ዮሐንስ ምዕራፍ 05. አማኞች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የሐይማኖት መሪዎችን ይመርጣሉ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ምዕራፍ አራት ውስጥ ኢየሱስ በክረምት ከመከር ወቅት አራት ወር በፊት ሰማርያ ውስጥ ነበረ። መከር ማለት ዘሩ ከተክሉ ላይ ተቀጥፎ የሚወሰድበት ጊዜ ነው። በመከር ጊዜ ቀድሞ የሚደርሰውና የሚታጨደው ሰብል ገብስ ነበር። በሚያዚያ አጋማሽ አካባቢ የገብስ መከር በዓመቱ ዋነኛው በዓል በፋሲካ ጊዜ ይታጨዳል። ይህም ለሰባት ቀናት ከሚከበረው ከቂጣ በዓል ጋር በአንድ ላይ ነበር የሚከበረው። በተጨማሪም ቀድሞ የሚታጨደው የመጀመሪያው ገብስ የበኩራት በዓል ይከበርበታል።
ፋሲካ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ በቀራንዮ የመገደሉ ጥላ ነው። የበኩራት በዓል ትንሳኤውን ይወክላል፤ በዚህም በዓል ጊዜ ኢየሱስ ከስስት ቀናት በኋላ ከሙታን በኩር ሆኖ ተነሳና ከዚያም ከመቃብራቸው ወጥተው የተነሱትን የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በትንሳኤው አስከትሎ አስነሳቸው። ከዚያ በኋላ ከሙታን የተነሱት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ኢየሱስ ከትንሳኤው አርባ ቀን በኋላ ወደ ሰማይ ባረገበት ቀን ከምድር ላይ ተሰብስበው ወደ ሰማይ ሲወሰዱ እና ከእርሱ ጋር እንደ ደመና ሲገለጡ የመከሩ ጊዜ ተጠናቀቀ። ስለዚህ የብሉይ ኪዳን የመከር አጨዳ ለአርባ ቀናት ነው የተከናወነው። በዚህ የመከር ጊዜ ውስጥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከምድር ውስጥ በትንሳኤ ተነቅለው ወጡ፤ ከዚያ በኋላ ከምድር ላይ ታፍሰው ወደ ሰማይ ተወሰዱ። በዮሐንስ ምዕራፍ አራት ውስጥ ኢየሱስ በሰማሪያ በነበረ ጊዜ ያየው የነጣ እርሻ እና ለመታጨድ የደረሰው መከር ይህ ነው።
የቂጣ በዓል የሚከበርባቸው ሰባቱ ቀናት ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሊመራት የሚመጣውን መንፈስ ቅዱስን የሚወክሉ ነበሩ።
የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዓመት በዓሎች የሚከበሩባቸው ቀናት የተቀራረቡ ነበሩ። ከፋሲካ ሃምሳ ቀናት ካለፉ በኋላ የስንዴ መከር በጴንጤ ቆስጤ በዓል አካባቢ ይደርሳል። ይህም በዓል መንፈስ ቅዱስ ደቀመዛሙርቱን በመሙላት የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ያስጀመረበትን የበዓለ ሃምሳ ቀን ይወክላል። እነዚህ ከልባቸው የተሰጡ አማኞች ዘሮች ስለነበሩ የመጨረሻው ዘመን አማኞች ልክ እነዚህን እንዲመስሉ ነው መመለስ ያለባቸው።
የሚታጨደው ዘር ልክ የተዘራውን ዘር መምሰል አለበት።
ከዚያ በኋላ በመሃል ጥቂት ወራት እና ሁለት በዓላት አሉ፤ እነርሱም ኢዮቤልዩ እና የዳስ በዓላት ሲሆኑ ሁለታቸውም ከስርየት ቀን ጋር በጥቅምት ወር ውስጥ ነው የሚከበሩት። የወይን መከር የሚደርሰው በዚህ ወቅት ነው።
በታላቁ መከራ ጊዜ አይሁዶች ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ የሚጠሩቸው ሁለቱ መለከቶች ሁለቱን ነብያት ሙሴ እና ኤልያስን ይወክላሉ። የስርየት ቀን 144,000ው አይሁዳውያን ኢየሱስን ፊት ለፊት የሚገናኙበትና በእጆቹ ላይ ያሉትን የችንካር ምልክቶች የሚያዩበት ቀን ነው። የዳስ በዓል ሚሌንየም በሚባለው ጊዜ ውስጥ በ1,000 ዓመቱ የሰላም ዘመን ውስጥ አይሁዳውያን ለራሳቸው የሚሰሩዋቸውን ቤቶች ይወክላል።
ዮሐንስ 5፡1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
ክረምቱ አልፎ እርሻዎች ለመከር የደረሱበት እና ገብስ የሚታጨድበት ጊዜ ነበረ። ይህ በዓል ከዓመቱ የመጀመሪያው የሆነው የፋሲካ በዓል ወይም ፋሲካን ተከትለው ከሚመጡት በዓላት አንዱ ነበረ።
ዮሐንስ 5፡2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።
ቤተሳይዳ ማለት “የምሕረት ቤት” ነው። ምሕረት የእግዚአብሔር ጸጋ ምልክት ነው፤ ይህም ለሰው የማይገባው የእግዚአብሔር መልካምነት ነው ምክንያቱም ራሳችንን ማዳን አንችልም። የምንቀበለው ምሕረት የመጣው ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ከተሰዋበት መስዋእትነት ነው። ሁለቱ እጆቹ እና እግሮቹ በሚስማር ተቸንክረዋል። ጎኑን በጦር ተወግቷል። በአጠቃላይ አምስት ከባድ ቁስሎችን ቆስሏል። ስለዚህ አምስት ቁጥር ሁልጊዜ ጸጋን እና ምሕረትን የሚወክል ቁጥር ሆኗል። ኢየሱስ ስለ እኛ ሐጥያት የከፈለውን ዋጋ እንድናስታውስ እነዚያን አምስት ጠባሳዎች ሁልጊዜም በአካሉ ላይ ተሸክሟቸው ይኖራል።
አራት ወንጌሎች ከሐዋርያት ሥራ ዙርያ ቆመዋል። ወንጌሎቹ በሐዋርያት ስራ ውስጥ የተገለጠችዋ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ምሕረት መስበክ ከመጀመሯ በፊት ክርስቶስ እንዴት መንገድን እንዳዘጋጀላት ይናገራሉ።
ውሃ እግዚአብሔር የሕዝቡን እምነት እና ልማድ አጥቦ የሚያነጻበትን ቃሉን ይወክላል።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
የቤተሳይዳ መጥመቂያ የምሕረት ቤት ሰዎች ወደ ውሃው ውስጥ የሚገቡበት አምስት መተላለፊያዎች ነበሩት።
በራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ዮሐንስ ከእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት ወይም ሕያዋን ፍጥረታት አይቷል።
እነዚህ አምስቱ እግዚአብሐየር በ2,000 ዓመታት ውስጥ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ የሚያቆምበትን ኃይል ይወክላሉ።
አንበሳው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የተዘራውን እውነተኛውን የሐዋርያት ቃል ይወክላል። በሬው በጨለማው ዘመን ብዙ የለፉትን እና በብዙ ቁጥር የተገደሉትን ክርስቲያኖች ትጋት ይወክላል። በዚያ ዘመን ከአስር ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ተገድለዋል። ሰውየው እንደ ሉተር እና ዌስሊ ያሉ የተሃድሶ መሪዎችን ጥበብ ይወክላል፤ እነርሱም ቤተክርስቲያንን በእምነት መዳን ወደሚለው እውነት ከመመለሳቸውም በላይ ቅድስናን እና ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን እንዲመጣ ያደረገውን የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው አምጥተዋል። ንስሩ ደግሞ በጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራዊ ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው መምጣታቸውን ይወክላል። በተጨማሪ የንስሩ አርቆ እና አጥርቶ ማየት የሚችል ዓይን ለዘመን መጨረሻ የተላከው ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መረዳት እንዲችል ዓይኑን ይከፍትለታል፤ ደግሞም የእነዚህ ሚስጥራት መገለጥ ብቻ ነው በዘመን መጨረሻ ላይ ያሉትን አማኞች የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያት ወዳመኑት እምነት ሊመልሳቸው የሚችለው።
ከዲኖሚኖሽኖች ተጽእኖ የተነሳ ወደ ልባችን ውስጥ የገባው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያለን ጥርጣሬ በቃሉ አማካኝነት ታጥቦ ሊወጣ የሚችለው በእነዚህ አምስት በሮች ብቻ ነው። እነዚህም በመካከል ላይ በዙፋኑ ወደተቀመጠው ወደ እግዚአብሔር ኃይል የሚያደርሱ አራት መንፈሳዊ ኃይላት ናቸው።
እያንዳንዱን የቤተክርስቲያን ዘመን አንድ እንስሳ ወይም አንድ ሕያው ፍጥረት ብቻ ነው እየመራ ያንን ዘመን ወደ እግዚአብሔር ዙፋን የሚያቀርበው። ንስሩ ለእኛ የተላከ መልአክ ወይም መልእክተኛ ነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር እውነት ወደተጀመረበት በተሃድሶ ተመልሶ ወደመጣው ወደ አንበሳው ቃል ዘመን ይመራናል። የበሬው ዘመን እና የሰውየው ዘመን ጊዜያቸው በታሪክ ውስጥ አልፏል፤ ስለዚህ ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። በሬው እና ሰውየው የቤተክርስቲያን ተክል በተዘራበት እና በሚታጨድበት ጊዜ መካከል ያለውን የእድገት ዘመን የሚወክሉ ናቸው። ያ ሁሉ ግን ሆኖ አልፏልና አይደገምም።
ስለዚህ ትኩረታችን በአንበሳው ላይ ነው፤ እርሱም በሐዋርያት የተተከለው የእግዚአብሔር ቃል ዘር ነው። ይህ ለምንድነው አስፈላጊ የሆነው? ምክንያቱም የሚበረው ንስር ዘሩ በምድር ላይ ከሞተው የቤተክርስቲያን ተክል ላይ ታጭዶ ወደ ሰማይ የሚወሰድበትን መከር ይወክላል።
