ዮሐንስ ምዕራፍ 01. እግዚአብሔር ወደ ምድር ወረደ። እግዚአብሔር የት ነው የሚኖረው?



First published on the 24th of April 2020 — Last updated on the 24th of April 2020

ዮሐንስ 1፡1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ከመጀመሪያ ጀምሮ እግዚአብሔር ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያኑ አባላት እቅድ ነበረው። እነርሱ የሙሽራዋ አካል ይሆናሉ። ሙሽራ ከማንም ይልቅ ወደ ባሏ ነው የምትጠጋው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እውነተኛ አካሉ ናት፤ ምክንያቱም እርሱ በሕዝቡ ልብ ውስጥ መኖርና ለእግዚአብሔር ቃል ወደ መታዘዝ ሊያመጣቸው ይፈልጋል።

ስለዚህ በዓይን የማይታየው የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖርበትን አካል እየፈለገ ነው፤ ምክንያቱም የራሱን ባሕርያት መግለጥና በአካሉ ማለትም በአማኞች አማካንነት ቃሉን ወደ ፍጻሜ ማምጣት ይፈልጋል።

የመጀመሪያውን ይበልጥ የተሻለ ለመረዳት ከፈለግን እግዚአብሔርን በራዕይ መጽሐፍ መጨረሻ ላይ በጥቂቱ እንመልከተው። በሰማያት በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት ወይም ሕያዋን ፍጥረታት አሉ። እነርሱም አንበሳ፣ ጥጃ፣ ሰው፣ እና ንሥር ናቸው።

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

ዓይኖች የሚያመለክቱት እውቀትን ነው። እነዚህ መንፈሳዊ እንስሳት ወይም ኃይላት ስለ ወደፊቱ ያውቃሉ (በፊት በኩል ዓይኖች የሞሉዋቸው) ስላለፈውም ያውቃሉ (በኋላ ዓይኖች የሞሉዋቸው)። እግዚአብሔር ከጊዜ ቀጠና ውጭ ስለሚኖር የወደፊቱንም ያለፈውንም ማየት ይችላል። እኛ ግን ተወልደን እስከምንሞት ድረስ በምንኖርበት ጠባብ የጊዜ ቧምቧ ውስጥ ተወስነን ነው የምንኖረው።

እነዚህ አራት መንፈሳዊ ኃይላት ወይም ሕያዋን ፍጥረታት ቤተክርስቲያንን በ2,000 ዓመታት ታሪኳ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ይቆጣጠሯታል፤ ደግሞም ይመሩዋታል።

አንበሳው የሚወክለው አዲስ ኪዳንን የጸፉበትን እንዲሁም ኢየሱስ በወንዶችና በሴቶች ልብ ውስጥ ይኖር ዘንድ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የተቀበሉበት የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ትመራበት የነበረውን የሐዋርያዊ አባቶችን እውነተኛ እምነት ነው። የዛን ጊዜ የሰው መሪዎች ቤተክርስቲያንን በሰው አስተሳሰብ እንምራ ብለው ሳይነሱ በፊት ሕዝቡ የሚያምኑት እና የሚኖሩት በመጽሐፍ ቅዱስ ነበር።

ጥጃ ማለት ያለደገ ትንሽ በሬ ነው። ይህም በ325 ዓ.ም ከተደረቀው የኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ እስከ 1520 ዓ.ም ድረስ ለ1,200 ዓመታት በቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ አገዛዝ ይወክላል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይታወቀውን ሥላሴ በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ቤተክርስቲያን ላይ መጫን ሰዎች ራሳቸውን መሪ አድርገው የእግዚአብሔርን ቃል እንደፈለጉት መተርጎማቸውን ያሳያል፤ ስለዚህ የቃሉ ብርሃን ደብዝዞ ሊጠፋ ችሏል። መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸው ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች እና ፖፕስ ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠሩዋት። እንደ “አንድ አምላክ በሦስት አካላት፣” “የመለኮት ሁለተኛው አካል፣” “በስብዕና እኩል ናቸው፣” “አንድ ባሕሪ” የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸው ቃላት ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እየራቁ በሄዱ ቁጥር አእምሮዋቸውን እያጨለመ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት ነው። ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቆ መሄድ ሕይወትን ማጣት ነው። ይህ እውነት በጥጃው ምስል አማካኝነት ተገልጧል።

በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለተጻፉ ሃሳቦች ተገልጠውልኛል በማለት መመካት ጀመረች።

የቤተክርስቲያን ዘመን ሙሉ ከግማሹ በላይ በዚህ መንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ ነው ያለቀው። ለጨለማው ዘመን ፖለቲካዊና ለሐይማኖታዊ ገዥ ማለትም ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አንንበረከከም ያሉ ከአሥር ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ሞቱ። ለጥጃው በሬ እስኪሆን ድረስ እንዲያድግ በቂ ጊዜ ነበረ። ነገር ግን በሬ ለሥራ እና ለመስዋእት የሚሆን እንስሳ ነው። በሬ በእድሜው መጨረሻ ሥጋ በጣም ስለሚያስፈልግ ይታረዳል። በበሬው የተወከለው የእግዚአብሔር መንፈስ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን መከራን እንድትታገስና ሰማዕት እንድትሆን አበርትቷታል።

እንደ ሰው ፊት የነበረው እንስሳ። ጀርመኒ ውስጥ በ1520 እንደተነሳው ማርቲን ሉተር የመሳሰሉ የተሃድሶ መሪዎች ሥራ ሳይጨመርበት በጸጋ ብቻ የመዳንን እውነት መልሰው ወደ ቤተክርስቲያን አመጡ። በ1750 አካባቢ እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የቅድስና እውነት እና የወንጌል ስርጭት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ፤ ይም በ1790 አካባቢ የተጀመረውን ታላቅ የወንጌል ስብከት ዘመን አስከተለ።

የሚበርረው ንሥር ሁለት ባሕርያት አሉት። ወደ ታላቅ ከፍታ መብረር ይችላል፤ በተጨማሪ ደግሞ አስደናቂ የማየት ችሎታ ስላለው ሌሎች ማየት የማይችሉትን ጥቃቅን ነገር አጥርቶ ያያል።

በ1906 አሜሪካ ውስጥ በአዙዛ መንገድ የተጀመረው ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ከመለኮታዊ ኃይል መገለጥ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለስ አደረገ። የንሥሩ ታላቅ ክንፎች በእግዚአብሔር መንፈስ ክልል ውስጥ ተዘርግተው ወደ ታላቅ ከፍታ ወጡ።

ከዚያ በኋላ በ1947 ዊልያም ብራንሐም አድማጮች በመጽሐፍ ቅዱው ውስጥ የተጻፉ ጥልቅ ሚስጥራትን መገለጥ መረዳት እንዲችሉ የሚያግዙ ስብከቶችን በካሴት መቅዳት ጀመረ፡- ለምሳሌ የእባቡ ዘር ምንድነው? አውሬው ማነው? የመጀመሪያው ሐጥያት ምንድነው? ሐጥያት የሰራችውን ሴትዮ ለመውገር ፈቃድ እየጠየቁት ሳለ ኢየሱስ ለምንድነው ሁለት ጊዜ ምድር ላይ የጻፈው? … እና ሌሎችም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን እነዚህን ምስጢራት ታውቃቸው ነበር ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ ይህ እውቀት ጠፋ። 1,200 ዓመታት በፈጀው የጨለማ ዘመን ውስጥ ስር የሰደዱ ስሕተቶች ለለውጥ ተሃድሶ መሪዎችና ለጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት መሪዎች እነዚህን እውነቶች ቆፍሮ ማግኘት አስቸጋሪ አድርጎባቸው ነበር።

ስለዚህ በስተመጨረሻ እግዚአብሔር የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት እንድትመለስ ይፈልጋል።

በዚህ መልኩ አራቱ እንስሳት የቤተክርስቲያንን የ2,000 ዓመታት ታሪክ ይተርካሉ።

ደግሞም በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሚገልጠው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ዙርያ አራቱ ወንጌሎች አሉ።

የሐዋርያት ሥራ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን በሥራ የተገለጠችበት መጽሐፍ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው ቤተክርስቲያን እንዲህ እንድትሆንለት ነው።

እያንዳንዱ ወንጌል ኢየሱስን ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት ወይም ኃይላት እንደ አንዱ አድርጎ ነው የሚገልጸው።

አራተኛው ወንጌል ዮሐንስ ነው።

ዮሐንስ ክርስቶስን እንደሚበርረው ንሥር አድርጎ ይገልጸዋል፤ ማለትም በመንፈሳዊ ከፍታ ላይ እንደሚበርረውና እጅግ አስደናቂ በሆነ ደረጃ አጥርቶ እንደሚያየው የእግዚአብሔር መንፈስ።

“በመጀመሪያ እግዚአብሔር … ” የሚለው ቃል የዘፍጥረት መጽሐፍ ታላቅ መንፈሳዊ መክፈቻ ነው።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥

መንፈስ አይታይም ደግሞም ቅርጽ የለውም። ስለዚህ የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን በሚታይ አካል ጠቅልሎ ማቅረብ አስፈለገው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ተጠቅልሎ ቀርቧል። እግዚአብሔር ቃሉን እንደ መንፈሳዊ አካል ተጠቅሞ በውስጡ በማደር የማይታየው የእግዚአብሔር መንፈስ በሰማያት ላሉ መላእክት ለሚባሉ መንፈሶች የሚታይ መሆን ችሏል።

የሕዋ ሦስቱ መስፈሪያዎች ርዝመት፣ ስፋት፣ እና ከፍታ ናቸው።

ጊዜ ደግሞ አራተኛው መስፈሪያ ነው ግን ጊዜ ደግሞ ከኋላ ወደ ፊት በአንድ አቅጣጫ ብቻ እየፈሰሰ የሚሄድ ስለሚመስል ለመረዳት ያስቸግረናል። አንዳንድ ጊዜ ስለ ጊዜ ቧምቧ እናወራለን። ስለዚህ ጊዜን በሦስቱ መስፈሪያዎች ማለትም በርዝመት፣ ስፋትና ከፍታ የተገነባውን ሕዋ የሚከብብ የማይታይ ግድግዳ አድርገን በምናባችን መሳል እንችላለን።

አምስተኛው መስፈሪያ ደግሞ የመልካም እና የክፉ መንፈሳዊ ክልል ነው። እኛ ሁል ጊዜ በእውነት እና በስሕተት መካከል ያለማቋረጥ ምርጫ እና ውሳኔ ስለምናደርግ የእኛ መንፈስ ከመንፈሳዊው ክልል ጋር ዘወትር የተገናኘ ነው።

ይህ ክልል ሰይጣንና አጋንንቱ የሚኖሩበት ስለሆነ የጠፉ ነፍሳትም ሲሞቱ ወደዚህ ክልል ነው የሚሄዱት።

ስድስተኛው ቀጠና ሰማይ ወይም ሰማየ ሰማያት ሲሆን ይህም መላእክት የሚኖሩበት ክልል ነው።

እኛ ዙርያችንን በከበበን አምስተኛ ቀጠና አማካኝነት ከስድስተኛው ሰማያዊ ቀጠና ተከልለን ነው የምንኖረው። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ ስንሞት እግዚአብሔር ለእኛ የጠፉ ሰዎችን ክልል (አምስተኛውን ቀጠና) አምልጠን ቀጥታ ወደ ሰማይ (ስወደ ድስተኛው ቀጠና) የምንገባበትን መንገድ ሊያሳየን እንዴት ወደ ምድር እንደወረደ ማስረዳት ነው።

ዮሐንስ 14፡6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

ሲኦልን የምናልፍበት ወይም የምናመልጥበት መንገድ ኢየሱስ ነው።

እግዚአብሔር ራሱ ደግሞ ከእነዚህ ቀጠናዎች ሁሉ ውጭ ነው፤ በሰው አእምሮ ሊታሰብ በማይችል የቀጠናዎች ሁሉ ቀጠና ውስጥ ይኖራል።

በመጀመሪያ መጀመሪያው መች እንደነበር ባናውቅም እግዚአብሔር ቃል ተናገረና ለራሱ መንፈስ የሆነ አካልን አዘጋጀ። ከዚያም ሰማያትን ፈጠረ፤ መላእክትም ሲፈጥራቸው ያዩት ዘንድ ራሱን በሰማያት ወስኖ ለመኖር ፈቀደ። ይህም እርሱ የሚኖርበት የቃል-አካል እግዚአብሔርን ለሰማያዊው ክልል ገለጠው። (አንተ የማይታይ መንፈስ ነህ። ሥጋህ መንፈስህን እንደ ልብስ ይሸፍናል። ስለዚህ ሥጋህ ከአንተ ጋር ይኖራል ደግሞም ሥጋህ ማለት አንተው ነህ። ነገር ግን አእምሮህ ወይም ሃሳብህ መንፈስ ስለሆነ ዋናው ተቆጣጣሪ እንመሆኑ ከሥጋህ ይበልጣል።)

ሮሜ 8፡27 ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
ኤፌሶን 4፡23 በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥

“መንፈስ” እና “አእምሮ” የሚሉትን ቃላት እየለዋወጥን መጠቀም እንችላለን። ስለዚህ መንፈስ እና አእምሮ አንድ ናቸው። “መንፈስ” ምን እንደሆነ አናውቅም ነገርን ግን ሥጋችንን በሕይወት የሚያኖር መንፈስ በውስጣችን መኖሩን እናውቃለን። መንፈስ እንደ አባት ነው፤ ሥጋ ደግሞ እንደ ልጅ ነው። መንፈስ ወይም አእምሮ ሥጋችንን ያዝዘዋል።

ዮሐንስ 1፡2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

ስለዚህ እግዚአብሔር እኛ ልናየው እንድንችል እኛ ወዳለንበት ዝቅ ብሎ መውረድ ይፈልጋል።

መጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ራሱን ቃል በሚባል መንፈስ-አካል ውስጥ መወሰን ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚኖረው ቃሉ ውስጥ ነው።

እግዚአብሔር በሰማይ ውስጥ ለመኖር ሲፈልግ የኖረው ራሱን እጅግ በጣም ገድቦ ነው። የእግዚአብሔር ታላቅነት በጭራሽ በአእምሮ ሊታወቅ አይችልም። ምንም ያህል ታላቅ አድርገን ብናስበው ካሰብነው በጣም ይበልጣል።

መዝሙር 113፡6 በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤

የማይታየው እግዚአብሔር ሃሳቡ አባት ወይም አብ ተብሎ ይጠራል። ይህም ሃሳቡ የሚገለጠው በቃሉ ሲሆን ቃሉም ልጅ ወይም ወልድ ይባላል።

ብዙውን ጊዜ ሃሳቦቻችን ልንገልጣቸው ከምንጠቀማቸው ቃላትም ይልቅ ጥልቅ ናቸው።

ዮሐንስ 1፡3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

እግዚአብሔር ፍጥረትን በንግግር ሊፈጥር ፈለገ። ስለዚህ ፍጥረትን የፈጠረበትን ቃል ለመናገር ቃል-አካሉን ተጠቀመ።

የመንፈስ-አካሉ ከንፈሮች ዓለምን ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ቃላትን ሁሉ ተናገረ።

በእነዚያ ቃላትም ውስጥ እጅግ ታላቅ ኃይል ነበረ ምክንያቱም ቃላቱ ኃይል ወይም ኤነርጂ እና ቁስ አካል ሆኑ። ፍጥረት የእኛ አእምሮ ሊገነዘብ ከሚችለው ያልፋል። በሳይንስ ውስጥ ከሁሉ በላይ ኃይለኛው ሕግ ጉልበትን ያለማባከን ሕግ ነው። ይህ ሕግ ጉልበት ወይም ኤነርጂ ሊፈጠርም ሊጠፋም አይችልም ይላል። አንድም ሳይንቲስት እስከዛሬ ኤነርጂ አልፈጠረም። ሳይንቲስቶች ከምንም ነገር አንድ ነገር መፍጠር አይችሉም። እግዚአብሔር ግን ከሳይንስ ሕግ በላይ መሆኑን አሳየ፤ ምክንያቱም ኤነርጂን በመለኮታዊ ኃይሉ ከምንም ነገር ፈጠረ። ይህን ማድረግ የቻለ ሌላ ማንም የለም። እግዚአብሔር ብቻ ነው መፍጠር የሚችለው። እግዚአብሔር የዓለምን ኤነርጂ እና ግኡዝ አካል ፈጥሮ ብቻ አልተወም፤ ይህ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ የሚንቀሳቀስበትን እጅግ በጣም የተራቀቁ የፊዚክስ ሕጎችንም ፈጠረ።

ሳይንቲስቶች ኤነርጂ መፍጠር አይችሉም። ደግሞም የሳይንስ ሕግጋት ከየት እንደመጡም አያውቁም። ኢየሱስ ማንኛውም ሰው በተፈጥሮአዊ ችሎታው ማድረግ የማይችላቸውን ነገሮች በቀላሉ ሲያደርግ በማሳየት የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ከፍ ካለ ቀጠና እንደመጣ ይገልጣል።

ሳይንቲስቶች ዓለም የተፈጠረው ቢግ ባንግ የተባለ ታላቅ ፍንዳታ በፈነዳ ጊዜ ነው ይላሉ (ይህ ፍንዳታ ምን እንደሆነ እና እንዴት ሊፈነዳ እንደቻለ አይታወቅም ድጋሚ ተከስቶም አያውቅም። እውነተኛ ሳይንስ የሚደገም መሆን አለበት።) ይህ ፍንዳታ በዓለማችን ውስጥ ያለውን ኤነርጂ ወይም ጉልበት አመንጭቷል ይላሉ። ይህ አባባል ግን ቴርሞዳይናሚክስ የተባለውን የፊዚክስን ዋነኛ ሕግ ይቃረናል።

ሕጉ ኤነርጂ ሊፈጠር አይችልም ይላል። ስለዚህ የቢግ ባንግ ቲዎሪ የሚጀምረው የፊዚክስን ዋነኛ የመጀመሪያ ሕግ በመቃረን ነው። ይህ ጥሩ አጀማመር አይደለም።

ሳይንቲስቶች ስለ ዓለም አፈጣጠር የሚያወሩዋቸውን የውሸት ወሬዎች አትስሟቸው። ያለባችሁ ችግር ከሰዎች የመፍታት አቅም ያለፈ ነው? ከሆነ ልታናግሩ የሚያስፈልጋችሁ ኢየሱስን ነው። ኢየሱስ ይህንን ከሰው አእምሮ በላይ ትልቅ የሆነ ዓለም ፈጥሯል። እኛ የሚገጥመን ማንኛውም ከአቅማችን በላይ የሆነ ችግር ከእርሱ የመፍጠር ችሎታ ጋር ሲወዳደር እጅግ በጣም ትንሽ በጣም ኢምንት ነው።

እኛ መልመድ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ችግሮቻችንን እንዴት አድርገን ለእርሱ ማቀበል እንዳለብን ማወቅ ብቻ ነው። ይህም እምነት ይባላል።

ዮሐንስ በወንጌሌ ውስጥ ኢየሱስን የፈጠረን አምላክ አድርጎ ነው የሚያቀርብልን፤ ስለዚህ የተፈጥሮ ሕግጋትን እና የማሕበረሰብ ሕጎችን ሁሉ አልፎ የመሄድ አቅም ስላለው የከበቡንን ያስፈራሩንን ሁኔታዎች ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ያሳየናል። ታላቁ የኢያሪኮ ግምብ አጥር ሲፈርስ አንድ ጎኑ ብቻ ተርፎ ነበር። ያልፈረሰበት ቦታ ጋለሞታይቱ ረዓብ ትኖርበት የነበረው ቦታ ነው። ሴትየዋ በሐጥያት ነበር የምትኖረው ግን በአይሁዳውያን አምላክ ልታምን ወሰነች። ያ ታላቅ ከተማ በአንድ ቀን በወደቀበትና በጠፋበት ትልቅ ሁከትና ግርግር ውስጥ የእርሷ ቤት ብቻ ሳይፈርስ መቅረቱ እምነት ምን ዓይነት ታላቅ ኃይል መሆኑን ይመሰክራል። ዮሐንስ እንደሚያሳየን እግዚአብሔር በኢያሪኮ ውድመት ውስጥ ከተፈጠረው ግርግር መካከል አንዲት ሴት እንዳትጠፋ እርሷን ብቻ ነጥሎ በማየት ማዳን የሚችል አስደናቂ እይታ ያለው ንሥር ነው። ይህን ዓይነቱን አምላክ ማወቅ ታላቅ ዋጋ አለው።

መዝሙር 91፡7 በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

የእግዚአብሔር ቃል ለረዓብ እምነት ምላሽ ሰጠ፤ ከጥፋትም ከለላ ሆናት።

ዮሐንስ 1፡4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።

በሰውነታችን ውስጥ ያለው የማይታይ መንፈስ ግን ከአእምሮዋችንም ይበልጣል፤ ከሃሳባችንም ይበልጣል። ይህ መንፈስ ሕይወትም ነው።

ሕይወት ምን እንደሆነ በትክክል አናውቅም ምክንያቱም ምንጩ በጣም ከፍ ካለ መንፈሳዊ ቀጠና ነው።

እግዚአብሔር በቃል-አካሉ ውስጥ የሚኖረው ሕይወት የሰዎችንና የሴቶችን አእምሮ ሊያበራ የሚችል ብቸኛ ጥሩ ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም እንደ ቤተሰብ ወይም እንደ ማሕበረሰብ እርስ በራሳቸው እየተደጋገፉና እይተረዳዱ ማለትም ለእግዚአብሔር ቃል ሙሉ በሙሉ እያታዘዙ መኖር እንዲችሉ ያስተምራቸዋል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡44 ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤
45 ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች በአስደናቂ ሁኔታ እርስ በራሳቸው ይረዳዱና ማካፈልን ይለማመዱ ነበር። ወደ እነርሱ አርአያነት ልንመለስ እንችል ይሆን?

