የቤተክርስቲያን ዘመናት - ሎዶቅያ ክፍል 3 - ከ1966 ጀምሮ - ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የሎዶቅያ መንፈስ በሌኒን እና በሌሎች ኮምዩኒስቶች አማካኝነት በዘመኑ መጀመሪያ ላይ ነው የተመሰረተው። የራሺያ አብዮት በ1917 ዓ.ም. ሲፈነዳ ጀምሮ ሌኒን የአብዮቱ ሐዋርያ ተብሎ ተቆጥሯል። ሌኒን ከሞተ በኋላ እስታሊን በእርሱ ቦታ በመተካት ኮምዩኒስቶችን ከሌኒን ትምሕርት ፈቀቅ አድርጎ በሌላ መንገድ መርቷቸዋል። ነገር ግን ኮምዩኒስቶቹ ከሌኒን አስተሳሰቦች እየራቁ በሄዱ ቁጥር ይበልጥ ሌኒንን እያከበሩ ከፍ እያደረጉ እንደ “አምላክ” እስኪቆጥሩት ደርሰዋል።
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ነብይ በነበረው በዊልያም ብራንሐምም የሆነው ልክ እንደዚሁ ነው።
ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራት ገልጦ በማስተማር ቤተክርስቲያንን ወደ አዲስ ኪዳናዊ እምነት ሊመልሳት ነበር የመጣው። ነገር ግን የሜሴጅ ሰዎች የሰው ንግግር ጥቅሶችን እና የእነዚህኑ ጥቅሶች ትርጓሜ የእምነታቸው መሰረት በማድረግ ሕዝቡን በእምነታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከመሆን አርቀው ወሰዱ።
ልክ እንደ ኢየሱስ “… ተብሎ ተጽፏል” በማለት ፈንታ “ነብዩ እንዲህ ብሏል…” ወይም “ነብዩ እንዲህ ማለቱ ነው…” እያሉ መናገድ ይቀናቸዋል።
የሜሴጅ አማኞች ከመጽሐፍ ቅዱስ እየራቁ በሄዱ ቁጥር ወንድም ብራንሐምን እያከበሩና አምላክ እያደረጉት ሄዱ። ኋላም “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” “የእግዚአብሔር ድምጽ” ተደርጎ ተቆጠረ፤ ይህ የሚገርም እድገት ነው፤ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሚሰማ የተሰጠን የተስፋ ቃል ባይኖርም እንኳ።
የቤተክርስቲያን ድክመት ሁልጊዜም መሪ የሆኑ ሰዎችን ከፍ ማድረግ ነው።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጽአት ላይ መጥምቁ ዮሐንስ ልንከተል የሚገባንን አርአያ አሳይቶናል። ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ፡-
ዮሐንስ 3፡30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።
የኢየሱስን መምጣት ያበሰረ ነብይና መንገድ ጠራጊ የነበረ ይህ ሰው ኢየሱስን በሰውነቱ ሊገልጠው እንደ ደማቅ ብርሃን ሆኖ መጣ፤ ግን ከዚያ ወዲያ ቶሎ ደብዝዞ ጠፋ። እግዚአብሔር ክብሩን ከማንም ጋር አይጋራም።
ኢሳያስ 42፡8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ … አልሰጥም።
ኤርምያስ 17፡5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።
ሰው የሆኑ መሪዎች ላይ ዓይናችንን ስንጥል ዓይኖቻችንን ከጌታ ላይ እያነሳን ነው።
ኢሳያስ 2፡22 እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
ትኩረታችን በአንድ ግለሰብ ላይ መሆን የለበትም።
ኢዮብ 4፡18 እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤
መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤
ከሰው ሁሉ የተሻሉ የሚባሉት እንኳ ይሳሳታሉ።
እግዚአብሔር የዊልያም ብራንሐምን ንግግሮች ተጠቅሞ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት እንድንመለስ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጧል። ከዚያ በኋላ ትኩራታችን በዊልያም ብራንሐም ላይ መሆን የለበትም፤ ይልቁንም ንግግሮቹ ትክክል መሆናቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየፈተንን እያጣራን መቀበል አለብን እንጂ።
ከዚያ በኋላ ያመናችሁት ትክክል መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ማረጋገጥ መቻል አለባችሁ።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
የወንድም ብራንሐም ጥቅሶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ሊመልሱን ይገባል። እርሱ የመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊያርቀን አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ለዊልያም ብራንሐም ንግግሮች የሰጡትን ትርጓሜ መከተል አያስፈልገንም።
63-1110 በናንተ ውስጥ ያለው
መልዕክቱን በሙሉ እመኑ። እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌለ ግን በፍጹም አትመኑ።
63-0630M ሦስተኛው ፍልሰት
መልእክቱ ትክክለኛ እንደሆነ አውቃለው ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ።
57-0825 ዕብራውያን ምዕራፍ 2፣ ክፍል 1
አንድ ቀን በሌሊት መልአክ መጣና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገለጠልኝ። እኔም በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሳየው መልእክቱን ይዤ በዓለም ዙርያ ሁሉ ልሮጥ ተነሳሁ።
62-0318 ቃሉ የመጀመሪያው ዘር ነው ክፍል 2
አሁን ይህ ሁሉ የተናገርኩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ባይስማማ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይሔድ ከሆነ በሙሉ ስሕተት ነው፤ ስሕተት ነው።
የእግዚአብሔርን ትኩረት መሳብ የምንችለው እንዴት ነው? እግዚአብሔር ለቃሉ ክብር የሚሰጡ ሰዎችን ይመለከታል።
65-0429 የሙሽራይቱ መመረጥ
እውነተኛይቱ ሙሽራ የእግዚአብሔርን ዓይን የምትስበው ቃሉን በመጠበቅ ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ ሰው ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ጠቆመ። ዊልያም ብራንሐም የተጻፈው ቃል ወደሆነው ኢየሱስ ጠቆመን። ስለዚህ በድምጽ ተቀድተው የተቀመጡት የወንድም ብራንሐም መልዕክቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውረው የተቀመጡትን ምስጢራት የምንፈታበትን እውቀት ይሰጡናል።
ራዕይ 10፡7 … ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
በወንድም ዊልያም ብራንሐም የአገልግሎት ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተፈጽሞ አላለቀም ምክንያቱም በቴፕ ተቀድቶ የተቀመጠው ድምጹ እርሱ በ1965 ዓ.ም ከሞተ በኋላ እንኳ መሰማተቸውን ቀጥለዋል።
እዚህ ላይ የተሰጠው ትኩረት ተቀድቶ ለተቀመጠው ድምጽ እንጂ ለሰውየው አይደለም።
አገልግሎቱ በድንቅና በተዓምራት የታጀበ አስደናቂ አገልግሎት ነበረ። እንደ ሰው እርሱም የግል አመለካከቶች ነበሩት። የራሱ ቤተሰብና ሁለት ወንዶች ልጆችም ነበሩት። ነገር ግን በዚህ ቃል ውስጥ ከእነዚህ አንዳቸውም አልተጠቀሱም።
ትኩረቱ በድምጹ ላይ ብቻ ነው። ምስጢራቱን የገለጠው እኛን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ነው።
ጥቅሱ ግን ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው ምክንያቱም “የእግዚአብሔር ምስጢር (ነጠላ ቁጥር) ይፈጸማል (እንጂ ሊፈጸም ይችላል አይልም)”
ይህም የሚናገረው ዊልያም ብራንሐም ስለገለጣቸው ብዙ “ምስጢራት” አይደለም። ብዙ የተቆለፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት ስለመግለጡ ምንም ጥርጥር የለንም።
የእግዚአብሔር ምስጢር አካሉ ማለትም ቤተክርስቲያን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የተተከለች ዘር መሆኗ ነው። ይህ ዘር በጨለማው ዘመን አፈር ውስጥ ተቀብሮ ይቆያል። በማርቲን ሉተር ተሃድሶ ውስጥ “በእምነት የመዳን” ቅጠል አቆጠቆጠ። የጆን ዌስሊ የቅድስና እንቅስቃሴ የወንጌልን ዘር በዓለም ዙርያ በሚሽነሪዎች ዘመን ውስጥ በተነው። የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፍሬ ያፈራ ይመስል ነበር ግን በውስጡ የእውነትን ኃይል አልያዘም።
ወንድም ብራንሐም የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሊመልስ መጣ። የእግዚአብሔር ምስጢር ማለት በመጨረሻው ዘመን የሚታጨደው መከር ከመጀመሪያው ሐዋርያት ከዘሩት ዘር ጋር አንድ አይነት ሆኖ መገኘቱ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስን በአየር ላይ በመነጠቅ ለመገናኘት ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ? ይህ የሚወሰነው ምን ያህል ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት በመቅረባችሁ ነው። የመጨረሻ ግባችሁ መሆን ያለበትም ይህ ነው።
ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
እዚህ ቃል ውስጥ የተጠቀሰው የአራተኛው እንስሳ ድምጽ ብቻ ነው። ይህም የሚበርረው ንስር ነው።
ይህ ከሰባተኛው መልአክ ድምጽ ጋር ይገናኛል?
ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
እነዚህ አራት መንፈሳውያን ፍጡሮች ቤተክርስቲያንን ባለፉት 2000 ዓመታት በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲመሩ ቆይተዋል።
እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በሚለዋወጠው የዓለም ሁኔታ ውስጥ ራሱን እንዴት ለቤተክርስቲያን እንደገለጠ ያሳያሉ። የአንበሳው ዘመን በሐዋርያት አማካኝነት የመጣልንን እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ይወክላል። ቃሉ ቤተክርስቲያንን በመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ደግፎ አቆይቷታል፤ በነዚያ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን ቀስ በቀስ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን በመተው የሰዎችን አመራር ስትከተል እውነቱ እየጠፋ ሄደ።
ቀጣዮቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ማለትም 3ኛው እና 4ኛው እውነተኞቹ አማኞች ስለ እውነት የታገሉበት የለፉበት ግን እንደ በሬ የታረዱበት ዘመናት ናቸው፤ በእነዚያ ዘመናት ውስጥ የሮማ ካቶሊክ መጽሐፍ ቅዱስን እና እውነትን ለማጥፋት እንዲሁም ዓለምን ወደ ጨለማ ውስጥ ለመጣል ያላትን ኃይል ሁሉ ተጠቅማ የሰራችበት ዘመናት ናቸው። በነዚያ ዘመናት ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚቆተሩ ሰዎች ተገድለዋል።
በሰው መልክ የተወከለው 5ኛው ዘመን ውስጥ እንደ ማርቲን ሉተር ያሉ የተሃድሶ መሪዎች በእምነት የመዳንን እውነት መልሰው ሲያመጡ ጆን ዌስሊ ደግሞ በ6ኛው ዘመን ውስጥ የቅድስና ተሃድሶ እንዲመጣ አድርጓል። ከዚያ ወዲያ በዓለም ዙርያ ታላቁ የወንጌል ስርጭት ወይም የሚሽነሪዎች ዘመን ተከፈተ።
ሰባተኛው ዘመን ሲመጣ የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ በንስር ክንፍ ወደ መለኮታዊ ኃይል መጠቀ። ከዚያም አስደናቂው የንስር ዓይን ዊልያም ብራንሐም በተቀበለው የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት በመረዳትና በመግለጥ የሰባተኛው ዘመን መልአክ ሆኖ ተገለጠ። እርሱም በ1965 ከዚህ ምድር ከተለየ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራት መፍታት እንድንችል ይረዳን ዘንድ ድምጹ በቴፕ ተቀርጾ ተቀምጦልናል።
በ1947 ዊልያም ብራንሐም ስብከቱን በቴፕ ቀርጾ በማስቀመጥ የመጀመሪያው ሰባኪ ነበረ። (ከዚያ በፊት ሌሎች ሰባኪዎች ድምጾቻቸውን በጥቂቱ በተለያዩ ሚድያዎች ቀድተው አስቀምጠው ነበር።) ዊልያም ብራንሐም ስብከቶቹ እርሱ እስከሞተበት 1965 ድረስ ለ18 ዓመታት በቴፕ ሲቀረጹ ቆይተዋል።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ድምጹ በቴፕ ቅጂዎች እና በኢንተርኔት ከ50 ዓመታት በላይ ሲሰራጭ ቆይቷል። በእነዚህ ሃምሳ በላይ ዓመታት ውስጥ እና እርሱ ያዘጋጀው መረጃ በአስደናቂ መንገድ በኢንተርኔት ሊሰራጭ መቻሉ ድምጹ በዓለም ዙርያ ሁሉ በቀንም በሌሊትም በማንኛውም ሰዓት እንዲገኝ አስችሏል።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ይህንን በጥንቃቄ አንብቡ። የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል። ይፈጸማል የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ ሲነበብ የጥርጣሬ ድምጸት አለው።
ወንድም ብራንሐም ሁሉን አድሶ ቢሆን ኢየሱስ እንደተናገረው ይህ ጥርጣሬ እርሱን የሚመለከት አይሆንም። እርሱ በትንቢቱ ውስጥ የተሰጠውን ድርሻ የመፈጸም ችሎታውን በተመለከተ አንዳችም ጥርጣሬ የለም።
እንግዲህ ጥርጣሬው ምንን በተመለከተ ነው?