ዘሩ የሚታጨደው ተክሉ በሞተ ጊዜ ብቻ ነው። ስለዚህ ሰባተኛዋ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን በራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ ተፈርዶባታል። የሎዶቅያውያን የመጨረሻ የቤተክርስቲያን ዘመን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ከአፉ አውጥቶ ስለሚተፋት ትሞታለች።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
ይህም ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር እንድትለይ ያደርጋታል። ወደ ሐዋርያት የመጀመሪያ ዘመን የተመለሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው በመከሩ ጊዜ ተሰብስበው ወደ ሰማይ መሄድ የሚችሉት።
“የበጎች ገበያ፤” እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ የራሱ በጎች አድርጎ ነው የሚያያቸው።
ዮሐንስ 10፡2 በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
በሩ ኢየሱስ ነው። እርሱ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኢየሱስን ልንከተለው የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በማመን ብቻ ነው።
በዙፋኑ ዙርያ ያሉት አራቱ እንስሳት ሰዎችን የራሳቸው ተከታይ ሊያደርጉ አይደለም ተልእኮዋቸው። የእነርሱ ተልእኮ ሰዎችን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ወደተቀመጠው ወደ ኢየሱስ መምራት ነው።
ዮሐንስ 10፡3 ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
በረኛው ሰው ነው፤ እርሱም ለእረኛው (ለኢየሱስ) እንዲገባ እና በጎችን እየመራ እንዲወስዳቸው የሚፈቅድ (ወንጌላዊ፣ ወይም ሰባኪ ወይም አስተማሪ) ነው።
በጎች በረኛውን አይከተሉትም። ሰባኪዎች ሐጥያተኞችን እንዲድኑ ወደ ክርስቶስ ያመጡዋቸዋል፤ ይህም መልካም ነው። ከዚያ በኋላ ግን አዲሶቹን ክርስቲያኖች በተለያየ መንገድ ይቆጣጠሩዋቸውን ሰዎችን ተከታይ ያደርጓቸዋል። ስለዚህ ክርስቲያኖች መጨረሻቸው ትክክለኛ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት የተጻፈው የኢየሱስ ተከታይ ከመሆን ይልቅ የቤተክርስቲያን አባል ሆነው መቅረት ነው።
ቤተክርስቲያኖች የሰሩት ትልቅ ስሕተት በጎች እንዲከተሉት ብለው ሰውን መሪ አድርገው መሾም ነው።
ብቸኛው የበጎች መሪ ኢየሱስ ነው። እያንዳንዱ ሰው በግሉ ከኢየሱስ ጋር ሕብረት ማድረግ እና ኢየሱስን እንደ አዳኙ አድርጎ ማወቅ አለበት፤ ደግሞም ኢየሱስ በግሉ እና በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የግለሰቡ የእምነት መሰረት በመሆን በሕይወቱ ውስጥ የመጀመሪያውን ስፍራ መያዝ አለበት። ከጌታ ጋር ባለን ሕብረት ውስጥ ሰዎች ሊረዱን ይችላሉ፤ ነገር ግን የዚህን ዘመን ፓስተሮች ወይም ቤተክርስቲያኖች እንድንከተል አልታዘዝንም። ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል ሊረዱህ ይችላሉ ነገር ግን በፍጹም እራሳቸውነ እንድትከተል ሊያደርጉህ አይገባም።
“ፓስተራችሁን ተከተሉት፤ እርሱም ወደ ጌታ ያደርሳችኋል” የሚለው አባባል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ ጥቅስ አይደለም። ዓይናችሁን በፓስተራችሁ ላይ መትከል የምትችሉት ዓይናችሁን ከኢየሱስ ላይ ባነሳችሁ ጊዜ ብቻ ነው።
ፓስተርን መከተል ወደ መንፈሳዊ አደጋ ውስጥ ይከታችኋል፤ ምክንያቱም የምታምኑትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማረጋገጥ አትችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን በመጥቀስ ፈንታ ፓስተራችሁ የተናገረውን ስለምትጠቅሱ ሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያኖች ትሆናላችሁ። የራሳችሁ የሆነ አቋም አይኖራችሁም። ፓስተራችሁ እንድታምኑ የፈለገውን በማሰብ ተወስናችሁ ትቀራላችሁ።
ዮሐንስ 10፡4 የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
በጎቹ ማለትም እኛ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ብቻ መከተል አለብን። የሆነ ሰውን መከተል የለብንም። የሆነ ፓስተርን መከተል የለብንም። በብሉይ ኪዳን ውስጥ ፓስተር ተብሎ የሚጠራ አገልጋይ አልነበረም፤ ሆኖም ነብዩ ኤርምያስ በራዕይ ፓስተሮችን በማየት ወደ ፊት እንደሚመጡ እየተነበየ ስድስት ጊዜ አውግዟቸዋል። የፓስተሮች አገልግሎት የተበላሸ እና በጣም አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ አዲስ ኪዳን አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚጠቅሳቸው።
ቤተክርስቲያናችሁን ፓስተር የሚያስተዳድራት ከሆነ፤ ለዚህ አይነቱ አስተዳደር አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት እንደሌለው እወቁ።
እግዚአብሔር ቃሉን በገለጠልን መጠን ቃሉን መከተል አለብን። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የሚመራን።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ፍንጭ ይሰጠናል። የጊዜውን ምልክት ያሳየናል።
“ትራምፕ” (በእንግሊዝኛ መለከት ማለት ነው) የሚለው ቃል ሙታን በትንሳኤ የሚነሱበት ቃል ውስጥ ተጠቅሷል።
በ2016 አሜሪካ ውስት የተደረገው እልህ አስጨራሽ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ውድድር “ትራምፕ” የተባለውን ስም በየዕለቱ እንድንሰማ አስገድዶን ነበር። ምርጫውን ካሸነፈም በኋላ ያልተለመደና አነጋገሪ የሆነ አመራር ስልቱ ስም በየዕለቱ ከአርዕስተ ዜናዎች ውስጥ እንዳይጠፋ አድርጎታል። እጅግ ባልተለመደ ሁኔታ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሃገሮች ስለ ትራምፕ ሲያወሩ ልክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው “ዘ ትራምፕ” (መለከቱ) እያሉት ነው የሚያወሩት። ስለዚህ እግዚአብሔር እርሱን የዘመኑ ምልክት አድርጎ እየተጠቀመበት ነው። ወደ ትንሳኤው ጊዜ በጣም እየተቃረብን ነን። ትራምፕ ለምንድነው በጣም አስፈላጊ የሆነው? ምክንያቱም በምረጡኝ ዘመቻው ውስጥ ኢየሩሳሌምን የእሥራኤል ዋና ከተማ እንደሚያደርጋት ቃል ገብቷል። ይህም የትንቢት ፍጻሜ ነው።
ትንቢትን መፈጸም ከምንም ነገር በላይ ትልቅ ዋጋ አለው። የትንቢቱ መፈጸም ሰዎች ትንቢቱ የተፈጸመበትን ሰው ከመውደዳቸውም የበለጠ ዋጋ አለው።
የሜሴጅ ፓሰተሮች ትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውስጥ ይሸነፋል ብለው በተናገሩ ጊዜ እንዴት ነው ሊሳሳቱ የቻሉት? እነርሱ አንዲት ሴት አሜሪካን እንደምትመራ የሰሙትን ጥቅስ ሒላሪ ክሊንተን ምርጫውን ታሸንፋለች ብለው በመተርጎማቸው ነው የሳቱት። ይህ የውርደታቸው ትልቅ ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም የሰውን ንግግር ጥቅስ ትርጉም ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ እውነት አድርገው አምነው ነበር። የሜሴጅ ሰባኪዎች ሙሉ በሙሉ ተሳሳቱ፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሃሳብ እጅግ ብዙ ተራርቀዋል ማለት ነው። ነገር ግን ሞኞቹ የሜሴጅ ተከታዮች አሁንም የሜሴጅ ፓስተሮችን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር የሚቃረነውን የሰው ንግግር ጥቅሶቻቸውን እና ለጥቅሶች የሚሰጡዋቸውን ትርጓሜዎች ይከተላሉ፤ ምክንያቱም ሕዝቡም ይሁኑ ፓስተሮቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መተርጎም እንዳለባቸው አያውቁም።
የሜሴጅ ሰባኪዎች የሰው ንግግር ጥቅሶችን እንደ ገደል ማሚቶ ይደግማሉ።
“ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።”
እንደዚህ የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። “የቤተክርስቲያን ራሶች” የሚባሉ ሰዎች በአሜሪካ የምርጫ ውጤት ትንበያቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ተሳስተዋል፤ (ሰባት ራሶች ያሉትን የራዕይ 13 አውሬ እንድናስበው ያደርጉናል)። ከዚያም ብሰው ደግሞ እነዚህ ፓስተሮች በሌሎች ርዕሶች ላይ እርስ በራሳቸው ይቃረናሉ። ስለዚህ የሜሴጅ ቤተክርስቲያን አማኝ አባል በሆነበት የሜሴጅ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰማውን ማንኛውንም ትምሕርት እያመነ ነው የሚኖረው።