ሕይወታቸውን እግዚአብሔር የተቆጣጠራቸው ሰዎች የሚኖሩት ለሌላው ሰው ጥቅም ብለው ነው። እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ያለው ፍቅር፣ ለግለሰብም ሆነ ለማሕበረሰብ ያለው ፍቅር እግዚአብሔር ልቦናቸውን ባበራላቸው ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይገለጣል።

ለዚህ ዓይነቱ ሕይወት ትልቁ ምሳሌ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ እግዚአብሔር እንዴት ከፍ ካለ መንፈሳዊ ቀጠና ከመንፈስ አካል ወርዶ በሰው አካል ውስጥ እንደኖረ አሳየ። በኢየሱስ የማይታየው እግዚአብሔር እኛ ሰዎች ወደምንኖርበት ዝቅ ያለ ሕይወት ወረደ።

ቆላስይስ 2፡8 … ክርስቶስ
9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ነው በኢየሱስ የኖረው። ኢየሱስ የተባለው ሰው፤ ከእግዚአብሔር አካል ውጭ የነበረው፤ እግዚአብሔር ሰው ቢሆን ኖሮ ምን ዓይነት ሕይወት ይኖር እንደነበር እራሱ እየኖረ አሳየን።

ዮሐንስ 1፡5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

ኢየሱስ መልካም ብለን ልንገልጽ ከምንችለው በላይ መልካም ነው። ሰዎች ከእርሱ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። “ጠላቶቻችሁን ውደዱ።” “ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ግራ ጉንጭህንም ስጠው።” “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው።”

ሆይ ሆይ! በእንግሊዝኛ “ሁሉም ለእኔ፤ ሁሉም አሁን ይሰጠኝ” የሚል ታዋቂ ዘፈን አለ። የዚህ ዘፈን ዘፋኝ በኤድስ ነው የሞተው። ሁሉን ማግኘቱ ምንም አልጠቀመውም።

በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ጠላቶችን በመጥላት ውስጣዊ ጨለማ ተውጠው፤ ለደረሰባቸው በደል የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እየፈለጉ፤ ያለልክ ስግብግብና ራስ ወዳድ እየሆኑ ይኖሩ ስለነበር የኢየሱስ ሕይወት በዓይናቸው ፊት ከሚያበራው ደማቅ ብርሃን ጋር አብረው መኖር አልቻሉም። እርሱ በአንድ አካባቢ መገኘቱ ብቻ የአካባቢውን ሰዎች ጉድለትና ሐጥያት ያጋልጥ ነበር። ሐጥያት የሞላበት ሰው አንድ ፍላጎት ብቻ ነው የነበረው፤ እርሱም ይህንን የሚረብሸውን ደማቅ መብራት ማጥፋት ነው፤ ምክንያቱም ጨለማ በብርሃን ፊት የመቆም አቅም የለውም። ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች ሁልጊዜ ሊከስሱት ይፈልጉ ነበር፤ ምክንያቱም የእርሱ ብርሃን የእነርሱን ሐጥያት ፍንትው አድርጎ ያሳይ ነበር። የሰነዘራቸው ጠንካራ ወቀሳዎች በሐይማኖት መሪዎች ላይ ብቻ ነበር። (ዛሬ ወደ ምድር ቢመጣ ገንዘብን ሁሉ ለራሳቸው የሚሰበስቡትን ራስ ወዳድ ፓስተሮቻችንን ምን እንደሚላቸው መገመት ትችላላችሁ?)

መሲኁ እንደ ተስፋ ቃሉ መጣ፤ ነገር ግን በዚያ ዘመን የነበሩ አይሁድ ሊቀበሉት አልወደዱም። ብርሃንና ጨለማ አብረው መኖር አልቻሉም። አንዳቸው ብቻ እንጂ ሁለቱም በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ መኖር አይችሉም። እድሉ ሲሰጣቸው ሙታንን ከሚያስነሳ ሕይወት ሰጭው ኢየሱስ ይልቅ ነፍሰ ገዳዩን በርባንን መረጡ።

ዮሐንስ 1፡6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤

እግዚአብሔር በኢየሱስ ብርሃን ፊት ሊቆም የሚችል አንድ ሰው ነበረው። እርሱም አእምሮን ከሚያረክሰው የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ተጽእሮ ርቆ በምድረበዳ ያደገ ነብይ ነበር። ይህ ነብይ ለራሳቸው ሐብትን በማከማቸት ምኞት ከተጠመዱ ራሳቸውን ከሚያጸድቁ ጨካኝና ስግብግብ ሐይማኖተኛ ሰዎች ርቆ ነው የኖረው። (የዛሬ ቤተክርስቲያኖች ሕዝቡን ምን ያህል ነው የሚያበላሹት?)

ዮሐንስ 1፡7 ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።

ዮሐንስ ለሕዝቡ ስለ ኢየሱስ ሊነግር መጣ። ዮሐንስ ኢየሱስን ከዚያ በፊት አይቶት አያውቅም። ነገር ግን በሰዎች መካከል ሰው ሆኖ የሚመላለሰውን መሲኁን ለይቶ ማወቅ የሚችለው ዮሕንስ ብቻ ነበር። ሰዎች መሲኁን ማግኘት ከፈለጉ ዮሐንስ በሚጠቁማቸው አቅጣጫ መመልከት ነበረባቸው። ሰዎች የራሳቸውን መሲህ ለራሳቸው መምረጥ አይችሉም። መሲኁ ከሐይማኖት ቡድኖቻቸው ሁሉ ውጭ ሲመጣ በጣም ደንግጠዋል። ደግሞም በጣም የሚያከብሩዋቸውን የሐይማኖት መሪዎቻቸውንም መሲኁ ሲወቅስባቸው እጥፍ ድርብ ደንግጠዋል።

ነገር ግን ከኢየሱስ በፊት ዮሐንስም የሐይማኖት መሪዎችን አውግዞ ስለነበረ አስቀድመው ማስጥንቀቂያ አግኝተዋል። ዮሐንስ የሐይማኖት መሪዎቻቸውን እፉኝቶች ብሏቸዋል። እፉኝቶች መርዛማ እባቦች ናቸው።

ስለዚህ ነብይ ሕዝቡን ወደ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ወይም ወደ መሪዎቻቸው አይደለም የሚጠቁማቸው። ነብይ ሕዝቡን ከሐይማኖታዊ አመለካከት እንዲወጡ ነው የሚጠቁማቸው።

ለመጀመሪያው ምጻቱ ዮሐንስ ኢየሱስን ከሰዎች መካከል እየተመላለሰ ሳለ ጠቁሞ አሳያቸው።

ከዳግም ምጻቱ በፊት ደግሞ ዊልያም ብራንሐም ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መካከል ሲመላለስ እያሳየ ለሕዝብ ጠቆመ፤ በዚህም የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት እንድናስተውል ረድቶናል።

ዮሐንስ 1፡8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።

ዮሐንስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እየጠቀሰና በመለኮታዊ እቅድ ውስጥ ለኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ጠራጊ መሆኑን ድርሻውን በማወቅ በተንቀሳቀሰ ሰዓት የሚያበራ የእውነት ብርሃን ነበረ። አጭርና ኃይለኛ በሆነው አገልግሎቱ በሕዝብ ፊት በድምቀት አበራ። ሰዎች ግን ታላቅ ነብይ ሲያዩ ነብዩን እንደ ጀግና የመከተል ዝንባሌ አላቸው፤ ልክ ናቡከደነጾር ዳንኤልን በአምላኩ ስም ብልጣሶር ብሎ እንደጠራው።

ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌል ለኢየሱስ መምጣት መንገድ ሲጠርግ የነበረው ነብይ ብርሃን እንዳልሆነ በግልጽ ጠቅሶ ይናገራል።

ኢየሱስ ብቻ ነው ብርሃን። ኢየሱስ ቃሉ ነው። ማንም ነብይ ዛሬ ቢነሳ ቃሉን ሊተካ አይችልም። የየትኛውም ነብይ ንግግር ከእግዚአብሔር ቃል በላይ ሊሆን አይችልም። (የሜሴጅ ፓስተሮች ልብ በሉ።)

ዮሐንስ 1፡9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።

ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው እውነተኛው ብርሃን። የእግዚአብሔር ቃል ለግለሰቦች ለግል ሕይወታቸው (የእኔነታቸው ትንሽዬ ኩሬ ወይም የሕይወታቸው ትንሽዬ ክፍል) ደግሞም ለሚኖሩበት የቤተክርስቲያን ዘመን የሚሆን ምሪት ይሰጣቸዋል (በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ እንዲሁም በ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደ ታላቅ የሕይወት ወንዝ የሚፈስሰው የእግዚአብሔር ፈቃድ)

ኢየሱስን የግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል። ስትቀበለው እርሱ ሊገለጥበት የመረጠው እቃ ሆነሃል ማለት ነው። በቅድስና ኑር። ይህም እርሱ እያነጻህ ነው ማለት ነው። አገልግል፤ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀትም ተቀበል። ይህ ደግሞ እርሱ በአንተ ውስጥ ይሞላል ማለት ነው። ከዚያ እግዚአብሔር እንዲጠቀምብህ ዝግጁ ትሆናለህ። ስለዚህ አሁን ከራስህ ትንሽ ኩሬ የምታህል ፈቃድህ ፍላቶችህ ወጥተህ በእግዚአብሔር መመራት ትችላለህ።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የግል ፈቃድህን እንዲቆጣጠር ከፈቀድህለት በታላቅ ፍጥነት እንደ ወንዝ በሚፈስሰው ፍጹም ፈቃዱ ውስጥ አስገብቶህ ሊጠቀምብህ ይችላል። አንድ ምሳሌ ሊሆነን የሚችል ሰው የቀሬናው ስምኦን ነው፤ ያለፈቃዱ ተገድዶ የኢየሱስን መስቀል በመሸከሙ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ተመላልሷል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛ ብዙ ጊዜ ግራ የሚያጋባ ይሆንብናል ምክንያቱም የራሳችንን ምኞትና ምቾት፣ የራሳችንን ሰላምና ትርፍ ከምንፈልግበት የግል ፈቃዳችን በጣም የተለየ ነው።

ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ ተደላድሎ የተቀመጠውን ሰው ተደላድሎ እንዳይቀመጥ ያደርገዋል። ያልተጠበቀ ነገር እንድንጠብቅ ያስለምደናል። ቀድሞ የገባብንን እውቀት ማስወጣትና አዲስ እውቀት ማስገባት አለብን። ለራሳችን እቅድ ያወጣንበትን የሕይወት ፕሮግራም ስንተው የእግዚአብሔርን እቅድ እናገኛለን። ወደላይ የመውጫ መንገዱ ወደ ታች መውረድ ነው። የሰዎች አለመከናወን ለመንፈሳዊ ስኬት ዘር ነው። የእግዚአብሔር መንገድ ከእኛ መንገድ በጣም ይለያል። እኛ ሌሎችን እንድናገለግል የተመረጥን እቃ ነን እንጂ ራሳችንን የምናገለግል አይደለንም።

ዮሐንስ 1፡10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።

የማይታየው እግዚአብሔር በኢየሱስ ሥጋ ውስጥ በኖረ ጊዜ ወደ ሥጋዊ ፍጥረቶቹ ደረጃ ዝቅ ብሎ ወረደ። ነገር ግን ትሁት ሆኖ ነው የመጣው። ማንም ከማያውቃት አንዲት ድንግል የሚሸት ቦታ ውስጥ ተወለደ። እርሷም ከማግባቷ በፊት በማርገዟ ስሟ ጠፍቷል። ስለዚህ ኢየሱስም በብዙዎች ዘንድ ስሙ ጠፍቷል። ናዝሬት ደግሞ በምግባረ ብልሹነት የምትታወቅ ታናሽ ከተማ ናት።

ዮሐንስ 1፡47 ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው።

ዮሴፍ በሰዎች ዘንድ ብዙም የማይታወቅ ምስኪን አናጺ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ታዋቂ ሊያደርገው የሚችል አንዳችም ተፈጥሮአዊ ነገር ይዞ አልመጣም። ስለዚህ ዓለም ትኩረት አልሰጠውም፤ ምከንያቱም ሰዎች ሁሉ ፈጣሪን የሚያስቡት በብዙ መላእክት ታጅቦ የሚመጣ ጀግና አድርገው ነው።

ዮሐንስ 1፡11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።

የአብራሐም ልጆች ወደሆኑት ወደ አይሁዶች መጣ፤ እነርሱም እግዚአብሔር ለአብራሐም ቃል በገባለት በእሥራኤል ምድር ይኖሩ ነበር። መጣና ስለ መሲኁ የተነገሩ ትንቢቶችን ሁሉ ፈጸማቸው። ነገር ግን በትሕትና ዝቅ ብሎ ነው የመጣው፤ አቧራ በነካ ነጠላ ጫማ እየሄደ በአሕያ ላይ ተቀምጦ ነው የመጣው። እንዲህ ዓይነቱን ሰው ማን ዞር ብሎ ያየዋል?

የሮማ ገዥዎች ከብረት ለበስ ወታደሮቻቸው መካከል በኃይለኛ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ነው የሚሄዱት። ስለዚህ እነርሱ የሰውን ዓይን ሁሉ ይስባሉ።

ዮሐንስ 1፡12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

እግዚአብሔር ከአይሁዳውያን በላይ በሰማይ በሚኖርበት ጊዜ ያሕዌ ተብሎ ነበር የሚታወቀው (በብሉይ ኪዳን ውስጥ ባሕርያቱን የሚገልጡ ሌሎች ስሞችም አሉት)።

አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ ሆኖ በአይሁድ መካከል ሊኖር ወረደ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር። አማኑኤል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በሰው ስም ተሰየመና ኢየሱስ ክርስቶስ ተባለ።

ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር በኖረበት የሰው አካል ውስጥ ለሐጥያታችን ማስተሰርያ ይሆን ዘንድ መፍሰስ የሚችል ደም በደም ስሮቹ ውስጥ ኖረው። ስለዚህ ሊያድነን የሚችለው ኢየሱስ የተባለው ሰብዓዊ ስሙ ብቻ ነው። እግዚአብሔርም ከዚያ በኋላ እንደገና ራሱን ያህዌ ብሎ አልጠራም። በብሉይ ኪዳን ውስጥ በጣም ታዋቂ የሆነው ያህዌ የሚለው ስም አንድም ጊዜ አዲስ ኪዳን ውስጥ የለም።

እግዚአብሔር ሰው ሆነ። የሥጋ ዘመድ ቤዛ ሆነ። ኢየሱስ የሚለው ስም ሰውን የሚያድን እና በደሙ ከሐጥያት የሚያነጻ ብቸኛ ስም ነው።

እግዚአብሔር ከሰው ጋር የተዛመደበት መንገድ ጸጋው ነው፤ ጸጋ ማለት ለሰዎች የማይገባ እንዲሁም በሥራ ወይም ገንዘብ ሊገዛ የማይችል መልካም ነገር ነው። ጸጋ በነጻ ይሰጣል፤ በምስጋና እና በእምነት ብቻ ልቀበለው እንችላለን።

ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው ሕብረት የሚመሰረተው በእምነት ብቻ ነው፤ ይህም እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ማድረግ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እንደሚያደርግ በማመን ነው። ራሳችንን ማዳን የምንችልበት መንገድ የለም። በእምነት ብቻ ኢየሱስ እንደሚያድነን እናምናለን እንጂ።

ከሐጥያታቸው ንሰሃ የሚገቡና ኢየሱስ ሐጥያትን ለማስተስረይ የከፈለውን ታላቅ መስዋእት በነጻ የሚቀበሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ኋይል ያገኛሉ። ደሙ ሐጥያታችንን አጥቦ ያነጻል፤ በደሙ ውስጥ ያለው ሕይወትም እርሱም ታላቁ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ከመንፈስ ዳግመኛ ስንወለድ በእኛ ውስጥ መኖሪያውን ያደርጋል። የእርሱ ሕይወት በእኛ ውስጥ መኖሩ ነው አዲስ ፍጥረቶች የሚያደርገን።

ሥጋችን ሳይሆን አዲሱ አእምሮዋችን ነው በእግዚአብሔር መልክ የሚፈጠረው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ሥጋ ያለው ሰው ሳይሆን መንፈስ ነው።

ዮሐንስ 1፡13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

ተፈጥሮአዊ ደም በወንድ ብልት ውስጥ በብዛት ሲያልፍ ብልትን እንዲቆም ስለሚያደርገው ወደ ወሲባዊ ድርጊት ያመራል። በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት የሴት የድንግልና መጋረጃ ይቀደዳል። በወንድ ዘር ውስጥ ያለው ሕይወት በሴት ማሕጸን ውስጥ ባለው የሥጋ አካል ይሸፈናል። ይህ የሰው ሕይወት ወይም ጽንስ ከተቀደደው መጋረጃ ኋላ ሆኖ ያድጋል። ስለዚህ የሞት ሕይወት እንዲፈጠር ያደርጋል።

ከሴት የተወለደ ሰው ለአንድ ሺ ዓመት ኖሮ አያውቅም።

ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

እግዚአብሔር ሕይወትን በምድር ላይ በፈጠረበት በሦስተኛው ቀን የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ መልካም ናቸው ተብለው ነበር።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
13 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን።

መብላት የተከለከለ አንድም የተፈጥሮ ፍሬ አልነበረም።

ስለዚህ “አትብሉ” የተባለው ፍሬ ምንድነው?

