ዮሐንስ ምዕራፍ 04. ለሳምራውያን የተገለጠው የመሲሁ ምልክት



First published on the 27th of September 2020 — Last updated on the 27th of September 2020

ዮሐንስ 4፡1 እንግዲህ፦ ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል ያጠምቅማል ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥

ፈሪሳውያን ቤተመቅደሱን የሚያስተዳድሩበትን ስልጣን ቀምተው ይዘዋል። የሙሴ ሕግ ስለ ፈሪሳውያን አንዳችም አይናገርም። የማይረቡ ሰዎች ብቻ ናቸው በሌሎች ሰዎች ላይ ጌታ መሆን የሚፈልጉት፤ መልካም የሆኑ ሰዎች ግን መልካም ስራዎችን በመስራት ከመጠመዳቸው የተነሳ በሌሎች ላይ ስልጣንን ለመፈለግ ጊዜም የላቸውም። በቤተመቅደስ ውስጥ ያሉት ፈሪሳውያን ምን እንደሚያስቡ እና ምን እንደሚናገሩ ኢየሱስ ያውቃል። የሐይማኖት መሪዎች ሁሉ እንደሚሆኑት ፈሪሳውያንም ሁልጊዜ ሃሳባቸው ስለ ራሳቸው ስልጣን እና ስ ገንዘባቸው ነው። ከቤተመቅደሱ ጋር የተያያዘ ሐይማኖታቸው ከፍተኛ የንግድና የገንዘብ ምንጭ ነበረ። እንደ ኢየሱስ ያለ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር ድሃ ሰባኪ በድሎት የሚኖሩበትን ኑሮ እንዲያከሽባቸው አይፈልጉም።

ኢየሱስ መሲህ ስለሆነ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ሃሳብ ያውቃል። ይህም የመሲህነት ምልክት ነው።

1ኛ ነገስት 8፡39 … አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና …

የሰዎችን የልብ ሃሳብ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። መሲህ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” -- አማኑኤል ነው። እርሱም የሰዎን ሃሳብ የሚያውቅ ሰው ነው።

ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ፈሪሳውያን የአይሁዳውያን መኖሪያ በሆነው ሃገር ውስጥ በይሁዳ ኢየሩሳሌም ውስጥ በቤተመቅደሱ ውስጥ የሚደረገውን አምልኮ የሚመሩ አይሁዳውያን ነበሩ።

ኢየሱስ ቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት የሐይማኖት መሪዎች ዘንድ ተወዳጅ አልነበረም። ኢየሱስ ለጻፎች እና ለፈሪሳውያን በተለሳለሰ ቃል ተናግሮ አያውቅም፤ ብዙውን ጊዜ ግብዞች ነው የሚላቸው። ኢየሱስ በመጀመሪያ ምጻቱ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን ግብዞች ካላቸው በዳግም ምጻቱ ሲመጣ የሚያገኛቸውን የቤተክርስቲያን መሪዎች ምንድነው የሚላቸው? ስለዚህ የአይሁድ ሐይማኖት ማእከል በነበረችው በኢየሩሳሌም ውስጥ ያሉ ሰዎች ኢየሱስን አይፈልጉትም ነበር።

አይሁዳውያን ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን መጥራት በጀመረበት በገሊላ ከተማም ውስጥ ይኖሩ ነበር። በገሊላ ኢየሱስ የመሲህነቱን ምልክት ለአይሁዳዊው ለናትናኤል የልቡን ሃሳብ በመግለጥ አሳይቶ ነበር። ኢየሱስ ናትናኤል ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ፤ በዚያን ዕለት እርሱጋ ከመምጣቱ በፊት የት እንደነበረ እና ባይገናኙም እንኳ ናትናኤል ከማን ጋር ይነጋገር እንደነበረ ሁሉ አውቋል።

ዮሐንስ 1፡48 ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።
49 ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።
50 ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።

አይሁዳዊው ናትናኤል ሃሳቡ፣ ባህርዩ እና ከሰዓታት በፊት ምን ሲያደርግ እንደነበረ ተገልጦ ሲነገረው ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን ተረዳ።

ኢየሱስ ግን ቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት ፈሪሳውያን ሃሳብ ደስ አላለውም። እነርሱ መጥምቁ ዮሐንስን ገፍተውታ፤ ዮሐንስን ያልገደሉትም ሕዝቡን ስለፈሩ ነው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ነብይ ነው ብለው ተቀብለውት ነበር።

ማርቆስ 11፡30 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ አላቸው።
31 እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ነው ብንል፦ እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
32 ነገር ግን፦ ከሰው ነው እንበልን? አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።

ደግሞም ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደሱ ውስጥ አባርሮ አስወጥቷቸዋል፤ ከዚያ ጊዜ ወዲህ ፈሪሳውያን ጠልተውታል። የሐይማኖት መሪ ገንዘብ የሚያገኝበትነ ምንጭ የነካችሁበት ጊዜ በጣም ይጠላችኋል። ኢየሱስ ግን በገንዘብ ብዛት አይደነቅም ነበር።

ሉቃስ 6፡24 ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥

ስለዚህ ኢየሱስ ፈሪሳውያን እርሱንም አንቀበልህም ማለታቸውን አውቋል፤ በተለይም በአገልግሎቱ ከመጥምቁ ዮሐንስ በላይ ስኬታማ በመሆኑ።

የሐይማኖት መሪዎች በጽኑ ተቃውሞ በሚቃወሙዋችሁ ቦታ ማገልገል በጣም ከባድ ነው። ሕዝብ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ከመስማታቸው በፊት የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ምን እንደሚሉ ነው የሚሰሙት። በዚህ ዘመን ካሉት የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን የተነሳ አብዛኛው አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ አያውቅም።

ዮሐንስ 4፡2 ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም።

ኢየሱስ እራሱ ማንንም አጥምቆ አያውቅም። ጥምቀት እርሱ ወደ ፊት ሊሞት ሊቀበር እና ከሙታን ሊነሳ እንዳለው የሚያመለክት ስርዓት ነበረ።

የሐይማኖት መሪዎች ታላቅነታቸውንና ስልጣናቸውን ለማሳየት ብለው አዲስ አማኞችን ካላጠመቅን ይላሉ። ኢየሱስ ግን እንደዚያ አያደርግም ነበር።

ዮሐንስ 4፡3 ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤

ስለዚህ ይሁዳ ውስጥ ባሉት አይሁዳውያን መካከል በማገልገል የመጥምቁ ዮሐንስን አገልግሎት ከማደብዘዝ ብሎ ኢየሱስ ገሊላ ውስጥ ወዳሉት አይሁዳውያን ለመሄድ ወሰነ። በተጨማሪ ደግሞ የፈሪሳውያን ተቃውሞ በይሁዳ ውስጥ ያሉት አይሁዳውያን የኢየሱስን ቃል እንዳይሰሙ ያደርጋቸዋል።

አንድ ፓስተር አንድ ሰውን ካወገዘ የቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ የተወገዘውን ሰው ያወግዛሉ። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን የፓስተሩ መንፈስ በሕዝቡ ላይ ይጋባል፤ ከዚህም የተነሳ ትክክለኛ ክርስቲያን መሆን አይችሉም። ጊዜው የክረምት አጋማሽ በመሆኑ ቅዝቃዜው ለመንገድ ከባድ ቢሆንም ኢየሱስ ተነስቶ ወደ ገሊላ ረጅም መንገድ በእግሩ ሄደ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ መታዘዝ መስዋእትነት ይጠይቃል።

ነገር ግን በይሁዳ እና በገሊላ መካከል ግን ሰማርያ የምትባል ከተማ ነበረች።

ዮሐንስ 4፡4 በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት።

ሳምራውያን አይሁዳውያን እና አሕዛብ ሲጋቡ የተፈጠሩ ክልሶች ነበሩ። ከሰማርያ ወደ አሶር ተማርከው የሄዱት የመጀመሪያዎቹ አይሁዳውያን ተመልሰው አልመጡም፤ ምክንያቱም ቤተል እና ዳን ከተማ ውስጥ የወርቅ ጥጃዎችን ያመልኩ ነበረ። በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረገውን እውነተኛውን አምልኮ ትተዋል። ወደ ምርኮ አገር ከሄዱ በኋላ ከታሪክም ውስጥ ተረስተዋል። ሐሰተኛ ሐይማኖት ሰዎችን ወደ እውነት ሊመልሳቸው አይችልም።

