አንበጣ እና ማር
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
መጥምቁ ዮሐንስ ከሚበላው ምግብ ምን እንማራለን? የአንበጣና የበረሃ ማር ትርጉም ምንድነው?
First published on the 9th of December 2018 — Last updated on the 5th of November 2022ኢየሱስ ክርስቶስን ያስተዋወቀው መጥምቁ ዮሐንስ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ያደገው በረሃ ውስጥ ሲሆን መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር፡፡
ማቴ 3፡4 ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።
አንበጦች በመንጋ ተሰብስበው የሚሄዱ ሲሆን በመንገዳቸውም ላይ ያገኙትን ሁሉ ሙልጭ አድርገው ይበላሉ፡፡ ይህም ባህሪያቸው የአጋንንትን ሥራ ይወክላል፡፡ ዮሐንስ ሲበላቸው አንበጦቹን ይዘነጣጥላቸው ነበር፡፡
ይህም የዮሐንስን አገልግሎት የሚወክል ነው፤ ዮሐንስ አገልግሎቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃወሙትን የሐይማኖት መሪዎች ማውገዝ ነበር፡፡ አጋንንት ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ይቃወማሉ። ካህናት፣ ፃፎች፣ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃዊያን በሐይማኖት አማካኝነት ከፍተኛ ሐብት በማካበት ሰዎችንም ሁሉ በአንድነት በማሳደም ክርስቶስን ማለትም ቃሉን እንዲቃወሙ አነሳሱዋቸው፡፡ ዮሐንስ ደግሞ እፉኝቶች በማለት ዘነጣጠላቸው። እፉኝቶች (እባቦች) ከምላሳቸው ስር መርዝ አላቸው። የሐይማኖት መሪዎቹ የሚያሰራጩት የእግዚአብሔርን ቃል ሳይሆን የሐሰት ቃልን ነበር፡፡ ከሰባኪዎቹ አንደበቶች በሚያሳምን ንግግር የሚወጡት የሰዎች አመለካከቶችና ወጎች ሁሉ መንፈሳዊ መርዝ ናቸው፡፡
ኢየሱስ በጣም የተበሳጨባቸው ሁለት ጊዜያት በቤተመቅደስ ውስጥ በነበሩት ገንዘብ ለዋጮች ምክንያት ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሐይማኖትን ወደ ትልቅ የንግድ ስራ ቀይረውታል፡፡ ሊቀካህናቱ ቤተ መንግስት ውስጥ ይኖራል፡፡ በአሁኑ ጊዜም መጋቢው/ፓስተሩ የሚኖረው ከሁሉ በተሻለ ቤት ውስጥ ነው፡፡
የለበሰው ቀለል ያለ ልብስ እና የሚበላው ቀለል ያለ ምግብ ብልጽግና እግዚአብሔርን መምሰል ነው ብለው ያስቡ ከነበሩት የሐይማኖት መሪዎች ጋር ፊት ለፊት ይጋጭ ነበር፡፡ ጊዜ አልተለወጠም፡፡ ዛሬ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እየተጠባበቅን ባለንበትም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው፡፡
በዚህ ዘመን ግዙፍ ቤተክርስቲያኖች የስኬት መለኪያ ናቸው፡፡
ዮሐንስ ኢየሱስን አስተዋወቀ። የኢየሱስም መስዋዕትነት እንደ መልካም መአዛ ያለው ሽቶ ሆኖ ለመዳናችን ተከፍሎልናል፡፡
ይህም መልካም መዓዛ ያለው የኢየሱስ መስዋዕትነት የተመሰለው ጣፋጭ እና ሁልጊዜም የማይበላሽ በሆነው ማር ነው፡፡ ከምግቦች ሁሉ ብቸኛው የማይበላሽ ምግብ ማር ነው፡፡ ለመዳን አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፡፡ እርሱም በመስቀሉ ስር ንሰሐ መግባት ነው፡፡
ነገር ግን ከሦስት ነገሮች መዳን እንዳለብን ማስታወስ ይኖርብናል፡- ከሲኦል፣ ከኅሊናችን ኩነኔ እና ከታላቁ መከራ፡፡
ከሲኦል የምንድነው ንሰሐ በመግባትና ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን በመቀበል ነው፡፡