ወሲባዊ ግንኙት በቀጥታ ሲተረጎም “ሥጋዊ እውቀት” ነው።

ሰዎች ከሚያደርጉዋቸው ነገሮች ውስጥ መልካምም ክፉም በመሆን የሚታወቀብ ብቸኛው ወሲብ ነው። ከጋብቻ ውጭ ከሰርግ ቀን በፊትም እንኳ ክፉ ነው። ከሰርግ በኋላ ግን ወዲያው መልካም ይሆናል።

ከተቀደደው የሴት መጋረጃ በስተኋላ ተጸንሰን ስለምንወለድ የሚሞት ሕይወት ይዘን እንወለዳለን። የዚህም ማስረጃው ሆዳችን ላይ እምብርት የምንለው ጠባሳ ነው። እርሱም በሰውነታችን ላይ ያለው የአውሬው ምልክት ነው። ይህም ማለት መጨረሻችን መቃብር ነው ማለት ነው፤ መቃብርም በምድር ፊት ላይ ጠባሳ ነው።

በአእምሮዋችን ላይ ያለው የአውሬው ምልክት ከኢየሱስ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ዞር እንድንልና ወደ እሳት ባሕር እንድንገባ ያደርገናል።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

አንድ ሰው እንኳ 1,000 ዓመት ኖሮ አያውቅም። ከሰዎች ሁሉ በእድሜ ርዝማኔ የሚበልጠው ማቱሳላ 969 ዓመቱ ላይ ሞቷል።
ስለዚህ ከወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ ሰው ሁሉ ይሞታል።

ነገር ግን ዮሐንስ ደግሞ የሐጥያትንና የሞትን ክብረወሰን ስብሮ ያለፈውን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ የሆነውን ኢየሱስን ያስተዋውቀናል።

ዮሐንስ 1፡13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

ዘላለማዊ ሕይወት በተለየ መንገድ ነው የመጣው። የኢየሱስ ሥጋ የተጸነሰው ከማርያም መጋረጃ ጀርባ መጋረጃው ሳይቀደድ ነው። ኢየሱስ ከወሲብ አይደለም የተጸነሰው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ ያስቀመጠ አካል የጽንሱ አባት ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የእግዚአብሔር ሙሉ ማንነት በሙሉ ሰው በሆነው በኢየሱስ ሥጋ ውስጥ አድሯል።

ስለዚህ ከአዳም ውድቀት ወዲህ የመጀመሪያው ሐጥያት የሌለበት ሰው ኢየሱስ ሐጥያት ስላልነበረበት መሞት አያስፈልገውም ነበር።

ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።

ሁሉን የፈጠረው የእግዚአብሔር ቃል አሁን ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሚሆን የሰው ሥጋ ፈጠረ።

እግዚአብሔር ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ። እርሱ ብቸኛው ፍጹም ሰው ሆነ። በኢየሱስ ውስጥ ያደረውን የማይታየውን አምላክ ልናየው አንችልም፤ ነገር ግን ከቃሎቹ እና ከሥራዎቹ ተነስተን ምን ዓይነት መንፈስ በውስጡ እንዳደረ ማየት እንችላለን።

እርሱም ሰዎች ንሰሃ እንዲገቡ ያበረታታቸው ነበር። በሽተኞችን ፈወሰ። ሙታንን አስነሳ። ተዓምራትን አደረገ። እንዲህ ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ደግሞም ለሰዎች በልባቸው ውስጥ ያለው ሃሳብም ነገራቸው። ይህ የመሲኁ ምልክት ነው።

2ኛ ዜና 6፡30-31 … በማደሪያህ በሰማይ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው።

ዮሐንስ 1፡15 ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።

መጥምቁ ዮሐንስ አስደናቂ ነብይ ነበረ። እንደ መንፈሳዊ ጠራቢ የሐይማኖት መሪዎች ስለ ራሳቸው የነበራቸውን ግምት እየጠረበ ጣለ፤ የዘመኑን የሐይማኖት ቡድኖችና እውነትን እናስተምራችኋለን ይሉ የነበሩ “ቤተክርስቲያኖቻቸውን” እንዲሁም የሐይማት መሪዎቻቸውን እንደ መዶሻ አደቀቃቸው። መጥምቁ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ብቻ ጠቆመ እንጂ ወደየትኛውም የሐይማኖት ቡድን ወይም የሐይማኖት መሪ አልጠቆመም። (መጥምቁ ዮሐንስ የዛሬ ቤተክርስቲያን መሪዎችን ቢያናግራቸው ምን እንደሚላቸው ገምቱ። “እፉኝቶች” ሲል አይሰማችሁም? እናንተ ከምላሳችሁ ስር የእባብ መርዝ ያላቸሁ ሲል አይሰማችሁም?)

በዚያ ዘመን ታላቅ ነብይ ሆኖ እንደመነሳቱ ከሌሎች ሰዎች አንጻር እራሱን እና አገልግሎቱን ታላቅ በማድረግ መታበይ ይችል ነበር።

ነገር ግን አስገራሚ ምሳሌ ትቶልን አለፈ። ከሌሎች ሰዎች እንዴት እርሱ እንደሚበልጥ በማሳየት ፈንታ (ደግሞም ይበልጥ ነበር) ራሱን ከኢየሱስ ጋር በማስተያየት እጅግ በጣም ከኢየሱስ እንደሚያንስ ተናገረ። ዓላማው በሙሉ ለኢየሱስ መንገድን መጥረግ ነበረ። ኢየሱስን መጠቆምና ለሕዝብ መግለጥ ነበረ ሥራው፤ ከዚያ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስ ሰዎች ኢየሱስን መከተል እንዲችሉ ከመንገድ ዘወር ማለት ነበረበት።

(ወንድም ብራንሐምን ከፍ ከፍ የምታደርጉ የሜሴጅ ፓስተሮች ልብ በሉ።)

ነብዩ ዮሐንስ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክት ነበር። መዳረሻው ኢየሱስ ነበር። እስከ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክት ድረስ ብቻ ብትሄዱ ወደ መንገዳችሁ ፍጻሜ አትደርሱም።

ነብይ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት በከፊል ብቻ ይፈጽማል። ኢየሱስ ግን መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ በ30 ዓ.ም አካባቢ ተገለጠና ለሥድስት ወራት እየገነነ ቆየ። ሐዋርያው ዮሐንስ ግን ኢየሱስ ከመጀመሪያው ከጥንትም በፊት እንደነበረ ጻፈ። ስለዚህ ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስን በሁሉ ነገር ሙሉ በሙሉ ይበልጠዋል። ወደ መጥምቁ ዮሐንስ የሚጠቁሙ ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ። ነገር ግን እንዴት መተርጎም እንዳለብን ከተረዳን መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ወደ ኢየሱስ ይጠቁማል።

ኢየሱስ ከየትኛውም አስደናቂ ነብይ እጅግ አብዝቶ ይበልጣል። (የሜሴጅ አማኞች እባካችሁ ልብ ብላችሁ አድምጡ።)

ዮሐንስ 1፡16 እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤

ኢየሱስ በሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ሰው የተገለጠው እና ለሕዝብ የተዋወቀው በመጥምቁ ዮሐንስ አማካኝነት ነው። ከዚያም ሐዋርያው ዮሐንስ ታላቁን መንገድ ጠራጊ መጥምቁ ዮሐንስን መቀበል እንደማያስፈልገን ይነግረናል። የተቀበልነው እርሱ የገለጠውን ኢየሱስን ነው። የኢየሱስ ሙላት በአደባባይ ሲገለጥ መጥምቁ ዮሐንስ ሥፍራ ለቅቆ ይሄዳል።

ዮሐንስ የሚያወራለትን ቤዛነት እውን ሊያደርግ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።

ዮሐንስ ንሰሃ ግቡ ብሎ ሊነግረን ይችላል። ኢየሱስ ግን ንሰሃችን ፍሬያማ እንዲሆን ያደርጋል። ኢየሱስ ሞተ፤ ሐጥያታችንን ለማስወገድ ስለ እኛ ደሙን አፈሰሰ። ከዚያም የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን ለመኖር ይመጣል። የክርስቶስ ልብ በውስጣችን ሲኖር ስለ ዓለም እና በውስጧ ስላሉ ተግዳሮቶች አዲስ መረዳት እናገኛለን። የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን ሲኖር ጦርነታችንን እርሱ ይዋጋልናል።

ዮሐንስ ይህንን ሁሉ ሊያወራ ይችላል። ነገር ግን መከራን ሊቀበልና ወደ ፍጻሜ ሊያመጣ የሚችለው ኢየሱስ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ እኛ ያመጣው ጸጋ የሞገለጠው ኢየሱስ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ ነው። ጸጋውም ድርብ ሆኖ ነው የሚመጣው ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻ ነው ለወንጌሉ እቅድ ምላሽ የምንሰጥበትን እምነት ሊሰጠን የሚችለው።

ስለዚህ ስለ እኛ የሞተልንና አዲስ ሕይወት ሊሰጠን ወደ ልባችን የሚገባው ኢየሱስ ስለ እርሱ ሊነግረንና እርሱን ሊያስተዋውቀን ብቻ ከሚችለው ነብይ ከዮሐንስ እጅግ አብዝቶ ይበልጣል። ኢየሱስ ብቻ ነው ዳግም ልደትንና መዳንን እውን ሊያደርግልን የሚችለው። ስለዚህ ኢየሱስ አንደኛ ነው። ዮሐንስም ሆነ ሌላ ማንም ነብይ ከኢየሱስ ጋር ሊወዳደር አይችልም።

ዮሐንስ 1፡16-17 …ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።

ሙሴ የሕጉ ታላቅ ነብይ ነበረ። ሙሴ በአክብሮት የምናየው ታላቅ ሰው ነው። ነገር ግን ሙሴም እራሱ አሥርቱ ትዕዛዛት የተጻፉባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ወርውሮ በመስበሩ አሥርቱን ትዕዛዛት በመተላለፍ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። ይህ ድርጊቱ የሰውን ማንነት ይገልጣል። ሰው ደካማ እና በራሱ ፈቃድ ታውሮ የሚንቀሳቀስ ፍጡር ነው፤ ነገር ግን በሌላ ጊዜ ደግሞ በእግዚአብሔር ፍጸም ፈቃድ ውስጥ ሲመላለስ ቀይ ባሕርን እንደመክፈል የመሰሉ ድንቅ ሥራዎችንም ይሰራል።

ሐዋርያው ዮሐንስ ትልቅ ውሳኔ የሚጠይቅ ቦታ ላይ ይመጣል። እግዚአብሔን ያስተዋወቀን፣ አምስቱን ታላላቅ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፈውን ታላቅ ነብይ ይጠቅሳል። ይህም ነብይ ወደ እግዚአብሔርን ይመራን ዘንድ ሕጉን የተቀበለልን ሰው ነው። ነገር ግን የሰው ድካም ሕጉም መጠበቅ የማይቻል እንዲሆን አደረገ። ሥልጣን ፈላጊ ራስ ወዳድ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ነብዩ ሙሴ ለጻፋቸው ሕጎች የራሳቸውን ትርጓሜ አበጁ።

ማቴዎስ 23፡2 ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።

የሐይማኖት መሪዎች ሥልጣናቸውን (ወንበር ሥልጣንን ይወክላል) ያገኙት “ነብዩ ሙሴ እንዳለው…” “ነብዩ እንዳለው…” “ነብዩ እንዳለው …” እያሉ በመናገር ነው።

ይህ ምን ያስታውሳችኋል?

ከዚያም የሐይማኖት መሪዎች የሙሴን ንግግር ጥቅሶች ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ለመግፋትና ለመቃወም ተጠቀሙ።
ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ዛሬ የተመሰረቱት በሰው ንግግር ጥቅሶች ነው፤ ነገር ግን የተጻፈው ቃል ስለገፉት ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል።

ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ ግልጽ የሆነ መስመር ያሰምራል። ነብዩ ሙሴ ሕጉን አመጣ ነገር ግን የቃሉ (የኢየሱስ) ጸጋ እና እውነት ከየትኛውም ነብይ እጅግ ይበልጣሉ። እንደ ሙሴ ያሉ ነብያት የራሳቸው ውሱንነት አላቸው የራሳቸው ስሕተትም አላቸው ለእግዚአብሔር ጸጋ እና ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ግን አንዳችም ውሱንነት የላቸውም።

ሕጉ ትዕዛዛቱ ለሰዎች እጅግ ከባድ ከመሆናቸው የተነሳ ሰውን ኩነኔ ውስጥ ለማስገባት ብቻ ነበር የሚያገለግለው። ስለዚህ ኢየሱስ ከሕጉ አብዝቶ የሚበልጠውን የጸጋ ወንጌል ይዞ መጣ። ሕጉ ይኮንናል፤ ጸጋው ግን ያድናል። ሕጉ ሐጥያት የመስራት ፍላጎትን አያስወግድም።

ጸጋው ዳግመኛ እንደገና እንድንወለድ በማድረግ ልባችንን ይለውጠውና ሐጥያት የመስራት ፍላጎታችንን ያስወግደዋል።

ኢየሱስ አሁንም ከብሉይ ኪዳን ነብያት ሁሉ ታለቅ ነብይ ከሆነው ከሙሴ በላይ ከፍ በማለት እጅግ በልጦ ተገኝቷል። ሙሴ ግን የእረኛ በትር ብቻ በመያዝ በጊዜው የዓለም ኃያል የነበረውን ጦር ሰራዊት ድምጥማጡን ያጠፋ ሰው ነው። ይህም በጣም አስደናቂ ነው።
ቢሆንም ግን ሌላ ደግሞ ተለቅ ያለ ጠላት ማለትም ሞት ሙሴን አሸነፈው።

ኢየሱስ ግን መስቀል እና የእሾህ አኪሊል ብቻ እንደ ትጥቅ ይዞ ሰብዓዊ ድካም ውስጥ ሆኖ በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ታላቅ የሰይጣንንና የአጋንንት ሰራዊትን ብትንትናቸውን አወጣ። ሰይጣን የኢየሱስን ኃይል መቋቋም ስላልቻል በፍርሃት ሮጦ ተደበቀ። ከዚያም ኢየሱስ ሐጥያትን፣ ሞትን፣ ሲኦልን እና መቃብን ሁሉ ድል ነስቶ እሁድ ጠዋት ከሙታን ተነሳ። ይህም ድል የሙሴን ታላቅ ድል የሚውጥ ነው።

ሙሴን አሸንፎት የነበረውን ሞት ኢየሱስ አሸነፈው። ሙሴ እና የኤርትራ ባሕር አሁን የታሪክ አካል ናቸው። ኢየሱስ እና መስቀሉ ግን የታሪክ አካል ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም እርሱ ያደረገልንን በእምነት የምንቀበልበት ጸጋ ቢኖረን ዛሬም ሕይወታችንን መለወጥ የሚችል ኃይል ነው እንጂ። ምክንያቱም የክርስቶስ ጸጋ በነጻ መዳንን ይሰጠናል። ይህ ትክክለኛ እውነት ነው።

ዮሐንስ 1፡18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።

እኛ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያለብን ችግር እግዚአብሔርን ማየት አለመቻላችን ነው። ሰዎች እግዚአብሔርን ማየት አይችሉም፤ እግዚአብሔር ደግሞ መንፈስ ነው።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥

ስለዚህ እግዚአብሔር አብ ዘላለማዊው መንፈስ ሰው በሆነው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ አካል ውስጥ አደረ። አንድያ ልጅ ማለት እግዚአብሔር የመለኮት ሙላቱን ሊያኖር የሚችልበት አንድ ሰው ብቻ አዘጋጀ ማለት ነው። እንደ ኢየሱስ ያለ ሌላ ሰው አይኖርም።

ዮሐንስ 1፡19 አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ እሥራኤልን ልክ እንደ መንፈሳዊ አውሎ ነፋስ መታት። ሐይማኖታዊ ተቋማትንና የሐይማኖት መሪዎችን አወገዘ።

(የቤተክርስቲያን መሪዎች ልብ በሉ።) ስለሚመጣው መሲኅ በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። አይሁዶች ተደናገጡ። እርሱም አድማጮቹን የሚያስገርም ኃይለኝነት ይታይበት ነበር። በሥልጣን ይናገር ነበር። በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትንም አልፈለገም። ስለዚህ ማንነቱን የሚጠይቁ ተወካዮች ተላኩበት።

ዮሐንስ 1፡20 መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።

ክርስቶስ ማለት “የተቀባው” ማለት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ከእናቱ ማሕጸን ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ መቀባቱን መስክሯል። ይህን ሊክድ አልቻለም።

ነገር ግን ወዲያው የተቀባው ማለትም ክርስቶስ እርሱ አለመሆኑን አብራርቷል።

ከኢየሱስ ጋር ምንም አይነት እኩልነት እንዳለው ማስመሰል እንደሌለበት ተረድቷል።

በዮሐንስ ዓይን ኢየሱስ ሁልጊዜም ቁጥር አንድ ወይም አንደኛ ነው።

ዮሐንስ 1፡21 እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።

ቀጥሎ ደግሞ የመጣበት ጥያቄ ፈታኝ ነበር፤ ይህም ጥያቄ ዮሐንስ ስለ ራሱ አገልግሎት በትክክል ማወቁን ያሳያል።

“ኤልያስ ነህን?” ዮሐንስ “አይደለሁም” ብሎ መለሰ።

ኢየሱስ ግን ዮሐንስ ኤልያስ መሆኑን ተናግሯል።

ማቴዎስ 17፡12 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።
13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

ዮሐንስ ኤልያስ መሆኑን ደግሞም አለመሆኑን እንዴት ነው ልናብራራ የምንችለው?