የአሶራውያን ግዛት ከታች ያለው ካርታ ላይ በቀይ ቀለም ምልክት የተደረገበት ቦታ ተጀመረና አረንጓዴ ቀለም ወደተቀባበት ቦታ ሁሉ ተስፋፋ። ይህም ቢጫ ቀለም የተደረገበትን የእሥራኤልን ምድር ይጨምራል። ቢጫ ቀለም የተቀባበት የእሥራኤል ምድር ውስጥ የቀሩት ጥቂት አይሁዳውያን አሶራውያን ወደዚያ አምጥተው ካሰፈሩዋቸው አሕዛቦች ጋር ተቀላቅለው ተጋቡ፤ ተዋለዱ። ይህ ቢጫ ቀለም የተቀባው ቦታ ሰማሪያ ተብሎ ተጠራ፤ ከአይሁድ እና ከአሕዛብ ተዳቅለው የተወለዱት ሕዝብም ሳምራውያን ተባሉ።

ካርታው ላይ የወይን ጠጅ ቀለም የተቀባው የይሁዳ ግዛት ቢጫ ቀለም ከተቀባው ከእሥራኤል ግዛት በታች ነው የሚገኘው። አሶራውያን ይሁዳን ወደ ግዞት ቤት አልወሰዱም።

ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ሲወጣ ኢየሱስ መጀመሪያ ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ ነው የመጣው።

ዮሐንስ 4፡5 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤
ዮሐንስ 4፡6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።

ሲካር ከእብራይስጥና አራማይክ የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መዘጋት” ማለት ነው። ጉድጓዱ የፍጥረታዊ ውሃ ምንጭ ነው፤ ሳምራውያን ግን ከእውነኛው የመንፈሳዊ ውሃ ምንጭ ከመንፈስ ቅዱስ ተዘግተው ተለይተው ነበር።

የሲካር ከተማ ኢያሱ ቆሞ ለእግዚአብሔር የመታዘዝን በረከት እና ያለመታዘዝን እርግማን ካወጀባቸው ሁለት ተራሮች መካከል ነበረች። ኢያሱ የተስፋይቱን ምድር በጦርነት አሸንፎ በተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር በሁለቱ ተራሮች ላይ የቆመው። ኢያሱ ሲካር ውስጥ መጥቶ በቆመ ጊዜ ብርቱ ጠናካራ ሰው ነበረ።

ኢየሱስ ግን ረጅም መንገድ ሄዶ ነበር የመጣው ስለዚህ ደክሞት ተቀመጠ። ኢየሱስ ብርቱ ገዥ አይመስልም ነበር። ነገር ግን ሐጥያትን፣ ሲኦልን፣ እና መቃብርን በቁጥጥሩ ስር ሊያደርግ መንፈሳዊ ዘመቻ ላይ ነበረ። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ በሁለት ሺህ ዓመታት ታሪክ በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ዓለምን ሁሉ በወንጌል ለመግዛት ነበር እቅዱ።

የኤባል ተራራ ከሲካር በስተ ሰሜን የገሪዛን ተራራ ደግሞ ከሲካር በስተ ደቡብ ነበሩ።

ኤባል ማለት ውድመት ወይም ጥፋት ነው። ይህም ተራራ ከሐሰተኛ እምነት የተነሳ የሚመጡ እርግማኖች ታውጀውበታል።

ገሪዛን ደግሞ እግዚአብሔርን ለሚታዘዙና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ለሚያምኑ ሰዎች የበረከት ምንጭ ነው።

የሳምራውያን ምድር በአሶራውያውን ከተወረረ በኋላ በአሶራውያን ቁጥጥር ውስጥ ነበረ። ይህም እርግማን የመጣው በቤቴል እና ዳን ውስጥ ተሰርተው በቆሙት የወርቅ ጥጃ ጣኦታት የተነሳ ነበር።

ስለዚህ አሁን ኢየሱስ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ ሊገኝ የሚችለውን የዘላለም ሕይወት ለሳምራውያን አቀረበላቸው።

ዮሐንስ 4፡7 ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት።

ከዚህች ሴት ጋር ሆኖ ኢየሱስ ለ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ የነበረውን እቅድ ሊገልጥ ነው። ይህ ነው የእርሱ ጠለቅ ያለ እቅዱ። ሴትየዋ ሐጥያተኛ ሴት ነበረች፤ ነገር ግን ሐጥያተኝነቷ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ጊዜውን የሚጠቀመው ሐጥያተኞችን ለማዳን እንደሆነ ያመለክታል።

ዮሐንስ 4፡8 ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና።

ደቀመዛሙርቱ ትኩረታቸው ስጋዊ ነገር ላይ ነበረ፤ ኢየሱስ ግን ትኩረቱ መንፈሳዊ ነገር ላይ ነው። እኛ ክርስቲያኖች ራሳችን ቁሳዊ ፍላጎታችንን በማስቀደም ተመሳሳይ ስሕተት እንሰራለን።

ዮሐንስ 4፡9 ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።

ዘረኝነት ወይም የሌላ ብሔር ሰዎችን መጥላት ከጥንትም ጀምሮ ነበረ። አይሁዳዊ ሳምራውያንን አያናግርም ነበር። አንድ ሰው የማያውቃትን ሴት ማናገር የለበትም። እነዚህ ሁለት ነውር ተደርገው የሚቆጠሩ ልማዶችን በመጣስ ኢየሱስ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው እንደሚፈልግ እና እንደሚያድን ገለጠ።

ዮሐንስ 4፡10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።

ሴትየዋ ኢየሱስ በስጋ ሰው መሆኑን ማየት ትችላለች። ነገር ግን በኢየሱስ ውስጥ ተሰውሮ የነበረውን መለኮት እግዚአብሔር ማየት አልቻለችም።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

መሲህ ማለት እግዚአብሔር በሰው አካል ውስጥ በመካከላችን ሲመላለስ ማለት ነው።

ዮሐንስ 4፡11 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?

ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰበሰበውን የሕዝብ ብዛት እና የተገኘውን የገንዘብ መጠን የእግዚአብሔር በረከት ማረጋገጫ አድርገው እንደሚቆጥሩ የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ይህች ሴትም ፍጥረታዊ ከሆነው ነገር ውጭ ምንም ማየት አልቻለችም።

ዮሐንስ 4፡12 በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው።

ያዕቆብ የተባለው ሰው የሕዝቡ መጠሪያ እሥራኤል የተባለውን ስም የሰጠ ታላቅ ሰው ነው። ኢየሱስ ከያዕቆብ ሊበልጥ ይችላል? መልሱ ጥርጥር የሌለው “አዎን” የሚል መልስ ነው።

ያዕቆብ ደረቅ በሆነ ምድር ውስጥ ጥልቅ ጉድጓድ በመቆፈር ለልጆቹ ውሃ ሰጥቷል። ኢየሱስ ደግሞ ከያዕቆብም የበለጠ ጥልቅ ጉድጓድ በመቆፈር ሐጥያታችንን ተሸክሞ ሄዶ የሐጥያት አባት በሆነው በዲያብሎስ ላይ አራግፎ እኛን ሲኦል ውስጥ የሐጥያት ዋጋ ከመክፈል ነጻ ያወጣናል። ኢየሱስ በመንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ በሚኖሩ ልጆቹ ልብ ውስጥ በደምብ አጥልቆ ይቆፍራና በመንፈስ ቅዱስ የሕይወት ውሃ ይሞላቸዋል።

ዮሐንስ 4፡13 ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤

ዮሐንስ 4፡14 እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።

ሰማሪያ ውስጥ ያሉ የወርቅ ጥጃዎች እና ሌሎች ጣኦታት ሁሉ ሰው እንዲንከባከባቸው ይፈልጋሉ። ጣኦት የሚያመልኩ ሰዎች አምላካቸውን መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል። ኢየሱስ ይዞ የመጣው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ሲሆን እርሱም ሰዎች ውስጥ ከገባ በኋላ ሰዎቹን ይንከባከባቸዋል። እግዚአብሔር ሰዎችን መንከባከቡ ሰዎች አምላካቸውን ከመንከባከባቸው በጣም የተሻለ ሃሳብ ነው።

ዮሐንስ 4፡15 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።

ሴትየዋ በደምብ ባይገባትም በጣም ተገርማለች፤ ደገሞም ይህንን የሕይወት ውሃ ፈልጋለች። ነገር ግን ትጠባበቅ የነበረው የግል ምቾቷን የሚያስጠብቅላት ሐይማኖት ነበር። ውሃ ለመቅዳት ረጅም መንገድ ሄዳለች፤ ከዚያም ወደ ቤቷ ውሃ ተሸክማ ረጅም መንገድ ትመለሳለች። በየእለቱ ወደ ውሃ ጉድጓዱ የማትመላለስ ከሆነ ይህ አዲስ ሐይማኖት ብዙ ድካም ሊቀንስላት ነው። የግል ጥቅም ለማስከበር ብላ በተሳሳተ ዓላማ ነበር የምትመራው።

ብዙውን እግዚአብሔርን እናገለግላለን፤ ልባችን ግን በእግዚአብሔር ፍቅር ተሞልቶ አይደለም የምናገለግለው፤ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ጥምቅ ለማግኘት ብለን እንጂ። ይህም በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት ጥልቀት እንዳይኖረው ያደርጋል።