ከዚያም በኋላ በአግባቡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስንጠመቅ ንጹህ ህሊና ይኖረናል፡፡ ይህ ማለት የክርስትና ሕይወታችንን በተሳሳተ መንገድ ላይ አልጀመርንም ማለት ነው፡፡ ከዳንን በኋላ አልተታለልንም፡፡ የእርሱ ሙሽራ የሆነችው የቤተክርስቲያን አካል እንደመሆናችን መጠን የባላችንን ስም እንወስዳለን ወይም በእርሱ ስም እንጠራለን፡፡
ዛሬ እየተፈጸሙ ያሉት ስህተቶች (በተለይም የቤተ እምነቶች ሐይማኖታዊ መግለጫዎች ውስጥ) ምን እንደሆኑ ለማወቅና እንዲሁም የእግዚአብሔር የመጨረሻ ዕቅድ ምን እንደሆነ ለማወቅና በዳግም ምጽአቱ ሲመለስ እርሱን ለመቀበል መዘጋጀት እንድንችል የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ማወቅ ያስፈልገናል፡፡
በዚህ ዘመን በጣም ብዙ ሰው የተታለለበት ነጥብ ከሲኦል በመዳናችን ምክንያት በቀጥታ ጌታ ሲመጣ በአየር ላይ ልንቀበለው እንነጠቃለን ብሎ ማመኑ ነው፡፡
እግዚአብሔርን በመንፈስ እና በእውነት ማምለክ አለብን፡፡ ስለዚህም እውነቱን እንድናውቅ ይጠበቅብናል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ለዳግም ምጽአቱ የምንዘጋጅበት መንገድ አይደለም፡፡
ሰው ሁሉ በጅምላ እየተነዳ በሚወሰድበት የሐይማኖተኝነት መንፈስ ተጠርገን እንዳንወሰድ እውነትን ማወቅ አለብን። ይህም መንፈስ በክርስትናው ስጥ ሰላሳ ሺህ አይነት የቤተ እምነት ቡድኖችን እንዲፈለፈሉ አድርጓል (ልብ በሉ አንበጦች በቡድን ነው የሚንቀሳቀሱት)። እነዚህም እውነትን ያልያዙ ቤተ እምነቶች ብዙ ሰዎችን ወደ ታላቁ መከራ እየነዱ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ ምን ይበላ እንደነበር በተለይ ጠቅሶ የነገረን ለምንድነው? አንድ ሰው በረሃ ውስጥ ሲኖር ሊበላ ከሚችላቸው ነገሮች ሁሉ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ለምን ተጠቀሱ? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህች የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራይቱን ለመውሰድ ከመምጣቱ በፊት ምን መጠበቅ እንዳለብን ፍንጭ እየሰጠ ነው። ይህንንም ፍንጭ የሚያገኙት እውነትን በጥልቀት ለመቆፈር ፈቃደኛ የሆኑ ብቻ ናቸው፡፡
ዮሐንስ የበረሃ ሰው ነበር። ወደ ከተማ ሲገለጥ ለሚመጣው መሲህ የሚያዘጋጅ የንስሐ መልዕክት ይዞ ነበር የመጣው፡፡ መልዕክቱም ብዙ የሐሰት ትምሕርቶችን በተመለከተ ተግሳጽ የሚያስተላልፍ ነበር። ይህም ደግሞ በሐይማኖት መሪዎች ዘንድ አልተወደደለትም፡፡
ማቴዎስ 3፡1-2 በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።
3 በነቢዩ በኢሳይያስ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።
የዮሐንስ መልዕክት ግልጽ ሲሆን ዓላማውም ግልጽ ነበር፡፡ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች ላይ የማይደራደር ሲሆን ይህም የሐይማኖት መሪዎች ከነበሩት ካህናት፣ ጻፎች፣ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ጋር አጋጭቶታል፡፡
ማቴ 3፡7፡- ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ።
እንግዲህ ከዚህሁሉ ምን እንማራለን? ደግሞስ ይህ ከዮሐንስ አመጋገብ ጋር ምን ያገናኘዋል?