“ሜሴጅ ቤተክርስቲያን” የሚለው መጠሪያ እራሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
“የእግዚአብሔር ድምጽ” የሚለው መጠሪያ አዲስ ኪዳን ውስጥ ተቀባይነት የለውም።
የተለያዩ ፓስተሮች የግል አመለካከቶቻቸው እንደ ጉም ዓይኖቻቸውን ስለጋረዳቸው የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት አጥርተው ማየት አይችሉም። እምነት የሚወሰነው ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው። በሃገራችሁ ውስጥ እነርሱ የሚሰብኩት ሃሳብ የእናንተ እምነት መሰረት ይሆናል። ከዚያ ቦታ ተነስታችሁ ወደ ሌላ ቦታ ብትሄዱ ደግሞ እምነታችሁም ይለወጣል፤ ምክንያቱም በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ፓሰተሮች የተለያዩ እምነቶችን ነው የሚከተሉት። ነገር ግን የትም ብትሄዱ በሄዳችሁበት ቦታ ያለው ፓስተር እርሱ እንደሚያምነው እንድታምኑ ይፈልጋል። እውርን እውር ይመራዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገርን የሚያምን ሰውን ታላቁ መከራ የሚባል ጉድጓድ ነው የሚጠብቀው።
ዮሐንስ 10፡5 ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ተነስቶ የማይናገር ማንኛውም ፓስተር ወይም ሰባኪ ወይም ግለሰብ ቢኖር ሽሹት።
ሰባኪ የተሰጠው ሃላፊነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል እንድታምኑ የማድረግ ሃላፊነት ነው።
የተጻፈው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው “የእግዚአብሔር ድምጽ”።
በዘመኑ ፍጻሜ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ የተስፋ ቃል አልተሰጠንም፤ የተነገረን የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ እና ጩኸቱን እንደምንስማ ነው፤ እርሱም እኛን ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያዊ አባቶች በመመለስ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ወደ ፍጻሜ ያመጣዋል። ስለዚህ ሰውን ካልተከተልኩ አይሆንልኝም የምትሉ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተሉ፤ አዲስ ኪዳን ውስጥ የጻፋቸውን መልእክቶችም እመኑ። ጳውሎስ ሌሎቹ ሐዋርያት ከጻፉት ጋር ይስማማል። በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩትን እነዚያን የመጀመሪያ ሐዋርያት መከተል ከጀመራችሁ በተደጋጋሚ ወደ ኢየሱስ እንደሚያመለክቱዋችሁ እንጂ ወደ ራሳቸው እንደማያመለክቱዋችሁ ማየት ትችላላችሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ኢየሱስን ስትከተሉት በዚህ በጭንቅ ዘመን ውስጥ የምትሄዱበትን ምሪት ታገኛላችሁ። አለዚያ በነፋስ እንደሚፍገመገም ደመና እየተገፋችሁ የመጣው ክስተት ሁሉ ይውጣችኋል።
ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲኖሜኔሽኖች፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ አንድ እግዚአብሔር በሦስት አካላት፣ ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳት መሪያችን ነው። እነዚህ አነጋገሮች ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላት ናቸው።
ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩዋቸው ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም፤ ስለዚህ የሙታን ትንሳኤ ከመሆኑ በፊት ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ እኛ ልናውቅ አንችልም።
አዲሱን የኢየሱስ ስም የሚያውቅ አንድም ሰው የለም።
እነዚህ ሁሉ ሃሳቦች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም፤ ነገር ግን የሚያምኑባቸው ሰዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
የሜሴጅ ፓስተሮች ይህንን አዲስ ስም እናውቃለን ይላሉ። ሕዝቡ ደግሞ ከሞኝነታቸው ብዛት መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ስም ማንም አያውቅም ቢልም እንኳ ፓስተሮቻቸው እናውቃለን ሲሉ ያምኑዋቸዋል።
በእነዚህ ርዕሶች ላይ የሚናገሩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉ ሕዝቡን እያሳሳቱ ናቸው።
ዮሐንስ 10፡7 ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
10፡7 ልዩ ቁጥር ነው። ሊቀ ካሕናቱ በቤተመቅደሱ ውስጥ ከመጋረጃው በስተጀርባ ወደተሰወሩት ሚስጥራት መግባት የሚችለው በ7ኛው ወር በ10ኛው ቀን ብቻ ነበረ። በዚህ በስርየት ቀን እግዚአብሔር ከመጋረጃው በስተጀርባ ምን እየሰራ እንደነበር ማየት የሚፈቀደው ለአንድ ሰው ብቻ ነበረ።
10፡7 በራዕይ መጽሐፍ ውስጥም ይገኛል።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ስለዚህ 10፡7 የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ውስጥ እንድንገባ ከተከፈተው በር ጋርም የተያያዘ ቁጥር ነው።
በ1963 ለዘመኑ መጨረሻ የተላከው ነብይ በሰባት መላእክት አማካኝነት በመጡለት ተከታታይ ራዕዮች አማካኝነት ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማየት ችሏል፤ በዚያም አማካኝነት የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ተቀብሏል። ሰባቱ ማሕተሞች የሚፈቱበት ይህ ትንቢታዊ ክስተት የሚፈጸመው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው። ነገር ግን ፍጻሜውን አስቀድሞ በማየት ነብዩ ወደ እኛ ዘመን ተመልሶ መጥቶ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን መረዳት የሚያስችሉንን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት ልክ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖች በተረዱበት መልክ መግለጥ ይችላል። የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖች ልክ የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች ያመኑትን ሲያምኑ የዛን ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል፤ ጌታም ተመልሶ ይመጣል።
ወደ ዮሐንስ ምዕራፍ 5 እንመለስ፡-
ዮሐንስ 5፡3 በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።
በመንፈሳዊ ቋንቋ ይህ ሁሉ በሽታ ኢየሱስ በመጣበት ዘመን የአይሁድ ሕዝብ የነበሩበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነበረ። ደግሞ እግዚአብሔር በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ስላለችው ስለ ሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ከተናገረበት አገላለጽ ጋር ይመሳሰላል፤ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያንም እውር ተብላለች። በዳግም ምጻት ጊዜ ቤተክርስቲያን ልክ አይሁዶች በመጀመሪያው ምጻት ጊዜ እንደነበሩበት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው የምትገኘው።
ዮሐንስ 5፡4 አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት አንጻር ስንመከለተው በጎች እረኛውን ኢየሱስን ይከተሉ ዘንድ በዘመናቸው በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት በተገለጠላቸው መጠን ለእረኛው በር ይከፍቱ የነበሩ ሰባት በረኞች ነበሩ። ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን አንድ መልአክ (መልእክተኛ) ተመድቦ ነበረ፤ መልእክተኛውም ለአጭር ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ለዘመኑ አናውጦ ነበር። ሉተር መዳን በእምነት እና በጸጋ የሚለውን ቃል በማናወጥ እንዲታወቅ አደረገ። መለኮታዊ ኃይል እንዲናወጥና እንዲገለጥ ያደረገ ጴንጤ ቆስጤያዊ ሰባኪ ዊልያም ብራንሐም ነበረ፤ እርሱም ከመለኮታዊ ኃይል በተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥም እንዲናወጥ አድርጓል።