ኢዮብ እግዚአብሔርን ስለማገልገል የተሻለ ልብ ነበረው።

ኢዮብ 13፡15 እነሆ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን እጠባበቃለሁ፤

ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ልብ ነበረው፤ እራሱን ወጪ ካላስወጣው በቀር እግዚአብሔርን ለማገልገል ሃሳብ የለውም። አውድማው እና የመስዋእቱ በሬዎች በነጻ ተሰጥተውት ነበረ፤ እርሱ ግን የለም መክፈል አለብኝ አለ።

ያም ቦታ ኋላ ቤተመቅደሱ ተሰራበት።

2ኛ ሳሙኤል 24፡24 ንጉሡም ኦርናን፦ እንዲህ አይደለም፥ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ።

ዮሐንስ 4፡16 ኢየሱስም፦ ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት።

ኢየሱስ አስተሳሰቧን ለወጠላት። እርሷ የእግር መንገድ የሚቀንስላት ሐይማኖት ነው የፈለገችው። ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በእግሯ ወደ ቤት ተመልሳ ባልዋን ይዛ እንድትመጣ አዘዛት።

ዮሐንስ 4፡17 ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤
ዮሐንስ 4፡18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።

ሴትየዋ ከዚህ በፊት አምስት ጊዜ አግብታ እንደነበር አሁን ደግሞ ያላገባቸው ሰው ጋር አብራ እንደምትኖር ኢየሱስ ነገራት።

በመንገድ ደክሞት የተቀመጠ አንድ ሰው ስለ እርሷ ይህን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?

ወዲያው አእምሮዋ ወደ ከፍታ ወጣ። ይህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ነብይ መሆን አለበት። ቀጥታ እግዚአብሔርን የሚያደምጥ ሰው መሆን አለበት።

ዮሐንስ 4፡19 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።
ዮሐንስ 4፡20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው።

ሳምራውያን በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ በሚያመልኩ አይሁዳውያን ዘንድ የተናቁ ሰዎች ነበሩ። ስለዚህ ሳምራውያን በገሪዛን ተራራ ነበር የሚያመልኩት። ተራራውን የአምልኮዋቸው ማዕከል አድርገውታል።

ሴትየዋ ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበሩት ጻፎች እና ፈሪሳውያን ኢየሱስን አንቀበልም ብለው እንደገፉት አላወቀችም።

ዮሐንስ 4፡21 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።

እግዚአብሔር ቤተመቅደሱን በሰዎች ልብ ውስጥ የሚያደርግበት አዲስ ቀን እንደሚመጣ ኢየሱስ ነገራት። ንሰሃ በገባ ሰው ልብ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ሲኖርበት የእግዚአብሔር ዙፋን በምድር ላይ በዚያ ልብ ውስጥ ይመሰረታል።

እግዚአብሔር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በምድር ላይ የሚሰራበት መንገድ ይህ ነው።

ዮሐንስ 4፡22 እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።

ኢየሱስ የሳምራውያን አምልኮ ዋጋ እንደሌለው በግልጽ ተናገረ፤ ምክንያቱም ሳምራውያን የራሳቸውን ሕግ አዘጋጅተዋል፤ ለራሳቸውም በመረጡት ተራራ ላይ የአምልኮ ስፍራ ወስነዋል። እግዚአብሔር ግን በሰዎች አመለካከት እና ልማድ አይደሰትም።

የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የሚፈጸመው በአይሁዳውያን በኩል ነው። ኢየሱስ ሐጥያትን እና ሞትን እንዲያሸንፍ አይሁዳውያን እርሱን እንደ እውነተኛ የፋሲካ በግ መሰዋት አለባቸው።

ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

የቤተክርስቲያን ልማዶች እውነትን ያንኳስሳሉ። የኢየሱስን ልደት አክብሩ አልተባልንም። ዲሴምበር 25 ሮማውያን የሚያመልኩት የፀሐይ አምላክ ልደት ነበረ። ኤርምያስ ምዕራፍ 10 ዛፎችን ማጋጌጥ እንደሌለብን ይነግረናል። ክሪስማስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይታወቅ ቃል ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን ታላቁ ዓመት በዓል ብለን ስናከብረው እጅግ ተሳስተናል።

ቤተክርስቲያኖች የጌታ እራት የሚወስዱት በጠዋቱ የአምልኮ ፕሮግራማቸው ነው። ነገር ግን የጌታ እራት ነው የተባለው እንጂ የጌታ ቁርስ አይደለም።
ሰው እንደዚህ እያደረገ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ይለዋውጣል፤ ኢየሱስ ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ አምልኮ ከልብ ቢሆንም ከንቱ እንደሆነ ተናግሯል።

ዮሐንስ 4፡23 ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤

በጴንጤ ቆስጤ ዕለት የሆነው የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመንፈስ ውስጥ ያሉ ሶስት ደረጃዎችን አስተዋውቋል፤ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡- ከሲኦል ለመዳን ንሰሃ መግባት፣ ቅድስና፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ተዓምራዊ መገለጥ ማመን ናቸው።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

እግዚአብሔር የሚታይና የሚዳሰስ አምላክ አይደለም። ስለዚህ የሚገለጥበት ዋነኛ መንገዱ መንፈሳዊ ነው። እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንድናውቅም ይጠብቅብናል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ባናውቅ ወይም የማወቅ ፍላጎት ባይኖረን በእኛ ደስ አይለውም።

የኪንጅ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ብሎ መናገድ አንድ ሰው በመንፈስ አለመሞላቱን የሚያሳይ ምልክት ነው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላታችን የመጨረሻ ማረጋገጫ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል አንብበን መረዳት መቻላችን ነው።

ዮሐንስ 4፡25 ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።

ሴቲቱ ሊመጣ ያለው መሲህ መኖሩን ታውቃለች፤ ደግሞም መሲሁ የሰዎችን የልብ ሚስጥር እንደሚያውቅም ታውቃለች።

ዮሐንስ 4፡26 ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።

አይሁዳዊው ናትናኤል ኢየሱስ የልቡን ሃሳብ እና ወደ እርሱ ከመምጣቱ በፊት ምን እያደረገ እንደነበረ ሲገልጥለት እርሱ የእግዚአብሔር በስጋ መገለጥ መሆኑን ወዲያው ተረድቷል።

ሳምራዊቷ ሴት ናትናኤል የተረዳው መረዳት ላይ ለመድረስ ጥቂት ጊዜ ፈጅቶባታል። ኢየሱስ ማንነቱን የነገራት ጊዜ ግን ወዲያ በራላት።

ዮሐንስ 4፡27 በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም፦ ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።

ደቀመዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ግን እስካሁንም አይሁዳዊ ሰው ከሳምራዊት ሴት ጋር ለምን ያወራል በሚለው ስጋዊ ጥያቄያቸው ተጠምደው ቀሩ።

የሴቲቱ አእምሮ ጠለቅ ያለውን እውነት ለመረዳት በተከፈተ ጊዜ ወዲያው በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ምን እየተከናወነ እንደነበር ማየት አልቻሉም።

ሆኖም የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዓቱን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት ስለነበረ ሴቲቱን አንዳችም እንዳይጠይቋት አደረጋቸው። ከዚያም አልፎ መንፈስ ቅዱስ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ለምን ከሴት ጋር ትነጋገራለህ ብለው እንዳይጠይቁት አደረጋቸው። ደቀመዛሙርቱ ጣልቃ ቢገቡ የእግዚአብሔርን ስራ ሊያሰናክሉ ይችሉ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸጥ እንዲሉ አደረጋቸው። ወንጌል የሚሳካው አገልግሎቱን እግዚአብሔር በተቆጣጠረው ጊዜ ብቻ ነው።

ዮሐንስ 4፡28 ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም፦

ውሃ አስተምሕሮን ነው የሚወክለው።

ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት

ሴቲቱ (የቤተክርስቲያን ምሳሌ) የራሷ የግሏ የሆነ የሐይማኖት መሪዎችዋ ያስተማሯት የእምነት እንስራ ነበራት። እውነኛው ቃል የሆነውን ኢየሱስን ስታገኘው የቀድሞ ትምሕርቶቿን ወዲያው ጥላ ሄደች።

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ለመረዳት ትልቁ እንቅፋት የቤተክርስቲያን ሰዎች በቤተክርስቲያን በተማሩት እምነት ላይ የሙጥኝ ብለው ሲጣበቁ ነው።

