ዮሐንስ ምዕራፍ 02. እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር ያደረገውና በክርስቶስ የጸናው ቃልኪዳን ምንደነው?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ የእግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ እንደመሆኑ በሰዎች ሕይወት ዙርያ የሚከሰቱ ክስተቶችን ጠለቅ ያሉ መንፈሳዊ ትርጉም ያላቸው እውነታዎችን የሚወክሉ ምሳሌ እንደሆኑ ያስተውላል። ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌል እግዚአብሔር ከሰፊ እቅዱ አንጻር የሰዎችን ትንንሽ ምድራዊ ዝግጅቶች እንዴት እንሚመለከት ያሳየናል።
“ገሊላ” የሚለው ቃል “ክብ” የሚል ትርጉም ካለው ቃል ነው የመጣው።
ክብ ስዕል መሳል እርሳስ በአንድ መስመር ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲሄድ ያስችላል። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተፈጸመ ምድራዊ ክስተት ክርስቶስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሚያሰራውን አገልግሎት ያንጸባርቃል።
ለምሳሌ አንዲት ሴት የምታደርጋቸው ድርጊቶች ቤተክርስቲያን ያለችበትን መንፈሳዊ ሁኔታ ይወክላሉ። ምክንያቱም ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የራሱ ሙሽራ አድርጎ ነው የሚያያት።
የአዳም ሙሽራ ሴት ተብላ ነበር የምትጠራው (ምክንያቱም ከወንድ ተገኝታለችና)፤ በሐጥያት ከወደቀች በኋላ ግን የሕያዋን ሁሉ እናት ሆነች። ከዚያ በኋላ ሔዋን የተባለ ሰው ሰራሽ ስም ተሰጣት።
በእግዚአብሔር ሰፊ እቅድ ውስጥ ይህ ምን ያሳየናል?
በጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ አማኞች ክርስቲያኖች ተብለው ነበር የሚጠሩት ምክንያቱም የክርስቶስ እና የቃሉ ብቻ ስለነበሩ። ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከዚያ በ325 ዓ.ም ንጉስ ኮንስታንቲን ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ ስልጣን ሰጣት።
“የሮማ ካቶሊክ” የሚለው ሰው ሰራሹ ስም እነርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው መውደቃቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው።
ዲኖሚኔሽናል ወይም በራሷ ስም የምትጠራ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ አሳሳችነትን እና ፖለቲካዊ ስልጣንን ከሃብት ጋር አጣምራ ስትይዝ ራሷን እንዲሁም ፕሮቴስታንት እና ፕሮቴስታንት ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖችን ስትወልድ እናት ቤተክርስቲያን ብላ እስክትጠራ ድረስ ኃይሏ ተጠናከረ። የሮማ ካቶሊኮች የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ሰውን ነው የሾሙት። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሃሳቦችን እና ቃላትን አስተዋወቁ። ዲኖሚኔሽን ወይም በሰው ሰራሽ የሚጠሩ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። ሥላሴም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ክሪስማስ እና የክሪስማስ ዛፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናል፣ እና ፖፕ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። የጥንቷ የአዲስ ኪዳን አማኞች ቤተክርስቲያንን የሚመራ ፓስተር አልነበራቸውም። ፓስተር ወይም እረኛ የሚለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስድስት ጊዜ ቢወገዝም አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው። አዲስ ኪዳን ውስጥ እረኛ ፓስተር ነው ተብሎ አልተጻፈም። ያ ሰው ሰራሽ ሃሳብ ነው።
ስለዚህ እንደ ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ አንግሊካን፣ ክሪክ ኦርቶዶክስ የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ ስሞችን በመጠቀም ቤተክርስቲያኖች በሐጥያት መውደቃቸውን ነው የሚያሳዩት፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ቃላት እና ሃሳቦች ያምናሉ።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ጋለሞታ ለባሏ ታማኝ ያልሆነች ሴት ናት። ጋለሞታ ማለት ለመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ታማኝ ሆና የማትጸና ቤተክርስቲያን ናት።
የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ባል ነው። ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ልክ ተጽፎ በሚገኝበት መልኩ ኢየሱስ ነው። እንደ ክርስቲያንነታችን እኛ የኢየሱስ ስለሆንን ለእርሱ ብቻ ታማኝ ሆነን መጽናት አለብን። የሮማ ካቶሊኮች ራሳቸውን እናት ቤተክርስቲያን ብለው ይጠራሉ።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሐይማኖት ለማትረፍ በንግድ ላይ ያተኮረ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ላይ ዘዴ አዘጋጀች። አሰራራቸውን የቀለጠፈ ለማድረግ በቄስ ወይም በፓስተር የሚተዳደር ቤተክርስቲያን መሰረቱ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሄዳ የሥላሴን ትምሕርት አመጣች።
ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔርን የሚጠሩበት አንድ ስም የላቸውም፤ ምክንያቱም አምላካቸው የሦስት ግለሰቦች ሕብረት ነው። ፖለቲካ ውስጥ መግባታቸው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዝነኛ እንድትሆን አደረጋት። አሁን የተጠቀሱት ሁሉ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነቶች እና አሰራሮች ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሌሎች ቤተክርስቲያኖችም እነዚህኑ እምነቶችና አሰራሮች በመኮረጃቸው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልጆች ሆነዋል። ሮም ባለፉት 1,900 ዓመታት ውስጥ በብዙ ነውጦች ስታልፍ ባለመጥፋቷ እና በገንዘብ ሃብታም መሆኗ እንዲሁም በፖለቲካ ውስጥ ባላት ተሳትፎ የተነሳ በሰው ሁሉ አእምሮ በዓለም ዙርያ የታላቅ ቤተክርስቲያን ገጽታ ነው ያላት። ስለዚህ ንግዶቿ እና የገበያ እውቀቷ እንዲሁም ዘዴዎቿ ሌሎች ቤተክርስቲያኖች በመኮረጅ እንዲከተሏት ምሳሌ ይሆናሉ፤ ቤተክርስቲያኖችም የአስተምሕሮ ልዩነት እያለ እንኳ የሮማ ካቶሊክን ይከተላሉ። ንግድ የንግድ ምልክትን የሚወክሉ ስሞችን በመጠቀም ነው የሚሰራው ለምሳሌ ኮካ፣ አፕል፣ ጉግል፣ ናይኪ። ሮም ቅዱስ ጰጥሮስን የመንግስተ ሰማያት በር ጠባቂ አድርጋዋለች፣ ማርያምን ደግሞ ጸሎታችሁን የምትሰማ ሩህሩህ እናት አድርገዋታል፤ ወደ ሌሎች ቅዱሳንም መጸለይ ይቻላል ብለዋል። ፖፕ ጆን ዳግማዊ፣ እማሆይ ቴሬዛ፣ እና ፖፕ ፍራንሲስ በዓለም ዙርያ የተከበሩ የሮማ ካቶሊክ የንግድ ምልክቶች ሆነዋል። የካቶሊኮች ሁሉ ሃብት በአንድ ላይ ብዛቱ ከአእምሮ በላይ ነው። ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖችም ታዋቂ የንግድ ምልክት የሚሆኑ ስሞቻቸውን ወደ ገበያ ገፍተው እያወጡ ናቸው፤ ለምሳሌ ተ. ዲ. ጄክስ፣ ጆሴፍ ፕሪንስ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ እና ጃውል ኦስቲን። ልጆች ልክ እንደ እናታቸው ናቸው። እነዚህ ስሞች የንግድ ምልክቶች እንደመሆናቸው የሚሊዮን ዶላሮች ዋጋ አላቸው።
ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
ቤተክርስቲያኖች ኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው እንደሚወድቁ በማወቅ ኢየሱስ የተወሰኑ ቁልፍ የሆኑ መርሆችን ያስቀምጣል፤ ዓላማውም ቤተክርስቲያን እነዚህን መርሆች በመከተል በሰው ሰራሽ ብልጣ ብልጥ የገንዘብ ማስገኛ ሃሳቦች ተስባ ከመታለል እንድትተርፍ ነው።
በራዕይ ምዕራፍ 1 ውስጥ ኢየሱስ እራሱን አልፋ እና ኦሜጋ ብሎ ይጠራል፤ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ማለት ነው።
ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገው ተዓምር ቃና ዘገሊላ ውስጥ በተዘጋጀው የሰርግድ ግብዣ ላይ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ መለወጥ ነው።
ኢየሱስ የሚሰራው የመጨረሻው ተዓምር ሕያው የሆነችዋን የቤተክርስቲያኑን ሟች አካል ወደ ከበረ አካል መለወጥ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው የሙሽራይቱ አካል የሆኑት ሰዎች ወደ ሰማይ ተነጥቀው በመሄድ በሰማይ ውስጥ የሚደረገው የሰርግ ግብዣ ላይ እንዲገኙ ነው።
ዮሐንስ 2፡1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
ቃና አንዳንድ ጊዜ “የሸምበቆዎች ቦታ” የሚል ትርጉም አለው፤ በአቅራቢያውም ሸምበቆ የሚያድግበት ረግረግ ቦታ አለ።
ራዕይ 11፡1 በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።
2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
በትር መለኪያን ይወክላል።
እዚህ ክፍል ውስጥ ከመለኪያው ጋር ትኩረት የተደረገው ርዝመትን መለካት ላይ ሳይሆን የሶስት ዓመት ተኩልን የጊዜ ርዝመት መለካት ላይ ነው። የመለኪያ ተምሳሌት የሆነው በትር እግዚአብሔር ለአይሁዶች የተወሰነውን የጊዜ ርዝመት መጥኖ እንደቆረጠላቸው ያመለክታል።
ከመቅደሱ ውጭ ያለውን ለአሕዛብ የተሰጠውን እድሞ አለመለካት የሚያመለክተው ምንድነው?
ለአሕዛብ የተወሰነላቸውን የጊዜ ርዝመት አናውቅም። ጌታ የሎዶቅያውያንን የቤተክርስቲያን ዘመን መች መጥቶ እንደሚያስቆም አናውቅም።
የተለያዩ ክርስቲያኖች በ1844 ወይም በ1914 ወይም በ1975 ወይም በ2013 ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል ግን ሁላቸውም ተሳስተዋል።
የሜሴጅ አማኞች በ1970 ወይም በ1977 ከዚያም በኋዋላ በ2000 ሊሆን ይችላል ብለው ገምተው ነበር ግን አንዴም እንኳ አልተሳካላቸውም። ቀን በመቁጠር የተጠመዱ ክርስቲያኖች ከኢየሱስ ጋር አልተጋቡም።
ቅድስቲቱ የኢየሩሳሌም ከተማ የአይሁዶች ናት። “ቅድስት” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እየተረገጡ ሳለ እየረዳቸው መሆኑን ያመለክታል ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱስ።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ለበጉ ሰርግ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ለአይሁዶች የሶስት ዓመት ተኩል የመከራ ጊዜ ይጀምራል (ያልተነጠቁ አሕዛብም በመከራው ውስጥ ያልፋሉ)።
ራዕይ 11፡3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
ምስክሮቹ ሙሴ እና ኤልያስ የተባሉ የአይሁድ ነብያት ናቸው። እነዚህ ሁለት ትንቢቶች ተመሳሳይ የጊዜ ርዝመትን እንዲሸፍኑ ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እያንዳንዳቸው 30 ቀናት ባሉት ወር ነው የሚተመነው።
ይህንን ከኖህ የጥፋት ውሃ ቀናት ጋር አነጻጽሩ።
ዘፍጥረት 7፡24 ውኃውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።
ዘፍጥረት 7፡11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፥ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ፤
ዘፍጥረት 8፡4 መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።
ከሁለተኛው ወር 17ኛ ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ወር 17ኛ ቀን ያሉ ቀናት አምስት ወራት ናቸው። ይህም 150 ቀን ነው። በትንቢታዊ የወር አቆጣጠር አንድ ወር 30 ቀን ነው።
ስለዚህ “በበትር” መለካትን የሚያመለክተው “ቃና” የሚለው ቃል የመሲሁን አገልገሎት በተመለከተ የአንድን ትልቅ ትንቢት ጊዜ ለመለካት የሚያገለግል መለኪያ ነው።
ኢየሱስ በአይሁዳውያን መካከል የሰባት ዓመት አገልግሎት ሊኖረው ይገባ ነበር።
አገልግሎቱን በጀመረበት ጊዜ አካባቢ ኢየሱስ ወደ ሰርግ ቤት ተጋበዘ። ስለዚህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቀኑ መቆጠር ስለተጀመረ በታሪክ እንደተመዘገበው ሶስት ዓመት ተኩል ካለፈ በኋላ ኢየሱስ በቀራንዮ ተሰቀለ። የእግዚአብሔር ሰዓት መቁጠሪያ የሆኑት አይሁዶች አልቀበልም ስላሉት ከእሥራኤል ጋር የተያያዘው ትንቢታዊ የዘመን ቀመር በቀራንዮ አቁሟል። ስለዚህ አይሁዶች ቃል ከተገባላቸው የጊዜ ርዝመት ግማሹን ብቻ ነው የተጠቀሙት።
ቤተክርስቲያን ወደ በጉ የሰርግ እራት ግብዣ ልትታደም ስትነጠቅ እግዚአብሔር ለቀሩት ስስት ዓመት ተኩል ጊዜ በታላቁ መከራ ወቅት ወደ እሥራኤል ስለሚመለስ ተቋርጦ የነበረው ትንቢታዊ ሰዓት መቁጠሩን (ይህም ኢየሱስ በፊት ባገለገለበት የሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ላይ ይደመራል)።
ይህም እውነት ቤተክርስቲያኖች ቤተክርስቲያኖች ያልገባቸውን ወሳኝ ትንቢት ያብራራልናል።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
ኢየሱስ የሰባት ዓመት አገልግሎት ነበር ማገልገል የነበረበት። አገልግሎቱ ግን የዘለቀው ለሶስት ዓመት ተኩል ብቻ ነው ምክንያቱም አይሁድ አልቀበልም አሉትና በሰባቱ ዓመታት እኩሌታ ላይ ገደሉት። በመስቀል ላይ በሞተም ጊዜ እግዚአብሔር የመቅደሱን መጋረጃ ቀደደው። ያም የአይሁድ ሕግ እና መስዋእቶቹ ከዚያ በኋላ እንዲያቆሙ አረደገ።
አይሁዶች ይህንን እውነት ባለመቀበል የተቀደደውን መጋረጃ ሰፍተው ትርጉም የሌላቸውን መስዋእቶች ማቅረብ ቀጠሉ፤ እግዚአብሔር ግን በ33 ዓ.ም ኢየሱስ ሲሞት መቅደሱን ትቶ ሄዷል። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሮማውያንን ልኮ በ70 ዓ.ም መቅደሱንም እንዲያፈርሱ አደረገ። የዛን ጊዜ መስዋእቶቹ ማብቃታቸውን ሁሉም አምኖ ተቀበለ።
መጥምቁ ዮሐንስ የቃልኪዳኑ መልእክተኛ ነበረ። እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ከአብራሐም ጋር አደረገ በክርስቶስ ደግሞ ቀራንዮ ላይ አጸናው። ስለዚህ ዮሐንስ ኢየሱስ ቃልኪዳኑን እንደሚያጸና አድርጎ አስተዋወቀ።
ሚልክያስ 3፡1 እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡
አንድ ሳምንት ሰባት ዓመታትን ለመግለጽ ያገለግላል።
ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።
ቤተክርስቲያኖች የክርስቶስ ተቃዋሚ ከእሥራኤል ጋር የሰባት ዓመት ቃልኪዳን ያደርጋል ይላሉ። ይህ ግን እውነት አይደለም። የሐሰት ዜና ነው።
ቃልኪዳኑ ጸንቷል፤ ታዲያ ከጸና በኋላ መች ነው የሚደረገው?
ደግሞስ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚናገርለት ቃልኪዳን የምን ቃልኪዳን ነው?
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ … አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል … ።
ቃልኪዳኑን የሚያጸናው የክርስቶስ ተቃዋሚ አይደለም፤ እግዚአብሔር ነው ቃልኪዳኑን የሚያጸናው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ቃልኪዳን የገባው መች ነው?
እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር ቃልኪዳን የገባው በዘፍጥረት ምዕራፍ 15 ነው።
መጀመሪያ ቃልኪዳኑ ለአብራሐም የተስፋይቱን ምድር እሥራኤልን ለመስጠት ብቻ ይመስል ነበር።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ዘፍጥረት 17፡19 እግዚአብሔርም አለ፦ በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤
ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
እግዚአብሔር የተስፋይቱ ምድር ለይሳቅ እንድትተላለፍ ከዚያም ደግሞ ለልጆቹ ለአይሁዶች እንድትተላለፍ ፈለገ።
የግብጽ ወንዝ በትክክል የትጋ እንደሆነ ለማመልከት ከባድ ነው። የናይል ወንዝ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ጌሴም በናይል ወንዝ እና በሲና በረሃ መካከል ነው። የግብጽ ወንዝ ናይል ከሆነ በጌሴም የነበሩት አይሁዶች ሙሴ በመጣበት ሰዓት እዚያው ባሉበት በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ነበሩ ማለት ይሆናል።
ጋዛ፣ ዌስት ባንክ፣ ዮርዳኖስ በከፊል፣ እና ከሶርያ ላይ ዳጎስ ያለ መሬት በሙሉ እግዚአብሔር ለአብራሐም ያበረከተለት ስጦታዎች ናቸው።
ቃልኪዳኑ ግን መሬት ከመስጠትም ያለፈ ጠለቅ ያለ ትርጉም ነበረው።
ጰውሎስ እውነቱን ገልጦ ሲጽፍ ቃልኪዳኑ ከአይሁድ ጋር ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያስረዳል።
ገላቲያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ቃሉ መሰረት ቃልኪዳን እያደረገ ነው።
ገሊላ በኡደት ድግግሞሽን የሚፈጥር የክብ ቅርጽን ያሳስባል።
ይህም ክብ ዙር አይሁዳውያን በተስፋይቱ ምድር ለ2,000 ዓመታት የኖሩበት፤ ከዚያም ዙሩ ሲገጥም ኢየሱስ በቀራንዮ የተሰዋበት፤ ከዚያም በኋላ ኡደቱ እንደገና ሲገጥም ዳግመኛ የተወለዱ አማኞች ወደሚኖሩበት የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ዘመን ታሪክ ያመራል።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
የሰባት ዓመት እኩሌታ ሶስት ዓመት ተኩል ነው። ኢየሱስ ለሶስት ዓመት ተኩል አገልግሏል። የእርሱ ሞት በመቅደሱ የሚቀርቡ መስዋእቶችን ሁሉ ዋጋ አሳጥቷቸዋል። የእነዚያ እንስሳት ደም ሐጥያት ይቅር እንዲባል በማድረግ ይሸፍን ነበር። ነገር ግን እነዚያ መስዋእቶች ሐጥያት የማድረግን ፍላጎት ማጥፋት አይችሉም ነበር።
የኢየሱስ ደም ሐጥያትን አጥቦ ማስወገድ የሚችል ደም እንዲፈስ እንዲሁም በኢየሱስ የደም ስር ውስጥ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ንሰሃ ወደ ገቡ ሰዎች ልብ ውስጥ መጥቶ በእነርሱ ውስጥ በመኖር ሐጥያት የመስራትን ፍላጎት እንዲያጠፋላቸው አደረገ።
ስለዚህ የብሉይ ኪዳን መስዋእቶች ቀርተዋል። ነገር ግን ይህ እንዴት አድርጎ ነው እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር የገባውን ቃልኪዳን ያጸናው?