ድምጹን የሚሰሙ ሰዎች ይኖራሉ ግን ከሰሙ በኋላ በሜሴጅ ሰባኪ ፓስተሮቻቸው አማካኝነት ይታለላሉ፤ መሪዎቻቸውም ከዊልያም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶችን ይወስዱና አጣምመው በመተርጎም ሕዝቡን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳያመኑ ያደርጉዋቸዋል።
1965-1127 መስማትን ሰምቼ ነበር አሁን ግን አየሁ
እግዚአብሔር ሆይ ይህንን የመሰለ ክብር የተሞላ ሰዓት አንድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም የነጎድጓድ ድምጽ ይሰማል የእግዚአብሔርም ልጅ ከሰማያት በታላቅ ድምጽ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት ይወርዳል፤ የዚያን ጊዜ በክርስቶስ ሆነው የሞቱት ያንቀላፉት ይነሳሉ።
ዊልያም ብራንሐም በሕይወቱ የመጨረሻ ወር ውስጥም የመላእክት አለቃውን መውረድ ሲጠባበቅ ነበር። ደግሞም ብራንሐም ብርቱው መልአክ ከመውረዱም በፊት ድምጹን የሚያሰማውን ነጎድጓድ ሲጠባበቅ ነበር። የመላእክት አለቃውን “ድምጽም” ሲጠባበቅ ነበር።
ይህንን በጥንቃቄ ማሰብ አለብን።
እንዲህ ብሎ ነው የተናገረው፡- “የነጎድጓድ ድምጽ ይሆናል… የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ይመጣል”
ስለዚህ “ድምጹ” እርሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መገለጥ የሰበከበት ድምጽ አይደለም ማለት ነው።
ድምጹ በስተመጨረሻ ሙሽራይቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ሙሉ በሙሉ በተረዳች ጊዜ እና ወደ ሐዋርያት ትምሕርት በተመለሰች ጊዜ ነው የሚሰማው።
ሙሽራይቱ ወደ እውነት ከመመለሷ በፊት ጌታ ሊመጣ አይችልም።
በስተመጨረሻ ሙሽራይቱ ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ስትመለስ በዚያን ጊዜ ድምጹ የተባለው ይፈጸማል።
ነገር ግን መልአኩ በሚወርድበት ጊዜ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ መገኘቱ የግድ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከሚመለሱት አማኞች ውስጥ አብዛኞቹ በ1965 ገና አልተወለዱም ነበር።
63-0421 የድል ቀን
ድል አግኝተናል። ብዙ ጦርነቶችን ተዋግተን ድል አድርገናል። ታላቅ ድል በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየመጣ ነው፤ በጣም ቅርብ ነው። ሙሉ የሆነው ድላችን በጣም ቅርብ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ሰማያትን ቀዶ በመላእክት አለቃ ታላቅ ድምጽ ተመልሶ ሲመጣ ይሆናል። ከዚያ ወዲያ መቃብሮች ይከፈታሉ ሙታንም ከመቃብራቸው ይወጣሉ።
… አንድ ቀን ዓይናችሁ እያየ በታላቅ ድምጽ ከሰማይ ይወርዳል በታላቅ የመላእክት አለቃ ድምጽ ይመጣል። በክርስቶስም ያንቀላፉ ይነሳሉ።
ድምጹ ገና ወደ ፊት ነው የሚሆነው።
ይህ የሆነው በ1963 ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ተሰብኮ አንድ ወር ካለፈ በኋላ ነበር፤ እርሱም በዚያን ጊዜ “ድምጹ” ገና ወደ ፊት ይመጣል ብሎ ሲጠባበቅ ነበር።
“ድምጹ” ግን የሚያመለክተው የእርሱን መልእክት ነው። ታድያ ይህ እንዴት ገና ወደፊት ይሆናል?
“ድምጹ” ማለት ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን መግለጡ አይደለም።
“ድምጹ” ማለት እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ለመመለስ እስክንችል ድረስ እውነትን ስንረዳ ስናስተውል ነው።
ትኩረት የሚደረገው ታፔላው አቅጣጫ ጠቋሚው መንገዱን ማለትም በቃሉ ውስጥ ኢየሱስን በማሳየት የጠቆመን የመጨረሻው ዘመን ነብይ ላይ አይደለም። (እርሱ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ሐዋርያት ትምሕርት እንድንመለስ ነግሮናል።)
ትኩረቱ ሊደረግ የሚገባው መንገዱ ላይ ነው። እኛ በአዲስ ኪዳን ትምሕርት መሰረት መመላለስ እንችል ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው መንገድ ላይ መሆን አለብን።
የተጻፉት ምስጢራት ከተገለጡ በኋላ ግን ሰይጣን እንዴት አድርጎ ነው “በሜሴጅ እናምናለን” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም) የሚሉትን “የሜሴጅ አማኞችን” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም) ሊያስታቸው የቻለው? እነዚህ ሜሴጅ የሚባሉ ሰዎች ባፕቲስቶችን፣ ሜተዲስቶችን እና ሌሎች ክርስቲያኖችን ለምን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስሞች ራሳቸውን ይጠራሉ ብለው ይተቻሉ፤ ነገር ግን ራሳቸውም ሜሴጅ የሚለው ስማቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
60-0515M የተገፋው ንጉስ
ከዚያ በኋላ ጠላት ገባ ጥቂት ወደሆኑ የእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ገብቶ የእያንዳንዱን ሰው ቀኝ አይን ሊያወጣ ነበር። ጠላት ሁልጊዜ ይህንን ለማድረግ ነው የሚሞክረው፤ ቢቻለው ሁለቱንም ዓይን ማውጣት ይፈልጋል፤ ይህንንም የሚፈልገው ሰዎች ምን እየሰሩ እንደሆነ እንኳ ማየት እንዳይችሉ ነው። ዛሬም ሰይጣን በያንዳንዱ ክርስቲያን ላይ ይህንን ሊያደርግ ነው የሚፈልገው፤ የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ዓይን ማውጣት ይፈልጋል፤ ከዚያም ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ትተው በፍጥረታዊ አእምሮዋቸው እና በፍጥረታዊ ዓይናቸው ብቻ እየተመሩ እንዲሄዱ ማድረግ ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚያ ጊዜ ታላቅ ሽንፈት ሲመጣ ሳኦል ሁለት በሬዎችን አረደና ቆራርጦ ለሕዝብ ሁሉ ላከ። እዚህ ላይ ልብ ብላችሁ ብታስተውሉ ደስ ይለኛል። ሳኦል የበሬውን ቁርጥራጭ ወደ እሥራኤል ዳርቻ ሁሉ በመልእክተኞች ከላከ በኋላ እንዲህ አለ፡- “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግ”።
ለማታለል ብሎ ሳኦል እንዴት ራሱን ከእግዚአብሔር ሰው ጋር አንድ ሊያደርግ እንደሞከረ አያችሁ?
ይህ የክርስትና ባህርይ አይደለም።
ሕዝቡ የፈሩት በሳሙኤል ምክንያት ነው።
ሳኦል ግን ሕዝቡ በሙሉ ወጥተው እንዲከተሉት ማድረጉ ተሳካለት ምክንያቱም ሕዝቡ የፈሩት ሳሙኤልን ነበር።
“ከሳሙኤልና ከሳኦል ኋላ ተከትለው ይውጡ።”
ሳኦል ሃሳቡ የራሱ ስለነበረ ሕዝቡ እንዲከተሉት በራሱ ስም ብቻ መጠየቅ ነበረበት። በግሉ ባደረገው ውሳኔ ውስጥ የነብዩን የሳሙኤልን ስም የመጠቀም መብት አልነበረውም። ሳኦል የራሱ አመራር የራሱ ሃሳብ ያለው ሰው ነው። ግን ነብዩ ሳሙኤል ከእርሱ ሃሳብ ጋር እንደተስማማ አድርጎ ተናገረ። ሳሙኤል ግን ሳኦል እንዳለው አላለም ነበር። ሕዝቡ ሳሙኤልን ስለፈሩ ብለው ለሳኦል ታዘዙለት።
የታዘዙለትም ሳሙኤል የሳኦልን ሃሳብ የሚደግፍ መስሏቸው ነው።
የሜሴጅ ፓስተሮች የዊልያም ብራንሐም ንግግሮችን እየጠቀሱ የራሳቸውን ሃሳብ እንዲደግፉላቸውና ፓስተሮቹን ሕዝቡ እንዲከተሉላቸው አድርገው ይተረጉሙዋቸዋል። ሕዝቡ ወንድም ብራንሐምን እንደ መጨረሻ ዘመን ነብይ ስለተቀበሉት ይፈሩታል ያከብሩትማል። ስለዚህ ሕዝቡ የወንድም ብራንሐምን ንግግሮች ጠቅሰው እያጣመሙ የሚያስተምሩ ፓስተሮችን ይፈሩዋቸዋል፤ ምክንያቱም ከወንድም ብራንሐም ጋር መከራከርን አይፈልጉም።
ይህንን ፍርሐት ለማባባስ የሜሴጅ ሰባኪዎች የወንድም ብራንሐም ንግግሮች አንዳችም ስሕተት የለባቸውም ፍጹም ናቸው ሊታረሙ አይችሉም ብለው ለሕዝቡ ይነግራሉ። ከዚያም የብራንሐም ንግግር ጥቅሶች በአንዳንድ ርእሰ ጉዳዮች ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ተክተው ቁጭ ብለዋል። ወንድም ብራንሐም “የእግዚአብሔር ድምጽ” ስለሆነ ማንም እርሱ በተናገረው ላይ ጥያቄ ማንሳት አይችልም።
እንደዚያ ግን መሆን የለበትም።
62-1104M የስድብ ስሞች
እንግዲህ ይህን ማድረግ የምትችለው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነች። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን “በስድብ ስሞች የተሞላች ነች”። ሜተዲስት፣ ፕሬስቢተሪያን፣ ሉተራን ሁላቸውም ራሳቸውን “የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያ” ብለው ሰይመዋል፤ ግን ስሞቻቸው የስድብ ስሞች ናቸው!
እራሳችንን “ሜሴጅ ውስጥ ነን” ብለን መጥራት ልክ “ባፕቲስት” ነን የማለት ያህል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ አሰራር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሜሴጅ ቤተክርስቲያን የምትባል ቤተክርስቲያን ስለመኖርዋ አልተጻፈም።
ለምንድነው ያልተጻፈው?
ወንድም ብራንሐም ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ሊመልሰን ነው የመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት፣ አማኞች፣ ክርስቲያኖች ብቻ ተብለው ነው የተጠሩት። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አይነት ክርስቲያኖች መሆን ከፈለግን ደቀ መዛሙርት፣ አማኞች ወይም ክርስቲያኖች ብቻ ተብለን ነው መጠራት ያለብን።
የጥንቶቹ ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡት በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ነበር፤ ይህም ከስደት ለማምለጥ አስችሏቸዋል። ኔሮ በ64 ዓ.ም ክርስቲያኖች ላይ ስደት ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ በ250 ዓመታት ውስጥ በቀጠለው የስደት ጊዜ በሮማ ግዛት ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ክርስቲያኖች ተገድለዋል። ከዚያም በ313 ዓ.ም ኮንስታንቲን የተባለው የሮማ ግዛት ንጉሥ በሚላን ባወጀው አዋጅ ክርስቲያኖችን መግደል እንዲቆም አደረገ።
ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
ጥቂት ሰዎች በመኖሪያ ቤት ውስጥ ይሰበሰቡ ነበር። በዚያ ጊዜ የቤተክርስቲያ ራስ ተደርጎ የሚቆጠር ፓስተር የለም። ጳውሎስ በመልዕክቱ የሚናገረው ሎዶቅያ በምትባል ከተማ ውስጥ በሰው ቤት ስላለችዋ ቤተክርስቲያን ነው። እኛ በሎዶቅያ ዘመን ውስጥ እንገኛለን። ይህ ቃል ከእኛ ዘመን ጋር የሚያገናኘው ነገር ይኖር ይሆን?
