጀራ ቢኖርህ ሌባ ሊሰርቅብህ ይችላል፤ በልብህ ውስጥ ያስቀመጥከውን የእግዚአብሔር ቃል ግን ማንም አይወስድብህም።

ሉቃስ 10፡41 ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥
42 የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።