ዮሐንስ ምዕራፍ 03. ሐጥያትን ለማሸነፍ ብቁ የሆነ አንድም ሰው የለም
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 3፡1 ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦
ፈሪሳዊ “የተለየ” ማለት ነው።
“ኒቆዲሞስ” ደግሞ “የሕዝብ ገዢ” ማለት ነው።
ፈሪሳውያን እራሳቸውን ወግ አጥባቂ ሐይማኖታዊ ድርጅት አድርገው ከሕዝብ ለይተው ነበረ።
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የመጀመሪያው ቁጥር የሐይማት ዓለም የሚያመጣውን ችግር በቀጥታ ይጠቅሳል፤ ይህም ችግር ሰዎች መሪ ወይም ገዥ ሲሆኑ ሕዝቡ በመሪዎች ውስን እውቀት ምክንያት በመረዳት ተገድቦ እንደሚቀር ያሳያል።
ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ሰዎች በተሻለ ጠለቅ ባለ መረዳት እንደሚያስተውሉ ያስቡ ነበር።
አይሁዳውያን ተማርከው ባቢሎን ውስጥ ይኖሩ በነበረ ጊዜ ከቤተመቅደሱ ርቀው ነበር። የዚያን ጊዜ አይሁዳውያን በሰውኛ ጥበብ ምኩራብ ብለው የሚጠሩዋቸውን “ቤተክርስቲያኖች” ፈጠሩ፤ እያንዳንዱንም አንድ ሰው እንዲያስተዳድራቸው ወሰኑ። ይህም ጥሩ ሃሳብ ይመስል ነበር። ይህ የአንድ ሰው መሪነት የነበረው አሰራር ፈሪሳውያን በሚባሉ ቡድኖች ተጠለፈ።
ምኩራቦች ላይ ሰው መሪ ሆኖ ሲሾም መሪው የግል አመለካከቱን እና ልማዳዊ አስተሳሰቦችን ጉባኤው ላይ መጫን ጀመረ። ሰው “እኔ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ” በሚልበት ፍልስፍና ፈሪሳውያን መሪዎች ጉባኤያቸውን ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አለያይተው ሕዝቡ ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እየፈጸመ መሆኑን እንዳያስተውሉ አደረጓቸው። አይሁዳውያንም ኢየሱስን መከተል ትተው ከመሪዎቻቸው ከፈሪሳውያን ጋር ተጣበቁ።
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ ፈሪሳውያን ከአይሁድ ሕዝብ ብዙዎቹን በምኩራቦች አማካኝነት በቁጥጥራቸው ስር አድርገዋል። ልክ ዛሬ አንድ ፓስተር አንድ ቤተክርስቲያንን እንደሚመራው ነው አንድ ፈሪሳዊ ምኩራብን የሚመራው። እነዚህ መሪ ሰዎች የሕዝቡን አእምሮ በመቆጣጠር በስተመጨረሻ ሕዙቡ ኢየሱስን እንዲገፉ አደረጉ።
ጉባኤው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሪው ወይም የአስተዳዳሪው ተገዥ ይሆናል። ከዚያ በኋላ የተማረኩ ምርኮኛ ሕዝብ ይሆናሉ።
የኒቆላዊነት መነሻው ይህ ነው፤ ኒቆላዊነት ማለት በሕዝቡ ወይም በጉባኤው ላይ ገዥ መሆን ነው። አንድ ቅዱስ ሰው በቤተክርስቲያን ላይ ባለ ስልጣን እንዲሆን መሾም ነው።
እግዚአብሔር ይህንን ይጠላል።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
ከዚህ የተነሳ ግራ የሚያጋባ ነገር ይፈጠራል። ቤተክርስቲያን ሰዎች ለኢየሱስ ዳግም ምጻት እንዲዘጋጁ ማድረግ ሃላፊነቷ ሆኖ ሳለ ሰዎች ወደ ጌታ እንዲመጡ እና እንዲድኑ ትመራቸዋለች፤ ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ እነዚሁ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንዳያምኑ ታደርጋለች።
ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ሊያናግር በመጣ ጊዜ ስለ ራሱ አንድ ነገር ተገነዘበ፤ ይህም ቁልፍ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እውቀት እንዳልነበረው ነው። ከዚህም የተነሳ በምኩራብ ውስጥ ያሉ ሰዎች በመሪዎቻቸው ስሕተት እና መሃይምነት ታስረው እንደሚኖሩ ገባው። ዛሬ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተመሳሳይ ችግር አለ። በዚህ ዘመን በዓለም ውስጥ 45,000 የተለያዩ ዲኖሚኔሽናል እና ዲኖሚኔሽናል ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ያሉ ሲሆን እነዚህ ሁሉ እያንዳንዳቸው እኔ ነኝ ትክክለኛ ይላሉ። ይሄ ከገቡበት በቀላሉ የማይወጡበት መንፈሳዊ አረንቋ ነው።
ይህ የአይሁድ ሕዝብን የሚገዛ የሕዝብ አለቃ እግዚአብሔርን ለማገልገል ካለው ቅን ፍላጎት የተነሳ ወደ ኢየሱስ (ወደ እግዚአብሔር ቃል) ሲመጣ እራሱ ስለምን ያወራ እንደነበር አለማወቁን ተገነዘበ። ለዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የነበረውን የልብ ሃሳብ ምን እንደሆነ እንኳ አላወቀም። መሃይም የቤተክርስቲያን መሪዎች ከአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አላቸው። ከስልጣናቸው መውረድ እምቢ ይላሉ።
ዮሐንስ 3፡2 መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።
በሌሊት ተደብቆ ወደ ኢየሱስ መጣ። ማንም እንዳያየኝ ብሎ ፈርቷል። ይህም በሐይማኖታዊ ዓለም ውስጥ ያለውን ፍርሃት የሚያሳይ አሳዛኝ ክስተት ነው። ሰዎች የሆነ ነገር ልክ እንዳልሆነ ያውቃሉ ግን ፊት ለፊት ስሕተት ነው ብለው ለመናገር ይፈራሉ። በተጨማሪም በኢየሱስ ማለትም በእግዚአብሔር ቃል መታረም እንደሚያስፈልገው ገብቶታል ነገር ግን በግልጽ መታረም ያስፈልገኛል ለማለት ይፈራል። በዚህ ዘመንም ሰው የተናገረውን እየጠቀሱ የመናገር ውጤቱ ይህ ነው።
ዛሬ ቤተክርስቲያኖች “… ተብሎ ተጽፏል” የሚለውን ቃል መቀበል አይፈልጉም። በትክክል መጽሐፍ ቅዱስን እንከተል የሚል አቋም ያለው ሰው እንደ አፈንጋጭ ይቆጠራል።
ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ቢያምኑበት ቤተክርስቲያንን ፓስተር አይመራትም ነበር። በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ቤተክርስቲያን በፓስተር ተመርታ አታውቅም። ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በሰው ቤት ውስጥ የሚሰበሰቡ የጥቂት ሰዎች ቡድን ነበሩ።
ሮሜ 16፡5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
ቤተክርስቲያኖች በመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው መሰብሰብ ያለባቸው። ይህ ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ጠቃሚ ምክር ነው።
ኢየሱስ ልዩ ሰው መሆኑን ኒቆዲሞች አስተውሏል። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑም ገብቶታል።
“… እናውቃለን” የሚለው ንግግር ፈሪሳውያን በሙሉ ኢየሱስ እውነተኛ መሆኑን እንዳወቁ ይገልጻል። ነገር ግን ምኩራቦቻቸውን ደግሞ ምን እንደሚያደርጓቸው ግራ ገብቷቸዋል፤ ምክንያቱም ምኩራቦች የገቢ ምንጮቻቸው ነበሩ።
ስለዚህ ቤተክርስቲያኖችም መጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሆኑን አይክዱም ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዳዊ ትምሕርቶቻቸውን ሙጭጭ ብለው ይይዟቸዋል። ክሪስማስ፣ የገና ዛፍ፣ ዲሴምበር 25፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ካርዲናል፣ ፖፕ፣ የቤተክርስቲያን ሕንጻ፣ አንድ አምላክ በሶስት አካላት፣ አንድ ባህሪ፣ የመለኮት ሁለተኛው አካል፣ ሥላሴ፣ የጥንቸል እንቁላል፣ ኤቮልዩሽን፣ ቢግ ባንግ።
ስለዚህ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከፊሉን የሚያምኑበት፣ ቀሪውን እንደ አላስፈላጊ ትተው የሚያፉበት፤ ከዚያም ሌላ ከአረማውያን ሐይማኖቶችና ስሕተት ካለባቸው ሳይንሳዊ ቲዎሪዎችም (ግምቶች) ጨምረው በመውሰድ የሚያምኑበት አደገኛ ዘመን ውስጥ ነን።
ደግሞ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስን ከሌላ ጥቅስ ጋር አዛምደን አስተያይተን መተርጎምም ትተናል።
በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እናጠምቃለን ኢየሱስ እንደዚህ አጥምቁ ብሏል ብለን።
እዚህ ቃል ውስጥ ግን ስም አልተጠቀሰም። ሶስት ማዕረጎች ብቻ ናቸው የተጠቀሱት።
ማቴዎስ 28፡19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥
በኢየሱስ ስም ማጥመቅን ልክ እንዳልሆነ ቸል እንለዋለን፤ ምክንያቱም እንደዚህ ብሎ የተናገረው ጴጥሮስ ነው ብለን፤ ጴጥሮስ ደግሞ ከኢየሱስ እኩል አይደለም።
በዚህ ቃል ውስጥ ስም ተጠቅሷል፤ እርሱም የኢየሱስ ስም ነው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ … አላቸው።
ጳውሎስም በጌታ በኢየሱስ ስም ያጠምቅ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 8፡16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር … ።
አሁንም ስም ተጠቅሷል፤ እርሱም የኢየሱስ ስም ነው።
ስለዚህ ሐዋርያቱ ለጥምቀት የተጠቀሙት ስም የኢየሱስ ስም ነው። እኛ ግን ተሳስተዋል እንላለን።
ጳውሎስ ግን ከዚህ የተለየ ወንጌል ብንሰብክ የተረገምን እንደምንሆን ተናግሯል። ስለዚህ ጳውሎስ ተሳስቷል ማለት አንችልም።
ገላትያ 1፡9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
ከጳውሎስ ጋር አልስማማም የምትሉ ከሆነ ከባድ ችግር ውስጥ ናችሁ።
ጳውሎስ የምናደርገውን ማንኛውንም ነገር በኢየሱስ ስም ማድረግ እንዳለብንም ነግሮናል።
ቆላስይስ 3፡17 እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
እዚህ ቃል ውስጥም አንድ ስም ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ እርሱም የኢየሱስ ስም ነው።
“በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ።” ጥምቀት በሥራ የሚከናወን ድርጊት ሲሆን በቃል ንግግርም የታጀበ ነው።
ስለዚህ ጥምቀት በሥራም በቃልም የሚከናወን ድርጊት ነው።
ከዚህም የተነሳ ጳውሎስ ያስተማረው ጥምቀት ትክክለኛ ነው፤ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ ግን ስሕተት ነው (ምክንያቱም በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ስንል ምንም ስም አልጠራንም)።
ጥምቀት የሞት፣ የቀብር እና የትንሳኤ ተምሳሌት ነው።
የሞተው፣ የተቀበረውና የተነሳው ኢየሱስ ብቻ ነው።
አብ እና መንፈስ ቅዱስ አልሞቱም፣ አልተቀበሩም፣ ከሙታንም አልተነሱም። ታዲያ ጥምቀት ውስጥ እንዴት ይገቡበታል?
ቁልፍ የሆነው ጥያቄ የሚከተለው ነው፡- “የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስም ማነው?”
ለዚህ ጥያቄ ቤተክርስቲያኖች መልስ የላቸውም። በመለኮት ውስጥ ላሉት ሶስት አካላት አንድ ስም መስጠት አይችሉም።
የክርስቶስ ሐዋርያት ስሙ ኢየሱስ ነው ብለዋል።
መለኮትን እንዴት ነው የተረዱት?