ሮሜ 16፡3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ሮም ውስጥ ስሕተትን አጥብቀው ለመቃወም ተገድደዋል ምክንያቱም ሰዎች መሪ የሚሆኑበት የቤተክርስቲያኖች ሥርዓት ዋነኛ መነሻው እዚያ ነበር። ስለዚህ በሰዎች ከመገዛት ለመዳን ፍቱን መድሐኒቱ በቤቶች ውስጥ በትንንሽ ጉባኤዎች መሰብሰብ ነው።
የክርስትና ሕይወታችንን የምንጀምረው ንሰሐ በመግባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ሕብረት በመጀመር ነው። ከዚያ በኋላ ግን አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንቀላቀልና የቤተክርስቲያን ሕብረት ውስጥ ገብተን እንቀራለን። ከዚህም የተነሳ ከኢየሱስ ጋር ያለን ሕብረት ሁለተኛ ደረጃ ቦታ ይይዛል። በመጽሐፍ ቅዱስም ፈንታ የቤተክርስቲያን እምነቶችን እንቀበላለን።
ቀስ በቀስም በውስጥችን “በክርስትና” ፈንታ “ቤተክርስቲያናዊነት” እያደገ ይመጣል።
ክርስትናችንም ከደረጃ በታች የወረደ ክርስትና ይሆናል ምክንያቱም የምንኖረው ሌሎች ሰዎች ከእኛ ምን ይጠብቃሉ ብለን እያሰብን ነው። ስለዚህ ሌሎች ሰዎችን ልናስገርም የምንችልበት ጥቅስ እንፈልጋለን። ቤተክርስቲያን እና ፓስተሩ ሐሳባችንን ሲቆጣጠሩ ኢየሱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛ ቦታ ይይዛሉ። በሕይወታችን ውስጥ ቤተክርስቲያን የኢየሱስን ቦታ ይዛ ትቀመጣለች ። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
አንድ ነገር ለምንድነው የምታምነው? ምክንያቱም ቤተክርስቲያኔ ስላስተማረች ነው።
ይህ አይነቱ አካሄድ የሚመራን ወደ አውሬው ምልክት ነው፤ እርሱም በቤተክርስቲያኖች የተከፋፈለ ሐይማኖት ነው።
VICARIVS = በ … ፈንታ FILII=ልጅ DEI = እግዚአብሔር
V I C A R I V S F I L I I D E I ይህ ጽሑፍ በሮማውያን ቋንቋ በላቲን “በእግዚአብሔር ልጅ ፈንታ” የሚል ትርጉም ይሰጣል።
ከላይ የተጠቀሱት የላቲን ፊደላት የቁጥር ዋጋም አላቸው። የእያንዳንዱ ፊደል ቁጥር ይህ ነው፡-
5 1 100 1 5 1 50 1 1 500 1
ስንደምራቸው የሚሰጡን ውጤት
= 666
63-0319 ሁለተኛው ማሕተም
ነገር ግን ይህ አሳሳች መንፈስ በሥጋ ሲገለጥ፤ ሥጋ ሆኖ ሲመጣ፤ ይህ የተሳሳተ ትምሕርት በሰው ውስጥ የክርስቶስን ቦታ ለመውሰድ ሥጋ ለብሶ መጥቷል፤ ከዚያ በኋላ ልክ ክርስቶስ እንደሚመለከው ይመለካል።
የክርስቶስን ቦታ የሚወስድ ሰው አሳች ነው።
61-0611 ራዕይ ምዕራፍ 5፤ ክፍል 1
… ሰዎች ብዙ ጊዜ ነብይ ብለው ቢጠሩኝ ጸጥ ብዬ እቆማለው ምክንያቱም ነብይ ማለት በአዲስ ኪዳን ዘመን ውስጥ “ሰባኪ፣ ትንቢት ተናጋሪ፣ ቃሉን የሚናገር ሰው” ማለት ነው። ይህ ተልዕኮዬ ስለሆነ ልቀበለው እችላለው። ነገር ግን “የተቀባ ወይም ክርስቶስ” ብላችሁ ብትጠሩኝ በጣም ይበዛብኛል። ይህን በፍጹም ልቀበለው አልችልም።
… ካናዳ ውስጥ ከስብሰባ ስወጣ በዚያ ሃገር ውስጥ ባሉ ኢስኪሞዎች ወይም በኢንዲያኖቹ መካከል መስፋፋቱን ሰማሁ።
… ከዚህም የተነሳ የሰላሳ አንድ ዓመታት አገልግሎት በሰይጣን ጉድጓድ ውስጥ መግባቱን ሳስብ ይዘገንነኛል… እኔ ከሞትኩ በኋላ
ምን ሊሉ ይሆን? “ይኸው ሞተ” ከማለት ውጭ ምን ይላሉ። ከዚያ በኋላ በሰዎች ላይ ያመጣሁት ተጽእኖ ምን ሆኖ እንደሞቀር ታያላችሁ፤ ከዚያ በኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይሉኛል። ይህም ሳስበው ይዘገንነኛል።
… እኔም እንዲህ ስል አሰብኩ፤ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ጠላቴ ቢሆን ቀላል ነበር፤ ስቄበት ማለፍ እችል ነበር፤ ነገር ግን ከተወደዱ ወንድሞች ዘንድ ሲመጣ ስሜቴን የሚጎዳው ይህ ነው።
... ከጌታ ዘንድ ጉብኝት ተቀብዬ ነበር። ብዙ ደስ የሚሉ ጉብኝቶችን አይቻለው። … አንድ ጊዜ ግን ቢጫ እና ጥቁር ቀለም ያለው እፉኝት እግሬ ላይ ነደፈኝ። ደሜ ግን እጅግ የበለጸገ ስለነበረ የእባቡ መርዝ ምንም ጉዳት ሊያደርስብኝ አልቻለም። ጎንበስ ብዬ እግሬ ላይ የተነደፍኩበትን ቦታ ተመለከትኩ። ከዚያም ጠብ መንጃ አንስቼ እፉኝቱ ላይ ተኮስኩበትና በጥይት ወገቡን መታሁት።
አንድ ወንድም እንዲህ አለ… ዞር ብዬ የእባቡን አናት በጥይት ልመታው ስዘጋጅ አንድ ወንድም እንዲህ አለ “ተው ተው አትተኩስበት፤ አጠገብህ ያለውን በትር ተጠቀም”። ከዚያ በትሩን ለማንሳት ዘወር ስል እየተሽሎከለከ ውሃ ውስጥ ገባ።
ውሃ አስተምሕሮን ይወክላል።
ይህ የተቀጠቀጠ እባብ “የመለኮትነት አስተምሕሮ” ምሳሌ ነው -- ማለትም ወንድም ብራንሐምን የተቀባው ክርስቶስ ብሎ የመጥራት።
ሊገድለው ሞከረ ግን አልተሳካለትም። እስካሁንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የአስተምሕሮ ኩሬዎች ውስጥ ተደብቆ ይገኛል እንጂ እንደ ሕይወት ውሃ በሚፈስሰው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አይደለም።
ወንድም ብራንሐምን ከኢየሱስ እኩል ከፍ ማድረግ የዚህ የተቀጠቀጠው እባብ ትምሕርት ነው።
ይህ አስተምሕሮ ምንጩ የሰባቱ ነጎድጓዶች እምነት ነው ምክንያቱም እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተገለጡም፤ ስለዚህ የጥቅሶች ኩሬ ብቻ ናቸው። ራሳቸውን የሜሴጅ ሰባኪ ብለው ከሰየሙ እንዲህ አይነት አታላዮች ራሳችሁን ጠብቁ።
ሰዎች ወንድም ብራንሐም ክርስቶስ ነው ብለው ማሰብ ጀምረዋል፤ ነገር ግን ወንድም ብራንሐም የመጣው ከቃሉ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግለጥ ነው። እርሱ ክርስቶስን ሊተካ አልመጣም።
1964 03 24 ሰባተኛው ማሕተም
በመካከላችን አንድም ታላቅ ሰው የለም።
እኛ ታላላቅ ሰዎች ወይም ታላላቅ ሴቶች አይደለንም -- ሁላችንም በአንድ አይነት ደረጃ ላይ የምንገኝ ወንድሞች እና እሕቶች ነን።
እኛ ታላላቆች አይደለንም። ማንም አንድን ሰው ከሌሎች ሰዎች በላይ ታላቅ ማድረግ አይችልም -- ይህ ሊደረግ አይችልም። በጭራሽ፤ ሁላችንም ሰዎች ነን።
ነገሮችን ለመተርጎም አትሞክሩ።
በጭምትነት ክብርን እና ምስጋናን ለኢየሱስ ክርስቶስ እየሰጣችሁ ከመኖር ውጪ አንዳችም ነገር ለማድረግ አትሞክሩ።
ማንንም ሰው “አመሰግናለው” አትበሉ። … ስለ አንድ አገልጋይ ወይም ስለ አንድ ነገር ስታስቡ በእርሱ ዘንድ መላካምንት አለ ብላችሁ አታስቡ፤ ምክንያቱም አንዳችም የለም፤ ማንም ይሁን ማን መልካምነት የለውም። አንድም ሰው በራሱ መልካምነት የለውም።
እውነቴን ነው። እዚህ የተሰበሰቡ ብዙ መለከቶች ቢኖሩ እና የአንዳቸውን ድምጽ ብንሰማ መለከቱ በራሱ አይደለም ድምጽ ያሰማን የሚነፋው ሰው እንጂ፤ መለከቶቹማ በራሳቸው ዲዳ ናቸው። አንስቶ የሚነፋው ሰው ነው መለከቱ ድምጽ እንዲፈጥር የሚያደርገው።
መለከቱ በራሱ አንዳች ድምጽ ማሰማት አይችልም። ድምጹ የሚመጣው መለከቱን ከሚጠቀምበት አእምሮ ያለው ሰው ዘንድ ነው። ስለዚህ መለከቶች ሁሉ አንድ ናቸው።
ሰዎች ሁሉ አንድ አይነት ናቸው፤ ክርስቲያኖች ሁሉ አንድ አይነት ናቸው።
…እዚህ ውስጥ ሰውን ማስገባት አንፈልግም።
እኔን ሙሉ በሙሉ እርሱኝ።
እኔ ወንድማችሁ ነኝ፤ ልክ እንደ እናንተው በጸጋ የዳንኩ ሐጥያተኛ ነኝ። በሕይወት ልኖር የሚገባኝ አይደለሁም፤ ይህ እውነት ነው፤ ይህን የምናገረው ትሁት ልሁን ብዬ አይደለም፤ እውነት ስለሆነ እንጂ።
እኔ ውስጥ ምንም ነገር የለም፤ አንድም መልካም ነገር የለም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ እነዚህን የፈዘዙ ዓይኖቼን ሲከፍት ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ ያሉ ነገሮችን አይቼ ተመለስኩ…
ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹ ሲፈቱ የወደፊቱን ጊዜ በራዕይ አየ።
ከዚያም ይህንን ያየውን የወደፊት ዘመን ሊነግረን ተመለሰ።
ወንድም ብራንሐም የማሕተሞቹ መፈታት ወደ ፊት የሚፈጸም ክስተት እንደሆነ ነው ያየው። ሰፋ አድርጎ ነው የገለጠልን ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዩ ሙሽራዋ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ነው የሚፈጸመው።
64-0315 ተጽእኖ
ይህ በጣም ጠቃሚ ምሳሌ ነው። ሁልጊዜ ትንሽነታችሁን አስቡ እንጂ ትልቅነታችሁን አይደለም።
እኛ አሜሪካኖች ዛሬ የምናስበው ሁልጊዜ ከሁሉ መብለጣችንን ታላቅነታችንን ብቻ ሆኗል። በቃ ከታላቅነታችንና ከትምክህት በስተቀር ምንም አይታየንም። “አገራችን ታላቅ ናት፤ ድርጅታችን ታላቅ ነው፤ ሁሉ ነገራችን ታላቅ…” ኦህ ትልቅ፣ ትልቅ፣ የሚታየን ሁሉ ትልቅ ብቻ ነው።
ከዚያ በኋላ… አንድ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለዚህ የምናገኛው ምሳሌ አለ። አንድ ነብይ ነበረ፤ እርሱም ዋሻ ውስጥ ገባ እና… ኤልያስ። እግዚአብሔርም ኤልያስን ከዋሻው ውስጥ እንዲወጣ ሊነግረው ፈለገ። ከዚያም እሳት እና ጢስ መጣ ደግሞም ኃይለኛ ነፋስ ተራሮቹ ላይ ነፈሰ፤ ደግሞም ነጎድጓድና የምድር መንቀጥቀጥ፣ እንዲሁም ሌላም ነገር።
ነብዩ ግን ንቅንቅ እንኳ አላለም።
እግዚአብሔርም በዚህ ሁሉ ግርግር ውስጥ አልነበረም። ነገር ግን ትንሽዬው የዝምታ ድምጽ በተናገረ ጊዜ ኤልያስ ፊቱን ሸፍኖ ወጣ።
በመሬት መንቀጥቀጥና በእሳት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል በትንሽ የዝምታ ድምጽ በመጣ ጊዜ ነው።
ታላላቅ ቤተክርስቲያኖቻችን ሳይሆኑ፣ ግርግሮቻችን ሳይሆኑ ከቃሉ የሚመጣው ትንሽ የዝምታ ድምጽ ተረስቷል። ይህ ትንሽ የዝምታ ድምጽ ሰዎችን ወደ ንሰሐ ሊጠራ ይገባል። እርሱም እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ የሚልከው ድምጽ ነው!
እርሱም እግሮቹን ሸፈነ፤ ደግሞም… በእግዚአብሔር ፊት ታናሽነታችንን አስተዋለ።
… ኦህ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እጅግ ታላቅ ነገር ይሆናል፣ እንደዚህ ትልቅ ደግሞም በታላቅ ትህትና ስለሚሆን ሳታስተውሉት ሊያመልጣችሁ ይችላል አልፋችሁት ልትሄዱ ትችላላችሁ።
ትልቅና የተሻለ ነገር ማሳደድ የአሜሪካዊነት መንፈስ ነው እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም።
ፈሪዋውያን ትልቅና የተሻለ ነገር ይፈልጉ ነበር።
ማቴዎስ 23፡5 ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥
እግዚአብሔር በትንንሽ ቡድኖች መካከል እንደ ሩት ቃርሚያ በሚሰበስቡት መካከል ይሰራል።
ዘካርያስ 4፡10 የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው?
64-0629 በፊታችን የተገለጠው ኃያል አምላክ
እርሱም እግዚአብሔር በክርስቶስ፤ አምላክ በሰው ውስጥ፤ የመለኮት ሙላት በአካል በሰው ውስጥ መገለጡ ነው። እግዚአብሔር በሰው ውስጥ!