ወደ ከተማ ከተመለሰች በኋላ ተሰምቶ የማይታወቅ ነገር አደረገች፤ ሄደችና ወንዶቹን ሁሉ አነጋገረች።

ዮሐንስ 4፡29 ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች።

ይህ ሰው የበፊት ኑሮዋን እንዲሁም አሁን ያለችበት ሁኔታ ገልጦ ነግሯታል። አምስት ባሎች ሞተውባት ከስድስተኛ ሰው ጋር እንዲሁ እየኖረች ነበር። አሁን ግን በስተመጨረሻ እውነትን አግኝታለች፤ ስለዚህ ለምድራዊ ሰላም ብላ ከወንዶች ጋር መታሰር ነጻ ወጥታለች። ከዚህ በኋላ ከየትኛውም የቤተክርስቲያን ቡድን ጋር መታሰር አበቃ። ኢየሱስን እራሱን ፊት ለፊት አግኝታዋለች፤ ይህም እግሮችዋን በዘላለም ሕይወት ጎዳና ላይ መንገድ አስጀምሯታል፤ በዚህ የምድር ሕይወት ውስጥ ብትጎዳም እንኳ አይቆጫትም።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ወዲያም የእግዚአብሔር ፈቃድ ከራሷ ምቾትና ከግል ፈቃዷ በላይ ትልቅ ሆኖ ታያት።

ኢየሱስ አካባቢያዊ ክስተቶችን በመጠቀም ጠለቅ ያሉ መንፈሳዊ እውነቶችን ለቀጣዮቹ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ እንዲደርሱ እያስተጋባ ነበር።

በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያን በሰባተኛው ዘመንዋ ላይ ደርሳለች። ስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት አልፈዋል፤ አሁን ደግሞ በሰባተኛው መልአክ ወይም መልእክተኛ ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱ የእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈውን ቃል ሚስጥራት በሙላት ወደ መረዳት ሊያደርሰን በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ሚስጥር መረዳት የምንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

አሁን ስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ስላለፉ የተገለጠው ቃል ክርስቶስ ሳምራዊቷን ሴት እንዳናገራት እኛንም ማናገር ይችላል።

ዮሐንስ 4፡30 ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ይህ መንፈሳዊ መረዳት ነው። ኢየሱስን ለማግኘት ከሚኖሩበት ወጥተው ሄደዋል።

በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ያንኳኳል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

ኢየሱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉ ግለሰቦች ነው ጥሪውን የሚያቀርበው እንጂ ለቤተክርስቲያን በሙሉ አይደለም።

ኢየሱስ ዛሬ ምንድነው የሚመክረን?

ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

መሪ የሆኑት ፓስተሮች ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ምን ማለት እንደሆኑ ባለማወቃቸው የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን አብዛኛውን ክፍል ቸል ብለን እንድናልፍ ከሚያደርገን በዲኖሚኔሽኖች ከተከፋፈለው የሐይማኖት ዓለም መውጣት አለብን። በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ካለው መሃይምነትና ስሕተት አምልጦ መውጣት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማግኘት ቁልፍ ነው።

ዮሐንስ 4፡31 ይህም ሲሆን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ፦ መምህር ሆይ፥ ብላ ብለው ለመኑት።

አሁንም ደቀመዛሙርቱ በስጋዊ ወይም በፍጥረታዊ ደረጃ ነበር የሚንቀሳቀሱት። ምግብ መግዣ ገንዘብ ስለያዙ ምንም ችግር የሌለ መስሏቸዋል።

የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ተመላላሾችም ተመሳሳይ ስሜት አላቸው። እግዚአብሔር ቁሳዊ ፍላጎታቸውን እስከሞላላቸው ድረስ ሌላ ምንም ችግር እንደሌለባቸው ይመስላቸዋል።

ዮሐንስ 4፡32 እርሱ ግን፦ እናንተ የማታውቁት የምበላው መብል ለእኔ አለኝ አላቸው።

ኢየሱስ ትኩረቱን ያደረገው ከፍ ባለው መንፈሳዊ ዓለም ላይ ነበር። ነፍስን የሚመግብ መንፈሳዊ መብል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 3፡1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
2 ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም።

ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች እውነተኛ መንፈሳዊ ምግብ ማኘክ አይችሉም። ጠለቅ ያለ እውነት ያለባቸው አስተምሕሮዎችን መረዳት አይችሉም። ሰዎች ተሰብስበው አንዲት ሴትን በድንጋይ ለመውገር የተዘጋጁ ጊዜ ኢየሱስ በምድር ላይ ለምን ሁለት ጊዜ እንደጻፈ ጠይቋቸው፤ ከዚያ ግራ ሲጋቡና የሚመልሱት ሲያጡ ታያላችሁ። ሆኖም ግን የክርስቶስ ልብ አለን ይላሉ። ነገር ግን ክርስቶስ ምን ያደርግ እንደነበረ አንዳች አያውቁም። ስለዚህ ራሳቸውን እያታለሉ ናቸው።

ዮሐንስ 4፡33 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፦ የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን? ተባባሉ።

ደቀመዛሙርቱ አሁንም መረዳት ያቃታቸውን ስለ ቤተክርስቲያን ዘመናት አስቀድሞ የተገለጠውን መንፈሳዊ ሚስጥር ወደ ፍጥረታዊ ስጋዊ ነገር አወረዱት።

ይህም ልክ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ጠለቅ ያሉ ጉዳዮችን እንደሚያቃልሉት ነው። ሔዋን አንድ የዛፍ ፍሬ በላችና ከዚያ ልጅ በመውለድ ተቀጣች? የምር? ስትጠይቋቸው የተለመደ ግራ የመጋባት ዓይን ታዩባቸውና ከዚያ ጥያቄውን የጠየቃቸውን ሰው ትተውት ይሄዳሉ። አዳም እና ሔዋን አንድ የዛፍ ፍሬ በልተው ነገር ግን ለምንድነው የተለያየ ቅጣት የተቀጡት? እግዚዘብሔር ሔዋንን ልጅ በመውለድ የቀጣት ለምንድነው? አዳምን ልጅ በመውለድ መቅጣት አያመችም። ለምንድነው አዳምን መቅጣት በማይቻልበት ቅጣት ሔዋን የተቀጣችው? ለዚህም ጥያቄ የክርስቶስ ልብ አለን የሚሉ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የማይችሉ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች መልስ የላቸውም።

ዮሐንስ 4፡34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።

እግዚአብሔር በዘመናችን ትልቅ እቅድ አለው። ትኩረታችን መሆን ያለበት በእግዚአብሔር እቅድ ላይ ነው። ደቀመዛሙርቱ በቁሳዊ ፍላጎት መሟላት ተጠምደው እንደነበረ በቁሳዊ ፍላጎት መሟላት ሃሳባችን መጠመድ የለበትም። እግዚአብሔር የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ገልጧል፤ ይህም መገለጥ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ያመነችውን በማመን ለሙታን ትንሳኤ እንዘጋጅ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለመረዳት ያስችለናል።

ለዘመናችን ዋነኛው የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነው። እግዚአብሔር በሰፊው እቅዱ ውስጥ እንድንመላለስና ፈቃዱን እንድንፈጽም እና የእኛን ምድራዊ ኑሮ በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮችን ለእርሱ እንድንተውለት ይፈልጋል። እኛ ግን ቀኝ ኋላዘ ዙር የተባልን ይመስል ትኩረታችንን በመብልና በልብስ በኑሮ ጉዳይ ላይ አድርገን ለማብራራት የሚከብዱንን ጥቅሶች ቸል እንላቸዋለን። ከባድ ጥቅሶችን ማብራራት ብዙ ጥረት ይጠይቀናል። እኛ ኑሮዋችንን የሚያቀልልንንና ድሎት የሚያመጣልንን የብልጽግና ወንጌል ነው የምንፈልገው። ይህን የምንፈልገውም ሃብታም ለመሆንና ጥሩ ክርስቲያን የመሆናችን ማስረጃ በገንዘብ ያገኘነው ስኬታችን እንደሆነ ማሳየት ስለምንፈልግ ነው። ኢየሱስ ለሃብታሞች ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው ቢልም እንኳ ጥሩ ክርስቲያን መሆናችንን ማሳየት የምንሞክረው ሃብታም በመሆን ነው። ደግሞ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን መረዳት ባንችልስ ምን አስጨነቀን? እንዲህ እያልን ራሳችንን እናጃጅላለን። ከጥያቄ መሸሽን እንደ መልካም ስነ ምግባር እንቆጥረዋለን። መጽሐፍ ቅዱስን ለምን መረዳት እንደማይችሉ ሰዎች በዘዴ ያብራራሉ፤ እንዲህ በማለት፡- ይህን ብናውቀውም “አይጠቅመንም”። ይህ ዓይነት ዘዴ እንደ ትልቅ አስተዋይነት ይቆጠራል። ይህን ሁሉ ስናስብ ጌታ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ መቆሙ አያስደንቅም።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

ከሁሉ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ነው ትኩረት መስጠት ያለብን። ከዚያ በኋላ የኑሮዋችንን ጉዳይ ለእግዚአብሔር መተው እንችላለን።
ከዚህ ቀጥሎ ኢየሱስ ጠለቅ ያለ እውነት ይገልጣል።