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

ኤልያስ ሁለት ነገሮችን ማድረግ አለበት። አባቶችን ወደ ልጆች እንዲሁም ልጆችን ወደ አባቶች መመለስ አለበት።

ከዚህ ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስ ግማሹን ብቻ ነው ያደረገው።

ሉቃስ 1፡17 እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።

በሕጉ ልማድ ውስጥ ታስረው የቀሩት አመጸኞቹ የአይሁድ ሕዝብ አባቶች በመጥምቁ ዮሐንስ አማካኝነት ኢየሱስን እና የአዲስ ኪዳን እውነትን ወደ ያዙት ደቀመዛሙርቱን ወደሚከተሉት ወደ ልጆቻቸው አዲስ ትውልድ መመለስ ነበረባቸው።

ለዚህ ነው ኢየሱስ ዮሐንስ ኤልያስ ነው ብሎ የተናገረው።

የዮሐንስ አገልግሎት ግን ሁለተኛ ምዕራፍ ነበረው። ደቀመዛሙርቱ የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች ይሆናሉ። ከዚያ በኋላ ከ325 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1520 ዓ.ም ድረስ ሰዎች በጨለማው ዘመን ውስጥ ከእውነት መስመር የሚስቱበት ጊዜ ይመጣል። ከዚያም ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን ይመልሰዋል። እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ በ1750 ዓ.ም ጆን ዌስሌ ቅድስና እና የወንጌል አገልግሎትን ወደ ቤተክርስቲያን ይመልሳል፤ ይህም ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። ከዚያም በ1906 የጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ እንዲመጣ አድርጓል።

ስለዚህ አሁን የቀረው የተሃድሶ መሪዎች በሙሉ ፈልገው ማግኘት ያልቻሉትን ነገር ግን የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምታውቃቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መልሶ የሚያመጣ የመጨረሻው ዘመን ኤልያስ ነው። እኛ ሐዋርያዊ አባቶች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ወደ ጻፉት እውነት መመለስ ያብን የመጨረሻው ዘመን ልጆች ነን።

ዊልያም ብራንሐም ይህንኑ ሊያደርግ የተላከ የመጨረሻ ዘመን ኤልያስ ነው።

ለዚህ ነው ዮሐንስ ሲጠይቁት በሚልክያስ ትንቢት ውስጥ ይመጣል የተባለለት ኤልያስ አይደለሁም ያለው፤ ምክንያቱም ያ ትንቢት በ2,000 ዓመታት የሚራራቁ ሁለት አገልግሎቶችን ነበር የሚገልጸው። እነዚህን ሁለቱንም አገልግሎቶች ብቻውን ሊፈጽም የሚችል ነብይ የለም።

ደግሞም እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነብይም በትንቢት ተነግሮለት ነበር።

አይሁድ “ነብዩ ነህን?” ሲሉም ጠየቁት።

ዘዳግም 18፡15-16 … አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።

ሙሴ ስለ ኢየሱስ ትንቢት መናገሩ ነበር። ይህ ትንቢት አይሁድ ኢየሱስን መስማት እንዳለባቸው የሚናገር ነው ምክንያቱም ኢየሱስ ሕጉን ወደ ጸጋ ይለውጠዋል። ሙሴ የሕጉ ታላቅ ነብይ ነበር። ማንም ተቀናቃኝ የሌለው የአይሁድ መሪ ነበር። ከዚያም ኢየሱስ ደግሞ ተቀናቃኝ የሌለው የጸጋ መሪ ሆኖ ይገለጣል። የሐጥያታችንን ዋጋ በመክፈል ወደ ሰማይ የሚያስገባው ብቸኛው በር ይሆናል።

ሙሴ የመጀመሪያውን የአይሁድ ፍልሰት ከግብጽ እየመራ እንዳስወጣ ሁሉ ኢየሱስም ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ፍልሰት ከይሁዲነት እየመራ ያስወጣል።

አስደናቂው የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት የአይሁድ ሕዝብ የለውጥ ጊዜ መቅረቡን እንዲያስተውሉ ረድቷቸዋል። ስለዚህ ዮሐንስ ማን መሆኑን እና ምን እያደረገ እንደነበር በጣም አሳስቧቸው አጥብቀው ጠይቀውታል።

ዮሐንስ የተበረዘውን ነገር ግን ለእነርሱ የተመቻቸውን “የቤተክርስቲያን” ሥርዓት እየሰባበረባቸው ነበር። እነርሱ ደግሞ ዮሐንስ ከታዋቂ የሐይማኖት ተቋሞቻቸው ለምሳሌ ከፈሪሳውያን ወይም ከሰዱቃውያን ወይም ከሄሮድስ ወገኖች፣ ወይም ከካሕናት ወይም በምድረበዳ ከሚቀመጡት ከኤሰኖች ወይም ከቀናኢዎች ወገን አለመምጣቱ አስጨንቋቸዋል። በእነርሱ አስተሳሰብ እግዚአብሔር ከታዋቂ ሐይማኖታዊ ተቋሞች ውጭ ሊሰራ አይችልም። እነርሱ የጠበቁት እግዚአብሔር መሲኁን ለማስተዋወቅ ከሚያውቋቸው ሐይማኖታዊ ተቋሞች ውስጥ አንድ ሐይማኖታዊ መሪ እንደሚልክ ነበር።

(ዛሬ በዓለም ላይ 45,000 ልዩ ልዩ ቡድናዊ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ኢየሱስ ሲመለስ ለቤተክርስቲያን መነጠቅ የምታዘጋጀን ከእነዚህ ሁሉ ውስጥ የትኛዋ ቤተክርስቲያን ነች?)

ዮሐንስ 1፡22 እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።

እነዚህ ዮሐንስን ሊጠይቁት የመጡ ሰዎች የባለሥልጣኖች ተላላኪ ብቻ ናቸው። እነዚህ ሰዎች እውነትን ለራሳቸው ፈልገው አይደለም የመጡት። እነርሱ ከሌሎች ሰዎች ትዕዛዝ ተቀብለው የተሰጣቸውንም መልስ ለላኳቸው ሄደው ለመናገር ነው የመጡት። (የበላዮቻቸው ከእነርሱ ጥቂቶች ብቻ የሚሰሩበት ቦታ ነው።) ስለዚህ ዮሐንስን ማንነትህን ካልነገርከን ብለው አጥብቀው ጠየቁት። የት ነው የተማርከው? በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤት ነው የተመረቅኸው? ከየትኛዋ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ነው የምታገለግለው? ሲቪውንና የብቃት ማረጋገጫውን በሙሉ ማየት ፈለጉ።

በእነርሱ የሐይማኖት ተቋም ውስጥ የታቀፈ ካልሆነ በቀር ለመቀበል ከበዳቸው።

ዮሐንስ 1፡23 እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
የዮሐንስ መልስ ለእነርሱ አስደንጋጭ ነበር።

“በልጅነቴ ወደ ምድረበዳ ሄድኩ። በዚያ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን ተለማመድኩ። እግዚአብሔርም ከናንተ የሐይማኖት መሪዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤቶችና ሐይማኖታዊ ቡድኖቻችሁ ጋር አንዳችም ዝምድና እንዳይኖረኝ ነገረኝ። እግዚአብሔር የኢሳይያስን ትንቢት እንድፈጽም አዘዘኝ። እኔ በበረሃ ውስጥ ያደግሁ ሰው ስለሆንኩኝ ድምጼ የሚያስደነግጥ ሊሆንባችሁ ይቸላል። በረሃ ውስጥ ኑሮ ከባድ ነው ግን ውስብስብ አይደለም። ድምጼ ሕዝቡንና የሚያስደነግጥና አታላዮቹን የሐይማኖት መሪዎች የሚኮንን የመለከት ድምጽ ነው። እነዚህም የሐይማኖት መሪዎች በሐሰተኛ ፈገግታቸው እንዲሁም ወቀሳ አልቀበልም በማለታቸው ሕዝቡን በተንኮል ገንዘብ በሚያገኙበት ጠማማ መንገዳቸው ሲመሩ የቆዩ ሰዎች ናቸው። የተጣመመውን የሐይማኖት አመራር ማድቀቅ የሚመጣውን መሲኅ እርሱም ጌታ እግዚአብሔር የሆነውን ይቀበሉ ዘንድ ሕዝቡን ለማቃናት የሚጠቅም ብቸኛ መንገድ ነው። እግዚአብሔረ ሕዝቡ ንሰሃ እንዲገቡ፤ በጭምተኝነት እንዲኖሩ፣ እንዲሁም የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል እንዲያምኑ ይፈልጋል። የሕይወት መዳን ያለው በሚመጣው መሲኅ እጅ ነው እንጂ በተለያዩ የሐይማኖት ቡድኖች እጅ አይደለም።”

በሆሳዕና እለት ሕዝቡ ኢየሱስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲመጣ እንዳጨበጨቡለት ሁሉ በቀጣዩ አርብ እለት ደግሞ በጲላጦች የፍርድ ሸንጎ ውስጥ የሐይማኖት መሪዎቻቸውን ተከትለው በኢየሱስ ላይ ፈረዱበት። በጌታ መምጣት ጊዜ ሁሉ ታላቆቹ የእውነት ጠላቶች ሆነው የሚነሱት ሁልጊዜ የሐይማኖ መሪዎች ናቸው።

ስለዚህ ዛሬ ከማን ነው መጠንቀቅ ያለብህ? ከፓስተሮች። ከቢሾፖች። ከሐዋርያዎች። እንዲሁም ከሌሎችም ራሳቸውን ከሾሙ የቤተክርስቲያን መሪዎች።

ዮሐንስ 1፡24 የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና፦

የፈሪሳውያን አገልጋዮች ተጨንቀዋል። ፈሪሳውያን እንደ (መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ያልሆኑት) ነገር ግን ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ፋሽን የሆኑት የምኩራቦች መሪዎች ናቸው። መቅደሱ ፈርሶ ስለነበረ መቅደስ አልነበረም። ስለዚህ ፈሪሳውያን እንቅስቃሴያቸው ከቤተመቅደስ አምልኮ ውጭ ነበር። ከዚያም ገቢያቸውን እና በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ሥልጣን ለማስጠበቅ ሲሉ ፈሪሳውያን ከባቢሎን ግዛት ከተመለሱ በኋላ በእሥራኤል ውስጥ ምኩራቦችን ሰሩ። ከዚያ በኋላ አዳዲስ ትዕዛዛትን አወጡ፤ ለምሳሌ አንድን ፈሪሳዊ የምኩራብ አለቃ አድርጎ መመደብ። ይህ አሰራር ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አሰራር ነበር፤ ግን ደግሞ ሕዝቡን ለመቆጣጠር እና የፈሪሳውያንን ቡድን ለማጠናከር ደግሞ በጣም አዋጪ ነበር። የቤተክርስቲያን “ቡድን” ወይም ዲኖሚኔሽን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አሰራር ነው፤ ደግሞም ሕዝብን በቁጥጥር ስር ለማድረግና በተሳሳተ ሥርዓት ውስጥ ለመምራት አመቺ መንገድ ነው።

የዛሬ ቤተክርስቲያኖች ይህንኑ ልማድ በመከተል ፓስተሮችን በቤተክርስቲያን ላይ አለቃ አድርገው ይሾማሉ። ሆኖም ግን “ፓስተር” ማለትም እረኛ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን በጣም የሚያስፈራው ነገር ደግሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሥድስት ጊዜ ተወግዟል። ስለዚህ ፓስተር የቤተክርስቲያን መሪ እንዲሆን አዲስ ኪዳን ውስጥ ሥልጣን የሚሰጠው ቃል የለም። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ተደርጎ ነው የሚታየው። ነገር ግን ማንም ቢሆን ሁለት ራስ ሊኖረው አይችለም። ስለዚህ በመጨረሻው ዘመን በሎዶቅያ ቤተክርስቲያን እውነተኛው የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል።

ዮሐንስ 1፡25 እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።

አሁን ደግሞ ለምን ማጥመቅ እንደጀመረ ይጠይቁታል። ጥምቀት አዲስ ነገር ነበር።

ዮሐንስ 1፡26 ዮሐንስ መልሶ፦ እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል፤

ዮሐንስም እርሱ የሚያጠምቅበት የውሃ ጥምቀት በሕዝቡ መካከል ቆሞ የነበረውን ነገር ግን ሕዝቡ የማያውቁትን መሲህ እንደሚገልጥላቸው ተናገረ። አይሁድ ከሐጥያታቸው ንሰሃ ለመግባታቸው ምልክት ይሆን ዘንድ በዮሐንስ እጅ ተጠመቁ። መሲሁ ግን ሐጥያት አይኖርበትም።

ስለዚህ እርሱ የሚጠመቅበት ጥምቀት የመስዋእቱን በግ ለማጠብ የሚፈጸም ድርጊት ብቻ ነው የሚሆነው፤ እርሱም እንደ መስዋእቱ በግ ከታጠበ በኋላ ደሙ ለዓለም ሁሉ ሐጥያት ማስተሰርያ ይውላል። ኢየሱስም ከሞተ በኋላ መንፈሱ የእሳት ቃጠሎ እና ስቃይ ወዳለበት ወደ ሲኦል በመውረድ ሰይጣንን አሸንፎ የሞትንና የሲኦልን ቁልፎች ከእጁ ይነጥቀዋል።

2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።

ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል ይመላለስ ነበረ ግን እርሱ ክርስቶስ መሆኑን በመጠቆም የሚያሳያቸው ነብይ ካሌለ ሕዝቡ ሊያውቁት አይችሉም።

በዳግም ምጻቱ ጊዜ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ድሮ ያመነችባቸውን ነገር ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ የጠፉትን ምስጢራት የሚገልጥልን ነብይ ያስፈልገናል። እነዚህ የጠፉ ሚስጥራት ከተገለጡ በኋላ ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ማየት እንችላለን።

አንዲት ሐጥያተኛ ሴትን በድንጋይ ሊወግሯት በተዘጋጁ ጊዜ ለምድ በምድር ላይ በጣቱ ሁለት ጊዜ እንደጻፈ መረዳት እንችላለን።

ከትንሳኤው በኋላ የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ማርያም እግሮቹን ያዘች። በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ግን ኢየሱስ አትንኪኝ ብሏታል። እነዚህ የተለየዩ ክስተቶች ትርጉማቸው ምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልገናል።

በባዶው መቃብር ውስጥ ሁለት መላእክት እንደነበሩ ተጽፏል ግን ማቴዎስ እና ማርቆስ ውስጥ አንድ መልአክ ብቻ ነው የተጠቀሰው።

እነዚህ ልዩነቶች የሚነግሩን ነገር አለ። የእግዚአብሔር ሚስጥር (ቃሉ) ተገልጧል ካልን እነዚህ ልዩነቶች ለምን እንደኖሩ ማወቅ አለብን።

እነዚህ የወንጌል ጸሐፊዎች የየራሳቸውን አመለካከት የሚያንጸባርቁ አራት ደራሲዎች አይደሉም። እነዚህን አራት ሰዎች የሚመራ አንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ልዩነት የሚነግረን ሚስጥር አለ።

ነገር ግን የለመድነው ቤተክርስቲያኖች መሃይምነትን ለመሸፋፈን የሚሰጡትን መልስ መስጠት ነው፡- “አስፈላጊ አይደለም። በሕይወቴ መዳን ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ የለም።” የመልሳችን እውነተኛ ትርጉሙ፡- አናውቅም፤ ባናውቅም ግድ የለንም የሚል ነው። ይህ ትልቅ ግድ የለሽነት ነው። በእውነቱ ንሰሃ ከገባህና ልብህን ለኢየሱስ ከሰጠህ በኋላ ድነሃል። ከዚያ በኋላ መዳንህን ሊነካብህ የሚችል ምንም ነገር የለም። የአውሬውን ምልክት ካልተቀበልክ በቀር።

ነገር ግን ኢየሱስ ያረደገው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎት ማጣትህ ከእርሱ ጋር ያለህ ሕብረት ጥልቀት እንደሌለው ያሳያል። ልክ እንደ አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት። እነዚህ የነጹ ሴቶች፣ የዳኑ ቤተክርስቲያኖች ናቸው ገን የማወቅ ፍላጎት የላቸውም። ለማየት ወይም የእግዚአብሔርን ቃል ለመግለጥ የሚያስፈልግ ብርሃን የሚሆን ዘይት የላቸውም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ሳያውቁ ኢየሱስን እናውቃለን ብለው በመሃይምነታቸው ይደሰታሉ። ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የማናውቅ ከሆነ ኢየሱስን እናውቃለን ማለት የለብንም። በዛሬው ዓለም ግን መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ የሚያስመሰግን ባሕርይ ሆኖ ይቆጠራል።

ዮሐንስ 1፡27 እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው አላቸው።

ታላቅ ነብይ እና የኢየሱስ መንገድ ጠራጊ የሆነው ዮሐንስ በድጋሚ ከኢየሱስ እንደሚያንስ በአጽንኦት ይናገራል። ይህ ድርጊቱ ለነብያት ሁሉ ጥሩ ምሳሌ ነው። ነብያት ከእኛ ጋር ሲነጻጸሩ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፤ ከኢየሱስ አንጻር ግን እጅግ ታናሽ ናቸው።

አሁን ደግሞ በጣም ታላቅ የንሥር እይታ እናያለን። የጫማ ማሰሪያ?

የዳንኤል ምስል ውስጥ የባቢሎን መንግሥት የተወከለው በወርቅ ራስ ነው፤ የፋርስ መንግስት ደግሞ ደረት እና ክንድ። ሆዱ እና ጭኖቹ የግሪክ መንግሥት ናቸው። ከዚያ በታች ያሉት ባቶች ቅልጥሞች የሮማ መንግስትን ይወክላሉ። እግሮቹ ውስጥ ግን የሁሉም ነገር አቅጣጫ ተለወጠ።

በእነዚህ የአሕዛብ መንግሥታት ዘመን መዳን በአይሁድ በኩል ለአሕዛብ አይደርሳቸውም ነበር። መዳን ከአሕዛብ ምስሉ ጀርባ ባለው አረንጓዴ መስመር ተወክሏል። ከዚያም መስቀሉጋ ስንደርስ “ሽግግር” ሆኗል ምክንያቱም ቀጥ ብሎ ከላይ ወደ ታች የሚወርደው አረንጓዴው የመዳን መስመር በእግሮቹ በኩል አግድም መሄድ ይጀምራል። ስለዚህ እግሮቹ የ2,000 ዓመታቱን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላሉ። የአሕዛብ ሮም ጠንካራ ብረት ነበረች። የሮማ ካቶሊኮች በእግሮቹ ውስጥ ያሉት የብረት ስብርባሪዎች ናቸው። ሙሽራዋ ደግሞ በእግሮቹ ውስጥ ያለው ሸክላ ነች። በዚህ ምስል ውስጥ ካሉ ነገሮች ሁሉ መካከል አትክልት ሊያድጉ የሚችሉት በሸክላው አፈር ውስጥ ብቻ ነው።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ሙሽራዋ ያለማቋረጥ ስለሚቀዋወሙ ሊቀላቀሉ አይችሉም። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እውነትን ትይዛለች ግን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ሥላሴ የሚል ቃል በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስን መግፋት ትጀምራለች። ከዚያም እግዚአብሔር እንደ ሦስት አካላት ተደርጎ መታየት ሲጀምር የእግዚአብሔር ስም ይጠፋል። አብ ያህዌ ነው፤ ወልድ ደግሞ ኢየሱስ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም።

ለሦስት አካላት ሁለት ስም ብቻ እናገኛለን። ይህ በቂ አይደለም። የእግዚአብሔር ስም ማነው ብለን ስንጠይቅ ለሦስት አካላት የሚሆን አንድ ስም ማግኘት አይችሉም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በሦስት ማዕረጎች ተተክቶ ቀረ።

ክርስቲያኖች እንደሚሉት የእግዚአብሔር ስም የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው። ግን ያ ስም ማነው? ክርስቲያኖች ለዚህ ጥያቄ መልሱን አያውቁም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም ጠፍቶባቸዋል። በጣም ግዴለሾች ሆነዋል።

ሰውን በመልካችን እንፍጠር። በምድር ላይ ያሉ ሁለት ሰዎች በሰማይ ውስጥ ያሉ የሦስት አካላት መልክ ናቸውን?

ሐዋን ሴት ነች። እንዴት ነው በወንድነት ለሚታወቀው መለኮት መልክ ወይም ምሳሌ የምትሆነው?