ነገር ግን ውሃው ተመልሶ በተረጋጋ ጊዜ እያንዳንዱ ዘመን እየደበዘዘ አለፈ፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ዘመን ከዚያ በኋላ መልእክተኛውን ወይም ሌላ የቤተክርስቲያን መሪን መከተል ጀመረ። የእያንዳንዱ መልእክተኛ ዓላማ ሰዎች ኢየሱስን እና መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቀው ወደ መከተል እንዲመለሱ ለማድረግ ነበረ። ነገር ግን ሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ለማድረግ የሚቀልላቸው አንድ ሰውን እንደ መሪ መከተል ነበረ። ሰዎች በራሳቸው ማሰብ አቆሙ፤ መሪ ተብለው የተሾሙባቸውን ሰዎች መከተል ጀመሩ፤ ከዚያም ትክክለኛ እውነት ተብሎ የተነገራቸውን የሰው ንግግር ጥቅስ እንደ ገደል ማሚቶ ደጋገሙ።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ወቅት ከአይሁዳውያን እይታ አንጻር በመጥበቂያው ውስጥ የተፈጠረው ክስተት በመጀመሪያው ፍልሰት ወደ ተስፋይቱ ምድር የመጡበትን ጉዞዋቸውን አመላካች ነበረ።
ዮሐንስ 5፡5 በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
ለምንድነው ለ38 ዓመታት የታመመው? ይህ ሰው የአይሁድ ሕዝብ በሙሴ የተመሩበትን ጊዜ ይወክላል፤ ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ድንበር እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ መጣ፤ ከዚያም በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ያሉትን ግዙፍ ሰዎች ለማሸነፍ የሚበቃ ብርታት እንደሌላቸው ወሰነ። እነርሱም ጦርነቶቹን እግዚአብሔር ስለ እነርሱ እንደሚዋጋላቸው ረሱ። ስለዚህ ሁላቸውም ሞተው እስኪያልቁ ድረስ እግዚአብሔር ለ38 ዓመታት በበምድረ በዳ ውስጥ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው። ከዚያ በኋላ ልጆቻቸው ጠላቶቻውን በማሸነፍ ከዘሬድ ወንዝ ጀምረው የተስፋይቱን ምድር እንዲወርሱ ተፈቀደላቸው።
ዘዳግም 2፡14 የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው የሰልፈኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
15 ከሰፈርም መካከል ተቈርጠው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ።
አይሁዳውያን በምድረ በዳ ውስጥ ለ38 ዓመታት በተንከራተቱ ጊዜ አንዳችም አቅም አልነበራቸውም። ወዴትም አልደረሱም። ክርስቲያኖች ለብዙ አስርት ዓመታት ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ ግን ብዙ ዓመታት ካለፋቸው በኋላ ቤተክርስቲያን መሄድ በጀመሩ ጊዜ ያውቁ ከነበረው ብዙም የበለጠ አያውቁም።
የሰውየው በሽታ አይሁዳውያን በምድረ በዳ ውስጥ ያባከኑዋቸውን 38 ዓመታት የሚያመላክት ነበረ።
“ቤተክርስቲያንን መቀላቀል” ወይም “የትኛው ቤተክርስቲያን ነው አባልነትህ?” የሚባሉት አነጋገሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።
ዮሐንስ 5፡6 ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው።
ዮሐንስ 5፡7 ድውዩም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።
ይህ ሰው የሚረዳውና ወደ ውሃው ውስጥ እንዲገባ የሚያግዘው ሰው አልነበረውም፤ ልክ አይሁዶች በምድረ በዳ ውስጥ ሳሉ የሚረዳቸው ሰው እንዳልነበረ። ታላቁ መሪያቸው ሙሴ እንኳ ወደ ተስፋይቱ ምድር ውስጥ ሊያስገባቸው አልቻለም።
ሙሴ የሕጉ ተምሳሌት ነበረ፤ ኢያሱ ደግሞ የጸጋ ተምሳሌት ነበረ።
አይሁዳውያንን ወደ እሥራኤል ምድር ውስጥ ለማስገባት የመሪ ለውጥ ያስፈልግ ነበር። ይህ በሽተኛ ሰው አሁን እውነተኛውን መሪ ኢየሱስን አገኘ። ዓይኖቹን በኢየሱስ ላይ በማድረግ እና ማንንም ሰው ባለመከተል እንዲሁም በማንም ሰው እገዛ ላይ ባለመደገፍ ሰውየው ተለወጠ፤ ደግሞም ተፈወሰ።
ዮሐንስ 5፡8 ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
የባከነበት የ38 ዓመት ሕይወቱ አበቃ።
የእሥራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ ኢያሱ የእግዚአብሔር ኃይል ምልክት የሆነውን ታቦቱን ካሕናቱ በትከሻቸው ተሸክመው እንዲሄዱ አደረገ።
ኢየሱስ ደግሞ እግዚአብሔር በበሽታ ላይ ያለው ኃይል ምልክት እንዲሆን ይህ ሰውዬ ታሞ በነበረበት ጊዜ ይተኛበት የነበረውን አልጋ በትከሻው ላይ እንዲሸከም አደረገ።
ዮሐንስ 5፡9 ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ።
ሰንበት አይሁድ ቅዳሜ ዕለት ከሥራ የሚያርፉበት ቀን ነበረ።
ሰንበት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተምሳሌት ነው፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ባለማመን እና በሐጥያት ከገባንበት ድካም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው የሚያሳርፈን።
ወደ እረፍቱ ከገባ በኋላ እግዚአብሔር ወደ መፍጠር ሥራው አልተመለሰም። ቅዳሜ ዕለት እረፍት ካደረጉ በኋላ በቀጣዩ ቀን ወደ ስራ መመለስ ግን እግዚአብሔር ያረፈበትን ዓይነት እረፍት ማረፍ አይደለም።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደ መስረቅ፣ ሐሰት መናገር፣ ማጨስ፣ መጠጣት፣ ነውረኛ ቀልዶችን ማውራት ከመሳሰሉት የሐጥያት ስራዎቻችን ያሳርፈናል፤ ከዚያም በኋላ ወደነዚህ የሐጥያት ስራዎች አንመለስም።
ስለዚህ እውነተኛው እረፍት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
ሰንበት ማለት እረፍት ነው። መንፈስ ቅዱስ ከሐጥያት ያሳርፈናል።
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት የእግዚአብሔር መንፈስ በተወሰነ መጠን መጥቱ ወደ ሰው ውስጥ ሲገባ እና ሕይወቱን ሲቆጣጠር ነው። ይህ ልምምድ አንድን ሰው የኢየሱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታይ ያደርገዋል።
የእግዚአብሔር ሰባተኛ ቀን ከአርማጌዶን በኋላ የሚመጣው የ1,000 ዓመታት እረፍት ነው። የዚያን ጊዜ እውነተኛ ኃይሉን እናያለን።
ዮሐንስ 5፡10 ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው፦ ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።
ይህ ፈውስ በሰንበት ስለተከናወነ ስራ መስራት ነውና ሰንበትን ማፍረስ ነው ብለው በመቃወማቸው አይሁዳውን ግብዝነታቸውን እያሳዩ ነበር ምክንያቱም እነርሱ በሰንበት እንስሶቻቸውን ውሃ ለማጠጣት ይወስዱ ነበር። የታመመ እንስሳ ቢያዩ ደግሞ እንስሳውን በሰንበት ያስታምሙታል። እንስሳ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅ ሰንበት ነው ብለው ጉድጓድ ውስጥ ትተውት አይሄዱም። ጎትተው ያወጡታል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል።
ነገር ግን ዲያብሎስ ሰዎች ኢየሱስን ብቻ እንዲከተሉ አይፈልግም። ሰዎች የሚመራቸው ሰው እንዲፈልጉ ያደርጋል፤ ልክ አይሁዳውያን የሚከተሉት ሰው እንዲኖራቸው ብለው ሳኦል ንጉስ ሆኖ እንዲሾምላቸው እንደጠየቁበት ጊዜ።
2ኛ ነገሥት 25፡13 ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዓምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬ ሰባበሩ፥ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
ባቢሎናውያን በቤተመቅደሱ የነበረውን የናሱን ኩሬ ወይም ከናስ የተሰራውን የናስ ባሕር የሚባለውን መታጠቢያ ሰባበሩትና ይዘውት ሄዱ። ልክ እንደዚሁ ክርስቲያኖች ተሞኝተው በተለያዩ አቅጣጫዎች የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን በመከተል የእግዚአብሔርን እቅድ ያበላሻሉ፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን እምነቱ የተለያየ ነው።
ኢየሱስ መጥመቂያውን ተጠቅሞ አንድ ሰውን ፈወሰ፤ ባለ ሙሉ ጤና አደረገው፤ ሰውየውም ለመፈወሱ ምልክት እንዲሆን በደዌ ተኝቶበት የነበረውን አልጋ ተሸከመ፤ ከዚያም በላይ ኢየሱስን በራሱ ለመከተሉ እና ሰው የነገረውን ሳይሰማ እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች የነገሩትን ሳይሰማ ለመከተሉ ሽልማት እንዲሆነው ነው አልጋውን የተሸከመው።
1ኛ ዜና 23፡25 ዳዊትም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቶአል፥ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም ይቀመጣል።