ዮሐንስ 4፡35 እናንተ፦ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ።

ሶስቱ ታላላቅ የእሥራሴል ዓመት በዓሎች ከተለያዩ የመከር ወቅቶች ጋር የተያያዙ ናቸው። ከሁሉ አስቀድሞ በፋሲካ ወቅት ለመከር የሚደርሰው ገብስ ነው፤ በመቀጠል ስንዴ በጴንጤ ቆስጤ በዓል አካባቢ ለመታጨድ ይደርሳል፤ በስተመጨረሻ የወይን ፍሬ በክረምት የዳስ በዓል አካባቢ ነው የሚደርሰው።

ስንዴ እና ገብስ በሕዳር ተዘርተው በክረምት ዝናብ ሲዘንብ ነው ለመታጨድ የሚደርሱት። የገብስ መከር በሚያዚያ አጋማሽ አካባቢ በኩራቱ ይደርሳል።

ያም ጊዜ ከፋሲካ ጋር ይገጣጠማል።

ኢየሱስ የሚናገርበት ወቅት በክረምት አጋማሽ አካባቢ ነበር። ከታሕሳስ አጋማሽ እስከ ጥር አጋማሽ (1 ወር) እስከ የካቲት አጋማሽ (2 ወር) እስከ መጋቢት አጋማሽ (3 ወር) እስከ ሚያዚያ አጋማሽ (4 ወር እና ከዚያ በኋላ በፋሲካ በዓል አካባቢ መከሩ መታጨድ ይጀምራል)።

ልብ በሉ፤ ጊዜው የክረምት አጋማሽ ቢሆንም እንኳ ኢየሱስ ልደት ስለማክበር አልተናገረም። የእርሱን ልደት አክብሩ ተብለን አልታዘዝንም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዲሴምበር 25 አንድም ጊዜ አልተናገረም። ይህ ቀን ከመጀመሪያው አሕዛብ የፀሃይን አምላክ የሚያመልኩበት ዕለት ነው።

ነገር ግን መሲሁ በትንቢት መፈጸም መጥቶ ስለነበረ መንፈሳዊው መከር የዛኔውኑ ለመታጨድ አስቀድሞ ደርሶ ነበር፤ ሳምራውያን እና አይሁዳውያን ኢየሱስን ሊቀበሉት ዝግጁ ቢሆኑ ኖሮ ኢየሱስ ዓለምን የሚገዛበት የአንድ ሺህ ዓመቱ ሰላም በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግስት በመሆን ይመሰረት ነበር።

ኢየሱስ ግን ይህ እንደማይሆን አስቀድሞ አውቋል ምክንያቱም አይሁዳውያን አንቀበልህም ይሉታል።

መከር ማለት ዘሩ ከተክሉ ላይ ተቀጥፎ የሚሰበሰብበት ጊዜ ነው።

አይሁዳውያን ኢየሱስን አንቀበልህም ቢሉትም እንኳ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ግን ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ከመቃብራቸው ወጥተው ከሙታን ሊነሱ ችለዋል።

ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

ስለዚህ የብሉይ ኪዳን መከር ማለት የእነዚህ ቅዱሳን ከመቃብራቸው ወጥተው በሕይወት መነሳታቸው ነው፤ ከዚያ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ባረገበት ቀን ከምድር ላይ ተስበው አብረውት ወደ ሰማይ ሄደዋል (እንደ ደመና ያሉ ምስክሮች ሆነው)።

ከዚያም ኢየሱስ ዘመናትን አሻግሮ ወደፊት በቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ የሚሰበሰበውን ታላቅ መከር ተመለከተ።

ይህ መከር ምርቃት ወይም ተጨማሪ ነው። አይሁዳውያን መሲሁን አንቀበልም ስላሉ እግዚአብሔር አሕዛብን ለማዳን ወደ አሕዛብ ዘወር አለ።

መከር ማለት አጫጆች ዘሩን ከተክሉ ላይ ቀጥፈው ሲሰበስቡ ነው። በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ከመቃብሮቻቸው ውስጥ በትንሳኤ ተጎትተው ይወጡና እውነተኛ አማኞች በሙሉ ከምድር ላይ ተነጥቀው በመሄድ በአየር ላይ ጌታ ሲመጣ ይቀበሉታል።

ዮሐንስ 4፡36 የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፥ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል።

ኢየሱስ ቀጥታ ወደ ዋናው ነጥብ በመምጣት በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ ሰዎች የዘላለም ሕይወትን እንደሚያተርፉ ተናግሯል።

ትክክለኛው ሽልማት ይህ ነው። በዚህ ዓለም መከራ ውስጥ ልናልፍ እንችላለን፤ ኋላ ግን ሽልማታችን የዘላለም ሕይወት ነው።

ኢየሱስ በድጋሚ በሰብል ኡደት ውስጥ ሁለት ክፍሎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፤ እነርሱም፡- በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚደረገው ዘር የመዝራት ስራ እና በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚደረገው አጨዳ ናቸው።

በትንሳኤ ቀን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ከሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዳሳን ሙሉ በሙሉ ወደ መጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት ከተመለሱ አማኞች ጋር አብረው ይደሰታሉ። በዚሁ አያይዞ ኢየሱስ አዲስ እውቀት ይገልጣል፡- ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጀመሪያውን ዘር በመዝራት ኡደት ተመስለዋል። ዘሩ በምድር ውስጥ መቀበር አለበት፤ ከዚያም ዘሩ ደረጃ በደረጃ ቅጠል እና አበባ እንዲሁም ለሚያፈራው ፍሬ መሸፈኛ ወደሚያወጣ ተክል ያድጋል። በስተመጨረሻም ፍሬው መጀመሪያ የተዘራውን ዘር በሚመስልበት ጊዜ ለመታጨድ ይደርሳል።

ዋናው ነጥብ ይህ ነው። የሚታጨደው ዘር በፊት ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ነው የሚሆነው።

ኢየሱስ አልፋ እና ኦሜጋ፤ ፊተኛ እና ኋለኛ ነው። እርሱ ራሱ ዘሪውም አጫጁም ነው።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያቱ መጽሐፍ ቅዱስን በጻፉ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ዘርቷል። ከዚያ በኋላ እውነት ጠፋችና በጨለማው ዘመን አፈር ውስጥ ተቀበረች። በማርቲን ሉተር የተጀመረው ተሃድሶ የእውነት ቅጠል ማቆጥቆጥ ነው። ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና ወንጌልን ስለ ማሰራጨት ሰበከ፤ ይህንንም ተከትሎ ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን ተጀመረ፤ በዚህም ዘመን ወንጌል ከአበባ ላይ በነፋስ እንደሚበትን ቢጫ ዱቄት ወደ ዓለም ሁሉ ተዳረሰ። በ1906 የተነሳው ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ተሃድሶ አመጣ፤ እርሱም የተዘራውን ዘር የሚመስል የዘር አቃፊ ነው ነገር ግን በዚያ ጊዜ ሰዎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን መግለጥ ስላልቻሉ ዘር አቃፊው በውስጡ ዘር አልነበረውም። በ1963 የሰባቱ ማሕተሞች ሚስጥር ተገለጠ፤ ይህም የሆነው የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያለችዋ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ሚስጥር ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ አማኞች በመረዳት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ እንድትችል ነው። አእምሮዋች የእውነትን መገለጥ ሲያገኝ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ቃል ዘር ተመልሶ ይመጣል።

የመጨረሻው ዘመን በመጀመሪያው ዘመን የተዘራውን የእምነት እና የቃል ዘር መልሶ ሲያጭድ የዛን ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይጠናቀቃል።

ኢየሱስ በወይን እርሻ ውስጥ ስለሚሰሩ ሰራተኞች ምሳሌ ተናግሯል። የዳስ በዓል የሚከበረው ከወይን እርሻ ላይ የወይን ፍሬ በሚታጨድበት ጊዜ ነበር። የዳስ በዓል በምድር ላይ የሚመጣውን የ1,000 ዓመት የሰላም መንግስት ይወክላል (ብዙዎች ሚሌኒየም የሚሉት) እርሱም ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ ነው የሚመጣው። በዚያ ዘመን ውስጥ ሰዎች ቤቶችን ይሰራሉ፤ በሰላም ይኖሩባቸዋል።

ማቴዎስ 20፡1 መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።

2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።

ዲናሩ የሚወክለው በ1,000 ዓመት መንግስት ውስጥ ቦታ የሚሰጣቸውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ነው። እነዚህ የመጀመሪያ ሰራተኞች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ይወክላሉ።

ማቴዎስ 20፡9 በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
10 ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
11-12 ተቀብለውም፦ እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።
14 ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤

መጨረሻ የመጡት ሰራተኞች ደግሞ በመጨረሻው በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን የሚኖሩ ክርስቲያኖችን ይወክላሉ።