አሁን እግዚአብሔር በሰዎች ውስጥ መሆኑ ነው፤ የመለኮት ሙላት በአካል በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሱን ይገልጣል፤ ቃሉን ይፈጽማል።
… እርሱም አለ፤ “የሰው ልጅ በሚገለጥበት ጊዜ።” የሰው ልጅ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደገና በሰዎች ውስጥ ተገልጦ፤ የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን ግን የሰው ልጅ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንደገና በመጨረሻዎቹ ቀናት። ይህን ለማድረግ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተስፋ ሰጥቶናል።
… አሁን የእግዚአብሔር ክብር በናንተ ሥጋ ውስጥ ተደብቋል።
“እግዚአብሔር በሰዎች ውስጥ።” እግዚአብሔር በሕዝብ ውስጥ -- በአንድ ሰው ውስጥ አይደለም።
“የሰው ልጅ እንደገና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተመልሶ።”
በበዓለ ሃምሳ ቀን እንደሆነው እግዚአብሔር አሁንም ወደ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተመልሶ መግባት ይፈልጋል።
ትኩረቱ እግዚአብሔር በአንድ ግለሰብ ውስጥ ማለትም በዊልያም ብራንሐም ውስጥ ስለመኖሩ አይደለም፤ ያ ቢሆን ራሱን ከፍ ያደርጋል።
ትኩረቱ ል በበዓለ ሃምሳ ቀን እንዳደረገው የእግዚአብሔር ሙላት በቤተክርስቲያን ሙላት ውስጥ ለማደር ነው።
… ለዚህ ዓለም ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን አሳዩዋቸው፤ የዚህን ዓለም ገበያ ሳይሆን ዓለምን ሁሉ የሚሞላ የእግዚአብሔር መገኘት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ያለበት መንፈሳዊ መነቃቃት፤ እግዚአብሔር ራሱን በሥጋ በሰው አካል የሚገልጥበት መነቃቃት። ሃሌሉያ! ይህ እንደሚፈጸም አምናለው።
… እርሱ ሲገለጥ ማየት ይሁንልን፤ የመቅደሱን መጋረጃ የቀደደውና ከዚያም ከመጋረጃው ውስጥ ወጥቶ የሄደው እራሱ ሲገለጥ ማየት ይሁንልን፤ እርሱም በበዓለ ሃምሳ ቀን ተመልሶ የሰው ሥጋ ውስጥ ገብቷል፤ ከክብር ወደ ክብር ሰዎችን እየለወጠ ይገኛል።
የበዓለ ሃምሳ ዕለት እግዚአብሔር በ120 ሰዎች ውስጥ ነበረ። ወደነዚያ ቀናት መመለስ አለብን። እግዚአብሔር በአንድ ሰው ውስጥ ብቻ ወደሚገለጥበት ሳይሆን እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ወደሙሚገኝበት።
62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን
ታውቃላችሁ እነዚያ ሰዎች ሲወጡ አንዳንዴ ስድስት ወይም ስምንት ብቻ ሆነው አንድ ላይ ሊሄዱ ይችላሉ። እነርሱ ዓለምን አናወጡ። አቂላ እና ጵርስቅላን የምታስታውሷቸው ከሆነ አጵሎስ ከእነርሱ ጋር በነበረ ጊዜ ለሥድስት ወይም ስምንት ብቻ ሆነው ታላቅ መነቃቃት ውስጥ ነበሩ። ቤተክርስቲያኑ በሙሉ ሥድስት ወይም ስምነት ሰው ብቻ ሊሆን ይችላል። አሁን እዚህ የተሰበሰባችሁ ሰዎቸ ከእነርሱ አምስት ሥድስት ወይም ሰባት እጥፍ በቁጥር ትበልጣላችሁ።
እንደምታውቁት ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት ብቻ ነበሩት። እኛ ሁል ጊዜ የሰው ብዛት ነው የምናስበው፤ እግዚአብሔር ግን ከብዙ ቁጥር ጋር አይደለም የሚሰራው። እግዚአብሔር የሚሰራው ከእነዚህ በቁጥር ታናሽ ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው። አያችሁ? በዘመናት ውስጥ ሁሉ ተመልከቱ፤ ሰዎችን ባናገረ ቁጥር ሁልጊዜ ከጥቂቶች ጋር ነው የሰራው ከጥቂት ሰዎች ጋር ተነጋገረ እነርሱንም ሾማቸው። እንደዚህ ባለ መንገድ መሥራት የእግዚአብሔር ፈቃዱ ነው። እንደዚህ መሥራት ነው የሚወደው። እኛም ደግሞ እግዚአብሔር በመካከላችን እንዲሆን እና እነዚህን ነገሮች እያደረግን መኖር ነው የምንፈልገው።
እግዚአብሔር ሰዎች ጥቂት ቁጥር ባላቸው ሕብረቶች ውስጥ እንዲሆኑ ነው የሚፈልገው።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን (አውሬው) በሰው የሚሾም እና የሚተካካ ፖፕ አላት።
ፕሮቴስታንቶች ይህንን አሰራር ኮርጀዋል። ዛሬ ፓስተሮች ጡረታ ሲወጡ ልጆቻቸው እየተኩዋቸው ነው። አባት በልጅ እየተተካ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ውስጥ የራሳቸውን መንግሥት እየመሰረቱ ነው።
በመጨረሻው ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር እየፈለገ ያለው የቤተክርስቲያን ልምምድ አይደለም።
እያንዳንዱ ሰው በግሉ ከእርሱ ጋር ሕብረትና የግል ልምምድ እንዲኖረው ይፈልጋል ምክንያቱም ቤተክርስቲያን እውር እና ለብ ያለች እንደሆነች ያውቃል። ቤተክርስቲያን ጥቂት ከእግዚአብሔር ቃል ጥቂት ደግሞ የሰዎችን ጥቅስ እና አመለካከት ቀላቅላ ነው የምትጠቀመው።
በአንድ ቡደን ውስጥ የመሆን ፍላጎትህ በብዙ ሰዎች ግፊት እና ተጽእኖ ይደረግብሃል። ባቢሎን የተገነባቸው ለአንድ ሰው መገዛትን በማስገደድ ነው። በዚህም መንገድ ከኢየሱስ ጋር ያለህን የግል ልምምድ ታጣዋለህ።
65-1128M እግዚአብሔር ያዘጋጀው ብቸኛ የአምልኮ ሥፍራ
ታክሰን ውስጥ ዛሬ ጠዋት እያሰብኩ ነበር እና ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር አለ… ሁልጊዜ ሰዎችን “ቤተክርስቲያናችሁ የትም ይሁን የት መሄድ አለባችሁ” እያልኩ እመክር ነበር። ከዚያም ሰዎች ቤተክርስቲያን መሄድ ትተው ሌላ ቦታ ሲሄዱ አይቻለው። ከዚህም የተነሳ “ምን ሆነዋል?” ብዬ እጠይቅ ነበር።
አንዳንዶቹ ሄድኩ “መጀመሪያ በሄድክበት ቀን የኛ ቤተክርስቲያን አባል ሁን ይሉሃል። እሺ ካላልካቸው አይቀበሉህም።” አያችሁ? በግድ ነው አባል የሚያደርጉዋችሁ፤ በግዴታ ከሆነ ደግሞ ባቢሎን ነው ማለት ነው።
በክርስቶስ ግን በፍላጎታችሁ ነው የምትከተሉት፤ በግድ አይደለም፤ ልባችሁ ይስባችኋል እንጂ።
እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ስሙን ባቢሎን ውስጥ አላኖረም። ዛሬም በቤተክርስቲያኖች ባቢሎን ውስጥ ስሙን አያኖርም። ሰዎች ስሙን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊጠሩ ይችላሉ እርሱ ግን በጭራሽ ስሙን በዚያ አያኖርም።
በ1965 ወንድም ብራንሐም ሰዎችን ቤተክርስቲያን እንዲሄዱ ይመክራቸው የነበረ ጊዜ የራሱን ምክር ይጠራጠር ነበር።
ቤተክርስቲያኖች እናንተ በእምነት እንድትመስሉዋቸው ማስገደድ ብቻ ነው ሃሳባቸው።
ይህም የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ይጨምራል።
የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችም በፓስተሮች አምባገነንነት የሚመሩ ናቸው። ስለዚህ እነርሱ ከሚሉት ጋር ካልተስማማችሁ አይፈልጉዋችሁም። ለራሳችሁ ማሰብ አይፈቅዱላችሁም። አለመስማማትም አይፈቀድላችሁም።
65-1128M እግዚአብሔር ያዘጋጀው ብቸኛ የአምልኮ ሥፍራ
እርሱም እንዲህ አለ “እኔ የማሳይህና መስዋእትህን የምቀበልበት ሥፍራ ስሜን አኖርበት ዘንድ በመርጥሁት ቦታ ነው። በዚህ ስሜን አኖርበት ዘንድ በመረጥሁት ቦታ በደጁ ትገባለህ። ወደዚያም ትመጣለህ።”
እነርሱ ደግሞ እንዲህ ይላሉ “ይህች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት።” በዚህ አዋጃቸው ውስጥ የረሱት ነገር ቢኖር “ተቃዋሚ” የሚለውን ቃል አለማስገባታቸው ነው። ክርስቶስ ያስተማረውን ሁሉ ይቃወማሉ። ዘመናዊ ፈሪሳውያን ሁሉ።
ክርስቲያን፣ ደቀመዝሙር፣ ወይም አማኝ ከሚለው ስም ውጭ በሌላ በማንኛውም ስም ስንጠራ የክርስቶስ ተቃዋሚዎችን ጎራ ተቀላቅለናል። ሜተዲስት፣ ሉተራን፣ ባፕቲስት፣ ፔንቲኮስታል፣ ኢን-ዘ-ሜሴጅ።
ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጋር ስናነጻጽራቸው እነዚህ ስሞች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆናቸውን እናያለን። መከተል ያለብን ግን የጥንቷን ቤተክርስቲያን አርአያነት ነው።
ሜሴጅ ወይም ዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተቃረነች ጊዜ ወዲያ የክርስቶስ ተቃዋሚ ትሆናለች።
ፓስተሮች ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን እየሰነጣጠቁ እንደፈለጉ እየተረጎሙ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለተጻፉ ምስጢራትን ለመግለጥ እየሞከሩ ናቸው፤ ለምሳሌ የሰባቱን ነጎድጓዶች ቃል ለመተርጎም ያደረጉት ሙከራ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል። ያልተጻፈውን ለማብራራት መሞከር መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሰዎችን ብቻ ሊያስደንቅ የሚችል የሞኝ ሥራ ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩት ቃል አልተጻፈም፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ ሌሎች ሰባት ነገሮች ጋር ልናያይዛቸው አንችልም።
ፖፑም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ልዩ ልዩ ምስጢራትን ያምናል ለምሳሌ ሥላሴ፣ ፑርጋቶሪ፣ ክሪስማስ፣ ኩዳዴ እና የመሳሰሉትን።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፈ ነገር ማመን የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ሊያስገባችሁ አይችልም ምክንያቱም ልክ እንደ ቫቲካን መሆናችሁ ነው፤ ማለትም እንደ ባቢሎን ምስጢር።
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን -- የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 3
ኦህ ይገርማል! በራዕይ 12 ጋለሞታይቱ ብዙ ልጆች ነበሯት። እነዚህ ልጆች ልክ እንደ እናታቸው ናቸው። ቃሉን ወደ ጎን ይተዋሉ፤ የእግዚአብሔርን መንፈስ ሥራ ይክዳሉ፤ ምዕመናንን የበታቻቸው አድርገው ይገዛሉ፤ ሕዝቡ በእነርሱ በኩል ካላለፉ በስተቀር እግዚአብሔርን ማምለክ እንዳይችሉ ያደርጋሉ አለዚያ ደግሞ እነርሱ በወሰኑበት መንገድ ካልሆነ በቀር። መንገዳቸውም የሰይጣን ክሕደት ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደለም።
64-0629 በፊታችን የተገለጠው ኃያል አምላክ
እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲወጡ ጥሪ እያቀረበ ነው፤ ከአስመሳዮች ቤተክርስቲያን መካከል በሥጋዊነት ከሚመላለሱት መካከል እንዲወጡ እየተጣራ ነው፤ ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ፕሬስቢተሪያን ብቻ ሳይሆኑ ከፔንቲኮስታል ቤተክርስቲያኖችም ጭምር።
የግል ጉዳይ ነው። በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ብቻ ያለ ጉዳይ። ወደ እግዚአብሔር ተለይተህ መቅረብ ያለብህ አንተ ነህ እንጂ ቤተክርስቲያንህ፣ ቡድንህ ወይም ፓስተርህ አይደለም፤ አንተ ነህ።
ዋናው ቁም ነገር ይህ ነው። ሦስተኛው የሕዝብ መውጣት ቤተክርስቲያንን ለመቀላቀል አይደለም። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሕብረት ልታደርግ ትችላለህ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ማስቀደም አለብህ። አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ብለህ አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ማመቻመች የለብህም።
የግል ጉዳያችንን ከቤተክርስቲያን ቡድናዊ አስተሳሰብ ጋር መቀላቀል የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ በራስህ አእምሮ አስብ። ፓስተሩ በአንተ አእምሮ ለአንተ ሊያስብልህ አይችልም።
ወንድም ብራንሐም እውነትን ገልጧል፤ ስለዚህ አሁን እያንዳንዳችን ስለተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል በየግላችን መገለጥን መቀበል አለብን።
ከፊት ለፊታችን ሁለት ምርጫዎች አሉን።
ወይ ወደ ጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እንመለሳለን አለዚያ ደግሞ የጋለሞቶች እናት ወደ ሆነችዋ ወደ ጋለሞታዋ ሮም ልማዶች እንመለሳለን።
ፖፑ በአውሮፓ ውስጥ ብቸኛው ፈላጭ ቆራጭ ነው። የፖፑ አምባ ገነናዊ የቤተክርስቲያን አገዛዝ ሥርዓት ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልኮ ገብቷል።
መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አይለውም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ እንኳ ፓስተሩ የበጎች እረኛ ነው አይልም።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
ስለዚህ የእኛ ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሥርዓት እንድንከተል አታሎናል።
ለምሳሌ፡ የሮማ ካቶሊኮች በ350 ዓ.ም አካባቢ የሮማ የፀሃይ አምላክን ልደት ክብረ በዓል በመኮረጅ ክሪስማስን ተቀበሉ፤ ክሪስማስም በዲሴምበር 25 ቀን 274 ዓ.ም በሮማዊው ገዥ ኦውሬሊያን አማካኝነት እንዲከበር ተወሰነ።
መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ የጌታን ልደት እንድናከብር አላዘዘንም። ዛሬ ግን ለሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች እና ለፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ክሪስማስ ዋነኛው በዓላቸው ነው።
ዓይኖቻችሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስታነሱ መጨረሻችሁ ሮምን መኮረጅ ነው የሚሆነው። የሮማ ካቶሊክ መሪዎች በጣም ብልጦችና አታላዮች ናቸው።
ለዚህ ነው ራዕይ 10፡7 ምስጢሩ “ይፈጸማል” ያለው።
የሮማ ካቶሊክን አርአያነት በመከተል ስለተጠመድን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት የመመለሱን ምስጢር ልንፈጽም ጊዜ እንኳ ማግኘት አልቻልንም።
ሮም ብዙ አሳሳች መስህብ የሞላባት “የባቢሎን ምስጢር ናት”። የሮማ ካቶሊክን የሚከተሉ 1200 ሚሊዮን ሰዎች አሉ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰዎችን የምትስብ ቤተክርስቲያን ናት፤ ለዚህ ነው ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ በአንዲት ውብ ሴት የተወከለችው።
ኢየሱስ ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክት ሲጠይቁት መጀመሪያ የሰጠው መልስ ትልቁ ጠላታችን አሳቾች እንደሚሆኑ ነው የገለጸው።
ማቴዎስ 24፡3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ሕዝቡ መሪዎቻቸው ካሳቱዋቸው ወደ የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ወደነበረችበት እምነት አይመለሱም።
የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በኃላፊነት የሚገዛት ፓስተር አልነበራትም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያልተጻፈውን የሰባቱን ነጎድጓዶች ምስጢር ለመረዳት አልሞከረችም፤ የሰባተኛው ማሕተም ዝምታ ምን እንደሆነ እንዲሁም ያልተጻፈው የኢየሱስ ስም ማን እንደሆነ ለመግለጥ አልሞከረችም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው የሰበከችው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2 ቃሉን ስበክ፤
ሉቃስ 4፡8 ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን እያንዳንዱን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ትመረምር ነበር፤ እንደውም መልእክቱ የተነገረው በታላቁ ሐዋርያ በቅዱስ ጳውሎስ አፍ ቢሆን እንኳ እውነተኛነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ከመፈትሽ አትመለስም።
ልክ እንደ ኢየሱስ ለሰይጣን መልስ ሲሰጡ “ተብሎ ተጽፏል…” ይሉ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤
11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
“እነዚህም” -- ከአንድ በላይ ሰዎች። ፈትሸው እውነት መሆኑን ያረጋግጡ ነበር። የቤርያ ሰዎች ለራሳቸውም ታማኞች ናቸው። የሰሙት ሃሳብ ትክክለኛ መሆኑን መርምረው አረጋግጠው የግል መገለጥ ይቀበሉ ነበር።
በተጻፈው ቃል አማካኝነት ይመረምራሉ፤ ለራሳቸው የማሰብ ነጻነት ነበራቸው።
የፓስተሩን ንግግር ሰምተው እንደ ገደል ማሚቶ አይደግሙም ነበር።
ወንድም ብራንሐም በ1965 ከተለየን በኋላ የሰባተኛው ዘመን ቤተክርስቲያን ብዙ አይነት ችግሮች ውስጥ ገባች።
በ1966 አዲስ ዘመን ተጀመረ።
ከዚያ ወዲያ የቀረልን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንድንመለስ የሚመራን ድምጹ እና ሊያስቱን ጥቅሶችን አጣመው የሚተረጉሙ የሜሴጅ ሰባኪዎች ናቸው።
የሞባይል ስልክ ሱስ ሰዎች ምንም የማይጠቅም የመረጃ ብዛት እንዲቀበሉ አድርጓቸዋል።
ይህም በቀላሉ ተቀብለን ወደ ልባችን የምናስገባቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ብዛት ምን ያህል እንደሆኑ ያመለክታል።
የተሰነጣጠቁ እና ተጣመው የተተረጎሙ ጥቅሶች የሰሩት የሸረሪት ድር በድግግሞች እውነት ወደ መምሰል የደረሱ ውሸቶችን አበራከተ፤ እነዚህም ውሸቶች አንዳች የመጽፍ ቅዱስ ድጋፍ የላቸውም።
ወንድም ብራንሐም የመጨረሻው ዘመን ነብይ ነው ብለው ያመኑ ሰዎች መካከል ትልቅ ግራ የመጋባት ምክንያት የሆነው በ1963 የታየው ታላቅ ደመና ነበር።
አለማወቅና የተሳሳቱ መግለጫዎች ምን ያህል ብዙ ስሕተቶችን እንደወለዱ ለመረዳት ስለ ደመናው እውነቱን አጣርተን ማወቅ አለብን።
ይህ ደመና መከሰቱ የሜሴጅ ሰባኪዎች ምን ያህል እውነትን ፈትሸው ለማጣራት ሰነፎች መሆናቸውንም በሚያሳዝን መልኩ አጋልጧል። የሜሴጅ ሰባኪዎች እንደ ቤሪያ ሰዎች አይደሉም።
ነገሩ ሁሉ የጀመረው በፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነበር። አንድ ሮኬት 75-3-5 የሚባል የኮድ መጠሪያ ካለው ማስወንጨፊያ ቦታ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሙገኘው ከቫንደንበርግ ኤይር ፎርስ ኪይሆል 4 የሚባል የወታደራዊ ቅኝት ሳተላይት ተወነጨፈ። ሮኬቱ ከመስመሩ ሲወጣ ከምድር 44 ኪሎሜትር (144¸000 ጫማ) ከፍታ ላይ ከቀኑ 7፡52 ሰዓት ላይ ሆን ተብሎ እንዲቃጠል ተደረገ። ሮኬቱ ጠጣርነቱን እንደያዘ እንዲቆይ ድጋፍ የሚሰጠው አካል ነበረው፤ ይህም አካል እንደ ቦምብ በመፈንዳት ብዙ ጭስ ፈጠረ። ሮኬቱ በበረራው ውስጥ የታሰበለት የመጨረሻ ከፍታ ላይ ስላልደረሰ የነዳጅ መያዣው ውስጥ ብዙ ነዳጅ ነበረው። ከዚህም የተነሳ በፍንዳታው የተፈጠረው ጭስ እጅግ ብዙ ነበር። በሰዓቱ የነበረው ነፋስ ጭሱን ወደ ምሥራቅ እየገፋው በሰሜን አሪዞና የነበረው የፍላግስታፍ ከተማ ሰማይ ላይ ወሰደው።
ነገር ግን በዚያ ከፍታ ላይ አየሩ በጣም ስስ ስለነበረ የጭሱ ብናኞች በጣም በመበታተናቸው የተነሳ በቀን ብርሃን አይታዩም ነበር።
ከሰማያዊው ሰማይ ላይ በከባድ ድምቀት ታበራ ከነበረችው ፀሃይ የተነሳ ጭሱን ከምድር ላይ ሆኖ ማየት አይቻልም ነበር።
በዓይን የማይታየው የጭስ ብናኝ ከሰዓት በኋላ ወደ ምስራቅ መብነኑን ቀጠለ። ከምድር በ20 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ያለ ደመና በጣም በስሱ ስለሚበታተን በጠራራ ፀሃይ ሊታይ አይችልም።
ከምድን በላይ በ20 ኪሎሜትር ወይም በ80 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ በቂ እርጥበት ወይም ውሃ ስለማይኖር በዓይን የሚታይ ደመና ሊፈጠር አይችልም።
ከ80 – 85 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የአየሩ ሙቀት ከዜሮ በታች 123 ዲግሪ ከደረሰ ትንንሽ የውሃ ትነት ሞለኪዩሎች እና ሜቴን የተባለ ጋዝ በአንድነት በሌሊት የሚያበራ ሰማያዊ ቀለም ያለው ደመና ሊፈጥሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ክስተት በ40 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ አይፈጠርም። ለዚህ ነው ሳይንቲስቱ ጄምስ ማክዶናልድ በሌሊት ሰማያዊ ቀለም የሚፈጥሩ ደመናዎችን ብዙም ትኩረት የማይሰጣቸው።
በሌሊት ሰማያዊ ብርሃን ስለሚያበሩ የጭስ ደመናዎች ጥቂት እንመልከት።
ከ80 እስከ 85 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ በሰሜን ዋልታ አካባቢ ጥቂት በሌሊት የሚያበሩ ደመናዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ።
የቀሩት ደመናዎች በሙሉ የሚፈጠሩት ከምድር በ20 ኪሎሜትር ከፍታ በታች ሲሆን 99 ደመናዎቹ በመቶ የውሃ ትነት ይዘት አላቸው።
ስለዚህ ከ20 ኪሎሜትር ከፍታ እና 80 ኪሎሜትር ከፍታ መካከል የውሃ ትነት የያዙ ደመናዎች የሉም። ከ20 እና 80 ኪሎሜትር ከፍታ መካከል ባለው ክልል ውስጥ ደመና ካያችሁ ሰው ሰራሽ ደመና ነው።
አንድ ሊትር ነዳጅ ሲቃጠል አንድ ሊትር ያህል የውሃ ትነት ይፈጥራል። ይህ የውሃ ትነት ከአውሮፕላን ሞተሮች ወይም ከሮኬት ሞተሮች ሲወጣ ከ20 እና 80 ኪሎሜትር ከፍታ መካከል ባለው የአየር ክልል ውስጥ ሰው ሰራሽ ደመና ይፈጥራል። ነገር ግን ሳይንቲስቱ ጄምስ ማክዶናልድ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ያለው ሰማይ ላይ አንዳችም አውሮፕላን ወይም ሮኬት እንዳላለፈ አረጋግጧል።
በአየር ላይ ከፈነዳው ሮኬት የሚወጣው ስብርባሪ እና ጭስም ከ20 እስከ 80 ኪሎሜትር ከፍታ ውስጥ ባለው የአየር ክልል ላይ ሰው ሰራሽ የጭስ ደመና ሊፈጥር ይችላል።
ከ20 ኪሎሜትርና ከ80 ኪሎሜትር ከፍታዎች መካከል ያሉ ሰው ሰራሽ ደመናዎች ብዙውን ጊዜ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ እና ከመውጣቷ በፊት ብቻ ነው የሚታዩት። ዓለም አቀፉን የጠፈር ምርምር ጣቢያ ማየት የምንችለው ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ባሉት አሥር ደቂቃዎች ወይም ከመውጣቷ በፊት ባሉት አሥር ደቂቃዎች ውስጥ ከአናታች በላይ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ነው። ይህ ለምንድነው የሆነው?
በ40 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ አየሩ በጣም ስለሚሳሳና ጭስ በጣም በስሱ ስለሚበታተን በደማቅ ሰማይ ላይ ጭሱ ሊታየን አይችልም። ከ20 ኪሎሜትር ከፍታ በታች ሲሆን ብቻ ነው አየሩ ጥቅጥቅ ባለበትና የውሃ ትነትን በሚሸከምበት ከምድር የሚታይ ደመና ለመፍጠር የሚበቃ ውፍረት አየሩ የሚኖረው።
ፀሃይ ከአድማስ በታች ስታዘቀዝቅ ለጥቂት ደቂቃ ከጠለቀች በኋላ ከደመናው የስረኛ ክፍል ላይ ብርሃኗ ያንጸባርቃል። ከላይ ያለው ሰማይ ጥቁር በሚሆንበት ጊዜ ይህ የጭስ ደመና በ40 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ከሆነ ለግማሽ ሰዓት ያህል መታየት ይችላል። ከዚያም በላይ ከፍ ያሉ ደመናዎች ደግሞ ረዘም ላለ ሰዓት መታየት ይችላሉ።
የጭሱ ደመና ፍላግስታፍ አካባቢ ከምሽቱ 12፡40 ሰዓት ላይ ልክ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ሲደርስ ሰማዩ በደምብ ጨለም ብሎ ስለነበረ ደመናው በደምብ ይታይ ነበር። ከዚያም በኋላ ከዚህ ደመና የሚበልጥ በጣም ታላቅ ደመና 20 ማይልስ ያህል ከፊቱ ርቆ ተከሰተ። ትልቁም ደመና የነበረበት ከፍታ 42 ኪሎሜትር ነበረ (30 ማይልስ)። ይህ ትልቅ ደመና ለ28 ደቂቃ ያህል እየታየ ቆይቷል።
ይህ ደመና በመልአክ ክንፍ ምክንያት የተፈጠረ መለኮታዊ ሊሆን የቻለበት ምክንያት በዚያ ከፍታ ላይ በሰው ሰራሽ መንገድ ደመና ሊፈጠር ስለማይቻል ነው። ዛሬ በዚያ ከፍታ ላይ ኬሚካል በመርጨር ደመና መፍጠር እንችላለን። ነገር ግን ይህ ዘዴ በ1963 ገና አልተፈጠረም ነበር።
ይህ ፎቶግራፍ ደመናው በሚሄድበት መስመር ውስጥ ከነበረው ዊንስሎው ከሚባል ከተማ ነው የተነሳው።
ሳይንቲስቱን ጄምስ ማክዶናልድ ግራ ያጋባው ይህ ነው። ሁለት ደመናዎች ነበሩ። አንደኛው ደመና የጠፈጠረው አየር ላይ በፈነዳው ሮኬት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደመና ግን በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ሊታወቅ አልቻለም።
ከዚህ በታች ያለው ምስል ፎቶግራፍ አይደለም ግን ሁለቱ ደመናዎች እንዴት ይታዩ እንደነበር ለማስረዳት የተዘጋጀ ሥዕል ነው።
የውሃ ትነት ደመናዎች ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ይጠቁራሉ። ፀሃይዋ ከጠለቀች በኋላ የሚያንጸባርቁት ደመናዎች ማንጸባረቃቸው ብቻ በምን ያህል ከፍታ ላይ እንዳሉ ይገልጣል። የብዙ ሰዎችንም ትኩረት የሳበው ይህ ነው።
በዚህ ከፍታ ላይ ኖርማሉ የውሃ ትነት ደመና ሊፈጠር አይችልም። ደግሞም በዚያ ቀን ፍላግስታፍ አካባቢ ሰው ሰራሽ በሌሊት የሚያበሩ ደመናዎች ተፈጠሩ እንዳይባል አንድም ሮኬት ወይም አውሮፕላት በዚያ በኩል አላለፈም።
ስለዚህ ትልቁ ደመና በመልአክ ክንፍ አማካኝነት ብቻ ነው ሊፈጠር የሚችለው። ደመናው በሰማያት ላይ የተከሰተ ምልክት ነው። የለመድነው አይነት ደመና በዚያ ከፍታ ላይ ሊፈጠር አይችልም።
ዊልያም ብራንሐም ስለ ደመናው አንዳችም አያውቅም ነበር። በዚያ ሰዓት እርሱ ደመናው ከታየበት ቦታ 200 ማይልስ ያህል ወደ ደቡብ የሚርቅ ታክሰን የሚባል ከተማ ውስጥ ነበር። ስለ ደመናው ያወቀው ላይፍ መጽሔት በግንቦት ወር እትሙ ገጽ 112 ላይ ያሳተመውን ጽሁፍ በማንበብ ነበር።
ከዚህ በታች ያለው ፎቶ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም በታክሰን ካለው የጠፈር ምርምር ጣቢያ ነው የተነሳው። ደመናው ውስጥ የሚታይ ፊት አልነበረም።
በሕይወቱ የመጨረሻው ዓመት በ1965 ወንድም ብራንሐም ደመናውን የሰማይ ምልክት ነው ብሎ ነበር የገለጸው።
65-0718 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር መመልከቻ ማዕከል ውስጥ ሆነው ምን እንደተፈጠረ በማሰብ ሲገረሙ ነበር። ታክሰን ውስጥ ያሉ ታላላቅ የጠፈር መመልከቻ ማእከሎች ፎቶ አንስተውታል። ቢሆንም ግን ምን እንደሆነ ሊያውቁ አልቻሉም። በጋዜጦችም ውስጥ “ይህ ክስተት ምን እንደሆነ ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን?” እያሉ በመጠየቅ ይጽፉ ነበር። በዚያ ከፍታ ላይ አንዳችም ጉም ሊኖር አይችልም፤ አየርም የለም፣ እርጥበትም የለም። ደመናው የታየው ከምድር በሰላሳ ማይልስ ከፍታ ላይ ነበር፤ ይገርማል።
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህም ነገሮች ሲሆኑ፣ በልዩ ልዩ ቦታዎችም የምድር መናወጥ በሚሆንበት ጊዜ በሰማይ ላይ ምልክት የሰው ልጅ ምልክት ይታያል።” “በዚያ ቀን” በሉቃስ ውስጥ እንደተጻፈው “የሰው ልጅ እንደገና ራሱን ይገልጣል፤ እርሱ ራሱ ይገለጣል”። የዚያን ጊዜ ዓለም እንደ ሰዶምና ገሞራ ትሆናለች!