26 ሌዋውያንም ከእንግዲህ ወዲህ ማደሪያውንና የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ አይሸከሙም አለ።
አይሁዶች ኢየሩሳሌም ከገቡ በኋላ በዳዊት ልጅ በሰለሞን ዘመን እረፍት አገኙ። የሰለሞን መንግስት ሰዎች “ሚሌንየም” ብለው ለሚጠሩት የ1,000 ዓመት መንግስት ምን እንደሚመስል ማሳያ ነበረ።
አልጋ በዋነኝነት ለማረፊያ ነው የተሰራው። ካስፈለገን ግን ለታመሙ ሰዎችም አልጋ እናነጥፋለን። ኢየሱስ ሰውየውን በፈወሰበት ጊዜ በደዌ ተኝቶበት የነበረውን አልጋ ወደ ትክክለኛ አገልግሎት መለሰው፤ ለማረፊያነት ብቻ እንዲሆን አደረገው። ይህም ነገሮችን ወደነበሩበት የመመለስ ኃይሉን ያሳያል።
አልጋውነ በመሸከሙ የተፈወሰው ሰውዬ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ እረፍቱን ተሸከመው።
በሽታ እና ሞት አልጋ ላይ እንድንቀር ያደርጉናል። በደዌ የተኙበትን አልጋ ተሸክሞ መሄድ ግን በሐጥያት ውጤቶች ላይ ድል መጎናጸፍን ያመለክታል።
የሙታን ትንሳኤ በሐጥያት መዘዞች ላይ የሚደረገው የመጨረሻው ድል ነው።
ዮሐንስ 5፡11 እርሱ ግን፦ ያዳነኝ ያ ሰው፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
12 እነርሱም፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰው ማን ነው? ብለው ጠየቁት።
13 ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም።
ኢየሱስ ከዚህ ተዓምር የሚገኘውን ዝና አልፈለገውም። በአሁኑ ውድድር በሞላበት ዘመን ግን ፓስተሮች በሙሉ ምን እንዳደረጉ ዓለም ሁሉ እንዲያውቅላቸው ሮጠው በኢንተርኔት ያውጁታል።
ኢየሱስ ሰውየውን እንደገና ያገኘው ጊዜ ሌላ ጠለቅ ያለ ጉዳይ እንዳለ ይነግረዋል። አንዴ ኢየሱስን ካገኘው በኋላ ሰውየው ወደ ሐጥያት መመለስ የለበትም።
ዮሐንስ 5፡14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።
ሰንበት -- “ደግመህ ሐጥያት አትስራ”፡- መንፈስ ቅዱስ ከሐጥያት ያሳርፈናል። ከሐጥያት መመለስ በፈውስ ከተገለጠውም ኃይል የሚበልጥ ዋጋ አለው።
የተፈወሰው ሰውዬ በዕድሜው መጨረሻ መሞቱ አይቀርም። ከሐጥያት ነጻ በመውጣት ግን የዘላለም ሕይወትን እናተርፋለን።
ዮሐንስ 5፡15 ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ።
ኢየሩሳሌም የአይሁዳውያን የሐይማኖት ማዕከል ነበረች። አይሁዳውያን ለብዙ ጊዜ በሐይማኖት መሪዎቻቸው ተጽእኖ ስር ከመቆየታቸው የተነሳ የኢየሱስን የመፈወስ ኃይል ማስተዋል አልቻሉም። ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወሱ ከአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች የሚበልጥ ኃይል እንዳለው ግልጽ ነበር፤ በዚህም የሐይማኖት መሪዎች በቅናት አብደውበታል። እያንዳንዱ አይሁዳዊ እርሱ የሚከተለው የሐይማኖት መሪ ታላቅ እንደሆነ ያስባል፤ አሁን ግን ከእነዚህ መሪዎች ሁሉ ውጭ የሆነው ኢየሱስ ሁሉንም በለጣቸው። እግዚአብሔር ከሐይማኖታዊ ቡድናቸው ውጭ ሄዶ መስራቱን አይሁዶች መቀበል አቃታቸው። አይሁዶች ልክ እንደ ዛሬዎቹ ክርስቲያኖች ሆነው ነበር፤ የዛሬ ክርስቲያኖች 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ቢኖሩም እንኳ እግዚአብሔር በዋነኝነት በእነርሱ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ይመስላቸዋል።
ዮሐንስ 5፡16 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።
ስለዚህ ፈውስን “ስራ” ብለው መደቡትና በዚህ ምደባቸው መሰረት ማንኛውም ዓይነት ፈውስ በቅዳሜ ሰንበት እንዳይደረግ እገዳ ጣሉ። ዋነኛው ችግራቸው ግን ከኢየሱስ ጋር በኃይል ሊመጣጠኑ እንደማይችሉ በግልጥ መታየቱ ነው - ምክንያቱም ከአይሁዳውያን አንዳቸውም መፈወስ አይችሉም ነበር -- እግዚአብሔር ብቻ ነበር መፈወስ የሚችለው። ይህም ደግሞ ከሐይማኖት መሪዎቻቸው የበለጠ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ነበረው ማለት ነው።
በቅዳሜ ሰንበት ደግሞ ካሕናት እና ሌዋውያን ሐይማኖታዊ ስርዓቶችን ለመፈጸም ተግተው ይሰሩ ነበር። ኢየሱስ ደግሞ መሲሁ፣ አማኑኤል (ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር”) ነበረ። ስለዚህም እርሱ እውነተኛው ሊቀ ካሕናት ነበረ። ገበሬዎች እንስሶቻቸውን በሰንበት ውሃ ሲያጠጡ ዝም ብለዋቸዋል። አንድ በሬ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅ በሰንበትም ቢሆን ጎትተው ያወጡታል። ነገር ግን ሰውን ከበሽታ መፈወስ አይፈቅዱም። ኢየሱስ ላይ ጥፋት ለማግኘት የማያደርጉት ነገር አልነበረም።
በዚህ ዘመን አብዛኛው ክርስቲያን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ለማለት ይሞክራል። ኢየሱስ ደግሞ ቃሉ ነው። ስለዚህ የዘመናችን ክርስቲያኖች ኢየሱስ ላይ ስሕተት ለማግኘት እየሞከሩ ናቸው።
ዮሐንስ 5፡17 ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።
የፈውስ ኃይሉን በመጠቀም ኢየሱስ ካሕናቱ ሊወዳደሩት በማይችሉት መልኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን አሳየ። አእምሮዋቸውን መቆጣጠር እስኪሳናቸው ድረስ ሐይማኖታዊ ቅናት የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ መመሪያ እንዲደነግጉና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው መመሪያቸውን የጣሰ ሰውን ሁሉ እንዲያወግዙ አደረጋቸው። በተለይም የእነርሱን መመሪያ የጣሰ ሰው ከእነርሱ የሚበልጥ ኃይል ከተገለጠበት ጉዱ ፈላ። ልክ እንደ ዛሬ ቤተክርስቲያኖች ይመስላሉ።
እያንዳንዱ ፓስተር የራሱ መመሪያ አለው፤ እንዲህ የሚል፡- “የእኔን አመለካከት ማመን ብቻ ነው የሚፈቀድላችሁ።”
ስለዚህ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት ብቻ በመመላለስ የሰዎች ሐይማኖታዊ አመራር ጠላት ሆነ።
ዮሐንስ 5፡18 እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።
ሰዎች ኢየሱስ የእውነት እግዚአብሔር መሆኑን ማመን አይችሉም።
ዮሐንስ 5፡19 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።
እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ ነበረ። እርሱ ያደርግ የነበረውን አንድም ሰው ማድረግ አይችልም። በእርሱ ውስጥ የነበረው እግዚአብሔር ነው እንደዚያ ዓይነት ኃይል የነበረው።
ዮሐንስ 5፡20 አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።
ኢየሱስ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ኃይል መግለጥ መቻሉ ለአይሁዶች ማን መሆኑን እንዲያውቁ ምልክት ሊሆናቸው ይገባ ነበር።
ዮሐንስ 5፡21 አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ኢየሱስ ሙታንን ያስነሳ ነበረ። ከዚያም በላይ ደግሞ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ እና እግዚአብሔርን ለማገልገል ፍላጎት እንዲኖራቸው በመንፈስ ሙታን የነበሩ ሰዎች ልብ ውስጥ እምነትን ይቀሰቅስ ነበር።
ዮሐንስ 5፡22 ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።
እግዚአብሔር አብ ፈራጅ አይደለም። የፍርድ ቀን ሲመጣ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው ዋነኛው ዳኛ ሆኖ የሚገለጠው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር እውነት እና ፍርድ በአንድነት ለሰው ከሚያስፈልገው ይቅርታ እና ምሕረት ጋር የተገለጠበት ሰው ነው። ኢየሱስ በውስጡ እግዚአብሔር በውጭው ግን ሰው ነበረ፤ ስለዚህ ሁለቱንም በትክክል የሚያውቅ መካከለኛ እርሱ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
በስተመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ቃል ነው የሚፈረድብን። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ነው ፈራጅ የሚሆነው።
ነብዩ ዳንኤል በፍርድ ቀን ሰውን የሚመስሉ ሁሉት አይቷል።
በዘመናት የሸመገለው ነጭ ጸጉር ነበረው፤ ይህም ዳኞች የሚያደርጉትን ነጭ ዊግ ይመስላል። ረጅም ጸጉር ዝቅ ብሎ የመገዛት ተምሳሌት ነው፤ ማለትም ዳኛው ለእግዚአብሔር ቃል ዝቅ ብሎ ይገዛል ማለት ነው።
ዳንኤል 7፡9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።