በዚህ ምሳሌ ውስጥ ትኩረት የተሰጠው የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን እና የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያሉ አማኞች እኩል ክፍያ ማግኘታቸው ላይ ነው። ለመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ዘመን እውነት የገለጠ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ነው ለመጨረሻውም የቤተክርስቲያን ዘመን እውነትን የሚገልጠው። በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያሉ ልጆች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደ ነበሩት ሐዋርያዊ አባቶች እምነት ይመለሳሉ።

ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እና በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን መካከል ምንም ልዩነት መኖር የለበትም።

እግዚአብሔር የተገለጠውን ቃል ብዙ ሰዎች እንዲከተሉ ይፈልጋል፤ ነገር ግን ብዙ ክርስቲያኖች ከቤተክርስቲያን ልማዶቻቸው እና ከፓስተሮቻቸው አመለካከት ጋር ተጣብቀው መቅረት ይፈልጋሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ከሚወድዱት የበለጠ ቤተክርስቲያንን ይወድዳሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን ንግግሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አስበልጠው ያከብራሉ። እግዚአብሔር የመጀመሪያውነ እውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እየገለጠ ነው፤ ቤተክርስቲያኖች ግን ጆሮዋቸውን አልሰጥ ብለዋል። ከዚያ ይልቅ ሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽናዊ እምነታቸውን ታቅፈው መቀመጥ መርጠዋል።

ዮሐንስ 4፡37 አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና።

አንድ ዘመን ብቻ ነው እውነትን የዘራው -- ይህም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ሌላ የቤተክርስቲያን ደግሞ በስተመጨረሻ ያጭዳል -- ይህም ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ማጨድ ማለት ፍሬውን ከተክሉ ላይ ቆርጦ መውሰድ ነው። የመጀመሪያው ዝናብ የትምሕርት ዝናብ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ተረድተን ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ ያስችለናል። የኋለኛው ዝናብ የመከር ዝናብ ስለሆነ ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ቅዱሳን ከመቃብራቸው ውስጥ ያወጣቸዋል፤ በዚያው ሰዓት በሕይወት ያሉ ቅዱሳን ደግሞ ወደማይሞት አካል ይለወጣሉ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም በአንድነት ከምድር ላይ ተነስተው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ይነጠቃሉ።

ለእኛ የተሰጠን ትልቅ ማስጠንቀቂያ ይህ ነው፡- አንድ የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው እውነትን የዘራው -- ይህም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን።

ሰባተኛው ወይም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ያንኑ ዘር ማለትም የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበረውን ዓይነት ተመሳሳይ አስተምሕሮ ማጨድ አለበት።

ዮሐንስ 4፡38 እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ምንም ማመካኛ የለውም። የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ አባቶች ሊተክሉት የታገሉለትን፣ መከራ የተቀበሉለትንና የደከሙለትን ትምሕርት ማመን አለብን። ሐዋርያዊ አባቶች የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ለመጻፍና የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን መሰረት ለመጣል ደክመዋል። እውነት ጸንታ እንድትቆም ሲሉ ታግለዋል፤ ተገድለዋል። በ64 ዓ.ም ሮማዊው ንጉስ ኔሮ ክርስቲያኖችን በጭካኔ የማጥፋት ዘመቻ አስነስቷል። በ300 ዓ.ም አካባቢ ዲዮክሊቲያን የተባለ ሮማዊ ንጉስ ክርስቲያኖችን በጭካኔ መግደል ጀመረ፤ እንዲሁም ሐዋርያት የጻፉዋቸውን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትና መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ዘመቻ ጀመረ። ደግነቱ ብዙ ቅጂዎች ተዘጋጅተው ስለነበረ አንዳንዶቹ ሳይጠፉ ሊተርፉ ችለዋል። ከዚያ በኋላ ቀጣዮቹ የቤተክርስቲያን ዘመናት በጣም ከባድ በሆኑ ስደቶችና መከራዎች ውስጥ አልፈዋል። በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በጨለማው ዘመን ውስጥ ሰማእት ሆነዋል። ከቁጥር በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖች በበሽታ ወይም ወንጌልን ሊሰብኩ በወጡበት ተገድለው ሞተዋል። ዛሬ ያለንበት ዘመን ላይ ለመድረስ ክርስቲያኖች በብዙ ትግል ውስጥ አልፈዋል። በ1611 ዓ.ም በቋንቋ ችሎታቸው የላቁ 47 ሰዎች ተባብረው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉመዋል። የ1769 ዓመተ ምሕረቱ ወጥ ትርጉም በስተመጨረሻ እስከሚጸድቅ ድረስ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ለ160 ዓመታት በተደጋጋሚ ተፈትሾ ትክክለኛነቱ ተረጋግጧል። በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ውስጥ የወንጌል ስርጭቱ የጀርባ አጥንት ሆኖ በማገልገሉ በዚያ ዘመን ውስጥ በድጋሚ ትክክለኛነቱ ተፈትሾ ታይቷል። ስለዚህ ስሕተት የሌለበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በእጃችን እንዲገባ ብዙ ተደክሞበታል። እኛ ምንም የምናበረክተው አዲስ አስተዋጽኦ የለም። በአሁኑ ሰዓት በሕትመት እና ስርጭት ከዋሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መካከል በሚገባ ተፈትሾ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን ነው። አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በማዘጋጀት መድከም አያስፈልገንም። ፍጹም ሆኖ የተዘጋጀውን ትርጉም ልናሻሽለው አንችልም። ተጽፎ ባለበት እያነበብነው ማመን አለብን። ደግሞም ሚስጥራቱን መረዳትም አለብን፤ ምክንያቱም የእኛ ሃላፊነት ሐዋርያቱ መጀመሪያ ይከተሉት ወደነበረው እምነት መመለስ ነው። ሐዋርያቱ የዘሩትን ብቻ ነው ማጨድ የምንችለው።

ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክሉትን ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ የተጻፉትን ሰባት የእግዚአብሔር መንግስት ምሳሌዎች አስቡ።

የመጀመሪያው ምሳሌ ውስጥ እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ዘር የሚዘራ ዘሪ አለ፤ ይህም ዘር በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በሐዋርያት ተጽፎ የተቀመጠው እውነት ነው። ሐዋርያቱ የጻፉትን ብቻ ነው ማመን የምንችለው። ክፉ ወፎች ይህንን ዘር ሊያጠፉት ሞከሩ።

ሁለተኛው ምሳሌ ውስጥ በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰዎች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ተጣብቀው ከመኖር ይልቅ ቸልተኛ ሲሆኑ እናያለን፤ ስለዚህ የሰው አመለካከትና የልማድ አረም ቤተክርስቲያን ውስጥ ገባ። እነዚህ ስሕተቶች በስተመጨረሻ ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱና በእውነት እና በስሕተት መካከል ያለውን ልዩነቶች እስከሚያጋልጡበት ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተደብቀው ይቆያሉ።

በሶስተኛው ምሳሌ ውስጥ አንድ ትልቅ ዲኖሚኔሽናዊ ዛፍ ያድግና በቅርንጫፎቹ ውስጥ ክፉ ወፎች ይጠለሉበታል (እነዚህ ወፎች በመጀመሪያው ምሳሌ ውስጥ ዘሩን በልተው ሊያጠፉት የሞከሩ ወፎች ናቸው) አሁን በዚህ ምሳሌ ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሆነው በቅርንጫፎች ላይ ይቀመጣሉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ መሪ ከሆኑ ሰዎች ተጠንቀቁ። ይህ ልክ ያልሆነ ስርዓት ነው።

አራተኛው ምሳሌ፣ መካከለኛው ምሳሌ ወይም መካከለኛው ዘመን የጨለማው ዘመን አንዲት ሴት (የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን) አውሮፓን ስትቆጣጠር ያሳያል። አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ትያጥሮን የሚባል ሲሆን ትርጉሙም “ጨቋኝ ሴት” ማለት ነው። የሕይወትን እንጀራን ወስዳው የሶስት ሰዎች ሥላሴ አደረገችው። ይህም ብልሽት ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች የእግዚአብሔር ስም እስኪጠፋባቸው ድረስ እየተባባሰ ሄደ። የኢየሱስን ስም በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ለወጡት። ነገር ግን የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም። እነዚህ ማዕረጎች ናቸው እንጂ ስሞች አይደሉም። ከዚህም የተነሳ የክርስቲያኖች አምላክ ስም የለውም።

አምስተኛ ምሳሌ ክርስቶስ በቀራንዮ ሆኖ ዓለምን ሲገዛ ያሳያል፤ ከዚህም የተነሳ መዳን በእምነት ነው ብሎ የሰበከው የማርቲን ሉተር ተሃድሶ ለሰዎች ሁሉ ሊዳረስ ችሏል።

ስድስተኛው ምሳሌ ኢየሱስ በቀራንዮ ሆኖ እንቁ ሲገዛ ያሳያል፤ ይህም የሰማይን ደጅ ይወክላል። ይህም የታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን ውስጥ የነበረው የተከፈተ በር ነው።