እንደ አብ እግዚአብሔር ከአይሁዳውይን በላይ ነበረ። ያህዌህ ብለው ይጠሩት ነበር። ይህ ስም ጌታ ማለት ነው።
እንደ ልጅ ወይም ወልድ ደገሞ እግዚአብሔር ከአይሁዳውያን ጋር ነበረ። እነርሱም ኢየሱስ ብለው ጠሩት።
እንደ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በውስጣችን ነው፤ በመሆኑም እኛን “የተቀባን” ያደርገናል፤ ይህም በግሪክ ቃል ክርስቶስ ማለት ነው። ክርስቶስ።
የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ኢየሱስ ነው። ነገር ግን የትኛው ኢየሱስ መሆኑን ለመለየት ቢያንስ በስሙ ላይ አንድ ማዕረግ መጨመር ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ብዙ ሃገሮች ኢየሱስ ወይም ጂሰስ የሚለውን ስም የሰዎች ስም አድርገው ይጠቀማሉ።
ስለዚህ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ጌታ ኢየሱስ፤ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወይም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሐዋርያቱ ተሳስተዋል ወይም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች አስያፈልጉም ከማለት በዚህ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ሁሉ አስማምተን መቀበል እንችላለን። ሐዋርያትን ያስተማራቸው ኢየሱስ እራሱ ስለነበር እርሱ ሲናገር ምን ማለቱ እንደሆነ ተረድተዋል።
ዮሐንስ 3፡3 ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
የእግዚአብሔርን መንግስት “ማየት” ማለት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እና ጥቅስን ከጥቅስ ጋር አያይዞ በማዋሃድ አንድ ወጥ የሆነ ግጭት የሌለበት መልእክት ማግኘት መቻል ነው።
መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው እውነት።
ዮሐንስ 17፡17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
የእኛ ድርሻ መጽሐፍ ቅዱስን ማስተካከል፣ ማሻሻል ወይም መግፋት አይደለም። የእኛ ድርሻ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸውን ቃሎች ማገናኘትና ማያያዝ ነው። ይህን ማድረግ የምንችለው ግን ዳግመኛ ከተወለድን ብቻ ነው። ዳግመኛ ለመወለድ እግዚአብሔርን ከመንፈሱ ሰፍሮ በልባችን ውስጥ እንዲያሳድር ንሰሃ መግባት አለብን። ከዚያም ያ መንፈስ ልባችንን ለማንጻት በውስጣችን ያድጋል። ከዚያ በኋላ መንፈሱ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እስኪቆጣጠር ድረስ ሲያድግ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን እንጠመቃለን። ከዚያም በመቀጠል መንፈሱ በውስጣችን ይበልጥ እያደገ ሲሄድ ለዘመናችን የተገለጠውን ቃል ማየት ወይም ማስተዋል እንችል ዘንድ በክርስቶስ አካል ውስጥ በተመደበልን ቦታ ያስቀምጠናል። ከዚያ በኋላ ነው በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት እግዚአብሔር ምን እየሰራ እንደሆን ማየት የምንችለው።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረናል። በራሳችን ሰውኛ ጥበብ በመመራት የእግዚአብሔርን መንገድ ወይም ፈቃድ ማግኘት አንችልም።
ስለዚህ መውሰድ የሚያስፈልገን እርምጃ የራሳችንን ፈቃድ እንደ መስዋእት ለኢየሱስ አሳልፈን መስጠት ነው። የዛን ጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ የእኛን ውስን ፈቃድ ይተካዋል፤ እግዚአብሔርም ዓላማውን ለማስፈጸም በእኛ መስራት ይጀምራል፤ የእግዚአብሔርም ዓላማ እኛ ለመስራት ከምናስበው እጅግ የተለየ ነው። እግዚአብሔር ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይፈልጋል።
ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር እርሱ እንደሚያስበው እንድናስብ ይፈልጋል። እግዚአብሔር የሚፈልገው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ እንድናምን ነው። እግዚአብሔር ማንም ሰው በኢየሱስ እና በእኛ መካከል እንዲቆም አይፈልግም።
ዮሐንስ 3፡4 ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።
ኒቆዲሞስ ከመንፈስ ስለመወለድ አንዳች የሚያውቀው ነገር አልነበረም። እርሱ የሚያውቀው በስጋ ስለመወለድ ብቻ ነበር።
በስጋ መወለድ ውስጥ ግን ችግር አለ፤ ምክንያቱም ሁላችንም እንድንሞት ያደርጋል።
ድንጋል ማርያምን መሆን ያለባት ሔዋን ነበረች። ሔዋን በመንፈስ ቅዱስ ትጋረድና ኢየሱስ ከእርሷ ሊወለድ ይችል ነበር። ከዚያም እርሱ ያድጋል፤ ሐጥያት የሚባል ነገር በምድር ላይ ስለማይኖር መሞትም አያስፈልገውም ነበር። ከዚያ በኋላ እርሱ ቃሉን በመናገር ብቻ ቅዱሳኑን ሁሉ ከምድር አፈር ይፈጥራቸው ነበር። ምድርን በትክክል ለመሙላት የሚበቃ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ብቻ ይፈጥር ነበር።
ከልክ ያለፈ የሕዝብ መብዛት ችግር አይፈጠርም ነበር። ወደ ሲኦል ተጥለው የሚቃጠሉ ሰዎችም አይኖሩም ነበር።
ሔዋን ግን ሕይወትን በወሲጋቢ ግንኙነት በኩል ለማምጣት መረጠች፤ ይህም ስጋዊ እውቀት ይባላል። ከሰዎች ድርጊት ውስጥ በአንድ ጊዜ መልካምም ክፉም የሆነው ወሲብ ነው። ከጋብቻ በኋላ መልካም ነው፤ ከጋብቻ ውጭ ግን ክፉ ነው።
በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ።
ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።
በዚህ ቃል ውስጥ ወሲባው ግንኙት በመብላት ተመስሏል።
በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን 1,000 ዓመት ነው።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
1,000 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የኖረ አንድም ሰው የለም። ከሁሉም ሰው በላይ ረጅም እድሜ የኖረው ማቱሳላ 969 ዓመቱ ላይ ነው የሞተው።
ኢየሱስ ግን ለየት ስላለ መወለድ ነው የሚናገረው፤ ይህም ልደት የዘላለም ሕይወትን የሚያስገኝ ነው፤ ምክንያቱም በተፈጥሯዊ መንገድ የተወለደ ሕጻን ሁሉ አርጅቶ መሞቱ አይቀርም።
ዮሐንስ 3፡5 ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ውሃ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለዘመናችን የተገለጠውን ሁሉ ማመን እና መታዘዝ አለብን።
ደግሞም ንሰሃ መግባት እና የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ሕይወታችን ውስጥ እንዲገባ መጠየቅ አለብን። ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እንዲያድግ ብሎም ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እስኪቆጣጠር ድረስ ፈቃዳችንን ለእርሱ ማስገዛት አለብን። ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፤ ሲመራንም ለዘመናችን የተጻፈውን ቃል በመገለጥ እናስተውለዋለን።
የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል አያስፈልግም አይጠቅምም ማለታችንን እናቆማለን። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ማለትንም ጨርሰን እናቆማለን። አንድ ጥቅስ ትርጉሙን እንደፈለግነው እንዲሆንልን ብለን ማሻሻልና መለወጥም እንተዋለን።
የዛሬዋን የዘመን መጨረሻ ቤተክርስቲያን እናስብ። በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ካሉት አራት ሕያዋን ፍጥረታት መካከል የሰው ፊት ባለው ሕያው ፍጥረት ዘመን የተዘጋጀው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የሌለበት መመሪያችን ነው።
በተሃድሶ ዘመን እግዚአብሔር የሰዎችን የቋንቋ ችሎታ በመባረክ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል መተርጎም እንዲችሉ አደረገ። ተርጓሚዎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ለማለት እንደፈለገ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት አልሞከሩም፤ ነገር ግን ቃል በቃል በጥንቃቄ ተርጉመውታል።
መጽሐፍ ቅዱስን እንለውጣለን ወይም እናሻሽላለን ብለን ጊዜያችንን ማባከን የለብንም። የመጽሐፍ ቅዱስ ተምሳሌቶች እና ምስጢራት ምን ማለት እንደሆኑ የሚገልጥልንን ጠልቆ ማየት የሚችለውን ንስር ማዳመጥ አለብን።
ከዚያ በኋላ የተወሰኑ ቃሎችን ትተን እንድናልፍ የሚያስገድደንን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እርስ በእርሳቸው እንዲጋጩ የማድረግ ልማድ ትተን ጥቅሶችን በትክክል ማገናኘትና ማስታረቅ እንችላለን።
ሁልጊዜም አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንጻር ነው መፍታት ያለብን፤ እንጂ የሆነ ሰው በተናገረው ንግግር ተመርኩዘን አይደለም የምንፈታው።
ለምሳሌ፡-
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤
ብዙ ቤተክርስቲያኖች “እርሱም” የተባለው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም ከአይሁድ ሕዝብ ጋር የሰባት ዓመት ቃልኪዳን ያደርጋል ይላሉ።
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አይናገሩም።
ልብ ማለት ያለብን ነገር ቃልኪዳኑን ያጸናዋል እንጂ አያደርገውም። የክርስቶስ ተቃዋሚ ቃልኪዳኑን መች ነው ያደረገው? ይህንን ጥያቄ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም ቃልኪዳኑን የሚያጸናው ይክርስቶስ ተቃዋሚ ነው የሚለውን አመለካከት የሚደግፍ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
ይህንን ዳንኤል ውስጥ ያለውን ቃል በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት ስንፈታው ምን ዓይነት ትርጉም እንደምገኝ ተመልከቱ። ሙሉ በሙሉ የተለየ መልስ ነው የምናገኘው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር የተስፋይቱን ምድር እሥራኤልን ሊሰጣቸው ከአብራሐም እና ከዘሩ ከአይሁድ ጋር ቃልኪዳን አደረገ።
ነገር ግን ይህ ቃልኪዳን ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ትርጉም ነበረው።
ከአብራሐም እምነት የተወለደው መንፈሳዊ ዘር ክርስቶስ ነው።
ገላትያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
ይስሃቅ በስጋ የአብራሐም ዘር እንደመሆኑ ለአይሁዶች የእሥራኤልን ምድር መውረስ ይችላል።
የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር የሆነው ኢየሱስ ግን የሚወርሰው ከእሥራኤል ምድርም እጅግ አብዝቶ የሚበልጥ ርስት ነው።
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
ይህ ቃልኪዳን ክርስቶስ በመስቀሉ በተሰዋበት መስዋእት አማካኝነት እግዚአብሔር በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ሲያጸናው “ለብዙዎች” (ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን) የዘላለም ሕይወትን በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ውስጥ ይሰጣል (ይህም ጠላቶች የሌሉበት ዘላለማዊና ከእሥራኤል እጅግ የሚበልጥ የተስፋ ምድር ነው)።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
ኢየሱስ ለሰባት ዓመታት ማገልገል ነበረበት። ነገር ግን ከሶስት ዓመት ከግማሽ በኋላ ተገደለ። ይህም የሱባኤው ወይም ለአይሁድ ቃል የተገባው የሰባት ዓመት እኩሌታ ነው።
ኢየሱስ ሲሞት እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን መጋረጃ ቀደደው። በዚህም የአይሁድ የእንስሳት መስዋእት አበቃ። ኢየሱስ ከተሰዋበት መስዋእት የሚበልጥ መስዋእት አልተገኘም።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
ቤተመቅደሱ በ70 ዓ.ም ፈረሰ፤ በቦታውም የአይሁድ ቤተመቅደስ በነበረበት መሬት ላይ አሁን የሙስሊሞች የኦማር መስጊድ እና ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለ የሙስሊሞች ሕንጻ ናቸው ያሉት።
ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
አንባቢው ያስተውል ከሚለው ቃል አንጻር ስናስብ ይህ ቃል ስለ ብዙ ክስተቶች ነው የሚናገረው።
ዛሬ ስንመለከት መቅደሱ በነበረበት ቦታ ላይ የሙስሊም መስጊዶች ብቻ ናቸው ያሉበት። ስለዚህ እስልምና የጥፋት እርኩሰት አካል ነው።
እስልምና ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን አይቀበልም። እስልምና ኢየሱስ ለሐጥታችን በመስቀል ላይ እንደሞተልን አያምንም።