እስቲ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ « ማር » የተፃፈውን እንመልከት፡፡
ማር፡-
ዮሐንስ ከሚበላቸው ምግሞች የመጀመሪያው ማር ነው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ዓይነት ማር አይደለም፤ የበረሃ ማር መሆኑ በጥንቃቄ ተጠቅሷል፡፡
ይህም በማንኛውም የሰው ሰራሽ ሂደት ያልተነካካ ማር ማለት ነው፡፡ አንዳችም የሰው አመለካከት እና ሰው ሰራሽ ወጎች ያልነካኩት፡፡
ማር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ የተጠቀሰ ሲሆን እንዴት እንደተጠቀሰ ተከታትለን ስናጠና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ማወቅ እንችላለን፡፡
ዘጸአት ውስጥ ማር የተስፋይቱ ምድር ውስጥ ከሚገኙ በረከቶች አንዱ ነው፡፡
ዘፀአት 3፡17 ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ በላቸው።
በመጽሐፈ ሳሙኤል ውስጥ የዓይን መከፈት ወይም መገለጥ መቀበልን ያመለክታል፡፡
1ኛ ሳሙኤል 14፡25 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ዱር ገባ፤ ማርም በምድር ላይ ነበረ።
26 ሕዝቡም ወደ ዱር በገባ ጊዜ እነሆ፥ የሚፈስስ ማር ነበረ፤ ሕዝቡ መሐላውን ፈርቶ ነበርና ማንም እጁን ወደ አፉ አላደረገም።
27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ባማለ ጊዜ አልሰማም ነበር፤ እርሱም በእጁ ያለችውን በትር ጫፍዋን ወደ ወለላው ነከረ፥ እጁንም ወደ አፉ አደረገ ዓይኑም በራ።
ዮናታን ማሩን በልቶ ዓይኑ ስለበራ ፍልስጤማዊያንን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻልና እስራኤልን እንዴት ማዳን እንደሚቻል ተገለጠለት፡፡ እዚህጋ ማር ከእሥራኤልና ከዮናታን መዳን ጋር እንዴት እንደተያያዘ ልብ በሉ። ዮናታን ሌላው ሰው ሁሉ ከሚያምነው በተቃራኒ መሄድ ነበረበት፡፡ ይህም የራሱን እና የሕዝቡን ሁሉ ሕይወት ማዳን አስችሎታል። ሳኦል ግን ይከተል የነበረውን ሐሰተኛ መገለጥ ዮናታን ባለመታዘዙ ሊገድለው ይፈልግ ነበር።
አባል ከሆንክበት ቤተክርስቲያን ወይም አጥቢያ በተቃራኒ ለመቆም ዝግጁ ነህ?
1ኛ ሳሙኤል 14፡44 ሳኦልም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ እንዲህም ይጨምርብኝ፤ ዮናታን ሆይ፥ ፈጽመህ ትሞታለህ አለ።
45 ሕዝቡም ሳኦልን፦ በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኃኒት ያደረገ ዮናታን ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም አሉት። ሕዝቡም እንዳይሞት ዮናታንን አዳነው።
ሳኦል ሕዝቡ የእውነትን መገለጥ እንዳያገኝና በክፋት ላይ የበለጠ ድል እንዳይጎናጸፍ የሚከለክለውን ጨቋኝ የሆነውን የዚህን ዘመን የሐይማኖት ስርዓት ወይም ቤተ እምነቶችይወክላል፡፡
ስህተት ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት መዘጋጀት እንዳንችል ያግደናል፡፡
በድጋሚም በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ማር ከወርቅ ይልቅ የከበረ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ስናስተውል የሚሰጥ ሽልማት ተደርጐ ተጠቅሷል፡፡
መዝሙር 19፡9 የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
ከዚህም በተጨማሪ መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ማር የእግዚአብሔር ሕዝብ የሰዎችን ምክር ከመከተል ይልቅ ቃሉን ሲሰሙ የሚሰጣቸው ሽልማት መሆኑ ተጠቅሷል። ማር የእግዚአብሔርን ሕዝብ ረሃብ የሚያጠግብ መብል ነው፡፡
መዝሙር 81፡10 ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም።
11 ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም።
12 እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ።
13 ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን
14 ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤
15 የእግዚአብሔር ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘላለም በሆነ ነበር፤
16 ከስንዴም ስብ ባበላቸው ነበር፥ ከዓለቱም ማር ባጠገባቸው ነበር።
አዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ረሃባችንን ለማጥገብ ቃል ገብቷል።
ሉቃስ 6፡21 እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና።
እውነትን ስንራብ እና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስንፈልገው እግዚአብሔር የቃሉን መገለጥ፣ ጥበብን፣ እና ማስተዋልን እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ ይህም ጠላታችንን ለማሸነፍ ብርታትና ኃይል ይሰጠናል፡፡