የግብጻውያን ሥላሴ ተመሳሳይ ችግር ነበረው። ለሥላሴያዊ አምላካቸው አንድ ስም ሊሰጡት አልቻሉም። ስለዚህ ለሦስቱም አምላኮቻቸው ስም አወጡላቸው። (ሆረስ ብዙውን ጊዜ ኦሲሪስ ተብሎ ይጠራል፤ አይሲስ ደግሞ ሚስቱ ናት። ሴብ ልጅየው ነው።)
አይሲስ በአሁኑ ዘመን ከአይኤስአይኤስ (ISIS) ከሚባለው የአሸባሪ ቡድን የተነሳ አጸያፊ ስም ሆኗል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው በተቃራኒ ሊመሩን ከሚፈልጉ መንፈሳዊ አሸባሪዎች መጠንቀቅ አለብን።

ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያኖች በሊቀ ጳጳሳት፣ በካርዲናሎች፣ እና በፖፕስ አመራር ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቃ ሄደች። በስተመጨረሻ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታውቃቸው የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በሙሉ በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፉ። በ1520 ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። በ1750 አካባቢ ጆን ዌስሊ ቅድስናን እና አገልግሎትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ በማምጣቱ ታላቁ የወንጌል ሥርጭት ዘመን በ1790 አካባቢ ሊጀመር ችሏል። ከዚያም በ1906 የጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ።

ከዚያ በኋላ ደግሞ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታውቃቸው የነበሩ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መልሶ የሚያመጣልን የመጨረሻ ዘመን ነብይ አስፈለገን። ነገር ግን የተጻፉት የቤተክርስቲያን ዘመን ሚስጥራት በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ በሰባት ማሕተሞች ታትመው ተዘግተዋል። እነዚህ ማሕተሞች ልክ የጫማ ማሰሪያ እንደሚፈታው መፈታት አለባቸው። የጫማ ማሰሪያዎቹ ከተፈቱ በኋላ በአሕዛብ ምስል ውስጥ ያለው እግር ይገለጣል።

የዛኔ የቤተክርስቲያንን የ2,000 ዓመታት ታሪክ መረዳት እንችላለን።

ከዚያ በኋላ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችው እምነት ምን እንደነበር ማወቅ እንችላለን።

ይህን ካወቅን በኋላ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንችላለን።

መጥምቁ ዮሐንስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በጴንጤ ቆስጤ እለት ከመጀመሯ በፊት ነው የተገደለው፤ ከዚህም የተነሳ የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን እምነቷ ምን ዓይነት እንደነበረ አላወቀም። ስለዚህ እነዚህን የጥንቷን ቤተክርስቲያን ምስጢራት ሊገልጥ አልቻለም።

መጥምቁ ዮሐንስ ለዚህ ነው መሲኁን እንደሚያስተዋውቅ ነገር ግን የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ ቁ እንዳልሆነ የተናገረው፤ ምክንያቱም የጫማው ማሰሪያ የሰባቱን ማሕተሞች ምስጢራት መገለጥ ይወክላል። ሰባቱ ማሕተሞች የሚጻፉት ግን ዓመታት ካለፉ በኋላ በሐዋርያው ዮሐንስ እጅ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ነብይ እንደመሆኑ እነዚህ ምስጢራት አንድ ቀን የመጨረሻው ዘመን ኤልያስ በሆነው በወንድም ብራንሐም አማካኝነት በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እንደሚገለጡ ያውቅ ነበር። ነገር ግን መጥምቁ ዮሐንስ እርሱ ራሱ ለዚህ አገልግሎት የተጠራው ነብይ እንዳልሆነ ተረድቷል።

መጥምቁ ዮሐንስ የታላቅ አገልግሎቱ ወሰን ወይም ገደብ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ የሚያውቅበት አስደናቂ መንፈሳዊ ዓይኖች ነበሩት። በጣም አስገራሚ ሰው ነበር። እያንዳንዱ ነብይ በተሰጠው አገልግሎት ላይ ገደብ አለው። (የሜሴጅ ፓስተሮች ይህን ልብ በሉ።)

ዮሐንስ 1፡28 ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ።

ቤተራባ ማለት “የወንዝ መቋረጫው ቤት” ወይም “የመሻገሪያው ቦታ” ነው።

ይህ ሩቅ የሆነ ካርታ ላይ ለማግኘት የምንታገልለት ትንሽ ከተማ ለምንድነው የተጠቀሰው?

እግዚአብሔር ታላቁ የንሥር ዓይን ያለው መንፈስ በልቡ ውስጥ ሰፊ የሆነ እቅድ እንዲሁም ብዙ ክርስቲያኖች እንደማያስፈልግ ነገር ዘንግተው የሚያልፉዋቸውን ጥቃቅን ዝርዝሮች አጥርቶ የሚመለከትበት የጠራ እይታም አለው። “የማያስፈልግ ወይም የማይጠቅም” ማለት “አልገባኝም ደግሞም ለመረዳት ግድ የለኝም” ብሎ ከመናገር ማምለጫ መንገድ ነው። ሙሽራ ለመሆን በዝግጅት ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ለወዳጇ ንግግር እንዲህ ያለ ምላሽ ትሰጣለች ተብሎ አይጠበቅም። በሌላ አነጋገር ለኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርሱ ለተናገረው ቃል ምንም ግድ እንደሌለህ ንገረው፤ የዛኔ ሙሽራዋ አካል ውስጥ እንዲሆኑ ከሙፈልጋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ትሰረዛለህ።

መዳን እንዴት ከአይሁዶች የ2,000 ዓመታት ቤተክርስቲያን ታሪክን ወደሚወክለው የአሕዛብ እግር ምስል “እንተሸጋገረ” ተመልክተናል።

ቤተራባ የዮርዳኖስ ወንዝ “የመሻገሪያው ቦታ” ነው። ዮሐንስ በዚህ ቦታ ላይ ያጠምቅ የነበረው መሲኁ ሲመጣ የብሉይ ኪዳን ሕግ ወደ አዲስ ኪዳን ጸጋ “እንደሚሻገር” ስላወቀ ነው።

በዚህ ክልል ውስጥ የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ሦስት ጊዜ ተደጋግሟል። እያንዳንዱም ሽግግር ወደፊት ስለሚሆን ጠለቅ ወዳለ መንፈሳዊ ክልል ሽግግር የሚጠቁም ነበር።

ኢያሱ እና አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድር ተሻገሩ።

ኤልያስ እና ኤልሳዕ ከእሥራኤል ወጥተው ሲሄዱ ዮርዳኖስን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ተሻገሩ።

ኤልሳዕ ወደ እሥራኤል ሲመለስ ዮርዳኖስን ከምሥራቃዊው ዳርቻ ወደ ምዕራብ ተሻገረ።

እነዚህ ወንዝ የመሻገር ድርጊቶች የሚያመለክቱት ምንድነው? እስቲ ሰፋ አድርገን እንመልከት።

የሙሴ ሕግ የአይሁድን ሕዝብ የተሻሉ ሰዎች ማድረግ አልቻለም። ስለዚህ ይህንን ለማመልከት እግዚአብሔር ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገባ አልፈቀደለትም። ኢያሱ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ይወክላል። ዮርዳኖስ ሞትን ማለትም ለራስ መሞትን ይወክላል። ስለዚሀ ኢያሱ ያደረገው ነገር ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመሻገርም ያለፈ ነው። የኢያሱ መሻገር ክርስቲያኖች ለራሳቸው ሞተው መንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸውን እንዲሞላ እና ፍጹም ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር ቃል እንዲመራቸው ሲፈቅዱ የሚያደርጉትን እውነተኛውን “መሻገር” ያመለክታል። ይህም ከራሳችን ፈቃድ (ከጠባቡ ሃሳባችን) ወደ እግዚአብሔር (ትልቁ የእግዚአብሔር እቅድ) የምናደርገው “ሽግግር” ነው።

የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን አማኞች ሐዋርያት እየመሩዋቸው በነበረ ጊዜ ይህንን ሽግግር አከናውነዋል። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር የሚጠላው የሰዎች አመራር ወይም ኒቆላዊነት ቤተክርስቲያንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አርቆ ይዟት ሄደና ቤተክርስቲያን ታውቀው የነበረው እውነት በብዛት በጨለማው ዘመን ውስጥ እንዲጠፋ አደረገ።

የእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ውስጥ የመጨረሻው ክፍል ሁለት የሕዝብ ወገኖች ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን እውነት እንደሚመለሱ የሚናገር ተስፋ ነው። ድንኳኑ ባለ ሰባት ቅርንጫፍ መቅረዝ ነበረው (ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክል) እና በቅድስት ሥፍራ የሚበላ 12 የገጽ ሕብስቶችን የተሸከመ ጠረጴዛ ነበረው (ይህም ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባት ያለባቸውን 12 የእሥራኤል ነገዶች ይወክላል)።

ስለዚህ ኤልያስ በሰረገላ ወደ ሰማይ ሊነጠቅ ዮርዳኖስን ተሻገረ። ይህም በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ኤልያስ ልጆችን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና ወደ ሐዋርያዊ አባቶች የአዲስ ኪዳን ትምሕርት እንደሚመልሳቸው የሚጠቁም ውብ ማሳያ ነው። እነዚህ ልጆች (ማለትም ወንድም ብራንሐም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የመለሳቸው የመጨረሻ ዘመን ሙሽራ አካሎች) ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ። ሙሽራይቱ ከሙዋችነት ወደ አለመሞት ማለትም ከምድር ወደ ሰማይ “ትሻገራለች”።

ነገር ግን ሌላም ነብይ፤ ለአይሁዶች የሚላከው ኤልያስ ስለተጻፉት ምስጢራት ከወንድም ብራንሐም ትምሕርት ውስጥ መማር አለበት። ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ዮርዳኖስን ተመልሶ በመሻገር የጥንቷን ቤተክርስቲያን ወንጌል ይቀበልና በታላቁ መከራ ወቅት ለሚኖሩ 144,000 አይሁዳውያን ይዞላቸው ይሄዳል።

ይህ ሁሉ “መሻገር” የሚሳካው ከአንድ ሰው የተነሳ ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ብቻ ነው እንዲከናወን ማድረግ የሚችለው።

ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ አሁን ኢየሱስን በትኩረት እንድናየው አድርጎ ያቀርብልናል።

ዮሐንስ 1፡29 በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።

ቃሉ (ኢየሱስ) በውሃ ውስጦ ቆሞ ወደ ነበረው ነብይ መምጣቱን ልብ በሉ። ውሃ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። እውነተኛ ነብይ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው የሚቆመው።

ኢየሱስ አገልግሎቱን ይጀምራል፤ አገልግሎቱም የሚጠናቀቀው የዓለምን ሁሉ ሐጥያት በቀራንዮ ሲሸከምና እንደ ሐጥያት ተሸካሚነቱ ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል በመውረድ የሐጥያት ጀማሪና የሐጥያት አባት በሆነው በዲያብሎስ ላይ ሐጥያታችንን ሲያራግፍ ነው።

ኤፌሶን 5፡25-26 … በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

ከዚያም የሐጥያትን ዋጋ ለመክፈል የፈሰሰው የጌታ ደም ከሐጥያት ያነጻናል ምክንያቱም ስለሞቱ የተነገሩ 33 ትንቢቶች እርሱ በተሰቀለበት ቀን ተፈጽመዋል። ስለዚህ በእርሱ ሞት ስለ መሲኁ የተነገሩ ትንቢቶች ሁሉ በትክክል ተፈጽመዋል። እርሱ የሞተው ስለመሞቱ በተናገሩት የእግዚአብሔር ቃል ትንቢቶች መሰረት ነው። ስለ ቀራንዮ የተናገሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ መፈጸም ማለት በእርሱ የመስዋእትነት ሞት ላይ እምነታችንን ብንጥል እነዚህ ሁሉ የተፈጸሙ ጥቅሶች እንደ ወንዝ እየፈሰሱ ሐጥያታችንን ያጥባሉ ማለት ነው።

ዮሐንስ 1፡30 አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ በድጋሚ ኢየሱስ መሲኁ መሆኑን አስረግጦ ይመሰክራል። ዮሐንስ ሰዎች ሁሉ መሲኁ የትኛው እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እርሱን ከሕዝብ መካከል ነጥሎ ያሳያል። ዮሐንስ ቀድሞ የመጣው ኢየሱስን ለመጠቆም ነው። ደግሞም ኢየሱስ እውነተኛው መሲኅ እንደሆነም መስክሯል። ከሰዎች ላይ የሐጥያትን ቀምበር እንደሚሰብር በትንቢት የተነገረለት ኢየሱስ ነው።

ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ይጠቁማል፤ ሐጥያትንና ሞትን ድል የሚነሳው ግን ኢየሱስ ብቻ ነው።

ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር በሥጋ ሲገለጥ ነው። ስለዚህ እርሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ እግዚአብሔር የኖረበት የመንፈስ አካል ነበረ።

ዮሐንስ 1፡31 እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ ስለዚህ በውኃ እያጠመቅሁ እኔ መጣሁ።

ዮሐንስ ቀድሞ ኢየሱስን አላየውም ነበር። ነገር ግን ዮሐንስ ነብይ ስለነበረ ሁል ጊዜ ቃል ወደ ነብይ እንደሚመጣ እርግጠኛ ነበረ።

የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ልትወልደው የስድስት ወር እርጉዝ በነበረች ጊዜ ገና ኢየሱስን የጸነሰችዋ ማርያም ወደ ኤልሳ ቤጥ መጥታ በእርሷ ዘንድ ለሦስት ወራት ቆየች። ስለዚህ ኢየሱስ ቃሉ ወደ ዮሐንስ ወደ ነብዩ ዮሐንስ በማሕጸን ውሃ ውስጥ እያለ መጣ።

ከሦስት ወራት በኋላ ልክ ዮሐንስ ሊወለድ ሲል ማርያም ሄደች። በሚወለድበት ጊዜ ውሃው ይፈስሳል፤ ስለዚህ ቃሉ በነብዩ ዘንድ የቆየው ነብዩ ውሃ ውስጥ ሳለ ብቻ ነበር።

ከሰላሳ ዓመት በኋላ ዮሐንስ ሰዎችን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ እያጠመቀ ሳለ ልክ እንደ ጽንሱ ጊዜ አሁንም ኢየሱስ (ቃሉ) ቃሉ ነው ወደ ነብዩ ወደ ዮሐንስ የመጣው ዮሐንስ በዮርዳኖው ውሃ ውስጥ እያለ። የእግዚአብሔር ቃል ሁልጊዜ ወደ ነብይ ይመጣል።

ዮሐንስ 1፡32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።

ሐዋርያው ዮሐንስ ኢየሱስን እንደ ታላቅ ንሥር ነው የሚያስተዋውቀው፤ ማለትም እንደ እግዚአብሔር። ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ በውሃ ውስጥ ገብቶ መጠመቁን ሳይጠቅስ በቀጥታ የመንፈስ ቅዱስን እንደ እርግብ መውረድና በኢየሱስ ላይ ማረፍ ነው የሚተርክልን።

ይህም ሰውየው አገልግሎቱን እንዲጀምር ተቀባ ማለት ነው።

የሐዋርያት ሥራ 10፡38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥

መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጡ አልገባም።

መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ኖረበት። ይህም መቀባት እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አይደለም።

መጥምቁ ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስን የተቀበለው የእናቱ ማሕጸን ውስጥ ሳለ ነበር።

ሉቃስ 1፡15 በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤

ዮሐንስ ደጋግሞ ኢየሱስ ከእርሱ እንደሚበልጥ ይመሰክር ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ሊጠመቅ ወደ ውሃው በመጣ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ባይኖር ኖሮ ዮሐንስ ከእርሱ በብዙ በበለጠ ነበር።

ዮሐንስ 1፡30 አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

የኢየሱስ ሥጋዊ አካሉ ከዮሐንስ ቀድሞ አልተወለደም። ዮሐንስ ከኢየሱስ በሥድስት ወር ቀድሞ ነው የተወለደው። ኢየሱስ ግን የመንፈስ ቅዱስን ሙላት ገና ሲጸነስ ነው የተቀበለው። የእግዚአብሔር መንፈስ ሁልጊዜም ከመጀመሪያው በፊት ሁሉ ነበረ። ይህ የዘላለማዊነት ጽንሰ ሃሳብ ለእኛ ለሰዎች ሊገባን አይችልም።

ዮሐንስ 3፡34 እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

የመለኮት ሙላት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የገባበት በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ከሆነ ኢየሱስ ተለውጧል ማለት ነው።
ኢየሱስ ግን በፍጹም አይለወጥም።

ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ በማንኛውም ሰዓት የመለኮት ሙላት በውስጡ ቢገኝበት ሁልጊዜም በውስጡ የመለኮት ሙላት ነበረው ማለት ነው።

ዮሐንስ 1፡33 እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።

መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ወረደበትና ኖረበት፤ እንጂ ወደ ውስጡ አልገባም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ በእርሱ ላይ በመኖር በአደባባይ “የተቀባ” ወይም ክርስቶስ አድርጎታል (“ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “የተቀባ” ማለት ነው።)
መጥምቁ ዮሐንስ በእምነት ነበር የተሰማራው። ኢሳይያስ በትንቢቱ በምድረበዳ ስለሚጮኸው ድምጽ የተናገረውን ቢፈጽመው ከዚያ ኢየሱስ ወደ እርሱ እንደሚመጣ አምኖ ነው አገልግሎቱን የጀመረው፤ ምክንያቱም ኢየሱስን ከሰዎች መካከል የትኛው ሰው እንደነበረ አያውቀውም ነበር።

ሐዋርያው ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ እንዳረፈበት እንጂ ወደ ውስጡ እንዳልገባ በድጋሚ አጽንኦት ሰጥቶ ይነግረናል። ይህንን ማስተዋል አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ወደ ኢየሱስ ውስጥ የገባ እና ሰው ከመሆን አምላክ-ሰው ወደመሆን የለወጠው ይመስላቸዋል። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው ምክንያቱም ኢየሱስ አይለወጥም።

ኢየሱስ በሕዝብ ፊት ሹመት ወይም ቅባት እየተቀበለ ነበር። ለምን?