ስለዚህ እስልምና ውስጥ ሙስሊሞችን የሚያድናቸው አዳኝ የለም። ሙስሊሞች እራሳቸውን ማዳን አለባቸው። እስልምና ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ መንገድ ብሎ የሚያስተምረም የመልካም ሥራ ፍሬዎችን ነው፤ ይህም አስተማማኝ መንገድ አይደለም። ማንም ሰው ለመዳን እርግጠኛ የሚያደርገውን መልካም ስራ መስራት አይችለም። ሌላው የሚገርም ነገር ጦረኛ የሆነ የእስልምና ክንፍ ደግሞ ራስን ማጥፋት ወደ መንግስተ ሰማይ መግቢያ “እርግጠኛ” መንገድ ነው ብሎ ማስተማሩ ነው። ይህም ጦረኛ እስልምናን የሞት ሐይማኖት ያደርገዋል።
አይኤስአይኤስ የጦረኛ እስልምና አንዱ ገጽታ ነው። እነርሱ የሚኖሩት ሰዎችን ለመጥላት፣ ለማጥፋትና ሃገሮችን ለማውደም ነው።
ዮሐንስ 3፡6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
ሥጋ እንዲሞት ተፈርዶበታል። ሥጋ በሐጥያት ባርነት ስር ነው። ስለዚህ ሰዎች እውነትን መረዳት የማይችል የወደቀ የሐጥያት ባህርይ አላቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 … ዕለት ዕለት እሞታለሁ።
በየዕለቱ ለራሳችን መሞት አለብን። ሰዎች መሪ ሆነው እንዲመሩት አምነን መከተል አንችልም ምክንያቱም ልክ እንደ እኛው እነርሱም በመሃይምነታቸው የተነሳ ችግር አለባቸው። የሰው ባህል ወደ እግዚአብሔር አይመራንም።
የሐጥያተኛ ሰዎች አእምሮ በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ ነው ያለው፤ ስለዚህ ሊታመኑ አይችሉም።
ከኢየሱስ ውጭ ማንም ሊታመን የሚችል የለም።
ሰዎች ሁሉ እንዲሞቱ እና ሲኦል እንዲገቡ ተፈርዶባቸዋል፤ ደግሞም ማንም ሰው ራሱን ከሞት ማዳን እንደማይችል ሁሉ ማንም ሰው በሚሰራው መልካም ሥራ አማካኝነት መዳንን እንደ ደሞዝ ሊያገኝ አይችልም።
ሥጋ ለባሽ ሁሉ ከተወለደበት ደቂቃ ጀምሮ ተፈርዶበታል።
ከዚህ የተነሳ ከሰው ጥበብ እና ጥረት አንጻር ሕይወት ከንቱ ድካም ናት።
መክብብ 1፡2 ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።
ከሰዎች ሁሉ ሃብታም እና ከሰዎች ሁሉ ጠቢብ የሆነው ሰውም ቢሆን ዕድሜው ሲያልቅ ይሞታል። የሰው ሃሳቦች የሞትን መጋረጃ ጠርምሰው ማለፍና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት መናገር አይችሉም። የሰው ሃሳቦችም ሆኑ መልካም ስራዎች ሐጥያታቸውን መሻር አይችሉም፤ ወይም የሐጥያታቸውን ውጤትና ቅጣት ማስቀረት አይችሉም።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሰዎችን ሥጋ ወይም የሰዎችን ሃሳብ በጭራሽ አያምንም።
የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ልባችን ውስጥ ገብቶ የእኛን ፈቃድ መግደል ይፈልጋል። የእግዚአብሔር መንፈስ የእርሱን የማዳን እቅድ እንድንከተል ይፈልጋል፤ ይህም ከሰው ሃሳብ እና ከሰው ጥረት ጋር ምንም ዝምድና የለውም።
ወደ ሰማይ መግቢያ መንገድ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር እጅ ነው ያለው። እርሱ ካልፈለገ እያንዳንዱን መከራ በተመለከተ ማብራሪያ መስጠት አይጠበቅበትም። ምክንያቱም ቢያስረዳንም እንኳ ውስን የሆነው አእምሮዋችን የእግዚአብሔርን የጠለቀ ሃሳብ እንዲሁም በሐጥያት እርግማን የተወሳሰበውን የሰው እና የፍጥረት ችግር መረዳት አይችልም።
ለዚህ ነው እግዚአብሔር እንድንታዘዘው ብቻ የሚያዝዘን። መንፈስ ስጋ ከለበሱ ሰዎች የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። ለዘመናችን በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ሙሉ የሆነ እምነት ሊኖረን ይገባል። ሌላውን ሁሉ ለእርሱ መተው አለብን።
ዮሐንስ 3፡7 ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ።
ሕጻን ልጅ ሲወለድ ምንም አያውቅም፤ ምንም ማድረግም አይችልም። ስለዚህ የወላጆቹ እንክብካቤ ያስፈልገዋል፤ ወላጆቹን መታዘዝም አለበት። ወላጆቹ ልጃቸውን ይወዳሉ፤ ለልጃቸው አስፈላጊ የሆነውን ነገር ሁሉ ያደርጋሉ። ሕጻኑ ሕጻን ባለበት ሰዓት ብዙም ችግር ሊደርስበት አይችልም ምክንያቱም ምንም ነገር ስለማያደርግ እራሱ ላይ ጉዳት አያደርስም። መንቀሳቀስና አንዳንድ ነገሮችን ማድረግ መቻል በሚጀምርበት ጊዜ ግን ራሱን የመጉዳት እድሉ እየጨመረ ይሄዳል። ሕጻኑ በዙርያው ያሉ ነገሮችን ምንነት ስለማያውቅ ምን እንደሚጎዳው እና ምን እንደማይጎዳው ለይቶ አያውቀም። ወላጆቹ የሚነግሩትን የሚሰማ እና የሚታዘዝ ልጅ ብዙ ጉዳት አይደርስበትም።
ስለዚህ ዳግመኛ መወለድ አለብን። አዲስ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ማደግ አለበት። በውስጣችን ያለው የራሳችን መንፈስ መሞትና መጥፋት አለበት። አሮጌው ፍጥረታችን አቅም እያጣ ሲመጣ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቃል ወደሚመራን የእግዚአብሔር መንፈስ ይበልጥ ታዛዦች እንሆናለን በእርሱም እንደገፋለን።
በራሳችን ጉልበት ሰይጣንን ለማሸነፍ እና ወደ ሰማይ ለመድረስ አቅም የለንም።
ሰይጣን ከባድና በቀላሉ የማንረታው ጠላት ነው። ኢየሱስ ብቻ ነው ሊያሸንፈው የሚችለው። አንድም ሰው በራሱ ሊያሸንፈው አይችልም።
ዮሐንስ 3፡8 ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።
እውነተኛው ውግያ ያለው ከፍ ባለው በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ነው። ይህ ጦርነት በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ያለ ጦርነት ነው። ከፍ ባለው በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እግዚአብሔር ሰይጣንን እንዴት እንደሚዋጋው የምናውቀው ነገር የለም። መናፍስት ምን ዓይነት ነገሮች እንደሆኑ አናውቅም። ነፋስ ከየት ተነስቶ መጨረሻው የት እንደሚሆን እንኳ አናውቅም። በላያችን ላይ ሲነፍስ የሚሰራቸውን ሥራዎች ብቻ እናስተውላለን እንጂ።
የእግዚአብሔር ሃሳቦች እና ስልቶች ከእኛ ሃሳብ በጣም ከፍ ያሉ ናቸው። የትኛውም የጦር ጀነራል እቅዱን ለጠላቱ አይገልጥም።
ስለዚህ በዚህ በፍጥረታዊ ዓይን የማይታይ መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸውን አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ብቻ ልናውቅና በግልጽ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ልናስተውል እንችላለን። ከዚያ ውጭ የቀረውን ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
እግዚአብሔር የራሱን ሃሳብ ተከትሎ ነው የሚሰራው። እግዚአብሔር እቅዱን ከሰይጣን በመሰወር ሕይወታችንን እኛ ወዳላሰብነው ጭራሽም ወደማንፈልገው እንግዳ ነገር ውስጥ ሊያስገባ ይችላል፤ በዚህም እግዚአብሔር ፈቃዱን በሕይወታችን ውስጥ ይፈጽመዋል።
የቀሬናው ስምኦን የኢየሱስን መስቀል በግዴታ ነበር የተሸከመው። በራሱ አስቦ በፍላጎቱ አይሸከመውም ነበር። ተገድዶ ቢሆንም በሕይወቱ ካደረጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ የበለጠ መልካም ሥራ ነበር የሰራው።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ እና የሆነ ሰውን መከተል ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መታዘዝ የሚፈልግ ስነልቦና ማጎልበት አለብን።
ከዚያ በኋላ እግዞአብሔር ከሰዎች ፍላጎት እና አስተሳሰብ በተለየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መንገድ ሊመራን ይችላል። ለምናምነው ነገር ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ምስክርነት መጠየቅ አለብን።
የሚያስተምረን ሰው ምንም ያህል ኃይለኛ ወይም ዝነኛ ቢሆን እንኳ የሚያስተምረን ነገር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያልተጻፈ ከሆነ ልንቃወመው መቻል አለብን። እግዚአብሔርን ማስቀደም አለብን። ከኢየሱስ ጋር ሲነጻጸሩ ሰዎች በሙሉ ዋጋ የላቸውም።
ከመንፈስ ከተወለድን በኋላ የምንታዘዘው የተጻፈውን ቃል ብቻ ነው። እንጂ ሌላ ማንንም አንታዘዘም። ሰው ሁሉ ስጋ ለባሽ ስለሆነ ይሳሳታል። ሁሉን የሚያውቅ አንድም ሰው እንኳ የለም። እውቀት የበቃው አንድም ሰው የለም። እያንዳንዱ ሰው መማር፣ ስሕተቶቹን ማረም፣ እና እንደገና መማር ያስፈልገዋል።
ፍጹም የሆነ ሰው አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ። ኢየሱስ ለእኛ የተገለጠው የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው። እርሱን ልንታዘዝ የምንችለው የተጻፈውን ቃል በማመን ብቻ ነው።
በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ከሰይጣን እና ከአጋንንት ሰራዊቱ ጋር በሚያደርገው ውግያ ውስጥ ጠቃሚ አገልጋዮች እንሆናለን። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አምናለው የሚል አቋም ሲኖራችሁ የእግዚአብሔር መፍትሄ አካል ትሆናላችሁ እንጂ ለእግዚአብሔር እንቅፋት አትሆኑም።
ዮሐንስ 3፡9 ኒቆዲሞስ መልሶ፦ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው።
ኒቆዲሞስ ምንም አልገባውም። የአይሁድ ሕዝብ አለቃ ለተከታዮቹ ሲነግራቸው የነበረው መልካም ምክር በሙሉ ጥቅሙ ጊዜ ማባከን ብቻ ነበረ። የአይሁድ ሕዝብ እየተለወጡ የተሻለ ሰው እየሆኑ አልነበሩም። ሐጥያትን የማድረግ ፍላጎታቸው አልቀነሰም። የሐይማኖት መሪዎቻቸው ኢየሱስን ይቃወማሉ። ነገር ግን ኢየሱስ የሚናገረውን ሁሉ የሚያውቅ ብቸኛ ሰው ነበረ።
አይሁዶች ብሉይ ኪዳንን ተከትለዋል፤ ነገር ግን በገዢዎቻቸውና በሐይማኖት መሪዎቻቸው አመራር የተነሳ ወዴትም ፈቀቅ አላሉም።
የሰው አመራር ለእሥራኤል መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ አምጥቶባታል። መሲሁ መጥቷል፤ አይሁዶች ግን ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም። መሪዎቻቸው ኢየሱስን እንዲከተሉ አይፈቅዱላቸውም። መሪዎቻቸው ስለ እምነት አንዳች የሚያውቁት ነገር የለም። ስለ መሲሁ የተነገሩ ቃሎች በሙሉ በዓይናቸው ፊት እየተፈጸሙ፤ መሲሁም መጥምቁ ዮሐንስ በግልጽ ካስተዋወቀው በኋላ ቢመጣም እንኳ አይሁዶች ይገፉታል እንጂ አይቀበሉትም።
ኢየሱስ አይለወጥም።
በዳግም ምጻቱ ጊዜ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ከፊቱ ቀድሞ የሚወጣው የተጻፈው ቃል ሚስጥር መገለጥ ሲሆን የሜሴጅ መሪዎች የተጻፈውን ቃል አንቀበልም እያሉ ያልተጻፈውን የሰባቱን ነጎድጓዶች ቃል ለመተርጎም ይሞክራሉ፤ የሰባተኛውን ማሕተም ትርጉም እንዲሁም የኢየሱስን አዲስ ስም በሰዎች ንግግር ጥቅስ ላይ ተመርኩዘው እናውቃን ይላሉ። በእነዚህ ርዕሶች ላይ ብዙ የተለያዩ አመለካከቶች አሉ።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ለመቀበል ራሳችሁን መግዛት ካልቻላችሁ የፈለጋችሁትን ምረጡና እመኑ።
እነዚያን ትምሕርቶች የምታምኑ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል አታምኑም ማለት ነው።
የካቶሊክ ፖፕ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ አስተምሕሮዎችን ያምናል።
ለምሳሌ “ፖፕ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። “ካርዲናል” እንዲሁም “ሊቀጳጳሳት” እና “ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው” የሚል ቃልም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም።
ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን መሰነጣጠቅ እና መተርጎም የለመዱት የሜሴጅ ፓስተሮች የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ በ1963 እና በ1965 መካከል መጥቷል ይላሉ። ብዙዎች ጌታ በ1963 ተመልሶ መጥቷል ይላሉ። ይህ እውነት ከሆነ የምሕረት ዘመን አብቅቷል ማለት ነው፤ ለሙሽራይቱ ብቻ ካልሆነ በቀር። (እስቲ ይህ እውነት ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩን።)
መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት ጀምረን እስከ ራዕይ ድረስ በጥንቃቄ ብንመረምር እንኳ ከእነዚህ ትምሕርቶች አንዳቸውንም ማግኘትና እውነት እንደሆኑ ማረጋገጥ አንችልም። ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፍላግስታፍ ከተማ ላይ ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል የተፈጠረው ደመና እና ማርች 8 ቀን 1963 ታክሰን አሪዞና አካባቢ ወንድም ብራንሐምን ሊጎበኙ የመጡት ሰባት መላእክት የመጡበትን ቀን ልብ ብለን ስናስብ ደመናው የተፈጠረው ከመላእክቱ መሄድ ጋር ተያይዞ እንዳልሆነ መረዳት እንችላለን። አሜሪካ በ1977 ትጠፋለች ተብሎ የተተነበየው ትንቢት ሳይፈጸም ማለፉ የሜሴጅ መሪዎች የሰው ጥቅሶችን ፍጹም ስሕተት የሌለባቸው እውነቶች አድርገው መከተላቸው ታላቅ ስሕተት መኖኑን የሚጠቁመን ማስጠንቀቂያ ነው። ከዚያ ቀን ከ1977 በፊት ትንቢቱና ማመናችንን ለማሳየት ሥራዎቻችንን እንድንተው ተነግሮን ነበር።
አሜሪካ የምትጠፋበትን ቀን ሲተነብዩ የነበሩ እነዚያ ሰባኪዎች እራሳቸው አሁን የራሳቸውን ትንቢት እየካዱ ናቸው። ይኸው አይደል የሰው አመራር?