ገላቲያ 3፡29 እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።
“የተስፋው ቃል።” አይሁዶች የተስፋ ምድር ተሰጥቷቸው ነበር። የክርስቲያኖች ተስፋ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
የክርስቲያኖች ምድር የእግዚአብሔር ቃል ነው። ክርስቲያን የሚያምነው እና የሚኖረው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ልክ እግዚአብሔር ለተስፋይቱ ምድር ደንበር እና ወሰን እንዳበጀላት መጽሐፍ ቅዱስ ለሃሳባችን እና ለድርጊታችን ድንበር ያበጃል።
ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።
ከዋክብት ሊቆጠሩ አይችሉም። ብዛታቸው ለመቁጠር አዳጋች ነው። ስለዚህ በሰው ታሪክ ውስጥ እጅግ ብዙ ሚሊዮን አይሁዶች ይኖራሉ።
ነገር ግን ይህ ቃል ዳግመኛ ለተወለደችው ቤተክርስቲያን ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው። ይህም የአብራሐም ዘር ከአውሬው ምልክት ጋር አንድ ላይ አይቆጠርም ማለት ነው። የአውሬው ቁጥር 666 ነው።
ይህ ቁጥር ትርጉሙ ምንድነው? ለዚህ ጥያቄ ፍንጭ የምናገኘው ከዮሐንስ ምዕራፍ 6፡66 ነው።
ብዙዎቹ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን ከመከተል ወደ ኋላ አፈገፈጉ።
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ለመቀበል እምቢ ማለት ሰዎች የአውሬውን ምልክት እንዲቀበሉ የሚያደርግ መሰረታዊ እርምጃ ነው።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አትከራከሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስን አትቃወሙ። ቃሉ ውስጥ የተጻፈውን እንዲሁ እመኑ።
የአብራሐምን እምነት በተመለከተ እግዚአብሔር ሲናገር እምነቱ ጽድቅ ነው አለ።
ዘፍጥረት 15፡6 አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።
ሮሜ 1፡17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ …
እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው ሙሉ ልባችን በእርሱ ላይ ጥለን እንድናምነው ነው፤ በእርሱ ማመናችንም መጽሐፍ ቅዱስን እንድናምን ያደርገናል።
ገላቲያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
ስለዚህ የቃልኪዳኑ ጠለቅ ያለ ትርጉም የአብራሐም የእምነት ልጅ የሆነውን ኢየሱስን ነው የሚያመለክተን እንጂ የአብራሐም ፍጥረታዊ ልጅ የሆነውን ይስሐቅን አይደለም።
ዘፍጥረት 15፡7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ አለው።
ስለዚህ እግዚአብሔር በኤፍራትስ እና በጤግሮስ ወንዝ አካባቢ ካለው ከባቢሎን ግዛት አብራሐምን አወጣው። ባቢሎናውያን እና ግብጻውያን የሥላሴ አስተምሕሮ የጀመሩ ሕዝቦች ናቸው፤ በእነርሱ ከተጀመረ በኋላ በስተ ምስራቅ ወደ ሕንድ ተዛመተ። ከዚህ በታች ያለው ምስል ሕንዶች ሶስት አካላት በአንድ አምላክ ውስጥ እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ ለማሳየት ያደረጉት ሙከራ ነው።
ከዚህ በታች ያለው ስዕል ግብጻውያን የሶስት ሰዎችን ሥላሴነት ለማሳየት ያደረጉት ሙከራ ነው።
ይህም ከዘመኑ የቤተክርስቲያኖች እምነት ብዙ የተለየ አይደለም።
ዘፍጥረት 15፡8 አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ።
አሁን እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ሊያደርግ ነው።
ዘፍጥረት 15፡9 እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።
54-1212 በራሱ ማለ
እንዲህ አለ፡- “ሂድ እና የሶስት ዓመት ጊደር አምጣልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም ነገር ከሶስት ጋር የተያያዘ ነው። ሶስት ወደ አንድነት ይደባለቃል። አያችሁ? አባት፣ ልጅ፣ መንፈስ ቅዱስ ሶስት አምላኮች አይደሉም፤ አንድ እንጂ። እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ሶስት ነገሮች አይደሉም፤ ሶስቱም የአንዱ ፍቅር ባህርያት ናቸው እንጂ።
ደግሞም መጽደቅ፣ መቀደስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ሶስት የተለያዩ የጸጋ መረከቶች አይደሉም፤ ነገር ግን አንድ ሥራ በሶስት መንገድ ሲገለጥ ነው እንጂ። በእምነት ስለመጽደቅ ለሉተር የገለጠለት ያው መንፈስ ቅዱስ እራሱ ነው ለዌስሊ ስለ ቅድስና የገለጠለት፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ አሁን ደግሞ ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይገለጣል፤ የተለያዩ መንፈስ ቅዱሶች ሳይሆኑ ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
….. እያንዳንዱ ነገር ሶሰት ዓመት መሆን አለበት። በሶስት የተለያዩ አስተዳደሮች ውስጥ ያልፋል፡- አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ።
ዘፍጥረት 15፡10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልከፈለም።
እያንዳንዱን እንስሳ ለሁለት ሰነጠቀ፤ ይህም ድርጊት ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳንን ይወክላል።
ዋኖስዋ እና እርግቧ ለሁለት አልተሰነጠቁም ወይም ለሁለት አልተከፈሉም። እነርሱም መዳንን እና ፈውስን ይወክላሉ። እነዚህ ሊከፈል ሊሰነጠቅ ከማይችለው ከቀራንዮ የተገኙ ሁለት በረከቶች ናቸው። መዳንን ካገኘህ ፈውስንም ማግኘት ትችላለህ።
እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ያደረገው ከአብራሐም ጋር ነበር ነገር ግን ቃልኪዳኑን ወደ ተጨባጭ እውነታ አምጥቶ ያጸናው በቀራንዮ ነው።
ቃልኪዳኑም ለእሥራኤል በሚሰጣት የተስፋ ምድር ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ከዚያም አልፎ በአዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ውስጥ የዘላለም ሕይወት ነው።
የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖች ናቸው። የእኛ ተስፋችን መንፈስ ቅዱስ ነው። የምንኖርበትም ምድር የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
54 12 12 በራሱ ማለ
ቀጥሎ ጊደሯን እና ፍየሉን ሌሎቹንም ነገሮች ቆራረጣቸውና አንዱን በሌላው አንጻር አስቀመጣቸው፤ ይህም ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን ተገጣጥመው እንደሚሻገሩ ያሳያል።
የእያንዳንዱ እንስሳ ለሁለት የተከፈለ ሥጋ አዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን በአንድነት አንድ ታሪክ እንደሚናገሩ ያሳያል።
በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ፍጥረታዊ እና መንፈሳዊ መገለጥ ይወክላሉ።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
በቀራንዮ መንፈስ ቅዱስ መስዋእት ሆኖ ከተሰዋው የኢየሱስ አካል ውስጥ ፈሰሰ።
56-0815 እምነት
ፓለስታይን እና በምስራቅ ያሉትን ሃገሮች ሄዳችሁ ብታዩ መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ መጽሐፍ ይሆንላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ ምስራቃዊ መጽሐፍ ነው። ከምስራቅ ሕዝቦች እይታ አጻር ስትመለከቱት አዲስ መጽሐፍ ይሆንባችኋላ።
በዚያ ጊዜ ሰዎች ቃልኪዳን ሲገቡ አንድ እንስሳ አምጥተው ያርዳሉ። እንስሳውን ይገድሉትና ቃልኪዳኑን በወረቀት ወይም በበግ ቆዳ ላይ ጽፈው በታረደው እንስሳ ሥጋ ላይ ይቀድዱታል። አንድ ሰው አንዱን ቅዳጅ ይወስደዋል፤ አንድ ሰው ደግሞ ሌላኛውን ቅዳጅ ይወስደዋል። ከዚያም በእግዚአብሔር ስም ይምላሉ፤ መሃላቸውም ይህንን ቃልኪዳን ብናፈርስ ሥጋችን እንደዚህ እንስሳ ለሁለት ይሰንጠቅ ማለታቸው ነው። የሚገርም ሊሻር የማይችል ቃልኪዳን ነው። እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ለአብራሐም ልክ እንደዚያ ነው የገባለት።
…. አሁን ተመልከቱ፤ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ልክ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጅ እንደነበረ፤ አብራሐም ግን እርሱን እንደሚወልደው በምን አወቀ? እነዚህን እንስሳት በሚያርድበት ጊዜ እግዚአብሔር ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ለአብራሐም እየነገረው ስለ ክርስቶስ እየነገረው ነበር።
እግዚአብር ቃልኪዳኑን ለማጽናት በቀራንዮ ምን አደረገ? የራሱን ልጅ ወደ ቀራንዮ ይዞ ሄደ፤ በቀራንዮ መስቀል ላይም ሰነጠቀው።
እርሱም እንዲህ አለ፡- “አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለው።” እርሱም - እግዚአብሔር መንፈሱን ከአካሉ ውስጥ ገንጥሎ አወጣና ሥጋውን ወደ ክብር አገባው (ይህን ታምናላችሁ?) በግርማው ቀኝ ተቀምጦ በእርሱ ውስጥ የነበረውን መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ እርሱ ያደርግ የነበረውን ሁሉ በማድረግ ቃልኪዳኑን እንዲያጸና ወደ ቤተክርስቲያን ላከው። ቃልኪዳኑን በዚህ እና በዚያ እንዲጽፍ…
56-0815 እምነት
ወንድሞች በዚህ ዓለም ውስጥ ቃልኪዳኑ ተጠብቆ ሊቆይ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ እናንተ እና እኔ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ስንቀበል ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር የክርስቶስ ሥጋ እንደመጋረጃው እንዲቀደድ ያደረገው መንፈስ ቅዱስን ለእናንተ እና ለእኔ ሊልክልን ብሎ ነው። በመነጠቅ ልንሄድ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ያ አካል መንፈስ ቅዱስን መልሶ ለመውሰድ ሲመጣ ነው፤ በዚያ ጊዜ በቃልኪዳኑ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይነጠቃሉ። ቃልኪዳኑም በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚሆን መገረዝ ነው፤ ያም የአብራሐም ዘር ነው። አሜን። ኦህ። እኔ እራሴ መጮህ ያምረኛል። አቤት።
እግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሰጠ እና ክርስቶስን በቀራንዮ ሰነጠቀው። በበዓለ ሃምሳ እለት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ላከ፤ ስለዚህ በክርስቶስ ውስጥ የነበረው መንፈስ በእናንተ ውስጥ ስለሆነ እናንተ አዲስ ፍጥረት ናችሁ። ክርስቶስ እንዲህ አለ፡- “እኔ የምሰራውን ሥራ እናንተም ትሰራላችሁ፤ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ሃሌሉያ።
ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ በቀራንዮ ልጁን ይዞ ሄደና ሥጋውን እንደ መቅደሱ መጋረጃ ቀደደው ነፍሱን እና አካሉን፤ ከዚያ አካሉን ከፍ አደረገውና በቀኙ አስቀምጦት ኢየሱስ እስኪመለስ ድረስ ንፈስ ቅዱስን ስራውን በምድር ላይ እንዲቀጥል ወደ ቤተክርስቲያን ላከው።
56-0816 የመንፈስ ቅዱስ ሥራ
ቃልኪዳኑንም ይጽፈዋል … በብሉይ ኪዳን ውስጥ በመቅደሱ ቅድስተ ቅዱሳን ትዕዛዛቱ በድንጋይ ጽላቶች ላይ ነበር የተጻፉት። እርሱ ግን እንዲህ አለ፡- “ከእነዚያ ወራት በኋላ መንፈሴን አፈስሳለው ቃልኪዳኔንም በልባቸው ጽላት ላይ እጽፈዋለው፤ በልቦናቸውም ውስጥ አደርገዋለው።” አሜን። አያችሁ?
ከዚያም እግዚአብሔር ኢየሱስን ማመናችሁን በአፋችሁ ስትናገሩ በመንፈስ ቅዱስ የሰላም ቃልኪዳንን በልባችሁ ላይ ይጽፈዋል።
ከዚያም በክርስቶስ ውስጥ የነበረው መንፈስ በእናንተ ውስጥ ይኖራል፤ እርሱም በውስጣችሁ በመኖር ክርስቶስን መስላችሁ እንድትመላለሱ ያደርጋችኋል። እግዚአብሔርም በእነዚህ አካሉ በሚባሉ ሕዝብ ውስጥ ሐዋርያት፣ ነብያት፣ አስተማሪዎች፣ ወንጌላውያን፣ እና እረኞችን አስቀምጧል።
ዕብራውያን 8፡10 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።
የቃልኪዳኑ እውነተኛ ዓላማ በቀራንዮ ከክርስቶስ ስጋ ውስጥ የወጣውን መንፈስ ቅዱስ ለመውሰድና ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት መኖር ይችሉ ዘንድ ንሰሃ ወደገቡ ሰዎች ልብ ውስጥ መንፈሱን ለመላክ ነው።
ዘፍጥረት 15፡11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።
የአሞራዎቹ ትርጉም ምንድነው?
ማርቆስ 4፡3 እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።
4 ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።
ማርቆስ 4፡14-15 ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል።
ስለዚህ ሰይጣን ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ከመቀበል እምቢ እንዲሉ ያደርጋል። ሰዎች የአውሬውን ምልክት እንዲቀበሉ የሚያደርጋቸው የእግዚአብሔርን ቃል አለመቀበላቸው ነው።
አብራሐም ግን በእግዚአብሔር ቃል የሚያምን ሰው ነበረ። ለዚህ ነው አሞራዎቹን ሊታገሳቸው ያልቻለው፤ አሞራዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል በከፊል የማይቀበሉ ሰዎች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች ከፊሉ የእግዚአብሔር ቃል አላስፈላጊ ነው ወይም ስሕተት አለበት ይላሉ።
ማቴዎስ 24፡28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።
ለእያንዳንዱ ዘመን ትኩስ ስጋ ወይም አስተምሕሮ ይቀርብለታል።
ዕብራውያን 6፡6 በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።
የካዱ እና የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል አልቀበልም ያሉ ሰዎች ክርስቶስን የእውነት እንደገና ይሰቅሉታል። እውነተኛዎቹ አማኞች ግን ማለትም ንስሮቹ ሌሎች ሰዎች የናቁትን ያጣጣሉትን ለዘመናችን የተገለጠውን ቃል ይፈልጉታል።
ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። ለዘመናችን የተሰጠንን የተገለጠ የእግዚአብሔር ቃል የሚጠሉ ሰዎች አሉ። እውነትን ካመንክ ማንም አይቀበልህም።
ቃልኪዳኑን ወደ ፍጻሜ የሚያመጣው አብራሐም እራሱ እንዳልሆነ ለማሳየት እግዚአብሔር አብራሐምን እንቅልፍ ያስተኛዋል። ይህ የጸጋ ቃልኪዳን ነው። ቃልኪዳኑ ተፈጻሚነቱ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር በሚሰራው ሥራ ብቻ ነው የሚወሰነው። ቦኤዝ ሩትን ተቤዣት።
ከሩት የሚጠበቅባት ነገር ቢኖር ከቦኤዝ እግር ስር ተኝታ እርሱ የሚቤዥ ዘመድ ማድረግ የሚገባውን እስኪያደርግ ድረስ መጠበቅ ብቻ ነበር። እርሱም ጫማውን ማውለቅ ነበረበት። ኢየሱስ ክብሩን ሁሉ በሰማያት አውልቆ ማንም ሰው ከማያውቃት አንዲት ሴት የሚሸት በረት ውስጥ ለመወለድ ወደ ምድር ወረደ። ማርያም ዮሴፍን ከማግባቷ በፊት ለሶስት ወራት ኤልሳቤጥጋ በመቆየቷም የተነሳ ከጋብቻ ውጭ ተጸንሶ የተወለደ ልጅ የመባልን የስድብ ስም ለመሸከም እንኳ እምቢ አላለም። እውነተኛው መንገድ ሁልጊዜም ቀላሉ መንገድ አይደለም።
ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
56-0815 እምነት
አሁን ምን እንዳደረገ አስተውሉ። ከዚያም እንዲህ አለ፡- “አብራሐም ሆይ፤ አሁን ከዚህ ጉዳይ አስወጣሃለው። በዚህ ጉዳይ ውስጥ አንተ ምንም የምታዋጣው አስተዋጽኦ የለም።” አብራሐምም አንቀላፋ። እንቅልፉንም ሲተኛ መጀመሪያ ያየው ከባድ ጨለማ ነበር፤ ሞት ወደያንዳንዱ ሰው የሚመጣ ሞት። “ለሰዎች አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኋላ ፍርድ ተመድቦባቸዋል።” ከባድ ጨለማ ስለነበረ ፍርሃትም ወደቀበት። አብራሐም ጨለማ መጣበት።
መዝሙር 23፡4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
ከዚያ በኋላ ግን የሚጨስ እቶን አየ። እያንዳንዱ ሐጥያተኛ ሲኦል መግባት ይገባዋል። እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን እያጸናው ነው… ተመልከቱ። ከሚጨሰው እቶን በኋላ አብራሐም ትንሽ ነጭ ብርሃን አየ፤ እርሱም መዳን ነው። ይህም ትንሽ ነጭ ብርሃን ወደተሰነጠቁት እንስሳት ሄዱ በመካከላቸው አለፈ፤ ይህም ትንሽ ነጭ ብርሃን ከአብራሐምም ጋር ቃልኪዳኑን አጸደቀ። ስለምን እየተናገረ ነበር?