ዳዊት በነብዩ ሳሙኤል የአይሁድ ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ነበር። ነገር ግን ጠላቱ ሳኦል እስኪሞት ድረስ ዳዊት እንደ ንጉሥ ወደ ሥልጣኑ መውጣት አልቻለም።

ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የአይሁድ ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቷል። ይህም ከሐጥያት ዓለም ሐጥያት ወደሌለበት ዓለም “መሸጋገሪያ” ነበር፤ ምክንያቱም የእርሱ አካል የመጀመሪያው ፍጹም ንጹህ የሆነ አፈር ነበረ።

የሰላም ተምሳሌት የሆነችዋ እርግብ የየዋሕነት ተምሳሌት በሆነው በግ ላይ ብቻ ነው የምታርፈው።

ነገር ግን የዳዊት ልጅ ኢየሱስ “የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ሐይማኖት፣ ፖለቲካ እና የገንዘብ ኃይል አውሬ መንፈስ” አርማጌዶን ውስጥ እስኪሞት ድረስ እንደ ንጉሥ ወደ ሥልጣኑ መውጣት አይችልም። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ መጀመሪያ ለ1,000 ዓመት በብረት በትር ይገዛል። ይህን የሚያደርገው ሐጥያት የሌለበት መንግሥት ስለሚፈልግ ነው። ነገር ግን ከአርማጌዶን በኋላ የሚተርፉ ወንጌልን ሰምተው የማያውቁ አሕዛብ ይኖራሉ። እነዚህም ሰዎች በሺው ዓመት መንግሥት ውስጥ ይኖራሉ ግን ሥርዓት ይዘው መኖር አለባቸው።
የሺው ዓመት መንግሥት የመጀመሪያው ሰማይ ነው፤ በምድር ላይ ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበት ጊዜ የመንግሥተ ሰማይ የመጀመሪያ ቅምሻ ነው።

ሰይጣን በምድር ላይ መንቀሳቀስ በማይችልበት ሁኔታ ታስሯል ምክንያቱም ኢየሱስ በምድር ላይ እየገዛ ነው።

ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር ደግሞ ከ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የተወጣጡ ከሙታን የተነሱ ቅዱሳን አሉ። እነርሱም ፍጹም በሆነ ሐጥያት በሌለበት የከበረ አካል ውስጥ ነው የሚኖሩት።

ከሺ ዓመቱ መንግሥት በኋላ የመጨረሻው የጎግ እና ማጎግ ዓመጽ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ባሕር እንደ ቦምብ ይፈነዳና የምድርን ሽፋን ገጽ ገንጥሎ ያነሳል። ይህንንም ተከትሎ ሐጥያት የሌለበት አዲስ ምድር ይገለጣል።

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ የዘላለም ንጉሥ ይሆናል።

ኢየሱስ የአይሁድ ሊቀካሕናት እንዲሆንም ጭምር ነው የተቀባው።

ዘጸአት 29፡4 አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።
ዘጸአት 29፡5 ልብሶችን ወስደህ ለአሮን … ታለብሰዋለህ፥ …

7 መጠምጠሚያውንም በራሱ ላይ ታደርጋለህ፥ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ።

የመጀመሪያው ሊቀካሕናት አሮን ነው። እርሱም በነብዩ በሙሴ እጅ ከታጠበ በኋላ ነው በዘይት የተቀባው። ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ ማለትም የአዲሱ ኪዳን ሊቀካሕናት ነው። እርሱም በነብዩ መጥምቁ ዮሐንስ እጅ መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ነበረበት።

ስለዚህ ክርስቲያኖች ኢየሱስን የራሳቸው ሊቀካሕናት፣ ንጉሥ፣ እና መስዋእት አድርገው ሲቀበሉ የአሮጌውን ኪዳን ትዕዛዝ እየታዘዙ ነው።

ኢየሱስም ሕጉን አይሁዳውያን ሊፈጽሙት ከሚችሉበት እጅግ ከፍ ወዳለ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።

ዮሐንስ 1፡34 እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ።

መጥምቁ ዮሐንስ የመጨረሻውን የማረጋገጫ ማሕተም ለኢየሱስ ሰጠ። ይህም የመጥምቁ ዮሐንስ የአገልግሎቱ ፍጻሜ ነበር። መሲኁን አስተዋውቋል። ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን አድርጓል። መጥምቁ ዮሐንስ እውነተኛውን መሲኅ ለሕዝብ ለይቶ አሳይቷል።

አዳም በሐጥያት ከመውደቁ በፊት የመጀመሪያው ፍጹም የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ። ዮሐንስ አሁን ትክክለኛውን ታሪክ መዝግቦልናል።

ከአዳም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍጹሙ የእግዚአብሔር ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጧል።

ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥

አሁን በመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ውስጥ ቁልፍ የሆነ ሰዓት ላይ ደርሰናል።

ዮሐንስ ከአገልግሎቱ ታላቅነት የተነሳ እርሱም ታላቅ አገልጋይ ስለነበረ እርሱን የሚከተሉ ደቀመዛሙርት አፍርቷል። ዮሐንስ የእውነት አስደናቂ ሰው ነበረ። ደቀመዛሙርቱ እርሱ የሚናገረውን ሁሉ በማመን አጥብቀው ተከትለውታል።

ዮሐንስም መከተል ያለባቸውን ትክክለኛ መንገድ አሳይቷቸዋል።

አንዴ ዮሐንስ ኢየሱስን ከጠቆማቸው በኋላ ደቀመዛሙርቱ ነብዩን መጥምቁ ዮሐንስን መከተል አቁመው ኢየሱስን የእግዚአብሔር ቃልን መከተል ጀመሩ።

ዮሐንስ 1፡36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።

ዮሐንስ ግን የራሱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድንቅ አገልግሎት ከማስተዋወቅ ይልቅ ለደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን እንዲከተሉ ወደ ኢየሱስ መጠቆም ጀመረ። የወንድም ብራንሐም ጥቅሶች ወደተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ሊጠቁሙን ይገባል።

ከዚያም ሁለቱ ደቀመዛሙርት አንዴ ከነብዩ ቃል መገለጥን ካገኙ በኋላ ማለትም ነብዩ ዮሐንስ የጠቀሰው ትንቢት ስለ እግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚያብራራ ካስተዋሉ በኋላ ወደ ኢየሱስ ማለትም ወደ እግዚአብሔር ቃል ሄዱ።

ዮሐንስ 1፡37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።

ይህ የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ዋነኛ ቁም ነገሩ ነው። የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ዮሐንስ ስለምን እንደተናገረ በትክክል ቢገባቸው ኖሮ ዮሐንስን ሳይሆን ኢየሱስን ይከተሉ ነበር።

ዊልያም ብራንሐም የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ታምንበት የነበረውን በጨለማው ዘመን ውስጥ የጠፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ሊገልጥ መጣ። የዊልያም ብራንሐም አገልግሎት ብዙ ደቀመዛሙርትን ሳበ። የተጻፈውን ቃል እየገለጠ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ሁለት ምርጫ ከፊታቸው ቀርቦላቸው ነበር።

የመጀመሪያው አማራጭ ወንምድ ብራንሐምን ከፍ ከፍ ማድረግና መከተል ነበር። ይህም የተሳሳተ ምርጫ ነበር፤ ምክንያቱም ይህንን ሲመርጡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ትምሕርታቸውን የመሰረቱት የዊልያም ብራንሐምን ንግግር ጥቅሶች ወስደው በመተርጎም እና የእርሱን ንግግር “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ሳይሆን ከፍ አድርገው “የእግዚአብሔር ድምጽ ነው” በማለት ነበር።

ወይም ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የእውነተኛዋ ሙሽራ አካል የሆኑ አማኞች በመጽሐፍ ቅዱስ ወደተጻፈው የጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንዳለባት ተገንዝባለች። ስለዚህ የተጻፉተን ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተከታትለው በማየት እምነታቸውን በቃሉ ላይ ይመሰርታሉ። በዚህ መንገድ በጥቅሶቹ አማካኝነት ያገኙትን የኢየሱስ መገለጥ ተከትለው በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ኢየሱስን ያዩታል።

መጥምቁ ዮሐንስ ብዙ ደቀመዛሙርት ነበሩት ነገር ግን በዚያ ጊዜ ኢየሱስን የተከተሉት ሁሉት ደቀመዛሙርት ብቻ ነበሩ።

ይህም ሰዎች እንዴት በቀላሉ በታላቅ ነብይ ኃይለኛ አገልግሎት ሊማረኩ እንደሚችሉና ደቀመዛሙርትም በስተመጨረሻ ነብዩን የላከውን እግዚአብሔርን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ነብይ ተከትለው ሊቀሩ እንደሚችሉ ያሳየናል።

ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል በጣም ጥቂቶች፤ ከዊልያም ብራንሐም ደቀመዛሙርት መካከልም በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው ይህን የተገነዘቡት።

በኮምዩኒዝም ታሪክ ውስጥ ከዚህ ጋር በጣም የሚመሳሰል ክስተት አለ። ኮምዩኒስቶች ከሌኒን ትምሕርት ብዙ እየራቁ በሄዱ ቁጥር ሌኒንን ይበልጥ እያከበሩና እንደ አምላክ ከፍ እያደረጉ ሄዱ። ይህም ትምሕርቱን ላለመከተላቸው እንደ ማካካሻ ነው። የሌኒንን ትምሕርቶች አጣመሙ፤ ግን ካሳ እንዲሆን ደግሞ ሌኒንን አመለኩ።

ወንድም ብራንሐም የመጣው ወደተጻፈው ቃል ሊመልሰን ነው። የዊልያም ብራንሐም ተከታዮች እምነታቸውን በተጻፈው ቃል ፈትሸው ማረጋገጥን በተዉ መጠን ይበልጥ ወንድም ብራንሐምን ከፍ ከፍ ማድረጋቸውን እንዲሁም ወንድም ብራንሐምን እና ጥቅሶቹን ማምለካቸውን ቀጠሉ።

ዮሐንስ 1፡38-39 ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ ትርጓሜው መምህር ሆይ ማለት ነው።

ይህ ጠለቅ ያለ ጥያቄ ነው።

እነዚህ ደቀመዛሙርት ማወቅ የፈለጉት ኢየሱስ በፍጥረታዊ ቤት የሚኖርበትን አድራሻ ለማወቅ ነበር።

ነገር ግን የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን የሚያስተዋውቅ ወንጌል ነው፤ እርሱም በዚያ የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክን በሙሉ ከፊት ለፊቱ ማየት በሚችለው ታላቅ ንሥር ተመስሏል። ቤተክርስቲያንን በ2,000 ዓመታት ውስጥ ሁሉ እንደ አካሉ በአንድ ጊዜ ያያታል። ኢየሱስ ትክክለኛው የቤተክርስቲያን ራስ ነው።

ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

ስለዚህ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ማለትም የአማኞች አካልን ለማዳን በ2,000 ዓመታት ውስጥ የት ነው መኖሪያውን የሚያደርገው?
ኢየሱስ የሚኖረው በተገለጠ ቃሉ ውስጥ ነው።

በዚያ በጥንቱ ዘመን እንኳ ኢየሱስ ቋሚ መኖሪያ ቦታ አልነበረውም፤ ምክንያቱም ስለ እርሱ የተጻፉ ትንቢቶችን ሁሉ ለመፈጸም ወደተለያዩ ቦታዎች ይዘዋወር ነበር። ኢየሱስ ወንጌላዊም ሐዋርያም ስለነበረ ከቦታ ቦታ ይዘዋወር ነበር። ኢየሱስ ሁሉንም አገልግሎትች አገልግሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰጠው ድርሻ ለአይሁዶች መሲሃቸው ሆኖ መምጣት ነበር። ይህም ጥሪው አገልግሎቱ በእሥራኤል የተስፋ ምድር ውስጥ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል።

አይሁድ እንደማይቀበሉት ለመጨረሻ ጊዜ በቀራንዮ ካረጋገጡለት በኋላ መኖርያው የት ነው የሚሆነው?

የኢየሱስ መኖርያው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በሆኑ ዳግመኛ በተወለዱ ወንዶች እና ሴቶች ልብ ውስጥ ነው።

ሐዋርያቱ በጌታ ፊት የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አባቶች ሆነዋል። ከዚያ በኋላ ግን ቤተክርስቲያን ወደ ሰው አመራር ዘወር ስትል በጨለማው ዘመን ውስጥ ክሕደት ገባ። ከዚያ በኋላ ቆይቶ በ1520 ማርቲን ሉትር ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት ብቻ ነው ብሎ ያስተማረ ጊዜ ተሃድሶ ሆነ። በ1750 አካባቢ እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ቅድስናን እና የወንጌል ስብከትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ፤ ያንንም ተከትሎ ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን መጣ። በ1906 በጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ ቤተክርስቲያን ተመለሰ። ከዚያ በኋላ የቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮችን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ማምጣት ነበረ፤ ይህም የሚደረገው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ምሳሌዎችን እና ምልክቶችን በትክክል በመተርጎም እንዲሁም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንዳመነችው ማመን ነው።

ይህም የሚሆነው ለሁለት ቡድኖች ብቻ ነው። ዊልያም ብራንሐም እኛ ክርስቲያኖች እንደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እንድናምን እና እንድንመላለስ የሚያስችሉንን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮች ገልጦ ያስተምራል። ከዚያም ሙሴ እና ኤልያስ በታላቁ መከራ ወቅት እሥራኤል ውስጥ 144,000ውን የተመረጡትን በሚጠሩ ጊዜ ለአይሁዳውያን እነዚህኑ ሚስጥራት ገልጠው ያስተምራሉ።

ኢየሱስ በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በሃሳቡ የያዘው ትልቁ እቅድ ይህ ነው።

ኢየሱስ በተጨማሪ ደግሞ የደቀመዝሙርን እውነተኛ የልብ ፍላጎት ማወቅ ይፈልጋል።

እርሱን የምንከተለው ለጥቅም ነው? ጌታ ብለው ጠሩት፤ ይህም እርሱ ከሁሉ የበላይ መሆኑን የሚያመለክት አጠራር ነው።

እነዚህ የነብዩ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት ዮሐንስን ከኢየሱስ ጋር እኩል ለማድረግ ከፍ አድርገውት አያውቁም። (የሜሴጅ ፓስተሮች እባካችሁ ልብ በሉ።)

በዘመናቸው ከሁሉ በላይ ታላቅ የነበረውን ነብይ ትተው ሄዱ ምክንያቱም ኢየሱስ እውነተኛው ጌታ እንደሆነ፤ ዮሐንስ ሳይሆን ኢየሱስ ፍጹሙ እውነት እንደሆነ ስላወቁ ነው።

ስለዚህ አሁን ኢየሱስ የት እንደሚኖር ማወቅ ፈለጉ።

ዛሬ ኢየሱስ የሚኖረው በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መካከል ነው። ኢየሱስ ማን መሆኑን ማወቅ ከፈለግን ዛዜ በእኛ ዘመን እርሱን በትክክል የምናውቅበት ብቸኛው እውነኛ መገለጥ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ነው።

ዛሬ ኢየሱስ የሚኖረው ባለፈው ዘመን በሰራው ሥራ ትዝታ ውስጥ አይደለም። እውነትን ለሚወዱ እና ለመማር ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ኢየሱስ የሚኖረው ዛሬ በምንቀበለው በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ውስጥ ነው።

“ከዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የምታገኙት አምላክ” ዘላለማዊ እጣ ፈንታችሁን ይወስነዋል።

ክርስቶስን ልታገኙት የምትችሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ብቻ ነው። እዚያ ውስጥ ፈልጉት።

ኢየሱስን መከተል ከድሮም ቀላል አልነበረም። ኢየሱስን የሚከተል ሰው ኑሮው ይለወጣል። ኢየሱስ ሌሎች ሰዎች በኖሩበት አልኖረም። ኢየሱስን ብንከተለው ይለውጠናል።

ዮሐንስ 1፡40 መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ።

“መጥተህ እይ” የሚለው ቃል የመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች አንድ በአንድ ሲፈቱ በዙፋኑ ዙርያ የነበሩት አራት እንስሳት ለዮሐንስ የተናገሩት ቃል ነው።

ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

“መጥተህ” የሚለው ቃል ካለንበት ተነስተን መንቀሳቀስ አለብን ማለት ነው። ኢየሱስን መከተል ማለት ደግሞ ሁሉጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እንሆናለን ማለት ነው።

እየበረረ ያለ ንሥር ከቆመ ይወድቃል።

እውነትን ከያዛችሁ መገለጥ አያቆምም። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየተረዳችሁ ስትሄዱ እውነት ይበልጥ ጠለቅ እያለ እየተገለጠ እየተገለጠ ይሄዳል።

“እይ።” ኢየሱስን መከተል ማለት የተጻፈውን ቃል ውስጥ ጠለቅ ያለ እይታ ማለትም መረዳት እያገኘን እንሄዳለን ማለት ነው።

እምነታችን ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ጥቅሶችን ማገናኘት እንለምዳለን። በወራጅ ወንዝ ውስጥ እንዳለው ጥልቅ ሞገድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚሄደውን የሃሳብ ሞገድ መከታተል እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት ወንዝ ነው።

ኢየሱስ ወደሚኖርበት ቦታ ወሰዳቸው። ኢየሱስ ዛሬ የሚኖረው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፋን ቃል ሚስጥሩን ማወቅ ከፈለጋችሁ የዊልያም ብራንሐም ጥቅሶችን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መልሳችሁ በመውሰድ በቃሉ መመርመር አለባችሁ።

የሱ ጥቅሶች የሚናገሩት ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገኘ ትምሕርቶቹን በትክክል መረዳታችሁን ታረጋግጣላችሁ።

ዮሐንስ 1፡41 ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ።

እንድሪያስ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበረ። እርሱም ነብዩ መጥምቁ ዮሐንስ ከተናገራቸው ጥቅሶች ተነስቶ ጥቅሶቹ ወዳመለከቱት ወደ ቃሉ ወደ ኢየሱስ ሄደ። ከዚያም ቃሉን ኢየሱስን ሰምቶ ታዘዘ። ይህ ነው ቁልፉ ሃሳብ። የነብዩ ጥቅሶች ቃሉን ገለጡለት፤ ከዚያም ቃሉን (ማለትም ኢየሱስን) መከተል ቻለ። ከዚያም ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ታዘዘ።

ነብዩ ቃሉን ገለጠለት፤ እርሱም ከዚያ ወዲያ ቃሉን ተከተለ እንጂ ነብዩን አልተከተለም።

ዮሐንስ 1፡41 እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።

እንድሪያስ የነብዩ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበረ ግን ወንድሙን ወደ ነብዩ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ አልመራውም።

እንድሪያስ ወንድሙን ወደ ኢየሱስ ማለትም ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው የመራው።

ሰዎችን ወደ ዊልያም ብራንሐም ጥቅሶች መምራት የእኛ ጥሪ አይደለም።

እነዚያ ጥቅሶች የእግዚአብሔርን ቃል ገልጠውልናል፤ ስለዚህ አሁን እኛ ሰዎችን ወደተገለጠው ቃል ማለትም ወደተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ነው መምራት ያለብን።

መጥምቁ ዮሐንስን በግል ያውቀው የነበረው እንድሪያስ ወንድሙን ጴጥሮስን ወደ ኢየሱስ ይዞ በመምጣቱ የመጥምቁ ዮሐንስን ትምሕርት በትክክል መረዳቱን ያሳያል። ነገር ግን በወንጌል አገልግሎት ስኬት ሲመዘኑ ጴጥሮስ እንድሪያስን በብዙ በልጦታል። ጴጥሮስ ከነብዩ መጥምቁ ዮሐንስ ጋር በግል አለመተዋወቁ ወደ ኋላ ሊያስቀረው አልቻለም።

እንድሪያስ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበረ፤ ጴጥሮስ ግን የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር አልነበረም። መጥምቁ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ እያመለከተ በነበረ ጊዜ እንኳ ጴጥሮስ የመስማት እድል አላገኘም ነበር። እንድሪያስ በፍጹም ልቡ የተሰጠ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ቢሆንም እንኳ ጴጥሮስ ግን መጥምቁ ዮሐንስን ባይከተልም ከእንድሪያስ ይልቅ የተሻለ የኢየሱስ ደቀመዝሙር ሊሆን ችሏል። ለኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ጠራጊ የነበረውን ነብይ ተከታይ መሆን እንድሪያስን ከኢየሱስ ደቀመዛሙርት መካከል ሁሉ ታላቅ ደቀመዝሙር ለመሆን አላበቃውም። እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እንድሪያስ ብዙ የተጻፈ ነገር የለም። ጴጥሮስ ከእንድሪያስ ይልቅ አስደናቂ አገልግሎት አገልግሏል፤ ከዚያም በላይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለት መጽሐፎችን ጽፏል። የነብዩ መጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር መሆን ለየት ያለ ጥቅም የለውም።

ስለዚህ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር ለሰዎች ስለማስረዳት ስናስብ ከወንድም ብራንሐም ጋር በግል መተዋወቅ ምንም ልዩ ጥቅም የለውም። የእግዚአብሔረን ቃል ለመረዳት እና ለመታዘዝ ነብዩን በግልህ ማወቅ የግድ አያስፈልግህም።

ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል ምናልባት እንድሪያስ ብቻ ነው የኢየሱስ ደቀመዝሙር የሆነው።

ስለዚህ የዊልያም ብራንሐም ደቀመዝሙር መሆን በራሱ የእውነተኛዋ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ማለትም የቃሉ መሪ መሆንህን የተረጋገጠ አለመሆኑን ያመለክታል።

ከጥቅሶቹ ተነስተን የቃሉን መረዳት ወደ ማግኘት መሸጋገር አለብን። ከጥቅሶቹ ጋር ታስረን አንቀርም። ከዚያም ሌላ ደግሞ ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር እንዲጋጩ አድርገን መተርጎም የለብንም።