ዮሐንስ 3፡10 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
የሐይማኖት መሪዎች ምን ያህል ብቃት እንደሚጎድላቸው ኢየሱስ በግልጽ ያሳየናል። መረዳት ያልቻሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገፋሉ፤ ነገር ግን ሙሉውን እውነት ይዘናል ይላሉ። ይህ እርስ በርሱ የሚምታታ ነገር ነው። መረዳት ያልቻልካቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ካሉ ሙሉውን እውነት አልያዝክም ማለት ነው።
ዮሐንስ 3፡11 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
ኢየሱስ ማለት ሰውም እግዚአብሔርም በአንድ አካል ነው። ሰብዓዊ ሰው እንደመሆኑ በውስጡ ለሚኖረው መለኮታዊ መንፈስ ሙሉ በሙሉ ይገዛል።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ኢየሱስ ብቻ ነው ሙሉውን እውነት የሚያውቀው። ያም እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል። የዚያ ዘመን የሐይማኖት መሪዎች ግን ስለ እርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን አንቀበልም አሉ።
ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ቃል ብቻ አያምኑም። አስተዋይ ምሑር መስለተው መታየት ስለሚፈልጉ በራሳቸው አስተሳሰብ ይፈላሰፋሉ። በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ፍላጎት መቀነስ በዚህ ዘመን አሳዛኝ ውጤት አስከትሏል፤ ይኸውም ብዙ የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሆነው መቅረታቸው ነው። አንድ ክርስቲያንን ስለ አንድ ሃሳብ እውነትነት በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማስረጃነት ማረጋገጫ ስጥ ብላችሁ ጠይቁት። ይሞክርና ወዲያው አቅቶት ይተዋል።
ሃሳባቸውን ከዘፍጥረት ጀምረው እንዲያስረዱ ጠይቋቸው። ቀጥሎ ወዴት እንደሚሄዱ ይጠፋቸዋል።
ዮሐንስ 3፡12 ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
መንፈሳዊ እውነቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉ ታሪኮች እና ተምሳሌቶች ውስጥ ተደብቀው ነው የሚገኙት። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑትን ጥቅሶች ከዘፍጥረት ጀመሮ እስከ ራዕይ ድረስ አያይዞ የተጻፉትን ሚስጥራት የሚገልጥልን ሰው ያስፈልገናል።
እንኳን መንፈሳዊ ይቅርና ምድራዊ ፍጥረታዊ ነገር እንኳ በሚገባ አናስተውልም።
የመሬት ስበት ነገሮችን ወደ ምድር የሚስብበትን አሰራር ሚስጥር ሊያብራራ የሚችል አንድም ሳይንቲስት የለም።
የኤሌክትሪክ ቻርጅ ምን እንደሆነም አናውቅም።
የተፈጥሮ ሕጎች ከየት እንደመጡ አናውቅም፤ ለምን የኤልክትሪክ ኃይል ከምድር ስበት ኃይል አንድ ሺህ ጊዜ እንደሚበልጥም አናውቅም።
የአየር ትንበያዎቻችን ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ ናቸው። የእስቶክ ማርኬት ገበያዎች ብዙ ጊዜ በሰዎች ገንዘብ ላይ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያደርጋሉ።
ዶክተር ሮበርት ኦፐንሄይመር በ1945 የመጀመሪያውን አቶሚክ ቦምብ የሰራውን ቡድን ይመራ ነበር። ዶክተር ኦፐንሄይመር ሳይንሳዊ ጠበብት ነበረ። አንድ ጋዜጠኛ አተም ምንድነው ብሎ የጠየቀው ጊዜ የሰጠው መልስ “የማናውቀውን ነገር የሚያደርግ የማናውቀው ነገር” ብሎ ነበር የመለሰለት።
ስለዚህ ኢየሱስ እንዳስጠነቀቀን በፍጥረታዊው ዓለም እንኳ ብዙ የማናውቀው ነገር ካለ በሰው አቅም የሆነው አእምሮዋችን መንፈሳዊውን ዓለም ሊያውቀው አይችልም።
ስለዚህ ለራሳችን እና ለአመለካከታችን መሞት እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ ማመን አለብን። ብቸኛው አስተማማኝ የሕይወት መመሪያችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
የመንፈስ ዓለምን ማየት ከፈለጋችሁ ወደዚያ ለመግባት መሞት ያስፈልጋችኋል። ግን ተጠንቀቁ፤ በመንፈስ ዓለም ውስጥ መልካምም ክፉም ነገር አለ። በመንፈስ ዓለም ውስጥ ወደ ጥፋት ክልል ብትገቡ ምንም አይጠቅማችሁም።
ስለዚህ በምድር እስካለን ድረስ መንፈስ ቅዱስ በማይታየው መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ምን እየተደረገ እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስተምረን ከፈለግን “ለራሳችን መሞት” አለብን።
ኤፌሶን 6፡12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
ዮሐንስ 3፡13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ያለው ጦርነት ከሚደረግበት ከፍ ካለው ከመንፈሳዊ ዓለም ሰማያዊ ጥበብ ለማግኘት ወደ ሰማይ የሄደ እና ሰማይ ውስጥ ምን እንደሚደረግ ያየ አስተማሪ ያስፈልገናል። ይህም አንድ ሰው ብቻ ነው። ኢየሱስ ብቻ።
ከሰማይ ወርዶ ወደ ምድር መምጣቱ በፊት በሰማይ እንደነበረ ያረጋግጥልናል።
እርሱ ሰውም እግዚአብሔርም ስለሆነ ለሰዎች ፈጽሞ የማይቻል ነገር ያደርጋል። ይህም በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም መኖሩ ነው።
የሰዎች ጥበብ ከየት እንደመጣን፤ ለምን በዚህ እንደምንኖር እና ወዴት እየሄድን እንዳለን ሊነግረን አይችልም።
ሳይንቲስቶች ከመጀመሪያው ምንም ያልነበረ ነገር እንዴት ወደ መኖር እንደመጣ ማስረዳት አይችሉም። እኛም ራሳችን ሙት የነበረ ነገር እንዴት ሕያው ሊሆን እንደቻለ አናውቅም።
ስለነዚህ ወሳኝ ርዕሶች እውቀት ማግኘት ከፈለግን ከላይ የሚመጣ ጥበብ ያስፈልገናል።
ጠለቅ ያለ መረዳት ያስፈልገናል። ኢየሱስ በምድር ባለበት በዚያው ሰዓት በሰማይ የሚሆነው እንዴት ነው? ሰማይ ከፍ ያለ ክልል ነው፤ የመንፈስ ክልል ነው። በውስጣችን ያለው የሕይወት መንፈስ ከሰማይ ጋር የግንኙነት መስመር መፍጠር የምንችልበት ብቸኛ መንገድ ነው። ለዚህ ነው የምንጸልየው።
የመለኮት ሙላት በኢየሱስ ውስጥ በአካል በሙላት ይኖራል። በእርሱ ውስጥ የኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ በሰማይ ነበረ፤ በዚያው ሰዓት የስጋ አካሉ ደግሞ በምድር ነበረ።
ምድርን እንደ አንድ ቀጠና አስቡ፤ እንደ ረጅም ቀጥ ያለ መስመር።
ሰማይ ደግሞ ከፍ ያለ ቀጠና ሲሆን በቀረው የወረቀት ገጽ በሙሉ ልንወክለው እንችላለን።
ከፍ ያለው የሰማይ ቀጠና እንዴት መስመሩን እንደሚነካ ተመልከቱ። አጫጭሮቹ አረንጓዴ መስመሮች ወደ ላይ እና ወረ ታች መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ወደ ጎን እና ወደ ጎን ብቻ ነው መንቀሳቀስ የሚችሉት፤ ከዚህም የተነሳ ሰማይ መኖሩ እንኳ አይሰማቸውም።
አንድ ሰው አጭር አረንጓዴ መስመር ነው ብላችሁ አስቡ።
ኢየሱስም እንደ ሰው አጭር አረንጓዴ መስመር ነው። የእግዚአብሔር ልጅ። ታዲያ በእርሱ ውስጥ የሚኖረው የመለኮት ሙላት የት ነው ያለው?
ከእርሱ በላይ የተሰመሩ ብዙ ድርብርብ መስመሮች አሉ። እነዚህ መስመሮች ቁጥራቸው ወሰን የለውም።
ስለዚህ ኢየሱስ “የመስመሮች መስመር” ነው። በእርሱ ውስጥ የሚኖረውን ይህንን ወሰን የሌለው መንፈስ መጽሐፍ ቅዱስ “የነገስታት ንጉስ” በማለት ይገልጸዋል።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤
15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል።
ስለዚህ ኢየሱስ ልዩ ነው። በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይንቀሳቀሳል። ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል ሰው የለም።
ዮሐንስ 3፡14 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ … የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
ሕዝቡን እባብ ከነደፋቸው በኋላ ከመርዙ እንዲፈወሱ ሙሴ በምድረበዳ እባብን በእንጨት ላይ ሰቀለ። ይህም እስከዛሬ ድረስ የሕክምና ሙያ አርማ ሆኗል።
እባቡ የሚያመለክተው የሐጥያትን ክፋት ነው። ግን ክፉው የተሰቀለው መች ነው? ሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድር ተጥሏል።
የሰው ልጅ እግዚአብሔረ በሰው የስጋ አካል ውስጥ ሲኖር ማለት ነው። ሲሰቀልም በሰማይና በምድር መካከል ከፍ ማለት አለበት። ይህም የእኛን ምድራዊ የኩነኔ፣ ውርደት፣ እና የሐጥያት ሸክም መሸከም አለበት ማለት ነው። ነገር ግን ለሐጥያት መድሃኒት መስጠት የሚችለው ሰማይ ብቻ ነው። ይህም እግዚአብሔር በሰዎች ሐጥያት ምክንያት መሰቃየት አለበት ማለት ነው። እኛ ሰዎች ሐጥያት ሰርቶ ለማያውቀው ለብቸኛው ንጹህ ሰው የስቃይ ምክንያት ሆንን።
ስለዚህ ኢየሱስ ዋነኛው አያዎ ዘይቤ ሆነ። ከሰማይ የመጣው ንጹህ ሰው የዓለምን ሁሉ ሐጥያት ተሸካሚ ሆነ።
ከሰማይ የወረደው ንጹህ ሰው የምድር ሐጥያተኞች በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እርሱ በብዙ መከራ ተሰቃይቶ ሞተ።
ከሰማይ የወረደው ፈጣሪ በፍጥረቶቹ እጅ ተሰቃይቶ ተገደለ።
ሰዎችን ሁሉ የሚወደው እርሱ በሰዎች ጥላቻ እና ጭካኔ ምክንያት ተሰቃየ።
ቀራንዮ የብዙ ተቃራኒ ክስተቶች ትዕይንት ነበር፤ ያን ሁሉ ሊሸከም የቻለውም ኢየሱስ ብቻ ነው። እርሱ ያደረገውን ሊያደርግ ብቁ የሆነ ሰው አንዳችም አልነበረም።
ዮሐንስ 3፡15 … በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ … ።
ስለዚህ በእርሱ እና ለእኛ ባደረገው ነገር ሁሉ ሙሉ እምነት ሊኖረን ይገባል።
ለራሳችን ሐጥያት ስርየትን ማድረግ አንችልም። በብሉይ ኪዳን ውስጥ የንጹህ በግ ጠቦት ደም ሲፈስስ ሐጥያትን ያስተሰር ነበር። እንስሳ ግን ከሰዎች በታች ዝቅ ያለ ፍጡር ስለሆነ የበግ ጠቦት ንጹህ ሕይወት ወደ ሰው ልብ ውስጥ ገብቶ አማኙን የተሻለ ሰው አድርጎ ሊለውጥ አይችልም። ከዚህም የተነሳ ሰው የበግ ጠቦት መስዋእት ካቀረበ በኋላ ከሐጥያቱ ይነጻ ነበር ግን ሐጥያት ከመስራት ፍላጎት ነጻ አይወጣም ነበር። ከዚህም የተነሳ ሁልጊዜ ሐጥያት በሰራ ቁጥር ለሐጥያቱ እንስሳትን እየገደለ የደም መስዋእት ማቅረብ ግድ ሆኖበት ነበር።
እንስሳት ከሐጥያት ንጹህ ናቸው ግን የዘላለም ሕይወት የላቸውም። ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ሊሰጡን አልቻሉም።
ከዚህም የተነሳ ሰው የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ብሎ ሊሰዋ የሚችለው ምንም ነገር አልነበረም።
ኢየሱስ ሲያስተምር የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ቁልፉ እምነት ብቻ ነው አለ። የዘላለም ሕይወት የሚሰጠን እርሱ በመስቀል ላይ መሞቱ ሐጥያታችንን እንደሚያስተሰርይልን ማመን ነው።
ጻድቅ በእምነት ይኖራል። መዳን በመልካም ስራዎች አይገኘም።
እምባቆም 2፡4 … ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።
ኤፌሶን 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ጸጋ ለተቀባይ የማይገባ ስጦታ ነው። እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ስራዎች ያድኑናል ብለን የምናስብ ከሆነ ተሳስተናል፤ ምንም አይጠቅሙንም።
ስለዚህ መዳናችን ሙሉ በእግዚአብሔር እጅ ነው እንጂ በእኛ እጅ አይደለም።
ዮሐንስ 3፡16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
ሰው በከባድ ሁኔታ በሐጥያት ተጠላልፏል። እግዚአብሔር ግን ለእኛ ካለው ከፍቅሩ ታላቅነት የተነሳ ሰው ሆኖ መጣና የእኛን በደል ሁሉ በራሱ ላይ ለመሸከም ፈቀደ። ሐጥያታችንን ከላያችን ላይ ከወሰደልንና ሐጥያት አልባ ካደረገን በኋላ መንፈሱን ሰፍሮ በውስጣችን ማሳደር ይችላል። በዚህ ዓለም ውስጥ ያለው ብቸኛ ዘላለማዊ ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ በኢየሱስ መስዋእትነትና በኢየሱስ መልካም ስራዎች የተነሳ የዘላለም ሕይወት መቀበል እንችላለን።
ይህ ሁሉ ግን ከእኛ ነጻ ፈቃድ ጋር የተያያዘ ነው። እኛ ሮቦቶች አይደለምን። ንሰሃ ለመግባትና ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለብን። ወላጆች የሕጻን ልጃቸውን ሕይወት እንደሚቆጣጠሩ ሁሉ ሕይወታችንን እርሱ እንዲቆጣጠረው ፈቃደኛ መሆን አለብን።
ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በሙሉ ለማመን ፈቃደኛ መሆን አለብን። በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ለመኖርም ፈቃደኛ መሆን አለብን።
እርሱ ሳያስገድደን እኛ ለመታዘዝ መፈለግ አለብን።
ዮሐንስ 3፡17 ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
ኢየሱስ ሐጥያተኛውን ዓለም ሊኮንን ሊፈርድበት አልመጣም፤ ሊያድን መጣ እንጂ። እኛ የማይገባንን እድል ሊሰጠን ነው የመጣው።
ሰዎች ምንም ያህል ሐጥያተኞች ቢሆኑም እንኳ ወደ ተራ ሰዎች መጣ። እነዚህ ሰዎች በሆሳእና ዕለት እርሱ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲመጣ አወደሱት። ከዚያ በኋላ ግን የሐይማኖት መሪዎች እነዚህኑ ሰዎች በሚቀጥለው አርብ እለት ኢየሱስን እንዲሰቅሉ አሳመኑዋቸው።
ስለዚህ ኢየሱስ ግብዞች ብሎ ያወገዛቸው ሰዎችም ነበሩ። እነርሱም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ናቸው፤ ምክንያቱም እነዚህ መሪዎች ሕዝቡን ወደ ኢየሱስ ሊጠቁሙ ሲገባቸው በዚያ ፈንታ ሕዝቡ ኢየሱስን አንቀበልም እንዲሉ ነው ያስተማሩዋቸው።
ማቴዎስ 23፡13 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
የሐይማኖት መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ጸንተው አይቆሙም፤ ሕዝቡን ደግሞ በመሪዎቹ የተሳሳተ መንገድ ተከትለው እንዲሄዱ ያስፈራሩዋቸዋል።
ዛሬ ዲኖሚኔሽናል እና ዲኖሚኔሽናል ያልሆኑ 45,000 ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እነዚህ እያንዳንዳቸው ትክክል ነን ይላሉ። ከዚህ የተነሳ ብዙ ክርስቲያኖች ይታለላሉ።