ዳንኤል 7፡13 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
በዘመናት የሸመገለው እግዚአብሔር አብ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም አብ በማንም ላይ አይፈርድም።
ራዕይ ውስጥ ዮሐንስ ኢየሱስን ነጭ የዳኛ ዊግ አድርጎ ያየዋል።
ራዕይ 1፡14 ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤
ዳንኤል ያየው ራዕይ “በሰውኛ ዘይቤ” ነው የተገለጠው። የዳኛ ባሕርያት፣ ምሕረት እና እውነት፣ ሁለት የተለያዩ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ነው የተገለጡት።
እነዚህ ባሕርያት ግን ሁለቱም በኢየሱስ ውስጥ አሉ። የሰው ልጅ እንደመሆኑ ከሰዎች ጎን በመቆም ለሰዎች ምሕረትን ማሳየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን በዘመናት የሸመገለ እንደመሆኑ (ኢየሱስ ከመጀመሪያም ነበረ) ያለምንም ማመቻመች እውነት በሆነው በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መፍረድ አለበት። ስለዚህ ምሕረትንም እውነትንም ማሳየት የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።
መዝሙር 85፡10 ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤
ዮሐንስ 5፡23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ … ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።
ልጁ መንፈስ የሆነው እግዚአብሔር አብ በውስጡ የሚኖርበት ሰው ነው።
ኢየሱስን አልቀበልም የሚል ሰው በውስጡ የሚኖረውን እግዚአብሔርንም አልቀበልም ብሏል።
ዮሐንስ 5፡24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው እቅድ መሰረት በቀራንዮ የነፍሳችንን መዳን ይፈጽመዋል። እራሳችንን ማዳን ስለማንችል ወደ ሰማይ ለመግባት ብቸኛ መንገድ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ማመን እና መከተል አለብን።
ዮሐንስ 5፡25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
የመጀመሪያው ትንሳኤ ማለትም የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን የሚነሱበት ሊፈጸም በጣም ቀርቦ ነበር።
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ሐጥያታችንን ተሸክሞ በመውሰድ ወደ ሲኦል ወርዶ በዲያብሎስ ላይ አራገፈው። ከሞት ሲመለስ የብሉይ ኪዳንን ገነት በመጎብኘት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን በሙሉ ከሞት አስነሳቸው፤ እነርሱም ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ተከትለው ከሙታን ተነሱ።
ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
ማቴዎስ 27፡53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
ትንሳኤ እግዚአብሔር በሞት ላይ የሕይወት ኃይል እንዳለው ያሳየበት ዋነኛ ማረጋገጫ ነው።
ዮሐንስ 5፡26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።
ዮሐንስ 5፡27 የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው
እነደገና ኢየሱስ ዳኛ ወይም ፈራጅ መሆኑ አጽንኦት ተሰጥቶበታል። በዘመናት የሸመገለው ማለት ለረጅም ዘመናት ኖሯል፤ ደግሞም ጠቢብ ነው ማለት ነው። ልታታልሉት አትችሉም። የሰው ልጅ ማለት ሰው ነው፤ የእኛ ድካምና ችግር ከእርሱ የተሰወረ አይደለም ማለት ነው።
ጠቢብ እና አስተዋይ መሆኑ ትክክለኛ ብዙ ዳኛ ያደርገዋል።
ዮሐንስ 5፡28 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ … በዚህ አታድንቁ።
በብሉይ ኪዳን የነበሩ አማኞች ከእርሱ ትንሳኤ በኋላ ወዲያው ከሙታን ተነስተው ከመቃብራቸው ይወጡና ከእርሱ ጋር እንደ ደመና ያሉ (ምስክሮች) ሆነው አብረውት ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ።
ዮሐንስ 5፡29 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።
ሁለቱ ትንሳኤዎች በመካከላቸው የ3,000 ዓመታት ክፍተት አለ።
• የሕይወት ትንሳኤ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ወዲያው ተፈጸመ።
• ከ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ የ1,000 ዓመቱ የሰላም ዘመን ይመጣል፤ ከዚያ በኋላ አጠቃላይ የሙታን ትንሳኤ ይሆናል። ይህን ተከትሎ ከብሉይ ኪዳን ዘመን እና ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ የማያምኑ ሰዎች ይፈረድባቸው ዘንድ ከሙታን ይነሳሉ።
ሰዎች አንድ ጥቅስ በሺዎች ዓመታት የሚራራቁ ሁለት ክስተቶችን ሊገልጽ አይችልም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ሊገልጹ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ብዙ ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት እንችላለን።
ለምሳሌ ኢየሱስ ከነብዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ምዕራፍ 61፡1-2 አነበበ።
ሉቃስ 4፡18 የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ
ሉቃስ 4፡19 የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል
ኢየሱስ ግን ከቁጥር 2 ውስጥ ግማሹን ብቻ ነው ያነበበው። ኢሳይያስ ውስጥ የተጻፈው ጥቅስ ምን እንደሚል ተመልከቱ።
ኢሳይያስ 61፡2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥
የተወደደችው የእግዚአብሔር ዓመት የመጀመሪያውን ምጻቱን ነው የሚያመለክተው። ከጥቅሱ ውስጥ ኢየሱስ ሳያነብብ የተወው አምላካችን የሚበቀልበት ዓመት የሚለው ክፍል ከ2,000 ዓመታት በኋላ የሚመጣውን ታላቁን መከራ በተመለከተ ነው የሚናገረው።
ዮሐንስ 5፡30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።
የኢየሱስ ስኬታማነት ሚስጥር የራሱን ፈቃድ አለመፈለጉ ነው። እኛ ልንከተል የሚገባን ምሳሌ ይህ ነው። ኢየሱስን ሁልጊዜ የሚያሳስበው የእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ ነበረ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአካል በእርሱ ውስጥ በሙላት ይኖር ነበረ።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ይህ ለእኛ ምሳሌያችን ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ በተወሰነ መጠን በእኛ ውስጥ የሚኖር ከሆነ እኛም ፍላጎት የሚኖረን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ ነው። የራሳችን ፈቃድ ከዚያ በኋላ እንደ ጉም በንኖ ይጠፋል።
ዮሐንስ 5፡31 እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤
በራሳችን ላይ ትኩረት ማብዛት የለብንም። የሰዎችን ትኩረት ወደ ራሳችን መሳብ የለብንም።
ዮሐንስ 5፡32 ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።
ታላቅ ነብይ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ አስቀድሞ መስክሮለታል።
ዮሐንስ 5፡33 እናንተ ወደ ዮሐንስ ልካችኋል እርሱም ለእውነት መስክሮአል።
ዮሐንስ 5፡34 እኔ ግን ከሰው ምስክር አልቀበልም፥ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ።
ኢየሱስ ግን የየትኛውም ሰው ምስክርነት አላስፈለገውም። በሰው መሪዎች ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት የእግዚአብሔር እቅድ አካል አይደለም። ስለዚህ ኢየሱስ ሰዎች ታላቅ ነብይ ሲያገኙ የሚሰሩትን ስሕተት በተመለከተ ሊያስጠነቅቃቸው ፈልጓል። በተለይም ደግሞ ከኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት በፊት የሚገለጠውን የኤልያስ መንፈስ በተመለከተ። ይህ የኤልያስ መንፈስ በመጥምቁ ዮሐንስ ውስጥ ነበረ። ነገር ግን የዮሐንስ ተከታዮች ሲሰሩት ከነበረው ከባድ ስሕተት መዳን አስፈልጓቸዋል። (ይህም የዊልያም ብራንሐም ተከታዮች ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት ከሚሰሩት ስሕተት ጋር ተመሳሳይ ነው)።