የሜሴጅ አማኞች በጥቅሶች ላይ በተመሰረተው የፓስተሮቻቸው ትምሕርት የተነሳ የገቡበትን ብዙ ስሕተት ስናየው በወንድም ብራንሐም ላይ ትኩረት ካደረጉ ሰዎች መካከል በጣም ጥቂቶቹ ብቻ የተጻፈውን ቃል ሚስጥራት በመግለጥ እንደሚሳካላቸው እናስተውላለን። በዚህ ዘመን ውስጥ ጥቅሶች ላይ ትኩረት ከመብዛቱ የተነሳ አብላጫዎቹ ባይሆኑም ብዙዎቹ የሜሴጅ ተከታዮች የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይም የመሆን አደጋ ውስጥ ናቸው።

ይህንን ችግር በተመለከተ ኤርምያስ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፡፡
2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡

የሜሴጅ ፓስተሮች አመለካከታቸውን ከሚቃረኑ ሰዎች ሁሉ መራቅ ያስደስታቸዋል።

የብዙዎቹ ፓስተሮች መፈክር፡- “ሁሉም ሰው የእኔን አመለካከት የመቀበል መብት አለው” የሚል ነው።

ከወንድም ብራንሐም ጥቅሶች ውስጥ መገለጥ (መረዳት) ብናገኝ ያንን መረዳት ወይም መገለጥ ወይም አስተምሕሮ በተጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ተከታትለን ማግኘት መቻል አለብን። ኢየሱስን መከተል የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ብቻ ነው። ኢየሱስ ዛሬ መኖሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፤ በተገለጡት የቃሉ ሚስጥራት ውስጥ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የማንረዳ ከሆነ ኢየሱስን የእውነት እየተከተልነው ነን ማለት አንችልም።

ኢሳይያስ 28፡10 ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።

ዮሐንስ 1፡42 እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።

ድንጋይ ትንሽዬ መደበኛ የሆነ ቅርጽ የሌለው ጠንካራ ነገር ነው። እርሱም የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ በግል ማግኘትን ይወክላል።

ይህም በግልህ ስታጠና የሚገለጥልህ ነገር ነው። ስለዚህ የሌላ ሰውን አመለካከት እየሰማህ እንደ ገደል ማሚቶ አትደግምም። መንጋውን ተከትለህ አትሄድም። መንጋውን ከተከተልክ አፈር እየበላህ ትኖራለህ። ልክ ዘፍጥረት ውስጥ እንዳለው እባብ።

63-0728 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሚስጥር መገለጥ ነው
“የእኔ ቤተክርስቲያን…” አትበሉ፤ “የእኔ ቤተክርስቲያን” የሚባል ነገር የለም።

አንድ ሰው አንድ ግለሰብ ነው! በሲኦል ያሉ አጋንንት በሙሉ ይህንን ትምሕርት ይቃወሙታል። በሲኦል ያሉ አጋንንት ሁሉ ይህንን እውነት ይቃወሙታል፤ ግን እውነት ነው።

ኢየሱስ፡- “ስማኝ ጴጥሮስ፤ አንተ እና ዮሐንስ እንዲሁም የተቀሩት ሕዝብ በሙሉ፤ እናንተ መገለጥን አግኝታችኋል፤ ስለዚህ አሁን ቤተክርስቲያን በሙሉ ድናለች” አላለውም።

እርሱን በግሉ ብቻ ነው የተናገረው። “እልሃለው” አንተን እልሃለው፤ እንጂ እላችኋለው አላለም። “አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለው።” ጴጥሮስ የሚለው ቃል ድንጋይ ማለት ነው። ድንጋይ ማለት “የመሰከረው” ወይም “የተለየው” ማለት ነው።

በአንድ የተለየ ድንጋይ፤ በአንድ የተለየ ነገር፤ አያችሁ፤ ተለይቶ የወጣ፤ ቤተክርስቲያን ተለይታ የወጣች እንደመሆኗ፤ በዚህ ድንጋይ ላይ በዚህ “መገለጥ”። “ሥጋ እና ደም አልገለጠልህም። ነገር ግን በዚህ መገለጥ ላይ ተለይቶ በወጣው ቡድን በእነርሱ ውስጥ ቤተክርስቲያኔን እሰራለው። የገሃነም ደጆች በሙሉ ቢሰበሰቡ ሊቋቋሟት አይችሏትም።”

“ከራሳችሁ አንድ ጸጉር እንኳ አይጠፈም። እናንተ የእኔ ናችሁ! በመጨረሻው ቀን ከሙታን አስነሳችኋለው፤ የዘላለምን ሕይወት እሰጠዋለው፤ በመጨረሻውም ቀን አስነሳዋለው።” አያችሁ፤ ይህ ነው መገለጡ። አስነሳቸዋለው ሳይሆን አስነሳዋለው ነው ያለው፤ ስለ ግለሰብ ነው የሚናገረው!

ስለ ቡድን ሳይሆን ስለ ግለሰብ ነው! ሲኦል በሙሉ ይቃወመዋል።

ኢየሱስ የፈለገው በራሳቸው አእምሮ ማሰብ የሚችሉና እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተከታትለው ፈልገው ማግኘት የሚችሉ ደቀመዛሙርትን ነው። እንደዚህ አይነቶቹ ደቀመዛሙርት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳች ጥርጣሬ የላቸውም። እያንዳንዱ ድንጋይ ራሱን ችሎ ይቆማል። እያንዳንዱ አማኝ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት በራሱ ማሰብ መቻል አለበት እንጂ ዝም ብሎ የቤተክርስቲያን ሃሳቦችን ወይም የሰው ልማዳዊ ወጎችን ወይም የሰዎችን አመራር ተቀብሎ መቀመጥ የለበትም።

ቤተክርስቲያኖች የመሪዎቻቸውን ሃሳብ ተቀብለው መኖር ነው የሚፈልጉት።

56-1207 ስጦታዎች
… ቤተክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን መንፈስ ሳይሆን የፓስተሩን መንፈስ ነው የሚቀበሉት። ይህ እውነት ነው። አንዳችን የሌላችን መንፈስ አያስፈልገንም፤ ይህ አስፈላጊ አይደለም። የሚያስፈልገን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ቤተክርስቲያን ሂዱና ፓሰሰተሩ እንዴት እንደሚያረገው ተመልከቱ። ከዚያም ጉባኤው በሙሉ ልክ እንደ ፓስተሩ ሲሆን ታያላችሁ።

ቤተክርስቲያንን እያፈረሰ ያለው ይህ ነው፤ ማለትም ሰውን ለመምሰል መሞከር።

ጴጥሮስ ሁልጊዜም በራሱ ለማሰብ ዝግጁ ነበር። የትኛውንም ቡድን ለመምሰል በመፈለግ አልታሰረም። ጴጥሮስ የራሱን መረዳት ወይም መገለጥ ቀጥታ ከእግዚአብሔር ነው የሚቀበለው። በሌሎች ሰውች አመለካከት ላይ ተደግፎ አያውቅም።

ጴጥሮስ የቡድኑ አባል ቢሆንም ግን በራሱ አእምሮ ለማሰብ ባለመፍራቱ ከእነርሱ የተለየ ነበር።

ኒቆላዊነት አንድ ቅዱስ ሰውን ከቡድን መካከል ከፍ የማድረግ ልማድ ነው። በዚያ ቡድን ውስጥ ትችት አይፈቀድም። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከባድ ጥያቄዎች መጠየቅም አይፈቀድም። ሰዎች ሁላቸውም አንድ ዓይነት ሃሳብ እንዲያስቡ በሚገደዱበት ቡድን ውስጥ አባል እንዲሆኑ እንጂ በራሳቸው እንዲያስቡ አይፈቀድላቸውም። የተለየ ሃሳብ ያለው ሰው ስለሚባረር ቡድኑ የተስማማበትን ሃሳብ እንደ ገደል ማሚቶ መድገም ብቻ ነው የሚፈቀደው። በእንደዚህ ዓይነት ቡድኖች መካከል ሰው የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አይቶ በራሱ መገለጥ ማግኘት አይችልም። የቤተክርስቲያን መሪው የተናገረውን በጭፍን ሰምቶ መቀበል ብቻ ነው የሚፈቀደው።

በሎዶቅያውያን ዘመን ውስጥ ይህ በቤተክርስቲያኖች ላይ የሰለጠነ የፓስተሮች አገዛዝ የተጻፈውን ቃል ከቤተክርስቲያን ገፍቶ እንደሚያስወጣው ኢየሱስ ያውቅ ነበር። ስለዚህ ጴጥሮስን በራሱ አእምሮ መረዳት ስለመቻሉ አድንቆታል። ጴጥሮስ አመለካከቱን የሚገዳደሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሲያቀርቡለት የሚደናገጥና አርተፊሻል ፈገግታው የሚደበዝዝበት ጮል ፓስተር አልነበረም።

ዮሐንስ 1፡44 በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና፦ ተከተለኝ አለው።

ኢየሱስ ደቀመዝሙር ሲመርጥ ያ ሰው እርሱን (ቃሉን) እንዲከተል እንጂ ሌላ ሰውን እንዲከተል አይደለም የሚፈልገው።

ዮሐንስ 1፡45 ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።

ቤተሳይዳ “ዓሳ የሚጠመድበት ቤት” ማለት ነው። ይህ የሚያሳየን ነገር አለ። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ “ሰውን አጥማጆች” እንዲሆኑ ነው የፈለገው፤ ስለዚህ የስሙ ትርጉም “ዓሳ የሚጠመድበት ቤት” ወደሆነው ከተማ ሄደ። የቤተሳይዳ ከተማ ከገሊላ ባሕር በሰሜን ዳርቻ ዓሳዎች የሞሉበት ንጹሕ ውሃ ያለበት ቦታ ነው።

ይህም በስተመጨረሻ ዓለም በሙሉ በሚሽነሪዎች ዘመን በወንጌል መረብ የሚጠመድበትን አዲስ ኪዳንን የሚያመለክት ተምሳሌት ነው።

የገሊላ ባሕር ውሃ እረፍት የሌላቸውንና ባዶ አእምሮዋቸውን በስግብግብነትና በራስ ወዳድነት ለመሙላ በሚያደርጉት ሙከራ በነውጥ ውስጥ የሚኖሩትን የዓለም ሕዝብ ይወክላል።

ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።

ዓሳ አጥማጅ ዓሳውን ከውሃ ውስጥ ጎትቶ ያወጣና ዓሳለው ከውሃው በላይ ወዳለው ዓለም “እንዲሻገር” በዚያም እንዲሞት ያደርገዋል።

ይህም ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኝ አድርገው የሚቀበሉ ሐጥያተኞች ከፍ ወዳለ መንፈሳዊ ደረጃ ተጎትተው እንደሚወጡና በዚያም ለራሳቸው በመሞት እግዚአብሔር ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠር እንደሚፈቅዱ ያመለክታል።

መጥምቁ ዮሐንስ ከሙት ባሕር በስተሰሜን ውሃው በጣም ጨውማ ከመሆኑ የተነሳ ለዓሳዎች የማይመችበት ቦታ ነበር የሚያገለግለው። ይህም አይሁድን ማዳን ያልቻለውን የአይሁድ ሕግ ያመለክታል፤ የአይሁድ ሕዝብ የሐይማኖር መሪዎቻቸውን እያደመጡ በመታለላቸው የተነሳ ሕዝቡ መሲሃቸውን ሊገድሉ ችለዋል። ሐይማኖተኛ ፓስተሮች ዛሬ ሕዝቡን በማሳሳት ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ትተው የሰዎችን ጥቅስ እንዲከተሉ ያደርጋሉ። ከዚያም ሕዝቡ ወደ ሰርጉ ግብዣ ሳይሆን ወደ ታላቁ መከራ እየሄዱ ካሉት ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ጎራ ይቀላቀላሉ።

ዛሬ የሜሴጅ ፓስተሮች ሕዝባቸውን ሲያታልሉ በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ማመን ትተው በጥቅሶች ላይ እንዲደገፉ ያደርጉዋቸዋል። በታማኝነት መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተሉ ሰዎችን ተግተው ስማቸውን ያጠፋሉ። ለዚህ ነው በመጨረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ውጭ የቆመው።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

ቤተክርስቲያኖች ከኢየሱስ ጋር እራት አይበሉም። ግለሰቦች ብቻ ናቸው እራት ከኢየሱስ ጋ ያሚበሉት። ከቤተክርስቲያን ጋር መመሳሰል እግዚአብሔርን አያስገርመውም።

ዮሐንስ 1፡45 ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።

ፊሊጶስ መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተል ሰው ነው። ፊሊጶስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በደምብ ያውቃል፤ ደግሞም ስለ መሲሁ የተነገሩ ትንቢቶችን አንድ በአንድ አጥንቷል። ፊሊጶስ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ በመምራት የሚያምን ሰው እንጂ ሰዎችን ወደ አንድ ሰው ወይም ወደ አንድ ነብይ አልነበረም የሚመራው። ስለዚህ ኢየሱስ ሐዋርያ እንዲሆንለትና ወደፊት ወደ ጌታ የሚመጡ ክርስቲያኖችን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እንዲመራለት ፈለገው። እውነት ተመስርታ የምትደላደለው እንደዚህ ነው። በአንድ ርዕስ ላይ የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተከታትለን ማጥናት አለብን። ፊሊጶስ ኢየሱስ መሲኁ መሆኑን ያወቀው በዚህ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በሙሴ ሕግ (የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ አምስት መጽሐፎች) ውስጥ የተጻፉ ትንቢቶችን እንዲሁም በሌሎች የብሉይ ኪዳን ነብያት የተጻፉ ትንቢቶችንም ይፈጽም ነበር።

ፊሊጶስ ብሉይ ኪዳንን አጥንቷል። ስለ መሲኁ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አንድ በአንድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት ይችልበታል። ወዲያው በኢየሱስ አመነ፤ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ስለ ኢየሱስ እንደሚናገር አይቷል።

“የዮሴፍ ልጅ” የሚለው አገላለጽ አሳዳጊው ላይ ያተኮረ ነው። ዮሴፍ በሥጋ የኢየሱስ አባት አልነበረም።

ሉቃስ 1፡34 ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

የኢየሱስ አባት መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ ለራሱ መኖሪያ እንዲሆን አካሉን በማርያም ማሕጸን ውስጥ ፈጠረ። ማርያም ለጽንሱ መያዣ ብቻ ሆና ነው ያገለገለችው። በኢየሱስ ውስጥ ያደረው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነበር። ከዚህ ጽንስ አድጎ ሙሉ ሰው የሆነው ልጁ ነው።

ዕብራውያን 10፡5 ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤
ዕብራውያን 2፡16 የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።

የሰው የሕይወት ዘር የወንድ እስፐርም ሴል ነው። ይህ የወንድ እስፐርም ሴል ከሴት እንቁላል ሥጋን ያገኛል።

እግዚአብሔር በማርያም ማሕጸን ውስጥ እስፐርም ዘር እና እንቁላል ፈጠረ። ከዚያም እግዚአብሔር መንፈሱን በዚህ ዘር ውስጥ ሰወረ።

ኢሳይያስ 45፡15 የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

እግዚአብሔር በአንድ ሴል ውስጥ ተሰወረ። ዓለም ሁሉ የማትበቃው ታላቁ አምላክ በትንሽዬ ጽንስ ውስጥ ተሰወረ። ሰይጣን በዚህ ተሞኘ። ይህ የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት መገለጫ ነው።

54-1212 በራሱ ማለ
እግዚአብሔር ዝቅ ብሎ በመውረድ ድንግል ማርያምን በመንፈሱ የጋረዳት ጊዜ እር እራሱ ሕይወት ሆነ። ሕይወት እንደ ጥላ ተዘረጋና በራሱ ዙርያ የደም ሴል ሰራ።

የደም ሴል ከወንድ እንደሚመጣ አሁን ሁሉም ሰው ያውቃል። አይደል? ይህ ልክ አይደል? ሕይወት ያለው በደም ሴል ውስጥ ነው፤ የደም ሴል የሚመጣው ደግሞ ከወንድ ነው እንጂ ከሴት አይደለም። ሕይወት ያለው በዚያ ነው፤ በወንድ እስፐርም ውስጥ ነው። ልብ በሉ። ከዚያ እግዚአብሔር እራሱ በድንግል ማርያም ማሕጸን ውስጥ መጥቶ በፈጠረው የደም ሴል እራሱን ከበበ።

እግዚአብሔር በሰዎች ጥረት አይመሰጥም፤ በቅንነት ቢያደርጉትም፤ ብዙ መስዋእት ቢሰዉም እንኳ አይገርመውም። ማርያም በማሕጸንዋ ውስጥ ለተፈጠረውና ላደገው ጽንስ ምንም ያደረገችለት ነገር የለም። እርሷ የነበራት አንድ ነገር ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማለትም ለቃሉ ራሷና ማስገዛት ብቻ ነው።

ዮሐንስ 1፡38 ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው።

የአሥሩ ቆነጃጅት ምሳሌ ክርስቲያኖችን በሁለት ጎራ ይከፍላቸዋል። እነርሱም፡- መብራታቸውን የሚያበሩበትና የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የሚያስተውሉበት የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ያላቸው እና መብራት የሚለኩሱበት ዘይት ስለሌላቸው ብርሃን የማያገኙ እና በዚህም ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ብዙ ጉዳዮችን መረዳት የማይችሉት ሰነፍ ቆነጃጅት ናቸው። እነዚህን ሰነፍ ቆነጃጅት መለየት በጣም ቀላል ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምሳሌ “ካሕን ያልሆነው ዳዊት ለምንድነው የገጹን ሕብስት በልቶ ያልተቀጣው? ነገር ግን መልካም የነበረው ንጉሥ ኦዝያን መቅደስ ውስጥ ገብቱ የካሕኑን እጣን ስላጠነ በለምጽ ተመቷል።” ብላችሁ ብትጠይቋቸው የዛሬ ክርስቲያኖች የሚሰጡዋችሁ መልስ አየሩን የሚያጨልም መልስ ነው። “ይህን ማወቅ አስፈላጊ አይደለም” “ምንም አይጠቅምም” “መዳኔ ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም” የሚል መልስ ይሰጡዋችኋል። ሁለት ችግር ነው ያለባቸው፡- አንደኛ አያውቁም፤ ሁለተኛ ደግሞ የማወቅ ፍላጎት የላቸውም። የራሳቸው ፓስተሮችም ይህንን ጥያቄ መመለስ ማብራራት አይችሉበትም፤ እነርሱም በራሳቸው ማሰብ ካቆሙ ቆይተዋል። ከቡድናቸው ውጭ ከሆነ ሰው ለመማር ደግሞ ፈቃደኞች አይደሉም፤ ምክንያቱም ከቡድናቸው ውጭ ከሆነ ሰው መማር ቤተክርስቲያናቸው ሙሉውን የእውነት ሚስጥር እንዳላወቀች ያሳያቸዋል። ሎዶቅያ ውስጥ ያሉት “ምንም አያስፈልገኝም” ይላሉ። መታረም አያስፈልጋቸውም ምክንያቱም “ሁሉንም ያውቃሉ”። ከቤተክርስቲያናቸው ውጭ የሆነ ሰው እንዲያስተምራቸው አያስፈልጋቸውም። በተቀመጡበት የመሃይምንት ጨለማ ውስጥ ተመችቷቸዋል። ስለዚህ እባካችሁ አትረብሹን ይላሉ። ይህም ከባድ እንቅልፍ የመተኛት ምልክት ነው።

ስለዚህ ልባሞቹ ቆነጃጅት የሚገነቡት በሰዎች ጥረት አይደለም። እግዚአብሔር ግን ለራሱ ሥጋን ያዘጋጃል፤ እርሷም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተችው እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ናት።

ዮሐንስ 5፡39 … መጻሕፍትን ትመርምራላችሁ

ዮሴፍ በማርያም ማሕጸን ውስጥ የተሰራውን ሕጻን ሊያሳድገው ተቀበለው። ስለዚህ ኢየሱስ የዮሴፍ የማደጎ ልጅ ሆነ። ዮሴፍ ግን የንጉሥ ዳዊት የልጅ ልጅ ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደ አፈጻጸሙ በመቀበል ያለ ወንድ ዘር በሆነው ልደት የተነሳ ከሰው አመለካከት ውጭ በሆነ መንገድ ዮሴፍ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ኢየሱስን የዳዊት ልጅ እና የአይሁድ ንጉስ እንዲሆን አበቃው። በእግዚአብሔር ሰፊ እቅድ ውስጥ ዮሴፍ መጫወት ያለበት ሚና ይህ ነው። እንደ ሰው ለማርያም እና ለሕጻኑ ኢየሱስ የሚበሉትን ማዘጋጀት ነበረበት። ኢየሱስ በ12 ዓመቱ ወደ መቅደስ ከሄደ በኋላ ግን ስለ ዮሴፍ ምንም የተባለ ነገር የለም። ዮሴፍ የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል፤ በዚያ ሰዓት ሕጻኑን የማሳደጉ ትርጉም ባይገባውም እንኳ።

ኢኮንያን የዳዊት የልጅ ልጅ ነበረ ግን በጣም ክፉ ሰው ስለነበረ እግዚአብሔር ከእርሱ ልጆች አንዳቸውም እንኳ የአይሁድ ንጉስ እንደማይሆኑ ተናገረ። ይህም የዳዊትን ሥርወ መንግሥት በልጁ በሰሎሞን በኩል እንዳይቀጥል አደረገው። በዚህ ምክንያት ዮሴፍ ከኢኮንያን የልጅ ልጆች ስለተወለደ ንጉስ መሆን አልቻለም።

ኤርምያስ 22፡28 በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን?

እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?

30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።

ነገር ግን የዳዊት የመጀመሪያ ልጅ ናታን ወደ ማርያም የሚደርስ የዘር ሃረግ አለው። ማርያም ለዚህ ነው ወደ ኤልሳቤጥ ሄዳ ሦስት ወር ቆይታ የመጣችው፤ ስዚህ ዮሴፍን ስታገባው የሶስት ወር ነፍሰጡር ነበረች። ይህም ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል። ስለዚህ ኢየሱስን ሳይወልደው በማሳደጉ ዮሴፍ በሕጋዊ መንገድ ከናታን የዘር ሃረግ የመጣ ልጅ ሊኖረው ችሏል፤ እርሱም በኢኮንያን ላይ ከታወጀው እርግማን ነጻ የሆነ ልጅ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ነው የአይሁድ ንጉስ መሆን የሚችለው፤ ምክንያቱም የነገስታቱ የዘር ሃረግ በኢኮንያ አብቅቷል።

ከዚህ በጣም አስፈላጊ ትምሕርት እንማራለን። እግዚአብሔርን በፍጹም ፈቃዱ ውስጥ ልናገለግለው የምንችለው ቃሉን በመፈጸም ብቻ ነው። ብዙውን ጊዜ እንደ ዮሴፍ መጽሐፍ ቅዱስን የመከተልን አስፈላጊነት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን አንገነዘብም። ነገር ግን ምን ጊዜም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ስንፈጽም የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ አንድ እርምጃ እንዲሄድ አስተዋጽኦ እያደረግን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ማመንም ሆነ ማድረግ ትልቅ አደጋ አለው።

ዮሐንስ 1፡47 ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።

ናዝሬት ክፉ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ነበረች። በዚያች ከተማው ውስጥ የሚፈጸመው ክፉ ሥራ እና ወንጀል በጣም ብዙ ነው። ናዝሬት ማለት እንደ ዛሬዋ በቁማር እንደምትታወቀው የላስቬጋስ ከተማ ናት። ሰው ከዚህ ዓይነት ከተማ መልካም ነገር ይመጣል ብሎ አይጠብቅም። ግን ከዚህ ደግሞ ሌላ ትምህርት እንማራለን። ሰውን ከመጣበት ቦታ የተነሳ ልንፈርድበት አይገባንም። ከዚህች ክፉ ከተማ ውስጥ ከሰዎች ሁሉ ፍጹም የሆነው ሰው መጣ።

ዮሐንስ 1፡48 ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።

ኢየሱስ በናትናኤል ልብ ወይም አእምሮ ውስጥ ያለውን ሃሳብ አየ። ይህ አይነቱ ችሎታ ለአይሁድ መሲኁን የሚለዩበት ምልክት ነው።

ኢየሱስ እንዲህ ማለት ነው፡-“እኔ ከዛሬ በፊት አይቼህ አላውቅም ግን ስለ አንቱ ሁሉን አውቃለው። አንተ ምንም ተንኮል የለብህም። በጭራሽ ተንኮለኛ ሰው አይደለህም።”

ኢየሱስ በጊዜ ወደ ኋላ ሄዶ የሰዎችን የኋላ ታሪክ ማየት እንደሚችል ደግሞም በዓይን የማይታየው የመንፈስ ዓለም ውስጥ በመግባት የሰውን ሃሳብና ስሜት መመርመር እንደሚችል አሳየ።

ዮሐንስ 1፡49 ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።

ናትናኤልም እንደሚጠበቀው ደንግጧል። አግኝቼው የማላውቀው ሰው እኔን እንዴት ሊያውቀኝ ይችላል? ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ይሄ ኢየሱስ ምን ዓይነት ሰው ነው?

የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር፤ ሁሉን ማየት እንደሚችለው ንሥር አድርጎ ይገልጥልናል።

ናትናኤል በቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት ውስጥ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አካል የሚሆኑትን ግለሰቦች ሁሉ የሚወክል አንድ ግለሰብ ነው። ስለዚህ ሁላችንም መረዳት እንዳለብን እርሱም ኢየሱስ ከሰዎች ውስን እይታ የሚበልጥ የማየት ችሎታ እንዳለው ተረድቷል። ኢየሱስ ጊዜን ፈጥሯል፤ ደግሞም በአምስተኛው ቀጠና ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ዓለምም ፈጥሯል። ስለዚህ ከሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ባለ ቀጠና ውስጥ ስለሚኖር በጊዜ ወደ ኋላ ማየት ይችላል፤ ወደ ፊት መመልከትም ይችላል። እኛ ሰዎች ግን የአሁኗን ቅጽበት ብቻ ነው ማየት የምንችለው። ናትናኤል ወዲያው ኢየሱስ አስደናቂ ሰው መሆኑ ገባው።

ነገር ግን ናትናኤልን የሚያስደንቀው ሌላም ተጨማሪ ነገር ሆነ። ኢየሱስ ናትናኤልን በፍጥረታዊ ዓይኖቹ ሊያይ ከሚችልበት በጣም እሩቅ በነበረ ሰዓት ሊያየው መቻሉ ናትናኤልን በጣም አስደንቆታል።

ስለዚህ ኢየሱስ የጌዜም የርቀትም ጌታ ነው (ፍጥረታዊው ዓለም የሚለካው በጊዜ እና በቦታ ነው)፤ ከዚያም በላይ መንፈሳችንና ውስጣዊው ሃሳባችንንም ሁሉ ማየት ይችላል። ይህ በሃሳባችን ውስጥ ያለው የመንፈስ ክልል የመልካም እና የክፉ እውቀት ቅልቅል ነው። እኛ ሰዎች ሁል ጊዜ በእውነት እና በስሕተት መካከል ውሳኔ ማድረግ አለብን።

ዮሐንስ 1፡50 ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።

1ኛ ነገሥት 8፡39-40 … በማደሪያህ በሰማይ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።

የልብን ሃሳብ መግለጥ የሚችል ሰው መሲኁ መሆን አለበት። እግዚአብሔር አብ መንፈስ ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ በሰው ውስጥ ቢያድር ያ ያደረበት ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

ናትናኤል አንድ ታላቅ መገለጥ አገኘ። እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ የሚኖረው በኢየሱስ ውስጥ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ወዴት ነው የሚኖረው?

ኢየሱስ ለትልቁ መገለጥ ዓይኖቹን ሊከፍትለት ፈለገ። እግዚአብሔር በጸጋው ለእያንዳንዴ ዳግመኛ ለተወለደ ክርስቲያን ከመንፈሱ የተወሰነ መጠን ሰፍሮ ይሰጣል። ከእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ተሰፍሮ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በልቡ ውስጥ እንዲኖር የተሰጠው መንፈስ በ2,000 ዓመታት ውስጥ ለኖሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ተሰጥቶ በስተመጨረሻ ወደ አንድነት ሲሰበሰብ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ይሆናል።

ኢየሱስ መሲኅ እንደመሆኑ በአይሁዳውያን መካከል በአካል የሚኖርበት ሰፈር ወይም ቤት የትጋ እንደሆነ ማወቅ ቁምነገር አልነበረም።

ቁምነገሩ አይሁዳውያን አልቀበል ሲሉት ለመሞት ማሰቡ ነበር።

በቤቱ ውስጥ ከተወለደ ሁለት ዓመቱ ላይ ሰብዓ ሰገል ሲመጡ ከርቤ የሰጡት ለዚህ ነበር። የሞቱ ሰዎች ሲቀበሩ እሬሳቸው አስቀያሚ ሽታ ስለሚፈጥር ከርቤ ጥቅሙ ሽታውን መቀነስ ነው። ሰብዓ ሰገል ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ዓላማ ለሐጥያታችን ለመሞት መሆኑ ገብቷቸዋል።

የወርቁ ስጦታ ደግሞ ትርጉሙ ኢየሱስ በሥጋ የመጣ እግዚአብሔር መሆኑን እውቅና መስጠታቸውን ያመለክታል።

እጣኑ እሳት ውስጥ ሲገባ ደስ የሚል መዓዛ ያለው ጭስ የሚፈጥር ከዛፍ የሚገኝ የደረቀ ፈሳሽ ነው። የሚቃጠል መስዋእት ውስጥ በእሳት የተቃጠለ ሥጋ ሽታው ደስ አይልም። የእጣኑ መዓዛ ግን የመስዋእቱን ሽታ ደስ እንዲል ያደርገዋል።

ስለዚህ የሰብዓ ሰገል ስጦታ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ማወቃቸውን ያሳያል።

እርሱ የእግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ ነው፤ የተገለጠውም ደስ የሚያሰኝ መስዋእት ለማቅረብ ነው። ሰዎችን በሐጥያት ከመሞት ሊያድን ነው የመጣው። ሰብዓ ሰገል የእግዚአብሔርን ሰፊ እቅድ ተረድተዋል። ለዚህ ነው የጥበብ ሰዎች የሆኑት።

ከዚያም እግዚአብሔር መንፈሱን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ውስጥ ሲያፈስሰው፤ ኢየሱስም መንፈሱን በሙሉ በ2,000 ዓመታት ውስጥ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ልበ ውስጥ ሊያፈስሰው ወሰነ።

2ኛ ዜና 6፡18 በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?

ናትናኤል ያየውና የሰማው ሁሉ ከአእምሮው በላይ ሆነበት። ስድስተኛው ቀጠና መልካም ነገር ብቻ የሚገኝበት (ክፉ የሌለበት) እጅግ በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ሰሎሞን ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ብሎ ነው የሚጠራው። ሃሳቡን እንኳ ለመረዳት ከሰዎች አእምሮ በላይ ነው። ይህ ሁሉ ሰፊ ዓለም ግን እግዚአብሔርን ሊይዘው አይችልም።

እንደዚያም ሆኖ ግን ይህ ኢየሱስ የተባለ ሰው በሰውነቱ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሙላት ተሸክሟል!

ቃላት ሊገልጹት አይችሉም። ለእርሱ የምናቀርባቸው የምስጋና ቃላት በሙሉ ትክክለኛ ናቸው ግን እጅግ በጣም ያንሱበታል። ኢየሱስ እንዲሁ ከሰው አእምሮ ወይም በቃላት ከመግለጽ አቅም በላይ ነው።

እና የት ነው የሚኖረው?

እውነተኛ መኖሪያው ልትወለድ ባለችው በቤተክርስቲያን ልብ ውስጥ ነው፤ በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ለተገለጠላቸው የእግዚአብሔር ቃል በሚታዘዙ አማኞች ልብ ውስጥ ነው መኖሪያው። እርሱ ራስ ነው፤ በዓለም ዙርያ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ደግሞ የክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ናቸው።

ዮሐንስ 1፡51 ኢየሱስም መልሶ፦ ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው።

ናትናኤልን ከርቀት ማየቱ ኢየሱስ በርቀቶች ሁሉ ላይ ስልጣን እንዳለው ያሳያል። በአንድ ጊዜ የፈለገበትን ቦታ የፈለገበትን ዘመን ማየት ይችላል። ደግሞም ከአምስተኛው የሰው መንፈስ ቀጠና በላይ ነው የሚኖረው፤ ምክንያቱም አምስተኛው የሰው መንፈስ ቀጠና የመልካም እና የክፉ ድብልቅ ነው።

ዮሐንስ 1፡52 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።

መላእክት። በብዙ ቁጥር ነው የተገለጸው። ሁለቱም።

ይህ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር በሰማያዊ ስፍራ ከፍ ብሎ ሁሉን በሚያዩ ዓይኖቹ ድንቅ እይታ እያየ እንደሚበርር ንሥር የሚገልጥልን የዮሐንስ ወንጌል ነው።

ልክ የመጀመሪያው ምዕራፍ ገብቶናል ብለን ማሰብ ስንጀምር ኢየሱስ እኛ የምናውቀው እውቀት ምን ያህል ትንሽ መሆኑን እንድናስተውል ሌላ ገጽታውን ያሳየናል። በምዕራፉ ውስጥ የመጨረሻው ቁጥር ጭንቅላታችንን እንድናክክ ያደርገናል።

የሰው ልጅ መሆኑ ዓላማው ሰውን ለማዳን የሥጋ ዘመድ ቤዛ ሆኖ መምጣቱ ነው። ስለዚህ መስዋእት ከሚሆነው ከሥጋዊ ሰውነቱ ባሻገር ወደ መንፈሳዊ አካሉ ማለትም በየዘመናቱ በቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት ውስጥ በየስፍራው ሁሉ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎችን ወንጌሉ ሲሰራጭ በያሉበት ያያቸዋል።

ዮሐንስ 5፡3 በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።

የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በውስን አእምሮዋቸው ሊያስተውሉ የማይችሏቸው ብዙ ሚስጥሮች ሞልተውበታል።

ሆኖም በያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ክርስቲያኖች ዲያብሎስን ለመዋጋት እንዲችሉ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ማወቅ አለባቸው።

ዮሐንስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ብዙውን የተጻፈውን ሚስጥር ተረድታለች። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሌሎች ያልታወቁ ሚስጥራትም ነበሩ። ሁሌም አንድ የማናውቀው ነገር ይኖራል፤ ስለዚህ ዲያብሎስም ሊያውቀው አይችልም። እግዚአብሔር እቅዱን ሁሉ ግንጥ አለማድረጉ ሰይጣን ላይ ስልታዊ ማደናገሪያ ለማድረግ ያመቸዋል።

ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ለመንጠቅ መቼ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም።

ራዕይ 8፡1 ላይ ሰባተኛው ማሕተም ሲፈታ ጸጥታ ብቻ እንደሆነ ይናገራል።

በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩት ቃል አልተጻፈም።

በራዕይ ምዕራፍ 19 ውስጥ አዲሱን የኢየሱስ ስም ማንም እንዲያውቀው አልተፈቀደለትም

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እነዚህን ሚስጥራት አላወቀቻቸውም።

ነገር ግን እስከ ሶስተኛው ሰማይ የተነጠቀ ጳውሎስ የተባለ መልአክ ወይም መልእክተኛ ነበራቸው።

2ኛ ቆሮንቶስ 12፡2 ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ።
3 እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤
4 ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።

መላእክት እና የዳኑ ነፍሳት ባሉበት በስድስተኛው ሰማይ ክልል ውስጥ ያሉ ነገሮች ውስን የሆነው አእምሮዋችን ሊያስተውል ከሚችለው በላይ የመጠቁ የረቀቁ ከመሆናቸው የተነሳ የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን መልአክ ወይም መልእክተኛ ጳውሎስ በዚያ የሰማውን በሙሉ ሊነግረን አልቻለም።

ሆኖም ግን ጳውሎስ የአዲስ ኪዳንን ግማሽ መጸሕፍት እንዲጽፍ ያስቻለውን ብዙውን መገለጥ አግኝቷል።

እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን የኢየሱስ አካል (እርሱ በአማኞች ልብ ውስጥ ስለሚኖር) የሆነችዋ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የተለያዩ የሰይጣን ጥቃቶችን መቋቋም የሚያስችላትን ምሪት ከሰማይ የሚቀበል መልእክተኛ ወይም መልአክ ይኖረዋል።

ሰባተኛው መልአክ ወይም መልእክተኛ ማርች 8 ቀን 1963 በታክሰን ከተማ አሪዞና ውስጥ ሳንሴት ፒክ አካባቢ ወደ ሰባት መላእክት ጉባኤ ተነጥቆ ከዚያ በኋላ ወደ ጄፈርሰንቪል ኢንዲያና በመመለስ በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፈውን የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ገልጦ እንዲያስተምር ተልኳል።

እነዚህ ሰባት መላእክት እንያንዳንዳቸው በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ መልእክተኞችን በዘመናቸው ውስጥ እንዲመሩ ሊያግዟቸው የተላኩ ናቸው። ወደ ሰማያዊ ስፍራ የተነጠቁትም የመጀመሪያው ዘመን መልእክተኛ እና የመጨረሻው ዘመን መልእክተኛ ብቻ ናቸው።

ሌሎቹ አምስት መልእክተኞች በአገልግሎታቸው ሲመራቸውና ሲያግዛቸው የነበረውን መልአክ አላወቁም። እነዚህ ሰባት ሰዎች በዘመናቸው ውስጥ የሚመጡትን ስሕተቶች እንዲለዩ እና የሚያስችል ሰማያዊ መገለጥ እና ዘመናቸውን ለመምራት የሚያስፈልጉ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የገለጡላቸዋል። እነዚህ መገለጦች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ሳትጠፋ የምትቆይበትን እውቀት ያቀብላሉ።

ኢየሱስ ለናትናኤል የእግዚአብሔርን ሰፊ እቅድ ያስተውል ዘንድ ዓይኑን ከፈተለት። ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የእግዚአብሔር መንግስት ናቸው። በምድር ላይ የሚሆነው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል የሚደረገው ታላቅ ትግል ነጸብራቅ ነው።

ኢየሱስ ማለትም የተጻፈው ቃል በሰማይ እና በምድር መካከል ሊያገናኝ የቆመ ድልድይ ነው። መልእክተኞቹ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል መገለጥ በዘመናቸው ለሚኖሩ እውነተኛ አማኞች እንዲያመጡ ከሰማይ የሆነ ማስተዋል ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ መልአክ ወይም መልእክተኛ ኢየሱስ በተጻፈው ቃል ውስጥ ለዚያ ዘመን የት እንደሚገኝ ፈልጎ ማግኘት ይጠበቅበታል።

ስለዚህ የኢየሱስ መኖሪያ በዚያ ነው። ለዘመኑ በተጻፈው ቃል መገለጥ ውስጥ ነው ኢየሱስ የሚኖረው።

የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን የተረዳችውን የተጻፈውን ቃል መረዳት ብንችል ሙሽራችንን አግኝተነዋል ማለት ነው።

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23