ዛሬ እግዚአብሔር የተሰወሩትን የቃሉን ሚስጥራት ለሕዝብ መግለጥ ይፈልጋል። እግዚአብሔር ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዲያውቁ ይፈልጋል። ነገር ግን እራሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ያልተረዱ የቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን የማያስፈልጉ፣ የማይጠቅሙ ወይም ስሕተት ያለባቸው እያሉ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል እንዳያምኑ ያደርጓቸዋል። ልክ ኢየሱስ በጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ውስጥ እንደተፈረደበት ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ሁሉ ትክክለኛ ሆኖ ቃል በቃል በጥንቃቄ የተተረጎመው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስም ዛሬ በቤተክርስቲያን መሪዎች እየተፈረደበት ነው።
ቃሉ ማለት ኢየሱስ ነው። እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ታሪክ እራሱን ይደግማል።
ክርስቶስ በቀራንዮ በተሰዋበት መስዋእት ከሲኦል እንድናለን። እርሱ ከሲኦል አድኖናል ምክንያቱም የሐጥያትን ዋጋ የዛሬ 2,000 ዓመት ከፍሎታል። እራሳችንን ከሲኦል ማዳን አንችልም። እርሱ የሚያደርግልንን የሐጥያት ይቅርታ በእምነት መቀበል ብቻ ነው የምንችለው። ይህ ለእኛ የማይገባን ቸርነት ነው። ምሕረትን ለእኛ ያዘጋጀልን የእርሱ ጸጋ ብቻ ነው።
ግን ደግሞ ሊመጣ ካለው ከታላቁ መከራም ጭምር መዳን ያስፈልገናል።
የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በጥልቀት በመረዳት ብቻ ነው የቤተክርስቲያኖችን የአስተምሕሮ እና የትንቢት ስሕተቶችን ማምለጥ እንዲሁም እግዚአብሔር በተገለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አማካኝነት ከፊታችን ሊመጣ ካለው ከታላቁ መከራ ሊያድነን እንዲመራን የሚያስችለንን በቂ እውነቶችን መማር የምንችለው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እያየን “ይህ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም፤ ስለዚህ ጠቃሚ አይደለም፤ ለእኔም አያስፈልገኝም” ማለት የለብንም። እንዲህ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች የክርስቶስ ሙሽራ አካል አይሆኑም። የትኛዋም ሙሽራ የባሏን ቃል ስትሰማ እንዲህ ዓይነት ግድ የለሽ ምላሽ አትሰጥም።
አንድ ምሳሌ እንመልከት። ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን ከመገበ በኋላ 12 መሶብ ቁርስራሾች ተሰበሰቡ፤ 4,000 ሰዎችን ከመገበ በኋላ ደግሞ 7 መሶብ ቁርስራሾች ተሰበሰቡ። ደቀመዛሙርቱን ኋላ ሲያናግራቸው የተረፉት ቁርስራሾች ለምን 12 እና 7 መሶብ እንደሆኑ ጠይቋቸዋል።
ማቴዎስ 16፡9 ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
ኢየሱስ ሙሽራይቱ እርሱ የሚያደርገው ነገር ትርጉሙ ምን እንደሆነ እንድታስተውል ይጠብቅባታል። መሃይምነታችንን የምንሸፋፍንባቸው መልሶች አያስደንቁትም። መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ አያኮራም።
የአይሁድ ቤተመቅደስ ውስጡ ጠረጴዛ ላይ 12 የገጽ ሕብስት እና ባለ ሰባት ቅርንጫፍ መቅረዝ ነበሩ።
ስለዚህ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ 12 እና 7 ልዩ ትርጉም አላቸው። እነዚህ ተምሳሌቶች በጣም አስፈላጊ ናቸው፤ እግዚአብሔርም እንድናውቃቸው ይፈልጋል። ሰዎቹን በማብላት እና ቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት እቃዎች ቁጥር አማካኝነት ሊነግረን የፈለገው ምንድነው?
ሙሽራዋ ብቻ ናት እነዚህን ሚስጥሮች የማወቅ ፍላጎት የሚኖራት። ሰነፎቹ ቆነጃጅት (ንጹህ የዳኑ ክርስቲያኖች) ሰነፎች ናቸው ምክንያቱም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አያስፈልጉም ብለው ያስባሉ። ማወቅ አልፈለጉም።
ልባሞቹ ቆነጃጅት ግን “ማወቅ አለብኝ” ይላሉ። በመማር ነው ልባም መሆን የምነችለው።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት “ማወቅ አለብኝ እንዴ?” ይላሉ።
ዮሐንስ 3፡18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
እግዚአብሔርን ማመን የእምነት መሰረት ነው። አካላችሁ የሚንቀሳቀሰው በአእምሮዋችሁ መሪነት ነው፤ አእምሮዋችሁ ሃሳባችሁን በሙሉ እንዲሁም ድርጊቶቻችሁንና የሰውነታችሁን ስራዎች በሙሉ ይመራል። ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ … ባል የሚስት ራስ ነውና።
ኢየሱስ እምነታችንን እና ስራችንን ሁሉ መምራት ይፈልጋል፤ በዚህም ለዘመናችን የተገለጠውን ቃል ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሁሉ ማድረግ ይችላል። እኛ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ መገዛት እና የተገለጠው ቃሉ የሚያዝዘንን ብቻ ማድረግ አለብን። ስጋው በቀራንዮ ተፈርዶበታል። ስለዚህ በተጻፈው ቃል ውስጥ ብቻ ተወስነን ብንኖር አካሉ ውስጥ ነን ማለት ነው፤ ስለዚህ ፍርድን ተቀብለን አልፈናል።
ስለዚህ ኩነኔ የለብንም።
የራሳችንን ሃሳብ ብንፈጽም ወይም የቤተክርስቲያናችንን ልማድ ብንከተል የፓስተራችንንም አመለካከት ብንከተል ከመጽሐፍ ርቀን እንሄዳለን። ይህ አለማመን ነው። መጽሐፍ ቅዱው ውስጥ የተጻፈውን ካላመንን ከሐጥያቶች ሁሉ የሚበልጠውን ሐጥያት እየሰራን ነን።
ስለዚህ በደለኞች እንሆናለን።
በኢየሱስ ስም ማመን አለብን። ሊያድነን የሚችል ሌላ ስም የለም።
የሐዋርያት ሥራ 4፡12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
የእግዚአብሔር ልጅ ሞቶልናል፤ ተቀብሯል፤ ከዚያም ከሙታን ተነስቷል።
አብ እና መንፈስ ቅዱስ አልሞቱም፤ አልተቀበሩም፤ ስላልሞቱ ከሙታንም አልተነሱም። ስለዚህ የተለያዩ አካላት ከሆኑ ሊያድኑን አይችሉም። አብ እና መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ናቸው፤ ሐጥያታችንን የሚያነጹበት ደም የላቸውም። ስለዚህ የሚያድነን የኢየሱስ ስም ብቻ ነው።
አብ ስሙ ያህዌህ ነበረ። መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም አልተሰጠውም። ክርስቶስ ማለት የተቀባው ማለት ነው። ግን የተቀባው የሚለው ቃል የተቀባውን ሰው የሚያመለክት ነው። ክርስቶስ የሚለው ቃል የቀቢው የመንፈስ ቅዱስ ስም አይደለም።
በመለኮት ውስጥ ሶስት አካላት ካሉ፤ ስም ያላቸው አብ እና ወልድ ብቻ ናቸው። ስለዚህ ለሶስት አካላት ሁለት ስም ብቻ እናገኛለን። ያህዌህ እና ኢየሱስ። የአካላቱ ቁጥር እና ስሞቹ በትክክል አይገጣጠሙም።
ነገር ግን እርግጠኛ የምንሆንበት ለሶስት አካላት የሚሆን አንድ ስም የለም። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ስም አልባ ይሆናል።
“በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” የምትሉ ጊዜ ሶስት ማእረጎችን ጠቀሳችሁ እንጂ አንድም ስም አለመጥራታችሁን ልብ በሉ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ስማ ባለመጥቀስ የስምን ጉዳይ ቸል ብላችሁ ታልፋላችሁ።
የእግዚአብሔር ልጅ ማለት እግዚአብሔር ሰው ሲሆን ነው። የሰውነት ስሙ ኢየሱስ ይባላል። እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቷል፤ መቀባቱ የተቀባው ወይም ክርስቶስ አድርጎታል።
የእግዚአብሔር ሙላት በኢየሱስ ስጋዊ አካል ውስጥ አደረ።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ኢየሱስ መጥቶ የሙሽራይቱ አካል የሆኑትን እስኪወስዳቸውና የማይሞት ዘላለማዊ አካል እስኪሰጣቸው ድረስ ስሙ ብቻውን ያድነናል።
ከዚያ በኋላ ሐጥያት መስራት አይችሉም። ከዚያ በኋላ ሙሽራይቱ መዳን አያስፈልጋትም። ለዚህ ነው ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ አዲስ ስም ይዞ የሚመጣው። በአሁኑ ሰዓት ይህንን አዲስ ስም ማንም አያውቀውም።
ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
ዮሐንስ 3፡19 ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
ሰዎች ላይ ኩነኔ መምጣቱ ከመልካም ይልቅ ክፉውን ስለምንመርጥ ነው። ጨለማ በግብዝነት ተንኮል የምናስብበትን ክፉ ስራችንን ይደብቅልናል። ራስ ወዳድነት ተገልጦ ሲታይ የሚያኮራ ስላልሆነ የልባችን ክፉ ሃሳብ እንዲታይብን አንፈልግም።
ባር ማለት “የእከሌ ልጅ” ነው። አባ ማለት ደግሞ “አባት” ነው።
ስለዚህ ኢየሱስን በመግፋት አይሁዶች በርባንን መረጡ፤ የስሙም ትርጉም “የአባቱ ልጅ” ማለት ነው። በርባን ነፍሰ ገዳይ ነበረ።
ማርቆስ 15፡7 በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።
ዮሐንስ 8፡44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።
በርባን የአባቱ የዲያብሎስ ልጅ ነበር። አይሁዶችም ከኢየሱስ ይልቅ እርሱን ነው የመረጡት።
አይሁዶች ለምንድነው ይህንን የተሳሳተ ምርጫ የመረጡት? የሐይማኖት መሪዎቻቸው እንደዚህ እንዲመርጡ ስላስገደዱዋቸው ነው።
ማርቆስ 15፡9 ጲላጦስም፦ የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን? ብሎ መለሰላቸው፤
የካሕናት አለቆች ኢየሱስን ያስያዙት በቅናት ነበር። የኢየሱስ ቅዱስ ሕይወት የእነርሱን እርኩሰት አጋለጠባቸው።
ማርቆስ 15፡10 የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።
11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።
የሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡ ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔር ቃልን መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም እንዲሉ አስገደዱዋቸው።
የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን መረዳት ስለማይችሉ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ እያሉ በመናገር ነው። ከዚህም የተነሳ ሰዎች የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እንዳያምኑ ያደርጋሉ።
ዮሐንስ 3፡20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገርን ማመን ጨለማን ማስፋፋት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማይከተሉ ሰዎች ዘንድ ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ጥላቻ አለ።
የተፋቱ ሰዎች ድጋሚ ማግባት ሲፈልጉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ራቅ ይላሉ።
ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።
ለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መብት የሚሟገቱ ሰዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚከለክሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይቃወማሉ፤ ያወግዛሉ።
ሮሜ 1፡26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤
27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ምንጊዜም ክፉ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎችን ይቃወማቸዋል። እነርሱም በበኩላቸው ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ይቃወማሉ።
ዮሐንስ 3፡21 እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።
እውነትን ከልቡ የሚከተል ሰው ሕዝቡ ምን እያሉ ነው ብሎ ሕዝቡን አይከተልም።
ሕይወታችንን በሙሉ ተጨባጭ እውነታዎችን እየሸሸን እናሳልፋለን። ይህም እውነትን ወይም ተጨባጭ የሆነ ክፋትን መጋፈጥ የማይችል ደካማ አቋም ነው።
ፓስተሮች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት የሐይማኖት ገበያተኞች የአስራት ገንዘባቸውን አውጥተው የሚገዙትን የሐይማኖት ሸቀጥ በማምረት ነው። የሚያመርቱትን ሸቀጥ የገበያተኞቻቸውን ፍላጎት እና ስሜት እየተከተሉ ይለዋውጡታል። ለጉባኤው መጽሐፍ ቅዱስን መርምሮ እውነትን እንዲያገኝ አይመክሩትም። ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን አያውቅም። የተሳሳተ እምነታቸውን ለመደገፍ መሪዎች በየጊዜው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ይለዋውጣሉ። ይህም በውስጡ ምንም ቁምነገር የሌለው አስተምሕሮአዊ ገለባ ነው።
ዮሐንስ 3፡22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።
ይሁዳ የሚለው ስም ትርጉሙ “እግዚአብሔር ይመስገን” ማለት ነው። በመልካም ክስተቶችም ሆነ በክፉ ውስጥ አቋማችን እግዚአብሔርን ማመስገን ነው መሆን ያለበት።
ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
በሕይወታችን የሚገጥሙንን አደጋዎች ለመቋቋም ከመሰረታዊ ነገሮች መጀመር አለብን። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ይችላል። ሕይወታችንን ለመቅረጽ መልካምም ሆነ ክፉ አጋጣሚዎችን ይጠቀማል። መልካም እና ክፉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው።
በጣም ክፉ ነገር ደርሶብናል ብለን የምናምን ከሆነ የእውነት እግዚአብሔርን አንወድደውም ማለት ነው።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማገልገል የምንፈልግ ከሆነ ስለ ሁኔታዎች ማማረር የለብንም።
ሐጥያት ክፉ ውጤቶችን ያስከትላል። ነገር ግን በክፉ ክስተቶች መካከልም ቢሆን እግዚአብሔር የራሱ የሆነ እቅድ አለው፤ ዓላማውንም መፈጸም ይችላል።
ሕይወታችንን ለእርሱ አሳልፈን ብንሰጥ እርሱ በሚመራን መንገድ ሳናጉረመርም ደስ ብሎን መሄድ አለብን። ሁልጊዜም ማስታወስ ያለብን የእግዚአብሔር ዓላማ የሚፈጸምበት መንገድ እኛ በምናስበው ወይም በምንመርጠው መንገድ አለመሆኑን ነው። እግዚአብሔር በሚያስብበት ደረጃ ልናስብ አንችልም።
ስለዚህ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ እርሱን ማመስገንን መለማመድ አለብን። ይህ በጣም ከባድ ልምምድ ነው።
ለሰዎች ሁሉ ከባድ ወደሆነው ጥያቄ እንምጣ፡- ስቃይ እና መከራ ያለው ለምንድነው?