ሰባተኛው ምሳሌ እረፍት የሌላቸው ሕዝቦችና አሕዛቦች የሞሉበትን በባሕር ውስጥ የተጣለ መረብ ያሳያል። ኢንተርኔት ወደ ሁሉም ሕዝብ ተዳርሷል፤ ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ለማሰራጨት ያገለግላል -- ከዚያ በኋላ ፍጻሜው ይመጣል።

ዮሐንስ 4፡39 ሴቲቱም፦ ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ ብላ ስለ መሰከረችው ቃል ከዚያች ከተማ የሰማርያ ሰዎች ብዙ አመኑበት።

ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን ልታውቅ የቻለችው የልቧን ሃሳብ እና የቀድሞ ታሪኳን ገልጦ ስላሳያት ነው።

የልብን ሃሳብ ማወቅ የተባለው ምልክት ኢየሱስ ናትናኤልን ባናገረው ጊዜ ለአይሁዳውያን እንዲታይ ተደርጓል።

ቀጥሎ ደግሞ የሴቲቱን የልብ ሃሳብ የማወቅ ምልክት የአይሁድ እና የአሕዛብ ክልስ ለሆኑት ለሳምራውያንም ታይቷል።

የልብን ሃሳብ ማወቅ የመሲሁ ምልክት በመሆኑ አይሁድንም ሳምራውያንንም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን እንዲያውቁ ረድቷቸዋል።

ይህም እነርሱ ለመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እንዲዘጋጁ አድርጓቸዋል፤ የዛኔ የጀመረው ዘመን ውስጥ አይሁዳውያን ኢየሱስን በመግፋታቸው እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ዘወር ሊል ችሏል።

ዮሐንስ 4፡40 የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ለመኑት፤ በዚያም ሁለት ቀን ያህል ኖረ።

ኢየሱስ በእነዚህ ምሳሌዎች አማካኝነት ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚገልጹ መሰረቶች እየጣለ ነበር። ሐዋርያቱ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ከመሰረቱባት ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው መከር ወይም ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል አማኞች እስከሚነጠቁበት ዘመን ድረስ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እስኪጠናቀቁ ድረስ ሁለት ሺህ ዓመታት ይፈጃሉ። ለ2,000 ዓመታት ኢየሱስ ሰባት ቅርንጫፍ ባሉት መቅረዝ በተወከሉት ቤተክርስቲያኖቹ መካከል ይመላለሳል። በእግዚአብሔር የጊዜ አቆጣጠር ይህ ሁለት ቀን ብቻ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሰዎችን 1,000 ዓመት አንድ ቀን አድርጎ ነው የሚቆጥረው። ስለዚህ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያኖች ጋር ደስ እያለው ሁለት ቀናትን አሳልፏል።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

አንድ ወገን ማለትም አሕዛብ ግን የመሲሁን ምልክት አላዩም። ስለዚህ እግዚአብሔር ከአሕዛብ መካከል ነብይ አስነስቶ ወደ መጀመሪያዎቹ የሐዋርያት ጥንታዊ ትምሕርት ቢመልሰን ልንደናገር አይገባም። እግዚአብሔር ለአሕዛብም የልብን ሃሳብ የማወቅን ምልክት ሊያሳያቸው ይፈልጋል።

ዮሐንስ 4፡41 ስለ ቃሉ ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤

ሕዝቡ ሴቲቱ (ቤተክርስቲያን) ስለ ኢየሱስ በነገረቻቸው ተደንቀዋል። ነገር ግን ኢየሱስ እራሱ እየተናገረ ሲሰሙ ደግሞ ይበልጥ ተደነቁ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የነገረቻቸውን ብቻ ሰምተው መኖር ለምደዋል፤ ደግሞም ቤተክርስቲያን ለስብከት የምትጠቀምባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብቻ ነው የሚያውቋቸው። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገሩትን በመስማት ተወስነው ከሚቀሩ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው ማጥናት ቢጀምሩ ይበልጥ ይደነቁ ነበር። “ቤተክርስቲያን ተመላላሾች” ፓሰተሮቻቸው የተናገሩትን እንደ ገደል ማሚቶ መድገም ብቻ ነው የሚያውቁት፤ ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንድነው የተጻፈው ቢባሉ የሚያውቁት በጣም ጥቂት ነው።

ዮሐንስ 4፡42 ሴቲቱንም፦ አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም፥ እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።

ዋናው ነጥብ ይህ ነው። በኢየሱስ ማመን እና መጽሐፍ ቅዱስን ለራስህ ማንበብ አለብህ። ፓስተሩ ስለተናገረ አይደለም ማመን ያለብህ፤ በግልህ መረዳትን አግኝተህ፤ ከየትኛውም ቤተክርስቲያን ጋር ምንም ጉዳይ ሳይሆርህ ከኢየሱስ ጋር የግል ሕብረት ውስጥ መግባት አለብህ። እነዚሀ ሰዎች መሰረታዊ እውነት ገብቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችሁ ስታነብቡ በኢየሱስ ማመንን ሰባኪዎች ስለ ኢየሱስ ነግረዋችሁ ካመናችቸሁት ይበልጥ ትርጉም ያለው ይሆንላችኋል። ሁላችንም መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት ላይ የተመሰረተ የግል ሕብረት ከኢየሱስ ጋር ማድረግ አለብን። ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ከበድ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን ስትጠይቋቸው ትተው የሚሄዱበት ምክንያት በራሳቸው ስለማያስቡ ነው። ልማዳቸው ሌላ ሰው ሲናገር የሰሙትን በስንፍና መጥቀስና ከባድ ጥያቄዎችን አይጠቅሙም ብሎ ማለፍ ነው። ሃሳባቸውን ሌሎች ሰዎች እንዲያስቡላቸው ይተዋሉ፤ ከዚህም የተነሳ እነዚያ የሚተማመኑባቸው ሰዎች በማያውቁዋቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተከታዮቻቸውም መሃይም ሆነው ይቀራሉ። ስለዚህ እነርሱም የመሪዎቻቸውን ስሕተቶች ይደግማሉ። በዚህም መንገድ እራሳቸውን ከጌታ ያርቃሉ። ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን በራሳቸው አንብበው እንዲረዱ ያስተማራቸው የለም። ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር በታገለ ጊዜ ያገኘውን ዓይነት እውቀት ከእውነት ጋር የጠበቀ ሕብረት የላቸውም።

ግንኙነታችን በቀጥታ ከኢየሱስ ጋር መሆን አለበት። በፓስተር ላይ የተደገፈ የእጅ አዙር ሕብረት መሆን የለበትም።

ዮሐንስ 4፡43 ከሁለቱ ቀኖችም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።
44 ነቢይ በገዛ አገሩ እንዳይከበር ኢየሱስ ራሱ መስክሮአልና።

ለምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ነብይ ሁል ጊዜም በገዛ ሃገሩ አይከበርም። ይህም እንግዳ የሆነ የሰዎች የአስተሳሰብ ውድቀት ነው። የገንዘብ እና የስልጣን ፍቅር ላጠመዳቸው የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ታላቅ ስጋት ነበረ። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ከስንፍናቸው ብዛት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማመን ትተው የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን ነው የሚያምኑት። የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች የአይሁድ ሕዝብ ኢየሱስን እንዲሰቅሉ አሳምነዋቸዋል። የአይሁድ ሕዝብ ኢየሱስን በመጀመሪያው ምጻቱ እንዳይቀበሉት በዋነኛነት ምክንያት የሆኑት የሐይማኖት መሪዎች ናቸው። የኢየሱስ ዳግም ምጻት ሲቃረብ ደግሞ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል እንዳይቀበሉ ዋነኛ ምክንያቶች የሚሆኑት የቤተክርስቲያን ፓስተሮች ናቸው።

አይሁዳውያነ የሐይማኖር መሪዎቻቸውን ማዳመጥ ባያበዙ ኖሮ እና ብዙ ጊዜያቸውን ስለ ኢየሱስ አገልግሎት የሚናገሩትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በማንበብ ቢያሳልፉ ኖሮ ኢየሱስን እንደ መግደል ያለ ከባድ ስሕተት ባልሰሩ ነበር።

ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን ንግግር ሰምተው መድገም ቢቀንሱና መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው በማጥናት ብዙ ጊዜ ቢያሳልፉ እንደ ግለሰብ ከኢየሱስ ጋር ጠንከር ያለ የግል ሕብረት ይኖረን ነበር። ከኢየሱስ ጋር የሚኖረን የግል ሕብረት ሊጠነክር የሚችለው ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር ካለን የግል ሕብረት ጋር በተመጣጠነ ደረጃ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ እውነት ነው። ለመረዳት ከባድ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይጠቅምም ብለን የምናልፈወው ከሆነ ኢየሱስ እራሱ አይጠቅምም እያልን ነው። ይህም ማለት ከኢየሱስ ጋር ጠንከር ያለ የግል ሕብረት የለንም ማለት ነው። ከኢየሱስ ጋር የተያያዘ ነገር ሁሉ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አድርገን መመልከት አለብን።