ማቴዎስ 24፡30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
ፍጥረታዊው ሰማይ ከአናታችን በላይ የምናየው ከባቢ አየር ነው። ይህ ታላቅ “ትንግርት” የሆነ ደመና ድንገት በታላቅ ከፍታ ላይ ሲገለጥ ተፈጥሮአዊ የፊዚክስ ህጎችን ሁሉ ጥሶ ነው የተገለጠው። ደመናው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ካልሆነ በቀር በዚያ ከፍታ ላይ ሊከሰት አይችልም።
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
ይህ ቁልፍ ነጥብ ነው። ደመናው ራሱን የቻለ ተፈጥሮአዊ ክስተት አልነበረም።
ደመናው በሰማይ ላይ በታላቅ ከፍታ በተገለጠ ጊዜ የአንድ ታላቅ ክስተት ምልክት ሆኖ ነው የመጣው።
ስምንት ቀናት ካለፉ በኋላ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ደቡብ ሁለት መቶ ማይልስ ርቀት ላይ ደመናውን የፈጠሩት ሰባት መላእክት ሳንሴት ፒክ (ወይም በሌላ አጠራሩ ሳንሴት ማውተን) የሚባል አካባቢ ወርደው ከወንድም ብራንሐም ጋር ተነጋግረው በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፈውን የሰባቱን ማሕተሞች ምስጢር እንዲያስተምር ትዕዛዝ ሰጥተውታል።
ከዚህ በታች ያለው ምስል እነዚያ ስብከቶች የተጻፉበት መጽሐፍ የፊት ሽፋን ነው።
ይህ የማሕተሞቹ መፈታት አይደለም፤ ምክንያቱም ማሕተሞቹ የሚፈቱት ሙሽራዋ በንጥቀት ጊዜ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ ነው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ክስተቱ በሰማያት ላይ ከመገለጡ በፊት አስቀድሞ በምድር ላይ በነብይ ሊታወጅ ይገባል።
ደመናው በውስጡ የሚታይ ፊት አልነበረውም።
ወንድም ብራንሐም ከፍላግስታፍ በስተደቡብ 200 ማይልስ ርቀት ላይ የምትገኘው ታክሰን ውስጥ ስለነበረ ደመናውን አላየውም። ፌብርዋሪ 28 ቀን 1963 አንድም መንፈሳዊ የነበረ ሰው ደመናውን አላየውም።
የአደን ወቅት ከዚያ ወዲያ በቀጣዩ ቀን ማርች 1 ቀን 1963 ነበር የተከፈተው። ማርች 4 ቀን 1963 ወንድም ብራንሐም ሂውስተን ቴክሳስ ውስጥ “ፍጹም የሆነው” በሚል ርዕስ ሰብኮ ነበር። ቤኪ የምትባለዋ የብራንሐም ልጅ 'Return to Sunset' በሚለው መጽሐፏ እንደተናገረችው ብራንሐም ወደ ሳንሴት ፒክ የሄደው በማርች 6 ቀን 1963 ነበር።
ሰባቱ መላእክት ማርች 8 ቀን (ደመናው ከተገለጠ ከ8 ቀናት በኋላ) የማይታዩ ሆነው ወደ እርሱ መጥተው ወደ ጄፈርሰንቪል እንዲመለስና በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ያሉትን የማሕተሞቹን ፍቺ እንዲገልጥ ነገሩት። ከዚያ መላእክቱ ማንም ሳያያቸው ተመልሰው ሄዱ።
ከዚያ በኋላ ወንድም ብራንሐም ታላቅ ስሕተት ሰራ።
ነቢያት ሊሳሳቱ ይችላሉ። ግን በመሳሳታቸው ብቻ ነብይነታቸው አይሻርም።
የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ ሆኖ የተገለጠው መጥምቁ ዮሐንስ በስተመጨረሻ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን ተጠራጥሯል።
ኢየሱስ ስለዚህ ትልቅ ስሕተት ዮሐንስን አልነቀፈውም። በዚያ ፈንታ የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ ዮሐንስን አረመው እንጂ።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ሲሳሳት የኢየሱስን ምሳሌ መከተል አለብን።
55-0607 እውነተኛው የወይን ግንድ እና ሐሰተኛው የወይን ግንድ
እግዚአብሔር ግን በነብያቶቹ እና በባለራዕዮቹ በኩል እነዚህን ነገሮች በትክክል እንደሚገልጣቸው ተናግሯል።
ለአገልጋዮቹ የማይገልጥላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ በድንጋይ ላይ የተቀመጠውን ያዕቆብን ተመልከቱ።
በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ሳለ የሚወደውን ልጁን የዮሴፍን ቀሚስ አመጡለት… ደግሞ ነብይ እንደነበረ ታውቃላችሁ።
ቀሚሱን ይዘውለት መጡና “ልጅህን አውሬ በልቶታል” አሉት። ግን የነገሩት እውነት አልነበረም። እርሱም ከዚያ በኋላ ለአርባ ዓመታት ያህል ምንም አላወቀም።
ይስሐቅንም እዩት ዓኖቹ ፈዘው በተቀመጠበት፤ ያዕቆብ ይመጣና “እኔ ኤሳው ነኝ” ይለዋል። እርሱም ነብይ ነበር ግን ኤሳው መስሎት ተታልሎ ባረከው…
ኤልያስን ተመልከቱት በተቀመጠበት አንዲት ሱነማዊት ሴት መጥታ በፊቱ ስትወድቅ። እርሱም እንዲህ ይላል “ነፍሷ አዝናለች፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ሰውሮታል”። ነብያት ሁሉንም ነገር የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም። ነብያት የሚያውቁት እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ብቻ ነው። ነብያት የማይሳሳቱ ሰዎች አይደሉም።
መጽሐፍ ቅዱስ “ኤልያስም እንደ እኛው አይነት ድካም ያለበት ሰው” እንደነበረ ይናገራል፤ ያለፈባቸው ውጣውረዶች ብቻ ናቸው ከእኛ የሚለዩት።
ወንድም ብራንሐም ደመናው የጠፈጠረው ሰባቱ መላእክት ከሳንሴት ፒክ ከእርሱ ዘንድ ተለይተው ሲሄዱ መሰለው።
ነገር ግን ደመናው የታየው መላእክቱ ወደ እርሱ ከመምጣታቸው ከስምንት ቀናት ቀድሞ እንዲሁም እርሱ ከነበረበት ቦታ በ200 ማይልስ ወደ ሰሜን ርቆ ነው።
ከዚያ አሳዛኝ ስሕተት በመነሳት ብዙ የተሳሳቱ ትምሕርቶች ተፈልፍለዋል።
ወንድም ብራንሐም ከሞተ በኋላ ይህ ፎቶ ታትሞ በዓለም ዙርያ ሁሉ ተሰራጭቷል።
ለሜሴጅ አማኞች ግን ደመናው ምልክት ሳይሆን ክርስቶስ እራሱ ነበር ብለው አመኑ።
አስተሳሰባቸው በጣም እየተበላሸ መስመር እየለቀቀ ሄደ።
ደመናውም በእነርሱ አነጋገር በፍላግስታፍ ከተማ ላይ አልነበረም -- የሜሴጅ አማኞች እንደሚሉት ደመናው 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቃ የምትገኘው ሳንሴት ማውንተን ላይ ነበረ (አካባቢው በሌላ መጠሪያው ሳንሴት ፒክ ወይም ሳንሴት ተብሎ ይታወቃል)።
ስሕተት ስሕተትን ይወልዳል።
ብዙ የሜሴጅ አማኞች በተለይም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የተገለጠው ደመናው የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ነው ብለው አመኑ። ቀኑ የአደን ወቅት ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀድሞ ነው። ነገር ግን በዚያ ቀን ወንድም ብራንሐም በሕገወጥ መንገድ ለአደን ሊሰማራ አይችልም።
ምን ያህል እንደሳቱ ልብ በሉ።
ወንድም ብራንሐም ደመናው “የጌታ ምጽአት ነው” ብሎ አልተናገረም፤ ተከታዮቹ ግን እርሱ የተናገራቸውን ቃላት ጠቅሰው እንደዚያ ብለው ተረጎሙ። ይባስ ብለው በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የማዕድን ቁፋሮ የሚደረግበት አካባቢ “ኢየሱስ መጥቷል” የሚል ስዕል ስለው በታፔላ ሰቀሉ።
ስለዚህ ከ1966 ወዲህ አዲስ ዘመን ተከፈተ -- ይህም ዘመን የወንድም ብራንሐም ጥቅሶችን እየወሰዱ ከሃሳባቸው ጋር እንዲስማማ አድርገው ጠምዝዘው የሚተረጉሙበት ዘመን ነው።
አክራሪነትም በመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ ሐሰተኛ ዜና እንዲተካ አደረገ።
ፔሪ ግሪን የላይፍ መጽሔትን የጀርባ ሽፋን ፎቶ ኮፒ አንስቶ ለወንድም ብራንሐም አሳይቶታል። ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው የዛኔ ነበር።
ፎቶ ኮፒው ግን ትክክለኛ ኮፒ አልነበረም፤ ደመቅ ያሉ ፈዘዝ ያሉ ቦታዎች ነበሩት።
ወንድም ብራንሐም ይህን ፎቶ ኮፒ ሲያየው ሆፍማን የተባለ ጀርመናዊ ሰዓሊ የክርስቶስ ፊት ብሎ የሳለውን ስዕል አስታወሰው።
ወንድም ብራንሐም ከሞተ በኋላ ተከታዮቹ ይህንን የተነካካ ፎቶግራፍ አሳተሙ።
ከዚያም በኋላ እጅግ ብዙ ሰዎች ይህ ፎቶ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከፍላግስታፍ ከተማ ሰማይ ላይ የተነሳ እውነተኛ ፎቶ አድርገው አመኑ።
ፎቶው የክርስቶስ ፊት በደመናው ውስጥ ብቅ ሲል ያሳያል። ያ ፎቶም ቢሆን ከክርስቶስ ራስ በላይ ቀስተ ደመና ስለማያሳይ አላስደሰታቸውም። ከዚህ በታች የምታዩት በፎቶሾፕ ወይም እጅ ሥራ የተነካካ ምስል እንጂ እውነተኛ ፎቶ አይደለም።
ወደ ፎቶ እጅ ሥራው እንመለስ። አሁን የፎፍማን ስዕል ደመናው ውስጥ ሆኖ ይታያል።
በዚህ እጅ ሥራ ውስጥ የደመና ፎቶግራፍ ምን ያህል እንደተለወጠ አስተውሉ። ይህም የሜሴጅ ሰባኪዎች እግዚአብሔር በሰማይ ላይ ያሳየውን ምልክት በወንድም ብራንሐም ስሕተት ላይ ከተመሰረተ ትምሕርታቸው ጋር እንዲገጥም ብለው ምን ያህል እንደለወጡት ያሳያል።
ብራንሐም ደመናው በታየበት ከተማ ውስጥ ጭራሽም አልነበረም። ደመናው ከሳንሴት ማውንተን (ሳንሴት ፒክ) በላይ አልታየም።
ነገር ግን ለውጥ አንዴ ከተጀመረ ማቆሚያ የለውም።
ከራሱ በላይ በስሱ የተጨመረውን ቀስተ ደመና ተመልከቱ።
ቀስተ ደመናውስ መጀመሪያ አልነበረም፤ አሁን ከየት መጣ?
ደመናው በላይፍ መጽሔት ገጽ 112 ላይ ነበር የታተመው፤ በዚያው ገጽ ጀርባ ገጽ 113 ላይ የሆኖሉሉ ጨረቃ እና ቀስተ ደመና ፎቶ ነበረ። ራዕይ ምዕራፍ 10 ግን ስለ ጨረቃ ምንም አይናገርም።
እግዚአብሔር በኖኅ ዘመን የገባው ቃልኪዳን ምልክቱ በፀሃይ ብርሃን የሚፈጠር ቀስተ ደመና ነው።
እስቲ በገጽ 112 ጀርባ ላይ የታተመው የጨረቃዋ ቀስተ ደመና ገጽ 112 ኮፒ ሲደረግ ቀለሙ አልፎ ቅጂው ላይ ወጣ እንበል። እነደዚያ አይነት ነገር ቢፈጠር የሚወጣው ምስል ከዚህ በታች የምታዩትን ምስል አይነት ነው የሚሆነው።
ቀስተ ደመናው በጣም ፍዝዝ ይላል ምክንያቱም ልታዩት ከፈለጋችሁ የፊተኛውን ገጽ በኩል አልፋችሁ በጀርባው ያለውን ማየት አለባችሁ።
ግልጽ እንዲሆን ብለን ደመቅ ያለ ቀለም ያለውን ቀስተ ደመና እንሳልበት።
ፊቱ እንዲታይ ብለን ከፎቶኮፒው ላይ የነበረውን ጥላ ደመናው ውስጥ እንጨምርበት።
ግን ቀስተ ደመናው ያለቦታው ይመጣል። ከራሱ በላይ በመሆን ፈንታ በአንገቱ ትይዩ ይሆናል።
ፎቶሾፕ እጅ ሥራ ተጠቅመን ፊቱን እንጨምርበት።
ግን ጭንቅላቱ ወደ ጎን ይጋደማል። ወደ ላይ ቀጥ ብሎ አይቆምም።
ስለዚህ ፎቶግራፉን 90 ዲግሪ ወደ ቀኝ ማዞር አለብን።
አሁንም ግን ቀስተ ደመናው ከራሱ በላይ አይደለም። የደመናው ፎቶግራፍ ወደ ላይ ቀና ብሎ የቆመ ሰው ራስ እንዲመስል ተብሎ ዘጠና ዲግሪ እንዲዞር ተደርጓል።
ራሱ ወደ ላይ ቀና ብሎ ሲቆም ቀስተ ደመናው ከራሱ በላይ አይሆንም።
ይህም አተረጓጎም በራዕይ ምዕራፍ 10 መሰረት ፈጽሞ ስሕተት ነው።
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
ደመናውም በምድር ላይ የቆመ ሰውን ራስ አይወክልም። ምክንያቱም ደመናው ከ42 ኪሎሜትር ከፍታ አንዳችም ዝቅ ብሎ አልወረደም።
ደመናው ከምድር ጋር ትይዩ አግድም የተንሳፈፈ ሰውን ራስ ነው ሊወክል የሚችለው።
ደመናው በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ወደ ምድር የሚወርደውን መልአክ ሊወክል አይችለም።
የምድር ገጽ እንዴት ጠፍጣፋ እንደሆ ተመልከቱ። ደመናው ፎቶግራፍ በተነሳበት አካባቢ አንዳችም ሳንሴት ማውንተን የተባለ ተራራ የለም። ሳንሴት ማውንተን የተባለው ተራራ ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቆ ነው የሚገኘው።
ራዕይ ምዕራፍ 10፡1-3 ላይ ያለው ሃሳብ በስዕል ቢገለጽ ምን ይመስላል?
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥
ከመጀመሪያው ደመናው ምን ይመስል ነበር?
ደመናው በእርግጥ የራዕይ 10፡1-2 ቃል ፍጻሜ አይደለም።
ስለዚህ የተፈጠረው ስሕተት ምንድነው?