ምሳሌ 24፡13 ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፤ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው።
ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።
ኢሳያስ ውስጥም ማር መብላት ውጤቱ ትክክለኛውን መንገድ የመምረጥ ጥበብን እንደሚሰጥ ተጽፏል፡፡
ኢሳያስ 7፡15 ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል።
የማርን ምሳሌነት መገንዘብ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ማር በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ተጠቅሶ ስናገኘው ምንን እንደሚያመከልክት በትክክል መረዳት እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስንና በውስጡ ያሉትን ተምሳሌቶች ከነትርጉማቸው እንድናውቅ ይፈልጋል፤ ይህም ትንቢቶቹን በትክክል ለመተርጐም እንድንችል ይረዳናል፡፡
ራዕይ 10፡9 ወደ መልአኩም ሄጄ፦ ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ አልሁት። እርሱም፦ ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች አለኝ።
ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።
እስካሁን ባየነው መሰረት ዮሐንስ የበላው ትንሽ መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል (መጽሐፍ ቅዱስ) እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ እንዲሁም ሰይጣንንና የጨለማ ኃይላትን ሁሉ እንዴት እንደሚያሸንፋቸው የሚያሳየውን ጣፋጭ መገለጥ እና መረዳት የምናገኘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ ይህን መገለጥ መቀበል ሽልማቱ የዘላለም ሕይወትን ማግኘትና ከታላቁ መከራ ማምለጥ ነው፤ ግን መራራ ዋጋ ያስከፍላል ይህም በብዙዎች ዘንድ እንዲሁም በሐይማኖት ማሕበረሰብ ዘንድ ጭምር ተቀባይነትን ማጣት ነው፡፡ ስለ እውነት ብለን በምንም ዓይነት መራራ ሁኔታ ውስጥ ብናልፍም እግዚአብሔር የሚታደገን ሲሆን እንዴት እንደታደገን የምንሰጠው ምስክርነትም በአፋችን ውስጥ ጣፋጭ ቃል ይሆናል፡፡ እነዚህን መራራ ጊዜዎች መዋጥና ማብላላት አለብን ምክንያቱም ባህሪያችን የሚቀረፀው በሽንፈትና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች መዶሻነት ከተቀጠቀጠ በኋላ ነው፡፡ ከዋክብቱን ከማየታችን በፊት በጨለማ መከበብ ያስፈልገናል፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ በኤልያስ አገልግሎት ኢየሱስን እንዳስተዋወቀው፤ ከቤተክርስቲያን መነጠቅ በፊት በድጋሚ የኤልያስ ዓይነት አገልግሎት እንደሚኖር መጽሐፍ ይናገራል፡፡
ማቴዎስ 17፡10 ደቀ መዛሙርቱም፦ እንግዲህ ጻፎች፦ ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
12 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።
13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።
ኢየሱስ ኤልያስ መጀመሪያ ይመጣል ብሏል (በመነጠቅ ጊዜ ከዳግም ምፅአቱ በፊት) ነገር ግን አስቀድሞ በዮሐንስ መልክሞ መጥቶ ነበር፡፡ ስለዚህ በመጨረሻው ዘመንም ተመሳሳይ መልዕክት እንደሚመጣ መጠባበቅ እንችላለን፡፡ ይህም መልዕክት የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት እና መገለጥ የሚያመጣ ነው፤ ቢሆንም ግን በዘመኑ የሐይማኖት ተቋማት ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አስተውሉ። ደቀመዛሙርቱ የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ዓላማ ምንም አልገባቸውም ነበር፡፡ በራሳቸው የዕለት ተዕለት የሕይወት ፍላጐትና ሐይማኖታዊ ልማዶች በመተብተባቸው በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ወሳኝ የሆነውን ሥራ ማስተዋል አልቻሉም፡፡ እራሳቸውን እንደ ጥሩ ሐይማኖተኛ አይሁድ ይቆጥሩ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዘመናቸው ምን እንዳደረገ አላወቁም፡፡ ዛሬም ክርስቲያኖች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው፡፡ ቤተክርስቲያን በመመላለሳችን ብቻ እራሳችንን እንደ ጥሩ ክርስቲያኖች እንቆጥራለን፤ ግን እግዚአብሔር የዘመናት እቅዱን ለመፈጸም ዛሬ ምን እያደረገ እንዳለ አናውቅም፡፡ በአሁኑ ወቅት 30 ሺህ ዓይነት የተለያዩ ቤተእምነቶች ይገኛሉ፡፡ እያንዳንዱ መቶ ወይም ከዚያ በላይ ቤተክርስቲያኖችና ከፍተዋል። ሁሉም እኛ ትክክል ነን ቢሉም ትምሕርታቸው ግን አንዱ ከሌላው ይጣረሳል። ይህ የባቢሎን ዓይነት ግራ መጋባት አሳማኝ ከሚመስሉ አመለካከቶችና ልማዳዊ ትምሕርቶች ጋር ስላጠላለፈን እንደደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የመጨረሻውን የእግዚአብሔር ስራ ልንስተው እንችላለን፡፡ እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ቤተእምነቶችና የቤተክርስቲያን ቡድኖች አንድ የጋራ ነገር አላቸው፤ ሁሉም በራሳቸው የሚመኩ፣ እውነትን በሙሉ ተረድተው የጨረሱና ምንም የማይስፈልጋቸው እንደሆኑ ይሰማቸዋል፡፡ ምንም አይነት ምክር ወይም ከቡድናቸው ውጭ የሚመጣ ምንም ዓይነት እርማት እንደማያስፈልጋቸው ያምናሉ፡፡ እያደገ የሚሄድውን ቁጥራቸውንና ሐብታቸውን ተመልከቱ፤ ከዚህ የተነሳ ትክክል እንደሆኑ ያስባሉ፡፡