መንፈሳዊ አእምሮ ካለህ ይህ ተምሳሌት በቀላሉ ይገለጥልሃል። ስለ ክርስቶስ ነበር የሚናገረው። እነዚያ እንስሳት እያንዳንዳቸው፤ እነዚያ ወፎች እያንዳንዳቸው፣ ሁሉም ነገር ክርስቶስ በቀራንዮ የሚሰራውን ነበር የሚያመለክቱት። እስቲ አሁን በደምብ እንድታስተውሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ልስጣችሁ።
56-1209E ያህዌ ይርኤ
ስለዚህ ሞት መጀመሪያ ይመጣል። ከዚያም በሚጨሰው እቶን የተመሰለው ሲኦል ነው የሚቀጥለው። ከዚያ በመቀጠል ብርሃን አየ። አሁን ተመልከቱ። ይህም ብርሃን ቃልኪዳኑ እንዲፈጸም በተሰነጠቁት እንስሳት ሁሉ መካከል አለፈ፤ ይህም እግዚአብሔር በተስፋው ዘር አማካኝነት ኢየሱስን በማስነሳት ቃልኪዳኑን ከምድር አሕዛብ ሁሉ ጋር እንደሚያጸናው የሚያመለክት ነው፤ ለዚህም ነው አብራሐም የአሕዛብ አባት የተባለው።
አስተውሉ፤ ከዚያ በኋላ ነው ስሙን ከአብራም ወደ አብራሐም የለወጠለት።
ለሁለት የተከፈሉት የእንስሳቱ ስጋ ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳንን ይወክላሉ። ኢየሱስ በሁለቱ ኪዳኖች መካከል መጣ። አራቱ ወንጌሎች በሁለቱ ኪዳኖች መካከል እንደ መሸጋገሪያ ያገለግላሉ። ኢየሱስ ሲሞት ወደ ጨለማው የሲኦል ክልል ወርደ፤ በዚያም ሰዓት እንደ እሳት የሚነድደው መንፈስ ቅዱስ ነው ብርሃን የሆነለት እና የሞትን መክፈቻዎች ከሰይጣን እጅ የቀማው። ሐጥያታችንን ወስዶ ሰይጣን ላይ አራገፈውና በሁለቱ ኪዳኖች መካከል አልፎ በመሄድ ሁሉም ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው መሰረት መከናወኑን አረጋግጦ ከሲኦል የመዳናችን ጉዳይ እርግጥ እንዲሆን አደረገ።
ዘፍጥረት 15፡13 አብራምንም አለው፦ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።
የአብራሐም ፍጥረታዊ ዘሮች አይሁዳውያን ሲሆኑ እነርሱም ሙሴ መጥቶ ነጻ እስከሚያወጣቸው ድረስ ግብጽ ውስጥ በባርነት ይቆያሉ።
የአብራሐም መንፈሳዊ ዘሮች ማለትም በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በዲኖሚኔሽናል ባሕሎች ውስጥ በባርነት ተይዘው ሰባተኛው መልአክ መጥቶ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮች እስኪገልጥላቸው ድረስ በባርነት ይቆያሉ።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
57-0106 ያህዌ ይርኤ
አባቶች አርጅታችሁ ይሆናል፤ እናቶችም አርጅታችሁ ይሆናል፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተስፋውን ልንገራችሁ፤ በትንሳኤ እንደገና ወጣት ትሆናላችሁ። ደግሞም የእግዚአብሔርን ቃል ተስፋ እሰጣችኋለው፤ መቼም ቢሆን መላእክት አትሆኑም። ሰው ነው የምትሆኑት። እግዚአብሔር ሰው አድርጎ ሲፈጥራችሁ ኋላ ሰውነታችሁን ለማጥፋት ሳይሆን ለማስነሳት ነው። ሐጥያት አጥፍቷችሁ ነበር፤ ሕይወት ግን ዘላለማዊ ያደርጋችኋል። መላእክት አትሆኑም። እግዚአብሔር መላእክት እንድትሆኑ ቢፈልግ ኖሮ… መላእክት አድርጎ ይፈጥራችሁ ነበር። ሰው እንድትሆኑ ነው የፈለገው፤ ስለዚህ ሰው አድርጎ ነው የፈጠራችሁ።
ስለዚህ ልጁን ወሰደውና የሐጥያተኛ የሚመስል ሥጋ አዘጋጀለት፤ ወደ ቀራንዮ ወሰደው (አሁን አድምጡ።) ወደ ቀራንዮ ወሰደውና በዚያ እግዚአብሔር ከሰው ዘር ጋር የሚገባውን ቃልኪዳን ጻፈ። ኦ ወንድሜ ሆይ ተመልከት። ጌታ ኢየሱስን ነጻ አውጪውን ወሰደውና ወደ ቀራንዮ ይዞት ሄደ፤ በዚያም እንደ መጋረጃ ቀደደው። አካሉን ወደ ሰማይ ወስዶ በቀኙ አስቀመጠው፤ ሌላኛውን ክፍል ደግሞ ወደ ምድር ላከው እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው። ያ መንፈስ ቅዱስ እራሱ አሁን በምድር ላይ ነው። እርሱም የክርስቶስን አካል እየሰራ ነው። በትንሳኤ ቀንም በበዓለ ሃምሳ ቀን የወረደው መንፈስ ቅዱስ እራሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የነበረው መንፈስ ቅዱስ እራሱ በቤተክርስቲያን በአማኞች ውስጥ ከተገኘ ነው ወደ ቃልኪዳኑ ውስጥ የሚገቡትና የአብራሐም ዘር የሁሉም ነገር ወራሽ የሚሆኑት! አሜን። እግዚአብሔር ይህንን እንደሚያደርገው ምሏል። እንደሚያደርገው የተስፋ ቃል ሰጥቷል። እንደሚያደርገው ቃልኪዳን ገብቷል። እንደሚያደርገው ለማረጋገጥ ክርስቶስን ከሙታን አስነስቷል። አንዳችም የሚያስፈራን ነገር እንደሌለ ሊያረጋግጥላችሁ ብሎ ኢየሱስ በምድር ሳለ ይሰራ የነበረውን ሥራ መስራት እንዲቀጥል መንፈስ ቅዱስን ልኳል።
ቃና ትልቅ መንፈሳዊ ትርጉም ያላቸው ነገሮች የሚከሰቱበት ቦታ ይመስላል።
የመሲሁ ምልክት የሰዎችን የልብ ሚስጥር መግለጥና ከጊዜ እንዲሁም ከቦታ ርቀት አሻግሮ ማየት ነው።
1ኛ ነገስት 8፡39-40 … በማደሪያህ በሰማይ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።
ኢየሱስ የመሲህነት ምልክቱን ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጠው ከቃና ለመጣው አይሁዳዊ ለናትናኤል ነው።
ዮሐንስ 21፡2 እንዲህም ተገለጠ፦ ስምዖን ጴጥሮስና ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ከገሊላ ቃና የሆነ ናትናኤልም የዘብዴዎስም ልጆች ከደቀ መዛሙርቱም ሌሎች ሁለት በአንድነት ነበሩ።
ዮሐንስ 1፡48 ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።
49 ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።
50 ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።
ኢየሱስ የናትናኤልን ልብ አውቆታል፤ ፊት ለፊት ሳያገኘው በፊት በርቀት አይቶታል፤ ፊሊጶስ እንደሚጠራውም ቀድሞ አውቋል።
ናትናኤልም ኢየሱስ በተስፋ ቃል የተነገረለት ንጉስ መሆኑን እውቅና ሰጠ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከትልቅ የቦታ ርቀት አልፎ ማየት እንደሚችል እንዲሁም በጊዜም ወደ ኋላ ተመልሶ ማየት እንደሚችል አሳይቶታል። ከዚያም በላይ የሰዎችን የልብ ሃሳብም ጭምር ማየት ይችላል።
ሶስተኛው ቀን።
ዮሐንስ ኢየሱስን እንደ በራሪ ንስር አድርጎ ያቀርባል፤ ይህም እግዚአብሔርን የሚወክል አገላለጽ ነው። ስለዚህ ዮሐንስ በሰዓቱ እየሆኑ የነበሩትን ክስተቶች ከ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ አንጻር በእግዚአብሔር ሰፊ እቅድ ውስጥ ነው የሚመለከተው።
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያቱ ቤተክርስቲያንን እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መሰረቷት። የሰዎች መሪነት ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር ሲጀምር የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የነበራት እውቀት በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፋ። ከዚያ በኋላ ጠፍቶ የነበረው እውቀት የሚመለስባቸው ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ተከትለው መጡ። ጀርመኒ ውስጥ በ1520 ማርቲን ሉተር በስራ ሳይሆን የምንድነው በእምነት መሆኑን በማስተማር የሳርዲስ ቤተክርስቲያን ዘመንን ተሃድሶ አመጣ። ይህም የመጀመሪያው የተሃድሶ ዘመን ወይም “ቀን” ነበር።
በ1750 አካባቢ እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ በቅድስና የመኖር እና ወንጌልን የማሰራጨትን አስፈላጊነት ባስተማረ ጊዜ የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ዘመንን ተሃድሶ አመጣ። ይህም ተሃድሶ በ1790 አካባቢ የተጀመረውን ታለቁን የወንጌል ስርጭት ወይም ሚሽነሪ ዘመን አስጀመረ። ይህ ሁለተኛው ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ትምሕርቶች የመመለስ የተሃድሶ ዘመን (ወይም ሁለተኛ ቀን) ነበረ።
ሶስተኛው የተሃድሶ ዘመን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ሁለት ደረጃዎች ነበሩት። በ1904 የዌልሽ መነቃቃት ከዚያም በ1906 ደግሞ ዝነኛውና ለአራት ዓመታት የዘለቀው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን መለኮታዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ያመጣው የአዙዛ እስትሪት መነቃቃት ሆነ። ከዚያ በኋላ በ1947 እና በ1965 መካከል ዊልያም ብራንሐም አሜሪካ ውስጥ ተነስቶ ለመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በመጀመሪያው ዘመን ተገልጠው የነበሩ ኋላ ግን በጨለማው ዘመን የጠፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ሊመልስልን ፈለገ። ከእርሱ በፊት የተነሱት የተሃድሶ መሪዎች እነዚህ ምስጢራት በአግባቡ አልተገለጡላቸውም ነበር።
ስለዚህ አሁን በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ በአዲስ ኪዳን እውነቶች ተሃድሶ ውስጥ “በሶስተኛው ቀን” ላይ ነን። የእኛ ሃላፊነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ምስጢራት መገለጥ ማግኘት ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እየተመለስን ባለንበት ሰዓት የመጨረሻው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማስረጃ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መግለጥ ነው።
ሰርዴስ፣ ፍልድልፊያ፣ ሎዶቅያ። እነዚህ ሶስት ዘመናት ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የመመለስ ተሃድሶ ዘመናት ናቸው። በሶስተኛው የተሃድሶ ዘመን መጨረሻ (በሶስተኛው “ቀን”) ቤተክርስቲያን ለበጉ እና ለሙሽራይቱ ሰርግ ወደ ሰማይ ተጠርታ ትሄዳለች።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጋለሞታዎች እናት ተብላ ትታወቃለች፤ እነዚህም ጋለሞታዎች የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች እና ካቶሊክ ያልሆኑ ዲኖሚኔሽናዊ እንዲሁም ከዲኖሚኔሽን ውጭ ያሉ ቤተክርስቲያኖች ናቸው። ዲኖሚኔሽን የሚለው ቃል እራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ነው፤ ከዚህም የተነሳ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። የተቀሩት ወንድም ብራንሐም የተናገራቸውን ቃሎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደው የማይመረምሩ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ የተገለጡትን ሚስጥራት አያገኙዋቸውም።
እንደዚህ ዓይነት ክርስቲያኖች ጥልቅ የሆኑትን መገለጦች አያስፈልጉም ወይም አይጠቅሙም ብለው ይገፉዋቸዋል። ከዚህም የተነሳ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን መረዳት አይችሉም፤ ለምሳሌ ሐጥያት ስትሰራ ስለተያዘችዋ ሴት ሊጠይቁት ሲመጡ ኢየሱስ ምድር ላይ ለምን ሁለት ጊዜ እንደጻፈ ቢጠየቁ መልስ የላቸውም። ከዚህም የተነሳ የተሳሳቱ አስተምህሮዎቻቸውን አጥብቀው ይዘው ይቀጥላሉ።
ዮሐንስ 2፡1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ እንደተባለችው ሁሉ ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።
ማርያም የጥንቷ እስከ 170 ዓ.ም የዘለቀችው በኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን የነበረችዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።
ልክ ማርያም ለተወሰኑ ወራት ኢየሱስን በሆድዋ እንደያዘችው ይህች የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል ትሸከማለች።
ኢየሱስ ማርያምን በስም አይጠቅሳትም። ለምን? ዮሐንስ አመለካከቱ ሁልጊዜ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ እይታ ነው። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ደቀመዛሙርት ወይም ክርስቲያኖች ብቻ ተብላ ነው መጠራት ያለባት። የትኛዋም ቤተክርስቲያን እንደ ሮማን ካቶሊክ፣ ሉተራን፣ ሜተዲስት፣ ፔንቲኮስታል፣ ሜሴጅ አማኞች የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ ስሞችን መጠቀም የለባትም። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንደዚህ ዓይነት ስሞች አልነበሩዋትም። ክርስቲያን ተብለው ብቻ ነበር የሚጠሩት፤ ትርጉሙም ክርስቶስን የሚመስሉ ማለት ነው።
የመጀመሪያዋ ሴት ሔዋን የተባለውን ስም ያገኘችው በሐጥያት ከወደቀች በኋላ ነው። ክርስቲያኖች በሆነ የቤተክርስቲያን ስም ከተጠሩ በኋላ ወደ አለማመን ወይም ሐጥያት ውስጥ ወድቀዋል ማለት ነው።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት አማኞች ክርስቲያኖች ብቻ ተብለው እንደሚጠሩ በማወቁ ዮሐንስ የኢየሱስን እናት በስም አይጠቅሳትም። በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በየትኛውም አካባቢ የነበረች ቤተክርስቲያን የራሷ ስም አልነበራትም።
ይህም ከኋላ የተነሱ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ለራሳቸው ስም ባለማውጣት እናታቸው የሆነችውን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን መከተል እንዳለባቸው ያሳያል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እናት ቤተክርስቲያን እኔ ነኝ ትላለች ግን አነርሱ ሃብታቸው እና ኃይላቸው እየገነነ የመጣው በ325 ዓ.ም ከተደረገው የኒቅያ ጉባኤ በኋላ ነው።
ትክክለኛዋ እናት ቤተክርስቲያን ግን የመጀመሪያዋ ሐዋርያት የመሰረቱዋት ቤተክርስቲያን ናት።
ዘጸአት 20፡12 አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
አምስተኛው ትዕዛዝ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ያዝዛል። ግን ደግሞ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ትርጉምም አለው።
አዲስ ኪዳንን ወደጻፉት ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ አለብን። እውነተኛዋ እናት ቤተክርስቲያን ወደ ሆነችው የደ መጀመሪያዋ ቤተክርስያን እምነት መመለስ አለብን። ይህም የሞቱት ክርስቲያኖች ከሙታን በሚነሱበት እና ሕያዋን ክርስቲያኖች የከበረውና የማይሞተው አካላቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ ረጅም እድሜ ይሰጠናል። በአንድነት ሆነን ከኢየሱስ ጋር በምድር ላይ ለዘላለም እንኖራለን።
ለዘላለም ማለት በእውነትም ረጅም እድሜ ነው።
በዘመን መጨረሻ ላይ ያለችዋ ቤተክርስቲያን ስለዚህ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነቶችና ልምምድ መመለስ አለባት።
የበቆሎ ዘር ይተከልና የተወሰኑ የእድገት ደረጃዎች ውስጥ ካለፈ በኋላ ለመከር ጊዜ ልክ መጀመሪያ የተዘራውን ዓይነት ዘር ይሰጣል።
ኢየሱስ የሚሰራው የመጨረሻው ተዓምር መሽራይቱን ወደ ከበረው አካል መለወጥ እና በሰማያት ወደተዘጋጀው ሰርግ መጥራት ነው። ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ መጀመሪያ የሰራው ተዓምር በሰርግ ቦታ ላይ ነበር።
ራዕይ 19፡7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።
9 እርሱም፦ ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ። ደግሞም፦ ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። የመጨረሻው ዘመን ሙሽራ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ከኢየሱስ ጋር በሰማይ ለሚደረገው ጋብቻ ራሷን ማዘጋጀት አለባት። ማንም ወደዚያ ሰርግ እንዲሁ ተነስቶ መሄድ አይችልም። እያንዳንዱ ታዳሚ ካልተጠራ በቀር ወደ ሰርጉ መሄድ አይችልም። ሁላችንም ያንን እኩለ ሌሊት ላይ የሚደረገውን ጥሪ እንጠባበቃለን። እስከዚያ ድረስ ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ልባሞቹም ሰነፎቹም ቆነጃጅት በሰዎች ልማድ ውስጥ እንቅልፋቸውን ተኝተዋል። ራሳቸውን በራሳቸው በሚያጸድቁበት ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን ስርዓታቸው ውስጥ ከባድ እንቅልፍ አንቀላፍተዋል።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
ቤተክርስቲያኖችን ለእውነታው ለማንቃት የተሞሉበትን የሰው ወግ አራግፈው እንዲጥሉ የሚያደርግ ከቤተክርስቲያን ውጭ የሚመጣ የጩኸት ድምጽ ያስፈልጋል።
“ተነስታችሁ ውጡ።” የትኛውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ብትሆኑ ለመዘጋጀት አይረዳችሁም። ጌታ ሲመጣ እርሱን ለመገናኘት መውጣት አለባችሁ።
የሙታን ትንሳኤ የሚሆነው በመላእክት አለቃ ድምጽ ነው። የዚህ መልአክ ጩኸት ቤተክርስቲያኖችን ያነቃቸዋል።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
የዊልያም ብራንሐም መልእክት ሙሽራዋ ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በመመለስ ለጌታ ምጻት እንድትዘጋጅ የሚያስችላትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የሚገልጥ ጩኸት ነበር።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ነገር ግን ይህ እንኳ ቤተክርስቲያንን ከእንቅልፏ አያነቃትም።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