የሜሴጅ አማኞች ወንድም ብራንሐም ፈጽሞ የማይሳሳት ሰው መስሏቸዋል፤ ስለዚህ እምነታቸውን እርሱ በተናገራቸው ቃላት ላይ ብቻ መመስረት እንደሚችሉ አስበዋል።
ስለዚህ ከንግግሮቹ የወሰዱዋቸውን ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መፈተሽ እንዳለባቸው አላሰቡም።
ይህ ታላቅ ስንፍና ነው። ማንበብና በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መፈተሽ ትጋት የሚጠይቅ ሥራ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ለማወቅ ብቻ ብዙ ማንበብ ይጠይቃል።
በአንድ ርዕስ ላይ ሙሉ እውቀት ለማግኘት የሚጠቅሙትን ጥቅሶች በሙሉ ለማግኘት ደግሞ የበለጠ ጥረት ይጠይቃል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ነብይን ማረም አይቻልም ይላሉ።
ስለዚህ ነብዩ ከተሳሳተ ስሕተቶቹን እየደገምክ መቀጠል አለብህ። (እንዴት ያለ ቂልነት ነው።)
መላእክቱ ደመናው ከታየ ከ8 ቀናት በኋላ ነው ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡት። በመጡበት ቀን አንድም ደመና አልሰሩም።
ከዚያ በኋላ ከበድ ያለ ችግር ገጠማቸው። የተለያዩ ጥቅሶች ሲወሰዱ አንዳንዴ እርስ በራሳቸው ይጋጫሉ።
አንዳንዶች ደመናው የክርስቶስ ምጽአት ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ወንድም ብራንሐም ማርች 24 ቀን 1963 ስለ ሰባተኛው ማሕተም መገለጥ ሲሰብክ ጌታን ወደ ምድር አመጣው ይላሉ።
ስለዚህ ይህ ቀን ከደመናው መታየት አንድ ወር አልፎ እንደመሆኑ መጠን ለጌታ ምጽአት የተለያዩ ቀኖች ተነግረውናል።
63-1110M አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት
ሰባተኛው ማሕተም ጌታን ወደ ምድር ያመጣዋል።
ነገር ግን አሁንም አስቸጋሪ ነገር አለ፤ ምክንያቱም ብራንሐም ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም ብሏል፤ ስለዚህ ማሕተሙ ምስጢር እንደሆነ ቀርቷል።
64-0719M የኢዮቤልዩ በዓል
ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም። ሲፈታ ጌታ ይመጣል።
ከዚያም በሕይወቱ የመጨረሻ ዓመት ላይ የጌታን ምጽአት እስካሁን እየተጠባበቅሁ ነኝ ብሏል።
65-0725 ተራራው ላይ ያለው መስህብ ምንድነው
ወደ ተራሮቹ ሰላምታ እንልካለን፤ ፕሬስኮት አሪዞና ውስጥ ወንድም ሊዮ መርሲየ እና የእርሱ ቡድን ተራራው ላይ ወጥተው የጌታን መምጣት ይጠባበቃሉ። በታክሶን ለተሰበሰቡት ሰላምታንን እንልካለን፤ የጌታን ምጻት ለመጠባበቅ በዚያ ተሰብስበዋል። ደግሞም በሒውስተን ቴክሳስም ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት። እዚያ ቺካጎ ውስጥ ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም። በምሥራቅ በውቂያኖሱ ዳር ኒው ዮርክ ውስጥ እና ኮኔቲከት ውስጥ ለተሰበሰቡትና የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም። እዚህ ቢመጡ ለእነርሱ የሚሆን መቀመጫ ቦታም የለንም። ስለዚህ በስልክ በመጠቀም ቃሉን እንልክላቸዋለን። ዛሬ ማታ በክላርክስቪል ለተሰበሰቡት ለወንድም ጁንየር ጃክሰን እና ለቡድኑ እንዲሁም ለወንድም ራድል እና አብረውት የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ቡድኖቹ ሰላምታ እንልካለን።
እኛም ደግሞ ዛሬ ማታ እዚህ በቤተክርስቲያን በተሰበሰብንበት የጌታን ምጻት እንጠባበቃለን።
ስሕተት ግን ባለበት ቆሞ አይቀርም። ስሕተት ልክ እንደ ቫይረስ መልኩን እየቀየረ ይባዛል።
“ደመናው የጌታ ምጽአት ካልሆነ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መሆን አለበት።”
የሜሴጅ ሰባኪዎች ከፍላግስራፍ በስተ ምስራቅ ሰማይ ላይ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ለ28 ደቂቃዎች የታየው ደመና የሰማይ ምልክት ብቻ መሆኑን ለማመን እምቢ አሉ።
ይህ ደመና የግድ ከሰማይ ምልክትነት ያለፈ ተዓምር እንዲሆን ፈልገዋል።
ስለዚህ በታላቅ ከፍታ ላይ የታየው ደመና በድንገት የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ እንደሆነ ተቆጠረ። እንደዚያ ቢሉም እንኳ ደመናው ግን ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ወደ ምድር አልወረደም።
ሰባቱ መላእክት ማርች 8 ቀን 1963 ሲወርዱ አንዳችም ደመና አልሰሩም -- ወደ ምድር ሲወርዱም ሆነ ተመልሰው ወደ ሰማይ ሲወጡ ደመና አልፈጠሩም።
አንዳንዶች ደመናው መልአኩ አይደለም አሉ። ግን የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ደግሞ ወርዷል አሉ። ሆኖም መልአኩ መች ወይም የት ቦታ እንደወረደ ግን እግርጠኛ አይደሉም።
ሁላቸውም ግን ወንድም ብራንሐም ምድር ላይ በሕይወት ሳለ መልአኩ ወርዷል ብለው አጥብቀው ያምናሉ።
ይህም ትልቅ የስሕተት ትምሕር ለመመስረት ይጠቅማቸዋል።
መልአኩ ወርዶ ከሆነ እንኪያስ ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ደግሞ ሕዝቡ እንዲያምኑላቸው የሚፈልጉት ይህንኑ ነው፤ ምክንያቱም ሰባቱ ነጎድጓዶች ተናግረዋል ከተባለ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈውን ይኸው የተናገሩት ቃል ብለው “ለመግለጥ” ያመቻቸዋል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች እዚህ ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነግጣሉ፤ ብዙዎቹ የሜሴጅ ቡድኖች ጥቅሶችን እና ጠምዝዘው የተረጎሙዋቸውን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ ማድረግ ለምደዋል።
ልክ የመጀመሪያውን በ1963 የተነሳውን ኦሪጅናል የደመና ፎቶግራፍ በእጅ ሥራ ነካክተው እንደለወጡት ጥቅሶችንም ወደፈለጉት ሃሳብ ይጠመዝዛሉ።
ታዲያ ለምንድነው ሁለት ደመናዎች የኖሩት?
63-0623 ቅጥር በፈረሰበት በኩል መቆም
እርሱም ወደ ተራራ ወጣሁ አለ። ወደ ተራራው በወጣም ጊዜ እኔ በዚያ ቆሜ ነበር። ከደመናውም ድምጽ መጣ (ወንድም ሮይ አልነበረም?) እና እንዲህ አለ “ይህ ባሪያዬ ነው። ለዘመኑ ነብይ እንዲሆን፤ ሙሴ ሕዝቡን እንደ መራ ይህን ሕዝብ እንዲመራ ጠርቼዋለው። የሌለ ነገር ተናግሮ መፍጠር በሚችልበት ሥልጣን እንዲናገር ተሰጥቶታል።”
ወይም ከዚያ ጋር ተቀራራቢ ነገር ነው የሰማሁት፤ እንደ ሙሴ ለምሳሌ ተናግሮ ዝንቦች እንዲመጡ እንዳደረገው። ደግሞ ስለ ጥርኞቹ እና ስለ ሌሎችም የተከሰቱ ነገሮች በተመለከተ እናውቃለን። ሃቲ ራይት የምትባይው ኋላ የተቀመጥሽው ትንሽ ልጅ፤ እቤት ውስጥ ምን እንደተፈጠረ ታውቂያለሽ ብዬ አምናለው። እርሱም ሙሴ ያደረገውን እኔም እንዳደረግሁ ነገረው።
ሚልክያስ 4፡4 ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።
5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
የሙሴ አገልግሎት በሆነ መንገድ ከወንድም ብራንሐም አገልግሎት ጋር ይያያዛል።
ሙሴ እሥራኤል ከግብጽ የወጡበትን የመጀመሪያውን የሕዝብ መውጣት መርቷል። በዚያ ዘመን ሕጻናት በፈርኦን ተገድለዋል። ጉዞው በሁለት ክፍል ነበር የተደረገው። መጀመሪያው ሙሴ ሕዝቡን እስከ ተስፋይቱ ምድር ድንበር ድረስ አደረሳቸው። ከዚያም ሙሴ ሲሞት ኢያሱ ተረከና ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር አገባቸው። ከታች ባለው ካርታ ውስጥ ቀዩ መስመር በሙሴ አማካኝነት የወጡበትን የመጀመሪያውን ጉዞ ያመለክታል።
ዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ሲደርሱ ኢያሱ መረከቡ ፋይዳው ምንድነው?
ዮርዳኖስ “ለራስ መሞትን” ያመለክታል።
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ውስጥ ነው የተጠመቀው።
ጥምቀት የሞት ምሳሌ ነው። ከውሃ በታች ሆናችሁ መተንፈስ አትችሉም።
61-0316 ቤተክርስቲያን ከጸጋ ይልቅ ሕግን ስትመርጥ
“ዮርዳኖስ” ማለት “ሞት” ነው።
ከመሻገራችሁ በፊት ለራሳችሁ መሞት አለባችሁ። ሄዳችሁ ብታዩ ሰዎች ለብ ያለ ሕይወት ሲኖሩ ትመለከታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚያው ብሏልና።
እዚያ ተራራው ላይ ያሉ ወንድሞች የተባረኩ ነበሩ። በልጽገዋል። የሚበሉት ተትረፍርፎላቸዋል። መና ከሰማይ ይወርድላቸው ነበር። መና መውረዱ ጥሩ ቢሆንም ግን ተስፋቸውን ገና አልወረሱም። ልክ እንደ ሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የፔንቲኮስታል ቤተክርስቲያን ዘመንም እንደዚያው ነው። በረከት በዝቶላቸዋል። እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ጋር አይደለም፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊያስገባቸውም አልቻለም፤ ምክንያቱም እነርሱ ለራሳቸው ሃሳቦች መሞታቸውን የሚገነዘቡበት ቦታ እስኪደርሱ ድረስ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ዝግጁ አልነበሩም። ከዚያም እግዚአብሔር ተቀበላቸው።
ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሊገልጥልን ብቻ ነው የሚችለው።
እኛ ግን በየግላችን መሞት እና እግዚአብሔር ለመሻገር እንዲያስችለን መፍቀድ አለብን።
ስለዚህ ኢየሱ መንፈስ ቅዱስን ይወክላል።
60-0515E ልጅነት ክፍል 1
የኛ ኤፌሶን ወይም የእኛ ኢያሱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
“ኢያሱ” ማለት “ኢየሱስ፣ አዳኝ” ነው።
ኢየሱ ማለት መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፤ ኢያሱ መንፈስ ቅዱስን በፍጥረታዊውም በመንፈሳዊውም ዓለም ይወክለዋል፤ ማለትም መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ የሚዋጋ ነው። እርሱ ታላቁ መሪያችን ነው። እግዚአብሔር ከኢያሱ ጋር እንደነበረ ሁሉ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በመካከላችን እየተንቀሳቀሰ ነው።
ሁለተኛው ፍልሰት ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ከአይሁዶች መካከል ያወጣበት ነው። በዚያ ጊዜ ሔሮድስ አይሁዳውያን ሕጻናትን ገደለ። ኢየሱስ ሞተና ከሞት ተነሳ። ከዚያም ምድርን ትቶ ሲሄድ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተመዘገበውን ታሪክ ሊሰራ እና ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሊመራት መጣ።
ሦስተኛው ፍልሰት ሙሽራይቱ ከቤተክርስቲያን ለቅቃ መሄዷ ነው።
እኛ ወደ በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ ነበሩ ሐዋርያት አባቶች እምነት መመለስ ያለብን መንፈሳዊ ልጆች ነን።
ወንድም ብራንሐም የተናገራቸውን ጥቅሶች እየወሰዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወዳልሆኑ እምነቶች የሚጠመዝዙ ሰዎች መንፈሳዊ ልጆችን በታላቁ መከራ በኩል ወደ ሞት እየነዱዋቸው ነው። ዛሬ በዓለም ላይ ስንት የተለያዩ “የሜሴጅ” ትምሕርት አይነቶች እንዳሉ ተመልከቱ። እንዲህ ሁሉ ተለያይተው ሁላቸውም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። ብዙ ሰዎች በእነርሱ እየተታለሉ ነው።
እስከ 1965 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት አንብበን እንደምንረዳ አሳይቶናል። ከዚያም እርሱ ከሄደ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንደ ኢያሱ እየመራን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት እንመለስ ዘንድ ወደ እውነት ሁሉ ሊያደርሰን ይገባል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
ዛሬ ብዙ የሜሴጅ ሰባኪዎች ስለ ራሳቸው ብዙ ያወራሉ፤ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
ዳንኤል 11፡14 በዚያም ዘመን ብዙ ሰዎች በደቡብ ንጉሥ ላይ ይነሣሉ፤ ከሕዝብህም መካከል የዓመፅ ልጆች ራእዩን ያጸኑ ዘንድ ይነሣሉ፤ ነገር ግን ይወድቃሉ።
የዚህ ትንቢት ትርጉም ምንም ይሁን ምን መሪዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደርጉ ዘንድ ሰይጣን እንደሚገፋፋቸው ያሳያል። ከዚያ በኋላ ሰዎች ዓይናቸውን ከክርስቶስ ማለትም ከቃሉ ዞር ያደርጉና ወደ መሪዎቻቸው ይመለከታሉ። በዚህም መንገድ መሪዎች ሕዝቡ ከክርስቶስ እን ከእውነት ጋር በግል ያላቸውን ሕብረት ያስጥሉዋቸዋል። ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመራት ሲያቆሙ ነጠላ ዜማቸው “መሪዬን ተከተል” የሚል ይሆናል።
የእኛ ኢያሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ በምናምነው ትምሕርት ውስጥ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መከተል አለብን።
ሰዎች የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን አለማወቅ ስለሚከተሉ ብዙም የሚጠባበቁት ነገር የለም። መሪዎቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን ስለማያስተውሉ ሕዝቡም መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተዋልና ለማወቅ ተነሳሽነት የላቸውም።
የራሳችንን አስተሳሰብ ለማጠናከር ብለን እውነታውን እንጠመዝዘዋለን። በስተመጨረሻ አስሩም ቆነጃጅት ልባሞቹም ሆነ ሰነፎቹ እንቅልፋቸውን ይተኛሉ።
በዚያ የጠፈር መመልከቻ ማዕከል ውስጥ ሆነው ምን እንደተፈጠረ በማሰብ ሲገረሙ ነበር። ታክሰን ውስጥ ያሉ ታላላቅ የጠፈር መመልከቻ ማእከሎች ፎቶ አንስተውታል። ቢሆንም ግን ምን እንደሆነ ሊያውቁ አልቻሉም።
በጋዜጦችም ውስጥ “ይህ ክስተት ምን እንደሆነ ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን?” እያሉ በመጠየቅ ይጽፉ ነበር። በዚያ ከፍታ ላይ አንዳችም ጉም ሊኖር አይችልም፤ አየርም የለም፣ እርጥበትም የለም። ደመናው የታየው ከምድር በአርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ነበር፤ ይገርማል።
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህም ነገሮች ሲሆኑ፣ በልዩ ልዩ ቦታዎችም የምድር መናወጥ በሚሆንበት ጊዜ በሰማይ ላይ ምልክት የሰው ልጅ ምልክት ይታያል።” “በዚያ ቀን” በሉቃስ ውስጥ እንደሚለው “የሰው ልጅ እንደገና ራሱን ይገልጣል፤ እራሱ ይገለጣል።”
በሕይወቱ የመጨረሻ ዓመት ውስጥ ወንድም ብራንሐም ታላቁ ደመና ምልክት ነው ብሎ ነበር።