ከምግቦች ሁሉ ብቸኛው የማይበላሽ ምግብ ማር ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃልም በፍጹም አይለወጥም፤ ዘመንም አያልፍበትም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የነበረው ኃይል አሁንም ያው ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስና ሐዋርያት ሐብታሞች አልነበሩም፡፡ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ምንም ዓይነት ሜጋ ቸርች የለም፡፡ “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ አዲስ ኪዳን ውስጥ እረኛ አንድም ጊዜ “ፓስተር” አልተባለም። ወደ አዲስ ኪዳን መሠረታዊ እውነቶች መመለስ አለብን፡፡
አንበጣ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንበጦች ከመቅሰፍት ጋር ይያያዛሉ፡፡ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ በተቆጣ ጊዜ የአምበጣ መንጋ ላከባቸው፡-
ዘጸአት 10፡12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በግብፅ አገር ላይ እንዲወጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ ስለ አንበጣዎች በግብፅ አገር ላይ እጅህን ዘርጋ አለው።
አንበጦች የብዙሃኑን አመለካከት፣ አስተምህሮ ወይም አስተሳሰብ ይወክላሉ፡፡ እነዚህ አመለካከቶች እንደመቅሰፍት ይስፋፋሉ፡፡ የአንድ ሰው መሪነትን አያስፈልጋቸውም፡፡ ለብዙሃኑ ምኞት የሚያደላ አስተሳሰብ ስለሆነ በቀላሉ ይዛመታል፡፡ አንበጦች አጋንንትን የሚወክሉ ሲሆን ባህሪያቸውም ልክ እንደአ ሸባሪዎች ነው፡፡ እንደ ሳዳም ሁሴን አይነቱን መሪ መግደል ይቻላል፤ ነገር ግን የሽብር እንቅስቃሴው በመሪዎች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ አሸባሪነትን የሚያንቀሳቅሰው ኃይል ጥላቻ እና ስልጣን ለመያዝ የሚደረግ ደም የማፍሰስ ጥማት ነው፡፡ መሪው በሌለበት ሌሎቹ ግድያውን ይቀጥላሉ፡፡
ምሳሌ 30፡27 አንበጣዎች ንጉሥ የላቸውም፥ ሁላቸው ግን በመልካም ሥርዓት ይሄዳሉ።
ናሆም 3፡15 በዚያ እሳት ይበላሻል፥ ሰይፍ ያጠፋሻል፥ እንደ ደጎብያ ይበላሻል፤ እንደ ደጎብያ ብዢ፥ እንደ አንበጣም ተባዢ።
16 ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፤ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም።
17 በአንቺ ዘንድ ዘውድ የጫኑት እንደ አንበጣ፥ አለቆችሽም እንደሚንቀሳቀሱ ኩብኩባዎች ናቸው፤ በብርድ ቀን በቅጥር ውስጥ ይቀመጣሉ፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ያኰበኵባሉ፤ ስፍራቸው በየት እንደ ሆነ አይታወቅም።
የሕዝቡ ጀግኖች፤ ፓስተሮች ወይም መሪዎች በቤተክርስቲያኖቻቸው ውስጥ፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ታዋቂ የሆሊውድ አክተሮች ወይም ዝነኛ ሙዚቀኞችም ቢሆኑ አመለካከቶቻቸውን ያሰራጫሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሕዝብ መሪዎች እንደ ግብረሰዶማዊነት፣ ጽንስ ማቋረጥ፣ ከስቃይ ለመገላገል በሚል ሰበብ የሚፈፀም ግድያን፣ ዝግመተ ለውጥንና የመሳሰሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አመለካከቶች ያስፋፋሉ፡፡ እነዚህ አመለካከቶች ከሌሎች የተሳሳቱ እምነቶች ጋር ተዳምረው ብዙሃኑን ሕዝብ ወደ ታላቁ መከራ ከዚያም ወደ ሞት ይነዱዋቸዋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ፀሐይ ያበራል፤ በቃሉም ውስጥ የክርስቶስ እውነት እንደ ሰማይ ፀዳል ይደምቃል። ይህም ብርሃን ከታላቁ መከራ ለማምለጥና የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት የሚያስፈልገንን እውነት ይገልጥልናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የብዙሃኑ አመለካከት የተሳሳተ መሆኑን በመግለጥ አንድ ሰው ለቤተክርስቲያን መነጠቅ እንዲዘጋጁ ያደርጋል፡፡ በዚህ በሚያበራ ብርሃን ፊት አንበጦች ከመሸሽ ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማጽናና መከተል አይችሉም፡፡