ይህ ነው ዛሬ መነቃቃት እንዲኖረን የሚያስፈልግበት ዋነኛ ምክንያት። የዲኖሚኔሽኖችን መነቃቃት አይተናል፤ ትክክለኛ መነቃቃት ግን እስከ አሁን አልመጣም። በፍጹም፣ በጭራሽ፣ የለም፤ ትክክለኛ መነቃቃት አይተን አናውቅም። ሚሊዮን፣ ሚሊዮን፣ ሚሊዮን የቤተክርስቲያን አባላትን ሰብስበዋል ግን እውነተኛ መነቃቃት ሆኖላቸው አያውቅም። በፍጹም።
ሙሽራዋ እስከ አሁን ድረስ መነቃቃት አልሆነላትም። አያችሁ? መነቃቃት አልመጣም፤ ሙሽራዋን የሚያነቃ የእግዚአብሔር መገለጥ አልታየም። አያችሁ? እየፈለግነው ነን። ሙሽራዋን ከእንቅልፏ ለማንቃት የእነዚያ የማይታወቁ ነጎድጓዶች ድምጽ ያስፈልጋል። እርሱ መነቃቃትን ይልካል። ቃል ገብቷል። ተመልከቱ አሁን። እርሷ ሞታ ነበር።
መልእክቱ በጩኸት ከተላለፈ በኋላ የመላእክት አለቃ ይወርድና አንድ እግሩ ን በምድር አንድ እግሩን በባሕር አድርጎ በመቆም ሞተው የተቀበሩ ሞታንን እንዲነሱ ይጠራቸዋል።
ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥
ይህ የሚሆነው መጽሐፉ በተከፈተ ጊዜ ነው። ምስጢራቱ ከተገለጡ በኋላ ነው።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
“በታላቅ ድምጽ ጮኸ” እና “በጮኸም ጊዜ” የሚሉት ሁለቱም አገላለጾች የሚናገሩት ስለ ሙታን ትንሳኤ ነው።
ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
64-0119 ሻሎም
ነገር ግን አስታውሱ፤ ቀጥታ ወደ ሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብትገቡ፣ “ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሏል። ታላቁ ገዥ መጥቶ በትሩን ሲሰነዝር “ከዚያ በኋላ ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር፣ አንድ እግሩን በባሕር አድርጎ ሲቆም ቀስተ ደመና ከራሱ በላይ ጋርዶት ሲቆም “ከዚህ በኋላ ጊዜ አይኖርም” ብሎ ማለ። ያ ጊዜ ሲመጣ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ተኝተው ሲቀሩ እናንተ ግን ተነስታችሁ ትገባላችሁ።
ስለዚህ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ሙታንን የሚያስነሳው የመላእክት አለቃ ነው። አንበሳው እንደ ይሁዳ አምበሳ በድል በአሸናፊነት ሲያገሳ በሰይጣን ላይ ትልቅ ድል ለመጎናጸፍ ሙታንን ያስነሳል።
ከዚያ ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ያሰማሉ፤ ቃላቸውም ለሙሽራይቱ ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት ይሰጣታል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ከዚያ በኋላ የሚመጡ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች አሉ፤ እነርሱም ምን እንደተናገሩ አልተጻፈም። እውነት ነው፤ እኔም እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ሙሽራዋ ለመነጠቅ የሚያዘጋጅ እምነት እንድታገኝ በመጨረሻዎቹ ቀናት ደምጻቸውን እንደሚያሰሙ አምናለው፤
መጀመሪያ ትንሳኤው ይቀድማል። ከዚያም በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ስጋቸው የማይሞት ሆኖ ይለወጣል። ከዚያ በኋላ ወደ ሰርጉ ግብዣ የሚጠራቸው የእግዚአብሔር መለከት ይነፋል።
(ትራምፕ ፕሬዚዳንት መሆኑ ሁሉም ሰው ስለ ትራምፕ እንዲያወራ ምክንያት ሆኗል።
[ትራምፕ የሚለው ስም ትርጉሙ መለከት ነው።] ይህ ለዘመኑ ተብሎ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ የሚሆን ምልክት ነው፤ የእግዚአብሔር መለከት ሊነፋ ጊዜ እንደቀረበ ያመለክታል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ብዙ ሰዎችን የሚያስደነግጡ ሰዎች ከሚጠብቁት ውጭ የሆኑ እርምጃዎችን ወስዷል። ይህም ፈጽሞ ያልጠበቅነው ነገር ሊከሰት እንደሚችል የሚያሳይ ማስጠንቀቂያ ነው። )
ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ ሰዎች መሲህ ይመጣል ብለው ከሚጠብቁበት ፍጹም በተለያ መንገድ መጣ። ዮሴፍ እና ማርያም ታዋቂ ሰዎች አልነበሩም። ናዝሬት መጥፎ ከተማ ነበረች። ሰዎች ኢየሱስ ከትዳር ውጭ የተወለደ ሰው ነው ይሉ ነበር ምክንያቱም ማርያም ከጸነሰች በኋላ ኤልሳቤጥጋ ሄዳ የሶስት ወር ነፍሰጡር ሆና ቆይታ ስትመለስ ነው ያገባቸው።
ስዚህ የኢየሱስ ዳግም ምጻትም እኛ ከምናስበው እጅግ በተለየ መንገድ ነው የሚሆነው።
በእግሮቻችን ጣቶች ቆመን መጽሐፍ ቅዱስን መፈተሽ አለብን።
በሰማያት ስለሚደረገው ስለበጉ የመጨረሻ ሰርግ አንዳንድ ፍንጮችን ማግኘት እንድንችል በቃና የተደረገውን የመጀመሪያውን ጋብቻ እንመልከት
ዮሐንስ 2፡2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀማሙርት አልተጋበዙም ነበር፤ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ብቻ ናቸው የተጋበዙት።
የዊልያም ብራንሐም ደቀመዛሙርት አይጋበዙም፤ የእግዚአብሔር ቃል የሆነው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ብቻ ናቸው የሚጋበዙት።
ማንም ሰው ሳይጋበዝ ወደ ሰርጉ መታደም አይችልም።
ራዕይ 4፡1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።
“ከዚህም በኋላ።” የቤተክርስቲያን ዘመናት ከተጠናቀቁ በኋላ ዮሐንስ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተጠራ። ወደ ላይ የምንሄደው እግዚአብሔር ከጠራን ብቻ ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሙሉ ቃሉ ነው። ሙሉ በሆነው ቃል የሚያምኑ ብቻ ናቸው ወደ በጉ ሰርግ እራት የሚጋበዙት። እነዚህም እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ የሚመሰርቱ እውነተኛ ደቀመዛሙርት ናቸው።
ጠንቃቃ መሆን አለብን። እግዚአብሔር በቃሉ በኩል ይጠራናል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን መረዳት ካልቻልን ከቤተክርስቲያኖቻችን ወጎች እና ከሰዎች አመለካከት ጋር ታስረን እንቀራለን፤ በዚህም የተነሳ የእግዚአብሔርን ቃል ቸል እንላለን። ከዚያ በኋለ ወደ ሰርጉ እርታ ግብዣ አይላክልንም።
በሉቃስ ወንጌል አንድ ምሳሌ ውስጥ አንድ ሰው እራት አዘጋጅቶ ጥሩ ጥሩ እንግዶችን (የዳኑ ክርስቲያኖችን) ሁሉ ጋበዘ። አንዳቸውም ለግብዣው ምላሽ አልሰጡም (ከቤተክርስቲያኖቻቸው ወግና አመለካከት ጋር ቀሩ) ስለዚህ እርሱም ቸል አላቸውና ሊጋበዙ የማይገባቸውን ሰዎች መረጠ።
ሰዎች ትራንምፕ መናኛ ሰው ነው ይላሉ። እግዚአብሔር ጻድቃንን ትቶ ወደ ተራ ሰዎች ዞር እያለ እንደሆን ይህ ምልክት ይሆን?
ሉቃስ 14፡24 እላችኋለሁና፥ ከታደሙት ከእነዚያ ሰዎች አንድ ስንኳ እራቴን አይቀምስም አለው።
ስለዚህ የበጉ የሰርግ እራት እኛ ከምናስበው በጣም የተለየ ነው የሚሆነው። ሰርጉ ኢየሱስን ከሚወድዱት በላይ ቤተክርስቲያናቸውን ለሚወድድ የቤተክርስቲያን አባላት አይደለም።
ሰርጉ የዘመን መጨረሻ መገለጥን ለሚወድዱ ግለሰቦች ነው።
ዮሐንስ 2፡3 የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
ወይን መገለጥ የሚያመጣውን መነቃቃት ይወክላል። ፍጥረታዊ ወይን ሰውን ደስ ያሰኛል። ከፍጥረታዊ ወይን የሚገኝ ደስታ ግን ወዲያው ይጠፋል። መንፈሳዊ ወይን ማለት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ምን ማለት እንደሆነ መገለጡን ያገኘህ ጊዜ የምትቀበለው ደስታ ነው። ጠለቅ ያለ መረዳት ስናገኝ መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ እንድናጠና እንዲሁም ቃሉን እየተወያየን እና እያሰብን የበለጠ ጊዜ እንድናሳልፍበት ያነሳሳናል፤ ቢዚህም ይበልጥ ጠለቅ ያለ መረዳት እናገኛለን። የቃሉ ሚስጥር እየተገለጠ ሲሄድ ይህ ደስታ በልባችን ውስጥ እየበዛና እየጠለቀ ይሄዳል።
ማርያም ሴት እንደመሆኗ እናት ቤተክርስቲያንን ወይም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተመሰረተችውን የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ትወክላለች። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ሁሉ የሚወለዱባት ቤተክርስቲያን መሆን ነበረባት። ኋላ የመጡት ቤተክርስቲያኖች በሙሉ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ያለችዋን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን መምሰል ነበረባቸው።
ማርያም እንደ ሴትነቷ ለፍጥረታዊ ወይን ጥያቄ ታቀርባለች፤ ምክንያቱም ወይን አልቆ ነበር።
ኢየሱስ የሚሰጣት መልስ ደግሞ ከጥያቄዋ ጋር በፍጹም የማይገናኝ ይመስላል።
ዮሐንስ 2፡4 ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ የተገለጠው ሁሉን ማየት እንደሚችል ከፍ ብሎ እንደሚበርር ንስር ሲሆን ይህም እግዚአብሔርን የሚገልጥ ተምሳሌት ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ በአንድ ውስን ቦት የሚደረግ ክስተትን አይቶ በዚያ ውስጥ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ እውነትን ያገልጣል።
አንቺ ሴት ብሎ አናገራት። እናቴ ብሎ አንድ ጊዜ እንኳ አይጠራትም። ለምንድነው እናቴ የማይላት? የለበሰው ሥጋ ሙሉ በሙሉ የተፈጠረው በእግዚአብሔር ነበር። ኢየሱስ ከማርያም የወረሰው አንዳችም ነገር የለም። ማርያም የኢየሱስ ሥጋ ጽንስ በነበረ ጊዜ ያደገበት መቆያ ብቻ ነበረች። እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱስ።
ደግሞም እርሷ በእርሱ ውስጥ ሆኖ ተዓምራትን ለሚሰራው መንፈስም እናት እንዳልሆነች መግለጡ ነበር።
ሉቃስ 1፡35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
በማርያም ማሕጸን ውስጥ ያደረው ጽንስ ቅዱስ ነበረ። ስለዚህ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነውና በእግዚአብሔር ነበር የተፈጠረው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በዚያ ቅዱስ ጽንስ ውስጥ ተሰውሮ ነበረ።
ኢየሱስ ሰፊውን እውነት ነው የሚመለከተው። ማርያም የተባለችዋ ሴት የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበረችዋን ቤተክርስቲያን ትወክላለች። እርሷም ወይን ማለትም መገለጥ የሚያመጣውን መነቃቃት ትለምናለች። ይህ ግን ለማግኘት የማይቻል ነው ምክንያቱም መገለጥ የሚገኘው በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። በኢየሱስ ደም ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በቀራንዮ ሲሞት ብቻ ነው የሚወጣው። ከዚያ በኋላ ተመልሶ ቤተክርስቲያን ላይ የሚወርደው በጴንጤቆስጤ ዕለት ነው። የመንፈስ ቅዱስ መውረድም ደቀመዛሙርትን በኃይል ስላነቃቃቸው ሌሎች ሕዝቦች ሊሰሙዋቸው እስከሚችሉ ድረስ በሌሎች ልሳናት ተናገሩ። ሲናገሩም ሳለ እንደ ሰከረ ሰው ተንገዳገዱ።
ሐዋርያው ጴጥሮስም ለተሰበሰበው ሕዝብ ደቀመዛሙርት ፍጥረታዊ ወይን እንዳልጠጡ ያስረዳቸው ነበር፤ ደቀመዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተጠምቀው በወንጌል ውስጥ ስለላው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ተረድተው ተነቃቅተው ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡15 ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤
ስለዚህ ኢየሱስ ማርያምን በተናገራት ጊዜ በሰዓቱ ከነበረው ሁኔታ አሻግሮ እየተመለከተ ነበር የተናገረው፤ ማለትም ቤተክርስቲያን የሚያነቃቃትን መንፈሳዊ የመገለጥ ወይን ልታገኝ የምትችለው እርሱ በመስቀል ላይ ከሞተ እና መንፈስ ቅዱስም በጴንጤቆስጤ ዕለት ከወረደ በኋላ ብቻ ነው። በዚያ ሰዓት ኢየሱስ ስለምን እየተናገረ እንደነበር ማርያም ምንም አልገባትም።
አንድ ጥቅስ ለመረዳት ስላቃተን ብቻ ጥቅሱ ምንም የማይጠቅም ነው ማለት የለብንም።
ማርያም በኢየሱስ መልስ ሙሉ በሙሉ ግራ ብትጋባም ተዓምራት ማድረግ የሚችለው እርሱ ብቻ መሆኑ ግን ገብቷታል። እርሷም ለሰራተኞቹ እርሱ የሚላቸውን እንዲታዘዙ በመናገር እምነቷን ገለጠች። ሁል ጊዜ ቃሉ እንድናደርግ የሚነግረንን በመታዘዝ ማድረግ አለብን። በፍጹም የማንጠብቀውን ነገር እንድናደርግ ቢያዝዘንም ሁልጊዜ ቃሉ የሚለንን ማድረግ አለብን። ኢየሱስ ፈጽመን ያላሰብነውን ነገር አድርጉ ብሎ ያዝዘናል።
እግዚአብሔር እኛ እንደምናስበው ነው የሚያስበው ብላችሁ እንዳታስቡ። እግዚአብሔር ከእናንተ አስተሳሰብ ጋር እንዲስማማ አትጠብቁ።
ዮሐንስ 2፡5 እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
ሊፈጸም ላለው ተዓምራት ለመዘጋጀት ሰራተኞቹ ኢየሱስ የሚነግራቸውን ቃል መታዘዝ ነበረባቸው። ወደ አዲስ የማይሞት አካል መለወጥ ከፈለግን ቃሉ የሚነግረንን መታዘዝ አለብን። ሰውን እንደመሪ ብትከተሉ ትጠፋላችሁ። የቤተክርስቲያንን ወግና ልማድ ብትከተሉ ትከስራላችሁ። ቃሉ የሚነግራችሁን ብቻ አድርጉ። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ልክ እንደ ማርያም የእግዚአብሔርን አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ኢየሱስ በመጽሐፍ መልክ የሚነግራችሁን ብቻ ታዘዙ ብላ ትነግራቸዋለች።
ዮሐንስ 2፡6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
ስድስት የሰው ቁጥር ነው። ሰው በስድስተኛው ቀን ተፈጠረ። ሰባት ደግሞ የሙሉነት ቁጥር ነው፤ ለምሳሌ በሳምንት ውስጥ ሰባት ቀናት አሉ። ስድስት ግን ለሙላት አንድ ይጎድለዋል። ሰው ከሙላት የሚጎድለው በሕይወቱ ውስጥ ሐጥያት ስላለ ነው።
ስድስት የውሃ ጋኖች ትኩረት ሰው ላይ እንደሆነ ይገልጣሉ።
ጋኖቹ የተሰሩት ከድንጋይ ነበር።
ድንጋዩም የሰው ልብ የእግዚአብሔርን ቃል ላለመቀበል እንዴት እንደ ደነደነ ያሳያል።
በተፈጥሮአችን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል መታዘዝ አንፈልግም።
የራሳችንን መመሪያ ማውጣትና የራሳችንን አስተምሕሮ ማበጀት እንመርጣለን።
ዘካርያስ 7፡12 የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።
ልብን ማጠንከር ማለት ለመለወጥ እምቢ ማለት ነው። ዘመናዊ ጂዮሎጂስቶች የድንጋዮችን ጥንካሬ ከማጥናታቸው በፊት አዳማንት ከድንጋዮች ሁሉ ጠንካራ ድንጋይ እንደሆነ ይታሰብ ነበር፤ ልክ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮች ሁሉ በጠንካራነቱ እንደሚታወቀው አልማዝ።
ዘካርያስ እንደሚለው በራሳችን ፈቃድ ለመመላለስ ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን ስንገፋው ልባችን ለማመን ከሚቻለው በላይ ደንዳና እንደሚሆን ይናገራል።
እግዚአብሔር አሥርቱን ትዕዛዛት በድንጋይ ጽላቶች ላይ የጻፈው የሰው ልብ ምን ያህል ደንዳና መሆኑን ለማመልከት ነው።
2ኛ ቆሮንቶስ 3፡3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የተመሰረተው በሁለት ቁልፍ ነጥቦች ላይ ነው።
መጀመሪያ ኢየሱስ ለመዳናችን አስፈላጊ የሆነውን ዋጋ መክፈል ነበረበት። ይህንንም በቀራንዮ ፈጸመው።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እኛ የግል ፈቃዳችንን ለእርሱ በመተው እርሱ ልባችንን እንዲያለሰልሰው መፍቀድ አለብን።
እኛ እግዚአብሔርን ለማገልገል ዝግጁ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሶስት ነገሮችን ማድረግ አለበት።
አንደኛ እኛ የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበለው እኛን ያድነናል። የዛን ጊዜ አዳኛችን ነው ነገር ግን ጌታችን አልሆነም። ሰዎች ኢየሱስ እንዲያድናቸው ይፈልጋሉ ነገር ግን እንዴት መልበስ እንዳለባቸው፤ ምን ማመን እንዳለባቸውና እንዴት መኖር እንዳለባቸው እንዲነግራቸው አይፈልጉም።
ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ መቀደስ ነው፤ ይህም የግል ፈቃዳችንን አሳልፈን በመስጠት ኢየሱስ ሕይወታችንን እንዲያነጻውና በቅድስና እንድንኖር እንዲያደርገን ስንፈቅድ ነው የሚፈጸመው።
ሶስተኛው ደረጃ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሲሆን ይህም እርሱ ሙሉ በሙሉ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠርና የእግዚአብሔርን ቃል እንዲገልጥልን ስንፈቅድ ነው የሚፈጸመው። ከዚያ የግል ፈቃዳችንን ለእርሱ አሳልፈን እንሰጣለን። እዚህ ደረጃ ላይ ስንደርስ ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ዝግጁ የምንሆነው።
እግዚአብሔር አንድን ሰው ሲጠቀምበት እና ያንን ሰው በመንፈሳዊ ስጦታዎች እና በቁሳዊ ስኬት ሲባርከው ያ ሰው ብዙውን ጊዜ ይህ ሁሉ እኔ ልዩ ሰው በመሆኔ እና ከሌሎች የተሻልኩ ሰው በመሆኔ ነው ብሎ ማሰቡ አይቀርም።
54-0306 እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው በሁኔታዎች ያልተመሰረተ ኪዳን
“እንግዲህ በባንክ ያስቀመጣችሁትን በሙሉ ተጠቅማችሁበታል።” ያንን አስቀምጠውና ቀሪውን አይቼ እስከሚቀጥለው ጉባኤ ድረስ ለመኖር ይበቃኝ እንደሆን እወስናለው። ከዚያ የተረፈውን በሌሎች ሃገሮች ለሚደረጉ የወንጌል አገልግሎቶች ድጋፍ እንዲሆን እሰጣለው። ይህ እውነት ነው። ለራሴ ምንም አላስቀርም። ብዙዎቹ ልብሶቼ እና የምጠቀምባቸው ነገሮች ሰዎች ሰጥተውኝ ነው። ሰዎች ይሰጡኛል። እንደ ተራ ሰዎች ዝቅ ብለን እንኖራለን፤ ግን ሚሊየነር መሆን ብፈልግ እንደምችል እግዚአብሔር ራሱ ያውቃል።
ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ወስጄ ለንግድ እጠቀመው ዘንድ ከእኔ ይራቅ።
በሕይወቴ እንዲህ ዓይነት ነገር ማድረግ አልፈልግም። በፍጹም አልፈልግም።
ለአገልጋይ ፈተና የሚሆንበት ነገር አንዱ ገንዘብ ነው፤ ሌላው ደግሞ ስነምግባር የጎደለው ኑሮ፤ ሐጥያተኛ በነበርኩ ጊዜ ከእነዚህ ሁሉ ተቆጥቤ ለመኖር ጥረት አድርጌያለው።