እግዚአብሔርን ስለ ሁሉም ነገር ስናመሰግነው ሕይወታችንን በሙሉ የሚቆጣጠረው እርሱ መሆኑን እያመለከትን ነው። ልክ በነጭ ወረቀት ላይ ደስ የሚል ስዕል ለመሳት እንደሚሰመሩ ጥቁር መስመሮች መልካም እና ክፉ ክስተቶች ሊገጣጠሙ ይችላሉ። ደስታችንን የያዘው ጽዋ የሚቀረታ በሐዘን ስለታም ቢላዋ ነው። ሁለቱም አስፈላጊዎቻችን ናቸው። ደስታ በልባችን የሚመሰለውን ስሜታችንን ከፍ ያደርገዋል። ይህም ሰው መሆናችንን ያሳያል። ስሜቶቻችን በዛፍ ውስጥ እንዳሉ ፈሳሽ ንጥረ ነገሮች ናቸው፤ ሕይወት ይሰጣሉ ግን ከጉዳት ጥበቃ አያደርጉልንም። ምክንያታዊ አስተሳሰብ፣ እምነት፣ እና እውነት ሐዘንን እና ስቃይን እንድንቋቋም አእምሮዋችንን በትክክል መምራት ይችላሉ። ስለዚህ ራስ በክፉ ዘመን ውስጥ መከራን ተቋቁመን እንዲሁም አብበን የማለፍ ተምሳሌት ነው። ልክ ለዛፍ ግንድ ጥበቃ እንደሚያደርግለት ቅርፊት ነው። ራስ እና ልብ ተባብረው መስራት አለባቸው። ጤናማ አስተሳሰብ እና ስሜቶች ውስብስብ በሆነ ዝምድና ይጣመራሉ።
ስለ እኛ የተጻፉ እውነታዎችን እንመልከት።
1ኛ ዮሐንስ 5፡19 ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
ራዕይ 12፡9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
ኤፌሶን 2፡2 በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።
ሰይጣን አየሩን ይገዛል፤ ስለዚህ በአየር ሁኔታ መዛባት ስለሚፈጠሩ አደጋዎች እግዚአብሔርን ተጠያቂ አታድርጉ።
አዳም ሐጥያት ወደ ዓለም እንዲገባ ሲፈቅድ ሰይጣን ምድርን ተቆጣጠረ።
እግዚአብሔር ከአዳም እና ከሔዋን የደበቀው እውቀት ሰይጣንጋ አለ ብላ ሔዋን አመነች። የሰይጣንን መንግስት ከነብልጥ እና አስደሳች ሃሳቦቹ ጋር የራሷ ልታደርግ ፈለገች። ትክክል እና ስሕተት የሆነውን በራሷ የመለየት ብቃት እንዳላት አመነችና ወሰነች። ክፉ ምን እንደሆነ እና መልካም ምን እንደሆነ ያወቀች መሰላት።
ሔዋን የኤደን ገነትን ጠባብነት አልወደደችውም። ሰፋ ያለ ቦታ ፈለገች።
ሐዋን ሴት ነበረች። በሴትነቷም የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ነበረች።
ልክ እንደ ሔዋን ቤተክርስቲያኖችም ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስን ደስ እንዳላቸው ማሻሻል፣ ማስተካከል፣ በውጡ ያልተጻፉ ቃሎችን መጨመር እንዲሁም የማያስፈልጉ፣ የማይጠቅሙ ወይም ስሕተት የሆኑ ቃሎችን ቆርጠው ማስወጣት ይፈልጋሉ።
ሔዋን የበለጠ እውቀት እና ጥበብ ፈለገች። ነጻ ፈቃድ ነበራት። የመምረጥ ነጻነት አላት። ስለዚህ እግዚአብሔር የመረጠችውን ሰጣት።
ሁሌ እንዲታዘዝ በፕሮግራም እንደተሞላ ሮቦት አልነበረችም። በደመ ነፍስ የሚመራ እንስሳም አልነበረችም።
ሔዋን ሐጥያቷ የሚያስከትልባትን ውጤት አላወቀችም። ከገነት ተባረረችና በሰይጣን መንግስት ውስጥ መኖር ጀመረች።
በዓለም ውስጥ በሚደረገው ነገር ደስተኛ ካልሆናችሁ ዓለም የምትተዳደረው በሰይጣን መሆኑን አስታውሱ። በዚህ ዓለም ውስጥ ለሚደረገው ክፋት ሁሉ ተጠያቂው ሰይጣን ነው። ሔዋን የሰይጣንን ጥበብ ፈለገች። አይሁድ ነፍሰ ገዳዩን በርባንን መረጡ። በእውነቱ ለምርጫችን ተጠያቂዎች እኛው ራሳችን ነን እንጂ በሌላ ሰው ላይ ማሳበብ አንችልም። እግዚአብሔርንም ተጠያቂ ማድረግ አንችልም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰይጣን ሰዎችን እንዴት እያደረገ እንደሚመራ እንድናይ ለሰይጣን ፈቃድ ሰጥቶታል።
ሰይጣን ገነት ተሰጥቶት ነበረ፤ ግን ምን እንዳደረገው አያችሁ? ጦርነት። በሽታ። ስቃይ። ሞት። ጥላቻ። ጭካኔ። ራስወዳድነት።
አደንዛዥ እጽ። ወሲባዊ ብልግና እና እርኩሰት። መርዝ። ብክለት።
እስካሁን እንዳየነው ይህንን ውስብስብ የፍጥረት ዓለም የማስተዳደር ብቃት እንደሌለው መረዳት አለብን። ሰይጣን ልክ የራሱን ሃገር እንደሚያወድም እና የራሱን ሕዝብ እንደሚዘርፍ አምባገነን መሪ ነው። አምባገነኑ መሪ ፈገግ ይላል፤ ሕዝቡ ግን መከራ ይበላሉ። ከዚያ ሐገሪቱ ትፈርሳለች።
ዕብራውያን 6፡18 … እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል
እግዚአብሔር መዋሸት አይችልም። ስለዚህ ሰዎች የዲያብሎስን ምክር መከተል ከፈለጉ እግዚአብሔር ይፈቅድላቸዋል። ይህ ነጻ ፈቃድ ለሰዎች ተሰጥቷል።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የሰይጣን ክፉ እቅድ የሚያስከትለውን መከራ እና ሰቆቃ ማስቆም አይችልም።
እግዚአብሔር የሰዎችን የተሳሳተ ምርጫ ውጤት ቢከለክል ሊዋሽ ነው ማለት ነው፤ ደግሞም ሰይጣናዊ ሐጥያት የሚያስከትለውን ክፉ ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዳናይ ያደርገናል።
ሰዎች በሐጥያት ለመኖር መርጠናል፤ ስለዚህ ሐጥያት የሚያመጣቸውን ሰቆቃዎች በሙሉ ማየት አለብን።
ሔዋን የሰይጣንን ምክር ፈለገች። ስለዚህ ለ6,000 ዓመታት ሰይጣን ሰዎችን ሲመክር ቆይቷል፤ በምክሩም እግዚአብሔር የፈጠረውን ውብ የኤደን ገነት አስቀያሚ ኦና ምድር አድርጓል፤ በዚህም ምድር ውስጥ ሰዎች በአእምሮዋቸው ብልሃት የሚፈጥሩት ቴክኖሎጂ በሰዎች ክፉ ሃሳብና እርኩስ ምኞት የተነሳ ለክፉ ዓላማ ይውላል።
እግዚአብሔር በተጨማሪ ሰዎች በሰይጣን አመራር ስር ሆነው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩም ፈቅዷል።
አዳም እና ሔዋን ያለ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብነትና ቁጥጥር የራሳቸውን ስራ መስራት ፈለጉ። ሰዎች ራሳቸውን በፖለቲካ ሲመሩ ቆዩ፤ ፖለቲካ ግን ፈላጭ ቆራጭነትን፣ ጨቋኝነትን፣ ምግባረ ብልሹነትን፣ ኢፍትሃዊነትን፣ ግፍን፣ ጦርነትን፣ ወንጀልን፣ ስግብግብነትን እና ድህነትን ወለደ። ሐብታሞች በሃብታቸው እየጨመሩ ድሆችም የባሰ ድሃ እየሆኑ ሄዱ። ዘመን ባለፈ ቁጥር የሃብት ክፍፍል ኢፍትሃዊነት እየተባባሰ ሄደ።
ንቁ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ሳይንቲስቶች ሆኑ። ነገር ግን የሰው እውቀት የተገኘበት ዛፍ ፍሬው መልካም እና ክፉ በአንድነት ነው። በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ፈጠራዎቻቸው መካከል ክፉ የሆኑትን አልኮል፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ብክለት፣ መርዝ፣ ቦምብ፣ የጦር መሳሪያ፣ የአየር ለውጥ፣ ፖርኖግራፊንም ጭምር ፈጠሩ።
አተምን መሰንጠቅ እንደተማርነው ሁሉ ትዳሮችን መሰንጠቅም ተምረናል።
ከሳንሳዊ ምርምራችን ውስጥ ትልቅ ውጤት ያመጣነው ሕጻናት እንዳይሞቱ አዛውንትም በሕይወት እንዲቆዩ የሚያደርጉ መድሐኒቶችን መፍጠራችን ነው። ነገር ግን የሰው ጥበብ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። የጥሩ ሕክምና አገልግሎት ክፉ ውጤቱ በየአስራ አምስት ዓመቱ ምድር መሸከም ከምትችለው በላይ አንድ ሺህ ሚሊዮን ሕዝብ በላይዋ ላይ እንዲበዛ ማድረግ ነው። እንደዚህ ያህል የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር ለሁሉም የሚበቃ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ማቅረብ አይቻልም። በአሁኑ ሰዓት ከዓለም ሕዝብ ግማሹ በከተሞች ውስጥ ነው የሚኖረው፤ ይህም ባለፈው መቶ ዓመት ውስጥ በከተሞች በጣም ብዙ የላስቲክ ቤቶች እንዲፈጠሩ አድርጓል። የሕዝብ ብዛት የሚያመጣው ጫና ሰዎች ሳይሞቱ እንዲቆዩ ማድረግ እንጂ በትክክል እንዲኖሩ አያደርግም። ከፊታችን በሚመጡት ዓመታት ውስጥ የዓለም ትልቁ ፈታኝ ችግር የሚሆነው የሕዝብ ቁጥር ከልክ በላይ መጨመር ነው።
ስለዚህ ሰይጣን ለሰዎች ክፉ መሪ ሆኗል። ግን ምን ይደረግ ሰዎች ደግሞ የመረጡት እርሱን ነው።
እግዚአብሔርን የገጠመው ችግር እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ለሰዎች ነጻ ምርጫ ሰጥቷቸው ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር መገዛትነ እንዲፈልጉ የሚያደርገው እንዴት ነው?