ዮሐንስ 4፡45 ወደ ገሊላም በመጣ ጊዜ፥ የገሊላ ሰዎች ራሳቸው ደግሞ ለበዓል መጥተው ነበርና በበዓል በኢየሩሳሌም ያደረገውን ሁሉ ስላዩ ተቀበሉት።

ገሊላ ውስጥ የነበሩ አይሁዶች በኢየሱስ በጣም ተደንቀው ነበር። አይሁዳውያን እንደመሆናቸው ለፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተመቅደስ ሲሄዱ ኢየሱስን በስራው አይተውታል። ከሰዎች ሁሉ ልዩ መሆኑን አስተውለዋል። ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር የግል ሕብረት አልመሰረቱም። ብቸኛው ራስ እርሱ መሆኑን እውቅና አልሰጡም። ቀላሉን መንገድ በመምረጥ የሐይማኖት መሪዎቻቸው የነገሩዋቸውን ብቻ በጭፍን ለመታዘዝ ወሰኑ። እነዚህ አይሁዳውያን የሐይማኖት መሪዎቻቸው ጠማማ ምክር ባይመክሩዋቸው ኖሮ ኢየሱስን አይገፉትም ነበር። መሲሁን እንዲቀበሉ ለመዘጋጀት ሊደሩዋቸው ይጠበቅባቸው የነበሩ መሪዎቻቸው እራሳቸው የአይሁድ ሕዝብ መሲሁን እንዳይከተሉ አጣመሙዋቸው። የሰዎች ሐይማኖታዊ አመራር በጣም አደገኛ ነው። የመሪዎች ልብ ያለው ስልጣን እና ገንዘብ ላይ ነው። ይህ አይነቱ ዝንባሌ የጀመረው በሐዋርያው ይሁዳ ነው። ስሕተት በቤተክርስቲያን ውስጥ ከላይ በአመራር ቦታ ላይ ካሉ ሰዎች እንጂ ከቤተክርስቲያን ውጭ አይደለም የሚመጣው።

ዮሐንስ 4፡46 ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ።

ኢየሱስ የመጀመሪያውን ተዓምር ሰርግ ቤት ውስት ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ ወደ ለወጠበት ወደ ቃና መጣ። መጨረሻ ላይ የሚያደርገው ተዓምር በሰማይ ለሚደገሰው ለበጉ ሰርግ ነው፤ በዚያን ጊዜ የቃሉን ውሃ ሚስጥር በመገለጥ ወደሚሆን የመነቃቃት ወይን ጠጅ ይለውጠዋል፤ በዚህ ሂደት ውስጥ የተጻፈውን ቃል በዘመን መጨረሻ ላለችው ለሙሽራው ይገልጥና አካሏ ከሟች አካልነት ወደማይሞት አካል እንዲለወጥ ያዘጋጃታል።

በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ በዘመን መጨረሻ ሙሽራይቱን በሰማይ ለሚደገሰው ሰርግ የሚያዘጋጅበትን ሌላ ሚስጥር ይገልጣል።

አባትየው ልበ ሰፊ ሰው ነው -- ልበ ሰፊ። አንድን ሰው ልበ ሰፊ የሚያደርገው ምንድነው? የእግዚአብሔርን ቃል በፈቃደኝነት መቀበል እና እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ነው ሰውን ልበ ሰፊ የሚያደርገው።

የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።

ዮሐንስ 4፡47 እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።

ይህ አባት እና ልጅን የሚያሳይ ታሪክ ነው። አባትየው ልክ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በቤርያ ከተማ እንደ ነበሩት አማኞች ልበ ሰፊ ነው።

በዘመን መጨረሻ አካባቢ ቁልፍ የሆነው ክስተት የዘመን ፍጻሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን የሚገልጥ ነብይ መነሳቱ ነው፤ እርሱም ዓላማው በዘመን ፍጻሜ ያሉት አማኝ ልጆችን ልበ ሰፊ የሆኑት የጥንት ሐዋርያዊ አባቶች ወዳመኑት እምነት እንዲመለሱ መርዳት ነው።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

እርግማኑ በታላቁ መከራ ዘመን ከሚፈነዳው የኑክሊየር ቦምብ በኋላ ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ የሚመነጨው ጨረር ነው።

ነገር ግን ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ልጆች ወደ አባቶች መመለስ አለባቸው።

ስለዚህ በበሽታው ሊሞት የደረሰው ልጅ ልበ ሰፊ ወደ ሆነው ወደ አባቱ ጤንነት መመለስ አለበት።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በሰዎች አመለካክት በመበከሉ የተነሳ በሽተኛ ሆኗል፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝባቸው ስሕተትን፣ ልማዶችን እና የሰው አመለካከቶችን እውነት አድርገው እንዲቀበሉ አድርገዋቸዋል።

ዮሐንስ 4፡48 ስለዚህም ኢየሱስ፦ ምልክትና ድንቅ ነገር ካላያችሁ ከቶ አታምኑም አለው።

የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች ያለባቸው ትልቅ ችግር ምልክቶችን እና ድንቆችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ አስፈላጊ አድርገው መቁጠራቸው ነው። ተዓምር ካዩ ያምናሉ።

ዮሐንስ 20፡27 ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።
28 ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።
29 ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።

ተዓምራት እምነትን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ነገር ግን ተዓምራትን ያላዩ ሰዎች ካዩ ሰዎችም በላይ የተሻለ እምነት ይኖራቸዋል፤ ምክንያቱም እምነት የሚገነባው የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ነው። እምነት ተዓምራትን በማየት ላይ ጥገኛ አይደለም።

ሮሜ 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።

አንዳንድ ንሰሃ እንኳን ያልገቡ ሰዎች ተዓምራትን ያደርጋሉ። ጌዴዎን ከሁለት አሕዛቦች አፍ ሕልም እና ፍቺውን ሰምቷል።

ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

ዮሐንስ 4፡50 ኢየሱስም፦ ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ አለው። ሰውዬውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ።

“ሰውየውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ፤” ለዚህ ሰውዬ የስኬቱ ቁልፍ ኢየሱስ የነገረውን አምኖ መሄዱ ነው። ሐዋርያዊ አባቶች ለኢየሱስ ቃል ይሰጡ የነበረው ምላሽ ይህንን የሚመስል ነው።

ዮሐንስ 4፡51 እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና፦ ብላቴናህ በሕይወት አለ ብለው ነገሩት።

ልጅየውም በርቀት ሳለ ተፈወሰ።

ዮሐንስ 4፡52 እርሱም በጎ የሆነበትን ሰዓት ጠየቃቸው፤ እርሱም፦ ትናንት በሰባት ሰዓት ንዳዱ ለቀቀው አሉት።

ሰባተኛው ሰዓት የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ተምሳሌት ነው፤ በዚህ በሰባተኛው ዘመን የዘመን መጨረሻ ላይ ያሉ ልጆች በቤተክርስቲያን ውስጥ ሳሉ ከያዛቸው ገዳይ ከሆነው የአለማመን በሽታ ይፈወሳሉ፤ ከዚያም ሐዋርያዊ አባቶች ወደ ጻፉት ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ይመለሳሉ።

ዮሐንስ 4፡53 አባቱም ኢየሱስ፦ ልጅህ በሕይወት አለ ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ።

ኢየሱስ ቃሉን ለጥንቷ የቤተክርስቲያን አባቶች ሰጠ። እኛ ደግሞ እንደ ልጆች በዘመንም በስፍራም ከጥንቷ ቤተክርስቲያን በጣም ሩቅ ነን። ነገር ግን ኢየሱስ በርቀትም ቢሆን እምነታችንን መፈወስ እና የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ያመነችውን እንድናምን ማድረግ ይችላል። ኢየሱስ አባቶችንም ልጆችንም በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይችላል። ከትንሳኤ በኋላ የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ቅዱሳን ከሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ጋር ይገለጡና በአስተምሕሮ ላይ ዓይን ለዓይን ይተያያሉ ወይም ይስማማሉ። ከዚያም በሕይወት ያሉት ቅዱሳን አካላቸው የማይሞት ሆኖ ሲለወጥ ሁለቱም ወገኖች በአንድነት በአየር ላይ ይነጠቃሉ።

ዮሐንስ 4፡54 ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛ ምልክት ነው።

በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ በዘመን ፍጻሜ ሊያደርገው ያሰበውን ተዓምር ምሳሌያዊ በሆነ ተዓምር ገለጠ። እነዚህም የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ተዓምራት ናቸው። አልፋ እና ኦሜጋ የሆነው የማይለወጠው አምላክ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፣ ዛሬ፣ እስከ ዘላለምም ያው ነው።

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23