ከእነዚህ ሌላ ፈተና የሚሆንበት ደግሞ ታዋቂነት ነው።
ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ሰውን ሲባርከው፤ ትንሽዬ አገልግሎት ሲሰጠው እራሱን ከሌሎች ሰዎች የተሻለ አድርጎ ማሰብ ይጀምራል። እንዲህ ማሰብ ሲጀምር ውድቀቱ ጀምሯል ማለት ነው።
ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው አራተኛው ደረጃ ከሁሉም በላይ ከባዱ ደረጃ ነው፤ አራተኛው ደረጃ እግዚአብሔር እኛን በራሱ ፍጹም ፈቃድ በሰፊ እቅዱ ውስጥ እንዲያስገባን የምንፈቅድበት ነው።
ይህ ሁልጊዜም እኛ ካሰብነው ወይም ካቀድነው የተለየ ነው የሚሆነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንገድ ከእኛ መንገድ የተለየ መሆኑን እንረሳለን። ለቤተክርስቲያን ልማዶች መገዛት፣ እራስን ከፍ ከፍ ማድረግ፣ የሃብት አጓጊነት፣ ብልህ መስሎ መታየትን መፈለግ፣ መገፋትን በብርቱ እንድንፈራ የሚያደርግ ቡድንን የመቀላቀል ፍላጎት፣ እና በሌሎች ላይ ገዥ የመሆን ምኞት ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖችን ከጠባቡ መንፈሳዊ መንገድ ያስወጧቸዋል።
ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
ስለዚህ በጣም ጥቂት ክርስቲያኖች ናቸው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛው ምንም ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል አድርገው በመቀበል እምነታቸውን የሚመሰርቱበት።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
ይህንን ቃል ስናነብብ ኢየሱስ ስለ ታላላቅ ቤተክርስቲያኖችና ብዙ ሕዝብ ስላለባቸው ጉባኤዎች እየተናገረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
ዮሐንስ 2፡6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
የማንጻት ስርዓት የቅድስና ተምሳሌት ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱስ።
ስለዚህ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ያመለክታል፤ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትም በቅድስና ሕይወት እንድንመላለስ ከማስቻልም በተጨማሪ በአስተሳሰባችን ውስጥ ያለውን ጥርጣሬ አስወግዶ የመጽሐፍ ቅዱስን መገለጥ መረዳት ያስችለናል።
አንድ እንስራ ማለት የ34 ጋሎን በርሜል አንድ አራተኛ ማለትም 9 ጋሎን ወይም ሰላሳ ስድስት ሊትር ማለት ነው።
እንስራዎቹ የተለያየ መጠን ውሃ የሚይዙ ነበሩ። እግዚአብሔር ለሰዎች እንደሚሰጣቸው የአገልግሎት ሃላፊነት ዓይነት መንፈሱን በተለያየ መጠን ያድላቸዋል።
ጸጋው በእምነት አድኖን ከሆነ ወደ ሲኦል አንገባም ማለት ነው።
የመጀመሪያው ደረጃ ከሲኦል መዳን ነው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ተቀበልነው ማለት የእኛ ጌታ ሆኗል ማለት አይደለም። እንዲያድነን እንፈልጋለን ነገር ግን እንዴት መልበስ እንዳለብን እንዴት መኖር እንዳለብን እንዲነግረን አንፈቅድም። መዳን እንፈልጋለን ግን የፈለግነውን እያደረግን መኖርና ሐጥያት ስንሰራ የማይወቅሰንን ሕሊና ይዘን መቀጠል እንፈልጋለን።
ሕይወት ግን ቀላል አይደለም።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡3 … በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
አዳኛችን ጌታችንም ሊሆነን ያስፈልገናል። ኢየሱስ ሕይወታችን ውስጥ በሁሉም አቅጣጫ ጌታ መሆን ይፈልጋል። መዳን ከሲኦል ከማምለጥም ሌላ ደረጃ እንዳለው እንረሳለን፤ ሌላኛው ደረጃ ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ ወደ ሰማይ በመነጠቅ ከታላቁ መከራ ማዳንንም ይጨምራል።
ከሰነፎቹ ቆነጃጅት መዳን አለብን፤ እነዚህ ንጹሕ ሕይወት የሚኖሩ ሴቶች (የዳኑ ቤተክርስቲያኖችን የሚወክሉ) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን የሚወክለው ዘይት የሌላቸው ናቸው። ዘይት ብርሃን ይሰጣል። ብርሃን ደግሞ ነገሮችን ማየት ያስችለናል። ያለ ዘይት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ በቂ ብርሃን የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለምን እንደሚናገር መረዳት አይችሉም። “ለምድነው አራት ወንጌሎች ያሉት?” ተብለን ስንጠየቅ ወይ “በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ሴቶቹ ከትንሳኤ በኋላ የኢየሱስን እግር ሲይዙ በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ግን ኢየሱስ ማርያምን አትንኪኝ የሚላት ለምንድነው” ተብለን ስንጠየቅ፤ አለማወቃችንን ድንቁርናችንን ለመሸፋፈን እና ከጥያቄዎች ለማምለጥ እነዚህን ዝርዝሮች ማወቅ ብዙም አስፈላጊ አይደለም እንላለን። እነዚህ የተሰወሩ ሚስጥራት ትርጉማቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ ከመንፈስ ቅዱስ ዘይት በቂ ብርሃን ማግኘት አለብን።
መዳን አንድ እርምጃ ነው፤ ከዚያ ቀጥሎ ግን ሕይወታችንን ሙሉ ለሙሉ ኢየሱስ እንዲቆጣጠር አሳልፈን የምንሰጥበት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ያስፈልገናል።
ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ከሲኦል ውስጥ የራሳችንን መዳን በመፈጸም ራሳችንን ማዳን አንችልም። ከሲኦል መዳን በእምነት የምንቀበለው በጸጋ የሚሰጠን ስጦታ ነው፤ ምክንያቱም በምንም መንገድ እኛ በምንሰራው መልካም ሥራ ላይ የተመሰረተ አይደለም።
ነገር ግን ከዳንን በኋላ የምናምነው እና የምናደርገው ነገር ሁሉ በሰማያት ወደተዘጋጀው የበጉ ሰርግ እራት ላይ እንጋበዝ ወይ አንጋበዝ እንደሆን ይወስናል። ልክ በቃና እንደሆነው ሁሉ ካልተጋበዝን በቀር ወደ ሰርጉ የእራት ግብዣ መግባት አንችልም። ስለዚህ ምን ማመን እና ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ ያስፈልገናል።
የመጀመሪያው ሰርግ ላይ ኢየሱስ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጧል። ስድስቱ የውሃ ጋኖች (ሐጥያተኛ የሆንን ሰዎችን ይወክላሉ) ሁለት ወይም ሶስት እንስራ ውሃ መያዝ አለባቸው። ከአስራ ስምንት እስከ ሃያ ሰባት ጋሎን ማለት ብዙ ውሃ ነው። ኢየሱስን እና መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቀው የሚከተሉ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው ወደ ሰርጉ የሚታደሙት።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎች አስፈላጊ አይደሉም ወይም አይጠቅሙም የምትሉ ከሆነ ወይም ከሲኦል መዳኔ ላይ ምንም ተጽእኖ የላቸውም የምትሉ ከሆነ ወደ ሰርጉ አትጠሩም። መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር ቃሉን እንድንፈልግ ተጠርተናል።
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ አስፈላጊ ነው።
ዮሐንስ 2፡7 ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
ስለዚህ ኢየሱስ ጋኖቹን እስከ አፋቸው ድረስ እንዲሞሉ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው። ጋኖቹ የቻሉትን ያህል ሞሉባቸው። ጋኖቹም ብዙ ውሃ ያዙ።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
ውሃ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማመን እና ቃሉን መታዘዝ ያነጻናል።
የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ብቻ ነው እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኘው መንገድ እንድንመላለስ የሚያስችለን። የሰዎችን አመለካከት እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን ግላዊ አስተሳሰብ ማዳመጥ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን መስማት ነው የሚያዋጣን።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቃችን ማስረጃው መንፈስ ቅዱስ የቃሉን ሚስጥር ለአማኙ መግለጥ ሲችል ነው።
መንፈስ ቅዱስ ተዓምራትን ያደርጋል ነገር ግን ያ ሁለተኛ ነገር ነው። ዋነኛ ሥራው የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር በመግለጥ ቤተክርስቲያንን ወደ እውነት መምራት ነው።
ስለዚህ እንስራችንን በቃሉ ውሃ መሙላት አለብን።
ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት ከእኛ የሚጠበቅብን ልባችንን በእግዚአብሔር ቃል መሙላት ነው። ቃሉን በአእምሮዋችን እና በትዝታችን ሁሉ መሙላት አለብን።
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነው፤ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባንም እንኳ አስፈላጊ ነው። ልክ ሰዎቹ ጋኖቹን በውሃ እንደሞሉዋቸው መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ አንብቡት እና በአእምሮዋችሁ ውስጥ ሸሽጋችሁ አስቀምጡት።
ከዚያ በኋላ እንግዳ ነገር ሆነ። ምንም ዓይነት በዓይን የሚታይ ምልክት ሳይፈጠር ውሃው ወደ ወይን ጠጅ ተለወጠ።
በዚህ የዘመን መጨረሻ ጊዜ እግዚአብሔር በድንገት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚያስችላችሁን የቃሉን መገለጥ ይሰጣችኋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ተዓምር መስራት የሚችለው በእንስራችሁ ውስጥ በሞላችሁት ውሃ ላይ ብቻ ነው። እንስራችሁ እስከ አፉ ድረስ ጢም ብሎ ካልሞላ መጽሐፍ ቅዱስን ከቁም ነገር አልቆጠራችሁትም ማለት ነው፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ምንም ማድረግ አይፈልግም። ነገር ግን የሚችሉትን ያህል ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን እና በውስጡ የተጻፉትን ጠለቅ ያሉ የዘመን መጨረሻ መገለጦች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተከታትለው በማንበብና በመማር አእምሮቸውም ጢም አድርገው የሞሉ ሰዎች አካላቸው በድንገት ከሟች ወደማይሞት አካል ሲለወጥ ያያሉ። ከዚያ በኋላ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ።
ዮሐንስ 2፡8 አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
ስለዚህ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ ተለወጠ፤ የሰርግ ቤቱ ሃላፊም ተገረመ።
ዮሐንስ 2፡9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦
ሰውየው የሰርግ ቤቱ አለቃ የሆነው ሰው ይህ የዘመን መጨረሻ መገለጥ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም። አገልጋዮቹ ግን ማንም የማያውቃቸው እነርሱ ግን አውቀዋል።
ማርቆስ 10፡42 ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።
የክርስቲያን መሪዎች ትልቁ ድክመታቸው ይህ ነው፡- አለቃ መሆን እና ሰዎችን እንደፈለጉ ማዘዝ። ሃላፊ የሆነው ሰውዬ በሃላፊነት ቦታ ቢቀመጥም እንኳ ሰርግ ቤት ውስጥ ምን እንደተደረገ አላወቀም።
43 በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥
ልናደርግ የምንችለው ትልቅ ነገር ቢኖር ዝቅ ብለን ማገልገል ነው። አገልጋዮች ታላላቅ ሰዎች እንዳልሆኑ እወቁ።
44 ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤
ከሁሉ ታላቅ የሆነው ክርስቲያን ራሱን ዝቅ የሚያደርገው አገልጋይ ነው።
ሰዎች ከሚጋልቧቸው እንስሳት መካከል ከአህያ በታች ዝቅ ያለ እንስሳ የትኛው ነው?
(እናንተ በትልልቅ ቤቶች ውስጥ የምትኖሩ እና በውድ መኪኖች የምትሄዱ የሜሴጅ ፓስተሮች አድምጡ።)
ሐዋርያት የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን መሰረቱ እና ከዚያ በኋላ ዞር አሉ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ አንድም ትልቅ ሰው ቤተክርስቲያንን እንዲመራ አልፈለገም። ኢየሱስ የፈለገው የቃሉን ውሃ ለሕዝቡ የሚያቀርቡ ሰራተኞችን ብቻ ነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድር ፓስተር አልነበራትም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምትተዳደረው በሽማግሌዎች ነበር። እነርሱም የተሾሙት እንዲያገለግሉ እንጂ እንዲገዙ አልነበረም። ታላላቅ የተባሉ ሰዎች ወይን ከወዴት እንደሚመጣ አማኞችን የሚያነቃቃ መገለጥ ከየት እንደሚገኝ አያውቁም፤ ምክንያቱም የራሳቸውን ስልጣን በማደራጀትና ጉባኤውን ለራሳቸው በማስገዛት ተጠምደው ነው የሚኖሩት።
ኢየሱስ የጠራን አገልጋዮች እንድንሆን ነው። በሰዎች ላይ ጌታ እንድንሆንባቸው አይፈልግም።
እውነተኞቹ አገልጋዮች አንዳችም ዝና የማይፈልጉ ሽማግሌዎች ናቸው፤ እነርሱም ኢየሱስን እና ቃሉን ለማገልገል እና ለመታዘዝ ብቻ ነው ፍላጎታቸው።
ጳውሎስ የኤፌሶን ከተማ ሽማግሌዎችን ወደ ሚሊጢን ከተማ ጠራቸው።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
ጨካኝ ተኩላዎች ማለት ሰዎችን የራሳቸው ተከታዮች የሚያደርጉ የዚህ ዘመን አገልጋዮች፣ ፓስተሮች እና ጳጳሳት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ታላቅ ነበሩ።
እነርሱ ቤተክርስቲያንን በተጻፈው ቃል መሰረት ላይ ተከሏት። የዚህ ዘመን ራሳቸውን የሾሙ ሐዋርያት ግን ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ጸንተው አይቆሙም።
የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትተው ያልተጻፉ ሚስጥራትን ይቆፍራሉ። ይህም ሰዎች እነርሱ ብልሆች እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፤ ነገር ግን ብልሃት ማንንም አላዳነም።
የሽማግሌዎች ሕብረት ቤተክርስቲያን የምትመራበት ትክክለኛ አገልግሎት ነበረ።
አንድም ሰው በሕዝቡ ላይ ስልጣን መያዝ የበለትም።
ዛሬ በዘመን ፍጻሜ እውነት ከወዴት እንደሚመጣ የሚያውቅ አንድም የቤተክርስቲያን ገዥ የለም።
ዛሬ ታላላቅ የተባሉት የቤተክርስቲያን ገዥዎች በሙሉ ከሰው ንግግር በተወሰዱ ጥቅሶች እና በጥቅሶች ትርጓሜዎች ላይ ነው የሚደገፉት። ቤተክርስቲያንን የሚገዙ ታላላቆቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች በእውነት መጽሐፍ ቅዱስን ቢታዘዙ ኖሮ ታላቅም አይሆኑም በቤተክርስቲያን ላይ ራሳቸውንም ገዥ አያደርጉም ነበር።
ዮሐንስ 2፡10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
እንደ ማርቲን ሉተር ወይም ጆን ዌስሊ የመሳሰሉ የተሃድሶ መሪዎች ትልቅ ተጽእኖ አምጥተዋል ነገር ግን ከዓመታት በኋላ ተከታዮቻቸው ከእነርሱ በወሰዱዋቸው የንግግር ጥቅሶች አማካኝነት ለቤተክርስቲያኖቻቸው ስም ሰይመው እንቅስቃሴው እንዲዳከም አደረጉ። የተከታይ ቁጥር እንዳይቀንስ ማድረግ ችለዋል፤ ነገር ግን የእንቅስቃሴው ጥራት እና በዓለም ላይ ያለው ተጽእኖ ተዳክሟል።
ነገር ግን ከዊልያም ብራንሐም ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን ይዘው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚሄዱ እና የእርሱን ንግግሮች በእግዚአብሔር ቃል ፈትሸው መርምረው ለሚያረጋግጡ ሰዎች የዘመን መጨረሻ ሚስጥራት የተሃድሶ መሪዎችም ሆኑ የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ከሚያስተምሩት ትምሕት እጅግ የተሻለ መገለጥ ስለሚሆንላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ተምሳሌቶችን እና ጥቅሶችን በተሻለ መንገድ መረዳት ይችላሉ።
እያንዳንዱ የተሃድሶ መሪ በራሱ ዘመን ከነበሩ የቤተክርስቲያን አሰራሮች ራሱን ያላቀቀ ሰው ነበረ፤ ይህም ነጻነቱ ጥሩ መገለጥ እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ መረዳትን የሚያነቃቃ በመሆኑ ጥሩ የወይን ጠጅ ነበረ። ነገር ግን የተሃድሶ መሪው በሞተ ጊዜ ተከታዮቹ እርሱ በተናገራቸው ንግግሮች ዙርያ አዲስ ስም ያለው ቤተክርስቲያን ይመሰርቱና ከዚያ ወዲያ የወይን ጠጁ መናኛ ይሆናል። ከዚያ ወዲያ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው አንብበው መረዳት አይችሉም፤ ራሳቸውን በራሳቸው ለሾሙ የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ተገዥ ይሆናሉ፤ መሪዎቻቸውም የእግዚአብሔርን ቃል ሳይሆን የሰውን ጥቅሶች በመተርጎም ይበረታሉ። የእነዚህ ትምክሕተኛ መሪዎች ስሕተት እና መሃይምንት የወይን ጠጁ እንዲኮመጥጥ አደረገው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ተፈትሾ የሚገኘው የተጻፉት ሚስጥራት መገለጥ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታውቅ የነበረው ነገር ግን ኋላ በጨለማው ዘመን የጠፋውን ተሰውሮ የቆየ እውነት የሚገልጥ ከሁሉ ይልቅ የሚጣፍጥ የወይን ጠጅ ነው። ጥንታዊ እውነቶችን ፈልገን እናገኝ ዘንድ ተባርከናል፤ ምክንያቱም እነዚያ ጠለቅ ያሉ መገለጦች አሁን በቀላሉ መገኘት እንዲችሉ ተደርገዋል።
ነገር ግን አንድ የማስጠንቀቂያ ቃል ጣል እናድርግ። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ያመነችውን ብቻ ነው ማመን ያለብን። እነርሱ ያላመኑትን ነገር የምታምኑ ከሆነ ተሳሳታችኋል !