አንበጦች እውነትን ያጠፋሉ
ኢዮኤል 1፡4 ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፤ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፤ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።
ሰዎች ቀስ በቀስ የዓለምን እና የቤተ እምነቶችን አመለካከቶች መቀበል ሲጀምሩ መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ይላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባቸውን ይቀንሳሉ፤ መረዳታቸውም እየቀነሰ ሄዶ ከአንድ ትውልድ ዘመን በኋላ እውነቱ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ በመጀመሪያ ይታወቅ የነበረው እውነት ሙሉ በሙሉ በዓለማዊ አመለካከቶች ተውጦ ይቀራል፡፡
ነገር ግን እውነት በመጨረሻዎቹ ቀናት በድጋሚ ስፍራውን እንደሚይዝ የሚናገር የተስፋ ቃል አለ፡፡
ኢዮኤል 2፡25 የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት በኤልያስ አገልግሎት ተመስሏል፡፡ ነገር ግን ዮሐንስ ምንም ነገር ወደ ቦታው አልመለሰም ወይም መታደስን አላመጣም፡፡ ዮሐንስ ከትንቢቱ ውስጥ ለትንቢቱ ፍጻሜ የሚያስፈልገውን ዝግጅት ብቻ ነው የሰራው፡፡
ዮሐንስ 1፡22 እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።
23 እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
24 የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና፦ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።
ከማቴዎስ 17 ኤልያስ እንደሚመለስና ሁሉን እንደሚያስተካክል ከዚህ በፊት አንብበናል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ስለዚህ ይህ ትንቢት ከመጥምቁ ዮሐንስ ሌላ በሆነ ኤልያስ ሊፈጸም ይገባዋል፡፡ ሚልኪያስ ውስጥ የተጻፈው ትንቢት ውስጥ ከአስፈረው የእግዚአብሔር ቀን በፊት ኤልያስ ተመልሶ እንደሚመጣ ተጽፏል፡፡
ሚልኪያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
ስለዚህ በመጨረሻው ጊዜ ኤልያስ ይመጣል በአግልግሎቱም አንበጦች የበሏቸውን እውነቶች ሁሉ ወደ ቦታቸው ይመልሳቸዋል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ኤልያስ የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ጥላ ነበረ፡፡ ሁለቱ ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች አሏቸው፤ ሁለቱም የበረሃ ሰዎች ነበሩ፤ ሁለቱም ደግሞ በወቅቱ ከነበረው የሐይማኖት ተቋም በተቃራኒ ሰብከዋል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ ሁለቱም ከመነጠቅ በፊት በመጨረሻው ጊዜ የሚኖረውን የኤልያስን አገልግሎት የሚጠቁሙ ጥላዎች ናቸው፡፡ ልክ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሁሉ በመጨረሻው ዘመን የሚመጣው ኤልያስም ምግቡ አንበጣና (ብዙሃኑ ሕዝብ የማይቀበለው መልዕክት መስበክ) እና የበረሃ ማር (እኛን ለዳግም ምፅአቱ ለማዘጋጀት በዘመናት ውስጥ ተሰውረው የቆዩ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እንዲገልጥ እግዚአብሔር ይጠቀምበታል)።
ወደ ዮሐንስ ራዕይ ስንመለስ የአንበጦችን ተምሳሌትነት መገንዘብ እንችላለን፡-
ራዕይ 9፡3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።
(በሐይማኖት ውስጥ የሚንቀሳቀስ አጋንንታዊ አሰራር ለእስራኤል ጥላቻ አለው እንዲሁም ብዙሃኑን ለማስተማር እምነትን እና አመለካከትንም በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አስደግፎ መናገርን አይወድም)፡፡
ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው (ለመናደፍና ለማሰቃየት)።
ጭስ የፀሐይን ብርሃን ይሸፍናል፡፡ ቤተ እምነቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመለወጥ እንደ ሥላሴ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን ያስተምራሉ፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ይሸፈናል፡፡
እምነታቸው ምንጩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ከሌለው ከጥልቁ ጉድጓድ ነው፡፡