ዮሐንስ 5፡35 እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፥ እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ።
መጥምቁ ዮሐንስ በራሱ ዘመን ከነበሩ ሰባኪዎች ሁሉ በጣም ይበልጥ ነበር። ዮሐንስ በመረዳቱና በእውቀቱ ከፍ ያለ ሰው ስለነበረ ተከታዮቹ እርሱ በዘመናቸው በነገሰው መንፈሳዊ ጨለማ ላይ ባበራው ብርሃን በጣም ተደንቀዋል። ስስዚህ የዮሐንስ ተከታዮች በዮሐንስ ብርሃን ደስ እያላቸው ኖረዋል።
ግን ሁሉም ነገራቸው ዮሐንስ ስለተባለው ሰውዬ ሆኖ ቀረ።
ዮሐንስን ብቻ ይከተሉ ነበር። ዮሐንስን ከፍ ከፍ በማድረጋቸው ዮሐንስ እያሳያቸው የነበረውን ማየት አቃታቸው፤ ዮሐንስ ሊያሳያቸው የፈለገው ኢየሱስን መከተል እንዳለባቸው ነበረ።
ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
ኢየሱስ ከዮሐንስ በላይ እጅግ ታላቅ ነበረ።
ከእነዚህ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ እንድሪያስ ነበረ።
ከዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል የኢየሱስ ቀደመዝሙር የሆነውና ኋላም ሐዋርያ የሆነው እንድሪያስ ብቻ ነው።
ዮሐንስ ኢየሱስን ከሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ሰው አድርጎ አሳይቷቸዋል።
ከዚያም ዮሐንስ ሲናገር የሰሙ እና ዮሐንስ የተናገረውን ያስተዋሉ ሰዎች ኢየሱስን ሊከተሉ ችለዋል።
ዮሐንስ ሲናገር የሰሙ ሰዎች ዮሐንስ ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር መረዳት ነበረባቸው። በትክክል መረዳታቸውንም ኢየሱስን በመከተላቸው ገለጡ። ኢየሱስ ከዮሐንስም እጅግ ታላቅ መሆኑን ተገነዘቡ።
ዮሐንስ 5፡36 እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።
በዘመን መጨረሻ ዊልያም ብራንሐም በመጽሐፍ ቅዱስ በቃሉ ገጾች ውስጥ ኢየሱስ ሲመላለስ ገልጦ አሳየ።
ወንድም ብራንሐም እየተናገረ የነበረውን የተረዱ ሰዎች እምነታቸውን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በተጻፈው እውነት ላይ ብቻ በመመስረት ከዚያ በኋላ ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይከተሉታል።
ነገር ግን በመጥምቁ ዮሐንስ ጊዜ እንደሆነው ከዊልያም ብራንሐም ደቀመዛሙርት መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው የተገለጠውን ቃል ኢየሱስን የሚከተሉት።
ዮሐንስ 5፡37 የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፡፡ ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤
በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሚላክልን ቃል አልተገባልንም። እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ማየት አንችልም።
ኢየሱስ ይፈጽማቸው የነበሩ ቃሎችን እግዚአብሔር እርሱን እንደ ላከው የሚያረጋግጡ ምስክሮች እንደሆኑ ይናገር ነበር።
ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት እንዳለን ብቸኛው ማረጋገጫችን ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መታዘዛችን ነው፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መቻላችንን ያሳያል። ትንሽ መገለጥ ካለን የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታችንም ትንሽ ሆኖ ይቀራል። የኢየሱስን ሃሳብ በትንሹ እናስተውላለን።
ዮሐንስ 5፡38 እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም።
የሰው ንግግር ጥቅሶችን የተለያዩ ትርጉሞች እየሰጠናቸው ከምንጠመዝዛቸው ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ መቆየት አለብን፤ መጽሐፍ ቅዱስን በማስተዋል ማንበብ አለብን።
ለሰው ንግግሮች የሚሰጣቸው የተለያዩ ትርጓሜዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አብረው አይሄዱም።
ልክ ሥላሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕት እንደ አለመሆኑ ሁሉ ከተለያዩ የሰው ጥቅሶች ላይ ተነስነት የምንደርስባቸው መደምደሚያዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይደሉም።
መጽሐፍ ቅዱስን መርምሩ ተብለናል።
ዮሐንስ 5፡39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
ከዚህ በታች የተጻፉትን የሜሴጅ ተከታዮች የሚጠቀሙዋቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አነጋገሮች ተመልከቱ፡-
“ሜሴጅ ውስጥ ነኝ” ወይም “የሜሴጅ አማኝ ነኝ።”
“የወንድም ብራንሐም ስብከቶች የእግዚአብሔር ድምጽ ናቸው።”
“ሜሴጅ ውስጥ ከሆናችሁ ብቻ ነው መዳን የምትችሉት።”
“ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው”
“አስራት የፓስተሩ ነው”
“ነብዩ ላይ ልትፈርድበት አትችልም”
“አንዲት ሴት አሜሪካን ትመራለች፤ ስለዚህ ሒላሪ የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች”።
ከእነዚህ አባባሎች አንዳቸውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።
ትራምፕ ምርጫውን ማሸነፉ የሜሴጅ ፓስተሮች ከእግዚአብሔር ሃሳብ ምን ያህል ርቀው መሄዳውን አጋልጧል።
ዮሐንስ 5፡40 ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።
ክርስቲያኖች እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለመመስረት እሺ አይሉም ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁም። መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ይበዛባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ገጹ በጣም የሚበዛ መጽሐፍ ነው። ውስጡ በጣም ብዙ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ክፍሎች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ከባድ ስራ ማብዛት ነው።
ስለዚህ ጥቅሶችን መሰነጣጠቅና ማገጣጠም ይቀልላል።
ዮሐንስ 5፡41 ከሰው ክብርን አልቀበልም፤
የቤተክርስቲያን ሰዎች ከፓስተራቸው ጋር መቃረን ያስፈራቸዋል።
ከፓስተሩ ጋር ከተቃረንክ ፓስተሩም በዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችም ይጠሉሃል።
ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከቆምክ ቤተክርስቲያን ከሚመላለሱ ሰዎች ዘንድ ክብር አታገኝም።
ዮሐንስ 5፡42 ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በራሳችሁ እንደ ሌላችሁ አውቃችኋለሁ።
ነገር ግን ፓስተሮቹ እርስ በራሳቸው በሃሳብ አይስማሙም። በመካከላቸው የእምነት አንድነትን ለመፍጠር እንኳ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመለስ አይችሉም።
ፓስተሮች እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አያይዘው አያቀርቡም። ሕዝቡ ደግሞ ከፓስተሮች ጋር በመስማማት በፓስተሮች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ይጥራሉ። ይህንን ተቀባይነት ለማግኘት በጣም ከመፈለጋቸው የተነሳ ከፓስተሩ ጋር የማይስማማ ሰውን ሁሉ ያወግዛሉ።
ፍቅር ከባድ ስራ ይጠይቃል። እግዚአብሔርን የምንወድድ ከሆነ ቃሉን በሙሉ መውደድና ለማወቅ መፈለግ አለብን። በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች እና እርስ በራሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ ማለት አንችልም። ለመረዳት የሚከብዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በውስጣቸው የያዙትን ጠለቅ ያለ እውነት ለመረዳት መታገል አለብን። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዱንም ክፍል እንኳ የማይጠቅም ወይም የማያስፈልግ አድርገን ሳንቆጥር ተግተን መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር የሚያደርገን የእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ ነው።
ምሳሌ 30፡5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤
ዮሐንስ 5፡43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።
የሰው ስም እንወዳለን። የቤተክርስቲያን መሪ የሆኑ ሰዎችን ከፍ ከፍ እናደርጋለን። ነገር ግን አንድ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ከተጣበቀ ወዲያው ትተነው እንሄዳለን።
ዮሐንስ 5፡44 እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
የቤተክርስቲያን ሰዎች መሪዎቻቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ ይወዳሉ፤ መሪዎችም ሕዝቡ በሚሰጡቸው ክብር መቀበል እና እራሳቸውን ታላቅ ማድረግ ይወዳሉ። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ከመሪዎቻቸው ጋር ካልተስማሙ አይሆንላቸውም፤ መሪዎቻቸውም ተከታዮቻቸውን ስለ ታማኝነታቸው ያመሰግኑዋቸዋል።
በድሮ ዘመን አይሁዳውያንም ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። እነርሱም ከመሪዎቻቸው ጋር መስማማት የሞትና የሕይወት ጉዳይ ሆኖባቸው ነበር።
መሪዎቻቸው ከሕዝቡ በላይ ከፍ ብለው መታየትን፤ ከሁሉ በላይ መከበርን ይወዱ ነበር። ሰዎች ደግሞ መሪዎቻውን የሚያከብሩት አንዳች ጥቅም እናገኛለን ብለው ነው። ሰዎች የአንድ ሐይማኖተኛ ቡድን አባል መሆን የግድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል፤ ምክንያቱም የሐይማኖት ቡድን አባላ መሆናቸው ለነፍሳቸው መዳን የግድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል።
ዮሐንስ 5፡45 እኔ በአብ ዘንድ የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ አለ፤ እርሱም ተስፋ የምታደርጉት ሙሴ ነው።
አይሁዳውያን ነብዩን ሙሴን ከፍ ከፍ በማድረጋቸው የሚድኑ መስሏቸዋል። ነገር ግን ሙሴ እራሱ ነው የሚፈርድባቸው።
አይሁውያን የሙሴን የሰንበት ቀን በኢየሱስ ላይ ለመፍረድ ተጠቀሙበት። ሆኖም የሙሴ ሕግ እራሱ ካሕናት እና ሌዋውያን በሰነበት ዕለት በአምልኮ ሰዓት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ብዙ ስራ እንዲሰሩ ያዝዛቸዋል። ኢየሱስ ደግሞ እውነተኛው የአይሁዳውያን ሊቀካሕናት ነበር።
የዘመን መጨረሻ ላይ የተገለጠውን ነብይ የሚከተሉ እና ንግግሮቹን በመጽሐፍ ቅዱስ ተፈትሾ ሊረጋገጥ በማይችል መንገድ የሚተረጉሙ የሜሴጅ አማኞች ወንድም ብራንሐም ይፈርድባቸዋል ምክንያቱም ወንድም ብራንሐም የተናገረውን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያረጋግጡ ነግሯቸዋል። እርሱ የተናገራቸው ንግግሮ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተኩ አልፈለገም፤ ምክንያቱም የንግግሮቹ ዓላም መጽሐፍ ቅዱስን መግለጥ ነበረ።
ዮሐንስ 5፡46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።
ሙሴ ሊመጣ ስላለው ነብይ ጻፈ።
ዘዳግም 18፡18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤
በኢየሱስ የተገለጠው ከተፈጥሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ኃይል ያለ ምንም ጥርጥር ሙሴ የተናገረለት ነብይ እርሱ መሆኑን ይመሰክራል። ሙሴም ይህ ታላቅ ነብይ ለአይሁዳውያን ብዙ የሚነግራቸው እንዳለው ተናግሯል። ስለዚህ አይሁዳውያን ሊሰሙት ይገባ ነበር።
ሙሴ ንጹሁን የፋሲካ በግ አስተዋወቃቸው። ኢየሱስ ንጹሁ የፋሲካ በግ ነበር።
ሙሴ አሮንን አጠበውና ሊቀ ካሕናት አድርጎ ቀባው።
ዘጸአት 29፡4 አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።
ዘጸአት 29፡7 የቅብዓትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባውማለህ።
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ አጠበው፤ ከዚያ በኋላ ዮሐንስ እያየ መንፈስ ቅዱስ እንደ እርግብ ወርዶ በአደባባይ ኢየሱስን ሊቀ ካሕናት አድርጎ ቀባው።
ዮሐንስ 5፡47 መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?
አይሁዳውያን ሙሴን እንከተላለን ይላሉ ግን እርሱ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ የተወሰኑትን ብቻ መርጠው ነው የሚያምኑት።
ከዚያ በኋላ በጣም ብዙ ሰው ሰራሽ ጠማማ ሃሳቦችን በራሳቸው አምጥተው የሰንበት ሕግ ናቸው አሉ። ነገር ግን ዋነኛውን ቁምነገር ስተዋል -- እርሱም ኢየሱስ ስለ እርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን በሙሉ በትክክል መፈጸሙ። ፈሪሳውያንን እና ሰዱቃውያንን የአይሁድ ሐይማኖት መሪ አድርጎ መሾም ትልቅ ስሕተት ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በመሪነታቸው ተጠቅመው ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ፈጥረው የአይሁድ ሕዝብ እንዲያመኑባቸው አድርገዋል።
አይሁዳውያን ሙሴ ከጻፋቸው እውነቶች ውስጥ የተወሰኑትን ማመን አልፈለጉም፤ ምክንያቱም ሙሴ የጻፋቸው እውነቶች እነርሱ ተማርከው ባቢሎን ውስጥ በነበሩ ሰዓት ከፈጠሩዋቸው ምኩራቦች፣ ከፈሪሳውያን፣ እና ከሰዱቃውያን ጋር አይማሙም። አይሁዶች ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተጻፈው ቃል ይልቅ በብዛት የሐይማኖት መሪዎቻቸው የሚነግሩዋቸውን ነው ለማመን የሚመርጡት። አንድ ጊዜ ለሐይማኖት መሪዎች ጆሮህን ከሰጠህ በኋላ የእነርሱን አመለካከት በመከተል ከመጽሐፍ ቅዱስ እየራቅህ ትሄዳለህ።
ስለዚህ ኢየሱስን አንቀበልም ብለው ገፉት፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ክርስቲያኖች ዛሬ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወኑ ክፍሎችን አይቀበሉም ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክሪስማስ አይናገርም፣ የክርስቶስን ልደት ስለማክበር፣ ስለ ዲሴምበር 25 እና ስለ ገና ዛፎችም አይናገርም። ግን ክርስቲያኖች ደግሞ ይህን ታላቅ በዓል ማክበር ይፈልጋሉ። እግዚአብሔርን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው መንገድ ሳይሆን በራሳቸው መንገድ ማገልገል ይፈልጋሉ። እስቲ ዲሴምበር 25 የአሕዛብ የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን መሆኑን ንገራቸው፤ የዛኔ ማንም እንደማይቀበልህ ታያለህ።
የሜሴጅ ፓስተሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚከተሉትን ማግኘት አይችሉም፡-
“ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።”
“የዊልያም ብራንሐም ንግግሮች ፍጹም ስሕተት የሌለባቸው እውነቶች ናቸው።”
“በ1963 የታየው ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነው።”
“የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ዊልያም ብራንሐም ምድር ላይ ሳለ መምጣት አለበት።”
“ሰባቱ የራዕይ ምዕራፍ 6 ማሕተሞች በሙሉ ተፈተዋል።”
“የጌታን አዲሱን ስም እናውቃለን።”
ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት አስተምሕሮዎች መከተል ማለት ወንድም ብራንሐም ያስተማራቸውን ትምሕርቶች እውነት መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መርምራችሁ አታረጋግጡም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ከላይ የተቀመጡት አተረጓጎሞች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይስማሙም።
ስለዚህ በነብዩ ንግግሮች ላይ ትልቅ ትኩረት በማድረግ የሜሴጅ ተከታዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው ሄደዋል።
ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የእርሱን ቃል የሚያምኑ የሜሴጅ ሰባኪዎች ማግኘት አይችለም። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ማለትም ቃሉ በዚህ በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ከቤተክርስቲያን ውስጥ ተገፍቶ ወጥቶ ከውጭ ቆሟል። ይህም አይሁዳውያን በጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ውስጥ ኢየሱስን ከመካዳቸው ጋር ተመሳሳይ ነው። ሰዎች የሐይማኖት መሪዎችን ጥቅስ ይፈልጋሉ -- ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አይፈልጉም።