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ተመልሳ ትመጣለች እንጂ አትሻሻልም።
ኤልያስ አዳዲስ ሃሳቦችን አያመጣልንም፤ ወደ ጥንታዊ እውነቶች ይመልሰናል እንጂ።
ተሃድሶ ማለት ወደ ቀድሞ ወይም ወደ መጀመሪያ ሁኔታ መመለው ነው።
ልክ የመጀመሪያዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እንደምታምነው ማመን እንደምታደርገው ማድረግ አለብን።
አሁን እናንተ የምታምኑትን የትንቷ ቤተክርስቲያን ታምን ነበር? መልሱ “አይ አታምንም” ከሆነ እንግዲያውስ የሳታችሁት እናንተ ናችሁ።
ዮሐንስ 2፡11 ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ኢየሱስ በሰርግ ቤት ውስጥ የሰራው የመጀመሪያ ተዓምር ውሃን ወደ ወይን ጠጅ ለወጠ። ከሰባተኛው መልአክ ንግግር ጥቅሶች ውስጥ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ብናገኝ እኛም በመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚደረገው ተዓምራት ተካፋይ እንሆናለን፤ በዚህም ውስጥ መጀመሪያ እምነታችን ሙሉ በሙሉ ንጹህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ይሆናል፤ ከዚያም አካላችን በአየር ውስጥ ለመነሳትና ጌታን ለመቀበል ወደ ላይ ከፍ ማለት እንዲችል ይለወጣል።
ደቀመዛሙርቱ በኢየሱስ አመኑበት። እኛም ልናምንበት ይገባናል። እርሱ ቃሉ ነው።
የተገለጠውን ቃል ማመን እና መከተል አለብን እንጂ የተጻፈውን ቃል መገለጥ ያመጣልንን ነብይ አይደለም ማመንና መከተል ያለብን።
ዮሐንስ 2፡12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።
ከሰው አመለካከት አንጻር እናትየው እና ወንዶሞቹ ለኢየሱስ ከሁሉም ነገር በላይ አስፈላጊ ናቸው። ደቀመዛሙርት መጨረሻ ላይ ነው የተጠቀሱት፤ ስለዚህም በአስፈላጊነታቸው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እዚህጋ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ መረዳት እናገኛለን። ከሁሉ ይልቅ በዝቅተኛ አስፈላጊነት ደረጃ መጨረሻ ላይ የተጠቀሱት ደቀመዛሙርት ቤተክርስቲያን የመትከልን ከባድ ስራ የሚሰሩት እነርሱ ናቸው። ማርያም እና የኢየሱስ ወንድሞች ቀድመው በመጠቀሳቸው ይበልጥ አስፈላጊ ቢመስሉም በቤተክርስቲያን ተከላ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና እምብዛም ነው።
ከዚህ የምንማረው ምንድነው?
በሰው ዓይን አስፈላጊ ሆኖ መገኘት በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ ምንም እርባና የለውም።
እውነተኛው ስራ የሚከናወነው የማይጠቅሙ በሚባሉ ሰዎች ነው። ቤተሰባዊ ዝምድን አንዳችም ቦታ የለውም።
ኢየሱስ ለዋነኛው ስራ ከስጋ ቤተሰብ ውጭ የሆኑ ሰዎችን መረጠ እንጂ ቤተሰቦቹን አልመረጠም።
በቤተሰብ እና በስጋ ዝምድና አስታክኮ ማድላት በእንግሊዝኛ ኔፖቲዝም ይባላል።
ለዘመድ ማድላት በሰው ታሪክ ውስጥ ከባድ ችግሮችን የፈጠረ በሽታ ነው። ኢየሱስ ግን አንድ ጊዜም እንኳ በዘመድ አድሎ አድርጎ አያውቅም።
አውሮፓ ውስጥ የናፖሌዎን መንግስት ሊወድቅ የቻለበት ከፊሉ ምክንያት የተቆጣጠራቸው ግዛቶች ውስጥ ብቃት የሌላቸውን ቤተሰቦቹን በስልጣን ቦታ ላይ በማስቀመጡ ነው። እርሱ አስተዋይ መሪ ነበረ፤ እነርሱ ግን አልነበሩም። ከዚያ በኋላ የናፖሌዎን መንግስት ተንኮታኩቶ ወደቀ።
ማቴዎስ 13፡55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን?
ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
እነዚህ ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ የተወለዱ የዮሴፍ እና የማርያም ልጆች ናቸው።
ከኢየሱስ ወንድሞች አንዱ ስሙ ያዕቆብ ነበረ።
ኢየሱስ ከመረጣቸው ደቀመዛሙርት መካከል ሁለት ያዕቆብ የሚባሉ ነበሩ። እነዚህ ሁለቱ ብቻ ናቸው በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ እስከነአባታቸው ስም የተጠቀሱት። በሌላ አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስ ሊያሳየን የፈለገው ነገር አባታችሁ ማን መሆኑ ከማን ወገን መሆናችሁ ልዩ ወይም ተፈላጊ ሰው እንደማያደርጋችሁ ነው፤ ምክንያቱም ሌሎቹ ደቀመዛሙርት አባታቸው ማን እንደሆነ ሳይጠቀስ ተመርጠዋል።
ማቴዎስ 10፡2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
3 ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥
እና ሁለቱ ያዕቆብ የተባሉ ደቀመዛሙርት አባቶቻቸው በስም ለምንድነው የተጠቀሱት?
ይህ ቁልፍ ነጥብ ነው። ሁለቱ ያዕቆብ የተባሉ ደቀመዛሙርት እስከነአባታቸው በስም የተጠቀሱት አንዳቸውም የኢየሱስ የስጋ ዘመድ አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ከራሱ ቤተሰቦች አንዳቸውንም ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ አልመረጠም።
በዚህ ዘመን አንድ ታዋቂ ሰው የቤተክርስቲያን ድርጅት ከከፈተ በኋላ የራሱን ልጅ በመሪነት ቦታ መተካቱ በጣም የተለመደ ነገር ነው፤ ልጅየው ግን ብቃቱ በድንገት በዚያ ቤተሰብ ውስጥ መወለዱ ብቻ ነው። ዋነኛው ምክንያት ግን ገንዘቡ ከቤተሰብ እንዳይወጣ ለማድረግ ነው። ፓስተሩ እና ቤተሰቦቹ የሁሉ ነገር ተቆጣጣሪ ይሆናሉ። ሁሉም ሰው ግን ዓይኖቹን ጨፍኖ እውነታው ይህ መሆኑን እንደማያውቅ ያስመስላል።
ዘፍጥረት ውስጥ በሰዶም ከተማ ላይ እሳት ከመውደቁ በፊት ሶስት መልእክተኞች ወደ ሰዶም መጡ። ባለፈው ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ያሉ ሶስት ታዋቂ አገልጋዮች ተነስተው ነበር።
በብዙዎች ዘንድ በዘመኑ ከሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ወንጌላዊ የተባለው ቢሊ ግራሐም ጴንጤቆስጤያዊ ካልሆኑ ቤተክርስቲያኖች የተነሳ መልእክተኛ ነበረ።
በታላላቅ ተዓምራት በታጀበ አገልግሎቱ የሚታወቀው ኦራል ሮበርትስ ለጴንጤቆስጤያዊ ዘመን መልእክተኛ ነበረ።
ዊልያም ብራንሐም በመለኮታዊ አሰራር ታላቅ ስጦታ ያለው አገልጋይ ሲሆን ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ታምን የነበረውን ነገር ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ የጠፋውን የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር እንዲገልጥ የተላከ አገልጋይ ነበረ። እርሱ ለእውነተኛዋ ሙሽራ የተላከ መልእክተኛ ነው፤ የእውነተኛዋ ሙሽራ አካሎችም እርሱ የተናገራቸውን ንግግሮች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው በመሄድ በመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው እምነታቸውን ያረጋግጣሉ። የዊልያም ብራንሐም ተዓምራዊ አገልግሎት ኃይል ዓለምን አናወጠ።
ያስተማራቸው ትምሕርቶች ግን ቸል ተብለዋል።
እነዚህ ሶስት ሰዎች በጣም አስደናቂ ነበሩ። ዓለም ላይ እውነተኛ ተጽእኖ አምጥተዋል።
አንድ የግል ምስክርነት ላካፍላችሁ። ስለ ቤተክርስቲያን ወይም ስለ እምነት አንዳችም ፍላጎት ያልነበረኝ ደንዳና ሐጥያተኛ ሆኜ ነበር ያደግሁት። ከሐይማኖት ርቄ ብቆይም እንኳ ግን ቢሊ ግራሐም ስለተባለው ኃይለኛ ወንጌላዊ በተደጋጋሚ እሰማ ነበር። እርሱን ታዋቂ ያደረጉት ተከታዮቹ ብቻ አልነበሩም። የሚያደርጋቸው የወንጌል ስብከት ዘመቻዎች ዓለም ላይ ሁሉ እንደ ሞገድ ይዳረሱ ነበር። እንደ እኔ ያለ በእግዚአብሔር መኖር የማያምን ሰው እንኳ ከእምነት ርቄ ብኖርም ለመስማት አንዳች ፍላጎት ባይኖረኝም ወሬውን ስሰማ በአገልግሎቱ መገረሜ አልቀረም።
ዛሬ ግን እውነታው ተለውጧል። ቤተክርስቲያንን ቤተሰብ ተቆጣጥሯታል።
መጎናጸፊያውም ከአባት ወደ ልጅ ይተላለፋል።
የኦራል ሮበርትስ ልጅ ሪቻርድ ሮበርትስ ድርጅቱን እየመራው ነው።
ፍራንክሊን ግራሐም ከቢሊ ግራሐም ተቀብሎ እየመራ ነው።
ዊልያም ብራንሐም ከሞተ ከብዙ ዓመታት በኋላ ልጅየው ጆሴፍ ብራንሐም ቦታውን ተክቶ አባቱን “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ከፍ አድርጎ “የእግዚአብሔር ድምጽ” አድርጎታል። ነገር ግን ከዊልያም ብራንሐም ጋር የነበረው መለኮታዊ ኃይል አሁን የለም።
ከእነዚህ ሶስት ልጆች መካከል አባቶቻቸው የነበረውን ዓይነት ታላቅ ተጽእኖ አንዳቸውም የላቸውም።
የመጀመሪያዎቹ ሰባት የሮማ ግዛት ነገስታት ስልጣን ከቤተሰባቸው እንዳይወጣ የተጠቀሙት ስርዓት ኔፖቲዝም ነበረ፤ ይህም ስልጣን በቤተሰብ ውስጥ እንዲቀር ማድረጊያ ዘዴ ነው።
እነዚህ በራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ እንድንጠነቀቃቸው የተነገረን ነገስታት ናቸው። የመጀመሪያው ምንም ርሕራሄ የማያውቀው ዩልየስ ቄሳር ነበረ፤ እርሱም በሮም ታላቅ ኃይልን መሰረተ። የዩልየስ ቄሳር ቤተሰብ ለ100 ዓመታት ያህል ስልጣንን የሙጥኝ ብሎ በመያዝ ጨቋኝነቱን ሲያበዛ በተረገጠው ሕዝብ መካከል ሐዘን፣ ጭካኔ፣ ተንኮል፣ ሴራ፣ ነፍስ ግድያ፣ ሃብት ማግበስበስ እየበዛ ሄደ።
ኔሮ ስለተባለው ዮሐንስን በ64 እና በ68 ዓ.ም መካከል ወደ ፍጥሞና ደሴት ስላሳደደው ስለ ስድስተኛው የሮማ ንጉስ ዮሐንስ በራዕዩ ውስጥ ሲጽፍ “አንዱም አለ” ይላል። ኔሮ ከቄሳር ጋር በቤተሰብ ስለሚዛመድ የተሰጠው ፈላጭ ቆራጭ ስልጣን ለአእምሮ የሚከብድ ጭካኔ የተሞላ አውሬ ስላደረገው የመጀመሪያውን የክርስቲያኖች ስደት የጀመረው እርሱ ነው። ሰዎች በስነምግባራቸው የወደቁበት አወዳደቅ ዘግናኝ ነበር።
ከዚህ ጠንከር ትምሕርት እንማራለን። የእግዚአብሔር ወንጌል ከአንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ልጅየው አይተላለፍም።
ንጉስ ዳዊት ፖለቲካዊ መንግስቱን ወደ ልጁ ወደ ሰሎሞን ማለስተላለፍ ይችላል።
በመንፈሳዊ ሕይወት በኩል ግን ሰሎሞን በሰበሰበው የሃብት ብዛት ተዋጠ፤ ሃብቱም በዓመት 666 ታለንት ወርቅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአውሬው ምልክት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ የተጠቀሰበት ቦታ ይህ ነው፤ መገለጫውም ሰዎች ከተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ዘወር ብለው ሊያጠግብ የማይችለውን የሃብት ምኞት ሲያሳድዱ እየደበዘዘ የሚሄደው መንፈሳዊነታቸው ነው ።
1ኛ ነገስት 10፡14-15 … በየዓመቱ ለሰሎሞን የሚመጣለት የወርቅ ሚዛን ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበረ።
ከዚያ እንግዶች ከሆኑ ሴቶች ጋር ወደቀ፤ ስሕተት በሆኑ እምነቶቻቸውም ተሳበ።
በመንፈሳዊነት ስናስበው ይህ መልካም ምስክርነት አይደለም።
ሰሎሞን ግን በሰበሰበው የሃብት ብዛት ሰውን ሁሉ አስደንቆ ነበር።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡4-5 … አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
ሃብታም መሆን የግድ የእግዚአብሔር በረከት ተደርጎ መቆጠር የለበትም። በምድር ላይ በሃብት አንደኛ የሆኑት ሰዎች ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም።
ከዚህ በታች ያለው የደቀመዛሙርት ስም ዝርዝር ነው።
ማቴዎስ 10፡2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
3 ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥
4 ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
ይህ አስፈሪ ነገር ነው። የደቀመዛሙርቱ ስም ዝርዝር የሚጠናቀቀው ኢየሱስን ማለትም ቃሉን አሳልፎ በሰጠው በይሁዳ ነው። የይሁዳ ውድቀት መንስኤው ምን ነበረ?
ገብጋባነቱና ለገንዘብ የነበረው ፍቅር ነው። ይሁዳ ልቡ በብልጽግና ወንጌል ላይ ነበረ።
ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ቃሉን ጥሎ ሄደ።
ከቃሉ ፊታችንን ዘወር ማድረግ ወደ አውሬው ምልክት ይዞን ይሄዳል።
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
የ666 ምልክት በምዕራፉ እና በቁጥሩ ውስጥ መገኘቱ የሚጠቁመን ነገር አለ።
ይህ ጠንከር ያለ ትምሕርት ነው። የገንዘብ ፍቅር ከእግዚአብሔር ቃል አርቆ ይወስደናል።
ስለዚህ እውነተኛው የኢየሱስ ቤተሰብ ማነው?