ሊጎዳ የሚችለው የጊንጡ መውጊያ ማለት ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶች የማሳመን ችሎታቸው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካሆኑ ትምሕርቶቻቸው ውስጥ ዋነኞቹ እንደ ሥላሴ፤ አንድነትበሦስትነት፣ ሦስትነት በአንድነት፣ ከሥላሴ ሁለተኛው አካል እንዲሁም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉትን ማዕረጎች ስም ናቸው ብለው ማስተማራቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚህ ዘመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ ከእንቅልፍ በድንጋጤ የሚያባንን ጥሪ ይደርሳቸዋል፤ የዛኔም የሐይማኖት መሪዎቻቸው እንዳሳቱዋቸው ይገነዘባሉ፤ ልክ የአይሁድ ሕዝብን ከጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ በፊት መሪዎቹ እንዳሳቱት፡፡
ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።
(እነዚህ አንበጦች እንደ ፍጥረታዊ አንበጦች ምግብ አይበሉም ምክንያቱም የአጋንንት መንፈስ ናቸው፡፡ሰዎችን አስተው የማጥፋት ችሎታቸው ዮሐንስ እነዚህን ክፉዎች ከአጥፊ የአንበጣ መንጋዎች ጋር እንዲያነፃፅራቸው አድርጐታል፡፡ እውነትን የሚያምኑ ሰዎች በነዚህ ሰዎች ተጽእኖ ስር አይወድቁም፤ ደግሞም ብዙሃኑንም አይፈሩም፡፡ እነርሱ በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመሩት)፡፡
የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር (በግንባርህ በኩል ወደ ጭንቅላትህ ውስጥ ስትገባ አንጐልህን ታገኛለህ፤ አእምሮህም አንጎልህ ውስጥ ነው ያለው፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ቃል መገለጥ አማካኝነት የመንፈስ ቅዱስን ምሪት የማይቀበሉ ሰዎች ብቻ ናቸው በታላቁ መከራ ወጥመድ ውስጥ የሚወድቁት)፡፡
ራዕይ 9፡5 ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም
(ጋኔን መንፈስ ነው፡፡ ሊገልህ አይችልም፡፡ ታላቁ መከራ ግን ይጀምራል)፡፡
አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።(የቤተክርስቲያን መሪዎች እንዳታለሏቸው በድንገት ሲገነዘቡ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በታላቁ መከራ ውስጥ እንደሚሞቱ ሲገነዘቡ የዳኑ ክርስቲያኖች የሚሰማቸውን ስቃይ አስቡት)፡፡
ራዕይ 9፡6 በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ አያገኙትምም፥ ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።
ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ የሚገቡ የዳኑ ክርስቲያኖች መጀመሪያ ከሁለቱ የአይሁድ ነብያት ከሙሴ እና ከኤልያስ እውነትን መማር አለባቸው፡፡ ሁሉን ቻይ አምላክ እና ጌታ የሆነውና ብቻውን ቅዱስ የሆነውን የበጉን መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ ለሌሎች ሁለት የመለኮት አካላት ቦታ አይኖርም፡፡
ራዕይ 9፡7፡- የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥
(ፈረሶች አመለካከቶችንና አስተምህሮዎችን የሚያስፋፋ ሰው ሰራሽ የሆነ ስርዓት ኃይልን ይወክላሉ)
የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥
(እነዚህ አንበጦች ወይም አጋንንት ሕዝቡ የሾማቸው ዘውድ የጫኑ የሕዝቡ ንጉስ ናቸው፡፡ ሰዎች መሪዎቻቸው፣ የሐይማኖትና የፖለቲካ መሪዎቻቸው በእርግጥ በጨለማው የአጋንንት ኃይል የሚመሩ መሆናቸውን ይገነዘባሉ)፡፡
ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፡፡
(ሰዎች ተግባራዊ የሚያደርጓቸው ሰው ሰራሽ ስርዓቶች)
ራዕይ 9፡8፡- የሴቶችን ጠጉር የሚመስል ጠጉር ነበራቸው
(ሴቶች ቤተክርስቲያኖችን የሚወክሉ ሲሆን፤ ሰው ሰራሽ ስርዓቶችም በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ይገኛሉ)፡፡
ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፡፡
(ለመዋጥና ለማውደም)
ራዕይ 9፡9፡- የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፡፡
(ብረት ማለት ጨቋኝ ማለት ሲሆን፤ የጥንት የሮማ ግዛት ኃይልና ጭካኔ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰዎች ታገዥ እንዲሆኑ ጫና ለማድረግ በድጋሚ ይነሳል)፡፡
የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ
(ይህ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ስርዓት ነው)
ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች
ራዕይ 9፡10፡- እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።
በራዕዩ ላይ የተጠቀሰው ጅራት የሚወክለው እነርሱ የሚያስተምሩትን ተረት ነው፡፡ በተረታቸው ውስጥ ያለው መናደፊያ ወይም መውጊያ ስሕተትን እንድናምን ማድረጊያ ነው፡፡ ለዚህ መልስ የምትስጠው ስትሞት ነው፡፡ “ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ?”