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል።
ምልክት የሆነው ደመና ከምድር በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ነበር የታየው። ከዚያ ከፍታ ወደ ታች ዝቅ አላለም።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 መላእክት ወደ ምድር አልወረዱም ወደ ሰማይም አልወጡም። ሰባት መላእክት ለ28 ደቂቃ ብቻ ክንፎቻቸውን ተጠቅመው ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ደመናውን ፈጠሩ፤ ያም ቦታ ወንድም ብራንሐም በሰዓቱ ከነበረበት ከ ታክሰን 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ራቅ ያለ ነበር።
እርሱም ስለ ደመናው አንዳች አላወቀም።
ደመናው የእርሱን ትኩረት ለመሳብ አልነበረም የተፈጠረው። ደመናው ትኩረት የሳበው ወደ ፊት ስለሚገለጡት ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ የኢየሱስ መንገድ ጠራጊ ስለነበረ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ነበረ።
ወንድም ብራንሐም ግን መንገድ ጠራጊ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስን የገለጠበት መልእክት ግን ሙሽራዋ ጌታ ሲመጣ እንድትቀበለው ያዘጋጃታል።
ድምጹ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራት ይገልጥ ዘንድ በሕዝብ ሁለ ዘንድ ይደመጣል።
59-1217 መንፈስ ቅዱስ የተሰጠው ለምንድነው
“መጥምቁ ዮሐንስ ለክርስቶስ የመጀመሪያ ምጽአት መንገድ ሊጠርግ እንደተላከ ሁሉ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት መንገድ የሚጠርግ መልእክትም ይደርሳችኋል።”
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
መጽሐፉን ይወስዳል… ከዚያም ማሕተሞቹን ይፈታና ለሰባተኛው መልአክ ያሳየዋል በዚህ ምክንያት ብቻ የእግዚአብሔር ምስጢር የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት ሆኗል።
ዊልያም ብራንሐም የተባለው ግለሰብ ሳይሆን በእርሱ አማካኝነት የተገለጠው እውነት።
ዊልያም ብራንሐም የተባለው ሰው ከ50 ዓመታት በፊት በሞተ ጊዜ አሁን በሕይወት ያሉት የሙሽራዋ አካል የሆኑት ሰዎች ገና አልተወለዱም ነበር። ነገር ግን ዛሬ ሁላቸውም ድምጹን ይሰማሉ፤ ስብከቶቹንም ያነባሉ።
ነገር ግን ሌላ አነስ ያለ ሁለተኛ ደመናም ነበረ። ይኸውም ከታላቁ ደመና ኋላ 20 ማይልስ ያህል ራቅ ያለ ትንሽ ደመና ነበር።
ከምድር በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ በታየው የጭስ ደመና በኢዮኤል ትንቢት የተነገረው የሰማይ ምልክት ማለትም የጢስ ጭጋግ ተፈጽሟል። ከውሃ ትነት የተፈጠረ ደመና ሳይሆን በከፍታ ላይ የሚሆን ሰው ሰራሽ የጭስ ደመና ነው።
ኢዮኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።
ለሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ከቤተክርስቲያን የመውጣት ፍልሰት የተሰጠ የሰማይ ምልክት ፍጥረታዊ የጭስ ደመና እንዲሁም ልዕለ ተፈጥሮአዊ የመላእክት ደመናም ነበር። ፍጥረታዊ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው በአንድነት።
የመጀመሪያው የሙሴ እና የኢያሱ ፍልሰት በምልክት ነበር የጀመረው። በሲና ተራራ (ወይም በኮሬብ ተራራ ደግሞም የእግዚአብሔር ተራራ ተብሎም የሚጠራው) ላይ የነበረው ቁጥቋጦ (ተፈጥሮአዊ) እና ቁጥቋጦው እየነደደ አለመቃጠሉ (ልዕለ ተፈጥሮአዊ)።
ፍጥረታዊ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው በአንድነት።
ከዚያ በኋላ ሙሴ አይሁዶችን ከግብጽ ይዞ ወጣ ኢያሱ ደግሞ ወደ ተስፋይቱ ምድር አገባቸው።
ዘጸአት 3፡1 ሙሴም የዮቶርን የአማቱን የምድያምን ካህን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ ወደ ምድረ በዳ ዳርቻም በጎቹን ነዳ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
3፡2 የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።
ሁለተኛው ፍልሰት በምልክት ነው የጀመረው። ይህም ምልክት በልዕለ ተፈጥሮአዊ መንገድ ከድንግል ማሕጸን የተወለደ ሕጻን በግርግም መወለዱ። ፍጥረታዊ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው በአንድነት።
ኢየሱስ ቤተክርቲያንን ከይሁዲነት ውስጥ ይዟት ወጣ። ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መራት።
ሉቃስ 2፡12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
ሦስተኛው ፍልሰት የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት የተገለጡበት የብራንሐም መልእክት እኛን ከቤተክርስቲያኖች የሚያወጣበት ነው። የተገለጡት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት-ምስጢራት ወደ ሐዋርያዊ አባቶች የመጀመሪያ እምነት ሊመልሱን ይገባል። ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት እንመለስ ዘንድ ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራት ለማብራራት የሰባቱን ማሕተሞች ትርጉም ገልጧል። ስለዚህ የእርሱ የሰማይ ምልክቶች ከምድር እጅግ በራቀ ከፍታ ላይ የተገለጡት ደመናዎች ናቸው። እነዚህም ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና እና አየር ላይ ከፈነዳው ሮኬት የወጣው ተፈጥሮአዊ የጭስ ደመና ናቸው። ይህም ልክ ሙሴ በቁጥቋጦው ውስጥ ሲነድ እንዳየው ልዕለ ተፈጥሮአዊ እሳት ነው።
ነገር ግን ትምሕርቶቹን በተሳሳተ መንገድ ከተረዳናቸውና ከጠመዘዝናቸው መጨረሻችን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያላመነችውን ነገር አምነን መቅረት ነው።
ይህ ምስል ፎቶግራፍ አይደለም ግን ፀሃይ በምትጠልቅበት ሰዓት ጨረሯ ሁለት በትልቅ ከፍታ ላይ ያሉ ሁለት ደመናዎችን ጨረሯ እንዴት አንጸባርቆ እንደሚያሳይ ያሳያል። የሰዎችንም ትኩረት የሳበው ጠቆር ካሉት ተፈጥሮአዊ ደመናዎች በላይ እነዚህ ሁለት ደመናዎች እጅግ ርቀው ከፍ ማለታቸው ነው።
ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና የሠሩት ሰባቱ መላእክት ከስምንት ቀናት በኋላ ወርደው ወደ ወንድም ብራንሐም በመምጣት የሰባቱን ማሕተሞች ትርጉም እንዲገልጥ ትዕዛዝ ሰጡት። በዚያን ዕለት ሰባቱ መላዕክት በሰው ዓይን አይታዩም ነበር። ደመናም አልተፈጠረም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት መገለጥ በግላችን እምነት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሕብረት እንዲኖረን ለማበረታታት ነው።
ሚልክያስ 4፡4 ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።
4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች ልጆች ሲሆኑ እነርሱም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ጻፉት ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት መመለስ አለባቸው።
ሙሴ መሪነቱን ለኢያሱ አስረከበ። ወንድም ብራንሐም ደግሞ ሲሞት እኛን ለመንፈስ ቅዱስ አሳልፎ ሰጠ፤ ዛሬ ምስጢራቱ ከተገለጡ በኋላ እያንዳንዳችንን በግል መጽሐፍ ቅዱስን እንድናስተውል ሊረዳን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን [በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ይላል] መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ልብ በሉ -- የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መሆኗ ቀርቷል። የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሆናለች። እያንዳንዱ ቡድን ለመልእክቱ የራሱን ትርጓሜ እየሰጠ ይሄዳል። የተሰወኑ ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች፣ በጣም ጥቂት የእግዚአብሔር ቃል እና በጣም ብዙ ሰው ሰራሽ አስተሳሰቦችን ተጠቅመው ነው የሚያስተምሩት። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ለየራሳቸው የሚያመቻቸው አመለካከት አላቸው።
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ከእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል።
ኢየሱስ በየቤተክርስቲያኑ ያለው የተለያየ የቡድን አስተሳሰብ አያስደስተውም።
አሁን ጥሪ የሚያቀርበው በቃሉ መሰረት ሊከተሉት ለሚፈሉጉ ግለሰቦች ነው።
የሦስተኛው ፍልሰት የመጨረሻ ደረጃ ግለሰቦች በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ብቻ ለመቆም የሚያበቃ መረዳት እና ቆራጥነት ሲኖራቸው ነው።
ስለ መጨረሻው ዘመን የሚናገር ሌላ ቃል የቤተክርስቲያኖችን መከፋፈል እና ከጌታ ጋር በግል ሕብረት የማድረግን አስፈላጊነት በተመለከት ይገልጻል። የግል ሕብረት እንጂ የቡድን የቤተክርስቲያን ልምምድ አይደለም።
ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።
2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
ባቢሎን ማለት በብዙ ልዩ ልዩ ስሞች የምትጠራው በሰዎች መሪነት የምትተዳደረዋ ቤተክርስቲያን ናት። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውን እንዲያምኑ ይገደዳሉ።
መልአክ ወይም መልእክተኛው በሰዎች ስለምትገዛዋ ሕዝቡ በመጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ ከሰዎች ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችንና ወጎችን እንዲያምኑ ስለምታስገድደዋ ቤተክርስቲያን በተመለከተ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል።
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
(በዚህ በሦስተኛውና ምስጢራዊው ፍልሰት ውስጥ) “ሕዝቤ ሆይ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ” የሚለን መልአኩ አይደለም። ይህ ከምድር ላይ ከሆነ ቦታ የመጣ የሰው ድምጽ አይደለም። ድምጹ የሚመጣው ከሰማይ ነው።
ሌላም ድምጽ ነበረ። ሌላኛውም ድምጽ በውስጣችን የምንሰማው የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ነው።
ምክንያቱም በሎዶቅያውያን በተፈጠረችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ከውስጧ ሳይሆን ከውጭ ቆሞ ግለሰብን ነው ወደ ራሱ የሚጠራው። ይህ ሊሆን የቻለው የእግዚአብሔር ቃል በሰው ንግግርና በሰው አመለካከቶች ስለተተካ ነው። አንድ ሰው ኢየሱስን ለማግኘት ከፈለገ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካለሆኑት የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችና እምነቶች ተነጥሎ መውጣት አለበት።
በመጨረሻው ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር የሚፈልገው የቤተክርስቲያን ልምምድ አይደለም። እግዚአብሔር የሚፈልገው እያንዳንዱ ግለሰብ ከእርሱ ጋር በግል ሕብረት እንዲያደርግ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ለብ ያለች መሆንዋን ያውቃል፤ ደግሞም ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወስዳ ከጥቂት የሰው ንግግር ጥቅሶች ጋር እና ከብዙ የሰው አመለካከቶች ጋር እንደምትቀላቅልም ያውቃል።
ከዚህም የተነሳ በአንድ ቡድን ውስጥ አባል ለመሆን በመፈለግህ ምክንያት በሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ይደረግብሃል። ባቢሎን የምትለመልመው ሰዎችን በግዴታ እንዲገዙላት በማስገደድ ነው። በዚህ አይነት ሂደት ውስጥ ከኢየሱስ ጋር በግል የሚኖርህን ሕብረት ታጣዋለህ።
ሦስተኛው ፍልሰት ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ያደረገው አገልግሎት ብቻ አይደለም።
የመጀመሪያው ፍልሰት ሙሴ ከሞተ በኋላ በኢያሱ አማካኝነት ቀጠለ።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
መጽሐፉን ይወስድና … ማሕተሞቹንም ይፈታቸዋል ከዚያም ለሰባተኛው መልአክ ያሳየዋል፤ ይህ ብቻ ማለትም የእግዚአብሔር ምስጢራት ብቻ ነው የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት።
65-0725 የተቀባው በዘመኑ መጨረሻ
አስተውሉ፤ ይህ መልእክተኛ መልእክቱን በሚጀምርበት ቀን … ማገልገል ሲጀምር አላልኩም፤ መልእክቱን ማወጅ ሲጀምር እንጂ። አያችሁ? የመጀመሪያው የፍልሰት ጥሪ በፈውስ፤ ሁለተኛው የፍልሰት ጥሪ ደግሞ ትንቢት በመናገር፤
ሦስተኛው የፍልሰት ጥሪ ደግሞ የቃሉ መተርተር፣ የምስጢራቱ መገለጥ።
ከነብያት በላይ ቃሉን ለመግለጥ ከነብያት የሚበልጥ ስልጣን ማንም የለውም።
ነብዩ ግን እውነተኛነቱ የሚረጋገጥለት በቃሉ ብቻ ነው።
ደግሞም አስተውሉ፤ ሦስተኛው የፍልሰት ጥሪ የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት ነው፤ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታትሞ የነበረውን እውነት ለመግለጥ ነው።
65-0725 የተራራው መስህብ ምንድነው
ስለዚህ ልቤን በዚህ መልእክት ላይ አድርጌያለው፤ እርሱም ሦስተኛው የፍልሰት ጥሪ ነው፤ እኔም ለዚህ አገልግሎት ታማኝ እና አክባሪ መሆን አለብኝ።
ስለዚህ ሦስተኛው ፍልሰት የሚከናወነው መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነቶች ሲመራ ነው።
ያም የሚሆነው ማሕተሞቹ በተፈቱ ጊዜ ወንድም ብራንሐም የማሕተሞቹን ጥልቅ ሚስጥር ገልጦ ሲያስተምር ነው።
ስለዚህ የጭሱ ደመና (ፍጥረታዊው) እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና በአንድነት በሰማይ ላይ ሆነው ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን ሊገልጥ እንደተላከ መስክረውለታል፤ እንዲሁም ለሙሽራዋ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው ማስተዋልና መረዳት የሚችሉበት መገለጥ ሊሰጣቸው እንደተላከ ደመናዎቹ መስክረውለታል።
መጽሐፍ ቅዱስን በግልህ በሙሉ ልብ እርግጠኛ ሆነህ ማመን አለብህ፤ እንጂ ሌሎች ሰዎች ስለተናገሩዋቸው ነገሮች ብለህ መሆን የለበትም።