የኤቮልዩሽን ቲዎሪን የፈጠረው ቻርለስ ዳርዊን ሕይወት ያለው አንድ ነጠላ ሴል ምንም ውስብስብነት የሌለው መስሎት ነበር። ይህም ሕያው ሴል በድንገት እንዲሁ በድን ከሆኑ ኬሚካሎች ውስጥ ብቅ ሊል ይችላል ብሎ አሰበ፤ በዚህ መንገድ ሕይወት ያለው ሴል ሲፈጠር ግን እስከዛሬ ድረስ ታይቶ አይታወቅም። ከቻርለስ የበለጠ የተማሩ የዚህ ዘመን ሳይንቲስቶች ቻርለስ ያልተወሳሰበ ሴል ብሎ የሚጠራውን የውስብስብነት ጥልቅ ጉድጓድ ብለው ነው የሚገልጹት። ሕይወት ውስጥ ያልተወሳሰበ ነገር የለም። ሕይወት ከዚህ ዓለም በላይ ከፍ ካለ አምስተኛ ቀጠና የሚመጣ መንፈስ ነው። ስለዚህ እኛ በምንኖርበት ባለ አራት ቀጠና ዓለም ውስጥ ሕይወት የሚገለጥበት ዓይነት እና ውስብስብነት ማለቂ የለውም።
የፍጥረታዊ ሕይወትን ውስብስብነት ተንትነን መጨረስ እንደማንችል ሁሉ የሰዎችን ማሕበረሰብ ውስብስብነትም ተንትነን መጨረስ አንችልም። ሰዎች በአእምሮዋቸው ውስጥ መፍጠር የሚችሉዋቸው መልካም ነገሮች እና ክፉ ሃሳቦች ማለቂያ የላቸውም። ስለዚህ የሰው ልጅ በአስደናቂ ፈጠራዊች ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ይሄዳል፤ ነገር ግን በሰብዓዊነቱ ደግሞ እየተበላሸ ይሄዳል። ሰው በማሕበራዊ ኑሮ ውስጥ በክፋት እየባሰ ሄዷል።
የሐጥያት ውስብስብነት እጅብ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ፈርጀ ብዙ ክፉ ውጤቶቹን መቋቋም አንችልም። “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ክፉ ነገር የማያስቆመው ለምንድነው?” ብሎ መጠየቅ ከንቱ ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር ቢያስቆመው እንኳ የሰዎችን የሐጥያት ችግር አይፈታም፤ ሐጥያታቸውን አያጠፋውም። ሐጥያት ልክ እንደ ካንሰር ነው። ዶክተሮች ከካንሰር ጋር በሚያደርጉት ውግያ በተወሰነ ደረጃ ተሳክቶላቸዋል፤ ነገር ግን ሊያጠፉት አልቻሉም። ልክ እንደዚያው ሐጥያትም ሰዎች ሊያጠፉት ቢታገሉ እንኳ መኖሩን ይቀጥላል።
በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእሥራኤል ውጭ ያሉት አሕዛብ በዓል እና ሞሎክ የተባሉ አማልክትን በሚያመልኩ ጊዜ ሕጻናትን ይሰዉ ነበረ። ዛሬ በዘመናዊ ጣኦት አምልኮ ሕጻናትን ሳይወለዱ ማስወረድ ተለምዷል። ሕጻናት እና አዛውንት እንዳይሞቱ የሚረዱ የሕክምና ባለሙያዎች እራሳቸው ደግሞ ያልተወለዱ ሕጻናትን ይገድላሉ። የ2016ቱን ሕዝባዊ ድጋፍ ያሸነፈችው ሒላሪ ክሊንተን ጽንስ የማቋረጥ ደጋፊ ነበረች። ደስ የሚለው ግን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አላሸነፈችም፤ ብታሸንፍ ኖሮ ይህ ያልተወለዱ ሕጻናት ላይ የሚረደገው ጭፍጨፋ ተስፋፍቶ እንዲቀጥል ታደርግ ነበር።
ከ1980 ወዲህ ባለፉት 37 ዓመታት ውስጥ ብቻ በዓለም ዙርያ አንድ ከግማሽ ቢሊዮን ሕጻናት ሳይወለዱ በጽንስ ማቋረጥ ተገድለዋል።
ሰው ነፍሱ ውስጥ በክፉ በሽታ ተይዟል። በጨለማ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነው። ብርሃን ከምድራችን ጠፍቷል።
1ኛ ዮሐንስ 3፡8-9 ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።
ኢየሱስ ብቻ ነው ሐጥያትን ሊያጠፋ የሚችለው። ሌላ ማንም አይችልም። ስለዚህ እምነት ሊኖረን እና ጦርነቱን ለእርሱ ልንተውለት ይገባል። ምንም ይምጣ ምን እርሱ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል፤ እኛም ሙሉ በሙሉ ልናምነው ይገባናል። የእኛ እውቀት ከንቱ ነው። የዚህች ዓለም ችግር ከእኛ አቅም በላይ ነው። ጦርነቱ መንፈሳዊ እና ከፍ ባለ በማይታይ ቀጠና ውስጥ የሚደረግ ነው። በምድር ላይ የምናየው በሙሉ በመንፈሳዊ ዓለም ለሚደረገው ነገር ጥላ ነው። ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ጸሎት፣ ምስጋና፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን እና እግዚአብሔር ጦርነቱን እንደሚያሸንፍ ማመን ብቻ ነው።
ለሰይጣን ክፋት እግዚአብሔርን ተጠያቂ ማድረግ ጊዜ ማባከን ብቻ ነው።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
እግዚአብሔር በስድስት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ ላይ ሕይወትን ፈጠረ። ስድስት ሺህ ዓመታት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ገነትን አበጀ።
የዚያን ጊዜ ሔዋን ተጨማሪ እውቀት በማግኘት አምላክ መሆን የምትችል መሰላት። ዓይኗ ሊከፈት ይችላል። የመልካም እና የክፉውን ልዩነት ማወቅ ትችላለች። የምርጫ እና የፈቃድ ነጻነት ስለነበራት እግዚአብሔር በዚያ መንገድ እስከፈለገችበት ድረስ እንድትሄድ ፈቀደላት። ስለዚህ እንደገና ለስድስት ቀናት ማለትም የስድስት ሺህ ዓመታት የሰው ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉንም ዓይነት መንግስት እና አስተዳደር እንዲሞክሩ ፈቀደላቸው፤ ሁሉንም ዓይነት ሐይማኖታዊ አምልኮ እንዲሞክሩ ፈቀደላቸው። የራስ ፈቃድ ማለት እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን ለማድረግ ነጻ እንዲሆን መተው ማለት ነው። በተጨማሪም ሰይጣን ደግሞ የፈለገውንና በክፉ ልቡ ያሰበውንና ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ መልቀቅ ማለት ነው። ሰይጣን ደግሞ ከእኛም የበለጠ በጣም ብልጥ ነው። ስለዚህ ሰዎችን ደጋግሞ ያታልላቸዋል። ሰይጣን በላይኛው በስድስተኛ ቀጠና ነው የሚኖረው፤ ይህም የጠፉ ፍጡራን መኖሪያ ቀጠና ነው።
የሰዎች አእምሮ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ በስድስተኛው ቀጠና ውስጥ ገባ ወጣ ማለት ይችላል፤ በዚያውም ከሰይጣን እና ከአጋንንቱ የተለያዩ ተጽእኖዎችን መቀበል ይችላል። ከዚያ በኋላ በምድር ላይ ትክክል ያልሆኑ ውሳኔዎችን እናደርጋለን።
ስለዚህ ሰይጣን ሲቆጣጠረው ከቆየው ከ6,000 ዓመታት የሰው ታሪክ ማብቂያ ላይ ዓለም በአዳት ክፍሎች ትከፋፈላለች። የሰውን ትምሕርት በጭራሽ የማታምነው የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችዋ እውነተኛ ቤተክርስቲያን አንድም ሰው ራስ ሆኖ እንዲመራት አትፈልግም፤ የምታምነውም ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው። እነዚህ ልባሞቹ ቆነጃጅት ይባላሉ። ከእነዚህ ሌላ ደግሞ ሰነፍ ቆነጃጅት አሉ፤ እነርሱም ንጹህ የሆኑ የዳኑ ቤተክርስቲያኖች ናቸው ግን መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበቢያ ብርሃን የሚሰጥ በቂ ዘይት የላቸውም። ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ብዙም መረዳት አይችሉም። እነዚህ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰነውን ክፍል ያምናሉ፤ የተወሰነውን ክፍል ደግሞ አያምኑም። ለቤተክርስቲያን መሪያቸው (እና ለመሪው ቤተሰብ) ታማኝ መሆን እና ዘወትር ቤተክርስቲያን መሄድ የሚያድናቸው ስለሚመስላቸው ሁልጊዜ በቤተክርስቲያናቸው ሰብሰብ ይላሉ። መጨረሻቸው ታላቁ መከራ ነው።
ታላቁ መከራ ውስጥ ሲገቡ ብቻ ነው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ምን ያህል እንደተታለሉ የሚገነዘቡት።
ቀጣዩ ክፍል ደግሞ ያልዳኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ግን ያላመኑ ሰዎች ሲሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ቤተክርስቲያናቸውን ይመርጣሉ። ይህ ምድብ ቤተክርስቲያን ጨርሰው የማይሄዱ ያልዳኑ ሰዎችንም ይጨምራል። እነዚህ ሰዎች የሚጠብቃቸው ታላቁ መከራ እና የፍርድ ቀን ነው። እጣ ፈንታቸው አስፈሪ ነው።
አራተኛው ቡድን ደግሞ ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው እየተመለሱ ያሉ አይሁዳውያን ናቸው። በታላቁ መከራ ወቅት እግዚአብሔር ከእነዚህ ጋር የተለየ ዓላማ አለው።
በስተመጨረሻ የ6,000 ዓመታቱ የሰው ታሪክ ዓላማው ሰይጣንን እና ክፉ ስራዎቹን ሙሉ በሙሉ አይተን እንድንጸየፍ እንዲሁም የሰዎችን ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ አመራር ከንቱነት እንድንገነዘብ ለማድረግ ነው።
ሰዎች እስከዛሬ የሞከሩት ነገር ሁሉ ተፈላጊውን ውጤት አላመጣም፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች የተሳካላቸው አንድ ነገር ልባሞቹንም ሰነፎቹንም ቆነጃጅት እንቅልፍ ማስተኛት ብቻ ነው።
የሚያውቁዋቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፤ ነገር ግን በቤተክርስቲያን መሪዎች መሃይምነት እና ስሕተቶች እንዲሁም የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ባለመቀበላቸው የተነሳ መረዳታቸውን የሚያጣምሙባቸው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም አሉ።
የቤተክርስቲያን ፓስተሮች እምነታቸውን ለማሳየት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማገናኘት ትተዋል። ከተጻፈው ቃል ውስት መረዳት የማይችሉት ብዙ ነው፤ ምክንያቱም እምነታቸው የተመሰረተው በሰዎች ንግግር ጥቅስ ነው። ዛሬ 45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን እምነቶች አሉ፤ እነዚህም ዲኖሚኔሽናል እና ዲኖሚኔሽናል ያልሆኑ ይገኙበታል። እንደዚህ በዓይነቱ የበዛ የሰው ትምሕርት ዓይነት አንዴ ከሰጠሙበት ሊወጡ የማይችሉበት አረንቋ ነው።
ወደ መጥምቁ ዮሐንስ እንመለስ።
ጥምቀት ለራስ ፈቃድ የመሞት እና የመቀበር ተምሳሌት ነው። እውነተኛ ንሰሃ እራስን ለመግደል እና የራስን ፈቃድ እንደ መስዋእት ለእግዚአብሔር አሳልፎ የመስጠት ፍላጎት ነው። ኢየሱስ በውስጣችን ገብቶ እንዲኖርና እኛ ያመሰቃቀልነውን ሕይወት እንዲቆጣጠር እንጋብዘዋለን። ከተጠመቁ በኋላ ከውሃ ውስጥ መውጣት የትንሳኤ ተምሳሌት ነው፤ ይህም በውስጣችን ያለው የእግዚአብሔር ሕይወት ነው። ለራሳችን መሞት አለብን፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ እውነትን አስቦ አስቦ ሊደርስበት አይችልም። በተጻፈው ቃል መመራት አለብን።
ዮሐንስ 3፡23 ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥ እየመጡም ይጠመቁ ነበር
ሄኖን ማለት የተፈጥሮ ምንጭ ውሃ ወይም የምንጮች ቦታ ማለት ነው።
ሳሌም ደግሞ ከተማ ነው። ሳሌም ማለት ሰላም ወይም ምንም ያልተሰበረ ማለት ነው።
በሰዎች አመለካከት ያልተሰበሩ እና ያልተበላሹ የእውነት ምንጮች የተጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ብቻ ናቸው።
የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ስናምነው እና ስንታዘዘው አጥቦ የሚያነጻን ብቸኛው ውሃ ነው።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
ዮሐንስ 3፡24 … ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።
ዮሐንስ ሰዎችን የእግዚአብሔር ቃል ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ጠቆማቸው። ዮሐንስ ቃሉን የመስበኩ አንዱ ውጤት ለሔሮድስ አግብታ የተፈታች ሴትን ማግባት ሐጥያት መሆኑን ፊት ለፊት መናገሩ ነው። ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መቆም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ አያደርግም በፖለቲካ ውስጥም ተቀባይነት አያስገኝም። ስለዚህ ወኅኒ ቤት ገባ።
ይህ ሁኔታ ዓለም እንዴት እውነትን እንደምትጠላ ያሳያል። ለመሲሁ የመጀመሪያ ምጻት መንገድ ሊጠርግ የተላከውን ነብይ ገፉት።
ኢየሱስ አይለወጥም።
ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።
ስለዚህ በመሲሁ ዳግም ምጻትም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚሆነው።
ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።
ትዳር የፈታ ሰው በድጋሚ ሲያገባ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ይተላለፋል። ቤተክርስቲያኖች ግን ተወዳጅነታቸውን ላለማጣት ብለው ትዳር የፈቱ ሰዎች እንደገና እንዲያገቡ ይፈቅዳሉ። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከእግዚአብሔር ቃል እየራቁ ይሄዳሉ፤ ሕዝባቸውንም በተሳሳተ መንገድ ይመራሉ። ኢየሱስ ቃሉ ነው፤ እርሱም አይፈለግም።
ይህ ግን አደገኛ ነገር ነው። መፋታት እና እንደገና ማግባት አመንዝራነት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 6፡9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ
የተፋቱ ሰዎችን የሚያጋቡ የቤተክርስቲያን ፓስተሮች ሰዎችን ከእግዚአብሔር መንግስት እያስወጡ ናቸው።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ የተፋቱ ሰዎችን ለማጋባት እምቢ ማለቱ ዮሐንስን ወደ እስር ቤት ውስጥ አስጣለው።