ማቴዎስ 12፡46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።
47 አንዱም፦ እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
48 እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
ኢየሱስ በስጋ ቤተሰቦቹ የነበሩትን ሰዎች ከማንም በላይ ከፍ አላደረጋቸውም። ከእነርሱ ጋርም ለጥቂት ዓመታት ብቻ ነው የኖረው።
እውነተኛ ቤተሰቦቹ በተመደቡበት የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጽሙ ዘንድ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉ አማኞች ናቸው።
ይህ ታላቅ ትምሕርት ነው።
ቤተሰብን ከእግዚአብሔር ቃል ማስቀደም አደጋ ነው።
ሉቃስ 14፡26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ለኢየሱስ እና ለቃሉ ሙሉ በሙሉ መሰጠት አለባችሁ። በእናንተ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት መካከል ቤተሰብም ሆነ ፓስተር ወይም ማንኛውም ሰው ጣልቃ መግባት የለበትም።
በቃና ከተደረገው ሰርግ በኋላ ሁላቸውም ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።
ቅፍርናሆም ማለት “የናሆም መንደር” ነው።
ናሆም የአሶር ዋና ከተማ ነነዌ እንደምትወድቅ ትንቢት የተናገረ ነብይ ነው።
ናሆም 1፡1 ስለ ነነዌ የተነገረ ሸክም፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው።
ነነዌ የዓለም ሁሉ መንግስታት ኃያል መንግስት ስለነበረች ሁሉ ነገር ተመችቷት ነበር።
ዮናስ በጎበኛቸው ጊዜ ሰምተውት ንሰሃ ገብተው ነበር። ነገር ግን በንሰሃ ከተመለሱ በኋላ በዚያ አልቀጠሉም። ከዚያ በኋላ ባቢሎን አሸነፈቻቸውና እነርሱ ተረስተው ቀሩ።
ቅፍርናሆምም ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ነው የሚገጥማት። ኢየሱስ ብዙ ጊዜ በቅፍርናሆም ነው የኖረው። በዚያም ብዙ ተዓምራትን አደረገ። መሲሁ በመካከላቸው ነበረ ሕዝቡ ግን እርሱን ለማመን እምቢ አሉ። ከአንዱ ሺህ ዓመታት በኋላ ቅፍርናሆም የድንጋይ ክምር ሆና ቀረች።
ቅፍርናሆም ኢየሱስ በአገልግሎቱ ዘመን ብዙ ተዓምራትን ያደረገባት ከተማ ናት።
ኢየሱስ ከናዝሬት ሲወጣ ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ በዚያ ኖረ። ቅፍርናሆም የጴጥሮስ፣ እንድሪያስ፣ ያዕቆብ፣ እና የዮሐንስ መኖሪያ ከተማ ናት።
ማቴዎስ 4፡12 ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።
13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።
14 በነቢዩም በኢሳይያስ፦
15 የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤
16 በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።
17 ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።
ስለዚህ ቅፍርናሆም የኢየሱስ አገልግሎት የተጀመረባት ከተማ ናት ማለት ይቻላል።
ኢየሱስ ወደ ፈለገበት ቦታ አይሄድም ነበር።
እርሱ የሄደበት ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጸፈለት ቦታ ነው። እድሜውን በሙሉ ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል በመገዛት ነው የኖረው።
በአገልግሎቱ ወቅት በቅፍርናሆም ከተማ ውስጥ በጣም ብዙ ተዓምራት ተደርጓል።
ማቴዎስ 8፡5 ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ብሎ ለመነው
መቶ አለቃው ባርያው ታሞ ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ቃሉን ብቻ ቢናገር ባርያው በርቀት ሆኖ ይፈወሳል።
ማቴዎስ 8፡14 ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤
15 እጅዋንም ዳሰሰ፥ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው።
ኢየሱስ እንዲከፍል የተጠየቀውን ግብር ሁሉ ከፍሏል፤ ዛሬ ግን ብዙ ክርስቲያኖች ግብር ከመክፈል ለማምለጥ ያጭበረብራሉ።
ማቴዎስ 17፡24 ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፦ መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን? አሉት።
ኢየሱስ ጴጥሮስን በአፉ ሳንቲም የያዘ ዓሳ እንዲያጠምድ አዘዘው። ያንንም ሳንቲም ተጠቅመው ግብር ከፈሉ።
ዓሳዎች እንኳ ለኢየሱስ አስራት ከፈሉ። በኖህ የጥፋት ውሃ ዘመን ውሃ ውስጥ የሰመጡ እሬሳዎችን እስኪጠግቡ በልተው ነበር። ስለዚህ እዳ ነበረባቸው።
ማርቆስ 1፡21 ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።
22 እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።
ኢየሱስ አንድ እውነት አስተማራቸውና ከአንድ ሰው ውስጥ እርኩስ መንፈስ አስወጣ።
ማርቆስ 2፡1 ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ።
እጅግ ብዙ ሕዝብ በዙርያው ተሰበሰቡ። አንድ ሽባ ሰው እንዲፈወስ ብለው ሰዎች በቤቱ ጣሪያ በኩል በቃሬዛ አወረዱት።
ከዚያ በኋላ አንድ ቀን ወደ ቅፍርናሆም ሲመጡ እያንዳንዱ ደቀመዝሙር እኔ ከሌሎቹ እበልጣለው እያለ መፎካከር ጀመረ። የሚሆኑት ነገር ልክ የዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎችና ፓስተሮች እንደሚሆኑት ነበረ። “እኔ ነኝ ሃላፊው። እኔ ካንተ እበልጣለው። እኔ ቢሾፕ ነኝ። እኔ ነኝ መሪው፤ እኔን አድንቁ። ቅኑብኝ። አምልኩኝ።” እኛ ሰዎች ልባችን በቀላሉ ራሳችንን በማክበር እና በትዕቢት ይሞላል።
ኢየሱስ አልተገረመባቸውም።
ማርቆስ 9፡33 ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው።
34 እነርሱ ግን በመንገድ፦ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ።
በመካከላቸው ማን ታላቅ እንደሆነ ይከራከሩ ነበር። ኢየሱስ ባለበት ጸጥ ይላሉ። ከእርሱ ጋር ሲነጻጸሩ ከምንም እንደማይቆጠሩ ገብቷቸዋል።
እኛ ሰዎች እርስ በራሳችን መወዳደር የለብንም፤ ምክንያቱም ራሳችንን ከሌሎች ጋር የምናነጻጽር ከሆነ በትእቢት ተነፍተን ሌሎች ሰዎችን ዝቅ እናደርጋለን። እራሳችንን ከኢየሱስ ጋር ማወዳደር ይሻላል፤ ምክንያቱም ራሳችንን ከእርሱ ጋር ስናስተያይ የማንጠቅም ባሪያዎች መሆናችንን በቀላሉ ማየት እንችላለን።
ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
ራስን ከፍ ማድረግ ማቆሚያ የሌለው እርግማን ነው። ራሳቸውን ከሌላው እንደሚበልጡ አድርገው የሚያስቡ ደቀመዛሙርት የተጠሩበትን ዓላማ አላወቁም።
በቅፍርናሆም ሳሉ የመከፋፈል ችግር ተነሳ። የእኛ ቤተክርስቲያን ከእናንተ ቤተክርስቲያን ትበልጣለች።
ማርቆስ 9፡38-39 ዮሐንስ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው። …
ሌላኛው በራስ ሃሳብ የመጠመድ እርግማን የእኔ ቡድን ትክክለኛ ነው የሚለው አስተሳሰብ ነው። ይህ ሰውዬ አገልግሎቱን ማቆም አለበት ምክንያቱም እኔን አይከተልም ወይም የእኔ ቡድን አባል አይደለም። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ቤተክርስቲያን ብቻ መኖር አለባት፤ እርሷም የእኔ ቤተክርስቲያን ናት። እኔን ካልተከተላችሁ ጠፍታችኋል።
የፓስተሮች መፈክር፡- ሁሉም ሰው የእኔን አመለካከት የመደገፍ መብት አለው።
ሉቃስ 4፡23 እርሱም፦ ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ፦ ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ አላቸው።
በቅፍርናሆም የተደረጉት ተዓምራቶች ዝና በዙርያ ባሉ ከተሞች ሁሉ ተሰማ።
ሉቃስ 4፡24 እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም።
25 ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤
26 ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።
ነብዩ ኤልያስ የሚያርፍበት ቦታ በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ቤት ነው የመራው እንጂ ወደ አይሁድ ቤት አልነበረም።
ይህም አይሁዳውያን እግዚአብሔር ለሰራው ሥራ ትኩረት ሳይሰጡ ሲቀሩ እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ዘወር እንደሚል የሚያመለክት ነበር።
ስለዚህ ቅፍርናሆም ውስጥ ለአይሁዳውያን ብዙ ተዓምራት ቢደረግም ኢየሱስ ግን በእርሱ ባያምኑ እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ዘወር ሊል እንደሚችል ነገራቸው።
በዚህ ንግግሩ ኢየሱስ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ነው ያስተላለፈው።
ቅፍርናሆም ውስጥ የተደረጉ ተዓምራቶች በሙሉ የሕዝቡን የማያምን ልብ ሊለውጡ አልቻሉም፤ ደግሞም እነዚያን በቅፍርናሆም የሚኖሩ አይሁዳውያንን ወደ ሲኦል ከመውረድ አያድኗቸውም። መለኮታዊ ተዓምራት ሲደረግ ማየት የቅፍርናሆም ሰዎችን ወደ ሰማያዊ ክልል ከፍ አደረጋቸው፤ ግን አማኞች አላደረጋቸውም።
ሉቃስ 10፡15 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።
17 ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።
20 ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
ተዓምራዊ ኃይልን መግለጥ ወይም ማሳየት መቻል አንድ ሰውን አማኝ አያደርገውም።
ስማችን በሰማያት በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ መመዝገብ አለበት። የበጉ የሕይወት መጽሐፍ ለዘመናቸው የተገለጠውን የተጻፈ ቃል የሚያምኑ ሰዎች ስም ዝርዝር ነው።
ማቴዎስ 7፡21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
ተዓምራዊ ኃይል መግለጥ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማታችንን ማረጋገጫ አይደለም።
ቀያፋ እና በለዓም ሁለቱም ክፉ ሰዎች ነበሩ፤ ግን ሁለታቸውም እውነተኛ ትንቢት ተናግረዋል።
ማቴዎስ 5፡45 … እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
እግዚአብሔር እውነትን የሚያምኑ ሰዎችን ይባርካል፤ ሐሰትን የሚያምኑ ሰዎችንም ይባርካል። ስለዚህ እግዚአብሔር ባረከህ ማለት እውነትን አምነሃል ለማለት አያስችልም።
ዮሐንስ 4፡46 ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ።
ኢየሱስ አሁንም ከርቀት ቃና ውስጥ ሆኖ ቅፍርናሆም ላለ የአንድ ሰው ልጅ ተዓምር አደረገ።
ዮሐንስ 6፡17 በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤
ወደ ቅፍርናሆም በጀልባ እየሄዱ ሳሉ ኢየሱስ እነርሱን ለማግኘት በማእበል ውስጥ በውሃ ላይ እየተራመደ መጣ። ኢየሱስ ካደረጋቸው ታላላቅ ተዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ ነው።
ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ፈተናቸው። ቅፍርናሆም ውስጥ ብዙ መለኮታዊ ተዓምራት አይተው ነበር። አሁን ደግሞ የተወሰነ ከበድ ያለ ትምሕርት እንዲሰሙ አደረገ።
ዮሐንስ 6፡56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
ዮሐንስ 6፡59 በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ።
60 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።
61 ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን?
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
በተዓምራት ተስበው የሚመጡ ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሲሰበክ ይሸሻሉ።
ተዓምራት ላይ ትኩረት የሚያበዙ አማኞች ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ጸንተው መቆም ያቅታቸዋል፤ ስለዚህ እራሳቸው ወደፈጠሩት ገለባ ብቻ ወደ ሞላው መላምት ዘወር ይላሉ።
ማቴዎስ 11፡20 በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦
21 ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤
ማቴዎስ 11፡23 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤
በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
ቅፍርናሆም ታላላቅና አስደናቂ ተዓምራት እንድታይ እና ጠለቅ ያለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርት እንድትሰማ በመንፈስ ከፍ ከፍ ተደርጋ ነበር።
ሰዎች በተዓምሩ ተደንቀው ነበር፤ ነገር ግን እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ፍላጎት አልነበራቸውም።
ሉቃስ 10፡23 ወደ ደቀ መዛሙርቱም ዘወር ብሎ ለብቻቸው፦ የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው።
24 እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ።
የወደፊቱን በራዕይ ተገልጦላቸው ያዩ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን መሲሁ ተገልጦ ቢያዩ እጅድ ደስ ባላቸው ነበር። የቅፍርናሆም ሕዝብ ግን ባዩት መለኮታዊ ተዓምር አልተለወጡም፤ ስለዚህ ኢየሱስ ያስተማራቸውን ጠለቅ ያለ ትምሕርት አልቀበልም አሉ። ለዘመኑ የተላከው ቃል በመካከላቸው አለፈ፤ እነርሱ ግን በራሳቸው የኑሮ ጉዳይ ስለተጠመዱ አላስተዋሉትም። ሁሉም ነገር ቀርቦላቸው ነበር እነርሱ ግን እያዩ ከእጃቸው ሾልኮ ወጣ።
እግዚአብሔር በዘመናችሁ እያደረገ ያለውን አለመቀበል በጣም አደገኛ ነገር ነው።
የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ኢየሱስ የሚናገራቸውን ሚስጥራት ሊያደምጡ በጣም ይመኙ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ነው ደቀመዛሙርትን “ብጹአን” ያደረጋቸው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታውቃቸው የነበሩትን ተሰውረው የነበሩ ሚስጥራት እግዚአብሔር ዛሬ እየገለጣቸው ነው። እንደዚህ ዓይነት እውነቶች ምን ለማየት መታደላችን ምን ያህል ታላቅ እድል መሆኑን መገንዘብ ካቃተን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ምንም ጉዳይ እንዲኖረው አይፈልግም፤ ምክንያቱም እርሱ በዚህ የዘመን መጨረሻ ላይ እየገለጠ ያለውን የማወቅ ፍላጎት የለንም። እኛ ግን በፓስተር የምትተዳደር ቤተክርስቲያናችንን ድንቁርና እና ውስንነት የመረጥን እንመስላለን። ቤተክርስቲያናችንም ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብዙውን ሳታብራራው ትታ ማለፍ ለምዳለች።
በመጽሐፍ ውስጥ ከተጻፉት የኢየሱስ ተዓምራት ኢየሱስ በቅፍርናሆም አገልግሎቱ ውስጥ ያደረጋቸው ተዓምራት በጥቂቱ እነዚህ ናቸው።
አገልግሎቱን ወደጀመረበት በመመለስ ኢየሱስ ከቃና ወጥቶ ብዙ ጊዜ ወደኖረበት ወደ ቅፍርናሆም ሄደ።
ዮሐንስ 2፡12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።
በቅፍርናሆም ውስጥ ያደረጋቸው መለኮታዊ ተዓምራት ሁሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል በእውነት እንዲያምኑ እንደማያደርጋቸው በማወቅ ኢየሱስ በቅፍርናሆም ያደረገውን ቆይታ በአጭሩ ለመቋጨት ወሰነ።
ኢየሱስ ማሳየት የፈለገው ነገር ቢኖር መለኮታዊ ተዓምራት በቅፍርናሆም ውስጥ የታሰበለትን ዓላም ማከናወን እንዳልቻለ ነው፤ ምክንያቱም ተዓምር የእግዚአብሔርን ቃል እንዳያምኑ ያደረጋቸውን የሰዎችን አለማመን ከልባቸው ውስጥ አላወጣውም።
ተዓምር ለግለሰቦች ጠቃሚ ነው ነገር ግን ሰዎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲመለሱ አያደርጋቸውም።
ተዓምራት የአገልግሎቱ መንገድ ነበረ፤ ነገር ግን ዋናው ቁምነገሩ እርሱ ይናገር የነበረው ቃል ነው። ቀሉ ነው ዋናው እንጂ ለቃሉ አጃቢ ሆኖ የቀረበው ነገር አይደለም።
ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር ተዓምራት ትኩረትን እንደሚስብ ነገር ግን የሰውን ትኩረት ለረጅም ጊዜ ሊገዛ እና ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ሊያደርግ እንደማይችል ነው።
ተዓምራት አስደናቂ ቢሆንም እንኳ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙም ትኩረት እንድናደርግ አይገፋፋንም፤ ላይ ላዩን እንድንነካካ ሊያደርገን ይችላል እንጂ። አስደናቂ የሆኑ ተዓምራዊ ትዕይንቶች የሰዎችን ስሜት ሊያነቃቁ ይችላሉ፤ ግን ብዙውን ጊዜ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ አያነሳሱዋቸውም፤ ከዚህም የተነሳ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሆነው ይቀራሉ። እነደዚህ ዓይነት ሰዎች ቢያምኑም እንኳ ለይስሙላ ነው የሚያምኑት።
ነገር ግን አንድ ሰውን የሳበው ከልብ የሆነ መጽሐፍ ቅዱስን የማወቅ ፍላጎት ከሆነ ምንም ችግር ቢያጋጥመው እንኳ እንዲህ ዓይነቱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ እየተደነቀ ጸንቶ ይቆያል። ለዚህ ሰው አእምሮ የእግዚአብሔር አስተሳሰብ በጣም አስደናቂ ስለሚሆንበት ይህ ሰው በእግዚአብሔር ሰፊ እቅድ ተመስጦ ይቀራል። ሰዎች በግላዊ ፍላጎቶቻቸው የተነሳ ብዙ ስሕተቶችን እያሰሩ ቢያወሳስቡዋቸውም እንኳ በብዙ ሺህ ዓመታት ውስጥ የሚፈጸመው የሰው ልጅ ታሪክ አቅጣጫ እና ስርዓት ባለው መንገድ ሲሄድ ማየቱ አጅግ ያስገርማል። እነዚህ ሰዎች ከአእምሮ እና ከሰው ጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ ደስ ያሰኛቸዋል። ስለዚህ ይበልጣ ማወቅ እና የሰው ልጅ ታሪክ ታላቅ ፍጻሜ አካል መሆን ይፈልጋሉ።
ደቀመዛሙርቱ ሰውን አጥማጆች ሆኑ። ተዓምራት ሲደረግ ከውሃው ላይ ላዩን የሚንሳፈፉ ትንንሽ ዓሳዎችን ይስባቸዋል። የተጻፈው ቃል መገለጥ ደግሞ በባሕር ጥልቀት ውስጥ የሚዋኙ ትልልቅ ዓሳዊችን ይስባቸውና ይይዛቸዋል።
ትንንሾቹ ዓሳዎች በተዓምራዊ ትዕይንቶች እና በሙዚቃ በመዝናኛ በመሳሰሉ ነገሮች የሚሳቡ እንቅልፍ የተኙ ቆነጃጅት ናቸው። ለመረዳት ቀላል የሆነውን የቃሉን ክፍል ያምናሉ፤ ከዚያም ማሰብ የሚጠይቀውን ከበድ ያለውን ክፍል ቸል ብለው ያልፋሉ። ዘይታቸው በጣም ትንሽ ስለሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ በቂ ብርሃን አይሰጣቸውም።
ስለዚህ የተጻፋን ማየትም ሆነ መረዳት አይችሉም።
ጠለቅ ባለው የባሕር ሞገድ ውስጥ የሚዋኙት ትልልቅ ዓሳዎች የሙሽራዋ አካሎች ናቸው። እነዚህ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል በሙሉ የሚያምኑ እውነተኛ አማኞች ናቸው። ቃሉ ለመረዳት ከበድ ሲል ልክ እንደ ጥሩ የወይን ጠጅ ያነቃቃቸዋል።
የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለማንበብና ምን ማለት እንደሆነ ለማስተዋል የሚበቃ በቂ ብርሃን የሚሰጥ ዘይት አላቸው። የተጻፉትን የእግዚአብሔር ቃሎች እርስ በእርስ ሲያገናኙ እና ለዘመናቸው የሆነው የእግዚአብሔር እቅድ ሲገለጥና ምሪት ሲሰጣቸው ያነቃቃቸዋል።
አሁን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። እርሱ ጌታ እንደመሆኑ ወደ መቅደሱ ይመጣል። እንዲሁም ተብሎ ተጽፏልና።
ሚልክያስ 3፡1 እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤
ዮሐንስ 2፡13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
ሌሎችን የአይሁድ በዓላት ሁሉ ያከብር እንደነበረው ፋሲካን በመቅደሱ ውስጥ ማክበር ፈለገ። እኛን ከሕግ እርግማን ነጻ ለማውጣት ብሎ እርሱ ሕጉን ሁሉ በማክበር ነበር የሚኖረው።
ዮሐንስ 2፡14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
ከዚያ አንድ ነገር ሲያይ አስቆጣው። ገንዘብ ለመሰብሰብ በማይጠግብ ፍለጎታቸው የተነሳ ሐይማኖትን መነገጃ ያደረጉ ሰዎች አናደዱት። እነዚህ መንፈሳዊ ደም መጣጮች ናቸው።
ዮሐንስ 2፡15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
ጅራፍ ወደ ጫፉ በቀጭኑ የተገመደ ገመድ ነው። እነዚህ ጅራፎች ሶስት አራቱ አንድ ላይ ሲሆኑ ጥሩ አለንጋ ይወጣቸዋል። ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ የተጠቀመው ጅራፍ ነው። በዘመን መጨረሻ ከጥንቶቹ በክፋታቸው የባሱ የሐይማኖት ነጋዴዎች ዳግም ምጻቱን የማያስተውሉ ስለሆነ በታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይሞታሉ። ለእነዚህ ሰዎች ብዙ ጅራፎች አንድ ላይ ሲገመዱ የስቅላት ገመድ ይሆኑባቸዋል።
ዮሐንስ 2፡16 ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።
እርሱም ሰዎቹን ገፍትሮ ከመቅደስ አስወጣቸው፤ በሌብነት የሰበሰቡትንም ገንዘብ በመጸየፍ መሬት ላይ በተነው። ኢየሱስን ያስቆጣው ነገር ሰዎች እግዚአብሔርን አገለገልን እያሉ ራሳቸውን ሃብታም ማድረጋቸው ነው።
የሚሸጡ እቃዎች ይዘው ነበር። ልክ እንደ ዛሬዎቹ ቤተክርስቲያኖች። እያንዳንዱ የሰላሳ ደቂቃ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መቋጫው የሚሸጥ መጽሐፍ ወይም ሲዲ እና ዲቪዲ ነው።
በሁሉም ፕሮግራም የማይቀረው ነገር ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ነው።
የዛሬዎቹን ሃብታም ፓስተሮችን ትልልቅ ቤቶቻቸውን እንዲሁም ብዙ ገንዘብ የተቀበጠበት የባንክ ሒሳባቸውን ስንመለከት የምናየው ኢየሱስ የተቆጣባቸው ሰዎች ላይ የነበረው ተመሳሳይ ስግብግብ መንፈስ ነው። ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ብዙ ሃብታም የቤተክርስቲያን መሪዎች ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ።
ሉቃስ 6፡24 ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።
ይህ ቃል የዚህን ዘመን ፓስተሮች እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ይመለከታል።
ቢሾፖችን፤ ሐዋርያዎችነ፤ ሊቀጳጳሳትን፤ ካርዲናሎችን፤ ፖፑን ሁሉንም ይመለከታል።
ወዮላችሁ የሚለው ቃል ከታላቁ መከራ ጋር የተያያዘ ነው። በፍጹመ በሰማያት ከተዘጋጀው የሰርግ ድግስ ጋር የተያያዘ አይደለም።
ንግድ በተጧጧፈበት ማሕበረሰብ መካከል ሐይማኖት እራሱ በገበያ ውስጥ ከሚሸጡ ሸቀጦች አንዱ ሆኗል።
ዮሐንስ 2፡17 ደቀ መዛሙርቱም፦ የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።
በዚህ ቃል ውስጥ ኢየሱስ መቅደሱ ውስጥ ሆኖ ምን እንዳስተማረ አልተጻፈም፤ የተጻፈው ሐይማኖታዊ ስራቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን ሃብታም ያደረጉ ሰዎችን እንዴት እንዳወገዛቸው ብቻ ነው።
ለመቅደሱ የነበረው ቅናት በቁጣ እንዲቆጣ ያደረገው እግዚአብሔርን ለገንዘብ እና ለትርፍ ብለው በሚያገለግሉት ላይ ነበር።
ንግዱ የሚካሄደው ሐይማኖተኛ ሰዎች ሊጠቀሙ የሚችሉትን ሸቀጥ በማቅረብ ነው።
ለገበያው እንዲመች ተብሎ ሸቀጡ ተስማሚ እንዲሆን ይደረጋል።
ታላላቅ ቤተክርስቲያኖች ቀለል ያለ ሐይማኖት ለሽያጭ ያቀርባሉ፤ በውሃ ቀጥኖ ስለሚቀርብ በቀላሉ ይሸጣል ምክንያቱም ማንንም አያስከፋም።
የሚያቀርቡት ሸቀጥ እንደገበያው ነፋስ እና ፍላጎት የሚለዋወጥ ነው። ሸቀጣቸውን መሸጥ ስለሆነ ፍላጎታቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማጣመማቸው ምንም አይጨንቃቸውም።
ምክንያቱም ለእነርሱ ትልቁ ነገር እውነት ሳይሆን ሽያጭ ነው።
አንድ ታዛቢ እንደተናገረው ታላላቅ ሃብታም ቤተክርስቲያኖች የማይረባ ምግብ በልቶ ለወፈረ ሰው ሆድ ውስጥ በቀላሉ ሊፈጭ የሚችል ተራ ምግብ ያቀርባሉ።
ለእነዚህ ሰዎች ከአስተምሕሮ ይልቅ መንፈሳዊ ልምምዶቻቸው ይበልጡባቸዋል። የገበያ አጥኝዎች እንደሚናገሩት ሰዎች ስለ መዳን ከምትነግሩዋቸው ይልቅ ጭንቀትን ስለመቀነስ ብትነግሯቸው ተመልሰው ይመጣሉ። ከመለወጥና መልካም ከመሆን ይልቅ መልካም ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ላይ ነው ትኩረቱ። በዚህ መንገድ ብዙ ገንዘብ ተዝቆ ይገባል።
የገንዘብ ትርፍን ማሳደድ ለሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ማቅረብ ሳይሆን የሚፈልጉትን ማቅረብ ላይ እንድታተኩሩ ያደርጋችኋል። የሚፈልጉትን ስታቀርቡላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወደናንተ ይመጣሉ።
ከእያንዳንዱ የቲቪ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ሁልጊዜ ገንዘብ አምጡ የሚባልበት እና ሐይማኖታዊ ሸቀጥ ግዙ ተብሎ የሚወተወትበት ሰዓት አለ።
ንግድ የሚሰራው እንደ አፕል፣ ጉግል፣ ኮካኮላ የመሳሰሉ ገበያ ላይ ታዋቂ በሆኑ ስሞች አማካኝነት ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጴጥሮስን የመንግስተ ሰማያት ደጅ ጠባቂ አደረገችው፤ ማርያምን ደግሞ ሁሉ ጊዜ ወደ እርሷ ሲጸልዩ የምትሰማ ሩህሩህ እናት አደረጓት። እማሆይ ቴሬዛ እና ፖፕ ፍራንሲስም ሌሎቹ የተከበሩ የንግድ ምልክቶች ናቸው።
አሁን ከሮማ ካቶሊክ ማሕጸን የወጡ ቤተክርስቲያኖችም “የንግድ ምልክት” ማበጀትን ከእናታቸው ተምረዋል። ጃውል ኦስቲን፣ ጆሴፍ ፕሪንስ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ እና ቲ. ዲ. ጄክስ በጣም ብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኙ የንግድ ስሞች ሆነዋል።
ኢየሱስ በድህነት ቢኖርም እንኳ ቤተክርስቲያን በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች ንግድ ውስጥ እንደምትገባ አውቋል። በሰማይ ሃብት እንደተጠመደች እያስመሰለች እውነታው ሲመረመር ግን ቤተክርስቲያን ማንም የማይነቀንቃት የምድር ሃብት ሰብሳቢ ሆናለች።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብቻዋን የአውሮፓ እና የአሜሪካ ሃብት ውስጥ አንድ ሶስተኛውን ተቆጣጥራለች።
ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ነጋዴዎችን አባረራቸው። ሲያያቸው በጣም ተቆጣ።
በገንዘብ ብዛት የጠገቡ ሐይማኖተኛ ነጋዴዎችን እየገረፈ ከቤተመቅደሱ ሲያስወጣ ምን ሊነግረን አስቦ ነው?
ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የት ነው?
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
17 ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።
ይህ ድርብ ትርጉም አለው። እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ያኖረዋል፤ ከዚያም የቅድስና ሕይወት እንዲኖሩ ይጠብቅባቸዋል። እንዲህም ማድረጉ እያንዳንዱን ሰው በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ያደርገዋል።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ … ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
ከዚያም በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ታላቅ መንፈሳዊ የክርስቶስ አካል ወይም የሕያው እግዚአብሔር ቤተመቅደስ ይሆናሉ።
ስለዚህ ኢየሱስ እየነገረን ያለው መንፈሳዊ አካሉን ወይም ቤተመቅደሱን ገንዘብ መሰብሰቢያ የንግድ ቤት በማድረግ ያረከሱ የቤተክርስቲያን መሪዎችን በሙሉ ይይዛቸውና ከመንፈሳዊ ቤተመቅደሱ እንደሚያስወጣቸው ነው። የሙሽራይቱ አካል አይሆኑም። እርሱ ተመልሶ ሲመጣም ወደ ሰማይ አይነጠቁም። ወዲያ የሚገጥማቸው እጣ ፈንታ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።
ማቴዎስ 19፡24 ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።
ሃብታም መሆን ወደ እግዚአብሔር አያቀርባችሁም።
ዮሐንስ 2፡18 ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት።
ኢየሱስ ገንዘብ የሚልጡበትን ገበያ ብትንትኑን አወጣላቸው። ገንዘብ የሚያገኙበትን ስራቸውን ስላፈራረሰባቸው በጣም ተቆጥተውበት ሊገድሉት መማከር ጀመሩ።
ድምጻቸውን ሳያሰሙ ዛቻቸውን ጀመሩ። ከሮማውያን ጋር በአንድነት ሆነው ብዙ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ኃይል አከማችተዋል፤ ስለዚህ ንግዳቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባ መበጥበጡን ካላቆመ እንዲገደል ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ። ይህን ለማድረግ ካሰቡ የሚከለክላቸው እንደሌለ ያውቃሉ።
ከዚያ ቀጥሎ ከሶስት ዓመታት በኋላ ገንዘብ ለዋጮችን ባስወጣ ጊዜ እንዲገደል ለማድረግ ወጥመዳቸውን ያዘጋጃሉ።
እነርሱን ለማስፈራራት ምን ምልክት ማሳየት ይችል ይሆን?
ከምልክቶች ሁሉ ታላቅ የሆነውን ምልክት ነገራቸው፤ እርሱም ከሙታን ትንሳኤ ነው። በእርግጥ ከሮማውያን ጋር ተሻርከው ሊያስገድሉት ይችላሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከሙታን ተመልሶ ይነሳል።
በእለተ አርብ ይገደልና ይቀበራል። ቅዳሜ በመቃብር ውስጥ ይቆይና እሁድ ከሙታን ይነሳል። ስለዚህ ሶስቱ ቀናት ከሞቱ ጋር ይያያዛሉ። አርብ በከፊል፣ ቅዳሜ ሙሉ ቀን፣ እና እሁድ በከፊል።
ዮሐንስ 2፡19 ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
ዮሐንስ 2፡20 ስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።
አይሁድ ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር አንዳችም አልገባቸውም።
ቤተመቅደሱ የንግዳቸውና የገቢ ምንጫቸው ማዕከል ነበረ። ያለ መቅደሱ ሞቅ ያለ ክፍያ የሚያገኙበት ሌላ መንገድ አልበራቸውም። ነገር ግን ይህ ሁሉ በተራው እስኪወድም ድረስ አርባ ዓመት ብቻ ነበር የቀራቸው። መቅደሱ እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አይሁዳውያን ከአርባ ዓመታት ወዲያ በሮማውያን እጅ እንዲጠፉ ተቀጥሮላቸው ነበር።
ከዚያ ወዲያ አይሁድ ቤተመቅደሳቸውን መልሰው መገንባት አይቻላቸውም።
ሔሮድስ ቤመቅደሱን ማደስ የጀመረው ከክርስቶስ ልደት 20 ዓመታት በፊት ነበረ።
መልሶ ሲገነባውም የተሻለ እና ተለቅ ያለ አድርጎ ነበር የገነባው። ስለዚህ በ26 ዓ.ም ነበር ግንባታው የተጠናቀቀው። ኢየሱስ በ30 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፋሲካን ለማክበር ወደ ሲመጣ የመጣበት ጊዜ መቅደሱ ተገንብቶ ካለቀ ገና አራት ዓመቱ ነበር። አዲስ እና ውብ ሕንጻ ስለነበረ አይሁዶች ዓይናቸውን ጥለውበት ይወዱታል ይኮሩበታል። ነገር ግን ኢየሱስን ሊያጠፋ በሞከረ ጊዜ ያ ሔሮድስ እራሱ ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ብዙ አይሁዳውያን ሕጻናትን ገድሏል። በዚያ ሙከራው ሔሮድስ አልተሳካለትም ነበር። ነገር ግን በብዙ ወጪ በግሉ አውጥቶ ያሰራው ቤተመቅደስ በ70 ዓ.ም እንዲፈርስ ተቀጥሮለት ነበር።
ዮሐንስ 2፡21 እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።
ኢየሱስ መቅደሱን መልሶ የመገንባት ፍላጎት አልነበረውም። እርሱ ከሞተ በኋላ በቤተመቅደስ ውስጥ ሆኖ ማምለክ ይቀራል ምክንያቱም እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን መጋረጃ ቀድዶታል። ከዚያ በኋላ ቤተመቅደሱ ይፈርስና ሁለተኛ ተመልሶ አይሰራም።
የአይሁድ ሕግ ማዕከል የነበረው ቤተመቅደስ የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማዕከል በሚሆንበት በአዲስ ኪዳን የጸጋ ወንጌል ስለሚተካ ከዚያ በኋላ አስፈላጊነቱ ያበቃል።
የኢየሱስ ዓለማው ለመሞት እና ከዚያ በኋላ ከሞት ለመነሳት ነበር።
የአካሉ ቤተመቅደስ በሮማውያን መስቀል ላይ ይፈርሳል፤ ነገር ግን ያ የአካሉ ቤተመቅደስ በትንሳኤ ተመልሶ ይነሳል። ስለዚህ የአይሁድ ቤተመቅደስ ማድረግ የማይችለውን ነገር ኢየሱስ ያደርገዋል። ኢየሱስ በሮማውያን እጅ ከሞተ በኋላ ተመልሶ ከሙታን ይነሳል።
እነዚህ የቤተመቅደስ አይሁዶችና ነጋዴዎች በስተመጨረሻ ኢየሱስ ካልተገደለልን ይላሉ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ በትንሳኤው ለማመን እምቢ ይላሉ።
እነርሱ ራሳቸው ደግሞ በተራቸው በ70 ዓ.ም ሮማውያን 1,100,000 አይሁዶችን ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲገድሉ ይሞታሉ። አይሁዳውያን ላይ የተፈጸመው የመጀመሪያው ጭፍጨፋ ይህ ነው። እርሱም መሲሁን ስለመግደላቸው የከፈሉት ዋጋ ነው።
መቅደሳቸው ፈረሰ፤ ተመልሶም አልገነባም።
በቤተመቅደስ ውስጥ ሲነግዱ የነበሩት አይሁዶች እርሱን ሊገድሉ የሚችሉ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን በራሳቸው ላይ ምን ዓይነት ፍርድ እየከመሩ እንደነበረ አላወቁም።
ዛሬ እነርሱም ሆኑ ቤተመቅደሳቸው ጠፍተዋል። ኢየሱስ ግን እስከዛሬም በክብሩ በሕይወት አለ።
ስለዚህ ኢየሱስ የተወላቸው ምልክት አለ። ምልክቱም ሮማውያን እርሱን በመስቀል ሰቅለው ከገደሉ በኋላ ከሞት መነሳት መቻሉ ሲሆን፤ አይሁዶች እና መቅደሳቸው ሮማውያን ካጠፉዋቸው በኋዋላ ግን ተመልሰው መነሳት አልቻሉም።
ትልቁ ችግር ግን አይሁዶቹ ተጠምደውበት የነበረው ሐይማኖትን ለንግድ የሚያውል ክፉ የሆነ መንፈስ በዘመን መጨረሻ ቤተክርስቲያን ውስጥ አድጎ ተስፋፍቶ መምጣቱ ነው። እነዚህ ነጋዴ የሆኑ የሐይማኖት መሪዎች ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።
ዮሐንስ 2፡22 ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
ደቀመዛሙርቱ የወንጌሉ እቅድ ሙሉ በሙሉ የገባቸው ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ነበር።
እነርሱ ያነብቡ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር የያዘው። ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አካል ሆነው ነው የተጻፉት። ኢየሱስ የተናገረውና ያደረገው ነገር በሙሉ ብሉይ ኪዳንን ከአዲስ ኪዳን ጋር ያያይዛል።
ዮሐንስ 2፡23 በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
ተዓምራቱ ብዙ ሰዎችን ይስቡ ነበር፤ ኢየሱስ ግን ተዓምራት አይተው ሊከተሉት በመጡ ሰዎች አልተደነቀም። ኢየሱስ የፈለገው ሰዎች በተዓምራዊ ምልክቶች እየተደነቁ እንዲከተሉ ሳይሆም መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን እንዲያምኑ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማመን እና በቃሉ መገለጥ መደሰት በተዓምራዊ ምልክቶች ከመገረም አልፎ ከእግዚአብሔር ጋር ጠለቅ ያለ ሕብረት ማድረግን ይጠይቃል።
ተንኮለኛ ጠላቶች እውነተኛ ተከታዮች ነን ብለው ማስመሰል ይችላሉ።
እነዚህ የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ ሃሰተኛ ወዳጆች ናቸው። በምልክቶች እና በድንቆች ላይ የተመሰረተ እምነት ላይ ላዩን ብቻ ነው የሚሆነው ምክንያቱም ስሜትን ብቻ ነው የሚያነቃቃው። ሰዎችም ቃሉን ፈላጊዎች ሳይሆኑ ምልክት ፈላጊዎች ሆነው ይቀራሉ።
ዮሐንስ 2፡24-25 ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤… አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።
ሰዎችን ልናታልል እንችላለን እግዚአብሔርን ልናታልለው ግን አንችልም።
ኢየሱስ በሆሳዕና ዕለት አህያ ላይ ተቀምጦ ሲገባ እያጨበጨቡለት የነበሩ ሰዎች እራሳቸው በቀጣዩ አርብ እለት ይሰቀልልን ብለው ይጮሁ ነበር።
ውዳሴያቸው በአንድ ሳምነት ውስጥ ወደ ጥላቻ ተለወጠ።
እነዚህ አይሁዶች የሐይማኖት መሪዎቻቸውን መከተል ስለለመደባቸው ለራሳቸው ማሰብ አልቻሉበትም።
ስለዚህ የራሳቸውን መሲህ ፈረዱበት፤ ምክንያቱ ደግሞ የሐይማኖት መሪዎቻቸው እንዲፈርዱበት ስለነገሩዋቸው ነው።
ሕዝቡ ለራሳቸው ማሰብ ትተው መንጋውን ይከተሉ ነበር። ልክ የዛሬ ክርስቲያኖችን ይመስላሉ። መንጋውን የምትከተሉ ከሆነ የምትበሉት አፈር ነው። አፈር ደግሞ የእባቡ ምግብ ነው።
ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቀው አያውቁም፤ ከቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ጋር በአስተሳሰብ መቃረን ያስፈራቸዋል፤ ከቤተክርስቲያንም እንዳይባረሩ ይፈራሉ።
በራሳቸው አእምሮ ማሰብ የማይችሉ የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች እንደዚህ ናቸው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የምታስተምራቸውን ትምሕርት እየደጋገሙ ከማውራት በቀር ምንም አያውቁም። ዛሬ 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በሞሉበት ዓለም እና ሁላቸውም እኛ ትክክለኞች ነን በሚሉበት ጊዜ በራሳችን አእምሮ ማሰብ አለመቻል አደጋ አለው። እናንተ የምትከተሉዋት ቤተክርስቲያን ትክክለኛ የመሆን እድሏ አንድ ከ45,000 ነው። ይህም ማለት ትክክለኛ የመሆን እድሏ እምብዛም ነው ማለት ነው። ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ አስሩም ቆነጃጅት (የዳኑ ጥሩ ቤተክርስቲያኖች) በሙሉ እንቅልፋቸውን ተኝተው ነበር።
ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
በጣም የሚያሳዝነው ነገር የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሰው ሰራሽ ልማዶች ለመከተል ወስነዋል፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም የጥንቷን የአዲሰ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሳይሆን እራሷን እናት ቤተክርስቲያን ብላ ሰይማለች።
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ፓስተር የሚለው ቃል አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን ፓስተር የቤተክርስቲያን መሪ እንዲሆንም ስልጣን አልተሰጠውም፤ ነገር ግን የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ፓስተርን የቤተክርስቲያን መሪ አድርገው ይሾማሉ። ፓስተሩ ብቻ ያስባል እነርሱ ደግሞ አያስቡም ከእርሱ ጋር መቃረንም እንደ ሞት ያስፈራቸዋል።
ዮሐንስ 2፡25 … ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና … ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።
እያንዳንዱ ሰው ሌሎችን ለማስደነቅ ብሎ የራሱን ፊት ይወለውላል። ኢየሱስ በጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ፊት በቆመ ሰዓት ግን በዚያ ሸንጎ ውስጥ የነበረ ሁሉ ፈረደበት እንጂ ማንም ለእርሱ የተከራከረለት አልነበረም። እኛ ሰዎች ልክ እንደዚህ የማንጠቅም ነን።
በመንገዳችን መሰናክል ሲገጥመን ወዲያው ወደ ኋላ እናፈገፍጋለን።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ዓለም ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እውነት ሲነቅፍ ለተጻፈው ቃል በመቆማችን የሚደርስብንን ስደትና ቀልድ ለመቋቋም ዝግጁ ነን?
የቀሬናው ስምኦን ብቻ ነው ኢየሱስን መስቀል በመሸከም ያገዘው፤ እርሱም ተገድዶ ስለሆነ ነው።
ማቴዎስ 27፡32 ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
ዓለም ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በሚቃወምበት ጊዜ የእኛ አቋም ምን ይሆን?
ዓለም ሁሉ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ሲገፋ አቋማችን ምን ይሆን?