የሞት መውጊያ ኃጢያት ነው፡፡ ኃጢያት አለማመን ነው፤ ማለትም ከቃሉ የተለየ ትምሕርትን ማመን ነው።
ራዕይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው
(በመጨረሻም እነዚህ አመለካከቶችና አስተምህሮዎች አንድ ምንጭ እንዳላቸውና ምንጫቸውም ሰይጣን እንደሆነ ይገለጣል፤ ያኔ ግን ሰዎች እጅግ ይረፍድባቸዋል፡፡ ንጉሥ ዘውድ ይደፋል፡፡ ፖፕ ኒኮላስ 1ኛ በ860 ዓ.ም. አካባቢ ዘውድ በመድፋት የመጀመሪያው ጳጳስ ነበር፡፡ ያኔ ለመጀመሪያም ጊዜም የምዕራባዊ ቤተክርስቲያን መሪ ዘውድ ጫነ፡፡ ይህም ከ1300 መጀመሪያዎቹ አንስቶ ጳጳሳት የሚደፉት ባለ ሦስት ድርብ ዘውድ ሆኖ ተለወጠ)፡፡
እርሱም የጥልቅ መልአክ (መልእክተኛ) ነው፥
(ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም)
ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል
(እነዚህ ቃላት ትርጉማቸው አጥፊ ማለት ነው፤ እውነትን ያጠፋሉ)
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ስናምንና ስንከተለው፤ አጋንንታዊ የአንበጣ መንጋዎችን አምልጠን ከታላቁ መከራ በፊት በሚሆነው መነጠቅ እንነጠቃለን፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንደ ተስፋ ቃሉ በዊሊያም ብራንሃም አማካኝነት ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን ለመግለጥ እና በጨለማው ዘመን የጠፉ እውነቶችን ለመመለስ የነብይን አገልግሎት ልኳል። እነዚህም የመለኮት ትምሕርቶች፣ የመጀመሪያው ኃጢአት፣ የውሃ ጥምቀት፣ ሰባቱ ማሕተሞች እንዲሁም ከፍቺ በኋላ ምንም ጋብቻ መደረግ የለበትም የሚሉትን ትምሕርቶች (ምክንያቱም የጋብቻ ቃልኪዳን እስከሞት ድረስ ነው) እና የመሳሰሉ ብዙሃኑ የማይቀበሉዋቸው አስተምህሮዎች ናቸው፡፡ ብዙሃኑ ባይቀበሉዋቸውም ግን ጤናማና መጽሐፍ ቅዱስን እየመረመሩ ለሚቀበሉዋቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚገለጡ እንደ በረሃ ማር የሚጣፍጡ እውነቶች ናቸው፡፡
ራዕይ ምዕራፍ 9 የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን ስለወረሩትና ስለተቆጣጠሩት አሳቾች ገልጦ ይናገራል፡፡
ከሰማይ የወደቀው ኮከብ የሚወክለው በሰማይ የነበረ መንፈሳዊ አካል ነገር ግን በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ላይ አምጾ ተረግሞ ወደ ዲያቢሎስነት የተቀየረ ፍጡርን ነው። በአሁኑ ወቅት የዚህ ክፉ መንፈስ ሥራው በሲኦል ጉድጓድ ውስጥ ያሉትን አጋንንት ሁሉ ፈቶ በመልቀቅ እና በመጀመሪያ የቤተ እምነት አመራሮችን በመቆጣጠር በክርስቶስ ሙሽራ ላይ ለጥቃት ዘመቻ ማሰማራት ነው።
የሰዎች ዓይን በአመለካከት እና በሰዎች ወግ ጭስ ታውሯል፤ በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን በጠፋበት ጨለማ ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪዎች ስህተትንና አላዋቂነትን ማስፋፋት ይችላሉ፡፡
በዚህ እውነታና ልቦለድ በተደበላለቀበት ጊዜ ውስጥ ከትልቁ በሚወጡት የአንበጣ መንጋዎች አማካኝነት የአጋንንት አሰራር ያንቀላፉ ክርስቲያኖችን በምቹ እንቅልፋቸው አስተኝቶ ያቆያቸው ዘንድ እንደ ልቡ ይሰራል፡፡ እነዚህ ሰዎች ድነዋል፤ ግንየመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማይደግፋቸው የብልጣብልጦች ትምሕርትተውጠው ታላቁን መከራ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ አሥሩ ቆነጃጅት (ንጹህ ቤተክርስቲያኖች) እንቅልፍ ተኙ፡፡ አምስቱ ለመብራታቸው ዘይት አዘጋጅተዋል፡፡ የመብራቶቸቹ ብርሃን ጥቅሙ ለማየት ነው፡፡ ይህም የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ለማየትና ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ነው፡፡
ሉቃስ 18፡8 …ነግር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
ነገር ግን ብዙ ሰዎች የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙ እና የሚገነዘቡ አይመስልም፡፡