ስለዚህ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት መንገድ የሚጠርገውን ነብይ የተፋቱ ሰዎች ድጋሚ እንዲያገቡ የሚፈቅዱ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ይቃወሙታል።
መፋታት ሙሽራይቱ ለበጉ ሰርግ የምትዘጋጅበት መንገድ አይደለም።
ዮሐንስ 3፡25 ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።
ጥምቀት ዮሐንስ የጀመረው አዲስ ነገር ስለነበረ አይሁዳውያን የውሃ ጥምቀት ከመታጠብ እና ከመንጻት ጋር የተያያዘ ነገር ይኖረው ይሆናል ብለው አሰቡ። ካሕናቱን የሚያግዙ ሌዋውያን ለአገልግሎት ሲዘጋጁ በውሃ በመታጠብ ይነጹ ነበር።
ዘኁልቁ 8፡6 ከእስራኤል ልጆች መካከል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው።
7 ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም።
ሊዊ ማለት “የተገናኘ” ማለት ነው።
ሌዋውያን እሥራኤል ውስጥ መሬት አልነበራቸውም፤ ስለዚህ ከተሞች ውጥ በእሥራኤል ነገዶች መካከል በመኖር ካሕናትን በሐይማኖታዊ አገልግሎቶች እያገዙ አይሁዶችን ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ።
ነገር ግን ገላን በውሃ መታጠብ እውነተኛው የመንጻት መንገድ መሆኑ ቀርቷል።
በቀራንዮ መንፈስ ቅዱስ ንሰሃ ወደሚገቡ ሰዎችና ሴቶች ልብ ውስጥ ለመግባት ጊዜው እየደረሰ ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስ ወደ ልባቸው ውስጥ መግባቱም ሰዎችን ከውጭ በኩል ሳይሆን ከውስጥ በኩል ያነጻቸዋል።
የሐዋርያት ሥራ 15፡8 ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤
9 ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም።
የአዲስ ኪዳን ትኩረቱ ከውጭ በኩል ማንጻት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን የሚያበቃ ውስጣዊ እምነት ነው። የአዲስ ኪዳን እውነት ሃሳባችንን እና ልባችንን እንዲያነጻው አዲስ መንፈስን መንፈስ ቅዱስን መቀበል ነው።
ዮሐንስ 3፡26 ወደ ዮሐንስም መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ አሉት።
አይሁዶች ወደ ሄኖን መጥተው ለመጥምቁ ዮሐንስ እርሱ ራሱ በቤተራባ አካባቢ በዮርዳኖስ ማዶ ያጠመቀው ኢየሱስ ሌሎች ሰዎችን እያጠመቀ መሆኑን ነገሩት። ይህ ኢየሱስ የሰዎችን ትኩረት የሚስብ ሰው እየሆነ መጥቷል። ሰው ሁሉ ወደ እርሱ እየሄደ ነበር። ኢየሱስ ከዮሐንስ በላይ ታዋቂ እየሆነ ሄደ።
ዮሐንስ ሰዎችን ወደ ቃሉ ጠቆመ (ወደ ኢየሱስ) ስለዚህ ቃሉ ከዮሐንስ በላይ ታዋቂ እየሆነ ሄደ። ዮሐንስ በዚህ አልተከፋም? የሜሴጅ ሰባኪዎች በወንድም ብራንሐም እና እርሱ በተናገራቸው ቃላት ጥቅሶች ላይ ትኩረት ያበዛሉ። ነገር ግን ከዚህም ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር እምነታችንን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መስርተን ማጽናት ነው።
ዮሐንስ 3፡27 ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም።
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔር ስጦታ ይሰጣቸዋል። ስለዚህ ሰው እግዚአብሔር በሰጠው ስጦታ በማገልገል ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ምስጋነው መሰጠት ያለበት ለእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ሰው ትክክለኛውን ነገር ስለማድረጉ ምስጋና ባያገኝ ምንም ችግር የለም። የእግዚአብሔር ዓላማ እስከተፈጸመ ድረስ ቁምነገሩ ያ ብቻ ነው። የሰውን አድናቆት አለማግኘት ምንም ቁምነገር አይደለም።
ዮሐንስ 3፡28 እናንተ፦ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን፦ ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ።
ዮሐንስ እኔ ኢየሱስ ነኝ አላለም። ዮሐንስ ኢየሱስን ለአይሁድ ሊያስተዋውቅ ነው የተላከው። ነብይ አምላክ አይደለም።
ዮሐንስ 3፡29 ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።
ነብይ ከእግዚአብሔር አጠገብ በመቆም ይደሰታል።
ሙሽራው ኢየሱስ ሙሽራይቱን በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይማርካታል። ኢየሱስ ብቻ ነው በ2,000 ዓመታት ውስጥ መጓዝ እና ለዘመናቸው የተገለጠውን እውነት የሚያምኑ ክርስቲያኖችን ለይቶ ለራሱ ማድረግ የሚችለው። ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ነው አስፈላጊው። መጥምቁ ዮሐንስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በጴንጤ ቆስጤ ዕለት ከመወለዷ አስቀድሞ ነው የመጣው። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አካል አልነበረም። እርሱ መሲህ ከመምጣቱ በፊት የተላከ የአይሁድ ነብያት የመጨረሻ ነብይ ነበረ። ዮሐንስ እራሱን የኢየሱስ ጓደኛ አድርጎ ነው የሚቆጥረው። እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው። ስለዚህ ኢየሱስ መስበክ መጀመሩን ሲያይ ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለሕዝቡ በማስተዋወቁ ይደሰታል።
ኢየሱሰ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ድምጽ።
ዮሐንስ ነገሮች ከአይሁድ ሕዝብ አልፈው እንደሚሄዱ ተረድቷል፤ ምክንያቱም አይሁዶች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። ነገር ግን ሌላ ቡድን ማለትም ሙሽራይቱ ወደ አደባባይ ብቅ ልትል ነው። ዮሐንስ ልትመሰረት ስላለችው የአሕዛብ ቤተክርስቲያን የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የተሰጠውን ሥራ በሚገባ ማከናወኑን ብቻ እና የእግዚአብሔር ድምጽ የሆነው ኢየሱስ ለሕዝቡ እየተናገረ መሆኑን ብቻ ነው የሚያውቀው። ይህም ለዮሐንስ ታላቅ ደስታ ሰጥቶታል።
ለመጀመሪያው ምጻት መንገድ ጠራጊ የነበረው ነብይ የእግዚብሔር ድምጽ አልነበረም፤ ነገር ግን ስብከቱ መልእክቱ የእግዚአብሔርን ድምጽ በመግለጡ ተደስቷል፤ የእግዚአብሔርም ድምጽ የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ ነው።
ሕዝቡም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዮሐንስን ሳይሆን ኢየሱስን ማዳመጥ ጀመሩ።
ዮሐንስ 3፡30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።
የመጥምቁ ዮሐንስ ንግግር ጥቅሶች ቃሉን (ኢየሱስን) ለሕዝቡ ገለጡ። ኢየሱስ ተቀናቃኝ ወይም ተፎካካሪ የለውም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ እያደገ ሲሄድ የነብዩ ዮሐንስ አስፈላጊነት ደግሞ እየቀነሰ ሄደ።
ነብዩ በእርግጥ ታላቅ ነብይ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናቸው አይችልም። ኢየሱስ ብቻ ነው ማዳን የሚችለው።
ነብዩ የእግዚአብሔር በስጋ መገለጥ አይደለም። እግዚአብሔር በስጋ የተገለጠው በኢየሱስ ነው። አማኑኤል።
ነብዩ ከድንግል አይደለም የተወለደው፤ ኢየሱስ ነው ከድንግል የተወለደው።
በመንፈሳዊ ነገር መጥምቁ ዮሐንስ ከሕዝቡ በላይ ከፍ ያለ ሰው ነው። ኢየሱስ ግን ከመጥምቁ ዮሐንስም በላይ ከፍ ብሏል።
ዮሐንስ 3፡31 ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
ዮሐንስ መጥረቢያ የዛፍን ስር ሊቆርጥ መዘጋጀቱን የመሳሰሉ ምድራዊ ነገሮችን ማውራት ይችላል። ዮሐንስ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን የእፉኝቶች ብሎ ነው የገለጻቸው።
አሁን ግን ፊት ለፊት የቆምነው እግዚአብሔር በአካል ውስጥ ሆኖ ከተገለጠበት ከኢየሱስ ጋር ነው። እርሱ የመጣው ከፍ ካለው ከሰማያዊ ክልል ነው፤ በዚያም በሰማያት ባለበት የሰውን ታሪክ ያለፈውንና የወደፊቱን በአንድ ላይ ማየት ይችላል። ስለዚህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ ነው፤ በእውቀቱ እና በእይታው ብቻ ሳይሆን በኃይልም ከሁሉ በላይ ነው። ማንም ምንም ነገር ሊያስተምረው አይችልም።
ዮሐንስ 3፡32 ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
ኢየሱስ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ ሊነግረን ይችላል። በዚያ ሰዓት የነበረውን የአይሁዶች ሁኔታ እንዲሁም ሐይማኖታቸውን እና ወደ ፊት እርሱን እንደሚገፉትም፤ ከዚያ እርሱ ወደ አሕዛብ ዘወር እንደሚልም ያውቃል። አይሁድ ግን በሐይማኖት መሪዎቻቸው በመነሳሳት ኢየሱስን አንቀበልህም ይሉታል።
የቤተክርስቲያን አባላት ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ካስተማሩዋቸው ትምሕርቶች ጋር የሚቃረኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ የተገለጡ የእግዚአብሔር እውነቶችን አንቀበልም ይላሉ።
ዮሐንስ 3፡33 ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያምኑ ግን የተጻፈው ቃል እውነት መሆኑን ይመሰክራሉ፤ ደግሞ እውነት ስለሆነም ማንም ሰው የተጻፈውን ቃል መለወጥ አይችልም።
ዮሐንስ 3፡34 እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
እግዚአብሔር የሚልከው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚናገር ሰውን ብቻ ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሙሉ ቃል ነው፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር የመለኮት ሙላት በእርሱ ውስጥ ነው የሚኖረው።
ኢየሱስ በፍጹም አይለወጥም።
ስለዚህ ኢየሱስ እስከ አሁንም ድረስ ሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት ነው።
ኢየሱስ እንደ እኔ እና እንደ እናንተ መንፈስ ቅዱስ ተሰፍሮ አይደለም የተሰጠው። እርሱ መንፈስ ያለ መስፈሪያ ሙሉ በሙሉ ተሰጥቶታል።
አንድ ሰው የተናገራቸውን ሃሳቦች በሙሉ ልቅም አድርጎ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት ጥቅሶች መሰረት ሲያሳያችሁ ብቻ ነው የነገራችሁ ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን እርግጠኛ የምትሆኑት።
ዮሐንስ 3፡35 አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።
ኢየሱስን ለራሳችን ማየት የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ ነገሮች ሁሉ ጋር ይስማማል።
ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ነገር አንዳችም አይለውጠውም። ስለዚህ የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ካመናችሁ የሚመራችሁንና የሚጠብቃችሁን የእግዚአብሔር ሃሳብ አግኝታችኋል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ መጠን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሚያስባቸው ነገሮች ሁሉ አሉት።
ዮሐንስ 3፡36 በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
መሰረታዊው ወንጌል ይህ ነው። ከሐጥያታችሁ ንሰሃ በገባችሁ ጊዜ ኢየሱስን የግል አዳኛችሁ በማድረግ ወደ ልባችሁ ውስጥ ተቀበሉት።
ያነጻችሁ እና ይቀድሳችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ይደግ። ከዚያ መንፈስ ቅዱስ የተጻፈውን ቃል እንድታምኑ በሚያደርጋችሁ ጊዜ ሕይወታችሁን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር እና የእግዚአብሔርን ቃል እንዲገልጥላችሁ ፍቀዱ። በውስጣችሁ የሚያድገው መንፈስ ቅዱስ የዘላለም ሕይወት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን የማያምኑ ግን ሕይወትን አያዩም። ሕይወት የእናንተ ኑሮ አይደለም። በኑሮዋችሁ ውስጥ የምታገኙት ስኬት አይደለም። ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስን ከማመናችሁ ወይም ከአለማመናችሁ ጋር የተያያዘ ነው።
የተገለጠውን መጽሐፍ ቅዱስ የማናምን ከሆነ ጉዳችን ፈላ።
ስለዚህ መዳናችን መጽሐፍ ቅዱስን በማመናችን ላይ የተመሰረተ ነው። ስኬታችንም ሆነ ኪሳራችን ሁለተኛ ነገር ስለሆኑ ሕይወት ከእነዚህ ጋር አይያያዝም። ሰዎች እንደመሆናችን ከሰራነው ወይም ካልሰራነው ነገር አንጻር በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ እንደ ዝርዝር ሳንቲሞች በጣም ትንሽ ነን።
ዋናው ቁም ነገር ኢየሱስ በሰራው ስራ እና በተናገረው ቃል ማመናችን ነው። ኢየሱስ ብቻ ነው ዘመዳችን የሆነው ቤዛችን። ከሲኦል ያዳነን እርሱ ብቻ ነው። በሰው ዘር ላይ ከሚመጣው ከእግዚአብሔር ቁጣ ከታላቁ መከራ ሊያድነን የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።